WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
ትግሬወች የኢትዮጵያ እጢወች
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 8:37 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም እንመሰግናለን፡
በቅድሚያ ከአሁን በፊት ዋርካ ላይ በተናጠል ሃሳብ የሰጥሁህ ቦታ ለመኖሩ ብዙም ስለማላስታውስ በአዲስ ወዳጅነት ነው ይህን የምጽፍልህ። ወደምላሸ ከማለፌ በፊት ግን በጽሁፍህ ውስጥ የታዘብሁት አንድ ነገር ቢኖር የምትጠቀማቸው ምሳሌዎች እውነት እውነት የመሸተትና የማሳመን ሃያል በኔ ውስጥ አላቸው። ሰዎች ከራሳቸው ልምድ ተነስተው የሚሰጡትን ምሳሌ እወዳለሁ። ስለቫቲካኑ የጻፍኸውንም አንብቤ ረክቸበታለሁ…። ከላይ በተነሳው “የትግሬ -ወያኔዎች” ዙሪያ መልኩን እየቀያየረ ብዙ ብዙ የጻፍንበት ቢሆንም በአንተ አገላለጽ ላይ እየወደድሁ ያልተቀበልሁትን ግን ልነግርህ ዝግጁ ነኝ።

በትክክልም የዩኒቨሪስቲው “ሃጎስ” መገንጠልን ስታነሳበት ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ በመጨርሻም ጎጃሜ አገባ እንበል። ይህ ግን ታላቁን የትግሬ ወያኔዎች አገረ -ኢትዮጵያን ከምድረ -ገጽ የማጥፋት ገጽታ ይፍቀዋል ብሎ ማሰብ እጅግ የዋህነት ነው። ሌላ ምንም ሳይሆን ለዚህ ትልቁ ተምሳሌት በመለስ የፖለቲካ ጡቻ በዝረራ የወደቁት እነገብሩ አስራት መስቀል አደባባይ ላይ ቆመው “ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል እስከ ወደብ -አልባ ማድረግ ለፈጸምነው በደል ይቅርታ አድርጉልን” በአሉ በሳምንቱ ያቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅት “አረና ትግራይ” የሚል ነው። ይህ የሚያሳየው የትግራይ ህዝብ አእምሮው የተገራና እኛንም ያስተናግደናል ብለው የሚያምኑ በዘሩ ከተደራጀንለት ብቻ ነው የሚል እምነታቸውን ነው።

በተረፈ ስለኦሮሚያ መገንጠል ሲነሳም ሆነ ስለሌላ ተገንጣይ ነን ባይ ድርጅቶች ስንከራከር “ተጋብተን ተዋልደን” የሚለው ገለጻ ለኔ እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ነው። ሰዎች በሰውነታቸው ተፋቅረው ቢጋቡ ግለሰባዊ ምርጫቸው ወይም የፍቅር ፍላጻ ጠልፎ አስሯቸው ነው እንጅ የፖለቲካ አቋማቸው ነጸብራቅ ነው ማለት ትልቁን አገራዊ አጀንዳ ያስታል። እንዲያማ ቢሆን ፈረንጅ ያገባው ነጋሶ ጊዳዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል ? ለኔ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቁ ችግር ከዚህ ይጀምራል በአዲስ መስመር ተከተለኝ…

ሰሞኑን ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ተከታትለህ ይሆን ?... (http://news.bbc.co.uk/panorama/hi/front_page/newsid_9694000/9694094.stm )
ይህን ዘገባ ስመለከት አንድ ምስል አዕምሮየ ላይ ተሰክቶ ቀረ። አሜሪካውያን በደረሰባቸው የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ እየማቀቁ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ጫካ ውስጥ ድንኳን ዘርግተው እየኖሩ በሁለት ዛፎች መሃል አንጠልጥለው ሰንደቅ -አላማቸውን ሰቅለዋታል። ይህ ነው ለኔ ታላቅ ስብዕና ማለት በጊዚያዊ ችግር ብታዝን እና ብትከፋም በአገርህና በሰንደቅ -አላማህ ላይ ተስፋ አለመቁረጥ። የትግራይ ወያኔዎችን ጨምሮ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ስር -ሰድዶ የሚንገላጀጀው ዘረኝነት የተጣባው ትልቁ ሃቅ አገር ውስጥ ለሚፈጠር ችግር ሁሉ መፍትሄው ከአገር እና ከሰንደቅ አላማ መሸሽ ነው።

የትግራይ -ወያኔዎችን ግን እጅግ ልዩ የሚያደጋቸው ያኔስ አገር በበደለቻቸው ወቅት ዘራቸውን ይውደዱና አገራቸውን ይጸየፉ ይባል። እንዴት መላዋ አገረ -ኢትዮጵያን ተቆጣጥረው አሁንም በዘረኝነታቸው ይኖራሉ ? ትግራይ ውስጥ ሰው ሲሞት አልብሰው የሚያወጡት ሰንደቅ አላማኮ የህውሃት ነው። ለአገራዊ ክብረ -በዓላት ይዘውት የሚወጡትኮ የህውሃትን በደም የተዋጀ ጨርቅ ነው። እና የነሱን ተሟጦ ያለቀለት ኢትዮጵያዊነት በአንድ ግለሰብ ዘለላ -እንባ እና በትዳሩ አዋዝተህ የማሳመን ሃይልህ ምን ያለ ሃቅም ይኖረዋል ?!

እሽ አንተ ባልኸው ልሂድና እስኪ አሁን አጋጣሚው ከሚያገጣጥምህ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ ጋር ስለአገርህ ሃሳብ ተለዋወጥ ? እውነት ወያኔ እያደረሰ ስላለው በደል ስለአንዱም ያምኑልሃል ?

በተረፈ፣ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን አስመልክቶ ያቀረብኸውን ምሳሌም ሆነ መደምደሚያ ከልብ እቀበለዋለሁ። ኦሮምኛ ተናጋሪው ህብረተሰብ ትክክለኛ የፍትህ ጥያቄ ነው ያለው። ፖለቲከኞቹ ግን በስሙ የቆሸሸ ተግባር ለመፈጸም ነው እየተጣጣሩ ያሉት። ክሊንተን አንድ ነገር ተናግሮ ነበር የሰው ልጅ ታላቅነቱ ስልጣን የመያዝ ብቃቱ አይደለም የልቁንስ ስልጣኑን ለምን ይጠቀመዋል የሚለው ነው።” ኦሮምኛ ተናጋሪው በየወቅቱ ከሚያስመሰክርልኝ የዋህና ታላቅ -ስብዕናው አንዱ የሆነውን የቅርብ ጊዜ የህይወት ገጠመኘን ነግሬህ ልሰናበት።

ያው እንደምታውቀው ሰሞኑን የነጀኔራል ከማል ኦነግ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ፍቅር ወያኔን ሲያንጨረጭር ኢትዮጵያዊውን ደግሞ ያስደሰተ ጉዳይ ነው። ታዲያ ገና ዜናው በመጣ ሰሞን አንድ ስሙ -ይናገር የሚባል የዋርካ ሰው ፓልቶክ ላይ የተገንጣይ ነን ባይ ኦሮሞዎችን ገድል ነገረኝና እስኪ እኔም ልታዘብ ብዬ ጎራ አልሁ። ወንድሜ ! የማይነገር ሃጢያት የማይዘራ እሾህ የማይሸረብ የተንኮል እና የዘለፋ አይነት የለም። እስኪ እድሌን ልሞክር ብየ ከፓልቶክ በተሰናበትሁ በስንትና ስንት ዘመኔ ማይክ ጨበጥሁና በሚሉት ሁሉ ሃሳብ እንደማልስማማ በአግባቡ አስረድቸ ስውርድ እንኳንስ አንዲት የተቃውሞ ሃሳብ ሊሰነዘርብኝ ይቅርና “የሰለጠነው -አቢሲኒያዊ” የሚል ቅጽል ተሰጠኝ። በፍቅርም አስተናግደውኝ ተለየሁ። ከዛን እለት ወዲህም አልተመለስሁም። ይህ ማለት በአግባቡ ሃሳብ ብትለዋወጣቸው ኦሮሞዎች ፍጹም የፍቅር ተሸናፊዎች ናቸው። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ነው ብየ የማስበው አእምሯቸው እና ማንነታቸው በንጹሃን ደም አለመቆሸሹ ነው። የሃጢያት ድንግል የሆነ ሁሉ አዕምሮ ለፍቅር ቶሎ ይገዛል። እንደትግራይ -ወያኔ አይነት ጥይትን እንደክላሲካል ሲያዳምጡ እና ከሚፈሰው ወንዝ ጋር የተቀላቀለ የአገር -አስከባሪ -ወታደር -ደም ለቀመሰ ግን ፍቅር አይገባውም።

ጨርሰሁ
ጥልቁ -ብሄረ ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
እንድሪያስ

አለቃ

Joined: 19 Mar 2004
Posts: 2130
Location: *****

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 5:37 pm    Post subject: Reply with quote

ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:በአግባቡ ሃሳብ ብትለዋወጣቸው ኦሮሞዎች ፍጹም የፍቅር ተሸናፊዎች ናቸው። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ነው ብየ የማስበው አእምሯቸው እና ማንነታቸው በንጹሃን ደም አለመቆሸሹ ነው። የሃጢያት ድንግል የሆነ ሁሉ አዕምሮ ለፍቅር ቶሎ ይገዛል። እንደትግራይ -ወያኔ አይነት ጥይትን እንደክላሲካል ሲያዳምጡ እና ከሚፈሰው ወንዝ ጋር የተቀላቀለ የአገር -አስከባሪ -ወታደር -ደም ለቀመሰ ግን ፍቅር አይገባውም።

ጨርሰሁ
ጥልቁ -ብሄረ ኢትዮጵያ

ኦነግ የኃጢያት ድንግል ነውና አእምሮ ለፍቅር ቶል ይገዛል :: ምን ማለቱ እንደሆኑ በውል አልገባኝ ብሏል ወገኖቼ :: ድንግል በመሰረቱ ለልጃገረድና ለመሬት የምንጠቀመው ቃል ነው :: ኦነግ ሲፈጠር ጀምሮ ኃጢያት ሰርቶ የማያውቅ ንጹህና ቅዱስ ኃይል ነው ለማለት ይሆን ?
ኧረ ለመሆኑ በደኖ አሶሳና አርባጉጉ ያለቁት ዜጎች ንጹሃን አልነበሩም እንዴ ? ያቆሸሹትስ የማንን አእምሮና ማንነት ነበር ? የታሊባንን ? የአልቃይዳን ? የሂዝቡላህን ? የአልሻባብን ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 6:20 pm    Post subject: Reply with quote

ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:

በተረፈ ስለኦሮሚያ መገንጠል ሲነሳም ሆነ ስለሌላ ተገንጣይ ነን ባይ ድርጅቶች ስንከራከር “ተጋብተን ተዋልደን” የሚለው ገለጻ ለኔ እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ነው። ሰዎች በሰውነታቸው ተፋቅረው ቢጋቡ ግለሰባዊ ምርጫቸው ወይም የፍቅር ፍላጻ ጠልፎ አስሯቸው ነው እንጅ የፖለቲካ አቋማቸው ነጸብራቅ ነው ማለት ትልቁን አገራዊ አጀንዳ ያስታል። እንዲያማ ቢሆን ፈረንጅ ያገባው ነጋሶ ጊዳዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል ? ለኔ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቁ ችግር ከዚህ ይጀምራል በአዲስ መስመር ተከተለኝ…

ዝርፍጡ መሀይም ሰላም ብያለሁ Laughing

ያንተ ድንቁርና ደግሞ ለከት የለውም ... ሳህሊለነ ያስብላል ... አንድ ስቴፕ ፈንጠር ብለህ ማሰብ እንኳን የማትችል ለፍዳዳ ... በጋብቻ ከሚተሳሰሩት ጥንዶች በላይ ጋብቻው የሚያፈራቸው "ልጆች " እንዴት ነው አልታይ ያሉህ Question የማይገናኘውን የነጋሶ ታሪክ አንስተህ ስታበቃ የደንቆሮ መደምደሚያም አስቀምጠሀል :: ነጋሶ ነጭ ስላገባ ነጭ መሆን አለበት ? እንደ ጂጎሎ አንዲት አሮጊት ነጭ አግብተህ ነው እንዴ የካናዳ ሲትዝንሺፕ ያገኘሀው Laughing

... ከራስ በላይ የማያስብ የብልሹ ማህበረሰብ ውጤት ማለት እንዲህ ነው ! ጋብቻ ልጆችን ያፈራል ...ልጆች ደግሞ እንደገና ተጋብተው የልጅ ልጆችን ያፈራሉ ... ዘብሄረ ኢትዮጵያ ማለት እነዚህ ናቸው :: ... ሁሉንም ዘር በደማቸው የከተቡ ወይም ሁሉም ዘር ደማቸውን የከተበው :: የማይመጥንህን ስም ሰጥተህ ደግሞ ዘብሄረ ኢትዮጵያ ይባልልኛል Rolling Eyes ዳሩ ምን ያደርጋል ... ቁራ ጩኸት እንጂ ማመዛዘንን የት ያውቅና Laughing ... ትላንትም ዛሬም ነገም ኢትዮጵያን አስተሳስሮ ያቆያት : ያስተሳሰራትና የሚያስተሳስራት ህዝቡ በጋብቻ በአበልጅ ወዘተ እንደ ወተትና ውኃ ስለተዋኅደ እንጂ የአጼዎች : ፕሬዝዳንቶችና //ሮች ጉልበት እንዳይመስልህ Rolling Eyes

ሓየት ... "ዲቃላው " Laughing
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 6:36 pm    Post subject: Reply with quote

እንዲህ ያለውን ጥያቄ የሚመልሱልህ ወያኔ ወገኖች አታገኝምና እኔው እመልስልሃለሁ።

ቅቅቅ እንድሪያስ አሁን በዚች ጽሁፍ ብቻ ለሚያውቅህ እውነትም ስለኦነግ ሃጢያት ልትናገር የመጣህ እንጅ ትላንት ስታብጠለጥላቸው የነበሩትን ወያኔዎች ልትሟገትላቸው እንዳልሆነ አያቅም። Wink ኦነግ ውስጥ ለፖለቲካ ጥቅማቸው የሚራወጡ እንኳንስ ትላንት ዛሬም በፓልቶክ ላይ የሚሰነዝሩትን የምኞት ሞትና ጭፍጨፋ እየሰማሁና እያነበብሁት እንደሆነ እኔም በጽሁፌ ከላይ ገልጨዋለሁ። ከላይ የጠቃቀስሃቸው ግድያዎች ግን የተፈጸሙት በራሱ በወያኔ ታጣቂዎች ለመሆኑ ብዙ ማስረጃ ያለ ሲሆን ሚስታቸውን ልጆቻቸውና አብሮ አደጎቻቸውን ከነነፍሳቸው ገደል ውስጥ ሲጣሉ የተመለከቱት የበደኖ አባት “ይህን የሚሰራው መለስ ነው” ብለው ያጋለጡበትንና ኤዲት ያልተደረገውን ከአገርህ ልጅ ታማኝ (ጎንደሬ (ጋይንቴ ) ነኝ ብለኸን የለ ) (የእናት ሆድ ዥንጉርጉር አንዱ ታማኝ አንዱ ከሃዲ ) እሱ የለቀቀውን ቪዲዮ ፈልገህ ተመልከት።

በተጨማሪም (ምናልባት መለስን የማምለክ ቅዠትህ ካለቀቀህና “ይህማ የግለሰብ አስተያየት ነው” ) የምትል ከሆነ ያኔ መዐህድን / አስራት እንዲያቋቁሙ የገፋቸውን የታሪክ ትውስታ ከአዕምሮየ ጨልፌ ላካፍልህ። ፕር አስራት በአንድ የምክክር ስብሰባ ላይ “እረ ሰዎች በኢትዮጵያዊነታቸው እየተጨፈጨፉ ነው መንግስትህ ይታደጋቸው” ብለው ሲጠይቁት መለስ ምን እንዳለ ታቃለህ “ምን ያድርጉ ለዘመናት ተሸክመውት የኖሩት ግፍ ገንፍሎባቸው ስለሆነ ይህን የሚያደርጉ ምንም ማድረግ አንችልም” አላቸው።

እናም ኦነግ እንደመንግስት ቆሞ መንግስታዊ ጥፋት እስካልፈጸመ ድረስ አዕምሮው ድንግል ነው። ወያኔዎች ጫካ እያላችሁ ላፈረሳችሁት ድልድይ እና ለዘረፋችሁት ባንክና ዬእህል ክምችት ማንም ወቅሷችሁ አያውቅም ለምን ? ትግል ውስጥ ነበራችሁና። መንግስት ከሆናችሁ በኋላ ግን እንደመንግስት ሳይሆን ያው እንደወንበዴነታችሁ አላችሁና በታሪክም ይቅር አትባሉም። እና አንድ በትግል ላይ ብቻ የኖረውን ኦነግን መውቀስ እንደማይገባ ከላይ ያስቀመጥሁትን የክሊንተን ጥቅስ ደገምሁልህ
የሰው ልጅ ታላቅነቱ ስልጣን የመያዝ ብቃቱ አይደለም የልቁንስ ስልጣኑን ለምን ይጠቀመዋል የሚለው ነው።” "

ድንግል ሴት ድንግል መሬት እንደሚባለው ሁሉ ኦነግም ሆነ ኦሮምኛ ተናጋሪው ለስልጣን ድንግል ነው። ይህም ማለት አገሪቱን ሰው በመሆናቸው እንጅ በኦሮሞነታቸው ይግዙ የሚል ቅንጣት ታህል እምነት አለኝ ማለት አይደለም። ካስፈለገ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

እንድሪያስ ይህን ስታነብ ምን ይሰማህ ይሆን ?...
አየ ዘመን አንተ ለወያኔ ስትከራከር እኔ ደግሞ ...

እንድሪያስ እንደጻፈ(ች)ው:
ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:

በአግባቡ ሃሳብ ብትለዋወጣቸው ኦሮሞዎች ፍጹም የፍቅር ተሸናፊዎች ናቸው። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ነው ብየ የማስበው አእምሯቸው እና ማንነታቸው በንጹሃን ደም አለመቆሸሹ ነው። የሃጢያት ድንግል የሆነ ሁሉ አዕምሮ ለፍቅር ቶሎ ይገዛል። እንደትግራይ -ወያኔ አይነት ጥይትን እንደክላሲካል ሲያዳምጡ እና ከሚፈሰው ወንዝ ጋር የተቀላቀለ የአገር -አስከባሪ -ወታደር -ደም ለቀመሰ ግን ፍቅር አይገባውም።

ጨርሰሁ
ጥልቁ -ብሄረ ኢትዮጵያ

ኦነግ የኃጢያት ድንግል ነውና አእምሮ ለፍቅር ቶል ይገዛል :: ምን ማለቱ እንደሆኑ በውል አልገባኝ ብሏል ወገኖቼ :: ድንግል በመሰረቱ ለልጃገረድና ለመሬት የምንጠቀመው ቃል ነው :: ኦነግ ሲፈጠር ጀምሮ ኃጢያት ሰርቶ የማያውቅ ንጹህና ቅዱስ ኃይል ነው ለማለት ይሆን ?
ኧረ ለመሆኑ በደኖ አሶሳና አርባጉጉ ያለቁት ዜጎች ንጹሃን አልነበሩም እንዴ ? ያቆሸሹትስ የማንን አእምሮና ማንነት ነበር ? የታሊባንን ? የአልቃይዳን ? የሂዝቡላህን ? የአልሻባብን ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ዱራሰንበት

ዋና አለቃ

Joined: 01 Apr 2004
Posts: 4079
Location: Dedessa Death Camp, Tach Birr Sheleko

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 9:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጥልቁ

ድንገት ገብቼ ከዚህ በታች የጠቀስሁትን በማዬቴ ነው የሚከተለውን የምለው :: በጣም የሚበረታታና አስፈላጊ አስተያዬት ከመሆኑም በላይ ወቅታዊም ነው ::
ያለመታደል ሆኖ ተመሳሳይ ሀሳብና አስተያዬት በዚህ በዋርካ ሲስተናገድ በጊዜና በተከፈተው ዓምድ ልዩነት ምክንያት አላስፈላጊ ንትርክ ጊዜ ሲባክን አያለሁ :: ባለፈው የሚያስቅና የሚያስቀልድ ፍልስፍና ብለህ የተቸህበትን አስተያዬት ነው በጥቅስ ውስጥ ያስቀመጥሁት አስተያዬት የሚያንፀባርቀው :: በአግባብና በቃላት በሀረግም ሆነ በአረፍተ -ነገር ቢለያይም በትርጉም ግን አንድ ነው :: ለምን ያን አደረግህ ብዬ አልተችም ::
መልሱን ባለመታደላችን ነው ብዬ እዘጋዋለሁ :: ይኸው አላስፈላጊ እሰጥ አገባ ---ተመሳሳይ አገራዊ ግብና ዓላማ በያዙ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥም ጊዜን ገንዘብንና አልፎ አልፎም መስዋዕትነትን እያስከፈከ ይኸው ኢትዮጵያውያን በዘረኛ ባንዳዎች ቀንበር ሥር ህይወትን እንድንገፋ ምክንያት ሆኗል :: ይህንን በዚህ ላብቃና የተቀስሁትን ሀሳብህን በኢትዮጵያውያን ላይ እንዲሰራ በማንፀባረቁ በኩል በርትተህ ብትቀጥል ምኞቴ ነው ::

ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:

ሰሞኑን ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ተከታትለህ ይሆን ?... (http://news.bbc.co.uk/panorama/hi/front_page/newsid_9694000/9694094.stm )
ይህን ዘገባ ስመለከት አንድ ምስል አዕምሮየ ላይ ተሰክቶ ቀረ። አሜሪካውያን በደረሰባቸው የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ እየማቀቁ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ጫካ ውስጥ ድንኳን ዘርግተው እየኖሩ በሁለት ዛፎች መሃል አንጠልጥለው ሰንደቅ -አላማቸውን ሰቅለዋታል። ይህ ነው ለኔ ታላቅ ስብዕና ማለት በጊዚያዊ ችግር ብታዝን እና ብትከፋም በአገርህና በሰንደቅ -አላማህ ላይ ተስፋ አለመቁረጥ። የትግራይ ወያኔዎችን ጨምሮ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ስር -ሰድዶ የሚንገላጀጀው ዘረኝነት የተጣባው ትልቁ ሃቅ አገር ውስጥ ለሚፈጠር ችግር ሁሉ መፍትሄው ከአገር እና ከሰንደቅ አላማ መሸሽ ነው።

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 12:28 am    Post subject: Reply with quote

ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም እንመሰግናለን፡
በቅድሚያ ከአሁን በፊት ዋርካ ላይ በተናጠል ሃሳብ የሰጥሁህ ቦታ ለመኖሩ ብዙም ስለማላስታውስ በአዲስ ወዳጅነት ነው ይህን የምጽፍልህ። ወደምላሸ ከማለፌ በፊት ግን በጽሁፍህ ውስጥ የታዘብሁት አንድ ነገር ቢኖር የምትጠቀማቸው ምሳሌዎች እውነት እውነት የመሸተትና የማሳመን ሃያል በኔ ውስጥ አላቸው። ሰዎች ከራሳቸው ልምድ ተነስተው የሚሰጡትን ምሳሌ እወዳለሁ። ስለቫቲካኑ የጻፍኸውንም አንብቤ ረክቸበታለሁ…። ከላይ በተነሳው “የትግሬ -ወያኔዎች” ዙሪያ መልኩን እየቀያየረ ብዙ ብዙ የጻፍንበት ቢሆንም በአንተ አገላለጽ ላይ እየወደድሁ ያልተቀበልሁትን ግን ልነግርህ ዝግጁ ነኝ።

በትክክልም የዩኒቨሪስቲው “ሃጎስ” መገንጠልን ስታነሳበት ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ በመጨርሻም ጎጃሜ አገባ እንበል። ይህ ግን ታላቁን የትግሬ ወያኔዎች አገረ -ኢትዮጵያን ከምድረ -ገጽ የማጥፋት ገጽታ ይፍቀዋል ብሎ ማሰብ እጅግ የዋህነት ነው። ሌላ ምንም ሳይሆን ለዚህ ትልቁ ተምሳሌት በመለስ የፖለቲካ ጡቻ በዝረራ የወደቁት እነገብሩ አስራት መስቀል አደባባይ ላይ ቆመው “ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል እስከ ወደብ -አልባ ማድረግ ለፈጸምነው በደል ይቅርታ አድርጉልን” በአሉ በሳምንቱ ያቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅት “አረና ትግራይ” የሚል ነው። ይህ የሚያሳየው የትግራይ ህዝብ አእምሮው የተገራና እኛንም ያስተናግደናል ብለው የሚያምኑ በዘሩ ከተደራጀንለት ብቻ ነው የሚል እምነታቸውን ነው።

በተረፈ ስለኦሮሚያ መገንጠል ሲነሳም ሆነ ስለሌላ ተገንጣይ ነን ባይ ድርጅቶች ስንከራከር “ተጋብተን ተዋልደን” የሚለው ገለጻ ለኔ እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ነው። ሰዎች በሰውነታቸው ተፋቅረው ቢጋቡ ግለሰባዊ ምርጫቸው ወይም የፍቅር ፍላጻ ጠልፎ አስሯቸው ነው እንጅ የፖለቲካ አቋማቸው ነጸብራቅ ነው ማለት ትልቁን አገራዊ አጀንዳ ያስታል። እንዲያማ ቢሆን ፈረንጅ ያገባው ነጋሶ ጊዳዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ይሰራል ? ለኔ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቁ ችግር ከዚህ ይጀምራል በአዲስ መስመር ተከተለኝ…

ሰሞኑን ቢቢሲ ያቀረበውን ዘገባ ተከታትለህ ይሆን ?... (http://news.bbc.co.uk/panorama/hi/front_page/newsid_9694000/9694094.stm )
ይህን ዘገባ ስመለከት አንድ ምስል አዕምሮየ ላይ ተሰክቶ ቀረ። አሜሪካውያን በደረሰባቸው የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ እየማቀቁ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ጫካ ውስጥ ድንኳን ዘርግተው እየኖሩ በሁለት ዛፎች መሃል አንጠልጥለው ሰንደቅ -አላማቸውን ሰቅለዋታል። ይህ ነው ለኔ ታላቅ ስብዕና ማለት በጊዚያዊ ችግር ብታዝን እና ብትከፋም በአገርህና በሰንደቅ -አላማህ ላይ ተስፋ አለመቁረጥ። የትግራይ ወያኔዎችን ጨምሮ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ስር -ሰድዶ የሚንገላጀጀው ዘረኝነት የተጣባው ትልቁ ሃቅ አገር ውስጥ ለሚፈጠር ችግር ሁሉ መፍትሄው ከአገር እና ከሰንደቅ አላማ መሸሽ ነው።

የትግራይ -ወያኔዎችን ግን እጅግ ልዩ የሚያደጋቸው ያኔስ አገር በበደለቻቸው ወቅት ዘራቸውን ይውደዱና አገራቸውን ይጸየፉ ይባል። እንዴት መላዋ አገረ -ኢትዮጵያን ተቆጣጥረው አሁንም በዘረኝነታቸው ይኖራሉ ? ትግራይ ውስጥ ሰው ሲሞት አልብሰው የሚያወጡት ሰንደቅ አላማኮ የህውሃት ነው። ለአገራዊ ክብረ -በዓላት ይዘውት የሚወጡትኮ የህውሃትን በደም የተዋጀ ጨርቅ ነው። እና የነሱን ተሟጦ ያለቀለት ኢትዮጵያዊነት በአንድ ግለሰብ ዘለላ -እንባ እና በትዳሩ አዋዝተህ የማሳመን ሃይልህ ምን ያለ ሃቅም ይኖረዋል ?!

እሽ አንተ ባልኸው ልሂድና እስኪ አሁን አጋጣሚው ከሚያገጣጥምህ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ ጋር ስለአገርህ ሃሳብ ተለዋወጥ ? እውነት ወያኔ እያደረሰ ስላለው በደል ስለአንዱም ያምኑልሃል ?

በተረፈ፣ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን አስመልክቶ ያቀረብኸውን ምሳሌም ሆነ መደምደሚያ ከልብ እቀበለዋለሁ። ኦሮምኛ ተናጋሪው ህብረተሰብ ትክክለኛ የፍትህ ጥያቄ ነው ያለው። ፖለቲከኞቹ ግን በስሙ የቆሸሸ ተግባር ለመፈጸም ነው እየተጣጣሩ ያሉት። ክሊንተን አንድ ነገር ተናግሮ ነበር የሰው ልጅ ታላቅነቱ ስልጣን የመያዝ ብቃቱ አይደለም የልቁንስ ስልጣኑን ለምን ይጠቀመዋል የሚለው ነው።” ኦሮምኛ ተናጋሪው በየወቅቱ ከሚያስመሰክርልኝ የዋህና ታላቅ -ስብዕናው አንዱ የሆነውን የቅርብ ጊዜ የህይወት ገጠመኘን ነግሬህ ልሰናበት።

ያው እንደምታውቀው ሰሞኑን የነጀኔራል ከማል ኦነግ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ፍቅር ወያኔን ሲያንጨረጭር ኢትዮጵያዊውን ደግሞ ያስደሰተ ጉዳይ ነው። ታዲያ ገና ዜናው በመጣ ሰሞን አንድ ስሙ -ይናገር የሚባል የዋርካ ሰው ፓልቶክ ላይ የተገንጣይ ነን ባይ ኦሮሞዎችን ገድል ነገረኝና እስኪ እኔም ልታዘብ ብዬ ጎራ አልሁ። ወንድሜ ! የማይነገር ሃጢያት የማይዘራ እሾህ የማይሸረብ የተንኮል እና የዘለፋ አይነት የለም። እስኪ እድሌን ልሞክር ብየ ከፓልቶክ በተሰናበትሁ በስንትና ስንት ዘመኔ ማይክ ጨበጥሁና በሚሉት ሁሉ ሃሳብ እንደማልስማማ በአግባቡ አስረድቸ ስውርድ እንኳንስ አንዲት የተቃውሞ ሃሳብ ሊሰነዘርብኝ ይቅርና “የሰለጠነው -አቢሲኒያዊ” የሚል ቅጽል ተሰጠኝ። በፍቅርም አስተናግደውኝ ተለየሁ። ከዛን እለት ወዲህም አልተመለስሁም። ይህ ማለት በአግባቡ ሃሳብ ብትለዋወጣቸው ኦሮሞዎች ፍጹም የፍቅር ተሸናፊዎች ናቸው። ለዚህም ትልቁ ምክንያት ነው ብየ የማስበው አእምሯቸው እና ማንነታቸው በንጹሃን ደም አለመቆሸሹ ነው። የሃጢያት ድንግል የሆነ ሁሉ አዕምሮ ለፍቅር ቶሎ ይገዛል። እንደትግራይ -ወያኔ አይነት ጥይትን እንደክላሲካል ሲያዳምጡ እና ከሚፈሰው ወንዝ ጋር የተቀላቀለ የአገር -አስከባሪ -ወታደር -ደም ለቀመሰ ግን ፍቅር አይገባውም።

ጨርሰሁ
ጥልቁ -ብሄረ ኢትዮጵያ

ሰላም ጥልቁ -ብሔረ -ኢትዮጵያ :

አስተያየትህ እንደስምህ ጥልቅ ነው :: ትንሽ እንዳስብ አድርጎኛል :: የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነትና የኦነግን ጸረ -ኢትዮጵያዊነት በአንድ ዓይነት ዓይን ማየቴ ምናልባት ስህተት ሊሆን ይችላል :: ደም የቀመሰና ደም ያልቀመሰ አንድ አይደለም : በእውነቱ ትክክል ነህ !! የኦነጎቹን ጉዳይ በሚገባ ታዝበሃል :: እኔም በቅርብ አመታት በደንብ እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር አብዛኛውን ኦነጋዊ (አባል ሆነም ደጋፊ ) መራራ ስሜት እንዲይዝ ያደረገው ነገር "ያልሠለጠነው አቢሲንያዊ " እንደልቡ የሚለቀው ያልተገራና ከወንድማዊነት ያልመነጨ አነጋገር ነው ብዬ አምኛለሁ ::

የትግራውያኑ ጉዳይ እንግዲህ መቼም ጥይት ቦምብና ጦርነት የሰዉን መሬቱንም ልቡንም ቢያደርቀውም : መቼም የማይሠረይ ነገር የለምና ስለጥቂቶቹ ስንል "ተጋብተን ተዋልደን ተዋድደን " በሚለው ዘፈን ላይ ሙጭጭ እንበል የሚል አቋም ነው ያለኝ :: Stick to your story! ነው ነገሩ :: "ተጋብተን ተዋልደን ተፋቅረን ...." ምክንያቱም : ብሔረ ኢትዮጵያ እንድትኖር ይህ ፍቅርን የማይፈራ የትውልድ ክፍል ሊበረታታ ይገባዋል - በቁጥር አንድም ይሁን ሁለት :: ሌላውን የጥፋት ውኃ ጠራርጎ የሚወስደው ቀን ሲመጣ በመርከብ ሆኖ የሚተርፈው ሁል ጊዜም በጣት የሚቆጠር ቅን ሰው ብቻ ነው :: ለአስተሳሰብም እንደዚያው ይመስለኛል ::

በነገርህ ላይ የዩኒቨርስቲው "ሃጎስ " የኢሀዴግን ወንጀል አስመልክቶ ብነጋገረው አያምንልኝም :: እሱ ላይ ልክ ብለሃል :: የሚያውቀው ነገር ቢኖር አገሪቱ በልማትና በዲሞክራሲ ጎዳና ላይ እየተራመደች እንደሆነ ነው :: አነጋገሩንና አስተሳሰቡን ሳይ ከጀርባ ያለው አሰምፕሽን እንደዛ ይመስለኛል :: ሁሉ ነገር ኖርማልና ሴፍ ይመስለዋል :: ከሌላው ህብረተሰብ መነጠሉን ግን አይፈልገውም :: ከደረቅ ወያኔዎች በጣም ይለያል :: ይህ ሌላውን ለማዳመጥ የሚያስችል ክህሎት እንዲያዳብር ትልቅ ቅድመ -ሁኔታ ነው እላለሁ - አስ ሎንግ አዝ የገራዶ ቢጤ ብአዴኖች ደግሞ መጥተው "የኢትዮጵያ ካንሰር " ብለው ዲፌንሲቭ ሞድ ውስጥ ካልከተቱት በቀር ::

አማራው ጋር ትልቅ ችግር አለ :: በጣም ዲፌንሲቭ ሞድ ውስጥ ለራሱ ገብቶ ሌላውንም እያስገባው ይገኛል :: ከዚህ በፊት በአደዋ በማይጨው ከሌሎች ጋር ሆኖ ካሳየው ጀግንነት የበለጠ ጀግንነት አሁን ማሳየት የሚጠበቅበት ይመስለኛል - ኢትዮጵያ በኢትዮጵያነቷ እንድትቀጥል ከፈለገ :: ቁርጠኝነቱ ካለ ደግሞ ቀላል ነው :: የሚጠበቅበት እኮ ትምክህተኛው እንዲህ አደረገን ብሎ የሚዝተውንና በስማ በለው የሚነጫነጨውን በጠላት እንደከብት የሚነዳ ጸረ ኢትዮጵያዊ ኃይል ሁሉ "I understand" ማለት ብቻ ነው :: "ቁስልህ ይሰማኛል :: አግዘኝና አብረን እናድነው :: ያለፈው ዘመን ችግር ሁሉ አዎን ተፈጥሯል - ልክ ነው :: ክፉ ክፉውን ከኋላችን እንተወውና መልካም መልካም የሆነውን ነገር ብቻ ለይተን እናውጣ - ከዚያም አብረን እናስኪደው " ማለት ብቻ ነው !! እያንዳንዱ አማራ ይህን አይነት አነጋገር መናገር ቢለምድ የብዙዎችን ጽንፈኞች አስተሳሰብ መቀልበስ የሚችል ይመስለኛል ::

እርግጥ ነው : ለምንም ዓይነት ሰላማዊ ፖለቲካ የማይገዙ ብዙ የሰይጣን ፈረሶች በማንኛውም ቡድን ውስጥ አሉ :: ቢሆንም ለነርሱ ተብሎ ቀናውና መልካሙ አማራጭ ወደጎን አይተውም ::

አሁን ጥያቄው ለአማራው ይህን ማን ያስተምረው ?!! የሚል ነው :: እርሱ ከሌላው ከተባበረ ወያኔያዊ ትግራዋይነት ኃይል አይኖረውም የሚል እምነት አለኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 4:02 am    Post subject: Reply with quote

እስከዛሬ ከጻፍካቸው ሁሉ ሊገባኝ ያልቻለ ፖስት ቢኖር ይሄኛው ነው ::

ከሁሉም ቢሆን ጽንፈኛ አይጠፋም ያልከው አባባል ትክክል ሆኖ መጠን እና ኢንቴንሲቲው ግን ይለያያል :: የሆነ ሆኖ እንደዚህ ያለ ጉዳይ ( ጎሳን መሰረት ያደረገ ክርክር ) ሀሳብ መወያየት አይመቸኝም ::

ፋይዳውም አይታየኝም ፎር ዛት ማተር ...

ናፖሊዮን ዳኘ ::

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:

ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 12:02 am    Post subject: Reply with quote

ይህ አምድ ላይ የጀመርነውን ውይይት ልቤ እየወደደው ጊዜ ቢያጥረኝ ዘገየሁበት… ለነገሩ ጠቅለል እያለ ያለ ስለሆነ ከላይ የተሰነዘሩትን ሃሳቦች አጣቅሸ የራሴን ሃሳብ እሰጣለሁ።

ዱራሰንብት፦ ለሰጠኸኝ አስተያየት አመሰግናለሁ። አንድ ሁለት ግን ማለት እወዳለሁ። (ከታች ያለው አንቀጽ ለአንተ ምላሽ ብየ ላቅርበው እንጅ የሚያነበኝ ሁሉ እንዲረዳኝ በማሰብ ነው )

ያው እንደምታውቀኝ እዚህ ዋርካ ውስጥ በማልደግፈው ሃሳብ ዙሪያ ያልነካካሁት ሰው የለም። እኔንም ያልነካካኝ አለ ብየ አላምንም። እንዴውም ያኔ በምርጫ 97 ሰሞን “በቅንጅት መሪዎች አፈርሁባቸው” ብየ የጻፍሁት ወገናዊ የቁጭት ሃተታ የአዲስ ዘመን ማድመቂያ መሆኑን የጥንቱ የዋርካ ወዳጀ ሲነግረኝ ምን ያህል እንደተነካሁ እኔ ነኝ የማቀው። ግን የተፈጥሮ ጉዳይ ነው። በኔ ዘነድ ጠላት እንዳይሰማው የሚል ሃሜት የለም። እናም ባለፈው በተጎሻሸምነው ዙሪያ ፍጹም ከክፋት የራቀ ሃሳቤ መሆኑን ተረዳኝ። አሁን አሁን ግራ እየገባኝ የመጣው እኛ በኢትዮጵያዊነት ምንም አጸጽ በሌለብን የዋርካ ተሳታፊያን ዙሪያ ያለው ሴንሲቲቪቲ እያስጨነቀኝ ነው።

በስም መጠቃቀስ የምንችል በርከት ያልን፦ በኢትዮጵያዊ ማንነታችን የምንኮራ የዘረኝነት ድር በአእምሯችን ላይ ያላደራ የዋርካ ተሳታፊያን አለን። ማለት ግን በሃሳብ አንጋጭ ማለት አይደለም። እንዴውም እኛን ከወያኔዎች ልዩ የሚያደርገን የሰውነታችን መገለጫ መነቃቀፍ መቻላችን ነው። በራሱ የማይተማመን ግብዝ ስርዓት ብቻ ነው ችግሩ ሳይነገረው እራሱ በሚፈጥረው አለም እራሱን እንደወያኔ እያንቆለጳጰሰ የሚኖረው። እናም ለከት ባለው ሁኔታ እኛም እርስ ዕርስ በሃሳብ መጋጨታችን እራሳችንንም በሃሳብ ለማጎልበት ይረዳናል። እኔ ለምሳሌ ለአንተ ምላሽ ከመጻፍ ይልቅ የታቀፉት የንጽሁሃን ደም ለሚያስለፈልፋቸው እነ ሓየት መጻፍ በጣም ይቀለኛል። ግን ደግሞ በተቃራኒው እንደ ሓየት ያለ ድንብርብር ወያኔ እኔ የጻፍሁትን ሲደግፍ ካየህ ወይ እኔ የጻፍሁት ላይ ወያኔን የሚያስደስት እጸጽ አለው አለያም (በሸክስፒር አነጋገር ) የነሓየት በደም የተጨማለቀ እጅ “በውቂያኖስ ታጥቦ ጸድቶ” የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ቀርቦታል ማለት ነው። አለበለዚያ ወያኔ የሚደግፈው ጽሁፍ መጻፍ አልችልም። እናም በበኩሌ በሃሳብ እርስ እርስ ብንተራረም ደስ ይላል። ይሄው ሰሞኑን በየካቲት ሰመዓታት ዙሪያ ተድላ እና ናፖሊዮን መጠነኛ የሃሳብ ልዩነት አሳይተዋል። እኔ በጣም ወድጀዋለሁ። የሁለቱን ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት ግን የሚያነቃንቅ አይደለም።

እናመሰግንሃለ፡
በሃሳብ አንድ ስለሆን ብዙም የምለው ያለ አይመስለኝም። ቀደም ብየ ስጽፍ አንድ የብዕሬ ጉንጭ ላይ እያለ የዘነጋሁትን ሃሳብ አንተው ጽፈኸው ሳይ በጣም ደነቀኝ።

Quote:
በነገርህ ላይ የዩኒቨርስቲው "ሃጎስ " የኢሀዴግን ወንጀል አስመልክቶ ብነጋገረው አያምንልኝም :: እሱ ላይ ልክ ብለሃል :: የሚያውቀው ነገር ቢኖር አገሪቱ በልማትና በዲሞክራሲ ጎዳና ላይ እየተራመደች እንደሆነ ነው :: አነጋገሩንና አስተሳሰቡን ሳይ ከጀርባ ያለው አሰምፕሽን እንደዛ ይመስለኛል :: ሁሉ ነገር ኖርማልና ሴፍ ይመስለዋል :: ከሌላው ህብረተሰብ መነጠሉን ግን አይፈልገውም :: ከደረቅ ወያኔዎች በጣም ይለያል ::

እዚህ ላይ ነው ቁምነገሩ። “ሃጎስ” እንባው የሚያቀርር ዘረኝነቱን ዘንግቶት ኢትዮጵያዊነቱ አሳዝኖት አይደለም። እኔ በአገሬ “የቀጣፊ እንባ እምቧይ እምቧይ ያክላል” የሚባል ተረት አለ። አንድ ሌባ ሰርቆ ሲያዝ እንባው ዝርግፍግፍ የሚል ከሁለት በአንዱ ምክንያት ነው። ወይም ተጸጽቶ አለበለዚያም ስለተያዘ ተቆጭቶና ተናድዶ። “ሃጎስ” እና ዘመዶቹን የሚያስነባቸው የአዞነት ሴል ስላለባቸው ብቻ ነው። እየበሉ የማልቀስ እምባ። እንጅማ ከዘረኝነት ተላቅቆ በንጽሁ ልብ ሲቪላይዝድ ሆኖ ለመኖር ሌላ የትም ሳይሄዱ አጠገባቸው ያለውን ሌላውን ህብረተሰብ አያዩም ?!

ለዚህ ነው መክበድና መዋለድ በኔ የፖለቲካ አመለካከት ውስጥ ቦታ የለውም የምልበት ምክንያት። የፖለቲካ እምነት በደም የሚወረስና የሚያበለጽጉት አይደለም። እንዴውም እንደኛ ባሉ ድሃ አገራት ፖለቲካ እጅግ ትርፍ ነገር ነው። ፖለቲካው ሊጠቅመን የሚችል በህግ ለመተዳደር እና አገርን በዲፕሎማሲ ለማስከበር ብቻ ነው። ትልቁ የኛ ርሃብ በማህበረሰብ ደረጃ ተከባብሮ እንደትግሬ -ወያኔዎች ሳይሆኑ ከባንዳነት የጸዳ አዕምሮ ይዞ የመኖር ብቻ ነው። አዕምሮውን እኩይ በሆነ ፖለቲካ ያነጸ ግን የጋብቻ መነጸሩ የሚያሳየው የራሱን ቤተሰብ ብቻ ነው። ለምሳሌ የቁርጥ ቀን ሲመጣ “ሃጎስ” ጣራው ላይ የሰቀላትን ክላሽ ይዞ እሱ እራሱ ጣራ ላይ ይወጣና አነጣጥሮ የሚተኩስ ወደጎጃም በረንዳ ነው እንጅ በሚስቴ ጎጃሜ ነኝ ብሎ…። ለዚህ ነው ከላይ ያልሁትን የአሜሪካኖችን የባንዲራ ፍቅር ያስቀመጥሁት። የፖለቲካ አመለካከታችን የታነጸው በኢትዮጵያዊነት ከሆነ ለዘራችን ግድ አይኖረንም። እኔ ለምሳሌ ልክ / ብርሃኑ ባለፈው እንዳለው ያደግሁበት አካባቢየን ዘፈን ሥሰማ ሁለመናየ ይደንስ ይሆናል። ለደቂቃ ግን ያካባቢየን ሰው ከሰውነቱ አልቄ እና ከሌላው አቅርቤ በዘር መነጸር አስቤው አላቅም። ምክንያቱም አካባቢ ይህንንም አያቅምና። ይህን ጥሉ ይህን ውደዱ የሚባልበት አካባቢ ስላልሆነ ሁሉም በሰውነቱ ብቻ ነው ተዋውቆ አብሮ የሚኖረው።

አሁን ደግሞ ወደ ናፖሊዮን፦
ይች የጽንፍ ነገር እስኪ በሚገባኝ ቋንቋ ትንሽ ልበልባት። ለመንደርደሪያ ግን የበርናርድ ሾውን ጥቅስ ላስቀምጥ፦
“ማለዳ ከእንቅልፌ የምነሳው፣ መተኛቱ በቅቶኝ ሳይሆን ይችን ያህል የምተኛባትን አልጋየን በችግር እንዳልሸጣት ፈርቸ ነው።”

ጽንፍ
የቋንቋውን የቁም ትርጉም ተወት ላድርገውና በኔ እምነት አንድ ነገር እንደሚገባኝ ከሆነ ሁላችንም ለምናምንበት ነገር ጽንፈኞች ነን። አገራዊ አስተዳደርን ስንመለከት የራሳችን የሆነ እምነት ተከታይ የራሳችን አይነት ፍላጎት አራማጅ የራሳችን አይነት የፖለቲካ ጽንሰ -ሃሳብ ያለው አገራችንን ቢመራት የየሁላችንም ፍላጎት ነው። ቁምነገሩ ያለው ግን ያለው እውነታ ያንን ይፈቅዳል ወይ የሚለው ነው። እዚህ ላይ እንዴውም የሰሞኑን የእስልምና እምነት ተከታዮች ጭቅጭቅን በፓልቶክ ሳዳምጥ አንዲት ሴት የሰነዘረችውና በአቡ -ሃይደር በሚባል ሰው የተደጋግፈውን ሃሳብ ሰምቸ ፈዝዠ የቀረሁበትን ላስቀምጥ። የውይይቱ አቅጣጫ ምንድነው ያላችሁ እንደሆነ “እንዴውም ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት እስላማዊ አስተዳደር ነው ያለን የሰው ሃይልም ያንን ያግዛል አይነት ነበር።” ልብ በሉ እንግዲህ እኔ አንድ የተዋሃዶ ልጅ እና የእስልምናን ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ ጠንቅቄ የማውቅ ሰው ይህን ሥሰማ ምን ሊሰማኝ እንደሚችል። ግን ምን ያደርጋል ሁሉም የየራሱ አይነት መንግስት የመመስረት አለም ውስጥ ተዘፍቋልና እገነዘበዋለሁ።

የትግራይ -ወያኔዎች እነመለስን ከነለሃጭ ከነንፍጣቸው የሚወዱበት ምክንያት አለም እየሄደችበት ያለችውና በዘር ስም የሚፈጸም ግፍ የሚያስከትለውን አጠፌታ አጥተውት ሳይሆን አዕምሯቸው የራሳቸውን ዘር ማምለክ ላይ ቆሞ ስለቀረ ነው። እኛም በዘረኝነት ወይም አንድ ወጥ በሆነ የፖለቲካ አካሄድ ላይ የተመስረተ አገር ይኖረናል ብለን ማመኑ የከፋ ችግር አለው። ይህም ነው የወያኔን እድሜ የቀጣጠለው። ወያኔ ከኦነግና ከሻቢያ ጋር ተመሳጥሮ የአረብና የምዕራቡን አለም ከጎኑ ለማሰለፍ ይዞት የተነሳው አላማ አንዲትና አንዲት ብቻ ነው። ኢትዮጵያ የምትባል አገርን የመገነጣጠል። በድብቅ ሳይሆን ግልጽ እየነገሩን ተዋግተው አገሪቱን ተቆጣጠሩ። አገሪቱ ከዚህ አይነት ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃ እያየናትም “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” የምንለውም እንዴት አገራችንን መልሰን እንደ አገር እናግኛት በሚለው ከመስማማትና ስትራቴጅ ከማውጣት ይልቅ ስንቧጨቅ ይሄው ዛሬ ወያኔ ምድረ -ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት መንፈስን ከአገር ቤት እስከ ውጭ ለመቆጣጥር ለመቃተቱ እነሓየት ክቡ በቂ ምስክሮች ናቸው።

በርናንርድ ሾው የጠቀሳት “አልጋ” ለኔ ኢትዮጵያ ናት። ፈጽሞ አገራችንን ላለማጣት ከተፈለገ ሌት ተቀን እየሸረሸራት ያለው ወያኔ ላይ እናነጣጥር። ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያ መገነጣጠል ለኔ ምኔም አይደለም የሚለውን ሁሉ ድርጅት ወደ አንድ ጎራ እየሰበሰብልን ያለው የኛ ጥረት ሳይሆን የወያኔ ለከት ያጣ ተግባር ነው። ዛሬ ተቆራርሶ ለተለያዩ ዓገራት ባለሃብቶች ያልተሸጠ የመሬት ክፍል በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል የለም። ከአሁን በኋላ ኦሮሚያን እገነጥላለሁ የሚለው ጦርነቱ ከወያኔና ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚለው ጋር ሳይሆን ከአረብ ባለሃብቶች ጋር ነው። የጋምቤላ ነጻ አውጭም የሚዋጋው ህንድን ነው። የኦጋዴኑም ከስዊድንና ከቱርክ ጋር ነው።… ብቻ ምን አለፋን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ለገበያ የቀረበች አገር ናት። ስለዚህ የትኛውም ጽንፍ ላይ እንቁም ብንል ተጠቃሚው መሃል ላይ ያለው ወያኔ ነው።

Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 12:32 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጥልቁ ,

ከእኔ ሀሳብ ጋር በተያያዘ የሰጠኸው ትንተና በፍፁም የተሳሳተ ግምት ላይ ( ስለ እኔ እምነት ) የተመሰተ ይመስላል :: በአልጋውም ቲዎሪ ላይ የምለው ይኖረኛል :: ስመለስ ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 1:07 am    Post subject: Reply with quote

Laughing

ልጓም በወሬ አይፈታምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምምም
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 1:42 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም እናመሰግንሃለን

በዚህ ርእስ ላይ ማንበብን እንጂ መሳተፍን አልፈለኩም ነበር ..ግን ዝም ብዬ ማለፍም ሀጢያት መስሎ ተሰማኝ ..እና ወደ ራሴ ሀሳብ ከመሄዴ በፊት ሀሳብን ጥርት ባለ መልኩ መረዳት ስለፈለኩ በጥያቄ ለመግባት ተገደድኩ ....

Quote:
የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነትና የኦነግን ጸረ -ኢትዮጵያዊነት በአንድ ዓይነት ዓይን ማየቴ ምናልባት ስህተት ሊሆን ይችላል :: ደም የቀመሰና ደም ያልቀመሰ አንድ አይደለም

በጣም የምታስቅም ...የምትገርምም አባባል ሆና አግኝቻታላሁ . Very Happy እስቲ ለምን በአንድ አይን ማየቱ ስህተት እንደሆነ አስረዳን . Question

Quote:
እኔም በቅርብ አመታት በደንብ እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር አብዛኛውን ኦነጋዊ (አባል ሆነም ደጋፊ ) መራራ ስሜት እንዲይዝ ያደረገው ነገር "ያልሠለጠነው አቢሲንያዊ " እንደልቡ የሚለቀው ያልተገራና ከወንድማዊነት ያልመነጨ አነጋገር ነው ብዬ አምኛለሁ ::

ለመሆኑ ባንተው ትንታኔ "ያልሰለጠነው አቢሲንያን " እነማን ናቸው ... Question እንዳው በነካካ እጅህ አቢሲኒያ ማለትስ ምን ማለት ነው . Question

Quote:
አማራው ጋር ትልቅ ችግር አለ :: በጣም ዲፌንሲቭ ሞድ ውስጥ ለራሱ ገብቶ ሌላውንም እያስገባው ይገኛል

የትኛው አማራ ነው (አማርኛ ተናጋሪ ለማለት ነው Question) እንዲህ አንተ ያልከው ችግር ውስጥ የገባው ..እስቲ ከምሳሌ ጋር በተጨባጭ ለማስረዳት ሞክር ..ለምን Question Question

Quote:
ያለፈው ዘመን ችግር ሁሉ አዎን ተፈጥሯል - ልክ ነው :: ክፉ ክፉውን ከኋላችን እንተወውና መልካም መልካም የሆነውን ነገር ብቻ ለይተን እናውጣ - ከዚያም አብረን እናስኪደው " ማለት ብቻ ነው !! እያንዳንዱ አማራ ይህን አይነት አነጋገር መናገር ቢለምድ የብዙዎችን ጽንፈኞች አስተሳሰብ መቀልበስ የሚችል ይመስለኛል ::

Very Happy ለምን ንግግርህን አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ብቻ አነጣጠርክ . Question

በመጨረሻም ..
Quote:
አሁን ጥያቄው ለአማራው ይህን ማን ያስተምረው ?!! የሚል ነው :: እርሱ ከሌላው ከተባበረ ወያኔያዊ ትግራዋይነት ኃይል አይኖረውም የሚል እምነት አለኝ ::

አማርኛ ተናጋሪው (አማራ አላልኩም ) በአንተ አስተያየ መሀይም ...ምንም የማያውቅ ..ዶማ ነገር ሆነብህ . Question ለመሆኑ ኢትዮጲያዊነት ማለት ላንተ ምን ማለት ነው . Question ይህንን ከመለስክ በኋላ ..የራሴንም አንድ ሁለት እላለሁ ..ዘንድሮ መቼም ዋርካ የማያሰማን ጉድ የለ ..እስቲ ቀጥል . Wink

አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 3:59 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አንፌቃ :

በመጀመርያ ዝም ብለህ ከመናገርህ በፊት ያልገቡህን አባባሎች ለመጠየቅ በመወሰንህ በጣም ጥሩ አድርገሃል :: ጽሑፌ ግልጽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ :: የበለጠ ግልጽ እንዲሆንልኅ ለማድረግ ልሞክር :: ያንን የማደርገው ከመስመርና መስመር መሃል የደበቅሁት አባባል ያለ እንደመሰለህ ስለተረዳሁ : የተጻፈውን ብቻ እንድታነብ ለመርዳት ያህል ነው ::

አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም እናመሰግንሃለን

በዚህ ርእስ ላይ ማንበብን እንጂ መሳተፍን አልፈለኩም ነበር ..ግን ዝም ብዬ ማለፍም ሀጢያት መስሎ ተሰማኝ ..እና ወደ ራሴ ሀሳብ ከመሄዴ በፊት ሀሳብን ጥርት ባለ መልኩ መረዳት ስለፈለኩ በጥያቄ ለመግባት ተገደድኩ ....

Quote:
የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነትና የኦነግን ጸረ -ኢትዮጵያዊነት በአንድ ዓይነት ዓይን ማየቴ ምናልባት ስህተት ሊሆን ይችላል :: ደም የቀመሰና ደም ያልቀመሰ አንድ አይደለም

በጣም የምታስቅም ...የምትገርምም አባባል ሆና አግኝቻታላሁ . Very Happy እስቲ ለምን በአንድ አይን ማየቱ ስህተት እንደሆነ አስረዳን . Question

ደም የቀመሰ - ሥልጣን ላይ ለመውጣት ሲል : በልዕለ ኃያላን አገሮች ግፊት ወይም አስታጣቂነት : ሌላውን በግፍ ጨርሶ : ለራሱም በጭካኔ ለተሳሳተ ዓላማ ለሥልጣን ሲል ብቻ ተሰውቶ : ደም አፍስሶና ተፋስሶ ዙፋን ላይ የወጣ ::

ደም ያልቀመሰ - የዚያን ዕድል ያላገኘ ::

በሲ አይ እምነት መሠረት አንድ የሦስተኛው ዓለም አገር ገዢ ፓርቲ የግድ በደም መፋሰስ ውስጥ ያለፈ መሆን አለበት :: ለምን ቢሉ : ደም የቀመሰ ገዢ : ቅንዝንዝ ስለሆነና ሥልጣኑን ከሚያጣ ሞቱን ስለሚመርጥ : እነርሱ ለሚያቀርቡለት ማንኛውም ቅድመ ሁኔታ ተናግረው ሳይጨርሱት በፊት አድርጎላቸው ጭራውን በመቁላት ተገዢነቱን ያሳያልና :: አሁን ተመለሰልህ ?

Quote:
Quote:
እኔም በቅርብ አመታት በደንብ እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር አብዛኛውን ኦነጋዊ (አባል ሆነም ደጋፊ ) መራራ ስሜት እንዲይዝ ያደረገው ነገር "ያልሠለጠነው አቢሲንያዊ " እንደልቡ የሚለቀው ያልተገራና ከወንድማዊነት ያልመነጨ አነጋገር ነው ብዬ አምኛለሁ ::

ለመሆኑ ባንተው ትንታኔ "ያልሰለጠነው አቢሲንያን " እነማን ናቸው ... Question እንዳው በነካካ እጅህ አቢሲኒያ ማለትስ ምን ማለት ነው . Question

ጥልቁ : ኦነጎቹን ፓል ቶክ ላይ ሲያናግራቸው : ምናልባት ያለውን ችግር አክኖውሌጅ ከማድረግ በመጀመር በወንድማዊነት ስላነጋገራቸው : ዕድል እንክዋ ይሰጡኛል ብሎ ያልገመታቸው ኦሮሞዎች ወንድሞቹ "የሰለጠነው አቢሲንያዊ " ብለው ሰየሙት :: አማራንና ትግሬን አቢሲንያውያን እንደሚሏቸው ታውቃለህ አይደል ?

እኔ ደግሞ ያንን አይነት አነጋገርና አቀራረብ የማይቀርብና : ይልቁንም ኦሮሞዎች ስለመብት በሚጮሁበት ጊዜ "ጋላ ምናባቱ ደግሞ " ዓይነት ንግግር ተናግረው የባሰውን አማራውንና ትግሬውን የሚያስጠሉትን አማራዎችና ትግሬዎች ለጥልቁ ከሰጡት ስም በመነሳት "ያልሠለጠኑ አቢስኒያውያን " እንደሚሏቸው በመገመት በኮቴሽን ውስጥ እንደምታየው አሰፈርኩልህ :: እኔና ጥልቁ ተግባብተናል :: አንተም ይገባሃል ብዬ እገምታለሁ ::

አቢሲንያ ምን ማለት ነው ላልከው : አቢሲንያ ኢትዮጵያን የሚወክል ስም አይደለም :: አቢስ በሚባለው የኩሽ ልጅ ስም የተሰየመና ሰሜኑን ክርስቲያን ክፍል ከሌላው የኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕዝብ ለይቶ ለመምታት የእንግሊዝ በጥባጮች ሆን ብለው እንዲገንን ያደረጉት ስም ነው ::

Quote:
Quote:
አማራው ጋር ትልቅ ችግር አለ :: በጣም ዲፌንሲቭ ሞድ ውስጥ ለራሱ ገብቶ ሌላውንም እያስገባው ይገኛል

የትኛው አማራ ነው (አማርኛ ተናጋሪ ለማለት ነው Question) እንዲህ አንተ ያልከው ችግር ውስጥ የገባው ..እስቲ ከምሳሌ ጋር በተጨባጭ ለማስረዳት ሞክር ..ለምን Question Question

እዚህ ዋርካ ላይ አንድ ብዬ ልጀምርልህና - ገራዶ ::

ሌሎችም ብዙ አሉ - ስማቸው የጠፉኝ :: ኦሮሞዎች (ምናልባትም የኦነግ አባላት የሆኑ ኦሮሞዎች ): እየተሳደቡ ወይም እየተራገሙ በሚመጡበት ጊዜ : እንደጥልቁ ፈራ ተባ ብለውም ቢሆን በወንድማዊ ውይይት ቢጀምሯቸው : በቀላሉ ሊግባቡዋቸው እንደሚችሉ ባለመረዳት : "ጋላ ቅማሉን በዱላ " "ጋላና አር ..." ምናምን እያሉ ዋርካን የሚያግማሙትን ኢግኖራንቶች ነው የምልህ :: ዐወቅሃቸው አይደል ? (ገራዶ እንኳን እንዲህ ደረጃ አልደረሰም :: ቢሆንም "ስንጠላችሁ በግድ ውደዱን ነው እንዴ ? ወደኛ አትምጡብን እንጂ !" እያለ ብአዴናዊ ክልሉን ሲያሰምር አይቼ ብዙ ጊዜ አማራው ይህን አይነት አቋም ሊይዝ እንደማይገባው ለማሳመን ተከራክሬዋለሁ :: ሌሎቹን ግሞች ግን ከነግም ተረታቸው ከመተው ውጪ ምንም ላደርጋቸው አልቻልኩም )::

Quote:
Quote:
ያለፈው ዘመን ችግር ሁሉ አዎን ተፈጥሯል - ልክ ነው :: ክፉ ክፉውን ከኋላችን እንተወውና መልካም መልካም የሆነውን ነገር ብቻ ለይተን እናውጣ - ከዚያም አብረን እናስኪደው " ማለት ብቻ ነው !! እያንዳንዱ አማራ ይህን አይነት አነጋገር መናገር ቢለምድ የብዙዎችን ጽንፈኞች አስተሳሰብ መቀልበስ የሚችል ይመስለኛል ::

Very Happy ለምን ንግግርህን አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ብቻ አነጣጠርክ . Question

ምክንያቱም : ሁሉም እርሱ ላይ ስለሆነ ሆድ የባሰው !! አይደል እንዴ ?! ትምክህተኛ : ያለፈው ዘመን እንዲህ አድርጎ አገዛዙን በሌላው ላይ ጭኖ ወዘተረፈ እየተባለ የሚሰደበው እሱ አይደለ ? ተሳዳቢዎቹን ጸረ -ኢትዮጵያ ኃይሎች ብያቸዋለሁ :: ወያኔዎችንና ኦነጎችን ይመለከታል :: ሆኖም : አማራው ለዚህ ትችት ከላይ እንደጻፍኩልህ አይነት የተግማማ ስሜታዊ መልስ በመስጠት ራሱን ምንም ውንጀላ ሊደርስበት የማይገባ አድርጎ ባስቀመጠ መጠን ይኸው ትምክህተኛ የሚባለው ስድብ እየበዛበትና አገር እየፈራረሰ ይመጣል እንጂ ምንም ጥቅም የለውም :: ግልጽ አይደለም ይሄ ?

Quote:
በመጨረሻም ..
Quote:
አሁን ጥያቄው ለአማራው ይህን ማን ያስተምረው ?!! የሚል ነው :: እርሱ ከሌላው ከተባበረ ወያኔያዊ ትግራዋይነት ኃይል አይኖረውም የሚል እምነት አለኝ ::

አማርኛ ተናጋሪው (አማራ አላልኩም ) በአንተ አስተያየ መሀይም ...ምንም የማያውቅ ..ዶማ ነገር ሆነብህ . Question

ምን ዐውቃለሁ አንፌቃ ? አንተው ንገረኝ እንጂ ?!! እስቲ እንደጥልቁ ወይም እንደኔ ከኦሮሞዎች ጋር በአግባቡ ለመነጋገር ለምን አልቻለም ? ለምን ዘሎ "ጋላና አር " ምናምን ምናምን የሚል ዝብዘባ ውስጥ ይገባል ?

በዚህ አማራውን አትውቀሰው ካልከኝ - አንፌቃ : ይሄ ነው ዶማነት ብዬ እነግርሃለሁ ::

Quote:
ለመሆኑ ኢትዮጲያዊነት ማለት ላንተ ምን ማለት ነው . Question ይህንን ከመለስክ በኋላ ..የራሴንም አንድ ሁለት እላለሁ ..ዘንድሮ መቼም ዋርካ የማያሰማን ጉድ የለ ..እስቲ ቀጥል . Wink

አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ

ኢትዮጵያዊነትማ ኢትዮጵያዊነት ነው :: ሁላችንም በመንፈስ እናውቀዋለን :: በተግባር መተርጎም ነው እንጂ ያቃተን ::

አሁን ይልቅ አማራውን ማን ያስተምረው ? እንዴት ከኦሮሞ ወንድሞቹ ጋር በጸባይ ኮሚኒኬት ማድረግ እንዳለበት ? ምክንያቱም ከላይ እንዳልኩህ ኦሮሞዎቹ (በተለይ ኦነጎቹ ) ክርር ያለ የጥላቻ ወሬ እያወሩ ቢያናድዱንም : በአግባቡ የሚያነጋግራቸውና እንደሰው የሚቆጥራቸው ቢገኝ ልባቸው ወዴትም አልሄደም ነው የምልህ ::

በዚህ ዘመን እኮ "ስምሽ ማነው ?" ብሎ "አያንቱ " ብላ ስትመልስ "አያንቱ ?!" ብሎ ሳቅ በሳቅ የሚሆን አማራ ነው ያለው ?!!! ያውም የተማሩ የተመራመሩ ናቸው እኮ ?! በየጊዜው እየሰማሁ የሚገርመኝና የምታዘበው ነገር ነው :: ይሄ ነው አማራነት ? ይሄ ነው ወይ ኢትዮጵያዊነት ? ይሄ ነው የእግዚአብሔር ሕዝብነት ? ይሄ ነው ክርስትና ?!!!

እንዲህ ተኩኖስ እንኳንስ ኢትዮጵያዊነትን የመሰለ የሞራል ልዕልና የተላበሰ ማንነት ቀርቶ : ጎንደሬነትና ጎጃሜነት እንኳ ይገኛል ?

አንተ የኔን ጽሑፍ በዋርካ ታዘብኩ ትለኛለህ ::

እኔ ስንቱን እያየሁ እስካሁን ተገርሜያለሁ መሰለህ ?!! [/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 4:44 am    Post subject: Reply with quote

አይ መልካም ..ይመችህ ..አሁን አመጣጥህ ከየት እንደሆነ ገብቶኛል ..በሁሉም ሀሳብህ ባልስማማም Exclamation Exclamation

መልካም ውይይት

እኔ ስንቱን እያየሁ እስካሁን ተገርሜያለሁ መሰለህ ?!!
[/quote]
_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Sun Feb 26, 2012 2:23 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
...አገራዊ አስተዳደርን ስንመለከት የራሳችን የሆነ እምነት ተከታይ የራሳችን አይነት ፍላጎት አራማጅ የራሳችን አይነት የፖለቲካ ጽንሰ -ሃሳብ ያለው አገራችንን ቢመራት የየሁላችንም ፍላጎት ነው። ቁምነገሩ ያለው ግን ያለው እውነታ ያንን ይፈቅዳል ወይ የሚለው ነው።ሰላም ጥልቁ :

በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ መመላለስ እንደሌለብን ቢገባኝም የተሳሳተ በመሰለኝ ግንዛቤ ላይ ተመስርተህ ትንተና ስለሰጠህ እሱን ማረም ስላለብኝ በአጭሩ የለው አለኝ ::

እንዳልከው በየትኛውም ሀገር ፖለቲካ ( እና ዘመንም ጭምር ምናልባት ) የፖለቲካ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ መሰረቱ ዓለምን የምናይበት እና የምንረዳበት መነጻር ነው :: ፋይዳ አላቸው ሲግኒፊካንት ናቸው ብለን በምንላቸው እና ፋይዳ የላቸውን በምንላቸው ነገሮች ላይ ተመስርተን ነው :: የዛኑ ያህል የጉዳይዮችን ፋይዳ ስንለካ ባለን ግንዛቤ ; የእምነት ጥንካሬ ; ንቃተ ህሊና እና ሌሎች ጉዳዩች ላይ ይመሰረታል :: (ሪላቲቪቲም የሚመጣው እዚህ ላይ ነው )::

ማንነትን በሚመለከት ጉዳይ ግን ማንነት ፒዮርሊ ሶሻል ኮንስትራክሽን አይደለም :: ከለሌ ከሌላው ---ፖለቲካ እና እምነትም በማንነት ስሪት ላይ የየራሳቸው የሆነ ትልቅ አስተዋጾ አላቸው :: ያሉን ጥቂት የታሪክ ሰዎች አንዴ በፖለቲካ ተጽዕኖ ምክንያት ሌላ ጊዜ ደሞ በሪሶርስ እና ጊዜ እጥረትም ምክንያት በነበረን ማህበራዊም ሆነ ፖለቲካዎ ታሪክ ላይ መደረግ ያለበትን ያህል ምርምር ሊያደርጉ አልቻሉም ::

ያሆ ሆኖ ግን እንዲሁ በወፍ በረር ያሉትን መረጃዎች ግት ውስጥ በማስገባት ; ታሪካችንን እና የውጭ ሀይሎችን የረቀቀ እና ያልረቀቀ ጣልቃ ገብነት ግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎችን አሰላለፍ ስናጤነው የምናገኘው ከሁለት ወይ ከሶስት ያለፈ ቡድን አይሆነም ::

አፈጣጠሩ እና ምህዋሩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሳለ በዓለም ላይ ባለው ነባራዊ ሁኔታ እና በግንዛቤ ማደግም በትክክልም በኢትዮጵያ በታሪካችን ውስጥ በነበረው የፓወር ሪሌሺን የተጎዱ የህበረተሰብ ክፍሎች ነበሩ ብሎ ችግሩን ኦውን በማድረግ በማንኛውም ሀገር ታሪክ ውስጥ እንደነበረው የስልጣን ክፍፍል እና ጭቆና ችግሩን ኦውን በማድረግ ---የኢትዮጵያዊነትን መሰረት ሌሎች በጎ ጎኖቹን አሽቀንጥሮ መጣል ሳያስፈልግ እንዲያውም ክብር እና ተገቢውን ትርጉም እየሰጡ ---ፕሮፕለማቲክ የሆነውን ፓርት ለማስተካከል የሚሰሩ ከምር ኢትዮጵያውያን የሆኑ የፖለቲካ ድርጂቶች አሉ :: ጥሩ የነበረውን የኢትዮጵያዊነታችንን ፓርት አጥብቆ የሚይዘውን እና በምክንያታዊነትም ጭምር እየመዘነ በነዚህ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ትርጉም አግኝቶ አጥብቆ የያዛቸውን የህብረተሰብ ክፍል ጽንፈኛ ማለቱ ብዙ ትርጉም አላይበትም :: ራሴን ከዚህኛው ክፍል እመድባለሁ :: እንደዛም ሆኖ ግን የእኔ አይነት እምነት ብቻ ያለው ( የፖለቲካ የማህበራዊ እና የእምነትም ጭምር ) ኢትዮጵያን ሊያስተዳድር ይገባል የሚል ቅዠት የለኝም :: እንደዛ ከሆነ እውነትም ጽንፈኝነት አለ :: ግን ትክክል አይመስለኝም :: ለምሳሌ የኢትዮጵያን እስልምና እንደኢትዮዊ እምነት የምቆጥር ሰው ነኝ :: ለምሳሌ ዋቄ ፈቻውን (ለሚያምኑበት ) እንደ ኢትዮጵያዊ እሴት እና ባህል የማይ ነኝ :: ነገሩ ከአስተዳደጋችን ብቻ የመጣ ሳይሆን የሪኮግኚሽንን ፋይዳ እና ትርጉም ስለምንረዳ ነው ::

ወደ ሌላኛው ብድን ስሄድ ---የኢትዮጵያን ታሪክ ጨለማማ ገጽታዎችን አጠንክሮ በመያዝ ---ከራሳቸውም ትርጎሜ እና እይታ ባለፈ ...የኢትዮጵያን ታሪክ ትርጉም ከውጪ ሀገር መሰሪ የታሪክ ጸሀፊዎች እና ከነዙት ሀገር የማፈራረስ ፕሮፓጋንዳ ( ሌላው የአፍሪካ ክፍል ያስቡትን በቀላሉ ለማሳካት ሰለቻሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሞከሩት አይነት ሙከራ አላስፈለጋቸውም ነበር ) የፖለቲካ አጀንዳ ቀርጸው ጽንፍ በመያዝ ከፈረንጆቹ እኩል ወይንም ከዚያ በላይ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተነሱ ደነዝ የፖለቲካ ቡድኖች ደሞ አሉ :: እንደ ህወሀት ያሉት በሆነ አጋጣሚ የሀይል ሚዛኑ ሲቀየር እና ስልጣን እጃቸው ውስጥ ሲገባ በኢትዮጵያ ላይ ያነሳሳቸውን ጥላቻቸውን እንደያዙ ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ላይ ተነዝቶ የነበረውንም ጸረ -ኢትዮጵያዊነት ፕሮፓጋንዳ እየተንከባከቡ በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጥላቻ ተጠብቆ በእነሱ ቁጥጥር ስር ሆኖ እንዲኖር እየፈለጉ ; ""ህገ -መንግስታዊ "" ዋስትናም ለመጠባበቂያ አስቀምጠውለት በሌላ በኩል ደሞ ኢትዮጵያ በታሪክ አድርሳዋለች ከሚባለው ኢፍትሀዊ የስልጣን ክፍፍል እና የሀብት ስርጭት የበለጠ በዘረፋየታጀበ የስልጣን ሞኖፖል የፈጠሩብት ሁኔታ አለ :: ለምሳሌ የኦሮሞ ህዝብ በታሪክ ደርሶብኛል ከሚለው ነገር የበለጠ ህወሀት አድርሶበታል :: ነገር ግን የተነዛው የጸረ -ኢትዮጵያዊነት ፕሮፓጋንዳ በጣም ጠንካራ ስለነበረ ዛሬ ከሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ጋር እንታገላለን ብሎ ከኦነግ ውስጥ የወጣውን የፖለቲካ ቡድን ተቃውሞ ጽንፈኛ አቋም ይዞ የቀረው ቡድን ህውሀት ካደረሰው ቅጥ ያጣ የመብት ረገጣ እና አፈና የበለጠ ---የዜግነት ትርጉም እና ግንዛቤ የስብአዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ባልነበረበት ከመቶ አመት በፊት በነበረች ኢትዮጵያን የነበረውን የፊውዳል ኢትዮጵያ አስከፊ ገጽታ እንደዳዊት እየደገመ ከግፈኛው የህወሀት ቡድን ጋር ለመደራደር ሆዱ ሲጮህ እናያለን :: እንሰማለን :: ያደርጉታልም :: ሁለቱን ቡድኖች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ለዲሞክራሲያዊነት ያላቸው ፍቅር ሳይሆን ለኢትዮጵያ ያላቸው ጥላቻ ነው :: አንደኛው ተሳክቶለት ስልጣን የያዘ ነው :: ሌላኛው ያልተሳካለት እና እድሜውን ሲንከራተት የጨረሰ ነው :: ለኢትዮጵያ ካላቸው ጥላቻ በተጨማሪ እነዚህን ቡድኖች የሚያመሳስላቸው ፅንፈኛ የሆነ የፖለቲካ አቋማቸው ነው :: ከሌሎች የፖለቲካ ቡድን ጋር ተነጋግሮ ሰጥቶ የመቀበል ነገር የለም :: ያለነሱ በስተቀር ሌላው የፍትህን ትርጉም እና ምንነት አይረዳም :: በሌላ በኩል ግን የሁለቱም የፍትህ ሚዛን ምን ያህል ጠንጋራ እንደሆነ በተደጋጋሚ በተግባር አሳይተዋል ::

ሶስተኛ ብየ በምከፍለው የፖለቲካ ቡድን ውስጥ ደሞ የግሎባላይዜሽን ጭርፎች አሉ :: በሀገር ውስጥም በውጭም :: እነዚህኞቹ ደሞ ከላይ ካስቀመጥኳቸው ሁለት ቡድኖች በተለየ ሁኔታ ""መሀል መንገድ "" አለ በማለት ዱብ እንቅ እያሉ ያሉ ናቸው :: በነገሩ በዓነታቸው ሁለት ናቸው :: እንደ ልደቱ እና የሱ ፓርቲ የፖለቲካ ትክለ ሰውነቱን ለዚህ ዓይነት ፓለቲካ አዘጋጂቶ እያሳበረ ከህወሀትም ከግሎባላይዜሺኑም እያለ የሚሄድ ቡድን አለ :: ከእሱ ደሞ በእድሜ የሚያንስ ሌላ ራሱን በማደራጀት ላይ ያለ ቡድን አለ :: ይሄኛው ቡድን ደሞ ህወሀትን የሚጠላ ነገር ግን በውጪ ሀይሎች በኢትዮጵያ ላይ ባላቸው የፖለቲካ የኢኮኖሚ የባህል እና የእምነትም ጭምር አጀንዳ አምኖ የተጠመቀ የሚመስል ቡድን አለ :: ይሄኛውም ግሩፕ የራሱ የሆነ በብልጣብልጥነት የሚያራምደው የራሱ ጽንፈኝነት አለው :: ወደ መጨረሻ አካባቢ እንዳልከው ....የተለያዮ የክርክር አጀንዳዎች ያነሱ እና ኢትዮጵያ ተስፋ የሌላት ሀገር ናት :: አልቆላታል ይሉሀል :: በመቀጠል የሚሻለው ነገር ኮምፕሮማይዝ ነው ይሉሀል :: ምንድን ነው ኮምፕሮማይዙ ከማን ጋር ብየ ስጠይቅ ---የምዕራቦቹ አጀንዳ ሆኖ አገኘዋለሁ :: ""እነሱም ይጠቀሙ እኛም እንጠቀም :: ሀገሪቱ ከምትበታተን "' ይሉሀል :: እስካሁን ባደረኩት ረዣዥም የስልክ ውይይት ሁለት ጊዜ እንደዚህ አይነት መልስ ነው ያገኘሁት ::

ስናጠቃልለው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስፐክትረም ላይ ቢያንስ ሶስት አይነት ጽንፈኝነት አለ ::

የመጀመሪያው ለነበሩ ችግሮች እውቅና ሰጥቶ አንተ እንዳልከው ከባንዲራው እና ከሀገሩ ሳይሸሽ ነገር ግን ጥሩ የሆኑ እሴቶቻችን አይሸጡም አይለወጡም የሚለው ወገን አለ ::

እንደ ህወሀት እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ከምቀላቀል አንገቴን ለሰይፍ የሚለው ጽንፈኛው አይነት የኦነግ ቡድን አለ :: ፅንፈኝነታቸው ጸረ -ኢትዮጵያዊነት ነው መሰረቱ :: ኦነግ በባዶ ሜዳ አውሮፓ ለአውሮፓ እየዞረ ክችች ሲል ህወሀት በውጭ ሀገር እንደዚህ ባሉ ድርጂቶች በሀገር ውስጥ ደሞ ""ኢሀዴግ እህት "" ድርጂቶች ተከልሎ ስልጣኑን በበላይነት ይዞ የማይቆይ ከሆነ ኢትዮጵያ የምትበታተንበትን ሁኔታ ያመቻቻል ::

ሶስተኛው ደሞ በአጭር አማርኛ ዘመናዊ ባንዳ ነው :: በዲሞክራሲያዊነት በምክንያታዊነት እና በጸረ -ህወሀት ትግል ተከልሎ የሌሎች ሀገሮች እና ህዝቦችን አጀንዳ ለኢትዮጵያ በሚደረግ የፖለቲካ ትግል ሸፋፍኖ ሊያመጣ የሚፈልግ ቡድን ነው ::

የመጨረሻዎቹ ሁለት ቡድኖች ጋር ኮምፕሮማይዝ ማድረግ የሚቻልም የሚያስፈልግም አይደለም ብየ አምናለሁ :: ነጥባችን ኢትዮጵያዊነት እስከሆነ ድረስ :: ይሄ ታዲያ እንደጽንፈኝነት ሳይሆን መታየት ያለበት እንደ መሰረታዊ የፖለቲካ ልዮነት ነው ::

አልጋ ያልከው ቲዎሪ ከላይ ካነሳሁት ነጥብ አንጻር ከሶስተኛው ብድን ጋር መደራደር ጋር ሊስማማልኝ አልቻለም ::

ትልቁ የኔ ነጥብ በራሳችን እና በማንነታችን ማመን ነው :: ሀገር ቤት ያለው የፖለቲካ ሀይል አደረጃጀቱን አስተካክሎ እና ቁርጠኝነት ጨምሮበት ያለውጪ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት እና ርዳታ በህወሀት ላይ በየቦታው መዐት በማፋፋም ብቻ በታሪክ ውስጥ የነበሩት ችግሮቻችን መፍትሄ ተሰጥቷቸው ኢትዩጵያን ኢትዮጵያዊ በሆነ ሁኔታ በፖለቲካ ትራንስፎርም ማድረግ ይቻላል :: የፖለቲካ ትራንስፎርሜሽን ደሞ የሌሎች ትራንስፎርሜሺኖች መሰረት ነው ብየ አምናለሁ :: እንጂ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከውጪ ሰዎች ጋርም ሆነ ከነሱ ኢትዮጵያዊ ተወካዮች ጋር ማበርም ሆነ መደራደር ነጥቡ አይታየኝም :: በዚሁ እንጨርሰው ይሆን ?

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Mon Feb 27, 2012 3:50 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ናፖሊዮን :
በጣም ደስ የሚል መጣጥፍ ነው :: ብዙ የምለው አለኝና ጊዜየን አመቻችቸ እመለሳለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
Page 2 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia