WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ኢስላምን እንዲያውቁት (አርካኑል ኢማን /የእምነት ማዕዘናት )
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 36, 37, 38, 39  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሱባና ወስላታ

ዋና ኮትኳች

Joined: 10 May 2011
Posts: 628

PostPosted: Mon Jan 02, 2012 11:07 am    Post subject: Reply with quote

ቢስሚላሂ ዘመድኩን አስፈንድዶ በበዳው ውሻው አላህ ስም ሙሓመድ ሸርሙጣ ነው Laughing Laughing Laughing Laughing ቂቂቂቂቂቂቂቂቂ ቃቃቃቃቃቃቃቃ

እናታችሁ ሞታ ከሆነ ከመቃብር ቆፍራችሁ አውጡና ለዚያ አስከሬን ለሚበዳው ነቢያችሁ ስጡና በድቷት የጃን ልብስ አልብሶ ወደ አላህ ገሃነም ይላካት

ወሬ አታብዛ እናትህን ከመቃብር ቆፍረህ አውጣና ለዚያ ውሻ ነቢይህ ስጠውና በድቷት የሰማይ ቤት ልብስ አልብሶ ወደ አላህ ገሃነም ይላካት
I (Muhammad) put on her my shirt that she may wear the clothes of heaven, and I SLEPT with her in her coffin (grave) that I may lessen the pressure of the grave. She was the best of Allah s creatures to me after Abu Talib" The prophet was referring to Fatima , the mother of Ali.Narrated by ibn abbas. Sunan abu dawud book 2 Number 403 (Ali Sina Page 6 and Hadith 34424)
ይሄው ይህ ውሻ አላህ አፉን በድቶት አፍና ቂጡ ሲዋሽ ተመለከት ::

5a. A ishah said: The Apostle of Allah peace be upon him married her when she was six and had intercourse with her when she was nine. (Sunan Nas ai, Book of Marriage, no.3255)

5b. A ishah said: The Apostle of Allah peace be upon him married me when I was seven and had intercourse with me when I was nine. (Sunan Nas ai, Book of Marriage, no.3256)

5c. A ishah said: The Apostle of Allah peace be upon him married me when I was nine and I accompanied him for nine years. (Sunan Nas ai, Book of Marriage, no.3257)

5d. A ishah said: The Apostle of Allah peace be upon him married her when she was nine and died when she was eighteen. (Sunan Nas ai, Book of Marriage, no.3258)

5e. A ishah said: The Apostle of Allah peace be upon him married me when I was six and had intercourse with me when I was nine and I was playing with dolls. (Sunan Nas ai, Book of Marriage, no.3256)እናትህንም ከመቃብር አውጥተህ ስጠውና ይብዳት ከዚያ የሽኝት ልብስ ያልብሳትና ወደ አላህ ጋሃነም ይላካት

የወራዳው ከአስከሬን የተጨማለው ውሻ የሴይጣን ነብይ ጌታ
_________________
የሐዋርያት ሥራ 4:12 መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲስ

ኮትኳች

Joined: 18 Dec 2004
Posts: 216
Location: united states

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 7:34 am    Post subject: Reply with quote

Flame እንደጻፈ(ች)ው:
...ዝምድናን ማቋረጥ ከከባድ ኃጢአቶች እንደ አንዱ ተቆጥሯል :: ችግረኛ በሆነ ዘመድ ላይ አንድ ችግር ወይም አደጋ ቢደርስ የመርዳት አቅም ያላቸው ዘመዶቹ ለችግሩ የመድረስና እርዳታ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው :: በበጎ ፍቃድ ልገሳም ቤተዘመድ የሆነ ሰው ከሌላው የቅድሚያ መብት አለው ::

...4 አንድ ሰው ከሞት በኍላ ያፈራው ሀብት ባንድ ሰው እጅ ብቻ እንዳይከማችና እንዳይበሰብስ በማድረግ ዝምድና ያለው ሁሉ ድርሻውን መካፈል በሚችልበት ሁኔታ ኢስላም የውርስ ሕግ ደንግጓል :: ከሁሉም ይበልጥ የሚቀርቡ ዘመዶች ወንድ ልጅ : ሴት ልጅ : ሚስት : ባል : አባት : እናት : ወንድምና እህት ናቸው :: ስለዚህ ከሌሎች በፊት የነዚህ ዘመዳሞች በሸሪዓው ተብራርቷል :: ሁሉም ካልተገኙ ቀድሞት ያለውን ዘመድ ድርሻ : በቅደም ተከተሉ መሠረት ቀጥሎ ያለው ዘመድ ያገኛል :: በዚህ ዓይነትም የሟቹ ሃብት በብዙ ዘመዶቹ መካከል ይሰራጫል :: ይህ የኢስላም የውርስ ሕግ በጥንቱም ሆነ በዛሬው ዓለም ሕጎች ውስጥ እምነት የሚጣልበት ነው :: ዛሬ አንዳንድ ሕዝቦች በዚህ ሕግ ላይ የኢስላምን አርአያነት ማጤን ቢጀምሩም ሙስሊሞች ራሳቸው ባለማወቅና በጅልነታቸው ምክንያት ይህን ህግ የሚቃረን መደንገጋቸው በጣም የሚያሳዝን ነው :: በብዙ አካባቢዎች በተለይም በሀገራችን - ሴት ልጆችን ውርስ የመንፈግ በሽታ በሙስሊሞች መካከል ተዛምቷል :: ይህ ደግሞ አስከፊ ግፍና ግልጽ የሆነውን የቅዱስ ቁርኣን ውሣኔ መቃወም ነው :: ..

ሴት ልጅ ከወንድ የውርስ ድርሻ አንድ ሁለተኛውን (ግማሽ ) እንደምታገኝ ኢስላም ደንግጓል :: ለምን ? ለምሳሌ አንድ ሴት ልጅ አለች .... ስሟ ሠላም ይባላል :: ሁለት ወንድሞች አሏት :: አባታቸው በድንገት ሲሞት ትቶላቸው የሄደው ብር 2,500 አለ :: ሠልማ ከሁለት ወንድሞቿ ጋር በሸሪዓው ሕግ መሠረት ተካፈለች :: ወንድሞቿ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሺህ ብር ሲያገኙ እሷ የደረሳት ብር 500.00 ሆነ :: ወንድሞቿ ከደረሳቸው ውርስ ግማሹን ማለት ነው :: እዚህ ማጤን የሚገባን ጉዳይ አለ :: ሠልማ ከዚህ ድርሻዋ ላይ ምንም ዓይነት የቤት ወጪ የማውጣት ግዴታ የለባትም :: ከቤተሰቧ ጋር እያለች ሙሉ የቤት ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ የተጫነው በወንድሟቹ ወይም በአንድ ወንድሟ ወይም በቅርብ ወራሽ በሆነው ወንድ ልጅ ላይ ነው :: አግብታም ባሏ ቤት ስትገባ ሠልማ ሙሉ የቤትም ሆነ ለኑሮዋና ለሕይወትዋ አስፈላጊ የሆኑትን ወጪ የመሸፈን ኃላፊነት የሚሸከመው ባል ነው :: የሠልማ ውርስ (ብር 500) ከወንድሞቿ ጋር አባቷ ቤትም እያለች ሆነ ትዳር መስርታ ከባሏ ጋር ስትኖር ተቀማጭ ሀብቷ እንደሆነ ይቆያል ማለት ነው :: በውርስ ገንዘቧ እንዳሻት የመጠቀም መብቷም እንደተጠበቀ ይቆያል ::

...
ከቤተሰብ ግንኙነቶች ... Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Sun Jan 08, 2012 8:11 am    Post subject: Reply with quote

...- ከቤተሰብ ግንኙነቶች በኍላ ሰው ከወዳጆቹ : ከጎረቤቶቹ : ከመንደርተኞቹ : ከሀገሩና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብረው ከሚሳተፉ ሰዎች ጋር ግንኙነት ይፈጠራል :: እነዚህን በሙሉ በፍጹምነት : በእኩልነትና በመልካም ሥነ ምግባር እንዲቀርባቸው : በመጥፎ አነጋገርና በሚያስከፋ አባባል ከማስቀየሙ እንዲቆጠብ : ከነርሱ ጋር እንዲተጋገዝና እንዲረዳዳ : ሲታመሙ እንዲጎበኛቸው : ሲሞቱ እንዲቀብራቸው : በችግር ጊዜ እንዲካፈላቸው : ድሆቹን : ችግረኞቹንና አቅመ ደካሞቹን *በስውርና በይፋ እንዲረዳቸው : የሙት ልጆችንና ሚስቶችን በርህራሄ እንዲዛቸው : የተራበን እንዲያበላ : የታረዘውን እንዲያለብስ : ሥራ እንዲያገኝና ሠርቶ እንዲኖር : ሥራ አጥን እንዲደግፍ : አላሀ የለገሰውን ፀጋ ለመንደላቀቂያና ለመቀናጫ እንዳያውለው ኢስላም ያዛል ... Arrow

* ምንዳችሁን ላለማርከስ ችግረኛን በስውር እርዱት :: .የእርዳታ እጅ ስትዘርጉ በመመፃደቅ ሰው እንዲያያችሁ ለጉራና ለመታየት ብላችሁ አትፎልሉ :: ይሁንና ግልፅ የወጡ የጎዳና ተዳዳሪ ምስኪኖችን በይፋ መርዳት አይከለከልም :: ማለት በስውር የምትረዱበት ምክንያት የለም :: በስውር መርዳት ያለብን ሰው ማን ነው ? በአንድ ወቅት ስመ -ጥር የነበረ : ራሱን ችሎ በጥሩ የኑሮ እድገት ደረጃ ላይ የነበረ ሰው ግን የአምላክ ፍርድ ሆኖ የሚቀምሰው አቶ ከሰው እጅ እየተሸማቀቀ ....."ይሄ ሰው ጥንት ሃብታም እያለሁ ያቀኝ ይሆን ?" እያለ ተሳቆ ለመለመን ሲገደድ .......ዛሬ ቀን ጥሎት የሚቀምሰው ቢያጣ - ፊት ማሳጣት የለብንምና እንዲህ ዓይነቱን በስውር እርዱት ይላል ኢስላም ::

Arrow

ሠላም ቆዩን !

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Wed Jan 11, 2012 7:28 am    Post subject: Reply with quote

...ከወርቅና ከብር በተሠሩ እቃዎች መብላት : መጠጣትን : ከንፁህ ሐር የተሠሩ ልብሶች መልበሰን : ገንዘብን ለቅንጦትና ለመንደላቀቂያ ነገሮች ላይ ማባከንን : ሸሪዓው ሃራም አድርጓል :: ይኸውም ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ሀብት አንድ ግለሰብ ብቻ እንዳሻውና ፍላጎቱ እንዳዘዘው መጠቀምና መንጠባረር ተገቢ ባለመሆኑ ነው :: የብዙ ሺህ መብተኞች ሕይወት ማዳን የሚችለውን ሀብት በጌጥ መልክ አንድ ላይ ማንጠልጠል : በዕቃ መልክ ማኖር ወይም ቤት ውስጥ ማንጠፍ ወይም በመብራት መልክ ማባካን ከግፍ የሚቆጠር ነው :: ይህ ሲባል ደግሞ ኢስላም አንድ ሰው ያፈራውን ሀብት ሁሉ መንጠቅ ይፈልጋል ማለት አይደለም :: ሠርቶ ያፈራው ወይም ከወላጆቹ የወረሰው ሀብት ሁሉ ሕጋዊ ንብረቱ ስለሆነ በገንዘቡ መደሰት ይችላል :: በሚለብሰው ልብሱ : በምግቡ : በመኖሪያ ቤቱና በሚጠቀምበት ማጓጓዣው የአላህን ጸጋ ማንፀባረቅ ይፈቀድለታል :: የኢስላም ትምሕርቶች ዓላማ ግን አንድ ሰው መካከለኛ የሆነ ጥሩ ኑሮ እንዲኖርና ከመጠን በላይ መንደላቀቅን ማስቀረት : አላህ በሰጠን ጸጋ ሁሉ ለዘመዳችን : ለወዳጃችን : ለጎረቤቶቻችን : ለሀገር ልጆችና ለመላው የሰው ልጆች ያለብንን ሰብዓዊ ግዴታ መፈጸም ነው ::

...:- አሁን ደግሞ ከዚህ ጠባብ ክልል ወጥተን የመላውን ዓለም ሙስሊሞች ወደሚያጠቃልለው ሰፊ ክልል መግባት እንችላለን :: ኢስላም በዚህ ክልል ውስጥ ሙስሊሞች ሁሉ በበጎ ዓላማና የአላህን ትእዛዝ በመፈጸም ላይ እንዲተባበሩና እርስ በርሣቸው እንዲተጋገዙ የሚያደርጋቸው ሕጎችና ደንቦችን ደንግጓል :: በተቻለ መጠን መጥፎ ሥራዎችና አስከፊ ድርጊቶች በዓለም ላይ እንዲያንሰራሩ በፍጹም አይፈቅድም :: ቀጥለን ደግሞ ከነዚህ ሕጎች አንዳንዶችን እናያለን Arrow

ሠላም ቆዩን !www.ethioislamicart.com
http://www.peacetv.in/about.php
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Tue Jan 17, 2012 7:55 am    Post subject: Reply with quote

1...ለማህበራዊ ሥነ ምግባር ጥበቃ ሲባል ጋብቻን በሚከለክል ዝምድና የማይገናኙ ሴቶችና ወንዶች ነጻና ልቅ በሆነ መንገድ እንዳይቀላቀሉ : ሴቶች ከወንዶች በተለየ ቦታ እንዲኖሩ : የሴቶች ከፍተኛ ትኩረት ለቤተሰቡ ኑሮ አስፈላጊ የሆኑት ግዴታዎችን በመፈጸም ላይ እንዲያውሉ : ከቤታቸው መውጣት የግድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም አጊጠውና አብለጭልጨው እንዳይወጡ : ተራ የሆነ ልብሳቸውን ለብሰው አካላቸውን በሙሉ እጅና ፊታቸውን በጣም አስፈላጊ የሆነ ችግር ካልኖር በስተቀር ሙሉ በሙሉ ተሸፍነው እንዲወጡ ኢስላም ያዛል :: ይህም በሸሪዓው ውስጥ "ሂጃብ " ወይም "መሸፋፈን " በመባል የሚታወቀው ነው :: በሌላ በኩል ደግሞ ወንዶችም ከሚስቶቻቸው ውጭ ያሉትን ባዕድ ሴቶች ከማየትና ከማሽኮርመም እንዲጠነቀቁ : ሳይስቡ ዓይናቸው በሴቶች ላይ ካረፈ እይታቸውን ወድያውኑ እንዲለውጡና በድጋሚ እንዳይመለሱበት ኢስላም ያዛል :: ስለዚህም እያንዳንዱ /ወንድና ሴት / ሰው ሥነ ምግባሩን መጠበቅ ግዴታው ሲሆን በልቡ ውስጥ ቀለል ያለም ቢሆን ሕጋዊ ትዳርን በመተላለፍ ሥጋዊ ፍላጎቱን የማርካት ዝንባሌ እንዲፈጥርበት ዕድል መስጠት እንኳ አይገባውም ::

2... ማህበራዊ ሥነ ምግባርን ለመጠበቅ ሲባል ወንድ ከእንብርቱ እስከ ጉልበቱ ያለውን የገላውን ክፍል እንዳይገልጥ : ሴት ደግሞ ከፊቷና ከመዳፎቿ በቀር የተቀሩትን የአካሏን ክፍሎች እንዳትገልጥ ኢስላም ከልክሏል :: ይህም በሸሪዓው ውስጥ 'ሲትር " ወይም "ሽፋን " /ገበና ሽፋን " በመባል ይታወቃል :: ማንኛውም ወንድና ሴት ይህን የአለባበስ ደንብ የመከተል ጥብቅ ግዴታ አለበት :: በዚህም በሰዎች መካከል የማፈር ስሜት እንዲጸነስ : ሰውን በመጨረሻ ወደ ልቅነትና የሥነ ምግባር መዳሸቅ የሚጎትቱ መጥፎና አስከፊ ድርጊቶች እንዳይዛመቱ በማለም ነው ኢስላም ይህን የደነገገው ::

3.. Arrow

ሠላም ቆዩን !

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Mon Jan 23, 2012 8:11 am    Post subject: Reply with quote

3...ኢስላም የሰውን ምግባር የሚያበላሹ ወራዳ ፍላጎቶቹን የሚቀሰቅሱ : ጊዜውን : ጤንነቱንና ገንዘቡን በከንቱ የሚያባክኑ የጭፈራና የጨዋታ ዓይነቶች ሁሉ አይወድም :: ጨዋታ በመሠረቱ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው :: የሰውን መንፈስ ለማደስና የመሥራት ብቃቱን ከፍ ለማድረግ : ለማነቃቃትና : ለማዝናናት : ከሥራ ትጋት ጋር የግድ አስፈላጊ ነው :: ታዲያ ንቃት የሚያስገኝ መንፈስን የሚያረካ ጨዋታ መሆን አለበት እንጂ መንፈሱን የሚያስጨነቅና ውጥረት የሚያስከትል ጨዋታ መሆን የለበትም :: ወንጀሎች እንዲፈጽሙ የሚጋብዙ : ብዙ ሺህ ሰዎች ተሰብስበው የሚመለከቷቸው ዝቃጭ እይታዎች : ወሲብ ነክ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቁ ጭፈራዎች ለልቅነትና ለሥነ ምግባር ብልሽት የሚያዘጋጁ ሰው ሰራሽ ትእይንቶች ላይ ላዩን የሚያስደስቱና ጥሩ መልክ ያላቸው መስለው ቢታዩም እንኳ የሕዝቦች ሥነ ምግባርና ባህላቸውን የሚያበላሹ መቅሰፍት ናቸው ::

4...የሙስሊሞችን አንድነትና ማህበራዊ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እርስ በርሳቸው መከፋፈልን እንዲጠነቀቁ : ቡድናዊነትና ልዩነት ከሚያስከትሉ ምክንያቶች እንዲርቁ ኢስላም በጥብቅ አዟል :: በአንድ ነገር ላይ ከተለያዩ ጉዳዩን ወደ አላህ መጽሐፍ -ቅዱስ ቁርኣን -ወደ ነብዩ ሙሐመድ /../ ሐዲስ ውሣኔ በፍጹምነት : በጠራ ቅን ልቦና እንዲመለሱ : በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነት ካልተገኘ ግን ጉዳዩን ለአላህ በመተው እርስ በርስ ከመፋጨት እንዲቆጠቡ : በማህበራዊ ደህንነትና መድህን በሆኑ ትሩፋት ሥራዎች ላይ እንዲረዳዱ : የመሪዎቻቸውን ትእዛዝ እንዲያከብሩ : ከተንኮልና ከፈተና ሰዎች እንዲርቁ : ኃይላቸውን እንዳያዳክሙና ሕዝባቸውን በውስጣዊ የርስ በርስ ጦርነት እንዳያጋልጡ ኢስላም አበክሮ ያሳስባቸዋል ::

5... Arrow

ሠላም ቆዩን !

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Wed Jan 25, 2012 8:47 am    Post subject: Reply with quote

1...ለማህበራዊ ሥነ ምግባር ጥበቃ ሲባል ጋብቻን በሚከለክል ዝምድና የማይገናኙ ሴቶችና ወንዶች ነጻና ልቅ በሆነ መንገድ እንዳይቀላቀሉ : ሴቶች ከወንዶች በተለየ ቦታ እንዲኖሩ : የሴቶች ከፍተኛ ትኩረት ለቤተሰቡ ኑሮ አስፈላጊ የሆኑት ግዴታዎችን በመፈጸም ላይ እንዲያውሉ : ከቤታቸው መውጣት የግድ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም አጊጠውና አብለጭልጨው እንዳይወጡ : ተራ የሆነ ልብሳቸውን ለብሰው አካላቸውን በሙሉ እጅና ፊታቸውን በጣም አስፈላጊ የሆነ ችግር ካልኖር በስተቀር ሙሉ በሙሉ ተሸፍነው እንዲወጡ ኢስላም ያዛል :: ይህም በሸሪዓው ውስጥ "ሂጃብ " ወይም "መሸፋፈን " በመባል የሚታወቀው ነው :: በሌላ በኩል ደግሞ ወንዶችም ከሚስቶቻቸው ውጭ ያሉትን ባዕድ ሴቶች ከማየትና ከማሽኮርመም እንዲጠነቀቁ : ሳይስቡ ዓይናቸው በሴቶች ላይ ካረፈ እይታቸውን ወድያውኑ እንዲለውጡና በድጋሚ እንዳይመለሱበት ኢስላም ያዛል :: ስለዚህም እያንዳንዱ /ወንድና ሴት / ሰው ሥነ ምግባሩን መጠበቅ ግዴታው ሲሆን በልቡ ውስጥ ቀለል ያለም ቢሆን ሕጋዊ ትዳርን በመተላለፍ ሥጋዊ ፍላጎቱን የማርካት ዝንባሌ እንዲፈጥርበት ዕድል መስጠት እንኳ አይገባውም ::

2... ማህበራዊ ሥነ ምግባርን ለመጠበቅ ሲባል ወንድ ከእንብርቱ እስከ ጉልበቱ ያለውን የገላውን ክፍል እንዳይገልጥ : ሴት ደግሞ ከፊቷና ከመዳፎቿ በቀር የተቀሩትን የአካሏን ክፍሎች እንዳትገልጥ ኢስላም ከልክሏል :: ይህም በሸሪዓው ውስጥ 'ሲትር " ወይም "ሽፋን " /ገበና ሽፋን " በመባል ይታወቃል :: ማንኛውም ወንድና ሴት ይህን የአለባበስ ደንብ የመከተል ጥብቅ ግዴታ አለበት :: በዚህም በሰዎች መካከል የማፈር ስሜት እንዲጸነስ : ሰውን በመጨረሻ ወደ ልቅነትና የሥነ ምግባር መዳሸቅ የሚጎትቱ መጥፎና አስከፊ ድርጊቶች እንዳይዛመቱ በማለም ነው ኢስላም ይህን የደነገገው

3...ኢስላም የሰውን ምግባር የሚያበላሹ ወራዳ ፍላጎቶቹን የሚቀሰቅሱ : ጊዜውን : ጤንነቱንና ገንዘቡን በከንቱ የሚያባክኑ የጭፈራና የጨዋታ ዓይነቶች ሁሉ አይወድም :: ጨዋታ በመሠረቱ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው :: የሰውን መንፈስ ለማደስና የመሥራት ብቃቱን ከፍ ለማድረግ : ለማነቃቃትና : ለማዝናናት : ከሥራ ትጋት
ጋር የግድ አስፈላጊ ነው :: ታዲያ ንቃት የሚያስገኝ መንፈስን የሚያረካ ጨዋታ መሆን አለበት እንጂ መንፈሱን የሚያስጨነቅና ውጥረት የሚያስከትል ጨዋታ መሆን የለበትም :: ወንጀሎች እንዲፈጽሙ የሚጋብዙ : ብዙ ሺህ ሰዎች ተሰብስበው የሚመለከቷቸው ዝቃጭ እይታዎች : ወሲብ ነክ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቁ ጭፈራዎች ለልቅነትና ለሥነ ምግባር ብልሽት የሚያዘጋጁ ሰው ሰራሽ ትእይንቶች ላይ ላዩን የሚያስደስቱና ጥሩ መልክ ያላቸው መስለው ቢታዩም እንኳ የሕዝቦች ሥነ ምግባርና ባህላቸውን የሚያበላሹ መቅሰፍት ናቸው ::

4...የሙስሊሞችን አንድነትና ማህበራዊ ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እርስ በርሳቸው መከፋፈልን እንዲጠነቀቁ : ቡድናዊነትና ልዩነት ከሚያስከትሉ ምክንያቶች እንዲርቁ ኢስላም በጥብቅ አዟል :: በአንድ ነገር ላይ ከተለያዩ ጉዳዩን ወደ አላህ መጽሐፍ -ቅዱስ ቁርኣን -ወደ ነብዩ ሙሐመድ / . . / ሐዲስ ውሣኔ በፍጹምነት : በጠራ ቅን ልቦና እንዲመለሱ : በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነት ካልተገኘ ግን ጉዳዩን ለአላህ በመተው እርስ በርስ ከመፋጨት እንዲቆጠቡ : በማህበራዊ ደህንነትና መድህን በሆኑ ትሩፋት ሥራዎች ላይ እንዲረዳዱ : የመሪዎቻቸውን ትእዛዝ እንዲያከብሩ : ከተንኮልና ከፈተና ሰዎች እንዲርቁ : ኃይላቸውን እንዳያዳክሙና ሕዝባቸውን በውስጣዊ የርስ በርስ ጦርነት እንዳያጋልጡ ኢስላም አበክሮ ያሳስባቸዋል

(የመጨረሻው ክፍል ቀጥሏል ..)
5...ሙስሊሞች ሳይንስና ስነጥበብን እንዲቀስሙ : ሙስሊም ካልሆኑት ወገኖች ጠቃሚ የሆኑ መንገዶችን እንዲገበዩ ተፈቅዶላቸዋል :: በግላዊ አኗኗራቸው ግን እንሱን እንዳይመስሉ ተከልክለዋል :: የራሱን ትቶ ሌላውን መምሰል የሚፈልግ ሕዝብ በራሱ ላይ ዝቅተኛነትን : ውርደትን : ድክመትን የሚቀበል የሌሎችን ቀደምትነት : ኃያልነትና ምጥቀት በአምልኮት የሚቀበል ሕዝብ ብቻ ነው :: ይህ ደግሞ ከሁሉም የከፋ ዝቃጭ ባርነት ነው :: ውርደትና ውድቀትን መቀበል ነው :: ውጤቱም የተከታዩ ጀሌ ሕዝብ ባህልና ስልጣኔ ውድመት ነው :: በዚህ ምክንያት ነው ነብዩ ሙሐመድ /../ ባዕድ ሕዝቦችን መከተል : ባህልና የአኗኗር ስልታቸውን መምረጥ አጥብቀው የከለከሉት :: የማንኛውም ሕዝብ ኃይል በአለባበስ ወጉና በአኗኗር ስልቱ ላይ የሚመሠረት ሣይሆን ባለው ዕውቀት : ባለው የድርጅትና የቅንብር ጥራትና በሥራ ብቃቱ ላይ መሆኑን ትንሽ እንኳ ማሰብ የሚችል ሁሉ ይገነዘበዋል :: ኃይል : ሙሉነትና ምጥቀት የሚፈለግ ሰው ለሃያልነቱ : ለምጥቀቱና ለብቃቱ መንስኤ የሆኑትን ከባዕድ ሕዝቦች ይቅሰም እንጂ ሕዝብን አዋርዶ : ሉአላዊነቱን አውርዶ ወደ ባዕድ ሕዝቦች ተጽእኖ ሥር በማንበርከክ በመጨረሻ ሕልውናውን ወደሚያሳጣው መንገድ አያዘንብል ::

ሙስሊም ያልሆኑትን ሰዎች በአድሏዊነትና በጠባብነት ዓይን እንዳይመለከቱ : አማልክቶቻቸውን እንዳይዘልፉ : ሙሀዎቻቸውን እንዳይወቅሱ : እምነታቸውን እንዳያንቋሽሹ ሸሪዓው ሙስሊሞችን በጥብቅ አሳስቧል ::

ሐቁን ለመናገር በዘር : በብሔር ወይም በቆዳ ቀለም ላይ በመመርኮዝ ሰውን ከሰው የሚለዩ ሸሪዓዎችና እምነቶች በሙሉ የዩኒቨርሳል ሸሪዓ መሆን አይችሉም :: የዚህ ዘር አባል የሌላውን አባል መሆን እሱነቱን ማጥፋት በፍጹም አይችልም :: የዓለም ሕዝቦች በሙሉ ተሰብስበው ያንድ ዘር ያንድ አገር ሰዎች መሆን እንደማይችሉ በጣም ግልጽ ነው :: የአፍሪቃዊው ጥቁረት የቻይናው ቢጫነት ወይም የፈረንጁ ንጣት ተፈጥሮ ነውና ሊለወጥ አይችልም :: በዚህ የሚያምኑ ሃይማኖቶች ከሕዝቦች መካከል በአንድ የተለየ ሕዝብ ዘንድ ብቻ ነው መፈጠርና መኖር የሚችሉት :: ባንፃሩ ኢስላም ደግሞ ዓለም አቀፋዊ የሆነ ዘለዓለማዊ ሸሪዓውን ይዞ የመጣ ስልሆነ "ላኢሏህ ኢለሏህ " በሚለው ቃልተውሂድ ያመነ ሰው ሁሉ የሙስሊሙ ሕዝብ አንድ አካል ሆኖ የተቀሩት ሙስሊሞች የሚያገኙትን መብቶች ሁሉ ያላንዳች ልዩነት ማግኘት ይችላል :: በዚህ ሸሪዓ ውስጥ የዘር : የቋንቋ : የሀገር ወይም የቀለም ልዩነት በፍጹም ቦታ የለውም :: ሸሪዓውም ዘለዓለማዊ ሸሪዓ ነውና ድንጋጌዎቹ በአንድ በተወሰነ ሕዝብ ልማድ ወይም የተለየ ዘመን ላይ የተመረኮዘ ሣይሆን በሰው ልጅ ተፈጥሮ መርህ ላይ የታነጸ ነው :: ይህ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በማንኛውም ዘመንና ሁኔታ ነዋሪ በመሆኑ በዚህ ላይ የተመሠረቱት ሕግጋትም በሁሉም ዘመንና ሁኔታ ቋሚና ነዋሪ ናቸው ::

...............................ተፈጸመ ................................................

ሠላም ቆዩን !

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Sat Feb 04, 2012 9:19 am    Post subject: Reply with quote

ባለን መርካት : ፈጣሪያችን በሰጠን ጸጋ መደሰትና ማመስገን መቻል : ማንነታችንንና ዙሪያችንን አምኖ መቀበል ታላቅ የሕይወት መመሪያ ነው :: ይህ ነው የደስታ ምንጭ :: ሕይወት በቃኝ አትልምና የሰው ልጅ ባገኘውና ፈጣሪ በለገሰው ሁሉ ደስተኛ መሆን መቻልን አስቀድሞ ሲያውቅ ነው በተረጋጋ መንፈስ ኑሮውን በመምራት የሚሻሻለው :: ኑሮህን እያማረርክ : የሌላውን ሰው ሕይወት እየተከታተልክ አይደለም መሻሻልና ማደግ የሚመጣው :: ከሁሉም በላይ ባለን መርካት የምንችለው ልባችን ከፈጣሪያችን ጋር ተዋሕዶ : በሃይማኖት ሲደነድን : እንዲሁም እውነተኛ አማኞች ስንሆን ነው :: ያኔ ነው ባለን የመደሰት ምስጢር ምን ያህል ሕይወታችንን እንደሚያረጋጋ የምንገነዘበው :: የዲታዎችን ኑሮ ዘወትር የሚከታተል ወይም የሚመኝ እንደምን ደስተኛና የተረጋጋ መልካም ሕይወት ያገኛል ? በአንፃሩ የበታቾቹን እያየ : እየጸለያለቸው : ባለው ተደስቶ ተመስገን ፈጣሪ የሚል ፈጣሪ ይጨምረዋል ...ይረዝቀዋል :: ደስተኛም ይሆናል ::

በጣም የሚስበኝ አንድ የቻይናዎች ምሳሌ በእንግሊዝኛ እንዲህ ይነበባል :- .

"I complained I had no shoes until I met a man who had no feet."

በዉቡ አማርኛችን
"ጫማ የለኝም ብዬ ሳለቅስ እግር የሌለውን አይቼ ተጽናናሁ "

"ኢስላምን እንዲያውቁት " አጭር ቀጣይ ጽሁፍ እስክንገናኝ ሠላም ቆዩ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Tue Feb 07, 2012 7:49 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን /አሰላማሊኩም
ውድ የሀገር ልጆች በተለይ ፍሌምና ዘይነባ ስነምግባርን የሚገነባ ውይይታችሁን አደንቃለሁ ::ያለኝ ይበቃኛል የሚለውም ቃል ለክርስቲያኖች ሀዋርያዊ ቃል የተሰጠን ነው ::
እንዲህ ደርዝ ያለው ውይይት በሁሉም ዋርካዊያን ሊበረታታ ይገባዋል ::በትክክል የሙስሊም እህቶቻችን የተከበረ ገላቸውን መሸፈን በጣም እደግፋለሁ ያንን የክርስትና እምነትም ይደግፈዋል እነደእናታችን ሳራ እያለ ::ከዚህ በተረፈ የእኔ ጥያቄ የሽሪያ ህግ ነው :: በሀገራችን ሙስሊም ሴት አማራጭ ይሰጣት የሚለውን አዋጅ አከብራላሁ ::አያድርስ እንጂ በፍቺ ጊዜ ሴቲቱ አብራ ከደከመችበት እኩል የመካፈል መብቷን ማጣት አይገባም ::የሙስሊም ወንዶች ጭምር የንጽህና አጠባበቅን ሊመሰግን እንጂ በደንቁርና ባህል ሊያስደብ አይገባም ::

ዲጎኔ ሞረቴው ተሀድሶ ጸሎት ቤት ቃጥባሬ መስጂድ ፊትለፊት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Sat Feb 11, 2012 9:39 am    Post subject: Reply with quote

ዲጎኔ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለሁላችን ይሁን /አሰላማሊኩም
ውድ የሀገር ልጆች በተለይ ፍሌምና ዘይነባ ስነምግባርን የሚገነባ ውይይታችሁን አደንቃለሁ ::ያለኝ ይበቃኛል የሚለውም ቃል ለክርስቲያኖች ሀዋርያዊ ቃል የተሰጠን ነው ::
እንዲህ ደርዝ ያለው ውይይት በሁሉም ዋርካዊያን ሊበረታታ ይገባዋል ::በትክክል የሙስሊም እህቶቻችን የተከበረ ገላቸውን መሸፈን በጣም እደግፋለሁ ያንን የክርስትና እምነትም ይደግፈዋል እነደእናታችን ሳራ እያለ ::ከዚህ በተረፈ የእኔ ጥያቄ የሽሪያ ህግ ነው :: በሀገራችን ሙስሊም ሴት አማራጭ ይሰጣት የሚለውን አዋጅ አከብራላሁ ::አያድርስ እንጂ በፍቺ ጊዜ ሴቲቱ አብራ ከደከመችበት እኩል የመካፈል መብቷን ማጣት አይገባም ::የሙስሊም ወንዶች ጭምር የንጽህና አጠባበቅን ሊመሰግን እንጂ በደንቁርና ባህል ሊያስደብ አይገባም ::

ዲጎኔ ሞረቴው ተሀድሶ ጸሎት ቤት ቃጥባሬ መስጂድ ፊትለፊት

ሠላም ያገር ልጅ ዲጎኔ :: ሠላምና ጤና የዘወትር ቀለብህ ይሆኑ ዘንድ እምኝልሃለሁ ::

በኢስላም ጋብቻ ሲመሰረት ብዙ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ :: (በዚሁ ዓምድ ላይ በዝርዝር መጻፌን አስታውሳለሁ ) በማህብረሰቡ ውስጥ ተመጣጣኝ ተጓዳኞች ከሚለው ጀምሮ ምስክሮችን ጨምሮ ከሁሉቱም ወገን ተወካይ በተገኙበት የሚካሄድ "ውል " ነው :: ውል ደግሞ ሲፈርስ ውሉን ማን አፈረሰ ? ለምንስ ፈረሰ የሚለውን መርምሮ እንጂ መብት ለማስጠብቅ ሲባል ብቻ በዳዩን አመንሽንሾ አይሽኝም :: የሌላውን መብት ስሸረሽር የእኔ መብት መጠረጉን ማወቅ አለብኝ :: የጋብቻ ውል ሲፈጸም በቂ ምስክሮች እንዳሉ ሁሉ ሲፈርስም ከሁሉቱም ወገን የሚገቡ ተወካዮች አሉ ::

ፍቺን በሚመለከት የሴት ልጅ መብት ምን ይመስላል የሚለውን ለመረዳት በቀጥታ ወደ ሸሪዓው በመሄድ ለመረዳት መሞክር ይመረጣል :: ኢትዮጵያም ያሉ የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ሙስሊም ሴት ስትፈታ መብቷና ድርሻዋን አጠያይቀህ ለመረዳት ሞክር :: የምዕራባውያኑ የፍቺ ኮንሰብት እንዳይብስህ ጠንቀቅ በል :: (በፈረንጆች አቆጣጠር ) አብራ ያፈራችውን የባሏን ሃብት ለመካፍል ስትል ብቻ በውሃ ቀጠነ ፍቺ የምትጠይቅ ሴት መብቷ ተጠበቀላት ብለን የምናስበው ምኑ ነው ?
divorce could be good business እኮ ..አይመስልህም ?

ጋብቻ በሁለት የሚጣጣሙና የሚስማሙ ተቃራኒ ጾታዎች መካከል የሚደረግ ውል ነው የሚለውን እናስብበት :: ከዚያ ደግሞ marriage contract breaker የውሉ አፍራሽ ማነው ..ምክንያቱስ የሚለውን በማየት : እንዲሁም አብረው ሆነው ያፈሩትን ሁሉ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው ፍቺ የሚካሄደው -በኢስላም :: ባዶዋን ትባረራለች የሚል የኢስላም ሸሪዓ የለም :: በተለይ ልጆች ካላትና መሄጃ ከሌላት ሕጉም : ሕብረተሰቡም : ኮመን ሴንሱም የባሏን ቤትና ንብረት እንድትካፈል ያዛል :: ልብ በል የጋብቻ ውሉን ያፈረሰው ማነው የሚለው ላይ ለምሳሌ በወላጆቿ ሃብት ተመክታ ያላንዳች መንስኤ ፍቺ የምትጠይቀዋ ቀብራሪት ደግሞ እንኳን ለመካፈል ባልዋ ለጋብቻ ያወጣላትን እንድትመልስለት ሁሉ ሸሪዓው የሚያዝበት ሁኔታ አለ :: ባሏን የምትበድል ሚስት የለችም አንልም :: በደል የምታደርስ ሚስትም እንኳ እሷ በእራሷ አነሳሽነት ፍቺ እስካልጠየቀች ድረስ ባዶዋን አትወጣም :: ክህደትና እምነት ማጉደል የሚታይበት ጋብቻስ ? ለዚህ ነው ማን ነው ፍቺ ጠያቂ ? ለምን ? የሚለውን መርምሮ ነው ሸሪዓው የሚበይነው የምልህ :: በተለይ እምነትና ክህደት ያደረሰ ጋብቻውን ብቻ ሳይሆን እራሱንም ይከሰራል :: እዚህ ላይ ጎዝ ዊዝ ሀፍ ኦፍ ኢቲ ብሎ ነገር አለ እንዴ ? ባል ግዴታውን ያልተወጣና ኃላፊነቱን የዘነጋ መሆኑን አስመስክራ ሚስት ፍቺ ከጠየቀች ሸሪዓው እንዲሁ ለሚስት የሚጠብቅላት ድርሻ አለ ::

ባል የቤተሰብ መሪ ነው :: ቤተሰቡን የማስተዳደርና የመምራት ኃላፊነት አለበት :: በዚህ ቤተሰባዊ ሕይወት ጉዞ ባል ለበቂ ምክንያት የበላይነት የለውም አልልህም :: ሁለት የበላይ ባንድ ቤተሰብ ውስጥ መኖር አያስማማም :: ማለት አይመካከሩም ማለት አይደለም :: ማለት ሚስት ተሰሚነት የላትም ማለትም አይደለም :: ባል እንዳሻው በካልቾ ብሎ ሚስቱን ያላንዳች ሀቅና መብት ያባራል የሚል ኢስላማዊ ሸሪዓ የለም :: ይቺ የምትባረረዋ ሚስት እኮ እህት : ልጅና እናትም ናት - ለባል :: እስኪ አስበው ሸሪዓውንም በዐረብኛ አንብበውና ተረድተው ብይን የሚሰጡት ዳኞች እንዲሁ ሴት ልጅ :: እህትና እናት አላቸው .....የምልህ ቢያንስ እናት የሌለው ወንድ የለም :: ኢስላም ሴትን አይጨቁንም :: ምናልባት ትዕቢተኛና ጋጠ ወጥ ወንድ ሴትን ይጨቁን ይሆናል - በሃይማኖት ሽፋን ::

ሠላም ቆዩን !

"And when you divorce women and they fulfil their term [of their 'Iddah], either keep them according to reasonable terms or release them according to reasonable terms, and do not keep them, intending harm, to transgress [against them]. And whoever does that has certainly wronged himself. And do not take the verses of Allaah in jest. And remember the favour of Allaah upon you and what has been revealed to you of the Book [i.e., the Quran] and wisdom [i.e., the Prophet's Sunnah] by which He instructs you. And fear Allaah and know that Allaah is Knowing of all things." [Quran 2:231]Last edited by Flame on Sun Feb 12, 2012 7:03 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Wed Feb 15, 2012 9:04 am    Post subject: ኢስላምና ሙስሊሞች Reply with quote

1. ኢስላምና ሙስሊሞች

ኢስላም የሃይማኖት ስም ነው :: ሥርወ ቃሉም "ሲልም " ወይም "ሰላም " የሚል ሲሆን ትርጉሙም ሰላም ማለት ነው :: ሰላምታ ለመለዋወጥ ሰላም ማለት ደግሞ : ሰላምን መመኘት ሊሆን ይችላል :: ከፈጣሪ ውብ ሥሞች አንዱ "ሰላም " የሚለው ነው :: ቃሉ ከዚህም የሰፋ ትርጉም ያለው ሲሆን : ለአንድ አምላክ ራስን በማስገዛት : ከፈጣሪ ጋር : ከራስ ጋር : ከአካባቢዎችና ከሕዝቦችም ጋር በሰላም መኖርን ያመለክትል :: ይህም በመሆኑ ኢስላም አጠቃላይ የአኗኗር ሥርዓት ነው :: (Islam is way of life) ሙስሊም ከነዚህ ክፍሎች በሙሉ በሰላምና በውሁድ (in harmony) እንዲኖር ይጠበቅበታል :: ስለዚህ በማንኛውም ሥፍራ ታዛዥነቱን : ወገናዊነቱንና ታማኝነቱን ለዓለማት ጌታ : ለአላህ (.) ያደረገ ማንኛውም ሰው ሙስሊም ይባላል ::

2. ሙስሊሞችና ዐረቦች :_ Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Sat Feb 18, 2012 8:31 am    Post subject: ሙስሊሞችና ዐረቦች Reply with quote

2. ሙስሊሞችና ዐረቦች

ኢስላምን የሚከተሉ ሁሉ ሙስሊሞች ይባላሉ :: ሙስሊሞች የሚለው ቃል ዐረቦች ከሚለው ቃል ጋር ማምታታት አይገባም :: ሙስሊሞች ዐረቦች : ቱርኮች : ፐርሺያዎች : ህንዶች : ፓኪስታኖች : ሀበሾች : አውሮፓውያን : አፍሪካውያን : አሜሪካውያን : ቻይናውያን ወይም ሌሎች ሕዝቦች ሊሆኑ ይችላሉ ::

አንድ ዐረብ ግን ሙስሊም : ክርስትያን : አይሁድ ወይም አዋማ ሊሆን ይችላል :: ዐረብኛ ቋንቋን የራሱ አድርጎ የወሰደ ሰው ዐረብ ተብሎ ሊጠራ ይችላል :: ሆኖም የቁርኣን ቋንቋ ዐረብኛ ነው :: በዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች ቁርኣንን ለማንበብና ለመረዳት ይችሉ ዘንድ ዐረብኛን ይማራሉ :: ከቁርኣን : በዐረብኛ ቋንቋ ይሰግዳሉ :: ከሰላት በስተቀር ወደ አላህ ለመቅረብ በማንኛውም ቋንቋ መጸለይ ይቻላል ::

በዓለም ከአንድ ነጠብ ስድስት ቢሊየን (1.7 ቢሊየን ) በላይ ሙስሊሞች ሲኖሩ ወደ 320 ሚሊየን የሚጠጉት ዐረቦች ናቸው :: ከነርሱም መሀከል 10 በመቶ የሚሆኑት ሙስሊሞች አይደሉም :: በመሆኑም ከዓለም ሙስሊም ሕዝቦች ውስጥ ዐረቦች የሆኑት 20 በመቶ ግድም የሚሆኑት ብቻ ናቸው :: (1.7 ቢሊዮን ሙስሊም 288 ሚሊዮን ዐረቦች ናቸው /17%/)

Countries With The Largest Muslim Populations (2009):

Country Number of Muslims
Indonesia..... 203 million
Pakistan....... 174 million
India............. 161 million
Bangladesh. 145 million
Egypt............. 79 million
Nigeria.............78 million
Iran................ 74 million
Turkey........... 74 million
Algeria........... 34 million
Morocco......... 32 million
Iraq..................30 million
Sudan............. 30 million
Afghanistan.. 28 million
Ethiopia......... 28 million (ከዚህ በላይ እንደሆነ ይገመታል )
Uzbekistan.... 26 million
Saudi Arabia 25 million
Yemen.......... 23 million
China............. 22 million
Syria.............. 20 million
Russia............ 16 million

Sources for Population Information
The Pew Forum on Religion & Public Life (October 2009)
CIA Online World Factbook (April 2009)
U.S. Census Bureau, International Data Base (December 2008)

Suggested Reading
Introduction to Islam
Top 10 Myths About Islam

3...አላህ አንዱና ብቸኛው አምላክ Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 6:53 am    Post subject: አላህ አንዱና ብቸኛው አምላክ Reply with quote

አላህ አንዱና ብቸኛው አምላክ

በዕለታዊ ኑሮአችን በሁሉም ሥፍራና ጊዜ የአላህ ፍራቻ ልባችን ውስጥ እስካለና በምናደርገው ሁሉ የአላህ ውዴታ ካለ : ሕግጋቱን ከተከተልን : የአላህን ትእዛዝ በመጣስ ማግኘት የምንችለውን ጥቅም ሁሉ ወደ ጎን ከተውን : ትእዛዙን በመፈማችን የሚደርስብንን ወይም ሊደርስብን የሚችለውን ጉዳት ሁሉ ከታገስን : ይህ ሁሉ አላህን መገዛት /ኢባዳ / ነው ::

አላህ የአንዱና የብቸኛው አምላክ መጠሪያ ሲሆን በተጨማሪም ዘጠና ዘጠኝ ውብ መጠሪያ ስሞች አሉት ::

ቸሩ :
ሩህሩህ :
አዛዡ :
ፈጣሪው :
ዐዋቂው :
ጠቢቡ :
አልፋ ...ኦሜጋ የመሳሰሉት ስሞች አሉት :: የመላው የሰው ልጆች ፈጣሪ እሱ ነው :: የክርስትያኖች : የአይሁዶች : የሙስሊሞች : የቡድሃዎች : የአዋማዎች ሁሉ አምላክ እርሱ ነው :: ሙስሊሞች እምነታቸውን በአላህ ላይ ይጥላሉ :: የእርሱን እርዳታና አመራር ይፈልጋሉ ::

ሙሐመድ (..) Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Sat Feb 25, 2012 7:57 am    Post subject: Reply with quote

4. ሙሐመድ /../
ሙሐመድ /../ የአላህን መልዕክት (ኢስላምን ) ለማስተላለፍ በአምላክ የተመረጡ ነቢይ ናቸው :: ነቢዩ ሙሐመድ በሳውዲ ዐረቢያ በመካ ከተማ .. 570 ተወለዱ :: በዐርባ አመታቸው የኢስላም መልዕክተኛ እንዲሆኑ በራዕይ የተቀበሉትም መመሪያ ቁርኣን ሲሆን መልዕክቱ ኢስላም ተባለ ::

ነቢዩ ሙሐመድ ለሰው ልጅ ከተላኩት ነቢያትና መልዕክተኞች የመጨረሻው ናቸው :: እርሳቸው ለነዚያ የሃይማኖት ባለቤት የሆኑ ሰዎችን (የኢሣን : የሙሴን : የዳዊትን : የያቆብን : የኢስሐቅንና የኢብራሒምን ) ትክክለኛውን መልዕክት ለማሳወቅ ለአይሁዶች : ለክርስትያኖችና ለሰው ዘር በሙሉ የተላኩ ናቸው ::

ከነቢዩ ሙሐመድ በፊት ለመጡ ነቢያትና መልዕክተኞች ሁሉ መደምደሚያ ናቸው :: እርሳቸውም አላህ በነብያትና በመልዕከተኞች ያወረዳቸውን ትዕዛዞች ከብረዛና ከክለሳ አንጥረው ለሰው ልጆች ሁሉ በተሟላ መልኩ አደረሱ :: የቁርኣንን ትምሕርት የማብራራት : የመተርጎምና የመተግበር ኃላፊነትንም በአደራ ተቀበሉ :: ሙስሊሞች በኖህ : በኢብራሂም : በኢስሐቅ : በኢስማኤል : በያቆብ : በሙሴ : በዳውድ : በኢሣና በሙሐመድ ነቢያትነት ያምናሉ :: ሁሉም ነቢያት በእርግጥ የኢስላም ነቢያት ናቸው ::

የኢስላም ምንጮች Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Flame

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2004
Posts: 306

PostPosted: Wed Feb 29, 2012 8:42 am    Post subject: Reply with quote

5. የኢስላም ምንጮች

ሕጋዊ የኢስላም ዋና ዋና ምንጮች ቁርኣንና ሐዲስ ናቸው :: ቁርኣን ትክክለኛው የአላህ ቃል ነው :: ዋናው የአላህ ቃልነቱና መጠኑ እንከን የለውም :: ሐዲስ የነቢዩ ሙሐመድ ንግግሮች : ተግባሮችና ያጸደቃቸው ዘገባ ነው :: የነቢዩ ንግግሮችና ተግባራት ሱናህ ይባላል :: ይህም በተከታዮቻቸው ስለነቢዩ ሙሐመድ ሕይወት የተፃፈ ታሪክ ነው :: ስለዚህም የነቢዩ ሙሐመድ "የሕይወት ሲራህ " ይባላል :: ለሙስሊሞች የዕለት ተዕለት አኗኗር ምሳሌነት አለው ::

6. በጥቂቱ ስለ ኢስላማዊ መሠረት ሃሳቦች Arrow

ሠላም ቆዩን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 36, 37, 38, 39  Next
Page 37 of 39

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia