View previous topic :: View next topic
Author
Message
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Sun Feb 19, 2012 7:54 am Post subject: ድምጻችን ይሰማል !
ኢትዮጵያ ውስጥ በመናፍቃን የተገነባው ቤት ይፈርሳል !" "አህባሽ እያቀጣጠለ ያለው እሳት ይጠፋል ! " "የአክሱም ሃውልት ወደቤቱ እንደተመለሰው ሁሉ የኢትዮጵያ መጅሊስ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ሊመለስ ይገባል፡፡ " ዳዒ ያሲን ኑሩ
http://www.youtube.com/watch?v=rb9qhhddAzM
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ውልጮ Joined: 04 Feb 2004 Posts: 376
Posted: Sun Feb 19, 2012 4:39 pm Post subject: Re: ድምጻችን ይሰማል !
ወልድያ
የምጠይቀው ቸግሮኝ ሰንብቼ ነበር አንተም /ቺም ሆነ ሌላ
ቢመልሰው 'አህባሽ ' የሚለው ቃል ምንን ነው የሚወክለው በጀርባውስ ያለው ምንድን ነው ::
በቪዲዮዎው ካየሁት ትኩርቴን የሳበው ወጣቱ ተናጋሪ ከውጭ ስለመጣው አካል ጠቅሶ ራሳችንን ችለን በኢትዮጵያ በቀል መጅሊስ ነው የምንመራው ያለው በጣም ያኮራል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Mon Feb 20, 2012 7:23 am Post subject: Re: ድምጻችን ይሰማል !
ውልጮ እንደጻፈ(ች)ው : ወልድያ
የምጠይቀው ቸግሮኝ ሰንብቼ ነበር አንተም /ቺም ሆነ ሌላ
ቢመልሰው 'አህባሽ ' የሚለው ቃል ምንን ነው የሚወክለው በጀርባውስ ያለው ምንድን ነው ::
በቪዲዮዎው ካየሁት ትኩርቴን የሳበው ወጣቱ ተናጋሪ ከውጭ ስለመጣው አካል ጠቅሶ ራሳችንን ችለን በኢትዮጵያ በቀል መጅሊስ ነው የምንመራው ያለው በጣም ያኮራል ::
ሰላም ውልጮ
አህባሽ ቤዙን ሊባኖስ ያደረገ በሞሳድ በስውር እንድሚደገፍ እና ከፍተኛ የፋይናንስ እገዛ እዳለው የሚነገር ሙስሊም ነኝ የሚል ነው ሆኖም በአለም ዙርያ በኑፋቄ (heresy) እና ጥመት deviation ) የተወገዘ አንጃ ነው
አሁን አቧራ ያስነሳው ግን እምነታቸው ሳይሆን የወቅቱ የኢትዮጵያ
እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሹማምንት የሁለም ሙስሊሞች ተወካይ
መሆናቸውን ከቁም ነገር ሳያስገቡት ከመንግስትና ከሌሎች አካላት ??? በሚደረግላቸው ከፍተኛ ድጋፍ የአህባሽ ጀመዓ የእምነት ፍልስፍና ከሊባኖስ ኢምፖርት በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የወደፉቱ ብቸኛ የእስልምና አቅጣጫ እንዱሆን በማድረግ
ተግባር ላይ ተጠምደው መታየታቸው ነው፡፡
ሆኖም ይሄ ነገር የመግስት ቅጥረኛ በነበረው በመጅሊሱ ላይ back fire አድርግዋል ህዝቡ ጥቃቅን ልዩነቶቹን አስወግዶ አወክሉኝም ባለው መጅሊስ ላይ በአንድነት ተነስትዋል መንግስትም የህዝቡን ድምጽ ከመስማት በቀር የሚጫወትባቸው ብዙ ካርዶች እጁ ላይ የቀሩ አይመስልም
የኢትዮጵያን ልማት እንደግፋለን አሸባሪነትን እንዋጋለን ሆኖም ጥያቅያችን እራሳችን በመረጥነው መጅሊስ እንተዳደር መፈክሩም <<አባይ ይገደባል መጅሊስ ይወገዳል >> የሚል ነው
ስለአህባሽና ስለተቃውሞ እንቅስቃሴው አንዳንድ መረጃዎችን ለመለጠፍ እሞክራለው
ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ውልጮ Joined: 04 Feb 2004 Posts: 376
Posted: Mon Feb 20, 2012 2:31 pm Post subject: Re: ድምጻችን ይሰማል !
ጤናይስጥልኝ ወልድያ
ስለማብራሪያው በጣም አመስግናለሁ :: ለወደፊትም በገባኸው
ቃል የምትለጥፋቸውን ለማንበብ በጉጉት እጠብቃለሁ ::
በነገራችን ላይ ባለፈው መልክትህ ቪዲዮውን ስመለከት
ሁለተኛውን ተናጋሪ ትንሽ አላመንኳቸውም ስርገው የገቡ
የመንግሥት ካድሬ ይመስላሉ ተሳስቼ ሊሆን ይችላል ቢሆንም
ጥንቃቄ ይሻል ትግላችሁ አቅጣጫውን ቢያሰፋው ለወገን
ይበጃል ብዬም አስባለሁ ::
የጂጅዬን ካህን የሚለውን ዘፈን (ቀልጦ እንደሚበራ ሻማ
መብራት በሌለው ከተማ እየቀለጠ በራልኝ እየሞተ አኖረኝ
እያለች የምታቀነቅነውን )ስምቼ እስከመቼ ወደሚለው ዘፈን እየተሸጋገርኩ ነው ::
በቸር ያውለን !!!!!
ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው : ውልጮ እንደጻፈ(ች)ው : ወልድያ
የምጠይቀው ቸግሮኝ ሰንብቼ ነበር አንተም /ቺም ሆነ ሌላ
ቢመልሰው 'አህባሽ ' የሚለው ቃል ምንን ነው የሚወክለው በጀርባውስ ያለው ምንድን ነው ::
በቪዲዮዎው ካየሁት ትኩርቴን የሳበው ወጣቱ ተናጋሪ ከውጭ ስለመጣው አካል ጠቅሶ ራሳችንን ችለን በኢትዮጵያ በቀል መጅሊስ ነው የምንመራው ያለው በጣም ያኮራል ::
ሰላም ውልጮ
አህባሽ ቤዙን ሊባኖስ ያደረገ በሞሳድ በስውር እንድሚደገፍ እና ከፍተኛ የፋይናንስ እገዛ እዳለው የሚነገር ሙስሊም ነኝ የሚል ነው ሆኖም በአለም ዙርያ በኑፋቄ (heresy) እና ጥመት deviation ) የተወገዘ አንጃ ነው
አሁን አቧራ ያስነሳው ግን እምነታቸው ሳይሆን የወቅቱ የኢትዮጵያ
እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሹማምንት የሁለም ሙስሊሞች ተወካይ
መሆናቸውን ከቁም ነገር ሳያስገቡት ከመንግስትና ከሌሎች አካላት ??? በሚደረግላቸው ከፍተኛ ድጋፍ የአህባሽ ጀመዓ የእምነት ፍልስፍና ከሊባኖስ ኢምፖርት በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የወደፉቱ ብቸኛ የእስልምና አቅጣጫ እንዱሆን በማድረግ
ተግባር ላይ ተጠምደው መታየታቸው ነው፡፡
ሆኖም ይሄ ነገር የመግስት ቅጥረኛ በነበረው በመጅሊሱ ላይ back fire አድርግዋል ህዝቡ ጥቃቅን ልዩነቶቹን አስወግዶ አወክሉኝም ባለው መጅሊስ ላይ በአንድነት ተነስትዋል መንግስትም የህዝቡን ድምጽ ከመስማት በቀር የሚጫወትባቸው ብዙ ካርዶች እጁ ላይ የቀሩ አይመስልም
የኢትዮጵያን ልማት እንደግፋለን አሸባሪነትን እንዋጋለን ሆኖም ጥያቅያችን እራሳችን በመረጥነው መጅሊስ እንተዳደር መፈክሩም <<አባይ ይገደባል መጅሊስ ይወገዳል >> የሚል ነው
ስለአህባሽና ስለተቃውሞ እንቅስቃሴው አንዳንድ መረጃዎችን ለመለጠፍ እሞክራለው
ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Tue Feb 21, 2012 12:04 pm Post subject:
ቀዩ ካርድ !
ሩቂያ ሰ ./ አዲስ ነገር ኦንላይን )
በአዲስ አበባ የአሊያ ትምህርት ቤት እና መስጂድ የተጀመረው የሙስልሞች የአደባባይ ተቃውሞ ስምንተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረበት በዚህ ሳምንት አገር አቀፍ መልክ እየያዘ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ ነገር ያደረሱዋቸው መረጃዎች ጠቆሙ። ሰሞኑን ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰበውን 300 ሺህ ፊርማ ጨምሮ በድምሩ ከ 500 ሺህ በላይ የአቤቱታና የተቃውሞ ፊርማ ተሰብስቦ በሕዝብ ለተመረጠው ኮሚቴ መድረሱ ተዘግቧል። ሁኔታው እጅግ እያሳሰበው የመጣው መንግሥት የተወካዮቹን ቁጥርና አይነት በመጨመር ነገሩን ለማብረድ እየሞከረ ነው።
የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን በዛሬው ዕለት ለስምንተኛ ሳምንት በአወሊያ መስጂድ በቀጠለው የዓርብ ስግድት ተቃውሞ በመቶ ሺህ ሊገመቱ የሚችሉ ምእመናን መገኘታቸውን ተመልክተዋል። በዛሬው ዕለት በሕዝብ የተመረጠው (17 አባላት ያሉት ) ጊዜያዊ ኮሚቴ የካቲት 5 ቀን ከመንግሥት ጋራ ስላደረገው ውይይት ባቀረበው ሪፖርት መንግሥት እስከ የካቲት 26 ቀን ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ቃል መግባቱን ገልጿል። ኮሚቴው “እስከ የካቲት 26 መልስ ካልሰጠን፣ መልስ አንሰጥም ማለት ነው። ሁላችሁንም የሚያስደስት መልስ እንሰጣለን፣ ነገር ግን ታገሱ” የሚል ማስተማማኛ ከመንግሥት እንደተሰጠው ሪፖርቱን በጉጉት ሲጠብቅ ለነበረው ሕዝብ አስታውቋል። እስከዚያው ድረስም ጊዜያዊ ኮሚቴው በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሔድ ኢማሞች፣ ሙስሊም ባለሃብቶች እና ምሁራን የሚገኙበት የምክክር መድረክ ለማዘጋጀት ማቀዱን ገልጿል። ኮሚቴው “በአዲስ አበባ ምእመናን የተመረጠ ነው” ከሚል መነሻ የአዲስ አበባውን መጅሊስ እንዲረከብ የቀረበው ሐሳብ በኮሚቴው በራሱ ውድቅ ተደርጓል። የኮሚቴው አባላት በንባብ ባቀረቡት ሪፖርት “ዛሬም ሆነ ወደፊት በየትኛውም የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ አንሠራም። ለምርጫም አንቀርብም” በማለት ችግሩን የመፍታት እንጂ ሥልጣን የመያዝ ፍላጎት እንደሌላቸው በይፋ አስታውቀዋል። ይህም ለሕዝብ ያላቸውን ታማኝነት የሚያረጋግጥ ተደርጎ ተወስዶላቸዋል።
ከጊዜያዊ ኮሚቴው ጋራ የተገናኘው የመንግሥት ተወካዮች ቡድን በተመሳሳይ ከእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ ) አመራሮችም ጋራ መወያየቱ ታውቋል። በዚህ ውይይትም ከደኅንነት ሹማምነት መካከል አንዱ ናቸው የተባሉት (አለቃ ) ጸጋይ ለመጅሊሱ አመራሮች ጠበቅ ያለ መሳሰቢያ መናገራቸውን የቅርብ ምንጮች ተናግረዋል። “ራሳችሁንም መንግሥትንም ከዚህ አጣብቂኝ አውጡ። አለበለዚያ ቀዩን ካርድ ለእናንተ ማውጣታችን አይቀርም።” በሌላ በኩል እየቆየ ነገሩ ያሳሰበው የሚመስለው ኢሕአዴግ በየደረጃው የሚገኙ ሙስሊም አባላቱን “በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመመካከር” በሚል ለነገ ቅዳሜ ስብሰባ መጥራቱን የተለያዩ የአዲስ ነገር ምንጮች ገልጸዋል።
ይኸው ከዓርቡ ሳምነታዊ ስግደት ጋራ ተያይዞ በመገለጥ ላይ ያለው በመጅሊሱ ላይ ያነጣጠረ ተቃውሞ ወደሌሎች ከተሞችም መዛመቱ እየተነገረ ነው። ከዚሁም ጋራ ተያይዞ ዛሬ ዓርብ የታተመው “ሠለፊያ” ጋዜጣ እንደዘገበው ከአፋር፣ ጅማ፣ ገለምሶ፣ አሰላ፣ ወልቂጤ፣ ትግራይ፣ ከኩፍቱ፣ አላማጣ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን የተሰበሰበ ከ 300 ሺህ የሚበልጥ የሕዝብ አቤቱታ ፊርማ በሕዝብ ለተመረጠው ጊዜያዊ ኮሚቴ ቀርቧል። ይሁንና ይህንን የአቤቱታ ፊርማ ለማሰባሰብ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች የታሰሩባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውም ተዘግቧል። በዚህም በወልቂጤ 15፣ በምዕራብ ወለጋ 5፣ በትግራይ 18 ሰዎች መታሰራቸው ተነግሯል። በአዲስ አበባም በንፋስ ስልክ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ከአራት ያላነሱ ሰዎች መታሰራቸውን ምንጮች ለአዲስ ነገር ገልጸዋል።
በመጅሊሱ ላይ የሚደረገው ተቃውሞና ግፊት ቀጥሎ የአፋር ኡለማዎች ከዚህ በኋላ ለፌዴራሉ መጅሊስ እውቅና እንደማይሰጡ በመግለጽ ለመጅሊሱ ለራሱ እና ለመንግሥት በደብዳቤ ገልጸዋል። በሶማሌ ክልልም የአሕበሽን ስልጠና ተካፍለው የተመለሱና የመጅሊሱ የሥራ ሐላፊዎች ሳይታሰሩ እንዳልቀረ ተሰምቷል፤ ሆኖም የአዲስ ነገር ዘጋቢዎች ጉዳዩን ለማረጋገጥ አልቻልንም።
በሌላ በኩል በውጭ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንም በየአገሩ በሚገኙ ኮሚኒቲዎቻቸው በኩል ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፤ ለጊዜያዊ ከሚቴው ያላቸውን ድጋፍ፣ ለመጅሊሱ ያላቸውን ተቃውሞ የሚገልጹ ደብዳቤዎችን በላካቸው ታውቋል። ጊዜያዊ ኮሚቴው በሪፖርቱ እንዳለው የትግራይ ሙስሊሞች ኮሚዩኒቲ በካናዳ፣ የአፋር ኮሚዩኒቲ በካናዳ፣ የኦሮሞ ሙስሊሞች ኮሚዩኒቲ በካናዳና በዳላስ፣ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኔትወርክ በአውሮፓ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌዎች ኮሚዩኒቲ በካናዳ ከእነዚሁ ውስጥ የሚተቀሱ ናቸው። ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል የተባለው የሙስሊም ዳያስፖራ ኮሚቴ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማነጋገር በቅርቡ አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል።
ተቃውሞ የበረታበት መጅሊስ የካቲት 3 እና 4 ቀን በአዲስ አበባ መስጂዶች ስብሰባ ቢጠራም ብዙ እንዳልጠገኘለት የአዲስ ነገር ምንጮች ገልጸዋል። በአንዳንዶቹ መስጅዶችም ስብሰባዎች በጠብና በሁከት ተጠናቀዋል። በሰለሃዲን መስጂድ በተቀሰቀሰ ጠብ ከመጅሊሱ ተወክለው የተላኩት ሰዎች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸውና ከመካከላቸውን የተፈነከቱ እንደነበሩ እማኞች ገልጸዋል። መጅሊሱ የሾማቸው የመስጂዱ ኢማም በጠቡ መካከል እጃቸው ሳይሰበር እንዳልቀረ ተሰምቷል። ትናንት ሐሙስ የበኒን መስጂድ ምክትል ኢማም መጅሊሱን በመደገፍ መናገራቸው ያስነሳው ረብሻም የፖሊስን ጣልቃ መግባት የጋበዘ ነበር። ሰውየው እንዲህ አሉ፣ “መጅሊስን መቃወም ሐራም ነው።” እንደተሰማው ኢማሙ ከመስጂዱ የወጡት በፖሊስ ታጅበው ነው።
በተቃውሞና በግፊት ከየአቅጣጫው የተወጠረ የሚመስለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ ) አመራር ከአጣብቂኙ በአሸናፊነት ለመውጣት ጥረት ማድረጉ እንዳልቀረ ለማወቅ ተችሏል። ታዛቢዎች የመጅሊሱ የመጫወቻ ካርዶች እንዳለቁ ያምናሉ። የመጨረሻው ካርድ በአቶ መለስ እጅ የሚገኘው ካርድ ነው። መጅሊሱ በፖለቲካው መስክ ተቃዋሚዎቹን “በአክራሪነት” እና “በሽብርተኝነት” በመፈረጅ የመንግሥትን ድጋፍ የማግኘት ስትራቴጂው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መሥራቱ ቢታወቅም ገንፍሎ የወጣውን የበርካታ ሙስሊሞች ተቃውሞ ሊገታ የሚችል አልሆነም። መንግሥትም የሕዝብን ጥያቄ “የአክራሪ እና የሽብርተኛ” እያለ መጠርጠሩን ሙሉ በሙሉ ባይተውም መጅሊሱን እንደቀድሞው በደፈናው ከመደገፍ ስትራቴጂው በማፈግፈግ ላይ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ። በብዙ መልኩ መንግሥትም ቢሆን ብዙ ካርዶች በእጁ የሉም።
በቅርቡ “በኢትዮጵያ ውስጥ የአልቃኢዳ መረብ ተጋለጠ” በሚል የተሰራጨውን ወሬ እንደታሰበው የብዙ ሙስሊሞችን ትኩረት የሚስብ እንዳልሆነ አንድ አስተያየት ሰጪ ለአዲስ ነገር ተናግረዋል። “አሁን ለሌላ አጀንዳ ጊዜ የለንም፤ በመጅሊሱ ላይ ባነጣጠረው ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃውሞዋችን ውጤት እስክናገኝ አንቀጥላለን” ብለዋል እኚሁ ማንነታቸውን መግለጥ ያልፈለጉ ግለሰብ። ብዙ ታዛቢዎች መንግሥት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንዳደረገው የለውጥ ጠያቂዎችን ፍላጎት በማኮላሸት፣ ታማኞቹ ባሉበት እንዲቀጥሉ ያደረገበትን ስትራቴጂ በመጅሊሱ ላይ መድገም መቻሉን ይጠራጠራሉ። ምክንያታቸው ደግሞ ይህኛው የሙስሊሞች የለውጥ ጥያቄ ይፋ የወጣ የሕዝብ ድጋፍ ስላለው በቀላሉ ለማዳፈን የማይቀል መሆኑ ነው። በተጨማሪም መንግሥት ከዚህ ቀደም በ 1987 በአንዋር መስጊድ የተከሰተው አይነት ግጭት በሙስሊሞች መካከል እንዲነሳ ፈጽሞ እንደማይፈልግ ብዙዎች ይገምታሉ። “መንግሥት ከአንዋር መስጊዱ ጥፋት ትምህርት ወስዷል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ቀደም ሲል የጠቀስናቸው ምእመን ይናገራሉ። ቀዩ ካርድ የሚገኘው በሕዝበ ሙስሊሙ እና በመንግሥት እጅ ነው። መንግሥት ቀዩን ካርድ ለመጅሊሱ ቀድሞ ካልሰጠ ካርዱ በእርሱ ላይ እንደማይመዘዝ ማስተማመኛ ያለው አይመስልም። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ቀጣዮቹን ዓርቦች የሚጠብቁት ለፈጣሪያቸው የተለመደውን ምስጋጋና ልመናቸውን ለማቅረብ ብቻ አይደለም። ቀዩ ካርድ።፤
ምንጭ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Sat Feb 25, 2012 7:59 am Post subject:
የትላንቱን የአወልያ ውሎ በተመለከተ ከፌስ ቦኦክ ያገኘሁት ይህን ይመስላል
አወሊያ 8ኛውን ሳምንት የህዝብ ተቃውሞ አስተናግዳ ዋለች !
የሙስሊሙ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥባቸው ለየካቲት 26 ቀጠሮ በተያዘበት ሁኔታ አወሊያ በዛሬው ዕለት ባልተጠበቀ የህዝብ ማዕበል ተጥለቀለቀች፡፡ በዕለተ ረቡዕ ምሽት ራዲዮ ፋና ያስተላለፈው ሚዛናዊነት የጎደለው ፕሮግራም የብዙሃንን ቀልብ ሰብሮ ከተቃውሞ የትዕይንት መድረኩ ያርቃቸዋል የሚል ግምት የተሰጠው ቢሆንም በተቃራኒው “የኛ ሰዎች የሚሉትን መስማት አለብን” በማለት መንፈሰ ጠንካራው ሙስሊም ህብረተሰብ በአወሊ ተገኝቷል፡፡ አወሊያ ዛሬም ከ 100 ሺህ በላይ ሙስሊሞችን አስተናግዳለች፡፡ ዕለቱን በጉጉት ሲጠባባቅ የከረመው ሙስሊም ህዝብ አወሊያ መድረስ የጀመረው ገና በማለዳ ነበር፡፡የተለያዩ መልዕክት በሚያስተላልፉ መፈክሮች ያሸበረቀችው አወሊያ ምድረ -ጊቢው በቅፅበት ሰው በሰው ለመሆን በቃች፡፡ከመጀመሪያው የጁምዓ አዛን በኋላ ከመድረክ የተሰማውን የማስጠንቀቂያ መልእክት ተከትሎ ኢስላማዊ አንድነትን በማስመልከት በኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ የቀረበው በይዘቱ ለየት ያለ፣ ብዙሃኑን የማረከና ጠንካራ መልዕክት የተላለፈበት ዳዕዋ የዕለቱ መድረክ ፈር ቀዳጅ ሆኗል፡፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ በተለየ ሁኔታ ለአንድነትና ለመቻቻል በተለይም በዚህ ቀውጢ ቀን ከሙስሊሙ ኡማ የሚጠበቀውን ኃላፊነት በማስመልከት ያቀረበው ዳዕዋ ሚናው ከአስተማሪነት የላቀ ነበር፡፡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በታዳሚው ዘንድ ጉርምርምታ የፈጠረው የማይክራፎን ችግር የጥቂት ሰዎችን ሃሳብ መስረቁ አልቀረም፡፡
የጁምዓ ሰላት ተከትሎ የቀጠለው የዕለቱ ትዕይንት በርካታ ክንውኖችን አስተናግዷል፡፡ በዕለቱ አብዛኛው ተሳታፊ “መጅሊስ አይወክለኝም !” የሚል መልእክት ያዘለ “ባጅ” ደረት ላይ የለጠፈ ሲሆን በእጃቸውም ሳምንታዊ እና የተቃውሞው አካል የሆነቸውን “ድምፃችን ይሰማ” በራሪ መፅሄት ይዞ ተስተውሏል፡፡ በዕለቱ ከቀረቡ፣ በመፈክርና ተክቢራ ከታጀቡት የመድረክ ዝግጅቶች መካከል በሴት እህታችን አማካይነት የቀረበውና የሳምንቱን ውሎ የሚተነትን የአስተማሪነትና አዝናኝነት ይዘት የነበረው የዜና ዘገባ ይገኝበታል፡፡ይህን ተከትሎ ከእስከዛሬው ለየት ባለ መልኩ ህዝቡን በሃይለ ቃል የመፈክር ስሜት ይዞ የተጓዘውና በዶ /ር ኢብራሂም “አይሆንም !” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ንባብ ከፍተኛ መነቃቃትን ከመፍጠሩ በሻገር ፈፅሞ የማይረሳ ትዝታ ጥሎ አልፏል ማለት ይቻላል፡፡
ሰፊውን የመድረክ ሰዓት የወሰደው ዝግጅት ወቅታዊው የመጅሊስ ፕሬዝዳንት አቶ አህመዲን በራዲዮ ፋና ያቀረቡትን ተረት ተረት የተመለከተ ነበር፡፡ የግለሰቡን ውሸት የተሞላበት ንግግር ለህዝብ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አወሊያን፣ ተማሪዎቹንና ውስጣዊ ስርዓቱን አስመልክቶ ከኮሌጁ ተማሪዎች መካከል ተማ ተውፊቅ የሰውዬውን ንግግር ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚያደርግና በመረጃ የታገዘ ማስተባበያ አቅርቧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ አህመዲን አወሊያ ኦዲት የሚባል ነገር አያውቀም ሲል ያሰሙትን ውንጀላ አስመልክቶ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ቁልጭ ያለ መረጃ ለህዝቡ በማስተላለፍ አራቁቷቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ አህመዲን መጅሊስን፣ የራሳቸውን ወደ ስልጣን አመጣጥ እና ምርጫን በማስመልከት የሰጡትን በውሸት የታጨቀ ንግግር ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በታሳታፊው ዘንድ አግራሞትን በጫረ ሁኔታ የሰውዬውን ንግግር ቃል በቃል ከጫወታ ውጭ አድርጓል፡፡
ሰፊ ህዝባዊ መሠረት ያለው የሙስሊሞች ተቃውሞ ህብረ ብሄራዊ ይዘትነቱን ያመላከቱና በትግሪኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የቀረቡት ሁለት ግጥሞች የአንድነት ስሜቱን ጥንካሬ ሰጥተውታል፡፡ አህባሽን ከቱርክ፣ የመን፣ሴኔጋል ወዘተ አገራት እናስመጣለን እያሉ መጅሊሶች ሰሞኑን እያራገቡት ያለውን ወሬያቸውን አስመልክቶ “እነኚ ሰዎች ማንን ነው የሚሸውዱት ? ሊባኖስ መሰረቱን ያደረገውና በነዚህ አገሮች ቅርንጫፉን የዘረጋውን ቡድን የአገር ስም ለውጦ መልኩን ቀይሮ ሊያመጡት ነው፡፡” ሲል የመጅሊስን ተንኮል ያጋለጠው ታዋቂው ዳዒ ኡስታዝ በድሩ ነበር፡፡ አህባሾች ሱፍይ ነን እያሉ ያምታታሉ ሰዎች ተጠንቀቋቸው የሚል አዝናኝ ይዘት ያለው መልዕክት ታዋቂው “ደረሳው በከተማ” መነባንቡን አቅርቧል፡፡
የመጨረሻውና በኡስታዝ ሠይድ የቀረበውን ረዥም ዱዓ ተቀድሞ የቀረበው ፕሮግራም የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ንግግር ነበር፡፡ በዋናነነት ትኩረት ሰጥቶ የነበረው በፋና ተጋብዘው የተቀረፀው የአንድ ሰዓት ከሃያ ዝግጅት ተዛብቶ፣ ሚዛናዊነት ጎድሎትና የተላለፈውን መልዕክት ገፍቶ የቀረበ መሆኑን በማስረዳት ነበር፡፡ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለአዘጋጁ መልዕክት ያስተላለፉ መሆናቸውን ገልጧል፡፡ በቀረጻ ፕሮግራማቸው ሂደት ያልዳሰሱት ተጨባጭ ሃቅ እንዳልነበረ ያስረዳው ኡስታዙ ህዝቡ የጣለባቸውን አደራ ሳያዛንፉ የጠራ መልዕክት በሚዲው በኩል እንዳስተላለፉ በአፅኖት አብራርቷል፡፡ ህዝቡም ይህንን ተረድቶ የግንዛቤ ማስተካከያ እንዲያደርግ መልዕክቱን ያስተላለፈው ኡስታዙ መንግስት ሚዲያውን ተጠቅሞ ያስተላለፈውን አጭርና አግባብነት ያለውን መልዕክት ለሰፊው ህዝብ ያላቸውን ከበሬታ ያሳያል በማለት ንግግሩን ቋጭቷል፡፡
የዕለቱ ዝግጅት እንከን አልባ ሆኖ በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ ከአወሊያ እስከ ፓስተር አካባቢ የተመመው የህዝብ ጅረት በሠላም ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡
ድምፃችን ይሰማ !
ይህ በንዲህ እንዳለ እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የቀጠለውን ተቃውሞ ፈር ለማሳት መጅሊስ የተለያዩ ጥረቶች አድርጎ የነበረ ከነዚም መሀል ህዝቡ መጅሊስ አይወክለንም የሚል ባጅ ለጥፎ ወደመስጊዱ ሲገባ ከመጅሊስ የተላኩ ቅጥረኞች ኢህአድግ አይወክለንም የሚል መፈክር ሲበትኑ የነበረ ሲሆን ሆኖም ብዙ ወረቀት ሳይበተን በታኞቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ጥረት በመደረጉ ሳይሳካላቸው መቅረቱንና ከመቶ አርባ ሺ በላይ የተገመተው ሰው እንዳመጥጡ ወደየቤቱ ተመልስዋል
ህዝቡ ለተለያዩ ሲናሪዮዎች እራሱን ማዘጋጀት ይጠበቅበታል ከነዚህም አንዱ ተደጋግሞ እንደታየው ረብሻ በማስነሳት ወይንም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር የተቃውሞውን መሪዎች ለቅሞ በማሰር ተቃውሞውን ማኮላሸት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ሆኖም ህዝቡ ለዚህ ቀድሞ በስነልቦና መዘጋጀትና ያለመሪም ቢሆን አላማው ግብ እስኪመታ ተቃውሞውን በሰላማዊና በሰለጠነ መልክ መቀጠል ይጠበቅበታል !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ውልጮ Joined: 04 Feb 2004 Posts: 376
Posted: Sat Feb 25, 2012 2:01 pm Post subject:
ዜናውን ስላካፈልክ በግሌ አመሰግናለሁ ::
ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው : የትላንቱን የአወልያ ውሎ በተመለከተ ከፌስ ቦኦክ ያገኘሁት ይህን ይመስላል

Posted: Fri Mar 09, 2012 9:13 pm Post subject:
1/2 ሚልዮን ሙስሊሞች ዛሬ በአወልያ አህባሽንና መጅሊስን ተቃውሞ ዋለ !!!
አላሁ አክበር !!!አላሁ አክበር !!! አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብን ያስተናገደዉ የአወልያ የጁምአ ዉሎ !!!! በዛሬዉ እለት በአወልያ አምስ መቶ ሺህ የሚጠጋ ሙስሊም ህብረተሰብ ለጁምአ ሰላትእና ዉጤት ለመስማት እንደተገኘ ተገለፀ ::የጁምአ ሁጥባ በአወልያ መስጂድ ምክትል ኢማም በኡስታዝ ሱለይማን የቀረበ ሲሆን ሁጥባዉም የአህባሽን ጥመት በማስመልከት የቀረበ ነበር ::ሁጥባዉም እንደተናቀቀ የጁምአ ሰላት በኡስታዝ ሱለይማን ኢማምነት የተሰገደ ሲሆን በሰላቱም ላይ በተደረገዉ የቁኑት ዱአ የአብዛኛዉ ሙስሊም አይን በእንባ እንደታጠበ ተመልክቷል :: ሰላቱም ከተጠናቀቀ ቡሀላ መድረክ መሪዉ መድረኩን በመረከብ ህዝቡ አንድነቱን እስከመጨረሻዉ ለመጠበቅ እጅ ለእጅ በመያያዝ ቃልኪዳን እንዲገቡ በማድረግ ፕሮግራሙን መጀመሩን በተክቢራ አብስሯል :: የመጀመሪያዉ ፕሮግራም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ከመንግስት ጋር የሙስሊሙ ተወካዮች ያደረጉትን ዉይይት ምን ይመስል እንደነበር በደንብ አብራርቷል :: በፌደራልጉዳዮች ሚኒስተር ለኮሚቴዎቹ ተገብቶላቸዉ የነበረዉን ቃል በሙሉ ያልፈፀመ መሆኑን ገልፀዋል :: ከዚህም መካከል የስም ማጥፉቱ እንደሚቆም እና ማንኛዉም ሰዉ አይታሰርም ብሎ ቃል የገባ ቢሆንም ከዛ ቡሀላ ግን በጣም ብዙ ሰዎች መታሰራቸዉን እና የኮሚቴዎቹን ስም ማጥፉት መቀጠሉንም ገልፀዎል ::በየካቲት 26ቱም ስብሰባ ሚዲያዎች የቀረፁትን ለህዝብ ከመቅረቡ በፊት ኮሚቴዎቹ እንደሚያዩት ቃል ቢገባላቸዉም ስብሰባዉ ሳያልቅ ኮሚቴዎቹ ለመግሪብ ሰላት በወጡበት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዴታ አቶ ሙሉጌታ ለሚዲያ ዉጤቱን ማስተላፉቸዉን ጨምረዉ ገልፀዋል :: በሁለተኛዉ ፕሮግራም ህዝበ ሙስሊሙ በጉጉት ሲጠብቀዉ የነበረዉ የየካቲት ሀያስድስቱን የመንግስት ምላሽን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች ሰብሳቢ በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ቀርቧል :: በሪፓርቱም መሰረት መንግስት ሰጠሁት ያለዉ ምላሽ ሙስሊሙ የጠየቃቸዉን ጥያቄዏች በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም ሲዞዞር እንደነበር ገልፀዎል :: በመንግስት የተሰጠዉ ምላሽ እላዩ ሲታይ መልስ የሚመስል ነገር ግን ምላሹ ብዥታ ያለበት እና ጥልቅ ማብራሪያ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዎል ::
ምላሾቹ ግልፅ ባለመሆናቸዉ እንዲብራሩ ቢጠየቁም እንዳልተብራራላቸዉ ገልፀዎል :: በመንግስት ምላሽ መሠረት የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ በተቻለ መጠን በፍጥነት በገለልተኛ ወገን ይካሄዳል የሚል የተዳፈነ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አህባሽን በተመለከተ አህባሽ አዲስ ሳይሆን የቀድሞዉን እስልምና የሚያስተምር ነዉ :: በማንም ሰዉ ላይ ጫናም ሆነ ግዳጅ አላደረገም ስለዚህ አህባሽ ይቀጥላል ማለታቸዉን እና አወልያ አክራሪዏችን ሲፈለፍል የኖረ ተቖም ስለነበር መጅሊስ ተረክቦት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ ቀጥሎ ሳላ ለህዝብ ይሰጥ ብሎ ማለቱ ተገቢ አይደለም በመሆኑም በመጅሊስ ስር እንዳለ ይቀጥላል በማለት መንግስት ምላሹን የሰጠ መሆኑን ገልፀዎል :: በዉይይቱ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ዉይይቱን ወደሌላ አቅጣጫ ለመዉሰድ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ጨምረዉ ገልፀዎል :: በዉይይቱ መጨረሻ ላይም ኮሚቴዎቹ መንግስት የሰጠዉ ምላሽ ለጥያቄዎቻችን የተሟላ ምላሽ ባለመሆኑ ለሚቀጥለዉ የመንግስት አካል እስከ ጠ /ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ድረስ ጥያቄዎቹን እንደሚያቀርቡ በመግለፅ ስብሰባዉን መጨረሳቸዉን እስታዉቀዋል :: ኡስታዝ አቡበከር ሪፓርቱን ከጨረሰ ቡሀላ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ለፌደራል ጉዳዮች የገባዉን የኮሚቴዉን አቖም የሚገልፅ ደብዳቤ ለህዝቡ አንብበዋል :: በመጨረሻም የመጅሊስን ታሪክ እና ግድፈቶች በማስመልከት ሀሰን አሊ ፕሮግራም አቅርቧል :: የዛሬዉ ተአምራዊ የአወልያ ሰልፍ ዱአ በማድረግ ተጠናቖል :: ሁለተኛዉየትግል ምእራፍ መጀመሩም የዛሬዉ የአወልያ ዉሎ አሳይቶናል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ውልጮ Joined: 04 Feb 2004 Posts: 376
Posted: Sat Mar 10, 2012 1:15 pm Post subject:
ስላካፈልከው ዜና በግሌ አመሰግናለሁ ::
ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው : 1/2 ሚልዮን ሙስሊሞች ዛሬ በአወልያ አህባሽንና መጅሊስን ተቃውሞ ዋለ !!!

Posted: Sun Mar 11, 2012 2:48 pm Post subject:
ወገኔ ውልጮ እጅግ አመሰግናለው ከአንዳንድ እውር ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነን ብለው ከሚያስቡ ሆኖም ግን በአስተሳሰባቸው ከወያኔ ምናልባትም የከፉ ሊሆኑ ከሚችሉ ሰዎች በተጻራሪ የወገኖቼ ጉዳይ ጉዳዬ ነው ብለህ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተህ መከታተልህ ከጠባብነት የጸዳህ መሆኑን ያሳያል
ከአክብሮት ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Thu Mar 15, 2012 12:57 pm Post subject:
ሰላም
የተደገሰልንን ድግስ ከቪዲዮው ያዳመጡ
ሀምሌ 7፤ 2003 በሀረር ካምፓስ የአህባሽ ስልጠና ላይ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ /ር ሽፈራው ተክለማርያም ያቀረቡት ዛቻ "እኛ የምናስተምርበት መንገድ ትንሽ ለየት ትላለች፡ ስንፈልግ ቆንጠጥ እናረጋለን : እናንተ ደግሞ ከማድረጋችን በፊት ዳበስ ዳበስ እያደረጋችሁ ታስተምራላችሁ :: ሁለቱን ደምረን እንደምንም እናስተካክላለን ፤ የማይማር ካለ በሚማረው መልኩ እንዲማር እናረጋለን ::”
http://www.youtube.com/watch?v=zH6rs8Bu7LY&sns=fb
ይህንንም ማስጠንቀቅው ያንብቡ
ማስጠንቀቂያ !!!! ሙስሊሞች ሆይ ንቁ !!! እየተደገሰልን ያለውን ለሙስሊሞች ሁሉ በማሳወቅ ኢስላማዊ ሃላፊነታችሁን ተወጡ !!!
መንግስት የህዝብ ሙስሊሙን ቀጥተኛ ጥያቄ በፍጥነት በመመለስ ፋንታ ኮሚቴዎቻችንን በማጥቃት ጥያቄያችንን ለማስቀልበስ ሙከራውን ተያይዞታል። የደህንነት ድርጅቶች የህዝብ ብሶት የወለደውን ጥያቄያችንን ችላ በማለት ‹‹ችግር የሚፈጥሩት አቡበከር አህመድና አህመዲን ጀበል ናቸው፤ አቀናባሪዎቹ ሁለቱ ናቸው›› በሚል ነጥሎ ለመምታት ጥረት እያደረጉ ነው። ሁለቱንም ከአልሸባብ እና ከግንቦት 7 ድርጅቶች ጋር አያይዞ ለመክሰስ ዝግጅት እያደረጉ ናቸው። ከነሱ በማለፍ የሌሎቹን የኮሚቴ አባላት የኋላ ታሪክ እንዲያጠኑ የመጅሊሱ ተራ ሌባ ጀማል ሙሐመድ ሳላህና ኮማንደር ሙራድ ከሌላ አንድ ግለሰብ ጋር የተመደቡ ሲሆን ሸክ ዩሱፍንና ሸክ መከተን ‹‹ዱሮ ሸሪዓ ፍርድ ቤት እያሉ ሙስና አጭበርብረዋል›› በሚል የሃሰት ስም ማጥፋት ዘመቻ ሊያካሂዱባቸው እንቅስቃሴ ላይ ናቸው። የዳኢ ያሲን ኑሩን ስም ለማጥፋት ‹‹ጎንደር እያለ ያልሰራው ሐራም የለም፤ ጠጪ ነበር ሰካራም ነበር›› በሚል ስም ለማጥፋት፣ ዳኢ አቡበከር አህመድንም እንዲሁ ‹‹ደሴ እያለ መጥፎ ሰው ነበር›› በሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ ለማጧጧፍ አስበዋል።
የኮሚቴውን ጥያቄ ተቀብሎ አካሄዳቸውን የሚያወግዝ የሽማግሌዎች ተቃራኒ ቡድን ካሁን በፊት ያቋቋሙ መሆኑም ይታወሳል። አሁንም ይህ በ 1987 ብጥብጥ ዋነኛ ተዋናይ በነበሩት ግራዝማች ሃዲስ ኑርሁሴን የሚመራው ቡድን እንቅስቃሴውን የጀመረ ሲሆን ከአስራ ሰባቱ ኮሚቴዎች ውስጥ ሸምገል ያሉትን ነጥሎ ለማውጣትና ኮሚቴውን ለሁለት ለመክፈል በደህንነት ድርጅቶች በኩል ጥረት እየተደረገ ነው !!! ሽማግሌዎቹን የኮሚቴ አባላት ‹‹ወጣቶቹ ሌላ አጀንዳ ያላቸው ናቸው ! የሚሰሩትን አታውቁም ! አሸባሪዎች ናቸው ! እናንተን ተጠቅመው ሊሸውዷችሁ ነው !›› እያሉ ለመወስወስና ከኮሚቴው ለማስወጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። እንደነሱ ሤራ በሆነ አንድም ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ባልተረፈ ነበር !!! ግን አላህ (ሱ .ወ ) ሴራቸውን ደጋግሞ ያከሽፈዋል ! አላሁ አክበር !!!!
ኮሚቴዎችንን ለማሸማቀቅ በርካታ መንገዶችን እየተጠቀሙ ሲሆን በተረበሸ መንፈስ ውስጥ እንዲሆኑ በየሄዱበት እየተከታተለ ሰላም የሚነሳ የደህንነት ቡድን ተመድቦባቸዋል። በበርካታ መኪኖች ሆነው አላስወጣ አላስገባ እያሉ ሲሆን ወዳጆቻቸውን፣ ዘመዶቻቸውን እና ጓደኞቻቸውን ‹‹ሊታሰሩ ነው ! ሊፈረድባቸው ነው !›› በሚል ወከባ ለመረበሽ፣ ጉዳዩን እርግፍ አድርገው እንዲተዉት ለማስወትወት ጥረት እያደረጉ ናቸው። ቤት አከራዮቻቸው ጋር በመሄድም ‹‹ለአሸባሪ ቤታችሁን አከራይታችኋል›› እያሉ ማስፈራራት ጀምረዋል። ይህም አልበቃ ብሎዋቸው ጠጋ ብሎ በወዳጅነት መንፈስ ከኮሚቴዎቹ መረጃ እየወሰደ የሚያቀብላቸው ሰው ለመመልመል ደፋ ቀና ሲሉ ከርመዋል ! በልቡ ስንጣሪ ኢማን እንኳ ያለው ለኢስላም እንጂ ለሙናፊቆች እንደማይወግን የረሱት ይመስላሉ !!! አላሁ አክበር ሚን ኩሊ ከቢር !!!
ከታላቁ የጁሙኣ ተቃውሞዋችን ጋር በተያያዘ አባዲና (ፖሊስ ሬዲዮ መገናኛ ) በሚገኘው መስሪያ ቤት የሚሰራው አቶ ተክላይ የተባለ የደህንነት አመራር የተመደበ ሲሆን ሙሉጌታ የተባለው ከፍተኛ የደህንነት አመራር በርካታ ጺምና የሙስሊም ገጽታ ያላቸውን ደህንነቶች በብዛት አስመጥቷል። ጁሙኣ አወሊያ አምጥተው አንዳች ነገር ሊያስደርጓቸው ይችሉ ይሆናል የሚል ግምት አለ !!! አላሁ አክበር !! ይህ ሁሉ ምጥ ውስጥ ከመግባት ቀላል ጥያቄዎቻችንን መመለስ አይቀላቸውምን ? ምን ነካቸው ? የሚመክራቸው የለምን ? አላሁ አክበር !!! እስካሁን ስንቴ ለማስበጥበጥ አሰቡ… ጌታችን አላህ ፈተናነ ከላያችን ላይ አነሳልን እንጂ !!! አላሁ አክበር !!!
ልበ ደረቅ የሆኑት የመጅሊስ አመራሮች አህመዲን አብዱላሂና አዛም ከሌላ ሶስተኛ ሰው ጋር ሆነው ባለፈው ሳምንት ቱርክ ሄደው ነበር። እዚያም ወቅፈል ኢክላስ የተባለውን አደገኛ የአህባሽ ድርጅት ያነጋገሩ ሲሆን በቅርቡ ከዚሁ ድርጅት ጋር ስራዎችን መስራት ሊጀምሩ ነው። ምስኪኖች !!! አህባሽን የተቃወምነው ከሊባኖስ ስለመጣ መሰላቸው እንዴ ? አህባሽ ከቱርክ መጣ ከማርስ ያው ሁሌም አህባሽ ነው፤ እንቃወመዋልን ! አላሁ አክበር !!! ከቱርክ ሲመለሱ ወደ አቡዳቢ የሄዱ ሲሆን እዚያም ታላቁን የሱፊያ አሊም ሸክ ሐበብ አሊ ጀፍሪን ተገናኝተዋል። እኒህ በታላላቅ ኢስላማዊ ቻናሎች ላይ የሚታወቁትና ተወዳጁ ሸክ ጠማማው አብደላ ሐረሪ ካከፈሯቸው ምሁራን አንዱ ሲሆኑ መጅሊሶቻችን ያነጋገሯቸው በአንዋር መስጊድ ተገኝተው ጁሙኣ እንዲያሰግዱና ንግግር እንዲያደርጉ ነው። ሸኩ አገራችን ውስጥ እየተረደገ ስላለው የአህባሽ ዘመቻ ምንም የሚያውቁት ነገር የለምና እሺ ብለዋል ! ቢያውቁማ እንኳን ካከፈራቸው የኢስላም ጠላት ድርጅት ጋር ሊሰሩ ይቅርና ዞር ብለው ባላዩዋቸውም ነበር !!!! አላሁ አክበር ! ሸኩን አጉል ሊጠቀሙባቸው እንደሆነ ለመንገር ጥረት እየተደረገ ሲሆን የመጅሊሱ ሐሳብ ግን ‹‹አብደላ ሀረሪ ካከፈሯቸው ጋር እንኳን ተቀራርበን እንሰራለን›› በሚል ገጽታ ግንባታ ሊሞክሩ ነው ! ሰው እስከመጨረሻው እንደጠላቸው አልገባቸውም !!!
ከርታታውና ሙናፊቁ የመጅሊሳችን መሪ አህመዲን አብዱላሂ ከቱርክና አቡዳቢ መልስ በርካታ ብር አጭቆ በፕሌን ድሬዳዋ ሄዷል። እዚያም በፓትሮል ተቀብለውት በገጠርና በከተማ እየዞረ ‹‹ወሀቢዮች ከስልጣናችን ሊያወርዱን ነው ! እንተጋገዝ !›› እያለ የስኳርና የጫት መግዣ ብር እያደለ ይገኛል። አላሁ አክበር !!! ሁሉም እንደሱ ዲኑን በብር የሚሸጥ መስሎታል !!! የህዝብን ጥያቄ በኪሎ ስኳርና በኪስ ገንዘብ የሚሸጥ ከቶስ የት ይገኛል ? ደግሞም አወሊያ የሚሰበሰበውን ህዝበ ሙስሊም ‹‹ወሃቢያ›› የሚል ተለጣፊ ስም በመስጠት ለመከፋፈልና የመዝሃብ ጨዋታ ለመጫወት የሚፈልገውን ይህን ከርታታ ሙናፊቅ ንገሩት… እኛ ሙስሊሞች እንጂ ወሃቢዮች አይደለንም ! የመዝሃብ ልዩነታችንን ወዲያ ገፍተን ለአንድ አላማ የቆምን ሙስሊሞች ነን !!! አላሁ አክበር !!!
የህዝቡ አንድ ሆኖ አህባሽን መቃወም እንቅልፍ የነሳው ይሃው ሰውዬ ካሁን ቀደም እስራኤል ኤምባሲ በመሄድ ‹‹መንግስት ከስልጣናችን ሊያወርደን ስለሆነ አንድ መላ በሉ !›› ሲል ያለቀሰባቸው ሲሆን እነሱም ‹‹አይዞህ እኛ አለንልህ›› ብለውታል። አላሁ አክበር ! እኛ ሙስሊሞች ደግሞ ሲጨንቀን ለሊት ተነስተን ወደአላህ እናለቅሳለን ! አህመዲን አብዱላሂ ከመንፈስ አባቱ አብደላ ሀረሪ በወረሰው መሰረት ይሁዶች ጋር ሄዶ እያለቀሰ ነው ! ሰው ከወደደው ጋር ይቀሰቀስ የለ ? በዚህ ድርጊቱ የተነሳ ደህንነቶች ተቆጥተዋል። ‹‹እኛ እያለን ምን እዚያ ድረስ ያስኬደዋል›› በሚል ስላጋፈጣቸው ተናድደዋል !!!
ከሀረር የህዝቡን ጥያቄና ብዙ ሺህ የፔቲሽን ፊርማዎችን ይዘው መጥተው አቤቱታ ያቀረቡት እና በአወሊያ ንግግር ያደረጉትን የሀረር ኮሚቴዎች የክልሉ መንግስት እያናገራቸው ሲሆን ‹‹እኛ እዚሁ ተነጋግረን መፍታት እየቻልን ለምን እዚያ ድረስ ትሄዳላችሁ ?›› በማለት በብርም ጭምር ለመደለልና ጥያቄያቸውን ለመቀልበስ ጥረት እያደረጉ ነው !!! አዛምን የመሳሰሉ አህባሾችን ላለማጣትም ለምርጫ የሚሆኑ ሰዎቻቸውን እያዘጋጁ ነው፡፡ አላሁ አክበር !!! እነሱ ሁሌም እንዳሴሩብን ናቸው !!! አላህ ደግሞ ሁሌም ሴራቸውን ያከሽፍባቸዋል !!! በዲናችን ለሚመጣ ቅንጣት አንፈራም !!!! አላሁ አክበር !!! እስከመጨረሻው አላሁ አክበር !!!
ያለፈውን የጁምዓ የአወልያ ውሎ ESAT እንደዘገበው
http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=vm78A7qNeJ8TOMORROW ’ S JUMAA PRAYER WILL BE IN AWOLYA. THE NUMBER OF PEOPLE IS EXPETCTED TO BE 1 MILLION. THE PEOPLE ASKS THE RIGHT TO HAVE FREEDOM OF RELIGION AND THE RIGHT TO ELECT THEIR REPRESENTATIVES.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Thu Mar 15, 2012 1:34 pm Post subject:
ሰላም ውልድያ፡
አሁን ያለውን ግርግር ተከትሎ በግሌ ሳጣራ የደረስሁበት ፣ በአካባቢየ የሚገኙ ሙስሊሞች እጅግ በሚገርም ሁኔታ ተደራጅተው ፣ ግርምምምምምምምምምምምም የሚል እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳሉ ታዝቢያለሁ። አንተ የምትለው በህዝብ በተመረጡ “አዲስ መጅሊስ ይቋቋም” የሚለው ከጥያቄያቸው አንዱ ቢሆንም ፣ እስልምና እምነት ግን በኢትዮጵያ እንዳልነበረ ወደሚሆንበት አቅጣጫ መሄዱን ነው የታዘብሁት። ሌላው ቀርቶ አሁን በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች የተቃውሞ ድምጽ “በአንድ በመጅሊሱ” ላይ ያነጻጸረ ይምስል እንጅ ፣ ውስጡ ግን ሙስሊሙን ህበረተሰብ ከፋፍሎታል። የተከፋፈለበትን ሃሳብ ቆየት እያልን በውይይቱ የምናነሳው ይሆናል።
እኔ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ የታዘብሁት ጉዳይ ፣ እራሱ መጅሊሱን የሚቃወሙትም ክፍሎች ፣ ለአገራችን አስጊ የአክራሪነት ስሜት እያስተዋልሁባቸው ነው። ወያኔም የመከፋፈያ ዱላውን እያሳረፈባችሁ ያለው … ይህ ጸረ -መጅሊስ እንቅስቃሴያችሁ ጥሎ የሚያልፈው የሙስሊም -የሞራል -የበላይነት እንዳይኖር ነው። ይህን ያህል ሚሊዮን ህዝብ ፣ በአገሪቱ በነጻነት የእምነት መሪውን መረጠ ማለት ፣ ለወያኔ የስልጣን ዘመን ከፍተኛ ስጋት መሆኑን ያቃል። ስለዚህ ፣ ኢትዮጵያዊውን ሙስሊም እርስ በ እርሱ (በኑፋቄ ) ፣ ከሌላ እምነት አማኝ ኢትዮጵያዊ እና ከሌላው የአለማት ክፍል ጋር በጽንፈኝነት ስም ማጋጨት ነበረበት ፤ እናንተም ግን በደምብ እየተመቻችሁለት ነው።
ትክክለኛው መፍትሄ መሆን ያለበት፡
1ኛ ) ሃባሾች በሚያስተምሩት ዙሪያ የምታነሷቸው ጥያቄዎች እጅግ ተራ እና እርስበርሳችሁ የበለጠ የሚከፋፍሏችሁ መሆኑን በመረዳት ፣ በመጅሊሱ ላይ ማተኮር። (ባሁኑ ሰዓት በሽዎሽ ለሚቆጠሩ የክርስትና አይነት መንስኤው ሁሉም እንደየፍላጎቱ መጽሃፍ ቅዱስን እየተረጎመ በመፈርጠጡ ስለሆነ ፣ እናንተም ወያኔ የሚሰጣችሁን የምትከፋፈሉበት የቤት ስራ አትስሩ )
2ኛ ) ጥያቄያችሁ የአምልኮ ነጻነት መሆኑን በመረዳት ፣ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ በነጻነት አምላኪ መሆን የምትችሉ ባለእምነት መሆን እንደማትችሉ በራሳችሁ ያለፉት 20 የወያኔ አመታት እና ፣ በኦርቶዶክሱ ላይ የተደረገ እና እየተደረገ ያለውን በማመዛዘን ፣ ነጻነት በጋራ የሚመጣ እና ሁሉም እኩል ሊያግኘው የሚገባ መሆኑን በማስተዋል ፣ ትግላችሁን አገራዊ ቅርጽ ማስያዝ።
3ኛ ) የምትቃወሙት መጅሊስ በወያኔ የተቋቋመ መሆኑን አሳምራችሁ እያወቃችሁ እና ወያኔም የሚጠቅመውን እንደሚያውቅ በመረዳት ፣ በተዛዋሪ መንገድ ወያኔን በቃን እያላችሁ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ … “አባይን እንገድባለን” ፣ “አዲስ ለመጅሊሱ የሚመረጡት አንደኛው መስፈርታቸው ወያኔ መሆን አለባቸው” የሚለው የጅል ሃሳብ ፣ ራሳችሁን ከማጃጃል አልፎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋርም እያጋጫችሁ እንደሚሄድ ልብ ብትሉ ይበጃል። ወያኔ እንደሆነ ፍጹም አይታለልላችሁም።
ጥልቁ ዘ -ብሄረ ኢትዮጵያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ወልድያ Joined: 24 May 2010 Posts: 483
Posted: Thu Mar 15, 2012 2:59 pm Post subject:
ሰላም ጥልቁ
ችግሩ ምናልባት ግልጽ አልሆነልህ ይሆናል
እኛ መጅሊስ ውስጥ የትገጠገጡት ሰዎች ካድሬዎች እንደሆኑ ከድሮም እናውቃለን ሆኖም ችለኛቸው ኖረናል
መጅሊስ ውስጥ የተገጠገጡት ሌቦች እንደሆኑ እናውቃለን አንድ ምሳሌ ላሳይህ መጅሊስ ባሁኑ ሀጅና ኡምራ ከአንድ ሰው 40000 ብር ይቀበል ነበር አንድ ተግዋዥ ደግሞ ለትከትና ለለላ ወጪው ከ 30000 ብር በላይ አያስፈልገውም ይህም ማለት ከአንድ ሰው 10,000.00 ብር ያተርፉ ነበር ለሀጅና ኡምራ 10000 ሰው ተጉዝዋል ከአስር ሺ ሰው በሰው አስር ሺ እያተረፈ በጠቅላላ ከመቶ ሚልዮን በላይ ትርፍ አግኝትዋል ገንዘቡን ማን እንደሚካፈለው አምላክ ይወቅ አንድም የልማትና የእርዳታ ስራ መጅሊሱ ሲሰራ ታይቶ አያውቅም ይህ ለእርዳታ ከሚያገኘው ሚልዮኖች ለላ ነው ይህንንም አይተን እንዳላየ ዝም ብለን አለፍን
አሁን ግን በእምነታችን መጡ በስንት መስዋእትነት የተገነቡ መስጂዶቻችን ላይ መማር አትችሉም ተባልን መንግስት የመረጠላችህን ካልሆነ አሉን እና አህባሽ ሆነ ማንም በራሱ ተንቀሳቅሶ ተከታይ ማፍራቱን አልተቃውምንም ነበር አህባሾች በፊትም ማእከል ኖርዋቸው ያስተምሩ ነበር አሁን ግድ በግድ እነሱን ብቻ መከተል አለባቹህ ተባልን
ወንድሜ ትልቁ አንተ ኦርቶዶክስ ነህ ልበል ከአንተ እምነት ያፈነገጠ እራሱን ግን ኦርቶዶክስ ነኝ የሚል ሰባኪ በቤተ እምነትህ መጥቶ ቢሰብክ ምናልባት አክራሪ እንዳትባል (ክርስትያን አክራኢ ነው ተብሎ ባያውቅም ) ልትትገሰው ትችላለህ ወይንም ይህ ትምህርት ልክ እንዳልሆነ አንተ በፈንታህ ታስተምራለህ እንበል ሆኖም አሁንም በኦርቶዶክስ አመራር ላይ ያሉት ልክ እንደሙስሊምቹ በመንግስት የተሾሙ ናቸውና ከመንግስት ተመሳጥረው ይህን አፈንጋጭ እምነት ካልሆነ ለላ አይኖርም ብለው ቢመሳጠሩብህ ምን ታደርጋለህ ? ሁላችንም የተበደልን ቢሆንም የኛ ቀይ መስመሩን አልፎዋል
አንድ ነገር ግን ላረጋግጥልህ እነሱ እንለያያለን ብልው የሸረቡት ነገር በጣም ተለያይቶ የነበረውን ሙስሊም አንድ አድርጎ እራሳቸው ላይ ባክ ፋየር አድርግዋል !
የሚመረጠው አዲስ መጅሊስ ወያኔ መሆን አለበት የሚል ነገር ከየት እንዳገኘህ አላውቅም የኛ ተቃውሞ መንግስስት ታልቃ አይግባብን ነው ! ቢሆንም መንግስት እንደነመንግስትነቱ ተቅዋማትን መቆጣጠር እንዳለበት እናምናለን ጣልቃ አይግባ ብቻ ነው ነው ጥያቄው
ለላው አባይ ይገደባል የምንለው ልማትን እንደምንደግፍ ለማሳወቅ ነው እኔ በግሌም እውን አባይ የሚገደብ ከሆነ ለዚህ ታሪካዊ ስራ ገንዘቤንም እውቀቴንም ሰውቼ አሻራዬን ባሳርፍበት ደስ ይለኛል ማንም አለማው ልማት ከሆነ አልቃወምም
አንድ ነገር ልጠይቅህ ?
Quote:
እኔ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ የታዘብሁት ጉዳይ ፣ እራሱ መጅሊሱን የሚቃወሙትም ክፍሎች ፣ ለአገራችን አስጊ የአክራሪነት ስሜት እያስተዋልሁባቸው ነው።
እንዴት አስጊ አክራሪ እንደሆኑ አስረዳኝ እስኪ ?
ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Thu Mar 15, 2012 3:34 pm Post subject:
ሰላም ወልድያ፡
ያው የኦርቶዶክሱን ጉዳይ በደምብ ስለማታቀው ይሆናል እንጅ ፣ በአሁኑ ሰአት የቤተ ክርስቲያኒቷ ጳጳስ ሆነው የምታያቸው ግለሰብ ፣ ወያኔ ጫካ በሚኖር ጊዜ እርሳቸው በአሜሪካ ውስጥ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን “እራሴን በ እምነት አግልያለሁ” ብለው የምዕራቡን መናፍቅ የተጎናጸፉ ነበሩ። ወያኔ ግን ድጋሜ በክላሽና በደም አጥምቆ የቤተክርስቲያኗ ራስ አደረጋቸው። በአሁኑ ሰአት በነ በጋሻውና በመሰሎቹ የሚሰራው ከቤተክርስቲያኗ ቀኖና ውጭ የሆነው ስርዓተ -ትምህርትም ወያኔ የጫነብን ችግር ነው። ስለዚህ ሁላችንም አንድ ነን። ያም ሆኖ ግን ፣ ኦርቶዶክሱ በእምነቱ አልተናወጠም። እውነቱን አንቆ ይዞ ያችን ቀን ይጠብቃል። እናንተም ፣ ልዩነታችሁን ለወያኔ አታስፉለት። በአክጅራሪነት ዙሪያ የራሴን ትዝብት ልንገርህ …
ለምሳሌ የሃባሽ አስተምሮት ይዞብን መጣ ብላችሁ ከምትነቅፉት አንዱ ሰላት ሲሰገድ ወዴት አቅጣጫ ነው መዞር የሚለውን እንደምሳሌ እንውሰድ። ይህን በ እምነት አይን ስናየው ትልቅ ነገር ነው። ግን ደግሞ ፣ ማንም አስገድዶ ፊትህን እንደማያዞርህ እስካወቅህ ድረስ ፣ አንዳች የልዩነት መንስኤ አድርጎ በፊት አዟዟር አቅጣጫ ከሌላ ሙስሊም ወንድምህ ጋር መነቃቀፍ እና መለያየት ለወያኔ ሲሳይ መሆን ነው። ሌላም ልጨምር … ከአክራሪነት አንጻር ማለቴ ነው። ይህ ውዥንብር ከተነሳ ወዲህ … አንዳንድ ተራማጅ የነበሩ ሙስሊም ጓደኞቸ እጅግ ፈንጠር ብለው በስሜት እየከነፉ ሲሆን ፣ ሌላው ቀርቶ በሚለብሱ የሱሪ ርዝመት እና እጥረት ፣ በሚያሳድጉት የጺም ብዛት እና በተለያዩ የመወዳደሪያ መስፈርቶች ፣ ክርስቲያኑን “ካፊር” ከማለት አልፈው ሄደው የገዛ ሙስሊም ወገናቸውንም በ እምነቱ ደረጃ መስጠት እየተስተዋለባቸው ነው። ይህን ከኔ ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰማኸው እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ባይገርምህ ፣ ትንሽ እራሴን ለመቆጠብ እየሞከርሁ ነው እንጅ ፣ ከዚህም የከፋ እንቅስቃሴ እየተመለከትሁ ነው። ለዛውም ከአገራችን ሁላችንም ርቀን ባለንበት የበአድ ምድር።
ወያኔን ስለመደገፍም … ይሄው እናንተው እራሳችሁ ዋርካ ላይ የለጠፋችሁትን ተመልከት፦
http://dimtsachinyisema.wordpress.com/2012/02/27/%e1%8b%ab%e1%88%8d%e1%88%b0%e1%88%9b-%e1%8b%ad%e1%88%b5%e1%88%9b-%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%88%9b-%e1%8b%ab%e1%88%b0%e1%88%9b/#more-53
መስጅሊስ ውስጥ ተመርጦ ለመግባት “ከኢህአዴግና ከመንግስት ጋር መስራት የሚችል” የሚልን መስፈርት ምን አመጣው ?! የአባይ ግድብ ወሬ የአንድ ሰሞን የወሬ ፍጆታ እንጅ ያን ያህል ታሪካዊም ሆነ ከወያኔ ጋር የሚያጎዳኝም ሆነ አገራዊ አጀንደ እንዳልሆነ ቆይቶ ይገለጽላችኋል።
ለሃጅ የተበላውም ገንዘብ ይበላ … ነጻ መጅሊስ በኖራችሁ ጊዜ ይጣራል። እስከዚያ ድረስ ግን እንደ “የሙስሊሞች ጉዳይ” አይነት ነጻ ፕሬስን ይዛችሁ ህዝቡን ማንቃት። እንጅ … ወያኔ የሚሰጣችሁን የመከፈፋፈያ አጀንዳ አታሳፉ። አንድ ሁኑ። አንድነታችሁ ግን በአገራዊ አጀንዳ ላይ ይመስረት እንጅ … በሁሉም መስኪ ኢ -ዴሞክራሲያዊ የሆነው ወያኔ ለሙስሊሙ ዴሞክራሲያዊ ይሆናል የሚል ህልም የምታልሙ ከሆነ ፣ ፍችው የ እሳት እራት የመሆን ነው።