WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 354, 355, 356 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 17, 2012 3:05 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የሱቁ ጌታ :-

አየህ 'የታገሠ ከሚስቱ ይወልዳል ' ይባላል :: ዋርካን አየሃት አይደለም Exclamation እባክህ እኒያን የምንወዳቸውን ወገኖቻችንን በሚጥማቸው ቋንቋ ለምነህ አምጣልን ::

ደግሞ መጣሁ ብለህ እንደተለመደው በዚያው ቀልጠህ እንዳትቀር Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ::

ተድላ

********************************************* ተድልሽ ስላም ነው Question ይህው እኛም ብቅ እያልን ነው

ባለሱቅቅቅቅቅ ቀጥልልልል አንተ ኡጋንዳ ፈቲ እንጀራ ከናፈቀህ ዲሲ አይደለም ላንተ ለሌላም እንተርፋለን ቅቅቅቅቅ ገደልከኝ ከምር ግን አሳዘንከኝ ............እስቲ ደመቅመቅቅቅ አድርግልን ቤታቸንን ተድልሽ እንዳለውም ዘግተው የጠፍት ይመጣሉ ቅቅቅቅቅቅቅቅ

መልካም ዊኪንድድ
የግልልልልል .
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Feb 18, 2012 12:10 am    Post subject: Reply with quote

አደቆርሳ እንደፃፈው
Quote:
ካምፓላ መአት የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች አሉ ነው የምትለኝ ? ገሪም ነው !
ይገርምህል በኢትዮጵያ ከነበረው የቀይ ሽብር ዘመቻ እልቂት የባሰ ከሩዋንዳና ቡሩንዲ አካባቢ ተነስቶ እስከ ኡጋንዳ በደረሰ ጊዜ እዛ ስለነበርኩ ብዙ ክፉና የማይረሱ ነገሮችን ተመልክቻለሁ ::
እነዚያ ሰዎችና እኛ አፈጣጠራችንም ይለያያል ብዬ ብዙ ግዜ ድምዳሜ ላይ ሁሉ እደርስ ነበር ግን ነገር ሲያልፍ ተረት ይሆናል እንደሚሉት እየሆነ ነው እንጂ እኛም ሃገር በደንብ የተደረገ ነገር ነው ::
እናልህ ወንድምዬ መቼም ያንዱ ሞት ላንዱ ሽረት ነው ይባል የለ በእልቂቱ ዘመን ያላሰብኩት ነገር ገጠመኝና እለት ተለት ምግቤም መኝታዬም ሆቴል ነበር ታዲያልህ ያኔ የኢትዮጵያ ምግብ ቁጥር አንድ ተመጋቢ ነበርኩልህ ::ማደሪያ ሳይኖረኝ ማደሪያ ያጣ አስጠግቼ አጠገበኝ :
ሳሙኤል ይባላል ወላጆቹቹ ኡጋንዳውያን ናቸው የተወለደው ግን ሩዋንዳ ነው ኡጋንዳን በጭራሽ አያውቃትም በጣም የተመቻቸ ኑሮ ይኖር ነበር ችግሩ ሲነሳ ሳሙኤል የመጀመሪያው ሰለባ ሊሆን የሚችል መሆኑን ቀድሞ ያውቃል ቢሆንም ሳይታሰብ ነገሩ አስጊ ሆነ ቤተሰቡም በአንድ ሌሊት ተበተነ እሱም መልኩን ለውጦ ከመሃላቸው ያመልጥና ወደ ኡጋንዳ ይመጣል ኡጋንዳ ማንንም አያውቅም : አይገርምህም ኡጋንዳ በገባ በሁለተኛው ቀን ከኔ ጋር ተገናኘን በጥቂት ደቂቃዎች ወሬ በኋላ ሊለየኝ አልፈለገም የዛንው ቀን አብረን ውለን አደርን ሌሊቱን ሙሉ ታሪኩን ሲያጫውተኝ ነጋ ::
የጦርነቱን አጀማመር ስለ ኪጋሊ ቤተሰቡና ኑሯቸው ስሎእ ፍልሰታቸውና መበተናቸው ወዘተ
በጣም ተደነቅኩ አከበርኩት ማድረግ ስላለበትም ሁኔታ እና ቤተሰቦቹን እንዴት ማግኘት እንደሚችል በሚያደርገው ትግል ውስጥም ሙሉ አጋሩ ሆንኩኝ በተለይም የትንሿ እህቱ ነገር እረፍት ነሳው ውሎ አድሮ ባደረገው ጥረት እግዚአብሄር ትልቅ ብሥራት አሰማው : ትንሿን እህቱን እዚያው ኡጋንዳ ውስጥ አገኛት ይሄ የሆነው ከኔ ጋር በተገናኘን በወሩ ይሆናል ታዲያ የዛን ቀን ወደማታ ጠራኝና ከዛሬ ጀምሮ እዚህ አናድርም አንተም እኔም ሆቴል እናድራለን እዚህም እያበሰልን አንበላም ሆቴል እንበላለን አለኝ
ይሄ ሰውዬ መቃም ጀመረ እንዴ ? አልኩኝ በሆዴ ቂጣ እየጋገርን በውሃ እያማግን የምንበላ ሰዎች በአንድ ጀምበር ሆቴል እንግባ ይለኛል እንዴ ? ለብሄራዊ ቡድን አልተመረጥን ወይ ኤን ኤች አር አልተቀበለን ምንድነው ነገሩ ? አልኩና ገረመኝ ወዲያው መኪና ተኮናተረና በሹፌር እየተነዳን ወደ ደቡብ ኡጋንዳ አመራን ሁለት ሶስት ከተሞችን እንዳለፍን ነገሩ አስተማማኝ ስላልነበረ እኛ ቀረንና ሹፌሩ ሌሊቱን ተጉዞ ልጅቱን እንዲያመጣ ተነገረውና ቀጠለ : እኔ ግን ሳሙኤልን ለዚህ ሹፌር ብር በድንብ ስጠው አልኩት .... እንደዚያ አይነት ሰው አይቼ አላውቅም ብቻ በቆምንባቸው አራት ቦታዎች አራቴ በልቷል ትንሽ እንደሄድን እርቦኛል ይልና ይበላል አሁንም ትንሽ እንደሄድን እራበኝ ይላል ብቻ መብላት መብላት አሁንም መብላት ነው መፈክሩ እንዲሁ እንደበላ ሸኘነውና በማግሥቱ ልጅቷን ይዞ ከተፍ አለ ::
የሳሚ ደስታ እስካሁን አይረሳኝም አብሬው ስደሰት ቆየሁና ....እዚህጋ የገረመኝን ልንገርህ ሴት እህቱን በዚያ ቀውጢ ጊዜ ለአንድ ሹፌር ይዘህልኝ ብሎ ሲልከው ይጠራጠረዋል አልያም ያስጠነቅቀዋል እያልኩ ብጠብቅ ምንም እንደውም ትዝም አላለውም ነበር እኔ ግን ክፋቴ ይሁን ደንቆሮነቴ አላውቅም ዝም ማለት አቅቶኝ ነበር :: ብታምንም ባታምንም አሁንም ቢሆን እንዲህ ያለ ነገር ቢገጥመኝ እጠራጠራለሁ እነሱኮ ምንም ምንም አይሉም ምናልባት ተናግረው ምንም ስለማያመጡ ይሆናል ብዬ ነው የማምነው እንጂ ንጹህ ስለሆኑ አይደለም እንደውም እስከ ቅርብ ሰዎች ድረስ ዝም የማይባባሉ ሌቦች እንደሆኑ ነው የማውቀው ::
ሌላው ደሞ ሹፌሩ እህቱን ሊያመጣ ሲሄድ እኛ ብቻችንን ስለነበርን ልጠይቀው ደጋግሜ የቃጣሁት ነገር ቢኖር ይሄን ያህል መአት ገንዘብ ይዘህ እንዴት ከኔጋር ቂጣ ስትበላ ከረምክ ?
የሚል ነበር ነገር ግን በመጨረሻ ትዕግስቴ አስደሰተኝ : ራሱ ነገረኝ እህቴ የት እንደደረሰች ሳላውቅ ምንም ማድረግ አልፈለኩም ነበር አለኝ :ምናልባት ገንዘቤ ቢያልቅና እዚህ ነኝ ድረስልኝ ብትለኝና baይኖረኝ ራሴን ከማጥፋት የተሻለ አማራጭ አይኖረኝም በዚህም ላይ ሴት ስለሆነችም በደህና አገኛታለሁ አላልኩም ነበር መታከም እንዳለባትና ከወዲሁ መዘጋጀት ስለነበረብኝ ነው ራሴን መቸገር አለብኝ ብዬ ያስቸገርኩት ብሎ ሲለኝ አደነቅኩት ::
አይ የኔ ነገር የጀመርኩትን ትቼ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገባሁ ጫፍ ካገኘሁኮ መመለስ አላውቅም ::
ግን ደሞ ተናግሬ የሚወጣልኝ ወይንም መናገር የማልችል ሰው ስልሆንኩ ይሆናል መጻፍ ስጀምር አፌ የተፈታ ሁሉ ይመስለኛል
ብቻ ዋናው ነገር ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶችን እለት በእለት መጎብኘት እየመረጥኩ መብላትና ያማረ ልብስ መልበስ የቻልኩት : በዚያው ብዙ ነገሮችም ተቃኑና ሁኔታዎች መልክ መልክ ያዙ ..... ሴትዮዬንም ለስራ መጥታ ሳለ አንድ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ተገናኝተን ለመተዋወቅ ቻልኩ ::
ይሄንን እንኳን ከዚህ ቀደም አጫውቼያችኋለሁ ብቻ ታሪክ ተለወጠ እልሃለሁ ::
በተለይ እዚያው ካባላጋላ የሃይልና የተፈጥሮ ፕሮዤ ነበረ ..... ኤጭ ተወኝ እባክህ ወንድሜ አታስለፍልፈኝ ::
ፊያሜታን ለማየት ቸኮልኩኝ መሰለኝ ምክንያቱም ካምፓላ የፍቅር ከተማ ናት ሰላማዊ ከተማ ናት በተለይም የቢክቶሪያ ሃይቅ ሰላማዊውን የፍቅር ንፋስ ወደከተማው ያነፍሳል እንደሚባልለት የካምፓላ ፍቅር ዋዛ እንዳይመስልህ ::
ለነገሩ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ሱዳንን የሚያህል የፍቅር ሃገር አለ ብዬ አላምንም የምን አላምንም ነው የለም :: ሱዳን ህዝቡም ባህሉም ልዩ ነውሰስቲ ፊያሜታ ጊላይን ይቅርታ ፊአ ሜታን አስተዋውቀን ::
ቸር ያቆየን

ዋርካ ደርቃለች ነው ጠፈፍ ብላለች የምትለው ፕሮፓጋንዳ ነው እንዴ ?
የአህያዋ ተረት ትዝ አለኝ ነገሩ ትንሽ ባለግ ያለ ተረት ስለሆነ ልተወው ግን አህያ በመጨረሻ
(ካላረገዝኩ አላምንም ) ያለችው አስተማሪነት ያለው ቁም ነገር ነው ::
ዋርካም እንደዛ ነው ካሁን በኋላ ያጸዱታል ብዬ አልገምትም ::

እኔም እመጣለሁ

አንቺ የግል
"አዲሳባ " ቁጭ ብለሽ .... ሰውን በቀላሉ ... እንጀራ ካማራቹ እዚህ ስትይ
ታበሳጫለሽ
ቀሽም ጣፋጭ ጉጂ

እመለሳለሁ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 18, 2012 10:51 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ወገኖቻችን :-

እንዴት ናችሁ ? ክረምቱ የከበዳችሁ ክረምቱን ያቅልልላችሁ : የበጋው ሐሩር ያቃጠላችሁም ከባህር ነፋሻውን አየር ይዘዝላችሁ :: ይኼው እናንተ ቤታችሁን ክፍት ትታችሁ ከሄዳችሁ ወራት መቆጠር ጀምረዋል :: በዚህ ሁሉ የዋርካ ትርምሥ ጊዜ በጽናት ከጎናችን ቆሞ ያልተለየን የሠፈራችን ኪዮስክ ባለቤት ቱጃሩ ወንድማችን ባለሱቅ ነው :: በጅሮንድ የግልም አልፎ አልፎ ትጎበኘናለች :: ለጊዜው ተለይታችሁን በመሄዳችሁ ቅር ቢለንም ጭራሽ ተራርቀን እንቀራለን ብለን ተስፋ አንቆርጥም :: በወገኖቻችን ላይ ተስፋ ከቆረጥን የምናስበው መልካም ነገር ሁሉ የተስፋ ጉም ሆኖ ይቀርብናልና Exclamation

እና አዲሱ ቤታችሁ ተመቻችሁ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

በሉ አትጥፉ ::

አክባሪያችሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Feb 20, 2012 7:10 pm    Post subject: Reply with quote

እንዴት ያናድዳል በናታቹ
ይህ የሞዛምቢክ ኢንተርኔት
ሁለት ቀን ሙሉ እኮ ነው የሞከርኩት ዋርካ ለመግባት ....
አቅሙ አልችል ብሎት እምቢ አለኝ እንጂ
ሂሂሂ አሁን የኮምፒተሬን ህመም የማወራበት ሰአት እንዲኖረኝ ትፈልጋላቹ
ለምን እንደጤፋሁ ማወቅ ነው ወይስ የጀመርኩት የፊአ -ሜታ ታሪክ ማወቅ ነው ምትፈልጉት
የራሳቹ ጉዳይ
እኔው መልሱን ልስጣቹ
እና እንዲህ ልቀጥል
.......................................//..................................
እኔና ፊአ -ሜታ በጣም ብዙ ያወራን ይመስለኛል እዛች ምግብ ቤት ሆነን
ምግቡን ግማሽ ያህል እንደበላሁ ነው ትዝ የሚለኝ
የሆነ ደስስስስስ የሚል ስሜት ተሰምቷቹ ያውቃል ....
እና ስሜት የምግብ ፍላጎታቹን ሲዘጋ ተሰምቷቹዋል
እንደዛ ነው የሆንኩት የዛን ቀን
ነርስ ናት
ስራ እየፈለገች ... እና የዛን ቀንም ዪኒሴፍ ቢሮ ሄዳ ስትመለስ ነበር ያገኘኃት
ከአስመራ በሱዳን በኩል እንደወታች ነገረችኝ
የምሰራው ከደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ካለች ትንሽዬ የድንበር ላይ ከተማ እንደሆነ ነገርኳት
ሰአቱ እንዴት ይሮጣል ግን ሰው የመንፈስ ምግብ ልመገብ ብሎ ሲጀምር
ኤኒዌይ
> አንተ መሄድ አለብኝ ... ብዙ ቆየሁ ... አለችኝ
+ እረ እኔም መሄድ ነበረብኝ ... "የያዘኝ ይዞኝ እንጂ " ብዬ ለራሴ አጉተምትሜ ...
ሂሳባችንን ከፍለን ወጣን
ሹፌሬ እስከሚጠብቀኝ ቦታ በእግር ሄድንና .... ላርድስሽ አልኳት
> ቅርብ ነው ቤት .. -ቦዳ ሄዳለሁ .... አለችኝ (ቦዳ = ሞተር -ብስክሊሊት ታክሲ )
+ ተይ ላድርስሽ ... ምንም ችግር የለውም እኮ ... እግረ -መንገዴን እው እኮ
> አይ ይቅርብኝ ... አመሰግናለሁ
አለችኝ እና ተለያየን
መኪና ውስጥ ገብቼ ሳያት ,.,,... ፋሲካ -ሆቴል \ፊትለፊት ያለውን መንገድ ተሻግራ ሄደች
ካሁን አሁን ቦዳ ትይዛለች ብዬ ስመለከታት ... በእግሯ አቀጠነችው
ቤቷ .. የት እንደሆነ ባላውቅም .. እሩቅ መሰለኝ
መኪናዬ ተነሳች .... ወደ -ስራ ልሄድ ነው
በእግሯ ስትኳትን በርቀት አየኃትና
አይ ያበሻ ነገር ብዬ ታዝቤ እንደመተው
ደወልኩላት
አይ የኔ ነገር ... አሁን ተለይታኝ ናፈቀችኝ ማለት ነው
ፍቅር በስተርጅና ... ሲለኝ ሰማሁት ሞፍቲ
> ሄሎ
+ እኔ ነኝ .... ግን ልክ አይደለሽም
> ምነው
+ ቦዳ ይዛለሁ ብለሽ በእግርሽ እየሄድሽ አይደለም .... ? እያየሁሽ እኮ ነው .... ምናለበት ቤትሽ ባደርስሽ
> ዎክ ማድረግ ስለፈልኩ እኮ ነው ... ለክፉ አይደለም
+ ኤኒዌይ ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል
> እኔም ብትል
+ ተይ እንጂ ..?... ከምርሽ ነው
> ማርያምን !... ምን አስዋሸኝ ... ደስ አለኝ ስላወራሁህ
+ ደስ ይላል ... ስሜት ሲመሳሰል ...
> አደራህን ደውልልኝ
+ እንዳይሰለችሽ እንጂ ....
> ውይ ,, በምን እድሌ
+ አንቺ ጣፋጭ ልጅ ነሽ ከምር
> አንተን ነህ ጣፋጭ .. ከምር
ዋውውውውውውውውውው ነፍሴ እፍረት በእፍረት .... ምን አይነቷ ልጅ ናት ባካቹ
ቃላትቶች አለቁብኝ ... ወይም ጠፉብኝ
ተሰናበትኳት

አደቆርሳዬ ... ገጥሞህ ያውቃል እንዲህ ያለ ነገር
አቤትትትትትትትትትትትት ስንቶቻቹ ይሄዬ ...
ይች አጭበርባሪ ...
ይሄ ... ቅንዝረኛ
እያላቹን እንደሆነ በደንብ ነው የሚታየኝ
እኔም እናንተ ቦታ ላይ ብሆን እንደሱ ነው ምለው
ግን ምናለበት ብንሆንስ !
ዝም ብሎ ሰው ማመን ደስ አይልም ?
አንዳንዴ እኮ ጥሩ ነው ... ለደቂቃም ቢሆን ... በገንዘብ ልታገኘውን የማትችለውን ደስታ ታገኝበታለህ ... ዝም ብለህ በእምነት በየዋህነት ሁሉንም መቀበል
ይህ የኔ ፍልስፍና ነው ... ይስራ አይስራ የራሱ ጊዳይ
እና ምን ይጠበስ ....... ነው ያላቹኝ አይደል
.......................
.........................................//...................................
ካንፓላ ብዙ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት አለ ወይ ያልከኝ አደቆርሳዬ
እኔ ብዙ ወጣ ወጣ የማልለው ባለሱ እንኳን ... ሁለት ፋሲካ አንድ አብነት .. አንድ ኢትዮጵያ ቪሌጅ ... እንደሁም አራት ወይም አምስት ስማቸን የረሳኃቸው ምግብ ቤቶች አውቃለሁ
እና ብዙ ነን ካምፓላ ውስጥ
እረ ምን ካምፓላ ውስጥ ... እኔ ምሰራበት ገጠር ከተማ ውስጥ እንኳን ሁለት የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች አውቃለሁ
እና ብዙ ኤርትራዊ እና ኢትዮጵያዊ እንደሚኖር ይሰማኛል

እረ 2009 አዲስ አመት አካባቢ ... የኦሮሞ ማህረሰቦች ... ቪክቶሪያ ሀይቅ አጠገብ ባህላዊ በአላቸውን ሲያከብሩ በቲቪ እና በጋዜጣ አይቻለሁ
አሁን ሁኔታው ተረስቶኛል እንጂ
ብዙ ያገር ሰው እንዳለ እና ብዙ የንግድ ድርጅቶችም እንዳላቸው ነው የተገነዘብኩት
አንተ በስብስቴ ጊዜ ያየሀት ኡጋንዳ በጣም ተቀይራለች
እርግጤኛ ነኝ ባንተ ጊዜ 6-የስልክ ካምፗኒ እንዳልነበረ ይረዳኛል
አሁን ብታይ ..............
ተወኝ አቦ ... አታበሳጨኝ ... ከጦብያ ጋር እንዳወዳድር እያደረክ
........................................//.........................................
እና
እንደዋወል ጀመርን ...
እኔና ፊአሜታ
ካለሁበት ገጠር ሆኜ
እንደገና ለመተያየት በጣም ጓጓን
የስራ ጉዳይ ሆነና ግን ....... አልሆነም
በየቀኑ በስልክ ማውራት ... መጠያየቅ ቀጠልን
ከወር ከምናምን በኃላ ግን
ፊአ -ሜታ ጠፋች
ስደውል .. ስልኳ ቢዚ .. ወይም አይመልስም ነው ሚለው
አንደኛ ቀን ..... ምናልባት ኔት ዎርክ ይሆናል ... ይሄ የአፍሪካ ኔት ዎርክ እኮ ... ዘመድ ያለያያል
ሁለተኛ ቀን //// ምናልባት እኮ ... ኤየር ታይም Air Time) አልቆባት ይሆናል
ሶስተኛ ቀን ..... ምናልባት ስልኳ ተሰርቆባት .....
አራተኛ ቀን ..... ምናልባት እኮ .... ስራ አግኝታ .. ቢዚ ሆና ....
ሳምንት ሆነ ....
ሁለት ሳምንት ... በፍፁም ታማ ይሆናል .. እንጂ ....
ምን አረኳት
ምን አጠፋሁ
ኢትዮጵያ ነው የምኖረው ብዬ እንደዋሼኃት ደረሰችበትና ... በመዋሼቴ ጣዝባኝ ዘጋችኝ ይሆን
ቢሆንስ ... ነግራኝ ብትዘጋኝ አይሻልም
ድውልልልልልልልልልልል
"the number is swiched off"
በቃ ልተዋት ለምን አስቸግራታለሁ
ምናልባት እኮ ቦይ -ፍሬንድ እንዳላት ደብቃኝ ... ከኔ ጋር ስታወራ ደርሶበት ...............
ምን ይታወቃል
ወር ሞላኝ መሰለኝ .... ሳልደውል
አንድ ቀን ዝም ብሎኝ ነሸጠኝ እና ... ደወልኩ
አቃጨለ
እንደገና አቃጨለ
በሶስተኛው ተነሳ ....
በትግርኛ
> ውለይ ፅብቅ መአልቲ ማርያም በተፀነሲ .. ወቅባቱ
አለችኝና ዘጋችብኝ
ምን እንዳለችኝ ሳይገባኝ ....
ስልኬን ይዤ ፈዝዤ ቀረሁ
አይ ባለሱቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አይበቃቹም ?

እመለሳለሁ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 21, 2012 4:57 am    Post subject: Reply with quote

አይበቃቹም .... ስል ሰምቶ አደቆርሳ
አይበቃንምምምምምምምም ጨምር አለኝ
እኔም ቀለሜን በጠዋቱ ይዤ ጭምርርር
........................//....................................
ካምፓላ ጓደኛዬ ጋር ደወልኩ .... አምቼው የበርጫ ጓደኛዬ
> አታ አድጊ ... የት ጠፍተህ ነው ባክህ
+ እንዴ እንዴ ባለሱቅ ... ከየት ተገኘህ .... በቀደም መጥተህ ብቻህን ምሳ እንደበላህ ሰማሁ .... ሶሪ ተኝቼ ስለነበር እኮ ነው
> እንዴ ቆይ አንተ ... ቀን ቀን ተኝተህ ማታ ማታ የሚስት ስራ ማን ሊሰራልህ ነው ?
+ አሀሀሀሀ ... አንተ ቀላጅ ... ለሱም ጊዝኣ አለ አብሽር .... ቆይ ለመሆኑ መቼ ነው ካምፓላ ምትመጣው
> ፊአ -ሜታን ያገኜህልኝ ቀን
+ ምን አልክ
> ፊአሜታን ታውቃታለህ
+ ነቨር ... ሰምቼ አላውቅም ... ካምፓላ ?
> አዎን ... ሰርቃኝ ጠፋች ..... እሷን ካገኘህልኝ ነው ምመጣው
+ ምን ሰረቀችህ ደሞ ... ያንተ ነገር
> ትንሹን አንጀቴን
+ ..? አካካካካ .... ማታመጣው የለም እኮ
> ከምር ነው እኮ
+ አትቸገር እሷ ወስዳ ከጠፋች ... እዚህ ብዙ አለ ...
> እውነት ግን ከምር አታውቃትም
+ ዌል ሳምንታዊ እና ወርሀዊ ስብሰባ ብሄድ ላገኛት እችላለሁ .... ጊዜ ስለሌለኝ ተሳትፌ አላውቅም እንጂ
> ስብሰባ አላቹ
+ አዎን በየወሩ አንዳንዴም በጎጥ በጎጥ በየሳምንቱ
> ምንድነው ምታወሩት
+ የተቸገረን መርዳት ... አዲስ መጤን ማለማመድ ..... ያለውን የስደተኝነት ፕሮሰስ ማስረዳት .... ባጠቃላይ መረዳዳት
> ዋውውውው .... ከኛ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጣም የላቃቹ ናቹ እናንተ ባክህ
ከምር ቀናሁ .... ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች .መሀከል የሌለ ነገር ስለሆነ .... እኔ ባየኃቸው አገሮች ማለቴ ነው
ድምምምም
+ እኔ ብዙ ጊዜ ስለማይመቸኝ አልሄድም እንጂ ... እንሰበሰባለን .... አሁን ነገር አታረሳሳ .... ማናት ፊአሜታ
> ፊያሜታ የሚል ስም አታውቅም
+ ሰምቼ አላውቅም .... ከየት ናት
> ኦሮማይ የሚል መፃፍ አላነበብክም
+ የምን መፃፍ
> ኢትዮጵያ እያለህ
+ 12 አመቴ እኮ ነው አሽቀንጥራቹ የወረወራቹኝ ... መፃፍ ለማንበብ አልደረስኩም ከኢትዮጵያ ስወጣ
> ረሳሁት .... ኤኒዌይ .. በአንድ መፃፍ ላይ ታዋቂ የአስመራ ገፀ -ባህሪ ናት ... የምትወደድ
+ እና አሁን እንዴት ትዝ አለችህ
> ባለፈው ካምፓላ የመጣሁ ጊዜ ... አብሬአት ምሳ በላሁ እና ....
+ ቅቅቅቅቅቅቅ አንተ አሪፍ ቀልደኛ ነህ .... እሺ
> አሁን ስልኳን ዘግታ ጠፋችብኝ
+ መቼ ነው የመጣችው ... ይህች አጭበርባሪ
> አጭበርባሪ አትመስልም .... ምስኪን ነገር ናት .... ከመጣች ገና ሶስት ወሯ መሰለኝ
+ ኦህ ... በል ተወው .. ወደ -ደቡብ አፍሪካ ሄዳልሀለች .. ወይም ለመሄድ መንገድ ላይ ናት
> እንዴ እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ
+ ብዙዎቻችን እንደመጣን የምናደርገው ነው .... ታሪኩ ረጅም ነው .... ከተሳካላት እርሳት ... ካልተሳካላት ስትመለስ ታገኛታለህ
> ወይ ጉድድድድ ... ታዲያ ምነው ብትሰናበተኝ ?
+ በድንገት ተነሽ ተብላ ይሆናል ... እንግዲህ የስደተኛ ነገር የራሱ ጊዜ እና እቅድ የለውም
> ግን እኮ በቅርብ ስልኳን አንስታ በትግርኛ ሰድባኝ ዘግታብኛለች
+ አሀሀሀሀሀ .... ምን ብላ ... እንዴት ስድብ እንደሆነ አወክ
> እንዴ ስድብ ባይሆን መልስ ስትጠብቅ ትዘጋብኛለች ?
+ እሷን እንደሆነች በምን አወክ
> በድምጧ
+ በል እንግዲህ ችግር ውስጥ ነው ያለችው ማለት ነው .... ጠብቃት ትደውልልሀለች
> እንዴ አንተ እንዴት አወክ
+ የአስመራ ልጆች እንደዚህ ናቸው .... ቅቅቅቅቅቅ .... ዝም ብለው አይዘጉም .... ከአቅማቸው በላይ የሆነ ችግር ካልገጠማቸው በስተቀር ....
> ምን ሊገጥማት ይችላል 3ወር ውስጥ
+ ብዙ ነገር .... ሀዘን ላይ ልትሆን ትችላለች ... ወይ ከቦይ -ፍሬንዷ ጋር ተጣልታ ሊሆን ይችላል .... ለመሆኑ ነግራሀለች እንዳላት
> እንደዚያ አይነት ጨዋታ ውስጥ አልገባንም ... የምናወራው ስለሌላ ሌላው ነበር እስከማስታውሰው
+ ዌል እንግዲህ እዚህ ከተማ ካለች ጠብቃት .... አለበለዚያ .. ሄዳለች እድሏን ልትሞክር .... ሳውዝ አፍሪካ ..... የኛ አሜሪካ
ህምምምምምምም
እንደዚያ ከሆነ በሄደችበት ይቅናት .... በዚያ በተቦጫጨረው ፊቷ ላይ ... በዚያ በሚያምረው አይኗ ውስጥ ያየሁት ጥልቅ ሀዘን .. እና የብቸኝነት አለም ... ምን እንደሆነ ማወቅ በጣም ጓጉቼ ነበር

ይቅናሽ በሄድሽበት ይቅናሽ ላንቺ
አይክፋሽ እንደኔ ተደሰቺ
እኔው ልጥቆርልሽ እኔው ልክሳ
ይውረድ በላዬ ላይ ያንቺ አበሳ

የሚል ዘፈን ለምን ትዝ አለኝ ባካቹ

እንመለሳለን ከፊአሜታ ጋር
ትንሿ ነበልባል
ጲርርርርርርርርርር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Feb 21, 2012 8:36 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
እንዴት ያናድዳል በናታቹ
ይህ የሞዛምቢክ ኢንተርኔት
ሁለት ቀን ሙሉ እኮ ነው የሞከርኩት ዋርካ ለመግባት ....
አቅሙ አልችል ብሎት እምቢ አለኝ እንጂ
ሂሂሂ አሁን የኮምፒተሬን ህመም የማወራበት ሰአት እንዲኖረኝ ትፈልጋላቹ
ለምን እንደጤፋሁ ማወቅ ነው ወይስ የጀመርኩት የፊአ -ሜታ ታሪክ ማወቅ ነው ምትፈልጉት
የራሳቹ ጉዳይ
እኔው መልሱን ልስጣቹ
እና እንዲህ ልቀጥል
.......................................//..................................

...
አይበቃቹም ?

እመለሳለሁ

የሠፈራችን ኪዮስክ ባለቤት Smile

አንድ ኢትዮጵያዊ ስለሞዛምቢክ ኢንተርኔት ቀርፋፋነት ማማረር አይችልም :: ቢያንስ እነርሱ አገር ከአንድ በላይ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሠጡ የግል ኩባንያዎች ይኖራሉ :: ስለዚህ ሽልንግህን ዱቅ አድርገህ የተሻለ የኢንተርኔት ፍጥነት ካለው አገልግሎት ሠጪ ተጠቀም ::

አደራ ከሞዛምቢክ ስትመለስ የሾላ ፍሬ ይዘህልን ተመለስ :: ምናልባት የሾላ ዛፎች ካላየህ እኔ ሥፍራውን ልጠቁምህ እችላለሁ Smile Smile Smile

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 21, 2012 3:56 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንዳለው
Quote:
አደራ ከሞዛምቢክ ስትመለስ የሾላ ፍሬ ይዘህልን ተመለስ :: ምናልባት የሾላ ዛፎች ካላየህ እኔ ሥፍራውን ልጠቁምህ እችላለሁ

ፕሊስ የት እንደሚገኝ ንገረኝ እና ልቅመሰው .... ወይም ስሙን በፈረንጅኛ አስተምረኝ
በነካካ እጅህ ታዲያ አረንጓዴው ወርቅ (በርጫ ) የት እንዳለ ጠቁመኝ
አደራህን
..........................................//........................................
አንድ ከሰአት በኃላ በሞባይሌ ላይ መልክት አገኘሁ
> አለህ ወይ ባገሩ .... ተቀየምከኝ ዎይ .... ይቅርታ በናትህ .... ከቻልክ ደውልልኝ
የሚል መልክት
መልክቱ ሲደርሰኝ .... ቀስስስስ ብላ በለሆሳሳ የምታወራ ነው የመሰለችኝ
እኔም ሳነበው እንደዚያ ነው ያነበብኩት
ገጠር ነበርኩ እና ደወልኩላት
> አንቺ !... በሰላም ነው ወይ የጠፋሽው
+ ወይኔ .... በናትህ ይቅርታ አስጨነኩህ አይደል
> እረ እንኳን ደህና ሆንሽ እንጂ ... የኔ ጭንቀት ምንም አይደለም .... ግን ምን ሆነሽ ነው እንዲህ የጠፋሽው
+ ብዙ ነው ታሪኩ .... መቼ ትመጣለህ ካምፓላ
> አላውቀውም ... የምመጣበትን ... ግን ግን ግን በናትሽ ምን ሆነሽ ነው እስኪ ጫፍ ጫፉን ንገሪኝ ምን እንደሆንሽ
+ በናትህ አታስጨንቀኝ .... ስንገናኝ .... ወይኔ ባገኝህ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለህ
> እኔም .... ግን ባለፈው በትግርኛ ሰድበሽኝ ለምን ዘጋሽብኝ
+ ዋእ ... እረ ስድብ አይደለም .... ደውልልሀለሁ አሁን ቢዚ ነኝ እኮ ነው ያልኩህ .... ውይ በናትኅኅኅኅኅ
> ቅቅቅቅቅ ገብቶኛል ለነገሩ ግን ትግርኛ እኮ አልችልም ....
+ አውቄአለሁ ... ግን ስላልተመቸኝ ነው .... በሰአቱ አማርኛም ጠፋብኝ
> ከቦይ ፍሬንድሽ ጋር ስለነበርሽ ነው አይደል ?
+ እንደሱ አይደለም ... ግን ስንገናኝ ብንጫወት ምን ይመስልሀል .... ፕሊስ ደውልልኝ ... ደሞ ... ከልብህ ይቅርታ አድርግልኝ
> እረ ምን ገዶኝ .... ምንም አላደረግሽም እኮ .... እንዲሁ ስትጤፊ አሳሰበኝ እንጂ
+ አመሰግናለሁ ስላሰብክልኝ .... ፕሊስ ... ካምፓላ
ውይ ድምፃ ደስ ሲልልልልል
አሁን አሁን ብረር ብረር አሰኘኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንፈራራ የሚሉት ብሽቅ ልጅ .... ፍቅር ነው ብሎ ስሜን ሲያጠፋ አየሁት በዚያኛው ቤት
ፍቅር እንደፍየል በየመንገዱ ሚይዘኝ ይመስልሀል እንዴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ደሞ በስተርጅና ... ልጆቼን እንደማሳደግ ... ፍቅር ማባርር ይመስልሀል ?
አቤት መሳሳትትትትትትትትት
ኤኒዌይ ... እንደምታስበው የሴት እና የወንድ አይነት ፍቅር አይደለም የሚሰማኝ
የሆነ የምትወደውን ስም ስታገኝ እና .... ስለሱ ብዙ ለማወቅ ስትሞክር የምትንገበገበው ግብግብ በሌላው ሰው አተያይ ፍቅር ቢመስል እንጂ ....
በፍፁም በምኔም ውስጥ ምንም የለም
እመነኝ ... ዝም ብለህ
ቢሆን እዚህ መጥቼ አላወራውም ነበር

የቤታቹ ፎንት ግን አሁንም አስቸግሮኛል ....
የደመደምኩት በኔ ኮምፒተር ነውና ... አዲሱን ገዝቼ እስከምገላገል ....
እዚህም እዚያም ነኝ
ለነገሩ ዋርካ አሁን ፅድትትትትትትትት ብላለች ብታያት
ባዲስ ሞድ የተሰፋ ነጭ በነጭ አድርጋ ... ጥለቱ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ... የሆነ አጭር ነጠላዋን ጀርባዋ ላይ ጣል አድርጋ

ሳሙኝ
እቀፉኝ
ውደዱኝ
ጥብቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ጭንቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ትንፋሽ እጥርርርርርርርር እስኪለኝ ድረስ
ስማቹ አሳምሙኝ
እያለቻቹ ነው
ዋርካ የጥንቷ የጠዋቷ

ተድላ ሀይሉም .... እየተጣራ ነው ከሰማቹት

አለበለዚያ እንዳላቃጥለው
ይላቹዋል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

እመለሳለሁ እስኪ

ከስራዬ እንዳልባረር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 1:24 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ ሀይሉ እንዳለው
Quote:
አደራ ከሞዛምቢክ ስትመለስ የሾላ ፍሬ ይዘህልን ተመለስ :: ምናልባት የሾላ ዛፎች ካላየህ እኔ ሥፍራውን ልጠቁምህ እችላለሁ

ፕሊስ የት እንደሚገኝ ንገረኝ እና ልቅመሰው .... ወይም ስሙን በፈረንጅኛ አስተምረኝ

የሠፈራችን ኪዮስክ ባለቤት :-

ብለህ ብለህ ሾላ አላውቅም እንዳትለን Smile Smile Smile አንድ ሠሞን እዚህ እናንተ ቤት እንዲያውም ከምድረ -ገፅ ለመጥፋት የተቃረቡትን የዱር ፍሬዎች (እነ ዶቅማ ) አንድ በአንድ እየዘረዘራችሁ እንዴት ለልማት ልታውሉ እንዳሠባችሁ ስታስነብቡን ነበር :: ታዲያ የእኔ ቢጤ የዋህ ዕውነት መስሎት እናንተን አምኖ የዱር ፍሬ ለማልማት አገሩ ሊገባ አስቦ ይሆናል Crying or Very sad

ሾላ በሣይንስ የተሠጠው ስም 'Ficus sycomorus' ነው :: ሁኔታውም የሚከተለውን ይመስላል :-
ምንጭ :- የሾላ ዛፍና ፍሬ ::

ሥፍራው ከጠፋብህ በአማንዶ ቲቫኔ ጎዳና በቅዱስ እንጦንዮስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አካባቢ ፈልገው :: ሌላም አካባቢ አይጠፋም ::

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
በነካካ እጅህ ታዲያ አረንጓዴው ወርቅ (በርጫ ) የት እንዳለ ጠቁመኝ
አደራህን

እንዴ ሶማሌዎቹ የት ሄዱና የእኔን ኮምፓስ የምትፈልገው Rolling Eyes Rolling Eyes ለመሆኑ ሶማሌዎች ከማፑቶ ለቅቀዋል ወይ ? እነርሱ ካሉ አረንጓዴውን ወርቅ እንደ አሊባባ በምትሃት ያመጡልሃል :: ብቻ እነርሱ የሚተራመሡበትን ሠፈር ማሠሥ ነው Smile

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 291
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 4:32 pm    Post subject: Reply with quote

ቃል በቃል ባይሆንም

"ሚስትህ ባንተ ላይ ከኔ በላይ ምን መብት አላት - የተለዋወጣችሁት ቀለበት ነው ቁምነገሩ ?
ባታውቀው ነው እንጂ እኔ ህይወቴን ልለውጥልህ ነበር ..."

ፊያሜታ ጊላይ በእጅጉ ተረብሻለች - በተባለችው ሰዐት "ሰውየዋን - የመሀል አገሩን " የነገሯት ቦታ ካልወሰደችው -- ሊገሏት ነው

ፊያሜታዬ ተጨነቀችብን

"አታ ግናይ " የሚለው ቃሏ የሰማሁት ያህል ሁሌም ያቃጭልብኛል
"አሳ አሳ ሸተትኩ " የሚለው ግልጽነቷም በጣሙን አስውቧታል

ባለሱቅ ያንተዋም "ፊአሜታ " ጭንቀት ታየኝ
እንደ በዓሉ ፊያሜታ -- ልታገኝህም ትፈልጋለች --- ምን ይሆን ጭንቀቷ ?

መጨረሻህን እየጠበቅን ነው -- ትዝታህ ማራኪ ነው
እነአደቆርሳም ተመልሰው ያን ጣፋጭ ጽሁፋቸውን ያስነብቡን ይሆን ? -- ክርስትያን ተስፋ አይቆርጥም --እስላምም ቢሆን -- እንጠብቃለን እዚችው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 7:55 pm    Post subject: Reply with quote

ጋሽ ኃይሉ
Quote:
በሣይንስ የተሠጠው ስም 'Ficus sycomorus' ነው

በጣም አመሰግናለሁ .... እስኪ በሳይንሳዊ ስሙ የሚሸጥ ካለ ብዬ ለማግኘት እፈልጋለሁ ...
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በነገርህ ላይ ያኔ ስለ ዶቅማ ሾላ እንጆሪ ዝግባ ስናወራ ... የሁሉም ስም ተገኝቶ ስሙ የጠፋው የዶቅማ ነበር ይመስለኛል
የፎረስትሪ ባለሙያ ስላልሆንኩ ሁሉንም ስም አልያዝኩም .... ሾላ ግን ከስሙ የበለጠ ትዝ የሚለኝ ... በልጅነቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስተማሪ ክፉኛ ስመታ መምህሩ ተቀምጠው የነበረው የሾላ ዛፍ ስር ነበር
ከዚያ በተረፈ ስራዬ ብዬ ስሙን አልያዝኩትም
አሁንም ለነገሩ 'Ficus sycomorus' ብዬ ገበያ ብወጣ እንደማላገኘው እርግጠኛ ነኝ
ለማንኛውም ፈልጌ ገዝቼ ቀምሼ ጣዕሙን በዋርካ መስኮት አቀብልሀለሁ
ተስማማን ?
...........................................
ብሩኬ
Quote:
"ሚስትህ ባንተ ላይ ከኔ በላይ ምን መብት አላት - የተለዋወጣችሁት ቀለበት ነው ቁምነገሩ ?
ባታውቀው ነው እንጂ እኔ ህይወቴን ልለውጥልህ ነበር ..."

ስትል ልቤን ነው ያጠፋኸው ከምር
እንዴት ያለ ወርቅ የሆነ አባባል ነው በግዚአብሄር

የኔዋን ፊአሜታ ከዋናዋ ፊያሜታ ጋር ፕሊስስስስስስስስ እንዳታወዳድራት
ከበአሉ ግርማ መንፈስ ጋር ታጣላኛለህና
አደራ
........................ ልቀጥል እስኪ .........................
ካምፓላ መጥቻለሁ
መቼ እንደሆነ ቀኑ ትዝ አይለኝም
ለፊአሜታ እንደመጣሁ ነግሬአታለሁ
ከዚያን ቀን በኃላ አሁንም በየጊዜው እየተደዋወልን እንገናኝ ስለነበር ... ቶሎ ለማግኘት አልጓጓሁም
ግን መምጣቴን ማወቅ ስላለባት ነገርኳት
ምክንያቱም ከሳምንት በኃላ ወዳገሬ ልመለስ ነው
ስለዚህ አግኝቻት ብለያት ምን ይላቹዋል
....................................//............................
ብንዝናና ምን ይልሻል ወይ ወይ
የእድሜ አውቶቡስ ያልፍብሻል ወይ ወይ
ደረጄና ኃብቴ እያሾፉብን ነው
...................................//...............................
ካምፓላ በመጣሁ በሶስተኛው ቀን ይመስለኛል ... ፊያሜታ ደወለችልኝ
> ባለሱቅዬ ... በናትህ ነገር የሚኡመጭ ከሆነ እንገናኝ
+ በምን እድሌ ... እሺ ... ስንት ሰአት
> ጠዋ ,,,,,,,,,,,,.... ይመችሀል ?
+ ምንም ችግር የለም ... እንደውም ቁርስ አብረን እንበላለን
> እሺ .. ግን የት ?
+ የኢትዮጵያ ቪሌጅ ... ብንገናኝ ምን ይመስልሻል
> እሺ ... ጠዋት 9ሰአት እዛ እጠብቅሀለሁ
+ አምላክ ያሳድረን ... እመጣለሁ ... 10ሰአት ግን ስብሰባ ነገር አለችኝ ... ብዙ አላጫውትሽም
> እሺ ... እኔም ብዙ ጊዜ አይኖረኝም ... አግኝቼህ አይንህን እያየሁ ይቅርታህን መቀበል ስለፈለኩ ነው ላገኝህ የፈለኩት
+ እኔም መሄዴ ስለሆነ ... ከመሄዴ በፊት ባገኝሽ ብዬ ነው
> ውይ ልትሄድ ነው
+ አዎን ስራዬን ጨርሻከሁ
> የት ነበር ያለሁት ያልከኝ
+ ኢትዮጵያ ነው ... ከዚያ እየተመላለስኩ ነው ምሰራው
> በጣም ያሳዝናል ... ግን ፕሊስ ከመሄድህ በፊት እንገናኝ ,... ነገ ጠዋት እጠብቅሀለሁ
+ እሺ የኔ ቆንጆ .... አሁን ደህና ደሪ ... ነገ 9ሰአት ኢትዮጵያ ቪሌጅ .. ኦክ !
> ፅቡቕ
+ ናይ ሰመናይ ፅብቅቲ ... ትንሿ ነበልባል ደህና ደሪ
> ቆይ ቆይ ... ከመዝጋትህ በፊት ... ለምንድነው ሁሌ ትንሻ ነበልባል ምትለኝ
+ ውይ አልነገርኩሽም እንዴ ,.,.... የጥንቷን ፊያሜታ ስለሚያስታውሰኝ ነው
> እና ትንሿ ነበልባል ምን ማለት ነው
+ የፊያሜታ ትርጉም ነው
> የፊያሜታ ትርጉም ?
+ አዎና ... ምነው አልነገርኩሽም እንዴ
> እንደነገርከኝ ትዝ አይለኝም ... ማነው ግን እንደሱ ብሎ የተረጎመው
+ መፃፍ ላይ ነው ያነበብኩት ... ምነው ትክክል አይደለም እንዴ
> ምምምምምም እንጃ እኔ አላውቅም ... ግን እናቴ አንዴ በጨረፍታ ስታወራ ትዝ የሚለኝ
ፊአ -ምታ ማለት ... ሀሜት ወዲያ በል ... እንደማለት ነው የተረዳሁት
+ ምን አልሽ ?... ሀሜት ወዲያ ?... ለምን
> እናቴና አባቴ መሀን ናቸው እየተባለ ይወራ ነበር .... ልጅ አይወልዱም ተብሎ ተወርቶ ... ከተጋቡ ከስንት ጊዜ በኃላ እንደሆነ አላውቅም ... እኔ ስወለድ ,.... ሀሜት ወዲያ ... የሚል ስም አወጡልኝ ... ፊያ -ሀሜታ .... በምንኛ እንደሆነ አላውቅም
መናገር አልቻልኩም ... ዝምምምምምምምም አልኩኝ በቃ
> እንዴ ባለሱቅ አለህ ?
+ አለሁ አለሁ እየሰማሁሽ ነው
> ምነው ዝም አልክ ታዲያ
+ በቃ ነገ ጠዋት እንገናን
> ችግር አለ ?
+ ችግር የለም .. ነገ እንገናኝ ... ደህና ደሪ ... የስልክ ገንዘቤን ልትጨርሺብኝ ነው .... ደህና ደሪ ሀሜት ወዲያ
> ደህና ደር ሸጋ ልጅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፊአ -ሜታ .... ሀሜታ ወዲያ .... እንዴት ሊሆን ይችላል
አዲአ ቋንቋ ፈጥረው መሆነ አለበት ... እንጂ
እናቷን ነገ ላግኛት

ደከመኝ
ደህና ደሩልኝ
ቸር ሰንብቱ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 8:02 pm    Post subject: Reply with quote

ተንዛዛሁ አይደል
በደንብ ገብቶኛል
ነገር ግን ሀዘን ላይ ስለነበርኩ ነው
ስብሀት ለአብ /እግዚአብሄር መሞቱን ሰምቼ ክፉኛ አዘንኩኝ
እድሜ የጠገበ ቢሆንም .... የሚሞት ስለማይመስለኝ ይሆን .... ወይስ እንደ -አጋፋሪ እንደሻው ሞትን እየሸሸ የሚኖር ስለሚመስለኝ
መሞቱ አስደንግጦኛል
አምላክ ነፍሱን ተቀብላ .. ከነ -በአሉ ግርማ ጋር ታኑረው
.................................ልቀጥል እስኪ ....................
በጠዋት 9ሰአት ላይ ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት ስሄድ .... ጭርርርርርርርር ብሏል
ወደውስጥ ብገባ ማንም የለም
ከወደ -ጓሮው በኩል
አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣለች
ፀጉሯን ወደኃላ ለቃው ......አቀርቅራ ተቀምጣ . ስትታይ ...
የሆነ ደስስስ የሚልና ... የሚያምር ትዕይንት ይሰጣል
ፊአሜታ እንዳልሆነች እርግጠኛ ነኝ
ምክንያቱም ያኔ ሳያት ...
እንዴ ፀጉሯን አይቼዋለሁ እንዴ ?
እሷን እንዳትሆን ብቻ
> ፊአ -ሜታ ... ብዬ ስጣራ
ብድግ አለችና ... ወደኃላዋ ዞር አለች
አይኔን ማመን አልቻልኩም
ለካስ ውብ ልጅ ናት ... ቆንጅዬ
ፊቷ ላይ ... በተለይ ቅንድቦቿ ላይ ያለው ስንጥር ምልክት አጭበርብሮብኝ እንጂ ...
ወየው እንዴት ታምራለች በናታቹ
ያኔ ያየሁት አይኗ ደሞ ...
+ መጣህ ... ውይ ባለሱቅዬ
> አንቺ አልመሰልሽኝም እኮ ....
አልኳት በመገረም እያየኃት
+ ምነው ተለወጥኩብህ እንዴ
> ... የዛን ቀን በደንብ አላየሁሽም ማለት ነው ... ስታምሪ
+ ሂይ ... በናትህ አታሹፍ ... አሁን ሳመኝ
እቅፍፍፍፍፍፍ አድርጌ ጉንጫልን ሳም ሳም ... አድርጌ ፊትለፊቷ ተቀመጥኩ
> ቁርስ ምን ትበያለሽ
+ ቁርስ ይቅር ... ለስላሳ ይበቃል .. ሰአት የለኝም
> ምን ሆነሻል ግን .. ምንድነው ችግርሽ ... ለምንድነው የጠፋሽው
+ በናትህ እንዳትቀየመኝ
> እረ በፍፁም ... እንዴ ምን ልሁን ብዬ ነው ምቀየምሽ ... ሰው .... ብዬ ልቀጥል ስል .. አቍረጠችና
+ ባለትዳር ነኝ ....
አለችኝ ,, እና ዝም ብላ አየችኝ
> ውይ ደስ ሲልልል ... ታዲያ በዚህ የተነሳ ይቀየመኛል ብለሽ አስበሽ ነው ... ምንም ችግር የለውም እኮ ... ወንድምሽ ነኝ አብሽር
+ ቴንኪውውው ... እንዴት ፈርቼ ነበር ለመንገር
> እንዴ ምን ያስጨንቅሻል ... እኔ ውዴ ሁኚ ብዬ አልጠየኩሽ ... አስቸግሬሻለሁ እንዴ
+ ሳይሆን ... በጣም ለመድኩህ .... በጣም ብዙ ብዙ ነገር ብናወራም .. ባለመናገሬ በጣም ይሰማኝ ነበር
> ይሄ ነው ችግርሽ ?.... በይ በደንብ እንተዋወቅ ... ባለሱቅ እባላለሁ ... ባለሶስት ትንንሽዬ ባለሱቆች አባት
+ ቅቅቅ ታድለህ
> አንቺስ ልጅ የለሽም
+ አለኝ ... ወንድ ልጅ ... አስመራ ነው ያለው
> ፅቡቕ ፅቡቅ ... ጥሩ ነገር ነው ... ደስ ይላል ልጅ በልጅነት አይደል
+ እኔ ግን ደስተኛ አይደለሁም
> ምነው ምን ገጠመሽ
+ ባለቤቴ ይደበድበኛል
> ምን ...አልሽ ?
+ ዝም ብሎ ይመታኛል
> ለምን ... ምን አድርገሽው .... ወጣ ወጣ ማለት ታበዣለሽ እንዴ ?.. ይቀናል ?
+ በሆነና ባላዘንኩ
> እኮ ለምንድነው ሚመታሽ
+ እንዴት ብዬ ልንገርህ .... አንተ አታውቅም እንደሆን እንጂ ... የአስመራ ወንዶች .. ሴቶችን በጣም ... አድርገው ,,,, እንደቤታቸው እቃ ነው ሚቆጥሩት .... እና እንደቤቱ እቃ እንዳንዱ እንድሆንለት ነው ሁሌ ሚያዘኝ
> አልገባኝም .. አልገባኝም ... አሁን እኮ ያለነው አስመራ አይደለም
+ እሱ ግን ከአስመራ ልጅ ጋር ነው
> ቆይ እስኪ እንዴት ነው ... ነገሩ ... በደንብ አስረጂኝ ... እንደቤት ውስጥ እቃ ስትይ
+ አያወራኝም ... አያናግረኝም .... እቤት ውስጥ እንዳለሁ አይቆጥረኝም .... ብኖርም ምግብ አብስሎ ለማቅረብና ... አልጋው ላይ በፈለገኝ ሰአት ዳብሶ ሊያገኘኝ የሚፈልገኝ እቃው ነኝ
> ይሄ ድሮ የቀረ ይመስለኛል .. የተሳሳትሽው ነገር ቢኖር እንጂ
+ ሙት እውነቴን ነው .... እየው ... እዚህ አገር ከመጣሁ ገና 3 ወሬ ነው ... አንድም ሰው አላውቅም ... አንተ የመጀመሪያዬ ነህ ... እንደልቤ የማወራው ማንም ሰው የለም ... አጠገቤ ያለው እሱ ስለሆነ ... ገና ሳወራው ... እንዲ ... አድርጎ ይመታኛል
> እንዴ አልገባኝም ... እስኪ በምሳሌ ንገሪኝ
+ ለምሳሌ ትላንትና .. ሶፋ ላይ ተቀምጠን ቲቪ እያየን ነበር
እና በርዕሰ ጉዳዩ ላይ .. አስተያየት ስሰጥ ... በግራ እጁ .... እዚህ አይኔ ላይ
ብላ እስካሁን ያላየሁትነ ከአይኗ በላይ ያለውን ብልዝ ስታሳየኝ
> እንዴ እንዴ .. ምንድነው ይሄ
+ እሱ ብቻ አይደለም ... ይህወልህ
ብላ ክንዷን ... ባቷን ... ሆዷን ....
እንዴት በልዟል ሰውነቷ
አይኗ እንባ አቀረረ
ልቤ ጭንቀቱን ጀመረ
ምንም ማድረግ ለማልችለው ... ነገር ... ለምን ....
> ለምን ግን ፖሊስ አትሄጅም
+ ቤተሰቤስ ... ጣጣው ብዙ ነው .. አንተ ስለኤርትራ ባህል ምንም አታውቅም
> እና እየደበደበሽ ልትሞቺ ነው ምትፈልጊው
+ አይ ምን መሰለህ
> ቆይ አሁን እኔ ምን ባደርግልሽ ደስ ይልሻል
+ ካንተ ምንም አልፈልግም ... አዳምጠኝ .... Let me talk and release my stress PLEASEEEEEEEEEE
የማወራበት ቦታ የለኝም ... የምናገረው ሰው የለኝም .... የማለቅስበት ቦታ የለም ... .. ካንተ ምንም አልፈልግም ... አውራኝ ላውራህ
> እሺ የኔ ቆንጆ ...... በቃ አንቺ አውሪ እኔ ልስማሽ
ልቤን እንዴት ሙቀት ተሰማው መሰላቹ
እኔ አንድ ተራ ባለሱቅ ... ተመርጬ ... ላውራልህ ,, ሚስጢሬን ... ስማኝ ... ተብዬ ስለመን ....
+ በጣም ደግ ሰው ነህ አንተ ግን
> በይ አሁን እሱን ተይና .. እስኪ ንገሪኝ ... እንዴት ተገናኛቹ .. እንዴት ተጋባቹ ... እንዴትስ ለዚህ ልትበቁ ቻላቹ
.......................................//...............................]
ፊያሜታ የመጨረሻ ክፍል
ውይ መጨረሻ አለው እንዴ ... ገና በእውኑም ያላለቀ ታሪክ ነው
እስካለበት ድረስ እንቀጥላለን

ደከመኝ ከምር

አንድም ሚያዝንልኝ የለም
ቲች ... ቀሽም ሁላ

ሰላም ሁኑ
በፍቅር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሰምፔር

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 20 Jun 2005
Posts: 64
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Feb 23, 2012 8:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ባለሱቅ
ደስ ይላል የምታስነብበን Very Happy ደክሞሀል እረፍት አድርግ ለማለት እና ለማመስገን ነው የገባሁት !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 5:57 am    Post subject: Reply with quote

አንፈራራ
እንደፃፈው
እዛኛው ቤት

Quote:
ኧረ ባለሱቅ ወንድሜ ...

በጣም የሚያሳዝን ወሬ ነው የነገርከን :: በእውነት ልጂቷ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ነች ያለችው :: አይ እህቴን ምን ዓይነት ችግር ውስጥ ናት ያለችው ....

የሚገርም ነው ከኤርትራውያን ጋር ለረጂም ጊዜ ከክብረ መንግስት ጀምሮ አብሬ ኖሬአለሁ ግን ወንዶቹ ለሴቶቻቸው እንዲህ መሆናቸውን አላውቅም ነበር :: ለዚህ ነው ለካ የትግሬ ማለት የኤርትራ ሴቶች የአማራ ወይም ትግሬ ያልሆነ ወንድ ይመርጣሉ የሚባለው ? በዚያው አኳያ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚታየው ሁኔታ ግን እርስ በርሳቸው ተፈላልገው ሲጋቡ ነው :: ሊገባኝ አይችልም ::

ለማንኛውም አሁን ያንተን ፊያሜታን ከተነከረችበት ማጥ ውስጥ ለማውጣት እንዴት ማድረግ እንደሚገባ ማሰብም መመካከርም ያስፈልጋል :: ምንም ሁለቱም ከአገራቸው ውጭ ቢገኙም ሰውየው እርሷን ሁሌ እንደ ኳስ ሊጫወትባት መብት የለውም :: እዚህ አሜሪካ ቢሆን ፖሊስ አንጠልጥሎ ነበር እስር ቤት የሚወስደው ::........

ቆይ ቆይ ቆይ እንዲያውም የሚገርም ነው አንድ የሆነ የተመሳሰለ ኬዝ ትዝ አለኝ እኔ ራሴ ለጉዳዩ የሩቅ ምስክር የሆንኩበት :: የሚገርም ነው እዚህ ያሉትም እዚያ አንተጋ እንዳሉት ከኤርትራ የመጡ ናቸው :: ባልየው ቀደም ብሎ እዚህ ተደራጅቶ ይኖር ነበር :: ከዚያም ልጅቷን ከአስመራ ካስመጣና ካገባት በኋላ ከቤት እንዳትወጣ አድርጎ : እንዳትማር እንዳትሰራ ከልክሎ : እየደበደበ የወሲብ ባሪያ አድርጓት ከቆየ 2 ዓመት በኋላ ; ልጂቷ እንደ ምንም ብላ በሰው እርዳታ ከጠበቃ ጋር ተገና ኘት :: ከዚያም ሁኔታው ፍርድ ቤት ደርሶ በመጨረሻም ሚስቲቱ የሰውየውን ሀብት እንድትወርስ ተፈረደላት :: ባልየው 8 ወር እንዲታሰርና የመኖሪያው ፈቃድ እንዲነጠቅ ከዚያም ከአገር እንዲወጣ ተፈረደበት :: የሁላችንንም አንጀት ነው ያራሰው ዳኛው ::

የአንተን ጓደኛ ጉዳይ የዩጋንዳ መንግስት እንዴት እንደሚያየው ማወቅ አይቻልም :: ግን እግዚአብሐር ይርዳት :: አንተንም ይርዳህ በጉዳዩ እንደተጨነክ ይገባኛል :: በርግጥም ሁኔታው አስጨናቂ ነው ::

እሰይ እሰይ አንፈራራዬ
እስኪ አብረን እንመካከራለን
ስሜቴ ስለተጋባብህ በጣም ነው ደስ ያለኝል ... ከምር

ሁሌ ምን እንደሚታየኝ ታውቃለህ ስለፊያሜታ ሳስብ
አጠገቡ ቁጭ ብላ ... የሆነ ነገር ልታወራ ስትጀምር
በቃሪያ ጥፊ ያገኘበት ቦታ ላይ አድርጓት ... ሂጂ ወደ -ጓዳ ግቢ ... ሲላት
ስታሳዝን ብታቅ

ሁሉም ኤርትራዊያን ግን እንደዚህ እንዳይደሉ ሌላ ጓደኛዬና ሚስቱን እንዴት እንደሚኖሩ ስለማውቅ ... መፍረድ በጣም ያስቸግራል

ለማንኛውም ከታሪኩ ጋር እንመለሳለን

ቸር እንሰንብት

ሴምፐር ወንድሜ ....
አንባቢ አያሳጣኝ ነው ሚባለው
የዘውትር አንባቢዬ ስለሆንክ በጣም አመሰግንሀለሁ ለሞራልህ

አትጥፋ ከእንግዲህም

ሰላምም
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 1:48 am    Post subject: Reply with quote

የሠፈራችን ኪዮስክ ባለቤት :-

እስከመቼ መልዕክት በመላክተኛ ይሆናል Rolling Eyes መቼም እኒያ ቤት ዘግተው ምናኔ የገቡት ወገኖቻችን ወደ ድሮ ቤታቸው አንድ ቀን ብቅ እንደሚሉና ጩኸታችን የቁራ ጩኸት ሆኖ እንደማይቀር ተስፋ አለኝ : ::

አንተን እዚህ በምትጽፋቸው ታሪኮች ስመዝንህ ደግሞ ምናልባት ለወደፊቱ ሣይካትሪ ብታጠና ጥሩ ይመስለኛል Rolling Eyes ብዙ አዕምሯቸው በጭንቀት የሚሠቃዩ ወገኖቻችንን ልታክም ትችላለህና ::

አንዳንድ የአገር ቤት ትዝታ ላጫውትህ :- ሾፌርና ፀጉር አስተካካይ የመንግሥት ሠላይ : ሊስትሮ የሠፈር ታሪክ አጫዋች : የአንተ ቢጤ ባለ ኪዮስክ የሠፈሩ ገንዘብ ሚኒስቴር : ልብስ ሠፊና ሸማኔ (በሴት ወዳጅነታቸው ስማቸው በጥሩ አይነሣም ) : እያለ ይቀጥላል :: አንተ የኪዮስክ ባለቤትነትህን ትተህ ወደ ሣይካትሪስትነቱ ተጠግተሃል Smile ::

በል የዚያችን ምስኪን የአሥመራ ልጅ ታሪክ ቋጨው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 375
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 2:36 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም ይሁን !!!
ቤቱ ለዘለአለም የተዘጋ መስሎኝ ብቅ ብዬ ማዬት እራሱ ትቼ ነበር :: ለካስ አሉልን እነ ባለሱቅ ::

ባለሱቅ !!!!!
አንተ አንዱ ትበቃናለህ !! ኦሮማይን በስም እንጂ ለማንበብ አልታደልኩም :: አሁን ግን ሳስበው በአሉ ግርማ እራሱ ካንተ በላይ ፊያሜታን የገለጸው አይመስለኝም :: በምናብ ያስተዋወቅከንን አሳዛኝ ልጅ ትንሽ የስዕል ችሎታ ቢኖረኝ ኖሮ እራስዋኑ ቁጭ አረጋት ነበር :: መጻፍ አንችል : መሳል አንችል ...ግን ምናባቱ ...እነ ባለሱቅንም ማድነቅ ከቻልን እራሱ ይበቃናል :: ችሎታህ ብቻ ሳይሆን ትዕግስትህም ግርም ይለኛል :: ምን ልናገር ከዚህ በላይ !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 354, 355, 356 ... 381, 382, 383  Next
Page 355 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia