WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 355, 356, 357 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Feb 26, 2012 4:47 pm    Post subject: Reply with quote

በጣምምምምምምምምምምምምም
ቢዚ ሆኛለሁ ... ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ማለፍ ስላልቻልኩ ነው በተሰረቀች ሰአት ብቅ ያልኩት
ጋሽ ተድላ ምን አለ መሰላቹ
Quote:
አንዳንድ የአገር ቤት ትዝታ ላጫውትህ :- ሾፌርና ፀጉር አስተካካይ የመንግሥት ሠላይ : ሊስትሮ የሠፈር ታሪክ አጫዋች : የአንተ ቢጤ ባለ ኪዮስክ የሠፈሩ ገንዘብ ሚኒስቴር : ልብስ ሠፊና ሸማኔ (በሴት ወዳጅነታቸው ስማቸው በጥሩ አይነሣም ) : እያለ ይቀጥላል :: አንተ የኪዮስክ ባለቤትነትህን ትተህ ወደ ሣይካትሪስትነቱ ተጠግተሃል ::

አቤት ነገር ማሳመር ስትችልበት
እንደው ግን ይሄ ጠጋ ጠጋ ... ማለት ሱቄን ለመውረስ ነው ወይስ የኔን ሱቅ አፍርሰህ ጠጅ ቤት ልትከፍትበት ... ሳይካትሪስት ሁን ምትለኝ
ደም ምን ደስ እንዳለኝ ታዋለህ ከአባባልህ ....
Quote:
ልብስ ሠፊና ሸማኔ (በሴት ወዳጅነታቸው ስማቸው በጥሩ አይነሣም )

የምትለዋ ፓርት ብዙ ነገር እንዳስታውስ አደረከኝና
አውርቼላቹ ይሆንንንን ብዬ የማስታወሻ ጭንቅላቴን ማሰራት አቅቶኝ ተውኩት
ልብስ ሰፊ እንደነበርኩ .. (ማለቴ ዘምዛሚ እና ልብስ ተኳሽ ) እንደነበርኩ ነግሬአቹ ከሆነ የልብስ ሰፊ ጉተማን ታሪክ ያጫወትኳቹ ይመስለኛል
አይ ጊዜ
እንዴት ደስ ይላል ግን ልብስ ሰፊ መሆን
ባሏ ፊት እኮ ነው ... ልለካት ብለህ ጡቷን ዳሌዋን ወገቧን እየተሽከረከር እያቀፍክ እያሸተትክ ምትዝናናው
አይ ጊዜ
ስንት ነገር አስታወስከኝ አቦ ... የልጅነት ጊዜዬን
ህምምምምምምምም
...............................................................//.....................
ጎሲና ጎስነት ጎሳ
አንተ ደሞ ምንድነው ያልከው
Quote:
መጻፍ አንችል : መሳል አንችል ...ግን ምናባቱ ...እነ ባለሱቅንም ማድነቅ ከቻልን እራሱ ይበቃናል ::

ድንቄም እራስህን ዝቅ አድርገህ ሞተሀል
ጣፋጭ ጉጂ
ይልቅ ያንን ሞፍቲ ያገርህን ልጅ በጉጂኛ አማላጅ ልከህም ቢሆን ተመለስ በለው
ጠፍቷል ጨዋታውን ይዞ
እነ -አንፈራራና አደቆርሳማ ...
ተዋቸው ቆይ እኔ ካልሰራሁላቸው

በተረፈ አሁን ጊዜ ውጥርርርር አድርጋኛለች
ሶሪ እመለሳለሁ

ቸር ቆዩን
በወዳጅነታችን እንሰንብት

አንተም ብቅ ብቅ እያልክ ማንበብ ብቻ ሳይሆን
በቤቱ ውስጥ ድድድድድድ በልበት በጣቶችህ ብዕር

ሰላም ሁኑ
እየጠበቀኝ ነው አለቃዬ ለእራት

ባይይይይይይይይይ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Feb 26, 2012 9:05 pm    Post subject: Reply with quote

እራት በልቼ መጣሁላቹ
ኢንተርኔት ሞዴም ስላለቀብኝ ኔት -ካፌ ውስጥ ሆኜ ነው በገንዘቤ ላወራቹ የመጣሁት
ስለዚህ ጊዜ አላጠፋም ወዳላለቀው ታሪክ ልውሰዳቹ
.............................................. ኡጋንዳ .... የኢትዮጵያ ቪሌጅ ሬስቶራንት .................................
..................... እኔና ፊያሜታ ለስላሳችንን እየጠጣን እናወጋለን ............
ያለችን ሰአት በጣም አጭር ናት
አቤት የሚጣፍጥ ሰአት ማጠሩ
ቀጥለናል ወጋችንን
> ትወጂዋለሽ ?
+ ምን አይነት ጥያቄ ነው ...
> ዌል ሶሪ ... ወደሽው ነው ያገባሽው አይደል
+ አዎና !... ግን የተጋባነው በቤተሰብ ነው ... ጥሎኝ እስከጠፋ ድረስ ወደው ነበር
> ጥሎኝ እሰከጠፋ ስትይ
+ አየህ ባለሱቅ ... አሁን እኔ እይዚህ ምታየኝ .. 6አመት ሙሉ ጠብቄው ሳጣው ፍለጋ መጥቼ ያገኘሁትን የባሌን ታሪክ ነው ማወራህ .... እና አዎን እወደው ነበር ... ነገር ግን ... ..
በናትህ አታስጨንቀኝ
> ኦኬ ንገሪኝ እኔ መጠየቄን ላቁምና አልንቺ አውሪልኝ ... እንዴት ተጋባቹ ,.... እንዴትስ ጥሎሽ ጠፋ
................... ከዚህ በኃላ ለሷ ተውላቹዋለሁ ... ታውራላቹ በራሷ አንደበት
ስንጋባ እናቱ አደራ አሉኝ
ፀባዩ በጣም ኃይለኛና የሰውን ስሜት የማያዳምጥ ስለሆነ ... ያስቸግርሻል .. እና አደራ ልጀ ... ቻይው ......... ችግር ካለ ለብቻሽን ከመወሰንሽ በፊት አማክሪኝ
ብለውኝ እንደነበር ትዝ ይለኛል
ተጋባን
ኦህ ሶሪ ... እንዴት እንደተዋቅወቅን ሳልነግርህ
ነርስ ነኝ ብዬ አልነበር
ሳዋ እያለን እኔ ነርስ ሆኜ እሱ ከዩኒቨርሲቲ ወጥቶ ሳዋ ለውትድርና ሲገባ ነው የተዋወቅነው
ዘምተሻል ወይ ኢትዮጵያን ለመውጋት ላልከኝ .... ያው ነርስ ሆኜ ዝምቻለሁ .... ግን በጦርነቱ አላምንበትም ...
እነ ብቻ እሱም እና ብዙ ጓደኞቼ አያምኑበትም ... እሱ አሁን አልፏል ...
እና እዛ ነርስ ሆኘ ነው የተዋወቅነው
ተጋባን
ልጅ መጣ
ልጄ በተወለደ ሁለት ወር ሳይሆነው ይመስለኛል ... ጠፋ
በቃ ጠፋ
እኔ ገደሉት ወይ ብዬ ስጨነቅ ... ከሳምንት በኃላ ስልክ ደወለልኝ ................................ ከሱዳን .... ካርቱም
ነደድኩ ... ተበሳጨሁ ... ለምን አላማከረኝም ብዬ
አየህ ምን እንዳናደደኝ አንተ አይገባህም ... ምክንያቱም ስለኤርትራ ምንም አታውቅም
ቢያማክረኝ እንቅፋት የምሆንበት መስሎሀል አይደልም ... አይደለም
አይደለም ዋናው ነጥብ እሱ አይደለም ... እኔ የሱን መውጣት አልቃወምም
ግን ሊነግረኝ ይገባ ነበር ....
ሊያማክረኝ ይገባ ነበር
አየህ አንተ አይገባህም እንጂ
ቢያማክረኝ ... እኔም ለመውጣት አልቸገርም ነበር
ይህንን ያህል ጊዜ አንለያይም ነበር
አንዲት ሴት ኤርትራ ውስጥ በህግ ጋብቻ ካላት ... ውጭ አገር መውጣት ብትፈልግ ,,, ባለቤቷ ፍቃድ መስጠትና መፈረም አለበት
ምን ማለት እንደሆነ ይገባሀል
አሰረኝ
በቃ አሰረኝ
እሱ ወደውጭ ወጥቶ እኔን አሰረኝ ...
ተበሳጨሁ .... ልፈታው ፈለኩ ....
ምንም አቃተኝ //// ለመፍታትም እሱ መኖር አለበት ... ከአገር ለመውጣትም እሱ መፈረም አለበት
ይገባሀል .. ምን ማለት እንደሆነ
ሰት ልጅ የወንድ ልጅ እቃው ናት .... በባህልም .. በመንግስትም ደረጃ
አያበሳጭም በናትህ
ውይይይይይይይ ሶሪ አስጨነኩህ አይደል
አውርቼው አላውቅም እኮ ... ግን በቃ በዛብኝ ... የማወራው ሰው አልነበረብኝ
አንተ ግን ምን አይነት ሰው ነህ .. በማርያም
ኦኬ ኦኬ ... እንዴት ወጣሁ መሰለህ
ባሌ አጠገቤ ሳይኖር አምስት አመት ያህል ከቆየ .... ለመውጣት የቤተሰቤ ፍቃድ በቂ ነበር ... እና
ብዙ ብዙ ለፍቼ ነው ልወጣ የቻልኩት ከኤርትራ በፍለጋ አግኝቼው ... 6አመት በኃላ ተገናኝተንም አሁንም እንደእቃው ሊያየኝ ይፈልጋል
ይደበድበኛል ... ይንቀኛል ... አይሰማኝም ... እያለሁ እንደሌለሁ ነው ሚቆጥረው እና ቆርጫለሁ
ግን አንተ ምን ትመክረኛለህ
.........................................//...................................
> እስኪ ምን እንዳሰብሽና ምን እንደቆረጥሽ ንገሪኝ
+ ኤርትራ እመለስና .. የናቱን ፍቃድ ,.. የቤተስቤ እርግማን
እንዳይኖር አድርጌ ፈታዋለሁ .... የሚያስጨንቀኝ ግን የልጄ ነገር ነው
ልጄ ያለአባት ሊያድግ ነው ....
ግን ለነገሩ እስከዛሬ ያላባት ነው ያደገው
በቃ አላውቅም እኔ ወስኛለሁ
> እና ለዚህ ጉዳይ ብለሽ ወደ -ኤርትራ ልትሄጂ ነው ?
+ አዎን ... ነግሬዋለሁ .... ልጄም ናፍቆኛል ... መሄድ አለብኝ
> ምን እንደምልሽ አላውቅም .... እዚሁ ወስነሽ ብትጨርሺው እወድ ነበር ... ምንም ላደርግልሽ ባለመቻሌ በጣም ነው ማዝነው .... ግን እንድረዳሽ የምትፈልጊው ነገር ካለ ................. በቃ ልትመለሺ ነው ማለት ነው ኤርትራ ....
+ ልጄን ይዤ እመጣለሁ ... እሰደዳለሁ
> ኦህ .... ማይ ጋድ
+ አታስብ ... አንተ በጣም ከምገምተው በላይ ነው ያደረክልኝ ... በትግስት ስላዳመጥከኝ በገንዘብ የማይለወጥ ነገር ነው ያረክልኝ .... አሁን ቅልልል ብሎኛል .. አመሰግናለሁ .... አሁን መሄድ አለብኝ .... እደውልልሀለሁ የተለወጠ ነገር ካለ
+ ደህና ሁንልኝ ... በጣም ነው የምወድህ .... ባቅፍህ ቅር ይልሀል
እውነቴን ነው ምላቹ እግሬ እራሱን ችሎ መሸከም ነው ያቃተው
ዝምምምምም ብዬ አየኃት
እንደፈለገችው ሆንኩላት
ሳመችኝ እና
በቆምኩበት ጥላኝ
ሄደች
ፊጧን አንዴ እንኳን አላዞረችም
በቃ ሄደች
...............................//...............................
ስትደውል እነግራቹዋለሁ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Feb 26, 2012 9:21 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
በጣምምምምምምምምምምምምም
ቢዚ ሆኛለሁ ... ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ማለፍ ስላልቻልኩ ነው በተሰረቀች ሰአት ብቅ ያልኩት
ጋሽ ተድላ ምን አለ መሰላቹ
Quote:
አንዳንድ የአገር ቤት ትዝታ ላጫውትህ :- ሾፌርና ፀጉር አስተካካይ የመንግሥት ሠላይ : ሊስትሮ የሠፈር ታሪክ አጫዋች : የአንተ ቢጤ ባለ ኪዮስክ የሠፈሩ ገንዘብ ሚኒስቴር : ልብስ ሠፊና ሸማኔ (በሴት ወዳጅነታቸው ስማቸው በጥሩ አይነሣም ) : እያለ ይቀጥላል :: አንተ የኪዮስክ ባለቤትነትህን ትተህ ወደ ሣይካትሪስትነቱ ተጠግተሃል ::

አቤት ነገር ማሳመር ስትችልበት
እንደው ግን ይሄ ጠጋ ጠጋ ... ማለት ሱቄን ለመውረስ ነው ወይስ የኔን ሱቅ አፍርሰህ ጠጅ ቤት ልትከፍትበት ... ሳይካትሪስት ሁን ምትለኝ

የሠፈራችን ኪዮስክ ባለቤት :-
ምን በወጣኝ የአንተን ኪዮስክ ወርሼ ከአገር ውስጥ ገቢ ጋር ድብብቆሽ እጫወታለሁ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ዘንድሮ 'ከአገር ውስጥ ገቢ ዐይን ይሠውርህ ' ሲባል አልሠማህም Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ... በገዛ ቤትህ እንደ ኬላ ጠባቂ ፈታሽ ወታደር 'Cash Register' እያስቀመጡ ዕንቅልፍ ከሚነሱ ሰዎች ጋር እንድጋፈጥ ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes በል በል በል ... እዚያው አንተ እንደለመድክበት ከእነርሱ ጋር ተለማምጠህ ኑር Cool እኔስ ንግድ ዕጣ ክፍሌ አይደለም ::

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
ደም ምን ደስ እንዳለኝ ታዋለህ ከአባባልህ ....
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ልብስ ሠፊና ሸማኔ (በሴት ወዳጅነታቸው ስማቸው በጥሩ አይነሣም )

የምትለዋ ፓርት ብዙ ነገር እንዳስታውስ አደረከኝና
አውርቼላቹ ይሆንንንን ብዬ የማስታወሻ ጭንቅላቴን ማሰራት አቅቶኝ ተውኩት
ልብስ ሰፊ እንደነበርኩ .. (ማለቴ ዘምዛሚ እና ልብስ ተኳሽ ) እንደነበርኩ ነግሬአቹ ከሆነ የልብስ ሰፊ ጉተማን ታሪክ ያጫወትኳቹ ይመስለኛል
አይ ጊዜ
እንዴት ደስ ይላል ግን ልብስ ሰፊ መሆን
ባሏ ፊት እኮ ነው ... ልለካት ብለህ ጡቷን ዳሌዋን ወገቧን እየተሽከረከር እያቀፍክ እያሸተትክ ምትዝናናው
አይ ጊዜ
ስንት ነገር አስታወስከኝ አቦ ... የልጅነት ጊዜዬን
ህምምምምምምምም
...............................................................//.....................

ልብስ ስፌት ማኅበር ውስጥ ዘምዛሚና ልብስ ተኳሽ ሆነህ እንደሠራህ አጫውተኸናል :: ነገር ግን ስለ 'ጉተማ ' ጀብዱ ያወራኸን ነገር የለም :: ወይስ እኔ የእናንተን ቤት በማላነብበት የጥንቱ ዘመን ጽፈኸው ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ካስታወስከው 'Copyright' ለጉተማ አድርገህ አጨውተን ::

ተድላ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከንቲባ .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 08 Jan 2010
Posts: 50
Location: Roma

PostPosted: Mon Feb 27, 2012 12:38 am    Post subject: Reply with quote

i Love this Guy

Quote:
ትልቁ የኪነጥበብ ሰው መምህር ጋዜጠኛ አርታኢና ደራሲ ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሄር አረፈ !
ዜናው ያስደነግጣል አይደል ? በጣም እንጂ ! በጣም ያስደነግጣል ::
ኖሮ ኖሮ ከመሬት ዞሮ ዞሮ ከቤት ...
እንዲሉ የተፈጥሮ ግዴታ ሆነና ጋሸ ስብሃት ወደማይወዳት ዓለም ቀድሞ ተጓዘ
ማንም ሠው በምድር ላይ ሳለ በሰራው ስራ እርሱ ሲያልፍ ስሙ ከመሬት ይቀራል ክፉም ሠው ክፋቱ ይቀርለታል
መልካምም ሠው መልካምነቱ ይቀርለታል :
ምናልባት የእግዚአብሄርንም ቃል ያየን እንደሆነ ለምድራችን የመኖሪያ
ጉልበት ሆኖ እናገኘዋለን :: ሠው የስራውን ዋጋ ያገኛል ይላ ልክ እንደዚሁ ነው
ጥሩ ሰዎች ጥሩ ስራቸው መጥፎ ሰዎችም መጥፎ ስራቸው በህይወት ሳሉም ጀምሮ ከጀርባቸው ምንም ያህል ሳይርቅ የሚከተላቸው ::
እነርሱ ካለፉ በኋላ ደግሞ እስከ ዘለዓለም ይኖርባቸዋል ወይንም ይኖርላቸዋል ::
ስብሃት ገብረ እግዚአብሄርን እንደ መታደል ሆኖ ጥቂት ቀናትን አብሬው ውዬ አውቃለሁ ዝምምምምምም
ብዬ ከአፉ የሚወጣውን ሳዳምጥ ውዬ አመሽ ነበር ብዙ ነገር ለመጠየቅ ስሜቴ ውጥርርር ቢያደርገኝም
የሚናገረው የሚያመልጠኝ ስለሚመስለኝ ከጥቂት ጉዳዮች በስተቀር ልጠይቀው አልቻልኩም ነበር ::
ከዚህ ቀደም አንድ ያላሰብኩት ቦታ ለስራ (በቀን ሰራተኝነት ) ሄጄ አንድ ላገኘው የማልችል በጣም በጣም ሃብታም ሰው
አጠገቤ ሆኖ አየሁትና ተገረምኩ : እንዴ እንትና ይሄውና አልኩ ለራሴ ዝም ብዬ የሚናገረውን እና የሚያደርገውን በጥሞና
ስከታተል ለሰዓት ቆየሁ ታዲያ በውስጤ አንድ ነገር አስብ ነበር በጣም ብዙ ገንዘብ ያለው ሃብታም ሰው እንዴት እንደሚኖር ምን
እንደሚበላ እንዴት እንደሚናገር ምን እንደሚያደርግ ወዘተ ከልጅነቴ ጀምሮ የራሴ የሆነ አመለካከት የነበረኝ ይመስለኛል .... ::
ያንን ሃብታም እንደዚያ አድርጌ የሚናገረውን የሚያደርገውን በጣም ያየሁትና የሰማሁት የተለየ ነገር የማይባቸው ስለሚመስለኝ
መሰሎኝ እንደሆነ አውቃለሁ :: ጋሼ ስብሃትን የተከታተልኩት ልክ እንደዚያ በነበረ ጥልቅ ስሜት ቢሆንም ወደውስጤ ለማስገባትና
መንፈሴን ለማርካት ሲሆን ሃብታሙን ሰው የተከታተልኩት ግን ለመገረም ይመስለኛል ::
እንጂ በእርሱ ሁኔታ ረክቼ ራሴን ለማዝናናት ሊሆን መቼም ከቶም አይችልም ::
የሚገርመው ነገር ግን ምንም የገረመኝም የተለየም ነገር አለማየቴ ሃብታም ማለት ?
ብሎ አዕምሮዬ ድሮ የሚስለው ሸራ የሌለው ሥዕል ስህተት መሆኑን ተረዳሁኝ ::
ስለዚህ ለውጡ ያለው ኪስ ላይ ብቻ ነው ማለት ነው አልኩና ከዚያ በኋላ ለሃብታም ኬሪዳሽ ሆንኩኝ :
ለችሎታ ሃብታሞች ግን ለጥበብ ባለጸጎች ግን ለድንቅ ደራሲያን ግን ያለኝ መገረም ውስጤን የሚነካ ፍላጎቴን
የሚያረካ ህይወቴን የሚያፈካ ቁምነገር ማግኘት ነው ::
ስለ ጸሃፊያን ግን በደንብ አስባችሁ ታውቃላችሁ ሴት ልጅ ለመውለድ እንደምታምጥ እነሱ ቃላትን ሲያምጡ ማሰብ ኦህ በጣም ነው የሚገርመኝ ::
በአሉ ግርማን የሚያህል ደራሲ መቼም ይፈጠራል የሚል እምነት አልነበረኝም ደራሲውን ሲጽፍ
ጋሽ ስብሃትን እንደቀረጸው ካወቅኩ በኋላ እንደገና ደራሲውን አነበብኩ ::
አንዲቱን ቀን በጠዋት እንደተገናኘን እንዴት አደርክ ጋሽ ሥብሃት ? አልኩት
እንዴት ላድር ትፈልጋለህ ? አልጋ ላይ ተኝቼ ነዋ !
ሳቅ አልኩና እንደምን አደርክ ማለቴ ነው አልኩት ስህተቱ የገባኝ መስሎኝ
ቀንቶኝ ነው ያደርኩት አለኝ
ምን ቀናህ ?
ከዚህ በላይ እኔም አላውቅ አለኝ ...........
በጣም ያሳቀኝ አባባል ነበር ::
ጸሃፊ ዘነበ ወላ ለጋሽ ስብሃት ግባ መሬት ስንብት ሲያደርግ እንዲህ አለ በሌለህበት ቦታ ሁሉ ያንተን ስም ሳነሳ በታላቅ ኩራት ነው !
ደስ ያለኝ አባባል ነው ::
ጋሽ ስብሃትን ከሚያስታውስበት ነገሮች ሁሉ ትልቁን ስጦታው እንዲህም ብሎኛል አለ ....
እድሜ ለአጤ ምኒሊክ ባንዲራን እና አማርኛን አምጥቶ እኔንና አንተን አገናኝቶ አንድ አደረገን
አለበለዚያማ እኔም ከመይ እያልኩ አንተም ሃይመሌ እያልክ ሳንግባባ እንቀር ነበር .....
አስተማሪና ድንቅ አባባል ነው ::
ኢትዮጵያ በውነት በዚህ ዘመን ያጣቻቸው ትልልቅ ሰዎች
በዓሉ ግርማ ጸጋዬ ገብረመድህን ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ጥላሁን ገስስ ሌሎችም ሌሎችም ታላላቆቹና ስመጥሮቹ
ኢትዮጵያውያን ትተውልን ያለፉት ውርስ ፍቅር ብቻ ነው ::
ልዩ በሆነውና በራሱ የአጻጻፍ ችሎታ አገር ያደነቀው ጸሃፊ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር ብዕሩ ሃሰትን በፍጹም አታውቅበትም ስታስረዳም ስትናገርም
እንደወረደች ናት ለዚህም ነው ሁለተኛው ስሙ <<እንደወረደ >> የተባለበት ::
ጋሽ ስብሃትን እንደወረደ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት :- ጽሁፎቹ ቅኔያዊነትን አያውቁም ገላጭ አረፍተነገሮችን አይከጅሉም አስረጅ አያሻቸውም
እንደው በቀጥታ የፈለገውን ቃልና ዓረፍተ ነገር ቁጭ በማድረግ ለእርሱ በተቸረው ልዩ የጽሁፍ ችሎታ በአንባቢው ስሜት ውስጥ ገብተው ሲዋኙ :
ከልቦና አለመጥፋታቸውና ዳግም መጽሃፉን ማንበብ አለማስፈለጉ ብቸኛ መግለጫው ነው :
የኢትዮጵያ የስነጽሁፍ ጥበብ እንዲያድግ እድሜውን የሰጠ ታላቅ ደራሲ : እንደለማኝ ለምኖ እንደመምህር አስተምሮ እንደድሃ አጥቶ እንደጸሃፊ ጽፎ
እንደጋዜጠኛ ዘግቦ ህይወቱን ለማስተስተማሪያነት ለወገኑ ገጸበረከት ያቀረበ ትልቅ ሠው ስብሃት ለአብ ገብረእግዚአብሄር እስከወዲያኛው አሸለበ ::
አፈሩን ያቅልልለት
እንዲሁም ተወዳጁና ባለ ብዙ ታሪኩ የጥበብ ሰው ሱዳናዊው መሃመድ ዋርዲ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ
እጅግ በጣም አሳዝኖኛል የእርሱንም ነፍስ ይማር ::

ቸር ይግጠመን አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

ቤቱ ጸድቷል ወሮበላው ሁሉ እስርቤት ገብተዋል አሁን ብትምለሱ ደስታዬ ነው ባካችሁ :
_________________
Ethiopia tikdem
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 28, 2012 8:43 am    Post subject: Reply with quote

ከንቲባ ወንድሜ
አመሰግናለሁ የአደቆርሳን ምርጥ ፅሁፍ እዚህ አምጥተህ በመለጠፍህ
አንተ አደቆርሳ
ስለ -ደራሲ ስብሀት /ግዚአብሄር የጥሣፍከውን አንብቤ ... በቅናት ድብንንንን ብዬልሀለሁ
ለምን ብትለኝ
እኔ ለምንድነው የማደንቃቸውና የምወዳቸውን ሰዎች ሳልጨብጣቸው የሚያልፉኝ
ከምር በጣም ቀናሁ
ማንም ከመሞት አይድንም .. ነገር ግን ከመሞቱ በፊት ያንን ሰው ምን ያህል እንደምንወደው እና እንደምናደንቀው የምንገልፅበት አጋጣሚ ቢፈጠር እንዴት መልካም ነበር
እዚህ ያለሁበት አገር በአመት አንዴ ወይም ሁለቴ ገንዘብ እየከፈልክ የምታደንቀውን ሰው እጅ የምትጨብጥበት ፕሮግራም አለ
ገንዘብ ከፍለህ ተሰልፈህ ጨብጠኸው .... እንደምታደንቀውና እንደምትወደው ነግረኸው ... እድለኛ ከሆንክ ፎቶ ተነስተህ ማለፍ
በገንዘብ የማይገኝ ደስታ እኮ ነው
አሁን ጥላሁንን በአሉ ግርማን ስብሀትን እንዲህ አድርገው ቢያቀርቡልን .... ምን ነበረበት አሰኘኝና ....
ድህነታችንን እናስታምም ... ፖለቲካችንን ... እናጠናክር ... ጠላቶቻችንን እናብዛ ... ወይስ እጅ ለመጨበጥ ስራት እንጨነቅ ሲሉኝ ሰማኃቸው ... እና -እንትና
ደሀ ድሮስ ድሀ አገር የተወለደ ... የኪነትሰው እንደደኸየ አይደል ሚያልፈው
ኤኒዌይ ....
ግሩም ደራሲ ነው ያጣነው .... በተረፈ የበአሉ ግርማን ደራሲውን በተመለከተ ... የገጠመኝን ገጠመኝ .. አንድ ቀን አጫውታቹዋ ;ለሁ
እግዜር የዛ ሰው ይበለን

እስኪ ደራሲው ውስጥ ያለውን ውሻ ታሪክ ማነው ሚያስታውሰኝ ?
ይሸለማል ከምር
............................................//.............................
ወንድሜ ተድላ
ስለጉተማ ለማውራት አንድ አዲስ ሙድ ያስፈልጋልና
ታገስ ካልተወራ ይነገራል
ምን ገዶን
አሁን ፊያሜታን እንሰናበታት
...................................//........................
> ሳትሰናበቺኝ እንዳትሄጂ ... ብያት
+ እረ በፍፁም አላረገውም .. ብላኝ
በአንድ ቀኑን በማላስታውስበት ቀን ስልክ ደወለችልኝ
ከደቡብ ሱዳን .... ጁባ
> ሄድሽ እንዴ ?
+ በድንገት ተነሺ አለኝና በሌሊት ይዞኝ ወጣ
> ላምን አስቸኮለሽ
+ ወደ -ሊቢያ ሊሄድ ስለተነሳ .... አስመራ ምትሄጂ ከሆነ አሁኑኑ ተነሽ ብሎኝ ... ስልክ መደወያ ጊዜም አጣሁ
> ሊቢያ ለምን
+ አላውቅም .... ካርቱም ስደርስ ደውልልሀለሁ ... አደራ ደውልልኝ
ብላኝ ተለያየን
በማግስቱ ስደውልላት ካርቱም ገብታለች ... ከሁለት ቀን በኃላ ወደ ኤርትራ በባስ እንደምትሄድ ነገረችኝ
እንዳለችውም ከሁለት ቀን በኃላ ሳይሆን ከአራት ቀን በኃላ አስመራ ሆና ደወለችልኝ
+ በአንድ ወር ውስጥ ሁሉንም ነገር ጨርሼ እመጣለሁ
> ,ምን አስበሻል
+ ብሩንዲ ወይም ሳውዝ አፍሪካ እሄዳለሁ ልጄን ይዤ
> ምን አለሽ እዛ
+ እድሌን ሞክራለሁ
> ህምምምምም ምንም ልልሽ አልችልም ... እስኪ በመጀመሪያ ተሳክቶልሽ ከአስመራ ውጪ እና ..... ካምፓላ ከተገናኘን ከብዙ ኤርትራዊያን ጋር አገናኝሽና .. የሚሆነውን እንመካከራለን
+ ውይ ደስታውን አልችለውም እንደገና ብንገናኝ .... ግን የምንገናኝ ይመስለኛል
> ይመስለኛል ... አንቺ ብቻ ይሳካልሽ
+ በአንድ ወር ውስጥ የሚያልቅልኝ ይመስለኛል ... አንተ ግን የት ነው ያለሁት አልከኝ
> ኢትዮጵያ
+ በቃ ኢትዮጵያ ነው ምመጣው
> እንደሱማ በቶሎ ሀሳብሽን መቀየር የለብሽም
+ ላንተ ብዬ መሰለህ ....
> ቢሆንም
+ ለማንኛም ከወር በኃላ ካምፓላ ካለህ እንገናኝ
> ሀራይ ... ከወር በኃላ እመለሳለሁ ይመስለኛል
+ እስከዚያ ድረስ ግን ትደውልልኛለህ አይደል
> በሚገባ ... እደውልልሻለሁ
+ በጣም አመሰግንሀለሁ
> አብሽር በርቺልኝ ናይ ሰመናይ ፅብቕቲ
+ እሺ ባለሱቅዬ
................................//.........................
ሁለት ወር ፈጀባት ጉዳዩዋን ለመጨረስ
በመጨረሻ ከሁለት ወር ተኩል በኃላ ተሳካላትና ካምፓላ መጣች
ይህ የሆነው ደሞ ዲሴምበር ለስራ በሄድኩ ወቅት ነው
ከባሏ ጋር መለያየት አልቻለችም እንዳሰበችው .... እንደነገረችኝ ከሆነ የቤተሰብ ግፊት እና ሀሳቧን ያለመቀበል ነገር ያለ ይመስለኛል
እሷ ግን ቆርጣለች
ባሏም ሊቢያ አልሄድም ...
ደቡብ ሱዳል ለንግድ ይመላለሳል
እቤቱ ቁጭ ብላ ልጇን ማሳደግ ጀምራለች
እሱ ሲመጣ ሲመጣ ብቻ ነው ነፍሷ ሚሰቃየውና ህይወቷን ምታማርረው
እሱ ለስራ ሲሄድ ከልጇ ጋር ጥሩ ጊዜ እያሳለፈች ነው
አንድ ቀን ቁጭ ብለን ስናወራ .... እኔ ... እሷ .. እና 8አመት ቆንጅዬ ልጇ
በነገራችን ላይ ለክጇ ጋር በጣም ተግባብተናል ... አማርኛ ባይችልም .. በምልክት
+ ባለሱቅዬ ... አንድ ነገረ ብጠይቅህ ቅር ይልሀል
> የፈለግሽውን ጠይቂኝ ... አትፍሪኝ
+ በእግዚአብሄር ይዘኸኝ ጥፋ
ማይ ጋድ
እንዴት አስደነገጠችኝ መሰላቹ
> እንደሱ ማድረግ ግብታዊነት ነው ... አይሆንም
ዝም አለች ... በጣም ተከዘች
+ ሶሪ ስለጠየኩህ .. በቃ እርሳው .... ሶሪ ሶሪ
አቤት ፊቷ ሲቀላ እና እፍረቷ ሲያሳብቅባት ስታምር
እስካሁን ግን ለምን እንድንተኛ አልጠየከኝም .... ስትለኝ ግን ተጭበረበረብኝ
እምነቴን ነገርኳት .... የሰው ወርቅ የሰው ነው .... መነካካት ጥሩ አይደለም .... ወደ -ሌላ ነገር ይወስደናል
እንዲሁ በጥሩ ጓደኝነት .. እህትና ወንድምነት ብንቆይ የበለጠ ........ ጥሩ ነው .... አልኳት
ከራሴ ጋር እየተፈታተንኩ
አቤት ስለራሴ ሳወራ ማሳመር ስችልበት
ብታምኑም ባታምኑም የሆነው ይኸው ነው
ኤኒዌይ
ታላቅ እህቷ ጋምቤላ እንዳለች .. እና ብዙ ጊዜ ነይ እያለች ትጨቀጭቃት እንደነበር ነገረችኝ .. እና
ኢትዮጵያ ለመሄድ እንደቆረጠች አበሰረችኝ
+ አዲሳባ አይሀለሁ አይደል
> ይመስለኛል ... በአመት አንዴ ... ግን እስካሁን ይህንን ያህል ጊዜ ስደውል ስልክ ቁጥሬን አይተሽ ግን እንዴት አልገመትሽም .. የት እንዳለሁ
+ እኔ እኮ ጠይቅሀለሁ እያልኩ ... 81 የሚጀምር ስልክ ቁጥር የኢትዮጵያ አይደለም .. ግን በናትህ የት ነው ያለኸው
> እሩ ምስራቅ
+ ነው ለካ ......... እኔ እኮ ሁሌ እጠይቅሀለሁ እያልኩ ... ግን የትስ ብትሆን እኔ ምንም ግድ አልነበረኝም ... ስለዚህ ነው ያልጠየኩህ ... ኢትዮጵያ ትመጣ የለ
> አዎን እመጣለሁ
+ ፕሊስ ጠይቀኝ ... የእህቴን ስልክ ቁጥር ያዘው
> ኢሺ የኔ ቆንጆ
+ በጣም አመሰግናለሁ ... በሀሳብ ስለረዳኸኝ ... እንዳወራ ስለፈቀድክልኝ .. ጥሩ ጓደኛዬ ስለሂንክ
> እኔም ክብር ይሰማኛል ... የታሪክሽ ተካፋይ በመሆኔ

በሄድሽበት ይቅናሽ ... ፊያሜታ
ኢትዮጵያ ስመጣ እደውልልሻለሁ

ጲርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር

ኦሮማይ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 28, 2012 5:07 pm    Post subject: Reply with quote

አንፈራራ ያለውን አያቹልኝ
ህምምምምም
Quote:

ባለሱቅ

ፊያሜታ ልጇን ይዛ ከባሏ ጋር ለአንዴና ለመጨረሻው ካልተለያየች በእርሱ እጅ ጠፊ ነች :: በእውነት የሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው :: ልትረዳት ከቻልክ በቶሎ መርዳት ነው በቶሎ ካለችበት ቦታ እንድትሸሽ ማድረግ ነው :: አሁን ገብተህበታልና ቶሎውኑ አንድ ነገር አድርግ በኋላ እንዳይጸጽትህ :: እንደሚመስለኝ ከሌላው ሁሉ ኢትዮጵያ ገብታ ብትገላገል ይሻላታል :: እኔ አንተን ብሆን የምመክራት ይህንኑ ነው ::

እሺ ..... በሌላ በኩል ደግሞ .... አንተ ግን ምን ትባላለህ ባክህ ? እርሷን በሃይል እንዳስቀየምካት ይገባሃል ?

እየነካካህ ዳር ሳታደርስ "ወንድም ልሁንሽ እህት ሁኝኝ " የሚል ፈሊጥ ጀምረሃል ... ምን የሚሉት ቋንቋ ነው ? "ወይ አይበላ ወይ አያስበላ " አሉ .....ኧረ ባለሱቅ ኧረ ተው ተው !!!! የአዶላ ልጅ እንዲህ ሲያደርግ አይቼም ሰምቼም አላውቅም ::

የአዶላ ልጅ እንደ ፊያሜታ ያለችውን ሲያገኝ የገናሌን ወንዝ ሳያሻግር አይመለስም እኮ፣ አቦ ተወኝ :: ቅቅቅቅቅ

ቸር ይግጠመን ::

እኔ የሰው ነገር አይስማማኝም ምንም ቢወጥረኝ
በዚህ ነገር ተማመንብኝ ... ከምሬ ነው
በተረፈ እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያ እንደምትሄድ ...
ተስማምተናልና
በቅርብ ደውዬ አረጋግጣለሁ
አስፈላጊ ከሆነ ይነገራቹዋል

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቸር እንሰንብት
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
brookk

ኮትኳች

Joined: 11 Nov 2003
Posts: 291
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Feb 28, 2012 6:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሀላፊነት መውሰድ በጣም ከባድ ነው - ስለሆነም አንድ የምናውቀው ወይም ሌሎችን ሊጠቅም ይችል ይሆናል ብለን የምናስበው ነገር ካለ - መኖሩን as FYI ለመግለጽ ፈራ ተባ እንላለን ? ምክንያቱም ላናስጨርስ ስለምንችል
ለማንኛውም የፊያሜታ ወገኔ ስሜት አሳዛኝ ነው -- በህይወቷ "በትዳሯ " ደስተኛ አትመስልም -- ደስታን ትሻለች - የማግኘት እድሏ ግን በሌሎች ሰዎች "ጥሩ መሆን " የሚወሰን ነው ::
ሰዎች ግን ለምን መጥፎ ይሆናሉ ? ይህ ባል ተብየው ለመሆኑ ይወዳታል ? ከወደዳት ለምንስ ጭንቀቷ አይታየውም ?
ብዙ ጊዜ እንደምለው - ትዳር የፍቅር ውጤት እንጂ የውለታ ምላሽ ወይም "የምን ይሉኛል " ነጸብራቅ መሆን የለበትም --
ካልወደዳት ለምን አይተዋትም ?
እንደገና -- ለማንኛውም ... የዚች ልጅ ውጭ የመውጣት ጉጉት አንድ ነገር አስታወሰኝ --- ካናዳ
በአንድ ወቅት የኔንም የሚስቴንም ዘመዶች -- በጉብኝትም በፋሚሊ ስፖንሰርም ለማምጣት እሯሯጥ ነበር - በነገራችን ላይ በውቅቱ ሁሉም ተሳክቶልኛል
በወቅቱ ግን በስደት ስላሉ የአገር ልጆችና እንዴት መምጣት እንደሚችሉ አንዱን አማክሬው ነው -- የሰጠኝን መልስ -- ሳስታውሰው አሁንም እውነትነቱ እጠራጠራለሁ -
አንድ ሰው እራሱን ስፖንሰር አድርጎ መምጣት ይችላል -- ማድረግ ያለበት -- እራሱን ችሎ መኖር እንደሚችል ማሳመንና ወደ $8,000 ዶላር አካባቢ ማስያዝ ነው (ይህ የኛን አይነቶቹን አገሮች ስደተኞች ብቻ ይመለከታል )

ይህ አዲስ ፓይለት ፕሮጀክት ነበር -- አሁንም ይኑር አይኑር አላውቅም - ለማጣራት እሞክራለሁ ::ከአምስት አመት በፊት የሰማሁት ነበር -- ፊያሜታ ይህንን ብር ከየት ታመጣለች ለሚለው መልስ ባይኖረኝም ይህ አንዱ ኦፕሽኗ ሊሆን ይችላል --- ሌላው ኢትዮጵያ የመሄድ ሀሳቧ በጣም አሪፍ ነው -- ይህን ህጻን ልጅ በየአገሩ ባታንከራትተው ተመኘሁ

ባለሱቅ ጠንካራ ነህ --- ባንተ ቦታ ያለ ሌላ ሰው -- በተለይም ከሷ ጥያቄው መቶ ሊሰጥ የሚችለው መልስ በፍጹም የተለየ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ
ይቺ ልጅ ንጹህ ፍቅር ጠምቷታል -- በአገር ልጅነት ያደረክላት "ኬር " ስሜቷን ስለነካው እራሷን ልትሰጥህ እንድትዘጋጅ አድርጓታል --- አይ ሆፕ የሰጠሀት መልስ እንዳሳፈራት ሁሉ ቅስሟን እንዳልሰበረው
ዘለህ እንድትከመርባት የማይፈለገውን ያህል ስሜቷንም እንዳትጎዳው ፕሊስ Laughing
በይሉኝታ ፍቅር ብቻ ሳይሆን "ሴክስም " ዋጋ እንደሌለው ግን አልረሳሁም

ፊያሜታ ጥዑሚ ነች --- ይቺ "ግናይ " Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Feb 29, 2012 5:18 am    Post subject: Reply with quote

አንፈራራ ሊያናድደኝ ሲፈልግ
Quote:

ባለሱቅ !

ለመጀመሪያው መልክት ስለሰጠኸው መልስ አመሰግናለሁ። እርሷም ኢትዮጵያ በሰላም ከልጅዋ ጋር እንደምትሄድ ተስፋ አለኝ። ይቅናት እላለሁ።

ለሁለተኛው አስተያየት ግን መልሱን ለመስጠት አለመፈለግህ ገርሞኛል። ያውም አንተ ! እንዲህ ዓይነት አስተያየት አይተህ የምታልፍ አይመስለኝም ነበር። ቅቅቅ

በል ቻው !አንተ ብሽቅ ጉጂ
ነገርኩህ እኮ ..... አንደኛ የሰው ወርቅ የሰው ነው ...
ሁለተኛ በእንዲህ አንየት ሁኔታ ያለን ሰው ለሌላ ችግር ለሌላ የስሜት መረበሽ .. ለሌላ እጦት መዳረግ አልፈልግም
ከተነካካህ ጣጣው ብዙ ነው .... ምን ማለት እንደፈለኩ ከገባህ
እኔ ደሞ ዝም ብዬ -ቢሻን - ብዬ አስተክዤ መሄድ አልችልበትም
እስኪ ጠይቁልኝ .... ምን አለችኝ ይላል
እንጨቱን ሰብሮልን በመሸከሚያችን
ውኃውን ቀድቶልን .. በመሸከሚያችን
አስቦ ተክዞ ሄደ ወዳጃችን
መባልን አልፈልግም ... በተለይ በምወደው ሰው ነፍስ ውስጥ
ስለዚህ እንዲሁ መዋደድ ሲቻል ... ለምን ሌላ ማስተከዝና ችግር ውስጥ ሰውን እንከታለን የሚል አመለካከት ስላለኝ
መነካካት አልፈለኩም
የአዶላ ልጅ በናንተ ዘመ ያሉት ይሆናል .... ገናሌን ሚያዘልሉት ..... በኛ ጊዜ ያሉት እነ -ሽልንጌን ብትጠይቃቸው ... ይነግሩሀል
ተንከባክበው አንፈራራን አሻግረው ነው ሚመለሱት እንጂ .... መንገድ የጠፋውን ሰው ወደ -ገናሌ ይዘው አይሄዱም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አደቆርሳና ራስብሩ ገደሉኝ ..... እኛስ ብለው ?
በናንተ ጊዜ ያሉት ደሞ ... ወደ -ማርያም ዳገት .... እንደቡጡ እሼቴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ድሮ ድሮ ያጫወትኳቹ ይመስለኛል ... ቡጡ እሽቴ .. አንዲት የሻኪሶ ልጅ ይዞ ሲሄድ .. እኛ ከኃላ እየተከተልን ምቀኛ የሆንንበት
አይ ልጅነትትትትትት
ቡጡዬ ... እክስሀለሁ .... በእህቴ በሉልኝ
ውይ ለካስ አሪፍ እህት የለኝም
አቦ ከሀረር አስመጣልሀለሁ ... በሉልኝ

ብሩኬ
እንደው ተባረክ አንተ ብቻ
አየኸው አይደል አንፈራራ የሚ ;ለውን
ለማንኛውም አመሰግንሀለሁ
በል አንተም አትጥፋ

ሰላም ሁኑልኝ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Feb 29, 2012 8:34 am    Post subject: Reply with quote

ባለ ሱቅ
ከሷ ጠባብ ሱቅህ ውስጥ ሆነህ የሀያ ሳንቲም ማስቲካ እያኘክህ አንድ አይነት ክብሪት ከምትቸረችር ምናለበት ግን ለዚያች ቀን እንኳን ወጣ ብትል ...ምኑስ ይታወቅ ነበር ...ባንተና በሷ ሰበብም ' አሰብ ሊመለስ ይችል ነበር ...ጨካኝ Smile

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:

+ ባለሱቅዬ ... አንድ ነገረ ብጠይቅህ ቅር ይልሀል
> የፈለግሽውን ጠይቂኝ ... አትፍሪኝ
+ በእግዚአብሄር ይዘኸኝ ጥፋ
ማይ ጋድ
እንዴት አስደነገጠችኝ መሰላቹ
> እንደሱ ማድረግ ግብታዊነት ነው ... አይሆንም
ዝም አለች ... በጣም ተከዘች
+ ሶሪ ስለጠየኩህ .. በቃ እርሳው .... ሶሪ ሶሪ
አቤት ፊቷ ሲቀላ እና እፍረቷ ሲያሳብቅባት ስታምር
እስካሁን ግን ለምን እንድንተኛ አልጠየከኝም .... ስትለኝ ግን ተጭበረበረብኝ
እምነቴን ነገርኳት .... የሰው ወርቅ የሰው ነው .... መነካካት ጥሩ አይደለም .... ወደ -ሌላ ነገር ይወስደናል
እንዲሁ በጥሩ ጓደኝነት .. እህትና ወንድምነት ብንቆይ የበለጠ ........ ጥሩ ነው .... አልኳት
ከራሴ ጋር እየተፈታተንኩ
አቤት ስለራሴ ሳወራ ማሳመር ስችልበት
ብታምኑም ባታምኑም የሆነው ይኸው ነው

ኦሮማይ

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Feb 29, 2012 2:11 pm    Post subject: Reply with quote

ጋሽ የተሞናሞነው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በጣም አሳቅከኝ
በቅድሚያ ለሰጠኸኝ አስተያየት አመሰግናለሁ
በተረፈ በሀሳብህ አልስማማም
ምክንያቱም እኔን ባለሱቅን አሰብ አያስጨንቀኝም
የህዝቡ ፍቅር እንጂ
ለአመታት የተተከለውን ጥላቻ ማስወገድና በፍቅር መኖር ነው የኔ ህልምም ምኞትም
ከተቻለ አንድ አገር ሆነን
ካልሆነ በኮንፌዴሬሽን
አለበለዚያ በጎረቤትነት ... በወንድማማችነት .. በፍቅር ... ለድሀው ህዝብ እየሰሩ መኖር
እንጂ አሰብ አያስጨንቀኝም
ገቢቶ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንድ ጉራጌ ምን እንዳለ ታውቃለህ ... ያን ብሄራዊ ውትድርና ተብሎ ታፍሶ ከሱቁ ተወሰደና
ወደ -ጦር ሜዳ በአይፋ መኪና ተጭኖ
ሲሄድ
ሲሄድ
ሲሄድ
አያልቅም
ጠየቀ አለቃውን
ሀምሳለቃ ... ጋሽ ሀምሳለቃ
ግን ይሄ ሁሉ መሬት የኢትዮጵያ ነው ... አለ ... ... ገዋኔን አልፈው ወደ -አፋር ድንበር እየተጠጉ ነበር ይህንንን ሲጠይቅ
ሀምሳለቃውም ... በሞራልና በቁጭት
አዎን ይህ ሁሉ የኛ የኢትዮጵያ መሬት ነው ... እኚህ ተገንጣይ ወንበዴዎች በአረብ ዶላር ሰክረው ሊሸጡብን ነው .. እነሱን ነው ልንዋጋ ምንሄደው .... ይለዋል
ጉሬው ተገርሞ
ግን ትርፍ ካወጣች ምናለ ብትሸጥ .... ያለንን አርሰን ከበላን አይበቃንም ... ይሄ ሁሉ አፉን ከፍቶ የተቀመጠ መሬት ይዘን .... ምን ያጣላናል ግን ,..... ብሎት እርፍ
በወኔ አጠገቡ የነበረው ሰው .... ታሪክስ .... ታሪካችንስ
ውይ እሱ ደሞ ምንድነው .... ዳቦ ይገዛል ...> ገንዘብ ያመጣል
አቤት እዛች አይፋ ውስጥ የነበረው ሰው የገላመጠውና የብሆዱ የሳቀው
አይ ጉሬ የኔ ቢጤ ....
እናልህ
አሰብን ሳይሆን ህዝቡን ልቡን መመለስ ቢቻል .. ያንን ነው የምመኘው
ለሱ ከሆነ ደሞ ገና ፊያሜታ ከእጃችን አልወጣችም
ያለችውም ኢትዮጵያ ነው
ካስፈለገህ አድራሻዋን ሰጥህና ... አንተ እንደሚሆን ታረግልኛለህ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደልከኝ

በተረፈ ሰላም እንሁን

በፍቅር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 01, 2012 8:23 am    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:13 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 01, 2012 3:14 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:16 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 01, 2012 4:33 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል !!!

Last edited by Gosa on Fri Jul 20, 2012 5:20 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 01, 2012 8:55 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ !!
በተጨማሪ 'ቀሽም ' ወይም 'ጣፋጭ ' ጉጂ የሚሉትስድቦችህ በጣም ተመችተውኛል :: ግፋበት :: ቢያንስ ጉጂ መሆኔን ያስታውሱኛል :: ደግሞ አዲሱ የነሞፊቲ ቤት በጣም ስላስቸገረኝ ትቼዋለሁ :: እነሀዶቆርሳ , አንፈራራንና አይፋን ሚስ ያረኳቸው ይመስለኛል :: እንደምንም ጎትጉተህ መልሳቸው እባክህን :: ይሄኔ እኮ ተደብቀው ያነቡት ይሆናል ይህንንም ቤት :: ማን ያውቃል ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 01, 2012 9:48 pm    Post subject: Reply with quote

ፈራሁኝ ብቻዬን መተኛት
እንዳለችህ በጣም እርግጠኛ ነኝ

ፕሊስስስስስስስስስስስ ጎሳ ወንድሜ
ብዙ ብዙ ነገር ነው ያስታወስከኝ
ናና ጨርስልኝ

አንተ ባለጌ ቤተስኪያን ውስጥ እያደርክ ... በአምላክ ቤት ውስጥ ልብህ ይወሰልታል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አንተን ነበር ይህንን የባህር ዛፍ እንጨት አሸክሞ ኮልፌ ገበያ ማስወጣት

በል ናና ጨርስልኝ
ብዙ ነገር እያስታወስከኝ ነው
እጠብቅሀለሁ እስክትጨርስ

ውይይይይይይይይይይይይይይ ታየችኝ ልጅቱ .... ብቻዋን በመስኮት በኩል ንፋሱና ጂኒው እየገቡ ሲአስቸግሯት ,... ፈራሁ ብላ አንተ ቤት ስትመጣ
አንተማ ... ቄስ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ድንቄም ዲያቆን

ቶሎ አቦ
ቀሽም ጉጂ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 355, 356, 357 ... 381, 382, 383  Next
Page 356 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia