WARKA Forum Index
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 
Become a supporting member
CyberEthiopia Home | About us | Contact us
መዳን በሌላ በማንም የለም ሐዋ 4;12
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General
 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Fri Feb 05, 2010 10:34 pm    Post subject: መዳን በሌላ በማንም የለም ሐዋ 4;12 Reply with quote

መዳን በማንም በሌላ የለም ሐዋ 412
ኦርቶዶክሳዊያን ከብዙ ፕሮቴስታንቶች ጋር በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ እንወያያለን። ሌላውን ብተወው እንካን እዚህ ዋርካ ውስጥ ከብዙዎች ጋር ተነጋግረናል። ለሁላችንም ለኦርቶዶክሳዊያን የሚጠቅሱልን ጥቅስ ሐዋ 412 ላይ የተጠቀሰውን በርእሱ ያስቀመጥሁትን “መዳን በሌላ በማንም የለም” የሚለው ቃል ነው። [/u][/b]በተለይም ሲናደዱና የሚሸነፉ ከመሰላቸው የሚጠቅሱት ጥቅስ መዳን በሌላ በማንም የለምና ኢየሱሰ ጌታ ነው የሚሉት ናቸው። ብዙ ፕሮቴስታንቶች ይህንን ጥቅስ የማናምን አይመስላቸውም ወይም ደግሞ ከራሳችን ፈጥረን ተጨማሪ ያመጣንበት ይመስላቸዋል። አንዳንድ በመጽሐፍት ያልዘለቁ ክርስቲያኖችንም ይህንን ጥቅስ የፕሮቴስታንት ጥቅስ ሲሉት ሰምቻለሁ። ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ሁሉ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መልእከት የራሷ ጥቅስ እንጂ የሌላ የሚሰጥ ጥቅስ የለንም።

ይህንን ጥቅስ ይዘው አንዳንዶች ለመዳን ከኢየሱስ ውጭ ወደ ላይም ወደ ታችም መሄድ አያስፈልግም ይላሉ። አወ እኛ ይህንን እናምናለን። መዳናችን የተፈጸመው በክርስቶስ ኢየሱስ ነው። አዳኝም እርሱ ነው ስብራታቸንን የጠገነ ከደዌችን የፈወሰን እርሱ ነው። ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን መድሃኒዓለም /የዓለም መድሃኒት፤ መዳኛ / ብላ የምትጠራው። እርሱ ስሙ ከስም በላይ የሆነ መዳኛ የሆነ ስም ነው። ስሙም ክቡር ስለሆነ እንዲሁ በየቦታው አታነሳውም ማንሳት በሚገባን ቦታ ግን የጌታን ስም እንጠራለን። አንዳንዶቹም እንደሚሉት ኢየሱስ ጌታ ነው ቱፓክ መላጣ ነው ብለን በጌታ ስም አንቀልድም።

ታዲያ አዳኝ ኢየሱስ ብቻ ከሆነ የቅዱሳን ስሞችን እንዴት እንጠራለን ?

አንዳንዶች ይህ ግራ ገብቷቸው ተወናብደው ቀርተዋል። መዳን በኢየሱስ ብቻ ከሆነ ለምን ጸበል እንሄዳለን ? መዳንስ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ከሆነ በቅዱሳን ስም በሆነ ጸበል እንዴት እንጠመቃለን ? መዳንስ በኢየሱስ ብቻ ከሆነ የቅዱሳንን በረከት እንዴት እንፈልጋለን ? ይህ ሁሉ ከፕሮቴስታንቶች የሚወርድና የሚዠጎደጎድ ጥያቄ ነው።
የነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ምርምር አያስፈልግም ነገር ግን የምታነበውን ታስተውለዋለህን ተብሎ እንደተጠየቀው ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ /ሐዋ 830/ መጽሐፉን በማስተዋልና በመረዳት በትህትናም ማንበብ ያስፈልጋል። ምክነያቱም መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ሳይሆን ትሁታን ይረዱታል። ሁሉን አውቀናል ከሚሉ ሰውሮ ጌታ ለታናናሾች ገልጾታልና።
በመጀመሪያ እንደቤተ ክርስቲያን እምነት በቅዱሳን ስም የሚደረግ ማናቸውም ነገር ራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አለበት። በቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምም ይሁን በቅዱሳን ስም የሚደረግ ነገር ሁሉ ራሱ ባለቤተ አለበት። ጸጋቸውን የሰጠ ክብራቸውን ያበዛ ራሱ ኢየሱስ ስለሆነ። ኢየሱስ ያልሰጠውን ስለጣን ቤተ ክርስቲያን ለቅዱሳን አልሰጠችም አትሰጥምም።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳኑ የሰጣቸው ክብር በምድር እንዲሁ የሚቀር በእኛ ብቻ የሚታይ አይደለም የዓለም ፍጻሜ ሲሆን እንዲፈርዱ ስልጣን ሰጧቸዋል። አንተ መንግስተ ሰማያት ትገባለህ አንተ አትገባም የማለት ስልጣን ኢየሱስ ሰጥቷል። ከዚህ የበለጠ ስልጣን በመንፈሳዊው አለም የለም። ከማማለድ ከማዳን የበለጠ ስልጣን መፍረድ ነው።
ማቴ 19-27-28 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን ? አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ስራ ይሰራል ከዚህም የሚበልጥ ብሎ በፍጹም እምነት እርሱን ለተከተሉ ቅዱሳን ሰጥቷል። ይህም ማለቱ ከእርሱ የሚበልጥ ስራ ምንድን ነው ? ኢየሱስ ሙታንን እንዳስነሳ ጎባጣ እንዳቀና ድውያንን እንደፈወሰ ድውየንን መፈወስ፤ ሙታንን ማስነሳት፤ ልዩ ልዩ ታምራት ማድረግ ነው። ይህም አንደኛ በህይወት እያሉ ቅዱሳን ፈጽመውታል አሁንም በስማቸው ታምራት ይደረጋሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ በጸበል ሰዎች ሲድኑ ነበር /ዮሐ 5/ ታዲያ በኢየሱስ ስም ብቻ ነው የሚዳን የሚለውን ቃል እንደመናፍቃኑ ከተረጎምነው መጽሐፍ ቅዱሱን የሚጋጭ አድርገነው ቀረን ማለት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መድሐኒቱ ነው። በቅዱሳንም ስም ይሁን በጻድቃን ስም ብንጠራ የሚያድነው እርሱ ነው ነገር ግን እርሱ ስለእነርሱ ይከብር ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው። የጴጥሮስ ጥላ ሲያድን በጥላው አድሮ የሚያድን እርሱ ነው። የጳውሎስም ጨርቅ ሲያድን የሚያድነው እርሱ ነው። ግን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ይከብር ዘንድ የእነርሱ ጨርቃቸው ያድናል፤ የሞተው ገላቸው ሰዎች የጣሉት የቀበሩት በድን ይፈውሳል፤ቀሚሳቸው ሃይል አለው። ስማቸውም ሀይል አለው። በድንግል ማርያም ስም ሰይጣን ይታሰራል፤ በጳውሎስ በጴጥሮስ ስልጣን ሰይጣን ይታሰራል፤ በቅዱስ ሚካኤል ሰይፍ ጠላት ሰልጣን ይታሰራል። እነርሱ እግዚአብሔር አለባቸውና።

ለመረጃ ይሆነን ዘንድ የሚከተለውን ጥቅስ ብቻ እንመልከት ሐዋ 1911-17
እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤

የጳውሎስን ታምር ብቻ እንመልከት፡ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጂ የሚያሰገርም ታምራት ያድርግ ነበር። ታምሩን የሚያደርገው /የሚያደነው / ራሱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፡ ከአካሉ ጨርቅ ከቀሚሱ ከሱሪው ማለቱ ነው። ከልብሱ ሲል ከሚደርበው ከልብሱ ሲል ደግሞ ከሚደርበው ከመጎናጸፊያው ይሆናል። በአጠቃላይ እግዚአብሔር ጳውሎስን ሁለንተናውን አክብሮታል። የማን ልብስ ነው ሊያደን የሚችል ከእውነተኞቹ ቅዱሳን ውጭ የማን ልበስ ነው መናፍስትን የሚየስወጣ እግዚአብሔር ካከበረው ቅዱስ ውጭ። በዚህም መንገድ የቅዱስ ጳውሎስ ከልብሱ ይልቅ ስልጣኑ ከልብሱ ይልቅ ስሙ እንዴት አይከብር። ለዚህም ነው የቅዱሳን ስሞች ያደናሉ እርሱ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና። በእነርሱ ይከብር ዘንድ ያድናልና።

አሁንም ማዳን የሚችለው እርሱ ኢየሱስ ነው እርሱ ግን በፈለገው አድሮ ያድናል። እግዚአብሔርን አሰራር ማን ይከሳል። አቤሜሌክን አብርሃም ይጸልይልህና እኔ ልማርህ ያለ አምላክ ነው። የዛሬዎችን አይነት ሰዎች እንደሚሉት ቢሆን ኖሮ ለምን መንገድ ያረዝማል ? ራሱ ማዳን እየቻለ እርሱ ይጸልይልህ እንዴት ይላል ? ለሶስቱ ሰነፎች ኢዮብ ይጸልይላችሁና ላድናችሁ እንዴት ይላል ? ራሱ በቀጥታ ማዳን ሲችል። ይህ ሁሉ እግዚአብሔር እንዲከበር ነው። ደግሞም የወዳጆቹን ክብር እግዚአብሔር መግለጥ ደስ ያሰኘዋል። በእውነት እግዚአብሔር ሚስጢሩን ከአብርሃም ይሰውራልን እንዳለው ራሱ ጌታ እግዚአብሔር። እግዚአብሄር ቅዱሳንን ስለሚያደርገው አስቀድሞ ይገልጣል አማክሮም ያውቃል፡ እርሱ ምክር የሚፈልግ ሆኖ አይደለም እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ መሆኑን መግለጥ ስለፈለገ እንጂ። እግዚአብሄር የቅርብ አብሮን ያለ ነው። ለበረከቱና ለስጦታው ወሰን የሌለው ነው። ለቅዱሳን የሰጣቸው ክብር ከዚህ አንጻር የምናየው ነው። እርሱ ፈቃዱ ስለሆነ የቅዱሳንን ስም እንጠራልን፡ እርሱ በእነርሱ አድሮ ስለሚያድን አድኑን ብለን አንማጸናቸዋልን። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ያልተረዱ ደግሞ እግዚአብሔርን ለማስተካከል መንገዱን ጠመዝማዛ አደረግኸው አስተካክል ብለው ከጌታ ጋር ይሟገታሉ። ጌታ ግን አሰራሩ ድንቅ ነው።

የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን የቅዱሳን በረከታቸው ድል የማትነሳ ሃይማኖታቸው ጥርጥር የሌለባት እምነታቸው ከእኛ ጋር ትሁን። አሜን
ጊዜ ካለን እንመለስበታለን። እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ ተጠቅመን እንድንድን ያድርገን። ኦርቶዶክሳዊያን ጨምሩበት። ጥያቄ ያላችሁ ሰዎችም ክርስቲያኖች ለጥያቄችሁ ሁሉ መልስ አለን። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና ::
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ሀሁሁሁ

ኮትኳች

Joined: 20 Jan 2006
Posts: 252

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 1:53 am    Post subject: Reply with quote

Salvation is found in no one else, for there is no other name under heaven given to men by which we must be saved

መዳን በማንም በሌላ የለም :: እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ሌላ ስም የለም ::

ዘእግዚነ

የመጽሀፊ ክፍል የሚያወራው ስለ ዘላለማዊ ህይወት "salavation " ነው :: ስለስጋ ፈውስ አይደለም ::

የስጋ ፈውስንም በተመለከተ

እግዚአብሔርም በሰዎች ተጠቅሞ የሚያሰገርም ታምራት ያድርግ ነበር አሁንም ያደርጋል :: የጠቀስከውን የመጽሀፍ ክፍል ብናይ በሀዋርያቶቹ ልብስ እንኩዋን ይጠቀም ነበር ::

ይህ የሚያፋቅ እውነት ነው :: ዛሬም እግዚያብሔር በተለያየ መንገድ ይሰራል ::

ችግሩ ያለው አገልጋዮቹ ስም ሀይል አለው የሚለው መረዳት ነው :: ከቃሉ ጋር የሚቃረን :: ራስህ የጠቀስከውን የመጽሀፍ ክፍል አስተውለህ ብታነበው የጳውሎስ ስም ሀይል አለው የሚል አይደለም :: የአስቄዋ ልጆች ከጳውሎስ ኮርጀው ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ ከዚያ አጋንንቱ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ ? አላቸው ..ከዚያ በረታባቸው አቆስላቸው ....

አስቄዋ ልጆች እንኩዋን በጳውሎስ ስም አላሉም ..አንተ አስቄዋ ልጆች እንዴት አትሻልም ...??????

አሁንም መዳን በማንም በሌላ የለም :: እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ሌላ ስም የለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ወቸውጉድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 11 Mar 2006
Posts: 1766

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 2:36 am    Post subject: Re: መዳን በሌላ በማንም የለም ሐዋ 4;12 Reply with quote

ዘእግዚነ እንደጻፈ(ች)ው:

ይህንን ጥቅስ ይዘው አንዳንዶች ለመዳን ከኢየሱስ ውጭ ወደ ላይም ወደ ታችም መሄድ አያስፈልግም ይላሉ። አወ እኛ ይህንን እናምናለን። መዳናችን የተፈጸመው በክርስቶስ ኢየሱስ ነው። አዳኝም እርሱ ነው ስብራታቸንን የጠገነ ከደዌችን የፈወሰን እርሱ ነው። ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን መድሃኒዓለም /የዓለም መድሃኒት፤ መዳኛ / ብላ የምትጠራው። እርሱ ስሙ ከስም በላይ የሆነ መዳኛ የሆነ ስም ነው። ስሙም ክቡር ስለሆነ እንዲሁ በየቦታው አታነሳውም ማንሳት በሚገባን ቦታ ግን የጌታን ስም እንጠራለን። አንዳንዶቹም እንደሚሉት ኢየሱስ ጌታ ነው
የኢየሱስን ስም ክቡርነት ካመንክና : ከዛ ስም ሌላ ምንም አዳኝ ስም ከሌለ : ከዚያ ስም ውጭ የሚጠራም አይኖርም :: መጽሀፍ እንደሚል "ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር : አምላክም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ ::..አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነውና ; የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል :: ይህንን የጌታ ኢየሱስን ስም በየስፍራው የሚጠሩ የተቀደሱ የአምላክ ልጆች ናቸው :: የጻድቃንንና የመላእክትን ስም ልንጠራ አይደለም የተጠራነው : ነገር ግን ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን የኢየሱስን ስም ልንጠራ ነው እንጂ :: ለዚህ ስም ፍጥረት ሁሉ ይንቀጠቀጣል :: ፊል 2:9-11
Quote:
[b]ታዲያ አዳኝ ኢየሱስ ብቻ ከሆነ የቅዱሳን ስሞችን እንዴት እንጠራለን ?
አዳኝ ኢየሱስ ብቻ ስለሆነ የሌሎችን ስም ለመዳን አንጠራም :: አጋንንታዊ አስተምህሮ ነው :: መጽሀፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ላይ የቅዱሳንን ስም ለመዳን እንድንጠራ አያዘንም :: አንድና አንድ ስም ብቻ እንጠራለን : እሱም ኢየሱስ ::
Quote:
አንዳንዶች ይህ ግራ ገብቷቸው ተወናብደው ቀርተዋል።
አንዱ አንተ ነህ ::
Quote:
መዳን በኢየሱስ ብቻ ከሆነ ለምን ጸበል እንሄዳለን ? መዳንስ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ከሆነ በቅዱሳን ስም በሆነ ጸበል እንዴት እንጠመቃለን ? መዳንስ በኢየሱስ ብቻ ከሆነ የቅዱሳንን በረከት እንዴት እንፈልጋለን ? ይህ ሁሉ ከፕሮቴስታንቶች የሚወርድና የሚዠጎደጎድ ጥያቄ ነው።
ይሄ ሁሉ መጽሀፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ ተራ ሀተታ ነው :: ጸበል የሚባል ነገር የለም :: ጸበል የጉድጉዋድ ውሀ ነው : ከዚያ ያለፈ ነገር የለውም :: የጌታ ኢየሱስ ስም እንጂ የጉድጉዋድ ውሀ ሀይል የለውም ::
Quote:
የነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ምርምር አያስፈልግም ነገር ግን የምታነበውን ታስተውለዋለህን ተብሎ እንደተጠየቀው ኢትዮጲያዊ ጃንደረባ /ሐዋ 830/ መጽሐፉን በማስተዋልና በመረዳት በትህትናም ማንበብ ያስፈልጋል። ምክነያቱም መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ሳይሆን ትሁታን ይረዱታል። ሁሉን አውቀናል ከሚሉ ሰውሮ ጌታ ለታናናሾች ገልጾታልና።
የጠቀስከው ክፍል ጸበልም ሆነ ቅዱሳን አዳኝ ናቸው አይልም ::
Quote:
በመጀመሪያ እንደቤተ ክርስቲያን እምነት በቅዱሳን ስም የሚደረግ ማናቸውም ነገር ራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አለበት። በቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምም ይሁን በቅዱሳን ስም የሚደረግ ነገር ሁሉ ራሱ ባለቤተ አለበት። ጸጋቸውን የሰጠ ክብራቸውን ያበዛ ራሱ ኢየሱስ ስለሆነ። ኢየሱስ ያልሰጠውን ስለጣን ቤተ ክርስቲያን ለቅዱሳን አልሰጠችም አትሰጥምም።
ሰኔ ጎልጎታን ጠቅሰህ ካላቀረብክ በቀር : በአምላክ ቃል ውስጥ እንዲህ አይነት አጋንንታዊ አስተምህሮ የለም ::
Quote:
ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳኑ የሰጣቸው ክብር በምድር እንዲሁ የሚቀር በእኛ ብቻ የሚታይ አይደለም የዓለም ፍጻሜ ሲሆን እንዲፈርዱ ስልጣን ሰጧቸዋል። አንተ መንግስተ ሰማያት ትገባለህ አንተ አትገባም የማለት ስልጣን ኢየሱስ ሰጥቷል። ከዚህ የበለጠ ስልጣን በመንፈሳዊው አለም የለም። ከማማለድ ከማዳን የበለጠ ስልጣን መፍረድ ነው።
ማቴ 19-27-28 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን ? አለው። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
ትፈርዳላችሁ ማለቱ ምን ማለቱ ይሆን ? እስቲ አብራራልኝ ? ጌታ ኢየሱስ ቃሌ ይፈርዳልም ብሏል ይሄንን ሲልስ ምን ማለቱ ነበር ?
Quote:
ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ስራ ይሰራል ከዚህም የሚበልጥ ብሎ በፍጹም እምነት እርሱን ለተከተሉ ቅዱሳን ሰጥቷል። ይህም ማለቱ ከእርሱ የሚበልጥ ስራ ምንድን ነው ? ኢየሱስ ሙታንን እንዳስነሳ ጎባጣ እንዳቀና ድውያንን እንደፈወሰ ድውየንን መፈወስ፤ ሙታንን ማስነሳት፤ ልዩ ልዩ ታምራት ማድረግ ነው። ይህም አንደኛ በህይወት እያሉ ቅዱሳን ፈጽመውታል አሁንም በስማቸው ታምራት ይደረጋሉ።
ሀዋርያቶች ያደረጉት ታምራት በሙሉ በጌታ ኢየሱስ ስም ሀይል እንጂ በራሳቸው አይደለም :: አንድም ቦታ ላይ በሀዋርያት ስም የተደረገ ታምር የለም ::
Quote:
በመጽሐፍ ቅዱስ በጸበል ሰዎች ሲድኑ ነበር /ዮሐ 5/ ታዲያ በኢየሱስ ስም ብቻ ነው የሚዳን የሚለውን ቃል እንደመናፍቃኑ ከተረጎምነው መጽሐፍ ቅዱሱን የሚጋጭ አድርገነው ቀረን ማለት ነው።
የት ነው ሰዎች በጸበል የዳኑት ? ማስረጃ አቅርብ :: ኢየሱስ ከሞሞቱ በፊት : የአምላክ መልአክ እየተገለጠ : ውሀውን ሲያናውጥ ቀድሞ የገባ ሰው ብቻ ይድን ነበር :: አንድ ሰው ብቻ ነው ይድን የነበረው :: ኢየሱስ ሞቶ ከሞት ሲነሳ ግን : አምላክ ኢየሱስን ጌታና ክርስቶስ አደረገው :: ስሙንም እጂግ ከፍ አደረገለት : ይህ ስም ብቻ ያድናል ; ይፈውሳል ይታደጋል ::
Quote:
ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መድሐኒቱ ነው። በቅዱሳንም ስም ይሁን በጻድቃን ስም ብንጠራ የሚያድነው እርሱ ነው ነገር ግን እርሱ ስለእነርሱ ይከብር ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው።
አንድም ቦታ የቅዱሳንን ስም እንድንጠራ አልታዘዝንም :: አጉል ትህትናንና የመላእክት አምልኮን የምትወዱት እናንተ : ወደ ክርስቶስ አትቀርቡም ::
Quote:
የጴጥሮስ ጥላ ሲያድን በጥላው አድሮ የሚያድን እርሱ ነው። የጳውሎስም ጨርቅ ሲያድን የሚያድነው እርሱ ነው። ግን እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ይከብር ዘንድ የእነርሱ ጨርቃቸው ያድናል፤ የሞተው ገላቸው ሰዎች የጣሉት የቀበሩት በድን ይፈውሳል፤ቀሚሳቸው ሃይል አለው።
ይሄ በነጴጥሮስ ስም ሀይል ታምር ተደረገ ማለት አይደለም ::
Quote:
ስማቸውም ሀይል አለው። በድንግል ማርያም ስም ሰይጣን ይታሰራል፤ በጳውሎስ በጴጥሮስ ስልጣን ሰይጣን ይታሰራል፤ በቅዱስ ሚካኤል ሰይፍ ጠላት ሰልጣን ይታሰራል። እነርሱ እግዚአብሔር አለባቸውና።
ፍካሬ ኢየሱስ ምእራፍ የለም ቁጥር ግዴለም Laughing Laughing
Quote:
ለመረጃ ይሆነን ዘንድ የሚከተለውን ጥቅስ ብቻ እንመልከት ሐዋ 1911-17
እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
አምላክ በጳውሎስ እጅ ብዙ ታምራት ያደርግ የነበረው : በኢየሱስ ስም ሀይል እንጂ በጳውሎስ ሀይል አልነበረም ::
Quote:
የጳውሎስን ታምር ብቻ እንመልከት፡ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጂ የሚያሰገርም ታምራት ያድርግ ነበር። ታምሩን የሚያደርገው /የሚያደነው / ራሱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፡ ከአካሉ ጨርቅ ከቀሚሱ ከሱሪው ማለቱ ነው። ከልብሱ ሲል ከሚደርበው ከልብሱ ሲል ደግሞ ከሚደርበው ከመጎናጸፊያው ይሆናል። በአጠቃላይ እግዚአብሔር ጳውሎስን ሁለንተናውን አክብሮታል። የማን ልብስ ነው ሊያደን የሚችል ከእውነተኞቹ ቅዱሳን ውጭ የማን ልበስ ነው መናፍስትን የሚየስወጣ እግዚአብሔር ካከበረው ቅዱስ ውጭ። በዚህም መንገድ የቅዱስ ጳውሎስ ከልብሱ ይልቅ ስልጣኑ ከልብሱ ይልቅ ስሙ እንዴት አይከብር። ለዚህም ነው የቅዱሳን ስሞች ያደናሉ እርሱ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና። በእነርሱ ይከብር ዘንድ ያድናልና።
ታምራቱ በኢየሱስ ስም ሀይል ነው የተደረገው :: የጳውሎስ ታምር አይደለም :: እዚሁ እኮ ታምረ ጳውሎስ ብለህ ገድል ልትጽፍ የፈለክ ያስመስልብሀል Laughing Laughing
Quote:
አሁንም ማዳን የሚችለው እርሱ ኢየሱስ ነው እርሱ ግን በፈለገው አድሮ ያድናል። እግዚአብሔርን አሰራር ማን ይከሳል። አቤሜሌክን አብርሃም ይጸልይልህና እኔ ልማርህ ያለ አምላክ ነው። የዛሬዎችን አይነት ሰዎች እንደሚሉት ቢሆን ኖሮ ለምን መንገድ ያረዝማል ? ራሱ ማዳን እየቻለ እርሱ ይጸልይልህ እንዴት ይላል ? ለሶስቱ ሰነፎች ኢዮብ ይጸልይላችሁና ላድናችሁ እንዴት ይላል ? ራሱ በቀጥታ ማዳን ሲችል። ይህ ሁሉ እግዚአብሔር እንዲከበር ነው። ደግሞም የወዳጆቹን ክብር እግዚአብሔር መግለጥ ደስ ያሰኘዋል። በእውነት እግዚአብሔር ሚስጢሩን ከአብርሃም ይሰውራልን እንዳለው ራሱ ጌታ እግዚአብሔር። እግዚአብሄር ቅዱሳንን ስለሚያደርገው አስቀድሞ ይገልጣል አማክሮም ያውቃል፡ እርሱ ምክር የሚፈልግ ሆኖ አይደለም እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ መሆኑን መግለጥ ስለፈለገ እንጂ። እግዚአብሄር የቅርብ አብሮን ያለ ነው። ለበረከቱና ለስጦታው ወሰን የሌለው ነው። ለቅዱሳን የሰጣቸው ክብር ከዚህ አንጻር የምናየው ነው። እርሱ ፈቃዱ ስለሆነ የቅዱሳንን ስም እንጠራልን፡ እርሱ በእነርሱ አድሮ ስለሚያድን አድኑን ብለን አንማጸናቸዋልን። የእግዚአብሔርን ሐሳብ ያልተረዱ ደግሞ እግዚአብሔርን ለማስተካከል መንገዱን ጠመዝማዛ አደረግኸው አስተካክል ብለው ከጌታ ጋር ይሟገታሉ። ጌታ ግን አሰራሩ ድንቅ ነው።
አንድም ቦታ ላይ የቅዱሳንን ስም ጥሩ አይልም ::
Quote:
ጥያቄ ያላችሁ ሰዎችም ክርስቲያኖች ለጥያቄችሁ ሁሉ መልስ አለን።
Laughing Laughing Laughing ከታምረ ማርያም ካልሆነ በቀር : ከአምላክ ቃል መልስ የላችሁም Wink Wink ፉከራም ይመስላል Crying or Very sad
_________________
"REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ጨምጫሚ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Sep 2009
Posts: 950

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 3:06 am    Post subject: Reply with quote

ዘእግዚነ የተባረከ ነገር እንደጻፍክ እግዜር ይባርክህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 4:45 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
[quote="ሀሁሁሁ "Salvation is found in no one else, for there is no other name under heaven given to men by which we must be saved
መዳን በማንም በሌላ የለም :: እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ሌላ ስም የለም ::

ሀሁ ቃሉን ምን አስደገመህ :: ከላይ እንደገለጽሑት ፈርተሀል ማለት ነው ወይስ ..........

Quote:
ዘእግዚነ

የመጽሀፊ ክፍል የሚያወራው ስለ ዘላለማዊ ህይወት "salavation " ነው :: ስለስጋ ፈውስ አይደለም ::

ጥሩ እስኪ ከቁጥር 1-14 ያለውን ቃል አንብበው :: የእኔ እምነት ዘለአላማዊ ህይወትም ሆነ በስጋ መዳን ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ናቸው :: በረከታቸ ትድረስንና ቅዱሳን ቢያድኑም በእርሱ በተሰጣቸው ጸጋ መሆኑንና ቅዱሳን አዳኑ ሲባል እግዚአብሔርም አብሮ እንዳለ እንደማይለይ ለመግለጥ ነው የፈለግሁት ::

[/quote]
Quote:
የስጋ ፈውስንም በተመለከተ
እግዚአብሔርም በሰዎች ተጠቅሞ የሚያሰገርም ታምራት ያድርግ ነበር አሁንም ያደርጋል :: የጠቀስከውን የመጽሀፍ ክፍል ብናይ በሀዋርያቶቹ ልብስ እንኩዋን ይጠቀም ነበር
ይህ የሚያፋቅ እውነት ነው :: ዛሬም እግዚያብሔር በተለያየ መንገድ ይሰራል ::

በእውነት ይህንን ካመንህ በአሁኑ ጊዜ ለምን ቤተ ክርስቲያንን ከሳሽ እንደሆነህ ታስተውለው ይሆን። እግዚአብሔር በፈለገው አድሮ ያድናል። እግዚአብሔር በውሃ ያድናል፤ እግዚአብሔር በእመነቱ ያድናል ሲባል ለምን ግራ ገባችሁ ወዳጀ ? ይህንን ልንገነዘብ ይገባል። እግዚአብሔር በመጽሐፉ ባልተጻፈም መንገድ ሊያድን ይችላል ቃሉን የሚቃረን እስካለሆነ ድረስ።

Quote:
ችግሩ ያለው አገልጋዮቹ ስም ሀይል አለው የሚለው መረዳት ነው :: ከቃሉ ጋር የሚቃረን ::

ሀሁ ከጳውሎስ ስምና ከጨርቁ የሚበልጠውን አሳየኝ እስኪ እንግዲህ ጨርቁ ከየት ሀይል አግኝቶ አዳነ ? በእውነት ጨርቅ ሊያድን ይችላል ? ያንተ ጨርቅ ያድናል እንደማያድን እርግጠኛ ነን :: ታዲያ ግኡዙ ነገር እንዲያድን ያደረገ እግዚአብሔር ከሆነ እግዚአብሔር በፈቀደው ያድናል የሚለውን ማመን ለምን አቃተህ ? ወይስ ጨርቅ ሀይል አለው የሚል ጥቅስ እንፈልግ :: ጨርቅ ሀይል አለው የሚል ጥቅስ አታገኝም :: ደግሞስ እግዚአብሔርን በአረፍተ ነገር ብቻ ልትወስነው ትፈልጋለህን ?

Quote:
አስቄዋ ልጆች እንኩዋን በጳውሎስ ስም አላሉም
.
እኔ ከእግዚአብሐየር ቃልና ከወዳጆቹ ህይወት እንጂ በሰይጣን መንፈስ ከሚሰሩት እንዴት ልማር ብለህ ነው ? ይህንን ይህንን ለእናንተ ሰጥተናል ::

Quote:
አሁንም መዳን በማንም በሌላ የለም :: እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠን ሌላ ስም የለም ::

ከላይ የተናገርሁትን አስታወስከኝ ለምን ኢየሱስ ጌታ ነው ቱፓክ መላጣ ነው [/code] የሚለውን መፈከር ረሳከው ?
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 5:28 am    Post subject: Re: መዳን በሌላ በማንም የለም ሐዋ 4;12 Reply with quote

ወቸውጉድ እንደጻፈ(ች)ው:
ነገር ግን ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን የኢየሱስን ስም ልንጠራ ነው እንጂ :: ለዚህ ስም ፍጥረት ሁሉ ይንቀጠቀጣል :: ፊል 2:9-11

ታዲያ ስሙ የተዋረደ ነው አያስፈለግም የሚል ጽሑፍ ከእኔ አንብበህ ይሆን ? ከላይ የጻፍኩትን አንብብ አሁንም ደግሜ የምነግርህ ግን እናንተ ስሙን መቀለጃ እንዳደረጋችሁት ነው በየጸሎት ቤታችሁ ኢየሱስ ጌታ ነው ቱፓክ መላጣ ነው የሚለውን መፈከራችሁን እስካልተዋችሁት ድረስ የኢየሱሰን ስም እየጠራን ነው ብለህ እንዳትናገር የእግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የሚለውን ትዕዛዝ እየተላለፋችሁ እንደሆነ ተገንዘቡ።

Quote:
አዳኝ ኢየሱስ ብቻ ስለሆነ የሌሎችን ስም ለመዳን አንጠራም :: አጋንንታዊ አስተምህሮ ነው :: መጽሀፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ላይ የቅዱሳንን ስም ለመዳን እንድንጠራ አያዘንም :: አንድና አንድ ስም ብቻ እንጠራለን : እሱም ኢየሱስ ::

ጅሉ አጋንንት አጋንንት የምትለው አንተ ነህ አንጂ እኔስ ጨርቁ ሊያድን የቻለን የጳውሎስን ስም ከመጥራት ወደ ሗላ አልልም። እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ እንደሚፈውስ አውቃለሁ። አንተ ግን ጨርቁ በራሱ አዳነ ልትለኝ እንደምትፈልግ ገብቶኛል እንደ እናንተ ሰዎች ማለት ነው።
Quote:
ጸበል የጉድጉዋድ ውሀ ነው : ከዚያ ያለፈ ነገር የለውም

እኔ ከሰማይ የወረደ ውሃ ነው አላልሁህም። እግዚአብሔር አዳኝ ስለሆነ ፈቃዱንም የሚቃወመው ስለሌለ በጸበሉም ይሁን በእምነቱ አድሮ ድሮ በጥንት ጊዜ እንደፈወሰ አሁንም ያድናል። ካልተዋጠልህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተጣላ። ወይም ፓራሲታሞል ዋጥና ተኛ Laughing Laughing

Quote:
የጠቀስከው ክፍል ጸበልም ሆነ ቅዱሳን አዳኝ ናቸው አይልም ::

ስንት ጊዜ ላስረዳህ ወዳጀ አዳኙ ከላይ እንደተጠቀሰው አንዱ እርሱ እግዚአብሔር ነው። ቅዱሳንን ግን እግዚአብሔር ለማዳን ይጠቀምባቸዋል በረከት ሰጥቷቸዋል። ጴጥሮስም ሆነ ጳውሎስ ሲያድኑ አብሯቸው እግዚአብሔር አለ። እግዚአብሔር በእነርሱ ለመዳን ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ ቅዱሳን አያድኑም ነበር። እግዚአብሔር ጸጋውን ከሰጠ ምን እንላለን። ገባህ ? ካልገባህ ወደ መካ ዞረህ ጸልይ መሐመድ ያስተምርሃል። Laughing Laughing

Quote:
ትፈርዳላችሁ ማለቱ ምን ማለቱ ይሆን ? እስቲ አብራራልኝ ? ጌታ ኢየሱስ ቃሌ ይፈርዳልም ብሏል ይሄንን ሲልስ ምን ማለቱ ነበር ?

ከላይ ጠቀምጧል አንብበው። ቅዱሳን ይፈርዳሉ። ቃሌ ይፈርዳል ሲል ቃሉ መመሪያ ይሆነን ዘንድ አለ። በዚያ ቃል የሄዱትና ያልሄዱት በቃሉ መሰረት ይለያሉ ማለት ነው። ከባድ ነገር አይደለም። ጌታ በእርሱ ዘንድ አድልኦ የለም የሚፈርደው በተቀመጠው ቃል መሰረት ነው።
Quote:
አጉል ትህትናንና የመላእክት አምልኮን የምትወዱት እናንተ : ወደ ክርስቶስ አትቀርቡም

እግዚአብሔር ትቢተኞችን ይቃወማል ትሁታንን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ወደ ክርስቶስ መቅረብ ማለት እኮ ትእዛዛቱን መፈጸም እንጂ እንዳንተ ኢየሱሰ ጌታ ነው ቱፓክ መላጣ ነው ብሎ ሰው ማደንቆር አይደለም። ሰነፍ።

Quote:
ታምራቱ በኢየሱስ ስም ሀይል ነው የተደረገው :: የጳውሎስ ታምር አይደለም :: እዚሁ እኮ ታምረ ጳውሎስ ብለህ ገድል ልትጽፍ የፈለክ ያስመስልብሀል

ከላይ ያልሁትን አንብብ። የተለየ ሐሳብ አልገለጽሁም አንተ ክርክር ስለምትወድ ነው። ገድለ ጳውሎስን መጻፍ ብችል እንዴት ታደየ ነበር ግን አላቻልሁም። አሁንም በኢትዮጲያ ውስጥ የሚደረጉ ልዩ ልዩ ታምራትን ለመጻፍ አስቤላሁ ታዲያ ገድለ ቅዱሳን የሚል መጽሐፍ ጠብቅ።
Quote:
ከታምረ ማርያም ካልሆነ በቀር : ከአምላክ ቃል መልስ የላችሁም ፉከራም ይመስላል

አንተ እግዚአብሔርን በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ብቻ የቀረ አድርገኸዋል ? እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው ስራውም ዘለኣለማዊ ነው። ታምረ ማርያም ሲጻፍም እግዚአብሔር ይሰራል ከተክለ ሃይማኖትም ጋር እግዚአብሔር ነበረ ወደ ፊትም ይኖራል። ፉከራችን በወንጌል አናፍርም ነው። አንዱን ጥለው ሌላውን አንጠልጥለው አንደሚሄዱ መናፍቃን ምን አሳፈረን።

የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተመሰገነ ይሁን።
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ጨምጫሚ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Sep 2009
Posts: 950

PostPosted: Sat Feb 06, 2010 7:21 am    Post subject: Reply with quote

ወቸጉድ ለምን ክርክር አስፈለገ ከዚህ በፊት ተሰለቻችተን የተውነውን ነገር ማንሳት አስፈላጊ አይመስለኝም እንደማታምን የታወቀ ነው እኛም ለማሳመን መሞከር ከንቱ ድካም ነው ስለዚህ ቺል አውት http://www.youtube.com/watch?v=lUGUYMtT2CI
ዘእግዚነ ወቸጉድ ማለት እኮ እዚ ላይ ሱፍ አርጎ እጁን እያወናጨፈ ሚከራከረው ፓስተር አይነት ነው Laughing ....... አሁን ይህ ፓስተር የመናፍቅ መንፈስ አደንዝዞታል አንድ ጊዜ ሰው በዚህ መንፈስ ከደነዘዘ ደግሞ የፈለገ ነገር ቢፈጠር በጭራሽ አያምንም Laughing Laughing Laughing Laughing እንደዚህ አይነቶቹን መተው ነው ሚሻለው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ሀሁሁሁ

ኮትኳች

Joined: 20 Jan 2006
Posts: 252

PostPosted: Mon Feb 08, 2010 8:56 pm    Post subject: Reply with quote

ዘእግዚነ እንደጻፈ ():

Quote:
እኔስ ጨርቁ ሊያድን የቻለን የጳውሎስን ስም ከመጥራት ወደ ሗላ አልልም። እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ እንደሚፈውስ አውቃለሁ

እንዴት የከፋ እምነት ነው ! እውን የጳውሎስን ስም የማዳን ሀይል አለው ብለህ ታምናለህ ?

ስልጣን ያለው ስም የኢየሱስ ስም ብቻ ነው ! የሚያድን የሚፈውስ ነጻ የሚያወጣ : የሚፈጥር የሚገል የሚያነሳ ..

ስሙ ብሩክ ይሁን

http://www.youtube.com/watch?v=knDuDtw2HZI&feature=related[/quote][/code]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Mon Feb 08, 2010 10:05 pm    Post subject: Reply with quote

ሀሁሁሁ እንደጻፈ(ች)ው:
ዘእግዚነ እንደጻፈ ():
Quote:
እኔስ ጨርቁ ሊያድን የቻለን የጳውሎስን ስም ከመጥራት ወደ ሗላ አልልም። እግዚአብሔር በእርሱ አድሮ እንደሚፈውስ አውቃለሁ

እንዴት የከፋ እምነት ነው ! እውን የጳውሎስን ስም የማዳን ሀይል አለው ብለህ ታምናለህ ?
ስልጣን ያለው ስም የኢየሱስ ስም ብቻ ነው ! የሚያድን የሚፈውስ ነጻ የሚያወጣ : የሚፈጥር የሚገል የሚያነሳ ..

ስሙ ብሩክ ይሁን

ሰላም ሀሁ : እኔ አንተ ስላላስተዋልህ ነው እንጂ ከላይ እንደገለጽሑት የጳውሎስን ስም ለምን እንደምጠራ የኢየሱስን ስም ደግሞ ለምን እንደምጠራ አውቃለሁ :: ሙሴ የአባቶቹን ሰም እንደጠራ እኛም የተወደዱ የሐዋርያትን ስም እንጠራለን :: እስኪ አንተ ሀሁን የዘለቀ እውቀት ካለህ ያነሳነው ርእስ ላይ የተጠቀሰውን አንድ ጥቅስ አብራራልኝ ::

እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።

1.እርኩሳት መናፍስት እንዴት በጨርቅ ሊዎጡ ቻሉ ?
2. አንተ እንደምትተረጉመው ከኢየሱስ ስም ውጭ እግዚአብሄር የማያድን ክሆነ ጨርቁ የኢየሱስ ስም ነበር የሚል ጽሑፍ የት አለ ?
3.ታዲያ ጨርቁ ካዳነ ሌላው ነገር አያድንም ለማለት እንዴት ደፈር ?

በመጨረሻ ግን የማሳስብህ ለምን ኢየሱስ ጌታ ነው ቱፓክ መላጣ ነው የምትለዋን መፈከር ረሳሀት ? ተሳዳቢው ወቸውጉድ በዚያው ጠፍቶ እንዳይቀር ጥራው ::
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ሀሁሁሁ

ኮትኳች

Joined: 20 Jan 2006
Posts: 252

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 1:04 am    Post subject: Reply with quote

ዘእግዚነ

ካሰመርክ ሁሉንም አስምረው እንጂ .

እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበርስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።

እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም። ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤

የተዐምራቱ ባለቤት እግዚያብሔር ነው :: በማን ተጠቀመ በጳውሎስ ..እግዚያብሔር የሚያስገርም ተአምራቶች በጳውሎስ እጅ ያደርግ ነበር :: ጳውሎስ በማን ስም ነበር ተአምራትን የሚያደርገው በእግዚያብሔር ስም ይህንን እንዴት እናውቃለን .. ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።

ጨርቁ በራሱ ፈውስ አላመጣው ..እግዚያብሔር ስለተጠቀመበት እንጂ ..አጋንንት የወጣው ጨርቅ ነክቶት አይደለም .በጨርቁ ላይ ካደረው ከእግዚያብሔር ሀይል የተነሳ እንጂ ..

ጨርቁን የወሰዱት ድውያን በጳውሎስ ስም አልተፈወሱም :: ጳውሎስ በሚሰብከው በጌታ እየሱስ ስም ነው የተፈወሱት ::

ዘእግዚነ

እግዚያብሔር በዘመናት በተለያየ መንገድ ይሰራል :: በተለያዪ ሰዎች ይጠቀማል :: በዘመናት እንግዳን ነገር ያደርጋል :: እርሱ እግዚያብሔር ነውና ::

ክብር ዝና ስግደት ሁሉ ለስሙ ብቻ ይሁን .

ካለበለዚያ

ለቀይ ባህር መከፈል - ሙሴን
ለዮርዳኖስ ተአምር - እያሱን

ወዘተ እያመሰገንን ልንኖር ነው ..

ክብር ለእግዚያብሔር ይሁን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 4:15 am    Post subject: Reply with quote

ሀሁሁሁ እንደጻፈ(ች)ው:
ዘእግዚነ

ጨርቁን የወሰዱት ድውያን በጳውሎስ ስም አልተፈወሱም :: ጳውሎስ በሚሰብከው በጌታ እየሱስ ስም ነው የተፈወሱት ::

ክብር ለእግዚያብሔር ይሁን

በማነኛውም መንገድ ይሁን የሚያድን እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ በመጀመሪያ ገልጫለሁ ::

ጨርቁን የወሰዱት ሰዎች በኢየሱስ ስም ተፈወሱ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ልታሳየኝ ትችላለህ ?
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ዘእግዚነ

ኮትኳች

Joined: 28 Oct 2009
Posts: 257

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 4:19 am    Post subject: Reply with quote

ሀሁሁሁ እንደጻፈ(ች)ው:
ዘእግዚነ

ጨርቁን የወሰዱት ድውያን በጳውሎስ ስም አልተፈወሱም :: ጳውሎስ በሚሰብከው በጌታ እየሱስ ስም ነው የተፈወሱት ::

በማነኛውም መንገድ እግዚአብሔር ብቻ አዳኝ እንደሆነ ካላይ ገልጨልሀለሁ :: አሁን ከተናገርክው የምጠይቅህ ጨርቁን የወሰዱ ሰዎች በኢየሱስ ስም ተፈወሱ የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ልታሳየኝ ትችላልህ ?
_________________
እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ማቴ 24፤13
http://www.wongelforall.wordpress.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ጨምጫሚ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Sep 2009
Posts: 950

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 10:51 am    Post subject: Reply with quote

የማቴዎስ ወንጌአስራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠራ ሁለት ሁለቱንም ይልካቸው ጀመር፥ በርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው፥
የማርቆስ ወንጌል
አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።
የሉቃስ ወንጌ
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።
እግዚአብሄር ለጻድቃንና ለመላእክቱ ስልጣን ይሰጣል ያድናሉ ይፈውሳሉ አጋንንትን ያስወጣሉ ..........በእግዚአብሄር ፈቃድ ....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ጨምጫሚ

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Sep 2009
Posts: 950

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 11:04 am    Post subject: Reply with quote

ሁሁሁ እየሱስ ክርስቶስ በሱ ስም ብቻ ሳይሆን በሚወዳቸው ሁሉ መላእክት ጻድቃን በማርያም ስም አጋንንት እንደወጡ ድውያን እንደፈወሱ እየሱስ ክርስቶስ ስልጣን ሰጥቷል ::
እንግዲህ የሚቀጥለው ጥያቄህ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ አሳየኝ እንደሆነ አልጠራጠርም !
ሳትጠይቀኝ ልመልስልህ ...... አልተጻፈም መጽሀፍ ቅዱስ ላይብረሪ ወይም ዊኪፒዲያ አደለም !...ግን ደግሞ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ በጻድቃን ስም ድውያን አይፈወሱም የሚል ጥቅስ የለም !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

ሸዋ ነህ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 07 Oct 2009
Posts: 63
Location: us

PostPosted: Tue Feb 09, 2010 3:04 pm    Post subject: Reply with quote

ጨምጫሚ :- ብዙ ጊዜ እንደታዘብኩህ ማጨብጨብ በጣም ተወዳለህ :: በውርስ ወይስ ከህይወት በልምድ የተገኘ ችሎታ ነው ይሄ አጨብጫቢነት ?
ሌላም ችሎታ አለህ :: ስለማታውቀው ነገር ልክ እንደምታውቅው ሆነህ በድፍረት ታብራራዋለህ ቂቂቂቂቂቂቂ አብራራው ጨምጭሜ !!
_________________
"REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post

Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia