View previous topic :: View next topic
Author
Message
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Sat Mar 24, 2012 6:34 am Post subject:
ወንድሜ ጥልቁ እንደምን አለህ ?!
ፓስትህን ካነበብኩ በኍላ አንደ ነገር ላብራራ በው ብቅ ያልኩት :: ዝቋላ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የተደረገውን ርብርብ እንደ አንድ ተአምራዊ ሀገራዊ ተልዕኮ አላየሁትም :: የጻፍኩትን እየው እንደገና
ነገር ግን በዚህ ቁም ነገረኛ በጠፋበት ዘመን በሆነው ነገር በማዘን ለጊዜው ማድረግ የሚቻለው እና የሚገባው እሳቱን ማጥፋት ስለነበር ትምህርታቸውን ትተው ተነስተው ያለምንም ነገር ወደ አካባቢው የተመሙ ተማሪዎች ስለ እምነታቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገራቸውም ጭምር የሚያስቡ ወጣቶች እንደሆኑ ለመገመት አያዳግትም :: ይብዛም ይነስም እንደዚያ አይነት ትውልድ በመኖሩ ልንደሰት ይገባል :: በቀጣይነት ደሞ ህወሀት ላሊበላን ወይ ሌላውን ሲያቃጥል እሳት ማጥፋት ብቻ ብቻውን ትርጉም እንደሌለው እና ሆነ ብሎ እሳት የሚለኩሰውን ሀይል መጋፈጥ የግድ እንደሆነ ይገባቸዋል :: ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ ::
የእምነትን ሰው ደሞ እንደ አለማዊው ፍርሀት እና ጥቅም አይበግረውም :: ካመነ አመነ ነው :: ትልቁ ቻሌንጂ በገዛ ሀገሩ የእከካሞቹ ህወሀቶች ተመጽዋች የሆነው ትውልድ አሞቱን ከቶ የአሸናፊነት ስነ ልቦናውን ገንብቶ በየቀኑ እየፈበረኩ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ሌሎች መገናኛዎች የሚግቱትን ባዶ ፕሮፓጋንዳ ተራምዶ አልፎ ለእውነት እና ለመርህ እንዴት ይሞታል ነው ጥያቄው ??? የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ረስቶ እኮ ከእነሱ ጋር የሚስቅ የሚጫወት አብሯቸው መለኪያ የሚጭብጥ ትውልድ አለ እየተባለ ነው የምንሰማው ...ይሔ ነው ፈተናው ! እነሱን እንኳን ማግለል ያልቻለ ትውልድ ! ሲለፋደዱበት ሌላው ቢቀር ተነስቶ አይሄድም ወደ ቤቱ ...ቁጭ ብሎ ከማዳመጥ ?!
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ናፖሊዮን እና ሌላም ተሳታፊ ኢ -ወያኔ ኢትዮጵያውያን፡
ልብ ብላችሁ እንደሆነ አላቅም እንጅ … ወያኔ ከረቀቀው የህይወቱ ማራዘሚያ ስልቱ አንዱ ፣ በተለያዩ ወቅቶች ጊዜውን እየጠበቀ የሚፈጽማቸው ታላላቅ ወንጀሎች አሉ። እነኝህ ወንጀሎቹ ቀጥተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጥቅማቸው ተሰልቶ እና ፣ በእሱ ስር ያሉ ካድሬዎቹን የሚፈትንባቸው ተግባሮች ናቸው።
በመጀመሪያ መታወቅ ያለበት ፣ እየተቃጠለ ያለን ገዳም ሊያድን የሄደን ምዕመን ከማመስገን አልፈን አንዳች አገራዊ መሰዋትነት እየከፈለ እንደሆነ አድርጎ ማወደሱን እኔ አልስማማበትም። በወያኔ ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚከናወንን ስራ ማቆላመጥ በግሌ አእምሮየን አይመጥነውም። ትክክለኛ ሰመአት ማለት ፣ የወያኔን የግፍ -ገደብ ጥሎ ማለፍ የሚችል ሰው ነው። የውርደቱ ነጸብራቅ የሆነ ሃውልት እያየ የሚቀመጥ አዲስ አበቤ ፣ ወንዝ ተሻግሮ እሳት አጥፍቶ መመለሱ ብቻውን በቂ አይደለም።
ወደ ወያኔ ስመለስ … እንደሚታወቀው፦ በተለያዩ አመተ ምህረቶች ፣ ወያኔ የመርካቶ -አዳራሽ ፣ ሸማ ተራ ፣ ኮልፌን እና መሰል አካባቢዎች በድቅድቅ ጨለማ ከነነጋዴዎች ንብረት በእሳት እያቃጠለ ሲያፈናቅልና ፣ ያንኑ መሬትም መልሶ እራሱ ለፈለገው ሲጠቀም አስተውለናል። መሬቱን ሲፈልግ ህዝቡን ማፈናቀል የሰሞኑን የጋምቤላውንም ጉዳይ ልብ እንበል። ቁምነገሩ ግን … ከሚያገኘው ጊዚያዊ የኢኮኖሚ ጥቅም በተጨማሪ … አባላት ካድሬዎቹንም ከህዝቡ ጋር ደም አቃብቶ ከሚኖርበት ዘዴው አንዱ ነው። የ 97ቱን ምርጫ ስናስታውስ ፣ ከምንም ነገር በላይ ወያኔን አጥነክሮት እንጅ አላልቶት አልሄደም። የሰሞኑን የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ እንዴት የተወሰኑ ሰዎች እንዲጮሁ በመፍቀድ የምእመኑን የልብ ትርታ ካዳመጠ በኋላ ፣ እንዴት መልሶ እንደተቆጣጠረው እንመልከት። ስለዚህ ፣ ወያኔ ለሚሰጠን ዜናዎች ምላሽ ከማቅረብ ላቅ ብለን መሄድ ካልቻልን ፣ የግፍ ዜና በላያችን ላይ ሲዘገብ ዘመናትን እንቆጥራለን።
ለዚህ ነው የሰሞኑን እሳት የማጥፋት ዜና ለመነሻነት እንጅ ለመድረሻነት መጠቀም የለብንም የምለው። ዝቋላስ በእሳት የመቃጠሉ ነገር የአይን ምስክር የሚገኝለት ሆነና እሳቱን ለማጥፋት ተሯሯጥን … በታሪካችን ታይቶ በማያቅ የግፍ እሳት የሚለበለበው ህዝባችን እና አገራችንስ እንዴት ነው ከወያኔ እሳት የሚድኑት ? እውነት የኦርቶዶክስ ችግር ይሄ የዝቋላ እሳትና የዋልድባ ገዳም መፍረስ ብቻ ነው ?! … እስኪ የዲያቆን ዳንኤልን ይችን አጋላጭ ጽሁፍ … የተሰወረችና እሳት -አልባ ግፍ እናብብ http://www.danielkibret.com/2012/03/1.html
ዛሬ የቸገረን ይሄ ነው፦
http://www.danielkibret.com/2012/02/yhlt-bt-mkr.html
ሰላም
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
negoageyo Joined: 10 Feb 2005 Posts: 117 Location: australia
Posted: Sat Mar 24, 2012 3:16 pm Post subject:
ተራ ስድብ ከምትለዋወጡ እኮ አንዳንድ ቁም ነገር ለመለዋወጥ ብትሞክሩ ጭንቅላታችሁ የሞላው ንፍጥ እውቀት ማስተናገድ አያቅተውም !!
[quote="ተድላ ሀይሉ "][quote="ጎማ እግሩ "]ተላ
እንዳንተ በመሰሉ ነፈዞች ስሜ በመጠራቱ ቢያሳዝነኝም ግን የቀን ቅዥት ስለሆኑኩብህ ደግሞ ይበልጥ አዘንኩኝ ::
ዋርካ ላይ የምመጣው የነፈዞችን ማላዘን በማየት ለመዝናናት እንጂ መልስ ለመስጠት አይደለም :: ስለሆነም የጠፋሁ እንዳልመስልህ የምትፅፈውን እያያሁ እዝናናለሁ :: በዓላማዬ እንድፀና የሚያደርገኝ ደግሞ አንተና መሰሎችህ በኢትዮጵያ ምድር ቦታ እንዳይኖራችሁ የማደርገው የትግል ጉዞ ነው :: ገና ይቀጥላል ::
ፈንዳ ደግሞ
[quote="ተድላ ሀይሉ "][quote="ኮኮቴ "]እናንተዬ
አሲንባን እግር ተወርች ታስሮ ከሚጠመቅበት ጠበል ፈቶ ; ሰሞኑን ዋርካ ውስጥ የለቀቀብን ማነው ? :D :D :D [/quote]
በአለቆቹ የወያኔ ቁንጮዎች ለእኛ የተመደበለን የሣምንቱ ተረኛ 'ጠርናፊ ' መሆኑ ነው :: በደንብ ካስተዋላችሁ ወያኔዎች ዋርካ ላይ በተራ በተራ እየመጡ ይጠምዱናል :: አንድ ሠሞን 'ጎማ እግሩ ' : "ዳግማዊ ዋለልኝ ' : 'ስልኪ ' ተረኞች ሆነው ይሠነብታሉ :: ከዚያ እነርሱ ደግሞ ለእነ 'ኣሲምባ ' : 'ቢትወደድ ' : 'ማካሮቭ ' ይለቅቃሉ :: ሠንበት ይልና ደግሞ የእነ 'ወዲ -ኒዮርክ ' ዓይነቱ የለቀቀ ወያኔ ዋርካን ይወርራታል :: እንዲህ እያሉ አበላቸውን ይበላሉ ::
[quote]ጠበሉ ካልተስማማው ደግሞ ; "ቀዳማዊያዋ እመቤት " በበላይ ከምታስተዳድረው የአእምሮ ህመምተኞች ሆስፒታል አስገቡት እባካችሁ ... እሷም ለካ ይሄ ነገር ታይቷት ነው "ደፋ ቀና " ብላ ሆስፒታሉን ትኩረት ያሰጠችው :lol:
ኮኮቴ [/quote]
ኮኮቴ :-
ከሆነላትስ ለውሽማዋ ለታምራት ገለታ ቃሊቲ ከዳሚ አድርጋ ብታስመድበው እኛም ትንሽ እናርፍ ነበር :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ተድላ [/quote][/quote]
አላልኳችሁም ነበር :) :) :)
ሠሞኑን አብያተ ክርስቲያናትን በማፍረስና በማቃጠል እንዲሁም ገዳማትን በቡልዶዘር በማረስ ተግባር ላይ ተጠምደህ የሠነበትክ ይመስላል :roll: :roll: :roll: :roll: የሣጥናኤል ቁራጭ በላዔሰብ ወያኔ :evil: :evil: :evil: ::
ተድላ [/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Sun Mar 25, 2012 5:15 am Post subject:
በዋልድባ ገዳም ጉዳይ ላይ በዚህ ሳምንት የቪኦኤው አዲሱ አበበ ሁለት ግሩም ቃለመጠይቆችን አድርጓል ...ድንገት ያልሰማችሁ ካላችሁ ለማስታወስ ነው ::
ሌላ ግን አንድ አስተያየት ሰጪ ""ሰው በስኳር ብቻ አይኖርም "" ሲሉ ነገሩን በምሳሌ አእቀምጠውታል ::
ስኳር የሚወዱት ህወሀቶቹ ነበር ...በትግሉ ጊዜ ስኳር የህወሀት ስቴፕል ፉድ ነበር ይባላል መቸም ወሬ አይደበቅ ምናለበት ዋልድባ ላይ አምጥተው ከሚጥዱት ስኳር ለሚወደው እና በጦርነቱ ለተጎዳው ትግራይ ክልል ወስደው ቢተክሉት ??
ስልኪ እንዴት ትላለህ ??
መነኮሳቱን ስኳር ለማስለመድ ጦርነት መግጠም ለምን ያስፈልጋችኍል ?? ዋልድባን የስኳር አውድማ ማድረግ ለምን ያስፈልጋችኍል ??
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
አንፌቃ Joined: 08 Dec 2004 Posts: 1919 Location: united states
Posted: Sun Mar 25, 2012 6:40 pm Post subject:
ሰላም ናፖሊዮን ..በዚህ አርእስት ብዙ ማለት ይቻላል ...ግን ምንም ዋጋ የለውም የሳይበር ቋሚ ወያኔዎች .. ይህንን አሳፋሪ ድርጊት ለመቃወም ... የመከራከሪያ ምርጉዛቸው ተሰብራ ...ሳንባቸው ተንፍሳ ነው የታየው .. አይደለም የዝቋላውን ቀርቶ ...የዋልድባውን እንኳን መቃወም አልቻሉም ... ነገሩ የፖለቲካው መጣመም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ...የእንጀራ ጉዳይ ሆኖ ነው ..
ትላንት ባለ ብዙ "ትርፍ ለም መሬት " ባለቤት ነን .. እናም ከኛ ተርፎ ለህንድ ..ለቻይና እና ለአረብ ለ 99 አመት ሊዝ በመስጠት 2015 መካከለኛ የኢኮኖሚ እድገት ካላቸው አገሮች እንደመደባለን እያለ የሚቃዠው ወያኔ ... ካልጠፋ ቦታ በልማት ስም "ገዳማትን " እያሳደደ ይገኛል ምክንያቱ ግልፅ ባይሆንም ...ልክ እንደ አህመድ ግራኝ ... እሳት በመልቀቅ እና አንዳንዴም በግዳጅ የአካባቢያቸውን ደን እየመነጠረ ...መነኮሳትን ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አስመስሏቸዋል .. ተተኪ የሌላቸው በብራና የተፃፍ ታሪኮች ብዙዎቹ ወደ አክሱም በመጉረፍ ላይ ናቸው ...ሌሎቹም እየተቃጠሉ ይገኛሉ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈፅሞበታል (ደኖቹ ተመንጠረዋል )...የዋልድባው ገዳም ትንሽ ከወያኔ መልስ መሳይ ያገኘውም ...የትናንትናዋ የጎንደሯ -ወልቃይት ..በዛሬዋ በትግራይ ክልል ስለተካለለች ብቻ ነው እንግዲህ ሀይማኖትንና ታሪክን ማጥፋት ከጀመራችሁ አይቀር ... በነካ እጃችሁ .. ከጎንደር - የጎንደርን ግንብ ..ከወሎ - የላሊበላን ...ከሀረር -የጀጎልን ...ከጅማ - የፈርንጅ አራዳን ..እንዲሁም ካዲሳባ -መርካቶን ወዘተ ...በሳት አጋዩና ገላግሉን ...ከስከሩ አይቀር ብሽቅጥ ይባል የለ . ግን አደራ በአክሱም እና በአድዋ ያሉትን ቤተ ክርስቲያናትም ሆነ ገዳማትን እንዳትነኩ ከዛ በኋላማ ..ብትፈልጉ ለሼሁ ..ካልሆነም ለቻይና ስጡትና ገላግሉን ...ምናልባትም ከአምስት አመቱ የጥፋት እቅዳችሁ መካከል የመጀመሪያዎቹ ሳይሆኑ ይቀራሉ _________________ Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Tue Mar 27, 2012 4:34 pm Post subject:
ሰላም አንቃፌ
እኔም የገረመኝኮ መሬት ያልታረሰ እና ሰው ያልተጠቀመበት ሰፊ መሬት አለ ሲባል ኖሮ ዛሬ ከመሬት ተነስቶ የእምነቱ ተከታዮች አለን የምንለውን ገዳም ለማረስ መሞከር :: ነገሩ ዝምብሎ በማናለብኝነት ብቻ የተሰራ የትዕቢት ስራ ሳይሆን ---በጥናት እና በሪኮሜንዴሽን የተደገፈ ስራ ነው :: ዛሬም ግን ተቃዋሚው አልባነነም በሬ ካራጁ ነው ነገሩ ...ህወሀትን እንደፈለጉ የሚጠቀሙበት የውጪ ሀይሎችም ናቸው ...ምክንያትም አላቸው ህወሀት የባንዳነት ተግባሩን እየተወጣ ነው ያለው
""ያልጠፋነው ከእግዚያብሄር ምህረት የተነሳ ነው "" የሚል የምወደው መዝሙር አለ ...እንደ አማኝ ስመሰጥ እንደኛ በሆዳምነት የቆረበ የግፍ ተባባሪ የሆነ ትውልድ እውነትም የሚማረው ከእግዚያብሄር ምህረት የተነሳ ነው ...እግዚያብሄር ለምህረት ምክንያት ይፈልጋል እንደሚባለው እንደዋልድባ ባለ ገዳም ውስጥ ሆነው ---የተማረው ያልተማረው እየተስገበገበ ህሊናውን የሚሸጥበትን ዓለም ንቀው ጸሎት በሚያደርጉ ለጽድቅ በቆሙ ክርስቲያኖች ምክያንያት እየተማርን እንዳለን መዘንጋት አያስፈልግም :: ከዚያም በላይ ደሞ ገዳማት የማንነታችንም መገለጫዎች ናቸው :: የሀገር ሀብት ናቸው :: ጠመንጃ እና ጉልበት አለኝ ብሎ በኢትዮጵያ ጠላቶች አድርግ የተባለውን ነገር ሁሉ የሚያደርግ ጎጠኛ ቡድን ነው ያለን ...እዚህ ደረጃ ላይ የተደረሰው ግን እንደ ታጋይ ጳውሎስ አይነት ጎጠኛ ሰው እና ያደረጋቸውን የማፈራረስ ስራ ታግሰን ዝም በማለታችን የተቃውሟችን ርባናቢስነት እና ምንም የማንፈጥር ወሬኞች እንደሆንን ግምት ወስደው ነው ! ገዳም ተቃጠለ ዝም ...ለታጋይ ጳውሎስ ሀውልት ተሰራ ዝም ...
በመሳደቡ በኩል የባህሪ ጉዳይ ነው ... ትላንትና በዲሲ የነበረውን ሰልፍ ለቪኦኤ ሊዘግብ በቦታው ተገኝቶ የነበረው አዲሱ አበበ ኤምባሲ በሚሰራ ዲፕሎማት ተሰድቧል ... ንቀታቸው እዚህ ደረጃ ደርሷል ...
አሁንም ሰሞኑን ትንሽ ከተጮኽ በኍላ ነገሩ ይለመድ እና በቸልታ ይተዋል ...ወያኔ ግን በየፈርጁ የኢትዮጵያን ግብዐተ መሬት እያፋጠነ ነው ...
አንፌቃ እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ናፖሊዮን ..በዚህ አርእስት ብዙ ማለት ይቻላል ...ግን ምንም ዋጋ የለውም የሳይበር ቋሚ ወያኔዎች .. ይህንን አሳፋሪ ድርጊት ለመቃወም ... የመከራከሪያ ምርጉዛቸው ተሰብራ ...ሳንባቸው ተንፍሳ ነው የታየው .. አይደለም የዝቋላውን ቀርቶ ...የዋልድባውን እንኳን መቃወም አልቻሉም ... ነገሩ የፖለቲካው መጣመም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን ...የእንጀራ ጉዳይ ሆኖ ነው ..
ትላንት ባለ ብዙ "ትርፍ ለም መሬት " ባለቤት ነን .. እናም ከኛ ተርፎ ለህንድ ..ለቻይና እና ለአረብ ለ 99 አመት ሊዝ በመስጠት 2015 መካከለኛ የኢኮኖሚ እድገት ካላቸው አገሮች እንደመደባለን እያለ የሚቃዠው ወያኔ ... ካልጠፋ ቦታ በልማት ስም "ገዳማትን " እያሳደደ ይገኛል ምክንያቱ ግልፅ ባይሆንም ...ልክ እንደ አህመድ ግራኝ ... እሳት በመልቀቅ እና አንዳንዴም በግዳጅ የአካባቢያቸውን ደን እየመነጠረ ...መነኮሳትን ዛፍ ያጣ ጉሬዛ አስመስሏቸዋል .. ተተኪ የሌላቸው በብራና የተፃፍ ታሪኮች ብዙዎቹ ወደ አክሱም በመጉረፍ ላይ ናቸው ...ሌሎቹም እየተቃጠሉ ይገኛሉ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈፅሞበታል (ደኖቹ ተመንጠረዋል )...የዋልድባው ገዳም ትንሽ ከወያኔ መልስ መሳይ ያገኘውም ...የትናንትናዋ የጎንደሯ -ወልቃይት ..በዛሬዋ በትግራይ ክልል ስለተካለለች ብቻ ነው እንግዲህ ሀይማኖትንና ታሪክን ማጥፋት ከጀመራችሁ አይቀር ... በነካ እጃችሁ .. ከጎንደር - የጎንደርን ግንብ ..ከወሎ - የላሊበላን ...ከሀረር -የጀጎልን ...ከጅማ - የፈርንጅ አራዳን ..እንዲሁም ካዲሳባ -መርካቶን ወዘተ ...በሳት አጋዩና ገላግሉን ...ከስከሩ አይቀር ብሽቅጥ ይባል የለ . ግን አደራ በአክሱም እና በአድዋ ያሉትን ቤተ ክርስቲያናትም ሆነ ገዳማትን እንዳትነኩ ከዛ በኋላማ ..ብትፈልጉ ለሼሁ ..ካልሆነም ለቻይና ስጡትና ገላግሉን ...ምናልባትም ከአምስት አመቱ የጥፋት እቅዳችሁ መካከል የመጀመሪያዎቹ ሳይሆኑ ይቀራሉ
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator