WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የሚገርሙኝ አንዳንድ ነገሮች ...
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue Mar 01, 2011 4:49 pm    Post subject: Reply with quote

ክቡ የተጻፈው ምን እንደሆነ እኮ ገብቶሀል :: እሺ ስድ ንባብ ነው የተጻፈው :: ማን በሎሬቶች ስፈርልኝ አለህ ? Laughing

መልዕክቱ ግን ሳይገባህ እንዳልቀረ እገምታለሁ :: ይሔን ያህልማ ደደብ አትሆንም መቸስ Wink ባባዊርቱ ዘሀር ስትቆምር አይቼህ እኮ ነው Laughing ያንተ ዘሀር ለዝርዝሩ - የተንጠለጠለው ሆድህ ይዘርዘር እና - እዚህ ተጫኑ ነው :: Cool

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
በለው ..በለው ...ምንድነው ይሄ ናፒ .. Very Happy ግጥም ነው ..ወይስ ግጥም - = ግም ነው ? Very Happy እንዴት ግጥም ይጻፍል ...ብለህ ብትጠይቀኝ እኮ አስተምርሀለሁ :: የጸጋየን ቤት የከበደ ሚካኤልን ቤት ...የኔን የክቡራን ቤት ኔም ኢት .. Wink ይሄ ሚሚንም ይጨምራል ቡዙ አላስከፍላትም ...የወዳጅ ዋጋ ነው የምጠይቃት ...ሰው ያለውን እኮ ነው ክፈል የሚባለው እንጂ የሌለውን እኮ አምጣ አይባልም .... Very Happy እስኪ እየተጫወታችሁ .. ይሄን ጉድ አልሰማችሁም ..?

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ምነው ... ሚሚቱ

ምነው ቆቂቱ

ክቡ በአባዊርቱ ...

ዘሀር እንዲህ መጫወቱ :: Laughing

በፍቅር ማሸነፍ ነው ክቡ ?

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ሚሚ ወይም ማሞ ( ምርጫው ያንቺ ነው ) አሁንም ለምን ግልጽ በሆነ ቆንቌ እንደማትጸፊ ሊገባኝ አልቻለም :: አማረ አረጋዊ ስለ ሀይሌ የጻፈውን ካንቺ ማየቴ ነው ... አማረ ሀይሌን በተመለከተ ስላለው ጉዳይ ወይም ስለጻፈው ሀቲት ራሱን አማረን ይመለከታል :: ከኔ ጋር የሚያገናኝው ጉዳይ የለም ..ሊኖርም አይችልም :: እኔ ሀይሌ የኢትዮጵያ ባለውለታ እንደሆነ ጠንቅቄ የማውቀውን ያህል አንዳንዴ የሀይሌ ነገሮች ደሞ በግሌ ያስደሙምኛል ..ከመንግስት ጋር ካለበት ሰጣ ገባ ( በነገራችን ላይ ሀይሌ ከመንግስት ጋር ምን አይነት ችግር አለበት ..?? ) ወይም ከአማረ ጋር ካለው እንኪያ ሰላምታ የኔን እይታ አታይዥዥው :: "ጋስፕ " የሆነ ነገር "ቫሊድ " የሆነ እውነት ነው ብሎ የሚከራከር ሰው ያናድድኛል ...:: ትግስትም የለኝም :: እኔ ይልቁኑ መሬት ላይ ባለ እውነታ ላይ ብቻ ነው ማውራት ነው የምፈልገው :: Are u with me mimye..?? ይህውልሽ ይሄ ሰውዬ ባለፈው አመት ኒውዮርክ ላይ ከሩጫ ወጣሁ አለ ልብ አድርጊ እንግዲህ ..ካገር ቤት ሲወጣ ስለዚህ ነገር ትንፍሽ አላለም ከውድድሩ በፊት ይሄ የመጨረሻው እንደሆነም ምንም ፍንጭ አልሰጠም ...ውድድሩ ተጀመረ ሀይላችን ሰውነቱን አሟ ሙቆ ሜዳ ገባ ;; ባልታሰበ ሁኔታ ውድድሩን መቀጠል አቃተውና አቌርጦ ወጣ :: እንደ ወጣ ሽንፈቱን በጸጋ መቀበል አልፈለገም :: ስፖርት እኮ ነው ሁልጊዜ እኮ አንደኝነት የለም :: ወንድማችን ሀይሌ የሚዲያ ሰዎችን ሰበሰበና እየተንሰቀሰቀ ሩጫ በቃኝ አለ :: እንግዲህ ይሄንን ሲል የግል ማናጃሩን እንኴን አላማከረም :: የዛኑ እለት ማታ ቆጨው መሰለኝ አይ አስብበታለሁ ..አለ :: ( በቲዊተር ላይ ):: በሁለተኛው ቀን የለም ትናንት ክፉ ቀን ነበር ...ከሩጫ አልወጣሁም አለ :: እሰየው ደግ አልን :: ...ግን አንድ ነገር አለ ...ሚሚዬ ሀይሌ ከሩጫው ይልቅ ሞር ቢዝነስ ኦሪየነትድ ሆኗል :: እሱ ከመሮጡ በፊት እነማን እነማን አሉ ብሎ ማጣራት ያደርጋል ይባላል ...በጣም የሚፎካከሩት ሰዎች ሲገቡ ጉልበቴን አመመኝ ብሎ ይወጣል ...ባለፈው አመት ጉልበቴን ብሎ ነበር ...አሁን ይሄንን ካለ አንድ አመት ሆኖታል ..እንኴን ሀይሌን የሚያህል ቡዙ የጉልበት ዶክተሮች ይቅርና የእኔም አይነት ምስኪን ጉልበቱ እንዲያገግምለት አንድ አመት በቂው ነበር ...ለቶኪዮ ማራቶን ላይ ከፍተኛ ልምምድ ላይ እንደንነበር አገር ምድሩ ያውቃል . ግን ..ላስት ሚኒት ላይ ጉልበቴን አለና አረፈው ...እኔ ጠየኩ ..b]]እንዴት ነው ይሄ ነገር ..?? ስማቸው በኦሎሚፕክ አደባባይ ለመጠራት የሚከብዱ የኬንያና የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎች መሳተፋቸውን ግልጽ ሲያደርጉ ሀይሌ ጉልበቱን ይታመማል ..ይሄ ነገር እንዴት ነው ..? ብዬ ግራ ገባኝ :: በዚህ የተነሳ ባግራሞት ዜናውን አወጣሁት :: ይህ በዚህ እንዳለ አንቺ ጋስፕ የሆነ ነገር ይዠሽ መጣሽ ...ያንተ ወንድም አማረ ያክስትህ ልጅ /ማርያም .. ማለት ጀመርሽ ....የኔ እይታ ግን ከላይ ከጠቀስኩልሽ ውጭ ዜሮ አምስት ሳንቲም ጭማሪ የለውም :: የገረመኝን ኢሹ ማንሳት ደሞ መብቴ መሰለኝ :: እንዴት ነው አሁን ገብቶሻል አመለካከቴ አይደል ሚሚዬ ..?

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Sun Mar 06, 2011 4:26 pm    Post subject: Reply with quote

ዘሀር ...ሱማሊኛ ነው እንዴ ናፒ ..? Very Happy ባማርኛ እኮ ዛር ነው የሚባለው ስላልገባኝ ነው ..:: Cool

አንባቢ ሆይ እንደምን አሉልኝ ...እቺን ቤት በስራ ውጥረት ምክንያት ረሳኌት ቡዙ የምነግርዎት ነገር ነበረኝ ...ጊዜው ሰላቶ ሆነ ( ክንፍ አወጣ በረረ ...ልልዎት ፈልጌ ነው ) ቀስ ብለው ካነበቡት ደሞ ሌላ ትርጉም አለው :: ሰምና ቅኔ ህብርና ቅኔ ቅኔና ቅኔ :: አለመተማመንን መከዳዳትን ባስቀመጡት ቦታ አለመገኘትን ቡዙ ነገርን ይገልጻል ይሄ ጊዜው "ሰላቶ " ሆነ ማለት የሚለው አባባል :: እንዲህ ህብርና ቅኔ እየቻልኩ ማትሪክ ባማርኛ B አመጣሁ ...ወይ ነዶ ...!! Very Happy
ሰሞኑን እዚህ ዋርካ ላይና እንዲሁም በውነታው ዐለም ያየሁትን ነገር ላጫውትዎት ፈልጌ ነበር :: ጊዜ እንዳገኝ በጸሎትዎና በቸርነትዎ ያስቡኝ እንጂ አንድ ደጎስ ያለ ጽሁፍ አቀርብልዎታለሁ :: እስከዛው ግን እንግዳ በባዶ ቤት አይሸኝምና እዚች ቤት ይግቡና ኢንተርተየንምንት ክፍል የሚለውን በመጫን የሚፈልጉትን ሙዚቃና ፊልም በነጻ ይጋበዙልኝ ...ጊዜ ካለዎት ነው ከሌለዎትም ምንም አይደለም :: መልካም ሰንበት :: Cool

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ፍርንትት

ኮትኳች

Joined: 06 Dec 2010
Posts: 457

PostPosted: Mon Mar 07, 2011 12:11 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን ከምር የሆነ እንትን ይጎድልሀል 'ለዛ ' ወይም 'ስታይል ' ስትላዘዝ አሰልች ነገር ነህ እዉነቴን ነው ምልህ :በዚያ ላይ ወያኔነትህ ሲታከልበት አስበው እንዴት እንደምታጥወለዉለን Smile
አሁን የፈለገ አጀንዳ የፈለገ ሚሽን ቢኖራት ተስፋየ ገብረ አብ በቃ የሆነ እንትን ነገር አላት ደጋግመው ቢያነቧት አትሰለችም :ወዳጀ እኛ ስንት የለመድን ልጆች ነን

በጅ የተነካካና ክፍቱን ያደረ ንፍሮ ታዉቃለህ ? Very Happy

ፍርንትት

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ዘሀር ...ሱማሊኛ ነው እንዴ ናፒ ..? Very Happy ባማርኛ እኮ ዛር ነው የሚባለው ስላልገባኝ ነው ..:: Cool

አንባቢ ሆይ እንደምን አሉልኝ ...እቺን ቤት በስራ ውጥረት ምክንያት ረሳኌት ቡዙ የምነግርዎት ነገር ነበረኝ ...ጊዜው ሰላቶ ሆነ ( ክንፍ አወጣ በረረ ...ልልዎት ፈልጌ ነው ) ቀስ ብለው ካነበቡት ደሞ ሌላ ትርጉም አለው :: ሰምና ቅኔ ህብርና ቅኔ ቅኔና ቅኔ :: አለመተማመንን መከዳዳትን ባስቀመጡት ቦታ አለመገኘትን ቡዙ ነገርን ይገልጻል ይሄ ጊዜው "ሰላቶ " ሆነ ማለት የሚለው አባባል :: እንዲህ ህብርና ቅኔ እየቻልኩ ማትሪክ ባማርኛ B አመጣሁ ...ወይ ነዶ ...!! Very Happy
ሰሞኑን እዚህ ዋርካ ላይና እንዲሁም በውነታው ዐለም ያየሁትን ነገር ላጫውትዎት ፈልጌ ነበር :: ጊዜ እንዳገኝ በጸሎትዎና በቸርነትዎ ያስቡኝ እንጂ አንድ ደጎስ ያለ ጽሁፍ አቀርብልዎታለሁ :: እስከዛው ግን እንግዳ በባዶ ቤት አይሸኝምና እዚች ቤት ይግቡና ኢንተርተየንምንት ክፍል የሚለውን በመጫን የሚፈልጉትን ሙዚቃና ፊልም በነጻ ይጋበዙልኝ ...ጊዜ ካለዎት ነው ከሌለዎትም ምንም አይደለም :: መልካም ሰንበት :: Cool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Wed Mar 23, 2011 8:59 pm    Post subject: Reply with quote

እንደምን አሉ እቺን የትዝብት አምዴ ተርስታ ድልድይ ስር ወድቃ ዶቅዶቄ በላይዋ ላይ ሄዶ አገኘኌት :: የዶቅዶቄውን ታልጋ ከፈለጉ ከላይ አለልዎት :: ደህና ነዎት ሆይ የተከበሩ አንባቢዬ ሆይ !! ቡዙ ነገር ላዋይዎ እየፈለኩ ጊዜ አጣሁ :: ባለፉት ሰሞናት ቡዙ ነገሮች አለፍኩ ደጉንም ክፉውንም :: አረበቾን የናጠው ማእበል , ጃፓን የገለባበጠው ሱናሚ --ምድረ ነገድጎአድ ( ሱናሚውን የቀሰቀሰው እሱ ነውና የምድር ከርስ ነውጥ ...) እኔንም ጥግ አስይዞኝ ነበር :: የነው ግን በዜና አልወጣም :: ግን በቸርነቱና በምህረቱ በስላሴዎች ቸርነትና አንድነት እንዲሁም ስምምነት ይሀውልዎ በህይወት ተገኘሁ :: ጣራ ላይ ወጥቼ ተረፍኩ ;: አንድዬ ፓራሹት ላኩልኝ :: Cool አናድንዴ እኮ እዳ ከሜዳ ይባላል ሌላ ጊዜ በሰፊው አጫውትዎታለሁ :: ብቻ ህይወት መኖራችን ራሱ በእግዚአብሄር የተወሰነልን የእድሜ ገደብ ስላለን ወይም ስለተሰጠን ነው ወይስ የመኖራችን እንድምታ ከክፉ አጋጣሚዎች ማምለጥ በመቻላችን ነው ? ለምሳሌ የጃፓን ሱናሚ በእግዚአብህእር እቅድ ውስጥ ኢንክሉሲቭ የተደረገ ነበር ..ወይስ የፓስፊክ ውቅያኖስ ወለል ከመሬት ወለል ጋር በተፈጥሮዋዊ ክስተት መንሸራተቱ ? ስላይድ መደራረጉ ..? ለምን እንዲንሸራተት ሆነ ? መሬት ውስጥ ያለው ቅምጥ ሀይል ለምን ቅምጥ ሆኖ አይቀመጥም ? እየወጣ ለምን ሰላማዊ ሰዎችን ይጨርሳል ..? እኔ ስለገረመኝ የገረመኝን ሳልርሳው ልጽፈው ብዬ ነው እርሶ ምን ይላሉ ?? አንዱ ጉደኛ ጎደኛዬ ደሞ በዚህ ሀሳብ ውስጥ ተደምሜ እያለሁ ...ምን አንዳለኝ ልንገርዎ ፈሳሽ ነገሮች እንዲፈሉ ሙቀት አያስፈልጋቸውም አለኝ :: ከፈለክ እንወራረድ አለኝ ...ምን ይመስልዎታል ልወራረድ ወይስ ይቅርብኝ ...?? ሰሞኑን ግን እየዞረ ሰዎችን ሲለምን አይቸዋለሁ :: ""ስለ ምነተ -ማርያም ስለ ወላዲት አምላክ .. በሚቀጥለው ሳምት የምከፍላችሁ አበድሩኝ "" ሲል ነበር .... Very Happy የተማረው ትምህርት ለዚህ ለዚህ ካልጠቀመው ታዲያ ምን ሊሆን ነው ...በቆሎ አይሸለቅቅበት ...ሰላም ይሁኑልኝ ...የታዘብኩትና ያስገረመኝን ነገሮች ሳገኝ ይዠልዎት እመጣለሁ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Sun Mar 27, 2011 1:28 pm    Post subject: Reply with quote

መቸም አጋጣሚዎች ይገርማሉ ..ላንዱ ስቃይ , ሀዘን , ሰቆቃ የሆነ የህይወት ክስተት ለሌላው ደስታ ሰላም እንደውም የእንጀራው መሶብ እንደሆነ ልብ ብለው ይሆን ? አላጤኑት እንደሆነ ቀስ ብለው ዙሪያዎን ይቃኙ :: ህይወት ያጋጣሚዎችና የፓራዶክስ ድምር ውጤት ( equation ) መሆኗን ይገነዘባሉ :: የመኪና ግጭት በየጊዜው ይደርሳል ..እንደ ውሀ የሚፈሱ የሚመስሉት መኪናዎች ተጋጭተው ሲያዩአቸው አንዳንዶቹ ሸረሪት ላይ ፍሊት የተነፋ እስኪመስል ድረስ ጭርምትምት ብለው ሌላ ቁስ ሆነው ያገኟቸዋል :: ለተጎዱት መጽናኛ ለሞቱት ደግሞ ሰማያዊ በረከትን ያውርስልንና ያቺ አንገቷ ብቻ የቀረች መኪና ግን የኌላ ኌላ የሌሎች የእንጀራ መሶብ ናት :: መኪናዋን ከዋና መንገድ ወይም ከገባችበት ጥሻ ጎትቶ የሚያወጣ ካምፓኒ ወይም ድርጅት ይፈለጋል :: የዚህ ካምፓኒ ባለቤት ደሞ በስሩ የሚቀጠራቸው የራሳቸው ጎታች መኪና ያላቸው ኮንትራክተር ሹፌሮች አሉት :: ሹፈሮቹ አንዱ ሁለት , አንዱ ሶስት አንዱ አራት ልጆች ይኖሩታል አንዳንዱ ደሞ ኮርማነት የሚሰማው የሁለት ቤት አስተዳዳሪ ይሆን ይሆናል :: እዚህ እኔ ያለሁት አገር ይሄንን በተመለከተ ህጉ ሁሉ የቆመው ለሴቶቻችን ነው :: እሷም ኮማሪት ( ሴት ኮርማ ) ብትሆንም ህጉ እሷን ይደግፋል :: ( እዚህ ጋም ህይወት አንፌይር መሆኗን ልብ ይበሉልኝ !) Wink ወደ ጉዳያችን እንመለስና እነዚህ ሁሉ የመኪና ግችቶችን በተስፋ የሚጠብቁ ምናልባትም መኪናዎች እስር በርስ እንዲላተሙ ጾም ጸሎት የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ :: ግጭት ከሌለና አሸከርካሪዎች በሰላም ወጥተው በሰላም የሚገቡ ከሆነ እነሱ ጾም ማደራቸው ነዋ ! ለዚህ ነው በመግቢያዬ ላይ የአንዱ እምባና ለቅሶ ለሌላው የንጀራ ሌማት ነው የምልዎት :: ለመቀበል ባንፈልግም በየደጃችን የምናየው መራራ እውነት ነው :: ትናንት ለምሳሌ መኪናዬን አቁሜ የምይዛቸውን አንዳንድ ወረቀቶችን ሳገለባብጥ የመኪናዬን ቁልፍ መርሳቴን ሳላውቅ በሩን ቅርቅም አድርጌ በላዩ ላይ ቆለፍኩበት እዛቸው ሳልነቃነቅ ውስጤን አንድ ነገር ቅር አለኝ :: በሹፌሩ መቀመጫ ላይ ቁልፌ ተቀምጣ አየሆአት :: የምትቀልድብኝም መሰለኝ ..ዘለልኩ ወደ ላይ ወደታች አልኩ ተአምር እንዲመጣ መኪናዬን ሰባት ጊዜ ዞርኮአት :: እንደ ኢያሪኮ ... Very Happy ወይ ጉድ .. አራቱም በር አብረው ያደሙ ይመስል እምቢኝ አሉ ...ባለቤትነቴን የተቀማሁ መሰለኝ ...ትንሽ ቆይቼ ሞል ዐካባቢ ስለነበርኩ እባካችሁ እርዱኝ መክፈቻ ካላችሁ ተባበሩኝ ስል አንዱን ሴኩሪቲ አስተዛዝኔ ተማጸንኩት :: "አይ እኛ መክፈቻ የለንም ባይሆን የሚከፍቱ ሰዎች ግን ቁጥር አለኝ ..በዛ ልተባበርህ እችላለሁ ...አለኝ ..." ሴኩሪቲ ሆኖ አንድ ረጅም የልብስ መስቀያ የመሰለ የሽቦ ዘንግ እንዴት ያጣል ..? እርግጠኛ ነኝ የራሳቸው መኪና ቢቆለፍባቸው ለክፉ ቀን ብለው ያስቀመጡት ይኖራቸዋል ;:: አናደደኝ :: " ያህውልህ አየሀት ? ትታያለች በሆነ ሽቦ እኮ ጎትተን ልናወጣት እንችላለን .." እያልኩ ላሳምነው ሞከርኩ :: " ብረዳህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አንፎርቺነትሊ እኔ ላደርገው አልችልም .." ካሜሪካኖች እንጊሊዝኛ የሚያስጠላኝ ቃል ይሄ "አንፎርቺትሊ " የሚሉት ነገር ነው አንፎችኒትሊ ከገባ የሄዱበት ጉዳይ አይፈጸምም :: "አንፎርቺነትሊ ያንተ ኬዝ ኴሊፋይድ አላደረገም .." "አንፎሪችነትሊ ያንተን ጉዳይ ይሄ /ቤት ሊያየው ስለማይችል ዘግተንዋል ..." "አንፎሪችነትሊ ክሬዲትህ ጥሩ አለመሆኑን በማየታችን የጠየክውን ፕሮጄክት ሰርዘንዋል ::" ..:: "አንፎርቺነትሊ " የገባበት አረፍተ ነገር ከሰሙ እርምዎን ያውጡ :: እውነቴን ነው የምልዎት :: እናም ይሄ ጠብደል ሴኩሪቲ አንፎርቺነትሊ ልረዳህ አልችልም ሲል ደገመልኝ ..."እና ምን ይሻላል ?" አልኩት :: ወዲያው ማስታወሻውን አወጣና ከመቅጽበት አንድ ቁጥር ሰጠኝ :: የሰጠኝን ቁጥር እንደመታሁ ባንድ ጥሪ ፈጣን መልስ አገኘሁ መጣን የት ነው ያለሀው ...የሚል ... ፈጣን ምላሽ :: መኪና ውስጥ ቁልፍ እንድረሳ ተስፋ ሰንቀው ምናልባትም ዱአ ይዘው የሚጠብቁኝ ሰዎች እንዳሉ ግልጽ ነበር :: እቺ የኔ ገጠመኝ ናት :: እርሶም ከዚህ በላይ ያጋጠመዎት ቡዙ ነገር ይኖራል :: ብቻ ባንድ ነገር እንስምማ እቺ አለም በፓራዶክስ የተሞላች የፓራድዶክስ ስብስብ ናት :: ሰላም ይሁኑ :: ሳልረሳው ይሄን ጉድ ስምተዋል ?
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ፍርንትት

ኮትኳች

Joined: 06 Dec 2010
Posts: 457

PostPosted: Sun Mar 27, 2011 3:17 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ የእበት ክምር አስመስለህ ደረትህብን እኮ Laughing እንዴው አንቀጽ ምናምን የሚባል ነገር አልሰማህም እንዴ Rolling Eyes Rolling Eyes ጎመኔ ቀለም መጠቀምህስ ልማታዊ ጋዜጠኛ ስለሆንክ ነው Laughing Razz Razz

PostPosted: Tue Mar 29, 2011 11:44 pm    Post subject: Reply with quote

እዚህ ዋርካ ውስጥ "ቅዥቢው " የሚባል ሲኒየር ሲትዚን አለ :: መቼም በኛ በኢትዮጵያውያን ባህልና ወግ በባህላችን ሲኒየርነት ወይም የእድሜ አንጋፋነት ያስከብራል ያኮራል እንደ ጥላ ከለላም ይታያል :: አንድ ሰው የሚከበረው ግን እድሜው እንደ ባቡር ፉርጎ ተቀጣጥሎ ለማስላት አስቸጋሪ ስለሆነ ሳይሆን ዋናው መከበሪያው ግብሩና ውሎው አንዲሁም አስተሳሰቡ ነው :: ከዚህ አንጻር ሲገመገመገም ታዲያ ቅዥቢው እድሜውን አይታችሁ ተግባሩን ስታጤኑ ከገለባ የቀለለ ሆኖ ታገኙታላችሁ :: ውድ አንባቢዬ ሆይ የአንድን ሰው ምንነትና ማንነት ከተለያዩ አንግሎች ማወቅ ይቻላል :: ከፊደል አጣጣሉ ከብእር አያያዙ , ከስም አወጣጡ ........ማንነቱን መተንበይ አያዳግትም ::ልብ ብለው እንደሆነ ያውሬ ስም ያላቸው ጸሀፊያንን ይመልከቱ አብረውም ደሞ የጽሁፋቸውንም ይዘት አብረው ያጢኑ :: ዋልያን ልብ ይሏል :: ከርከሮን ያጤኗል :: Very Happy መቸም ጠላት ቡዙ እንዳላፈራ ብዬ ነው እንጂ ስም እየጠቀስኩ እነግርዎት ነበር :: Wink ወደ ጉዳዬ ልውሰድዎና ይሄ ቅዥቢ የሚባለው ካራክተር አንድም ቀን ሰላማዊ የሆነ ጽሁፍ ጽፎ አያውቅም :: ስድሳዎቹን አክትሞ 70ኛውን የጀመረ የነ ኢያሱ አለማየሁ ( ሀማቱማ ) የትግል ጔደኛ ልሸክሽክህ , ላስገባልህ ...እያለ ሲጽፍ አያሳፍርም ...?? እሱ ለአዲሱ ትውልድ የሰጠው በረከት ይሄ ነው :: በረከተ -እርግማን :: ይሄ ማለት ግን ሌሎችን በሱ እድሜ ያሉትንና ከሱ ጋር በትግል የነበሩትን እንደሱ ናቸው ለማለት እንዳልሆነ አይደለም :: በጭራሽ :: ይሄ ግን መቅኖ ቢስ ነው :: ሰላቶም ወናፍም ነው እንዲሁም ዋንኬ ነው :: ስሙም ለዚህ ዋና ምስክር ነው :: ባደረኩት አንዳንድ ጥናት ቅዥቢው 70 መጀመሪያ የኢሀፓ ወታደራዊ ክንፍ በነበረው በኢሀሰ ውስጥ በለሳ አካባቢ ተሳትፎ አድርጎ ነበር :: ያኔ ለትግል ሲወጣ 30 አመት ጋሜ ነበር :: ምንጮች እንደነገሩኝ :: ቡዙዎች የዘመኑ ወጣቶች ትምህርት ከድል በኌላ በማለትና ፋኖ ተሰማራ በማለት ለሻይ ቤተሰቦቻቸው የሰጧቸውን ፍራንክ አጠራቅመው ጥይትና ጠመንጃ ገዝተውበት በረሀ ሲገቡ "ጋሜ ቅዥቡ " ትግል የግር ኴስ ሜዳ የሆነ ይመስል ኴስ ይዞ በረሀ እንደመጣ አብረውት የነበሩ ይናገራሉ :: ቅዝቢውና ጥቂት ጎአደኞቹ ትግሉን የለቀቁት በፖሎቲካ ልዩነት አይደለም :: ከአፈርና ከድንጋይ ጋር ከተማማለ ትውልድ "ጋር "መሬት ሆይ እንኪ ሰውነቴን ውሰጂ ያንቺው ነኝ " ብሎ ከተማማለ ትውልድ " ጋር አብሮ መጔዝ ስላልቻለ ነበር :: ጀግኖቹ ምንም ነገር በእጃቸው ሳይኖር አንድ ቀን ይሄን ከፊት ለፊት ያለ ተራራ እናቀጠቅጥዋለን እያሉ ሲማማሉ ቅዥቢውና ጥቂት አላማ ቢስ ጔደኞቹ ግን ጨለማን ተገን አድርገው ፍየልና በግ ለማስደንበር የከብት በረት እየዞሩ ያንቀጠቅቱ ነበር : ከብቶች ለማስደንበርና ከዛ ደሞ ጫካ ወስዶ አርዶ ለመብላት :: ቅዥቢው የተባረረው በትግል ጔደኞቹ ሳይሆን በእረኞች ነው :: ውድ አንባቢዬ ሆይ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘሁት "ዋንኬ ቕዥቢው " እንዴት ሱዳን እንደገባ አጫውትዎታለሁ :: ሰላም ይሁኑልኝ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com

Last edited by ክቡራን on Wed Mar 30, 2011 1:53 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቅዥቢው

ኮትኳች

Joined: 20 Jun 2009
Posts: 317

PostPosted: Wed Mar 30, 2011 12:39 am    Post subject: ኪኪኪ ... Reply with quote

ክቡራን ዛሬ ሳታስበው ለስራዬ ፋይዳ ያላቸው ሃረጎች ስለሞነጫጨርክ ደስ ብሎኛል ::አየህ "Cyber Vandalism" በሚል ርዕስ ላይ አንድ ጥናት በማድረግ ላይ ነኝ ::ለጥናቴ እንደ መነሻ አድርጌ ከዘረዘርኳቸው መላምቶች (Hypotheses) አንዱ Cyber vandalism not limited by age 'ሚል ነው ::እናም እኔን አስመልክትህ ከዚያች ቆሮቆንዳ ጭንቅላትህ በፈለቁ እንደ አስተሳሰብህ በተወላገዱ ወልጋዳ ቃላቶች የሞነጫጨርካቸው ወልጋዳ ሀረጎች ይህን መላምቴን 'ሚያጠናክሩ ሆነው ስላገኘኌቸው ለጥናቴ ከክፍያ ነጻ አስተዋጾ በማድረግህ ሉጢው አምባቸው ሾተል አስፈንድዶ ይሸክሽክህ በማለት ቅዥቢያዊ ምርቃት መርቄሀለሁ ...
በነገርህ ላይ እድሜየን አስመልክቶ ትክክልኛ መረጃ ከዚያች ካለሌዋ ታናሽ እህትህ ማግኘት ትችላለህ ምክኒያቱም እሷ አራት ጊዜ በሰርግ ስታገባ አራቱንም ጊዜ ሻማ ያዥ እኔ ነበርኩና ...
አያ ጫኔ እንዳልከው እድሜ ጸጋ ነው ጸጋም መስታወት ነው መስታወትም ሁሉን ያሳያል ...የኔ መስታወት ግን ከተሰበረ ሰነበተ ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Thu Mar 31, 2011 1:34 pm    Post subject: Reply with quote

Would you like listen in the worst music of the month? May be the worst music of the year? In my view this is the most awful clip I ever hared. Worst makeup, worst outlook and worst set up. Even the male player is not an artistic one; he lacks the magnetism and entertaining skill to act as lover. It looks that he is there because he is been told so to be there. A kind of cold blooded guy! I want be honest with you, I dont like it at all. Apart from the back ground pictures and the traditional customs they wear , the clip neither represent the way of life nor the people they thought . At some point you hear even Rap Music in the middle of traditional GURAGINA SONG. Other surprising event is that the lead singer wears sunglasses comparable in size to her face. Imagine having eye glasses in a cultural show is like someone offering you A ሽሮ ወጥ mixing with fruit slices and add piece of cheese cake on a top of It, all in one plate. ጉድ እኮ ነው :: I may be wrong but it is my take from the clip. Have your say. እስኪ እዩትና ፍርዳችሁን ስጡ :: To listen the clip click here.
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Sat Apr 02, 2011 9:00 pm    Post subject: Reply with quote

እሷ " እኔ የምፈልገው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ..?"

እኔ " እሺ አንቺ የምትፈልጊው ...?"

እሷ ከንፈሯን ጣል ፊቷን ፈገግ አድርጋ .." በቃ ቆንጆ ልብስ ለብሸ ሽክ ብዬ እቤት ውስጥ መቀመጥ ..."

እኔ " ....ምን አልሽኝ ..ጆሮዬን በትንሿ ጣቴ አከክ አደረኩት ""

እሷ " በቃ እኔ እምልህ አለ አይደለም እኔ ታውቃለህ ስራ መስራት አልወድም .."

እኔ "" አውቃለሁ .. ባለፈው ነግረሽኛል "

እሷ " ትዝ ይልህ እንደሆነ ባለፈው አክስቴ ልትጠይቀኝ መጥታ ክትፎ ኦርደር አድርጌላታለሁ ብየህ አልነበር ..? በውብ አይኗ ገረመመችኝ :: ውበቷ ደሞ ያለው አይኗ ላይ ነው ::

እኔ " አዎ በሚገባ አስታውሳለሁ ...እንጂ ..ላክስትሽ ካበሻ ቤት ኦርደር አድርገሽ ምሳ አንደጋበዥሻት ነግረሽኛል ..." እርምህን አውጣ ክቡራን ልታገባት ካሰብክ ኪችኑ ያንተ የግል ሀላፊነት ነው እያለችህ ነው :: ሸለለለ ሸለለለ ላላላ ሸለለለ ..

እሷ " ጔደኞቼ ሁሌም እቤት ሲመጡ ምን እንደሚሉኝ ታውቃለህ ?"

እኔ " ምን ይሉሻል .. ? " ባግራሞት

እሷ " የት ልትሄጂ ነው ይሉኛል ?"

እኔ " እቤትሽ ..ድረስ ጋብዘሻቸው መትጠው .. ለምን ልጄ ... አንዳንድ ሰው እኮ ድፍረቱ ይገርማል " ተቆርቆሪነቴን የወደፊት አባወራቴንም ለማሳየት እንደ መቆጣት አልኩ ::

እሷ " ሁሌም ለባብሼ ሽክ ብዬ ልክ የሆነ ቦታ እንደምሄድ ሆኘ ነው የምጠብቃቸው ...ፒክኒክ ወይም እራት የምወጣ ይመስላቸዋል ....እኔ ግን እቤት ውስጥ እንደዛ መሆን ደስ ይለኛል .."

እኔ .." ሁሌም ..?እንደዛ "ነሽ ማለት ነው ? "

እሷ " እኔ ታውቃለህ በጣም ደስ የሚለኝ ነገር እሱ ነው ...ሌላ ደሞ ደስ የሚለኝና ሚናፍቀኝን ነገር ልንገርህ ..

እኔ "ቀጥዬ እሰማለሁ .." በድምጽ ሳይሆን ባይኖቼ ::

እሷ " ሂልተን ወይም ግዮን ምሳ ወይም እራት በልቼ ...እቤት እመጣና ከማዘርና ከሰራተኛችን ጋር ቡና አስፈልቼ ሰርቪስ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ መጠጣትና ከነሱ ጋር ቁጭ ብሎ መጫወት .."

እኔ " እኔም የቡና ሰረሞኒ እወዳለሁ ..ግን እንድዛው የራት ልብስ እንደለበሽ ...ነው ወይስ ?

እሷ " .... ልብሴን መኝታ ቤት ገብቼ እቀይርና ቆንጆ ቱታ አደርግና ከዛ እያወሩ ቡና መጠጣት .. በጣም ደስ ይለኛል ..." ሌላ ድስ የሚለኝን ነገር ልንገርህ ..

እኔ " go ahead..! Maki ."

እሷ " ከወንድ ደስ የሚለኝ ደግሞ ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች የሚወድ ራሱን የሚጠብቅ ...ስታይል የሚከተል ...እንግዶች እቤት ሲመጡ እንደኔ ቆንጆ ልብስ ለብሶ የሚያስተናግድ " .በነገራችን ላይ ..እኔ ይሄንን እንዴት እንደማየው ታውቃለህ ...? በንግግሯ መሀል ጥየቀችኝ ::

እኔ " እንዴት ነው የምታዪው .. "

እሷ " ቆንጆ ልብስ መልበስህ አለ አይደል ለእንግዳህ ያለህን አክብሮት ( ሪስፔክት ) መግለጫ አድርጌ ነው የማየው ::

እኔ ' ህምምምም ..ሊሆን ይችላል ...እሺ .."

እሷ " ሌላ ደሞ የምወደውን ልንግርህ ..."

እኔ " ..ሌላም አለሽ ...? " ሳላውቀው ድምጸ ፈጠነ (

እሷ " አዎ ..እኔ ታውቃለህ ...ይሀውልህ ...

እኔ " እሺ ቀጥዪ . የሳሎን ቡቲክ :: "

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Tue Apr 05, 2011 3:36 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተከበሩ አንባቢዬ አንዳንድ ነገሮች ሲገርሙኝና ሲያጋጥሙኝ ቶሎ መጥቼ እዚህ መጥቼ ካላጻፍኴቸው ይረሳሉ .. ይትናሉ ... ኢቫፔሮት ያደርጋሉ Very Happy ይገርማል ትዝብቶች "ቮላታይል " ናቸው አይቆዩም በወረቀት ቶሎ ብለው ካልጫሩት እውነቴን ነው የምልዎት ውበታቸውም ግነታቸውም ትዝብትነታቸውም ሁለንተናቸውም እንዳለ ሆነው አይዘልቁም :: ትናንት ያሳቀኝና ያስደመመኝ ነገር ዛሬ ምንም ላይመስለኝ ይችላል :: ዛሬ የራሱ ትዝብት የራሱ ግርምት አለውና የትናንቱን ይዞብዎት ይሄዳል :: እና ያጋጠመኝን ልንገርዎት :: ጆርጂያ አቬኑው በሚባል መንገድ ሳልፍ ትንሽ እንደው አለ አይደል ( ምራቄን እየዋጠኩ ነው የምጽፍልዎ ) ቆረጥ ተደርጎ የሚበላ ስጋ አማረኝና አንድ የኢትዮጵያ ሱቅ ገባሁ አንድ ጠና ያለ ቱታ የለበሰ ሰው በሩ ላይ ቆሟል :: ሰላምታ ተለዋወጥንና የመጣሁበትን ጉዳይ ነገርኩት ::
" ለክትፎ የሚሆን ስጋ ፈልጌ ነበር "
" አይ ጾም እኮ ነው አሁን ስጋ አናስገባም አለኝ ::" እሺ ብዬ አመስግኝው ስወጣ
'' ቆይ እስኪ ሌላ አንድ ሱቅ አለ አንድ ሁለት ብሎክ ወደታች ስትወርድ የምታገኘው ሱቅ ውስጥ ግባና ጠይቃቸው ..እነሱ ይኖራቸዋል " አለኝ :: እኔም እሺ ብዬ ሴት የላከውና ስጋ ያየ ሞት አይፈራም የሚለውን ያልለቁትን አዲስ ዜማ እያንጎራገርኩ ወደ ተባለው ሱቅ ደረስኩ :: ፊት ለፊት ገንዘብ ተቀባዩ ከደንበኞች ጋር ያወራል :: አንዴ በንግሊዝኛ አንደ ባማርኛ አንዴ በስፓኒሽኛ እየቀደደ ደንበኞቹን ያስተናግዳል :: "ሀሪፍ " አልኩትና አልፌው ስጋ ወደ እየቆረጡ ወደ ሚሸጡት ሰው ሄድኩ :: ግድግዳው ላይ ከብቱ እዛ የታረድ እንዲመስል አንስ አነስ ያለ ጎራዴ የሚመስሉ ቢላዎች ተሰቅለዋል :: እሳቸው ደሞ የደንቡን ነጭ ልብስ አድርገው እያጸዳዱ ነበር :: የመዝጊያ ሰአት ይመስላል :: ሰላምታ ካቅረብኩ በኌላ ለክትፎ የሚሆን ስጋ እንዲቆርጡልኝ ጠየኴቸው
" አዪ ዘገየህ የለም ..." አሉኝ :: ምራቄ መድረቅ ጀመረ ::
"ምንም የለም ? " ተስፋ አልቆረጥኩም ::

"አይ የለም ዛሬ ቶሎ ነው ያለቀው "
" እንዴ ጾም አይደል ሰው ምን ነካው ?
" ቀና ብለው አዩኝና በትዝብት ...አይ እንተማ የኛ ጾመኛ በሚል አይን ገረፉኝ ::
"ታዲያ እዚህ መጥቼ ባዶ እጄን አልሂድ በቃ ለቁርጥ የምትሆን ይፈልጉልኛ .." ጠየኩ ድምጼን ወረድ አድርጌ ::
"እሱም የለም "

" ምን አይነት ጉድ እዚህ አካባቢ የሚኖር ሰው ሁሉንም ገዝተው ሱቁን ባዶ ያደርጉታል እንዴ ? ምን አይነት ቁጣ ነው ...ጾም አይደለም እንዴ ? ምነው የዚህ አካባቢ ክርስቲያን እንዲህ ጅብ ሆነ ? " ከራሴ ጋር እያወራሁ ልወጣ ስል
" ለጥብስ የምትሆን ትንሽ አለች እሷን ልቁረጥልህ ..?"
አሉኝ ::

" አዎ ጥሩ ነው እሷን ይስጡኝ " አልኩ እሷም አለቀች አንዳልባል በመፍራት :: ምን ይታወቃል ምናልባት ፍሪጅ ውስጥ እሳቸው ያላዩት ያደፈጠ አውሬ ይኖር ይሆናል ማን ያውቃል ...ይዘው እስኪመጡ ድረስ ባይኔ ጠበኮአቸው :: ከታናሽ በጎን የተቆረጠ የሚመስል ስጋ ይዘው መጡ ጠፈፍ ያለ ነው ቀይ ቀይ ኖሮት በጎን ደሞ በስሱ የሚውርድ ጮማ አለው ..."
ምን ያህል እናድርገው ?

" ስጋውን እያየሁ የትሪ ጥብስ ባምሮዬ ውስጥ ስለነበር ቶሎ አልሰማኌቸውም ነበር ::

" አንድ ፓውንድ ..ሁለት ፓውንድ አድርጉልኝ ...ፓውንዱ ስንት ነው ?

" 6.50 "

" አይ እንግዲያው አንድ ወይም አንድ ተኩል ይሁን ግድየለም ቢያልፍ ምንም አይደለም ..."

እሳቸው መቁረጥ ሲጀምሩ አይናቸውን ጠብቄ ሲያዩኝ ከፊት ለፊታቸው ካስቀመጡት የቲፕ ሙዳይ ላይ አንድ ብር አስቀመጥኩ :: አይን ላይን ተገጣጠምን ኮስታራ ግንባራቸው ፈታ ሲል አስተዋልኩ ::

"ጮማውን ላንሳው ?: "

" አዎ ግን ቡዙ አይነሳ ለማጣበሻ ይሆናል ::" ዘይት ሳይደረግ በጮማው ብቻ የሚጠበስ ጥብስ እጅ ያስቆረጥማል እርሶም ይሞክሩት አንባቢዬ :: Very Happy ጮማ ጥብስ አድባር ጥብስ የሚባለው እሱ ነው :: ስጋዋን በደንብ አሰማምረውልኝ አመስግኛቸው ወደ መክፈያው ስሄድ ገንዘብ ተቀባዩ ልጅ ( ቅድም ሲያወራ ነበር ያልኴችሁ ) ካንድ እሲፓኒሽ ጋር የሞቀ ወሬ በተሰባበረ ኢስፓኒሽኝ ይለዋል :: እኔ ከኌላዬ አንዲት ወጣት ልጅ ሌላ አንድ ሰው ለመክፈል ወረፋ ይዘናል :: አጅሬ ምን ያህል ከውጭ ሰዎች ጋር መግባባት እንደሚችል ሊያሳየን የሚሞክር ይመስላል ሁኔታው :: እንደውም እኛን ረሳን :: እንደገባኝ እስፓኒሹ አንድ ነገር ፈልጔል የፈለገውውን ነገር ግን ልጁ ያወቀው አልመሰለኝም :: በዛ ላይ ሞቅ ብሎታል ለማብረጃ ነው መሰለኝ ሌላ አንድ ፓክ ኮሩና ቢራ አዟል :: ልጁ እስፓኒሹ የጠየቀው ነገር አልገባውም እሱ ሌላ ነገር ይፈልጋል እቺ የኛ አራዳ ደሞ ፎን ካርድ ታሳየዋለች :: እስፓኒሹ አንገቱን በገንዘብ መክፈያው በኩል አሾልኮ የሚፈልገውን ባይኑ ሊያሳየው ይሞክራል :: አልተግባቡም :: ስገምት ስፓኒሹ የኛውን አገር ልጅ የጔቲማላ ወይም የኤልሳቭዶር ሰው አድርጎታል :: ይሄም የሆነብት ምክንያት ልጁ ራሱ አማርኛ ይናግር እንጂ ብሊች ውስጥ ተነክሮ የወጣ ነጭ አንሶላ ነው የሚመስለው ቀይ ነው :: ከጸጉሩ መከርደድ በስተቀር እነሱን ይመስላል :: " "ሆርሄ " እኔ እኮ ምልህ ይሄንን ነው ይለዋል " ልጁ ደሞ ይሄ የተሰባበረ ስፓኒሽኛ የትም እንደሚያደርሰው ስላላወቀ : " እኔኮ ሆሴ ስፓኒሽ ፖኪቶ ፖኪቶ ..ነው የምችለው " ምናምን ማለት ጀመረ :: ውነቴን ነው የምላችሁ ስፓኒሹ የባሰ ተናደደ :: እሱ ያገሬ የወንዜ ልጅ አገኘሁ ብሎ ደስ ብሎታል አሁን ዋና የሚፈልገውን ነገር ሲጤይቀው ስፓኒሽኛ አላውቅም ማለቱ የተጨበረበረ ያህል ተሰማው .. Very Happy ብዛ ላይ ጋል አድርጎ ነው የመጣው :: በኌላ አንድ አሜሪካዊ መጥቶ ሁላችንንም ገላገለን :: ነገሩ ካለፈ በኌላ ከኌላዬ የነበረቸው ልጅ በነገር ታኮ ነካ አደረገቸው " እንዼት ነው ከዚህ በፊት እዚህ ሲመጣ እኔ ከሁንዱራስ ነኝ ብለሀው ነበር እንደ ? " Laughing ልጁ አሽሙሯን አልወደድውም :: ምርቃናው ጠፋ :: ሰላማት :: Cool

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Mon Apr 18, 2011 7:08 am    Post subject: Reply with quote

ጠይና ይስጥልኝ የተከበሩ አንባቢ :: እቺ ቤት ርቃ ርቃ ወደ ኌላ ሄዳ ነበር ...በካቦ ጎትቼ ወዲህ ይዣት መጣሁ ....ሀሳብ ጠፍቶ ሳይሆን ጊዜ በብር የሚመነዘርበት አለም እየኖርን ፋታ ጠፍቶ ነው ችላ የተባለችው ...::
ዛሬ የታዘብኩትን ላዋይዎ ... ባለፈው እንዳልኩዎት ትዝብቴን በብእር ቀርቼ ( መቅራት ) ካላስቀመጥኩት የተናል :: ነገ የራሱ የሆነ ሌላ ግራሞትን ትዝብትን ይዞ ይመጣል :: ህይወት የዐጋጣሚዎች ስብስብ ብቻ ሳትሆን የትዝብትና የግርምት ድምርምር ውጤት ናት ብልዎት ትክክል ይሆን ? ብቻ እኔ የመሰለኝ ነው ...ለዛም ይሆናል ቅዱሱ መጽሀፍ ለነገ አትጨነቅ ነገ የራሱ ጭንቀት ... የራሱ የሆነ ሁከት አለው የሚለው ...እውነት እኮ ነው ምን ይታወቃል ነገ የሚሆነው ..! የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ ...ሀይ ስኩል የነበሩ ጔደኞቼ የሚሰጡኝ አክብሮት ነበር :: ታዲያ እኔ እቺን ነገር "ሴንስ " ማድረግ ጀምሬአልሁ በነገራችን ላይ በዚች ቃል አንዱ ፍንድቅድቅ በዚህ አባባሌ ሰሞኑን ሲፈነድቅ ነበር :: ሞኝ ተረቱ አልቆ ከተነገረ በኈላ ሰው ሁሉ ስቆ ሲጨርስ እሱ መሳቅ ይጀምራል ይሉኝ ነበር ...መምህሬ ይሄይስ :: Very Happy እና ወደ ጉዳዬ ልውሰድዎና ሻይ ቤትም ሆነ አንዳንድ ቦታም ከነዚህ ጔደኞቼ ጋር ሆኜ መታየትን እመርጣለሁ ..አርቲ ቡርቲውን ስናወራ አንዳንች ሌላችንን ባናከብርም ቁም ነገር ያለው ነገር ሲጀመር ግን ለኔ የሚሰጠኝ ለየት ያለ ክብር አለ :: ቀስ በቀስ ጫጫታው በረድ ሲል ይታወቀኛል እንደ ቀረበልን በራድ ሻይ አይነት :: ይቺ ነገር የልብ ልብ ሰጠችኝ :: ኩራትም ድፍረትም ወኔም ፈጠረችልኝ ;; ታዱያ ይሄን አልጠላሁትም :: እንደውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደድኩት መጣሁ ...ከበፊቱ የተሻልኩ ሆኘ ለመገኘት አዲስ ነገር ይዤ በየሳምንቱ ብቅ ማለትን አዘወተርኩ :: ቀስ እያልኩም ራሴን በነሱ ውስጥ ማየት ጀመርኩ :: አስተሳሰቤና አእምሮዬ በነሱ ተቀረጸ :: ምን አለፍችሁ የራሴ ሳልሆን የነሱ መሆን ጀመርኩ :: አዲስ ነእር ይዤ ብቅ ስለ የሻይ ፌሽታውም የዛኑ ያህል እየበረከተልኝ መጣ :: ይሄ ነገር ግን የኌላ ኌላ ችግር ይዞ አስከተለ :: እነሱ ከሚሰጡኝ አስተያየትና ግምት በመነሳት ሁሉንም ነገር አውቃለሁ የሚል የንቁራሪት አይነት እብጠት ውስጤ ተጸነሰ :: በተለይ አንደኛው ልጅ ሲሸረድደኝ ይሁን ከምሩ እስካሁን አላውቅም ( እምበርሀን ብቻ ናት የምታውቀው ) ምን አለኝ ...አንቺ እኮ መጽሀፍ ላይ ስምሽ የለም እንጂ አባቴ ይሙት ፈላስፋ እኮ ነሽ ...ብሎኛል :: Very Happy ዛሬ አብሮ አደግ ጔደኛዬ በህይወት የለም :: ቢኖር ኖሮ በጠየኩት ነበር :: እንደዚህ አይነት አስትያየቶች አሉታዊም አንቱታዊም ገጽታዎች አሏቸው :: ፈረንጆች "ፕሮስ አንድ ኮንስ " ይሏቸዋል ..አስማታዊ ትርጉም :: ጥሩው መልኩ ተደማጭ ለመሆን በየጊዜው አርስትን ለማዘጋጀት ማንበብ አዳዲስ ነገርን መፈላለግ መጠየቅን ስለሚሻ እግረ መንገዱንም የእውቀትን አድማስ ያሰፋል :: መጥፎው መልኩ ደሞ ራስን አዋቂና ሊቅ አድሮጎ የማየት ሌላውን ወደ ታች የመመልከት ከኔ በላይ ማንም የለም አይነት ስሜትና ወደ ላይ የመንጠራራትን አባዜ ይፈጥራል :: በዚህ አይነት ህብረተስብ ውስጥ ኖረውና አድገው አካባቢአቸው ከፈጠራቸው ትንሽ ኩሬ ውስጥ ወጥተው ትልቁ ውቅያኖስ ዘው ብለው ሶቶ መሪና የገቡ አሉ :: "ካሊቢሬት " ሳይደረጉ :: "ካሊቢሬት " = ሳይጠረቡ :: አሁንም አስማታዊ ትርጉም :: እነዚህ ሰዎች ታዲያ በትልቁ ባህር ውስጥ የሚኖሩት ኑሮ ሰላም ያለው አይደለም :: ያኔ በትንሿ ምንጭ ውስጥ እያሉ ተሰሚ እንጂ ሰሚ ስላልነበሩ አውሪ እንጂ አድማጭ ሆነው ስለማያውቁ ሌላው በሰላም ሲዋኝ እነሱ ይደፈቃሉ :: ሲመቻቸውም ይደፍቃሉ :: ውድ አንባቢዬ ሆይ ይሄ ሊሆን የሚችል ክስተት ነው :: ባህሪያችንን የሚወስነው የየኖርንበ ማህበረስብ ነው :: በርግጥ ለመሰራታዊው ሰዋዊ ባህሪያት ቤተሰቦቻችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ :: ለማህበራዊ ግንኙነት ግን የተማርንበት ትምህርት ቤት , የህይወት ልምዳችን , ያለፍንበት ጉዞ , ጕደኞቻችን ለኛ ያላቸው አመላከከት እኛ ለነሱ የምንሰጠው አስተያየት .. አሁን ለምንኖርበት ኑሮ ተዋጽኦች ናቸው :: ትምህርት ብቻውን ማንነትን አይቀርጽም :: ባለ ድግሪ ሆኖ ንፍጣም አለ :: ሳይማር ደሞ ትሁት , መልካም ብሩህ አስተሳሰብ ያለው በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ከሰዎች ጋር መኖር ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የገባው አለ :: መማር ማለት ራስን መግዛት ነው አጉራ ዘለልነት አይደለም :: ኮለኔል መንግስቱ /ማርያም ስልጣን ላይ ሲወጡ ዐገር ወዳድ ለውጥ ወዳድና እድገት ለማምጣት ቆርጠው የተነሱ የሌሎችን ሀሳብ በጽሞና የሚያደምጡ ናቸው ይባል ነበር :: ትንሽ ቆይቶ ግን እርሶ የኢትዮጵያ ብርሀን , የኢትዮጵያ ሻማ የኢትዮጵያ ጧፍ , የኢትዮጵያ ነዶ , የኢትዮጵያ ስንደዶ , የኢትዮጵያ ጥቁር አልማዝ እንዲሁም ኢንዲሚክ ወፍ ነዎት የሚሉ ሰዎች በዙሪያቸው በረከቱ :: ይባስ ብሎ ከጎአድ መንግሱት አመራር ጋር ወደፊት የሚባል መፈክርና ጔድ መንግስቱ መንግስት ናቸው የሚል መፈክር ባንዱ ካድሬአቸው ከተፈጠረ በኌላ መንጌ አንድ አይን ጠፉ :: ከዛን ጊዜ በኌላ ገበሬዎች ሄደው ዘንድሮ ምን ማምረት እንዳለባቸው መመሪያ ከሰጡ በሚቀጥለው የምርት ዘመን እሳቸው የጠቀሱት የእህል አይነት የአገሪቱን ጎተራ ይሞላል ...ጂኦሎጂስቶችን ምን አይነት "ኦር " ማውጣት አንዳለባቸው ከነገሩአቸው ርብርቡ ሁሉ እዛ ላይ ይሆናል :: አንድ ሰሞንማ ለዶክተሮች እንዴት ማከም እንዳለባቸው ዎርክሾፕ ሰጥተው ነበር ይባላል . Very Happy ነው እንግዲህ "ኢንዲሚክ ወፍ የተባለላቸው መንጌን እንደ ወፍ ካገር በረው እንዲጠፉ ያደረጋቸው :: እና እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይሄ ጥፋት የመንጌ ብቻ አይደለም ... በዙሪያቸው ያሉ ስብስቦች ለምንጌ " ሱፐርይርርና አሮጋንት ፐርሰናሊቲ "መፈጠር መዋጮ አድረገዋል :: ሰው ናቱራል ከሆነው እሱነቱ ወጥቶ ሰው ሰራሽ ሰው ሲሆን ራሱም ችግር ላይ ወድቆ ለሌላውም ችግር ይሆናል :: በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሳጥናኤል መልከ -መልካም እንደነበር እንደውም ሉሲፈር የሚባል ስም እንዳለው ከእግዛብሄር ዋና መላክቶች ሚካኤልና ገብሬል በላይም እንደነበር የእጊዚአብሄር ቃል ያስተምራል :: እንዳልኩት ሉሲፈር ቆንጆ ነበር :: አካባቢውን ዞር ዞር ብሎ ሲያይ በሱ አምሳል የተፈጠሩት በሙሉ እንደሱ ውብ መስለው አልታይህ አሉት :: እናም በልቡ ውስጥ ትእቢት ተጸነሰ :: ታዲያ የዚህ ትእቢት መጨረሻው 7ኛው ሰማይ ወደ ምድር መወረውር ሆነ :: ይሀው እሱ ምድር ላይ በመሆኑ እኛም ሁላችን መከራ እናያለን :: እሱም የዚህ ትልቅ ውቅያኖስ አካል ነውና :: ትእቢት መጥፎ ነው ለማንም አልበጀ ..ለሉሲፈርም አልሆነው ..የትቢት ትንሽም የለውም :: ሳምቡሳ ወይም ቦርዴ ጠላ የፈጠረውም ትእቢትም ሆነ የሉስፈርም ትእቢት መጨረሻቸው ወይም መድረሻቸው አንድ ነው ... እንጦርጦስ :: ቃለ ህይወት ያሰማልን ...መልካም ሆሳህና ይሁንልዎ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Ahmed-1

ኮትኳች

Joined: 19 Mar 2007
Posts: 151

PostPosted: Mon Apr 18, 2011 10:19 am    Post subject: Reply with quote

ጋሽ ክቡራን አማን ነህልኝ !
እንደዚህ እያለ የሚፈስ ሸጋ ፅሁፍ ሲገኝ ቁርቁርርርርር እያለ ይወርዳል :: ጋዜጠኛነት ሙያህ ይሆን ?

ስለመንጌና አሻጃግሬዎቹ የጻፍከው : የዳዊትን "ደም እንባ " መፅሐፍ አስታወሰኝ :: "ዕለተ እሁድ ቤተ መንግስት ዉስጥ ግራዉንድ ቴኒስ ከሊቀመንበሩ (ከመንጌ ) ጋር ስንጫወት ሆን ብለን እንሸነፍላቸው ነበር ..." ብሏል ዳዊት !

ሊቀመንበሩ ኳሷን ከመስመሩ ውጭ ሲሰርቩ ወይም ድሮፕ ሾት ሞክረው ኔቱን ባታልፍም እንዲሁ ለቆራጥ ሙከራቸው ብቻ ይጨበጨብላቸው ነበር :: እናም ዳኛው ባጨብጫቢዎች ጭብጨባ እየተጭበረበረ ነጥብ ቆጠራ ላይ ይሳሳታል :: መንጌ ሁሌ እንዳሸነፈ ነበር - ግራዉንድ ቴኒስ ! Laughing

ከአክብሮት ጋር !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5058

PostPosted: Tue Apr 19, 2011 1:01 am    Post subject: Reply with quote

Ahmed-1 እንደጻፈው
Quote:
ጋሽ ክቡራን አማን ነህልኝ !
እንደዚህ እያለ የሚፈስ ሸጋ ፅሁፍ ሲገኝ ቁርቁርርርርር እያለ ይወርዳል :: ጋዜጠኛነት ሙያህ ይሆን ?

ስለመንጌና አሻጃግሬዎቹ የጻፍከው : የዳዊትን "ደም እንባ " መፅሐፍ አስታወሰኝ :: "ዕለተ እሁድ ቤተ መንግስት ዉስጥ ግራዉንድ ቴኒስ ከሊቀመንበሩ (ከመንጌ ) ጋር ስንጫወት ሆን ብለን እንሸነፍላቸው ነበር ..." ብሏል ዳዊት !

ሊቀመንበሩ ኳሷን ከመስመሩ ውጭ ሲሰርቩ ወይም ድሮፕ ሾት ሞክረው ኔቱን ባታልፍም እንዲሁ ለቆራጥ ሙከራቸው ብቻ ይጨበጨብላቸው ነበር :: እናም ዳኛው ባጨብጫቢዎች ጭብጨባ እየተጭበረበረ ነጥብ ቆጠራ ላይ ይሳሳታል :: መንጌ ሁሌ እንዳሸነፈ ነበር - ግራዉንድ ቴኒስ !

ከአክብሮት ጋር !

ሰላም ወንድሜ አህመድ እንደምን አለህልኝ ? Cool ለመልካም አስተያየትህ ምስጋናዬ ይድረስህ :: ያልካትን የቴኒስ ጨዋታ እኔም የሆነ ቦታ አንቤባታለሁ :: ዙሪያችንን ካየሀው ህይወታችን ያንን ይመስላል :: ሩቅ ሳንሄድ ጊዜ ሲኖርህ እዚቹ ዋርካ ላይ ዝር ዞር በል :: በጽሁፌ ላይ ያነሳኌቸውን አስተሳሰቦች ትመዝንበታለህ ብዬ እገምታለሁ ::
ስላም ምሽት ( ቀን )
አክባሪህ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue Apr 19, 2011 2:13 am    Post subject: Reply with quote

ክቡ :

ለማሰብ እየሞከርክ እንደሆነ የሚያሳይ ፍንጪ አየሁ ...መቸስ በእግዚያብሄር ተስፋ አይቆረጥም (ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም እንደሚባለው ) Very Happy በዚሁ ከቀጠልክ አየነ -ህሊናህ ተገልጦ ""ዘርህ "" እና ሆድህ ህሊናህን ማዘዝ ስለሚያቆሙ ህሊናህ ዘለግ ብሎ ፍትሀዊነትን እና ኢፍትሀዊነትን - የሀገርን ትርጉም እና በዘር የማሰብን መናኛነት ልታይ እንደምትችል እገምታለሁ :: Idea አብረውን ያደጉት ትግሬዎች እንደነበሩ እኮ አሁን ነው ህወሀት ያስታወሰን :: ከምሬ ነው የምልህ ክቡ :: መታወቂያ ላይ ዘር ካልጻፋችሁ ሞቼ እገኛለሁ ያለ መንግስት እኮ ነው ህወሀት Idea

ለነገሩ የህወሀትን ግድም ማሻሻጥ አቁመህ እንደዚህ አይነት እንደ እንቁራሪት የማያሳብጥ ሀሳብ ያጻፈህ መሬት ላይ ያለው እውነታ ምንድን ነው Question Very Happy

ስለማበጥ ካነሳህ ዘንዳ - የመንጌን እንደተነተንከው (የጻፍከው ግነት ቢኖርበትም መሰረታዊ ነጥቡ ያስማማል ) እስቲ ስለ ብጻይ መለስም ትንሽ ህሊናህ የፈቀደልህን ያህል (ህሊናህ እና ሆድህ ሲከሻከሹ ይታየኛል ) ትንትን ::

አንዱ ትግሬ ሾፌር አሉ መለስ ዜናዊ ባይኖር እኮ ኖሮ በእውነት ይቺ ሀገር ምን ይውጣት ነበር ብሎ አለቀሰ አሉ ስለ መለስ ሲያወራ .. Laughing ብጻይ መለስ መለኮታዊ እንደሆነ የሚያስብም አለ አሉ (ጥራዝ ነጠቅነቱን የምናውቀው እኔና አንድየ ነን ) :: የጨናዊ ፎቶ በቁልፍ መያዣ ላይ በየታክሲው ውህጥ እና በሌሎችም ቦታዎች የመለጠፉን ነግር ምን ትላለህ Question በየፕሬስ ኮንፈረንሱ ህዝብ እና የፖለቲካ ሰዎችን የሚሳደበውን ነገር ምን ትለዋለህ :: ኢትዮጵያ መለስ ዜናዊ ከሌለ እክል ይገጥማታል እስከሚባል ድረስ ተደርሷል ...ልክ ያንተ ጓደኞች እንዳረጉህ ( አንድ አንተ የኮሌጂ ተማሪ ተገኝተህ ) መለስም ደደቢት ከተሰበሰበው ሰው አንተ ትሻላለህ እየተባለ እዚህ ደርሶ ነው መስል ... የእንቁራሪት እብጠት ያበጠው :: እስቲ ስለ እብጠት እና ስለ ተከበሩ ጨናዊ የምትለውን እንስማ (ለዛሬ እስቲ ህሊናህን አትጎትተው ) እውነቱን ተናገር ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ጠይና ይስጥልኝ የተከበሩ አንባቢ :: እቺ ቤት ርቃ ርቃ ወደ ኌላ ሄዳ ነበር ...በካቦ ጎትቼ ወዲህ ይዣት መጣሁ ....ሀሳብ ጠፍቶ ሳይሆን ጊዜ በብር የሚመነዘርበት አለም እየኖርን ፋታ ጠፍቶ ነው ችላ የተባለችው ...::
ዛሬ የታዘብኩትን ላዋይዎ ... ባለፈው እንዳልኩዎት ትዝብቴን በብእር ቀርቼ ( መቅራት ) ካላስቀመጥኩት የተናል :: ነገ የራሱ የሆነ ሌላ ግራሞትን ትዝብትን ይዞ ይመጣል :: ህይወት የዐጋጣሚዎች ስብስብ ብቻ ሳትሆን የትዝብትና የግርምት ድምርምር ውጤት ናት ብልዎት ትክክል ይሆን ? ብቻ እኔ የመሰለኝ ነው ...ለዛም ይሆናል ቅዱሱ መጽሀፍ ለነገ አትጨነቅ ነገ የራሱ ጭንቀት ... የራሱ የሆነ ሁከት አለው የሚለው ...እውነት እኮ ነው ምን ይታወቃል ነገ የሚሆነው ..! የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ ...ሀይ ስኩል የነበሩ ጔደኞቼ የሚሰጡኝ አክብሮት ነበር :: ታዲያ እኔ እቺን ነገር "ሴንስ " ማድረግ ጀምሬአልሁ በነገራችን ላይ በዚች ቃል አንዱ ፍንድቅድቅ በዚህ አባባሌ ሰሞኑን ሲፈነድቅ ነበር :: ሞኝ ተረቱ አልቆ ከተነገረ በኈላ ሰው ሁሉ ስቆ ሲጨርስ እሱ መሳቅ ይጀምራል ይሉኝ ነበር ...መምህሬ ይሄይስ :: Very Happy እና ወደ ጉዳዬ ልውሰድዎና ሻይ ቤትም ሆነ አንዳንድ ቦታም ከነዚህ ጔደኞቼ ጋር ሆኜ መታየትን እመርጣለሁ ..አርቲ ቡርቲውን ስናወራ አንዳንች ሌላችንን ባናከብርም ቁም ነገር ያለው ነገር ሲጀመር ግን ለኔ የሚሰጠኝ ለየት ያለ ክብር አለ :: ቀስ በቀስ ጫጫታው በረድ ሲል ይታወቀኛል እንደ ቀረበልን በራድ ሻይ አይነት :: ይቺ ነገር የልብ ልብ ሰጠችኝ :: ኩራትም ድፍረትም ወኔም ፈጠረችልኝ ;; ታዱያ ይሄን አልጠላሁትም :: እንደውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደድኩት መጣሁ ...ከበፊቱ የተሻልኩ ሆኘ ለመገኘት አዲስ ነገር ይዤ በየሳምንቱ ብቅ ማለትን አዘወተርኩ :: ቀስ እያልኩም ራሴን በነሱ ውስጥ ማየት ጀመርኩ :: አስተሳሰቤና አእምሮዬ በነሱ ተቀረጸ :: ምን አለፍችሁ የራሴ ሳልሆን የነሱ መሆን ጀመርኩ :: አዲስ ነእር ይዤ ብቅ ስለ የሻይ ፌሽታውም የዛኑ ያህል እየበረከተልኝ መጣ :: ይሄ ነገር ግን የኌላ ኌላ ችግር ይዞ አስከተለ :: እነሱ ከሚሰጡኝ አስተያየትና ግምት በመነሳት ሁሉንም ነገር አውቃለሁ የሚል የንቁራሪት አይነት እብጠት ውስጤ ተጸነሰ :: በተለይ አንደኛው ልጅ ሲሸረድደኝ ይሁን ከምሩ እስካሁን አላውቅም ( እምበርሀን ብቻ ናት የምታውቀው ) ምን አለኝ ...አንቺ እኮ መጽሀፍ ላይ ስምሽ የለም እንጂ አባቴ ይሙት ፈላስፋ እኮ ነሽ ...ብሎኛል :: Very Happy ዛሬ አብሮ አደግ ጔደኛዬ በህይወት የለም :: ቢኖር ኖሮ በጠየኩት ነበር :: እንደዚህ አይነት አስትያየቶች አሉታዊም አንቱታዊም ገጽታዎች አሏቸው :: ፈረንጆች "ፕሮስ አንድ ኮንስ " ይሏቸዋል ..አስማታዊ ትርጉም :: ጥሩው መልኩ ተደማጭ ለመሆን በየጊዜው አርስትን ለማዘጋጀት ማንበብ አዳዲስ ነገርን መፈላለግ መጠየቅን ስለሚሻ እግረ መንገዱንም የእውቀትን አድማስ ያሰፋል :: መጥፎው መልኩ ደሞ ራስን አዋቂና ሊቅ አድሮጎ የማየት ሌላውን ወደ ታች የመመልከት ከኔ በላይ ማንም የለም አይነት ስሜትና ወደ ላይ የመንጠራራትን አባዜ ይፈጥራል :: በዚህ አይነት ህብረተስብ ውስጥ ኖረውና አድገው አካባቢአቸው ከፈጠራቸው ትንሽ ኩሬ ውስጥ ወጥተው ትልቁ ውቅያኖስ ዘው ብለው ሶቶ መሪና የገቡ አሉ :: "ካሊቢሬት " ሳይደረጉ :: "ካሊቢሬት " = ሳይጠረቡ :: አሁንም አስማታዊ ትርጉም :: እነዚህ ሰዎች ታዲያ በትልቁ ባህር ውስጥ የሚኖሩት ኑሮ ሰላም ያለው አይደለም :: ያኔ በትንሿ ምንጭ ውስጥ እያሉ ተሰሚ እንጂ ሰሚ ስላልነበሩ አውሪ እንጂ አድማጭ ሆነው ስለማያውቁ ሌላው በሰላም ሲዋኝ እነሱ ይደፈቃሉ :: ሲመቻቸውም ይደፍቃሉ :: ውድ አንባቢዬ ሆይ ይሄ ሊሆን የሚችል ክስተት ነው :: ባህሪያችንን የሚወስነው የየኖርንበ ማህበረስብ ነው :: በርግጥ ለመሰራታዊው ሰዋዊ ባህሪያት ቤተሰቦቻችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ :: ለማህበራዊ ግንኙነት ግን የተማርንበት ትምህርት ቤት , የህይወት ልምዳችን , ያለፍንበት ጉዞ , ጕደኞቻችን ለኛ ያላቸው አመላከከት እኛ ለነሱ የምንሰጠው አስተያየት .. አሁን ለምንኖርበት ኑሮ ተዋጽኦች ናቸው :: ትምህርት ብቻውን ማንነትን አይቀርጽም :: ባለ ድግሪ ሆኖ ንፍጣም አለ :: ሳይማር ደሞ ትሁት , መልካም ብሩህ አስተሳሰብ ያለው በማህበራዊ ህይወት ውስጥ ከሰዎች ጋር መኖር ምን ማለት እንደሆነ በትክክል የገባው አለ :: መማር ማለት ራስን መግዛት ነው አጉራ ዘለልነት አይደለም :: ኮለኔል መንግስቱ /ማርያም ስልጣን ላይ ሲወጡ ዐገር ወዳድ ለውጥ ወዳድና እድገት ለማምጣት ቆርጠው የተነሱ የሌሎችን ሀሳብ በጽሞና የሚያደምጡ ናቸው ይባል ነበር :: ትንሽ ቆይቶ ግን እርሶ የኢትዮጵያ ብርሀን , የኢትዮጵያ ሻማ የኢትዮጵያ ጧፍ , የኢትዮጵያ ነዶ , የኢትዮጵያ ስንደዶ , የኢትዮጵያ ጥቁር አልማዝ እንዲሁም ኢንዲሚክ ወፍ ነዎት የሚሉ ሰዎች በዙሪያቸው በረከቱ :: ይባስ ብሎ ከጎአድ መንግሱት አመራር ጋር ወደፊት የሚባል መፈክርና ጔድ መንግስቱ መንግስት ናቸው የሚል መፈክር ባንዱ ካድሬአቸው ከተፈጠረ በኌላ መንጌ አንድ አይን ጠፉ :: ከዛን ጊዜ በኌላ ገበሬዎች ሄደው ዘንድሮ ምን ማምረት እንዳለባቸው መመሪያ ከሰጡ በሚቀጥለው የምርት ዘመን እሳቸው የጠቀሱት የእህል አይነት የአገሪቱን ጎተራ ይሞላል ...ጂኦሎጂስቶችን ምን አይነት "ኦር " ማውጣት አንዳለባቸው ከነገሩአቸው ርብርቡ ሁሉ እዛ ላይ ይሆናል :: አንድ ሰሞንማ ለዶክተሮች እንዴት ማከም እንዳለባቸው ዎርክሾፕ ሰጥተው ነበር ይባላል . Very Happy ነው እንግዲህ "ኢንዲሚክ ወፍ የተባለላቸው መንጌን እንደ ወፍ ካገር በረው እንዲጠፉ ያደረጋቸው :: እና እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይሄ ጥፋት የመንጌ ብቻ አይደለም ... በዙሪያቸው ያሉ ስብስቦች ለምንጌ " ሱፐርይርርና አሮጋንት ፐርሰናሊቲ "መፈጠር መዋጮ አድረገዋል :: ሰው ናቱራል ከሆነው እሱነቱ ወጥቶ ሰው ሰራሽ ሰው ሲሆን ራሱም ችግር ላይ ወድቆ ለሌላውም ችግር ይሆናል :: በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሳጥናኤል መልከ -መልካም እንደነበር እንደውም ሉሲፈር የሚባል ስም እንዳለው ከእግዛብሄር ዋና መላክቶች ሚካኤልና ገብሬል በላይም እንደነበር የእጊዚአብሄር ቃል ያስተምራል :: እንዳልኩት ሉሲፈር ቆንጆ ነበር :: አካባቢውን ዞር ዞር ብሎ ሲያይ በሱ አምሳል የተፈጠሩት በሙሉ እንደሱ ውብ መስለው አልታይህ አሉት :: እናም በልቡ ውስጥ ትእቢት ተጸነሰ :: ታዲያ የዚህ ትእቢት መጨረሻው 7ኛው ሰማይ ወደ ምድር መወረውር ሆነ :: ይሀው እሱ ምድር ላይ በመሆኑ እኛም ሁላችን መከራ እናያለን :: እሱም የዚህ ትልቅ ውቅያኖስ አካል ነውና :: ትእቢት መጥፎ ነው ለማንም አልበጀ ..ለሉሲፈርም አልሆነው ..የትቢት ትንሽም የለውም :: ሳምቡሳ ወይም ቦርዴ ጠላ የፈጠረውም ትእቢትም ሆነ የሉስፈርም ትእቢት መጨረሻቸው ወይም መድረሻቸው አንድ ነው ... እንጦርጦስ :: ቃለ ህይወት ያሰማልን ...መልካም ሆሳህና ይሁንልዎ ::

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 12, 13, 14  Next
Page 2 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia