View previous topic :: View next topic
Author
Message
ምረቱ Joined: 14 Jan 2007 Posts: 278
Posted: Wed Feb 01, 2012 8:21 pm Post subject: የፍቅር እና የሀብት ግብግብ
በኢትዮጵያ አቆጣጠር በሰማኒያዎቹ መጨረሻ እና ዘጠናዎቹ መጀመሪያ ኮሌጂ እና ዮኒቨርስቲ በነበርኩበት ጊዜ የኛ ትውልድ ብዙ ይኮነን እና ይወገዝ ነበር :: በብዙ ጉዳዮች :: እኔም ወደዛ አይነት ሜንታሊቲ የገባሁ እየመሰለኝ ራሴን አስቁሜ የምጠይቅበት ጊዜ ይበዛል :: እንዲህ ሳደርግ ""ለመሆኑ ከእኛ በፊት የነበረው ትውልድ እንዴት ነበር የሚያስበው ?"" የሚል ጥያቄ አነሳለሁ :: ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ ይጠቅማል ብየ ያሰብኩት አንድም የስነ -ጽሁፍ ስራዎችን ማገላበጥ ነው :: አንድም ቀደም ያሉ የጥበብ ስራዎች ላይ ሪፍሌክት ማድረግ ነው :: ዘመኑ በፈጠረው ቴክኖሎጂ እንደልብ ሊገኝ የቻለው ነገር ቢኖር ቆየት ያሉ የሙዚቃ ስራዎች ናቸው :: አብዛኛዎቹ ስሰማቸው መልዕክታቸው ጭምር የሚመስጠኝ የሙዚቃ ስራዎች ሲለቀቁ እልተወለድኩም ሁሉ :: በነዚህ ስራዎች ውስጥ ግን የማየው ድምጻዊዎቹን ብቻ ሳይሆን ግጥም የጻፉትን ስዎችም ጭምር ነው :: እነዚህ ጸሀፊዎች አንደኛ የነበሩበትን ዘመን (ጥሩም ይሆን መጥፎ ) ነው የሚያንጸባርቁት :: የማህበረሰቡ ውጤቶች እንደመሆናቸው በዚያን ጊዜ ስለነበረው ማህበረሰባዊ አስተሳሰብ ይነግሩናል :: በሌላ በኩል ደሞ እነዚሁ ጸሀፊዎች ማህበራዊ እሴትን ከመጤ አስተሳሰብ ለመከላከል በብዕራቸው የባህል አርበኛ ሆነው ማህበራዊ እሴትን ከጥፋት ሲከላከሉ እናያለን :: እሴትን የሚያፈርስ ሀሳብ ሲመጣ መጀመሪያ የሚደርሰው ከተማ እንደመሆኑ ባህልን እና እሴትን ለማዳን የሚደረገው የመጀመሪያው ግብግብ ከተሞች ላይ ነው የሚሆነው ::
ድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፍረው በስራ ወይ በእንደዚህ ያለ አጋታሚ ይኖሩ የነበሩ ፈረንጆች ጋር ተወዳጂተው የነበሩ ሀበሾች ""የወክ "" ማህበር ነበራቸው አሉ :: በሁኔታው ደሞ ብዙም የተደሰቱ የማይመስሉ የሀገራችን ልጆች በጊዜው ""ልወዝወዘው በእግሬ "" የሚል ማህበር አቋቁመው እንደነበር ይነገራል :: እኔ ራሴ Minutes of the Ethiopian millennium"" በሚለው የአቶ ተፈራ መጽሀፍ ውስጥ ያነበብኩ መሰለኝ ::
ወደ ዛሬው ጉዳይ ስገባ ልጂ ሆኘ በተለይም በፍንዳታነት ዘመን ብዙነሽ በቀለ የማደንቃት አይነት ዘፋኝ አልነበረችም ለኔ :: በትንሹም ቢሆን በነ ኤም ሲ ሀመር ; ትሬሲ ቻፕ ማን ዘፈኖች እማልል እንደነበር አስታውሳለሁ :: ኬኔዲ ምናምን :: ስሞኑን ግን የብዙነሽን ዘፈን መሰጥ ብየ አዳመጥኩት :: ስለ ፍቅር ምንነት እና በፍቅር እና በማቴሪያላዊነት ላይ በተነሳ ሽኩቻ ላይ ፍቅርን ይከላከል በነበረ ሰው የተጻፈ በሚመስል ግጥም ላይ የተሰራው ግጥም ድንቅ ሆኖ አገኘሁት :: በከፊል ግጥሙ እንዲህ ይነበባል
""ለሰው ቢናገሩት እውነት አይመስለውም
ፍቅር ስሜት እንጂ ገንዘብ አይገዛውም
ፎቅና ማርሴዲስ ስሜት አይሰጡኝም
እኔ ፍቅር እንጂ ሀብት አያሞኘኝም
አያገባው ገብቶ ሰው ይዘባርቃል
እኔ ስሜን እንጂ ምኞቴን ማን ያውቃል ?
ፍቅር ይርበኛል ፍቅር ይጠማኛል
ሀብት መሰብሰብ ግን ከንቱ ይመስለኛል ...::""
http://www.hubesha.com/audio.php?arid=22&abid=36
ጸሀፊዎቹ እና ድምጻውያኑ ስምምነት አላቸው :: የፈጠራቸውን ማህበረሰብ እሴትም እየተዋጉለት እንደነበር ነው የሚያሳየው :: የማህሙድን የጥላሁንን ከነሱም በኍላ የተነሱትን የነ ቴዎድሮስ ታደሰን ዘፈኖች ሳዳምጥ ተመሳሳይ ነገር አስተውላለሁ :: በተቃራኒው ደሞ አሁን የምሰማቸው ዘፈኖቹ እና አንዳንዴ በምስልም የማያቸው ትንሽ ወጣ ያሉ ሴክሺዋሊቲ ብቻ የወረራቸው ሆነው ይሰሙኛል (ብዙዎቹን ማለቴ ነው ) :: ተሳስቻለሁ ?? _________________ እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/294762583969356?ref=hl
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 969
Posted: Tue Feb 07, 2012 3:15 am Post subject:
አልተሳሳትክም ወንድሜ :: _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 969
Posted: Tue Feb 07, 2012 3:31 am Post subject:
Quote: አንድ ፖስት አጠፍተህ ወዲያውኑ ሌላ ፖስት ማጠፋት አትችልም እባክህ ከጥቂት ቆይታ በህዋላ እንደገና ይሞክሩ ።
---- you ዋርካ .........መች አጥፍቸ ሌላ ሞከርኩ ????? _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ገደል Joined: 02 Jan 2010 Posts: 487
Posted: Tue Feb 07, 2012 5:24 pm Post subject:
ጸጉር ሰንጣቂ አትበለኝና ... ምን ማለትህ ነው ? ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ነው ወይስ አንዱን ጨርሰህ ወደ ሌላው ?
Quote: ....ኮሌጂ እና ዮኒቨርስቲ በነበርኩበት ጊዜ ....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ምረቱ Joined: 14 Jan 2007 Posts: 278
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ምረቱ Joined: 14 Jan 2007 Posts: 278
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 969
Posted: Fri Feb 10, 2012 3:22 am Post subject:
የድሮ ሙዚቃዎች ...አሪፎች ናቸው :: ለዚህም ይመስላል የመጣው ትውልድ ሁሉ እየደጋገመ የሚዘፍናቸው :: የነማህሙድ ጥላሁን ዓለማየሁ ብዙነሽ ተዘራ ...ባህታ .. ሙዚቃዎች እየተሰረቁም እየተደገሙ መዘፈን የተጀምሩበትን የታየም ፍሬም ብንመለከት ሰላሳ ወይም ሃያ አምስት ቢሆን ነው ጋፑ ...አንዳንዴም ከዚያም ያንሳል :: ባንጻሩ ከሃያ አምስት ዓመት ወዲህ ተዘፈነው እንደገና ተደግመው ተዘፈኑ የምላቸው ...በነ ትዝብት ..የሉም :: ካሉ ለመታረም ዝግጁ ነኝ :: የኤፍሬም ..ጸሃየ ...ንዋይ ...ኬኔዲ ...ሐመልማል ...ወዘተ ዘፈኖች ሐያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በላይ ቢያስቆጥሩም ..ደግሞ ሊዘፍናቸው የከጀለ ..ሌባ ዘፋኝ አልታየም :: ይህ ደግሞ ሰርቆና ደግሞ በመዝፈን ገንዘብ ሊገኝባቸው የማይችሉ ዘፍኖች መሆናቸውን ያሳያል :: በርግጥ ሙዚቃዎቹ መጥፎ ሆነው አይደልም ...ግን ስሪታቸው ገንዘብ ያለመ እንጂ ጥራት ያለው ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆኑ ሰላልሆነ እንጂ ::
የቀድሞዎቹ ሙዚቃዎች ሲወጡ ዋና ዓላማ የነበረው እነሱም በተደጋጋሚ የገለጹት ... አሁንም እየገለጹ ያለው ምክንያት .... የየክፍሉ ውደድር ስለነበር ነው :: አንዱ ..አንዱን ለማሽነፍ የነበረ ትግል ..ጥረት ..... ከጥራት ጋር ወደ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎች አመራቸው :: ከዚያ ሌላ .. በዘመኑ የነበሩ ምርጥ ሰዓሊያን ..ሙዚቀኞች ...ዲፕሎማቶች ...ቢታተም ይታተም ..... ባይታተምም ሳጥን ወስጥ ለዘላለም ይቆለፍበት ብለው የሚሉ ደራሲያን ...ተዋንያን ...ገጣሚያን ...ወዘተ ነበሩን ...:: አሁንስ ? ዛሬ ጽፈው ጥቅም ሳይገኙበት እንቅልፍፍ ወስዷቸው ማደሩን እንጃ ::
ያም ሆነ ይህ .... ሁሉም ቀጥሏል :: መቀጠልም አለበት ..ያ የተፈጥሮ ህግ ነው :: ግን ...ቤሳ ቤስቲን ሳይከፈልህ አርባ ሁለት ኪሎሜትር በባዶ እግርህ ሮጠህ ወርቅ እናት አገርህ .እና ለሰንደቅህ ...አምጣ ..ቢባል የሚሮጥ አለ ? የምንወደው ኃይሌ እንኳ ንክች የሚያደርገው አይመስለኝም :: ወይም ...እምቅ ችሎታህን እንደቻልክ ጻፈው ..ቢታተም ይታተም ..ባይታተምም ይቅር ተብሎ ...እንደዳኛቸው ወርቁ ....ወይም እንደ ስብሃት የሚጽፍ አለ ? ወይስ ደግሞ እንደ በዓሉ ግርማ ወይም እንደ አቤ ጉበኛ ድንቅ ነገር ጽፎ ..ለሰነ -ጽሁፍ የሚሞት አለ ? አይመሰለኝም :: ወይ ተዘራ ሃይለሚካኤል ጊታሩን .....አሊያም እንደ ሳህሌ ደጋጎ አልጋ ይዞ በድህነት ..ከብዙ ትውልድ ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ፈጠራ በኋላ የሚሞት አለ ?
በፍጹም የለም ::
ይህ ነው በድሮዎቹ ..ውድድርን መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራ እና በአሁኖቹ ገንዘብን መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራ መካከል ያለው ልዩነት !
በኔ እምነት ...ጥላሁን ከሃምሳ ዓመት በላይ ዘፍኖ ካገኘው ገንዘብ ይልቅ ..ቴዲ አፍሮ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘፍኖ ያገኘው ገንዘብ ይበልጣል :: ግን ቴዲ ....የጥላሁንን ዓይነት ድንበር ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ይዋጡለት ይሆን ? ፍርዱን ለዘመን !
እስከዛ የድሮዎቹን ደጋግመን እየሰማን ...ከዛ ባለፈም እየደጋገሙም ሆኖ አሳምረውም ሆነ አበለሽተውም የሚዘፍኑትን መክታተል ነው :: _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ምረቱ Joined: 14 Jan 2007 Posts: 278
Posted: Fri Feb 10, 2012 7:56 am Post subject:
ግሩም ትንተና ነው የሰጠኸው ውቃው !
መጨረሻ ካነሳኽው ሀሳብ ብጀምር ምንም እንኳን ቴዲ አፍሮን ከነ ጥላሁን እኩል ባላስቀምጠውም የማደንቅበት ምክንያት አለኝ ::
በነጥላሁን ዘመን የሚሰራው ነገር ሁሉ ---ዘፈን በለው ድርሰት በለው ምን በለው ---ከስጋ ይልቅ ከነብስ ታር ትስስር የነበረው ነው :: ኤተርኒቲ ይታይበታል :: ይሄ ታዲያ ቀደም ብየ እንደገለጽኩት የማህበረሰብ የአስተሳሰብ ተጽዕኖ እና የጸፍቱም የአለም እይታም ነጸብራቅም ጭምር ነበር :: ስለዚህ እነ ጥላሁን በአርበኛ ህዝብ በአርበኛ ጸሀፍት ተከበው ስራቸውን በአርበኝነት መንፈስ ለህዝብ ሲያደርሱ የነበሩ ናቸው ::
በሌላ በኩል ቴድሮስ ካሳሁን የሚሞክረውን ያህል ዘመን አላደለውም ! ኦልሞስት ብቻውን ነው እየቀዘፈ ያለው :: ዛሬ እንደድሮው አርበኛ ህዝብ የለም የህብረተስቡን የዓለም እይታ እንደምታየው ነው ... የባህልም ሳልባጂ እየተከናነበ ""ዘመናዊነት "' ነው ማለት የሚያምረው ጉድ ትውልድ ላይ ነው የደረስነው !
ቀደም ያለው ማህበረሰባችን ስለ ህይወት እና ስለ ዐለም የነገበረው ግንዛቤ ጥበብን እና የጥበብ ሰዎችን ራሱ ሼፕ አድጎአል ::
ጀስት ኦፍ ዘ ቶፕ ኦፍ ማይ ሄድ አንዳንድ ብሂሎችን ባስታውስ :-
""ታስሮ መሄድ አይቀርም !"' [it's acceptance of death---embracing reality! -- ስለማይቀር አትዋሽ አትቅጠፍ ነው ነገሩ !]
""አለም አላፊ ነው መልክ ረጋፊ ነው "" ---ይኼኛው ሌላ የህብረተሰባችን የሞት እና የህይወት ፍልስፍና ነው :: አንድምታው የማያልፍ ---ኤተርናል የሆነ ነገር አለ ስለዚህ ዱ ጉድ ! ነው ነገሩ
እንዲህ ባለ ማህበረሰብ ውስጥ የነገሮች ጥሩና መጥፎነት ይመዘን የነበረው ነግሮች በሚኖራቸው የንዋይ ግምት ሳይሆን ባላቸው ፋይዳ እና ትክክለኛ ነገር በመሆናቸው እና ባለመሆናቸው ነው :: በጣሊያን ወረራ ጊዜ እኮ ጣሊያን ከራሱ ወገን ለወገኑ የስራ እድል እና ሹመት እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር :: ሰጥቷልም ! ነገር ግን በእንደዚህ ያለው ""እድል "" ተጠቃሚ መሆን እና መሾም መሸለም ሀገርን አሳልፎ ከመስጠት ጋር የተያያዘ ስለነበር ለብዙ አበሾች የሚቀመስ ነገር አልነበረም :: ያሸነፈውም የብዙሀኖቹ አበሾች እሳቤ ነው ::
እነ አበበ ቢቂላ የዚህ ብዙ ባልተደላደለ ሁኔታ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ጥሊያንን ካሸነፈው ትውልድ እያዮ ያደጉ ናቸው :: ይዘው ያደጉትም የአሸናፊነት ልቦናን ነው :: እምነትን ቀናዓነትን ነው :: ስግብግብነት እና ለገንዘብ መሞት የኢትዮጵያ ማህበረስብ ውስጥ ኖርም አልነበረም :: አበበ ቢቂላ ራሱ ለምን በባዶ እግሩ እንደሮጠ ካሸነፈ በኍላ ተጠይቆ በሰጠው መልስ --- የራሱን ሳይሆን የሀገሩን የኢትዮጵያን ኢንዱራንስ ለዓለም አቀፍ ማህበረስብ ለማሳየት እንዳደረገው ተናገሮአል ''ሀገሬ ኢትዮጵያ በሚያስቸግር ሁኔታም ውስጥ ሆና ነጻነቷን የማትሸነፍ ተንካራ እንደሆነች ለማሳየት ነው "" ያለ መሰለኝ ::
በሞት እና በህይወት ላይ ጥርት ያለ እይታ ስለነበረ በአሸናፊነት ስነ ልቦና ይኖር የነበረ ህዝብ ነበር :: ለእድገትም ሀገሪቱንም ለመለወጥ ጥሩ አሴት ይሆነን የነበረው እሱ ነበር ! ያንን አስጣሉት እንደምንም ብለው ! ዛሬ እንኳንስ በጥበብ ስራ እና በፀሀፍት ይቅርና ፖለቲካ ራሱ ንግድ ሊሆን ምንም አልቀረውም ...በተለይ ውጪ ያለው ፖለቲካ ! ""ሪያሊቲ "" እየተባለ ባህላችን መቀየር አለበት እየተባልን ነው :: ይሄ ይቀየር ይሄ ይቀየር የሚሉት ፈረንጆቹ ናቸው ! የሜዲያው ቅርጽ እና ይዘት ሳይቀር በእነሱ ነው ሪኮመንድ የሚደረገው
እና እንዳልከው በየመስኩ ቢዝነስ ሆነ ነገሩ ! ጸሀፍቶቹ የሚያራግቡት የሚያነሱት እና የሚጥሉት ነገር ከገንዘብ ጋር ብቻ የተገናኘ ኢትዮጵያዊ ለዛ የሌለው ! የሚወራው የሚጻፈው ስለ ሴክስ ...ስለ ሴክስ ማውራት ማስወራት በቃ የመጨረሻ ዘመናዊነት ተደርጎ ነው የተወሰደው ! ከምር በጣም ደባሪ ዘመን ላይ ነው ያለነው !
የዚህ ዘመን ብሂል ''ላይፍ ኢስ ሾርት "" ይልና ስለዚህ እንደፈለክ ሁን ! ደስ የሚልህን ነገር አድርግ ---እስካስደሰተህ የሚል አስተሳሰብ ይከተላል :: የበፊቱ ""አለም አላፊ ነው መልክ ረጋፊ ነው "" የሚለው አስተሳሰብ ---የሚጭንብህ የኤተርኒቲ መንፈስ ነው ...ኤተርናል የሆነ ነገር ስራ ነው መልዕክቱ ! ኖ ዳውት አሁን ያለው ትውልድ በሀይለኛው ብዙ የተሸወደባቸው ነገሮች አሉ !
ታንኪዮ ፎር ሼሪንግ ዮር ቶውት !
ምረቱ
ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው : የድሮ ሙዚቃዎች ...አሪፎች ናቸው :: ለዚህም ይመስላል የመጣው ትውልድ ሁሉ እየደጋገመ የሚዘፍናቸው :: የነማህሙድ ጥላሁን ዓለማየሁ ብዙነሽ ተዘራ ...ባህታ .. ሙዚቃዎች እየተሰረቁም እየተደገሙ መዘፈን የተጀምሩበትን የታየም ፍሬም ብንመለከት ሰላሳ ወይም ሃያ አምስት ቢሆን ነው ጋፑ ...አንዳንዴም ከዚያም ያንሳል :: ባንጻሩ ከሃያ አምስት ዓመት ወዲህ ተዘፈነው እንደገና ተደግመው ተዘፈኑ የምላቸው ...በነ ትዝብት ..የሉም :: ካሉ ለመታረም ዝግጁ ነኝ :: የኤፍሬም ..ጸሃየ ...ንዋይ ...ኬኔዲ ...ሐመልማል ...ወዘተ ዘፈኖች ሐያ አምስት ዓመታትና ከዚያም በላይ ቢያስቆጥሩም ..ደግሞ ሊዘፍናቸው የከጀለ ..ሌባ ዘፋኝ አልታየም :: ይህ ደግሞ ሰርቆና ደግሞ በመዝፈን ገንዘብ ሊገኝባቸው የማይችሉ ዘፍኖች መሆናቸውን ያሳያል :: በርግጥ ሙዚቃዎቹ መጥፎ ሆነው አይደልም ...ግን ስሪታቸው ገንዘብ ያለመ እንጂ ጥራት ያለው ትውልድ ተሻጋሪ እንዲሆኑ ሰላልሆነ እንጂ ::
የቀድሞዎቹ ሙዚቃዎች ሲወጡ ዋና ዓላማ የነበረው እነሱም በተደጋጋሚ የገለጹት ... አሁንም እየገለጹ ያለው ምክንያት .... የየክፍሉ ውደድር ስለነበር ነው :: አንዱ ..አንዱን ለማሽነፍ የነበረ ትግል ..ጥረት ..... ከጥራት ጋር ወደ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎች አመራቸው :: ከዚያ ሌላ .. በዘመኑ የነበሩ ምርጥ ሰዓሊያን ..ሙዚቀኞች ...ዲፕሎማቶች ...ቢታተም ይታተም ..... ባይታተምም ሳጥን ወስጥ ለዘላለም ይቆለፍበት ብለው የሚሉ ደራሲያን ...ተዋንያን ...ገጣሚያን ...ወዘተ ነበሩን ...:: አሁንስ ? ዛሬ ጽፈው ጥቅም ሳይገኙበት እንቅልፍፍ ወስዷቸው ማደሩን እንጃ ::
ያም ሆነ ይህ .... ሁሉም ቀጥሏል :: መቀጠልም አለበት ..ያ የተፈጥሮ ህግ ነው :: ግን ...ቤሳ ቤስቲን ሳይከፈልህ አርባ ሁለት ኪሎሜትር በባዶ እግርህ ሮጠህ ወርቅ እናት አገርህ .እና ለሰንደቅህ ...አምጣ ..ቢባል የሚሮጥ አለ ? የምንወደው ኃይሌ እንኳ ንክች የሚያደርገው አይመስለኝም :: ወይም ...እምቅ ችሎታህን እንደቻልክ ጻፈው ..ቢታተም ይታተም ..ባይታተምም ይቅር ተብሎ ...እንደዳኛቸው ወርቁ ....ወይም እንደ ስብሃት የሚጽፍ አለ ? ወይስ ደግሞ እንደ በዓሉ ግርማ ወይም እንደ አቤ ጉበኛ ድንቅ ነገር ጽፎ ..ለሰነ -ጽሁፍ የሚሞት አለ ? አይመሰለኝም :: ወይ ተዘራ ሃይለሚካኤል ጊታሩን .....አሊያም እንደ ሳህሌ ደጋጎ አልጋ ይዞ በድህነት ..ከብዙ ትውልድ ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ፈጠራ በኋላ የሚሞት አለ ?
በፍጹም የለም ::
ይህ ነው በድሮዎቹ ..ውድድርን መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራ እና በአሁኖቹ ገንዘብን መሰረት ያደረገ የፈጠራ ስራ መካከል ያለው ልዩነት !
በኔ እምነት ...ጥላሁን ከሃምሳ ዓመት በላይ ዘፍኖ ካገኘው ገንዘብ ይልቅ ..ቴዲ አፍሮ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘፍኖ ያገኘው ገንዘብ ይበልጣል :: ግን ቴዲ ....የጥላሁንን ዓይነት ድንበር ተሻጋሪ ሙዚቃዎች ይዋጡለት ይሆን ? ፍርዱን ለዘመን !
እስከዛ የድሮዎቹን ደጋግመን እየሰማን ...ከዛ ባለፈም እየደጋገሙም ሆኖ አሳምረውም ሆነ አበለሽተውም የሚዘፍኑትን መክታተል ነው ::
_________________ እግዚአብሔር ታላቅ ነው!