WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
WHO WROTE THE BIBLE?
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 6:35 pm    Post subject: Re: አፋልጉኝ Reply with quote

ሠላም ሞጥሟጣው ወዳጄ

ሽማግሌዎቹ አልደረሱም እንዴ ? የልጅህን ነገር አደራ ... Wink

እኔኮ በበስጫ የለቀለቅከው "መልስ " ነው ብየ ነበር ችላ ማለቴ :: ጥያቄው አልገባህም ይሆን ? ማቴ 1: 17 እንዲህ ይላል

17 እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።

17.So all the generations from Abraham to David were fourteen generations, and from David to the deportation to Babylon fourteen generations, and from the deportation to Babylon to the Christ fourteen generations.

ትውልድ (Generation) ይላል እንጂ መሪ : አገረ -ገዢ ወይም ንጉስ አይልም Laughing ሁለት ወንድማማቾች ቢነግሱ ባይነግሱ አንድ ትውልድ ናቸው ገባህ Question እየተቆጠረ ያለው የዘር ሀረግ genealogy ነው :: ሶስት አጎቶችና ሁለት ወንድሞች ቢኖሩህ አንድ ወንድም ብቻ ከነበራቸው ከአያትህ እስከ ብቸኛዋ ልጅህ (እጮዬ Laughing) ድረስ አራት ትውልድ እንጂ አስር ትውልድ የለም Laughing

ባጭሩ ይህንን ጥያቄ እስከመቼውም አትመልሰውም :: አስራ አራተኛው ትውልድ ቆጠራው ላይ አልተካተተምና Exclamation

ጥብርኤል ይከተልህና Wink

ሠላም ሁንልኝ

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
በማቲዎስ ወንጌል 1:12-17 ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ 14 ትውልድ አለ ይላል :: የተዘረዘሩት ስሞች ደግሞ 13 ናቸው :: 14ኛው የት ገባ ???

አፋልጉኝ Very Happy

ከባቢሎን ምርኮ በፊት እና ከባቢሎን ምርኮ በኋላ የሚለውን ይዘህ ስትቆጥር በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ያለውን አንድ ጄኔሬሽን ረሳከው ? በዚያ ዘመን ያለው ትውልድስ የጠፋው 14 ትውልድ አይደለም ? 2 ነገሥት በግልጽ እንደተጻፈው የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄምና ወንድሞቹ ተፈራርቀው እንደነጋሶ ጊዳዳና እንደግርማ ወልደጊዮርጊስ እንደመለስ ተቀምጦ በሚያሽከረክራቸው ፈርዖን ተሹመው ለይስሙላ "ነገሡ ":: አባትና ልጅ ሆነው ተወራርሰው ሳይሆን በአንድ ትውልድ ያሉ ወንድማማቾች ስለሆኑ አንድ ትውልድ ተብለው ተቆጥረዋል :: የእስራኤልን የክብር ዕቃ ለፈሮኦን ያስገበሩ ማፈሪያዎች ስለሆኑ : ታሪካቸው በዝርዝር ቢታወቅም (2 ነገሥት 23-25): እስራኤል ፋስት ፎርዋርድ አድርገው የኢዮስያስን የልጅ ልጅ ኢኮንያንን ከምርኮ በኋላ ይቆጥሩታል :: እኛ ከኃይለ ሥላሴ በኋላ መንግሥቱ : ከመንግሥቱ ኃይለማርያም በኋላ መለስ እንጂ : ተፈሪ በንቲ አማን አንዶም ነጋሦ ግርማ ምናምን እንደማንለው ሁሉ ::

ግን ይህን 14ኛው ትውልድ ጥያቄ እስከመቼ ነው ሪሳይክል የምታደርጉት ?

ሰምቼ የማላውቀው ጥያቄ እስቲ ጠይቀኝ ? ሊሰለቸኝ ነው አለዚያ ::

ሃሃሃ !

ጸዋር የተመለሱ ጥያቄዎችን አይንህ ማንበብ አይችልም አይደል ?

አይ የዴዪስት ነገር !

በል እንግዲህ ጮሪት እንዳለችው መጽሐፍ ቅዱስን አስተካክለው ማንበብ ያቃታቸው የአቴዪስቶች ዌብሳይቶች የሚያወሩትን ጥያቄ እያመጣህ ስትዘረዝር ክረም ::

ፎር : ይህን 14ኛውን ትውልድ ጥያቄ ድጋሜ ሌላን ዋርካዊ በሌላ ጊዜ ደግሞ ትጠይቀዋለህ ::

ሰው በገዛ እጁ ሃይማኖት -የለሽ ሆኖ ኢንሴኪዩር ከሚሆን : በቅድሚያ አጣርቶ ማንበብ ቢለምድ እንዴት መልካም ነበር ?!

ሄድኩ !

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 7:30 pm    Post subject: Reply with quote

-------.................................------............................--------

1)አብርሃም ...............................1)ዳዊት ..........................1)ኢኮንያን

2)ይስሐቅ ..................................2)ሰሎሞን .......................2)ሰላትያል

3)ያዕቆብ ....................................3)ሮብዓም ......................3)ዘሩባቤል

4)ይሁዳ ....................................4)አቢያ ..........................4)አብዩድ

5ፋሬስ .......................................5)አሣፍ ..........................5)ኤልያቄም

6)ኤስሮም ..................................6)ኢዮሣፍጥ ...................6)አዛር

7)አራም .....................................7)ኢዮራም ......................7)ሳዶቅ

8)አሚናዳብ ...............................8)ዖዝያ ............................8)አኪም

9)ነአሶን .....................................9)ኢዮአታም ...................9)ኤልዩድ

10)ሰልሞን ..............................10)አካዝ .......................10)አልዓዛር

11)ቦኤዝ .................................11)ሕዝቅያስ .................11)ማታን

12)ኢዮቤድ .............................12)ምናሴ .......................12)ያዕቆብ

13)እሴይ ..................................13)አሞፅ .......................13)ዮሴፍ

14)ዳዊት ..................................14)ኢዮስያስ ..................14)ኢየሱስ

)ከአብርሃም እስከ ዳዊት -----)ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ------)ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 7:37 pm    Post subject: Reply with quote

ዘርሽ ባይሆን ያንተ ይሻላል :: ንጉስ ዳዊትን ሁለቴ በመቁጠር የጎደለውን ሞላከው Laughing

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
-------.................................------............................--------

1)አብርሃም ...............................1)ዳዊት ..........................1)ኢኮንያን

2)ይስሐቅ ..................................2)ሰሎሞን .......................2)ሰላትያል

3)ያዕቆብ ....................................3)ሮብዓም ......................3)ዘሩባቤል

4)ይሁዳ ....................................4)አቢያ ..........................4)አብዩድ

5ፋሬስ .......................................5)አሣፍ ..........................5)ኤልያቄም

6)ኤስሮም ..................................6)ኢዮሣፍጥ ...................6)አዛር

7)አራም .....................................7)ኢዮራም ......................7)ሳዶቅ

Coolአሚናዳብ ...............................Coolዖዝያ ............................Coolአኪም

9)ነአሶን .....................................9)ኢዮአታም ...................9)ኤልዩድ

10)ሰልሞን ..............................10)አካዝ .......................10)አልዓዛር

11)ቦኤዝ .................................11)ሕዝቅያስ .................11)ማታን

12)ኢዮቤድ .............................12)ምናሴ .......................12)ያዕቆብ

13)እሴይ ..................................13)አሞፅ .......................13)ዮሴፍ

14)ዳዊት ..................................14)ኢዮስያስ ..................14)ኢየሱስ

)ከአብርሃም እስከ ዳዊት -----)ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ------)ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 7:40 pm    Post subject: Reply with quote

18 እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና ::

19 እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና ::

20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና ::ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ ::ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ ::

22 ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ ::

23 የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ ::

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው ::

25 ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው :: እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው ::አሜን ::

26 ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው :: ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ ::

27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ ::ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ ::

28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ::

29 ዓመፃ ሁሉ ግፍ መመኘት ክፋት ሞላባቸው ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን ክርክርን ተንኰልን ክፉ ጠባይን ተሞሉ የሚያሾከሹኩ

30 ሐሜተኞች አምላክን የሚጠሉ የሚያንገላቱ ትዕቢተኞች ትምክህተኞች ክፋትን የሚፈላለጉ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ

31 የማያስተውሉ ውል የሚያፈርሱ ፍቅር የሌላቸው ምሕረት ያጡ ናቸው ::

32 እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም ::

-----------------------ሮሜ 1:18-32
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 8:03 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ዘርሽ ባይሆን ያንተ ይሻላል :: ንጉስ ዳዊትን ሁለቴ በመቁጠር የጎደለውን ሞላከው Laughingሰላም ፀዋር :-

ስህተት ናቸው ብለህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምታወጣቸው ነገሮች ባብዛኛው ሙስሊሞች የሚጠቅሷቸው ናቸው ::እኔ እንኳ ስህተት የሚባሉትን መሰብሰብ ከጀመርኩ ዓመታት አልፈዋል ::እስካሁን 274 የመዘገብኩ ሲሆን አንዳንዶቹን እራሴው መመለስ ችያለሁ ::የቀሩትንም በየጊዜው መልስ ለማግኘት እየጣርኩ ነው ::የትውልድ ቆጠራውን በሚመለከት ሙስሊሞቹም ሆነ አንተ ከላይ ያቀረብኩትን ዝርዝር ለምን እንደማትቀበሉት አይገባኝም !ግልጽ እኮ ነው ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዘርዐይ :

ያንተን 14 ትውልዶች አቆጣጠር ስመለከት : ኤልያቄም የተባለውን የኢዮአስ ልጅ እንዳላካተትከው ስላየሁ ላስተካክል መግባቴ ነው ::

ኢኮንያን የኢዮስያስ ልጅ ሳይሆን የልጅ ልጅ ነው :: በመሃላቸው የኢኮንያን አባት ኤልያቄም አለ :: ኤልያቄምና ወንድሞቹ እየተፈራረቁ ነግሰዋል :: የነርሱ ትውልድ አንድ ትውልድ ነው :: ታሪካቸው በጠቀስኩት ምዕራፍ ውስጥ አለ :: እስራኤል ከጠፋው ትውልድ ጋር ስለሚቆጥሯቸው አይጠቅሷቸውም ::

ጸዋር ከአያት ወደ ልጅ አንድ ትውልድ ዘልሎ የቆጠረውን ማቴዎስን በጣም ተናድዶበታልና ( Evil or Very Mad Evil or Very Mad ) ዝም ብሎ እንዲናደድበት ተወው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 9:03 pm    Post subject: Reply with quote

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ዘርዐይ :

ያንተን 14 ትውልዶች አቆጣጠር ስመለከት : ኤልያቄም የተባለውን የኢዮአስ ልጅ እንዳላካተትከው ስላየሁ ላስተካክል መግባቴ ነው ::

ኢኮንያን የኢዮስያስ ልጅ ሳይሆን የልጅ ልጅ ነው :: በመሃላቸው የኢኮንያን አባት ኤልያቄም አለ :: ኤልያቄምና ወንድሞቹ እየተፈራረቁ ነግሰዋል :: የነርሱ ትውልድ አንድ ትውልድ ነው :: ታሪካቸው በጠቀስኩት ምዕራፍ ውስጥ አለ :: እስራኤል ከጠፋው ትውልድ ጋር ስለሚቆጥሯቸው አይጠቅሷቸውም ::

ጸዋር ከአያት ወደ ልጅ አንድ ትውልድ ዘልሎ የቆጠረውን ማቴዎስን በጣም ተናድዶበታልና ( Evil or Very Mad Evil or Very Mad ) ዝም ብሎ እንዲናደድበት ተወው ::

ሰላም እናመሰግንሃለን :-

እኔ ዋቢ ያደረግኩት ማቴዎስ ላይ ያለውን ብቻ ነው ::በዚህም መሠረት ኢዮአስ የሚባል ካለመኖሩም በላይ ኢኮንያን የኢዮስያስ ልጅ እንጂ የልጅ ልጅ አይደለም ::በተጨማሪም ኤልያቄምን ጽፌዋለሁ እሱም የአብዩድ ልጅ ነው ::

በነገራችን ላይ እኔ የምጠቀመው 1980.. በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የታተመውንና በተለምዶ ሰማንያ አሃዱ የሚባለውን ነው ::አንተስ ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Mar 02, 2012 10:55 pm    Post subject: Reply with quote

ታድያስ ዘርዐይ :

እኔ የምጠቀመው መጽሀፍ ቅዱስ እዚሁ ኦንላይን ባይብል ሰርች ላይ ያለውን ነው ::

እየጻፍኩ ያለሁት ስለ አብዩድ ልጅ ኤልያቄም ሳይሆን : ስለ ኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም ነው :: ኤልያቄም በፈርዖን "ኢዮአቄም " ተብሎ ስሙ ተለውጧል :: (በበፊቱ ፖስቴ ኢዮስያስን አንዴ "ኢዮአስ " አንዴ "ኢዮስያስ " ብዬ ጽፌዋለሁ :: የኔ ስህተት ነው :; )

ሙሉ ዝርዝሩን 2 ነገሥት ምዕራፍ 23 እንደሚከተለው አስፍሬልሃለሁ :-

34 ፈርዖን ኒካዑም የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፥ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ኢዮአክስንም ወስዶ ወደ ግብጽ አፈለሰው በዚያም ሞተ።
35 ኢዮአቄምም ብሩንና ወርቁን ለፈርዖን ሰጠው እንደ ፈርዖንም ትእዛዝ ገንዘብ ይሰጥ ዘንድ ምድሩን አስገበረ ለፈርዖን ኒካዑም ይሰጥ ዘንድ ከአገሩ ሕዝብ ሁሉ እንደ ግምጋሜው ብርና ወርቅ አስከፈለ።
36 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ እናቱም ዘቢዳ ትባል ነበር እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች።
37 አባቶቹም እንዳደረጉ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

ዜና መቃዕል ቀዳማዊ ምዕራፍ 3 ላይ የሚከተለው ይገኛል :

13 ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥
14 ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮስያስ።
15 የኢዮስያስም ልጆች በኵሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም።
16 የኢዮአቄምም ልጆች ልጁ ኢኮንያን፥ ልጁ ሴዴቅያስ።
17 የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ መልኪራም፥
18 ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።
19 የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ የዘሩባቤልም ልጆች ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 12:15 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም

ዘርሽ ዳዊትን ሁለት ጊዜ መቁጠር አንችልም :: Simply because he can't represent two generations!

ሮሜ 1:18-32 በተመለከተ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም :: እምነት በፍርሀት አይጸናም : በእውቀት እንጂ :: / የሚወደድና የሚደነቅ እንጂ የሚፈራ አይደለም :: መፍራትስ ድንቁርናን Exclamation ይልቁንም ጥቅሱን ስለሚያምኑበትና በእ / መቅሰፍትም ስለሚያምኑ Very Happy ለወንድሞቼ ሞካሪና ዘእግዚነ ቁጥር 23 ጋብዝልኝ :: ይህን ካነበቡ ብኋላም ክርስቶስን (እግዚአብሄራቸውን ) በአንበሳ (ባለ አራት እግር እንስሳ ) በመሰየማቸው ምን እንደሚሰማቸው ጠይቅልኝ Wink የንስሩን የላሟንና የሰውን ነገር ለጊዜው እንተወዋለን ::

@@ ሞጥሟጣው

ያንተ አልሞት ባይ ተጋዳይነት የትም አያደርስም አልኩህ ::

አንተ እንደምትለው አባትና ልጅ ነግሰው ልጅ ብቻውን ተጽፎ ከሆነ ለምን የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም :: ምን መልስ አለህ ? ከጅምሩ ቁጥሩ ላይ (14 ተብሎ ) የተካተተ አባት (ኢዮአቄም ?) ለምን ስሙ ሳይጻፍ ቀረ ? ስም ላይ ሲደረስ እጅ የሚያዝበት ምክንያት ምንድን ነው ? ከላይ እንደተኮላተፍከው አይነት ምክንያት ተቀባይነት የለውም :: ምክንያቱም ሁሉም ክፉ ያደረጉ መሆናቸውን 2 ነገሥት ላይ ተጽፏልና :: ከነ ተፈሪ ባንቲ ጋር ለማመሳሰል የሞከረው ደግሞ ብስለት የጎደለው ነው :: ምክንያቱም ኢዩአቄም ከባቢሎን ምርኮ ብኋላ ለአስራ አንድ አመታት ነው የነገሰው :: ለአስራ አንድ ሰዓታት አልነበረም Laughing አስራአንድ አመት ደግሞ ትንሽ ሆኖ እንዲሁ በቀላሉ ግምት ውስጥ ሳይገባ የሚቀርበት ምክንያት ሊኖር አይችልም ::

በተለይ ደግሞ ይህን ጥያቄ በደንብ እንድትመልስ ይሁን ::
ሁለቱም አባት ኢዩአቄምና ልጅ ኢኮንያም ከባቢሎን ምርኮ ብኋላ የነገሱ ናቸው :: ስለዚህ ትውልዱ ሲቆጠር ከሰለሞን እስከ ባቢሎን ምርኮ 13 ከባቢሎን ምርኮ ብኋላ እስከ ክርስቶስ ድረስ 15 ትውልድ መሆኑ ነው Laughing

ለዛውም ክርስቶስ ያለ ግብረ ስጋ ግኑኝነት የተጸነሰ ሳይሆን ከዮሴፍ የተወለደ መሆኑን ከተቀበልን ነው :: አለበለዚያ ግን ሁላ ቆጠራ ከንቱ ይሆናል Idea

ስለዚህ የተሻለ ሙከራ አምጣ :: ወይም እኔ ጉዱን አፈርጥልሀለሁኝ Rolling Eyes
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 12:25 am    Post subject: Reply with quote

በድጋሚ ሰላም እናመሰግንሃለን :-

የፀዋርን ጥያቄ ለመመለስ መጽሐፈ ነገሥትና ዜና መዋዕልን ማጣቀሱ ጉዳዩን በይበልጥ ያወሳስበዋል ::ማቴዎስን ብቻ ብንወስድ ግን በማያሻማ ሁኔታ መልስ እናገኛለን ::በአንተ አመለካከት ማቴዎስ ላይ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም (ኢዮአቄም ) ሥም ተዘሏል ::ምክንያቱም ኢዮአኪን የልጁ ልጅ ነው ብለሃልና ::እኔ እንደሚመስለኝ ግን ማቴዎስ ላይ ኢዮስያስም ኢኮንያንና ወንድሞቹን ወለደ ስለሚል ኢኮንያን ልጁም የልጅ ልጁም እንዴት ሊሆን ይቻላል ? ኢኮንያን የኢዮአቂም የአዲስ ኪዳን ሥሙ ነው እንዳንል አጠራሩ ይለያያል ::በዚህ መሠረት የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያንና የአዲስ ኪዳኑ ኢኮንያን ሥመ ሞክሼነት ነው እንጂ አንድ ሰው አይደለም ::ለማንኛውም የብሉይ ኪዳኑ ግራ የሚያጋባ ስለሆነ ማቴዎስን ብቻ ይዘን ብንወያይይ ይሻላል ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12

Last edited by ዘርዐይ ደረስ on Sat Mar 03, 2012 12:42 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 12:32 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም

ዘርሽ ዳዊትን ሁለት ጊዜ መቁጠር አንችልም :: Simply because he can't represent two generations!

እንዴት አንችልም ?ማቴዎስ ላይ እኮ የሚለው ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ 14 ትውልድ ነው ::ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ታዲያ ?መጽሐፉ ሁለት ጊዜ እየቆጠረው እኛ አንድ ጊዜ ብቻ የምንቆጥርበት ምክንያት ነው ያልገባኝ ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 12:59 am    Post subject: Reply with quote

ይሄማ ትክክለኛ አቆጣጠር አይደለም ዘርሽ :: ምን ችግር አለው የምትል ከሆነ ደግሞ በባቢሎን ምርኮ የነበረውን ትውልድም ሁለቴ ልንቆጥር ነው :: ምክንያቱም "ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ... እንዲህውም ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ..." ነው የሚለውና ዳዊትን በሁለተኛ ረድፍ መጀመሪያ ላይ እንደደገምከው ሁሉ ኢዩሲያስን በሶስተኛው ረድፍ በድጋሚ በማስቀመጥ ደግመህ መቁጠር ሊጠበቅብህ ነው ::

ሠላም

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም

ዘርሽ ዳዊትን ሁለት ጊዜ መቁጠር አንችልም :: Simply because he can't represent two generations!

እንዴት አንችልም ?ማቴዎስ ላይ እኮ የሚለው ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14 ትውልድ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ 14 ትውልድ ነው ::ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ታዲያ ?መጽሐፉ ሁለት ጊዜ እየቆጠረው እኛ አንድ ጊዜ ብቻ የምንቆጥርበት ምክንያት ነው ያልገባኝ ::

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 4:22 am    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
በድጋሚ ሰላም እናመሰግንሃለን :-

የፀዋርን ጥያቄ ለመመለስ መጽሐፈ ነገሥትና ዜና መዋዕልን ማጣቀሱ ጉዳዩን በይበልጥ ያወሳስበዋል ::ማቴዎስን ብቻ ብንወስድ ግን በማያሻማ ሁኔታ መልስ እናገኛለን ::በአንተ አመለካከት ማቴዎስ ላይ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም (ኢዮአቄም ) ሥም ተዘሏል ::ምክንያቱም ኢዮአኪን የልጁ ልጅ ነው ብለሃልና ::እኔ እንደሚመስለኝ ግን ማቴዎስ ላይ ኢዮስያስም ኢኮንያንና ወንድሞቹን ወለደ ስለሚል ኢኮንያን ልጁም የልጅ ልጁም እንዴት ሊሆን ይቻላል ? ኢኮንያን የኢዮአቂም የአዲስ ኪዳን ሥሙ ነው እንዳንል አጠራሩ ይለያያል ::በዚህ መሠረት የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያንና የአዲስ ኪዳኑ ኢኮንያን ሥመ ሞክሼነት ነው እንጂ አንድ ሰው አይደለም ::ለማንኛውም የብሉይ ኪዳኑ ግራ የሚያጋባ ስለሆነ ማቴዎስን ብቻ ይዘን ብንወያይይ ይሻላል ::

ዘርዐይ :

በጸዋር አፋልጉኝ ማስታወቂያ ላይ : ከማቴዎስ ወንጌል ብቻ አፋልጉኝ የሚል ማስጠንቀቂያ ስላላየሁ : ዜና መዋዕልንም መጽሐፍ ነገሥትንም ተጠቅሜያለሁ ::

አይይ ... ከማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ፈልጋችሁ አምጡ ከተባለ : ባጭሩ : ኤልያቄምና የሱ ትውልድ : ማቴዎስ ወንጌል ላይ አልተጻፈም የሚል ይሆናል ::

ስለዚህ :

) መልሱ አልተሰጠም ይሆንና :-

መልሱ አልተሰጠም ማለት ግን ጥያቀው መልስ የለውም ማለት እንዳልሆነ የነመጽሐፈ ነገሥትንና ዜና መዋዕልን ምስክርነት በማስታወስ :

ውይይቱን ለሁለታችሁ እለቃለሁ ::

መልካም ውይይት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የንጋት ጮራ

ኮትኳች

Joined: 01 Jan 2006
Posts: 249

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 6:40 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
አንቺም ሆነ እኔ የተጻፈን ነገር አንብበን ካካበትነው "እውቀት " (ላንቺ ደግሞ እምነት ) ውጪ የራሳችን የሆነ የፈጠርነው ነገር የለም :: የዛሬ ሁለት አመት ነጭ ጫጭሮ አንድ ላይ ለባብዶ ጠርዞ ይዞልሽ የመጣውን መጽሀፍ ነው የህይወት መመሪያሽ አድርገሽው ከወገኖችሽ ጋር ጦር የምትማዘዢበት :: እንዲህውም ለነዛ ነጫጭባ መነኮሳት ስትሰግጂ የምትኖሪው Laughing እኔ ደግሞ ካንቺ ለየት የሚይደርገኝ እነሱ ያመጡትን መጽሀፍም ከነሱ በኋላ ሌሎች የጻፏቸውን መጻህፍቶችንም ቀላቅዬ በማንበብ በበቃኝ ሳልሸነፍ ዛሬም እጠይቃለሁ :: የዕውቀት ምንጭ ጥያቄ ነውና :: ገባሽ ልዩነታችን ?

1 ኛ፥ በመጀመሪያ የራስህ የሆነ ጥያቄ አለህ ወይ ? እምነት የሌላቸው ፈረንጆችና እስላሞች የጻፉትን እየቃረምክ ታመጣና የራስህ ጥያቄ አስመስለህ ታቀርባለህ። ይሄ ተስፋየ ሃቢሶ የተባለው ሰውየ እንዳደረገው አይነት የሰውን የራስህ አስመስለህ ማቅረብ ተራ አጭበርባሪነት ነው። እንዲያውም በጓደኛየ እንዲህ አደረኩ እያልክ ተመጻደክ። የጠቀስኩልህ ምሳሌ ስላልገባህ ነው ያላፈርከው። አይደል ? እንግዲህ ስልልገባህ አንባቢዎችም ወደፊት እንኳን የምታመጣውን ትችት እንዲያውቁት በዚህ ከፈረንጅ የቀዳሃቸውን ትችቶች ፈረንጅ መልስ ሰጥቶባቸው እዚህ አሉልህ። እንግዲህ አዲስ ትችት ከየት ልታመጣ ነው ? ያለፉት ትችቶችህ ወደፊትም ልታነሳ አስበሃቸው የነበሩት ትችቶች ሁሉ ከነመልሳቸው እዚህ አሉ። አሁን ምን ይሻልሃል ?

http://kingdavid8.com/Contradictions/Home.html

ወደፊት እንድታውቅ የሰው ሃሳብ የኔ ነው ብሎ ማቅረብ ከኪስ አውላቂነት ያልተለየ ወራዳ ምግባር ነው። አሁን ያውልህ ለፈረንጅህ ትችት ፈረንጅ መልስ ሰጥቶልሃል።

2 ነጭ ጫጭሮ ይዞልሽ መጣ ያልከው ስለዘጠኙ ቅዱሳን ልትነግረኝ ፈልገህ ከሆነ እነሱ የመጡት (መጽሃፍ ቅዱስንም የጠረዙት ) እግዚአብሔርን ሊያገለግሉ ወደተቀደሰ ምድር ነው። በአንጻሩ አንተ የምታመልካቸው ነጮች እነ ሪቻርድ ዶውኪንስ ፍልስፍናቸው ሁሉ አንተን አዋርደው እራሳቸውን ለማድለብ ነው (ስላልገባህ ነው እንጂ ) እግዚአብሔርን የሚያገለግል ነጭ ጥሩ ሰው ነው። እግዚአብሄርን የሚሰድብ ከሆነ ኢትዮጵያዊም ክፉ ነው።

3 - ከሰው አፈጣጠር የዳርዊን አዝጋሚ ለውጥ በስንት ጣሙ እያልክ ስትመጻደቅ ነው የሙሉጌታን ሊንክ ያቀረብኩልህ። በእውነት የራስህ የሆነ አእምሮ ኖሮህ ቢሆን ኖሮ ጸሃፊው ያቀረበውን ጸረ አዝጋሚ ለውጥ ግምጋሜ ተቃውመህ የራስህን ትንታኔ ትሰጣለህ ብየ አስቤ ነበር አልሆነም። አላነበብከውምና አንብበው ምክንያቱን ዝቅ ብሎ አንተ ያነሳሃቸውን ጥያቄዎች አስቀድሞ መልሷቸዋል። ወረቀት ኮምፒውተር ወዘተ ከሳይንስ ጋር ግንኙነት የላቸውም ነው ጸሃፊው የሚለው። እውነትነት አለው። በነገራችን ላይ ዳርዊናዊ አዝጋሚ ለውጥ እውነት ሊሆን እንደማይችል በሂሳብ ሰንጠረዥ ነው ያረጋገጠው። አንተ አጅሬ እንደተለመደው እንዳነበብክ ፕሪቴንድ አደረግክ። እውነት ነው ጸሃፊው በሳይንስ ላይ የተነሳው ማን ሊሰማው ያልከው። ሳይንስ ተሳስቷል ብሎ የሚቀበለው ሰው አይኖርም ምንም ያቀረበው ነጥብ አሳማኝ ቢሆንም። ስለሳይንስ የተናገረውን ደግሜ ሳነበው እውነት ነው። ሳይንስ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል በተለይ ጸሃፊው ያነሳቸውን ጉዳዮች ስናይ። አቅሙን አላወቀም ያልከው ዳዊት ከጎልያድ ጋር ሲፋጠጥ አቅሙን አላወቀም ተብሎ ነበር - ማን ያውቃል እንደ ዳዊት እግዚአብሄር ቢረዳውስ ?

ኢትዮጵያዊት ጮሪት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 10:18 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ :-

እናመሰግንሃለን :-እኔ እንደተረዳሁህ የማቴዎስ ወንጌል ላይ ስህተት አለ ብለህ አምነሃል ::እኔ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስህተት የለም ብዬ የማምን ነኝ ::በተረፈ መጽሐፈ ነገሥትና መጽሐፈ ዜና ማቴዎስን ለማጠናከር ጠቅመው ቢሆን ኖሮ ማቴዎስ ላይ ብቻ ላይ እናተኩር ባላልኩህ ነበር ::አንተ የፀዋርን ጥያቄ መልሼአለሁ ብለህ የምታምን ከሆነ የሚከተሉትን ቅራኔዎች እንዴት ታስታርቃቸዋለህ ?

1)መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ .23 .30 ላይ ''የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወሰዱት ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት '' ሲል ዜና መዋዕል ቀዳማዊ .3 .15 ላይ ደግሞ የኢዮስያስን ልጆች ሲዘረዝር ''በኩሩ ዮሐናን ሁለተኛውም ኢዮአቄም ሦስተኛውም ሴዴቅያስ አራተኛውም ሰሎም ይላል ::በዚህ መሠረት ኢዮአክስ ከየት መጣ ?

2)ፀዋር እንዳለውና እኔም እንደማምንበት የትውልድ ሐረጉ ከየ ትውልዱ አንዳንድ ሰው ብቻ ነው እንጂ የወሰደው ከአንድ ትውልድ ከአንድ በላይ ሰው መውሰድ አይቻልም ::

3)ማቴዎስ ላይ ኢዮስያስም ኢኮንያንና ወንድሞችን ወለደ ይላል ::ስለዚህ ይኸኛው ኢኮንያን አንተ የምትለውና መጽሐፈ ዜና ላይ የተጠቀሰው የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን አንድ አይደሉም ::

4)ማቴዎስን ብቻ ወስደን መልስ አናገኝም ያልከው ለምን እንደሆነ ግን ብታብራራልኝ ጥሩ ነው ::እኔ ግን ከላይ ያቀረብኩት ዝርዝር ላይ ምንም ዓይነት ጥያቄ የለኝም ::

5)የኢትዮጵያ መሪዎችን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ ለማብራራት ያደርግከው ሙከራ ራሱ ትክክል አይመስለኝም ::

ፀዋር :- በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢዮስያስም ኢኮንያንም የኖሩ ስለሆነ ማቴዎስ ኢዮስያስን ከመድገም ይልቅ ኢኮንያንን ቢወስድ ስህተቱ ምን ላይ ነው ::

የንጋት ጮራ :ያመጣሽው ሊንክ አሁን እያከራከረን ያለውን ጥያቄ ባይመልስም ሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ስላሉበት ለፀዋር ብቻ ሳይሆን ለሌሎቻችንም አስፈላጊ ነውና እናመሰግናለሁ ::
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
Page 5 of 9

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia