WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
__________///__________
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዘኪዮስ 5

አዲስ

Joined: 13 Aug 2006
Posts: 37

PostPosted: Mon Dec 10, 2007 12:34 am    Post subject: Reply with quote

ሣሉቴ ... አልኩኝ ለመግባቴ

በቀደም ከሸራየ ጋር ሆኜ ዝም ብዬ ስቀድ ዋልኩኝ እሱ በብሩሽ ያጎረስኩት ቀለም ላይ ሙድ ይዞ ሲያገጥብኝ እነም ምናባ እያልኩኝ ስደግመው በቃ አለ አይደል እንደድሮ ጓደኞች ሆነን እያወራን የሆነ ሠኣት ላይ ቢራዬን ልጎነጭ አፍት ያህል ቆም ብዬ ሳየው ድብልቅ ያለ ፔንቲንግ ሆኗል ... እንዲህ እየተሳሳቅን በመላመድ ምሠራቸው ምስሎች ብዙም አይስቡኝም ነበር :: አለ አይደል ዝምብሎ የተለምደ ሕሳቦችን በቄንጥ ቀለምኛ ጥበቦች እየጎነጎኑ ቀባ ቀባ ሚደረጉ ...የቴክኒሻን ዓይነት ስራ ነው ሚመስሉኝ .... ዛሬ ዘኪን ሆኜ የመጣዉት ምናቦች ሲወለዱ የነዛ ውስጠ -ፅነሣቸው መንስሄ ምንድነው ብዬ ከራሴ ጋር ልጨቃጨቅም ነው አንዳንዴ አለ አይደል የሆነ ቦታ ዝምታ ...በራሱ ሲያፈጥ ጨዋታ ለማምጣት በመሳሣቅ ሚጀመረው ዓይነት የሐሳብ ፅንስ ሳይሆን ነርቮችን ቆንጥጠው ሕዋሳቶቹን ታክከው ብቅ ሚሉ ሕሳቤ -ፅነሣዎች አሉ አይደል .... የነዛስ መነሾነት ምንድነው ነው ? የስሜት ማዳመጥ አንድምታ ተርታ ናቸው ዓይነት ውስጤ ቢያቃጭልም እሺ ልለው ውስጤ እምቢ ይለኛል :: ወይም ነገርን ነገር ያነሠዋል ዓይነት .....

በዛች ብሽክሊሊት ልሦምሡምማ .....ወደዛኚያው ማዶ ካቻምናዎች .... አንድ ሌሊት ሠርቫይቪንግ ፒካሶን ያነበብኩበት ወቅት ነው .... እኔ ከሚስቴ አልተጣላሁም ልጆቼንም ተቆጥቼ አላማረርኩም 'ምክኒያቱም ምሽትም ልጆችም የሉኝምና .... ታዲያ ከሸራ ጋር ስፋጠጥ ሁለታችንም ተኳረፍን ሠኣታትም ነጎዱ .......ሌሊት ሲሆን ጫማዬን ተጫምቼ በእግሬ ወክ እያደረግኩኝ ወደፒያሳ አቀናው ካፊያው አዱገነትን ያበሳጫት ይመስል ነበር በዛ ብርቱካናም መብራት ጭልንጭል ያለው የምሽት ትዕይንት ምናብ የተራበው ውስጤን መገበው ሠንሻይን ባር ዲጄ ዳኒ የከፈተልኝን ሮክ ሙዚቃ ሠምቼ ውስጤን በጅን ካኮማተርኩት በኌላ ስወጣ ቁልቁለቱ ላይ አንዲት ጥቁር ውሻ አፏን ወደሠማይ ቀስራ ታላዝናለች አራስ ስለመሆኗ የጡቶቿ ግት መንጠልጠል ያስታውቅ ነበረ አንዲት ቡችላዋ በመኪና ተገጭታ ነበረ አጯጯዋ አንጀትን ይበላል ሢጋራዋና ይዛ በማዘን ምታያት የምሽት ሥሜት አዳኝ እንስት እንደኔው ልቧ እንደተነካ ያስታውቅ ነበረ ::
እናም ይህንን ሥዕል ውስጤ ጭርስ አድርጌው ቤቴ ገባው :: ለማግስቱ ዕንቅልፍ ካጠራቀምኩኝ በኌላ እኔና የተኳረፍነው ሸራ መተቃቀፋችን አይረሣኝም ....
ልምጣማ ወደዚህ ወደአሁኑ ዘኪዮስነቴ አሁን ዕይታ ጠኔ ነው ግና ሸራ ቀለም ልሶ ምስል ጎርሶ ያድራል እነኚህ የዛሬ ውልደተ -ምናቦች ፅንሣቸው ኬት ነው ? ነገ (በኔ ነገ ) ዋንቾን ሆኜ እመልሠው ይሆን ?

በነገና በዛሬ መዓላ ምናለ ፈጣሪ ለእንግዳ ብሎ ያኖረው ትርፍ ጊዜ ቢኖር ....
ሄድኩኝ ::

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Dec 15, 2007 3:49 am    Post subject: Reply with quote

::
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Dec 29, 2007 1:18 am    Post subject: Reply with quote

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Jan 12, 2008 5:36 am    Post subject: Reply with quote

እቺ የግል ቤቴ ጓሮ በመሄዷ ያኮረፈችኝ ስለመሠለኝ ነው እዚህ ያመጣዋት .....

አቤት ነገ ምጨምርባ _________________ ....????

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Jan 15, 2008 4:30 am    Post subject: Reply with quote

ሻሎም ብያለው ::

አራት መሀዘን ጨረቃዬ

በሕይወት ዘመኔ የገጠሙኝን መምሕራኖቼን ሳስባቸው አንዱ ካንዱ ያስቀኛል ያሣዝነኛል ተቀብሎ ማቀበል የተዋሀዳቸው ነበሩ ልበል ? ሁሉም የፊደል ግጥግጦች እንደሸሚዝ አዝራር አንዱ ቢጎል ብርድ ይሾልክ ይመስል .... ዳሩ የሸሚዙ ቢነቀል የሡሪ ቢገጥሙበት ቫራይቲ ይሆን ነበር ብለን ብናስበው አሪፍ ነው :: ቀሽምም ቢሆና የራሱን ጨምሮ ያስተማረኝን መምሕር ግን አልረሳዉም :: አለ አይደል አንዳንድ ሠው በአመሉ መለየት ይፈልጋል አንድ ጊዜ አንድ ጓደኛችን ማኪያቶ እንዳማረው እየለፈለፈ ካፌ ደርስን እዛ ስንደርስ 6ታችንም ማኪያቶ ስንል ''በቃ የኔን ቡና አድርገው '' አለ :: ሠው ብዙ ጊዜ ሥለራሱ ሲናገር ''እኔ ለነገሩ ግዴለኝም ...'' ማለት ይወድ የለ ከግድም ግድንግድ ግድ ያለው ሁላ ' ነው እንደዚህ ሚለው :: ምን ነበር ይሄንን የሕሳቤ ዝብዝብ እንዳጤን ያደረገኝ ?
አዎ አንድ ጊዜ የአማርኛ መምሕሬ ግጥም ፃፉ ብለው ትህዛዝ ይሠጡናል :: ጭለማ ውስጥ ሲኮን ሀሳብ ይመጣል ሲባል ሰማዉና በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ በጨረቃ ብረሐን ቅርፃቸዉን ሚቀያይሩ የሌሊት ዳመና ቁልሎች ሳይ አንዳች ስብጥርነታቸው ጨረቃይቱን የአራት መሐዘን አድርጎ አሳየኝ ይሄኔ አራት መሐዘን ጨረቃ ብዬ ፃፍኩኝ ... እኔ መቀለዴ ነበር ግን አለ አይደል በወነ ወቅት መምሕራንን ... ያልተለመደ ነገር በማድረግ አናዶ ክፍሉን ማሳቅ በመፈለግ ... በዛ ስሜት ነው የፃፍኩት ግና ቤቱን መቷል ግጥሙም ገጥሟል :: እንዲያዉም የሣድስ ሕጉን ሁሉ ጠብቋል ብቻ ሕሣቤው የሌለ ነበር ...
መምሕራችን ሢያዩት ከምን ላይ ገልብጠህ ነው ? ብሎ ተቆጡኝ እረ ቲቸር ላሾፍ ስል አሾፉብኝ ብዬ ስስቅ ለካስ ከምራቸዉን ነበር ... አልረሣዉም ያንን ግጥም ብዙ ክፍሎች ሄጄ ማንበቤን
ያቺን አራት መሐዘን ጨረቃዬን ዛሬ በለመደ ሽክርክሮሽ የአዙርዮሽ ሳፈጥን ዛሬ ውስጤ ታግሎ ያመጣው አንዳች ዘመንኛ ገፅ ላይ አገኘዉት ... ማን ነበር ሳንወለድ በፊት ሙቶች ነበርን ግን የማናስታውሠው ሞት ያለው ....????????? እንደዛ ማለት ሁሉ ይመስለኛል ዛሬ ያሰብናቸው ዛሬ የወለድናቸው ዛሬ የፈጠርናቸው ሚመስሉን ምናብ ወይም ቅፅበታዊ ሃሳብ ሁሉ አንድ በረሣነው የጊዜ ግሥጋሤ ውስጥ በራሡ አዚም ብልጭ ብሎ የጠፋ ነገር ነው :: ማንኛዎቹም ንሑስ ሃሣቦች ሊንሠላሠሉ ሚችሉት በትላንትናዎቹ ምልከታና ቀመር ነውና ....

ዛሬ ሸራዬ ላይ ስትዞር ማያስታውቅባት ምድር ወይም ምድር ላይ ምታፈጥባት ጨረቃ የመንሿከኳ የምሑር ላይ መሟዘዝ እኔ በፈለግኩት የተለየ ምልከታ ማሠብን ሥሻ ያቺ የልጅነቴ አራት መሐዘን ጨረቃ ታውሠችኝ :: በቄንጠኛ ጉምድማጅ ደመናዎች ብቅ ብላ ለእኔ ብቻ የተለየ ዕይታን የሠጠችኝ ....
እንዲህ ከሆነማ የልጅነት ስፖንጅ አሕምሮዋችን የሕይወት ቁማር አንቀዥቅዦ እንደአረምም እንደ ችግኝም ያሳደገንን የገጠመኝ ወይም የጊዜ ሂደት ምስጢርን እንዴት ነበር ? እያልን ወደውኃላ ስንተረትር ልንቆይ ሆነ .... ያስፈራል ልበል ?

እስቲ ጀንበሯ አላርም ሳይቀሰቅሳት ጨረቃዬን ልያትና አልጋዬ ውስጥ በሕልም ልብሠል

ካምሣሚዳ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::

Last edited by ዋናው on Wed Sep 22, 2010 1:25 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Feb 05, 2008 3:57 am    Post subject: Reply with quote

ኬፍ ኬፍ

እቺን እንዳሻኝ ምወራጭባትን ቤቴን በክልፍልፉ ጊዜ ወደጓሮ ተጠልዛ ባያት ውስጤን የሀዘን ድባብ ሞላው
ሠሞንኛ ሠንበታችን ደግሞ በዛች ፓልቶክ ዋርካችን ውስጥ ከነአቡቲና ከነያሚታ ጋር የቅብጥርጥር ጊዜ እያልን በሽክርክር ሃሣብ ምንፈራገጠው ነገር የሆነ ደስታ እየሠጠኝ ነው ልበል ዳሩ እኔ የእንዲህ ዓይነቱ ሡሠኛ አይደለው ውቅሽ ደግሞ እቺን አምዴን ሜታሊክ ብሏታል ለካስ ሰው ያነባታል ማለት ነው ብዬ ደስ አለኝ ቅቅቅቅ

ዛሬ (በኔ የዚች ቤት አቆጣጠር ) ከትላንት ወዲያ ዘኪዮስን ሆኜ ራሴን የጠየቅኩትን ጥያቄ ልመልስ ነው አመጣጤ መመለስም ባይሆን አለ አይደል እንዲያው ተወራጭ ተወራጭ ቢለኝ እንደማለት ....
የዛሬ የምስል ሃሣቦች ፅንሣቸው ምንድነው ....አሁን ሁሉም ነገር ግጥግጥ ብሎ የሚታይ የመላምት ሥብጣሬ የምክኒያትና የንሑስ ሐሳቦች ሕዋስ ዝውውር የሸበሸባቸው የዝርጉ ሠፊ ዓለም ዕይታ ጥላን ባንድ ብረሐን ማስታረቅን ሊደፍር ያሰበን ደፋር ገፅ ግና ሚጎናፀፈው ብረሐን ተርቦ ውስጡን እየተጋጋመ ያለ አንዳች ትልቅ ..... ነገርም .....ወይም የሆነ ....ምንትስ ሊባል ማይችል ዓይነት ነው ::
ያስብከዉን ታገኛለህ የሚሉት ዓይነት የነ ኔል ዶናልድ ወይም የነዋላስ ዋትላስ ዓይነት ሃሳብ ውስጤን የሞገትኩት ቀን ውስጤ ያሾፈብኝን ግን አልረሳዉም .... በእርግጥ ''እኔ የሕይወቴ ማስተር ፒስ ነኝ '' ሚባለዉን እቀበለዋለሁ መልካም ነገሮችን ባንዳች መግነጢሳዊ ሥበት ወደቆሌ መሠብሠብ እንደሚቻልም አስባለው .....ግና ሁሉንም የወናበዱና ባንዳች ሕግጋት ልክ ሆነው የተሸፈኑ ዕውነታዎችን ፈልጎ ማግኘቱ ............. ቢቻልም ይርቃል :: እንደ አቡቲ የልጅነት የሠማይና የምድር መጋጠሚያ ...

ምስል በርግጥ የትም አለ እዚህ ....እዛ ..... ብረሐን ኖሮ ቀለም ከተጥበረበረ ሁሌም ምስል ነው ዱዳ እና ዜመኛ የመለያየታቸዉን ያክል ምስሎች መለያየታቸው እንጂ ..... በእርግጥም እስከተደረሰበት ድረስ ዕይታ ይኖራል ....እስከታየበት ድረስ ደግሞ ከታቢው ባለው ክኅሎት ያስቀምጣል ...ሸላይ .......ዘናጪ ..... የቁጩ ..... ብሎ ደረጃ ሚሠጥ ስለሆነ ከጥንቱም ድንቁርናን የመፈርጠጥ መንደርደር ዛሬም ድረስ በማለክለክ አለና ነው ቅሉ .....

እስቲ ለዛሬ ይብቃኝ ቡዳ የበላዉን እንቅልፌን ማባበል አለብኝ

ኬር ይሁን

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun Feb 10, 2008 1:30 pm    Post subject: Reply with quote

ሠንበቶቼን አስባርኬ ጥፎሾቼን አስፈውሼ ደግሞ ብቅ እላለው : የእንቅልፌ ቡዳ ምናብ ቀለም ሚያስተፋትን ያቺን ብሕሬንም አይቶብኝ ይሆን 'ንዴ ብዬ ' ተጠራጥሬ ነው : እርሣሥኛ ማውራት አምሮኛልና ሠኞ እመጣለሁ ዳሩ እርሣስ ደስ ሚለው ቢዶለዱምም መፃፉ ነው ::

ቸር ያቆየን ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
T

ኮትኳች

Joined: 11 Aug 2007
Posts: 290

PostPosted: Mon Feb 11, 2008 4:14 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ውቅሽ ደግሞ እቺን አምዴን ሜታሊክ ብሏታል

በፍቅር ውድድ የማደርጋት ስም የለሿ ቤት ስም ስለወጣላት congra ለማለት ነው ብቅ ማለቴ
_________________
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Feb 12, 2008 3:52 am    Post subject: Reply with quote

T እንደጻፈ(ች)ው:

በፍቅር ውድድ የማደርጋት ስም የለሿ ቤት ስም ስለወጣላት congra ለማለት ነው ብቅ ማለቴ

እውነትም እቺ ነገር አንባቢ አላት ማለት ነው ::

ቲጂዬ ለመጎብኘትሽ አመሠግናለሁ ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ትርንጎ 123

ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2008
Posts: 190

PostPosted: Tue Feb 12, 2008 4:08 am    Post subject: Reply with quote

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:
.......መልካም ነገሮችን ባንዳች መግነጢሳዊ ሥበት ወደቆሌ መሠብሠብ እንደሚቻልም አስባለው .....ግና ሁሉንም የወናበዱና ባንዳች ሕግጋት ልክ ሆነው የተሸፈኑ ዕውነታዎችን ፈልጎ ማግኘቱ ............. ቢቻልም ይርቃል :

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:
ዛሬ ያሰብናቸው ዛሬ የወለድናቸው ዛሬ የፈጠርናቸው ሚመስሉን ምናብ ወይም ቅስፈታዊ ሃሳብ ሁሉ አንድ በረሣነው የጊዜ ግሥጋሤ ውስጥ በራሡ አዚም ብልጭ ብሎ የጠፋ ነገር ነው :: ማንኛዎቹም ንሑስ ሃሣቦች ሊንሠላሠሉ ሚችሉት በትላንትናዎቹ ምልከታና ቀመር ነውና ....

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:
እርሣሥኛ ማውራት አምሮኛልና ሠኞ እመጣለሁ ዳሩ እርሣስ ደስ ሚለው ቢዶለዱምም መፃፉ ነው ::
ቸር ያቆየን ::

አሜን ! አንተንም እርሳስህንም ቸር ያቆይልን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Feb 23, 2008 2:59 am    Post subject: Reply with quote

እንደምናስጥልኝ (በውቃውኛ )

ሠሞናቱን ጊዜ ምትባለው አዚም በራሷ ስልጣን የኔን እሺታና እምቢታ ሳትጠብቅ 'ንደእንዝርት ስታሾረኝ ከራረመች ታዲያ በድካሞች ክርከሣ መሀል ሆኜ ነፍሴን ከረፈፉ ስጋዬ ላይ ጋደም ሳደርግ ያቺ ብሽክሊሊት መረሳቷ እንዳስኮረፋት ሁሉ ለምቦጯን ዘርግታ በምናቤ ውልብ አትልም ..........? ናፍቃኝ ነበርና ፔዷሏን የሽክርክሪት ብዘውራት ወረቀት እና እርሳስ ሳንይዝ ውስጣችን ምንቸከችካቸው ስኬቾች ትዝ አሉኝ ዕይታ ....ምልከታ ..... ምናብ .... ሕሣቤ .... እያልን እንዲሁ እንጥመለመል ነበር በጋንጢት ተወለካክፈን ጊንጎኛ እንሽከረከር ነበር : መቼም ውስጥ አመላልሠው አስልተው አምጠው ያኖሩት ሃሣብ ወደር አይገኝለትም :: ካንዳች የጣቶች ቀልቃላ መስመሮች የላቀ ክብደት አለው :: ታዲያ የምጥ ትዝታዬን ቅጭሜ የዋልዮሽ ስል ...... እኔን ባሰኮረፈው የግዜ ሀያቶች ተርታ ሲንዠዋዠው ሢንዠዋዠው ሄደና ድንገት አንድ ቦታ ገጭ አለ ::
በጣም ምወደው አንድ አውራ ዶሮ ጊቢያችን ነበረ ግርማሞገሡ ለደብዚ ዶሮ (ወርቃበባ ) ከመጡላት ባሎች ያስከነዳ ነበር ታዲያ ይሄን ዶሮ ልፊያ አስተምሬው እኔ ሙዴ ግድድ ብሎ መተናት የፈልግኩኝ ቀን ሁሉ ይመጣና ልክ ፍቅር እንዳበዛች ድመት ይታከከኛል ሢለው ይዘልና ወገቤ ጋር ደርሶ ጃስስስ ብሎኝ ይመለሣል : አንገቱ እንዲሁም የግራና ቀኝ ክንፉ ላይ ያለው ወርቃማ አረንጓዴ ላባው በጣም ደስ ይል ነበር : ቤቱስጥ እንግዳ መቶ የዚህን ዶሮ ልፊያ ሲያይ ልክ ሠርከስ ምሠራ ያህል ነበር ኩራቴ ወይም ዶሮኛ ቋንቋ የቻልኩኝ ይመስለኛል : አንዳንዴ በግድ ክንፉን እይዘዉና አንገቱን ጠምልዬ ክንፉ ስር ውሽቅ አደርገዉና በክንፉ መሬት ላይ እደፈዋለሁ :: ሠዉነቱ ስለሚከብደው ክንፉን ዘርግቶ አንገቱን ማውጣት አይችልም ልክ እንደሞተ በድን ሆኖ ይተኛል ... ይሄን ጊዜ ገደልኩት ብዬ ለእኩዮቼ ዲስኩሬን እነፋለሁ ሢደነግጡ በጣቴ ገፋ ሳደርገው ቆሞ ክንፉን ያራግብና ተከሻዉን ያርገፈግፍና ለልፊያ ይዘጋጃል ይሄን ጊዜም ልክ የሞተን እንደሚፈውስ ቡጥርር እል ነበር ::ብቻ እኔና ይሄ ዶሮ ማናሣየው ትርዒት ዓይነት አልነበረም ምግብ ከእጄ ቀምቶ ሁሉ ይበላል :
አንድ ቀን ይሄ ቀበጥ ዶሮ በሌለዉበት ሊታረድ ትወሠነ ሚፍልቀቅለቀው ውሃ የርሡን ቆዳ ለመገሽለጥ መሆኑን ስሠማ ....... ፊትለፊቴ የተዘጋጀው ሣፋና ቢላ ለሡ መሆኑን ሥሠማ የጨውኩት ጩኸት አይረሳኝም ምክኒያታቸው ''እያረጀ ነው ጥፍሩ ተጥመልምሎ ሊታጠፍ ነው ...'' ነበር ...ምነው የሠውን ጥፍር እያዩ መፍረድ ቢቻል እዚች ምድር ላይ ግን እንደሠው ፀረ -ነፍሥ ይኖር ይሆን ? አረጀ ብሎ አብሮአደግ ዶሮዬን አንገቱን ለካራ ሲያዘጋጂት ሠው መሆኔን ነው ያስጠላኝ :: ዶሮው ዛሬ ልፊያዉን ቀንሷል ሆዱ አንድ ነገር የነገረው ይመስላል የኩራት አረማመዱ ግን እንዳለ ነበር :: በለቅሦዬ ምታሾፍ ሠራተኛችንን እኔና ዶሮዬ የንዴት እያየናት
''አፈር ብሉና ግን እውነት ይሄንን ዶሮ አርዳቹ ልትብሉ ነው ?'' አልኳት
''አይ ዋንቾ ... አንተ እንዲያው ለሸረሪቱም ለወፉም ለውሻዉም ለድመቱም ለዶሮውም እንዳዘንክ .... '' እያለች ለሚፍለቀለቀው እሣት እንጨት ትመግባለች

''ዛሬ እዚህ የፈላ ውሃ ውስጥ እኔም ዶሮዬም አብረን እንገባለን እንጂ ....''
አልኳትና ዶሮዬን ይዤ ከግቢው ወጥቼ ፈረጠጥኩኝ ከሚንቋቋ ድምፁ ጋር እየተፈራገጠ ቢያስቸግረኝም ነፍሡን ማትረፍ እንዳለብኝ በዶሮኛ ነገርኩት ያው የዶሮ አምላክ ካለ ያስተረጉምልኛል ብዬ .... ከሠፈሩ ርቄ ዘመድ ቤት ወሠድኩትና እንዲያስቀምጡልኝ ነገርክዋቸዉና አስሬው ተመለስኩኝ :: ፍል ውሃ ዶሮው ስላመለጠው በብሽቀት ክዳኑን ገፍትሮ እሣቱን ችስስስስስስስስ እያስባለ ነበር :: ግን ዶሮዬ ከሞት ተርፏል

''ከፈለጋቹ እኔን እረዱኝ ...'' አልኳት ለሠራተኛችን

ያልተለምደ የልጅነት ፀባዬን መምከር ጆሮዬ ሰልችቶት ነበርና የዛንም የዶሮ ሕይወት ማትረፌ እደትልቅ ብኩንነት ተቆጠረብኝ :: እኔ ግን ትንሳሔ ሆኜ ነበር ::ዛሬ ዛሬ ሳስበው የደስታዎቻችንን ምንጮች አቅጣጫ ላይ ያለማተኮራችን ሞኝነት ይገርመኛል :: ምናለ እስቲ የእኔን እና የዶሮዬን ቅርርብ በቀናነት ቢወስዱት የዶሮው ቤተሠቦች የሠው ያህል ስልጣን ቢኖራቸዉና እኔን ልክ እንደዛ ለካራው አጭተው ቆዳዬን በዛ ፍል ውሃ ቢያንፍሩጽ .... ብዬ አስበኩኝ ::ታዲያ የዛ ምስኪን ዶሮዬ ሕይወት ያለፈው በዛ ሚፍለቀለቅ ውሃና በዛ ካራ ዓይኔ እያየ ቢሆን ኖሮ ስጋ መብላት ለማቆሜ እርግጠኛ ነበርኩኝ ::

ስለምን ብዬ የልጅነት ዶሮዬን አስታወስኩኝ ...? ያቺ መከረኛ የሃሣብ ብሽክሊሊት ናት አይደል እስቲ ወደእርሳስ ፍልሚያዬ ልመለስ ግራጫ ምናቦቼን ደግሞ የለብስክሌቴ ሦምሶማ ሆኜ እዘበዝባለሁ ለዛሬው ግን ቅንጥት ያለች ትኵስ ቅዳሜ ተኳኩላ እየጠበቀችኝ ነው በመልካም እንቅልፍ ልቀድሳት ::
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 12:33 am    Post subject: Reply with quote

ከዚች ቅብጥርጥር ቤቴ ላይ አንድ ዘለላ ፅሑፍ ተገንጥሏል ይመለስ ብያለሁ Wink
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እህምም

አለቃ

Joined: 19 Dec 2005
Posts: 2400
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 3:08 pm    Post subject: Reply with quote

and I thought you wouldn't notice. Laughing ..እስቲ የጻፍከውን ምልሼ አነበውና ኢፍ አይ ጌት ኢንስፓየርድ ይጣፋል ምን ችግር .... Smile
_________________
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09/homage-to-darkness/

"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አቡቲ

ኮትኳች

Joined: 09 Mar 2005
Posts: 113
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 3:43 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ዋናው

Quote:
ዛሬ የፈጠርናቸው ሚመስሉን ምናብ ወይም ቅስፈታዊ ሃሳብ ሁሉ አንድ በረሣነው የጊዜ ግሥጋሤ ውስጥ በራሡ አዚም ብልጭ ብሎ የጠፋ ነገር ነው ::አልገባኝም ብታብራራልኝ ደስ ይለኛል

ሌላው ግን እንደ
Quote:
'ሚመስሉን
የሚመስሉን ፈንታ
Quote:
ቅስፈታዊ
ያይደለ ቅጽበታዊ
Quote:
'ንኳን
... የመሳሰሉት በቋንቋ የዕድገት ሂደት ውስጥ ምን አይነት ድርሻ አላቸው ?

Smile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 5:40 pm    Post subject: ኅህምም Reply with quote

አቡቲ እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ዋናው

Quote:
ዛሬ የፈጠርናቸው ሚመስሉን ምናብ ወይም ቅስፈታዊ ሃሳብ ሁሉ አንድ በረሣነው የጊዜ ግሥጋሤ ውስጥ በራሡ አዚም ብልጭ ብሎ የጠፋ ነገር ነው ::

በምናቤ መተሳሰቢያሕ ላይ በደምብ ሕትመተ -ቁሱ ሳይያያዝ ቀርቶ ነዋ ! ቢያያዝ ኖሮ ብልጪ ብሎ ድርግም ባላለም ነበር !! የየኔታን ግን ይመልሱ !

አልገባኝም ብታብራራልኝ ደስ ይለኛል

ሌላው ግን እንደ
Quote:
'ሚመስሉን
የሚመስሉን ፈንታ
Quote:
ቅስፈታዊ
ያይደለ ቅጽበታዊ
Quote:
"ንኳን
... የመሳሰሉት በቋንቋ የዕድገት ሂደት ውስጥ ምን አይነት ድርሻ አላቸው ?

Smile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 3 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia