View previous topic :: View next topic
Author
Message
ሊሊ ሞገስ Joined: 17 Jun 2007 Posts: 468
Posted: Wed Feb 15, 2012 2:02 am Post subject: የሁለቱ ሲኖዶሶች ድርድር ሳይግባቡ ተበተነ (ሰበር ዚኤና )
[ur=http://www.zehabesha.com/?p=4505]ዝርዝሩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ; አስተያየትዎን ኮመንት ቦክስ ውስጥ ያስፍሩ [/url] _________________www.zehabesha.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Wed Feb 15, 2012 9:52 pm Post subject:
መጀመሪያውንም ፈጽሞ የማይታረቅ አጀንዳ ይዘው ; እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ
1) አገር ቤት ያለው ሲኖዶስ የሚመራው በነመለስ ሆኖ እያለ ; እነ አቡነ መልከጸዲቅ ግን ; ለተገላቢጦሽ "የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ; ተቃዋሚዎችም ወደ አገር የመመለስ መብት ይኑራቸው " ይላሉ ; ሲደራደሩ :: እየተደራደሩ ያሉት ከአባ ገብረመድህን ጋር ወይስ ከመለስ
2) የነአባገብረመድህኑ ደግሞ ይባስ ... ታምራት ላይኔ ያመነውን የሸፍጥ ስራ ; እንደቅንጅት መሪዎች የሀሰት ይቅርታ ደብዳቤ ; ምንም ካልቸገራቸው ; መንፈሳዊ አባቶች እንዲጻፍላቸው ይጠብቃሉ
የዚህ ሁሉ ትርጉም የለሽ እርቅ ሙከራ መንስኤው አንድ ነው :: አገር ቤት ባለው ሲኖድስ ውስጥ የበቁ እና በእምነት የታነጹ ጥቂት አባቶች አሉ :: እነሱ ያለምንም ቅድመሁኔታ እርቅ ተደርጎ ቤተክርስቲያንን በሰላም ማየት ይሻሉ :: በተቃራኒው ደግሞ እነ አባ ገ /መድህን ይህን አይሹም ... በሲኖዶሱ ስብሰባ የሚወሰንን የእርቅ ጥያቄ ተከራክረው ለማስተውና ለማሳመን ስለማይችሉ ; "እሽ " ይሉና ; ሲኖዶሱ ሲበተን ግን ወደትክክለኛ ሰይጣናዊ ተግባራቸው ይመለሳሉ ::
ሊሊ ለዜናው አመሰግናለሁ ! በርቱ ሀበሻዎች
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጌታ Joined: 17 Apr 2005 Posts: 3226 Location: ዶሮ ተራ
Posted: Wed Feb 15, 2012 9:56 pm Post subject: Re: የሁለቱ ሲኖዶሶች ድርድር ሳይግባቡ ተበተነ (ሰበር ዚኤና )
ሊንኩን ለማስተካከል ያህል _________________ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የዘመኑ ልሳን Joined: 07 Jun 2005 Posts: 2930 Location: USA
Posted: Thu Feb 16, 2012 6:21 am Post subject:
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ፣ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ .ም፣ ማምሻውን በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት እየተካሄደ ነው፡፡ የዕርቀ ሰላም ውይይቱን በሚያስተባብረው የሰላም እና አንድነት ጉባኤ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ይኸው ሁለተኛ ዙር ንግግር ከየካቲት 4 - 9 ቀን 2004 ዓ .ም እንደሚቆይ ተገልጧል፡፡
ከየካቲት አራት ቀን ጀምሮ በዕርቀ ሰላሙ የመነጋገሪያ ሐሳቦች ላይ በሁለቱ አካላት ልዑካን ተወካዮች መካከል ሲካሄድ በቆየው የቅድመ ውይይት ንግግር ሰባት አጀንዳዎች ተለይተው ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ በተጀመረው ውይይት ዋነኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ የሚሆነው በአጀንዳ ተራ ቁጥር አንድ የተቀመጠው “ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተ” በሚል የተመለከተው ነጥብ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ አጀንዳ÷ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሡ በተደረገበት ሁኔታ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ወይስ አልተጣሰም ? የቅዱስነታቸው ቀጣይ ሁኔታስ ምን መሆን ይገባዋል ? የሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ባለው ሁኔታ ውይይቱ በመግባባት እየተካሄደ ስለመሆኑም የስብሰባው ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡ ከውዝግቡ በኋላ ስለተሾሙት ጳጳሳት፣ አንዱ በሌላው ላይ ስላስተላለፋቸው ውግዘቶች፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደረጉ የመንግሥት ጣልቃ ገብነቶች ተቋማዊ ነጻነት ስለማግኘት፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አሠራር እና የስምምነቶች አፈጻጸም እንዲሁም ስለ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያወሱት ቀሪዎቹ ስድስት አጀንዳዎች በዚህ ዙር ውይይት ይነሣሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የድሬዳዋ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ /ቤት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካን ቡድኑን በመምራት፣ የደቡብ ወሎ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በአባልነት፣ የአዲስ አበባ ሀ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ደግሞ በልዑካን ቡድኑ ፀሐፊነት በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያመሩት የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ .ም ነበር፡፡
በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሦስተኛው የልዑካን ቡድኑ አባል የሆኑት የሰሜን ምዕራብ ሸዋ -ሰላሌ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ አብረው አልተጓዙም፡፡ ብፁዕነታቸው ከየካቲት 2 ቀን ጀምረው በአዲስ አበባ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና በመከታተል ላይ ሲሆኑ ሕመማቸው የሳምባ ምች እና ስኳር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሆስፒታል ምንጮች እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት ብፁዕነታቸው ከሳምባ ምች ሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ከፍተኛ የስኳር መጠናቸውም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እና ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ እና መልአከ ገነት ገዛኸኝ የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
SOURCE
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዲጎኔ Joined: 19 Aug 2005 Posts: 3838 Location: united states
Posted: Thu Feb 16, 2012 7:31 am Post subject:
ሰላም ለሁላችን ይሁን
እርስበርሷ የምትለያይ መንግስት አትጸናም -ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመጀምሪያ ደረጃ ይህ ዋርካ ፖእልቲአክ ፐኦለቲካ ነክ ጉዳይ መወያያ ሲሆን ሊኡሊ ወደፖለቲካ እንዲገባ ለምን ፈለገች ?ቀጥሎ ደጀሰላም ስብሰባው እያመረበት ነው ሲል ሌላው
ደግሞ አለቀለት ገና ሰይጀመር የተጠናቀቀ ነው ይለናል ::የቱን እምነን ? እዚህ ነጻ መድረክ ላይ ስላመጣችሁት የመተቸት ሙሉ መብቱ አለን ::በተሀድሶና ወንጌላዊያንና መጥምቃዊያንና ጵንጤቆስጠዎች መሀል እንዲህ ውዝግብ ሲነሳ በነጻ ድህረገጽ ላይ አይቀርብም ::
ሀገር ቤት የመናገር የመጻፍ መብት ይፋ ይባስ ብሎ በሚከለክለበት ይህን ነገር ማቅረቡ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Thu Feb 16, 2012 7:57 am Post subject:
ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው : መጀመሪያውንም ፈጽሞ የማይታረቅ አጀንዳ ይዘው ; እንዴት ሊስማሙ ይችላሉ
1) አገር ቤት ያለው ሲኖዶስ የሚመራው በነመለስ ሆኖ እያለ ; እነ አቡነ መልከጸዲቅ ግን ; ለተገላቢጦሽ "የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ; ተቃዋሚዎችም ወደ አገር የመመለስ መብት ይኑራቸው " ይላሉ ; ሲደራደሩ :: እየተደራደሩ ያሉት ከአባ ገብረመድህን ጋር ወይስ ከመለስ
2) የነአባገብረመድህኑ ደግሞ ይባስ ... ታምራት ላይኔ ያመነውን የሸፍጥ ስራ ; እንደቅንጅት መሪዎች የሀሰት ይቅርታ ደብዳቤ ; ምንም ካልቸገራቸው ; መንፈሳዊ አባቶች እንዲጻፍላቸው ይጠብቃሉ
የዚህ ሁሉ ትርጉም የለሽ እርቅ ሙከራ መንስኤው አንድ ነው :: አገር ቤት ባለው ሲኖድስ ውስጥ የበቁ እና በእምነት የታነጹ ጥቂት አባቶች አሉ :: እነሱ ያለምንም ቅድመሁኔታ እርቅ ተደርጎ ቤተክርስቲያንን በሰላም ማየት ይሻሉ :: በተቃራኒው ደግሞ እነ አባ ገ /መድህን ይህን አይሹም ... በሲኖዶሱ ስብሰባ የሚወሰንን የእርቅ ጥያቄ ተከራክረው ለማስተውና ለማሳመን ስለማይችሉ ; "እሽ " ይሉና ; ሲኖዶሱ ሲበተን ግን ወደትክክለኛ ሰይጣናዊ ተግባራቸው ይመለሳሉ ::
ሊሊ ለዜናው አመሰግናለሁ ! በርቱ ሀበሻዎች
ሰላም ጥልቁ :-
በአባ ገብረመድህን በኩል ስለቀረቡት ተደራዳሪዎች ስለተወሠኑት ማንነት ወንድማችን 'የተሞናሞነው ' በሌላ ርዕስ ምንጭ ጠቅሶ አቅርቦልናል :: ምንጭ :- የተሞናሞነው : ዋርካ ፖለቲካ :: የኢትዮጵያ ኦ /ተዋህዶ ቤ /ክ በወያኔ የዘር ሰንሰለት ::
ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ ማለት የአዲስ አበባ ሀገረ ሥብከት ሥራ አስኪያጅ : የአባ ገብረመድህን የሥጋ ዘመድና ዋናው የወያኔ ተወካይ ናቸው ::
አቡነ ገሪማ ማለት በዓለማዊ ሥማቸው ዶክተር ግርማ የሚባሉትና የመንፈሣዊ ኮሌጅ ምሩቅ : በደርግ የአገዛዝ ዘመን ቤተክህነትን እንዲሠልሉ በኮሎኔል ተስፋዬ ወልደሥላሤ (ራሱ ማቹ የደርግ የደህንነት ሹም ኮሎኔል ተስፋዬ የመንፈሣዊ ኮሌጅ ምሩቅ ነበር ) የተመደቡ የሥለላ ሰው ናቸው : መንፈሣዊነትም የላቸውም ::
ከልዑካኑ መካከል የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሥብከት ሊቀ -ጳጳስ አቡነ ቀውስጦስ አባ ገብረመድህንን ደጋግመው በጠንካራ መንፈሣዊ ልዕልና የሚሞግቱ ሲሆኑ "በጤና እክል ምክንያት " በሚል ሠበብ በድርድሩ ላይ እንዳይገኙ ተደርገዋል ::
እንግዲህ አንተም እንደገለጽኸው እንዲህ ዓይነቱ 'ድርድር ' ዓላማው የአባ ገብረመድህንን ሕገ -ወጥ ሠይጣናዊ የወያኔን ሥራ ያለ ዕንቅፋት ለማስቀጠል እንጂ ከልብ የተደረገ የዕርቅ ድርድር አይደለም ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Thu Feb 16, 2012 5:28 pm Post subject:
አቡነ አትናቴዎስም ተገኝተዋል ይባላል ...እሺ ብለው ለአባ ጳውሎስ መልዕክተኛ ሆነው መምጣታቸው ገርሞኛል :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዲያስፖራ Joined: 29 Apr 2009 Posts: 658 Location: no
Posted: Thu Feb 16, 2012 5:31 pm Post subject:
የት ቦታ ነው ኢትዮጵያኖች ተስማምተው እርቅ የፈጠሩት ?? በይትኛውም ሁኔታ በ ፖለቲካ , በሀይማኖት , በጎሳ , በህብረተሰብ ወዘተ የት ቦታ እርቅ አድርገው ስምምነት የደረሱት ?? አለ እዚህ ቦታ ይምትሉ ካለ አሳዩን እንማርበት , እንዲያውም ኢትዮጵያኖች ቀኝ እግራቸው ከግራ እግራቸው ጋር ተጋጭቶ ማስማማት ይተቸገሩ እንጂ አንድ የሆኑበት የለም :: እንዲያውም እዚሁ ዋርካ ላይ በሀሳብ በአላማ የተለያዩ በሀገር ድረጃ ግን አንድ ነን ሲሉ አልታየም , አንዱ ያንዱን ዜግነት ሲቀማ እንጂ ሲስማማ አላየንም . ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው መታረቅ አቅቷቸው እኔ ብቻ የኢትዮጵያ መድሀኒት ይሉናል , ገጂው ኢህአደግ ደሞ የምን እርቅ ማን ከማን ጋር ተጣላ እያለ ይቀልድብናል ቀልዱን ሞቅ ሲያርገው ደሞ ግማሽ መንገድ ድርስ መጥተን ለእርቅ ዝጉጁ ነን ይለናል :: መረጃ እፈለጋለሁ ኢትዮጵያኖች በታሪካቸው ቁጭ ብለው ችግራቸውን በውይይት ይፈቱበት እርቅ ያድረጉበት :: እኔ የለም የለም ነው የምለው ስለዚህ ምንም ነገር አልጠብቅም ከየት መቶ ያልተዘራው ከየት ነው የሚታጨድ ?? _________________ ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Thu Feb 16, 2012 5:49 pm Post subject:
በጂምላ ኢትዮጵያውያኖች አይስማሙም የሚባለው አባባል ታሪካዊ መሰረትም የለውም :: ትክክልም አይደለም :: የጉዳዮን ጭብጥ ማየት እና መመዘን ያስፈልጋል ::
በዚህኛው ጉዳይ የታጋይ ጳውሎስ ቡድን የሚፈልገው በብልጣብልጥ መንገድ ነገሮችን እጁ ውስጥ አስገብቶ መውቀጥ ነው :: ሌላ ሌላውን ትተህ ...ይሄ ሰውየ በጉልበት ያለ አግባብ ፓትሪያርክ እንደሆነ ---ደብዳቤውን ጻፈ ከተባለው ከታምራት ላይኔ መረጃ እየቀረበ ያንን መካድ ምን ይባላል ?? ሌላኛውስ ወገን በዚህ ባይስማማ ይፈረድበታል ?? እኔ ከነጭራሹ ቢስማሙ ኖሮ ነበር የሚገርመኝ ::
ታጋይ ጳውሎስ እኮ ለህወሀት ታማኝ ሆኖ ለእምነቱ የሚቆረቆር ሰው ቢሆንም እኮ አንድ ነገር ነው ነገር ግን ይሄ ሰውየ ቤተ -ክርስቲያኒንቱ ለማርከስ እና ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳ ሰው ነው :: ኢትዮጵያዊው አማኝ በሱ ሲባረክ እና ሲፈታ ይገርማል በእውነት !
እና እየለየህ ወንድሜ አታጋግለው ጉዳዮን :: ፍሬ ነገሩን ነው አጥብቆ መያዝ ::
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ዲያስፖራ እንደጻፈ(ች)ው : የት ቦታ ነው ኢትዮጵያኖች ተስማምተው እርቅ የፈጠሩት ?? በይትኛውም ሁኔታ በ ፖለቲካ , በሀይማኖት , በጎሳ , በህብረተሰብ ወዘተ የት ቦታ እርቅ አድርገው ስምምነት የደረሱት ?? አለ እዚህ ቦታ ይምትሉ ካለ አሳዩን እንማርበት , እንዲያውም ኢትዮጵያኖች ቀኝ እግራቸው ከግራ እግራቸው ጋር ተጋጭቶ ማስማማት ይተቸገሩ እንጂ አንድ የሆኑበት የለም :: እንዲያውም እዚሁ ዋርካ ላይ በሀሳብ በአላማ የተለያዩ በሀገር ድረጃ ግን አንድ ነን ሲሉ አልታየም , አንዱ ያንዱን ዜግነት ሲቀማ እንጂ ሲስማማ አላየንም . ተቃዋሚዎች እርስ በርሳቸው መታረቅ አቅቷቸው እኔ ብቻ የኢትዮጵያ መድሀኒት ይሉናል , ገጂው ኢህአደግ ደሞ የምን እርቅ ማን ከማን ጋር ተጣላ እያለ ይቀልድብናል ቀልዱን ሞቅ ሲያርገው ደሞ ግማሽ መንገድ ድርስ መጥተን ለእርቅ ዝጉጁ ነን ይለናል :: መረጃ እፈለጋለሁ ኢትዮጵያኖች በታሪካቸው ቁጭ ብለው ችግራቸውን በውይይት ይፈቱበት እርቅ ያድረጉበት :: እኔ የለም የለም ነው የምለው ስለዚህ ምንም ነገር አልጠብቅም ከየት መቶ ያልተዘራው ከየት ነው የሚታጨድ ??
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ደብረብርሀን 33 Joined: 17 Aug 2011 Posts: 252
Posted: Fri Feb 17, 2012 2:43 am Post subject:
ህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስና ፓትራያክ : በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ እና ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ናቸው :: የወያኔን ሲኖዶስ እና ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ቀኖና ቤተክርስቲያን የጣሰውን : ሕጋዊ አልከው ከዚህ የበለጠ የወያኔነትህ ማስረጃ ይኖር ይሆን ይህን አምነህ አንተ እና መሰሎችህ የወያኔን ሲኖዶስ ሕጋዊ አላችሁት :: አሜሪካ ያለውን ሲኖዶስ እውቅና የሰጠችሁት አትመስሉም :: ታዲያ ከእናንተ ጋር ነው ወያኔን የምንታገለው የዘመኑ ልሳን የምትባል ሰው : ደርግ ናፋቂ , አምላኪና የደርቅ ቅሪት / remnant ብቻ ሳትሆን : አስመሳኝ ተቃዋሚ መሆንህና የወያኔ አገልጋይነትህ : አሁን አሁን በጣም እየተገለጸልኝ መጥቶል :: በስደት ያሉትን አባቶችን ማንነት , የኢትዮጵያዊነት ጽንአት አይበገሬነት የተረዳችሁ አትመስሉም ::ስለዚህ የፈለጋችሁትን የመዘባረቅ መብታችሁ የተጠበቀ ነው :: ወያኔ ያቋቋመውን ሲኖዶስ የማናምን ኢትዮጵያውያን ተዋህዶዎች ብዙ ነን :: የወያኔ ጳጳስና ካህናት ቡራኬ እርማችን ነው
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ፣ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ .ም፣ ማምሻውን በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት እየተካሄደ ነው፡፡ የዕርቀ ሰላም ውይይቱን በሚያስተባብረው የሰላም እና አንድነት ጉባኤ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ይኸው ሁለተኛ ዙር ንግግር ከየካቲት 4 - 9 ቀን 2004 ዓ .ም እንደሚቆይ ተገልጧል፡፡
ከየካቲት አራት ቀን ጀምሮ በዕርቀ ሰላሙ የመነጋገሪያ ሐሳቦች ላይ በሁለቱ አካላት ልዑካን ተወካዮች መካከል ሲካሄድ በቆየው የቅድመ ውይይት ንግግር ሰባት አጀንዳዎች ተለይተው ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ በተጀመረው ውይይት ዋነኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ የሚሆነው በአጀንዳ ተራ ቁጥር አንድ የተቀመጠው “ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተ” በሚል የተመለከተው ነጥብ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ አጀንዳ÷ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሡ በተደረገበት ሁኔታ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ወይስ አልተጣሰም ? የቅዱስነታቸው ቀጣይ ሁኔታስ ምን መሆን ይገባዋል ? የሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ባለው ሁኔታ ውይይቱ በመግባባት እየተካሄደ ስለመሆኑም የስብሰባው ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡ ከውዝግቡ በኋላ ስለተሾሙት ጳጳሳት፣ አንዱ በሌላው ላይ ስላስተላለፋቸው ውግዘቶች፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደረጉ የመንግሥት ጣልቃ ገብነቶች ተቋማዊ ነጻነት ስለማግኘት፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አሠራር እና የስምምነቶች አፈጻጸም እንዲሁም ስለ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያወሱት ቀሪዎቹ ስድስት አጀንዳዎች በዚህ ዙር ውይይት ይነሣሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የድሬዳዋ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ /ቤት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካን ቡድኑን በመምራት፣ የደቡብ ወሎ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በአባልነት፣ የአዲስ አበባ ሀ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ደግሞ በልዑካን ቡድኑ ፀሐፊነት በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያመሩት የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ .ም ነበር፡፡
በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሦስተኛው የልዑካን ቡድኑ አባል የሆኑት የሰሜን ምዕራብ ሸዋ -ሰላሌ ሀ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ አብረው አልተጓዙም፡፡ ብፁዕነታቸው ከየካቲት 2 ቀን ጀምረው በአዲስ አበባ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና በመከታተል ላይ ሲሆኑ ሕመማቸው የሳምባ ምች እና ስኳር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሆስፒታል ምንጮች እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት ብፁዕነታቸው ከሳምባ ምች ሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ከፍተኛ የስኳር መጠናቸውም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እና ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ እና መልአከ ገነት ገዛኸኝ የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
SOURCE
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የዘመኑ ልሳን Joined: 07 Jun 2005 Posts: 2930 Location: USA
Posted: Fri Feb 17, 2012 3:58 am Post subject:
ደብረብርሀን እኔ እንኳን የግሌን ሀሳብ ሳልጨምር ዜናውን እንደወረደ ነበር ያመጣሁት :: አንተን ቅር ያሰኝህ ሀሳብ ካለ እንኳን የእኔ ሳይሆን ዜናውን የጻፉት ሰዎች ነው ::
እኔ ከአንተ ጋር በዚህ ዙሪያ በአንድ ነገር ስማማለሁ :: ወያኔ ያለ አግባብ በታምራት ላይኔ በኩል እጋዊውን ፓትሪያርክ አውርዶ ሌላ ፓትሪያርክ እንዲሾም አስደርጓል :: ይህ ወያኔ በሀገሪቱ ከፈጸማቸው ትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው :: ፓትሪያርኩ ወደ ቦታቸው መመለስ እንዳለባቸውና ያለ አግባብ የተሾሙ አባ ጳውሎስ ህጋዊ ፓትሪያርክ እንዳይደሉ እዚህ ድረስ ካንተ ጋር እስማማለሁ ::
"ወያኔ ያቋቋመውን ሲኖዶስ " ስለምትለው ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም :: ወያኔ ገና ሳይመጣ የነበረ ሲኖዶስ ነው አሁንም ያለው :: ወያኔ ያለ አግባብ ፓትሪያርክ እንዲሾም አድርጓል እንጂ ሲኖዶስ አላቋቋመም :: ሲኖዶስ ግለሰቦች ሲሰደዱ የሚሰደድ ነገር አይደለም :: ለእኔ ኢትዮጵያዊ ጽናት ያላቸው ጳጳሳት የወያኔን ትንኩሳና ተጽህኖ ተቋቋመው በገጠርና በከተማ ህዝቡን እያገለገሉ ያሉት ጳጳሳት እንጂ እዚህ አሜሪካ በድሎት ያሉት በምን መዘዘኛ እንደዛ እንዳልካቸው አልገባኝም :: የፈለከውን የማለት መብት ስላለህ እዚህ ላይ ላብቃ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Fri Feb 17, 2012 5:05 am Post subject:
ሰላም ለሁሉም፡
ተድላ ለመረጃው አመሰግናለሁ ፣
ሞንሟናው ያቀረበልንን መረጃ አንብቤዋለሁ። እኔን የሚገርመኝ ነገር ግን ፣ የጥንት ቀኝ ገዥዎች ፡ ባሮቻቸውን አስጨንቀው ይገዟቸው የነበረው ፣ መረጃ በመንፈግ እና … ስለጌቶቻቸው አገዛዝ ትክክለኛነት ብቻ በመስበክ የነበረ ሲሆን ፣ አፍሪካ -አሜሪካውያን ነጻነታቸውን የተቀዳጁት ፣ ቤተ አምልኳቸው ውስጥ ተገናኝተው በመማማር ብቻ ነበር። እኛ ግን ፣ ስለወያኔ ከበቂ በላይ የሆነ መረጃ እያለን ፣ ዛሬም “ወያኔኮ የጥቂት ሆዳሞች ብቻ ስብስብ እንጅ ፣ ሁሉም ትግሬዎች አይደሉም” እያልን እራሳችንን እያጃጃልን እንኖራለን። ልብ እንበል … (ከአለማዊ እስከመንፈሳዊ ) በሁሉም መስክ በዘር ተደራጅተው አገሪቱን የያዟት የአናሳው የትግራይ ተወላጅ ሰዎች መሆናቸውን የተሟላ መረጃ ይዘን እየኖርን… ይህንኑ መረጃ ግን እራሳችን ምክንያት ፈጥረንለት እንክደዋለን።
እርቁን አስመልክቶ ፣
ቁምነገሩ ያለው… እንደኦርቶዶክስ አማኝነቴ እና እንደኢትዮጵያዊነቴ ፣ የዚህን እርቅ የመፈለጌን ያህል … ይህ እርቅ ፍጹም መፈጸም አይችልም። ፍጹም መታረቅ የማይችል ሃሳብን ለማስታረቅ መሞከር የማይቻል ነው። እንዴውም ከላይ የገለጽኋቸው የሃሳብ ልዩነቶች እጅግ ቀላልና መፈጸም የሚችሉ ናቸው። (1)ለምን ቢባል አቦነ መርቆሪዎስ “እሽ ታምሜ ነው የለቀቅሁት” ቢሉ ፣ ሃቁን የሚያቀው ህዝብ ከምን ይቆጥርዋል ? ‘ከምንም’ ያማ ቢሆን ትላንት “ወያኔን አጥፋቻለሁ ብላ ይቅርታ ጠይቃ ተፈታች” የተባለችውን ብርቱካን ዛሬ ኢትዮጵያዊው በክብር ባላስተናገዳት። (2) አባ ገብረመድህንም ፣ በስደት ያሉ ፖለቲከኞች ፣ አገራቸው ያለምንም ችግር የመግባት ፈቃድ ወያኔ ሰጥቷቸዋል ሊሉ ይችላሉ። (ወያኔስ የሚፈልገው ይህን አይደል እንዴ ?) እስኪ “ዛሬ ወደ አገሬ መመለስ ስለምፈልግ ይፈቅድልኝ” ብሎ “እያሱ አለማየሁ ወይም አረጋዊ በርሄ ወይም አብርሃም ያየህ ወይም… ) ለወያኔ ኢምባሲ ቢጠይቁ ፣ ወያኔ እጃቸውን ስሞ ተቀብሎ ለፕሮፖጋንዳ አይጠቀማቸውም ? (ተመልሰው ወደ ፖለቲካው ድርሽ እስካላሉበት ድረስ ?)
ቁምነገሩ ይሄ አይደለም ! በውጭ አገር ያሉት አባቶች “ሰላም አወረድን” ቢሉ ፣ ተከታዩ ነገር የሚሆነው ፣ በውጭ ያሉት አብያተክርስቲያናት ፣ ከሁለቱም ሲኖዶሶች እራሳቸውን አግልለው ቁጭ ይላሉ። ለምን ቢባል ፣ ወያኔ በውጭ ካሉት አባቶች የሚፈልገው አንዱ ፣ ከሁለቱም ያጡ አድርጎ ማስቀመጥ እንጅ ፣ አገራዊ እርቅ በሌለበት ሃይማኖታዊ እርቅን ፈልጎ ሊሆን አይችልም። ከዛም አልፎ ፣ የወያኔን ጸያፍ ተግባር በማውገዝ የሚታወቁትን በውጭ ያሉ አባቶች ድምጻቸውን የማፈን ፍላጎት ነው።
ዛሬ ዛሬ ፖለቲካው ጭምልቅልቅ ብሎ የሰከነ መሪ በተቃውሞው በኩል አለመኖሩ እንጅ ፣ ወያኔ እያደረገ ያለውኮ ማንነት የማኮሰስ ተግባር በብዙ አቅጣጫ ነው። ይቅርታን አስመልክቶ ምን ያህል ሸፍጥ እየሰራ እንደሆነ በየእለቱ እየታዘብነው ያለነው ነው። ልክ እንደይቅርታው ሁሉ ፣ በአገር አለመኩራት ፣ በዘረኝነት መታጠር ፣ በተቃዋሚው ወገን ተስፋ መቁረጥ ፣ ሃሳብን በመግለጽ ላይ ተስፋ መቁረጥ … እና መሰል ስብዕናን የሚንዱ ተግባራት መፈጸም ፣ የአምባገነኖች አንደኛው ክህሎታቸው ነው።
ታዲያ አሁን ደግሞ ፣ ለበርካታ ጊዚያት ሲደክምበት የነበረውና በከፊልም ቢሆን የተሳካለት ክርስቲያኑን በውጭ አገር የመከፋፈል ተግባሩ ፣ ይበልጥ ግቡን እንዲመታ አዲሱን መንገድ ተያይዞታል። ቀደም ብሎ እንደገለጽሁት ፣ በሲኖዶሱ ውስጥ ጥቂት የበቁ አባቶች በነጻነት ለቤተክርስቲያናቸው ሊታገሉ ይችላሉ ፣ ወያኔ ግን ይህንን ትግል (ሃይጃክ አድርጎ ) የሚጠቀመው ፣ ለራሱ ነው። ለምሳሌ የአባ ገብረመድህንን ሃውልት እንመልከት። ሲኖዶሱ “ይህ ሃውልት ቀኖና የጣሰ ስለሆነ ይፍረስ (ይነሳ )” አለ። ዛሬም ግን በወያኔ ተጠብቆ ይኖራል። የዚህ እንድምታ ምንድነው ? ያንን ሃውልት ለሚያይ ሰው ፣ ሲኖዶሱ ይህን የመወሰን ሃቅም እንዳለው አድርጎ ያሳምነዋል። ሃቁ ግን ሃውልቱ አለመፍረሱና የሲኖዶሱ ቃል ከቃልነት የማያልፍ መሆኑንም ነው። ይህ ትልቅ የስነ -ልቦና ቀውስን አይፈጥርም ብሎ የሚያምን ፣ እንደዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያለ ሰው ብቻ ነው። ለደካማው ትውልድ ግን የሚያስተላልፈው መልክት ፣ የአንድ አለማዊ ሰው ድንጋይ ከአንድ የቤተክርስቲያን እራስ ከሆነ ሲኖዶስ በላይ መሆኑን ነው።
ስለዚህ የወያኔ ትግል እጅግ ግልጽና ፊትለፊት የሆነ ሲሆን ፣ እኛ ግን እራሳችንን በሚያጭበረብር ምክንያት ሸብበን እንኖራለን። Alien Weisel, ስለናዚ ጭፍጨፋ በጻፈው Night በተሰኘው መጸሀፉ ውስጥ ፣ “ናዚዎች በሰውነታችን ያለንን ክብርና ማንነት ሁሉ ከውስጣችን ሲወስዱ ፣ ጭራሽ እንዳይወስዱብን እንጨነቅ የነበረው እግዚያብሄርን ከውስጣችን ነው” ብሏል። ወያኔም በሃቅሙ ፣ ከኢትዮጵያውያን ለመዝረፍ እየሞከረ ያለው ሌላው ሰይጣናዊ ስራው ፣ ፈሪሃ እግዚያብሄርንና በእግዚያብሄርም ተስፋ ማድረግን ነው።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሞካሪ Joined: 07 Sep 2006 Posts: 80
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Feb 19, 2012 8:33 pm Post subject: Re: የምስራች በኢ /ኦ /ተ /ቤ /ክን አንድነት ሊመጣ ነው
አሜን : እንደቃልህ አብይ ፆምን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ለትንሣኤ በዓል ያድርሠን ::
ስለዋናው ርዕስ ግን የመግለጫው ቃል የሚገኝበትን አድራሻ ከመለጠፍ በስተቀር ምንም ዓይነት አስተያዬት አልሠጠህም : ለምን ?
1 ..... Quote: "ልዑካኑ ከ 20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተን ተነጋግረናል :"
ብለዋል :: ታዲያ የእነርሱ ፊት ለፊት ቀርቦ መነጋገር ብቻውን መፍትሔ ያመጣል ?
2 ..... Quote: "የተነጋገርንባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች ቀኖና ቤተክርስቲያንና ብፁዑ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስን የሚመለከቱ ናቸው :: የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመመለስ ዕርቀ ሰላሙ መከናወን እንደሚገባው ተስማምተናል :: ይሁን እንጂ በጋራ ውይይታችን ላይ የኃሣብ ልዩነት ታይቷል ::"
ይህንን አንቀፅ በደንብ አበጥሮ መተንተን ያስፈልጋል :: ችግሩ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ጉዳይ ብቻ ነው ? የቤተ ክርስቲያን አንድነት ችግር ላይ የወደቀው ቀኖና ተጥሶ : በሕገ -ወጥ መንገድ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ መሾሙና የችግሩ ምንጭ አሁንም ያለው በሕገ -ወጡ ፓትርያርክ አባ ገብረመድህን ምክንያት መሆኑ እየታወቀ የችግሩ ምንጭ በተቃራኒው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ እንደሆኑ ተደርጎ እንዴት ውይይት ይደረጋል ? እንዲያውም የሰላምና ዕርቅ ኮሚቴ ተብዬው የወገነው ከአባ ገብረመድህን ወገን እንደሆነ ከአገላለፁ ይታወቃል :: እንደዚያም ሆኖ ተደራዳሪዎች ምንም ዓይነት ሥምምነት ላይ ያለመድረሣቸው ምን ያመለክታል ?
ስለዚህ እስከ ሐምሌ 2004 ዓ .ም . ድረስ ወያኔዎች ይህቺኑ እያመነዠኩ ሌላ ዙር የተንኮል ድራቸውን ሲያደሩ ይቆያሉ ማለት ነው ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4451 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Sun Feb 26, 2012 12:02 am Post subject:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-
ሠሞኑን ብዙ የተባለለት 'የዕርቅ ጉባዔ ' ምንም የተጨበጠ የሥምምነት ውጤት ሣይገኝበት በመጪው ሐምሌ ወር ለሌላ ዙር የፊት -ለፊት ውይይት ተቀጥሯል :: ለችግሩ መንስዔ ነው ተብሎ ስለሚታመንበት ጉዳይ ከእኛ ከኢትዮጵያውያን አልፎ የወያኔ አሣዳሪዎች ምን ዓይነት ዲፕሎማቲክ መልዕክት ይለዋወጡ እንደነበረ ከእስካሁኑ የ 'ዕርቅ ድርድር ' ጋር በማያያዝ አቢይ አፈወርቅ የሚከተለውን ጽሑፍ አቅርቦልናል ::
ምንጭ :- አቢይ አፈወርቅ : አቡጊዳ ድረ -ገፅ ላይ የተለጠፈ : ቅዳሜ የካቲት 17 ቀን 2004 ዓ .ም . :: የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች - በዊኪሊክስ ፋይሎች ::
Quote: ባለፈው ሳምንት የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ዜና ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገውን በአቡነ መርቆሪዎስ የሚመራውን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ /ክርስቲያን አዲስ አበባ ካለውና በተመሳሳይ መጠርያ በአቡነ ጳውሎስ ከሚመራው ቤ /ክርስቲያን ጋር ለማስማማት የተደረገው ጥረት ነበር። ሁለቱም ቤ /ክርስቲያናት ተወካዮቻቸውን ወደ አሪዞና ልከው መደራደራቸው ቢታወቅም የማይጣጣሙ ቅድመ ሁኔታዎቻቸውን እንደያዙ ለቀጣይ ውይይት በቀጠሮ ነበር የተለያዩት።
እኛም ዛሬ የሁለቱን ቤ /ክርስቲያናት ፍጥጫ በተመለከተ በዊኪሊክስ አማካኝነት የአሜሪካን ኤምባሲ ኬብሎች ላይ የቃረምናቸውን ጨምቀን እናቀርባለን።
ዊክሊክስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ የተለያዩ የኤምባሲው መልእክቶችን ይፋ ያወጣ ቢሆንም በተለይ ግን በሁለቱ ሲኖዶሶች ክፍፍል ዙሪያ ያተኮረባቸውን ሶስት በተለያዩ ጊዜያት የተላለፉ ሪፖርቶችን ብቻ ነቅሰን አውጥተናል። ሁለቱ ኬብሎች በፌብሪዋሪና በኤፕሪል 2007 ዓ .ም የተላለፉ ሲሆን አንዱ ደግሞ በጃንዋሪ ወር 2009 ዓ .ም ነበር ወደ ስቴት ዲፓርትመንት የተላከው።
በቅድሚያ ቤተክርስቲያኗ በሁለት የተከፈለችበትን መነሻ ምክንያት ለመፈተሽ ኤምባሲው ባደረገው ሙከራ ከሁለቱም ወገኖች የተንጸባረቁትን የተቃረኑ ሃሳቦች ያናጸሩበትን በወርሃ ፌብሪዋሪ የተላለፈውን ኬብል ጨምቀን እንደሚከተለው እንቃኝ።
“ፌብሯሪ 6 ቀን ሁለት የኤምባሲው ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ከሆኑት ከአቡነ ገሪማ እና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ከአቡነ ጢሞቲዮስ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል” ይላል ሪፖርቱ መግቢያውን ሲጀምር፦
“እነዚህ ሁለት የቤተ ክርስቲያኗ ሀላፊዎች በቤተ ክርስቲያኗ መሀል የተፈጠረው ክፍፍል አይነተኛ መነሻው 3ኛው ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሞቱበት ከ 1988 ዓ .ም የጀመረ ነው ባይ ናቸው። በወቅቱ 4ኛውን ፓትሪያርክ ለመመረጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሰናዳ አንዳንድ የደርግ ባለስልጣናት መርቆርዮስን ለማስመረጥ በሲኖዶሱ አባላት ላይ ተጽእኖ አድርገው ነበር፦ ሲሉ ይከሳሉ።”
እነዚህ ጳጳሳት የአቡነ ጳውሎስ መሾምንና ይህንኑ ተከትሎ አቡነ መርቀርዮስ የተሰደዱበትን ሁኔታ አስመልክተው የሰጡት ገለጻ ግን ከኤምባሲው የምርመራ ውጤቶች ጋር የማይጣጣም ሆኖ ተገኝቷል።
እነ አቡነ ገሪማ “…ህወሃት ደርግን አስወግዶ ስልጣን እንደያዘ አቡነ መርቆሪዮስ በጤና ችግር ምክንያት በሀላፊነቴ መቀጠል አልችልም ሲሉ ለሲኖዶስ አሳወቁ።” በማለት የአዲስ አበባዋን ቤተ ክርስቲያን ኦፊሺያል አገላለጽ ነበር ደግመው ያስተጋቡት።
በኢትዮጵያ ታሪክ አንድ ፓትሪያርክ በፈቃዱ ከሀላፊነቱ የተነሳበት ወቅት ኖሮ እንደማያውቅ ያስታወሰው የኤምባሲው ኬብል በተቃራኒው የቆሙትን የአቡነ መርቆሪዮስን ቡድን አቋም ደግሞ እንደሚከተለው አንስቶታል።
“ሲኖዶሱ አቡነ ጳውሎስን 5ኛው ፓትሪያርክ አድርጎ እንደመረጣቸው ሲገልጽ አቡነ መርቆሪዮስ ከ 4 ዋና ዋና ጳጳሳት ጋር በመሆን ከሀገሪቷ ተሰደዱ። ቆይተውም ከቤተ ክርስቲያኗ አመራርነት እንዲለቁ ከህወሀት ባለስልጣናት ማስፈራሪያና ጫና እንደተደረገባቸው ይፋ አደረጉ። አሜሪካ ሆነውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በስደት አቋቋሙ።
“አቡነ መርቆሪዮስ ትክክለኛው ፓትሪያርክ እሳቸው ብቻ መሆናቸውን ሲገልጹ የቤተ ክርስቲያኗ የቀኖና ህግ አንድ ፓትሪያርክ በህይወት እያለ እሱን አስወግዶ ሌላ ፓትርያርክ በላዩ ላይ መሾም አይፈቀድም። እኔን ግን በተጽእኖ አስወግደው ሌላ ሰው በላየ መጫናቸው ስህተት ነው።” በማለት ኮንነዋል።
ይህ የአቡነ መርቆሪዮስ ክስ ትክክለኛ መሆኑን ከሚያረጋግጡ መረጃዎች አንዱ ደግሞ ከሀላፊነታቸው እንዲወገዱ በተደረጉበት ሰዓት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ በጃንዋሪ 2009 ዓ .ም ለአምባሳደር ያማሞቶ የሰጡት ምስክርነት ነው።
አቶ ታምራት የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰውና ሀይማኖተኛ ሆነው ከእስር ቤት ከወጡ በሗላ በመጨረሻዎቹ ጊዜያት ሊሰሩ ያሰቧቸውን ተግባራት ለአሜሪካው አምባሳደር ዘርዝረው ነበር። ከዚህ መሀል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ።
“ኦሪጅናሉ ፓትሪያርክ ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ማዘዣው ላይ የፈረምኩት እኔ በመሆኔና ይህም ቤተ ክርስቲያኗን ለሁለት የከፈለ ሆኖ በመገኘቱ አሁን ሁለቱንም አስማምቶ አንድ ለማድረግ መሞከር እፈልጋለሁ።” አሉ።
ይህ ምስክርነት የአቡነ መርቆሪዮስ መወገድም ሆነ የአቡነ ጳውሎስ መሾም የፖለቲከኞች ውሳኔ መሆኑን ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ አቡነ ጳውሎስ ካለው መንግስት ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሰሩ በህዝቡም ዘንድ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ጥላቻ ያተረፉ ሰው ስለመሆናቸው በተለያዩ ቦታዎች ከቀረቡ የኤምባሲው ግምገማዎች ውስጥ ማስተዋል ይቻላል።
በአሁኑ ወቅት እንዳሉት አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባው ቤተ ክርስቲያን ሀላፊዎች ሁሉ ከትግራይ ብሔር የወጡ መሆናቸውን የሚያጣቅሰው የኤምባሲው የፌብሪዋሪ 2007 ዓ .ም መልእክት በሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት መሀል የነበረው ልዩነት እንዴት እየተባባሰ እንደኖረ በስፋት የዘረዘረ ሲሆን ዋና ዋናዎቹን ብቻ ነቅሰንና ጨምቀን እናያቸዋለን።
በ 1995 ዓ .ም የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን ከመርቆሪዮስ ጋር የተሰደዱትን 4 ጳጳሳት ማእረጋቸውን ሰርዣለሁ በማለት ቤተ ክርስቲያኗ ሰጥታቸው የነበረውን ስም ለሌሎች አራት አዳዲስ ተሿሚዎች መስጠቷን ገለጸች። የአቡነ መርቆሪዮስን ፓትሪያርክነት ግን በዚያን ወቅት ለመሰረዝ አልሞከረችም ነበር።
“ይህ በሆነ በተከታዩ አመት ደግሞ አቡነ መርቆሪዮስ አዲስ ቅዱስ ሲኖዶስ ከማቋቋማቸውም በላይ የቤተክርስቲያኗን መዋቅርም በአሜሪካ ውስጥ ዘረጉ። የሚለው ዊልገስ በተባለው የኤምባሲው ዲፕሎማት የተጠናከረው ሪፖርት ከ 1996 ዓ .ም ጀምሮ የሜይ 2005 ዓ .ምህረቱ ምርጫ እስከተካሄደበት ጊዜ ድረስ ሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት እምብዛም በአደባባይ ሳይካሰሱ መቆየታቸውን ይገልጻል።
እንዲያውም ከሁለቱ ፓትሪያርኮችና ቅዱስ ሲኖዶሶች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ባያበል ሙላቱ የተባለው ታዋቂ ባንከኛ ከኤምባሲው የፖለቲካ ኦፊሰር ጋር ፌብሪዋሪ 7 ቀን 2007 ዓ .ም ተገናኝቶ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያናት መሀል ኦፊሽያል ያልሆነ ግንኙነት ሲደረግ መቆየቱን መስክሯል።
“ከኤምባሲያችን ጋር ግንኙነት ያለው ባያበል ሙላቱ በሁለቱም ወገኖች መሀል ኦፊሽያል ያልሆነና በገለልተኛ ሰዎች መልእክት አስተላላፊነት የሚካሄድ ቋሚ ግንኙነት እንደነበር ነግሮናል። ይሁንና ውስጥ ለውስጥ መተቻቸታቸው ግን አልቀረም። የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን አዲሱ ቅዱስ ሲኖዶስ ህጋዊነት የለውም ስትል የአሜሪካዋ ደግሞ የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን የኢህአዴግ ተቀጽላ ሆናለች ስትል ነው የቆየችው።
ይህ በአቡነ ጳውሎስ የሚመራው ወገን ከህወሀት ኢህአዴግ ጋር የተገናኘ ነው የሚለው ክስ ደግሞ በህዝቡ ውስጥ ስር የሰደደ ተቀባይነት ያገኘ ስለመሆኑ በኬብሎቹ ውስጥ ተደጋግሞ ተገልጿል።
ለምሳሌ በአሜሪካ ያሉ ምእመናን በአብዛኛው የሚሄዱባቸውን ቤተ ክርስቲያናት የሚመርጡት ከፖለቲካ ስሜታቸው ጋር አገናዝበው ሲሆን የኢህአዴግ ደጋፊዎች በአቡነ ጳውሎስ ስር ወዳሉ ቤተክርስቲያናት ሲሄዱ አገዛዙን የሚቃወሙት ግን በአቡነ መርቆሪዮስ ወደሚመሩት ቤተ ክርስቲያናት ብቻ እንደሚሄዱ ተመልክቷል።
ይሁንና የ 2005ቱን ምርጫ ተከትሎ በአቡነ ጳውሎስ ላይ ጠንካራ ህዝባዊ ቁጣ በመቀስቀሱ አብዛኞቹ በሳቸው የሚመሩ ቤተ ክርስቲያናትን ደጋፊዎቻቸው ሳይቀሩ እርግፍ አድርገው እንደተዋቸው የኤምባሲው ጥንቅር ይገልጻል።
“ከ 2005 ዓ .ምህረቱ ምርጫ በሗላ የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን የገዛ ምእመኗን ለመከላከል ሳትሞክር በመቅረቷና ተቃዋሚዎችን የደገፉ አባላታ ላይ መንግስት የወሰደውን የሀይል እርምጃ ለማውገዝ እንኳን ያለመፍቀዷ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳባት።
“በአሜሪካ ያሉና በአቡነ ጳውሎስ ስር ይተዳደሩ ወደ ነበሩ ቤተ ክርስቲያናት ይሄዱ የነበሩ ደጋፊዎቻቸው መሀል አብዛኞቹ አመለካከታቸውን ቀይረው በአቡነ መርቆሪዮስ ስር ያሉ ቤተ ክርስቲያናትን ሙጥኝ አሉ። ይህም የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን በአሜሪካን ውስጥ የነበራትን ተከታይ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ አመነመነው።
“ሁኔታዋ ያሳሰባት የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን ጥለዋት የጠፉ የቀድሞ ተከታዮቿን ዳግም ለመማረክ በሚል ሶስት ታዋቂና ገለልተኛ የነበሩ ጳጳሳትን ሊቀ ጳጳሳት በማድረግ ወደ አሜሪካ ሸኘቻቸው። የተቆጣው ህዝብ ግን እነዚህን አዲስ ተሿሚዎች ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በመወገናቸው ምክንያት አገሸሻቸው።” የሚለው የኤምባሲው መልእክት በሁለቱም ወገን የቀጠለውን መናቆርና በየፊናቸው የወሰዷቸውን ርምጃዎች ይዘረዝራል።
የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን የአቡነ መርቆሪዮስን ፓትሪያርክነት ሰርዣለሁ ከማለቷና ከመገዘቷ አስቀድሞ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ያካተተ 20 ሰዎች ያሉበት ቡድን ለማደራደር ያደረገው ሙከራ መክሸፉን ያስታወሰው ሪፖርት ግዝቱን በተመለከተም ውስጥ አዋቂ የሆነውና ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለው ባያበል ሙላቱ ያቀረበውን ትችት አጣቅሷል።
“የሀይማኖት ማእረግን መግፈፍ ማለት ልክ አንድ ሰው ከፖለቲካ ስልጣኑ እንደማውረድ ቀላል አይደለም። ይህ ከአሁን በፊት ተወስዶ የማያውቅ ግዙፍ ርምጃ ነው። ምክንያቱም ሹመቱ የእድሜ ልክ ነውና።”ብሏል። ባያበል የእርቅ ሙከራውን በተመለከተ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በ 2ሺህ ዓመት ታሪኳ አይታው የማታውቀው አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባችው ይህንን በሁለቱ ወገኖች መሀል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ምንም እንኳን በርካታ ታዋቂ ሰዎች ቢጥሩም ሁኔታው ከመስከኑ በፊት እየባሰበት መሄዱ አይቀርም።” አለ።
እንዳለውም የአሜሪካኗ ቤተ ክርስቲያን በአጸፋ መልስ የአቡነ ጳውሎስን ፓትሪያርክነት ማእረግ ሰርዣለሁ በማለት ገዘተቻቸው። ከሁሉም በላይ የሚያስገርመው ግን በሀገር ቤት በነበሩ የተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗ ሀላፊዎች አማካኝነት በአደባባይ የወጡ መረጃዎች በተለይም የቤተ ክርስቲያኗን ሀብት እየዘረፉ በግል አካውንታቸው በማስገባትና የጠ /ሚ /ሩን የፖለቲካ ሀይል ተጠቅመው የሲኖዶሱን አባላት ሳይቀር በማስፈራራት ተግባራቸው የሚታወቁት አቡነ ጳውሎስ አሁንም በሰሜን አሜሪካ ያሉት የሀይማኖት አባቶች ጋር በአንድ በኩል ሰላም ለማውረድ እፈልጋለሁ እያሉ በሌላ በኩል ግን የፖለቲካ ጉልበት ተጠቅመው ለማጥቃት የጠነሱት ሴራ በኤምባሲው በኩል መጋለጡ ነው።
“የአዲስ አበባዋ ቤተ ክርስቲያን በኤምባሲያችን በኩል የአሜሪካ መንግስትን ርዳታ ለመጠየቅ ማሰቧን ተረድተናል።” የሚለው የኤምባሲው መልእክት፦
“በአሜሪካ ያለው ቤተ ክርስቲያን ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን’ የሚለውን ስም መጠቀም እንዳይችል እንድናግዳቸውና ዋና ዋናዎቹን የቤተ ክርስቲያኗን ሀላፊዎችም ወደ ኢትዮጵያ አስገድደን እንድንመልስላቸው ይፈልጋሉ።
“በእኛ በኩል በአዲስ አበባ ላሉት ፓትሪያርክና ለሲኖዶሱ ይህን መሰሉ ተግባር ህጋዊ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነና የባሰ ጉዳት ከማድረስ የማያልፍ እንደሆነ እናስረዳቸዋለን።” ይላል ወደ ስቴት ዲፓርትመንት የተላከው መልእክት።
ይህ ኬብል በማጠቃለያው ላይ ካሰፈረው አስተያየት መሀል ደግሞ የሚከተለው ይገኝበታል።
“የአዲስ አበባው ፓትሪያርክ የ 2005ቱን ምርጫ ተከትሎ የሀይል እርምጃና የጅምላ እስር በተፈጸመበት ወቅት የቤተ ክርስቲያን አማኞችን ለመከላክል ስላልሞክሩ ስር የሰደደ ጥላቻ አትርፈዋል። ምዕመናኑ ጋ ለመድረስም ይህ ነው የሚባል ጥረት አላደረጉም። በዚያ ላይ የጎላ ድምጽ ያላቸው በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ክፍፍሉን ተንተርሰው ጠ /ሚ /ር መለስንና መንግስታቸውን መኮነኛ ማድረጋቸው የፓትሪያርኩን ሚና ውስብስብ አድርጎባችዋል።
በሌላ የኤምባሲው ኬብል ላይ ደግሞ አቡነ ጳወሎስ ኤፕሪል 23 ቀን ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው ያደረጉት ውይይት በስፋት ተዘርዝሯል።
በዚህ ውይይት ወቅት “ኢትዮጵያ ትከሻው የሰፋ ታላቅ ወንድም ያስፈልጋታል” በማለት በአሜሪካ ላይ ያላቸውን መመካት የሚገልጹት አቡነ ጳውሎስ አሜሪካ ካሉት የሀይማኖት አባቶች ጋር ሰላም ለማውረድ በወቅቱ ስለተደረገው የድርድር ጥረት ተጠይቀው ነበር።
“ኢህአዲግ ስልጣን ሲይዝ በተፈጠረ ልዩነት ሳቢያ እሱና በአሜሪካ የሚኖሩ “ወንድሞቹ” ተከፋፍለው መቅረታቸው እንደሚቆጨው ነገረን። ይህንኑ የሚገልጽ መግለጫም በቅርቡ አሜሪካ ውስጥ እንዲወጣ ማድረጉን ጠቅሶ ይህም በስፋት እንደሚታመነው ሳይሆን አንድም ሰው ከኢትዮጲያ እንዲወጣ ያልተገደደ መሆኑን የሚገልጽ ነው አለን።” በማለት የሚጀምረው የኤምባሲው ሪፖርት ጳጳሱ ለድርድር ወደ አሜሪካ የላኳቸው አራት ሊቀ ጳጳሳት ሳይሳካላቸው ወደ አገር ቤት መመለሳቸውን አትቷል።
“ብዙ ሰዎች ለዚህ እኔን ነው ጥፋተኛ አድርገው የሚወቅሱኝ። ይሁንና አሁን የኔ ብቸኛ ፍላጎት ሁለቱን ቤተክርስቲያናት አንድ ማድረግ ነው። “ የሚሉት አባ ጳውሎስ በቅርቡ እሳቸው ራሳቸው አሜሪካንን የመጎብኘት ሀሳብ ይኖራቸው እንደው ሲጠየቁ ደግሞ፦
“እፈልግ ነበር። ይሁንና በአሜሪካው ቤተክርስቲያን ያሉ የተወሰኑ ሰዎች ይቃወሙኝ ይሆናል እንጂ።” ነበር ያሉት።
በአንድ በኩል “ከወንድሞቼ ጋር ተለያይቼ መቅረቴ ይቆጨኛል፣ ሰላም እንዲወርድም እፈልጋለሁ እያሉ በሌላ ጎኑ ደግሞ ‘ተቀናቃኞቼን አንቃችሁ አምጡልኝ’ በሚል ሴራ የሚማጸኑት አቡነ ጳውሎስ በስደት ካሉት አባቶች ጋር ለመስማማት ይህ ነው የሚባል በር ሲከፍቱ ታይተው አያውቁም።
ምንም እንኳን ኦርጂናሉ ፓትሪያርክ ህገ ወጥ በሆነ የፖለቲካ ውሳኔ መባረራቸውን በወቅቱ ትዕዛዙ ላይ የፈረሙበት አቶ ታምራት ላይኔ ሳይቀሩ ያረጋገጡት ጉዳይ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት የተሞከረው ድርድር በቀጠሮ ይቋጭ እንጂ የመሳካት ዕድሉ ግን የመነመነ ከመሰለባቸው ምክንያቶች ዓይነተኛው የአቡነ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን አቡነ መርቆሪዮስን “ከስልጣኔ የለቀቅኩት በህመም ምክንያት ወድጄ ነው።” ብለው እንዲዋሹ ቅድመ ሁኔታ በማቅረቧ መሆኑ ይታመናል።