WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5065

PostPosted: Mon Aug 11, 2008 5:07 pm    Post subject: Reply with quote

Rolling Eyes Listen the truth from the coach Rolling Eyes

http://www.ethiopiafirst.com/Radio/Dr_Woldemeskel_Kostere_11Aug08.mp3
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዶማው 2005

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 04 Jun 2005
Posts: 1631
Location: United States

PostPosted: Mon Aug 11, 2008 7:34 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ የኛ አገር ሩዋጮች መቸ እንደሚሮጡ ንገሩኝ ...ሜዳል ስቆጥር እኛ የለንበትም ገና ....ሰአት እና ቀን ...ፕሊዝ

ሰላም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Tue Aug 12, 2008 6:14 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዶማው አማን ነህ ? እንኳን ፕሊስ ተብለን ሳንባልም ከች ነው ........ ይኸው የመሮጫችን ሰሀት ......... ታዲያ ሰአቱ በቤጅንግ አቆጣጠር ነው ......
ዶማው 2005 እንደጻፈ(ች)ው:
እስኪ የኛ አገር ሩዋጮች መቸ እንደሚሮጡ ንገሩኝ ...ሜዳል ስቆጥር እኛ የለንበትም ገና ....ሰአት እና ቀን ...ፕሊዝ

ሰላም

Date Time (Beijing Time) Event
Friday,August 15,
19:10-19:35 Men's 1500m Round1
20:25-21:10 Women's 3000m Steeplechase Round 1
22:45-23:20 Women's 10000m Final

Saturday, August 16,
09:20-10:00 Men's 3000m Steeplechase Round 1

Sunday, August 17,
07:30-11:20 Women's Marathon Final
21:30-21:46 Women's 3000m Steeplechase Final
21:55-22:15 Men's 1500m Semifinals
22:45-23:20 Men's 10000m Final

Monday, August 18,
21:10-21:25 Men's 3000m Steeplechase Final

Tuesday, August 19,
10:00-10:30 Women's 1500m Round 1
19:35-20:41 Women's 5000m Round 1
22:50-23:00 Men's 1500m Final

Wednesday, August 20,
20:15-21:15 Men's 5000m Round 1

Thursday, August 21,
19:00-19:20 Women's 1500m Semifinals

Friday, August 22,
20:40-21:02 Women's 5000m Final

Saturday, August 23,
19:50-20:02 Women's 1500m

Final
20:10-20:30 Men's 5000m Final

Sunday, August 24
07:30-10:40 Men's Marathon Final
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዶማው 2005

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 04 Jun 2005
Posts: 1631
Location: United States

PostPosted: Wed Aug 13, 2008 5:16 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አንበርብር ..አመሰግናለው ...ወደ እኛው ሰአት እቀይረዋለው ..ታንክስ ኤጌን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ኩዛ

ኮትኳች

Joined: 09 Nov 2004
Posts: 441
Location: ባህር ማዶ

PostPosted: Wed Aug 13, 2008 7:12 am    Post subject: Reply with quote

ቀነኒሳ ሱፐርስታር
_________________

EthioTube - Broadcast Ethiopia
http://www.ethiotube.net
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Thu Aug 14, 2008 10:07 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዋርካ ስፖርት : በተለይም የቤጂንግ ኦሎምፒክ ተከታታዮች !

እኛ ኢትዮጵያዊያን በጉጉት የምንጠብቀው አትሌቲክስ (Track & Field) ነገ አርብ : August 15, 2008 ይጀመራል :: ነገ በጉጉት ከሚጠበቁት ውድድሮች አንዱ የሴቶች 10,000M ፍጻሜ ነው :: ይህ ውድድር የሚካሄደው 10:45PM (በቤጂንግ አቆጣጠር ) ወይም 10:45AM (Eastern Time) ነው :: {በነገራችን ላይ በቤጂንግ እና ዲሲ /ሌሎች የኢስተርን ታይም ዞኖች / መካከል ልክ 12 ሰዓት ልዩነት ነው ያለው .......ስለዚህ ውድድሩ ሲካሄድ ቤጂንግ ምሽት ሲሆን ዲሲ ግን ገና ጠዋት ይሆናል }:: ውድድሩ በሚካሄድበት ሰዓት ቲቪ ማየት ለማትችሉ እና ስራ ላይ ሁናችሁ ኮምፒዩተር ላይ ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ማየት የምትችሉ ይመስለኛል ... http://www.nbcolympics.com/trackandfield/index.html
*****ይመስለኛል ያልሁት ዛሬ ብዙ ውድድሮች እዚህ ዌብሳይት ላይ ላይቭ ሲተላለፉ ስለነበር እና እኔም አንዱን ውድድር ስሞክረው ያለምንም ችግር ማስተላለፍ ስለጀመረ ነው :: ከዛ ውጭ እንደሚተላለፍ ምንም ኮንፈርሜሽን የለኝም :: ለማንኛውም ሰዓቱ ሲደርስ ሊንኩን ከፍታችሁ ላይቭ ከሚተላለፉት ውድድሮች ውስጥ የሴቶች 10,000M መሮሩን ቼክ አድርጉ ..........እንደሚተላለፍ ተስፋ አለኝ :: ሌሎች ፕሮግራሞችንም እንደየፍላጎታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ ::

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ኩዛ

ኮትኳች

Joined: 09 Nov 2004
Posts: 441
Location: ባህር ማዶ

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 1:04 am    Post subject: Reply with quote

ምሩጽ ይፍጠር ሰንደቃችንን በቤጂንግ ሲያውለበለብ
_________________

EthioTube - Broadcast Ethiopia
http://www.ethiotube.net
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 1:29 am    Post subject: Reply with quoteእነዚያ ረጅም አራት አመታት አልፈውልን ወራቶችን ቆጥረን ሳምንታትን አምልጠን ከቀናቶች ሸሽተን ጀግኖች አትሌቶቻችንን ለማየት ሰሀታት ቀርተውናል :: አሁን ከእኛ የሚጠበቀው ቀናትን መቆጠር ሳይሆን ሜዳልያዎችን ይሆናል :: ከዛሬው ከሴቶች 10,000M ልጀምርና 1 ልበል :: በዛሬው 10,000M ሩጫ የሀገራችንን መስመር ከሚመሩት ውስጥ በጉጉት የምትጠበቀዋ ወጣቷ : ለግላጋዋ 23 አመቷ ጥሩነሽ ዲባባ ስትሆን ...... ጥሩነሽ እስካሁን 4 ግዜ የወርልድ ሻምፒወን በመሆን : እንዲሁም 5 ወርልድ ክሮስ ካንትሪ ቻምፒወን በመሆን በጥቅሉ 9 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በአንገቷ አጥልቃለች :: ጥሩነሽ 5 M ሪከርድ ባለቤትም ነች :: ጥሩነሽ በኦሎምፒክ መድረክ እስካሁን ወርቅን ያላገኘች ስትሆን ስለ ቤጅንጉ ተጠይቃ ስትመልስ "I race for my country. I do not want to disappoint my country."
...... "I would have liked to win gold. My aim is always gold."
ነበር ያለችው :: እንደርሷ አባባል ዛሬ በቤጅንግ ምሽት መላው ኢትዮጵያውያን አንገታቸውንየሚደፉበት አጋጣሚ አይታይም ማለት ነው :: ከላይ ስለ ጥሩነሽ አነሳን እንጅ ከጥሩነሽ ጀርባም ታላቅ እህቷ እጅጋየሁ : መስተዋት ቱፋና ውዴ አያሌውም የዛሬው የቤጅንግ አድማቂዎች ናቸው :: ምናልባት ዛሬ ልጆቻችን 1-3 ያለውን ቦታ ከተቆጣጠሩት 8 አመታት በፊት ሲድኒ የተሰራውን ታሪክ ይደግሙታል ማለት ነው ........... ድል ይሸተኛል ......... መሮጥ ... መሮጥ ... ሀይል ... ወኔ .... ጉልበት .... መሮጥ ...... መሮጥ መጨረሻ ድል ....... ከድል በኌላ ደስታ ..... የግል ደስታ የጋራ ደስታ ...... መልካም እድል ለጀግኖች አትሌቶቻችን ...........
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 3:42 pm    Post subject: Reply with quote

ShyBoy እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የዋርካ ስፖርት : በተለይም የቤጂንግ ኦሎምፒክ ተከታታዮች !

እኛ ኢትዮጵያዊያን በጉጉት የምንጠብቀው አትሌቲክስ (Track & Field) ነገ አርብ : August 15, 2008 ይጀመራል :: ነገ በጉጉት ከሚጠበቁት ውድድሮች አንዱ የሴቶች 10,000M ፍጻሜ ነው :: ይህ ውድድር የሚካሄደው 10:45PM (በቤጂንግ አቆጣጠር ) ወይም 10:45AM (Eastern Time) ነው :: {በነገራችን ላይ በቤጂንግ እና ዲሲ /ሌሎች የኢስተርን ታይም ዞኖች / መካከል ልክ 12 ሰዓት ልዩነት ነው ያለው .......ስለዚህ ውድድሩ ሲካሄድ ቤጂንግ ምሽት ሲሆን ዲሲ ግን ገና ጠዋት ይሆናል }:: ውድድሩ በሚካሄድበት ሰዓት ቲቪ ማየት ለማትችሉ እና ስራ ላይ ሁናችሁ ኮምፒዩተር ላይ ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ማየት የምትችሉ ይመስለኛል ... http://www.nbcolympics.com/trackandfield/index.html
*****ይመስለኛል ያልሁት ዛሬ ብዙ ውድድሮች እዚህ ዌብሳይት ላይ ላይቭ ሲተላለፉ ስለነበር እና እኔም አንዱን ውድድር ስሞክረው ያለምንም ችግር ማስተላለፍ ስለጀመረ ነው :: ከዛ ውጭ እንደሚተላለፍ ምንም ኮንፈርሜሽን የለኝም :: ለማንኛውም ሰዓቱ ሲደርስ ሊንኩን ከፍታችሁ ላይቭ ከሚተላለፉት ውድድሮች ውስጥ የሴቶች 10,000M መሮሩን ቼክ አድርጉ ..........እንደሚተላለፍ ተስፋ አለኝ :: ሌሎች ፕሮግራሞችንም እንደየፍላጎታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ ::

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !!!!

ትናንት የሰጠኋችሁ ሊንክ የሴቶችን 10,000M ውድድር ላይቭ የሚያስተላልፍ አይመስልም :: ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ሪቪው እንደሚያስተላልፈው ገልጿል እና እንደኔ ቲቪ ላይ ለማየት ያልተመቻችሁ እዚህ ሂዱና ተከታተሉ .... http://www.ethiopianreview.com/ 5ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው ውድድሩ ሊጀመር ::

ድል ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 4:23 pm    Post subject: Reply with quote

እንኳን ደስ ያለን !!!!

በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የትኛውም ሊንክ ላይ ላይቭ ማየት ባልችልም ላይቭ ቴክስት ኮሜንቶች ስከታተል ነበር ........ ቢቢሲ ጥሩነሽ ወርቅ እንዳገኘች ገልጿል :: ዝርዝሩን ገና አልገለጸም ::

በድጋሜ እንኳን ደስ ያለን !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 4:25 pm    Post subject: Reply with quote

! አሁን በትቂቱ ዘርዘር አድርገው ጻፉት

Code:
1618: Brilliant. Defending champion Tirunesh Dibaba bides her time before overtaking Turkey's Elvan Abeylegesse and sprinting home in a new Olympic record time of 29:54.68 - the second fastest women's 10,000m of all time. Brave run from Abeylegesse to claim silver with American Shalane Flanagan claiming bronze.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
sarandem

ዋና ኮትኳች

Joined: 11 Jul 2006
Posts: 539
Location: Nomad Cafe

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 4:32 pm    Post subject: Reply with quote

ውይ ሻይ ቦይ በመቼ ቀደምከኝ :: ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመርያውን የወርቅ ሜዳልይ ጀባ ብላናለች :: እንኳን ደስ ደስ አለን Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ወርቅሰው 1

ዋና አለቃ

Joined: 05 Nov 2003
Posts: 3350
Location: Sehalin

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 4:32 pm    Post subject: ጥሩዬ ! Reply with quote

በሬዱ ገነሙ !
የኢትዮጵያ አንበሳ ጥሩነሽ ዲባባ :: እንኳን ደስ ያለን የኦሎምኪክንም ሬከርድ በመስበር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዲያሊያ አስገኝታለች :: እጅግ ከፍተኛ ስራን የጠየቀ ሩጫ ነበረ :: ከሙቀቱ ጋር ግን ጥሩዬ ምንም ሳይመክታት የኦሎምፒክ ንግሥትነቷን አረጋግጣለች :: እጅግ ደስተኛ ነበርኩ :: ያኢንተሎ እረቢ ሲያኬኙ !!! አድካሚና እልህ አስጨራሽም ነበረ :: ግን አንበሳዋ ምንም አልበገራትም :: ጥሩ የመንፈስ መረጋጋቶች ይታዩባት ነበር :: እንደምታሸንፍም በሚገባ ታውቀው ነበር :: አባይ ለገሰም ብትሆን ደስተኛ የሆነች ይመስለኛል ደክሟት ስትተነፍስ ምነው አመመሽ ወይ ብላ የምትጠይቃትም ይመስል ነበር :: እጅግ ደስተኛ የሚያደርግ የቤይጂን ቀን ነበር ማለቱ ይሻላል ::አባይ ለገስም ጥሩዬን በመሳም ደስተዋን ስትገልጽላት ሲመለከቱት ምንኛ ያስደስት ነበር ::
ወርቅሰው 1
(ሰሐሊን )
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ብናስተውል

ዋና ኮትኳች

Joined: 31 Jan 2006
Posts: 987

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 4:50 pm    Post subject: Reply with quote

ዋውውውውውውውውው .....
እንኳን ደስ ያለን ወገኖቸ :: እጅግ በጣም ነው የተደሰትኩት :: ሰሞኑን ስራ ወጥሮኝ ዋርካ እርባኝ ሰንብታ ዛሬ ጎራ ስል ከድል ጋር በመሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል ::
አዎ ወርቅሰው እንዳልከውም እጅግ እልህ አስጨራሽ ውድድር ነበር :: የአገር ወኔ ነው ለጥሩዬ ድል ያበቃት እንጅ ሙቀቱ እጅግ እንደከበዳቸው ከነመስታውትና እጅጋየሁ ሁኔታ መረዳት ይቻላል :: ቢሆንም ግን ጥሩዬ ሁሌም አንበሳና የአገር ወኔ የሚያቃጥላትና ለምንም ለማንም የማትበገር አንበሳ በመሆኗ የቀድሞዋን ኢትዮጵያዊት ያሁኗን ቱርክ አበይ ለገስ ኃይለኛ ሩጫ ተቋቁማ ለድል በቅታለች ::
አበይ ለገስም እጅግ አደገኛ አትሌት መሆኗን የተመዘገበው የኦሎምፒክ ሪከርድ ያስመሰክራል :: ግን እንኳንም አንደኛ ወጥታ ጸጸት ውስጥ አልጨመረችን ::
ጥሩዬ ሁሌም መኩሪያችን እጅግ በጣም እንወድሻለን በርችልን ወርቃችን ::
የቤጅንግ ሙቀት ግን ለአትሌቶቻችን እጅግ የከበዳቸው ይመስለኛል :: 1500 ሜትርና 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ላይም ተስፋ የነበራቸው ልጆቻችን ወደ መጨረሻ አካባቢ ኃይል ሲያሳጣቸው ተስትወለዋል :: ለዚህም የአትሌትክስ ፌደሬሽኑ የቤጅንግን ሙቀት ሳይለማመዱት በቀጥታ ከአዲስ አበባ እያመጣ ማሰለፉ ተጠያቂ የሚሆን ይመስለኛል :: እስቲ ደግሞ እሁድ ደርሶ 10000 ሜትር ወንዶች አትሌቶቻችንን የድል ውጤት ለማየት ያብቃን ::

ከሜዳሊያ ሰንጠረዥ ሳትታይ የቆየችው አገራችንም በጥሩዬ አማካኝነት ዛሬ ዝርዝሩ ውስጥ ትገባልናለች ማለት ነው ::

በነገራችን ላይ በኢንተርኔት ለማየት ለምትፈልጉ የሚከተለውን ሊንክ ክሊክ በማድረግ በአትሌቲክስ ውድድር ሰአቶች ውስጥ ቻናል -1 ላይ መመልከት ትችላላቹህ :: 12 ቻናሎች አሉትና ሌሎች ስፖርቶችንም እንዲሁ ማየት ትችላላቹህ ::

http://www.eurovisionsports.tv/olympics/

የቤጅንግ ኦሎምፒክስ 10000 ሜትር ንግስት !!! ጥሩዬ !!!

ድል ለብርቅዬ አትሌቶቻችን ::
_________________
Selam le-Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Aug 15, 2008 5:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖቼ :-

እሰይ እሰይ እሰይ !!!

በጥሩነሽ አንድ ብለናል ::

ቀደም ብለው በተደረጉት የማጣሪያ ውድድሮች ደግሞ :
1,500 ሜትር ወንዶች : ደረሰ መኮንን እና ሙሉጌታ ወንድሙ ለተከታዩ ዙር ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ::

3,000 ሜትር መሠናክል ሴቶች : ዘምዘም አህመድ ለተከታዩ ዙር ውድድር አልፋለች ::

አትሌቶቻችን በቀሪዎቹም ውድድሮች ተጨማሪ ሜዳሊያዎች : ተጨማሪ ደስታ ያቀዳጁናል ::

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን !!!

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 53, 54, 55  Next
Page 2 of 55

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia