WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ወዲ ትግራይ እራሰህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ !!
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Hagoss

አዲስ

Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Sat Apr 17, 2010 10:43 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ደሐን ደሐን ትግራዋያት /!!
ሓየት 11 ለተጨማሪ መረጃህ አመሰግናለሁ ::

ከላይ የቀጠለ
በሕወሓት ውስጥ በተሰገሰጉ የሻቢያ ሰርጎ ገቦች

ፖለቲካን በተመለከተ የተፈጸሙት ደባዎች

1. 1966 ሕዝባዊ አብዮትን ተከትሎ ብዙ ብሔራዊና ሕብረብሔራዊ ድርጅቶች እንደተፈጠሩ ሁላችንም ከታሪክ ማሕደር የምንገነዘበው ሰለሆነ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ በድጋሚ ሁሉንም የድርጅት አይነቶችና ብዛት መዘርዘሩ አስፈላጊ አይሆንም :: ከነዝህ ከብዙዎቹ ድርጅቶች ውስጥ ሕወሓት አንዱ ድርጅት ስለነበር ትኩረቴም በዚሁ ድርጅት ዙርያ ይሆናል ::

ሕወሓት ( ሕዝባዊ ወያን ሓርነት ትግራይ ) በወቅቱ በነበሩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሌሎችንም የክፈለሀገሩን ተወላጆች ያካተተ ድርጅት 1967 . ተመሰረተ ::

ከላይ የተገለጹት የነመለስ -ስብሀት ቡድንም በድርጅቱ ውስጥ እንዲካተቱ ተድረገ :: በድርጅቱም ውስጥ ወሳኝ የስልጣን ቦታ ተርክበው ይኸው እስከ አሁን ድረስ አሉ ::

የሻቢያ ሰርጎ ገቦች በሕወሀት ውስጥ የተሰገሰጉት በእኛ የትግራይ ተወላጆች ወገናዊ የሆነ ቅን መንፈስና የውንድማማችነት አመለካከትና እምነት ስለነበረን , የትግል እንቅስቃሴአችን ደግሞ አትኩሮቱ ከጨቋኙ ስርኣት ጋር ነው ብለን በመወሰን ያለምንም ጥርጣሬ ሆነ የተንኮል እሳቤ ተቀብለን ትግሉን አብረን ወደፊት ለመግፋት ወስነን ተነሳን ::

ለዚህም ውሳኔ በየዋኽነት ሳንጠራጠር የሻቢያን ሰርጎገቦች እንድንቀበል ካድረጉት ምክናዬቶች ውስጥ በጥቂቱ ለመግለጽ ያክል :
1 በትግራይና በኤርትራ ተወላጆች መሀከል ምንም አይነት የቋንቋ ልዩነት አለመኖሩ

2 በመሀከላችን የባህል , የወግና የስነልቦና ልምዶች ምንም ኣይነት ልዩነቶች የሌላቸው በመሆናቸው ::

3- በጆግራፊ አዘረጋግ ኩታ -ገጠም በመሆናችን በትግራይና አሁን ራሳቸውን ኤርትራውያን ያሉት ህዝቦች በኗኗር ተሰባጥረው ስለሰፈሩ :: ከዚህም ጋር በተያያዘ የነ መለስ - ሰበሀት ቡድኖች ወላጆቻቸው አብዛኞቹ ትግራይ ውስጥ ይኖሩ ስለ ነበር እንደ ትግራዋይ አድርገን በማመናችን ::

ይህንንና ሌላውንም ውስጣዊና ውጫዊ ገጠመኞችን በመጠቀም የነ መለሰ -ስብሀት ቡድን የበግ ለምድ ለብሰው የቀበሮ ባሕታዊ ሆነው --------

-እንደ ድርጅት ሕወሓት ውስጥ ተሰግስገው

-እንደ ፖለቲካ አላማና ግብ ግን የሻቢያን አጀንዳ
በብብታቸው ውስጥ ሸጉጠው በመሰሪ ተንኮላቸውና ጥሬ በሚቆላ ምላሳቸው ትግራውያንን ጊዜና ወቅታዊ ገጠመኞችን በመጠቀም እኛ ሳናውቅ ለሊት ጨለማን ተገን አድርገው እየተደብቁ በማሴር ትግርራዋያንን ተራ በትራ እየነጠሉ :

1-ከድርጅቱ በማባረር ,

2 -በድብቅ በማሳፈን , ደብዛውን በማጥፋት (06 )

3 -በጦር ሜዳ ውስጥ እየተዋጋ እያለ ከሁዋላ እንዲገደል በማድረግ ,

4 -ድርጅቱን ጥሎ ወደ ውጭ አገር እንዲኮበልል በመገፋፋት

5- ፖለቲካውን ለመደበቅ እንዲመች በማይረባ ግድያ እንዲሞቱ በማድረግ >>> ( ክንፈ /መድሕን , አይሎም አርኣያ )

6- የትግራዋይንና የትግራዋይትን ሰነ ልቦና ለማዳከም ሻቢያን በጣም የሰለጠነና የገዘፈ አስመስለው ውስጥ ውስጡን በመለፈፍ የሕወሓትን መንፈሳዊ ጥንካሬ በመናድ 35 ኣመት ያክል እስከ አሁኒቷ ደቂቃና ሰኮንድ ታሪክ ይቅር የማይለው ደባና ወንጀል በድርጅታችንና በትግራዋይ ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸሙ ይገኛሉ ::

ይቀጥላል

ሀጎስ

ድቂ መቕለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣረጋዊ /ዮሀ

መንገደኛ

Joined: 23 Mar 2010
Posts: 7
Location: France

PostPosted: Sat Apr 17, 2010 5:52 pm    Post subject: Reply with quote

የሻኣብያ ጦር በደርግ በከባኣድ ሁኔታ ተመቶ ከተዳከመ በሁኣላ የነመለስ ቡድን 25, 000 ውድ የትግራይ ወጣቶች ለሻኣቢያ እንዲዋጉ ተደርገው ሳሕል በረሀ ላይ እንደ ጨው ቀልጠው ቀርተዋል :: በሻኣቢያ እና በነመለስ ቡድን በግፍ የተገደሉት ውድ የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ደርግ ከገደለው አይተናነስም :: We should be organized to dismantle the base of the Meles FASCIST group!!
_________________
Aregawi's sacrifice will not be in vain!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5446

PostPosted: Sat Apr 17, 2010 6:12 pm    Post subject: Reply with quote

እዚህ ዋርካ ላይ በሚሰጠው አስተያየትና በሚያቀርበው መረጃ በጣም የምተማመንበት ወዳጄ ስልኪ አንድ ቀን እንዲህ ብሎ መጻፉን አስታውሳለሁ :: በሳህል ውጊያ ላይ የትግራይ ወጣቶች ሻቢያን ይርዱ አይርዱ በሚለው ክርክር ላይ መለስና ስዬ በጭራሽ አይሄዱም ብለው መከራከራቸውንና በኌላ ግን መሄድ አለባቸው በሚለው ወገን መሸነፋቸውን ጽፎ አስነብቦን ነበር :: እስኪ መሬት እየረገጥን እንሂድ ..ማነው ይሄን ያስወሰነው ? ማንና ማንስ ደገፉ ? ማንና ማንስ ተቃወሙ ? በጥላቻ በቂም በቀል በብቀላ ሳይሆን በእውነትና በውነት ላይ ተመስርትቻሁ የምታውቁ ሰዎች ንገሩን ::
ክቡራን እውነትን ማወቅ ከሚፈልጉ ወገኖች ጎራ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
መቅደላዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Dec 2009
Posts: 599
Location: Ethiopia

PostPosted: Sat Apr 17, 2010 6:53 pm    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
እዚህ ዋርካ ላይ በሚሰጠው አስተያየትና በሚያቀርበው መረጃ በጣም የምተማመንበት ወዳጄ ስልኪ አንድ ቀን እንዲህ ብሎ መጻፉን አስታውሳለሁ :: በሳህል ውጊያ ላይ የትግራይ ወጣቶች ሻቢያን ይርዱ አይርዱ በሚለው ክርክር ላይ መለስና ስዬ በጭራሽ አይሄዱም ብለው መከራከራቸውንና በኌላ ግን መሄድ አለባቸው በሚለው ወገን መሸነፋቸውን ጽፎ አስነብቦን ነበር :: እስኪ መሬት እየረገጥን እንሂድ ..ማነው ይሄን ያስወሰነው ? ማንና ማንስ ደገፉ ? ማንና ማንስ ተቃወሙ ? በጥላቻ በቂም በቀል በብቀላ ሳይሆን በእውነትና በውነት ላይ ተመስርትቻሁ የምታውቁ ሰዎች ንገሩን ::
ክቡራን እውነትን ማወቅ ከሚፈልጉ ወገኖች ጎራ ::

መለስ ዜናዊ ለማጭበርበር እንዲመቸው "ሻእብያ " ውስጥ ውስጥ እንደሚሰራ እንዳይነቃበት : የትግራይ ወጣት ሻእብያን ለማዳን እንዳይዘምት ተናግሮ ይሆናል :: ይህም ምንም የውስጥ ጠላት የሚጠቀምበት ዘዴ ነው :: ስየ አብርሃ የትግራይ ወደ ኤርትራ ሻእብያን ለማድን እንዳይዘምት መቃወሙ ግን በኢትዮጲያው አርብኝነት ከምነሳት መሆኑ ታሪክ ይመሰክራል :: መልስ ዜናዊ በፀረ -ኢትዮጵያና በፀረ -ኢትዮጲያ አቆአሙ አሁንም እንደቀጠለበትና እያገርሽበትም ሂዳኦል :: መለስ ዜናዊ ካልተትካ ሁኔታው ለትግርይና ለኢትዮጲያ ጥሩ አይሆንም ::
_________________
United we stand, divided we fall!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1631

PostPosted: Sat Apr 17, 2010 7:08 pm    Post subject: Reply with quote

ስልኪን በምኑ አመንከው ?

ሁለታችሁም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናችሁ ::
ሌላው ሌላው ሌላው ማስረጃ ይቅርና ማነው አዲስ አበባ እንደገቡ ሰሞን ስለባንዲራችን መናቅ ሰዉ በሰፊው ሲያወራ " ባንዲራ ጨርቅ ነው " ያለው ? ........ ስዬ ወይስ መለስ ?
ማነው ህዝቡ ስለኤርትራ መገንጠል ተቆጭቶ ሲወራጭ " እኛ ጦርነት ሰልችቶናል : ከፈለጋችሁ ሂዱና ተዋጉ : መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ " ....... ያለው ?
ማነው " የኤርትራ ጥያቄ የኮሎኒ ጥያቄ ነው " ........ብሎ ደጋግሞ በመድረክ የተናገረ " ?
ማነው " ለኤርትራ መገንጠል የትግራይ ህዝብ ታላቅ ክንዋኔ አካሂዷል " ......... ብሎ እንደጉራ በቅርቡ ሲለፍፍ የነበረ ?
ማነው " ኤርትራን ሊነካ ያሰበ ካለ ድምጥማጡን እናጠፋዋለን " ............. ብሎ በቅርቡ የደሰኮረ ?

ምናለ ክቡራኖት እራሶን ትንሽ ቢያሰሩት ? ራሶት ላይ ባይቀመጡበት ? ራሶት ላይ የነገር በርጫ ባይቅሙበት ? እንደከበሩ በክብሮት ቢቀመጡ ?

ሀዲስ

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
እዚህ ዋርካ ላይ በሚሰጠው አስተያየትና በሚያቀርበው መረጃ በጣም የምተማመንበት ወዳጄ ስልኪ አንድ ቀን እንዲህ ብሎ መጻፉን አስታውሳለሁ :: በሳህል ውጊያ ላይ የትግራይ ወጣቶች ሻቢያን ይርዱ አይርዱ በሚለው ክርክር ላይ መለስና ስዬ በጭራሽ አይሄዱም ብለው መከራከራቸውንና በኌላ ግን መሄድ አለባቸው በሚለው ወገን መሸነፋቸውን ጽፎ አስነብቦን ነበር :: እስኪ መሬት እየረገጥን እንሂድ ..ማነው ይሄን ያስወሰነው ? ማንና ማንስ ደገፉ ? ማንና ማንስ ተቃወሙ ? በጥላቻ በቂም በቀል በብቀላ ሳይሆን በእውነትና በውነት ላይ ተመስርትቻሁ የምታውቁ ሰዎች ንገሩን ::
ክቡራን እውነትን ማወቅ ከሚፈልጉ ወገኖች ጎራ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Hagoss

አዲስ

Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Sun Apr 18, 2010 5:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች

ኣረጋዊ /ዮሓንስ , መቅደላዊ , ሀዲስ 1 ለተጨማሪ ገንቢ ሀሳብችሁ አመሰግናለሁ ::

ከላይ የቀጠለ ----> የነመለስ - የሻቢያ ሰርጎገቦች ቡድን በሕወሓት ድርጅት ውስጥ በጣም ወሳግኝ የስልጣን ቦታ በመቆጣጠራቸው በፖሊት ቢሮውም ሆነ በጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ የሚቀርቡትን ውሳነዎች እንዲወሰኑ የሚያደርጉት በተንኮልና በመሰሪ አካሄድ ነበር ::

ማለትም ከላይ እንደገለጽኩት ትግራዋያን እንዳይነቁ በጣም ስውር በሆነ ዘዴ ( ለብቻቸው ተነጋግረው ) እንዴት መደረግ እንደሚኖርበት ከተስማሙ በሁዋላ ከራሳቸው ድብቅ አጀንዳ ጋር እንደሚስማማ አድርገው የድርጅቱን ስም እንዲላበስ ብቻ ለውሳኔ እንዲቀርብ ያደርጋሉ :: ይህንንም በዝርዝር በጥቂቱ ብንመለከት :

1- ማቅረብ የሚፈልጉትን አጀንዳዎች ይከፋፈሉና ከትግራውያን ጋር ሲገናጙ በጫወታ መልክ ነግሩን አንስተው በጉዋደኝነት መልክ እያወጉ የትግራዊው ሀሳብ ምን አይነት እንደሆነ ይገመግማሉ ::

2- እያንዳንዱ የነመለስ - ሻቢያ ቡደን ከትግራውያኑጋር በሚያደርጉት ጫወታ የሀሳቡን አዝማሚያ ገምግመው ካሰባሰቡ በሁዋላ አሁንም በደብቅ ከተገናኝተው በአሰባሰቡት የተውናጠል ነጥብ ላይ ውይይት ያደርጋሉ ::

3- በተናጠል የተሰበሰቡት ሀሳቦች ለነ መለስ -ሻቢያ ቡደን የሚሳማማ ሆኖ ከተገኘ ተቃውሞ የማይገጠመው ሀሳብ ነውና እንደ "ፖዘቲቭ ""+"" ሆኖ ይቀመጣል ::

4- በተናጠል የተሰበሰበው ሀሳብ ከነ መለስ ሻቢያ ቡድን የማይስማማ ከሆነ ግን : አሁንም በተደጋጋሚ በጫወታ መልክ የተግራዊያኑ ሀስብ ተፈትሾ አቅዋሙን የማይለውጥ አይነት ሆኖ ካገኙት በሶስተኛ ዙር (በድብቅ ) የሌሎችን ድጋፍ ለማግኘት ተባባሪ ድምጽ ያሰባስባሉ ::

5- በዚህና በተመሳሳይ ስውር ደባ የሚነሱት ሀሳቦች ለእንሱ እንድሚመች አድርገው ካስተካከሉ በሁዋላ በስብሰባ ላይ የቀረቡትን አጀንዳዎች የነመለስ -ሻቢያ ቡድን ድብቅ አላማቸው ሳይነቃበት በድምጽ ብልጫ ውሳኔ እንዲያገኝ ያስደርጋሉ ::

ይቀጥላል ---->

ሀጎስ
ደቂ መቐለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Hagoss

አዲስ

Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Fri Apr 23, 2010 12:40 am    Post subject: Reply with quote

---የቀጠለ --->

ይህ ለውሳኔ የሚቀርቡትን ሀሳቦች ለማጽደቅ የሚጠቀሙበት አካሄድ ስሂሆን , የነመለስ -ሻቢያ ወኪሎች በርኢዮተ -ዓለም አመለካከት ደግሞ ከየት መጣ ሳይባል በድርጅቱ ላይ ... ስም (ማርክሲስት -ሌንኒስት ሊግ ትግራይ ) Marxist-Leninist League of Tigray (MLLT) ላይ የዓልባኒያን የፖለቲካ ርእዮተ -አለም ጫኑበት ::

የዓልባኒያ ኮሚኒስት ፓርቲ ርእዮተ -ዓለም የሚታወቀው በፓርቲው መሪ ENVER- HOXA ሆኖ በአጠራ Hoxhaism ተብለው ይሰየማሉ : Hoxhaismሞች እራሳቸውን የሚያስተዋዉቁት በዓለም ላይ ብቸኛው የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ሳይንሳዊ ሶሻሊዝምን ተግባራዊ የምናደርግ ጸረ ከላሾችና ብራዦች (Anti-revisionist of Marxsism-Lenenism) እኛ ነን በማለት ይለፍፋሉ ::

የነመለስ -ሻቢያ ሴረኞች የሚያሚያመልኩበት የሆክሲዝም ፊሎሶፊ የሚያነግባቸው የፖለቲካ ነጥቦችን በጥቂቱ ብናነሳ አሁን ሀገራችን ውስጥ የሚፈጽመውን ተግባር በማነጻጸር እንመልከት :

1.Hoxhaismሞች የእስታሊንን የፖለትካ እርምጃ ከልባቸው የሚደግፉ ናቸው :: የእስታሊን የፖለትካ አካሄድ መሰረታዊ እንቅስቃሴ ሶሻሊዝምን ተግባርዊ ለማድረግ ተቃዋሚን እንደ ጸረ አብዮት በመቁጠር መጥፋት አለባቸው ብሎ የሚያምን ነው :: ይህንንም እውን ለማድረግ The Red Terror ( ቀይ ሽብር ) ወይንም የእስታሊን በትር ተብሎ የሚጠራውን 20- 30 ሚልዮን የሚደርስ የህዝብ ፍጅትን ተግባርዊ ያደረገ ነው ::

ይህንን የፖለትካ እርምጃ ደርግ በወቅቱ የተጠቀመበት ሲሆን የነመለስ ሻቢይ ቡድንም ገና በጅምሩ የትግራይ ውጣቶችን ፈጅቶ መሀል አገር ከገባም ብሁዋላ 1997 ድሕረ ምርጫ የህዝብ ፍጅት ቀዋሚ መረጃ ነው ::

2. ስታሊን የገበረዎችን የሕብረት ስራ ማሕበር ለመመስረትና የመሬትን ፖሊሲ በመንግስት ቁጥጥር መር ስር ለማዋል በብዙ ምልዮን የሚቆጠረውን ገበረዎችን የፈጀ ፍልስፍና ነው ::

3. Hoxhaism ሞች (የዓልባኒያ ሶሻሊስት ተከታዮች ) የመንግስታዊ አንባገነንን መስርቶ ሚስጥራዊ ፖሊስን አቋቁሞ እያፈነ በስዉር ( The ""hiden part""of Red Army. ) ፍጅትን ተግባርዊ የሚያደርግ አካል ነው :: የነመለስ ሻቢያ ቡድንም ይህንኑ መስመር በመከተል በባዶ (6) ውስጥ እያሳፈኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠረውን የትግራይን ህዝብ ፈጅተዋል ::

ይቀጥላል --

ሀጎስ

ደቂ መቐለ

Last edited by Hagoss on Fri Apr 23, 2010 9:54 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቲዎደሮሰ ሳልሳ

ኮትኳች

Joined: 25 Feb 2010
Posts: 373
Location: Quara

PostPosted: Fri Apr 23, 2010 8:54 am    Post subject: Reply with quote

መቕደላዊ
ኤርትራዊ ዝበሀል ደም የለን :: ኤርትራ ናይታሪኽ አጋጣሚ ኾይኑ ሎሚ ሀገር ኮይኑ አሎ :: ስለዝኾነ ኤርትራዊነት ከም ኢትዮዽያዊነት ዜግነት እምበር ዘርኢ አይኮነን :: ትግራዋይ ማለት ዘርኢ እዩ :: ቶም አብ ኤርትራ ዘለው ተጋሩ ሕጂ ሽሞም ቐይሮም ብሄረ ትግርኛ ይበሀሉ :: ተጋሩ ይኹን ብሄረ ትግርኛ ኩላህና ሓደ ዘርኢ ኢና :: ስለዝኾነ ድማ ተዋሲብና ኢና :: ማንም ዓጋመ አቦታቱ ሸውዓተ እንተቖጺሩ ሓማሴን ወይ ካዓ ሰራየ ወይ አኮሎግዛይ ኣይሳኣኖን :: ዓድዋውን ከምኡ ; እንደርታውን ከምኡ :: ንሳቶምውን ከምኡ ::
ግን መለስ ዜናዊ ካብ ኻልኦት ብዝተፈለየ ንኤርትራ ከምዝሓልይ አነውን እሰማማዕ :: ምናልባች ናይ ኣዴኡ ኤርትራዊነት ስምዒት ኢንፍሉዌንስ ገይርዎ ይኸውን :: ኮይኑ ግና እዚ ናይመለስ ኢትዮዽያዊነት አብሕቶ ዘእትው አይኮነን :: ካብማንም ዝለዓለ እምበር ዝነኣሰ ኢትዮዽያዊ አይኮነን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Hagoss

አዲስ

Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Sun Jun 27, 2010 7:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዋርካ ቤተሰቦችና ትግራዋይ በሙሉእ
ይቀርታ በመዘግየተ መጣሁ : የጀመርኩትን እቀጥላለሁ ::

Last edited by Hagoss on Sun Jun 27, 2010 11:46 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 25 Jun 2010
Posts: 81

PostPosted: Sun Jun 27, 2010 8:18 pm    Post subject: Re: ወዲ ትግራይ እራሰህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ !! Reply with quote

ይህች የኤርትራ ደም ያለባቸው የህወሀት አባላት ናቸው ኢትዮጵያ ላይ ግፍ የሰሩት የምትለው አባባል ጊዜ ያለፈባት ናት ::
ትግሬዎች እኮ ያን ሁሉ እያወቁ ነው 20 አመታት በላይ ከህወሀት ጎን የቆሙት :: አሁንም ወታደር ሆነው ,ሰላይ ሆነው ,ካድሬ ሆነው እና ባለ ስልጣን ሆነው ኢትዮጵያን እያደሙ ያሉት አብዛኞቹ ትግሬዎች ናቸው :: ይሉቁኑ ለትግሬዎች የኢትዮጵያ ጠላትነት ምንጩ ከሀዲው ዮሀንስ መሆኑን መረዳት ይሻላል ::

Hagoss እንደጻፈ(ች)ው:
ተወላጅነታቸው ኤርትራዊ የሆኑት
ማለትም እንደ :
1.መለስ ዜናዊ ,
2.ሰብሀት ነጋ ,
3.በረኸት ሰሞኦን ,
4.ሳሙራ የኑስ .
5. አባይ ጸሀዬ -
6.ተከለወይኒ አሰፋ
7. ቅዱሳን ነጋ

በትግራ ነጻ አውጭነት ስም ሕወሀት ውስጥ ተሰግስገው ውስጥ ለውስጥ ለሻቢያ በመስራትና በመመሳጠር በትግርይ ሕዝብና በትግራይ ተወላጆች ላይ የፈጽሙትን ደባ እንደሚከተለው እንመልከት ::

በተለያየ ወቅት ስለ ኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልና ሻቢያን ስለተቃወሙ ብቻ ከሕወሀት የተባረሩ የትግራይ ተወላጆች

1. ዾክተር ሀረጋዊ በርሄ

2. ዶክተር ግደይ ዘርዓጽዮን

3. አቶ ገብረ መድህን አርዓያ

4./ አረጋሽ አዳነ

5.አቶ አለምሰገድ ገብረዓምላክ

6. አቶ ስዬ አብረሀ
ይቀጥላል

ሀጎስ
ደቂ መቕለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቤንዚን

ዋና ኮትኳች

Joined: 30 Jun 2008
Posts: 835

PostPosted: Mon Jun 28, 2010 12:32 am    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ ቴዎድሮስ ሳልሳ አንተ ደግሞ ይህን የቤተመንግስት ቁዋንቁዋ ቅቅቅቅ ዬት ተማርከው ? እስቲ ለሰፊው ሕዝብ ተርጉምልን ::

ሰላም ሁንልኝ

============================================

[quote="ቲዎደሮሰ ሳልሳ "]መቕደላዊ
ኤርትራዊ ዝበሀል ደም የለን :: ኤርትራ ናይታሪኽ አጋጣሚ ኾይኑ ሎሚ ሀገር ኮይኑ አሎ :: ስለዝኾነ ኤርትራዊነት ከም ኢትዮዽያዊነት ዜግነት እምበር ዘርኢ አይኮነን :: ትግራዋይ ማለት ዘርኢ እዩ :: ቶም አብ ኤርትራ ዘለው ተጋሩ ሕጂ ሽሞም ቐይሮም ብሄረ ትግርኛ ይበሀሉ :: ተጋሩ ይኹን ብሄረ ትግርኛ ኩላህና ሓደ ዘርኢ ኢና :: ስለዝኾነ ድማ ተዋሲብና ኢና :: ማንም ዓጋመ አቦታቱ ሸውዓተ እንተቖጺሩ ሓማሴን ወይ ካዓ ሰራየ ወይ አኮሎግዛይ ኣይሳኣኖን :: ዓድዋውን ከምኡ ; እንደርታውን ከምኡ :: ንሳቶምውን ከምኡ ::
ግን መለስ ዜናዊ ካብ ኻልኦት ብዝተፈለየ ንኤርትራ ከምዝሓልይ አነውን እሰማማዕ :: ምናልባች ናይ ኣዴኡ ኤርትራዊነት ስምዒት ኢንፍሉዌንስ ገይርዎ ይኸውን :: ኮይኑ ግና እዚ ናይመለስ ኢትዮዽያዊነት አብሕቶ ዘእትው አይኮነን :: ካብማንም ዝለዓለ እምበር ዝነኣሰ ኢትዮዽያዊ አይኮነን ::[/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1857
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Mon Jun 28, 2010 8:47 am    Post subject: Reply with quote

ዝም ብሎ መዛላበድ ሆነ ሰራቹህ :: ስንቱን ቀባጥራቹህ ትዘልቃላቹህ :: በስሜት አትነዱ ; የያዛቹህ አባዜ እስኪለቃቹህ በመጠበቅ ላይ ነን ::
_________________
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ካለድ

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Jan 2007
Posts: 594

PostPosted: Mon Jun 28, 2010 12:02 pm    Post subject: Reply with quote

የሻኣብያ ጦር በደርግ በከባኣድ ሁኔታ ተመቶ ከተዳከመ በሁኣላ የነመለስ ቡድን 25, 000 ውድ የትግራይ ወጣቶች ለሻኣቢያ እንዲዋጉ ተደርገው ሳሕል በረሀ ላይ እንደ ጨው ቀልጠው ቀርተዋል :
ወይ ጉድ አዎ ወይኔ ኤርትራ ምድር :መተው ሳህል :አካባቢ መስዋእትነት :ከፈለዋል :ግን 25,000 አይደለም :የምጡት :1450 ወታደሩች :ናቸው :ያኔ አይደለም : ወያኔ :ሽእቢይ :ይን :ይህል :የወታደር :ብዛት :አልነበርውም : የማይቅ :ውሽታም :ስው :ሲይስጠላኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
Hagoss

አዲስ

Joined: 10 Oct 2009
Posts: 28
Location: cyber

PostPosted: Mon Jun 28, 2010 10:52 pm    Post subject: Reply with quote

ደሓን ደሓን ህዝቢ ትግራዋይ እንዲሁም የዋርካ ተሳታፊዎች ::

ወደ ጀመርኩት ከመግባቴ በፊት ከላይ ሾተል ባነስኸው ነጥብ ላይ ትንሽ ለመጥቀስ ያክል ለማለት የምፈልገው :

ሾተል እንደጻፈው /ችው
Code:
ይህች የኤርትራ ደም ያለባቸው የህወሀት አባላት ናቸው ኢትዮጵያ ላይ ግፍ የሰሩት የምትለው አባባል ጊዜ ያለፈባት ናት ::

ከላይ የገልጽኵዋቸው የሻቢያ ሰርጎገቦች እኮ አሁንም / ሚንስተር እስከ የጦር ኮማንደር ድረስ በስልጣን ላይ ያሉ ናቸው እና ምኑ ነው ቀን ያለፈባት ነገር ?

Code:
ትግሬዎች እኮ ያን ሁሉ እያወቁ ነው 20 አመታት በላይ ከህወሀት ጎን የቆሙት :: አሁንም ወታደር ሆነው ,ሰላይ ሆነው ,ካድሬ ሆነው እና ባለ ስልጣን ሆነው ኢትዮጵያን እያደሙ ያሉት አብዛኞቹ ትግሬዎች ናቸው ::

ትግራዋይ በተወሰነ ደረጃ የነዚህ ሰርጎ ገቦች ባለስልጣን መሆናቸውን ማንም የካደ የለም :: ነገር ግን ሀቁ የነዚህን የሻቢይ ሰርጎ ገቦች አላማና ግባቸውን የነቁብቸው ትግራዋያን ምን ያክል ናቸው የሚለው ነው ነጥቡ :: በመሆኑም ነው አርእስቱን ""ወዲ ትግራይ እራስህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ "" ብዬ የሰየምኩት ::
የነ መለስ ስብሀትን የሻቢያ ሰርጎ ገብነት የነቁባቸው ትግራዋያን ጀጊናዎች ላይማ የደረሰውን ከላይ በዝርዝር ጠቅሻለሁ ::
Code:
 ይሉቁኑ ለትግሬዎች የኢትዮጵያ ጠላትነት ምንጩ ከሀዲው ዮሀንስ መሆኑን መረዳት ይሻላል ::

ሦተል በእነ መለሰ ቡድን ለመወደድ ስትል ኣጠቃላይ የትግርዋይን ሕዝብና ኣጼ ዮሀንስን መስደብ አስፈላጊ አይመስለኝም :: እንድያውም ላስታውስህና ከሀማሴኖች የበለጠ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወገኑን ያጠቃ የለም ::

ኣጼ ዮሀንስ በወቅቱ በነበረው ሜንታሊቲ ደረጃ ስልጣን ለማግኘት በጼ ቴኦድሮስ ላይ መሆን የማይገባውን ነገር ፈጽመው ይሆናል :: ነገር ግን በዝያን ጊዜ አንዱ ሌላውን ጥሎ መንገስ ወንጀል ባልነበረበት ወቅት ነው :: የብዙዎቹ የነገስታቶቻን ታሪክ በአንዱ ወይንም በሌላ መልኩ ተመሳሳይ ስለሆነ ታሪክን ወደ ሁዋላ መሸረቡ ለሀገራችን አይጥቅምም ::

አጼ ዮሀንስ ኢትዮጵያን የከዱ ስይሆኑ ለኢትዮጵያ ሀገራቸው በመተማ ላይ አንገታቸውን ለሴይፍ የሰጡ ንጉስ ናቸው :: ነገር ግን ባንዳዎቹ የሻቢያ ሰርጎ ገቦች ንጉሱ የወደቀበትንና ደሙ የፈሰሰበትን ምድር ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ለድርቡሾች በመቸርቸር ላይ ይገኛሉ :: ለምን ቢባል መሬቱም ንጉሱም የኛ አይደለም ብለው በልባቸው ስለሚያምኑ ነው ::

አቶ ሾተል !!ከመጨረሴ በፊት አንድ የምጠይቅህ ነገር ቢኖር ? ለትግራይ ህዝብ መጠቃት የቆምኩ ነኝ ብለህ ብዙ ስትጽፍ , ብዙ ኣውዲኦ ስታሰማ ከርመህ ምነው ዛሬ የትግሬ ክህደት የሚጀምረው ከኣጼ ዮሀንስ ነው ማለትህ ?

ሐጎስ
ደቂ መቕለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1526

PostPosted: Mon Jun 28, 2010 11:06 pm    Post subject: Reply with quote

Hagoss እንደጻፈ(ች)ው:
ደሓን ደሓን ህዝቢ ትግራዋይ እንዲሁም የዋርካ ተሳታፊዎች ::

ወደ ጀመርኩት ከመግባቴ በፊት ከላይ ሾተል ባነስኸው ነጥብ ላይ ትንሽ ለመጥቀስ ያክል ለማለት የምፈልገው :

ሾተል እንደጻፈው /ችው
Code:
ይህች የኤርትራ ደም ያለባቸው የህወሀት አባላት ናቸው ኢትዮጵያ ላይ ግፍ የሰሩት የምትለው አባባል ጊዜ
 ያለፈባት ናት ::

ከላይ የገልጽኵዋቸው የሻቢያ ሰርጎገቦች እኮ አሁንም / ሚንስተር እስከ የጦር ኮማንደር ድረስ በስልጣን ላይ ያሉ ናቸው እና ምኑ ነው ቀን ያለፈባት ነገር ?

Code:
ትግሬዎች እኮ ያን ሁሉ እያወቁ ነው 20 አመታት በላይ ከህወሀት ጎን የቆሙት :: አሁንም ወታደር ሆነው ,ሰላይ ሆነው ,ካድሬ ሆነው እና ባለ ስልጣን ሆነው ኢትዮጵያን እያደሙ ያሉት አብዛኞቹ ትግሬዎች ናቸው ::

ትግራዋይ በተወሰነ ደረጃ የነዚህ ሰርጎ ገቦች ባለስልጣን መሆናቸውን ማንም የካደ የለም :: ነገር ግን ሀቁ የነዚህን የሻቢይ ሰርጎ ገቦች አላማና ግባቸውን የነቁብቸው ትግራዋያን ምን ያክል ናቸው የሚለው ነው ነጥቡ :: በመሆኑም ነው አርእስቱን ""ወዲ ትግራይ እራስህን አጽዳ ከሻቢያ ሰላይ "" ብዬ የሰየምኩት ::
የነ መለስ ስብሀትን የሻቢያ ሰርጎ ገብነት የነቁባቸው ትግራዋያን ጀጊናዎች ላይማ የደረሰውን ከላይ በዝርዝር ጠቅሻለሁ ::
Code:
 ይሉቁኑ ለትግሬዎች የኢትዮጵያ ጠላትነት ምንጩ ከሀዲው ዮሀንስ መሆኑን መረዳት ይሻላል ::

ሦተል በእነ መለሰ ቡድን ለመወደድ ስትል ኣጠቃላይ የትግርዋይን ሕዝብና ኣጼ ዮሀንስን መስደብ አስፈላጊ አይመስለኝም :: እንድያውም ላስታውስህና ከሀማሴኖች የበለጠ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወገኑን ያጠቃ የለም ::

ኣጼ ዮሀንስ በወቅቱ በነበረው ሜንታሊቲ ደረጃ ስልጣን ለማግኘት በጼ ቴኦድሮስ ላይ መሆን የማይገባውን ነገር ፈጽመው ይሆናል :: ነገር ግን በዝያን ጊዜ አንዱ ሌላውን ጥሎ መንገስ ወንጀል ባልነበረበት ወቅት ነው :: የብዙዎቹ የነገስታቶቻን ታሪክ በአንዱ ወይንም በሌላ መልኩ ተመሳሳይ ስለሆነ ታሪክን ወደ ሁዋላ መሸረቡ ለሀገራችን አይጥቅምም ::

አጼ ዮሀንስ ኢትዮጵያን የከዱ ስይሆኑ ለኢትዮጵያ ሀገራቸው በመተማ ላይ አንገታቸውን ለሴይፍ የሰጡ ንጉስ ናቸው :: ነገር ግን ባንዳዎቹ የሻቢያ ሰርጎ ገቦች ንጉሱ የወደቀበትንና ደሙ የፈሰሰበትን ምድር ለታሪካዊ ጠላቶቻችን ለድርቡሾች በመቸርቸር ላይ ይገኛሉ :: ለምን ቢባል መሬቱም ንጉሱም የኛ አይደለም ብለው በልባቸው ስለሚያምኑ ነው ::

አቶ ሾተል !!ከመጨረሴ በፊት አንድ የምጠይቅህ ነገር ቢኖር ? ለትግራይ ህዝብ መጠቃት የቆምኩ ነኝ ብለህ ብዙ ስትጽፍ , ብዙ ኣውዲኦ ስታሰማ ከርመህ ምነው ዛሬ የትግሬ ክህደት የሚጀምረው ከኣጼ ዮሀንስ ነው ማለትህ ?

ሐጎስ
ደቂ መቕለ

ወዲ ሀጎስ ከመይ አለካ !!!

ከላይ የጻፈው ሾተል /የቪያናው አይደለም ..ሌላ የሱን ስም ለማጥፋት ..የገባ የስሙኒ ሎሚ የሚባል ያይምሮ ዝግመት ያለበት ሰው ነው .
_________________
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4  Next
Page 2 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia