WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ጥያቄ ለጸዋር - ስለባሃይ እምነት

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 8:14 pm    Post subject: ጥያቄ ለጸዋር - ስለባሃይ እምነት Reply with quote

የበሃቡላ (ባሃይ እምነት መሥራቹ ) ደጋፊ ጸዋር :

በቅድሚያ የባሃይን መሥራች ቡሃቡላን በማንቆለጳጰስ ጭራቸውን እየቆሉ ሲዘፍኑ የነበሩ ያንተ ቢጤ አሳዛኝ ኢትዮጵያውያንን ክሊፕ ልጋብዝህና :

http://www.youtube.com/watch?v=gqXPWjdLiA0

በመቀጠል : እንዲህ ብለህ ቆቁ ቤት በጻፍከው ጽሑፍህ መሠረት :-

Quote:
በሀዮች አንድ የሚሉት ነገር አላቸው :: የሙሴ ህግና ትንቢት በሙሴ ዘመን ለነበረው ትውልድ እንደመረዳቱ ብቃት ከእ / የተሰጠ ትምህርትና መመሪያ ነው ይላሉ :: ትምህርትና መመሪያ ለዚህ ዘመን ትውልድ አይመጥንም :: እንኳንና ለዚህ ዘመን ትውልድ ቀርቶ 2000 አመታት በፊት ለነበረውም አይመጥንም ነበር ይላሉ :: ስለማይመጥን ደግሞ / በሌላ ነብይ (ክርስቶስ ) በኩል ዘመኑን የሚመጥን የተሻሻለ ትምህርትና የህይወት መመሪያ (አዲስ (ቃል ) ኪዳን ) ሰጠ :: ዛሬ የሰው ልጅ የአስተሳሰብ አድማሱ ሲሰፋ ደግሞ እንዲሁ አንድ መሲህ ላከልን ብለው ያምናሉ :: መሲህ - ቡሀኡላህ ነው :: የበሀይ እምነት መስራች ነው :: የመጨረሻው መሲህ ነው ብለውም ያምናሉ :: የመጨረሻ ሲባል ከሱ ብኋላ የሚመጣ የለም ማለት አይደለም :: ወደፊትም እንዲሁ ዘመኑን የሚመጥን ነቢይ ይነሳል :: ዛሬ በምድር ላይ ያሉት ሁሉም እምነቶ / ወደዚች ምድር በላካቸው ነቢያት አማካኝነት የተመሰረቱ ናቸው ብለው ያምናሉ :: ቡድሀ : ሙሀመድ : ክርስቶስ : ክሪሽማ : ወዘተ ወዘተ ወዘተ ... የተለያዩ ሀይማኖት የሆኑበት ምክንያት ከአለማችን ስፋት አንጻር ህዝቡ ተበታትኖና ተራርቆ ይኖር ስለነበረ ነው :: ዛሬ አለም በሰው ልጅ የአስተሳሰብ አድማስ መስፋት ምክንያትና በቴክኖሎጂ ምጥቀት እንደ አንዲት ቀበሌ (ቪሌጅ ) የምትታይበት ሁኔታ ስላለ ትውልዱ አንድ መሆን በአንዲት ጥላ ስር መቆም አለበት ብለው ያምናሉ :: ክርስቲያን ሙስሊም ቡድሂዝም ሂንዱይዚም ... የሚባል የሽፋን ስም ተወግዶ በአንድ ጥላ ስር በመሰባሰብና ለሰላምና ለአንድነት በመዘመር ትውልድ ሁሉ የአንድ አባት አባላት የአንድ ሀይማኖት ተከታይ የሚሆንበትን የእምነት ክሪድ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ ::

እንግዲህ ይህ የሚያሳየን ከጠባቧ የያኔዋ የእስራኤል ምድር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የሰው ልጅ ሀይማኖት እንዴት evolve እያደረገ እንዳለ ነው ::ሙሴ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናቸው ለነበረው ትውልድ ከሰጧቸው ትእዛዛት መሃል (10 ትእዛዛትና 6 ቃላተ ወንጌል - እንዲሁም ሌሎች በተለይ : አብዛኞቻችን ክርስቲያኖች እንጂ ይሁዲ እምነት ተከታዮስ ስላልሆንን : ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰጣቸው ሕግጋት መሃል ) ለኛ ዘመን የትኛው እንደማይመጥን ብትነግረንና በምን ሕግ ሊተካ እንደሚገባ ብታስተምረን ምን ይመስልሃል ?

አንደኛ ...

ሁለተኛ ...

እስቲ ተንትናቸው ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 11:52 pm    Post subject: Reply with quote

ጸዋር ጥያቄ ትፈራለህ እንዴ ? ብቅ በል እዚህ ቤት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 12:27 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም አማች ሞጥሟጣው Very Happy

የሚመለከተኝን ጥያቄ ብትጠይቀኝ መልስ እሰጥህ ነበር :: ለምሳሌ ስለ ባሀይ ከጻፍኩት ትክክል ያልሆነ ካለ ወይም የተቀላቀለ ነገር ካለ ወዘተ እንጂ እኔ ጋር የማይገናኝ ነገር መጠየቅ ምን አመጣው Question እኔ ያንን የጻፍኩት የሰው ልጅ ሀይማኖት እንዴት evolve እያደረገ እንዳለ ለማሳየት ነው :: የሰው ልጅ ጎሳውን (ነገዱን ) ከሚወክል (ዘረኛ ) / አንስቶ እስከ የአለምን ህዝብ በሙሉ የሚያቅፍ (ኮስሞፖሊታን ታይፕ ) የሆነ / እንዴት እየፈጠረ እንዳለ ለማሳየት ነበር የተጠቀምኩበት ::

በጠየቅከው ዙርያ ዘርዘር ያለ ነገር ማወቅ የምትፈልግ ከሆነ ግን Progressive Revelation ብለህ ጎግል አድርግ :: ከባሀይ እምነት አንጻር ምን ማለት እንደሆነ በስፋት ተጽፎበት ታገኛለህ ::

በነገራችን ላይ እንዴት ነው የልጃችን ነገር : ዛሬም ካባቷ ጋር ትተኛለች እንጂ ለፀዋርስ አትዳርም ነው ውሳኔው ? Razz

ሠላም
_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 12:52 am    Post subject: Reply with quote

ጥያቄውማ የሚመለከተው አንተን ነው :: ያቀረብኩልህም አንተው ራስህ ከተናገርከው በመነሳት ነው :: ምነው ሸሸት ሸሸት አልክ ? በተናገርከው ነገር ኮንፊደንስ የለህም እንዴ ? መቼም ስለባሃይ ባታውቅ ስለርሱ አትመሠክርም ነበር ብዬ እገምታለሁ :: እና ዕውቀትህን ለኛም አካፍለን እንጂ ?!

እኛ ለክርስቲያኖች የክርስቶስ ሕግ አልፋ ኦሜጋ ፍጹም ነው ብለን እናምናለን :: አንተ ደግሞ እንደብሃዮች እምነት መሠረት ትእዛዙ እንደዘመኑ መቀየር አለበት እያልክ ነው ::

ታድያ ምኑ በምን መቀየር እንዳለበት ዘርዝራ ?! ዝም ብሎ "ተቀየሩ " ማለት ምን ትርጉም አለው ? ወዴት ነው የምንቀየረው ? ከሕግጋቱስ የቶቹን ነው የምንቀይራቸው ? ለምን ?

ምናልባት ከየት መጀመር እንዳለብህ ካላወቅህ : አንዱን ወንጌል ውሰድና ጌታ "እንዲህ አድርጉ : እንዲህ አታድርጉ " ብሎ ከዘረዘራቸው ዝርዝሮች ጀምር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 1:38 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ሙጢው Razz

የቄሶች የመረዳት ችሎታ ሁሌም በጥያቄ ምልክት እንደሆነ ነው :: በማይመለከተኝ ጉዳይ ለምን ታደርቀኛለህ ? ሰርች ማድረግ አትችልም ? ከፈለግክ የማውቀውን ያክል አስረድሀለሁ :: በደብተራ ተረት ተረት ከተተበተበው ከናንተ እምነት እጅግ በሚሻል ሁኔታ ሪዝነብል የሆኑ ነገሮች ቢኖሩትም እኔን ግን አይወክለኝም :: የኔን አመለካከት ደጋግሜ ቋቅ እስኪልህ ድረስ የነገርኩህ መሰለኝ :: መጽሀፉን / ነው የጻፈው ብዬ አላስብም :: ማስረጃዎች የሚያሳዩትም ያንኑ ነው :: / ካልጻፈው ደግሞ የጻፉት ሰዎች መሆናቸው ነው :: ሰው ሲጽፍ በወቅቱ ይመጥናል ያለውን ህግ ጻፈ :: ለምሳሌ ሙሴ አይንን በአይን : ጥርስን በጥርስ የሚል ህግ ነበረው :: "ባርያን " መግዛትና መሸጢ ተገቢ ነበረ :: ወንድና ሴት እኩልነት አይታይባቸውም :: በእ / የተመረጠና ያልተመረጠ ጎሳ /ነገድ የሚባል ዲስኩር ነበራቸው :: ይሄ ሁሉ ቅራቅንቦ የሰው ፈጠራ ነው :: የአስተሳሰቡን ያክል የፈጠረው :: ስለዚህ ከጅምሩ ለሙሴ የተሰጠ በእ / የተጻፈ ህግ የለም ብየ አምናለሁ :: መጽሀፉም ቢሆን "ህግ አይገዛንምና " ይላል እኮ :: አይልም እንዴ ? ክፉና ደጉን እንድትለይ ሆነህ ተፈጥረሀል :: ህይወት ተላብሰህ ወደዚች ምድር ብቅ ስትል አእምሮህ ሙሉ ሆኖ ነው የሚፈጠረው :: ስሜቶችህ በቦታቸው አሉ :: በስሜቶችህ አማካኝነት ክፉና ደጉን : ደስታና ሀዘንን : ሳቅና ለቅሶን : ፍቅርና ጥላቻን : ፍርሀትና ድፍረትን : ጭካኔና ርህራሄን : እውነትና ሀሰትን ... ወዘተ ትለያለህ :: ረቂቁ የፍጠርት ህግ የተጻፈው በዚህ መልኩ ልብህ ላይ ነው :: ይህ ነው የኔ እምነት :: የተጻፈና የተሞነጫጨረ ህግ ሙሉእነት ስለሌለው ህግ ብዬ አልቀበለውም :: ለምሳሌ ከአስርቱ ትዕዛዛት መካከል ሰው በሰውነቱ እኩል ስለመሆኑ የሚናገረው አንድም ነገር የለም :: የባርያን አብነት አነሳን :: ስለባርነት የሙሴ አምላክ ምን ያለው ነገር አለ ? ተቃወመ ? አልተቃወመም :: "በገንዘብ የተገዛውን ባርያችሁን ጭምር ቶራህን አስጠኑት " ነው የሚለው :: ልክ እኛ አገር ምን ያክል እውነት እንደሆነ ባላውቅም አጼው "ሰው እንዳይገደል እንትንም ቢሆን " እንዳሉት መሆኑ ነው :: ይሄ የሙሴ አምላክ : የናንተም አምላክ ነው :: በኔ ዘንድ ግን ቦታ የለውም ::

ምንድን ነው አትግደል ብሎ ህግ ? It is very basic eko Razz ሰው ህጉ ስለተጻፈ ነው መግደል ትክክል እንዳልሆነ የሚያውቀው ? ድመት ድመትን አይገድልም :: ውሻ ውሻን አይገድልም :: የዱር እንስሳት ጭምር ምሳላቸውን አይገድሉም :: ለነሱም ድንጋይ ላይ ስለተጻፈላቸው ነው Question ሊሆን አይችልም :: ተፈጥሮ የራስህን ወገን እንድተገድል አድርጋ አልቀረጸችህም :: እንደዛ አልተፈጠርንም :: ህጉ በልባችን አለ :: ይሄው ነው ::

ወደ ባሀዮች ስነመለስ ከላይ የገለጽኩትን በተወሰነ መልኩ የሚቀበሉ ይመስለኛል :: በመጀመሪያ እንገር ለባይብል እውቅና መስጠታቸው ከኔ የሚለያቸው ስታንድ ነው :: አሁንም ዴቪዲክ ጋርዲያን ብለው ያምናሉ :: የተመረጠው ዘር በነሱ ዘንድም አለ :: ይህን አልቀበለም እኔ :: "ቅዱሳን መጻህፍት በነቢያት አማካኝነት ከእ / የተሰጡ ትዕዛዛትና ህግጋት ናቸው " ብለውም ያምናሉ :: ይሄን አልቀበልም እኔ :: "ለዛሬ ዘመን አይመጥኑም ይላሉ እንጂ አይረቡም ወይም እውቅና የላቸውም " አይሉም :: ባይሆን ይህን እምነታቸውን በከፊል እጋራለሁ ::

በዚህ ጉዳይ ላይ ዘርዘር ያለ ነገር ማወቅ ከፈለክ በሰጠሁህ ፍሬዝ መሰረት ሰርች አድርግና ተረዳ :: የናንተ ህጎች የምትሏቸውን ጨምሮ ለዚህ ዘመን ትውልድ ይመጥናሉ የሚሏቸውን ሌሎችንም አካተው "The Twelve Principles of Bahaî " ብለው ሰይመዋቸዋል :: እሱን ማንበብና መረዳት ትችላለህ :: አንድ ለየት የሚል ምሳሌ ጥቀስ ካልከኝ ግን ክርስቶስ "ከኔ በቀር የሚያድን ማንም የለም - እውነትም መንገድም እኔ ነኝ " ያለውን የክርስቲያኒቲ መሰረት ተደርምሶና ተሻሽሎ ታየዋለህ :: ሁሉም ነብያት (እንደ አንዳንድ ክርስቲያኖች ክርስቶስንም ነብይ ነው የሚሉት እነሱ ) በእ / የተላከ ስለሆነ ሁሉም እምነት ትክክል ነው ይላሉ :: ቢሆንም ግን ወቅቱ አንድ የምንሆንበት ስለሆነ / የመጨረሻውን መሲህ ባሀኡላህን ላከልን ይላሉ ::

The Twelve Basic Principle

1. "The Oneness of the World of Humanity."

2. "The Independent Investigation of Truth."

3. "The Foundation of all Religions is one."

4. "Religion Must Be the Source of Unity."

5. "Religion must be in accord with Science and Reason.

6. "The Equality of Men and Women."

7. "Removal of all Prejudice; Religious, Racial, National, Political, etc."

8. "Universal Peace."

9. "Universal Education."

10. "The Spiritual Solution of the Economic Problem."

11. "A Universal Language."

12. "An International Tribunal, or Parliament of Nations---The Universal House of Justice with the Davidic Guardian."

ሠላም

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
ጥያቄውማ የሚመለከተው አንተን ነው :: ያቀረብኩልህም አንተው ራስህ ከተናገርከው በመነሳት ነው :: ምነው ሸሸት ሸሸት አልክ ? በተናገርከው ነገር ኮንፊደንስ የለህም እንዴ ? መቼም ስለባሃይ ባታውቅ ስለርሱ አትመሠክርም ነበር ብዬ እገምታለሁ :: እና ዕውቀትህን ለኛም አካፍለን እንጂ ?!

እኛ ለክርስቲያኖች የክርስቶስ ሕግ አልፋ ኦሜጋ ፍጹም ነው ብለን እናምናለን :: አንተ ደግሞ እንደብሃዮች እምነት መሠረት ትእዛዙ እንደዘመኑ መቀየር አለበት እያልክ ነው ::

ታድያ ምኑ በምን መቀየር እንዳለበት ዘርዝራ ?! ዝም ብሎ "ተቀየሩ " ማለት ምን ትርጉም አለው ? ወዴት ነው የምንቀየረው ? ከሕግጋቱስ የቶቹን ነው የምንቀይራቸው ? ለምን ?

ምናልባት ከየት መጀመር እንዳለብህ ካላወቅህ : አንዱን ወንጌል ውሰድና ጌታ "እንዲህ አድርጉ : እንዲህ አታድርጉ " ብሎ ከዘረዘራቸው ዝርዝሮች ጀምር ::

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 2:34 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ለምሳሌ ሙሴ አይንን በአይን : ጥርስን በጥርስ የሚል ህግ ነበረው :: "ባርያን " መግዛትና መሸጢ ተገቢ ነበረ :: ወንድና ሴት እኩልነት አይታይባቸውም :: በእ / የተመረጠና ያልተመረጠ ጎሳ /ነገድ የሚባል ዲስኩር ነበራቸው :: ይሄ ሁሉ ቅራቅንቦ የሰው ፈጠራ ነው :: የአስተሳሰቡን ያክል የፈጠረው :: ስለዚህ ከጅምሩ ለሙሴ የተሰጠ በእ / የተጻፈ ህግ የለም ብየ አምናለሁ :: ...... ለምሳሌ ከአስርቱ ትዕዛዛት መካከል ሰው በሰውነቱ እኩል ስለመሆኑ የሚናገረው አንድም ነገር የለም :: የባርያን አብነት አነሳን :: ስለባርነት የሙሴ አምላክ ምን ያለው ነገር አለ ? ተቃወመ ? አልተቃወመም :: "በገንዘብ የተገዛውን ባርያችሁን ጭምር ቶራህን አስጠኑት " ነው የሚለው :: ልክ እኛ አገር ምን ያክል እውነት እንደሆነ ባላውቅም አጼው "ሰው እንዳይገደል እንትንም ቢሆን " እንዳሉት መሆኑ ነው :: ይሄ የሙሴ አምላክ : የናንተም አምላክ ነው :: በኔ ዘንድ ግን ቦታ የለውም ::ጸዋር :

እንግዲህ ጥግ ጥጉን መጠማዘዝ ተውና ወደጥያቄዬ :: እኔ ያልኩህ : ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰጣቸው ሕግጋት መሃል የትኞቹ ይለወጡ ነው :: ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሴ በኋላ ነው የመጣው :: ስለዚህ : እንዳንተው አባባል : ከሙሴ ይልቅ ለዘመኑ የተሻለ ነበረ ::

አሁን ደግሞ የትኞቹ የኢየሱስ ትእዛዛትና ሕግጋት outdated ሆኑ ? ወንጌል እየጠቀስክ "ይህኛው ለዚህ ዘመን አይሠራም " "ይሄኛው አይሠራም " እያልክ አስረዳ እንጂ ?! ለዚህ ዘመን የማይሆነው outdated የሆነው ትእዛዝ /ሕግ የቱ እንደሆነ ተንትን :: አለዚያ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕግ ለዚህ ዘመን የማይመጥን ነው የሚለውን የባሃዮች ፍልስፍና ለምን ሪዝነብል ነው አልክ ?

ጥያቄዬ ' ግልጽ ነው !!

አንተው ራስህ ሪዝነብል ነው ስላልከው ስለዚህ የሕግጋትን እንደየዘመናቱ ማሻሻል ጉዳይ ሪስፖንሲቢልቲ ውሰድና : ሃሳብ ስጥ :: ባሃዮች ዌብሳይት ላይ አትንጠላጠል :: ያንተን ሃሳብ ነው የምፈልገው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Sun Mar 11, 2012 10:41 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ቄሱ

እንዲህ እንደዛሬ ጋጠወጥ ሳልሆን በፊት "አባ በመስቀሎ ይባርኩኝ " እል ነበር Laughing ቀረብህ ::

እኔ የምለው ? የጻፍኩትን አላነበብከውም Question አልገባህም Question ምንድን ነው ችግርህ Question አንድ ትልቅና መሰረታዊ አብነት እዛው ተጽፏል እኮ :: ከዛ ውጪ በዝርዝር እንዳቀርብልህ ከፈለክ አይመለከተኝም አልኩህ :: የሚመለከታቸውን ጠይቅ :: ለምሳሌ "በኢ / ሰለሞናዊው ስርወመንግስት ሊመሰረት የበቃው በንግስት ሳባ አማካኝነት ነው ብሎ ሙጢው አማቼ ያምናል " ብልና ሶስተኛ ወገን አድማጭ ግራ ቢገባው ንግስተ ሳባ እንዴት ስርወመንግስቱን እንዳመጣችው ማስረዳት ይጠበቅብኛል Question ያንተ ጥያቄ ልክ እንደዚህ ነው :: ከጻፍኩት መካከል ያልገባህ ካለ ወይም ትክክል አይደለም የምትለው ካለ መወያየት እንችላለን :: አንተ ስለምታምንባት ሳባ በዝርዝር ማስረዳት እንደማይጠበቅብኝ ሁሉ ስለ ባሀይ እምነት ዝርዝር ማቅረብም አይጠበቅብኝም :: ሲምፕሊ እምነቴ ስላልሆነ እያንዳንዱን ነገር ማወቅ አልችልምና ::

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ነገር ልበል :: ከላይም ጽፌልህ ነበር :: አንድም አላነበብከውም አለያም ነገሩ አልገባህም :: እናንተ ኦርቶዶክሶች ከሁሉ ጋር የምትጋጩት ለምንድን ነው Question ከተሀድሶው : ከጴንጤው : ከካቶሊኩ : ከእስላሙ : ከኢአማንያኑ : ከጆህቫው : ከባሀዩ : ... ወዘተ የምትጋጩት ለምንድን ነው ? "ሀይማኖት አንዲት ናት እርሷም ኦርቶዶክስ ናት " ብላችሁ ስለምታስቡ አይደል Question ይሄን ያስተማራችሁ ማን ነው Question ክርስቶስ አይደል Question ክርስቶስ ከእኔ በቀር ወደ አብ የሚያደርሳችሁ የለም ... እውነትም መንገድም እኔ ብቻ ነኝ አላችሁ :: እናንተ ደግሞ ቀበል አድርጋችሁ ያቺን እውነትና መንገድ በብቸኝነት የያዝናት እኛ ብቻ ነን ታላላችሁ :: ያልተበረዘች ያልተከለሰች የጥንቷ የጥዋቷ አዳኚትዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነች ትላላችሁ :: ሌላውስ ? ከሙስሊም በመወለዱ ሙስሊም ሆኖ የቀረው : ካቶሊክ , ጴንጤ , ጆህቫ , ወዘተ ሆኖ የቀረውስ ? የመዳን ተስፋ የለውም :: ገሀነም ይጠብቀዋል :: ይሄው ነው እምነታችሁ አይደል :: ይህን ያገኛችሁትም ከክርስቶስ / ነው :: እኔን ያልተከተለ ያን ጊዜ ጥርስ ማፏጨት ይሆናል ይላል Laughing እንግዲህ እዚህ ላይ ነው ባሀይ የሚገባው :: "!" ይላሉ ባሀዮች " አንተን የተከተለ : ሙሀመድን የተከተለ : ሙሴን የተከተለ : ቡድሀን የተከተለ ባሀኡላህን የተከተለ ... ሁሉ የእ /ርን መንገድ ተከተለ :: እውነትም መንገድም አንተ ብቻ ሳትሆነ ካንተ በፊትም ካንተ ብኋላም እንዳንተ ከእ / የተላኩ ነበሩ ... እነሱን የተከተለም ይድናል ... ::"

አሁንስ ገባህ ?

ይሄንን እንዳለ ካሻሻሉት በውስጡ ያለው ህግም ተሻሻለ ማለት ነው :: እንዴት ? የክርስቶስን ህግ ሳትከተል የቡድሀን ወይም የሙሀመድን ህግ ብትከተል /ርን ከማግኘትና ከመዳን የሚያግድህ የለም ማለት ነውና ::

ሠላም

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ለምሳሌ ሙሴ አይንን በአይን : ጥርስን በጥርስ የሚል ህግ ነበረው :: "ባርያን " መግዛትና መሸጢ ተገቢ ነበረ :: ወንድና ሴት እኩልነት አይታይባቸውም :: በእ / የተመረጠና ያልተመረጠ ጎሳ /ነገድ የሚባል ዲስኩር ነበራቸው :: ይሄ ሁሉ ቅራቅንቦ የሰው ፈጠራ ነው :: የአስተሳሰቡን ያክል የፈጠረው :: ስለዚህ ከጅምሩ ለሙሴ የተሰጠ በእ / የተጻፈ ህግ የለም ብየ አምናለሁ :: ...... ለምሳሌ ከአስርቱ ትዕዛዛት መካከል ሰው በሰውነቱ እኩል ስለመሆኑ የሚናገረው አንድም ነገር የለም :: የባርያን አብነት አነሳን :: ስለባርነት የሙሴ አምላክ ምን ያለው ነገር አለ ? ተቃወመ ? አልተቃወመም :: "በገንዘብ የተገዛውን ባርያችሁን ጭምር ቶራህን አስጠኑት " ነው የሚለው :: ልክ እኛ አገር ምን ያክል እውነት እንደሆነ ባላውቅም አጼው "ሰው እንዳይገደል እንትንም ቢሆን " እንዳሉት መሆኑ ነው :: ይሄ የሙሴ አምላክ : የናንተም አምላክ ነው :: በኔ ዘንድ ግን ቦታ የለውም ::ጸዋር :

እንግዲህ ጥግ ጥጉን መጠማዘዝ ተውና ወደጥያቄዬ :: እኔ ያልኩህ : ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰጣቸው ሕግጋት መሃል የትኞቹ ይለወጡ ነው :: ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙሴ በኋላ ነው የመጣው :: ስለዚህ : እንዳንተው አባባል : ከሙሴ ይልቅ ለዘመኑ የተሻለ ነበረ ::

አሁን ደግሞ የትኞቹ የኢየሱስ ትእዛዛትና ሕግጋት outdated ሆኑ ? ወንጌል እየጠቀስክ "ይህኛው ለዚህ ዘመን አይሠራም " "ይሄኛው አይሠራም " እያልክ አስረዳ እንጂ ?! ለዚህ ዘመን የማይሆነው outdated የሆነው ትእዛዝ /ሕግ የቱ እንደሆነ ተንትን :: አለዚያ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕግ ለዚህ ዘመን የማይመጥን ነው የሚለውን የባሃዮች ፍልስፍና ለምን ሪዝነብል ነው አልክ ?

ጥያቄዬ ' ግልጽ ነው !!

አንተው ራስህ ሪዝነብል ነው ስላልከው ስለዚህ የሕግጋትን እንደየዘመናቱ ማሻሻል ጉዳይ ሪስፖንሲቢልቲ ውሰድና : ሃሳብ ስጥ :: ባሃዮች ዌብሳይት ላይ አትንጠላጠል :: ያንተን ሃሳብ ነው የምፈልገው ::

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 2:54 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
የክርስቶስን ህግ ሳትከተል የቡድሀን ወይም የሙሀመድን ህግ ብትከተል /ርን ከማግኘትና ከመዳን የሚያግድህ የለም ማለት ነውና ::

በጣም ጥሩ !

የመጨረሻ አጭር ጥያቄ ልጠይቅህና ላብቃ ::

ባንተ አረዳድ : ከላይ በጻፍከው መሠረት ስንሄድ : አንድ ሰው የክርስቶስን ሕግ ሳይፈጽም : የቡድሃን : የሞሃመድን : የሙሴን ወይም የሌላን ሕግ ቢፈጽም እንደሚድነው ሁሉ : የሌሎችን ደግሞ ሕግ ሳይፈጽም : የክርስቶስን ሕግ ብቻ ቢፈጽምስ ይድናል ብለህ ታምናለህ ?

:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 3:58 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ሙጢነት Razz

ጥሩ ጥያቄ ነው :: መልሱም አጭር ነው :: እኔ ባሀይ ብሆን መልሱ አዎ ነበር :: እኔ ግን እኔ ነኝና "መዳን ከምን " ብዬ እጠይቅሀለሁ :: I don't believe in any of the so called devine or demonic interventions, so no need to be saved. After all, saved from who? from what?

Let me ask you my turn,

Do you believe that God's work is Perfect? If so, do you still believe that creation is God's perfect work? Again, if so, why intervention then?

Peace!

እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
የክርስቶስን ህግ ሳትከተል የቡድሀን ወይም የሙሀመድን ህግ ብትከተል /ርን ከማግኘትና ከመዳን የሚያግድህ የለም ማለት ነውና ::

በጣም ጥሩ !

የመጨረሻ አጭር ጥያቄ ልጠይቅህና ላብቃ ::

ባንተ አረዳድ : ከላይ በጻፍከው መሠረት ስንሄድ : አንድ ሰው የክርስቶስን ሕግ ሳይፈጽም : የቡድሃን : የሞሃመድን : የሙሴን ወይም የሌላን ሕግ ቢፈጽም እንደሚድነው ሁሉ : የሌሎችን ደግሞ ሕግ ሳይፈጽም : የክርስቶስን ሕግ ብቻ ቢፈጽምስ ይድናል ብለህ ታምናለህ ?

:

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 5:12 am    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ሙጢነት Razz

ጥሩ ጥያቄ ነው :: መልሱም አጭር ነው :: እኔ ባሀይ ብሆን መልሱ አዎ ነበር :: እኔ ግን እኔ ነኝና "መዳን ከምን " ብዬ እጠይቅሀለሁ ::

ባሃይ አንድነት ሊመሠርቱ ይገባቸዋል የሚላቸው አብዛኞቹ የዓለማችን ሃይማኖቶች : በተለያየ መልኩ : ዞሮ ዞሮ " የሰው ልጅ መዳን አለበት ' ብለው የሚያስቡ ናቸው :: አንዳንዶቹ ከጥንተ አብሶ ሲሉ : ሌሎቹ ከገሃነም : ሌሎቹ ከሰይጣን መንፈስ : ሌሎችቹ ከራሱ ..... ወዘተ እያሉ ይቀጥላሉ ::

ታድያ : አንተው ራስህ እንዳስቀመጥከው ባሀይ እነዚህን እምነቶች "ያው ከአንዱ እግዚአብሔር የመጡ ናቸውና ስለሰላምና ስለአንድነት በመዘመር በአንድ እምነት ሥር ሊሆኑ ይገባቸዋል " ይላሉ ብለህ ያስቀመጥከውን ትንተና እንዴት "ሪዝነብል " ነው ልትለው ቻልህ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፀዋር

ዋና ኮትኳች

Joined: 16 Feb 2010
Posts: 501

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 7:19 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ እንደሚከተለው መልስ ሰጥቼ ድርቀቱን ልቋጨው

ከላይ ገና ውይይቱን ስንጀምር የተናገርኩት እንዲህ ይላል

በደብተራ ተረት ተረት ከተተበተበው ከናንተ እምነት እጅግ በሚሻል ሁኔታ ሪዝነብል የሆኑ ነገሮች ቢኖሩትም እኔን ግን አይወክለኝም ::

ይህ ሲተነተን ምን ማለት ነው ያልን እንደሆነ "ከኦርቶዶክስ እምነት ውጪ የሆነውን በሙሉ በጠላትነት (መናፍቅነት ) ከሚመለከት እምነታችሁ ይልቅ ሁሉንም ለፍቅር የሚጋብዝ ይህ እምነት በጣም እጅግ በጣም ይሻላል " ማለት ነው :: "ሪዝናብል " ነው :: እንዲሁ መመሪያችን ትሉታላችሁ እንጂ መጽሀፉማ እርስ በእርስ ከመዋደደ አልፎ "ጠላቶቻችሁንም " እንድትወዱ ያስተምር ነበር እኮ Laughing

ሌላው ደግሞ እኔ እንደተረዳሁት ከሆነ ባሀዮች አንድ ነን የሚሉት በነቢያት የተመሰረቱ እምነቶች የሆኑ እንደሆን መሰለኝ :: ነቢያቱን / የላከልን ናቸው ይላሉ :: በነቢያት ያልተመሰረተ ሰው ሰራሽ ወይም ድንጋይ ሰራሽ ወይም ዛፍ በቀል ወይም ብረት ለበስ እምነት ከሆነ እንደ የእ / ሀይማኖት የሚመለከቱት አይመስለኝም :: ይህ እንግዲህ ግምት ነው :: ሪዝናብል የምልበት ምክንያት ግን ከላይ እንደገለጽኩት ባይብል መመሪያችን ነው የሚሉትን : ቁርዓን መንገዳችን ነው የሚሉትን : በቡድሀ መጽሀፍ እንመራለን የሚሉትን ወዘተ አንድ ነበርን ለአንድም ታሰብንና አንድ እንሁን : የሚል የመዋደድ ጥሪያቸው የዘመኑን ምክንያታዊነት ተላብሷል :: እንግዲህ ባይብል መመሪያቸው የሆኑ ብቻ እምነቶች አሉ :: ወረድ ብለን ስንመለከት ደግሞ አንዲት ኦርቶዶክስ ለሁለት ተሰንጥቃ ተሀድሶና ተዋህዶ ስትል : ተዋህዶም ለሁለት ተሰንጥቃ የውጪና የአገር ውስጥ ሲኖዶስ እያለች ስትሟሟ ታያለህ :: እርስ በእርስ የማይዋደድ እምነት ተሸክመህ የባሀይን reasonability መጠየቅ ነበርህ ?

ማንም ቢሆን በዚህ ምድር ላይ እስካለ ድረስ ከሞት ብኋላ ምን እንደሚጠብቀው አያውቅም :: አንድ ሰው ሲኦልን ስላመለከ "ሲኦል " ይጠብቀው ወይም / ስላመለከ "ገነት " ይጠብቀው የሚታወቅ ነገር የለም :: በዚህ እርግጠኛ ባልሆነ የድህረ -ሞት አለም ምክንያት በምድር ላይ ያለው ሰው ዛሬ እንደ ጠላት መተያየት ያለበት አይመስለኝም :: እንደ ሰውነቱ የፈለገውን ያመልካል ነገር ግን ለፍቅር ይጋበዛል :: ባሀዮች አንተ እንዳልከው "ሲኦል አምላኪዎችን " ጭምር የሚጋብዝ ጥሪ ካላቸው አሁንም ድንቅ ምክንያታዊነት እለዋለሁ :: ግብዣው እኮ በአዲስ የባሀኡላህ ህግ ለመመራትም ጭምር ነው :: ስለዚህ የመጀመሪያው እምነት ስህተት ከነበረም በአዲሱ እምነት እንደመዳን ሊቆጠር ይችላል :: እንደዛ አይደለም እንዴ እናንተስ የምታደርጉት ? ቃልቻ አምላኪውን ታጠምቁታላችሁ - ዳነ ይባላል :: ለነገሩ ከናንተ የሚኮበልል እንጂ ወደ እናንተ የሚመጣ እንጃ መኖሩን Laughing

እንግዲህ በሌላ አምድ ነው ልንገናኝ የምንችለው

እስከዛው ሠላምእናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ሙጢነት Razz

ጥሩ ጥያቄ ነው :: መልሱም አጭር ነው :: እኔ ባሀይ ብሆን መልሱ አዎ ነበር :: እኔ ግን እኔ ነኝና "መዳን ከምን " ብዬ እጠይቅሀለሁ ::

ባሃይ አንድነት ሊመሠርቱ ይገባቸዋል የሚላቸው አብዛኞቹ የዓለማችን ሃይማኖቶች : በተለያየ መልኩ : ዞሮ ዞሮ " የሰው ልጅ መዳን አለበት ' ብለው የሚያስቡ ናቸው :: አንዳንዶቹ ከጥንተ አብሶ ሲሉ : ሌሎቹ ከገሃነም : ሌሎቹ ከሰይጣን መንፈስ : ሌሎችቹ ከራሱ ..... ወዘተ እያሉ ይቀጥላሉ ::

ታድያ : አንተው ራስህ እንዳስቀመጥከው ባሀይ እነዚህን እምነቶች "ያው ከአንዱ እግዚአብሔር የመጡ ናቸውና ስለሰላምና ስለአንድነት በመዘመር በአንድ እምነት ሥር ሊሆኑ ይገባቸዋል " ይላሉ ብለህ ያስቀመጥከውን ትንተና እንዴት "ሪዝነብል " ነው ልትለው ቻልህ ?

_________________
I have great faith in fools; self-confidence my friends call it.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 10:15 pm    Post subject: Reply with quote

ፀዋር እንደጻፈ(ች)ው:
... ሁሉንም ለፍቅር የሚጋብዝ ይህ እምነት በጣም እጅግ በጣም ይሻላል " ማለት ነው :: "ሪዝናብል " ነው ::

... አንድ ነበርን ለአንድም ታሰብንና አንድ እንሁን : የሚል የመዋደድ ጥሪያቸው የዘመኑን ምክንያታዊነት ተላብሷል ::

ግሩም ነው ! እየተግባባን ነው !

ስለዚህ : እንግዲህ : እነዚህ ሃይማኖቶች በሙሉ ወደአንድ ይምጡና ባሃይ እንሁን ብለው (ወይም ሌላ ስም ሰጥተውት ) ሁሉም በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሃይማኖቶች አንድ ቢሆኑ : አንተ በግልህ በጣም ጥሩ ነው ብለህ ትደግፈዋለህ ?

ጥያቄ አትፍራ ጸዋር :: ብዙ ሰዎች እስከዛሬ ለተለያዩ ጥያቄዎችህ መልስ ጽፈዋል :: አንተም በተራህ መልስ መጻፍ አይድከምህ :: እንደምታየው በሰላም እየተወያየን ነው ::

:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መራራ

ውሃ አጠጪ

Joined: 25 Sep 2004
Posts: 1027
Location: united states

PostPosted: Tue Mar 13, 2012 11:07 am    Post subject: Reply with quote

በሬ እና በሬ መከሩ

. ቀንበር ሰበሩ
. ድንበር ዘለሉ
. ገደል ገቡ
. ተጃጃሉ

Laughing Laughing ሁለት በሬዎች እንደጉድ ይማከሩታል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 1:33 am    Post subject: Reply with quote

ጸዋር እዚህ ቤት ዘጋህ ማለት ነው ?

ያለህበት ቤት እመጣለሁ :: ጥያቄውን አንድ ስቴፕ ወደፊት ከመውሰድ ጋር !

:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia