WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አጋጣሚ ! ወይስ ተልእኮ ?
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሓየት 11

ዋና አለቃ


Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 7:19 am    Post subject: Reply with quote

... እንደጻፈ(ች)ው:
ሓየት 11 እንደጻፈ(ች)ው:
... እንደጻፈ(ች)ው:


በመጀመሪያ ልጃገረድ ስላልሆነች ተከፋሁ የሚል ምንም አይነት ነገር አላነሳሁም ይህ ነገር ማለትም ቨርጂኒቲ ለኔ ምንም ነገር እንዳልሆነ ነው የገለጽኩት እንደግና ማየት ይቻላል ነገር ግን እራሷ ስላነሳችው ነው እኔም የጠየኩት እናም ልምዱ ያላችሁ እኔም እንዳውቅ ብዬ እንጂ ለኔ ሆነች አልሆነች ትርጉም የለውም ::
ሌላው ለወረቀት ሲሉ እንኩዋንም እንደኔ ያለ ሸበላ ይቅርና እዚህም ሆነ ሌላው አገር ፔና በረንዳ አዳሪ ሽማግሌ ወዘተ . ያገባሉ
በዛ ላይ የስንቶቻችሁ አባቶች ናቸው እናቶቻችሁን በጠለፋ ያገቡት ?? ያልፈለገችውን ወንድ በግድ አግብታ እናንተን ያሳደገች ምናልባትም አሁንም ድረስ አብረው ያሉ ::
እናም በተፈጠረ ድንገተኛ ነገር ተጋባን እንጂ አስቤው አልሜው ያደረኩት ነገር አይደለም ::
ከልቧ ይቅር ባትለኝ ኖሮ አሁንም ድረስ አብራኝ አትኖርም ነበር በዚያ ላይ የጋብቻ ቀናችንን ሳይሆን እንድናከብር የጠየቀችኝ መጀመሪያ የተገናኝንበትን ቀን እንደሆነ ልብ በሉ ::
በተጨማሪም ከይቅርታዋ ሌላም ብጽፈው ራሱን የቻለ አጉዋጊ ልብ አንጠልጣይ የሆነ ታሪክ ሊወጣው የሚችል መስዋእትነት ከፍያለሁ ::
ባሁኑ ሰአት የሆነውን ሁሉ ቢያውቁም ቤተሰቦቿም ይወዱኛል :: እሷም ከልቧ እንደምትወደኝ አውቃለሁ እኔም ከልቤ እወዳታለሁ ::
...


እኔ ምልህ ነጠብጣቡ

የሰላም ትዳር እየኖርክ ከሆነ ይህን "የሞኝ ጀብዱህን " እዚህ መጻፍ ለምን አስፈለገ ? ወይስ ባለቤትህ ማንበብ አትችልምና ይህን ታሪካችሁን በሆነ አጋጣሚ ልታነበው አትችልም ብለህ አስበህ ነው Question

ትላንት ከፈጸምከው ብልግና የዛሬው ቂልነትህ ባሰ እልሀለሁ ወንድምህ ደግሞ :: የተዳፈነን እሳት የምትቆሰቁስ የዋህ ነህ :: ሳስብህ ደግሞ ዛሬም ምናባቷ ታመጣለች የሚል የአበሻ ሜንታሊቲህን ያልፋቅክ ይመስለኛል :: ብቻ ሰልጠን በል :: የጓዳህን ታሪክ ላደባባይ እያበቃህ አትጃጃል :: ለልጆችህ ማሰብ ጀምር :: ይሄኔ ባለቤትህ ዛሬም ለልጆቿ ብላ ችላህ እየነሮች ይሆናል :: አስተዋይ ሚስት ናት Wink


ሚስቴ ያልተማረች መሀይም አይደለችም ሁለታችንም እያየን ነው የምጽፈው የምደብቃት ነገር የለም ደግሞም አልፎ አልፎም ቢሆን ዋርካ ላይ ተሳታፊ ናት አይታዋለች ::
የጻፍኩት ግን እንደጀብዱ ሳይሆን ርእሱን ተመልከት ::
ታሪኩን አወከው አላወከው አታውቀኝ እንኩዋን ይህን ቀርቶ አባትህን የገደልኩት እኔ ነኝ ብልህስ የት ታውቀኛለህ


ወንድሜ እኔ ለራስህ ለትዳርህና ለልጆችህ ብዬ እንጂ ያንተን ታሪክ አውቀኩት አላወቅኩት እኔን ቅንጣት ታክል የሚጠቅመኝም የሚጎዳኝም ነገር የለው :: የዋህነትህን "ከጀብዱህ " ስልተረዳሁት አንድ ምክር ደግሞ ልለግስህ :: በነጠብጣብ ስም ዋርካ ላይ ስለተሳተፍክ ከማንም የተደበቅክ እንዳይመስልህ :: እንኳን አባትህን የገደልኩት ወንጀለኛ እኔ ነኝ ማለት ቀርቶ ሌላ ከግድያ አነስ ያለ ወንጀል ፈጽመህ እዚህ ኮንፌስ ብታደርግ እንኳን በቀላሉ ማንነትህ ትሬስ ተደርጎ ሊደረስብህ ይችላል :: እና በድጋሚ አትጃጃል - ወንድማዊ ምክሬ ነው :: ያለፈው አልፏል ልጆችህን እያሰብክ ኑር :: እንደክፉ "ወዳጅነትህ " ክፉ አባት እንዳትሆን Laughing
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
...

አዲስ


Joined: 13 May 2009
Posts: 26
Location: Ethiopia

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 11:04 am    Post subject: Reply with quote

ኪኮ እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
ኪኮ

ስምሽ ራሱ የዞረበት ይመስላል ልክ እንደአስተሳሰብሽ


ትርጉም የለሽ ከሆነው ካንተው ነጠብጣብ ነገር የኔ ስም አስሬ ትርጉም ይሰጣል ........ትልቅ ትርጉም ያለው አብሪቬሽን ነው .........የዞረብህስ ካልጠፋ ስም ነጠብጣብን የተጠቀምክ ስመ - ቢሱ አንተው ራስህ ነህ ? የኔ ስም የዞረበት ከሆነ ያንተ ትርጉም የማይሰጥ የነጠብጣብ ስብስብ ምን ሊባል ነው ?

Quote:
አስቦ ሸምቆ የገደለና ባርቆበት የገደለ ሁለቱም ገዳይ ቢሆኑም በህግ ፊት እኩል ቅጣት አያገኛቸውም ህግም ቢሆን ጥፋቱ የተደረገበትን ሁኔታ ይመረምራል ልክ እንዳንቺ በግምት አይፈርድም
Quote:ይህኮ ግልፅ ነገር ነው .....ልጅቷን ተመኘሀት .....ፈለግካት ..አገር አማን ነው ብላ በተኛችበት ሄደክ አንቀህ እንዳትጮክ አፏን አፍነህ ደፈርካት .......እንዴት ነው የደፈርካትኮ በእንቅልፍ ልብህ አደለም .....ደግሞ አታፍርም አፍ አለኝ ብለህ ታወራለህ !!!

የአቶ ጭድ ዘመድ መጣና በነጭ አመድ ተሸፍኖ ያለውን ፍም እሳት እባክህ ይህን ጭድ እከሌ ዘንድ አድርስልኝ ብሎ ሰጠው ፍምም ተቀበለና ሊያደርስ ቃል ገባ ::
በጉዟቸው ላይ በቀን ሲታይ አመድ ተሸፍኖ የጠፋ ቢመስልም ውስጡ ግን ፍም የነበረው እሳት ጭድን አንድዶ የተላከበት ቦታ ያደረሰው አመድ አድርጎት ነው ::
እናም ጥፋተኛው ማን ነው ?
Quote:አንተ ጭድ መሆንክን ብቻ ሳይሆን በቀላሉ በእሳት የምትቀጣጠል ገለባ መሆንክንም ጭምር ካመንክ ቀድሞውኑ እሳትን በአደራ ተቀብለህ ይዘህ መሄድ አልነበረብህም ......ፐሬድ !!!...ጥፋቱ የራስህ ነው ......ተዳፈነ ያልከው እሳትኮ እንደተዳፈነ ነበር ......አንተው ገለባው ራስህኮ ነህ የተዳፈነውን እሳት ገላልጠህ ...አረ ይቅርብህ ....ብሎ ቢጮህም እንኳን አልሰማ ብለህ ......የተቀጣጠልከው ..........እውነትም አንተ በርግጥ ጭድ መሆን አለብህ ....ገለባ !!!!


አንቺ ግን ህግ ምን እንደሆነ ሳትረጂ ተቆርቁዋሪ ትመስያለሽ ... ስንቶች ናቸው አገራችን ውስጥ በጠለፋ ተገደው ተወስደው ከተደፈሩ ቡሀላ በዛው ሚስት ሆነው ቀርተው አንቺን የመሳሰሉ የስንቶች እናት የሆኑት ያውም ከጠላፊ ባሎቻቸው ጋር ሆነው :: አባትሽ ሚስታቸውን (እናትሽን ) እንዴት እንዳገኙ ጠይቂ እስቲ ጠልፈው እንደሆን ይነግሩሻል አልያም የዘመዳቸውን ወይም የጎረቤታቸውን ታሪክ ይነግሩሻል

Quote:ፍራንክፈርት ነው የምኖረው ስትልኮ ትንሽም ቢሆን የተማርክ አይነት መስለከኝ ነበር ....ለካ 17 ኛው .ዘመን አልወጣህም ..........አገር ቤት ጠለፋ መኖሩ ያንተን ስህተት ትክክል አያደርገውም ........ዘመዶችህ አስገድደው ስለሚደፍሩ አንተም እንደነሱ ማድረግኮ የለብህም .......ለኔ ጠለፋ ጠለፋ ነው ........ደደብና እንዳልከውም ገለባ ወይም ጭድ ካልሆንክ በስተቀር አገር ቤት ያሉ ሰዎች ይጠልፋሉና ....አውሮፓ እየኖርክ እኔም ያገኘሁዋትን ሴት አስገድጄ እደፍራለሁ ብለህ አታስብም ነበር

እኔ እስር ቤት ብገባ እሷ የምትጠቀመው ምንድነው ?


ረዳት አልነበራትም እንጂ የተደረገውን ሁሉ ለፖሊስ አሳውቃ ....አንተ ሸቤ ብትገባ ኖሮ ....እሷም ያላንተ እርዳታ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተጠቂ በመሆኗ ብቻ ወረቀቷን በቀላኡ ታገኝ ነበር

Quote:
እውነቱን ልንገርሽና አንቺ ያላገኘሽውን ትዳር ነው ያገኘችው አንቺ በሰው እያየሽ የምትቀኚውን ያላገኘሽውን ትዳር ነው ያገኘችው ደስተኛ ነች :: ውጤቱን ነው ማየት ያለብሽ

ማፈሪያስ አንቺ ነሽ


በነገራችን ላይ እኔ ሴት አይደለሁም .........የትዳር ችግርም የለብኝም .......ሚስትህ ደስተኛ ከሆነች መልካም ......እጅግ በጣም ጥሩ አዕምሮ አላት ማለት ነው ....ግን አይመስለኝም ......በቃ አለማመን ደግሞ መብቴ ነው .....ይልቁንም የማወራው አደራ ከተባለ 24 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አደራውን ከበላ እምነተ -ቢስ ከሆነ .......ምንም ነገር ቢነገረኝ አላምነውም .....በቀላል አነጋገር ሚስቴ ይቅርታ አርጋልኛለች ምናምን ብለህ የቀባጠርከውን አላምንም ...........


ሰላም ወንድሜ ኪኮ

ስለይቅርታው ማመንና አለማመን መብትህ ነው አልጋፋህም
በመሰረቱ ጠለፋን ትክክል ነው ብዬ አይደለም የተናገርኩት እንዲያውም እኔ ከፈጸምኩት ድርጊት የከፋ ድርጊት እንደሆነ አሳምሬ አውቃለሁ :: ነገር ግን እኔ ያደረኩት አዲስ ነገር ሳይሆን የተደረገ ድርጊት መሆኑን ለማመልከት ነው :: ይህ ማለት ድርጊቱን ትክክል ያደርገዋል ማለት አይደለም ::
በመሆኑም የፈለገው አይነት ስህተት ቢፈጸምም አንተ መኖሩን በማታምነው ይቅርታ በሚባል ሁኔታ እርቀ ሰላም ወርዷል :: ላደረኩትም ጥፋት ከምታምነው በላይ መስዋእትነት እስከመሆን ያስከፈለ ካሳ ከፍያለሁ ያንን መናገር ስለማልፈልግ ነው ::ብታሰር ከምታገኘው ጥቅም ይልቅ በብዙ እጥፍ ነው የጠቀማት ... በዚህም እሷም ሆነች ቤተሰቦቿ ደስተኞች ናቸው :: የመኖሪያ ፈቃዷን በዚህ አገር ህግ ገና ከመምጣቷ እጇን ሳትሰጥ በመደፈሯ ብቻ ልታገኝ አትችልም ይህንን ህግ አሳምሬ አውቀዋለሁ በተግባርም ያየሁት ነው :: በራሷ ግን አታገኝም ብዬ መናገር አልችልም ልታገኝም ላታገኝም ትችላለች :: ባልም ቢሆን ከኔ የተሻለ ልታገኝም ላታገኝም ትችላለች ያንን መተንበይ አይቻልም ::
ደስተኛ ትዳር ስለመመስረቷ ግን ራሷ ብትመሰክር ደስ ይለኛል ::
መቼም እያስገደድኩኝ በር ዘግቼባት እንደማላኖራት ግልጽ ይመስለኛል ::
ላለፉት 10 አመታት ያህል ባሳየሁዋት ባህሪና በሰጠሁዋት ፍቅር እንዲሁም ባደረኩት ድርጊት ሁሉ ከልቧ ይቅር እንድትለኝ ማድረግ ችያለሁ ::
ይህን ራሷ ብትናገረው ደስ ይለኛል :: ወደፊትም ከማሳያት ባህሪ አልለወጥም እሷም ብትሆን ተፈቃሪ አስተዋይ መሆኗን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ ::
በተረፈ ግን መጥፎ ድርጊት ባጋጣሚም ሆን ሆን ተብሎ ሊፈጸም ይችላል ተመጣጣኝ ካሳና ይቅርታም ድርጊቱን ሊሸፍነው እንደሚችል ማወቅ ደግሞ አንድ ነገር ነው ::
ምናልባትም አንተ ጉድለትንም ሆነ ጥፋትን አጉልተህ የምታይና የይቅር ባይነት ባህሪ የሌለህ ልትሆን ትችላለህ :: እንግዲህ የተፈጥሮ ባህሪህ ከሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም :: ይቅር ባይነትን ግን ብታዳብር ለራስህም ከፍተኛ ጥቅም ታገኛለህ ::

ባለትዳር ከሆንክ ግን ሚስትህን ይቅርታ ከለመነችህ እስከምን ድረስ ነው ይቅርታ የምታደርግላት ?

አንተስ የትኛውን ጥፋት ነው ይቅርታ እንዲደረግልህ የምትፈልገው ? የማትፈልገውስ የትኛውን ነው ?? በሚስትህም ይሁን በሌላ በማንኛውም ሰው ሆነ ከሰው በላይ ባለ አካል ::

በስህተት ሴት ስላደረኩህ ግን ይቅርታ

ሰላም ሁን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3350
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 7:39 pm    Post subject: Reply with quote

ታሪኩ እውነት ተፈጽሞ ከሆነ ልጁ 'የዛሬ አስር ዓመት ያጠፋሁትን ጥፋትና በደሌንም ለመካስ ያደረኩትን ታሪክ አድምጡኝ ' አለ እንጂ መሳሳቴን ንገሩኝ አላለም :: እዚህ ሁልሽም እየተነሳሽ ሕግ እየጠቀስሽ ልጁ ላይ የምትፈርጂ ሁላ ዋርካ ላይ ስላላወጣሽው እንጂ ስንት ጉድ አለሽ ? ቅቅቅ

ከልጅቷ በላይ ይቅርታ አድራጊ የለምና ጥፋቱን አምኖ ይቅር ከተባለ give him a break!!
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
Page 4 of 4

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia