WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ኢትዮጵያ - በወያኔዎች ለሽያጭ የቀረበች አገር
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 12, 13, 14, 15  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Oct 17, 2011 12:41 am    Post subject: Reply with quote

አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው:
Ethiopia readies 3 mn hectare for investors

K Rajani Kanth / Chennai/ Hyderabad October 17, 2011, 0:57 IST
Ethiopia, a landlocked country located in the horn of Africa, is readying over 3 million hectare of land for investors to develop large-scale commercial farms, according to a government official. Arrow አዎን ልብ ያደማል ...የፋዚዝም አይነተኛ ገፅታ
We have developed 3.6 million hectare from the National Land Bank to attract foreign direct investments. Of this, we have already allotted 400,000 hectare, with 70 per cent being to Indian investors. The remaining three million-odd hectare is now available for local and foreign investors, said Esayas Kebede, director, ministry of agriculture and rural development, Ethiopia

http://www.business-standard.com/india/news/ethiopia-readies-3-mn-hectare-for-investors/452743/

አገሪቷ ባፋጣኝ ሁኔታ ለሽያጭ በቀረበችበት በዚህ አስከፊ ጊዜ ውስጥ ...እንኳን ከትግራይ አንዲት ኢንች መሬት ሊሸጥ ቀርቶ ....ጭራሽ የታላቋን ትግራይ ማስፋፋትና ግንባታ ስኬታማ ለማድረግ ወያኔ ..የግዛት ማስፋፋቱን በሰፊው ተያይዘውታል Wink ...ለዛም ታስቦ ይመስላል በሰፈራ መልክም ወያኔ ከትግራይ ብዛት ያለው ህዝብ ወደ ሰሜን ወሎና ምእራባዊ ጎንደር ትግራይን አጎራባች ቦታዎች ላይ ..እንዲሁም ለሱዳን ተሰጠ በተባለው ቦታ መተማና ሁመራ አካባቢ በርካታ ህዝብ በማስፈር ላይ እንደሚገኝ አገርቤት ደርሰው የመጡ ሰዎች በብዛት እየተናገሩ ነው .. እንግዲህ ልክ ሻቢያ አስመራ ሲገባ "ኤርትራን ለግል ...ኢትዮጲያን ለጋራ ብሎ የቻለውን ያህል ያገሪቷን ሀብት እንደዘረፈው ያህል ...ወያኔም ..."ትግራይን ለግል - -ኢትዮጲያን ለጋራ ብለው እየነገሩን ነው ....Exclamation Exclamation

ሰላም ውድ ወንድሜ አንፌቃ :-

ናዚዝም በኦስትርያ እና ጀርመን ምድር ተወልዶ : አድጎና ጎርምሶ በተባበረው የዓለም ሰላም ፈላጊ ሕዝብ ጡጫ ተደቁሶ ለጊዜውም ቢሆን ለማንቀላፋት ተገድዷል :: የግብር አምሣያዎቹ ፋሽዝምና የአፓርታይድ አገዛዝም እንዲሁ :: ነገር ግን እኒህን ሦሥት አስቀያሚ ሰው -በላ ሥርዓቶች ከአልባንያ ኮሚኒዝምና የማፍያ አደረጃጀት ጋር በማጣመር ሻቢያኒዝምና ወያኔይዝም በኢትዮጵያ ምድር ጎልምሠዋል :: የዓለም ሕዝብ በታሪኩ በአመዛኙ ወደ ኋላ የሚጎትቱት ሠይጣናዊ ርዕዮቶች ሲያጋጥሙት እኒያን በጋራ በመፋለም የዘለቄታ ሕልውናን ወደፊት ሲያስቀጥል ችሏል :: ሆኖም ወያኔን በሚመለከት ምዕራባውያንም ሆኑ አዳዲሶቹ ቅኝ ገዢዎች (ቻይና : ሕንድ : አረቦች : ወዘተርፈ ) የሚከተሉት ፖሊሲ በኢትዮጵያውያን ቁስል ላይ ሹል እንጨት የመሸንቆር ያህል የሚያሣምም ነው :: ምናልባት ዓለም መጥፊዋ ደርሶ ካልሆነ በስተቀር በረሃብ : በቸነፈርና በጉስቁልና በሚገረፍ ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ቅጥ ያጣ የግፍ ተባባሪ መሆን ምን ለማግኘት እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም :: ለማንኛውም ምንጊዜም የማይተወን : እኛ ግን ያስቀየምነው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይታረቀን ::

አክባሪህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
*ፍቅር *

አዲስ

Joined: 27 Apr 2011
Posts: 42
Location: usa

PostPosted: Mon Oct 17, 2011 1:47 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
እኛ ግን ያስቀየምነው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይታረቀን ::

ሰላም
እኔ በዚህ አባባልህ አልስማም ይቅርታ አድርግል እጅ :
ወያኔ 24/7 ይሰራል
እኛስ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 22, 2011 12:19 am    Post subject: Reply with quote

In terms of technological inputs, especially fertilizers and their distribution, there is a disheartening report from the Ethiopian Central Statistics Agency (CSA). According to the Agencys data from 2010, Ethiopia used 1.2 million tons of fertilizers. Of this amount, 433,515 tons was distributed in Tigray alone. Amhara and Oromia, the regions that have the most lands and agricultural activities received a total of 347,430 tons.

In addition, on the potentials of land grab for employment, I refer Mr. Flate to the above-mentioned World Bank report that this webpage had analysed in an article entitled http://transformingethiopia.wordpress.com/2011/08/23/part-ii-meles-says-no-land-grab-in-ethiopiaof 23 August 2011. It clearly concludes that there is nothing promising about land grabs in terms of employment creation, as shown here:

Given the central nature of asset and employment generation through planned investments, the level and recording of information on planned (temporary or permanent) employment and physical investment is surprisingly limited. The patchy data that are available suggest that investments create far fewer jobs than are often expected (or promised, as discussed later) and that their capital intensity varies widely. For example, projected job creation ranges from less than 0.01 jobs/ha (for a 10,000 ha maize plantation) to 0.351 jobs/ha (for an outgrower-based sugarcane plantation) in the Democratic Republic of Congo. Expected job creation in Ethiopia is similarly limited, with an average of 0.005 jobs/ha for cases where figures are givenCase studies point to high expectations in employment generation, which, at least in some cases, do not seem to be commensurate with the investment or the qualifications of the local populace. The extent to which assets are provided or local people gain access to knowledge and technology varies widely across investments. Most successful investments provide social services and encouragement for local entrepreneurship. As many of the projects considered began only recently, few positive impacts have yet materialized. Careful future monitoring
as well as attention to the time profile of benefits and the distribution of risks will be important.

For Prof. Ghosh, what is ignored in this unholy alliance between the government of Ethiopia and the Indian companies is water use. This refers to the quality of the agreement the Ethiopian government has signed with the companies. Ghosh revealed that in Ethiopia Indian companies are given agricultural lands carte blanche, since the agreements do not place any restrictions on both land and water use. For instance, this has enabled investing companies to do whatever they liked. For instance, the companies have ventured into opening canals and turning the direction of rivers.

This has already encroached in multiple ways on traditional rights of the indigenous populations, that for inexplicable reason have already been betrayed by their own government. In that, this corporate pattern of food production has already begun showing its dangerous features to the local people, which in the future is likely to affect the whole country. In that sense, the Indian professor says, land grab is a misnomer since what in reality it represents is a rush to grab surface and ground water and mineral inside the lands. This is consistent with historical experiences.

What are her fears and concerns for the future? As a concerned Indian, she opined, all Indians should be worried for these poor countries not only as a matter of international solidarity. But also because, if Indian companies are allowed to behave in such exploitative manner as all previous generations of colonialists had done toward local peoples and poor countries, they should also be concerned that there is no reason these investors and their corporations could not behave towards Indian citizens in the same manner in India itself.

http://transformingethiopia.wordpress.com
http://www.abugidainfo.com/index.php/19017/
_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Oct 22, 2011 2:01 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወንድሜ አንፌቃ :-

የገጠሩን ሠፊ መሬት መሸጥ ያልበቃው ወያኔ ሠሞኑን ደግሞ የከተማ ኗሪውን ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ ከይዞታው የሚነቅል አዋጅ አውጥቷል :: ይህ ሁሉ የወያኔ እርምጃ ወዴት ይመራል ? አል -ቃዳፊን የያዙት የሊቢያ ወጣት ተዋጊዎች በሕይወት እንዲቆይ ያልፈቀዱበት ምክንያት ያደረሠባቸው የተደራረበ ግፍ ነው :: በእርግጥ ወያኔን እና አል -ቃዳፊን ማነፃፀር አይቻልም :- ቢያንስ እርሱ አገሩን እንደ ቅኝ ግዛት አይቶ አያውቅም :: የወያኔዎች የግፍ አገዛዝ ግን ከገደቡ አልፎ ከፈሠሠ ቆየ :: ስለሆነም ወያኔን እና ደጋፊዎቹን የሚጠብቃቸው '-ሔግ ' የሚገኘው ፍርድ ቤት ሣይሆን ድምጥማጣቸውን የሚያጠፋ የሕዝብ ነውጥ ብቻ ነው ::

አክባሪህ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Oct 26, 2011 11:46 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ወያኔ ለራሱ ፍላጎት ሲል ካዋቀራቸው የባንቱስታን ግዛቶች መካከል 'የአፋር ክልል መንግሥት ' የሚባለው አንዱ ነው :: በተለይ ሡልጣን አሊሚራህ ካረፉ ጀምሮ ወያኔ የአካባቢውን መሬት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ተደጋጋሚ አፍራሽ ዘመቻዎችን አድርጓል :: ስለዚህ በቅርቡ በአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የእርስ በእርስ ብጥብጥ የሚያስነሣ ውሳኔ አስተላልፏል - መሬት ከአፋሮች ተነጥቆ ለወያኔ :: ወያኔ ዝርዝር አፈፃፀሙን በምን ሁኔታ ሊያከናውን እንዳቀደ ከተላላኪው መሐመድ ጠሃ አንደበት የቀረበውን ቃለ -መጠይቅ ተከታተሉት :: መሐመድ ጠሃ "የምንታገለው ከኅብረተሰቡ አመለካከት ጋር ነው ::" ይለናል : ወይ አለማፈር Embarassed Embarassed Embarassed

ምንጭ :- የማነ ናግሽ : ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ ጥቅምት 15 ቀን 2004 .. :: ‹‹የምንታገለው ከኅብረተሰቡ አመለካከት ጋር ነው››

Quote:
አቶ ጠሃ አህመድ፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ

በአፋር ክልል ዳሉል ወረዳ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝተዋል፡፡

አቶ ጠሃ አህመድ በአሁኑ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ተጠሪ ናቸው፡፡ የክልሉ መንግሥት ለዘመናት በጎሳ መሪዎች ይዞታ ሆኖ የቆየውን መሬት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ወደ መንግሥትና ሕዝብ ባለቤትነት ለማዘዋወር የሚያስችል አዋጅ አፅድቋል፡፡ የክልሉ አርብቶ አደሮችንም ወደ አርሶ አደርነት ለመቀየር በመንደር የማሰባሰብ የሠፈራ ፕሮግራም ለማከናወን አቅዷል፡፡ በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የማነ ናግሽ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ አቶ ጠሃን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡ - በአፋር ክልል መሬት ለብዙ ጊዜ በጎሳ መሪዎች ይዞታ ይተዳደር እንደነበር ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ምክር ቤታችሁ በዚህ ጉዳይ ላይ አዲስ አዋጅ አፅድቋል፡፡ ስለዚህ ነገር ሊያብራሩልኝ ይችላሉ ?

አቶ ጠሃ፡ - በአሁኑ ጊዜ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ መሆኑን በሚያረጋግጥ መልኩ አዋጅ ወጥቶለት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በተግባርም መሬት ተዘጋጅቶ ለአርብቶ አደሮች እየተከፋፈለ ነው፡፡ ለመላ ኅብረተሰቡ መሬት የማዳረስ ሥራ ይቀጥላል፡፡

ጎን ለጎን ደግሞ የአካባቢ ጥበቃና የገጠር መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ አቋቁመናል፡፡ ኤጀንሲው የመሬት ማረጋገጫ እስከ መስጠት ድረስ የሚሠራ ተቋም ሆኖ ነው የተደራጀው፡፡ ይህ ተቋም እስከ ታች ድረስ ጉዳዩን በሚገባ እንዲከታተል በማቴሪያልና በሰው ኃይል ተጠናክሮ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ የገጠር መሬት አስተዳደር ጉዳዩም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ለማስገባት ተቋማዊ አደረጃጀት ፈጥረንለታል፣ አዋጅና ደንብም ተዘጋጅቶለታል፡፡ በዚህ መሠረት መሬት ከግለሰቦች እጅ ወጥቶ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በተደነገገ መልኩ የሕዝብና የመንግሥት ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡ ማንኛውም ተግባራችን ሕገ መንግሥታችን የሚፃረር አይደለም፡፡ ፈቅደንና ወደን ያፀደቅነውን ሕገ መንግሥት ማክበርና መተግባር ስላለብን ይህን አሠራር መንግሥት አምኖበት፣ መሬቱ የመንግሥትና የሕዝብ መሆን አለበት ብሎ ቁርጠኛ አቋም ወስዶበታል፡፡

ሪፖርተር፡ - የዚህን አዋጅ መፅደቅ ተከትሎ የሕዝቡ ስሜት (ምላሽ ) ምን ይመስላል ?

አቶ ጠሃ፡ - ይኼ አዋጅ ከፀደቀ በኋላ ብዙ ሥራዎችና ጥናቶች ማድረግ ግድ ብሎናል፡፡ የመጀመሪያው ሥራ ግን ሕዝቡን ማሳመን ነው፡፡ ለብዙ ዘመናት በጭንቅላታቸው ውስጥ የነበረን አስተሳሰብ መቀየር መቻል ይኖርብናል፡፡ ያንን ለማሳካት ኮንፈረንስ ተዘጋጅቷል፡፡ ሕዝቡም መሬት የጎሳ ካልሆነ ተጠቃሚ አንሆንም አላለም፡፡ በግሉ የመጠቀም ማረጋገጫ ከተሰጠው መሬት በጎሳ ቁጥጥር ከሚሆን ይልቅ የግሉ ቢሆን ተጠቃሚ መሆኑን አምኖበታል፡፡ አዋጁን የሚቃወም ከተገኘም የጎሳ መሪዎች ናቸው የሚሆኑት፡፡ እነዚህ ደግሞ ከአጠቃላዩ ሕዝብ ሁለት በመቶ አይሞሉም፡፡ እነሱ ደግሞ የጎሳ መሪዎችና የንዑስ ጎሳ መሪዎች ናቸው፡፡ በሕዝብ ደረጃ ግን መሬት የጎሳ ይሁን ብሎ የሚያስብ የለም፡፡ ከዚህ አንፃር ቁርጠኛ አቋም ወስደን ለኅብረተሰቡ የሚያስገኘውን ጥቅም የማሳመን ሥራ መሥራት ነበረብን፡፡ ሕዝቡም ደስተኛ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀው 17 ዓመት በፊት ነው፡፡ እስካሁን በክልላችሁ መሬት በጎሳ መሪዎች መቆየቱ ተገቢ ነው ? እጅግ የዘገየ ዕርምጃ አይደለም ይላሉ ?

አቶ ጠሃ፡ - ከጊዜ አንፃር ስናይ ረዥም ጊዜ ነው፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ ካለው የቆየ አስተሳሰብ አንፃር ስናይ ግን ዘግይቷል ማለት አይቻልም፡፡ የምንታገለው ከኅብረተሰቡ አመለካከት ጋር ነው፡፡ የምንታገለው ከብዙ ሕዝብ ጋር ነው፣ የሚታገለው ጥቂት ነው፡፡ የምንታገለው ከኅብረተሰቡ ባህል ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ አንፃር ዕርምጃው የዘገየ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የተማረ ሰው አልነበረም፡፡ እኔ የተማርኩት በዚህ መንግሥት ነው፡፡ በዲግሪ ተመርቄም ይኼን ባህል (አመለካከት ) ከቤተሰቤ ማጥፋት አልቻልኩም፡፡ ሥር የሰደደ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አስተሳሰብ ስለሆነ በአንድ ጊዜ ለማስወገድ አስቸጋሪ ነው፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው አደረጃጀት ጎሳዊ ከመሆኑ ጋር ተይይዞ፣ መሬት ጋር በምትመጣበት ጊዜ የሚመጡ አዳዲስ አስተሳሰቦችና አሠራሮች ጥንቃቄ የሚሹ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡ - በአፋር ክልል መሬት በጎሳ መሪዎች እጅ ከመሆኑ ጋር ተይይዞ ምን ያህል ጉዳት ነበረው ?

አቶ ጠሃ፡ - ኅብረተሰቡ የመሬትን ጥቅም አለማወቁ መሬት በጎሳ መሪዎች እጅ እንዲቆይ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ጥቂት ግለሰቦች እንደፈለጉ እንዲያስተዳድሩ ያደረጋቸው የኅብረተሰቡ የራሱ አመለካከት ነው፡፡ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ከመኖር ውጭ አንድ ቦታ ላይ ቁጭ ብዬ ከመሬት ላይ አንድ ጥቅም አገኛለሁ የሚል አመለካከት አለመኖሩ ትልቁ ምክንያት ነው፡፡ ይኼ የጎሳ መሪዎች የፈጠሩት ነገርም አይደለም፡፡ እዚህ መሬት ላይ መሥራት የጀመረው የጎሳ መሪ ነው እየተጠቀመ ያለው፡፡ የማያርስ ተንቀሳቃሽ የሆነ የጎሳ መሪም አለ፡፡ ይኼ መሬቱን የሚያውቀው እንደ ጎሳ መሪ ግዛት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ እስከዚህ ድረስ የእኔ ጎሳ የሚኖርበት የእኔ ግዛት ነው ይላል፡፡ ይኼ መሬት ለእርሻም ሆነ ለሌላ ጥቅም ያልዋለ የጎሳ መሪዎች ይዞታ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሬቱን እየተጠቀሙ ያሉት የጎሳ መሪዎች ብቻ አይደሉም፡፡ ትንሽ የነቃ ከተማ ቀመስ ግለሰብም መሬቱን ከጎሳ መሪ ተቀብሎ እንደ ጎሳ መሪ ያከራያል፡፡ ግማሹ ስለመከራየቱም ግንዛቤ የለውም፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ምክንያት የሚሆነው፣ የጎሳ መሪዎች በኅብረተሰቡ ውስጥ እንቅፋት የሚሆኑበት ሁኔታ አለ፡፡ መሬቱ በእርሻ ከተያዘ ከብቶቼን የማረባበት ቦታ ይጠብበኛል የሚል ስጋት በአርብቶ አደሩ ዘንድ አለ፡፡ አንድ እንቅፋት እንዳይሆን ያለን ስጋት አንዱ ይኼው ነው፡፡ ከብቶቼን የት አውላለሁ ? የት አሳድራለሁ ? ከብቶቼ ምን ይበላሉ ? የሚል ስጋት ያድርበታል፡፡ አርብቶ አደሩን በመንደር ማሰባሰብ የተመረጠበት ምክንያትም ለእሱ እንደማይጠቅመው ስለታመነበት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የትኛው መንገድ ይጠቅማል ብሎ ሲጠይቅ ራሱ ያውቀዋል፡፡

ሪፖርተር፡ - ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ይኼ የጎሳ ሥርዓት ምን ያህል አስቸጋሪ ነበር ?

አቶ ጠሃ፡ - ቅድም እንዳልኩህ ኢንቨስትመንት ላይ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥሙ አንዳንድ ችግሮች አሉ፡፡ ለከብቶቻቸው የግጦሽ መሬት ሳይዘጋጅ የእርሻ ቦታ በስፋት ይያዛል፡፡ ቦታ በግጦሽ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ቦታ ነው፡፡ ሌላ ምርጫ ሳይበጅለት በመንግሥትም ይሁን በግል ኢንቨስተር ሰፊ የግጦሽ መሬት ግጭት ይፈጠራል፡፡ የሚሄድበት ቦታ ስለሌለው የግድ ወደ ግጭት ያመራል፡፡ መሬት ሁሉ ለግጦሽ አይጠቅምም ውስን አካባቢዎች ናቸው ለግጦሽ የሚውሉት ወቅትም አለው፡፡ በክረምትና በበጋ የሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ሲከለሉ፣ ከብቶቹ የሚበሉበት ቦታ ሲያጡ ወደ እርሻ ቦታ የሚለቁበት ሁኔታ ነበር፡፡ ኢንቨስተሩ ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ ዋናው ምክንያቱ ግን ለምን አረስክ ? አይደለም፡፡ ለከብቶቹ የግጦሽ መሬት ማጣት ነው፡፡ ሌላ አማራጭ ቦታ ቢዘጋጅለትና እዚህ ተጠቀም ቢባል አያስቸግርም፡፡ ከብቶቹ በባህላዊ መንገድ የሚረቡ ስለሆኑ አንድ ሰው እስከ 200 ከብቶች ይዞ የሚዞርበት ሁኔታ አለ፡፡ ከዚህ አንፃር ምን ያህል ሰፊ መሬት እንደሚፈልግ ማሰቡ ቀላል ነው፡፡ አማራጭ ከተዘጋጀለት ግን የሰው ንብረት ላጥፋና ላበላሽ ብሎ የሚያደርገው ነገር አይኖርም፡፡

ሪፖርተር፡ - አዋጅና ደንብ ከመውጣቱ በፊት ሕዝቡ በመሬት ይዞታ ላይ ያለውን አስተሳሰብ መቀየር መቅደም አልነበረበትም ?

አቶ ጠሃ፡ - ከዚያ በፊት የተሠሩ የማሳመን ሥራዎች አሉ፡፡ በአገር ሽማግሌዎችና በጎሳ መሪዎች በተለያዩ ጊዜያት የተወሰኑ ነገሮች አሉ፡፡ እስካሁን ድረስ ስንጣላ የነበርነው በውሳኔ ምክንያት አልነበረም፡፡ ይኼ መሆን የለበትም ብሎ በመቃወም በአደባባይ የሚንቀሳቀስ ኃይል የለም፡፡ ወደ ተግባር ሲመጣ ተግባሩ ላይ ጥቅሜ ይነካብኛል ብሎ የሚፈራና የሚሸሽ ሰው ነበር፡፡ በተጨባጭ በመርህ ደረጃ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ መሆን አለበት ብሎ በሚነገርበት ሰዓት በተቃራኒ የሚሰለፍ ሰው የለም፤ አላጋጠመንም፡፡ ነገር ግን ወደተግባር ሲገባ እንቅፋቶች አሉ፡፡

ሪፖርተር፡ - በተግባር ላይ የገጠሙዋችሁ እንቅፋቶች ምንድን ናቸው ?

አቶ ጠሃ፡ - አዋጁ የሚያስቀምጣቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለአንድ ሰው የሚሰጠውን ከፍተኛና ዝቅተኛ የመሬት ይዞታ ይገልጻል፡፡ ያንን በምንተገብርበት ሰዓት አዋጁ ላይ ከተደነገገው በላይ እጁ ላይ መሬት ይዞ የሚገኘው ሰው እንቅፋት መሆኑ አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ግማሽ (ትርፍ ) መሬቱ ሊወሰድበት ነው፡፡ አዋጁ የሚፈቅደው አሥር ሔክታር ከሆነ 80 ሔክታር በእጁ የያዘ ሰው 70 ሔክታር ሊያጣ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው እንቅፋት መሆኑ አይቀርም፡፡ ይኼ የሚያጋጥም እንቅፋት እንደሚሆን ቀድሞም የታሰበ ነገር ነው፡፡ ይኼ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ደግሞ የሚገለጸው በቀጥታ አይደለም፤ በተለያየ መንገድ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው የጎሳውን ሽፋን ተጠቅሞ ከአንድ ጎሳ ተወስዶ ለሌላ መሬት እየተሰጠ መሆኑን ይቀሰቅሳል፡፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ መሬት ይዘው ያከራዩ ነበር፡፡ እነዚያ ሰዎች ወደ ግል ይዞታቸው ሲመለሱ ከሌላው እኩል ሊሆኑ ነው፡፡ አብዛኛው አርብቶ አደር ግን ለመሬት ደንታ የለውም፡፡ የተወሰኑ የመሬትን ጥቅም የሚያውቁ ሰዎች ግን መሬት አድበስብሶ የመያዝ አዝማሚያዎች አሉ፡፡ ስለዚህ አርብቶ አደር የነበረውን ወደ አርሶ አደር በምንመለስበት ሰዓት መሬት ይጠባል፡፡ አንድ ሺሕ ሔክታር ለብቻው ሲጠቀም የቆየ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ አርብቶ አደሩ የመሬትን ጥቅም ካወቀ ግን በዚህ አንድ ሺሕ ሔክታር ላይ ነው የሚውለው፡፡ መከፋፈላቸው አይቀርም፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ሺሕ ሔክታር ይዞታ የነበረው ሰው ውሳኔው አይዋጥለትም፡፡ በተለያዩ መንገዶች እንቅፋት መሆኑንም ይቀጥላል፡፡

ሪፖርተር፡ - ሰፊ መሬት ይዘው ሲጠቀሙ ወይም ሲያከራዩ የቆዩ ሰዎች መሬታቸውን ሲነጠቁ ጥቅማቸው መጎዳቱ አይቀርም፡፡ መሬታቸው ስለተወሰደባቸው የሚሰጣቸው ካሳ የለም ?

አቶ ጠሃ፡ - አንድ ጎሳ ይዞታዬ ብሎ የከለለው መሬት አለ፡፡ ኢንቨስተር ሲያገኝ የሚያስቀምጥበት ወይም የሚጠቀምበት መሬት ነው፡፡ እሱ ምንም ወጪ ያላወጣበት ዝም ብሎ ለቆየ መሬት ላይ የሚከፈል ካሳ የለም፡፡ በጎሳ ስም መሬት ይዞታ ብቻ ስለነበር የሚከፈለው ካሳ አይኖርም፡፡ በጎሳ ስም ተይዞ የነበረው መሬት የጎሳው አባላት በስማቸው መሬት ከመያዙ ውጪ ምንም ስላልተጠቀሙበት የሚከፈል ነገር አይኖርም፡፡ የሕጉ ዝርዝር ነገር ገና ሒደት ላይ ቢሆንም፣ አንድ የጎሳ መሪ በራሱ ይዞታ ሥር የነበረውን መሬት ወጪ አውጥቶበት ለዘመናት ሲያርስ ከነበረ ግን የመሬቱ ዋጋ ሳይሆን የልፋቱ ዋጋ ሊከፈለው ይችላል፡፡ ዛፍና ድንጋይ የነበረበትን መሬት ጠርጎና አስተካክሎ ምቹ አድርጎ እያረሰበት የቆየ ከሆነና አሁን የእሱ ይዞታ ከጠበበ የሚከፈለው ዋጋ ይኖራል ማለት ነው፡፡ አሁን ግልጽ የሆነ የአፈጻጸም መመሪያ እየወጣ ነው፡፡ ለምን ያህል ? እንዴት ? የሚለውን ግን መመርያው የሚመልሰው ይሆናል፡፡ አዋጁ ግን አንድ ሰው ሊኖረው የሚችለውን ጣርያ ያስቀምጣል፡፡ ከዚያ ውጪ የሆነው በአፈጻጸሙ መመሪያ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡ - አርብቶ አደሩን ወደ ቋሚ አርሶ አደርነት ለመቀየር እየሠራችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ በአፋር ክልል ውስጥ ለግብርና ጥቅም ሊውል የሚችል ምን ያህል መሬት አለ ?

አቶ ጠሃ፡ - ምናልባት ለወደፊት እንጂ በአሁኑ ጊዜ ይጠባል ብለን አናስብም፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው አካባቢ የውኃ እጥረት አለ፤ ሁለተኛ አፈሩ ለእርሻ የሚሆን አይደለም፡፡ ከእሳተ ጎመራ ጋር በተያያዘ ዛፍ የማይበቅሉባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ በአብዛኛው ሊለማ የሚችለው መሬት አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ያለ ነው፡፡ ቢሆንም ግን በአግባቡ ከተከፋፈለ የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ የሚሆነውን አናውቅም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን መሬቱ አያንስም፤ አሁን ካለው የሕዝብ ቁጥር አንፃር መሬቱ ከበቂም በላይ ነው፡፡ ለኢንቨስትመንት የሚውል ሰፊ መሬት አለ፡፡ የሚያስጨንቀን ዋናው ጉዳይ ይህን መሬት በሕዝቡ እጅ የማድረጉ ጥያቄ ነው፡፡ በተንቀሳቃሽነት ላይ ከተመሠረተው አርብቶ አደርነት ተላቆ አንድ ቦታ ላይ ሰፍሮ የተረጋጋ ኑሮ የሚኖርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ ለዚህም የተወሰደው አንዱ አቅጣጫ የሠፈራ ፕሮግራም ነው፡፡ መንደር የማሰባሰብ ፕሮግራም ይዘናል፡፡ በዚህ ዓመት ብቻ 35 ሺሕ በላይ አባወራ እናሰፍራለን ብለን አቅደናል፡፡ በሦስት አዳዲስ መንደሮች ነው የሚሰባሰቡት፡፡ በቦታውም አስፈላጊው ግብዓት ይሟላላቸዋል፤ ሙያዊ እገዛ ይደረግላቸዋል፤ ልጆቻቸው ደግሞ ትምህርት የሚያገኙበት፣ የጤና አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ጥናቱም ተጠናቆ አካባቢዎች ተመርጠዋል፤ ወደ ትግበራ እየገባን ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ፕሮጀክቱ ምን ያህል ወጪ ይጠይቃል ?

አቶ ጠሃ፡ - ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመቀናጀት የሚሠራ ፕሮግራም ነው፡፡ ለእርሻ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በማቅረብና መለስተኛ ግድቦችን በመሥራት በገንዘብም ሙያዊ እገዛ በመስጠት የፌዴራል መንግሥት ያግዘናል፡፡ ጥናቱ ተጠናቆ የተገባደደ ቢሆንም፣ ወጪው ይኼን ያህል ነው የምንልበት ጊዜ አይደለም፡፡ሪፖርተር፡ - በክልሉ ውስጥ ሊለማ የሚችል ሰፊ መሬት በአዋሽ ወንዝ ዳርቻ ይገኛል፡፡ የአፋር ክልል መንግሥት በዚህ መሬት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በተንቀሳቃሽ ኑሮ ላይ ለተመሠረተውና ለረሃብ ለሚጋለጠው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ራዕይ አለው ?

አቶ ጠሃ፡ - መንግሥት መሬት ብቻ አይደለም እያለማ ያለው፡፡ ለኅብረተሰቡ የግጦሽ መሬት እያዘጋጀ ነው፡፡ የመሬት ባለቤት ለነበሩ ሰዎች ደግሞ ሌላ ቦታ ላይ መሬት እያዘጋጀና እያከፋፈለ ነው፤ ካሳም ይከፍላል፡፡ መሬት ያልነበራቸው ደግሞ መሬት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው፡፡ ስለዚህ መንደር ማሰባሰብ ስንል መንግሥት እያሰበ ያለው ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን በራሱ ወጪ አመቻችቶ መሬት እንደሚያከፋፍላቸው ነው፡፡ እነዚህ ሞዴል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሌላ ሰው ራሱ ወጪ አድርጎ ተጠቃሚ ይሆናል፤ የእነዚህን ሕይወት አይቶ ቀሪው ከእነሱ ልምድ ይወስዳል ብለን እናስባለን፡፡ ሰብስቡን የሚል ጥያቄም ከራሱ ይመጣል፡፡

ሪፖርተር፡ - ባለፉት 20 ዓመታት የአፋር ሕዝብ ይኼ ነው የሚባል ጥቅም አግኝቷል ብለው የሚናገሩት ነገር ምንድን ነው ?

አቶ ጠሃ፡ - አንደኛ ነገር የአፋር ሕዝብ ለዘመናት ተዘንግቶ የነበረ ሕዝብ ነው፡፡ ማለት የመሠረተ ልማት የሚባል ነገር አያውቅም፡፡ ለአፋር ተብሎ የሚታቀድ በጀት አልነበረም፡፡ ሕዝቡም አይጠይቅም፡፡ ጥያቄ የማይጠይቅና የማይታቀድለት ሕዝብ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ፍላጎቱ ተለይቶለት ባለው አቅም የሚያቅድለትና ያለውን ችግር የሚፈታለት መንግሥት አለ፡፡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት አግኝቷል፡፡ ባለፈው ሥርዓት ሦስት ቦታ (ሰሜን፣ ወሎና ሐረርጌ ) ተብሎ ተከፋፍሎ ነበር፡፡ አንዱ ሌላውን የማያውቅበት ሁኔታ ነበር፡፡ አሁን በራሱ ክልል መንግሥት፣ በራሱ ምርጫ የራሱን ፍላጎት የሚተገብርበት ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ ከዚህ በፊት እኔ ተወልጄ ባደግኩበት አካባቢ ትምህርት የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት እንደ መንግሥት ከተቋቋመ ከሦስት ዓመት በኋላ ዳሉል (የመጨረሻ ዝቅተኛ ቦታ ነው ) ድረስ ተጉዞ ነው ያስተማረን፡፡ ከዚያ በፊት ለመልዕክት የተላከ ሰው እንኳን አይደርስም፡፡ ነገር ግን በዚህ መንግሥት ለልማት ተደርሷል፡፡ የደርግ መንግሥት ሲያስተዳድር በወሬ ነበር የሚሰማው፡፡ የአውሮፕላን ድምፅ ነበር የሚሰማው፡፡ ይኼ መንግሥት ግን በሁለት ሦስት ዓመት ውስጥ ለማስተማር እዚያ ገጠር ውስጥ መግባቱ የሚደነቅ ነው፡፡ ይኼ የሚያሳየው ከአነሳሱ ጀምሮ ዓላማው ትልቅ መሆኑን ነው፡፡ እኔ በዚያ ሰዓት ባልማር ኑሮ አሁን በዚህ ቦታ ባልነበርኩ፡፡ 1986 . ነው ትምህርት ቤት የተጀመረው፡፡ ከተማ የሚባል የለውም፡፡ ሰው ይኖርበታል ወይ ተብሎ የሚታሰብ ቦታም አልነበረም፡፡ በመሃል አገር ‹‹ዳሉል ላይ ሰው አለ እንዴ ?›› ነበር የሚባለው፡፡ ከዚህ አንፃር ኅብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኗል፤ ልጆቹን አስተምሯል፡፡

በየአካባቢው ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ የመምህራን፣ የግብርናና የጤና ሳይንስ ኮሌጆች አሉ፡፡ ሰመራ ዩኒቨርሲቲም (የፌዴራል መንግሥት ) አለ፡፡ ከጤና አንፃር በወረዳ ደረጃ ድረስ ጤና ጣቢያ ተሰርቶአል፡፡ በዞን ደረጃ ደግሞ ሆስፒታሎች ተገንብተዋል፡፡ በእርግጥ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የባለሙያ እጥረት ያጋጥማል፡፡ መንግሥት ለዚሀ አማራጭ አስቀምጧል፡፡ ከደጋ አካባቢ የሚመጣ ሰው እዚያ አካባቢ የመሄድ ፍላጎቱ ዝቅተኛ ስለሚሆን፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍቶ ከእነዚያ ወረዳዎች አስተምሮ እያስገባ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በነርስ ደረጃ ብዙ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ራስን በራስ ማስተዳደር ስንል በራስ ቋንቋ ማስተዳደርና መሥራትን ይጨምራል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ግን የክልሉ መንግሥት ሲጠቀምበት የቆየው የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነበር፡፡ ይህ ተገቢ ነው ይላሉ ?

አቶ ጠሃ፡ - አዎ 20 ዓመት ሰፊ ጊዜ ነው፡፡ እየሠራን ያለነው ግን በየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ ነው ? 95 በመቶ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተይዞ ያለው በሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ነው፡፡ አሁን ግን የአፋርኛ ቋንቋ ማዕከል ተዘጋጅቶ አስፈላጊው ማቴሪያል በአፋርኛ ተዘጋጅቷል፡፡ በትምህርት ቤት ደረጃም ማስተማር ተጀምሯል፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ለመንቀሳቀስ ከተፈለገ ያለችው ጸሐፊ በአፋርኛ ለመሥራት ቋንቋውን መማር አለባት፡፡ እሷን ማስተማር አለብን፡፡ ወይም ደግሞ አፋር መሆን አለባት፡፡ በሕገ መንግሥቱ ላይ የመሥርያ ቋንቋ አፋርኛ ቋንቋ ነው፡፡ ወደ አፈጻጸም ለመግባት ግን እነዚህን ሰዎች መቀየር አለብን፡፡ ስለዚህ በየወረዳው መምህር ተመድቦ እንዲማሩ እየተደረገ ነው፡፡ ከእዚህ አንፃር 270 በላይ በአፋርኛ ቋንቋ የተመረቁ ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎች ባሉበት በአፋርኛ መሥራት እንዲችሉ የማድረግ ሥራ ነው እየሠራን ያለነው፡፡ በአሁኑ ደረጃ የተወሰኑ ሰዎችን መተካት እንችል ነበር፡፡ ያን ስንል ደግሞ የምናባርራቸውና ሥራ የምናሰጣቸው ወገኖቻችን ናቸው፡፡ ሥራ ለሚለቁ ሰዎች ሥራ መፈለግም የእኛ ኃላፊነት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር እነሱን ከማንሳፈፍ ይልቅ ባሉበት እንዲማሩ ነው ያደረግነው፡፡ በየመሥርያ ቤቱ አፋርኛ አስተማሪ ተቀጥሮ እየተሠራ ነው፡፡ እዚያ ደረጃ መድረሳችንን ስናውቅ ወደዚያ መግባታችን አይቀርም፡፡ ከአሁኑ በፊት በየመሥሪያ ቤቱ ተላላኪና ኃላፊው አፋር፣ መኸል ያለው ባለሙያ ግን የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር ነው እየተሠራ ያለው፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንድሪያስ

አለቃ

Joined: 19 Mar 2004
Posts: 2130
Location: *****

PostPosted: Thu Oct 27, 2011 9:48 am    Post subject: Reply with quote

ተድሌ :- ሰው ነህ አይሉህ አእምሮ የለህም ....ከእንስሳት ተራ ለመመደብም ኢንስቲንክቱ ስለሌለህ በጣም አስቸጋር ነው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እና ምንድን ነህ አንተ ?
እግዚዖ !!

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

ዲያስፖራ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Apr 2009
Posts: 714
Location: no

PostPosted: Thu Oct 27, 2011 10:45 am    Post subject: Reply with quote

እንድሪያስ አንተም ? አንተም ? አንተም ወያነ ሆንክ ?
እግዚኦ ማንን እንመን እንግዲህ ? እረ ጎበዝ ግዜው ከፋ !!
_________________
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1762
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Thu Oct 27, 2011 12:00 pm    Post subject: Reply with quote

እኔን የማይገባኝ ነገር ; ከእናንተ ጋር ያላበረ ሁሉ ለምንድን ነው ወያኔ የምትሉት ?

ዲያስፖራ እንደጻፈ(ች)ው:
እንድሪያስ አንተም ? አንተም ? አንተም ወያነ ሆንክ ?
እግዚኦ ማንን እንመን እንግዲህ ? እረ ጎበዝ ግዜው ከፋ !!

_________________
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Oct 27, 2011 8:14 pm    Post subject: Reply with quote

እንድሪያስ እንደጻፈ(ች)ው:
ተድሌ :- ሰው ነህ አይሉህ አእምሮ የለህም ....ከእንስሳት ተራ ለመመደብም ኢንስቲንክቱ ስለሌለህ በጣም አስቸጋር ነው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እና ምንድን ነህ አንተ ?
እግዚዖ !!

እኔ በአርአያ ሥላሤ የተፈጠርሁ ሰው ነኝ :: ያንተን ምንነት ግን ሰው ትሆን አሣማ አላውቅም :: ሻቢያ /ወያኔ መሆንህን ግን ጠንቅቄ አውቃለሁ Razz Razz Razz Razz

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Oct 28, 2011 6:17 pm    Post subject: Reply with quote

በአርአያ ሰላሴ ተፈጠርኩ ለምትለው ተድላ
ኑሮው እንዴት ይዞሀል ?
ያማርኛ አጻጻፍ - መናልባትም ያነጋገር ችሎታህን በማድነቅ ልጀምር :: እንዳው በደፈናው ውብ ነው - በቅን ላየው ስው ::
ከሞላ ጎደል በዛ ያሉ ጽሁፎችህን በማንበቤ የሚከተለውን ቀጥተኛ መጠይቅ ላቀርብ ፈልኩ ::

ባንተና ልብህ በሚደግፈው የፖለቲካ ድርጅት እምነት ለአንድ ሰው ኢትዮጵያዊነት መለክያው ምንድነው ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Nov 02, 2011 9:50 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

አቶ ደሣለኝ ራኽመቶ ከአፄ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ጥናት ላይ ብዙ ሥራ ያከናወኑ ናቸው :: በተለይም 'የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልማት መካነ ጥናት ተቋም ' ኃላፊ በነበሩባቸው ዘመናት ብዙ የጥናት ጽሑፎች ለሕትመት እንዲበቁ አድርገዋል :: 'የየዘመኑ ገዢዎች እኒያን የጥናት ጽሑፎች መሠረት አድርገው መፍትሔ ፈልገዋል ?' ለሚለው ጥያቄ እኔ ያለኝ ግንዛቤ 'ምንም አላደረጉም ' የሚል ነው :: እንዲያውም ገዢዎቹ ጥናቶቹ ከሚያመለከቱት በተቃራኒው አቅጣጫ ዕቅዶች እያቀዱና ሥራ ላይ እየዋሉ ኢትዮጵያ አሁን ለተዘፈቀችበት የችጋር አረንቋ ምክንያት ሆነዋል ::

አቶ ደሣለኝ ራኽመቶ በዛሬው ዕለት ረቡዕ ጥቅምት 22 ቀን 2004 .. ለንባብ በበቃው የሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ስለ ወቅቱ የመሬት ንጥቂያ የሠጡት ቃለ -መጠይቅ አለ : እስኪ አንብባችሁ የራሣችሁን ግንዛቤ ውሰዱ ::

ምንጭ :- ኃያል አለማየሁ : ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ ጥቅምት 22 ቀን 2004 .. :: ‹‹የመሬት ኢንቨስትመንቱ የእዚህችን አገር የምግብ ዋስትና አያረጋግጥም›› አቶ ደሳለኝ ራህመቶ፣ ተመራማሪ ::

Quote:
በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ መሆን የጀመረው ‹‹የመሬት ሽሚያ›› በአገራችንና በአፍሪካም ብዙዎችን እያሳሰበ ነው፡፡

ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመጉረፍ ላይ ያሉ ኩባንያዎች በተለይ አፍሪካን የትኩረታቸው ማዕከል አድርገዋታል፡፡ በርካታ የመካከለኛው ምሥራቅና የሩቅ ምሥራቅ አገሮች ኩባንያዎች 22 የአፍሪካ አገሮች ውስጥ እጅግ ሰፋፊ መሬቶችን የምግብ ምርቶችንና ባዮፊውል ለማምረት እየወሰዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የውጭ ኩባንያዎች መዳረሻ ሆነዋል፡፡ የአብዛኞቹ አገሮች ሕዝቦች ተጎጂዎች እየሆኑበት ነው በሚባለው በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ ጥናታቸውን ያወጡት የማኅበራዊ ጥናት መድረክ ተመራማሪው አቶ ደሳለኝ ራህመቶ፣ ይህንን እንቅስቃሴ የመሬት ኢንቨስትመንት ማለት እንደሚመርጡ፣ ነገር ግን መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ይህ የመሬት ኢንቨስትመንት ለአገሪቱ የምገብ ዋስትና ፋይዳ አይኖረውም የሚሉትን አቶ ደሳለኝ ኃያል ዓለማየሁ አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡ - ለኢንቨስተሮች በሚሰጡ ሰፋፊ መሬቶችና የምግብ ዋስትናን በተመለከተ አንድ ጥናት አቅርበዋል፡፡ ለባዮ ፊውልና ለእህል ልማት የሚውሉ መሬቶች በሔክታር ምን ያህል መሆን እንዳለባቸው የሚያስቀመጥ መመርያ እየተጣሰ እንደሆነ ይታያል፡፡ ለመሆኑ መመርያው ተግባር ላይ ውሏል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - በአንድ በኩል ውሏል ማለት ይቻላል፡፡ ክፍያን በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረው የመሬት ኪራይ በጣም አነስተኛ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ኪራዩንም የሚወስኑት የክልል መስተዳድሮች ነበሩ፡፡ እንደ .. 2008 በፊት የክልል መስተዳድሮች ሙሉ ኃላፊነት ነበራቸው፡፡ ስለዚህ አንድ ኢንቨስተር ለሚመለከተው የክልል መስተዳድር አመልክቶ መሬት ማግኘት ይችላል፡፡ የኪራዩን መጠን ክልሎች ነበሩ የሚያወጡት፡፡ ተመኑንም እያንዳንዱ ክልል በራሱ የመሬት አዋጅ አማካይነት ያስቀምጣል፡፡ የፌዴራሉ የግብርና ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ከአራት ዓመታት በፊት ሲቀበል 5000 ሔክታር በላይ መሬቶችን በፌዴራል ለማስተዳደር ነበር፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ የሁሉንም መሬቶች ኃላፊነት ጠቅልሎ መውሰዱ ይነገራል፡፡ ሆኖም ለማረጋገጥ ሞክሬ አልቻልኩም እንጂ 5000 ሔክታር በታች ያሉትም በግብርና ሚኒስቴር ኃላፊነት ሥር እንደሆኑ የሚሰማ ነገር አለ፡፡

ሪፖርተር፡ - ለፌዴራሉ መንግሥት የተሰጡበት ምክንያት ምንድን ነው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - አንድ ወጥ አመራር፣ ቅልጥፍናና የተሻለ አገልግሎት ኖሮ ኢንቨስተሮችን ለማስተናገድ የሚሉ ምክንያቶች አሉ፡፡ ይኼ ሆኖ ሳለ የኪራይ ክፍያው ግን እንደነበር ነው፡፡ በቅርቡ ካልተሳሳትኩ አምና ነው የግብርና መመርያ የወጣው፡፡ መመርያው ለክልሎች የአጠቃቀም ሐሳብ ለመስጠት የወጣ ነው፡፡ ራሱ የፌዴራሉ ግብርና ሚኒስቴር መመርያውን ሥራ ላይ ማዋል የጀመረው አሁን በቅርቡ ነው፡፡ ተመኑ በሥራ ላይ ውሏል፡፡ ከአዲስ አበባ እየራቀ ሲሄድ የመሬት ዋጋ እየቀነሰ ይሄዳል ይላል፡፡ ለምሳሌ ጋምቤላ ላይ በሔክታር 158 ብር በዓመት ይከፈላል፡፡ በፊት 30 እስከ 35 ብር ነበር፡፡

ሪፖርተር፡ - ሆኖም ግን መሬት ለኢንቨስትመንት በሚሰጥበት ጊዜ መመርያውን ባወጣው በራሱ በግብርና ሚኒስቴር ሕግ እንደሚጣስ በጥናትዎ አስቀምጠዋል፡፡ ለሰብል የሚፈቀደውን 20 ሺሕ ሔክታርና ለባዮ ፊውል የተፈቀደውን 50 ሺሕ ሔክታር መሬት በመጣስ አንዳንድ ኢንቨስተሮች በገፍ ወስደዋል ተብሏል፡፡ የዚህን ጉዳት እንዴት ያዩታል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ይህ እንግዲህ ራሱ የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ያወጣውን ደንብ አለማክበሩን እኮ ነው የሚያሳየው፡፡ ሌላ ምን ይባላል ? ራሱ ያወጣውን ሕግ በሥራ ላይ አላዋለውም፡፡

ሪፖርተር፡ - ምናልባት ተግባራዊ የሚያደርግበት ጊዜ ላይ ስላልደረሰ ይሆን ?

አቶ ደሳለኝ፡ - በሥራ ላይ ለማዋልማ እየተሞከረ ነው፡፡ የኪራይ ዋጋ ለምሳሌ ሥራ ላይ እየዋለ ነው፡፡ ሌሎቹ ሁኔታዎች ግን እንዴት እየተሠራባቸው እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ጥናቱን ያካሄድኩት ባለፈው ዓመት ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር መመርያውን በሥራ ላይ አላዋለም ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን የተሻሻለ ነገር ስለመኖሩ መመለስ ያለበት ራሱ ግብርና ሚኒስቴር ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ከውጭ ኢንቨስተሮች ጋር በተያያዘ በጥናትዎ ከተገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ተጨባጭ እውነታዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ የደረሱት ጉዳቶች ምን ምን እንደሆኑ ቢጠቃቅሱልን ?

አቶ ደሳለኝ፡ - የአካባቢ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ ገበሬዎችን ስናናግራቸው የተረዳነው እፅዋቶቻቸው እየጠፉባቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡ ዛፎች እየተቆረጡ ነው፡፡ በረጅም ጊዜ ሒደት ለአካባቢ አደጋ የሚፈጥር አካሄድ እየታየ ነው፡፡ ወደፊት የሚያሰጋን ነገር ትልልቆቹ ኢንቨስተሮች በእርሻቸው አካባቢ አግሮ ኬሚካሎችን መጠቀማቸው አይቀሬ መሆኑን ነው፡፡ እንደኛ ገበሬ በተፈጥሮአዊ መንገድ የሚያርሱ አይደሉም፡፡ አግሮ ኬሚካሉ ውሎ ሲያድር ውኃ ውስጥ ሰርጎ እየገባ ብዙ ጉዳት የማድረሱ ነገር አሳሳቢ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - አንዳንድ ኢንቨስተሮች ለአብነት ካሩቱሪ ለሚዲያዎች ሲናገር እንደሰማነው የተሰጠው መሬት ማዳበሪያ ሳያስፈልገው የሚታረስ መሆኑን ነው፡፡

አቶ ደሳለኝ፡ - በጊዜ ሒደት ማዳበሪያ መጠቀሙ አይቀሬ ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላ ሊታይ የሚችል ነው፡፡ ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ሲባል ማዳበሪያ መጠቀም ይመጣል፡፡

ሪፖርተር፡ - በጥናቱ የታየው አንኳር ጉዳይ የውጭ ኢንቨስተሮች ያገኙትን ትርፍና ገቢ ወደ አገራቸው መውሰድ እንደሚችሉ ነው፡፡ በውጭ ምንዛሪ ያገኙትን ገቢ በሙሉ መውሰድ ተፈቅዶላቸዋል ማለት ነው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - የኢንቨስትመንት አዋጁ እንደዚያ ነው የሚለው፡፡

ሪፖርተር፡ - የአገሪቱ ጥቅም ታዲያ የቱ ነው ? ምንድን ነው የአገሪቱ ትርፍ ?

አቶ ደሳለኝ፡ - እኔም አሳሳቢ ያልኩት ይህንኑ ነው፡፡ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አንዳንድ ኢኮኖሚስቶቻችንን ጠይቄያለሁ፡፡ ጥቅሙ የት እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል፡፡ አብዛኞቹ መሬት የያዙት ሰዎች ዛሬውኑ የግብርና ውጤት አይኖራቸውም፡፡ ግብርና ጊዜ ይወስዳል፤ ብዙ ሊመቻችለት የሚገባ ነገርም ይኖራል፡፡ የሚስተካከሉ ነገሮች ብዙ አሉ፡፡ እስካሁን ድረስ ትልልቆቹ አምራቾች አምርተው ወደ ገበያ አላወጡም፡፡ ሳዑዲ ስታር በዚህ ዓመት ወደ ወጭ እልካለሁ ብሎ ነበር፡፡ እውነትም ደርሶለት እንደሁ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ካሩቱሪም እልካለሁ ሲል ነበር፡፡ የዘራው ምርት በጎርፍ እንደተበላ አስታውቋል፡፡ ባኮ ላይ ያለው ምርቱም በአረምና በጎርፍ ተበልቷል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሰዎች ያገኙትን ገንዘብ ወደ ውጭ ይልኩታል ? አሊያም ምን ያደርጉታል ? የሚለው የሚታወቀው ከአምስት ዓመት በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ግን ያንን መገመት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡ - በአብዛኛው የተሰጣቸው መሬት አነስተኛ ገበሬዎች የነበሩበት ወይም ደግሞ ደን የነበረ መሆኑ ይነገራል፡፡ ኩባንያዎቹ የምግብ እጥረት ወዳሉባቸው አገሮቻቸው ኤክስፖርት እንደሚያደርጉም ግልጽ ነውና በአገሪቱ የምግብ ዋስትና ላይ ተፅዕኖ አያመጣም ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ይኼ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ መንግሥት ባወጣው የኢንቨስትመንት አዋጅ ኤክስፖርት ይበረታታል፡፡ ብዙ ኤክስፖርት ካደረግህ ብዙ ጥቅም ታገኛለህ፡፡ የፋይናንስ ማበረታቻ ይሰጥሀል፡፡ ስለዚህ አምርተው ወደ ውጭ የሚልኩ ይበረታታሉ፡፡ ግብርና ሚኒስቴር መሬቱን ሲሰጣቸው የውጭ ምንዛሪ ላይ በማተኰር ነው፡፡ መንግሥት የሚለው የውጭ ምንዛሪ እናገኝበታለን ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ግን እኰ የውጭ ምንዛሪውንም መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

አቶ ደሳለኝ፡ - ይችላሉ፡፡ በአዋጁ መሠረት ይችላሉ፡፡ እኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም፡፡ እናንተ ጥቅሙ የቱ እንደሆነ ብታነጋግሯቸው ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ የውጭ ምንዛሪ ይገኝበታል የሚባለው የመሬቱን ኪራይ መክፈላቸው ነው፡፡ እርግጥ ለአምስት ዓመትና ለመሳሰለው ሁሉ የእፎይታ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡ ሲከፍሉ ግን መንግሥት ያንን ይምራቸዋል ወይም ይተውላቸዋል ማለትም አይደለም፡፡ የመክፈያ ጊዜያቸው ሲደርስ ለእፎይታ የተሰጣቸውንም ደምረው ይከፍላሉ፡፡ የገንዘብ ምህረት አልተሰጣቸውም፤ ጊዜው ተራዘመላቸው እንጂ፡፡

ሪፖርተር፡ - ከታክስ ነው ማለት ነው መንግሥት የውጭ ምንዛሪ የሚያገኘው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - የመሬቱን ኪራይ መክፈል ሲጀምሩ ገንዘቡን ካገራቸው አምጥተው ይሁን ወይም ከሌላ ምንጭ ግልጽ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ግን መንግሥት ራሱ ኢንቨስተሮች ከአገር ውስጥ ባንኮች መበደር እንደሚችሉ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ካሩቱሪ ዘንድሮ 50 ሺሕ ሔክታር ላልማ ቢል ከባንክ በብር መበደር ይችላል ማለት ነው፡፡ ሌላው ነጥብ ኢንቨስተሮች ሁለት ዓይነት መሆናቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ለአብነት ሳዑዲ ስታርን ስናይ ከመሠረታቸው አምርተው ወደ አገሮቻቸው ለመላክ የመጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ አምርተው ወደ ዓለም ገበያ የሚያወጡ ናቸው፡፡ ህንዶች በሩዝ ምርት ራሳቸውን ችለው ተርፏቸው ወደ ውጭ ይሸጣሉ፡፡ ስለዚህ ካሩቱሪ እዚህ ሩዝ አምርቶ ህንድ ወስዶ ላይሸጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሕንድ በዘይት እህሎች፣ በጥራጥሬ ምርቶች፣ በአኩሪ አተር እጥረት ስላለበት ወደዚያ እንደሚልክ ይታሰባል፡፡ በአጠቃላይ ምርቱ እዚህ ቢመረትም የሚወጣ ነው ማለት ነው፡፡ ባዮፊውል የሚያመርቱት ላይ ያለው ዝንባሌ ምርቱ ከተገኘ በኋላ እዚሁ ይሸጣል የሚል ነው፡፡ እስካሁን ግን ይህንን ለማድረግ የቻለ የለም፡፡ ምርቱን ወደ ባዮፊውል ቀይሮ እዚህ ይሽጠው፣ ለውጭ ገበያ ያውጣው የታወቀ ነገር የለም፡፡ በምርቱ ሒደት ገና በሰብል ደረጃ ሳለ ችግር እየገጠማቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ጃትሮፋ መጤ ነው፡፡ እዚህ አገር አይታወቅም ነበር፡፡ ጃትሮፋ ለዚህ አገር መሬት ይስማማ አይስማማ፣ አዋጪ መሆኑ ገና አልታወቀም፡፡ ያዋጣል በሚል ግምት የተገባበት ነው፡፡ ሌላው የጉሎ ተክል እዚህም ያለ ቢሆን በኢንዱስትሪ ደረጃ ተመርቶ ባዮፊውል ወጥቶበት ገና አልተጀመረም፡፡ በኢንዱስትሪ ደረጃ ለባዮፊውል መድረሱም ገና አልታወቀም፡፡ አንዳንዶቹ በራሳቸው ተክለው፣ ሌሎቹ ደግሞ ገበሬው እንዲተክለው አድርገው እንገዛዋለን በማለት እያመረቱት ቢሆንም፣ ጥቅሙ ምን ያህል እንደሆነ ገና አይታወቅም፡፡

ሪፖርተር፡ - በጥናቱ ባዮፊውል ለአገር ውስጥ ፍጆታ እንደሚውል አረጋግጣችኋል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ኢንቨስተሮች አምርተው የትም መሸጥ መብታቸው ነው፡፡ እዚህ ወይም እዚያ ሽጡ ተብሎ ገደብ አልተቀመጠም፡፡ መንግሥት ለአገር ውስጥ ፍጆታ መዋል ያለበትን ለይቶ እንዲመረት ቢያደርግና ምርት እዚህ እንዲቀር ቢያደርግ ጥሩ ይሆን እንደነበር ጥናቱ አመልክቷል፡፡ መንግሥት ካመረታችሁት ይህንን ያህል በመቶውን አገር ውስጥ ሽጡ ቢል ኑሮ፣ ለምግብ ዋስትናችን ጥሩ ይሆን እንደነበር ጥናቱ ያመላክታል፡፡ ይኼ ግዴታ ግን የለባቸውም፡፡

ሪፖርተር፡ - ጥናቱ ያያቸው በዋናነት የእህልና የባዮፊውል ምርቶች ላይ ኢንቨስትመንት እየተካሄደ መሆኑን ነው፡፡

አቶ ደሳለኝ፡ - ኢንቨስትመንቱ ሦስት ዓይነት ዘርፎች ላይ እየተካሄደ ነው፡፡ አንዱ የምግብ እህል ነው፡፡ ትኩረቱም በሩዝና በቅባት እህሎች ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጥራጥሬዎችንም ይጨምራል፡፡ ሁለተኛው ባዮፊውል ነው፡፡ የምግብ እህልም ለባዮፊውል እንደሚውል በቆሎ ተጠቃሽ ነው፡፡ ሦስተኛው የኢንዱስትሪ ሰብሎች የሚባሉትን የሚመለከት ነው፡፡ የሸንኰራ አገዳና ጥጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ጥጥ አምርቶ እዚህ ፋብሪካ ካለው ለግብዓትነት ይጠቀምበታል፡፡ ወደ ውጭ እልከዋለሁ ካለም አይከለከልም፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የኮንትራት ውሉ ላይ እንዳሰፈረው አምራቹ ያመረተውን ምርት ምን እንደሚያደርግ ሙሉ መብትና ውሳኔ የራሱ የኢንቨስተሩ እንጂ የመንግሥት አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡ - በእኛ አገር የኢንቨስተሮቹ አትኩሮት ከምግብ ሰብል ወይም ከባዮፊውል ወደየትኛው ያመዘነ ነው ? አኃዞችስ ሊቀርቡበት ይችላሉ ?

አቶ ደሳለኝ፡ - አኃዝ ለማግኘት ስንሞክር የፌዴራል ግብርና .. 2008 በኋላ የሰጣቸውን የኢንቨስተሮች ጉዳይን ብቻ ነው የያዘው፡፡ ከዚያ በፊት ያለውን ክልሎች በራሳቸው ስለሰጡ የእነርሱ መረጃ የለውም፡፡ ሆኖም ግብርና ሚኒስቴር ካለው መረጃ ስንነሳ በብዛት ያተኰረው የኢንዱስትሪ ሰብሎች ላይ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ገና በግልጽ የታወቀ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡ - መንግሥት በኢትዮጵያ የመሬት ሽሚያ እንደሌለ ሽንጡን ገትሮ ይከራከራል፡፡ በቅርቡም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ አገሪቱ ካላት መሬት አኳያ እዚህ ግባ የማይባል መሬት ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ ጥናትዎን መሠረት አድርገው እንዴት ይመለከቱታል ? እውነት የመሬት ሽሚያ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ?

አቶ ደሳለኝ፡ - በቃላት መጫወትና መጣላት ጥቅም የለውም፡፡ ትልልቅ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ትልልቅ መሬት ተሰጥቷቸው ኮንትራት ፈርመው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ይህንን እንግዲህ የመሬት ሽሚያ እንበለው ወይም የግብርና መሬት ኢንቨስትመንት እንበለው (የዓለም ባንክ እንደሚለው ) የግብርና ማስፋፋት፣ ዘመናዊ ኢንቨስትመንት፣ የቱ መባል እንዳለበት ምናልባት የጋዜጠኞች ወይም የሌሎች ጉዳይ ነው፡፡ ሁኔታው ግን አለ፡፡ የመሬት ሽሚያ የሚለውን ቃል እኔ አልወደውም፡፡ ለምን ቢባል ገና ቁምነገሩ ላይ ሳንነጋገር ወደ ፀብ ስለሚያመራን ነው፡፡ ነገሩን በደንብ እንየውና እንመርምረው፡፡ እየተካሄደ ያለውን እንወቀው በሚል መነሻ እኔ ‹‹የመሬት ኢንቨስትመንት›› ማለቱን መርጫለሁ፡፡ የመሬት ሽሚያ ከተባለም የማየው ነው፡፡ አዝማሚያው በብዛት የውጭ ኢንቨስትመንት ላይ ነው፡፡ ከአንዱ በስተቀር የኢትዮጵያ ኢንቨስተሮች በንፅፅር ሁለት ወይም ሦስት ሺሕ ሔክታር ነው የሚያገኙት፡፡ ጥቂቶች አምስት ሺሕ የያዙ አለ፡፡ ዳያስፖራውም እንደዚያው ነው፡፡ የኢንቨስትመንት ፕሮግራሙ በግልጽ አይናገረውም እንጂ አዝማሚያው የውጭ ኢንቨስትመንትና ኢንቨስተሮች ላይ ቀልቡ ያረፈ ነው፡፡ መንግሥትም የውጭ ኢንቨስተሮች የተሻለ ካፒታል፣ የተሻለ ቴክኖሎጂ፣ የተሻለ የእርሻ ዘዴ አላቸው እያለ ነው፡፡ ካፒታል ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ካሩቱሪ ትልቅ ከባንያ ነው፡፡ የተሻለ የእርሻ ዘዴ አላቸው የሚለው ለእኔ ያጠራጥረኛል፡፡

ሪፖርተር፡ - መንግሥት ለውጭ ባለሃብቶች ያደላው የቴክኖሎጂ ሽግግር አገኛለሁ በማለት ነው፡፡ እርስዎ መስክ ሔደው ባካሄዱት ጥናት እነዚህ የሚባሉት ነገሮች እውነት ይታያሉ ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ቴክኖሎጂ ከየት ወዴት እንደሚሸጋገር ግልጽ አይደለም፡፡ መንግሥት ይህንን ግልጽ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ከኢንቨስተሩ ወደ አነስተኛ ገበሬዎች ይሻገራል ማለት ቀልድ ይመስለኛል፡፡ ኢንቨስተሩ በትልልቅ ማሽን ቢሠራ አንድ ሔክታር ወይም ግማሽ ሔክታር ላይ የሚያርሰው ገበሬ ያንን ተሞክሮ ይወስዳል መባሉ ለእኔ አይታየኝም፡፡

ሪፖርተር፡ - ስለዚህ ግብርና ላይ ምንም የቴክኖሎጂ ሽግግር አይኖርም ማለት ነው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - እኔ ምንም የቴክኖሎጂ ሽግግር የለም ባይነኝ፡፡ በጥናቱም ያስቀመጥኩት እርሱን ነው፡፡ ለምን ቢባል አነስተኛ መሬት ላይ የሚጣጣረው ገበሬ ከእነዚያ ግዙፍ ኩባንያዎች የሚወስደው ነገር መኖሩ አይታየኝም፡፡ የእርሻዎቹ ዓይነት የሚጠይቁት ቴክኖሎጂ የተለያየ ነው፡፡ ሰፋፊ እርሻዎችና ትናንሾቹ የሚመጣጠኑበት ምንም ነገር የለም፡፡ የአገር ውስጥ የግብርና ምሁራን እንደነ ካሩቱሪ ያሉት እዚህ መጥተው የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ ሳያውቁ ዘለው ወደ እርሻ መግባታቸውን እየተቹ ነው፡፡ ገበሬው በሚያየውና ባለው ዕውቀቱ መሠረት እነዚህ ኩባንያዎች የሚሠሩትን እያየ እየሳቀባቸው እኰ ነው፡፡ የእርሻ ዘዴያቸው ከገበሬው የሚሻል ሆኖ አልተገኘም፡፡ ምርታማነታቸውን ወደፊት ለማሳደግ አግሮ ኬሚካል በሰፊው እየረጩ የሚጠቀሙ ይመስለኛል፡፡ ይኼ ደግሞ አካባቢ ላይ የሚያመጣው ችግር ግልጽ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - በጥቅሉ ለእርሻ ዘርፍ ትልልቆቹ ኢንቨስትመንቶች የሚያመጡት የቴክኖሎጂ ልውውጥና ሽግግር የለም ብሎ መደምደም ይቻላል ማለት ነው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - እኔ እንደሚገባኝ አዎ፡፡

ሪፖርተር፡ - ከጥናትዎ አኳያ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች መሰጠቱ የሚያመጣውን ተፅዕኖ ነጥብ በነጥብ ቃኝተዋል፡፡ ጠቅለል ባለ ሁኔታ የሚያመጡትን ጉዳት ቢገልጹልን ?

አቶ ደሳለኝ፡ - የሚያሳስቡ ነገሮች አሉ፡፡ የውጭ ኢንቨስተሮች ካፒታሊስት ናቸው፡፡ ትርፍ ነው የሚፈልጉት፡፡ በተቻለ መጠን ቶሎ ትርፍ ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ አካባቢ ይጉዳ አይጉዳ ጥያቄ ውስጥ መግባት የሚፈልጉ አይመስለኝም፡፡ ይኼ ትልቅ ጉዳት ይፈጥርብናል፡፡ ሌላው ትልቅ ትኩረት ያስፈልገዋል የምለው ኢንቨስትመንቱ ሲሰጣቸው የሚያመርቱትን ወደ ውጭ መላኩ ላይ ያተኰረ ስለሆነ የአገሪቱን የምግብ ዋስትና የሚመለከትና የሚፈታ አይሆንም፡፡ ወደ ውጭም እንዲላክ የፋይናንስና ሌላም ማበረታቻ ይሰጠዋል፡፡ መንግሥት የሚፈልገው ወደ ውጭ መላኩን ነው፡፡ የውጭ ምንዛሪ አገኛለሁ በሚል ተስፋ፡፡ ስለዚህ ይኼንን ሁሉ መሬት ይዞ ምርቱን ወደ ውጭ መላክ የአገሪቱን የምግብ ዋስትና ችግር የሚያባብስ ነው፡፡ የምግብ ዋስትና ችግር እርግጥ ይህ መንግሥት የፈጠረው አይደለም፡፡ ቀድሞ የነበረ ነው፡፡ የሺሕ ዓመት ታሪክ ብናይ ይኼ አገር በምግብ ራሱን እንዳልቻለ እንረዳለን፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ለምን ኢንቨስትመንቱ ከምግብ ዋስትና ጋር መያያዝ እንዳልቻለ አሳሳቢ ነው፡፡ ለጊዜው እነዚህ እርሻዎች ቀጥታ ለምግብ ዋስትናው ችግር አስተዋፅኦ ባያደርጉም ውሎ አድሮ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ የሥነ ምኅዳር ችግሩ እንዳለ ሆኖ ነው እንግዲህ፡፡ በተለይ ኦሮሚያ ውስጥ የሚሰጡ መሬቶች የግጦሽ መሬቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ የአካባቢና የምግብ ዋስትናን ችግሮች ያባብሳሉ፡፡

ሪፖርተር፡ - ጥናቱ ለሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ቀርቧል ተብሎ ይገመታልና ምላሻቸው ምን ይመስላል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ጥናቱን ወስደን ባንሰጣቸውም የውይይት መድረክ አካሂደናል፡፡ ጥናቱም ለሕዝብ ይፋ ሆኗል፡፡ ተበትኗል፡፡ ባለሥልጣኖቹ ግን ያዩትም አይመስለኝም፡፡

ሪፖርተር፡ - ወደኋላ ልመልስዎትና አንዳንድ በመሬት አሰጣጥ ላይ የሚወጡ የመንግሥት መረጃዎች እርስ በርስ የሚጣረሱ ናቸው፡፡ ክልሎች የሚሉትና የፌዴራሉ የሚናገረው ይለያያል፡፡ ይህንን መስክ ሄዳችሁ እንዳጣራችሁ መገመት ይቻላል ? እንደዚህ ያለውስ አሠራር ምን ዓይነት ስጋት ያመጣል ?

አቶ ደሳለኝ፡ መሬት መስጠት የተጀመረው ይህ መንግሥት ሥልጣን በያዘ በሦስተኛና በአራተኛው ዓመት ገደማ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ለኢኮኖሚው ጥቅም በማለት መሬት ጠይቀው በየክልሉ መስጠት ከተጀመረ ቆይቷል፡፡ ያንን ክልሎች ነበሩ የሚያከናውኑት፡፡ እነኚህ መሬቶች ትንንሾች ናቸው፡፡ ግፋ ቢል 200 500 አልፎ አልፎ ሁለት ሺሕ ሔክታር የተሰጣቸው በርካቶች ናቸው፡፡ የመረጃ ቋቱን ተመልክተን ያረጋገጥነው ከወሰዱት አብዛኞቹ አልተጠቀሙበትም፡፡ አንዳንድ ቦታ እንዲያውም መሬቱ ላይ የነበረውን ዛፍ ጨፍጭፈው ከሸጡ በኋላ እጃቸውን አጣምረው ቁጭ ያሉ አሉ፡፡ እስካሁን ድረስ በቤንሻንጉል ይህ ነገር እየተከሰተ ሰዎችን ወደ ፍርድ ቤት ለማቅረብ እያሰቡ ናቸው፡፡ ሁኔታዎች የተቀየሩት የዓለም የምግብ ቀውስ ሲመጣ ነው፡፡ በተለይ 1998 . በኋላ ማለት ነው፡፡ ኢንቨስተሮች በተለይ የእስያዎቹ ህንድና ቻይና የምግብ ችግራቸውን ለመቅረፍ መሬት ባላቸው አገሮች ተከራይተን አምርተን ወደ አገራችን እንውሰድ ብለው ተነስተዋል፡፡ አፍሪካን መዳረሻ አድርገዋል፡፡ በተለይ የመካከለኛው ምሥራቆቹ የእርሻ መሬት ስለሌላቸው ይህንን መንገድ ይመርጣሉ፡፡ ብዙ ገንዘብ ቢኖራቸውም ገንዘብ አይበላም፡፡ በዓለም ገበያ ውስጥ በቀውሱ ምክንያት ምግብ ጠፍቷል፡፡ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ይዘህ ብትዞር ምግብ የሚሸጥልህ የለም፡፡ ወደ አፍሪካ ያመጣቸው ይኼ ነው፡፡ ይኼንን ነገር በኢትዮጵያ ብቻ መገደብ የለባችሁም፡፡ አፍሪካ በሙሉ ነው፡፡ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ በትንሹም ቢሆን ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ አንጎላን ጨምሮ 22 የአፍሪካ አገሮች እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የመሬት ኢንቨስትመንት እያሉ እየሰጡ ናቸው፡፡ የውጭ አገሮች ለምግብ ዋስትናቸው ሲሉ መምጣታቸው ነው የእኛንም መንግሥት መጠቀም አለብኝ ከሚል ስሜት የከተተው፡፡ የመሬት ኢንቨስትመንት ፕሮግራሙን ሰፋ አድርጎ ያወጣው ያን ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የያዙት እንዳሉ ናቸው፡፡
አንዳንዶቹ እየተወሰደባቸው ነው፡፡ በተለይ .. 2002 የኢንቨስትመንቱ ሕግ ሲመጣና ለጋሽነቱን ሲያሳይ ብዙ ኢንቨስተሮች ለመምጣት አበረታታቸው፡፡ የአፍሪካ ኅብረት ጉዳዩ አሳስቦት ውይይቶችን ማድረግ እየጀመረ ነው፡፡ በመሬት ኢንቨስትመንት ላይ አሳሳቢ ጉዳዮች እየተከሱ በመሆኑ አንድ ወጥ ፖሊሲ እንዲኖር እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡ - ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲነፃፀር የእኛ አሳሳቢነቱ ምን ያህል ነው ? በጣም የተጋለጠ ስጋት ጋርጦብናል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁሉም የሚታየው አንድ አይነት አካሄድ ነው፡፡

ሪፖርተር፡ - ጥናቱ እንደ መፍትሔ የሚያቀርባቸው አንኳር ነጥቦች ምንድን ናቸው ?

አቶ ደሳለኝ፡ - ነገሩ አሳሳቢ የሆነው መንግሥት ከመነሻው ከሕዝቡ ጋር ውይይት አለማድረጉ ነው፡፡ መንግሥት አጋጣሚውን ለመጠቀም በችኮላ የገባበት ነው፡፡ አንዳንድ ክልሎች ኢንቨስተሩ በጻፈው ደብዳቤ ብቻ መሬት ሲሰጡም ነበር፡፡ ወደኋላው ላይ በትንሹም ቢሆን መልክ እንዲይዝና አካሄድ እንዲኖረው እየተደረገ ነው፡፡ አንድ አካባቢ ላይ መንግሥት ራሱ ለእርሻ የሚሆን 50 ሚሊዮን ሔክታር መሬት አለኝ ብሎ ነበር፡፡ ቆየና ደግሞ 10 ሚሊዮን አለኝ ብሎ ጽፏል፡፡ አሁን አሁን መልክ ለማስያዝ እየተሞከረ ነው፡፡ ሆኖም በቅርብ የወጣው መመርያም ሙሉ ለሙሉ ሥራ ላይ አልዋለም፡፡ ስለዚህ ትልቁ ነገር የሕዝብ ውይይት ሊደረግበት የሚገባ ይመስለኛል፡፡ በርካታ ባለሙያዎች፣ ገበሬው ጭምር ሐሳብ ይስጡበት፡፡ ሌላው መሬት የመንግሥት በመሆኑ መንግሥት መስጠት ስለሚችል በየአካባቢው ያሉትን የግብርና ባለሙያዎች ሳያማክሩ ነው የሚገቡበት፡፡ ውይይትም አልተደረገም፡፡ ምክክር ያስፈልጋል፡፡ ሌላው ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ የውጭ ኢንቨስትመንት አይኑር የሚል ሰው አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የሚሰጠን ጥቅም በደንብ ታይቶ፣ የሚሰጥበት አካባቢ ያሉ ሰዎችንም አማክሮና ተወያይቶ ቢደረግ፣ ጥቅም የመጋራት ሥርዓት ቢኖረው የተሻለ ነው እላለሁ፡፡ ጥቅም መጋራት በዓለም ደረጃ በቅርብ የወጣ አሠራር ነው፡፡ የማዕድን ፍለጋ ላይ የሚሠሩ ኩባንያዎች ዱሮ እንደልባቸው ማዕድኑን አውጥተው መሸጥ ነበር ሥራቸው፡፡ አሁን ግን አንዳንድ አካባቢ የሚደረገው ኩባንያው ካገኘው ትርፍ 20 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ መልሶ ማዕድኑን ወዳገኘበት አካባቢ ኢንቨስት እንዲያደርግ ነው፡፡ ይኼን ዓይነት አመላካከት ቢኖር ጥሩ ነበር፡፡ ጋምቤላ ላይ አንድ ኢንቨስተር ገብቶ፣ ሠርቶ ከትርፉ ይህንን ያህል እዚያው ኢንቨስት አድርግ ቢባል ጥሩ ነበር፡፡ ሌላው ጥንቃቄና አስፈላጊ ቁጥጥር በአካባቢ ተፅዕኖ ላይ ሲደረግ አይታይም፡፡ ይህንን ቁጥጥር የሚያደርጉት በክልል ያሉ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮዎች ናቸው፡፡ ቁጥጥር ለማድረግ አቅሙም፣ ሙያውም በበቂ የላቸውም፡፡ እነሱ ይኼን አድርግ ያንን አታድርግ ብለው ኢንቨስተሩን ለመቋቋም አቅም የላቸውም፡፡ እነዚህ አካላት አቅም ካገኙ በኋላ ነበር ቢያንስ ኢንቨስትመንቱ መካሄድ የነበረበት፡፡ ገና አልሆነም፡፡ አሁንም ደግሜ የምናገረው የመሬት ኢንቨስትመንቱ የዚህችን አገር የምግብ ዋስትና አያረጋግጥም ነው፡፡ ይኼ ያሳስባል፡፡

ሪፖርተር፡ - አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከራከሩበትን ነጥብ ላንሳ፡፡ የተሰጠው መሬት ካለው ያልተነካ መሬት አኳያ የመሬት ሽሚያ አሳሳቢ አይደለም ብለዋል፡፡ አሁን ካለው መሬት ምን ያህሉ እንደተሰጠ ጥናትዎ ሊያየው ሞክሯል ?

አቶ ደሳለኝ፡ - አስቸጋሪ ነው፡፡ ካለን ከጠቅላላው መሬት አይደለም የተሰጠው፡፡ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ ለግብርና የሚውል መሬት ምን ያህል ነው ? ከዚህ ውስጥ ገበሬው የማይጠቀምበት ምን ያህል አለ ነው ጥያቄው፡፡ እንጂ በጠቅላላው ምን ያህል መሬት አለ አይደለም፡፡ ሊታረስ የሚችልና ከታረሰ የአካባቢ ጉዳት ሊያመጣ የማይችል ምን ያህሉ ነው እንጂ መነጋጋሪያው የአገሩቱ ጂኦግራፊያዊ ስፋትማ ትልቅ ነው፡፡ በእኔ ግምት በእነኚህ መስፈርቶች ስንነሳ ሊኖር የሚችለው መሬት በጣም ትንሽ ነው፡፡ መሬት ብዙ ስላለን እንሰጣለን የሚባለው ነገር ትክክል አይደለም ባይ ነኝ፡፡ ባዶ መሬት ስላለ ብቻ ጥቅም ላይ አልዋለም፤ ለውጭ መሰጠት አለበት ማለት አይቻልም፡፡ ከጥቅም አኳያ ሲታይም ገበሬው የሚያርሰው፣ ለግጦሽ የሚፈልገው፣ ለቤት መሥሪያና ለማገዶ፣ ለውኃ ምንጭነት የሚፈልገው መሬት ስላለ ገበሬው ያልያዘው፣ ያልተጠቀመበት የሚባለው አገላለጽ ትክክል አይደለም፡፡ ገበሬው የሚያርሳት አንድ ሔክታር መሬት ብቻ ተይዛ፣ ይህች ነች የገበሬው መሬት ሌላው ባዶ ነው ማለት ትክክል አይደለም፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Dec 02, 2011 1:33 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የመሬት ባለቤትነት መብት የአንድ አገር ዜጎች የሕልውናቸው መሠረት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም :: ኢትዮጵያውያን ለረዥም ዘመናት የራሣቸው መሬት ባለቤት የሚሆኑባት አገር እንዲኖራቸው ታግለዋል :: በንጉሣውያን የአገዛዝ ዘመን እንኳን የኢትዮጵያ ሕዝብ በየጊዜው የመሬት ይዞታ ሥሪት እንዲሻሻል ከፍተኛ ትግል አድርጓል :: እንዲያውም 1950 እና 60 ለኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ዋና መፈክር የነበረው "መሬት ለአራሹ " ነበር :: ነገር ግን ከዚያ የተማሪ እንቅስቃሴ የወጡ የወያኔ መሪዎች መሬትን በሚመለከት የሚከተሉት ፖሊሲ በተማሪነታቸው ዘመን ይሉ የነበረውን ተቃራኒ ነው :: እንዲያውም ወያኔዎች ከዚህም አልፈው የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መሬት ለሕንዶች : ለቻይኖች : ለአረቦችና ለምዕራባውያን ከዚያም አልፎ ለአንዳንድ አምባገነን የአፍሪቃ አገሮች ገዢዎች በካሬ ሜትር በትንሽ ሣንቲም በመቸብቸብ ላይ ናቸው :: በተቋም ደረጃ ጥናት እያደረጉ ይህንን የወያኔን ድርጊት ሃቁን ለሕዝብ በማሣወቅና ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ዘመቻ እንዲጧጧፍ በማድረግ ላይ ከሚገኙት አንዱ ካሊፎርኒያ ግዛት (አሜሪካ ) የሚገኘው የኦክላንድ ኢንስቲትዩት ነው :: ሠሞኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሩናንዳ ሚታ ለኢሣት ጋዜጠኛ አበበ ገላው ቃለ -መጠይቅ ሠጥተዋል : ተከታተሉት ::

ምንጭ :- Uploaded by ESATelevision on Nov 29, 2011, ESAT Ethiopia: Oakland Institute Director Anuradha Mittal on land grab in Ethiopia.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1762
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Fri Dec 02, 2011 3:18 pm    Post subject: Reply with quote

ተላ ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት አቃተህ ? የጭቃ እሾህ ::

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
በአርአያ ሰላሴ ተፈጠርኩ ለምትለው ተድላ
ኑሮው እንዴት ይዞሀል ?
ያማርኛ አጻጻፍ - መናልባትም ያነጋገር ችሎታህን በማድነቅ ልጀምር :: እንዳው በደፈናው ውብ ነው - በቅን ላየው ስው ::
ከሞላ ጎደል በዛ ያሉ ጽሁፎችህን በማንበቤ የሚከተለውን ቀጥተኛ መጠይቅ ላቀርብ ፈልኩ ::

ባንተና ልብህ በሚደግፈው የፖለቲካ ድርጅት እምነት ለአንድ ሰው ኢትዮጵያዊነት መለክያው ምንድነው ?

_________________
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Dec 02, 2011 9:14 pm    Post subject: Reply with quote

ቢተወደድ እንደጻፈ(ች)ው:
ተላ ለዚህ ጥያቄ መልስ መስጠት አቃተህ ? የጭቃ እሾህ ::

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
በአርአያ ሰላሴ ተፈጠርኩ ለምትለው ተድላ
ኑሮው እንዴት ይዞሀል ?
ያማርኛ አጻጻፍ - መናልባትም ያነጋገር ችሎታህን በማድነቅ ልጀምር :: እንዳው በደፈናው ውብ ነው - በቅን ላየው ስው ::
ከሞላ ጎደል በዛ ያሉ ጽሁፎችህን በማንበቤ የሚከተለውን ቀጥተኛ መጠይቅ ላቀርብ ፈልኩ ::

ባንተና ልብህ በሚደግፈው የፖለቲካ ድርጅት እምነት ለአንድ ሰው ኢትዮጵያዊነት መለክያው ምንድነው ?

እንዴ አንተ ወያኔ መቼ ነው የምትሻሻለው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ዕድሜ ልክህን ዘለፋ -አዘል ጥያቄ በመጠየቅ ጡረታ ልትወጣ ነው Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing መሠረተ ትምህርትም ቢሆን ተማርና አንድ አንቀፅ የሚሞላ በሥድብ ያልታጀለ አስተያዬት ለመሥጠት ሞክር Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 4:41 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የኢትዮጵያ መሬት በወያኔዎች በካሬ ሜትር እየተለካ እየተቸበቸበ መሆኑ ይታወቃል :: አሁን አሁን የያዙት የማደናገሪያ ሙግት "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የእርሻ ዘዴ እጅግ ኋላ ቀር በመሆኑ ያንን ለማሻሻል ከውጪ መዋዕለ -ንዋይና ቴክኖሎጂ ማስገባት አለብን ::" የሚል ነው :: ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ መንገድ እርሻ ማረስ የተጀመረው በአፄ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን ሲሆን 40 ዓመት በፊት ከአለማያ ኮሌጅና ከተለያዩ መለስተኛ የእርሻ ኮሌጆች (ጅማ : አምቦ : ደብረ ዘይትና አዋሣ ) ተመርቀው ይወጡ የነበሩ የእርሻ ባለሙያዎች ሠፋፊ እርሻዎችን በማልማት የእርሻ ሥራን ዘመናዊ ለማድረግ ከፍተኛ እርምጃ አሣይተው ነበር :: በኋላ ላይ ደርግ 1967 .. ስልጣን ሲይዝ "መሬት ለአራሹ " : "የግል የማምረቻ ድርጅቶች : ፋብሪካዎች : ባንኮችና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን እንዲሁም ሠፋፊ እርሻዎችን የመንግሥት : የሚያደርጉ አዋጆችን በማውጣት ተጀምሮ የነበረውን የካፒታሊስት ሥርዓት ግንባታ አጨናገፈው :: ቢሆንም ደርግ የወረሣቸውን የግል እርሻዎች "የመንግሥት እርሻዎች ሚኒስቴር " በሚባል መሥሪያ ቤት ሥር አዋቅሮ እስኪወድቅ ድረስ ሲያንቀሣቅሣቸው ኖሯል : ከፍተኛ የሆነ ምርትም ሲታፈሥባቸው ኖሯል :: ወያኔ እንደገባ ከሻቢያ ጋር ተመሣጥሮ እኒያን የመንግሥት እርሻዎች ንብረት ሙሉ በሙሉ ዘረፋቸው : እርሻዎችም የአይጥ መፈልፈያ ባድማዎች ሆነው ቀሩ :: አሁን ወያኔ አዲስ ቅኝ ገዢዎችን ከሕንድ : ሣዑዲ አረቢያ : ቻይና እና ሌሎች አገሮች እያስመጣ መሬትን ባልረባ ክፍያ 25 እስከ 99 ዓመት ድረስ በሚደርስ ሊዝ ይሸጣል :: ታዲያ ዘመናዊ እርሻ እንዴት ተደርጎ አሁን በወያኔ የአገዛዝ ዘመን እንደ አዲስ ወደ ኢትዮጵያ ገባ ተብሎ በጋዜጣ ይጻፋል ?

የዛሬ 40 ዓመት ሕንድ ዜጎቿ በርሃብ የሚያልቁባት የምድር ሲዖል ነበረች : ቻይናም 50 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎቿን ለረሃብ ገብራለች :: ዛሬ እኒህ አገሮች ከራሣቸው አልፈው ለእኛም "ቴክኖሎጂ አቋዳሽ " ሆነው ቀርበዋል :: እኒህ አገሮች የነበረባቸውን የምግብ ችግር የተወጡት የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ወይም የሩሲያ ኃብታም ገበሬዎችን " እና መሬታችንን በሊዝ ገዝታችሁ አልሙ : ለራሣችሁ ተጠቀሙ : እኛ በዕርዳታ ምግብ ኑሯችንን እንገፋለን ::" በሚል የወለፌንድ ፖሊሲ በመመራት አልነበረም : የራሣቸወን ዜጎች የተሻለ የእርሻ ምርት የሚያመርቱበትን ብልሃት ፈልገው ጠቃሚና የሚያሠሩ ፖሊሲዎችን በማውጣት ነበር :: ዲቃላው ወያኔ ግን ያንን አንሸዋሮ ሌላ ያወራል :: እስኪ ይህንን በጆናታን ሩግማን የተዘጋጀ "Channel 4" ዘገባ አንብባችሁ የራሣችሁን ፍርድ ሥጡ ::

ምንጭ :- Jonathan Rugman (Channel 4, Foreign Affairs Correspondent), Saturday 07 January 2012. Africa succumbs to colonial-style land grab.

Quote:
Nations like Ethiopia are desperate for the investment. But critics claim it's at the expense of smallholder farmers - many of whom say they're being thrown off their land to make way for the large multi-nationals.

Think of drought-stricken Ethiopia and you might not expect to see modern machinery owned by a foreign multinational, cultivating vast farms in one of the poorest countries in the world.

The goal here is simple: to double Ethiopia's agricultural production and to make it self-sufficient. So that handouts from Britain, America and others are no longer required.

Agrarian revolution

Vinay Shekar is on the front line of this agrarian revolution. He's a farm manager from India running an estate in Ethiopia.

His company is called Karuturi and these 29,000 acres are a small slice of its empire - with the Ethiopians pledging almost 800,000 acres to the Indian firm so far.

Ethiopia's land is owned by its post-Communist government - and that land can't feed its people. Farming methods are medieval, with the land parcelled up among millions of small scale tenant farmers. So now the country's Agriculture Minister, Ato Wondirad Mande, is giving foreign companies like Karuturi cheap leases to revolutionise food production.

He told Channel 4 News: "We give land because we cannot produce on that land. Because of lack of capital and technology, thats why. They open a big opportunity for employment and of course generation of taxes and other financial gain."

But farmer Gemechu Garbaba talks of loss, not gain. Hes pointing to Karuturi farmland, which he says the government took from him to give to the Indians instead.

"When they first came they told us an investor was coming and we would develop the land alongside one another,"Mr Garbaba told Channel 4 News. "They didn't say the land would be taken away from us entirely. I don't understand why the government took the land."

Mr Garbaba now grows maize on land nearby which he sublets each year from a neighbour. It is precarious, he says. He could lose his tenancy at any moment.

And at the family home his wife complains that the cattle have almost nowhere to graze because their old fields have gone.

"Since the land was taken away from us we are impoverished. Nothing has gone right for us, since these investors came," he added.

Next door Karuturi is beginning to work agricultural wonders. It runs the farm under a 50 year lease, and says it will sell most of its produce inside Ethiopia itself.

Who profits?

With their Indian manager watching them, these women say they are grateful to have a job earning just under fifty pence each per day.

Karuturi can see such good profits that it's investing nearly a billion dollars in Ethiopia. Though in an interview in 2010 the company's founder said it was shameful to accuse the firm of "land grabs" when the country's being transformed.

Sai Ramakrishna Karuturi, Managing Director at Karuturi Global, said: "Why do they need to import food? Its a shame, I sometimes feel like it's a conspiracy - that people want Africa to remain with a begging bowl.

"Here we are creating employment, food, wealth isn't that what Adam Smith spoke about - isn't that the reason the West is self sufficient? I don't think creating wealth is a crime."

Yet in this village hut everyone complains they have less food than before because Karuturi now farms where they once did.

Taresa Agasa helped put together a petition to change the governments mind. But when that didn't work, he took a job as a security guard for Karuturi for 45 pence a day.

He said: "We wish we could eat three times a day. I know my children want this. But I cannot provide that. We live and survive only if we have land. And we would rather have our land back."

Ethiopia's agriculture minister claims there is no conflict with local communities and no need to provide compensation.

Yet people here speak bitterly of forced evictions, and this is just a snapshot of a story now playing out all over Africa - as multinationals strike land deals with governments desperate for investment.

The risk is colonial style plantations with local people swept aside. In a world badly in need of more food, costing less.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 12, 13, 14, 15  Next
Page 13 of 15

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia