View previous topic :: View next topic
Author
Message
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Nov 28, 2011 4:17 am Post subject:
እሑድ ኅዳር 18 ቀን 2004 ዓ .ም .
ዓመታዊው የቤይሩት (ሊባኖስ ) ማራቶን
የቤይሩት ማራቶን በዓለም ዙሪያ እምብዛም የሚነገርለትና የሚታወቅ ታላቅ ውድድር አይደለም :: ቢሆንም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቅርብ ዓመታት በተከታታይ የሥፍራው አሸናፊዎች በመሆን ዝናቸውን ለመትከል በቅተዋል :: በዘንድሮው ውድድር በሴቶች ምድብ ሰዓዳ ከድር በ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 38 ሴኮንድ 1ኛ ስትሆን በወንዶች ምድብ ደግሞ የአገሯ ልጅ ታሪኩ ጅፋር በ 2 ሰዓት 11 ደቂቃ 14 ሴኮንድ ቀዳሚ በመሆን ውድድሩን አሸንፏል :: በዚህ ውድድር በሴቶችም ሆነ በወንዶች ምድቦች የሥፍራው ሬኮርድ ሰዓት ተሻሽሏል :: የኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ውጤት ብቻ የሚያሣየው ሠንጠረዥ የሚከተለውን ይመሥላል ::
ምንጭ :- Organizers (IAAF), Sunday, 27 November 2011. Course records fall in Beirut.
የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ሰዓዳ ከድር _____________ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 38 ሴኮንድ
2ኛ ..... ብዙነሽ ኡርጌሣ መሐመድ ___ 2 ሰዓት 32 ደቂቃ 52 ሴኮንድ
5ኛ ..... ሲሣይ መኣሾ አርሠዲ _____ 2 ሰዓት 36 ደቂቃ 22 ሴኮንድ
6ኛ ..... እታፈራሁ ታረቀኝ ጌታሁን __ 2 ሰዓት 38 ደቂቃ 47 ሴኮንድ
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ታሪኩ ጅፋር __________ 2 ሰዓት 11 ደቂቃ 14 ሴኮንድ
5ኛ ..... መሐመድ ተማም ሁሴን ___ 2 ሰዓት 13 ደቂቃ 37 ሴኮንድ
8ኛ ..... ሰሎሞን ሞላ __________ 2 ሰዓት 17 ደቂቃ 37 ሴኮንድ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Nov 28, 2011 5:25 am Post subject:
እሑድ ኅዳር 18 ቀን 2004 ዓ .ም .
የኤርቴል -ዴልሂ (ሕንድ ) የግማሽ ማራቶን ውድድር
የግማሽ ማራቶን ውድድሮች በማራቶን ውድድር ለወደፊት ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ተለይተው የሚታወቁበትና ማራቶን በመወዳደር ላይ የሚገኙት ደግሞ ወቅታዊ ብቃታቸው የሚፈተንበት መለኪያ ተደርጎ ይወሠዳል ::
በዘንድሮው የዴልሂ የግማሽ ማራቶን ውድድር የወንዶችን ምድብ ኢትዮጵያዊው ሌሊሣ ደሢሣ በ 59 ደቂቃ 30 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ርቀቱን ለመሸፈን ይወስድበት የነበረውን የራሱን የግል ሰዓት በማሻሻል አሸንፏል :: ሌሊሣ ለወደፊቱ በማራቶን የዓለምን ሬኮርድ ለመሥበር ብቃት ያለው አትሌት ይመሥላል ::
በሴቶች ምድብ የአሸናፊነቱን አክሊል የደፉት የዘወትር የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተፎካካሪ የሆኑት የኬንያ አትሌቶች ናቸው :: ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ከ 1ኛ እስከ 20ኛ ደረጃ ካሉት ደረጃዎች በወንዶች ምድብ አምሥት : በሴቶች ምድብ ደግሞ ሰባት ሥፍራዎችን ይዘዋል ::
የኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ውጤት ዝርዝር የሚከተለው መልክ አለው ::
ምንጭ :- Ram Murali Krishnan (For the IAAF), Sunday, 27 November 2011. In close races, Desisa and Kabuu prevail in New Delhi Half.
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ሌሊሣ ደሢሣ _____ 59 ደቂቃ 30 ሴኮንድ (በግሉ የርቀቱ ጥሩ ሰዓት )
6ኛ ..... ዲኖ ሠፈር ________ 1 ሰዓት 0 ደቂቃ 35 ሴኮንድ
7ኛ ..... ፈይሣ ሌሊሣ _______ 1 ሰዓት 0 ደቂቃ 50 ሴኮንድ
8ኛ ..... ጥላሁን ረጋሣ ______ 1 ሰዓት 0 ደቂቃ 59 ሴኮንድ
15ኛ ... ሹሚ ደቻሣ ________ 1 ሰዓት 3 ደቂቃ 10 ሴኮንድ
የሴቶች ምድብ
3ኛ ..... አሠለፈሽ መርጊያ _____ 1 ሰዓት 7 ደቂቃ 21 ሴኮንድ (በግሏ ለርቀቱ ጥሩ ሰዓት )
4ኛ ..... በላይነሽ ኦልጂራ _____ 1 ሰዓት 7 ደቂቃ 27 ሴኮንድ (በግሏ ለርቀቱ ጥሩ ሰዓት )
6ኛ ..... ማሬ ዲባባ __________ 1 ሰዓት 8 ደቂቃ 58 ሴኮንድ
8ኛ ..... አበሩ ከበደ __________ 1 ሰዓት 9 ደቂቃ 7 ሴኮንድ
9ኛ ..... ብዙነሽ በቀለ _________ 1 ሰዓት 9 ደቂቃ 8 ሴኮንድ
10ኛ .. መሪማ መሐመድ ______ 1 ሰዓት 10 ደቂቃ 46 ሴኮንድ
14ኛ .. አሃዛ ኪሮስ __________ 1 ሰዓት 12 ደቂቃ 51 ሴኮንድ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Dec 12, 2011 6:26 am Post subject:
እሑድ ታኅሣሥ 1 ቀን 2004 ዓ .ም .
39ኛው የሆኑሉሉ (ሐዋይ ግዛት - አሜሪካ ) የማራቶን ውድድር
ኢትዮጵያዊቷ ወይንሸት ግርማ የአገሯን ልጅ ምሥክር መኮንን በማስከተል አሸንፋለች :: ወይንሸት በ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 41 ሴኮንድ ውድድሩን ስትፈጽም ምሥክር በ 12 ሴኮንድ ተቀድማ በ 2 ሰዓት 31 ደቂቃ 53 ሴኮንድ ተከትላት ገብታለች ::
በወንዶች ምድብ ኬንያውያን ከ 1ኛ እስከ 6ኛ ያሉትን ደረጃዎች በሙሉ ተቆጣጥረው አሸንፈዋል ::
ምንጭ :- Honolulu Marathon, Sun Dec 11, 2011. ETHIOPIAN WINS WOMEN'S TITLE IN HONOLULU DEBUT.
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Jan 02, 2012 7:21 am Post subject:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-
ይህንን ዓምድ ዘንግቼው የሠነበትሁ እንዳይመስላችሁ : የአትሌቲክስ ዜና ድርቅ ስለነበረ እንጂ ! በሣምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ ታኅሣሥ 21 ቀን 2004 ዓ .ም . በዛ ያሉ የሩጫ ውድድሮች የተከናወኑበት ነበር : በተለይም ቅዳሜ ዕለት :: ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች አመርቂ ውጤቶች አስመዝግበዋል ::
የ 31ኛው የፒዮርባህ (ኦስትርያ ) አገር አቋራጭ የሩጫ ድድር ::
በውድድሩ በሴቶች ምድብ አዝመራወርቅ በቀለ ከአገሯ ልጅ ዓለም ፍቅሬ ክፍሌ ጋር እኩል በ 16 ደቂቃ 25 ሴኮንድ ጨርሣ በካሜራ የአገባብ ልዩነት ተጣርቶ አዝመራወርቅ አሸናፊ ሆናለች :: የወንዶች ምድብ አሸናፊ ኬንያዊው ሊኦናርድ ኮመን ነበር :: ሚሊዮን ዘውዴ የኋላሸት በ 18 ደቂቃ 59 ሴኮንድ ሦሥተኛ በመሆን አጠናቋል ::
ምንጭ :- Andreas Maier (for the IAAF), Sunday, 1 January 2012. Komon prevails in Peuerbach New Year's Eve run.
37ኛው የቦልዛኖ (ጣሊያን ) የ 10 ኪ .ሜ . የወንዶች እንዲሁም የ 5 ኪ .ሜ . የሴቶች የሩጫ ውድድሮች ::
በሁለቱም ፆታዎች አሸናፊዎቹ ኬንያውያን ነበሩ :: በወንዶች ምድብ ኢማኒ መርጋ በ 28 ደቂቃ 57 ሴኮንድ ሦሥተኛ ሲወጣ በሴቶች ምድብ ደግሞ አፍራ ጎደፋይ በ 16 ደቂቃ 3 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ሆናለች ::
ምንጭ :- Diego Sampaolo (for the IAAF), Sunday, 1 January 2012 Soi and Cheruiyot take thrillers in Bolzano.
የ 87ኛው የሣኦ -ፖሎ (ብራዚል ) የአገር አቋራጭ ውድድር ::
ውድድሩ ከባድ ዝናብ በነበረበት ሁኔታ በመካሄዱ ሯጮቹ ለማሸነፍ ተጨማሪ ከባድ ትግል ማድረግ ነበረባቸው :: ቢሆንም ኢትዮጵያዊው ታሪኩ በቀለ የወንዶች ምድብ አሸናፊ ሆኗል : የገባበትም ሰዓት 43 ደቂቃ 35 ሴኮንድ ነበር :: በሴቶች ምድብ ውዴ አያሌው በኬንያዊቷ ፕሪስካ ጄፔቶ በ 4 ሴኮንዶች ተቀድማ በ 48 ደቂቃ 52 ሴኮንድ ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች ::
ምንጭ :- Eduardo Biscayart (for the IAAF), Sunday, 1 January 2012. T. Bekele and Jeptoo beat the Sao Paulo New Year’ s Eve rain.
47ኛው የሣን ሲልቬስተር ቫሌካና : ማድሪድ (እስፓኝ ) የ 10 ኪ .ሜ . የሩጫ ውድድር ::
በዚህ ውድድር ሁለት አስደናቂ ክስተቶች ታይተዋል :- ወጣቱ ሐጎስ ገብረሕይወት በ 27 ደቂቃ 57 ሴኮንድ የወንዶች ምድብ አሸናፊ መሆኑና ለረዥም ጊዜ ከውድድር ርቃ የነበረችዋ የርቀቱ ንግሥት ጥሩነሽ ዲባባ በአሸናፊነት ዳግም ብቅ ማለቷ ነበር :: ጥሩነሽና ገለቴ በእኩል ሰዓት (31 ደቂቃ 30 ሴኮንድ ) ቢገቡም አሸናፊዋ የተለየቸው በካሜራ ምሥክርነት ነበር :: ዝርዝር ውጤቱ የሚከተለውን ይመስላል ::
የወንዶች ምድብ
1ኛ ..... ሐጎስ ገብረሕይወት ___ 27 ደቂቃ 57 ሴኮንድ
6ኛ ..... ባቲ መሐመድ ቡርቃ ___ 28 ደቂቃ 41 ሴኮንድ
የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ጥሩነሽ ዲባባ _____ 31 ደቂቃ 30 ሴኮንድ
2ኛ ..... ገለቴ ቡርቃ ______ 31 ደቂቃ 30 ሴኮንድ
10ኛ ... ረሒማ ጀዋር _____ 35 ደቂቃ 10 ሴኮንድ
ምንጭ :- Emeterio Valiente (for the IAAF), Sunday, 1 January 2012. Gebrehiwot surprises, Dibaba signals strong return in Madrid 10Km – San Silvestre Vallecana report.
በቸር ቆዩኝ ::
አክባሪያችሁ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Fri Jan 06, 2012 1:28 am Post subject:
ሐሙስ ታኅሣሥ 26 ቀን 2004 ዓ .ም .
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን :-
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር የተመሠረተበትን 100ኛ ዓመት በዓሉን በማክበር ላይ ይገኛል :: የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ለዚህ ዝግጅቱ ማዳመቂያ ካለፉ የአትሌቲክስ ውድድሮችና እንቅስቃሴዎች ጎላ ብለው የታዩ ውጤቶችን በተለያዩ ዝግጅቶች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል :: ስለ አፍሪቃ አህጉር የአትሌቲክስ እንቅስቃሴዎች እና ዋና ዋና ድሎች ካቀረቡት መካከል :-
@ ..... ኢትዮጵያዊው የማራቶን ጀግና ሻምበል አበበ ቢቂላ ለአገሩ ብቻ ሣይሆን ለአፍሪቃ አህጉር በኦሎምፒክ አደባባይ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘ አትሌት መሆኑን :
@ ..... ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ በሁለት የሩጫ ውድድር ዓይነቶች (5,000 እና 10,000 ሜትር የሩጫ ውድድሮች ) ወርቅ በማግኘት ከአፍሪቃ የመጀመሪያው አትሌት መሆኑን ::
@ ..... ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በባርሴሎና ኦሎምፒክ የደቡብ አፍሪቃዋን ኤሌና ሜዬር በመቅደም ለአገሯ በርቀቱ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማስግኘቷን :
@ ..... ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሤ እና ቀነኒሣ በቀለ በ 5,000 እና 10,000 ሜትር ርቀቶች የሩጫ ውድድሮች በክፍለ ዘመኑ እየተተካኩ ነገሥታት ሆነው መቀጠላቸውን :
@ ..... አዲሷ የረዥም ርቀቶች ሩጫ ንግሥት ጥሩነሽ ዲባባ በቤጅንግ ኦሎምፒክ በሁለቱም ርቀቶች (5,000 እና 10,000 ሜትር ) ወርቅ በማግኘት ብቸኛዋ ሯጭ መሆኗን ያትታል ::
ተጨማሪ መረጃዎችን ከሚከተለው ድረ -ገፅ ታገኛላችሁ ::
ምንጭ :- Phil Minshull (for the IAAF), Thursday, January 05, 2012. AFRICA: A Brief Glance through IAAF History – Area Athletes, PART ONE.
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Jan 11, 2012 4:54 am Post subject:
በሎንዶን ኦሎምፒክ በምትሃት ካልሆነ በስተቀር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ስፖርት ውጤት እንዴት መጠበቅ ይቻላል ?
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-
ባለፈው ዓመት በዳ -ኤ -ጉ (ደቡብ ኮርያ ) በተደረገው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የደረሠብንን ሽንፈትና ከዚያም የተከተለውን ውዝግብ ታስታውሣላችሁ :: ዛሬም ለዚያ አሣፋሪ ውጤት መገኘት ምክንያት የነበሩትን ሰዎች ከሥልጣናቸው ንቅንቅ ያደረጋቸው የለም : እንዲያውም እንደ ጥሩ ሥራ መሪ ጋዜጣዊ መግለጫ በመሥጠት ላይ ናቸው :: ታዲያ በአስማት ካልሆነ በስተቀር እኒህ ሰዎች ከሚመሩት የአትሌቲክስ ስፖርት ውጤት መጠበቅ ይቻል ይሆን
ምንጭ :- ደረጀ ጠገናው : ሪፖርተር ጋዜጣ : ቅዳሜ ታኅሣሥ 28 ቀን 2004 ዓ .ም . :: የለንደን ኦሊምፒክ የመጀመርያ ምዕራፍ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ማብራሪያ ተሰጠ ::
Quote: • የዶ /ር ወልደመስቀል ጉዳይ አጨቃጭቋል
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እያደረገ ያለውን የለንደን ኦሊምፒክ የመጀመርያው ምዕራፍ ዝግጅት የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሐሙስ ታኅሣሥ 26 ቀን 2004 ዓ .ም . በብሔራዊ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
የለንደን ኦሊምፒክ የጥር ወር ዝግጅትን አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ዶ /ር ይልማ በርታና ሌሎች የፌዴሬሽን ኃላፊዎችና አሠልጣኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አትሌቶች በወጣላቸው የሥልጠና ፕሮግራም መሠረት አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡
ዝግጅቱን በተመለከተ መገናኛ ብዙኀን በማናቸውም ጊዜና ወቅት ቦታው በመገኘት የታዘቡትን ለኅብረተሰቡ ማድረስ የሚችሉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በሚሰጣቸው ማናቸውም መድረኮች በሁሉም ስማቸው ሳይነሣ ቀርቶ የማያውቀው ዶ /ር መልደ መስቀል ኮስትሬ ጉዳይና ፌዴሬሽኑ ቅጥር ፈጽሞላቸው በአጭር ርቀት ሲያሠለጥኑ ቆይተው በዚህ ዓመት እንዲቀነሱ የተደረጉት አሜሪካዊው ዶ /ር ቻርልስ የንወና የንቦሪክ ሊሰናበቱ የቻሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ በዕለቱ ከተነሡት ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ፡፡
የፌዴሬሽኑም በተለይ በዶ /ር ወልደ መስቀል ጉዳይ ለቀረበለት ጥያቄ፣ ዶክተሩ በጤና ችግር እንዲሰናበቱ መደረጉንና በወቅቱም ግልጋሎታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት 120 ሺሕ ብር ተሰጥቷቸው ስለመሆኑ ጭምር ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ ይሁንና ‹‹በጤና ችግር›› የሚለው ስህተት እንደሆነና በአሁኑ ወቅት ዶ /ር ወልደ መስቀል እያሠሯቸው ያሉ አትሌቶች ውጤት እያስመዘገቡ ያሉበት ሁኔታ እንዳለም በመግለጽ ዶክተሩ ወደ ፌዴሬሽኑ ሊመጡ ያልቻሉበት ምክንያት አጥጋቢ አለመሆኑን በማከል ጥያቄው ተመልሶ ተንጸባርቋል፡፡ የዶ /ር ወልደመስቀልና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ክለብ አሠልጣኝ አቶ ካሱ ዓለማየሁ ከብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝነት የመቀነስ ጉዳይ በፌዴሬሽኑ በኩል ግልጽና ጥርት ያለ መልስ አለመሰጠቱን ተከትሎ ዛሬም እያከራከረ ስለመሆኑምና የሁለቱን የአሠልጣኞቹ ስንብት በፌዴሬሽኑ በኩል ጥርት ያለውን ማብራሪያ መስጠት አለበት ብለው የሚናገሩም አሉ፡፡
ላለፈው አንድ ዓመት አጭር ርቀት ላይ ሲሠሩ የቆዩትን አሜሪካዊውን ዶ /ር ቻርልስን በተመለከተ ግን አሠልጣኙን ሊተኩ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን አሠልጣኞች ቦታውን ተረክበው ተገቢውን ሥልጠና እየሰጡ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ ዶ /ር ቻርልስ ላለፈው አንድ ዓመት ሲያሠለጥኑ የቆዩት አምስት ሺሕ የአሜሪካ ዶላር እየተከፈላቸው ነበር፡፡
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1081 Location: ethiopia
Posted: Sun Jan 15, 2012 10:13 pm Post subject:
ሰላም ለቤቱ ባለቤትና ሌሎችም ተሳታፊዎች :-
በዚህ ርእስ ስር ተሳትፌ ባላውቅም መከታተል ከጀመርኩ ግን ሰንብቼአለሁ ::የ Houstonኑን ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውጤት ሰማሁና ወደ እዚህ በት ጎራ ስል አቶ ተድላን ለምን አልቀድመውም የሚል 'ሰይጣናዊ ' ሃሳብ መጣብኝ ::
ለማንኛውም በዚህ ውድድር ላይ በ ማራቶን 8249 አትለቶች ሲሳተፉ በግማሽ ማራቶን ደግሞ 9409 አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ውጤቱም እንደሚተለው ነበር ::
ምንጭ :- ከዚሁ Cyberethiopia
http://cyberethiopia.com/news/?id=178741
በወንዶች ማራቶን :-
1)ታሪኩ ጂፋር ...............................2:06.51(ባለፈው ዓመት በቀና ዳባ ያስመዘገብውን የ 2:07.04 ክብረወሰን ሰብሯል ::
2)ደበበ ቶሎሳ ................................2:07.41
3)ደምሰው ፀጋ ................................2:11.13
በሴቶች ማራቶን
1)ዓለሚቱ አበራ ............................2:23.14(በዚህም ውጤት ጠይባ ኤርኬሶ በ 2010 2:23.53 በመግባት ያስመዘገበችውን ክብረወሰን ሰብራለች ::
በወንዶች ግማሽ ማራቶን
1)ፈይሳ ሌሊሳ .....................59:22(በ 2007 አሜሪካዊው Ryan Hall ያስመዘገበውን ክብረወሰን (59:43) ሰብሯል ::
በሴቶች ግማሽ ማራቶን
1)በላይነሽ ኦልጂራ ...............1:08.26(በ 2010 አሜሪካዊቷ Shalane Flenagans የገባችበትን የ 1:09.41 ክብረወሰን ሰብራለች ::
* የተሰበሩት ክብረ ወሰኖች የ Houston ማራቶንን ብቻ የሚመለከቱ ናቸው ::
**የሯጮቹን ሥም ምናልባት በትክክል አላስቀመትኩትም ይሆናል :: _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Jan 15, 2012 11:53 pm Post subject:
ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ለቤቱ ባለቤትና ሌሎችም ተሳታፊዎች :-
በዚህ ርእስ ስር ተሳትፌ ባላውቅም መከታተል ከጀመርኩ ግን ሰንብቼአለሁ ::የ Houstonኑን ማራቶንና ግማሽ ማራቶን ውጤት ሰማሁና ወደ እዚህ በት ጎራ ስል አቶ ተድላን ለምን አልቀድመውም የሚል 'ሰይጣናዊ ' ሃሳብ መጣብኝ ::
ኧረ በጣም የሚደገፍ ተግባር ነው :: የውድድሩ ውጤት ደግሞ በጣም አስደሣች ነው :: በደንበኝነትህ ቀጥልበት ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Mon Jan 16, 2012 6:49 am Post subject:
እሑድ ጥር 6 ቀን 2004 ዓ .ም .
በሣምንቱ መጨረሻ ከተደረጉት ውድድሮች በሙምባይ (ሕንድ ) እና በሒውስተን (ቴክሣሥ ግዛት -አሜሪካ ) የማራቶን ሩጫዎች እንዲሁም በሲቪል (እስፓኝ ) የአገር አቋራጭ ሩጫ ኢትዮጵያውያን ውጤት ያገኙባቸው ናቸው :: በተለይ የማራቶን ውድድሮቹ በዛ ያለውን ደረጃ ከመያዝ አልፈው ሬኮርድ እየሠበሩ ያሸነፉባቸው ነበሩ ::
የሙምባይ (ሕንድ ) ማራቶን ::
የሴቶች ምድብ
1ኛ ..... ነፃነት አቻሞ አቤዮ _____ 2 ሰዓት 26 ደቂቃ 12 ሴኮንድ (በግሏ እና ለሥፍራው አዲስ ሬኮርድ )
2ኛ ..... ፋጡማ ሣዶ ደርጎ ______ 2 ሰዓት 30 ደቂቃ 20 ሴኮንድ
3ኛ ..... ማክዳ ሐሩን ___________ 2 ሰዓት 30 ደቂቃ 47 ሴኮንድ
4ኛ ..... አየሉ ለማ ገዳ _________ 2 ሰዓት 32 ደቂቃ 10 ሴኮንድ (ለግሏ አዲስ ሬኮርድ )
5ኛ ..... ሮማን ገብረሥላሤ ______ 2 ሰዓት 34 ደቂቃ 18 ሴኮንድ
6ኛ ..... ፋንቱ ጅማ ____________ 2 ሰዓት 34 ደቂቃ 27 ሴኮንድ
7ኛ ..... እህቱ ኪሮስ ረዳ _______ 2 ሰዓት 34 ደቂቃ 50 ሴኮንድ (ለግሏ አዲስ ሬኮርድ )
8ኛ ደፋ ታደሰ ግርማ ? ________ 2 ሰዓት 36 ደቂቃ 12 ሴኮንድ
9ኛ ..... ወርቅነሽ ቶላ __________ 2 ሰዓት 36 ደቂቃ 18 ሴኮንድ
10ኛ ... ማርታ ማርቆስ _________ 2 ሰዓት 36 ደቂቃ 51 ሴኮንድ
11ኛ ... አበራሽ ነጋሣ በዳሣ ______ 2 ሰዓት 37 ደቂቃ 17 ሴኮንድ
12ኛ ... ራዲያ አዲሎ ___________ 2 ሰዓት 37 ደቂቃ 34 ሴኮንድ
14ኛ ... ጋሉሜ ጫላ ____________ 2 ሰዓት 40 ደቂቃ 55 ሴኮንድ
15ኛ ..... ጣይሞ ሹምዬ __________ 2 ሰዓት 50 ደቂቃ 25 ሴኮንድ
18ኛ ..... ትዕግሥት ክፍሌ _________ 2 ሰዓት 56 ደቂቃ 3 ሴኮንድ
የወንዶች ምድብ
2ኛ ..... ራጂ አሰፋ _____2 ሰዓት 10 ደቂቃ 48 ሴኮንድ (ለግሉ አዲስ ሬኮርድ )
4ኛ ..... ገላ ኃይሉ _____2 ሰዓት 11 ደቂቃ 32 ሴኮንድ
6ኛ ..... ሲራጅ ገና ____ 2 ሰዓት 12 ደቂቃ 33 ሴኮንድ
14ኛ ..... አብዲሣ ሦሪ __ 2 ሰዓት 18 ደቂቃ 17 ሴኮንድ
ምንጭ :- Ram. Murali Krishnan (for the IAAF), Sunday, January 15, 2012. Abeyo notches course record, while Moiben edges Assefa in Mumbai.
የሲቪል (እስፓኝ ) የአገር አቋራጭ ሩጫ ::
ምንጭ :- Emeterio Valiente (for the IAAF, Sunday), January 15, 2012. Kipsang and Masai reign in rainy Seville.
የእኛ አትሌቶች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ያመጡት ባህርይ በማራቶኑ እንዲህ በየዓለም አቀፍ ውድድሮች ጥሩ ውጤት ሲያመጡ ይከርሙና ዋናዎቹ የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮናዎች ሲደረጉ ወገቤን ይላሉ :: እስኪ በዚሁ ያዝልቅላቸው ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Jan 17, 2012 12:20 am Post subject:
ሰኞ ጥር 7 ቀን 2004 ዓ .ም .
ከትላንት እሑድ የሩጫ ውድድሮች አንዱ ለ 35ኛ ጊዜ የተካሄደው የቪላ ላጋሪኛ (ጣሊያን ) የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ነበር :: በዚህ ውድድር ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታ ምድቦች ተከታትለው በመግባት አሸናፊዎች ሆነዋል :- የሴቶቹን ጎደፋይ አፈራ የወንዶቹን ደግሞ አጠናው ክንዴ ቀዳሚዎች ነበሩ :: ዝርዝሩ ውጤቶቹን እንሆ ::
የሴቶች ምድብ (5.5 ኪ .ሜ .)
1ኛ ..... ጎደፋይ አፈራ ___ 19 ደቂቃ 16 ሴኮንድ
2ኛ ..... ሮማን ግደይ ____ 19 ደቂቃ 19 ሴኮንድ
የወንዶች ምድብ (8.6 ኪ .ሜ .)
1ኛ ..... አጠናው ክንዴ ______ 25 ደቂቃ 27 ሴኮንድ
2ኛ ..... ፈቃዱ ሀፍቱ _______ 25 ደቂቃ 38 ሴኮንድ
3ኛ ..... ካሣ ሞከሻው _______ 25 ደቂቃ 43 ሴኮንድ
4ኛ ..... ገብረጻዲቅ አብርሃ ___ 26 ደቂቃ 5 ሴኮንድ
ምንጭ :- Diego Sampaolo (for the IAAF), Monday, 16 January 2012. Ethiopians dominate at Villa Lagarina XC.
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Fri Jan 20, 2012 10:51 pm Post subject:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-
ሠሞኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች 35 ብሔራዊ አትሌቶችን ከማንኛውም ኢንተርናሽናል ውድድር አግደዋል :: ምክንያት ተደርጎ የቀረበው "አትሌቶቹ ለብሔራዊ ቡድን ልምምድ ሲጠሩ አልመጡም " የሚል ነው :: ነገር ግን እኒህ አትሌቶች ጉዳት ሲደርስባቸው : ባልረባ አሠልጣኝ አሠለጣጠን ምክንያት ውጤት ሲያጡ : ከዚያም አልፈው በውጭ አገር ውድድሮች ካልተካፈሉ የሚበሉትና የሚጠጡት እንኳን ሲያጡ ፌዴሬሽኑ ዞር ብሎ አያያቸውም :: ነገር ግን በእነርሱ ሥም ተንጠላጥለው የጥቅም ኮሮጇቸውን ይሞሉበታል :: የፌዴሬሽኑ ሰዎች በዚህ ግትር አቋማቸው ከገፉበት በሚታጣው ውጤት እነርሱ በኋላ መደበቂያ ያጣሉ እንጂ በአትሌቶቹ የሚፈርድ ሕዝብ አይኖርም ::