View previous topic :: View next topic
Author
Message
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sat Mar 26, 2011 12:07 am Post subject: ሡልጣን ውይይቱ ተጀምሯል !
ሰላም ሡልጣን :-
ውይይቱን በዚያኛው ርእስ ሥር ከመቀጠል አዲስ ክፍል መክፈት አስፈላጊ መስሎ ታይቶኛል ::ታዲያ አንተም እንዳልከው በተቻለ መጠን ሥርዓት ባለው መልክ ቢካሄድ ጥሩ ነው ::ለዚህም በመጀመርያ በኔ በኩል ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለሁ ::አንተም እንዲሁ ታደርግና በውይይቱ አካሄድ ላይ የማንስማማ ከሆነ ሳይጀመር ይቆማል ማለት ነው ::
የኔ ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው
1)የምንወያየው በመፅሐፍ ቅዱስና በቑርኣን ላይ ብቻ ነው ::ይህም ማለት በሰዎች የተፃፉት ገድላት ;ድርሳናት ;መልክአት ወዘተ ...በኢስላምም በኩል ሐዲስ ወይም ሌሎች መፃሕፍት አይጠቀሱም ::ግለሰቦችም በዋቢነት አይጠቀሱም ::ማለትም እኔ አባድር ;የባሌው ሼህ ሑሤን ;አብዱል ቃዲር ጂላሌ ወዘተ ... እንዲህ ብለው ነበር ስለማልል አንተም እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወዘተ ውይይቱ ውስጥ አታስገባም ::
2)አንተም እንደምታውቀው መፅሐፍ ቅዱስ መጀመርያ የተፃፈው በዕብራይስጥ በአራማይክና በግሪክ ቋንቋዎች ነው ::የአማርኛው የትርጉም ትርጉም ነው ::ያም ሆኖ ግን በእኔ በኩል ከመፅሐፍ ቅዱስ ስጠቅስ የምጠቀመው በ 1980ዓ .ም . የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማኅበር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ያሳተመውን (በተለምዶ ሰማንያ አሃዱ የሚባለው ) ብቻ ነው የምጠቅሰው አንተም ከመፅሐፍ ቅዱስ የምትጠቅስ ከሆነ ይህንኑ እትም ብትጠቀም መልካም ነው ::
3)በኛ ውይይት መሐል ጣልቃ ገብተው ለመረበሽ የሚሞክሩ እንደሚኖሩ ሁለታችንም ካለን የዋርካ ልምድ የምናውቀው ነው ::ስለሆነም ለነዚህ ሰዎች መልስ አንሰጥም ::
4)በመሠረቱ እኔ ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ እውነት ይወስዳሉ የሚለውን አመለካከት አልቀበልም ::ትክክለኛው የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ክርስትና ሃይማኖት ብቻ ነው ብዬ ነው የማምነው ::አንተም እስልምናን ብቻ ነው እውነተኛ እንደምትል አውቃለሁ ::ሆኖም ግን አስፈላጊ ያልሆኑ ዘለፋዎች ከሁለታችንም እንደማይሰነዘሩ ተስፋ አድርጋለሁ ::
5)እኔ ብዙ ጊዜ week end ላይ ነው ዋርካ የምገባው ::በዚህም ምክንያት መልስ ሳልሰጥ ልቆይ እችላለሁ ::
6)ከዚህ በፊት ሁለታችንም ዋርካ ላይ የፃፍነውን እያነሳን ጊዜ ባናባክን ጥሩ ነው ::አይቻልም ማለት ግን አይደለም ::
እንግዲህ ሡልጣን የኔ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተስማሙህ ውይይቱ እዚህ ላይ ያቆማል ማለት ነው ::እስቲ ያንተን ደግሞ አቅርብና ልየው !
በተረፈ ከአንተ ቀድሞ ሌላ ሰው መልስ እንደሚፅፍ እርግጠኛ ነኝ :: _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Sat Mar 26, 2011 7:18 pm Post subject: Re: ሡልጣን ውይይቱ ተጀምሯል !
ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ሡልጣን :-
ውይይቱን በዚያኛው ርእስ ሥር ከመቀጠል አዲስ ክፍል መክፈት አስፈላጊ መስሎ ታይቶኛል ::ታዲያ አንተም እንዳልከው በተቻለ መጠን ሥርዓት ባለው መልክ ቢካሄድ ጥሩ ነው ::ለዚህም በመጀመርያ በኔ በኩል ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጣለሁ ::አንተም እንዲሁ ታደርግና በውይይቱ አካሄድ ላይ የማንስማማ ከሆነ ሳይጀመር ይቆማል ማለት ነው ::
የኔ ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው
1)የምንወያየው በመፅሐፍ ቅዱስና በቑርኣን ላይ ብቻ ነው ::ይህም ማለት በሰዎች የተፃፉት ገድላት ;ድርሳናት ;መልክአት ወዘተ ...በኢስላምም በኩል ሐዲስ ወይም ሌሎች መፃሕፍት አይጠቀሱም ::ግለሰቦችም በዋቢነት አይጠቀሱም ::ማለትም እኔ አባድር ;የባሌው ሼህ ሑሤን ;አብዱል ቃዲር ጂላሌ ወዘተ ... እንዲህ ብለው ነበር ስለማልል አንተም እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወዘተ ውይይቱ ውስጥ አታስገባም ::
2)አንተም እንደምታውቀው መፅሐፍ ቅዱስ መጀመርያ የተፃፈው በዕብራይስጥ በአራማይክና በግሪክ ቋንቋዎች ነው ::የአማርኛው የትርጉም ትርጉም ነው ::ያም ሆኖ ግን በእኔ በኩል ከመፅሐፍ ቅዱስ ስጠቅስ የምጠቀመው በ 1980ዓ .ም . የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማኅበር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ያሳተመውን (በተለምዶ ሰማንያ አሃዱ የሚባለው ) ብቻ ነው የምጠቅሰው አንተም ከመፅሐፍ ቅዱስ የምትጠቅስ ከሆነ ይህንኑ እትም ብትጠቀም መልካም ነው ::
3)በኛ ውይይት መሐል ጣልቃ ገብተው ለመረበሽ የሚሞክሩ እንደሚኖሩ ሁለታችንም ካለን የዋርካ ልምድ የምናውቀው ነው ::ስለሆነም ለነዚህ ሰዎች መልስ አንሰጥም ::
4)በመሠረቱ እኔ ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ እውነት ይወስዳሉ የሚለውን አመለካከት አልቀበልም ::ትክክለኛው የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ክርስትና ሃይማኖት ብቻ ነው ብዬ ነው የማምነው ::አንተም እስልምናን ብቻ ነው እውነተኛ እንደምትል አውቃለሁ ::ሆኖም ግን አስፈላጊ ያልሆኑ ዘለፋዎች ከሁለታችንም እንደማይሰነዘሩ ተስፋ አድርጋለሁ ::
5)እኔ ብዙ ጊዜ week end ላይ ነው ዋርካ የምገባው ::በዚህም ምክንያት መልስ ሳልሰጥ ልቆይ እችላለሁ ::
6)ከዚህ በፊት ሁለታችንም ዋርካ ላይ የፃፍነውን እያነሳን ጊዜ ባናባክን ጥሩ ነው ::አይቻልም ማለት ግን አይደለም ::
እንግዲህ ሡልጣን የኔ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተስማሙህ ውይይቱ እዚህ ላይ ያቆማል ማለት ነው ::እስቲ ያንተን ደግሞ አቅርብና ልየው !
በተረፈ ከአንተ ቀድሞ ሌላ ሰው መልስ እንደሚፅፍ እርግጠኛ ነኝ ::
በቅድመ ሁኔታው ተስማምቻለሁ
እኔ ካንተ የምፈልገውን በሚቀጥለው እገልጻለሁ _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Sat Mar 26, 2011 7:30 pm Post subject: የኔ መስፈርት
የኔ መስፈርት
ልዩነትን ማክበር
ማስረጃየ ካላሳመነህ ወይም ማስረጃህ ካላሳመነኝ ወደሚቀጥለው ውይይት እንሄዳለን ልዩነታችንን በማክበር ::
አላማችን እውነታ ነው ብለን ያመንንበትን ነገር መግለጽ እንጅ ማስገደድ አይደለምና !
የ እስልምና ሀይማኖት መመሪያ በዋነኝነት ቁርአን ሲሆን ማብራሪያው ደግሞ ሀዲስ የሚባለው ነብያዊ ቃል ነው ::
ይህ ለኢንፎርሜሽን ያክል ሲሆን ለውይይታችን ዋቢ አድርጌ አስፈላጊ ሲሆን ለማብራሪያ ሀዲስ እንድጠቀም ብትፈቅድልኝ ደስ ይለኛል :ይህ ከሆነ ከቁርአን እና ከሀዲስ ውጭ ማስረጃ አላቀርብም :: ውይይታችን እጥር ምጥን እንዲል ማለቴ ነው ::
ሀዲስ መጥቀስ አያስፈልግም ካልከኝ ውይይቱ እንዲቀጥል ካለኝ ፍላጎት አንጻር ቁርአንን በመጥቀስ እንወያያለን ::
በዋነኝነት
የሀይማኖታችን መመሪያ ግን ቁርአን እና ሀዲስ መሆኑን አትዘንጋ !!
ከተስማማን የመጀመሪያውን የጥያቄ እድል ለአንተ ሰጥቻለሁ
ከምስጋና ጋር _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sat Mar 26, 2011 11:13 pm Post subject: Re: የኔ መስፈርት
ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው : የኔ መስፈርት
ልዩነትን ማክበር
ማስረጃየ ካላሳመነህ ወይም ማስረጃህ ካላሳመነኝ ወደሚቀጥለው ውይይት እንሄዳለን ልዩነታችንን በማክበር ::
አላማችን እውነታ ነው ብለን ያመንንበትን ነገር መግለጽ እንጅ ማስገደድ አይደለምና !
የ እስልምና ሀይማኖት መመሪያ በዋነኝነት ቁርአን ሲሆን ማብራሪያው ደግሞ ሀዲስ የሚባለው ነብያዊ ቃል ነው ::
ይህ ለኢንፎርሜሽን ያክል ሲሆን ለውይይታችን ዋቢ አድርጌ
አስፈላጊ ሲሆን ለማብራሪያ ሀዲስ እንድጠቀም ብትፈቅድልኝ ደስ ይለኛል :ይህ ከሆነ ከቁርአን እና ከሀዲስ ውጭ ማስረጃ አላቀርብም :: ውይይታችን እጥር ምጥን እንዲል ማለቴ ነው ::
ሀዲስ መጥቀስ አያስፈልግም ካልከኝ ውይይቱ እንዲቀጥል ካለኝ ፍላጎት አንጻር ቁርአንን በመጥቀስ እንወያያለን ::
በዋነኝነት
የሀይማኖታችን መመሪያ ግን ቁርአን እና ሀዲስ መሆኑን አትዘንጋ !!
ከተስማማን የመጀመሪያውን የጥያቄ እድል ለአንተ ሰጥቻለሁ
ከምስጋና ጋር
በድጋሚ ሰላም እያልኩ :-
የአንተም መሥፈርቶች ውይይቱ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ስላልሆኑ የማልቀበልበት ምክንያት አይኖርም ::ሐዲስን በሚመለከት ግን ችግር ያለ ይመስለኛል ::ምክንያቱም ቑርኣንን እንጂ ሐዲስን የአላህ ቃል ነው ብለህ ስለማታምን ለኢስላም እውነተኛነት ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ ምን ያህል ሊጠቅም ይችላል '?ያም ሆነ ይህ ግን ይጠቅማል ብለህ ከገመትክ ውይይቱን ላለመጀመር ምክንያት አይሆንም ::
በተረፈ ጥያቄውን እንድጀምር ቅድሚያ ስለሰጠኸኝ ለመግቢያ የሚከተሉትን አቀርባለሁ ::
1)ባንተ አመለካከት ክርስቲያኖች ካፊር ናቸው ?
2)አንድ ሙስሊም ክርስትናን መቀበል ይፈቀድለታል ?
3)ዓረብኛ ከሌሎች ቋንቋዎች የተለየ ክብር አለው ብለህ ታምናለህ ?
4)በኢስላም አንድ ሰው ራሱን ቢገድል (suicide ቢያደርግ ) ምን ፍርድ ይጠብቀዋል ?
5) ኢትዮጵያ (ሐበሽ ) በኢስላም ባለንበት ዘመንም በነቢዩ መሐመድ የተነገረላት ልዩ ሥፍራ አላት ?
እንግዲህ ለጊዜው በቂ ይመስለኛል ::
በቸር ይግጠመን _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Sun Mar 27, 2011 7:41 am Post subject: Re: የኔ መስፈርት
[quote="ዘርዐይ ደረስ "] ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው : የኔ መስፈርት
ልዩነትን ማክበር
ማስረጃየ ካላሳመነህ ወይም ማስረጃህ ካላሳመነኝ ወደሚቀጥለው ውይይት እንሄዳለን ልዩነታችንን በማክበር ::
አላማችን እውነታ ነው ብለን ያመንንበትን ነገር መግለጽ እንጅ ማስገደድ አይደለምና !
የ እስልምና ሀይማኖት መመሪያ በዋነኝነት ቁርአን ሲሆን ማብራሪያው ደግሞ ሀዲስ የሚባለው ነብያዊ ቃል ነው ::
ይህ ለኢንፎርሜሽን ያክል ሲሆን ለውይይታችን ዋቢ አድርጌ
አስፈላጊ ሲሆን ለማብራሪያ ሀዲስ እንድጠቀም ብትፈቅድልኝ ደስ ይለኛል :ይህ ከሆነ ከቁርአን እና ከሀዲስ ውጭ ማስረጃ አላቀርብም :: ውይይታችን እጥር ምጥን እንዲል ማለቴ ነው ::
ሀዲስ መጥቀስ አያስፈልግም ካልከኝ ውይይቱ እንዲቀጥል ካለኝ ፍላጎት አንጻር ቁርአንን በመጥቀስ እንወያያለን ::
በዋነኝነት
የሀይማኖታችን መመሪያ ግን ቁርአን እና ሀዲስ መሆኑን አትዘንጋ !!
ከተስማማን የመጀመሪያውን የጥያቄ እድል ለአንተ ሰጥቻለሁ
ከምስጋና ጋር
በድጋሚ ሰላም እያልኩ :-
የአንተም መሥፈርቶች ውይይቱ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ስላልሆኑ የማልቀበልበት ምክንያት አይኖርም ::ሐዲስን በሚመለከት ግን ችግር ያለ ይመስለኛል ::ምክንያቱም ቑርኣንን እንጂ ሐዲስን የአላህ ቃል ነው ብለህ ስለማታምን ለኢስላም እውነተኛነት ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ ምን ያህል ሊጠቅም ይችላል '?ያም ሆነ ይህ ግን ይጠቅማል ብለህ ከገመትክ ውይይቱን ላለመጀመር ምክንያት አይሆንም ::
በተረፈ ጥያቄውን እንድጀምር ቅድሚያ ስለሰጠኸኝ ለመግቢያ የሚከተሉትን አቀርባለሁ ::
Quote: 1)ባንተ አመለካከት ክርስቲያኖች ካፊር ናቸው ?
እንደምታውቀው እምነቴ ኢስላም ነው ስለዚህ በአላህ አንድነት እና በነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም )
የመጨረሻ ነብይነት የማያምን የ ኢሳን (የ እየሱስን ነብይነት )የማያምን ካፊር ነው ::ይህ በቁርአን በግልጽ ተጠቅሷል ::ካፊር ብሎ የጠራቸው ደግሞ ፈጣሪ ነው ::ለምን እሱ ባወረደው መመሪያ እና ነብይ አላምንም ብለው ስለካዱ ካፊር የሚል ስም ተስጥቷቸዋል ::
ለምሳሌ ቁርአን '' ለቀድ ከፈረለዚነ ቋሉ ኢንነሏሀ ሁዎል መሲሁብኑ መርየም '' እነዚያ ኢሳ የመርየም ልጅ (እየሱስ )ራሱ ጌታ ነው የሚሉ በ እርግጥ ካዱ (ከፈሩ )ይላል ::
በሌላ የቁርአን አንቀጽ ደግሞ :-ለቀድ ከፈረለዚነ ቋሉ ኢንነሏሀ ሳሊሱ ሰላሰህ (እነዚያ አላህ 3ቱ ስላሴ )ነው ያሉ ሰዎች በ እርግጥ ካዱ (ከፈሩ ወይም ካፊር ሆኑ ) በማለት ቁርአን ይጠቅሳል ::ስለዚህ ካፊር ደግሞ እየሱስ ጌታ ነው ወይም አምላክ ሶስት ነው ብሎ እያመነ ከሞተ ለጀሀነም ነው ::በህይወት እያለ ተጸጽቶ ወደ ኢስላም እስካልተመለሰ ድረስ ::
Quote: 2)አንድ ሙስሊም ክርስትናን መቀበል ይፈቀድለታል ?
አንድ ሙስሊም ክርስትናን መቀበል አይፈቀድለትም ::ምክንያቱም በኢስላም አስተምሮ መሰረት ከ እምነት ወደ ክህደት መሄድ ወንጀል ነው እና :: ቅጣቱም የከፋ ነው ::ነገር ግን አንድ ክርስቲያን የነበረ እስልምናን እንዲቀበል አይገደድም ::ከሙስሊሞች ጋር እስካልተዋጋ ድረስ ::
Quote: 3)ዓረብኛ ከሌሎች ቋንቋዎች የተለየ ክብር አለው ብለህ ታምናለህ ?
አዎ !ምክንያቱም የታላቁ እና ተአምረኛው ቁርአን ቋንቋ ስለሆነ ከሁሉም ቋንቋዎች ብልጫ አለው ::ለዚህም ማስረጃ አለኝ ::አረበኛ በተፈጥሮ ገር ነው አረበኛ ተናጋሪ ያልሆነ ሁሉ በቀላሉ ሊማር እና ቁርአን መቅራት ይችላል ::
በአገላለጽ ችሎታው ማግኔቲክ ሀይል አለው ::ብዙ ነገሮች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠቀሱ ይችላሉ ::
Quote: 4)በኢስላም አንድ ሰው ራሱን ቢገድል (suicide ቢያደርግ ) ምን ፍርድ ይጠብቀዋል ?
አንድ ሰው ኑሮ መረረኝ ብሎ ራሱን ቢያጠፋ በኢስላም ታላቅ ወንጀል ነው ::ለገሀነም ነው ::
Quote: 5) ኢትዮጵያ (ሐበሽ ) በኢስላም ባለንበት ዘመንም በነቢዩ መሐመድ የተነገረላት ልዩ ሥፍራ አላት ?
1ኛ አዎ ! እርሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት የሆነ ንጉስ አለ እና ወደዚያ ተሰደዱ ብለው ተከታዮቻቸውን ወደ ሀበሻ የ እውነት ሀገር ልከው ንጉሱም በሰላም ተቀብሏቸው ለብዙ አመታት በደስታ ኖረዋል ::ሀገራቸው ሲረጋጋም በሰላም ተመልሰዋል ::
2ኛ ሀበሾች ካልወጉዋችሁ አትውጉዋቸው ብለው አሳስበዋል ::
3ኛ ሀበሾች ወደ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) በሄዱ ጊዜ እነሱን በማክበር ቆመው አስተናግደዋል
4ኛ ከ ቅዱስ ቁርአን የተወሰነ አንቀጽ በተነበበላቸው ጊዜ ነጃሽ (በወቅቱ የነበረው ንጉስ እና ቀሳውስት በተመስጦ ማልቀሳቸውን ቁርአን ይናገራል
4ኛ ከ እናታቸው ሞት በኍላ ያሳደገቻቸው ሀሊማ የምትባል ሀበሻ ስለነበረች እና እናቴ ብለው ስለሚጠሯት ይህም ለሀበሻ ልዩ ክብር አስገኝቷል
5ኛ በኢስላም የመጀመሪያው አዛን አድራጊ ቢላል ሀበሻ በመሆኑ ይህም ልዩ ክብር አሰጥቶናል
6ኛ ሙስሊም ስደተኞችን ያስጠጋው ንጉስ ሰልሞ ስለሞተ መሞቱ እንደተነገራቸው በነጋሽ ላይሰላተል ጋይብ (የ ርቀት ሰላት ሰግደውበታል )ሰላተል ጋይብ የተጀመረም በነጋሽ ነው ::
ሌሎችም ይኖራሉ ...ላለማርዘም ፈልጌ ነው ::
ከዚህ በኍላ እኔ ደግሞ መጠየቅ እችላለሁ ወይስ በኔ መልስ ላይ አስተያየት መስጠት ትፈልጋለህ ?
እንደ አካሄድ የተሻለው የኔን መልስ እስከምታብላላው ድረስ እኔ ብጠይቅህ ምን ይመስልሀል ?
ከምስጋና ጋር _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sun Mar 27, 2011 11:05 pm Post subject:
ሰላም :-
1ኛና 3ኛ ያሉ ጥያቄዎቼን በአጥጋቢ ሁኔታ መልሰህልኛል ::ሌሎቹ ላይ ግን እንደገና መጠየቅ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ ::
2ኛ )ወደ ክርስትያንንት የተቀየረውን ሙስሊምይጠብቀዋል ያልከው የከፋ ቅጣት በዚህ ዓለምም ነው ወዪስ በወዲያኛው ?(ዱንያና አኺራ )
4ኛ )እዚህ ላይ ማወቅ የፈለግኩት ኑሮ መረረኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋውን ብቻ ሳይሆን ራሱን ለመገደል ያነሳሳው ምክንያት ሌላም ሊሆን ይችላል ::
5ኛ )እዚህ ላይ እኔ ነኝ መሰለኝ ጥያቄውን ግልፅ ያላደረግኩት !አንተ የጠቀስካቸውን ታርኮች እኔም አውቃቸዋለሁ ::ንጉሥ አርማህ ሰልሞ ነበር ካልከው በቀር ሌሎቹ ላይ ቅሬታ የለኝም ::የኔ ጥያቄ ግን በአሁኑ ዘመን ያሉ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ያኔ በኢስላም የነበራትን ክብር ይሰጧታል ወይ ?ለማለት ነበር ::
በል እነዚህን ጥያቄዎች አብራራልኝና የአንተን ጥያቄዎች ማስከተል ትችላለህ :: _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Mon Mar 28, 2011 7:43 am Post subject:
ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም :-
1ኛና 3ኛ ያሉ ጥያቄዎቼን በአጥጋቢ ሁኔታ መልሰህልኛል ::ሌሎቹ ላይ ግን እንደገና መጠየቅ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ ::
ለመመለስ እሞክራልሁ ካላወቅኩ ደግሞ ጠይቄ እመጣለሁ ::
Quote: 2ኛ )ወደ ክርስትያንንት የተቀየረውን ሙስሊም ይጠብቀዋል ያልከው የከፋ ቅጣት በዚህ ዓለምም ነው ወዪስ በወዲያኛው ?(ዱንያና አኺራ )
ሙስሊም ሆኖ ሳለ ኢስላምን አልፈልግም ብሎ ወደሌላ እምነት የተመለሰ ሰው ቅጣቱ በዚህ ምድርም ይሁን በትንሳኤ ቀን አይቀርለትም ::
እዚህ ጋ መታወቅ ያለበት ጉዳይ አላህ ይህን ኢስላም ለሰው ልጆች ይበጅ ዘንድ ሙሉ አድርጎታል ::ከምንም እንከን የጠራ ሆኖ ሳለ ይህን የአላህ መመሪያ አልቀበልም ብሎ ወደ ክህደት እንደሚሄድ ልብ እንበል ::ይህ ሰው የፈጣሪ ባሪያ ነው ::እንኳንስ የፍጡራኖችን ሁኔታ የሚያውቀው እና ምንም ሚስጥር እሱ ዘንድ የማይደበቀው ፈጣሪ ይቅርና በባሪያ አሳዳሪ ስርዐት ጊዜ እንኳ አንድ ባሪያ አሳዳሪውን አልፈልግም ብሎ መሄድ ይችላል ?ተስማምቶ እስካልሸጠው ድረስ ጠፍቶ ቢሄድ እንኳ ታድኖ የሚወሰድበት እርምጃን ታውቀዋለህ ::
እኛ ደግሞ ወደድንም ጠላንም የፈጣሪ ባሪያዎች ነን ::ወደዚህ ምድር የመጣንበት ምክንያት እሱን ብቻ ለማምለክ ነው ::
ይህ ሰው ሙስሊም ሆኖ ሳለ ኢስላምን አልፈልግም ብሎ ወደ ክህደት ከሄደ ቅጣቱ በዚህ ምድር ሞት ነው ::ካፊር ሆኖ ከሞተ ደግሞ በትንሳኤ ቀን የሚጠብቀው ጀሀነም ነው ::ቅጣቱ ከመፈጸሙ በፊት ግን ወደ ኢስላም እንዲመለስ ይጠየቃል እምቢ ካለ ቅጣቱ ይፈጸምበታል ::
ነገር ግን ከአባት እና ከናቱ በመወራረስ ሙስሊም አይደለም ::አንብቦ እና አጥንቶ ሙስሊም መሆንም አልፈለገም ::ይህ ሰው ሙስሊሞችን እስካልተዋጋ ድረስ
እምነቱን እንዲቀይር አይገደድም ::በነገራችን ላይ የማንኛውም የሰው ዘር ተፈጥሮ ሙስሊም ነው !ቤተሰቦቹ ናቸው አይሁድ ወይም ክርስቲያን እንዲሆን የሚያደርጉት !!
Quote: 4ኛ )እዚህ ላይ ማወቅ የፈለግኩት ኑሮ መረረኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋውን ብቻ ሳይሆን ራሱን ለመገደል ያነሳሳው ምክንያት ሌላም ሊሆን ይችላል ::
ጥያቄህ ብዙም አልተብራራልኝም የተንዛዛ ሆኖ እንዳይሰለችህ በማለት ነው አሳጥሬ የመለስኩ ::
ሰው ራሱን የሚያጠፋበት ሌላ ምክንያት ምን ይኖራል ?በኑሮው ደስተኛ ባለመሆኑ እንጅ !ከቤተሰቡም ይጣላ ከስራ ባልደረቦቹ /ራሱን የሚሰቅለው ወይም መርዝ የሚጠጣው ምክንያቱ እኔ ካልኩህ አይዘልም ::
አሁንም ያልመለስኩልህ ከሆነ አብራርተህ ጠይቀኝ እመልሳለሁ ::
Quote: 5ኛ )እዚህ ላይ እኔ ነኝ መሰለኝ ጥያቄውን ግልፅ ያላደረግኩት !አንተ የጠቀስካቸውን ታርኮች እኔም አውቃቸዋለሁ ::ንጉሥ አርማህ ሰልሞ ነበር ካልከው በቀር ሌሎቹ ላይ ቅሬታ የለኝም ::የኔ ጥያቄ ግን በአሁኑ ዘመን ያሉ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ያኔ በኢስላም የነበራትን ክብር ይሰጧታል ወይ ?ለማለት ነበር ::
በአሁን ዘመን ያሉ ሙስሊሞች ኢትዮጵያ በኢስላም ያላትን ክብር ይሰጧታል ወይስ ያሰጧታል ? ብዙም ግልጽ አልሆነልኝም ::
ለማንኛውም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሀገራቸው ለኢስላም ታላቅ ባለውለታ መሆኗን ያውቃሉ ::
ሁላችንም ኢትዮጵያ እንግዳ የማክበር ባህሏ ሙስሊም ስደተኞችን ማስተናገዷንም ይጨምራል ::በሌላው አለም በነጃሽ እና በቢላል እንዲሁም ሙስሊሞችን ያስጠጋች ሀገር በመሆኗ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም በሌላው አለም ያሉ ሙስሊሞችም ያውቃሉ ::
አንዳንድ ሰዎች ኢስላም ኢትዮጵያ ውስጥ መጤ ነው ብለው ያምናሉ ::ሁሉም እምነቶች ግን ከሌላ አካባቢ በተለያየ ምክንያት የመጡ ናቸው ::አይሁድ እምነትም ይሁን ክርስትና ከሶሪያም ይምጣ ከሌላ በንግድም ይሁን በስደት ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡበት ዘመን ይለያይ እንጅ
ሁሉም እምነቶች መጤ ናቸው ::
ባይገርምህ ኢስላም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከተላኩበት መካ ከተማ 400 ኪሎሜትር የምትገኝ መዲና ሳይገባ በፊት ነው ኢትዮጵያ የገባ ..::
መታወቅ ያለበት ጉዳይ አላህ በየዘመናቱ ለኖሩ ህዝቦች የራሳቸውን መመሪያ አስይዞ ነብያት ልኮ ህዝቡ አንድ ፈጣሪን ብቻ እንዲያመልክ አድርጓል : ኦሪትን ለሙሴ ወንጌልን ለኢሳ ዘቡር (መዝሙርን )ለዳዊት ፉርቃን (ቁርአንን )ለሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ) በመስጠት ህዝባቸውን በተዋረድ በመመሪያቸው አስተዳድረዋል ::ኢሳ በወንጌል ካስተዳደረ በኍላ እንደተለመደው ወደ ቁርአን አጠቃላይ የሰው ልጅ መመሪያነት እና ወደ ነብዩ ሙሐመድ የመጨረሻ ነብይነት
በተደረሰበት ሁኔታ አይሁዶች ለምን ከአረቡ አለም ነብይ ይላካል በሚል ቅናት እውነታውን እያወቁ በነብዩ እና በቁር አን አላምንም አሉ !በመጽሀፋቸው ግን ይህ ነብይ እንደሚመጣ እና እንዲከተሉት ተጸፎ ነበር ::ክርስቲያኖች ደግሞ ባለማወቅ ወንጌልን የሙጥኝ በማለታቸው ከነብያት ወደ ነብያት በተደረገው ሽግግር ላይ በ እየሱስ አቆሙ (በመጽሀፋቸው )ሌላ ነብይ እንደሚመጣ እና የ እሱን መመሪያ እንዲከተሉት ግን ታዝዘው ነበር )
ከዚህ በኍላ ነው እንግዲህ ሙስሊም ሳይሆኑ በቁር አን እና በንብዩ ሙሐመድ ሳያምኑ በድሮ መጽሀፋቸው ያሉት (ቁር አን የመጽሀፉ ባለቤቶች ) አህለል ኪታብ ብሎ የሚጠራቸው ሰዎች ሲለሙ ተብለው አይገደዱም ::ያልኩህ ይህን ነው ::በምንም ተአምር እነሱ እምነታቸውን እንዲቀይሩ አይገደዱም ::ይህ ማለት ግን እምነታቸው ተቀባይነት አለው ማለት አይደለም ::ኢስላምን ሲዋጉ ግን
ነገሩ ይቀየራል ::ሙስሊም ሆነው እንደገና ወደ ክህደት እንመለሳለን ካሉ ደግሞ ቅጣቱ አሁንም በዚህ ምድር እና በክህደት ከሞቱ በመጨረሻው አለም ጀሀነም ይሆናሉ ::
ለምን ቢባል አላህ የመጨረሻ ነብይ አውርዶ መመሪያውም ለማንኛውም ዘመን እንዲያገለግል
ያለፈውን ህዝቦች ዜና ቁልጭ አድርጎ እየተረከ መጭው አለምንም እየተነበየ የሚገኘው እውነታው በሳይንስ ሳይቀር የተረጋገጠው ተአምረኛው ቁርአን መመሪያ አልቀበልም ብሎ ከኢስላም ሌላ ሀይማኖት የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም በመጨረሻዎ አለምም ከከሳሪዎች እንደሚሆን አላህ ደንግጓል ::ፈጣሪ የፈለገውን የመውቀሰን መብት አለውና !
ስለ ንጉስ አርማሀ መስለም ጥርጥር የለውም ::እኔ ለኢንፎርሜሽን ያክል ጨመርኩት እንጅ አንተ በዚህ ጉዳይ እንድታምን አትገደድም ::
ንጉሱ ለመስለሙ 2 ወፍራም ማስረጃዎች አሉ !
1ኛ የአለም ሙስሊሞች በሙሉ ታሪኩን ያውቃሉ ::ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከዶክተር ላፒሶ ውጭ ያሉ የሌላ እምነት ተከታዮች በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ታሪክ ሲጽፉ ወደ እምነታቸው ስለሚያዘነብሉ የተደበቁ ብዙ እውነታዎች አለ ::በትግራይ የነጃሽ ቀብር ያለውም በዚህ ምክንያት ነው ::
ዋናው ማስረጃ ግን ነብያዊ ሀዲስ ነው ::ሙስሊም ስደተኞች የመርየምን አንቀጽ ሲያነቡ ጉንጮቹ በ እንባ ራሱ :አብረው የነበሩ ቀሳውስትም አለቀሱ :;ከዚያም ነጃሽ ይህ ያነበብከው አንቀጽ እና በመጽሀፍ ቅዱስ ያለው የ እየሱስ ታሪክ ከአንድ ምንጭ ነው በማለት ሙስሊም ስደተኞች እሱ ሀገር እስካሉ ድረስ ጥበቃ እንደሚአይደርግላቸው እና ለጠላትም አሳልፎ እንደማይሰጣቸው ቃል በመግባት የቁረይሽ ካፊሮች ይዘው የመጡትን የ እጅ መንሻ (ጉቦ ) እንደመለሰ ኢስላም ዘግቦታል ::ይህ ንጉስ ሲሞት በ ክርስትና ፍታት እንደምትሉት አይነት የ እርቀት ሰላት ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰግደውበታል ::
በአለም ላይ ከንጉሶች ኢስላምን የተቀበለ የመጀምሪያው ንጉስ የሀበሻው ንጉስ ነው ::
አላስፈላጊ ማብራሪያ ውስጥ ገብቸ ከሆነ ይቅርታ !
እስከ አሁን ያለው የውይይት መንፈስ አስደስቶኛል ::ከልብ አመሰግናለሁ
Quote: በል እነዚህን ጥያቄዎች አብራራልኝና የአንተን ጥያቄዎች ማስከተል ትችላለህ ::
የኔን ጥያቄዎች ለማስከተል በመልሶቼ ላይ ያለህን አስተያየት ልስማ እና እቀጥላለሁ ::
ወገን ዘርአይ ደረስ .......
እኔ ለጥያቄ የሚያስቸኩለኝ ምንም ጉዳይ የለም እደርሳለሁ
አንድ ነገር ግን ልንገርህ ከዚህ ውይይት እኔ የምጠቀመው ታላቅ ቁም ነገር ሀይማኖቴን አውቀህ እንድታከብርልኝ እና እንድታከብረኝ እኔም ሀይማኖትህን አውቄ እንዳከብርህ እና እንዳከብርልህ በኢትዮጵያዊነታችን በሰላም እንድንኖር ከመፈለግ አንጻር ነው ::
አንድ እውነታ ልንገርህ ::
እኔ በተወለድኩባት ትንሽ ከተማ ታቦቱ የሚያልፈው በመስጊዳችን በር ነው ::ቄሶች መስጊድ አካባቢ ሲደርሱ ቆመው ይቀድሳሉ ከበሮ ይመታሉ :;እኛ ኢንጆይ እናደርጋለን እንጅ ቅሬታ የለንም ::ችግር የሚፈጠረው ከ እኛ አላዋቂዎች ወደ ነሱ ድንጋይ እንወርውር ሲሉ ከነሱም አላዋቂዎች ወደ መስጊድ ድንጋይ እንወርውር ሲሉ
እንጅ ሁሉም ሀይማኖቱን አክብሮ ቢኖር ሰላም እፈልጋለሁ ::
የሁሉም ሂሳብ የትንሳኤ ቀን ነው ! እንደ ሙስሊም እውነታውን ማመላከት እንጅ ማስገደድ አልታዘዝንም ::
የላሊበላ ውቅሮ አቢያተ ክርስቲያን ከዚያ ከቋጥኝ ድንጋይ እንደዚያ ተፈልፍሎ መሰራቱ እንደኢትዮጵያዊነቴ ለኔታሪኬ ነው ::ግብጽ በፒራሚዶቿ እንደምትኮራ እኔም በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያኖች ይህን በመስራታቸው ኩራቴ ነው ::ይህ ማለት በመጽሀፍ ቅዱስ እና በመስቀል አምናለሁ ማለት እንዳልሆነ ሁሉም ያውቃል ::
በቅርቡ ወደ ባህርዳር ለታሪካዊ ጉዞ ሄደን ጣናን ተሻግረን እኔ እና ጓደኞቼ ቤተክርስቲያኗን እና በውስጡ የነበሩትን መነኮሳት እንዲሁም በብራና እና በሌላ ማቴሪያል የተጽፉ
መጽሀፍ ቅዱስ እና ሌሎችንም ነገሮች አይተን በጉዟችን ተደስተናል ::አኩሪ ታሪካችን ነው እና !አንተ ወደ ሀረር ሄደህ የጅማ አባጅማርን ታሪክ በስጥያሉ በጥንት ጊዜ የኢስላም መገለጫ አልባሳትን እና መጽሀፍን ብትጎበኝ
የአስተሳሰብ አድማስህ ይሰፋል እንጅ የምትጎዳው ነገር የለህም ::
እኛ በኢትዮጵያ ላይ የምንፈልገው ነገር ይህ ነበር ::
ይህ ደግሞ ለማስመሰል አይደለም ::እውነታው ህሊናየ ላይ ነው ::ይቅርታ ......በተመስጦ ወደሌላ ታሪክ ገባሁ !!!!
አይ ኢትዮጵያ ....በአለም ላይ ሊኖርሽ የሚገባው ቦታ ይህ አልነበረም .....
ዳሩ ምንያደርጋል ትናንት ተርፎን እንዳላበላን መጠለያም እንዳልሰጠን በድህነት የምንታወቅ ሆነናል ::
ለዚህ ደግሞ ተጠያቂው ይህ ትውልድ ነው ::
ይህ ትውልድ አሁንም ቢሆን በራሱ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ጎጠኝነት ይታይበታል ::በተወሰነ መልኩ እንኳ ለነፍሱ ያላደረ ማህበረሰብ እጅግ አስቸጋሪ ማህበረሰብ ነው ::
ቢሰርቅ ቢያጭበረብር ....ቢገድል ...ፈሪሀ ፈጣሪ ከሌለው በማን ትገስፀዋለህ
አስረዘምኩት .....
ቸር እንገናኝ
ከብዙ ...ይቅርታ ጋር _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Wed Mar 30, 2011 11:26 am Post subject:
ሰላም ሡልጣን :-
አሁንም 5ኛው ጥይቄዬ ላይ ማብራሪያ እፈልጋለሁ ::እኔ ለማወቅ የፈለግኩት ባለንበት ዘመን ያሉት በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን ልክ በነቢዩ መሐመድ ዘመን እንደነበሩት ሰሓባዎች የተለየ ቦታ ይሰጧታል ?ወይስ እንደማንኛውም አገር ነች ? _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Wed Mar 30, 2011 1:45 pm Post subject:
ውድ ዘርአይ
በነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጊዜ ሰሀቦች ለኢትዮጵያ እንደሚሰጡት ክብር አሁን በአለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች ለኢትዮጵያ ክብር ይሰጣሉ ማለት ዘበት ነው ::
ለዚህም 2 ምክንያት ነው የማቀርብልህ
1ኛ ያ የሰሀባ ትውልድ እንቁ ትውልድ ነው :የነሱን አይነት ስ ብ እና በዚህ መድር የተላበሰ ሰው አለ ከተባለም እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው ::
ያ ትውልድ ሲወድህም ለአላህ ብሎ ነው ::ሲጠላህም ለአላህ ብሎ እንጅ በምድራዊ ጥቅም ታውሮ እንደ እኛ አንዴ ሰው አንዴ አፈር አልነበረም :;ስለዚህ እንደዚያ ትውልድ አድርጎ ኢትዮጵያን በንጽሁ መነጽር የሚያይ የለም :;ወይም እጅግ አናሳ ነው (ይህ የግሌ መላምት ነው ስህተትም ሊሆን ይችላል )
2ኛ ሀበሾች ድሮ ያለን ስም እና ክብር ተሰናብቶን ከሄደ በጣም ብዙ ዘመን አስቆጥረናል ::
በሰሀቦች ጊዜ የነበሩት ሙስሊም ሳይሆኑ እንኳ እነሱ ዘንድ ማንም የማይበደልበት ሚዛናዊ ስርአት የነበራቸው ዜጎቻችን አሁን እንደ ህልም ነው የሚታየው ::በትክክል
ፈሪሀ ፈጣሪ የነበራቸው እና እኛ በህፃንነታችን እነሱን በ እስተርጅና ያገኘናቸው ሙስሊም ያልሆኑ መልካም ጎረቤቶቻችን ከነሱ በኍላ ያለው ትውልድ ለነገሮች እና ለባህሉ ያለው አመለካከት ተቀይሮ በአሁኑ ሰአት ሙስሊምም ሆነ ክርስቲያን ጥንት ሀበሻ የነበራትን ክብር እንደያዘ ቆይቷል ለማለት አልደፍርም ::
ምክንያቱም በአሁን ጊዜ ቁጥራቸው የማይናቅ ሀበሾች በአሜሪካ እና በአውሮፓ በካሲኖ እና ዲስኮ ቤቶች በሳኡዲ አረቢያ ደግሞ አስካሪ መጠጥ አስጠማቂ እና ሻጭ በመሆን የሀገራቸውን ገጽታ በመጥፎ እንዲታይ ስላደረጉ ኢትዮጵያን በጥንቱ ገጽታዋ ትታያለች ለማለት ይከብደኛል ::
መልሴ ባያረካህ እንኳ የጥያቄውን መንፈስ አሁን ይበልጥ መረዳቴን ልገልጽልህ እወዳለሁ ::
በወዳጅነታችን እንሰንብት _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sun Apr 03, 2011 11:27 am Post subject:
ሰላም ሡልጣን :-
በቅድምያ አምስቱም ጥያቄዎቼ በአጥጋቢ ሁኔታ እንደተመለሱልኝ ስገልፅልህ በመልሶችህ ተስማምቼአለሁ ማለቴ እንዳልሆነ እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ ::በተረፈ ዛሬ ዋርካ ስገባ ያንተን ጥያቄዎች የማገኝ መስሎኝ ነበር ::ጥያቄዎችህ ገና ስላልቀረቡ የኔዎቹን ባስከትልስ ?
6)አንድ ሰው ሙስሊም ለመባል ቢያንስ ምን ምን ነገሮችን ማሟላት አለበት ?
7)በኢስላም ሴቶች የወንዶች ግማሽ አእምሮ ነው ያላቸው የሚባል አስተሳሰብ አለ ?
በኢስላም የወሊድ ቁጥጥር ማድረግ ጨርሶ የተከለከለ ነው ወይስ እንደሁኔታው ነው የሚወሰነው ?
9)ሴቶች ወንዶች ባሉበት የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር ይፈቀድላቸዋል ?
10)ጂሐድ (የጦርነት ) ለማወጅ ምን ምን ነገሮች መሞላት አለባቸው ?
በቸር ይግጠመን _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Sat Apr 09, 2011 12:48 pm Post subject:
[quote="ዘርዐይ ደረስ "]ሰላም ሡልጣን :-
በቅድምያ አምስቱም ጥያቄዎቼ በአጥጋቢ ሁኔታ እንደተመለሱልኝ ስገልፅልህ በመልሶችህ ተስማምቼአለሁ ማለቴ እንዳልሆነ እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ ::በተረፈ ዛሬ ዋርካ ስገባ ያንተን ጥያቄዎች የማገኝ መስሎኝ ነበር ::ጥያቄዎችህ ገና ስላልቀረቡ የኔዎቹን ባስከትልስ ?/[quote]
ይቻላል
ያው ዊክ ኢንድ ስለምትጎበኘኝ እኔም እስከዚያው በራሴ ሀጃ ቢዚ ልሁን ብየ ነው
Quote: 6)አንድ ሰው ሙስሊም ለመባል ቢያንስ ምን ምን ነገሮችን ማሟላት አለበት ?
አንድ ሰው ሙስሊም ለመባል ላኢላሀ ኢለላህ ሙሐመድ ረሱሉሏህ (በ እውነት የሚያመልኩት አምላክ ከላህ በስተቀር የለም ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ደግሞ የ እርሱ የመጨረሻ ነብይ ናቸው ብሎ ማመን ..ኢሳ ነብይ ነው ብሎ ማመን ሲሆን በቀን 5 ጊዜ የሚሰገደውን ሰላት ከሰገደ ሙስሊም ነው ማለት ይቻላል ::
Quote: 7)በኢስላም ሴቶች የወንዶች ግማሽ አእምሮ ነው ያላቸው የሚባል አስተሳሰብ አለ ?
ሴቶች የወንዶች ግማሽ አእምሮ አላቸው የሚል በኢስላም አላነበኩም ::ከወንዱ ያላነሰ ታላቅ ስራ ለኢስላም ያበረከቱ እናቶች እና እህቶች እንዳሉ ኢስላም አስተምሮናል ::በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ችኩሎች ስለሆኑ እና ርህራሄም በጣም ስለሚያጠቃቸው ወይም ሲቆጡ ውሳኔያቸው ቅጽበታዊ ስለሆነ እንደፍች እና አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እድሉ ለወንድ ተሰጥቷል ...
[quote] በኢስላም የወሊድ ቁጥጥር ማድረግ ጨርሶ የተከለከለ ነው ወይስ እንደሁኔታው ነው የሚወሰነው ?/[quote]
በኢስላም የሚወለደው ልጅ ለ እናቱ ህይወት አስጊ መሆኑ በታማኝ ዶክተር ከተረጋገጠ እንኳንስ ጽንስን አስቀድሞ ለመከላከል መድሀኒት መጠቀም ይቅር እና ጽንሱን ለ እናቱ ህይወት ሲባል ጽንሱን ማስወረድ የሚፈቀድበትም ኮንዲሽን ሊኖር ይችላል (ጽንሱ ወይም ብታረግዝ ለህይወቷ አስጊ መሆኑ ከታወቀ ) ከዚያ ውጭ ግን ችግርን በመፍራት ወይም ማሳደግ አልችልም በሚል ምክንያት የወሊድ መከላከያ መጠቀም አይፈቀድም ::
Quote: 9)ሴቶች ወንዶች ባሉበት የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር ይፈቀድላቸዋል ?
የሀይማኖት ትምህርት እንዳያስተምሩ የሚከለክላቸው ነገር የለም ቅድመ ሁኔታውን እስካሟሉ ድረስ :: ወንዶች በሴቶች ሴቶችም በወንዶች መፈታተን በማይፈጥር መልኩ እና የሂጃብን ስርአት በጠበቀ መልኩ ማስተማር ይችላሉ ::
ብዙ ጊዜ ግን ወንድ ምሁራን በበቂ ሁኔታ እስካሉ ድረስ ሴቶች ሴቶችን ቢያስተምሩ ይመረጣል :: እንዳልኩህ የሂጃብን ስር አት በጠበቀ ሁኔታ ወንዶች ሴቶችን ማስተማር ይችላሉ ::
Quote: 10)ጂሐድ (የጦርነት ) ለማወጅ ምን ምን ነገሮች መሞላት አለባቸው ?
መጀመሪያ ጂሀድ ማለት ምን ማለት ነው ?ጅሀድ ዝም ቢሎ የሚታወጅ ጦርነት አይደለም .ሙስሊሞች መብታቸው ሲጣስ እምነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ሲከለከሉ የሙስሊም ሀገር ሉአላዊነት ሲደፈር መንግስታት ተመካክረው የሚወስኑት ነገር ነው ::እና ጭቆናን ለመገፍተር የሚደረግ ነገር ነው ::ውደ ሩቅ አንሂድ እና እኔ ከባለበቴ ጋር እየሄድኩ ባለቤቴን ለመንጠቅ ከሚመጣ ማንኛውም ሀይል ጋር እንደ አስፈላጊነቱ መጋደሌ ጅሀድ ነው ክብሬን ወይም የቤተሰቤ ክብር እንዳይደፈር መከላከሌ ጅሀድ ነው ::ነፍሴን ከመጥፎ ለመከላከል ከራሴ ጋር የማደርገው ግብግብ ጂሀድ ነው ::በአረመኔ ባለስልጣን ፊት እውነት መናገር ጅሀድ ነው ::ጅሀድ ማለት ዝም ብሎ ሰው መግደል አይደለም ::ለዚያም ነው ቅድመ ሁኔታዎች አሉት የሚባለው ::አሁን በፍልስጤም እና በ ቺቺኒያ ግሮዝኒ የሚደረጉት ጦርነቶች ጅሀድ ናቸው
ምክንያቱም ፓለስታይኖችም መሬታቸውን ተነጥቀው መብታቸው እየተደረገ ለነፃነታቸው የሚያደርጉት ትግል ጅሀድ ነው :ጥንት አፍጋኒስታን በሩሲያ ላይ የዘመተች ጊዜ አፍጋን ያካሄዱት ትግል ጅሀድ ነው ስንት ተአምርም ታይቷል ::እና ተርምስ & ኮንዲሽንስ አለው ::እኔ ዛሬ ተነስቼ ጅሀድ ማወጅ አልችልም ::ብዙ ጊዜ ሀላፊነቱ በሀገር መሪዎች ላይ ነው ::ከሙስሊም ምሁራን ጋር በመወያየት እንደ ወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የሚታወጅ ነገር ነው ::
ያልተመለሰውን አዋቂዎችን ጠይቄ ለማብራራት ዝግጁ ነኝ ::
................... የኔ ጥያቄ ............................
1ኛ / አምላክ ሶስትም አንድም ንው የሚባል (ትሪኒቲ )
ብዙ መጽሀፍም ባንገላብጥ ሊገባኝ አልቻለም
አብ /ወልድ /መንፈስ ቅዱስ =አሀዱ አምላክ ትላላችሁ
ለመሆኑ ሶስቱ አንድ ናቸው ማለት እኩል ስልጣን አላቸው ማለት ነው ?ለምሳሌ እየሱስ ነው አምላክ ወይስ እግዜአብሄር ? እየሱስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ትላላችሁ እንዴት ?እግዜአብሄርስ ሰው ነው ወይ ?
2ኛ /አምላካችን እየሱስ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ስላለ ለ እኛ ብሎ ሞቶ ተሰቀለ የሚል እምነት አላችሁ ::
ለመሆኑ የሰው ልጆችን የማዳን ስልጣን ካለው ለምን መሞት አስፈለገ ?ስውን ከሀጢአት ለማንጻት እሱ መሞት አለበት (ጌታ ከሆነ )ወይስ ከፍላጎቱ ውጭ ተገደለ ?
ፈጣሪ እንዴት ሊሞት ይችላል ?እሱ 3 ቀን እና ሶስት ሌሊት መቃብር ውስጥ እንደቆየ ታምናላችሁ እስኪ ከመቸ ጀምሮ ?ቀናቶችን ቁጠርልኝ ..
ኤሎሄ ኤሎሄ ላማሰበቅተኒ ........ብትችል ይህችን ጽዋ ከኔ አንሳት ብሎ ጸሎት አድርጓል ...ከሱ በላይ ላለ አካል ይህ አካል ማን ነው ?የስልጣን ደረጃውስ ከ እየሱስ የሚለይ በምንድን ነው ?
አምላክ ሞተ ከተባለስ እስከሚነሳ አለምን ማን አስተዳደረ ?
3ኛ /በማቲወስ ምእራፍ 7 ቁጥር 21-23 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርስ እንጅ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት አይገባም ...ይላል
ምን ማለት ነው ?
4/ወንጀል የሰራ አማኝ ለነፍስ አባቱ (ለቄስ )ተናግሮ ይቅር የሚባልበት ምክንያት ምንድን ነው ?
5ኛ /
ማርያም እና ሌሎች አቦ ጊዪርጊስ ተክለሀይማኖት መድሀኒአለም እነማን ናቸው ስልጣናቸውስ ምንድን ነው ?
ሰው ሊሰግድላቸው ይገባል ?በራሳቸው የሆነ ነገር ማድረግ ይችላሉ ?ለምሳሌ መግደል ማዳን :ማክበር ማደህየት ይችላሉ ??
ክምስጋና ጋር _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ቸርነቱ Joined: 05 Sep 2010 Posts: 174
Posted: Sat Apr 09, 2011 5:58 pm Post subject:
[quote="ሱልጣን "][quote="ዘርዐይ ደረስ "]ሰላም ሡልጣን :-
በቅድምያ አምስቱም ጥያቄዎቼ በአጥጋቢ ሁኔታ እንደተመለሱልኝ ስገልፅልህ በመልሶችህ ተስማምቼአለሁ ማለቴ እንዳልሆነ እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ ::በተረፈ ዛሬ ዋርካ ስገባ ያንተን ጥያቄዎች የማገኝ መስሎኝ ነበር ::ጥያቄዎችህ ገና ስላልቀረቡ የኔዎቹን ባስከትልስ ?/[quote]
ይቻላል
ያው ዊክ ኢንድ ስለምትጎበኘኝ እኔም እስከዚያው በራሴ ሀጃ ቢዚ ልሁን ብየ ነው
Quote: 6)አንድ ሰው ሙስሊም ለመባል ቢያንስ ምን ምን ነገሮችን ማሟላት አለበት ?
አንድ ሰው ሙስሊም ለመባል ላኢላሀ ኢለላህ ሙሐመድ ረሱሉሏህ (በ እውነት የሚያመልኩት አምላክ ከላህ በስተቀር የለም ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ደግሞ የ እርሱ የመጨረሻ ነብይ ናቸው ብሎ ማመን ..ኢሳ ነብይ ነው ብሎ ማመን ሲሆን በቀን 5 ጊዜ የሚሰገደውን ሰላት ከሰገደ ሙስሊም ነው ማለት ይቻላል ::
Quote: 7)በኢስላም ሴቶች የወንዶች ግማሽ አእምሮ ነው ያላቸው የሚባል አስተሳሰብ አለ ?
ሴቶች የወንዶች ግማሽ አእምሮ አላቸው የሚል በኢስላም አላነበኩም ::ከወንዱ ያላነሰ ታላቅ ስራ ለኢስላም ያበረከቱ እናቶች እና እህቶች እንዳሉ ኢስላም አስተምሮናል ::በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ችኩሎች ስለሆኑ እና ርህራሄም በጣም ስለሚያጠቃቸው ወይም ሲቆጡ ውሳኔያቸው ቅጽበታዊ ስለሆነ እንደፍች እና አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እድሉ ለወንድ ተሰጥቷል ...
[quote] በኢስላም የወሊድ ቁጥጥር ማድረግ ጨርሶ የተከለከለ ነው ወይስ እንደሁኔታው ነው የሚወሰነው ?/ Quote:
በኢስላም የሚወለደው ልጅ ለ እናቱ ህይወት አስጊ መሆኑ በታማኝ ዶክተር ከተረጋገጠ እንኳንስ ጽንስን አስቀድሞ ለመከላከል መድሀኒት መጠቀም ይቅር እና ጽንሱን ለ እናቱ ህይወት ሲባል ጽንሱን ማስወረድ የሚፈቀድበትም ኮንዲሽን ሊኖር ይችላል (ጽንሱ ወይም ብታረግዝ ለህይወቷ አስጊ መሆኑ ከታወቀ ) ከዚያ ውጭ ግን ችግርን በመፍራት ወይም ማሳደግ አልችልም በሚል ምክንያት የወሊድ መከላከያ መጠቀም አይፈቀድም ::
Quote: 9)ሴቶች ወንዶች ባሉበት የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር ይፈቀድላቸዋል ?
የሀይማኖት ትምህርት እንዳያስተምሩ የሚከለክላቸው ነገር የለም ቅድመ ሁኔታውን እስካሟሉ ድረስ :: ወንዶች በሴቶች ሴቶችም በወንዶች መፈታተን በማይፈጥር መልኩ እና የሂጃብን ስርአት በጠበቀ መልኩ ማስተማር ይችላሉ ::
ብዙ ጊዜ ግን ወንድ ምሁራን በበቂ ሁኔታ እስካሉ ድረስ ሴቶች ሴቶችን ቢያስተምሩ ይመረጣል :: እንዳልኩህ የሂጃብን ስር አት በጠበቀ ሁኔታ ወንዶች ሴቶችን ማስተማር ይችላሉ ::
Quote: 10)ጂሐድ (የጦርነት ) ለማወጅ ምን ምን ነገሮች መሞላት አለባቸው ?
መጀመሪያ ጂሀድ ማለት ምን ማለት ነው ?ጅሀድ ዝም ቢሎ የሚታወጅ ጦርነት አይደለም .ሙስሊሞች መብታቸው ሲጣስ እምነታቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ሲከለከሉ የሙስሊም ሀገር ሉአላዊነት ሲደፈር መንግስታት ተመካክረው የሚወስኑት ነገር ነው ::እና ጭቆናን ለመገፍተር የሚደረግ ነገር ነው ::ውደ ሩቅ አንሂድ እና እኔ ከባለበቴ ጋር እየሄድኩ ባለቤቴን ለመንጠቅ ከሚመጣ ማንኛውም ሀይል ጋር እንደ አስፈላጊነቱ መጋደሌ ጅሀድ ነው ክብሬን ወይም የቤተሰቤ ክብር እንዳይደፈር መከላከሌ ጅሀድ ነው ::ነፍሴን ከመጥፎ ለመከላከል ከራሴ ጋር የማደርገው ግብግብ ጂሀድ ነው ::በአረመኔ ባለስልጣን ፊት እውነት መናገር ጅሀድ ነው ::ጅሀድ ማለት ዝም ብሎ ሰው መግደል አይደለም ::ለዚያም ነው ቅድመ ሁኔታዎች አሉት የሚባለው ::አሁን በፍልስጤም እና በ ቺቺኒያ ግሮዝኒ የሚደረጉት ጦርነቶች ጅሀድ ናቸው
ምክንያቱም ፓለስታይኖችም መሬታቸውን ተነጥቀው መብታቸው እየተደረገ ለነፃነታቸው የሚያደርጉት ትግል ጅሀድ ነው :ጥንት አፍጋኒስታን በሩሲያ ላይ የዘመተች ጊዜ አፍጋን ያካሄዱት ትግል ጅሀድ ነው ስንት ተአምርም ታይቷል ::እና ተርምስ & ኮንዲሽንስ አለው ::እኔ ዛሬ ተነስቼ ጅሀድ ማወጅ አልችልም ::ብዙ ጊዜ ሀላፊነቱ በሀገር መሪዎች ላይ ነው ::ከሙስሊም ምሁራን ጋር በመወያየት እንደ ወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ የሚታወጅ ነገር ነው ::
ያልተመለሰውን አዋቂዎችን ጠይቄ ለማብራራት ዝግጁ ነኝ ::
................... የኔ ጥያቄ ............................
1ኛ / አምላክ ሶስትም አንድም ንው የሚባል (ትሪኒቲ )
ብዙ መጽሀፍም ባንገላብጥ ሊገባኝ አልቻለም
አብ /ወልድ /መንፈስ ቅዱስ =አሀዱ አምላክ ትላላችሁ
ለመሆኑ ሶስቱ አንድ ናቸው ማለት እኩል ስልጣን አላቸው ማለት ነው ?ለምሳሌ እየሱስ ነው አምላክ ወይስ እግዜአብሄር ? እየሱስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ትላላችሁ እንዴት ?እግዜአብሄርስ ሰው ነው ወይ ?
2ኛ /አምላካችን እየሱስ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ስላለ ለ እኛ ብሎ ሞቶ ተሰቀለ የሚል እምነት አላችሁ ::
ለመሆኑ የሰው ልጆችን የማዳን ስልጣን ካለው ለምን መሞት አስፈለገ ?ስውን ከሀጢአት ለማንጻት እሱ መሞት አለበት (ጌታ ከሆነ )ወይስ ከፍላጎቱ ውጭ ተገደለ ?
ፈጣሪ እንዴት ሊሞት ይችላል ?እሱ 3 ቀን እና ሶስት ሌሊት መቃብር ውስጥ እንደቆየ ታምናላችሁ እስኪ ከመቸ ጀምሮ ?ቀናቶችን ቁጠርልኝ ..
ኤሎሄ ኤሎሄ ላማሰበቅተኒ ........ብትችል ይህችን ጽዋ ከኔ አንሳት ብሎ ጸሎት አድርጓል ...ከሱ በላይ ላለ አካል ይህ አካል ማን ነው ?የስልጣን ደረጃውስ ከ እየሱስ የሚለይ በምንድን ነው ?
አምላክ ሞተ ከተባለስ እስከሚነሳ አለምን ማን አስተዳደረ ?
3ኛ /በማቲወስ ምእራፍ 7 ቁጥር 21-23 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርስ እንጅ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት አይገባም ...ይላል
ምን ማለት ነው ?
4/ወንጀል የሰራ አማኝ ለነፍስ አባቱ (ለቄስ )ተናግሮ ይቅር የሚባልበት ምክንያት ምንድን ነው ?
5ኛ /
ማርያም እና ሌሎች አቦ ጊዪርጊስ ተክለሀይማኖት መድሀኒአለም እነማን ናቸው ስልጣናቸውስ ምንድን ነው ?
ሰው ሊሰግድላቸው ይገባል ?በራሳቸው የሆነ ነገር ማድረግ ይችላሉ ?ለምሳሌ መግደል ማዳን :ማክበር ማደህየት ይችላሉ ??
ክምስጋና ጋር
Bukhari:V3B48N826 "The Prophet said, 'Isn't the witness of a woman equal to half of that of a man?' The women said, 'Yes.' He said, 'This is because of the deficiency of a woman's mind
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sun Apr 10, 2011 12:03 am Post subject:
ሰላም ሡልጣን :-
ዛሬ አንድ ሌላ የዋርካ ታዳሚ ጣልቃ እስኪገባ ድረስ ለሁለት ሳምንታት ያህል ውይይቱ በሁለታችን መሐል ብቻ ነበር የተካሄደው ::የዋርካ ሪከርድ ሳይሆን ይቀራል ?
ወደ ጉዳዩ ስመለስ :-በኔ በኩል አስሩንም ጥያቄዎች መልሰህልኛል ::እስቲ ደግሞ ያንተን ልሞክረው ::
1)እኔ ሥላሴን የምረዳው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሦስት አማልክት ሳይሆኑ የአንድ አምላክ የተለያዩ መገለጫዎች እንደሆኑ ነው ::እኩል ሥልጣን አላቸው ወይ ላልከው ግን እኔ እንደምረዳው አብ ከወልድ እንደሚበልጥ ነው ::ለዚህም ምሳሌ ለመስጠት ያህል በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ቍ 36 ላይ እንደ ተፃፈው ''ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአብ ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ወልድም ቢሆን የሚያውቃት የለም ::'' ከዚህ በመነሳት ብቻ አብ ከወልድ እንደሚበልጥ መረዳት ይችላል ::ከላይ እንደገለፅኩት ግን አብም ወልድም አምላክ ናቸው ::እንዳልከውም ኢየሱስ በምድር ላይ ሲኖር ኃጢያት ካለመስራቱ በቀር እንደ ሰው ኖሯል ::ፍፁም ሰው የሚባለውም ለዚህ ነው ::ከላይ እንደገልፅኩትም የአምላክነት ባህርይም አለው ::እግዚብሔር ሰው ነው ወይ ላልከው ግን አይደለም ነው መልሴ ::
2)የኢየሱስ መሞትማ ያስፈለገበት ምክንያት ከአዳም የወረስነውን ኃጢያት ለማንፃት ነው ::እኛ እንድን ዘንድ ነው የእርሱ ሞት ያስፈለገው ::ይህ እንግዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ::ለምን እግዚአብሔር ለምን ሌላ መንገድ አልተጠቀመም ብዬ ከፈጣሪ ጋር ሙግት አልገባም ::የሚሻለውን የሚያውቀው እግዚአብሔር እንጂ የኛ ጠባብ አእምሮ አይደለም ::ኢየሱስ ከፍላጎቱ ውጪ ነው ወይ የተገደለው ላልከው እንደሚሰቀል በፊትም ያውቅ ነበር ::ለደቀ መዛሙርቱም ይህንኑ አስቀድሞ ነግሯቸዋል ::ነቢያትም ሺህ ዓመታት አስቀድመው ተገልጦላቸው ፅፈዋል ::ለምሳሌም ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53ን ማንበብ ይቻላል ::ፈጣሪ እንዴት ሊሞት ይችላል ላልከው የሞተው ሰው የሆነው ወልድ እንጂ እግዚአብሔር አይደለም ::እንዳልከው ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ያህል ከሞተ በኋላ ከሙታን ተነስቷል ::ከመቼ እስከ መቼ ላልከው እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም ::በተለምዶ ዓርብ ተሰቅሎ እሁድ ተነስቷል ይባላል ::መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ግን ቀን አይገለፅም ::''ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ?'' ያለው አብን ነው ::''አምላክ ሲሞት ዓለምን ማን አስተዳደረ ?'' ላልከው ልድገመውና የተሰቀለው እግዚአብሔር አብ ሳይሆን ወልድ ነው ::
3)ይህንን ያለው ለይስሙላ ብቻ ጌታዬ ጌታዬ እያሉት በተግባር ግን የእግዚአብሔርን ፍቃድ የማይፈፅሙትን ለመገሰፅ ነው ::
4)ለ ንስሐ አባት በመናዘዝ ብቻ ኃጥያትን ይቅር ማስባል አይቻልም ::
5)ማርያም የኢየሱስ እናት ስትሆን ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረከች ነች ::ታማልዳለችም ::መድኃኒየ ዓለም (የዓለም መዳኛ ) የኢየሱስ ክርስቶስ መጠርያ ነው ::አማኑኤልም እንደዚሁ ::ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደኛው ሰው ሲሆን ከፕሮቴስታንቶች በቀር በሁሉም አብያተ ክርስትያናት በቅዱስነት ይታወቃል ::በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ከክርስትያን ቤተሰብ ሶርያ ውስጥ የተወለደ ሲሆን እናትና አባቱ ከሞቱ በኋላ በወታደርነት ዲዮቅሊጥያን በተባለ የሮም ንጉሥ ስር ሲያገለግል ንጉሡ ለሮም አማልክት ቢሰግድ ሃብትና ክብር እንደሚሰጠው ካልሆነ ግን እንደሚገደል ቢነግረውም ኃይማኖቴን አልቀይርም ብሎ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው ::ዘንዶም እንደገደለ ይነገራል ::በአድዋ ጦርነት ወቅትም ከኢትዮጵያውያን ጎን ተሰልፎ ተዋግቷል ይባላል ::አቡነ ተክለ ኃይማኖት ግን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ውጪ በቅዱስነት አይታወቁም ::እነዚህና ሌሎችም ፃድቃንና ቅዱሳን በሥማቸው ቤተ ክርስትያን (ታቦት )ይሰየማል ::በእነርሱም የሚምሉ አሉ ::መማል ግን በመጽሐፍ ቅዱስ (አዲስ ኪዳን )የተከለከለ ስለሆነ ምእመኑ በልምድ ይጠቅምበታል እንጂ ትክክል አይደለም ::መግደል ማዳን ማደህየት ወዘተ ...በተወሰነ ደረጃ ማዳን ይችላሉ ብዬ አምናለሁ ::
መልስ መስጠት እንደዚህ ይከብዳል ለካ !ሁለታችንም ግን የኃይማኖት ሊቃውንት ስላልሆንም አጥጋቢ መልስ መስጠት አንችል ይሆናል ::በዚህ አጋጣሚ ግን ስለራሳችንም ኃይማኖት ሆነ አንዱ ስለሌላው የበለጠ መማር ይቻላል ::
ቸር ይግጠመን _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሱልጣን Joined: 03 Sep 2003 Posts: 463
Posted: Sun Apr 10, 2011 6:54 am Post subject:

ቸር ይግጠመን
ከአንዱ በስተቀር ሁሉም ተመልሷል ይህ ማለት ግን በ መልሱ ተስማምቻለሁ ማለት አይደለም (ይህ አባባል የአንተ ቢሆንም ስለተመቸኝ ተጠቅሜበታለሁ ኮፒ ራይት ካለው መቸም መልካም ፈቃድህን አትንፈገኝ
ዘርአይ
ተጨማሪ ማብራሪያ የምፈልገው አብ ከወልድ የሚበልጥ ከሆነ ማለትም እግዜአብሄር ከ እየሱስ ይበልጣል በስልጣን ማለት ነው ::እስኪ የምታውቀውን ያክል የስልጣን ደረጃቸው በጥቂቱ ግለጽልኝ
ለምሳሌ የሰውን ልጅ የፈጠረ ማን ነው ?አሁን ሲሳያችንን የሚሰጠን የሚገድለን ስንሞት የሚያስነሳን ማን ነው ?የሁለቶችን የስልጣን ደረጃ የቱ እንደሆነ አስረዳኝ
ሌላው አብሮ የሚሄድ በተወሰነ ደረጃ በራሳቸው የማድረግ ስልጣን ያላቸው ጻድቃን እንዳሉ ከመልስህ የተረዳሁ ይመስለኛል ስለዚህም ትንሽ አስረዳኝ ::
በአንድ ሀገር ሁለት መንግስት እንደሌለ እናውቃለን እንዴት ሁለት አምላክስ ሊኖር ቻለ ?እዚህ ላይ አብ እና ወልድን ነው የጠቀስከው መንፈስ ቅዱስ ስልጣኑ ምን እንደሆነ ስላልተብራራ ወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ናቸው ወይስ ይለያያሉ ?ማን ይበልጣል ?ስራቸውስ ምንድን ነው ::
ስለ ውይይቱ ጥሩ መንፈስ አመሰግናለሁ _________________ HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1087 Location: ethiopia
Posted: Sun Apr 10, 2011 6:18 pm Post subject:
ሰላም ሡልጣን :-
አባባሉ ከተመቸህ የ Copyright ማዕቀብ የለም ::ባንተ በኩልም እንደዚያው እንደሚሆን እገምታለሁ ::ወደ ውይይታችን ስመለስ ደግሞ :-
1)ስለ አብና ወልድ የ 'ሥልጣን ' ልዩነት ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀሃል ::ባለፈው ያልኩት እንዳለ ሆኖ ወልድ ለአብ ይታዘዛል አብ ግን ማንንም አያዝም ::ወልድ የማያውቃቸው ነገሮች ሊኖሩ ሲችሉ ከአብ ግን የተሰወረ ምንም ነገር የለም :.:ሰውንም ሆነ ሌሎች ፍጥረታትን ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም ፈጥረዋል ::የዕለት ሲሳያችንን የሚሰጠን አብ ሲሆን የምንሞተው ግን ከአዳም በወረስነው ኃጥያት ምክንያት ነው ::ከሙታን የሚያስነሳንም አብ ነው ::መነፈስ ቅዱስን በሚመለከት ከአብ የሰረጸ ሲሆን ለምሳሌ ኢየሱስ ሲጠመቅ በጴንጤ ቆስጤ ቀን ሐዋርያት ተአምራትን ሲሰሩ ወዘተ ...ኃይሉ ታይቷል ::ከአብና ወልድ ጋር ግን አናወዳድረውም ::
2)ቅዱስንና ጻድቃን እንደኛው የአዳምና የሔዋን ኃጥያት ያለባቸው ሰዎች ሲሆኑ ከተራው ሰው ግን በባህርያቸውና በሥራቸው ይለያሉ ::ለኃይማኖታቸው ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ከእግዚአብሔር የሆኑ ተአምራትን የሰሩም ሊሆኑ ይችላሉ ::ባለፈው ግልጽ አላደረግኩም ይሆናል እንጂ እነዚህ ሰዎች በራሳቸው የሚያደርጉት ምንም ነገር የለም ::በእግዚአብሔር ፈቃድ የሰው ልጆችን ሊረዱ ይችላሉ እንጂ ::
እኔ ደግሞ ልቀጥል
11)በኢስላም ንስሐ አለ ወይ ?
12)ዒሳ በመጨረሻው ቀን ይመጣል ብለህ ታምናለህ ?
13)አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ምን ትሆናለች ?
14)በኢስላምስ ጻድቃንና ቅዱሳን አሉ አይደለም ወይ ?
15)ከመካና መዲና በተጨማሪ ሁሉም ሙስሊም የሚቀበላቸው የተቀደሱ ቦታዎች አሉ ?
በተረፈ ውይይቱ ሥርዓቱን እንደጠበቀ መሆኑ አስደስቶኛል ::So far so good! ማለት የሚወድ አንድ አስተማሪ ትዝ አለኝ :: _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12