WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 312, 313, 314 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Oct 03, 2010 8:16 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ ትክክል ነህኮ የሚረባውንም የማይረባውንም ትሞነጫጭራለህ ምን ጎሽ ጎሽ አሪፍ ነው እንድንልህ ነው ?
አሁን ሰው ዶሮ እንዴት ያፈቅራል ? የሰው ፍቅር ሳትጨርስና ሳታስጨርስ የዶሮ ፍቅርርርርርር ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ !
ጠጅ የሚጠጣ ዶሮ አውቃለሁ የታወቀ ቀምቃሚ ነው ብቻ ፉጨት ሲሰማ ካለበት ከች ይላል ጠጅ በሰሀን ላይ ተደርጎ ሲሰጠው ቀጭ ቀጭ እያደረገ ይቀመቅማል ዶሮ ግን በተፈጥሮ ውሀ ሲጠጡ አያስደስቱም ........
ይጠጡ አህያና ግመል ::

ስለ ልጅ ስትናገር ልጅህ ወንድ እንደሆነ ነው ባለፈው ግን ሴት እንደሆነች ነበር የነገርከን ሁለት ናቸው እንዴ ?
ሞፊቲኮ ግን የሚጠፋው ልጅ እያዘለ እያቀፈ እያጠባ ምናምን አይደለም እሱ እንዲህ ያለውን ነገር አያውቅበትም ምክንያቱም እስከማውቀው ድረስ ሞፊቲ ጸሀይ ስትወጣ ይወጣል ጸሀይ ስትገባ ይገባል በቀን እቤት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም የሚባለው የድሮ ነገር ትዝ ይለኛል :: መቼም የልጅ ነገር የልጅ ነውና የሆነው አይታወቅም አንተም ልክ ልትሆን ስለምትችል ዝም ልበል ::

ስለ ግጥምህ የሰጠሁህ አስተያየት ያረካህ አይመስልም
ባለሱቅ አደቆርሳን እንዳንተ በሞቴ በሞቴ ብዬ ከጨረስኩ ቆይቻለሁ ይህ ቤት የፍቅርና የወንድማማች ቤት ነው እሱ ከማንም ያላነሰ ፍቅር እንደነበረው ሁላችንም እናውቃለን ፐርሰናል ፕሮብሌም ሊኖርበት ይችላል ከኛ ጋር ግን በፊትም አሁንም ፍቅር መሆኑን ነው የማውቀው ስለዚህ አስገዳጁ ፍቅር እንጂ ግብዣ አይመስለኝም ::
አደቆርሳ ቶሎ የሚቆጣና ቶሎ የሚከፋው ሰው መሆኑን አቃለሁ ቢሆንም ካልቻለ ለምን አትችልም ማለት አስፈላጊ አልመሰለኝም ::
ጽሁፎቹ አንባቢን ይጋብዛሉ አስታዋሽነቱ የሚደነቅ ነው
ውነት ለመናገር አንፈራራና አደቆርሳ ስለልጅነት ትዝታዎቻቸው ሲጽፉ ይገርመኛል በደንብ ከማስታወሳቸው ቃላትን አክሽንን ሁሉ አይረሱም ስለዚህ እነሱን ዋርካ ላይ ማየት በጣም በአድናቆት ነው ደስ የሚለኝ :: አደቆርሳ ጽፎ የሚጨርስ ባለመሆኑ ከምር በጣም እቀናለሁ በሆነች ነገር ላይ ብዙ ማለት ይችላል : በብዙ ጉዳይ ተሳታፊ ነው ይሄ ያስደስተኛል እኔን ብቻ አይደለም ሁላችንንም ማለት እችላለሁ :: ስለዚህ እኔም የጥሪህን መልክት ደጋፊ ነኝ እልሀለሁ
ስለ ግጥሞችህ በይዘታቸው ብቻ ሳይሆን በቶሎ የፈጠራ ቅልጥፍናቸውና የመልክት ማስተላለፍ ችሎታቸው አድናቆት እንዳለኝ በድጋሚ እገልጽልሀለሁ

እስቲ የዶሮዋን ፍቅር አምጣት መቼም ጉድ አያልቅብህም
ሞፊቲን ግን ለቀቅ አርገው ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Oct 04, 2010 1:20 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
እስቲ የዶሮዋን ፍቅር አምጣት መቼም ጉድ አያልቅብህም
ሞፊቲን ግን ለቀቅ አርገው

ራስ = እንዲህ ልክ ልኩን ንገርልኝ እንጂ እሄ ሱቅ በደረቴ የሚቻል አይምሰልህ ?
ለነገሩ ለኔ ትንሽ ስለሚያዝንልኝ በስድ ንባብ ሰደደው እንጂ በግጥምማ ቢያቀርበው ኖሮ :-

እራሱ መላጣ ሆዱ አስር ኪሎ
ሞፊቲ ይመጣል ልጅ ባንቀልባ አዝሎ !

ከማለት ወደ ኌላም ወደፊቲም አይመለስም ነበር ::በነገራችን ላይ ባለሱቅ የዶሮ ፍቅር የያዘው እንደዶሮ
ቶሎ ስለሚያመልጠው እንዳልሆነ ልትገነዘቡለት ይገባል ::
እኔ ሀሳቡን ቀድሜ ስለምረዳላት እባካችሁ ወደሌላ አታዙሩበት ::ለማንኛውም ወሬውን እስከሚጨርስ ታገሱት ::

ስለ አደቆርሳ በተነሳው ርዕስ እኔ ማለት ከምችለው በላይ እናንተ ስላላችሁ መጨመር የምችልበት ቃላት ማግኘት አልችልም ::
ናፍቆቱ ግን እንደሁላችሁም አንጀዋሎኛል ::ራስ ብሩ እንዳለው ፍቅር አሸንፎት በቅርቡ እንደምናየው ተስፋ አደርጋለሁ ::

ቸር እንሰንብት !!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Mon Oct 04, 2010 10:39 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ

የአምላክ ፈቃድ ከሆነ ከጥቂት ወራት በኍላ ወደ ኢትዮጵያ ስለምሄድ በዚያው ጊዜ ሦስት ፕሮጄክት ይዤ ስለምሄድ በአሁኑ ወቅት እነርሱን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና እያልኩኝ ነኝ :: ለዚህ ነው የጠፋሁት : ሆኖም አንዳንዴ ምን እንደሚጻፍ ለማየት ጎራ ማለቴ አልቀረም ::

መቼም ባለሱቅና ራስብሩ ቤቱ ባዶውን እንዳይሆን በጣም እየጣራችሁ ስለሆነ የምትመሰገኑ ናችሁ :: አንዳንዴ ግን Warka General ላይ ለማየት የማልፈልጋቸውን አንዳንድ ጽሁፎች ሳይ የኛ የራስብሩ ....ቤት እንዲሁም "ወሎ ገራገሩ " ሌላ ቤት ውስጥ በሆኑ ያሰኛል :: ግን ምን ማድረግ ይቻላል ?

ለማንኛውም አንድ የልጅነት ነገር ትዝ አለኝ ::

ኩሚና አካባቢ አንድ ሰርግ ነበር :: እኛም የአራዳ ልጆች ሳንጠራ ሄደን በላን :: ሁሉ በሽበሽ ነበር ::

ከዚያም ሙሽራውና አጃቢዎቹ በአንድ መኪና ተጭነው መጡ ::

የሙሽራው መኪና ምን ነበር ? ዚታዎ !!! Laughing Laughing

ሹፌሩ አንድ የጣልያን ክልስ ነበር :: ዚታዎ የማታውቁ የጭነት መኪና ማለት ነው ::

አሁን ሰርጉ ካበቃ በኍላ ሙሽሪትና ሙሽራ ከሹፌሩ ጋር ጋቢና ውስጥ ተቀመጡ :: ሚዜዎችና ደንገጡሮችና ሌሎች ሰርገኞች ላይ ተሳፈሩና ሄዱ :: የሙሺራው ቤት ከራስ ብሩ /ቤት ወረድ ብሎ ነው ::

እኔና ጓደኞቼ በእግራችን ወደ ቤት ማምረት ጀመርን :: ጉዟችንን እንደቀጠልን አሁን የመድሐኒአለም ቤተ ክርስትያንን አልፈን ቁልቁል መውረድ ስንጀምር ሙሽሮችን ጭኖ የነበረው ዚታዎ እንደገና ተመልሶ ወደ ሙሽሪት ቤት ሲሄድ አቀበቱን ተያይዞ አየን :: በአጠገባችን ሲያልፍ ላይ የነበረው የሹፌሩ ረዳት (ያው ስለምናውቀው ) ወደኛ እየጮኸ ወደ ሰርጉ ቤት ከተመለስን በመኪና ጭኖ እንደሚመልሰን ቃል ገባልን :: ከዚያ በኋላም ዚታዎው ወደ ሙሺሪት ቤት መንገዱን ቀጠለ ::

እኔና ጓደኞቼም ተመካከርንና በመኪና ለመሳፈር ብለን እንደገና ወደ ሰርጉ ቤት እንሂድ ተባባልን :: አሁን ወደ ሰርጉ ቤት ሩጫችንን ጀመርን :: ልክ ሰርጉ ቤት ልንደርስ ስንል ግን ዚታዎው ሰዎችን ጥቅጥቅ እድርጎ ጭኖ የመልስ ጉዞ ጀምርዋል :: ሁሉ ልፋት ::

እኛ ደግሞ እንደገና ብለን ከኩሚና እንደገና ወደ ቤት በእግራችን :: Laughing

እንዲያው በስም ነው አራዳዎች የተባልነው እንጂ ለካስ ፋራዎች ነበርን !! Sad

ለቦሪቲ የግል ቁሩንፉድ አይፋ / መናኸሪያ የጃማ ጦሲኝ ወረኢሉ ባለሱቅ ሞፊቲ ራስብሩ አደቆርሳ አደቆርሲት ቺኮና ሌሎችም የአክብሮት ሰላምታየ ይድረሳችሁ ::

ቻው !
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 04, 2010 7:35 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጥሣፈው
Quote:
አሁን ሰው ዶሮ እንዴት ያፈቅራል ? የሰው ፍቅር ሳትጨርስና ሳታስጨርስ የዶሮ ፍቅርርርርርር ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ !

ይህች ነገር ነገር አላት
እስኪ የየትኝኣውን ሰው ፍቅር ነው ጀምሬ ያላስጨረስኩት .... አውጣት አንተ ብሽቅ ራስብሩ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ስለዶሮዋ ከማውራቴ በፊት አንፈራራ ወንድሜ ሁሌ ሲያስተክዘኝ እና መላ ያጣሁለትን ነገር ..... ምናልባትም ሁለታችንም እኩል ሲያስጨንቀን እና ሲያሳስበንን የነበረውን ነገር ስላቀረበ እሱን ማንሳት ፈለኩ
አንፈራራ እንደፃፈው
Quote:
አንዳንዴ ግን Warka General ላይ ለማየት የማልፈልጋቸውን አንዳንድ ጽሁፎች ሳይ የኛ የራስብሩ ....ቤት እንዲሁም "ወሎ ገራገሩ " ሌላ ቤት ውስጥ በሆኑ ያሰኛል :: ግን ምን ማድረግ ይቻላል ?

አንፈራራዬ ይገርምሀል ይህንን ነገር በአሽሙር ብዙ ጊዝ አንስቼዋለሁ ብዬ አምናለሁ .... ሰሞኑን ደሞ ማየት የማልፈልጋቸውን አርስቶች እዚህ ዋርካ ጀነራል ላይ እያየሁ .... የመፃፍ ጉጉቴ ሁሉ እየጠፋብኝ ተቸግሬአለሁ
አይ -ዶኖ ... ምን ማድረግ እንደሚቻል .... ይህንን ቤት ሌላ አምድ ውስጥ ማስገባት ቢቻል .... ደስታዬ ወደር አልነበረውም
ምንም ልላቹ አልፈልግም ... ግን ይህንን ቤት ፍለጋ ዋርካ ጀነራል ስገባ ህምምምምም
ጥላሁን ምን አለ መሰላቹ
የማይ የምሰማው ሁሉ እያስጨነቀኝ
አገሬ ላይ ሆኜ አገሬ ናፈቀኝ
ኢሀዲግ አዲሳባ የገባ ሰሞን ስታዲየም ሲዘፍን መሰለኝ እዩዋት ስትናፍቀኝ በሚለው ዘፈኑ ላይ የገጠመው ግጥም ነው
እና ይህ ዋርካ ጀነራል የሚባል አምድ .... እንደ -ዋርካ ዜና መጥፋት ያለበት አምድ ነው ... ወይም ... ይህንን የኛን ቤት ወደ -ኪነጥበብ ገፅ መውሰድ ቢቻል .... ሙዳችን ሳይበላሽ እንደልባችን መጥሣፍ በቻልን ነበር እያልኩ ሁሌ ነው ማስበው
ምን አገባህ .... የራስህን ቤት ብቻ ጎብኝ /... ልባል እችላለሁ
አይን አይከለከል .... የራሴን ቤት እስክከፍት የማየው ነገር ... እያሳመመኝ .... ሞራሌን እየገደለብኝ ነው ያለው
ስንት ጊዜ ስንትናስንት ነገር ላወራ ከጅዬ እንደተውኩት ... አላህና ልቤ ብቻ ነው ሚያውቁት
አቦ ገላግሉኝ ከዚህ የዋርካ -ጀነራል ቤት
ራስብሩ ወንድሜ .... ይህንን ቤትር ወደ -ሌላ አምድ ውሰድልኝ በእግዜር ... በየሱስ .. ባላህ
የፈለከውን ዘዴ ተጤቀምና ... ገላግለን አቦ

አንፈራራዬ ከልጅነት ታሪክህ የበለጠ የነካኝን ጉዳይ ስላነሳህ ከልብ አመሰግንሀለሁ
በተረፈ
01 ልጅ ሆነህ ግን አራዳ ነኝ ለማለት መሞከርህ አስፎግሮሀል እኛ ዘንድ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ

ሰላም ቆዩኝ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Mon Oct 04, 2010 9:27 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ስለ ዋርካ ጀነራል ያነሳችሁት ትክክል ነው በመሰረቱ እኔ ጊዜው ስለማይበቃኝ በፍጹም ሌላ ሩም ክሊክ አላደርግም የምወደውን የተድላ ኃይሉን የስፖርት ዘገባ እንኳን በአምስትና ስድስት ቀን አንዴ ነው የማየው ሆኖም በጣም አልፎ አልፎ የሚገርሙ ርዕሶችን ሳይ ገጹን ገለጥ ማድረጌ አይቀርም ታዲያ እናንተ እንዳላችሁት ስላነበብኩትና ምነው ባልገለጥኩት ብዬ ቀኑን ሙሉ ሳዝን እውላለሁ በውነት ከእንዲህ ዓይነቱ ክፉ ነገር መራቅ ያስፈልጋል :: ሩሙን ወደ ዋርካ ፍቅር ለማምጣት ባለሱቅ ያቀረብከው ሀሳብ ጥሩ ነው
ነገር ግን የዋርካ ባለቤቶች እገዛ ሳያስፈልገን አይቀርም በቅርብ እንደሚተባበሩንም እምነቴ ነው ::

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ወገኖቼ

የአምላክ ፈቃድ ከሆነ ከጥቂት ወራት በኍላ ወደ ኢትዮጵያ ስለምሄድ በዚያው ጊዜ ሦስት ፕሮጄክት ይዤ ስለምሄድ በአሁኑ ወቅት እነርሱን ለማጠናቀቅ ደፋ ቀና እያልኩኝ ነኝ ::

ይህንን ያህል ግዜህንና ችሎታህን የሰዋህበትን አዲሱን ስራህን ልናይ ነዋ ! እሰይ እሰይ ብለናል እስከዚያው እግዚአብሄር ይርዳህ ወንድሜ አንፈራራ ::

የልጅነት ነገር ሲነሳ የባለሱቅ ተንኮል ነበር የሚያስቀኝ ለካ እንዲህም አለ ? በዚታ ለመጫን ብላችሁ ከኩሚና እስከ ራስብሩ ............... አቤት ልጅነት በሳቅ ፍንድት ነው ያልኩት ምን ያለበት ዝላይ አይችልም እንዲሉ ነው የሳቅኩት ! እኛም አንዴ ከኛ ሰፈር እስከ ቫይ ጊቢ በዚታዎ ሄደን በእግራችን ተመልሰናል አንተ ስትናገር ትዝ ብሎኝ እየሳቅኩ አብረን ለሄድነው ልጅ ብደውል ብደውል ላገኘው አልቻልኩም :: አሁን ሳስበው ያስቀኛልም ግን ደስም ይላል ከቫይ ጊቢ እስከ ከተማ በግምት 6 ኪሎሜትር አይሆንም ?

Quote:
የሙሽራው መኪና ምን ነበር ? ዚታዎ !!! Laughing Laughing
በጣም ገረመኝ የሙሽራ መኪና ኤኔትሬ ኤኔትሬውን በዘንባባና በአበባ ሽብርቅ አድርገው እየጨፈሩበት ሀይሎጋ ሲሉ :: እኔ ያየሁት ዚታዎ አጃቢ ሆኖ ነው የሙሽራ መኪና ላንድሮቨር አሀ ፈረስም አይቻለሁ ::

ደህና እደሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Wed Oct 06, 2010 9:08 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
በፖለቲካ እስረኛዋ ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር መለቀቅ የመጀመሪያው የደስታ መግለጫ መልዕክት የሞፊቲኮ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ::
<< እንኳን ለቤትሽ አበቃሽ ! እንኳንም ነጻ ወጣሽ ! >>

ሞፊቲ ምነው ጠፋህ ? በፌሽታ ደከምክ እንዴ ?
ራስብሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Oct 06, 2010 9:23 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ውድ ራስ ብሩ እውነት ብለሀል ::ትላንት እስር እንደምትፈታ ካወኩበት ሰአት አንስቶ ሁኔታውን በየደቂቃው እየተከታተልኩ ነበር ::ከስራም መጥቼ በፍጹም አልተኛሁም ::
እቤት መግባቷን ሳውቅ ነው አልጋዬ አረፍ ያልኩት ::
አሁንም የተለያዩ መገናኛዎችን በደስታ እየተከታተልኩ ስለሆነ ደስታው አልለቀቀኝም ::

ብርቱዬ የኔ እመቤት እንክዋን ለዚህ አበቃሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ !!!ምን ማለት እችላለሁ
እንኳን ደስ ያለን !!!

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Thu Oct 07, 2010 3:27 am    Post subject: Reply with quote

Posted: Wed Oct 06, 2010 9:54 am Post subject: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢዋ ልጆች

--------------------------------------------------------------------------------

ሰላም ሰላም ሰላም
የዋርካ ፍቅር ታዳሚዎች
እስኪ እባካቹህን ይህንን የተወለድኩበትን ቤቴን የማሳርፍበት ቦታ ጠጋ ጠጋ በማለት አበጁልኝ ....
እዚያ ዋርካ ጀነራል ውስጥ ሲንገላታ ... ነው የሚኖረው
ያገሬ ልጆች በቦምብ እና መድፍ ጥይት ድምፅ ጆሮውን አደንቁረውት ታሞዋል
እና እስኪ ሰላም እስኪፈጠር ድረስ በደባልነትም ቢሆን ትንሽ አሳርፉት
አደራቹን

ለራስብሩ አደቆርሳ ሞፍቲ አንፈራራ የግል ቅሩንፉድ መኑ ቺኮ ሽልንጌ እና ሁላቹም
ከዚህ በኃላ የቤታችን ግንኙነት ከዚህ በኩል ቢሆን እኔ እመርጣለሁ አንድ መፍትሄ እስኪገኝለት ድረስ

ወደዶሮዋ ታሪክ ከትንሽ ቀናት በኃላ እመለሳለሁ ::
ቤታችንን ከዚህ በኩል እንጎብኛት
ካልተመቻቹ ደሞ እንደተመቻቹ አድርጉት
ይህ የኔ ሀሳብ ነው
ምን ይመስላቹዋል ???
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
_________________
THANK YOU CYBERETHIOPIA

#################################################

ስላም ለቤታቸን ይሁን ባለፈው በተነጋገራቸሁት መስረት ወደ ዋርካ ፍቅር ተዛወራናል እና ቼክ አድርጉት
በብርትኳን መፈታትትት ከፍተኛ ደስታ ተስምቶኛል እልልልልልልልል ነው ያልኩት ከምር የኔዋ ጀግና በርቺልኝ

የግልልል
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Oct 07, 2010 5:57 am    Post subject: Reply with quote

ይህ ቤት ወደ
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=42699
እዚህ ቤት ተሸጋግሯል

ጦርነት ሸሽቶ ..... በጥገኝነት ዋርካ -ፍቅር ውስጥ ይገኛል እና

እዚያው ጎብኙን

ከሰላምታ ጋር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Oct 07, 2010 10:37 pm    Post subject: Reply with quote

አስቀድሜ ስለክቡር ደህንነታችሁ ያለኝን መልካም ምኞት እገልጻለሁ !
እንደምን ሰንብታችኍል ? ቸሩ ፈጣሪ ይመስገን እኔ በጣም ደህና ነኝ :: በድካሜ እና በብርታቴ ግዜ ሁሉ ቤታችንን ራቅ ባለ የጊዜ ስፋትም ቢሆን ጎራ እያልኩ አረፍ ሳልል አይሆንልኝም ::

ብዕርና ወረቀት ጊዜን አመቻችተው ሲገኙልኝ ደቂቃም አላባክንም ልቦናዬ እዚህች መድረክ ላይ ቁጢጥ ትልና ያየሁ የሰማሁትን በድጋሚ እየሳቅኩና እየተከዝኩ እጽፋለሁ
ጊዜው ይለፍ እንጂ ማየት አይሻለሁ
ሞት ካለየኝ በቀር በህይወት እያለሁ .................. እንዳለ የሀገሬ ዘፋኝ እድሜ ከተቸረን መተያየታችን አይቀርም
ዛሬ ግን ጊዜ አልሰጥ የሚል ትኩስ ምግብ ባለሱቅ አቅርቦ ከመሶቡ ለመቋደስ አላስቀምጥ ስላለኝ ወደ ዋርካ ለመገስገስ እንቅልፍ አጥቼ ነው ያደርኩና የዋልኩት ::
ስለሚከተለው አዋጅ መናገር ስላለብኝ መጣሁ !

ከዛሬ ጀምሮ ይህ ቤት ወደ ዋርካ ፍቅር ተዛውሯል
ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ?
የአምስት ዓመታትን ድካም በአንድ ጀምበር ዘግቶ መውጣት ነፍሴን አስኮርፏታል ::

እስከዛሬ ድረስ ለአምስት አመታት ግዜያችንን :ችሎታችንን : ጥሪታችንን የዋጀንበት : የሳቅንበት : ያዘንበት : መልካምና ትጉ ቁምነገሮችን የሰራንበት : ታሪካችንን አደባባይ የዘከርንበት : በፍቅር የማረክንበትና የተማረክንበት : ቤታችን በቃ ተዘጋ እና ሌላ አዲስ ቤት ተከፈተ ማለት ነው ?

እስከዛሬ ድረስ የነበረው ያሳለፍነው መዘክርነታችን አለቀለትና እንደሰነፍ ማስታወሻ ተጣለ ማለት ነው ?
የዘነጋናቸውን መጣጥፎች እንደገና እንድንፈትሻቸው ለማንበብና ለመጠየቅ የተገደድንባት ትምህርት ቤታችን ጊዜያችንን ገንዘባችንን ከሁሉ በላይ ደሞ በፍቅር የተፈተንንባትን ቤታችንን እንዝጋት ማለት ነው ?

በአዶላ ልጆች ደጋፊነት የሚያድጉት ረድ የሌላቸው ምስኪን ህጻናት ከጽንሱ መነሻነት ጀምሮ የነበራቸው የታሪክ መዝገብ ተረሳ ማለት ነው ?

የነ አንፈራራ ራስብሩ ወቤ (ጃሎ ) ኩቾ ሰፈር ዝምታ ባለሱቅ ሞፊቲ ቅሩንፉድ ቺኮኩባኖ የግልነስ ገተሜ ፈረንጅ ውሀ ክብረመንግሥት አይፋችን የቦሪቲ ሀገሬ ፖስታቤት ሰፈሬ ሳህሉውሀ ጉጂ ግርጃ ወዘተርፈ ትውስታና ጽሁፍ በዋርካ ጄኔራል አንዳንድ አስጸያፊ ጽሁፎች ምክንያት ዋጋ አጣ ማለት ነው ?

እኔ እስከምረዳው ድረስ በዋርካ ጄኔራል ጸያፍ ቃላትን የሚናገሩ የሚጽፉና የሚሳደቡ ሁሉ ግን አንዳቸውም ራስብሩ ቤት ገብተው ምንም ያደረጉት ነበር የለም !
ይህ ማለት ያከብሩናል ማለት ነው ! እርግጥ ነው ፍጹም ህሊናን የሚፈታተኑ ጽሁፎች ዋርካ እያስተናገደች መሆኗ እየተሰማ ነው ስለዚህ ከጸያፍ ነገር እሺ እንሽሽ እንበል ....
አሁን ያደረጋችሁት ግን አግባብ ነው ?
ምናልባት ቢሆንስ እንኳን የቤታችንን ጥሪት ይዛችሁ እንጂ ድካማችንን ጥሻ ውስጥ ሸጉጣችሁ እናንተ አዲስ ጎጆ የምትወጡበት ሁኔታ ተመችቷችኍል ? እኔ በውነት አልተስማማኝም ::
በደህና ጊዜ ያፈራናቸውን ልጆቻችንን እና ሀብትና ንብረት ትታችሁማ ስደት የለም ::
ስለዚህ ይሄ የማይሆን ጉዳይ ነውና ወደቤታችሁ ተመልሳችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ ::
የምወዳችሁ ወራ አዶላ አነጋገሬና አባባሌ በትልቅ አክብሮትና ትህትና መሆኑን ተረዱልኝ :
ደግሜ ለመናገር ያህል የቤታችንን ሙሉ ታሪክ ይዛችሁ ከሆነ የትም ብትገቡ ተቃውሞ ዲኖ : ነገር ግን እንደዚህ በአንድ ጀምበር የአምስት ዓመት ድካም ትቶ መሄድ ነፍሴን አስኮርፏታል :::::

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ !
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 08, 2010 3:57 pm    Post subject: Reply with quote

ዋውውውውውውውውውውው
ብራቮ ባለሱቅ
ለአመት የተዘጋ አንደበት በአንዲት ቀን ቦምብ ፍንዳታ ጎትተን አመጣነው
ብራቮ ባለሱቅ
ወዳታ ብለንሀል ... አንተ ቀዥቃዣ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
///////////////////////////////
አደቆርሳዬ .. ወንድሜ ወዳጄ ያገሬ ልጅ
እውነቱ ንገረኝ ካልከኝ ያንን ደባልነት ስጠይቅ እንዴት እንደከበደኝ እና እንደቀፈፈኝ ለመናገር ቃላቶች ያጥሩኛል

ሀሳቤም ደሞ ይህንን ገፅ በሌላ ገፅ በኩል ለማየት እንጂ ... ጨርሶ 5 አመት ፅሁፉን ዘግቶ አዲስ መክፈት አለነረም ... በፍፁም

ይህንን ቤት ከሌላ አምድ ለመገናኘት ከማሰብ የመጣ ትንሽዬ ጥፋት .... ግን ቦንብ አፈንድታ አንተን ይዛ የመጣች ጥፋት

ከልቤ ይቅርታ እንድታረጉልኝ እጠይቃለሁ .... ሀሳቤን በመጥፎ ወስዳቹት ለታዘባቹኝ ያገሬ ልጆች

እንዳልኩህ ይህንን ቤት ከሌላ አምድ ለመገናኜት ከነበረኝ ሀሳብ የተነሳ ነው .... ፊርማዬ ላይ ሊንኩን ያበጀሁት

እንዳላማረብኝ ግን ከአንድ ከማከብረው ሰው ስለተነገረኝ .... እግራቹ ላይ ወድቄ ይቅርታ በመጠየቅ ያንን የተውሶ የዳባል ቤት ትቼዋለሁ

ከሁ ;ሉም ያስደነገጠኝ እና የገረመኝ ግን 5 አመት ልፋት በከንቱ ለማስቀረት እንደተደረገ አድርጋቹ ስትቆጥሩ .ብኝ ..... እፍረቴ ቀይ ፊቴን አመድ አለበሰው

ለማንኛውም ....
ለሶስት ቀን ሽፍትነቴ እና ቀዥቅዝዣነቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ
ሀሳብም አላማዬም ግን አልነበረም ሌላ ሩም መክፈት
በቀላሉ አክሰስ ለማድረግ መስኮት ብትሆን ነበር አላማዬ
አልሆነም
ትቼዋለሁ
ከይቅርታ ጋር

አደቆርሳዬ ግን ስላየሁህ በጣም በጣም እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል
ያጠፋሁት ጥፋት ሁሉ ለራሴ ባንተ መምጣት እንደተካካሰ ነው የተሰማኝ
ለዚህ ነው በመግቢያዬ እንደገለፅኩት
እንኳን ቦንቡን አፈነዳሁት ያልኩት
አንተን ጠራልኛ !

በል እንግዲህ አትጥፋ ያገር ልጅ
የአንድ አመት ከረጢትህን ፍታና ... ጀባ በለን

በቀዳጅነታችን እንሰንብት
አሚን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Fri Oct 08, 2010 5:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

አደቆርሳሳሳሳሳሳሳሳሳ !!!!!!!!!!!! !!
አቤ .... በሶስት ቀን ውስጥ ሁለት የተለያዩ ደስታዎች !!!
አንተም ከቡርትዬ ብቅ አልክልን ?ደስታዬ ወደር የለውም ::ለካስ አንተን ያሰረህ ባለሱቅ ነበር ?እውነትም በትክክል
ጎትቶ ነው ያመጣህ ::ባለፈው እነ ራስ ብሩ ሲነጋገሩ እንደሰማሁት ከዋርካ ባለቤቶች በመነጋገር ፔጁን እንዳለ
ወደዋርካ ፍቅር ለመውሰድ ጥረት እንደሚደረግ ነበር ::እንዳልከው ይህን ሁሉ ልፋት ይዞ መሄድ ቢሆን ይመረጣል ::
አደቆርሳዬ በል አትጥፋ ::በተለመደው ሁኔታ ቶሎ ቶሎ ናልን ::

ቸር እንሰንብት :::
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማርቾረድ 86

መንገደኛ

Joined: 06 Oct 2010
Posts: 1
Location: tempe

PostPosted: Fri Oct 08, 2010 6:06 pm    Post subject: Re: ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!! Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
አያልቅበት ሌሊት ሌሊት መኪና ተራ የወጪ ከመጠየቅ በቀር በየቤቱ ልመና አያውቅም ነበር !!የሸዋን መኩዋንንት ስላስቸገረ በእኔ ትዕዛዝ የአዶላን አካፋ እንዲያነሳ ተገደደ ::በሁዋላም አቅሙ እየደከመ ሲመጣ ወደ /መንግስት መጣና የሌሊት ገጣሚ ሆነ ::የሚገርመው በረንዳ አዳሪም ሆኖ አገዛዙን በጣም ይዋጋ ነበር ::
ሰላምታዬ ከያላችሁበት ይድረሳችሁ !!!
This is Ras Biru Woldegabriel. ሶኦ ኢት ሙችት ረነውደ
ውድ የአዶላ ልጆች ይህቺን ጥሪ ሳቀርብ የክብረመንግሥት ልጆቸ እንድንሰባሰብ በማሰብ ነው ::
ያቺ እኛን ያስተማረች /ቤት አሁን አርጅታ ፈራርሳለች :: ዲፕሎማት ሚኒስትርና ሳይንቲስት ለመሆን የበቁ ታላላቅ ሰዎችን ያፈራች ያቺ ትንሽዋ ራስ ብሩ /ገብርኤል /ቤት ዛሬ በአጥንትዋ ቀርታለች ::የዋርካን አምድ ላዘጋጁልን ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለቦሬ ለሻኪሶና ለክ /መንግስት ልጆች ሁሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ :: /ቤታችንን እናድሳት !!
በመጀመርያ ግን መገናኘቱ አስፈላጊ ነውና : የካምቦ የፈረንጅ ውሀ ,የአራዳ ,የሜጫ ,የኩሚና ;የገበያ ክፍል ኩቾና ሌሎችም ተሰባሰቡ :ተገናኘተን እንኩዋን ትዝታችንን እናውጋ ::
.በሉ በቸር ይግጠመን :: ወዳጃችሁ ራስ ብሩ ነኝ ::

_________________
Nitesh Patel a blogger and internet marketing specialist which helps the business like PHP shopping Cart and Direct mail Tools .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Fri Oct 08, 2010 8:52 pm    Post subject: Reply with quote

ጉሮ ወሸባዬ ጉሮ ወሸባ . . . . ሰውዬው እንኳን በደህና መጣህ !
አዲሱ እንግዳችንም ማርቾረድ 86 ቤት ለእንግዳ ብለናል
ዛሬ ቤታችን የድሮ መልኳን ልትይዝ ዳር ዳር የምትል ይመስላል የጠፋም አዲስም እንግዳ ይዛ መታለችና
በቅድሚያ ለመናገር የምፈልገው ቢኖር ባለሱቅ የምናደርገው ነገር ሁሉ ጥሩ ለማድረግ ነው አደቆርሳም ያነሳው የራሱን ጥሩ አስተያየት ነው
አንተም ቸኩለሀል ምክንያቱም ያቀረብከውን ሀሳብህን ተቀብየ የዋርካ አድሚኖችን እየጠበቅን ነበር በመሀሉ የከፈትከው አደቆርሳም ቸኩሏል ምክንያቱም ብንቀይርም እንኳን ቤታችን ይዘጋል ብሎ እንዴት እንዳሰበ አላውቅም ቤታንን ትተነው እንሄዳለን ብለን እንኳንስ እኛ ተመልካችም አይጠብቅም ስለዚህ አስተያየቱ ለኔም ከብዶኛል ::
ዋናው ነገር ሁሉም ለበጎ ነው እዚህ ቤት ጥፋት የለም
ለማለት ነው ::
ማርቾረድ 86 በድጋሚ እንኳን በደህና መጣህ // ይልመድብህ //
ሠውዬው እንግዲህ የተከማቸውን ዘርገፍ ዘርገፍ እስክታደርግ ቸኩያለሁ ::

ደህና እደሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Fri Oct 08, 2010 9:12 pm    Post subject: Reply with quote

አደቆርሳ ! እንኳን ደህና መጣህ ! የዚህ ቤት ነገር ስለማይሆንልህ ነው :: አይደል ?

ትክክል ነው ሁላችችንንም ይነካናል :: ባለሱቅም ያንን እርምጃ የወሰደው ዋርካ ጄነራል ባጠቃላይ የጭቅጭቅ ቤት አልፎ አልፎም ከመስመር የወጣ አስነዋሪ ጽሁፍ የሚታይበት በመሆኑ ነው :: እኔም ቤታችን ወደ ሌላ ጊቢ ቢገባ ደስታየ ነው ግን ጉዞአችንን ጠቅልለን መሆን አለበት :: ማለት የተጻፉት ሁሉ አብረው መሄድ አለባቸው :: በዚህ ከአደቆርሳ ጋር እስማማለሁ ::

ግን ትንሽ ቅር የሚያሰኘው የዋርካ አስተዳዳሪዎች ለአቤቱታ ጆሯቸውን የማይሰጡ መሆናቸው ነው :: ሰዎች የሚያጸይፍ ነገር ሲጽፉ እያዩና ሌሎች ቅሬታቸውን ሲገልጹላቸው በግድየለሽነት አቤቱታውን ችላ ማለታቸው የሀላፊነት ጉድለት ስለሚመስልባቸው ሁኔታው ግን እንደዚያ ከቀጠለ ዋርካ ጨርሶ እንዳይዘጋ ያስፈራል ::

"Medrek" የሚባለው የውይይት ዌብሳይት ትዝ ይላችሁዋል ? በጣም በጣም ተወዳጅ ነበር :: ነገር ግን በፖለቲካና በሀይማኖት ንትርክ ምክንያት ቤቱ እየተበላሸ በመሄዱና እስተዳዳሪዎቹም ምንም የማረሚያ እርምጃ ባለመውሰዳቸው በመጨረሻ ተዘጋ :: በጣም ነበር ብዙዎቻችን ያዘነው :: ከአንድ ሁለት አመት በህዋላ አሁን ለማንሰራራት ቢሞክር ብዙም አልተሳካለትም ::

ስለዚህ ዋርካም ኣይነት ክፉ እድል እንዳይገጥመው ከአሁኑ መጠንቀቅ ይገባል ::

በተረፈ ለሁላችሁም ሰላምታየ ይድረሳችሁ ::
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 312, 313, 314 ... 381, 382, 383  Next
Page 313 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia