WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 314, 315, 316 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Oct 14, 2010 2:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሞፊቲኮ አመሰግናለሁ ! ጸሀፊውንም ኖሞናኖቶ ከልብ እናመሰግናለን !
ሁላችሁም ጠፋ ጠፋ ማለታችሁ አሳስቦኛል .......................
ባለሱቅ መልክት ሰድጄልሀለሁ መልስ ስጠኝ ::
ለሁሉም ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ዓለምን ያስደመመው ትልቅ የዘመናችን ድንቅ ጉዳይ ሁላችሁም በሚገባ እንደተከታተላችሁት ምንም ጥርጥር የለኝም ብቻ ዝም ብሎ ማለፍ ነፍሴን ስላስቻላትም ::
ባለሱቅ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ እውቀት አታጣምና ትንሽ ትለናለህ የሚል ጉጉት ነበረኝ
ለሁሉም የኔን ልተንፍስና ልቀመጥ
ቀደም ሲል እዚህችው ቤት ውስጥ ስለ ማዕድንና ናዳ ብዙ ብለናል ኑሮና ህይወታችን ከተወለድንበትና ካደግንበት አካባቢ ይህንንው የማዕድን ስራ የምናውቀውና ከፊሎቻችንም በዚያው ላይ የተመሰረተ ህይወት ስላሳለፍን እያሳለፍንም ስለሆነ ከየተለያዩ ምንጮች የቀራረምኩትን እና እግረመንገዴንም የእግዚአብሄርን ተአምር በጥቂቱ ለማለት ወደድኩ ::
ለማስታወስ ያህል በክብረመንግሥት ብዙዎቻችሁም የምታውቋቸው ለኩ ደምሴ ሞት እምቢ ኡታሎ የአስራት ኡታሎ አባት (የራስብሩ አጎት ) ቁምቢ ሮቢ እና ሌሎችም የናዳ ሰለባ የነበሩና ያለምንም አገልግሎት የተጣሉ ማእድነኞች ነበሩ አሁን ሁሉም በህይወት የሉም ::
ከናዳ እንዴት እንደተረፉና እንደተጎዱ ከዚህ በፊት ያልነው በቂ ስለሆነ የነሱን እዚህ ላይ ልተወው ::
በቺሊ በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ማዕድነኞች የተከፈተው ጉድጓድ በላያቸው እንደተዘጋባቸው ዜና በተነገረ ግዜ ቺሊ በአንድነት አለቀሰች : መላውም ዓለም አብሯቸው አዘነ የሀገሪቱ መሪዎችና ሚኒስትሮች አሰቡበት ወዲያውም ዘመቻ ፓሌሬንዞ ተቋቋመ ::
በዚህ ምንም አይነት ቸር ወሬ በማይሰማበት ክፉ ዓለም ይህንን የመሰለ ፈጣን ተአምር ማየታችን የእግዚአብሄር ሥራ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም ::
ከግዙፉ የአሜሪካ የናሳ ምርምር ተቋም እስከ ተለያዩ የከርሰ ምድር ጥናት ድርጅቶች ድረስ አለም ያላትን እውቀትና ጥበብ በመጠቀም የእነዚህን ሰዎች ህይወት ማትረፍ መቻል እጅግ አስገራሚ ነው :
በቺሊ የማዕድን ሥራ ላይ የነበሩት 32 ቺሊያውያን እና አንድ ቦሊቪያዊ 69 ቀናት የከርሰ ምድር ቆይታ በኍላ ዳግም በሰላም ይህቺን ምድር መቀላቀላቸው
የዓለማችን ታላቁና ብቸኛው የመልካም ዜና ምሳሌ ሆኖ ተገኝቷል :: ዘመቻ ፓሌሬንዞ በሰላምና በድል ተጠናቀቀ ::
በዚህም ላይ ሰዎቹን ለማውጣት የታሰበው 48 ሰዓታት የጊዜ ትልም 33ቱን ማዕድነኞች የቴክኒክ እና የህክምና ባለሞያዎቹንም ጨምሮ ለማውጣት የፈጀው ጊዜ ከታሰበው 48 ሰአታታ ከግማሽ ያነሰ (24) ሰአት የማይሞላ ወይንም 22 ሰአታት ብቻ ሆኖ ተጠናቋል :: ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሄር የጮኸው የቺሊ ህዝብና መንግሥት ተገቢውን ምላሽ በማግኘቱ አምላኩን አመስግኗል : ከዚህ አለም ብዙ ሊማር ይገባዋል ::
ቺሊ በአለም ካሉ የማዕድን አምራች ሀገሮች አንዷ ነች
ወደ 60% የሚጠጋው የሀገሪቱ የኤኮኖሚ ምንጭ ማዕድን ነው በቺሊ የመሬት ድርመሳ ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያው አይደለም በርካታ ግዜ አጋጥመዋል ይህንን የመሰለ ዝነኛ ታሪክ ግን በየትም ሀገር ታይቶ አይታወቅም ::
ማዕድነኞቹም አዲስ ባለሬኮርድ ሆነዋል
በከርሰ ምድር በቆዩበት ጊዜ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ተጸእኖ በሚያሳድርባቸው ጉዳዮች ላይ አንዳንድ የህክምና ጠበብት የሚያነሷቸው ነጥቦች ከግምት የሚገቡ ናቸው ::
አካላዊና ስነልቦናዊ ችግሮች ሊኖሩባቸው ስለሚችል በሆስፒታል እንዲቆዩ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል ::
ቶሎ ወደቤተሰቦቻቸው ቢቀላቀሉ የመነጫነጭ በህይወት አለመርካት አለመደሰት ወዘተርፈ የመሳሰሉት ሊከሰቱ እንደሚችሉም ጠበብቱ ይናገራሉ ::
ከዚህ ቀደም በአሜሪካን እና በቪየትናም ጦርነት ወቅት የአሜሪካ ወታደሮች ከብዙ የስቃይና የመከራ ግዜ በኍላ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኍላ ባጠቃላይ የነበራቸው ሁኔታ የአይምሮ አለመረጋጋት የቤተሰብ /የትዳር መረበሽና / ሰላም ማጣት እንዲሁም ለአልኮልና ለሱስ ቶሎ የመጋለጥ ሁኔታ እንደነበረባቸው መረጃዎች አረጋግጠዋል በእነዚህም ማዕድነኞች ላይ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከወዲሁ ጠበብት ስጋታቸውን ጀባ ማለታቸው ለአስገራሚው ክስተት መፍትሄ ወላጅ ይሆናል ተብሎ ይታመናል ::
በሀዘን አብሯቸው የተጎዳውን እና በሰቀቀን የኖረው ቤተሰባቸው በመንግሥታቸው ዕይታ ውስጥ መልካም የኑሮ ደጎማ ሊደረግላቸው እንደሚችል ይገመታል :
ከምግብ እስከ ቢራ ማምረቻዎች በርካታ የሀገራቸው ለጋሾችም ብዝ ስጦታዎችን ካሁኑ ቃል እየገቡላቸው ናቸው
አንድ የቺሊ ባለሀብት ብቻ ለእያንዳዳቸው 10 ሺህ ዶላር ሸልሟቸዋል ይህ አሀዝ በቺሊ የአንድን ሰው ህይወት ይቀይራል ::
በሌላ በኩል እያንዳዳቸው በተሰጣቸው የንግግር እድል የተናገሩት አስገራሚና አስደሳች ነው
በትውልዱ ቦሊቪያዊው እኔ ከእንግዲህ በኍላ የማዕድን ስራ ውስጥ አልገኝም ሌላው ይቅር የማዕድን ሰራተኛ የሆነ ማወቅም አልፈልግም ሲል አንዱ ቺሊያዊ ደሞ በተራው
እኔ እንደገና ተወልጃለሁ አሁን አዲስ ሰው ስለሆንኩኝ ስራዬን እንደገና ብዬ እጀምራለሁ ሲል ተደምጧል ::
ኮሎኔልና ራስብሩ እንኳን ደስ አላችሁ መላው ህዝብ እንኳን ደስ አለን እላለሁ

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ

_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Oct 14, 2010 8:26 pm    Post subject: Reply with quote

አደቆርሳ እንደጻፈ(ች)ው:
... በቺሊ በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩት ማዕድነኞች የተከፈተው ጉድጓድ በላያቸው እንደተዘጋባቸው ዜና በተነገረ ግዜ ቺሊ በአንድነት አለቀሰች : መላውም ዓለም አብሯቸው አዘነ የሀገሪቱ መሪዎችና ሚኒስትሮች አሰቡበት ወዲያውም ዘመቻ ፓሌሬንዞ ተቋቋመ ::
በዚህ ምንም አይነት ቸር ወሬ በማይሰማበት ክፉ ዓለም ይህንን የመሰለ ፈጣን ተአምር ማየታችን የእግዚአብሄር ሥራ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም ::
ከግዙፉ የአሜሪካ የናሳ ምርምር ተቋም እስከ ተለያዩ የከርሰ ምድር ጥናት ድርጅቶች ድረስ አለም ያላትን እውቀትና ጥበብ በመጠቀም የእነዚህን ሰዎች ህይወት ማትረፍ መቻል እጅግ አስገራሚ ነው :
በቺሊ የማዕድን ሥራ ላይ የነበሩት 32 ቺሊያውያን እና አንድ ቦሊቪያዊ 69 ቀናት የከርሰ ምድር ቆይታ በኍላ ዳግም በሰላም ይህቺን ምድር መቀላቀላቸው
የዓለማችን ታላቁና ብቸኛው የመልካም ዜና ምሳሌ ሆኖ ተገኝቷል :: ዘመቻ ፓሌሬንዞ በሰላምና በድል ተጠናቀቀ ::
በዚህም ላይ ሰዎቹን ለማውጣት የታሰበው 48 ሰዓታት የጊዜ ትልም 33ቱን ማዕድነኞች የቴክኒክ እና የህክምና ባለሞያዎቹንም ጨምሮ ለማውጣት የፈጀው ጊዜ ከታሰበው 48 ሰአታታ ከግማሽ ያነሰ (24) ሰአት የማይሞላ ወይንም 22 ሰአታት ብቻ ሆኖ ተጠናቋል :: ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሄር የጮኸው የቺሊ ህዝብና መንግሥት ተገቢውን ምላሽ በማግኘቱ አምላኩን አመስግኗል : ከዚህ አለም ብዙ ሊማር ይገባዋል :: ...

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ [/color]

ሰላም ወንድሜ አደቆርሳ : ሰላም የዚህ ክፍል ታዳሚዎች በሙሉ -

ስለቺሊው የማዕድን ጉድጓድ አደጋ ክስተት ዜና ስከታተል ሁልጊዜ የዚህን ክፍል ታዳሚዎች አስብ ነበር :: ከትላንት ወዲያ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ትላንት ረቡዕ ማታ ድረስ ሁኔታውን በቀጣታ ከሥፍራው በቢቢሲ ከሚተላለፈው ዘገባ እከታተል ነበር :: የእያንዳንዱ የማዕድን ቆፋሪ የግል ታሪክ በራሱ አንዳንድ ትልቅ መድበል የሚወጣው ነው :: ከሁሉም ያስገረመኝ ግን የቺሊው ፕሬዘዳንት ሴባስቲያን ፔኔራ ሁኔታ ነበር :: ለሁለት ቀናት ሙሉ ኃላፊነት ወስደው እያንዳንዷን ድርጊት ተከታትለውና ውሣኔ በመሥጠቱ እየተሣተፉ በመጨረሻም ከአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ጋር የሚያያዝ : ያለፈውንም የአገራቸውን ሥም በመጥፎ የሚያስጠራ የፒኖሼ ዘመንን የታሪክ ጠባሣ ፍፃሜ በሚያመለክት መልክ የማዕድን ጉድጓዱን የማሸግ ድርጊት ሲፈፅሙ ስመለከት ዓለማችን ለካ አሁንም ፈጣሪያቸውን የሚያምኑ : ፍፁም ትሁትና ጨዋ መሪዎች አላጣችም ብዬ ተደመምኩ :: የእናንተን ባላውቅም እኔ ግን በቺሊ ሰዎች ቀናሁ : መንፈሣዊ ቅናት ::

'እኛ ኢትዮጵያውያንስ መቼ ነው እንዲህ ያለ መሪ አገራችንን ሲመራ የምናየው ? መቼ ነው ሁላችንም በፍቅር : በመተሣሠብ : በአንድነት ቆመን ለአገራችን እና ለተተኪው ትውልድ መልካም ነገር ለማድረግ የምንነሣው ?' ብዬ አሠላሠልኩ :: ቢያንስ ቢያንስ የዚህ ክፍል ወገኖቼ ይህንን ተግባር የአቅማቸውን አስተዋፅዖ በማድረግ ጀምረውታል ብዬ ስለማምን የልቤን ለመተንፈስ ወደዚህ ዓምድ ጎራ አልኩ ::

እግዚአብሔር መልካም ኃሣባችሁንና ተግባራችሁን ከዳር ያድርሥላችሁ ::

አክባሪ ወንድማችሁ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Thu Oct 14, 2010 8:48 pm    Post subject: Reply with quote

በእውነቱ ተድላ እንዳልከው እኔም በቺሊው ፕሬዚደንት በጣም ተደንቄአለሁ ::

የቺሌ ዜጎች በጣም እድለኞች ናቸው :: የኛም ሕዝብ አንድ ቀን ቀን ይወጣለታል ::

ይቅርታ ቶሎ መሄድ ስላለብኝ ነው ::

ቻው !
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Oct 14, 2010 9:10 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ተድልሽ = ህመምህ እኔም አለ ::ምንም ሳልጨምርበት ያንተን ሀሳብ እኔም እንዲህ ብዬ እደግመዋለሁ ::

Quote:
እኛ ኢትዮጵያውያንስ መቼ ነው እንዲህ ያለ መሪ አገራችንን ሲመራ የምናየው ? መቼ ነው ሁላችንም በፍቅር : በመተሣሠብ : በአንድነት ቆመን ለአገራችን እና ለተተኪው ትውልድ መልካም ነገር ለማድረግ የምንነሣው ?' ብዬ አሠላሠልኩ :: ቢያንስ ቢያንስ የዚህ ክፍል ወገኖቼ ይህንን ተግባር የአቅማቸውን አስተዋፅዖ በማድረግ ጀምረውታል ብዬ ስለማምን የልቤን ለመተንፈስ ወደዚህ ዓምድ ጎራ አልኩ ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Oct 14, 2010 11:01 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ ተድላ ወደር የሌለው ምስጋናዬ ካለህበት ይድረስህ !
የማከብርዎ ኮሎኔል መሰንበቻዬን የተድላ ኃይሉን የስፖርት ሪፖርቶች ሳነብ በነበረበት ወቅት አንድ ነገር ተገነዘብኩ እርስዎ ልጅ ተድላ እያሉ የሚጠሩበት በቂና ጥሩ ምክንያት ሊኖርዎ እንደሚችል እገምታለሁ ሆኖም የተሰጠው ስም መልካም እንደሆን በማመን እኔም እንደ እርስዎ ልጅ እያልኩ ብጠራው ፍቃደዎ እንደሚሆን አምናለሁ ::
እጅግ የማከብርህ ልጅ ተድላ ይህንን አስደናቂ ታሪክ ከአንድ ቢሊየን በላይ የአለም ህዝብ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት እንደተከታተለው ሰማሁ እኔ ወንድምህ የተከታተልኩት ግን አብዛኛውን በራዲዮ ነው ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ሰባት የሚሆኑ የተለያዩ ጽሁፎችን ከዜና መጽሄቶች ድህረ ገጾችና ጋዜጦች አንብቤያለሁ ::
ራዲዮ ማዳመጥ በጣም እወዳለሁ ይህንን ልምድ ያገኘሁት ከአባታችን ይመስለኛል ለአባቴ እጅግም ፍቅር ሳይኖረኝ ነው ያደኩት ሆኖም አንዳንድ ውርሶቼን እወዳቸዋለሁ ::
ስለ አስተያየትህ እያመሰገንኩ ጠንካራ መልክትህን አደንቃለሁ
የቺሊው ፕሬዚዳንት አለምን ጉድ ያሰኘ ሥራ እና ምግባር በመስራት የመጀምሪያው ሰው ነው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም በረሀ ውስጥ ሙሉውን ሰአት ቆሞ እያንዳንዱን ሰራተኛ እያቀፈና አብሮ እየዘመረ ሲቀበል ኦህ ማይ ጋድ ልዩ ተአምር ነው ዘንድሮ የታየው ::
ውነትህን ነው ዐለማችን እንዲህ ያለም ሰው አላት እንዴ ? ያሰኛል ::
አውግስቶስ ፒኖቼን ማንሳትህ ደንቆኛል ትክክል ነህ የሰውዬውን መጥፎ ስራና ታሪክ የሻረ የቺሊን ህዝብ በታሪክ መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ያደረገ የመጀመሪያው መሪ ሆኗል ::
ቺሊ በአብዮት እሳት በተቀጣተለችበት ወቅት በአጭር ግዜ ውስጥ የመውደቋ ትልቁ ምክንያት በተፈጥሮ ያላት የማዕድን ምርትና ገበያው ነው : ያኔ ኢምፔሪያሊዝም የምንለው የአሜሪካው ሥርዓት ሥጋት ላይ በመውደቁ ቺሊን በአንድ ጀምበር እንድትንበረከክ አድርጎአታል ::
በፒኖቼ የፈሰሰው ደምና የቺሊ ጥፋት በታሪክ ሰፊ ቦታ ያለው ቢሆንም ዛሬ የአለንማችን ረሀብ ከስህተት መማርና ማስተማር ነው ይህንንም ረሀብ ለህዝባቸው አጥግበው የተገኙት የመጀመሪያ መሪዎች ብንላቸው ቺሊያውያን አይበዛባቸውም ::
በህዝባቸው አንድነት ዓለም ሊኮራ ይገባል !
ይህም የቺሊ አንድነትና ፍቅር ህዝባቸውን ከታላቅ ሞት እንዲታደግ ዋነኛ ምክንያት ነው

እንዳልከው እያንዳንዱ ማዕድነኛ ያለው ግለ ታሪክ አስደናቂና ልዩ ሆኖ በመገኘቱ ግዙፉ የፊልም ዓለም ሀሊይውድ ፊልም ለመሥራት ዝግጅቱን ማድረግ ጀምሯል
ታላላቅ ጸሀፍትና ደራሲያን ሞያዊ ምግባራቸውን ለአለም ሊገልጡ ከማዕድነኞቹ ቤተሰቦችና የቅርብ ወዳጆች የሙጥኝ ማለትን ጀምረዋል
ቀደም ሲል እንደተናገርኩት በዚህ ክፉና የጥፋት ዘመን ይህንን የመሰለ የመዳን ተስፋ ማየታችን አምላካችንን እንድናመሰግን እና እኛም እንድንዋደድ ትልቅ ትምህርት አግኝተናል ::
ኢትዮጵያችን እንደ እሾህ ሀረግ ከተጠመጠሙባት መሪዎቿ ድህነቷና የጥፋት መልክተኞ ከሆኑ ጠላቶቿ ነጻ ሆና ህዝቧና መላው ሀገሪቱ አንድ ሆነው የሚገኙበትን ቀን እንድናይ የአምላክ ፈቃድ ይሁን !
አሜን !

አንፈራራችን ስለ ቺሊው ፕሬዚዳንት አንድ ለማለት የፈለከው ነገር ነገር ግን ሰአት እንዳነሰህ መልክትህ ያስረዳል ግዜ ስታገኝ ያለህን አካፍለን ::

ሞፊቲኮ የናፈቀኝን ጽሁፍህን አንብቤ መርካት አልቻልኩም እንደው ነካ እድርገህ ነው የምትሄደው ጊዜ ጠፋ አይደል ?

ቸር ያቆየን
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Fri Oct 15, 2010 8:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
ሞፊቲኮ የናፈቀኝን ጽሁፍህን አንብቤ መርካት አልቻልኩም እንደው ነካ እድርገህ ነው የምትሄደው ጊዜ ጠፋ አይደል

ውድ አደቆርሳ =አንተን እየኮመከሙ ምን መጻፍ ያስፈልጋል ብለህ ነው ? አመት ሙሉ የናፈከንስ አንተው አይደለህ ወይ ?
እኔ እኮ ብጽፍም ለሞራል እንጂ በቁም ነገር እንዳይዶል ይታወቅ የለም ወይ ?
ይልቅስ እኔን ግርም ያለኝ የባለሱቅ ነገር ነው ::
አደቆርሳን ወልዳችሁ ካላመጣችሁ .....በጣም ናፈቀኝ .....ወደየት ሄጄ ላግኝው ..............አመት እኮ አለፈው ....
....ሲል ከርሞልህ አንተ ብቅ ስትል ናፍቆቱን እንኳ ሳይጨርስ ሌላ ቤት ውስጥ በርጫ ቤት በሙሽሪት
ስም ከፍቶልህ ሀድራውን አጣጡፎታል ነው የምልህ ::
በጣም የሚገርመው ነገር ገበያው ስለደራለት የሱቁን ስራ ትቶ ሺሻና የማናውቃቸውን የጫት ዘሮች
ሁሉ እያመጣ ሲሸጥ ያደገበትን የዶሌን ጫት ስሙን እንኳ አለማንሳቱ ቁጭት ውስጥ ከቶኛል ::

ራስ ብሩ =ምነው ሀለቃህ ሲመጣ ሸሸት ሸሸት ማለት ጀመርክሳ ? ወቤ እንኳ የሱን መምጣት እንደሰማ ደውሎልኝ
እንኳን ደስ ያለህ ሲለኝ የጠፉትንም ሁሉ ማነቃቃቱን ተረዳሁ ::

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት በጊኒ በሀገሩ ሜዳ ላይ ያን ሁሉ ውርደት ተከናንቦ ዛሬ ማዳጋስካርን ስላሸነፈ
ፌዴሬሽኑም ደጋፊውም ጮቤ ሲረግጥ በጣም ገረመኝ ::ለማይደገም ሁጤት ሊያውም በዚህ አንጨቆረር
ለወረደ .........ዝም ነው !!!!

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 15, 2010 9:28 pm    Post subject: Reply with quote

ይቅርታ ያገሬ ልጆች
ሰሞኑን ዙረት አብዝቼ የቺሊውን ታሪክ እራሱ መስማት አልቻልኩም
ለነገሩ ስለጉዳዩ ከሰማሁ የቆየሁ ቢሆንም .... ሰሞኑን ግን በእግዜርና በህዝቡ እርዳታ ከተቀበሩበት ግማሽ ኪሎሜትር ጥልቀት ጉድጓድ 69 ቀን በኃላ ሊወጡ እንደሆነና
ራስብሩም እንድንፀልይ ሲጠይቀን .... ፀሎቴን በተጤየኩት መሰረት ካደረስኩ በኃላ ....
ተመኘሁ
ክፉኛ ተመኘሁ
ቅናትም ያዘኝ
የምን ቅናት አትሉም
እግዜር እንደው በታምራቱ ,... ለዚች 50አመት በላይ
ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ሆና ... በኪሎሜትር ጥልቀት ጨለማ ውስጥ ተቀብራ ላለችው አገራችን
መቼ ነው መወጣጫ አንሳንሱር ተሰርቶላት .. እንደቺሊዎቹ የማዕድን ሰዎች በእልልታና በምስጋና መሬቷን ስመን
ተመስገን አምላካችን .. ተአምራቱ የማያልቅብህ ጌታ
ምስጋና ይገባሀል
እያልን የምንጭፍረውና .... የአለም ዜና ይህንን ተአምር የሚዘግብልን ........ ለሀገራችን
ብዬ የሞኝ ምኞት ተመኝቼ ከረምኩ እላቹዋለሁ

አደቆርሳ ወንድሜ ... እንዴት ነው ጂኦሎጂስት መሰልኩህ እንዴ ... ባለሱቅ ዘገባ ያቀርባል ብለህ እንዲህ የጠበከኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ቀሽም ነገር ነህ ከምር
ደሞ ባለሱቅ ብሎ ዘገባ አድማቂ .... ሂዶ ይህንን የዶሌውን ጫት ይቃም እንጂ
ሞፍቲ አንተ አቃጣሪ ... ቀናህ አይደል ... ያቺን የጫት ቤቷን ልጅ እንደተመኘሀት ስላላገኜሀት ... በቀደም ለመቃም የመጣህ ቀን
አታገኛትም እርምህን አውጣ
ጉልበቴ ላይ አስቀምጫት ነው ... ማስቅማት ... በሺሻ ....
ደሞ የዶሌ ጫት ይላል እንዴ .... የገራባ ክምር በለው እንጂ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ከድር ዶሌ እንዳይሰማኝ ብቻ

እስኪ ደሞ ትንሽ ጊዜና ጉልበት አጠራቅሜ እመለሳለሁ

ሰላም ሁኑልኝ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 15, 2010 10:16 pm    Post subject: Reply with quote

ድሮ ድሮ እትዬ ትሁኔ የምትባል ሴት አካባቢያችን ትኖር ነበር አሁን በህይወት የለችም :
እኔ ካወቅኳት ጀምሮ የታወቀች ቀምቃሚ ነበረች ሞቅ ሲላት በመሀረቧ አንኳር ጨው አታጣም ፈታ ታደርግና እንደከረሜላ አንዷን አንኳር ወደ አፏ ወርወር ታደርጋለች
ጨው የመጠጥን ሽታ የማገድ ችሎታ እንዳለው ከሷ ነው የተማርነው ::
ታዲያ ከካቲካላ ውጪ መጠጥ አትወድም ጥሩ ካቲካላ የምታወጣን ሴት በደንብ ታደንቃለች
ጸብና ነገር አታውቅም ብቻ ሞቅ ሲላት ኬሪዳሽ የምትለው ነገር ነበራት ::
አንዴ በጣም ልጅ ነበርኩኝ እሷ ደሞ ሁለት ልጆች ነበሯት
ሾእናሞ እና ኑኑ የሚባሉ :
እነዚህን ልጆች ምናልባት ባለሱቅ ልታውቃቸው ትችላለህ
ምክንያቱም ካደጉ በኍላ የአራዳ ልጆች ሆነው የተገኘውን እየሰራሩ ነው የኖሩት እንደውም እናታቸውንም ወደ አራዳ ያስገቧት እነሱው ናቸው ::
ታዲያ ያኔ ሾናሞ እና ኑኑ ከአማርኛ ይልቅ ሲዳምኛ መናገር ይቀላቸው ነበር መሰለኝ ካልተሳሳትኩ እድሜያቸው ሶስት አመት ቢሆን ነው ::
አንድ ቀን እትዬ ትሁኔ ቀን ላይ እቤት መጣችና ለእማማ የሆነ ለቅሶ አለብኝ በልጆቹ ምክንያት ስልሄድ ቀረሁ ምናምን ብላ አሳመነቻትና ልጆቼን እርስዎ ጋር ልተዋቸውና ልሂድ ስትል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነትን አግኝቶ ልጆቹን እኛ ቤት ትታቸው ወደ ለቅሶዋ ሄደች :
ብትጠበቅ ብትጠበቅ የውሀ ሽታ ሆነች እማማም ወደ ጉዳዩዋ መሄድ ስለነበረባት የልጆቹ ጥበቃ በኔ እጅ ወደቀ
አደራ ትሁኔም አሁን ትመጣለች ጠብቅ ብላኝ ወጣች
ነፍሱን ይማረውና በልጅነቴ የምወደው ጓደኛዬ ሰብስቤ ከበደ ውጪ ሆኖ ፉጨቱን ሲያሰማኝ ዘልዬ ወጣሁ
ከጎረቤት ማሳ ሸንኮራ የምንሰርቅበት ግዜ የከብቶች መግቢያ ሰአት ላይ ነው :
ጓደኛዬን ሳገኘው ልጆቹን ረሳኍቸውና ተያይዘን ወደ ሸንኮራ ሰረቃ ሸመጠጥን ጠርብ ጠርብ የሚያካክለውን ገንድሰን ይዘን ስንመለስ እነሾናሞ የሉም ምንም አልመሰለኝም እናታቸው የወሰደቻቸው ነው የመሰለኝ ወደ ሜዳው ወጣ ብለን ሸንኮራችንን ስንከሰክስ እትዬ ትሁኔ ከላይ ጨብ ብላ ወደግራና ቀኝ እያለች ስትመጣ አየኋት
ልጆቿን ፍለጋ እንደሆነ ገባኝና ሮጨ ወደቤት ሄጄ በየክፍሉ አየኍቸው .......................... (ሁለቱም ክፍል )
የሉም ሜዳም ላይ የሉም ደነገጥኩ እትዬ ትሁኔ በር ላይ ደርሳለች :
ሞቅ ሲላት ምንም አትናገርም ሁሉንም ነገር በአይኗ ነው የምትናገረው ወዲያው አንድ ሀሳብ መጣልኝ
አንቺ ስትቆዪ እቤት ወስጃቸው እንቺ ያለሽ መስሎኝ በር ላይ ትቻቸው ተመለስኩ አልኳት : ድንጋጤዋ በጡዘት አይታወቅባትምም ብቻ እማማን ፍለጋ አይኗን ስታማትር የለችም አልኳትና ፊቷን አዙራ ሄደች :
ውጪ ቁጭ ብዬ ሸንኮራዬን እየገረደምኩ ሳለሁ እማማ ሾናሞን እና ኑኑን ይዛ ከች አትልም ?
ክው ብየ ቀረሁ በቃ እንደዛን ቀን ቁጣ አይቼባት አላውቅም ልትበላኝ በኖርኩበት ሀገር ጉድ ልታረገኝ ነው አንድ ጀምበር ቁጭ ማለት አቅቶህ ? አንተ ቀትረ ቀላል ልትመታኝ ዱላ ብድግ ስታደርግ የቡናውን ማሳ ሜዳ አደረኩትና ፈትለክ ብዬ በቀጥታ እትዬ ትሁኔ
በጣም ይገርማል እንኳን የሰከረች መጠጥ ቀምሳ የምታውቅም አትመስልም :: ልጆቹን ነይና ውሰጂ ተብለሻል አልኳት ጠጋ ብዬ ሳያት አትናገርም እንባዋ ግን በአይኖቿ ይወርዳል እኔም እንባዋን ሳይ በጣም ደነገጥኩ :: ቀጥ ብላ ሄዳ አመጣቻቸው :
አድገን ትልልቅ ልጆች ሆነንም እትዬ ትሁኔ አትወደኝም ነበር :: ዘመኗን በሙሉ እንደጠላቺኝ በመኖሯ አሁንም ድረስ ሳስበው አዝናለሁ ::

እንዲህ ደሞ የማልረሳውን ቀን አስታውሳለሁ
ጎረምሶች ሆነን ሻኪሶ ጥምቀተ ባህር የሚባለው ሥፍራ እንደምታውቁት በማዕድን ፖሊስ ታጥሮ ሲጠበቅ ነበር የሚኖረው ብዙ የሻኪሶ ልጆች ማታ ማታ እየሾለኩ እየገቡ ድንጋይ እየሰበሰቡ ይወጡና ቀን ቀን እየተወቀጠ ታጥቦ የሚገኘው ወቅር ተሸጦ የቸርነት አቃራ ይቃምበታል ::
ይህንን ታሪክ ገበያ ክፍል ኬላው ጋር ቤት ተከራይተው ከሚኖሩ የቻኪሶ ልጆች በደንብ ተምሬዋለሁ ::
አንትዬ ከበደን ስለምወዳት የገበያ ክፍል እንጂ የሻኪሶ ልጅ አትመስለኝም አሁን ያለችበትን የሚያውቅ ቢነግረኝ ደስታዬ ወሰን የለውም ::
አንዱን ቀን ሻኪሶ ከአንትዬ ከበደ
ከጸጋዬ ግዛው
ሥንታየሁ ጎበና
መኮንን ገነነ
እሸቱ ጣፋ
መስፍን ሚደቅሳ ............ በነገራችን ላይ መስፍን ሚደቅሳ አሁን ከፍተኛ የመንግሥት ዲፕሎማት ሆኖ በውጪ ሀገር ይሠራል :: ወዘተርፈ ጥሩ የሆነ የማዕድን ምርት ስልት ተምሬያለሁ ይህንን ያነሳሁበት ምክንያት የወርቅ ጉዳይ ያስነሳው በመሆኑ ወደአንዲቷ እና ልዩ ገጠመኜ ልወሰዳችሁ ነው ::
በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት ገደማ ነው የደርግ መንግሥት ራሱን ይዞ ከመድረኩ ወርዶ ተራውን ለባለጋራዎቹ ለቋል ባለጋራዎቹ ደሞ ያኔ ጠመንጃ ከመተኮስ በስተቀር ምንም እውቀት አልነበራቸውም
በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አንድ ሰምተነው የማናውቀው ልዩ አትሞስፌር ነበር ............ የገንዘብ .............
አቅጣጫዎች ሁሉ መቀየር የጀመሩት ያኔ ነው
በአጋጣሚ ሶማሊያም የፈረሰችው ያኔ ስለነበር ቢሊሊቆ ክብረመንግሥትን መድረሻ አሳጥቷታል
ከሶማሊያ የሚጎርፈው መሳሪያ
የዝሆን ጥርስ ...
ቦካ
የነብር ቆዳ ...
ወርቅ
ታንታለም
የከበሩ ድንጋዮችና ሌሎች ማዕድናትን የጥቁሩ ገበያ ዋና ሸቀጦች ሆኑ
ክብረመንግሥት በየእለቱ አዳዲስ ሰዎችን ማየት የተለመደ ሆነ :
እየቆየም የተበተነው ሰራዊት የበዳኬሳን እና የዳዋን ሸለቆዎች ከተማው ማድረግ ጀመረ :
ክብረመንግሥት እለት ተእለት የኑሮው ሁኔታ እየተለወጠ መጣ :
ገበሬው እርሻውን አቁሞ ቁፋሮ ብቻ ተያይዟል
በገበያ እልህ የሚገዛ እንጂ የሚሸጥ አልታይ ማለት ጀመረ
በአንድ ቡና ቤት ውስጥ አስርና ከዛ በላይ ሴቶች ማስተናገድ ጀመሩ
የከተማው የውሀ ስርጭት ከፍተኛ እጥረት ገጠመው :
ጠጅ ከብር አራት በአንድ ግዜ በብር ሁለት ገባ
የእህል መገበያያ ስፍራ ገበያ መሆኑ ቀርቶ ወፍጮ ቤቶች መሆን ጀመሩ : የሸቀጥ መኪኖች ከተማውን አጣበቡት : በቀን ውስጥ ክብረመንግሥት የሚገባውና የሚወጣው መኪና ብዛት ታይቶ የማይታወቅ ሆነ ::
የአካባቢው ነጋዴዎች በቢሊሊቆ ግዠ ሰማይ ደረሱ ::
ይህንን በደንብ ያስተዋለው አደቆርሳ አንድ ዘመቻ ለመክተት ያሰበው ዘግይቶ ነው ::
በአንድ ሌሊትም ከውሳኔ ላይ ደረሰና በማግሥቱ ውጥኑን በግብር ለመተርጎም ለዘመቻ ከተተ ::

ይቀጥላል
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Oct 17, 2010 7:33 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
የአካባቢው ነጋዴዎች በቢሊሊቆ ግዠ ሰማይ ደረሱ ::
ይህንን በደንብ ያስተዋለው አደቆርሳ አንድ ዘመቻ ለመክተት ያሰበው ዘግይቶ ነው ::
በአንድ ሌሊትም ከውሳኔ ላይ ደረሰና በማግሥቱ ውጥኑን በግብር ለመተርጎም ለዘመቻ ከተተ ::

ይቀጥላል

በጉጉት አለቅን እኮ !? ኧረ ባክህ አደቆርሳ ቀጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥጥልልልልል !!!!!

_________________
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 18, 2010 4:21 pm    Post subject: Reply with quote

ኸረ ምንድነው ቤቱ ብርድ ብርድ ይላልሳ ?

ነበረ ሞራል ከየት ይምጣ !...... ድምጽ ነበር ዜማ ከየት ይምጣ ! አለ ክበበው ገዳ ውነቱንኮ ነው ::
ይሁንና ከክብረመንግሥት ዘምባባ ውሀ ዋደራ ሀረቀሎ ቢታታ እስከቦረና ያለውን ሁሉ አንድ ባንድ ላጫውታችሁ እና የቤቱ ሞራል ብቅ ብቅ ሲል ደሞ ወደመሰንበቻዬ ዞር ብዬ አምስት ወራት እንደከረጢት ብቅል የታጀለ ፖለቲካ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ እንዲሁም ማህበረሰብዓዊ አዳዲስ ጉዳዮችን ዓይኔ እንዳያቸውና ጆሮዬ እንደሰማቸው ላካፍላችሁ ዳር ዳር ብል ክብረመንግሥት ብሄድ ብመለስ አዋሳ ብቆይ አቋርጬው ወደ ኋላ ብገሰግስ ኸረ ... አዪዪዪዪይ የነበረኝ ፍላጎት በጥቂቱ መነቃቃቱን ቀንሷል ::
ለመሆኑ ራስብሩ ምንሆነህ ነው ? እርግጥ ነው ሁላችሁም አይመቻችሁ ይሆናል
ለምን አይመቻችሁም ብየ መጠየቅ ደግሞ ሞኝነት ይመስልብኛልና የአምላክ ፈቃዱ እስኪሆን መልካሙን ሁሉ እመኝላችኍለሁ

ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 18, 2010 8:13 pm    Post subject: Reply with quote

እንዴ
ምን ነካብኝ አደቆርሳን
ላንተ ብለን እኮ ነው ጣልቃ ላለመግባት ዝም ብለን የምትፅፈውን እየተጠባበቅን የተቀመጥነው
እንጂ ... የሚረባ የማይረባውን እንድናወራ ከግፈለክ እኮ .. እኔም የዶሮዋ ታሪክ አለኝ ... ይልቅ ቶሎ የተንጠለጠለውን ልባችንን አውርድ እና በአደብ እንድንጨዋወት አድርገን

ቢሊሊቆ መነገድ ጀመርክ .. ወይስ ... ምንድነው ያደረከው በዚያን ወቅት
እየጠበቅን እኮ ነው
ብለን አዋጅ ማወጅ አለብን እንዴ
ቀሽም ነገር ነህ ወላሂ
ጣልቃ ላለመግባት እና ላለመረበሸ እንጂ .... እግዚአብሄርን ... እኔም ብዙ የማወራውን ነገር እያስታወስከኝ ነው

ፕሊስ ቀጥል
አትጠብቀን ... እጃችንን እስክናጨበጭብ .... እየጠበቅንህ ነው ፕሊስ
ሞፍቲ ለምሳሌ እንቅልፍ የሚባል ነገር 4 ቀን በላይ አጠገቡ ደርሶ አያውቅም
እኔ መቸም ድንጋይ ስለሆንኩ እንጂ .... እንደሱ ሰው ብሆን .... ናፍቂት .. ትዝታ ..እና ... ፍቅር ...... ከሰውነት ተራ ያወጡኝ ነበር

እና አደቆርሳዬ
ፕሊስ ቀጥል
ቢሊሊቆ መኪና ገዛህ ወይ .... እንደ -ደርገባ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እየጠበቅን ነው .
ምጣና -ውጣ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Oct 18, 2010 9:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ባለሱቅ =በሳቅ ገደልከኝ ..........እውነትህን ነው ኮምፒውተሬን በቀን ስንት ግዜ መሰልህ የምከፍተው ::ጭራሽ ዛሬ የአደቆርሳን
ስም አይቼ ደስ ብሎኝ ስከፍት ኩምሽሽ ነበር ያረገኝ :;እንዳልከው ሁላችንም የአደቆርሳ ጭውውት
ጥሞን አጥብቀን እየጠበቅን እንጂ ትርኪ ምርኪውንማ እኔም ልጽፍለት
እችል ነበር ::ለዛውም ደግሞ ለአደቆርሳ ምስክር ሊሆን የሚችልለት ነገር እሱ ፖስት ባደረገ
በሀያአራት ሰአት ውስጥ 700 በላይ ሰው እንዳነበበው መረዳት ቢችል የሁሉም አይን እሱ ላይ እንዳፈጠጠ ይረዳ ነበር ::
ፕሊስ አደቆርሳ በጉጉት እየጠበቅንህ ስለሆነ ተሸክመህ የመጣኧውን ሞራልና ብርታት ሳትቀንስ ያለውን ሁሉ ዘርግፍልንንንንንንን

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 19, 2010 12:35 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:

ብለን አዋጅ ማወጅ አለብን እንዴ
ቀሽም ነገር ነህ ወላሂ

አንተ ቦርጫም ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ይመችህ አቦ

እነ አክሊለ በርሄ ሱቅ ይሸጥ የነበረ ልጅ ታስታውሳላችሁ ከአስካለ በፊት አንድ ቀይ ፈረንጅ የመሰለ ቀጭን ግን ንቁ ልጅ ነበር ስሙ አንዶም ነው የሚባለው ::
ነገሩን ከጥግ ለመጀመር ስለተመቸኝ ነው እሱን ያነሳሁት

ክብረመንግሥት በሄድኩ በሳምንት ውስጥ ሀሳቤ ሁሉ ተለዋወጠ ግራም ተጋባሁ በአለም ላይ ባለው ተለምዶ የመንግሥት M ሽር በተለይም coup de' tat በተካሄደባቸው ሀገራት ሁሉ አስገራሚ የሰው ልጆች የህይወት ለውጥ እንደሚታይ በመጻህፍትም በታሪክም በራዲዮም በወሬም እንሰማለን ሰዉ ያቺን ጊዜ እንደ እድል ሲመለከት አደቆርሳ ለምን ይተኛል ብዬ ለራሴ የክተት ዘመቻ አስታጠቅኩ ::
ሉቲንግ ይሉታል ነጮቹ እኛ ደሞ ምርጥ አጋጣሚ ልንለው ነው ማለት ነው
ዶሎ ኢትዮጵያ : ዶሎ ባዬ : ዶሎ ኦዶ : ሞያሌ ኢትዮጵያ : ሞያሌ ኬንያ : ወዘተ በውሀ ጥምና በመከራ የምናውቃቸው ቦታዎች ሁሉ ዛሬ የቢራ መጨለጫ ቦታዎች ሆነዋል :
ኦጎባ :ማንዴራ : ቦቆልማዬ :ዋጭሌ : ወዘተ የሚባሉትንም ቢያንስ ለማየት ጉጉቱ ከመጠን በላይ ሆነ በደርግ ፈንጂ የደነገጠ ግን ተርፎ የተመለሰ /የተበተነ /ማዶ ዳገቱ ላይ የሚኖር ወዳጄን ቀሰቀስኩና ያለቺንን ይዘን ወደበረሀው ልንወርድ ማታውን ዳዲ ስንቀዳ ስንማማል አድረን በማግስቱ በጠዋት ወደ አራዳ ወጣን ::
የደርቤን በረንዳ እና ቡና ማለፍ የማይችለው ወዳጄ ቅልጥሙን ሳብ ሳብ ሲያደርግ ተከተልኩታ ... እኔም ከበረንዳው ጫፍ ቁጭ እንዳልኩ ወደ ባላምባራስ ዓለም ዓየሁ ሆቴል በራፍ ዓይኔን ወርወር ሳደርግ ቀጠሯችንን አክብሮ የተገኘ ቱጃር ብቻውን ቁጭ ብሎ አየሁትና ጊዜ ሳላባክን ወደእሱ አመራሁ ቀረብ ብዬ ሰላምታዬን ሳቀርብ በደስታና በፈገግታ የቀለጠ ፊቱ ሲበራ እኔም አብሬ በራሁ ::
ሞቅ ባለ ሰላምታ ተገናኘን
ከተያየን ቆየን አዋሳን ተውከው እንዴ ? አዋሳን ልተዋትስ እችላለሁ ብለህ ነው ? ቢሆንም የተወለድኩትባትን እና ያደኩባትንት አዶላን እወዳታለሁ ::
እንደገና ፊቱ ሲበራ አየሁት ደስታው አስደሰተኝና እኔም ለግብዣ ተሰናዳሁ : ምናልባት እሱን ብጋብዝ መንገዳችን ማጠሯ አይቀሬ ነበር ::
ግን በል ባክህ ጥሩ ዱለት የምንበላበት ውሰደኝና ቁርስ እናድርግ ብቻዬን ደብሮኝ ነበር ሲለኝ
እንግዲያው አንድ ወዳጄ አለ .............
ጥብስ አስጠብሰን ቁጭ ብለን እየቀረጠፍን ሳለ
አንድ ትንሽ ስራ አለቺኝ እሷን እርዱኝ የሚገባችሁን እከፍላለሁ
ኸረ ምን ገዶን ምን ልንረዳህ እንችላለን ?
ስለ መብረቅ ብረት
ወርቅና ልዩ ልዩ ማዕድናት
ሜርኩሪ ቢሊሊቆ ወዘተ በደንብ አስረዳን
አንዱን ልንገራችሁ ::
<<በዚህ በገናሌ በኩል መብረቅ በተደጋጋሚ ይወርዳል መብረቅ የሚያርፍበት ቦታ ጎድጓዳ ይሆናል ያንን ስፍራ በመቆፈር ጥቅልል ብረት ይገኛል ከተገኘ ህይወታችሁን የሚቀይር ገንዘብ ታገኛላችሁ >> ነገሩ ባጭሩ ይህ ነው አሰብ አደረኩና
እስቲ እንደገና አስረዳን ብረት ምንድነው ለምን ይጠቅማል ? አልኩት
እሱ የሰጠኝ መልስ በአሁን አእምሮ ያስቃል ይህንን እና
የዚህን ጥያቄ መልስ ከዚህ በፊት ይህንን በተመለከተ በጻፍነው አስተያየት ላይ በዝርዝር መክተቤን አልዘነጋም ::
ስለ ሜርኩሪ ሲነሳም እንዲሁ በጣም የተለየና የሚያስቅ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሲሯሯጡ ማየት ምናልባት እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ሰከን ያላለ ጉዳይ ነበር :
ሜርኩሪ በፋብሪካ የተቀመመና የተዘጋጀ እንጂ በቀጥታ ከመሬት የሚወጣ ማዕድን መሆኑን እንኳ የማያውቁ ሜርኩሪ ለመነገድ የሚፈልጉ ባለገንዘቢች ቁጥር ቀላል አይደለም ::
አንድ የምታስታውሱትን ነገር ልድገመው በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት መገባደጃ ግድም ነው የለገደምቢ ወርቅ ልማት ድርጅት ሰራተኛ የሆነ አንድ ሰው /ስሙን መጥቀስ አያስፈልግም ብዙዎቻችሁም ታውቁታላችሁ / ከክሬሸር የሚወጣ አሸዋ ወርቁና አፈሩ ታጥቦ ወደ ፋርነስ ከመግባቱ በፊት ሜርኩሪ ይጨመርበታል ከዛም ከፍተኛ እቶን /ፋርነስ / ውስጥ ይጨመራል በእቶኑ ኃይል ሜርኩሪው ሲተን አፈሩም ሲጠፋ ወርቁ ብቻ ቀልጦ ይቀራል ያንን አቀዝቅዞ ስምና ምልክት ይታትምበትና ወደ ስቶር ይወሰዳል ይህ የመጨረሻው ደረጃ ነው ::
ሰውዬው ሜርኩሪው እንደተጨመረ ነገር ግን ወደ ፈርነስ ያልገባ ሰርቆ ያወጣና ካንድ ወዳጁ ቤት ወስዶ ወርቁን ከሜርኩሪ ለመለየት በአይረን ሳህን ሙከራ በሚያደርግበት ወቅት የተነነው ንጥረ ነገር የቤቱን አየር ስለበከለው የወዳጁ ሁለት ህጻናት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል ::
በሰራው ስህተት ክፉኛ የተጸጸተው ባለሞያ ለምርመራ በተወሰደም ግዜ መርቼ ላሳያችሁ ብሎ አዋጣ ወንዝ ዳር ወስዷቸው ሳለ ራሱን ማጥፋት አስቦ ኖሮ በድንገት ውሀ ውስጥ ዘሎ ሲገባ መርማሪው ጠንቃቃ ነበርና ተከትሎ ዘሎ በመግባት ከግለ ጥፋት አድኖት ምርመራው ከግብ ሊደርስ ችሏል ::
እንግዲህ ይህንን የመሰለ ክፉ ዜና የምንሰማበት ጉዳይ ለንግድ ውሎ የሚያመጣው ፋይዳ ምንም አልታይህ ብሎኝ የመብረቅ ብረቱም ኬሚካሉንም ትቼ ወደ ቢሊሊቆዬ ዘመቻዬን አጠናከርኩ ::
አሁንም ድንገተኛው የሀብት መጥለቅለቅ በተለያዩ ጓደኞቻችን እና የተለያዩ ሰዎች ዘንድ እየታየ ነው
ከዚህ አኵያ ደሞ ቆፍረው እና አምርተው ለመንግሥት በመሸጥ ራሳቸውን እየለወጡ ያሉ ወጣቶች ቁጥራቸው የትየለሌ ሆነ ::
ቻርሊ ...........ፍሪኪ .......... የሚባሉ አምራች ቡድኖች ታዋቂ እየሆኑ መጡ :
ከሁሉም በላይ የሚያስደንቀኝ ወያኔ ገና ሀገሩን እንኳ አረጋግታ ሳትይዝ ጫካ ውስጥ ቁጭ ብላ ከራሱ ከኢትዮጵያዊው ዜጋ ህገ ወጥ የወርቅ ምርት በገፍ በመግዛት ብቸኛ መሆኗ ነው ::
ሊቆፍር የመጣ መሳሪያ ቢኖረውም ወንጀል እስካልሰራበት ድረስ መብቱ ነው ይባላል ከተም ውስጥ ግን እንኳንስ መሳሪያ ዱላም በቅጡ መያዝ አይቻልም ::
ብቻ ጫካ ውስጥ መብት እንደልብ ነው ::
ህዝብ ይቆፍራል ወያኔ ይገዛል ::
ወዲያው ከለገደምቢ ምድበ ዋርዲያ በአንድ ባልዲ 80 ኪሎግራም ወርቅ ይዘው የተሰወሩ የወያኔ አባላት የከፍተኛ ወንጀል ዜና በተሰማ በአንድ ሌሊት ኬንያ ድንበር ላይ መያዛቸው ብዙ ነገሮችን ለአትኩሮት ከመጋበዙም ባሻገር ጥርጣሬን እና ጥንቃቄን ተክቷል ::
ሆኖም አንቀላፍቶ የነበረው የአካባቢው እንቅስቃሴ ከምንግዜውም በላይ እየገነነ መሄዱን አላገደውም ::

ዶሎ ኦዶ በዋሮ ሸራ የተወጠሩ ቤቶች በየበራቸው አሸዋ ውስጥ በተቀበሩ የቢራ ጠርሙሶች ቁልል ቁልል ያሉ ጉልቶች እንደሚታዩባቸው : አንድ ተጋጥሞ በተሰፋ ጆንያ 8 ሳጥን ቢራ ቅርቅብ አድርጎ የሚጭን ነጋዴ :
ዶሎ የቢራ ዋጋ እንደፈለገ ነው እዚህጋ 10 ብር ከጠጣህ ትንሽ አለፍ ብለህ 20 ሊሆን ይችላል ነገ ጠዋት ደሞ 8 ብር ይሆናል : ሲል ያጫወተኝን ለማየት ጉጉቴ ፋታ አጣ ::
መኪና በየአይነቱ ከሶማሊያ ይገባል እያንዳንዱ መኪና የማይጭነው አይነት ማሽን የጦር መሳሪያ የመኪና ሞተሮች የውሀ መሳቢያ የእንጨት መሰንጠቂያ ማሽን በኤሌክትሪክ የሚሰራ የዳቦ መጋገሪያ ኸረ ምኑ ዝም ብሎ ይጎርፋል ሁሉም ነጌሌ ቢተከሉ ራሷን የቻለች የኢንዱስትሪ ከተማ ይወጣት ነበር ::
ከነጌሌ ሻሸመኔ ድረስ ለመጫን ተነጋግረን የተዋዋልን መኪና ሌሊቱን ሀሳቡን ቀይሮ አንድ ሺህ ብር ጨምሮ ያድራል ::
በዚህ ላይ አቤት ጭካኔና ግድያ እንደሶማሊያ ያለ ጨካኝ አይቼ አላውቅም ነጌሌ ቦረና ሳለሁ የአንድ መኪና ሽያጭ ለሁለታችን አይጠቅምም ብሎ ወንድሙን የሚያጠፋ ሶማሊያዊ አይቻለሁ ::
በሚያደርሱት ወንጀል እነሱን መዳኘት አስቸጋሪም ስለነበር ህግም ብዙ አያያቸውም ወያኔም ገና ለራሷ እየተሯሯጠች ነው ምኑንም ልትጨብጠው አልቻለችም ::
ቢሆንም በአካባቢ መስተዳድሮች ሰው በህግ ጥላ ስር ሆኖ ያድር ነበር ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያሰኛትም አንዱና ትልቁ መገለጫችን ይህው ነው ::
ወያኔ አንፈራራን የተሻገረው በሰኔ አንድ ቀን መሆኑን ልብ ይሏል ::
እንግዳዬ ከሰጠን አሳይመንቶች ውስጥ የተመቸኝን ያገኘሁት ከነጌሌ ናዝሬት ድረስ ሶማሊያዊያንን ማድረስ ሲሆን ከእያንዳንዳቸው አምስት አምስት ሺህ ብር ክፍያ መቀበል አመቺው ነበር ያለበለዚያ ብቻዬን የምቀር ነው የመሰለኝ ::

መኪናው እንደጉድ ይንገጫገጫል ወፍራሟ ሶማሊያዊት አንድም ቃል አትተነፍስም ጸጥጥጥጥ ውሀ አይጠማት አይርባት ሰው ሲስቅ አትስቅ አትናገር አትጋገር ወይ አይደክማት ምንም ምንም ጭጭ ምጭጭ ነች : ቢተኮስም አትደነግጥም ::
እንዴ ይቺ ሴት ምንድናት እያልኩ ብቻ ቀልቤን ሳብ አድርጋዋለች ከመንገዱ አሰልቺነት ጋር ወፍራሙ ታፋዋ ጎኔን ተጭኖት አድክሞኛል ብነግራትም አትሰማኝም እንደምንም ቀስ ብዬ ገፍቻት ብድግ አልኩና ከውስጧ ወጥቼ ቆም አልኩ ::
የተቀባችው ሽቶ እስከዛሬም እንደዚያ ያለ ጥሩ መዓዛ አላውቅም ::
ሲያዩዋት ወርቅ የምትመስለው ላንድክሩዘሩ በዝላይ ሰማይና ምድሩን ልታገናኘው ምንም አልቀራት :
ትንሽ ቆይቼ ግን አድክሞኝ የነበረ ታፋ እንዴት ይገኝ ?
አይ ታፋ
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 19, 2010 12:47 pm    Post subject: Reply with quote

የሰው ኮንትሮባንድ አለ ቢሏችሁ ሰምቶ ለማያውቅ ሰው ግርምምም ማለቱ አይቀሬ ነው ::
ታዲያላችሁ ኮንትሮባንዳችንን ግጥም አድርገን ጭነን ስንገሰግስ የመጀመሪያው አስቸጋሪ ኬላ የገጠመን አፖስቶ ላይ ነው : እነዚህ ኢትዮጵያውያን ናቸው አይደሉም ንትርክ ያዝን በአጋጣሚ ጠባቂዎቹ የኦፒዲኦ እና የወያኔ አባላት ስለነበሩ ጉቦ መስጠትም አይቻልም በዚህ ላይ የቦረና ሰዎች ኦሮምኛ መቻል ነበረባቸው ቢሆንም እዛ አካባቢ የሚነገረው ሶማሊ ብቻ ነው ብለን ድርቅ አልን : መታወቂያ ምናምን ብለው በመጨረሻ የተሰጠን ውሳኔ ምን እንደነበረ ታውቃላችሁ ?
አይቻልም ተመለሱ !
እሺ ብለን ተመለስንና አለፍ ብለን ሰዎቹን በእግራቸው ከፊት ከፊት እየመራናቸው ተመልሰን ለማለፍ ምንም ያህል አልተቸገርንም ::
በዚሁ አይነት ሻሸመኔንም ሌላውንም እያለፍን ኮንትሮባንዳችንን በተፈለገው ስፍራ አደረስን ::
ያቺ ሰዓት ነች እንግዲህ የማትረሳኝ
ዝምተኛዋ እና የማትነቃነቀው ሴት ተናገረች ::
ካም ፕሊስ ?
ጠጋ አልኳት ያንን ደስ የሚል የሽቶ መአዛ እንደገና ማግ አደረኩት በአርባዎቹ መካከል ያለች ጎልማሳ ሴት
አንድ ወረቀት አወጣችና እያሳየቺኝ ፕሊስ ቴክ ዚስ አድሬስ : አነጋገሯ የተማረች ስለመሆኗ አያጠራጥርም ::
ናዝሬትን አላውቀውም ቢሆንም ለማለት አልቻልኩም
ከመኪናው ሌሎቹን ሁሉ አወረድንና እሷን ይዘን አድራሻውን ፍለጋ ቀጠልን :
የተባለው ቤት ቀበሌውና ቁጥሩ የተጻፈበት ትክክል ሆኖ ነገር ግን ቦታው ሌላ የሰው ቤት ሆኖ ተገኘ :
ብንጠይቅ ምንም ነገር የለም ሴትየዋን ለማን እንተዋት ወደከተማ መልሰን በይ ውረጂ እኛ ስራ አለብን !
እጄን ለቀም አድርጋ ወፈር ያለ ነገር ስታስይዘኝ ገንዘብ
መሆኑን አልተጠራጠርኩም ::
አጋጣሚ ፈለኩና ፈታ አድርጌ ሳየው ማመን አቃተኝ ሾፌሩን በቃ አንተ ሂድ ልበለው ? ከዚ በላይ ብር ኬት ላገኝ እችላለሁ ? ......... በቃ ሀብታም ሆንኩ ማለት ነው : አዞረኝ የምሆነውን ነገር አሳጣኝ እንኳንስ ባለመቶ ባለመቶ የአሜሪካ ዶላር ቀርቶ ብርስ ቢሆን ባለመቶ እኔ ይዤ አላውቅ :
አይ በቃ እኔ አልመለስም እዚሁ ነጋዴ ሆናለሁ ይቺንም ሴት ጥያቄዋን መፈጸም አለብኝ እያልኩ በቃ በሀሳብ ውጣ ውረድ በድንጋጤ ቀለጥኩ ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Nov 01, 2010 1:11 am    Post subject: Reply with quote

ድሮ ድሮ ክብረመንግሥት መብራት ሊጠፋ ሲል አንድ ሁለቴ ብልጭ ድርግም ብሎ እንጂ እንደ አዲስ አበባ እልም ብሎ አይቀርም ነበር : ዋርካም እንደክብረመንግሥት መብራት ምልክቷን ካሳየችን ቆየት ብላለችና ሰዎች አንድ መላ በሉ ::
አያቴ እንደወጣ የሚቀር የሰው ስጋ ብቻ ነው የሚለው ነገር ነበረው ውነቱን ነው ቁራ እንኳን ዘገየ እንጂ ተመልሶ መጥቷል
ስራ ፈቷ ቴሌፎኔ ኪሴ ውስጥ ስትንደፋደፍ ወጣ አደረኩና ሀሎ ስላት
ያለ ምንም ሰላምታ በል እንኳን ደስ አለህ ቤታችሁ ተከፍቶአል ስባል ከታች እስከላይ ነው የሳቅኩት :: እግረ መንገዴን ባለፈው ሳምንት ያደረኩት ትዝ አለኝና ሳቅ አልኩ የንዴት አይሉት የጥበብ ሳቅ
የተጠቀምኩበት ኮምፒውተር ደጋግሜ ብሞክረውም ዋርካን አልከፍት ሲለኝ ድሮስ የወያኔ ኮምፒውተር ምን ይረባልና ነው ያለ ፖለቲካ ኑሮ አታውቁ ብዬ ሰዎቹን ተናግሬያቸው መለየቴ ራሴን እስወቅሶኛል ሆኖም ሰዎቹ በዚህ አባባል ቅር የሚላቸው አይደሉም ቢሆንም ምግባሬ ትክክል ልነበረም :: አላዋቂነቴ እነሱ የዘጉት መሰለኝ እንጂ የዋርካን ልማድ መርሳት ስንፍና ነው ::
ለሁሉም ችግራቸውን ስለማላውቅ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ::
ግን በውነት ነው የምላችሁ በብዙ መልኩ ልጅ ተድላ ኃይሉን : ወረኢሉን : ደጉን : ክቡርነታቸው ሾተልን : ንጉሥ ጦናን : ፈላስፋውን ቆቅ : ዲጎኔን : በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሥጥ እንግዲህን : የፎካልጅን : ክቡራንን ወዘተ ሳንመረቅ እንደተለያየን የአንድ ትምህርት ቤት ልጆች እንደናፈቁኝ ሳልናገር መቅረት አልፈልግም :: መለያየታችን አሳዝኖኝ ነበር ::

አንዴ ፈቱሼ ሀሰንን አዲስ አበባ አግኝቼው ኖሮ
( በነገራችን ላይ ፈቱሼን በኳስ ጨዋታ ችሎታው ነው መሰለኝ አንቺ እንደሚሏት ትዝ ይለኛል እኔ ከታላቅነቱም አንጻር አንቺ ማለት አሳፍሮኝ አንተ እያልኩ አናግረው እንደነበር አስታውሳለሁ )
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደርግ ወደ መንበሩ ከመጣ በኍላ ቦይንጎቹን ወታደርና ክላሽ ማመላለሻ አድርጎአቸው መስሪያ ቤቱ ሊዘጋ ጥቂት እርምጃ ብቻ ስለቀረው መንግሥቱ ኃይለማሪያም የመጀመሪያውን የኤኮኖሚ ምክር ተቀብሎ ካፒቴን መሀመድን ከአሜሪካ አስመጥተው እንደገና ሲያዋቅሩት በርካታ የሞያው ባለቤቶች ከስራቸው ሊፈናቀሉ ተገደው እንደነበር ያጫወተኝን በደንብ አስታውሳለሁ ::
አቶ መለስ ደሞ ወያኔን እስከደገፈ ድረስ ማንም ሰው በኤኮኖሚ ላይ ስልጣን ያለው እስኪመስል ድረስ የሀገራችን የእድገት እርምጃ ሸፋፋ እንዲሆን አግዞታል ::
ይህንን ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም
በቀላሉ ኢንተርኔትና ቴሌፎን ሰፊ በሆነ ሁኔታ አገልግሎት ላይ ቢውሉ ሀገሪቱ ዘርፈብዙ እድገት ደረጃ እንደምታሳይ ጥርጥር የለውም ይህ የሚሆነው ደሞ ድርጅቶቹን ለሌሎች ካምፓኒዎች በመስጠት ሰፋፊ ስራዎችን በመስራት አልያም የራሳቸውን ጉልበት አሳድገው ፈጣን አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ ማድረግ ነው ::
በአቶ መለስ አመለካከት ግን ይህ ሌላ መልክ አለው
ለሌሎች ካምፓኒዎች ቢሰጥ አሁን መቶ በመቶ 35 ሚሊዮን በላይ የቴሌፎን ሰርቪስ ተቴቃሚዎች በቀጥታ የሚገኘው ገቢ ይጎድልባቸዋል ማለት ነው :
ይሄ የመንግሥት አመለካከት በጣም ይገርመኛል እድገት ሊኖረው የሚገባው ህዝብ ወይንስ መንግሥት ?
በርካታ አዋቂ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶችና መስሪያቤቶች በኢንተርኔት አገልግሎትን እየሰጡ መጠቀም እንዳይችሉ ታግደዋል : በዚህ ዘርፍ ሀገሪቱ ልትደርስ የችለችበት ቦታ ላይ ልትደርስ አልቻለችም ግን እኔ ብለፈልፍ ምን አመጣለሁ እግዚአብሄር አንድ ነገር ያምጣልን እንጂ ::
ብቻ እንዲህ በአለም ዙሪያ ያለውን በርካታ ኢትዮጵያዊ አንዲት ዌብ ሳይት ልታቆራርጠውና ልታለያየው ደስሲላት እየመጣች ሲከፋት እየሄደች ማንቆራጠጥ መቻሏ ለምንድን ነው ብዬ ራሴን ስጠይቅ መልስ ሆኖ ያገኘሁት የሀገራችን ማነቆ አናዶኝ ነው ::
ለማንኛውም በድጋሚ ለዋርካ ባለቤቶች ቺርስ ብያለሁ !

ባለፈው ወደጀመርኩት ወሬ ልመለስ አሁንም እንደልማዷ ወሬዬን ሳልጨርስ እልም እንዳትል !

ያንን ቱባ ብር ይዤ ስንት እንደሆነ የምቆጥርበት ግዜ ናፈቀኝ ሴትየዋን እንደምንም ቶሎ አንድ ነገር አድርጌ ማሳረፍ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ ::
ወደ ድረደዋ መውጫ መስመር ላይ ድሬደዋ ሆቴል የሚባል ነበረ ቀለሙ እንኳን አረንጓዴ ነው አይረሳኝም እዛ ወሰድኳትና በራሴ ስም አልጋ አስይዤ እኔ ወደ ላንድ ክሩዘራችን ገብቼ ወደከተማው ለመዝናናት ገባን እንደምንም ጊዜ አግኝቼ ገንዘቤን ስቆጥረው በጣም ተደሰትኩ ስንዝናና ሳለን << ፕሊሰ ዶንት ሌት አሎን >> የሚለው አባባሏ እያሳዘነቺኝ ይሁን ደስ እያለቺኝ ብቻ ቢራ መጨመርኩ ቁጥር አባባሏም እየጨመረብኝ መጣና ሞቅ ሲለኝ ቀጥብዬ ሄድኩ ::
መቼም እንደዚህ ያለች ዲሲፕሊንድ የሆነች አዋቂ የመናገር ችሎታዋ የላቀ የሴት ጎበዝ እስከዚያን ግዜ እድሜዬ ድረስ አጋጥሞኝ አያውቅም ነበር በአንድ የሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ መምህር የነበረች ስትሆን ባለቤቷም የክምና ዶክተር /ለግዜው የት እንዳለ አታውቅም / እና የአራት ዓመት ወንድ ልጅ እናት መሆኗን በሀዘን አጫወተቺኝ ::
በጣም አዘንኩ በመቀጠልም ቀጣይ መገዷን ወደ አውሮፓ እንደምታደርግና ነገርግን ከወዲሁ ልጇንና ባለቤቷን ለማግኘት ወደ አውሮፓ ለመደወል አንዳንድ ነገሮችንም እንድረዳት ጠየቀቺኝ
መልካም ነገር ግን እኔ ምን ልረዳሽ እችላለሁ ?
መጀመሪያ ጣሊያን ኤምባሲ አድርሰኝ
ጣሊያን ኤምባሲ ያለው አዲስ አበባ ነው
እዚህ የማን ኤምባሲ አለ ?
እዚህ ኤምባሲ የለም ይህ ሁለተኛ ከተማ ነው :
እባክህ ነገ አዲስ አበባ አድርሰኝ ከዛም ኤምባሲውን አገናኘኝ ወጪህን በሙሉ እከፍላለሁ ውለታህንም እመልሳለሁ ::
ሁኔታዋ አንጀቴን በላኝ በጣም ስላሳዘነቺኝ ብዙም ሳላንገራግር እሺ አልኳትና በማግሥቱ ጠዋት ይዥት ልሄድ ነግሬያት ወደ ክሩዘራችን ተመለስኩ ::
ክሩዘራችን ሊስማማ ስላልፈለገ እሱ ወደ አዶላ ሲመለስ እኔ እሷን ልብሷን አስቀይሬ ነጠላ አልብሼ እኔም ልብሴን ለውጬ ባርኔጣዬን ለጠፍ አድርጌ አቃቂ ድልድዩ ላይ ወርደን በእግራችን አቋርጠን የፈለግንበት ቦታ ደረስን ::
ለነገሩ አዲስ አበባ ከገቡ በኍላ ያለምንም ችግር ቤት መከራየት ሆቴል የማረፍ ሁሉንም ነገር የማድረግ መብት ነበራቸው
ከድንበር ሲገቡ ግን ለምን እንደሚከለከሉ ሊገባኝ አልቻለም ነበር ምክንያቱም አዲስ አበባ ውስጥ እንዳሻቸው ነው የሚኖሩት ::
በማግሥቱ የኤምባሲዋን የፍለጋ ውጤት አጠናቃ ያለሁበትን ስልክ ሰጥቻት ስለነበር ደውላ አገኘቺኝ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው ይህንን ሁሉ ታሪክ ያጫወትኳችሁ ያቺን የደስታ ቀኗን መርሳት ስለማልችል ብቻ ነው ::
ብዙዉን የምትናገረው በሶማሊኛ ነው ልጄም ባሌም ደህና ናቸው ጣልያን ገብተዋል ! ፈጣሪዋን ደጋግማ ደጋግማ ታመሰግናለች ከቆይታ በኍላ ስንገናኝ ማይ ጋድ ሰው እንዲህ ሲሆን አይቼ አላውቅም ፍራቷ ሁሉ ጠፍቷል አሁን ብትታሰርም ምንም ብትሆንም ግድ የላትም ::
Jኤን ይዛ ትስመኛለች በምራቋ ታሸኛለች የምትናገረውን አልሰማትም ትለፈልፋለች ደስታዋ እኔንም ከመጠን በላይ አስደሰተኝ ::
ተለይቻት ልሄድ ስል አትሄድም ነገ በባንክ ብር ይላክልኛል ገንዘቡም ባንተ ስም ይመጣል የሚገባህን ሳልሰጥህ አትሄድም ::
ልቤ ቢያመነታም እሺ አልኩና አንድ ቀን ጨምሬ የአምስት መቶ ዶላር ሀብታም ሆኜ ወደ ክብረመንግሥት ተመለስኩ ::

ከአዲስ አበባ ወደ አዶላ ስመለስ ደብረዘይት ሞጆ ዝዋይ መቂ ሻሸመኔ አዋሳ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት ከአንድ ወር እያልኩ በዚያን ግዜ የነበረውን ሁሉ ጠባሳው ያልደረቀ ግን እንዳለፈ ታሪክ እያስተዋልኩ አፖስቶን አልፌ የወንዶን ፒስታ እስከ ዋራ ድረስ ምንም ሳልቀምስና ሳላወራ ነበር የደረስኩት ::
ያንን ከአንድ ዓመት በፊት እያልኩ እያስታወስኩ የነበረውን ታሪክ ሳጫውታችሁ ባለሱቅ (እኔ ልንከራተትልህ ) ያለኝን እስክሞት አልረሳውም ::
ምክንያቱም ታሪኩን ማንም አያውቀውም ቢያውቀውም የኔ ስቃይ ሊገባው አይችልም ብዬ አስብ ስለነበረ አሁን ድረስ ራሴ በራሴ ያሳዝነኛል ::
የእስከዛሬው ህይወቴም ውጣውረድና ትግል የበዛበት መሆኑ ግርም ይለኛል
ፍዝዝ ያደርገኛል ያሰብኩት እንደሆን
ሠው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ሲሆን ..... አለ ............. ይርጋ ዱባለ ውነቱን ነው ::

እናንተዬ ስሙ ጠፋኝ የእጅጋየሁ ታምሩ ወንድም ? በኢፒለፕሲይ ይቸገር የነበረ ወይኔ ሰውየው አረጀሁ ማለት ነው ወዳጄኮ ነው እሱ ነጭ ቁጦ ጀባ ሲለኝ ነው የነቃሁት ያለምንም ጫት ያንን ሁሉ መንገድ በሀሳብ ያቺ ሶማሊያዊት እና የኔ ህይወት ሳስባቸው ማረፊያ ሳላገኝላቸው ቁጦ መቃም ጀመርኩ ::
ድሮ መኢሴማ ይሁን ሰበነክ የሚባል ነገር ተቍቁሞ ነበር በዛ ማህበር ውስጥ ያባላምባራስ ዓለማየሁ ቤት ይሁን የባላምባራስ መኮንን ባሬስታ የነበረ ጸጋዬ የሚባል ቀይ ሰውዬ ነበር (አዶላ 5 እርግጠኛ ነኝ ይህንን ቤት ያነባል አያነብም እርግጠኛ አይደለሁም እንጂ ወዲያው ነው የሚያውቀው ) እንደውም በኍላ ጥሩ የመድረክ ሰው ወጥቶት ቲያትር በመጫወት ልዩ ክህሎት እንደነበረው አስመስክሮም ነበር እሱን ቦሬ ላይ ቸስቶ አገኘሁትና ምሳውን በክትፎና በገተሜ በሳቅ በሳቅ አድርጌው በቀደዳ / ደረስን እሱን ያነሳሁት እንዲሁ የሱንም ህይወት ሲያጫውተኝ ስለደረስን የሰውን ልጆት አስገራሚ ህይወት እንድማርበት ያደረገኝ በመሆኑ ስላልረሳሁት ነው ::
በዚህ ዓይነት / ገባሁ
እንግዲህ የዚያን ጊዜው ደሞ ዘመነ ቢሊሊቆ ልዩ አጋጣሚ ነው ያልኩት ይሄው ነበር :

የተለያየንባትን አምስት ወራት ደሞ ነካ ነካ እስከማደርግ
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 314, 315, 316 ... 381, 382, 383  Next
Page 315 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia