WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለማይድነው ወያናይ - ለስልኪ
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 9:05 pm    Post subject: ይድረስ ለማይድነው ወያናይ - ለስልኪ Reply with quote

ለስልኪ :-

በመጀመሪያ ደረጃ በወያኔነትህ ሣታፍርበት በግልፅ ስለምትናገር ለአንተ ለፖለቲካ ባላንጣዬ በዓላማህ ላለህ ጽኑነት አከብርሃለሁ :: ቀጥሎ የማቀርብልህ ሐተታ በአንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ላይ ድርጅታችሁ ስለሚፈጽመው ቅጥ ያጣ ናዚያዊ ተግባር ነው :: አቶ አንዷለም አራጌ የእናንተን የወያኔዎችን ሕገ -አራዊት ተቀብሎ በአገር ቤት "በሕጋዊና ሰላማዊ ትግል " የሚሣተፍ ፖለቲከኛ ነው :: ይህንን ፖለቲከኛ "በሽብር ፈጠራ ተግባር " ጠርጥራችሁ በቃሊቲ እሥር ቤት አጉራችሁታል :: ከእርሱም ሌላ በተመሣሣይ ወንጀል አቶ በቀለ ገርባ (ከኦፊዴን ) እንዲሁም ጋዜጠኛው እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም እናንተን ወያኔዎችን በግልፅ በአደባባይ የሚቃወሟችሁን ኢትዮጵያውያን ቃሊቲ አጉራችኋል : የጥፋተኝነት ብይንም ሠጥታችኋል :: ይህ እናንተ ወያኔዎች ለአለፉት 21 ዓመታት ያለምንም ገደብ እንዳሻችሁ ስትፈጽሙት የኖራችሁት የአመፅ ተግባር ስለሆነ እንደ አዲስ ማንሣቱ አስፈላጊ አይደለም :: ነገር ግን አቶ አንዷለም አራጌን በአንድ በነፍስ ግድያ ወንጀል ዕድሜ ልክ በተፈረደበት ኢባስ አስፋው በተባለ እሥረኛ ለማስገደል አቅዳችሁ ያስፈፀማችሁት ተግባር እናንተን ጭራሽ ከሰው ፍጡር መሆናችሁን ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል :: አቶ አንዷለም አራጌ ባለፈው የካቲት 25 ቀን 2004 .. ከቃሊቲ የዜጎች ማሠቃያ የላከውን ደብዳቤ ይዘት አንብበውና በዚህ የዋርካ ዓምድ እንደተለመደው በግልፅ የአንተን አቋም አሣውቀን ::

ምንጭ :- አንዷለም አራጌ : የኅሊና እሥረኛ : የካቲት 25 ቀን 2004 . : ከቃሊቲ ወኅኒ ቤት ::

Quote:
ለተከበሩ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ
ለተከበሩ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ

ወንድማዊ የአክብሮት ሰላምታዬ ይድረስዎ

በዚህ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በእኔ ላይ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ በተከበረዉ ጋዜጣዎ መዘገቡን ሰማሁ። በቅድሚያ ጋዜጣዎ እዉነትን ለማሳወቅ ስላደረገችዉ ጥረት ከልብ እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። በጣም አመሰግናለሁ !

በዚህ ለኑሮም ሆነ ለማሰብ ፍጹም በማይመች ሁኔታ፣ ለዚያዉም ከተፈጸመብኝ አሰቃቂ ድብደባ ሳላገግም፣ ብእርና ወረቀት እንዳገኝ የጎተጎተኝን ጉዳይ፣ ከዚህ እንደሚከተለዉ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።

ባለሁበት ወህኒ ቤት ጋዜጦችን ቀርቶ መጻህፍትንም ማስገባት ባለመቻሌ፣ እናንተ በምትኖሩባት «አለም» ከሚቀርበዉ የመረጃ ማእጽ መቋደስ አልችልም። እንደሌላዉ እስረኛ ሁሉ በሕገ መንግስቱ መሰረት እንዳልጠየቅ አሳሪዎቼ ቢከለክሉም፣ እንዲጠይቁኝ ከተፈቀደላቸው ሁለት ሶስት ቅርብ የቤተሰብ አባሎች አልፎ አልፎ ወሬ መቃመሴ ግን አልቀረም።

ይህን በመሰለ ሁኔታ ዉስጥ ወህኒ ቤቱ በእኔ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ፣ የሰጠዉን ምላሽ ይዘት በመስማቴ፣ ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ የመናገር ፍላጎት ባይኖረኝም፣ በቀጥታና በዝርዝር ማስረዳት እንደሚገባኝ ከራሴ ጋር ስምምነት ላይ ደረስኩ።

አሁን ካለሁበት የእሥር ሁኔታና ከገጠመኝ የጤና መቃወስ አንጻር ሃሳቤን በወጉ ለማደራጀት መቸገሬን ግንዛቤ ዉስጥ አስገብተዉ፣ ሃሳቤን በሚከተለዉ አኳኋን እንዳቀርብ መልካም ፍቃድዎ እንዲሆን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ለሁለት ወራት ገደማ በማእከላዊ እሥር ቤት ከቆየዉ በኋላ ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት መዛወሬ ይታወሳል። በቃሊቲም ከሌሎች፣ በአንድ መዝገብ ከተከሰስን ሰዎች ተነጥዬ፣ አሰቃቂ ወንጀል ፈጽመዉ ያታሰሩና በተደጋጋሚ እያመለጡ ያስቸገሩ እስረኞች ወደሚታሰሩበት (የቅጣት ቤት ) ተወሰድኩ። ገና እግሬ የወህኒ ቤቱን ቅጥር ከመርገጡ ለምን ወደዚህ አይነት ቦታ እንደተወሰድኩ ለሰሚዉ ግራ እንደሚሆን እገምታለሁ። በወህኒ ቤቱ ዉስጥ ግማሽ ቀን እንኳን ባልቆየሁበት ሁኔታ «ለአያያዝ አስቸግሮን፣ ልዩ ጥበቃ ( Maximum Security Zone) ዉስጥ አስገባነዉ» ሊባል አይችልም። ዉሳኔው ቀደም ሲል መከሰስ እንዳለብኝ ከወሰኑት አሳሪዎች እንደተላለፈ መገመት የሚከብድ ጉዳይ አይደለም።

አሳዛኙ ጉዳይ በዚች እጅግ ጠባብና አራት ማእዘን ሰማይ ብቻ በሚታይባት እሥር ቤት ተወርዉሬ የአሳሪዎቼ የበቀል በትር ያልተለየኝ መሆኑ ነዉ።

በዚች የጭንቅ ማማ ሁለት ወራት እያገባደድኩ በነበርኩበት አንድ ምሽት፣ ድብደባዉን የፈጸሙብኝ አቶ ይብሳ አስፋዉ እንዲቀላቀሉኝ ተደረገ። አብረዉኝ ከነበሩት ከኦፌዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ጋር በመሆን፣ ጎናቸዉን ያሳርፉበት ዘንድ ወለሉን ካመቻቸንላቸው በኋላ፣ የእሥር ሕይወታችንን ቀጠልን። የተከሰስንበትን ሁኔታ፣ ቀደም ሲል ያለንን የእስር ተመክሮዎችና እንዳዴም ግለታሪካችንን መጨዋወታችንን አልቀረም።

ካንደበታቸው በተደጋጋሚ እንደሰማነዉ በበርካታ የነፍስ ማጥፋትና ከባድ የዘረፋ ወንጀል ምክንያት እንደታሰሩ ገለጹልን። አክለዉም ከዶር ታዬ ወልደሰማያት ከአቶ ታምራት ላይኔና ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር እንደታሰሩ አጫወቱን። «ለምን እኝህ ሰዉ ተለይተዉ ከእነዚህ ፖለቲከኞች ጋር ታሰሩ ? » የሚለዉን ጥያቄ ግን መመለስ አልቻልንም።

በሂደት ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸዉ እስረኞች፣ የማረሚያ ቤቱ ሰላይ፣ በእነርሱ አገላለጽ «ወሬ አቀባይ» መሆናቸዉን አስረዱን። እርሳቸዉ ግን ሌላዉን ታሪክ ባይነግሩንም አሁን ያለንባት ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከታሰሩ የመጀመሪያዉ እስረኞች አንዱ ስለመሆናቸው ገለጹልን።

ቃሊቲ ዉስጥም ሆነ ዉጭ፣ ፊት ለፊት መናገር ወይንም መተግበር፣ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ብዬ አምናለሁ። 1998-1999 ባለው ጊዜ በአብዛኛዎቹ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ዞኖችና በከርቸሌ ጨለማ ቤት ድረስም ስታሰር፣ የተከተልኩት ዘይቤ ይሄንኑ ነዉ። በሂደቱም ከአንድም እስረኛ ጋር የኃይል ነገር ይቅርና ሃይለ ቃልም ተለዋዉጬ አላወቅም። «ቦዘኔ» ክልል ተብሎ ይታወቅ በነበረዉ ዞን እንኳን ይህን የመሰለ ነገር አልፈጸምኩም።

በጊዜዉ አብረዉኝ የታሰሩ ጓደኞቼ እንደሚያስታወሱት አልፎ አልፎ ፀቤ ከፖሊስ ጋር ነበር። ከፖሊስም ጋር ቢሆን የነበረኝ አለመግባባት «ለምን የእስረኛ መብት አይከበርም ? ለምን እስረኝ ይደበደባል ? » በሚል ነበር። ይሄንንም በግልጽና በአክብሮትከመግለጽ ዉጭ የተለየ አቀራረብ ኑሮኝ አያዉቅም። አቶ ይብሳ አስፋዉንም ቢሆን ለረጅም አመታት የታሰሩና የዔች አይቪ ታማሚ በመሆናቸው፣ ከማክበርና ከመንከባከብ ዉጭ አንዳች ቅር የሚያሰኝ ነገር ተናግሪያቸው ወይንም ፈጽሜባቸው አላውቅም።

ነገር ግን ገና አንድ ሳምንት ሳይሞላቸው ጀምሮ፣ በጋዜጣ ላይ ሊገለጹ የማይችሉ አያሌ ፈታኝ ነገሮች ያደርሱብኝ ጀመር። መዝለፍ የእለት ተእለት ሕይወቴ ሆነ። እንደ ድመት በጥፍሬ ቆሜ መዉጣትና መግባት የዘዉትር የአኗኗር ዘይቤዬ ሆነ። ከአለፈዉ እሥር ተመክሮዬ በመነሳት ያረጋጋቸዋል ብዬ የማስበዉን ነገር ሁሉ ባደርግም አልተሳካልኝም። ያለ አንዳች ማጋነን ክብራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከተናካሽ ዉሻ ጋር ከመታሰር ፈጽሞ የተለየ አልነበረም። ጊዜዉ እየገፋ ሲሄድ ተራ ስድብ እየተሰደብኩም ሁሉንም በጸጋ ከመቀበል ባለፈ ሌላ አማራጭ አላገኙሁም። አስቀድሜ እንደግለጽኩት ያለሁበት እሥር ቤት ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ የሆኑ እስረኞች በሌሎች የወህኒ ቤቱ ዞኖችማ አደገኛ የተባሉ እስረኞች ለቅጣት የሚመጡባት ቤት ነች።

ታዲያ ሰዉዬዉ እኔና ሌሎች በጣት የምንቆጠር እስረኞች ወዳለንበት ቅጥር ለምን መጡ ? ከቀድሞ የእሥር ቤት ቆይታዬ እንደተረዳሁት እስረኞችን እንዲሰልሉ የሚመደቡ እስረኞች አሉ። ስለደብዳቤዬ ከታሳሪዎች ከተረዳሁትን በላይ፣ በተለያዩ ወቅት ከተለያዩ ፖለቲከኞች ጋር መታሰራቸው ለምን ይሆን ? የሚለዉ ጥያቄ እየተመላለሰ ሳያሳስበኝ አልቀረም። መጀመሪያ ባይገባኝም፣ በእድሜ የተፈረደባቸው እስረኛ በመሆናቸው፣ 16 አመታትም እንደሚሉት የታሰሩ በመሆናቸዉ፣ ክፍለ ሃገር በዝዉዉር ቢሄዱ ኑሮ እስከአሁን ሊፈቱ ይችሉ እንደነበር በማንሳት ይቆጫሉ። ወደ ክፍለ ሃገር ለመዘዋወር ጠይቀዋል። እስከ አሁንም ባይዘዋወሩም ውትወታቸዉን ቀጥለዋል። የወህኒ ቤቱን ሃላፊዎች ከረጅም ቆይታቸው የተነሳ እስከቤተሰብ ድረስ እንደሚያወቋቸዉና የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸዉ በተደጋጋሚ ሊያስረዱን ሞክረዋል።

ከድብደባው 10 ቀናት በፊት ወደ ዋናዉ የወህኒ ቤቱ ሃላፊ ቢሮ ቀን በቀን ማለት ይቻላል፣ በጥበቃ ፖሊሶች አማካኝነት ይመላለሱ ነበር። ሁኔታዉ ለሁላችንም ግልጽ ነበር። የስለላ ስራ እየሰሩ ነበር። በዚያ ወቅት በእኔ በኩል በወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 148 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ለፍርድ ቤት ለማቅረብ በመጻፍ ላይ ነበርኩን። ወረቀቱንም ልነጠቅ እንደምችል የራሴን ግምት ወስጃለሁ። የተለየ አማራጭም ሆነ የሚደበቅ ጉዳይ ባለመኖሩ የመጣዉ ይምጣ ብዬ መጻፌን ቀጠልኩ። የኔ ሃሳብ የነበረዉ ወህኒ ቤቱ በፍተሻ ሰበብ ይወስድብኛል የሚል ነበር። የተፈጠረዉ ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ሆነ።

ግልሰቡ 6/6/2004 . ከሰዓት በኋላ እንደተለመደዉ ዋና አስተዳዳሪዉ ቢሮ ዉለው መጡ። እንደመጡም ፍራሻቸዉን አሁን ወዳሉበት ዞን ለመላክ ሲሞክሩ ግራ ከመጋባት በዘለለ የተለየ ሃሳብ አልያዝኩም። መጻፌን ግን ቀጥያለሁ። በዚያዉ እለት ማታ ሽንት ቤት ገብተዉ ሲወጡ ቧንቧ «ባለመዝጋታችሁ ዉሃ ፈሰሰብኝ » በማላት እናንተ ትናንሾች በማላት ሦስታችንንም በጅምላ ሰደቡን። አሰዳደባቸዉንና ሁኔታቸዉ ከሌላ ጊዜ የከረረና እንደምንም ምክንያት ፈልገዉ አካላዊ ግጭት ዉስጥ ለመግባት የመፈለግ ፍላጎት ይነበብባቸዉ ነበር።

ሶስታችንንም ለመሃላ እንኳን አንዳች ሳንተነፍስ ምሽቱም እየገፋ ነበርና እንደተገረፉ ሕጻናቶች አፋችንን ዉጠን ወለሉ ላይ እንደ አስክሬን ተገጥግጠን አንቀላፋን። በማግስቱ የግድያ ሙከራ ባደረጉብኝ ቀን፣ አርፍደዉ ከእንቅልፍ ነቁ። አቶ በቀለ ገርባ ያነባል። እኔ አሁንም እየጻፍኩ ነዉ። አቶ ይብሳ እንደተነሱ በመጮህ ያዘጋጀሁትን በሶ ትጠጣላችሁ አትጠጡም ?» አሉ። ሁለቱ የነርሱን ድርሻ መጠጣታቸዉን ሲገልጹ እኔ መጠጣት እንደማልፈልግ ገለጽኩላቸዉ። ይሄ የሆነዉ ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ ነዉ።

ስምንት ሰዓት ተኩል ሲሆን በፀጥታ የተቀመጥኩበት ክፍል በር በኃይል ተከፈተ። ደብዳቤዬ ለረጅም ሰዓት ከቤት ዉጭ ቆይቷል። ሃሳባቸው ሌሎች እስረኞች ሲወጡ ጠብቀዉ ዉሳኔያቸዉን ለመፈጸም እየተጠባበቁ ነበር። እንደተረዳሁት። በአጋጣሚ ሁላችንም በስራ በመጠመዳችን ከተቀመጥንበት አልወጣንም። ጊዜ እየመሸባቸው ስለነበር ያላቸው አማራጭ ባለዉ ሁኔታ እርምጃዉን መዉሰድ ነበር። በሩን እንደከፈቱ ተንደርድረዉ በመግባት አሳልፈዉ ይሰጡብኛል ብዬ የሰጋሁባቸዉን ወረቀቶች ከሌሎች ወረቀቶች እየለዩ፣ ጉዳዩን ይከታተሉ ስለነበር፣ ከያሉበት ለቀሟቸዉ። ከማስታወሻ ደብተሮች በተጨማሪ 40 ገጽ ወጥ ጽሁፍና ሌሎችም ሰነዶችን በጄ ላይ የነበረዉን ጨምረዉ ነጠቁኝ።

ይሄ ነገር እንደሚመጣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እጠብቀዉ ነበርና ዝምታን መረጥኩ። በበኩሌ ከማንም ሰዉ ጋር ቢሆን ግብግብ መግጠም አልፈልግም። ዝምታዬ መፍትሄ አልሆነም። ከተቀመጥኩበት ተንደርድረዉ ከኮንክሪት ግድግዳ ጋር አጣብቀዉ ጭንቅላቴን ረገጡኝ። ተንሸራትቼ በቀኝ ጎኔ የሰሚንቶዉን ወልል ላይ ተነጠፍኩ። አሁንም አልበረደም። ከወለሉ ላይ ጭንቅላቴን ሶስት ጊዜ እንደረገጡኝ አቶ በቀለ መሃል በመግባት ለማስጣል ሲሞክሩ በሰመመን ዉስጥ ሆኜ እሰማለሁ። «እገለዋለሁ። ብገለዉ ስድስት ወር ብቻ ነዉ ካቴና የሚገባልኝ» ይላሉ። አቶ በቀለንም ዘወር ካላለ እንደሚደበድቡት ይዝታሉ። «ደብድበኝ እንጂ ስትጨርሰዉ ዝም ብዬ አላይም» እያሉ ግብግብ ገጥሟል።

ከዚህ በኋላ ሌሎች እስረኞች በመጨመራቸዉ ወለሉ ላይ እንደወደኩ ደብዳቤዬን ገፋፍተዉ አስወጧቸዉ። ትንሽ ራሴን ማወቅ ስጀምር ጭንቅላቴ ላይ ድብደባ ስለተፈጸመብኝ ሕክምና የማግኝበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹልኝ ፖሊሶችን ጠየኩኝ።

የተከበሩ አዘጋጅ፡

እስካሁን የገለጽኩልዎ ሁሉ እዉነት ስለመሆኑ በፈጣሩ ስም አረጋግጥልዎታለሁ።

ከፍ ብዬ አጠቃላይ ሂደቱን ልገልጽልዎ ሞክሪያልሁ። አሁንም ደግሞ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር ሁኔታዉን አስመልክቶ በጋዜጣዎ ባወጣዉ ምላሽ ላይ የእኔን እምነት እንድገልጽ ፈቃድዎትንና ትእግስትዎትን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

እዉነቱን ለመናገር የእኔ ጉዳይ በአሳሪዎቼ በአቶ አመለስ እጅ እንጂ በወህኒ ቤቱ አሊያም በፍርድ ቤቱ እጅ ነዉ የሚል አንዳች ብዥታ ኑሮኝ አያወቅም።

ስለዚህ ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎችም ሆነ ከፖሊሶች ጋር ከወንድማማችነትና ከአክብሮት ዉጭ ሌላ የተከተልኩት መንገድ ኑሮ አያውቅም። ደብዳቢዬ አስተዳዳሪው ቢሮ ሲመለሱ ግን ምን እየተጋገረ እንደነበረ ለማሽተት ብዙ አስቸጋሪ አልነበረም። የግድያ ሙከራዉም ቢሆን አሳሪዎቼ የወህኒ አስተዳደሩን በመጠቀም ሊወስዱብኝ ያሰቡት እርምጃ ነዉ የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በታች የማነሳቸዉ ነጥቦች የግድያ ሙከራዉ በአሳሪዎቼ እንጅ በደብዳቤዬ የግል ፍላጎት ላለመፈጸሙ አሥረጅ ናቸዉ ብዬ አምናለሁ።

1 ከሌሎች እስረኞች ተነጥዬ ከመጀመሪያዉ እንዲህ አይነት ቦታ የገባሁት ይኼን መሰል እርምጃ ለመዉሰድ ያመች ዘንድ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

2 እስካሁን በነበረዉ የወህኒ ቤቱ አሰራር፣ በእስረኛ ላይ የግድያ ሙከራ የሚያደርግ ቀርቶ ግጭት እንኳን ቢፈጥር አስተዳደሩ በአፋጣኝ በካቴና አስሮ ማማ በማስገባት ቅጣት ይፈጽም ነበር። እኔን ለመግደል የሞከሩት እስረኛ ግን ሊቀጡ ቀርቶ ከሦስት ሳምንታት በላይ አንዳች ተግሳጽ እንኳን ሳይደርስባቸዉ እኛ ካለንበት በእጅጉ በተሻለ ቦታ ታስረዉ ይገኛሉ።

3 ችግሩ እንደተፈጠረ ተጠርተዉ የመጡት የአስተዳደሩ አባላት ለአቶ ኢብሳ የጀግና አቀባበል ነበር ያደረጉላቸዉ ማላት ይቻላል። «አንተ ፖሊስ ወይንም የአስተዳደሩ አባል ባለመሆንህ ሰነዱን ቀድሞዉንም መንጠቅ አልነበረብህም። አሁንም በአስቸኳይ መልስ» ማለት ሲገባቸዉ ሰነዶቹን በፈገግታ ተቀብለዉ ሰዉዬዉን ወደ ተሻለ ማረፊያ ቤት እኔን ደግሞ ባላሁበት ቅጣት ቤት እንድቀጥል አድርገዋል።

4 ተጎድቼ ወደ ሕክምና እንዲወስዱኝ በምጠይቅበት ሰዓት ቢሮ አስገብተዉ ወረቀቱን የነጠቁኝ የረሃብ አድማ ለማድረግ ሃሳብ ላይ መሆኔን ስለደረሱብኝ መሆኑንና የወህኒ ቤቱ አስተዳደርም ይሄኑ እንደሚጠረጥሩ ገለጹልኝ። በእኔ በኩል የሚባለዉ ነገር ፍጹም ሃሰትና ነገሩን ለማድበስበስ ተብሎ የቀረበ መሆኑን ገልጬ የግድያ ሙከራዉ ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸዉንና ንብረቴን ከእነርሱ እንደምጠብቅ አስረዳሁ።

5 በደረሰብኝ ከፍትኛ ድብደባ እስከ አሁኗ ሰዓት ደረስ ከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ብሆንም ተገቢዉን የሕክምና ክትትል ማግኘት አልቻልኩም፡፡ሌሊትም ሆነ ቀን ከፍተኛ የስቃይ ስሜት ሲሰማኝ፣ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ፖሊሶችና በጤና ጣቢያዉ ያሉ የሕክምና ባለሞያዎች የቻሉትን ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ግልጽ በሆነ የአቅም ዉስንነት ምክንያት ጊዜያዊ ማስታገሻዎችን ከማድረግ ባለፈ፣ ከስቃዬ ሊታደጉኝ አልቻሉም። ይሄ ሁኔታ በዉል እየታወቀ የተሻለ የሕክምና ክትትል በድንገተኛ እንኳን እንዳገኝ አለመደረጉ፣ ያልተፈለገዉ ሕይወቴ ይቀጥል ዘንድ ባይፈለግ ነዉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለኝ።

6 ክስ የምመሰርት ከሆነ በአስተዳዳሪዎቹ ተጠይቄ ነበር። ግለሰቡ በራሳቸዉ ተነሳሽነት አደረጉት ብዬ እንደማላምን በመግልጽ ፈቃደኛ አለመሆኔን ገለጽኹ። አክለዉም ምስክሮች እንዳሉኝ ጠይቀዉ እነርሱ የራሳቸዉን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዉ ቢሄዱም በጉዳዩ ላይ ከዚህ ግባ የሚባል ነገር ሳያደርጉ አያሌ ቀናት አልፈዋል። ይሄም እዉነት በግለሰቡ የተፈጸመ ቢሆን ኑሮ ጉዳዩ በዚህ ሁኔታ በቸልተኝነት እንደማይያዝ መረዳት አያስቸግርም።

7 የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎች የተወሰዱብኝን ሰነዶች ሙሉ በሙሉ እንዲመልሱልኝ ብጠይቅም፣ ቀደም ብለዉ በጋራ እያየን የሚመለስ ካለ እንደሚመለስ የማይመለስ ካለ ለምን እንዳማይመለስ እንደሚገለጹልኝ ነግረዉኝ ነበር፡ በአጋጣሚ አደጋዉ ከተፈጠረ በኋላ ተቀይረዉ የመጡት አስተዳደሮችም በተገለጸዉ መሰረት ይፈጽሙልኛል ብዬ ባስብም፣ አልተሳካም። ከወሰዷቸዉ ሰነዶች የፍርድ ቤት የክስ ወረቀቴንና አንድ የተገነጠለ የደብተር ሽፋንና የተቀደዱ አንዳች ነገር ያልተጻፈባቸዉ የተቀደዱ ወረቀቶችን መለሱልኝ። ብዙ የደከምኩባቸው ጽሁፎች የዉሃ ሽታ ሆኑ። በሁኔታዉ ማዘኔንና አዲስ እንደመሆናቸዉም ከእነርሱ ጋር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት እንደማልፈልግ ገልጬ፣ መብቴን እየገፈፉ ግን በዝምታ እንደማልቀጥል ስገልጽላቸዉ፣ ደብዳቢዬን ወረቀቶቹን ከሰጡዋቸው እንደሚጠይቋቸዉ፣ ካልመለሱላቸው ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ገለጹልኝ። «ዶሮን ሲያታልሏት» የሚባለዉ በእንዲህ ያለ ጊዜ ነዉ። አንድ እስረኛ ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ እንደሆነ ማን ሊያምን ይችላል ? ሰነዱንስ ቀደም ብለዉ ሊመልሱልኝ፣ የማይመመለስም ካላ ለምን የሚለዉን እንደሚያስረዱኝ ተገልጾልኝ እንደነበረ ዘንግተዉት ወይንስ…… . !

8 እየተፈጸመብኝ ያለዉ ግፍ ሳያንስና ጥዋትና ማታ ከሞት ጋር ግብግብ በገጠምኩበት ሁኔታ፣ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር በጋዜጣዎ ላይ ነገሩን ተራ ጉዳይ ተራ ግጭት አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ፣ ሃዘኔን አክብዶታል። ስቃዬንም አብዝቶታል። ከፍ ሲል የገለጽኩት የግድያ ሙከራ ሲፈጸምብኝ አንዳች ቃል እንዳልተነፈስኩ፣ ራሴንም እንኳን ለመከላከል እንጄን እንዳላነሳዉ በሚገባ እየተረዱ፣ ጉዳዩን የግድያ ሙከራ ሳይሆን ግጭት ለማስመሰል መሞከራቸዉ ከበደል ሁሉ የከፋ በደል ነዉ።

በሰዉነት ከተቸረኝ ክብር ዉጭ የምጠቅሰዉ ሌላ ክብር የለኝም። ነገር ግን የወህኒ ቤቱ እርምጃ እኔን ተራ አምባጓሮ ፈጣሪ በማስመሰል ለማብጠልጠል የታቀደ እንደሆነ እገነዘባለሁ።

ለመሆኑ ምንስ የሃሳብ ልዩነት ቢኖረኝ ሰዉነቴን ይጠራጠራሉ ? ወይንስ ኢትዮጵያዊነቴን ? ከእስር አያያዝ ጀመሮ ከፍ ብዬ እስከ 7 ተራ ቁጥር የገለጽኳቸዉ በደሎች ሳያንሱ እኔን እንደ ምግባረ ብልሹ አድርገዉ ለአንባቢ ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዝኖኛል።

በአጠቃላይ ወህኒ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ እያሳየ ያለዉ ነገር በገሃድ የሚያሳየዉ የጉዳዩ ባለቤት አሳሪዎቹ መሆናቸዉንና ያንንም ለመሸፈን ሲሉ ከፍ ያለ ዉጥረት ዉስጥ መግባታቸዉን ነዉ።

ነገር ግን ይሄን መሰሉ ተግባር ለተቋም ግንባታም ሆነ ወንድማማችነትን እና መልካም ሁኔታዎችን ሲፈጠር አይታየኝም። የፓርቲዬ የአንድነት ለዲሞርካሲና ለፍት ፓርቲ አላማ እንዲህ አይነት የሸፍጥኛ የመጠፋፋት አዙሪት ቆሞ ፍትህ፣ ዴሞርካሲ፣ ነጻነትና ወንድማማችነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማማየት ነዉ።

ክቡርነትዎ እንዲረዱልኝ የምፈልገዉ ይሄንን የመሰለ ደብዳቤ ስጽፍ ማንንም ለመበቀል ወይንም ለማንቋሸሽ ሳይሆን እዉነቱ ፍንጥቅ ብሎ እንዲወጣ፣ ስቃዬን ሕዝብ እንዲያዉልኝ ከመሻት የተነሳ መሆኑን ነዉ።

ለዚህ እዉነት ደግሞ ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ።

መቼም እኔ ባለሁበት ሁኔታ ያለ ሰዉ ነገር ቢያበዛ ቅር እንደማይሰኙ ተምምኜ፣ ነገሬን ዘለግ ማድረጌን ይረዱልኝ። ስለትብብርዎ በቅድሚያ እያመሰገንኩ እዉነቱን የማሳወቅ ስራዎ እንዲሳካ እመኛለሁ !!!

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደሊል

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 22 Dec 2003
Posts: 87

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 10:20 pm    Post subject: Reply with quote

በጣም ያሳዝናል
ወይ አገር !
ወይ ወገን !
ብዙ ብናወራ ምን ዋጋ አለው ::
በአንድም ነገር ላይ መስማማት የማንችል ነንና , እንዲህ ይጫወቱብን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
salar

ኮትኳች

Joined: 10 Feb 2012
Posts: 270

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 10:25 pm    Post subject: Re: ይድረስ ለማይድነው ወያናይ - ለስልኪ Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ነገር ግን አቶ አንዷለም አራጌን በአንድ በነፍስ ግድያ ወንጀል ዕድሜ ልክ በተፈረደበት ኢባስ አስፋው በተባለ እሥረኛ ለማስገደል አቅዳችሁ ያስፈፀማችሁት ተግባር እናንተን ጭራሽ ከሰው ፍጡር መሆናችሁን ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል :: አቶ አንዷለም አራጌ ባለፈው የካቲት 25 ቀን 2004 .. ከቃሊቲ የዜጎች ማሠቃያ የላከውን ደብዳቤ ይዘት አንብበውና በዚህ የዋርካ ዓምድ እንደተለመደው በግልፅ የአንተን አቋም አሣውቀን ::

do you have a proof that the government is planning to get him killed by prison criminal if you don't... why don't you keep your shit for yourself you dumb knucklehead. andualem is a Terrorist(at least a Terrorist Agent) working for ginbot7 and the government have proof of that period. so shove your dildo in your ass and Stfu you dumb.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2962

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 10:40 pm    Post subject: Reply with quote

አይ ዠግናው አንዱአለም Wink Laughing Laughing

ወያኔን አንቀጠቅጣለሁ ብሎ እምቡር እምቡር ሲል እንዳልነበር በአንድ ወፈፌ እስረኛ ማለቃቀስ ጀመረ Laughing Laughing Laughing

1. ሰውየውን ልከው አስደበደቡኝ ለሚለው ማስረጃ የለውም ....የሱ ማስረጃ "በሂደት ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸዉ እስረኞች፣ የማረሚያ ቤቱ ሰላይ፣ በእነርሱ አገላለጽ «ወሬ አቀባይ» መሆናቸዉን አስረዱን። " እንዲሁም "ከድብደባው 10 ቀናት በፊት ወደ ዋናዉ የወህኒ ቤቱ ሃላፊ ቢሮ ቀን በቀን ማለት ይቻላል፣ በጥበቃ ፖሊሶች አማካኝነት ይመላለሱ ነበር። ሁኔታዉ ለሁላችንም ግልጽ ነበር። የስለላ ስራ እየሰሩ ነበር። " Laughing Laughing Laughing

አንዱአለም የቃሊቲ ጠንቋይ ሆነ እንዴ Questionቅቅቅቅቅቅቅቅ ለግል ጉዳይ የወህኒ ሀላፊው ቢሮ መሄድ አይቻልም ወይስ እስረኛው ጉዳዩን በመጀመሪያ ለአንዱአለም ማስረዳት አለበት Question Laughing Laughing Laughing

2. እሱ ራሱ እንደገለፀው አቶ ይብሳ የተባሉት ታሳሪ ወደክፍለሀገር ለመዘዋወር ጠይቀዋል ;እስካሁንም እየወተወቱ ነው ....ታዲያ የጠበቀ ግንኙነት ካላቸው ወይንም "ሰላይ " ከሆኑ ለምን አልተዘዋወሩም ......አንዱአለም እስኪታሰር አስራስድስት አመት እየጠበቁ ይሆን Question Laughing Laughing Laughing

በተጨማሪም ግለሰቡ ወደክፍለሀገር ለመዛወር እየወተወቱ እንደሆነ ካወቀ ወደወህኒው ሀላፊ ጋር ቢመላለሱ ምን አስገረመው Question Wink

3. አቶ ይብሳ በመንግስት የተላከ ከሆነ እስከዛሬ ለምን እነዶ / ታዬን ; አቶ ታምራት ላይኔን ወይንም አቶ ስዬ አብርሀን አልደበደበም ; ወረቀታቸውን አልነጠቀም ......አቶ በቀለ ላይስ ለምን ተመሳሳይ ድብደባ አልፈፀመም Question Rolling Eyes

በመጨረሻም እስረኛ በሰብአዊ አያያዝ መያዝ እንዳለበት ባምንም የአንዱአለም ፉገራ ግን አሁንም ከወህኒ አላቋረጠም ......."ለዚህ እዉነት ደግሞ ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ። " ብሎ ፅፏል Laughing Laughing Laughing Laughing ታዲያ ለመሞት ዝግጁ ከሆነ ህክምና አላገኘሁም ብሎ ለምን ያለቅሳል Question Razz Razz

Quote:
በደረሰብኝ ከፍትኛ ድብደባ እስከ አሁኗ ሰዓት ደረስ ከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ብሆንም ተገቢዉን የሕክምና ክትትል ማግኘት አልቻልኩም፡፡
Laughing Laughing Laughing

በተጨማሪም አቶ ይብሳ ደብድበዉት ገና እግራቸው ከመውጣቱ በመጀመሪያ የተናገረው ይህንን ነው

Quote:
ትንሽ ራሴን ማወቅ ስጀምር ጭንቅላቴ ላይ ድብደባ ስለተፈጸመብኝ ሕክምና የማግኝበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹልኝ ፖሊሶችን ጠየኩኝ።

Laughing Laughing Laughing Laughing

"እሞትልሀለሁ አላልሽኝም ወይ .....እንኳን ልትሞችልኝ ሀኪም አስጠራሽ " Razz Razz Razz Razz

አቶ አንዱለም ......ያለኸው የመኖሪያ ቤትህ አይደለም ......በሰራኸው ጥፋት ምክንያት ወህኒ ቤት ውስጥ ነህ .....ቧንቧ ሳትዘጋ እየቀረህ አብሮህ የታሰረ እስረኛ ላይ ወሀ አታስፈስስ Laughing Laughing Laughing አለበለዚያ አንደኛህን ፍርድ ቤቱ የእስር ጊዜህን በሸራተን አዲስ እንድትፈፅም ይፈቅድልህ ዘንድ ደብዳቤ ፃፍ Laughing Laughing Laughing

መልካሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ ...እንደዠግና ቆፍጠን በል Wink

ሠላም
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትልቅ ሰው

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 122

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:27 pm    Post subject: Reply with quote

ይሄ ዳግማዊ የተባለው የትኍናም ትግሬዎችን አስተሳሰብ በደንብ ይወክላል :: አይደለም የጦር ምርኮኛን በሰላም ልትይዙ የህግ ታሳሪም ላይ እንዲህ ትኍናም ናችሑ :: ይህ ከፍርሀትና ከታናሽነት ስሜት የሚመነጭ ነው :: አንተም አሁን ንፍጣም ትግሬ እንድሆንህ አነጋገርህ ያስታውቃል :: እኔ እስካሁን ጥሩ ስነምግባር ያለው ትግሬ በህይወቴ አይቸ አላውቅም :: ሀገር ቤትም እዚህም :: ልቅ አፎች ናቸው :: ስብእና የላችሁም :: ቢያንስ እንደ ታሳሪ ይህ ሊደርስበት አይገባም እንኳን ማለት ደንቡ ቢሆንም ግን ከትግሬ ይህንን እንኳን ማየት ዘበት ሆንዋል ኢትዮጵያ ውስጥ :: ደግነቱ ትግሬ ለትንሽ ቀን ነው :: እንደ አጤ ዮሀንስ አሁን ይጠፋሉ ለሚቀጥሉት መቶ አመታት ያው አንበጣቸውን እንዲበሉ እናደርጋቸዋለን :: ነው ወይስ ቀን የወጣ መስሎዋችሁ አንበጣዎቹን አጥፍታኍቸው ይሆን Laughing Laughing ቂቂቂቂቅቂቂቂቂ

ዳግማዊ ዋለልኝ እንደጻፈ(ች)ው:
አይ ዠግናው አንዱአለም Wink Laughing Laughing

ወያኔን አንቀጠቅጣለሁ ብሎ እምቡር እምቡር ሲል እንዳልነበር በአንድ ወፈፌ እስረኛ ማለቃቀስ ጀመረ Laughing Laughing Laughing

1. ሰውየውን ልከው አስደበደቡኝ ለሚለው ማስረጃ የለውም ....የሱ ማስረጃ "በሂደት ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸዉ እስረኞች፣ የማረሚያ ቤቱ ሰላይ፣ በእነርሱ አገላለጽ «ወሬ አቀባይ» መሆናቸዉን አስረዱን። " እንዲሁም "ከድብደባው 10 ቀናት በፊት ወደ ዋናዉ የወህኒ ቤቱ ሃላፊ ቢሮ ቀን በቀን ማለት ይቻላል፣ በጥበቃ ፖሊሶች አማካኝነት ይመላለሱ ነበር። ሁኔታዉ ለሁላችንም ግልጽ ነበር። የስለላ ስራ እየሰሩ ነበር። " Laughing Laughing Laughing

አንዱአለም የቃሊቲ ጠንቋይ ሆነ እንዴ Questionቅቅቅቅቅቅቅቅ ለግል ጉዳይ የወህኒ ሀላፊው ቢሮ መሄድ አይቻልም ወይስ እስረኛው ጉዳዩን በመጀመሪያ ለአንዱአለም ማስረዳት አለበት Question Laughing Laughing Laughing

2. እሱ ራሱ እንደገለፀው አቶ ይብሳ የተባሉት ታሳሪ ወደክፍለሀገር ለመዘዋወር ጠይቀዋል ;እስካሁንም እየወተወቱ ነው ....ታዲያ የጠበቀ ግንኙነት ካላቸው ወይንም "ሰላይ " ከሆኑ ለምን አልተዘዋወሩም ......አንዱአለም እስኪታሰር አስራስድስት አመት እየጠበቁ ይሆን Question Laughing Laughing Laughing

በተጨማሪም ግለሰቡ ወደክፍለሀገር ለመዛወር እየወተወቱ እንደሆነ ካወቀ ወደወህኒው ሀላፊ ጋር ቢመላለሱ ምን አስገረመው Question Wink

3. አቶ ይብሳ በመንግስት የተላከ ከሆነ እስከዛሬ ለምን እነዶ / ታዬን ; አቶ ታምራት ላይኔን ወይንም አቶ ስዬ አብርሀን አልደበደበም ; ወረቀታቸውን አልነጠቀም ......አቶ በቀለ ላይስ ለምን ተመሳሳይ ድብደባ አልፈፀመም Question Rolling Eyes

በመጨረሻም እስረኛ በሰብአዊ አያያዝ መያዝ እንዳለበት ባምንም የአንዱአለም ፉገራ ግን አሁንም ከወህኒ አላቋረጠም ......."ለዚህ እዉነት ደግሞ ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ። " ብሎ ፅፏል Laughing Laughing Laughing Laughing ታዲያ ለመሞት ዝግጁ ከሆነ ህክምና አላገኘሁም ብሎ ለምን ያለቅሳል Question Razz Razz

Quote:
በደረሰብኝ ከፍትኛ ድብደባ እስከ አሁኗ ሰዓት ደረስ ከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ብሆንም ተገቢዉን የሕክምና ክትትል ማግኘት አልቻልኩም፡፡
Laughing Laughing Laughing

በተጨማሪም አቶ ይብሳ ደብድበዉት ገና እግራቸው ከመውጣቱ በመጀመሪያ የተናገረው ይህንን ነው

Quote:
ትንሽ ራሴን ማወቅ ስጀምር ጭንቅላቴ ላይ ድብደባ ስለተፈጸመብኝ ሕክምና የማግኝበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹልኝ ፖሊሶችን ጠየኩኝ።

Laughing Laughing Laughing Laughing

"እሞትልሀለሁ አላልሽኝም ወይ .....እንኳን ልትሞችልኝ ሀኪም አስጠራሽ " Razz Razz Razz Razz

አቶ አንዱለም ......ያለኸው የመኖሪያ ቤትህ አይደለም ......በሰራኸው ጥፋት ምክንያት ወህኒ ቤት ውስጥ ነህ .....ቧንቧ ሳትዘጋ እየቀረህ አብሮህ የታሰረ እስረኛ ላይ ወሀ አታስፈስስ Laughing Laughing Laughing አለበለዚያ አንደኛህን ፍርድ ቤቱ የእስር ጊዜህን በሸራተን አዲስ እንድትፈፅም ይፈቅድልህ ዘንድ ደብዳቤ ፃፍ Laughing Laughing Laughing

መልካሙን ሁሉ እመኝልሀለሁ ...እንደዠግና ቆፍጠን በል Wink

ሠላም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:32 pm    Post subject: Reply with quote

ሽምበል ተላ

ያኔ ጥንት አያትህ ሲቀለዱ "ቀልድ መደብ ላይ ነው " ይሉ ነበር :: መጀመርያ ነገር ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለች :: በህዝብ የተመረጠው መሪዋም ኦህአዴግ ይባላል :: ባገሪትዋ ውስጥ ደሞክራሲና ዴሞክራቲክ ህግ አሉ :: ሁለቱም እንደሰላሴ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ አንዱ ያላንዱ ሊኖር አይችልም :: በሌላ አማርኛ ለዴሞክራሲ ዋስትናው ህጉ ነው :: ምንም እንኳ አንተ ባጥቢያ ኮኮብ ድንጋይ ነክሰህ - ቀጠል በጥሰህ ለቁሉቢው ተሰልህ ላፈሰስከው ደም ሁሉ ነሰሀ ገበተህ እንዳው በድፍኑ ፈርጥጠህ አገር ለቀህ የወጣህ የከርሞ ኢትዮጵያዊ ብትሆነም ወደድክም ጠላህም ህጉን ማክበር የግድ ነው :: ስይበር ወስጥ ግን መቅደድና መስፋት መብትህ ናቸው :: ለስነ -አእምሮህ በጎነትም ይረደሀል - ቀደድ - ፎክር - ግን ይስተዋል ::
እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንዱአለም ነጻ ፍርድ -ቤት ቀርቦ አቃቤ - ህጉ ያቀረበበትን ክስ የመካድ መብት አለው :: የቀረበውን መረጃ የመጠየቅ - የማጣራት ወይም የራሱ ጠበቃ የመቅጠር መብት አለው :: ከዛ ውጭ ግን ሌላ ሌላ ነው ::

ሻምበል
እንዳው ሳስብክ በታም ፈሪ ነገር ነክ ::
ለምን ጫካ አትገባም ? እውነት ዘራፍ በልና ጫካ ግባ - አንተ ሙተህ ሌላው ይለፈለት :: ዳሩ ምን ያደርጋል ቀደዳ ሙያህ ነው ::
በል ሰፋው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮኮቴ

ውሃ አጠጪ

Joined: 04 Nov 2009
Posts: 1153

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:38 pm    Post subject: Re: ይድረስ ለማይድነው ወያናይ - ለስልኪ Reply with quote

አይ ተድላ ወንድሜ
በሚገባ አቅደውና አስበውበት ያስፈጸሙትን ይህንን ዘግናኝ ግፍ በተመለከተ ; እንዴት ከነ ስልኪ ምላሽ ትጠብቃለህ :: ታእቢት ውድቀትን ትቀድማለች እንዲል መጽሀፉ ; ከግዜ ወደ ግዜ እየተቆለለ የመጣው ግፋቸው አብቅቶ ; በማናለብኝነት የተነፋፋው ታእቢታቸው ጠራርጎአቸው የሚሄድበት ግዜ ተቃርቧል :: ወንድማችንን እግዚአብሄር ከክፉ ሁሉ ጠብቆት ከውድ ቤተሰቦቹ ጋር የሚገናኝበትን ግዜ እንዲያሳጥርለት የዘውትር ጸሎቴ ነው ::

ኮኮቴ
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ለስልኪ :-

በመጀመሪያ ደረጃ በወያኔነትህ ሣታፍርበት በግልፅ ስለምትናገር ለአንተ ለፖለቲካ ባላንጣዬ በዓላማህ ላለህ ጽኑነት አከብርሃለሁ :: ቀጥሎ የማቀርብልህ ሐተታ በአንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ላይ ድርጅታችሁ ስለሚፈጽመው ቅጥ ያጣ ናዚያዊ ተግባር ነው :: አቶ አንዷለም አራጌ የእናንተን የወያኔዎችን ሕገ -አራዊት ተቀብሎ በአገር ቤት "በሕጋዊና ሰላማዊ ትግል " የሚሣተፍ ፖለቲከኛ ነው :: ይህንን ፖለቲከኛ "በሽብር ፈጠራ ተግባር " ጠርጥራችሁ በቃሊቲ እሥር ቤት አጉራችሁታል :: ከእርሱም ሌላ በተመሣሣይ ወንጀል አቶ በቀለ ገርባ (ከኦፊዴን ) እንዲሁም ጋዜጠኛው እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም እናንተን ወያኔዎችን በግልፅ በአደባባይ የሚቃወሟችሁን ኢትዮጵያውያን ቃሊቲ አጉራችኋል : የጥፋተኝነት ብይንም ሠጥታችኋል :: ይህ እናንተ ወያኔዎች ለአለፉት 21 ዓመታት ያለምንም ገደብ እንዳሻችሁ ስትፈጽሙት የኖራችሁት የአመፅ ተግባር ስለሆነ እንደ አዲስ ማንሣቱ አስፈላጊ አይደለም :: ነገር ግን አቶ አንዷለም አራጌን በአንድ በነፍስ ግድያ ወንጀል ዕድሜ ልክ በተፈረደበት ኢባስ አስፋው በተባለ እሥረኛ ለማስገደል አቅዳችሁ ያስፈፀማችሁት ተግባር እናንተን ጭራሽ ከሰው ፍጡር መሆናችሁን ጥርጣሬ ውስጥ ይከታል :: አቶ አንዷለም አራጌ ባለፈው የካቲት 25 ቀን 2004 .. ከቃሊቲ የዜጎች ማሠቃያ የላከውን ደብዳቤ ይዘት አንብበውና በዚህ የዋርካ ዓምድ እንደተለመደው በግልፅ የአንተን አቋም አሣውቀን ::

ምንጭ :- አንዷለም አራጌ : የኅሊና እሥረኛ : የካቲት 25 ቀን 2004 . : ከቃሊቲ ወኅኒ ቤት ::

Quote:
ለተከበሩ የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ
ለተከበሩ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ

ወንድማዊ የአክብሮት ሰላምታዬ ይድረስዎ

በዚህ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በእኔ ላይ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ በተከበረዉ ጋዜጣዎ መዘገቡን ሰማሁ። በቅድሚያ ጋዜጣዎ እዉነትን ለማሳወቅ ስላደረገችዉ ጥረት ከልብ እንዳመሰግን ይፈቀድልኝ። በጣም አመሰግናለሁ !

በዚህ ለኑሮም ሆነ ለማሰብ ፍጹም በማይመች ሁኔታ፣ ለዚያዉም ከተፈጸመብኝ አሰቃቂ ድብደባ ሳላገግም፣ ብእርና ወረቀት እንዳገኝ የጎተጎተኝን ጉዳይ፣ ከዚህ እንደሚከተለዉ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።

ባለሁበት ወህኒ ቤት ጋዜጦችን ቀርቶ መጻህፍትንም ማስገባት ባለመቻሌ፣ እናንተ በምትኖሩባት «አለም» ከሚቀርበዉ የመረጃ ማእጽ መቋደስ አልችልም። እንደሌላዉ እስረኛ ሁሉ በሕገ መንግስቱ መሰረት እንዳልጠየቅ አሳሪዎቼ ቢከለክሉም፣ እንዲጠይቁኝ ከተፈቀደላቸው ሁለት ሶስት ቅርብ የቤተሰብ አባሎች አልፎ አልፎ ወሬ መቃመሴ ግን አልቀረም።

ይህን በመሰለ ሁኔታ ዉስጥ ወህኒ ቤቱ በእኔ የደረሰዉን የግድያ ሙከራ አስመልክቶ፣ የሰጠዉን ምላሽ ይዘት በመስማቴ፣ ቀደም ሲል በጉዳዩ ላይ የመናገር ፍላጎት ባይኖረኝም፣ በቀጥታና በዝርዝር ማስረዳት እንደሚገባኝ ከራሴ ጋር ስምምነት ላይ ደረስኩ።

አሁን ካለሁበት የእሥር ሁኔታና ከገጠመኝ የጤና መቃወስ አንጻር ሃሳቤን በወጉ ለማደራጀት መቸገሬን ግንዛቤ ዉስጥ አስገብተዉ፣ ሃሳቤን በሚከተለዉ አኳኋን እንዳቀርብ መልካም ፍቃድዎ እንዲሆን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ለሁለት ወራት ገደማ በማእከላዊ እሥር ቤት ከቆየዉ በኋላ ወደ ቃሊቲ ወህኒ ቤት መዛወሬ ይታወሳል። በቃሊቲም ከሌሎች፣ በአንድ መዝገብ ከተከሰስን ሰዎች ተነጥዬ፣ አሰቃቂ ወንጀል ፈጽመዉ ያታሰሩና በተደጋጋሚ እያመለጡ ያስቸገሩ እስረኞች ወደሚታሰሩበት (የቅጣት ቤት ) ተወሰድኩ። ገና እግሬ የወህኒ ቤቱን ቅጥር ከመርገጡ ለምን ወደዚህ አይነት ቦታ እንደተወሰድኩ ለሰሚዉ ግራ እንደሚሆን እገምታለሁ። በወህኒ ቤቱ ዉስጥ ግማሽ ቀን እንኳን ባልቆየሁበት ሁኔታ «ለአያያዝ አስቸግሮን፣ ልዩ ጥበቃ ( Maximum Security Zone) ዉስጥ አስገባነዉ» ሊባል አይችልም። ዉሳኔው ቀደም ሲል መከሰስ እንዳለብኝ ከወሰኑት አሳሪዎች እንደተላለፈ መገመት የሚከብድ ጉዳይ አይደለም።

አሳዛኙ ጉዳይ በዚች እጅግ ጠባብና አራት ማእዘን ሰማይ ብቻ በሚታይባት እሥር ቤት ተወርዉሬ የአሳሪዎቼ የበቀል በትር ያልተለየኝ መሆኑ ነዉ።

በዚች የጭንቅ ማማ ሁለት ወራት እያገባደድኩ በነበርኩበት አንድ ምሽት፣ ድብደባዉን የፈጸሙብኝ አቶ ይብሳ አስፋዉ እንዲቀላቀሉኝ ተደረገ። አብረዉኝ ከነበሩት ከኦፌዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ጋር በመሆን፣ ጎናቸዉን ያሳርፉበት ዘንድ ወለሉን ካመቻቸንላቸው በኋላ፣ የእሥር ሕይወታችንን ቀጠልን። የተከሰስንበትን ሁኔታ፣ ቀደም ሲል ያለንን የእስር ተመክሮዎችና እንዳዴም ግለታሪካችንን መጨዋወታችንን አልቀረም።

ካንደበታቸው በተደጋጋሚ እንደሰማነዉ በበርካታ የነፍስ ማጥፋትና ከባድ የዘረፋ ወንጀል ምክንያት እንደታሰሩ ገለጹልን። አክለዉም ከዶር ታዬ ወልደሰማያት ከአቶ ታምራት ላይኔና ከአቶ ስዬ አብርሃ ጋር እንደታሰሩ አጫወቱን። «ለምን እኝህ ሰዉ ተለይተዉ ከእነዚህ ፖለቲከኞች ጋር ታሰሩ ? » የሚለዉን ጥያቄ ግን መመለስ አልቻልንም።

በሂደት ለረጅም ጊዜ የሚያውቋቸዉ እስረኞች፣ የማረሚያ ቤቱ ሰላይ፣ በእነርሱ አገላለጽ «ወሬ አቀባይ» መሆናቸዉን አስረዱን። እርሳቸዉ ግን ሌላዉን ታሪክ ባይነግሩንም አሁን ያለንባት ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከታሰሩ የመጀመሪያዉ እስረኞች አንዱ ስለመሆናቸው ገለጹልን።

ቃሊቲ ዉስጥም ሆነ ዉጭ፣ ፊት ለፊት መናገር ወይንም መተግበር፣ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ብዬ አምናለሁ። 1998-1999 ባለው ጊዜ በአብዛኛዎቹ የቃሊቲ ወህኒ ቤት ዞኖችና በከርቸሌ ጨለማ ቤት ድረስም ስታሰር፣ የተከተልኩት ዘይቤ ይሄንኑ ነዉ። በሂደቱም ከአንድም እስረኛ ጋር የኃይል ነገር ይቅርና ሃይለ ቃልም ተለዋዉጬ አላወቅም። «ቦዘኔ» ክልል ተብሎ ይታወቅ በነበረዉ ዞን እንኳን ይህን የመሰለ ነገር አልፈጸምኩም።

በጊዜዉ አብረዉኝ የታሰሩ ጓደኞቼ እንደሚያስታወሱት አልፎ አልፎ ፀቤ ከፖሊስ ጋር ነበር። ከፖሊስም ጋር ቢሆን የነበረኝ አለመግባባት «ለምን የእስረኛ መብት አይከበርም ? ለምን እስረኝ ይደበደባል ? » በሚል ነበር። ይሄንንም በግልጽና በአክብሮትከመግለጽ ዉጭ የተለየ አቀራረብ ኑሮኝ አያዉቅም። አቶ ይብሳ አስፋዉንም ቢሆን ለረጅም አመታት የታሰሩና የዔች አይቪ ታማሚ በመሆናቸው፣ ከማክበርና ከመንከባከብ ዉጭ አንዳች ቅር የሚያሰኝ ነገር ተናግሪያቸው ወይንም ፈጽሜባቸው አላውቅም።

ነገር ግን ገና አንድ ሳምንት ሳይሞላቸው ጀምሮ፣ በጋዜጣ ላይ ሊገለጹ የማይችሉ አያሌ ፈታኝ ነገሮች ያደርሱብኝ ጀመር። መዝለፍ የእለት ተእለት ሕይወቴ ሆነ። እንደ ድመት በጥፍሬ ቆሜ መዉጣትና መግባት የዘዉትር የአኗኗር ዘይቤዬ ሆነ። ከአለፈዉ እሥር ተመክሮዬ በመነሳት ያረጋጋቸዋል ብዬ የማስበዉን ነገር ሁሉ ባደርግም አልተሳካልኝም። ያለ አንዳች ማጋነን ክብራቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከተናካሽ ዉሻ ጋር ከመታሰር ፈጽሞ የተለየ አልነበረም። ጊዜዉ እየገፋ ሲሄድ ተራ ስድብ እየተሰደብኩም ሁሉንም በጸጋ ከመቀበል ባለፈ ሌላ አማራጭ አላገኙሁም። አስቀድሜ እንደግለጽኩት ያለሁበት እሥር ቤት ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ የሆኑ እስረኞች በሌሎች የወህኒ ቤቱ ዞኖችማ አደገኛ የተባሉ እስረኞች ለቅጣት የሚመጡባት ቤት ነች።

ታዲያ ሰዉዬዉ እኔና ሌሎች በጣት የምንቆጠር እስረኞች ወዳለንበት ቅጥር ለምን መጡ ? ከቀድሞ የእሥር ቤት ቆይታዬ እንደተረዳሁት እስረኞችን እንዲሰልሉ የሚመደቡ እስረኞች አሉ። ስለደብዳቤዬ ከታሳሪዎች ከተረዳሁትን በላይ፣ በተለያዩ ወቅት ከተለያዩ ፖለቲከኞች ጋር መታሰራቸው ለምን ይሆን ? የሚለዉ ጥያቄ እየተመላለሰ ሳያሳስበኝ አልቀረም። መጀመሪያ ባይገባኝም፣ በእድሜ የተፈረደባቸው እስረኛ በመሆናቸው፣ 16 አመታትም እንደሚሉት የታሰሩ በመሆናቸዉ፣ ክፍለ ሃገር በዝዉዉር ቢሄዱ ኑሮ እስከአሁን ሊፈቱ ይችሉ እንደነበር በማንሳት ይቆጫሉ። ወደ ክፍለ ሃገር ለመዘዋወር ጠይቀዋል። እስከ አሁንም ባይዘዋወሩም ውትወታቸዉን ቀጥለዋል። የወህኒ ቤቱን ሃላፊዎች ከረጅም ቆይታቸው የተነሳ እስከቤተሰብ ድረስ እንደሚያወቋቸዉና የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸዉ በተደጋጋሚ ሊያስረዱን ሞክረዋል።

ከድብደባው 10 ቀናት በፊት ወደ ዋናዉ የወህኒ ቤቱ ሃላፊ ቢሮ ቀን በቀን ማለት ይቻላል፣ በጥበቃ ፖሊሶች አማካኝነት ይመላለሱ ነበር። ሁኔታዉ ለሁላችንም ግልጽ ነበር። የስለላ ስራ እየሰሩ ነበር። በዚያ ወቅት በእኔ በኩል በወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ 148 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት ለፍርድ ቤት ለማቅረብ በመጻፍ ላይ ነበርኩን። ወረቀቱንም ልነጠቅ እንደምችል የራሴን ግምት ወስጃለሁ። የተለየ አማራጭም ሆነ የሚደበቅ ጉዳይ ባለመኖሩ የመጣዉ ይምጣ ብዬ መጻፌን ቀጠልኩ። የኔ ሃሳብ የነበረዉ ወህኒ ቤቱ በፍተሻ ሰበብ ይወስድብኛል የሚል ነበር። የተፈጠረዉ ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ሆነ።

ግልሰቡ 6/6/2004 . ከሰዓት በኋላ እንደተለመደዉ ዋና አስተዳዳሪዉ ቢሮ ዉለው መጡ። እንደመጡም ፍራሻቸዉን አሁን ወዳሉበት ዞን ለመላክ ሲሞክሩ ግራ ከመጋባት በዘለለ የተለየ ሃሳብ አልያዝኩም። መጻፌን ግን ቀጥያለሁ። በዚያዉ እለት ማታ ሽንት ቤት ገብተዉ ሲወጡ ቧንቧ «ባለመዝጋታችሁ ዉሃ ፈሰሰብኝ » በማላት እናንተ ትናንሾች በማላት ሦስታችንንም በጅምላ ሰደቡን። አሰዳደባቸዉንና ሁኔታቸዉ ከሌላ ጊዜ የከረረና እንደምንም ምክንያት ፈልገዉ አካላዊ ግጭት ዉስጥ ለመግባት የመፈለግ ፍላጎት ይነበብባቸዉ ነበር።

ሶስታችንንም ለመሃላ እንኳን አንዳች ሳንተነፍስ ምሽቱም እየገፋ ነበርና እንደተገረፉ ሕጻናቶች አፋችንን ዉጠን ወለሉ ላይ እንደ አስክሬን ተገጥግጠን አንቀላፋን። በማግስቱ የግድያ ሙከራ ባደረጉብኝ ቀን፣ አርፍደዉ ከእንቅልፍ ነቁ። አቶ በቀለ ገርባ ያነባል። እኔ አሁንም እየጻፍኩ ነዉ። አቶ ይብሳ እንደተነሱ በመጮህ ያዘጋጀሁትን በሶ ትጠጣላችሁ አትጠጡም ?» አሉ። ሁለቱ የነርሱን ድርሻ መጠጣታቸዉን ሲገልጹ እኔ መጠጣት እንደማልፈልግ ገለጽኩላቸዉ። ይሄ የሆነዉ ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ ነዉ።

ስምንት ሰዓት ተኩል ሲሆን በፀጥታ የተቀመጥኩበት ክፍል በር በኃይል ተከፈተ። ደብዳቤዬ ለረጅም ሰዓት ከቤት ዉጭ ቆይቷል። ሃሳባቸው ሌሎች እስረኞች ሲወጡ ጠብቀዉ ዉሳኔያቸዉን ለመፈጸም እየተጠባበቁ ነበር። እንደተረዳሁት። በአጋጣሚ ሁላችንም በስራ በመጠመዳችን ከተቀመጥንበት አልወጣንም። ጊዜ እየመሸባቸው ስለነበር ያላቸው አማራጭ ባለዉ ሁኔታ እርምጃዉን መዉሰድ ነበር። በሩን እንደከፈቱ ተንደርድረዉ በመግባት አሳልፈዉ ይሰጡብኛል ብዬ የሰጋሁባቸዉን ወረቀቶች ከሌሎች ወረቀቶች እየለዩ፣ ጉዳዩን ይከታተሉ ስለነበር፣ ከያሉበት ለቀሟቸዉ። ከማስታወሻ ደብተሮች በተጨማሪ 40 ገጽ ወጥ ጽሁፍና ሌሎችም ሰነዶችን በጄ ላይ የነበረዉን ጨምረዉ ነጠቁኝ።

ይሄ ነገር እንደሚመጣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እጠብቀዉ ነበርና ዝምታን መረጥኩ። በበኩሌ ከማንም ሰዉ ጋር ቢሆን ግብግብ መግጠም አልፈልግም። ዝምታዬ መፍትሄ አልሆነም። ከተቀመጥኩበት ተንደርድረዉ ከኮንክሪት ግድግዳ ጋር አጣብቀዉ ጭንቅላቴን ረገጡኝ። ተንሸራትቼ በቀኝ ጎኔ የሰሚንቶዉን ወልል ላይ ተነጠፍኩ። አሁንም አልበረደም። ከወለሉ ላይ ጭንቅላቴን ሶስት ጊዜ እንደረገጡኝ አቶ በቀለ መሃል በመግባት ለማስጣል ሲሞክሩ በሰመመን ዉስጥ ሆኜ እሰማለሁ። «እገለዋለሁ። ብገለዉ ስድስት ወር ብቻ ነዉ ካቴና የሚገባልኝ» ይላሉ። አቶ በቀለንም ዘወር ካላለ እንደሚደበድቡት ይዝታሉ። «ደብድበኝ እንጂ ስትጨርሰዉ ዝም ብዬ አላይም» እያሉ ግብግብ ገጥሟል።

ከዚህ በኋላ ሌሎች እስረኞች በመጨመራቸዉ ወለሉ ላይ እንደወደኩ ደብዳቤዬን ገፋፍተዉ አስወጧቸዉ። ትንሽ ራሴን ማወቅ ስጀምር ጭንቅላቴ ላይ ድብደባ ስለተፈጸመብኝ ሕክምና የማግኝበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹልኝ ፖሊሶችን ጠየኩኝ።

የተከበሩ አዘጋጅ፡

እስካሁን የገለጽኩልዎ ሁሉ እዉነት ስለመሆኑ በፈጣሩ ስም አረጋግጥልዎታለሁ።

ከፍ ብዬ አጠቃላይ ሂደቱን ልገልጽልዎ ሞክሪያልሁ። አሁንም ደግሞ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር ሁኔታዉን አስመልክቶ በጋዜጣዎ ባወጣዉ ምላሽ ላይ የእኔን እምነት እንድገልጽ ፈቃድዎትንና ትእግስትዎትን በአክብሮት እጠይቃለሁ።

እዉነቱን ለመናገር የእኔ ጉዳይ በአሳሪዎቼ በአቶ አመለስ እጅ እንጂ በወህኒ ቤቱ አሊያም በፍርድ ቤቱ እጅ ነዉ የሚል አንዳች ብዥታ ኑሮኝ አያወቅም።

ስለዚህ ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎችም ሆነ ከፖሊሶች ጋር ከወንድማማችነትና ከአክብሮት ዉጭ ሌላ የተከተልኩት መንገድ ኑሮ አያውቅም። ደብዳቢዬ አስተዳዳሪው ቢሮ ሲመለሱ ግን ምን እየተጋገረ እንደነበረ ለማሽተት ብዙ አስቸጋሪ አልነበረም። የግድያ ሙከራዉም ቢሆን አሳሪዎቼ የወህኒ አስተዳደሩን በመጠቀም ሊወስዱብኝ ያሰቡት እርምጃ ነዉ የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በታች የማነሳቸዉ ነጥቦች የግድያ ሙከራዉ በአሳሪዎቼ እንጅ በደብዳቤዬ የግል ፍላጎት ላለመፈጸሙ አሥረጅ ናቸዉ ብዬ አምናለሁ።

1 ከሌሎች እስረኞች ተነጥዬ ከመጀመሪያዉ እንዲህ አይነት ቦታ የገባሁት ይኼን መሰል እርምጃ ለመዉሰድ ያመች ዘንድ ነዉ ብዬ አምናለሁ።

2 እስካሁን በነበረዉ የወህኒ ቤቱ አሰራር፣ በእስረኛ ላይ የግድያ ሙከራ የሚያደርግ ቀርቶ ግጭት እንኳን ቢፈጥር አስተዳደሩ በአፋጣኝ በካቴና አስሮ ማማ በማስገባት ቅጣት ይፈጽም ነበር። እኔን ለመግደል የሞከሩት እስረኛ ግን ሊቀጡ ቀርቶ ከሦስት ሳምንታት በላይ አንዳች ተግሳጽ እንኳን ሳይደርስባቸዉ እኛ ካለንበት በእጅጉ በተሻለ ቦታ ታስረዉ ይገኛሉ።

3 ችግሩ እንደተፈጠረ ተጠርተዉ የመጡት የአስተዳደሩ አባላት ለአቶ ኢብሳ የጀግና አቀባበል ነበር ያደረጉላቸዉ ማላት ይቻላል። «አንተ ፖሊስ ወይንም የአስተዳደሩ አባል ባለመሆንህ ሰነዱን ቀድሞዉንም መንጠቅ አልነበረብህም። አሁንም በአስቸኳይ መልስ» ማለት ሲገባቸዉ ሰነዶቹን በፈገግታ ተቀብለዉ ሰዉዬዉን ወደ ተሻለ ማረፊያ ቤት እኔን ደግሞ ባላሁበት ቅጣት ቤት እንድቀጥል አድርገዋል።

4 ተጎድቼ ወደ ሕክምና እንዲወስዱኝ በምጠይቅበት ሰዓት ቢሮ አስገብተዉ ወረቀቱን የነጠቁኝ የረሃብ አድማ ለማድረግ ሃሳብ ላይ መሆኔን ስለደረሱብኝ መሆኑንና የወህኒ ቤቱ አስተዳደርም ይሄኑ እንደሚጠረጥሩ ገለጹልኝ። በእኔ በኩል የሚባለዉ ነገር ፍጹም ሃሰትና ነገሩን ለማድበስበስ ተብሎ የቀረበ መሆኑን ገልጬ የግድያ ሙከራዉ ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸዉንና ንብረቴን ከእነርሱ እንደምጠብቅ አስረዳሁ።

5 በደረሰብኝ ከፍትኛ ድብደባ እስከ አሁኗ ሰዓት ደረስ ከፍተኛ ስቃይ ዉስጥ ብሆንም ተገቢዉን የሕክምና ክትትል ማግኘት አልቻልኩም፡፡ሌሊትም ሆነ ቀን ከፍተኛ የስቃይ ስሜት ሲሰማኝ፣ በጥበቃ ላይ የሚገኙ ፖሊሶችና በጤና ጣቢያዉ ያሉ የሕክምና ባለሞያዎች የቻሉትን ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም ግልጽ በሆነ የአቅም ዉስንነት ምክንያት ጊዜያዊ ማስታገሻዎችን ከማድረግ ባለፈ፣ ከስቃዬ ሊታደጉኝ አልቻሉም። ይሄ ሁኔታ በዉል እየታወቀ የተሻለ የሕክምና ክትትል በድንገተኛ እንኳን እንዳገኝ አለመደረጉ፣ ያልተፈለገዉ ሕይወቴ ይቀጥል ዘንድ ባይፈለግ ነዉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አለኝ።

6 ክስ የምመሰርት ከሆነ በአስተዳዳሪዎቹ ተጠይቄ ነበር። ግለሰቡ በራሳቸዉ ተነሳሽነት አደረጉት ብዬ እንደማላምን በመግልጽ ፈቃደኛ አለመሆኔን ገለጽኹ። አክለዉም ምስክሮች እንዳሉኝ ጠይቀዉ እነርሱ የራሳቸዉን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዉ ቢሄዱም በጉዳዩ ላይ ከዚህ ግባ የሚባል ነገር ሳያደርጉ አያሌ ቀናት አልፈዋል። ይሄም እዉነት በግለሰቡ የተፈጸመ ቢሆን ኑሮ ጉዳዩ በዚህ ሁኔታ በቸልተኝነት እንደማይያዝ መረዳት አያስቸግርም።

7 የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎች የተወሰዱብኝን ሰነዶች ሙሉ በሙሉ እንዲመልሱልኝ ብጠይቅም፣ ቀደም ብለዉ በጋራ እያየን የሚመለስ ካለ እንደሚመለስ የማይመለስ ካለ ለምን እንዳማይመለስ እንደሚገለጹልኝ ነግረዉኝ ነበር፡ በአጋጣሚ አደጋዉ ከተፈጠረ በኋላ ተቀይረዉ የመጡት አስተዳደሮችም በተገለጸዉ መሰረት ይፈጽሙልኛል ብዬ ባስብም፣ አልተሳካም። ከወሰዷቸዉ ሰነዶች የፍርድ ቤት የክስ ወረቀቴንና አንድ የተገነጠለ የደብተር ሽፋንና የተቀደዱ አንዳች ነገር ያልተጻፈባቸዉ የተቀደዱ ወረቀቶችን መለሱልኝ። ብዙ የደከምኩባቸው ጽሁፎች የዉሃ ሽታ ሆኑ። በሁኔታዉ ማዘኔንና አዲስ እንደመሆናቸዉም ከእነርሱ ጋር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት እንደማልፈልግ ገልጬ፣ መብቴን እየገፈፉ ግን በዝምታ እንደማልቀጥል ስገልጽላቸዉ፣ ደብዳቢዬን ወረቀቶቹን ከሰጡዋቸው እንደሚጠይቋቸዉ፣ ካልመለሱላቸው ግን ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ገለጹልኝ። «ዶሮን ሲያታልሏት» የሚባለዉ በእንዲህ ያለ ጊዜ ነዉ። አንድ እስረኛ ከወህኒ ቤቱ አቅም በላይ እንደሆነ ማን ሊያምን ይችላል ? ሰነዱንስ ቀደም ብለዉ ሊመልሱልኝ፣ የማይመመለስም ካላ ለምን የሚለዉን እንደሚያስረዱኝ ተገልጾልኝ እንደነበረ ዘንግተዉት ወይንስ…… . !

8 እየተፈጸመብኝ ያለዉ ግፍ ሳያንስና ጥዋትና ማታ ከሞት ጋር ግብግብ በገጠምኩበት ሁኔታ፣ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር በጋዜጣዎ ላይ ነገሩን ተራ ጉዳይ ተራ ግጭት አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ፣ ሃዘኔን አክብዶታል። ስቃዬንም አብዝቶታል። ከፍ ሲል የገለጽኩት የግድያ ሙከራ ሲፈጸምብኝ አንዳች ቃል እንዳልተነፈስኩ፣ ራሴንም እንኳን ለመከላከል እንጄን እንዳላነሳዉ በሚገባ እየተረዱ፣ ጉዳዩን የግድያ ሙከራ ሳይሆን ግጭት ለማስመሰል መሞከራቸዉ ከበደል ሁሉ የከፋ በደል ነዉ።

በሰዉነት ከተቸረኝ ክብር ዉጭ የምጠቅሰዉ ሌላ ክብር የለኝም። ነገር ግን የወህኒ ቤቱ እርምጃ እኔን ተራ አምባጓሮ ፈጣሪ በማስመሰል ለማብጠልጠል የታቀደ እንደሆነ እገነዘባለሁ።

ለመሆኑ ምንስ የሃሳብ ልዩነት ቢኖረኝ ሰዉነቴን ይጠራጠራሉ ? ወይንስ ኢትዮጵያዊነቴን ? ከእስር አያያዝ ጀመሮ ከፍ ብዬ እስከ 7 ተራ ቁጥር የገለጽኳቸዉ በደሎች ሳያንሱ እኔን እንደ ምግባረ ብልሹ አድርገዉ ለአንባቢ ለማቅረብ መሞከራቸው አሳዝኖኛል።

በአጠቃላይ ወህኒ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ እያሳየ ያለዉ ነገር በገሃድ የሚያሳየዉ የጉዳዩ ባለቤት አሳሪዎቹ መሆናቸዉንና ያንንም ለመሸፈን ሲሉ ከፍ ያለ ዉጥረት ዉስጥ መግባታቸዉን ነዉ።

ነገር ግን ይሄን መሰሉ ተግባር ለተቋም ግንባታም ሆነ ወንድማማችነትን እና መልካም ሁኔታዎችን ሲፈጠር አይታየኝም። የፓርቲዬ የአንድነት ለዲሞርካሲና ለፍት ፓርቲ አላማ እንዲህ አይነት የሸፍጥኛ የመጠፋፋት አዙሪት ቆሞ ፍትህ፣ ዴሞርካሲ፣ ነጻነትና ወንድማማችነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለማማየት ነዉ።

ክቡርነትዎ እንዲረዱልኝ የምፈልገዉ ይሄንን የመሰለ ደብዳቤ ስጽፍ ማንንም ለመበቀል ወይንም ለማንቋሸሽ ሳይሆን እዉነቱ ፍንጥቅ ብሎ እንዲወጣ፣ ስቃዬን ሕዝብ እንዲያዉልኝ ከመሻት የተነሳ መሆኑን ነዉ።

ለዚህ እዉነት ደግሞ ግራና ቀኛቸዉን ለይተዉ ከማያወቁ ልጆቼ ተለይቼ ዘመኔን በሙሉ በወርደት ለመጨረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለመሞትም ዝግጁ መሆኔን አሳዳጆቼ እንዲያወቁት እወዳለሁ።

መቼም እኔ ባለሁበት ሁኔታ ያለ ሰዉ ነገር ቢያበዛ ቅር እንደማይሰኙ ተምምኜ፣ ነገሬን ዘለግ ማድረጌን ይረዱልኝ። ስለትብብርዎ በቅድሚያ እያመሰገንኩ እዉነቱን የማሳወቅ ስራዎ እንዲሳካ እመኛለሁ !!!

ተድላ

_________________
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:42 pm    Post subject: Reply with quote

አንተ ግን አሲምባ ግድ የለህም ደደብ ነህ ...እውነት አይደለም ወይ Rolling Eyes እች ጥቁር ቀይ ቀለም ዛሬ እነ ክብሮም ሲጠቀሙባት አይቼ ተመችታኛለች Laughing አሲምባ ግን ላስታውስህ ቅል ራስ ነህ ...አንተን ብዬ እኮ ነው እዚህ የመጣሁት አንተ የአረቄ ኮዳ Laughing

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:
ሽምበል ተላ

ያኔ ጥንት አያትህ ሲቀለዱ "ቀልድ መደብ ላይ ነው " ይሉ ነበር :: መጀመርያ ነገር ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለች :: በህዝብ የተመረጠው መሪዋም ኦህአዴግ ይባላል :: ባገሪትዋ ውስጥ ደሞክራሲና ዴሞክራቲክ ህግ አሉ :: ሁለቱም እንደሰላሴ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ አንዱ ያላንዱ ሊኖር አይችልም :: በሌላ አማርኛ ለዴሞክራሲ ዋስትናው ህጉ ነው :: ምንም እንኳ አንተ ባጥቢያ ኮኮብ ድንጋይ ነክሰህ - ቀጠል በጥሰህ ለቁሉቢው ተሰልህ ላፈሰስከው ደም ሁሉ ነሰሀ ገበተህ እንዳው በድፍኑ ፈርጥጠህ አገር ለቀህ የወጣህ የከርሞ ኢትዮጵያዊ ብትሆነም ወደድክም ጠላህም ህጉን ማክበር የግድ ነው :: ስይበር ወስጥ ግን መቅደድና መስፋት መብትህ ናቸው :: ለስነ -አእምሮህ በጎነትም ይረደሀል - ቀደድ - ፎክር - ግን ይስተዋል ::
እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንዱአለም ነጻ ፍርድ -ቤት ቀርቦ አቃቤ - ህጉ ያቀረበበትን ክስ የመካድ መብት አለው :: የቀረበውን መረጃ የመጠየቅ - የማጣራት ወይም የራሱ ጠበቃ የመቅጠር መብት አለው :: ከዛ ውጭ ግን ሌላ ሌላ ነው ::

ሻምበል
እንዳው ሳስብክ በታም ፈሪ ነገር ነክ ::
ለምን ጫካ አትገባም ? እውነት ዘራፍ በልና ጫካ ግባ - አንተ ሙተህ ሌላው ይለፈለት :: ዳሩ ምን ያደርጋል ቀደዳ ሙያህ ነው ::
በል ሰፋው

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኣሲምባ

ዋና ኮትኳች

Joined: 12 Oct 2006
Posts: 527

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:52 pm    Post subject: Reply with quote

የተመናመነው ::
ያልክው ሁሉ ትክክል ሊሆን ይችላል እስቲ ጨምርበት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
salar

ኮትኳች

Joined: 10 Feb 2012
Posts: 270

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 11:55 pm    Post subject: Reply with quote

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

ዳግማዊ ዋለልኝ እንደጻፈ(ች)ው:
አይ ዠግናው አንዱአለም Wink Laughing Laughing

ወያኔን አንቀጠቅጣለሁ ብሎ እምቡር እምቡር ሲል እንዳልነበር በአንድ ወፈፌ እስረኛ ማለቃቀስ ጀመረ Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 12:02 am    Post subject: Reply with quote

አንድ ወቅት የኔሰው ገብሬ ራሱን አጋዬ የተባለ ሰሞን እንድሪያስ ምናለ የላሜቦራ ነገር እምቡር እምቡር የሚለው ለትንሽ ቀን ነው :: እስኪረሳ ድረስ :: ከዛ ብኋላ "ደመ ከልብ " ሆኖ ይቀረአል ነበር ያለው :: እንዳለው አንድ ቀን የሻማ ነው የችቦ ስነ -ስርዓት ዲሲ ላይ ተደረገ በቃ :: ተረሳ ::

ዛሬም የአንዱአለም ደብዳቤ ለጥቂት ቀናት የመሳደብና የማመናጨቅ ስሜታችሁን ትወጡበትና ይረሳል :: ልክ የዛሬ አመት አካባቢ ከወህኒ ቤቱ ታዛቢዎች የተላከ ተብሎ በየድረገጹ እንደተበተነው 30 ገጽ ሪፖርት :: ይረሳል :: አዲስ ነገር ይመጣል :: ማለቃቀሱም ይቀጥላል ..... ኢህአዲግ አላማውን አሳክቶ "ራሱን በራሱ እስኪያጠፋ ድረስ " Idea

ሓየት
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እንድሪያስ

አለቃ

Joined: 19 Mar 2004
Posts: 2130
Location: *****

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 1:40 am    Post subject: Re: ይድረስ ለማይድነው ወያናይ - ለስልኪ Reply with quote

ኣሲምባ እንደጻፈ(ች)ው:እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አንዱአለም ነጻ ፍርድ -ቤት ቀርቦ አቃቤ - ህጉ ያቀረበበትን ክስ የመካድ መብት አለው :: የቀረበውን መረጃ የመጠየቅ - የማጣራት ወይም የራሱ ጠበቃ የመቅጠር መብት አለው :: ከዛ ውጭ ግን ሌላ ሌላ ነው ::ኣሲምባ :- ሌላ ሌላ ነው ብሎ ነገር የለም :: አንዱዓለም ማረሚያ ቤትም የህይወት ዋስትና ሊኖረውና ደህንነቱ ሊጠበቅለት ይገባል :: ለህይወቴ እስጋለሁ ከአለ የሚመለከተው ክፍል ሁኔታውን አጣርቶ ርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለበት :: በሁለት እስረኞች መካከል ድንገተኛ አለመግባባት ተፈጥሮ ቅራኔው በቀላሉ የማይበርድ ከሆነና ለሌላ ተጨማሪ ወንጀል የሚጋብዝ መሆኑ ከታመነበት እስረኞቹን ማለያየትና ተራርቀው እንዲኖሩ ማድረግ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ስራ ነው :: አንድ እስረኛ ለህይወቴ እሰጋለሁ ካለ ጥበቃ ሊደረግለት ወይም 'protection custody' እንዲቆይ ይደረጋል :: ጥበቃ ፖሊስ የእስረኞችንም ደህንነት ሊጠብቅ ነው እዛ የሚቆመው ::

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

በመጀመሪያ ደረጃ በወያኔነትህ ሣታፍርበት በግልፅ ስለምትናገር ለአንተ ለፖለቲካ ባላንጣዬ በዓላማህ ላለህ ጽኑነት አከብርሃለሁ ::

ተድሌ :- አንተ ተኝተህ ደቸሳህን እየበላህ ቅዠትህን ቀጥል :: አንተ ፖለቲከኛ አይደለህም :: የሆንክ ከመሰለህ ደግሞ የአንተ የፖለቲካ ባላንጣ ስልኪ ሳይሆን ቢተወደድ ይመስለኛል :: ቢተወደድም ይበዛብሀል ለአንተስ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዱሩ ቤቴ

አዲስ

Joined: 27 Feb 2012
Posts: 17

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 4:10 am    Post subject: Reply with quote

ጥያቄው የቀረበው ለሐቀኛው ወያኔ ነው :: የተቀራችሁ የወያኔ በቀቀኖች ዝም በሉ :: እኔም እንደ ተድላ ለስልኪ ክብር አለኝ ::
_________________
yalwequ Alequ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደብረብርሀን 33

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2011
Posts: 262

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 5:24 am    Post subject: Reply with quote

ሰላማዊ ወገኖቻችንና በግፍ ለሚያሰቃዩ ወያኔዎች : በህጋዊ መንገድ ፓለቲካዊ ተቃውሞቸውን : ለማሰማት የተደራጁትን ወገኖች : በእንደዚህ አይነት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ : ባዶ እጁን የሆነን ሰላማዊ ወገንን የሚያሰቃይ ወያኔን የሚያስከብረውና ጀግና የሚያደርገው ምንድን ነው Question ለስልኪም አይነቱና ለጌታውና ለባንዳው መለስ በስናይፐር አናቱን ከሁለት ማድረግ ብቻ ነው Exclamation
አቶ ተድላ ኃይሉ - ዋርካ ያለነው ተቃዋሚዎች ስናከብርህ
እንደዚህ ለወያኔ ብጣሻም እራስህን ዝቅ ማድረግህ ለምን እንደሆን አልገባኝም Exclamation ምን ለማድረግ ነው ልምምጡ Exclamation ከእነሱ መልካም ነገርና ጥሩ መልስ መቼም አንተ የምጠብቅ አይመስለኝም :: ታዲያ ለምን ጥቅም / Purpose እንደዚህ አይነት ራስህንም እኛንም የምናከብርህን አወረድከን Question እነሱን የሚያስፈልጋቸው ምን እንደሆነ እናውቃለን :: እስከዚያው ድረስ ግድየለም ሰላማዊ ዜጋን እንደፈለጉ ይጫወቱበት :: ጊዜያቸው ግን እንደሚመጣ ግን ጥርጥር የለንም Exclamation እንኳን ለስልኪ ይቅርና : ለጌታው ለባንዳው መለስም ክብር ሳይሆን ጥሩ የእስናይፐር ጥይት ብቻ ነው የሚገባቸው Exclamation

ዱሩ ቤቴ እንደጻፈ(ች)ው:
ጥያቄው የቀረበው ለሐቀኛው ወያኔ ነው :: የተቀራችሁ የወያኔ በቀቀኖች ዝም በሉ :: እኔም እንደ ተድላ ለስልኪ ክብር አለኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግዛቸው

ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Jul 2004
Posts: 1484

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 5:27 am    Post subject: Reply with quote

አቶ ተድላ ወያኔ እኮ ጨካኝ አረመኔ ነው ::
በካፕቴን ተሾመ ላይ ያደረሱትን በደል በደንብ ያነበብከው አልመሰለኝ ::

ወያኔ ምን ያክል ቂመኛ የሆነ አውሬ እንደሆነ እስካሁን አለመረዳትህ ገረመኝ ::
_________________
Visit My Blog
----===-----
ኢትዮ-ፈን ብሎግ |||
“Freedom is not free.”
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
Page 1 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia