WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ወያኔዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሣያጠፉ
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Mar 16, 2012 10:17 pm    Post subject: ወያኔዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ሣያጠፉ Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በኢትዮጵያ ማርክሲዝም -ሌኒኒዝም -ስታሊኒዝም -ኤንቨር ሆዣይዝም -ማዖይዝም እና መሠል የዕምነት -የለሽ ርዕዮተ -ዓለም የሚያራምዱ ፖለቲከኞች የፖለቲካውን ምኅዳር ከተቆጣጠሩበት 1967 .. ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ላለፉት 38 ዓመታት የተጫኑባት አፅራረ -ቤተክርስቲያን የሆኑ ገዢዎች አገሪቱን ለጥፋት : አማኞችንም ለመሠናክልና ሥቃይ ዳርገው ኖረዋል : አሁንም ያለው አገዛዝ በዚያው ቀጥሏል :: እንዲያውም ባለው ሁኔታ ያለውን በጎሣ ፖለቲካ ላይ የተመረኮዘ አገዛዝ ሊተኩ የተዘጋጁትም ካለው የባሠ እንጂ የተሻለ ነገር ይዘውልን አይመጡም ::

ከላይ ለመግቢያ የገለጽሁትን ኃሣብ ያቀረብሁት ያለምክንያት አይደለም :: የወያኔ እና ኢሕአፓ አባሎች በደርግ ዘመን ከደርግ ክትትልና ግድያ አምልጠው ተጠልለው ይኖሩ የነበሩበትንና ታሪካዊውን የዋልድባ ገዳም ወያኔዎች ሥልጣን ላይ ሲወጡ ድራሻባቱን ለማጥፋት የመጨረሻውን ዕርምጃ በመውሠድ ላይ ናቸው :: እስኪ የሚከተለውን ዘገባ አንብቡትና ምን ዓይነት የአፀፋ ዕርምጃ መውሠድ እንደሚገባን እንወያይበት ::

አንድ አድርገን መጋቢት 7 2004..:: ‹‹ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተን የተቀመጥን ሰዎች ነን›› የዋልድባ መነኮሳት ::

Quote:
ከቀናት በፊት በመንግስትና በዋልድባ ገዳም መካከል ስላለው ውዝግብ መረጃ አቅርበን ነበር አሁን እንደሰማነው ቅዳሜ 01/07/2004. እና ማክሰኞ 04/07/2004. በሽሬ ከመንግስት የተወጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት የገዳሙን አባቶች ለማነጋገር ፕሮግራም ይዘው ነበር ነገር ግን ከአባቶች በኩል በእዚያ ያሉ ሰዎች ለእኛ ጥሩ አመለካከት የላቸውም ስለዚህ በአማካይ ቦታ በአድርቃይ ስብሰባውን እናድርግ ያሉ ሲሆን በዚህ ተስማምተው ስብሰባውን አድርቃይ አድርገዋል፡፡

· ከቤተክህነት የተወከሉት አባት እንዴት ይህን ጉዳይ እኛ ሳናቀው የግል መገናኛ ብዙሀን ጋር ይዛችሁ ትሄዳላችሁ ይህ አግባብ ነው ወይ ? የሚል ጥያቄ የተጠየቁ ሲሆን የዋድባው አንድ አባት ‹‹መንግስት ለመገናኛ ብዙሀን የመፃፍም ሆነ የመናገር መብት እስከሰጣቸው ድረስ እኛ ጉዳዩን የፈለግነው ጋር ይዘን እንሄዳለን መብታችን ነው›› የሚል መልስ ሰጥተዋል መገናኛ ብዙሀን የህዝብን ድምጽ ተቀብሎ ለህዝብ እንዲያደርስ ፍቃድ ተሰጠው ህጋዊ ተቋም ነው እኛ ምንም ያጠፋነው ነገር የለም ቤታችን ሲፈርስ መሬታችን ሲታረስ እያየን ቤተክርነቱን መጠበቅ አይጠበቅብንም ተብለዋል ‹‹ነጻ ሚዲያ እስካለ ድረስ ጉዳዩን ነጻ ሚዲያ ላይ ማውጣት ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው›› ብለዋል፡

በተጨማሪ ከቤተክህነት የተወከሉ ሰው የዋልድባው አባት በሰጡት ሀሳብ ላይ ይህ የቤተክርስትያ አስተምህሮ አይደለም ጉዳዩን አንድ ላይ ሆነን ነበር መንግስት ዘንድ ማቅረብ የነበረብን ሲሉ ‹‹ እናንተማ ቤተክርስትያኗን ለመንግስት አሳልፋችሁ ለመስጠት ከመንግስት ጎን ተሰልፋችሁ መጣችሁ ይህን ጉዳይ ከናንተ ጋር ሆነን መንግስት ዘንድ ይዘን መቅረብ አንችልም እናንተ ሲጀምር ለቤተክርስትያን ህልውና የቆማችሁ አይደላችሁም›› ተብለዋል፤ ከተሰብሳቢ አባቶች በኩል ተገቢ አፍ የሚያስይዝ መልስ ተሰቷቸዋል

አይ ቤተክህነት ከአባቶች ጎን ቆሞ መንግስት ጋር ተገቢውን ጥያቄ ይዞ በመቅረብ ለዚህ የጭንቅ ጊዜ አጋር እደመሆን የራሷን አቋም ይዛ ከአባቶች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግባት ምን ይሉታል ? ገዳም ያሉ አባቶች ለነፍሳቸው ያደሩ መሆናቸው ዘነጋችኋቸው እንበል ? ቤተክህነት የራሱን ውሳጣዊ ችግር ሳይፈታ ይህን የሚያህል ቤተክርስትያን ላይ ያጋረጠን ክፉ ጊዜ ማለፊያ መንገድ ይጠቁማል ማለት ዘበት ነው ለነፍሳቸው ያደሩ አባቶች ከአምላካቸው ጋር ይፈቱታል ለእናንተ ለስጋውያን ግን ትንሽ ከበድ ይላል፡፡
ይህ ጉዳይ ለቢዮንሴ ወረብ ማስወረብን ያህል የቀለለ አይደለም ቆም ብላችሁ ተመልከቱ ነገንም አስተውሉ ከቤተክርስትያን ዘንድ ብቻም ወግኑ እናንተ ሀላፊነታችሁን መወጣት ቢያቅታችሁ ለባለቤቱ ተውለት የግብጽ መንግስት የኮፕቶችን ገዳም ለማደስ 14 ሚሊዮን ዶላር ከውጭ መንግስተት ጋር ተነጋግሮ እርዳታ እንዲያገኙ ሲያደርግ የእኛው ደግሞ ገዳማችንን ህልውናችንን አፍርሶ ስኳር ፋብሪካ ሊያቋቁም ተነሳ ይገርማ !!

· በስብሰባው ላይ የመንግስት ተወካዮች የስኳር ፋብሪካ ግንባታው ስራ አስኪያጅ እና የሚመለከታቸው አካሎች ከመንግስ በኩል የተገኙ ሲሆን ከአባቶች ወገን ደግሞ ሶስት አባቶች ተወክለው ስብሰባውን አድርገዋል፡፡ ስብሰባው ሲደረግ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ‹‹ በከተሞች አካባቢ የሥኳር ችግር አለ ማህበረሰቡ ስኳር እጅጉን እየተቸገረ ነው፤ ኪሎ ስኳር 18-20 ብር ገብቷል ይህ ግንባታ ቢከናወን ለሀገርም ለህዝብም ጥሩ ነው የሚል የተሞላውን ዲኩር አሰምቷል ›› ቀጥሎም ምንድነው ችግሩ በማለት ችግሩን ያልታየው ይመስል በጣም በመቆጣት ጥያቄ አቅርቧል ቁጣ እንኳን አንዳንዴ ከዘር ሊተላለፍ ይችላል አንዳንዴም ደግሞ ግቡን እንዲመታ የሚፈልጉትን ጉዳይ ጽንፍ ይዞ ሲሟገቱ ሳያቁት ሊቆጡ ይችላሉ በአንድ ጥናት ላይ ስልጣን ያላቻው ሰዎች ለመናደድ ቅርብ ናቸው ይላል ከአባቶች ዘንድ የተሰጠው ምላሽ ‹‹እኛን ገድላችሁ ፋብሪካውን መስራ ትችላላችሁ ራሳችንን ለሰይፍ ነው ያዘጋጀነው እኛ የዋልድባ አፈር ጠባቂ ነን እንጂ ጠባቂው መድሀኒአለም ነው ዋልድባን ብታከብሩት ትከበራላችሁ ዋልድባን ብታቀሉት ትቀላላችሁ ብለው በግልጽ ነግሯቿል›› ፡፡ እንዴት ደስ ይላል ቤተክርስትያ በአሁኑ ሰዓት እየተቸገረች ያለችው አቋም የሌለው ሰው በማጣቷ ነው ከመንግስት ፖሊሲ እና ከእድገትና ትራንስፎርምሽን እቅድ ጋር አብረው ራሳቸውን የሚቀያይሩ ሰዎች ተከባለች ቤተክርስያን አቋሟ ከመንግስ ጋር አብሮ የሚቀየር አይደለም የባለስልጣንን ሀሳብ ላይ ተመርኩዞ የሚንቀሳቀስም አይደለም ስለምናከብረው እና ስለ ምንፈራው ሰው ብለን የምንለዋውጠውም መሆን የለበትም እንደ ዋልድባ ገዳም አባቶች ብንኖርም ብንሞትም በእምነታችን ላይ አቋም ያስፈልገናል ፡፡ የእነሱ አቋም ‹‹አይሆንም ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተናል እኛን ሰውታችሁ አላማችሁን ማሳካት ትችላላችሁ›› የሚል ነው አራት ነጥብ፡፡

· ስብሰባውን በተጨማሪ ለአንድ ቀን ሙሉ መነኮሳት አቡነ መርቃርዮስ ባሉበት ተካሂዷል በጊዜው የታረሱትን ቦታዎች ተመልክተዋል አቡነ መርቃርዮስ ስብሰባውን በጸሎት አስጀምረዋል በውይይቱ መሀል ላይ ውይይቱ እየጋለ መጥቶ እንደነበር ለማወቅ ችለናል በሁለቱም በኩል ከረር ያሉ ቃላትን የመመላለስ ነገር ይታይበት ነበር ተብለናል አባቶች ነገሩ አላምር ሲላቸው ‹‹እናንተ የፈለጋችሁትን ማድረግ ትችላላችሁ እኛ ይግባኝ ለክርስቶስ ሰጥተናል ለምን ትጨቀጭቁናላችሁ ስራውን እየሰራችሁት አይደል ..››ብሎ ‹አሁንም እንሰየፋለን እንሰየፋለን ብሎ የመነኮሳት ማህበሩ ከስብሰባው ተነሳ በጊዜው የነበሩ የመንግስት ባለስልጣናት በአባቶች ሁኔታ በጣም መደንገጣቸውንም ለማወቅ ችለናል 18 ቤተክርስያ ፈርሰው ሸንኮራ ልማት የማይታሰብ ነው ብለው አቋማቸውን ገልጸውላቸዋል፡

· በትግረኛ ፕሮግራም የገዢው ፓርቲ ሰዎች ቦታው ድረስ በመሄድ የማይመለከታቸውን ሰዎችን በማነጋገር የውሸት ፕሮፖጋንዳ ለህዝቡ አናፍሰውለታል የገዳሙ አባቶች ልማቱ ላይ እንደማይቃወሙ በማስመሰል የምን ጊዜም ተግባሩ በቴሌቪዠን ያንጸባረቀ ሲሆን ይህን ጉዳይም አንስተው ጉባኤው ላይ ተነጋግረዋል የተሰራውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተመልክተናል የተሰራው ስራ እኛን አይወክልም የኛም ድምጽ አይደለም ብለዋቸዋል ፡፡ ይህ የህዝብን ድምፅ ለማፈን የሚደረግ ሴራ አጥብቀን እንቃወማለን ህዝቡ እያለ ያለው ልማታችን አይቋረጥ ገዳማችንንም አትንኩብን እንጂ ለልማት ከሆነ ገዳሙ ይፍረስ የሚል አቋም ያለው ማህበረሰብ የለም ይህን ነገር በህዝቡ ውስጥ አልሰማንም አላየንምም ብለዋል

· የልማት ስፍራው ላይ 3 መትረየስ ተጠምዶ በከፍተኛ ሁኔታ ፌደራል ፖሊስ እየጠበቀው ይገኛል በሁኔታው መወሰን ያልቻሉት ባለስልጣናት ጉባኤውን ለቅዳሜ አቦይ ስብሀት ባሉበት ሽሬ ላይ ይደረጋል ብለዋል አንድ አባት በሰጡት አስተያየት አይደለም አቦይ ስብሀት ጠቅላይ ሚኒትሩም ቢያደራድሩን ከአቋማችን ፍንክች የምንል መነኮሳት አይደለምን ራሳችንን ለሰይፍ ያዘጋጀን ሰዎች ነን ያለነው እኛን ገለው ፋብሪካውን መስራት ይችላሉ ብለዋል ፡፡ እኝው አባት አያይዘው ይህችን ቤተክርስትያ እየሸጧት ያሉት አቡነ ጳውሎና መንግስት ናቸው ማንም አይደለም ብለዋል በጉባኤው ሂደት ቅዳሜም ምንም አይነት ለውጥ ይመጣል ተብሎ አይጠበቅም ቅዳሜም ለውጥ ስለሌለ አንሰበሰብም የሚል አቋም እንዳለ ለማወቅ ችለናል

እኛ መሳሪያ የለንም ከናንተ ጋር ግንባር የምንገጥም ሰዎችም አይደለንም እናንተ በጉልበታችሁ ሁሉን ማከናወን ትችላላችሁ እኛም ለመሰዋት ዝግጁ ነን ይህን ስለቤተክርስትያን የምንቀበለው ሰማእትነት ነው ዋልድባ 4 ወንዞች የተከበበች ናት አይኗን፤ እግሯን ጥፍሯ ከአካላቷ አንዲቷም እንድትነካብን አንፈልግም የበፊት የዛሬ የወደፊት አቋማችን ይህው ነው ብለዋቸዋል

· እኛ በዚህ ያለነው ማህበረ መነኮሳት አቅም የለንም ማድረግ የምንችለው ለሰይፍ ተዘጋጅተን መቀመጥ ብቻ ነው ብለዋል አቅም ያላቸው በውጭ የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስን አማኞች በያሉበት በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ጥያቄያችን ያቅርቡልን ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ሀሳባችንን ተጋርተው ከአጠገባችን እዲቆሙ መልእክቴን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡

አባቶቻችን ይህችን እምነት ይዘው ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖላቸው አያውቅም ለክርስትያን ፈተና የህይወቱ አንዱ ክፍል ነው ፈተናን መወጣት የሚቻለው በጉልበት በገንዘብ ባስልጣን አይደለም እንደ ቤተክርስትያናችን አስተምህሮ ፈተናን ለመቋቋም ጾም ጸሎት ስግደት እና የትሩፋት ስራዎችን ከፅናት ጋር መስራት ግድ ይላል በአሁኑ ሰዓት የኛ ፈተናችን ይህ ነው ፈተናችንን በድል እንድንወጣ ሁላችን በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ሆነን ከገዳማውያን አባቶቻችን ጎን መቆም መቻል አለብን እነሱ የመጣውን ሊቀበሉ ወስነው ተቀምጠዋል ቤተመንግስት ድረስ ሄደው ያተረፉት ስድብ ብቻ ነው ስለዚህ በጾምና በጸሎት ከገዳማቸው ሆነው አምላክን ቢለምኑት ጸሎታቸውን እንደሚሰማ ካልሆነም በህይወት እያለን ይህን ማየት ስለማንፈልግ እኛን ገላችሁ መስራት ትችላላችሁ የሚል አቋም ወስደዋል ቤተክህነቱም ከመንግስት ጎን በመቆም ሊያስማማ ወደ ቦታው ተወካዩን ልኳል ይህም አለመታደል ነው እኛስ ምን ማድረግ አለብን ? ለሁላችን የምጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡ እስኪ በጸሎት እናስባቸው ይህንም የፈተና ጊዜ ቤተክርስትያን ታልፈዋለች አንጠራጠርም

‹‹መካሪ የሌለው ንጉስ ያለ አንድ ዓመት አይነግስ›› ይባላል እኛ አሁንም የአባቶቻችን ርዕስት ሲፈርስ የምናበት አይን የምንሰማበት ጆሮ የለንም ዋልድባ ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ እንድናስረዳችሁ ከፈለጋችሁ መልካም ያለበለዚያ በሞላ ቦታ አይናችሁን ከዋድባ ላይ ብታነሱ መልካም ነው ከእኛ ጋር ሳይሆን የምትጋፈጡት ከባለቤቱ ጋር መሆኑንም አትርሱት ባለቤቱ ደግሞ የሰማይና የምድር ፈጣሪ መድሀኒዓለም ነው የራሄልን እንባ የተመለከተ አምላክ የእነሱንም ይመለከታል ዓይንን የፈጠረ አምላክ ያያል ፤ጆሮን የፈጠረ ጌታም ዘንበል ብሎ እሪታችችን ኡኡታችን ይሰማል አንጠራጠርም በእናንተ ጩህት የሚመጣ ነገር የሰው ጆሮ ማደንቆር እንጂ ሌላ ነገር አይደለም የቅዱሳንን አጽም እንደ አልባሌ ነገር አትቁጠሩብን ለእናንተ ምንም ሊሆን ይችላል ለእኛ ግን ትርጉም ያለው ነገር ነው ለነገሩ መጠበቅ የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ ምን ዋጋ አለው የራስን ዝቅ አድርጎ የማየት ክፉ አመል ተጠናውቶናል እናም እኛ አንፈርድም፡፡ ገዳሙን ግን ለቀቅ አድርጉን ይህን ፅፌ ከጨረስኩኝ በኋላ ገዳሙ እየተጋፈጠ ያለውን ፈተና አስቤ እንባዬ መጣ ...... አይኔንም ሞላው……………
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Thu Dec 27, 2012 11:22 pm; edited 8 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የንጋት ጮራ

ኮትኳች

Joined: 01 Jan 2006
Posts: 254

PostPosted: Mon Mar 19, 2012 6:02 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ ሀይሉ

ይህ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው :: አሁን ካልጠፋ ቦታ ገዳም ሊያጠፉ መምጣታቸው አይገርምም ?? ስኳር ፋብሪካ ሌላ የትም ቦታ ሊስሩ ይችላሉ :: ምን ዋልድባ አስኬዳቸው ? ይህ calculated የሆነ በተዋህዶ ላይ ያነጣጠረ መሠሪ ፕላን ነው :: "ልማት ለማልማት " የሚል ሽፋን አጘኙለት :: መነኮሳቱ እንዴት ልብ የሚያርስ መልስ አላቸው ! ለነገሩ ስለ ዋልድባ ትንቢት እንዳለ ታውቃለህ ? ዋልድባን እናርሳለን የሚሉ ሰዎች የሚመጡበት ዘመን እንዳለና በዛ ጊዜ ብዙ ችግር እንደሚኖር ትንቢት አለ :: በውጭ አገር የምንኖር በአለን አቅም ሁሉ በጩከትም ቢሆን ይህን ጉዳይ ልንከላከል ይገባል ::

ኢትዮጵያዊት ጮሪት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 1:20 am    Post subject: Reply with quote

የንጋት ጮራ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ተድላ ሀይሉ

ይህ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው :: አሁን ካልጠፋ ቦታ ገዳም ሊያጠፉ መምጣታቸው አይገርምም ?? ስኳር ፋብሪካ ሌላ የትም ቦታ ሊስሩ ይችላሉ :: ምን ዋልድባ አስኬዳቸው ? ይህ calculated የሆነ በተዋህዶ ላይ ያነጣጠረ መሠሪ ፕላን ነው :: "ልማት ለማልማት " የሚል ሽፋን አጘኙለት :: መነኮሳቱ እንዴት ልብ የሚያርስ መልስ አላቸው ! ለነገሩ ስለ ዋልድባ ትንቢት እንዳለ ታውቃለህ ? ዋልድባን እናርሳለን የሚሉ ሰዎች የሚመጡበት ዘመን እንዳለና በዛ ጊዜ ብዙ ችግር እንደሚኖር ትንቢት አለ :: በውጭ አገር የምንኖር በአለን አቅም ሁሉ በጩከትም ቢሆን ይህን ጉዳይ ልንከላከል ይገባል ::

ኢትዮጵያዊት ጮሪት

እኒህ ወያኔ የሚባሉቱ የሥልጣን መንበር ላይ በክላሽንኮቭ ጠመንጃ አጋዥነት ሥልጣን ላይ የወጡ የቆዳቸውን ቀለም የሚቀያይሩ አጽራረ -ቤተክርስቲያን የሆኑ ኮሚኒስቶች ናቸው :: እኒህን በጭካኔ የሚስተካከሏቸው በካምቦዲያ ከአገራቸው ሕዝብ ሁለት ሚሊዮን ያህል የጨረሱት ካህመር ሩዥ የሚባሉት የእነርሱ ቢጤ ኮሚኒስቶች ናቸው :: እነርሱ በጉልበት የጎለቱት 'ታጋይ ፓትርያርክ ' ለዚህ ሁሉ ጥፋት ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው :: ስለዚህ ከጸሎት በላይ በተግባር የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የዘረጋውን የአፈና መረብ መበጣጠስ ያስፈልጋል :: በይሉኝታ ተይዞ በዝምታ ማለቅ አያዛልቅም ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 5:46 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

አቤል ዋቤላ የተባሉ ወገናችን የሚከተለውን አስተያዬት በመወያያ መድረካቸው ላይ አሥፍረዋል :: ጠንከር ያሉ ኃሣቦችን ያዘለ ሥለሆነ እንድታነቡት እዚህ አምጥቼ ለጥፌዋለሁ ::

ምንጭ :- አቤል ዋቤላ :: የዋልድባ ነገር ምንፍቅና (ከፍሎ ማመን ) ::

Quote:
ዋልድባ ታላቅ ገዳም ነው፤ ዝርዘር አያስፈልገውም፤ ስሙ ብቻ ገናናነቱን ይናገራል፡፡አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊው ልማታዊው መንግስት የስኳር ፋብሪካ እና ፓርክ ሊሰራ ነው ይህም ዝርዝር አያሰፈልገውም እምነቱ ይህን ያደርግ ዘንድ ግድ ይለዋልና፡፡ ይህን ተከትሎ ብዙ አይነት ድምጾች ሰምተናል እነርሱንም መድገም አያሰፈልግም እድሜ ለዚህ ዘመን ከልብ ከፈለጉት ያገኙታልና፡፡ ህመሜ ለአደባባይ የሚበቃ ስላልነበር ዝምታን መርጬ ነበር፡፡ ጉዳዩ የእምነት ስለሆነ እምነት ደግሞ ምስክርነትንም ስለሚጨምር ባይሆን ተናገሬ ውግዘትም በረከትም፣ ጥፊም ከተገኘ ልቀበል በሚል ይህን ጣፍኩኝ፡፡

የሁለት ርዕዮታት ፍጭት
አንዱ ርዕዮተ ዓለም (ሀይማኖት ) እንዲህ ያላል፡፡ ሰው ስነ ሕይወታዊ አሐድ (biological element)ነው፡፡ ከብዙ እንስሶችው ውስጥ አንዱ ነው ፡፡ ነገር ግን በአለማችን በአጋጣሚ ልዕለ ሀያል ሆኗል፡፡ እንዲሁ በአጋጣሚ በዘፈቀደ ሲኖር ሲኖር በዛ ተባዛ፡፡ምድርንም ሞላት፡፡ያው በሕገ አራዊት ጡንቻውን ያፈረጠመ ምግቡን አብዝቶ እንደሚሰበስብ የታወቀ ነው፡፡በዚህም ምክንያት የተዛባ የሀብት ክፍፍል በምድሪቱ ላይ ነገሠ፡፡በዚህ ጊዜ የእርሱ ጉዳት፣ ሕማም እና መከራ ያሳስባቸው ጥቂት ልሂቃን (ካህናት ) በእርሱ ተገብተው ይጨነቁለት ገቡ፡፡የሚበላው ተጨማሪ ነገር ለእግሩ ጫማ ለሆዱ ምግብ አንዳንዴም ስኳር ለደዌው መርፌና ክኒና አቀረቡለት፤ ይሄድበት ዘንድ አውራ ጎዳና የወፎቹም መንገድ እንዳይቀርበት ጠያራ አበጁለት ፡፡

እነሆ ከእነዚህ ሕዝቦች ጥቂቶቹ በኢትዮጵያ ይኖራሉ፡፡ የዚህ መንጋ ሊቀ ካህኑ መለስ ዜናዊ ይባላሉ፡፡ (ያው በጉልቤ ነው ራሳቸውን የቀቡት ) ባንድ ወቅት እንደሰማነው እኚህ ካህን ከልጅነት እስከ አሁኗ ደቂቃ እረፍትን እና እፍረትን አያውቁም (ከዚያ ዲስኩርም በኃላ ባተሌነታቸውና ባለጌነታቸው ቀጥሏል፡፡ ) እናም በኢትዮጵያ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ የምግብ እና የስኳር ችግር እንዳለባቸው ረጅም የችግር እና ችጋር ታሪካቸው ያሳያል ( 1977 .. ወደ ሀገራችን የመጡ የኩባ ወታደሮች ቢጫ ስኳር ይዘው እንደመጡ ባናይም ምዕመን ነንና አምነናል፡፡ ) የስኳርን አስፈላጊነት ለማስረዳት ከካህናት ወገን የነበሩት ታምራት ላይኔም ወደ ወህኒ የወረዱት ስኳር ሲልሱ ተገኝተው መሆኑን መጥቀስ ይበቃል፡፡ይህ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የስኳር ፍላጎት እንዳለ ያሳያል፡፡ እናም ልማታዊው መንግስት ይህንን ችግር ለመፍታት የደረቀ ሙዝ እየበሉ ከሚኖሩ (ያውም ያልተራጁ እና በሊግ ያልታቀፉ ) ሰዎች መሬት ቆርሶ ሸንኮራ አገዳ ሊተክልበት ዝግጅት መዠመሩ በድፍን የኩሽ ምድር ዜና ሆነ፡፡

ሁለተኛው ሀይማኖት (ርዕዮተ ዓለም ) እንዲህ ይላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በአርአያውን እና በአምሳሉ ፈጠረው፡፡ከግራ ጎኑ አጥንት አጋር ፈጥሮ እንዲህ አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። አነርሱም አልሰነፉም በዙ ተባዙ ምድርን ሞሏት፡፡በጥንት አባቶቻቸው ዘመን ሰይጣን ከፈጣሪያቸው አጣልቷቸው ነበርና እርቅ አስፈለገ፡፡ የሚገርመው አምላካቸው ራሱ ሰው ሆኖ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ ብዙ ህማም እና መከራን ተቀብሎ ሞቶ፤ ተሰቅሎ፤ ከራሱ ጋር አስታረቃቸው፡፡ይመሩበት ዘንድ ህግ ይኖሩበት እርስ በርስ ምክር እና ተግሳጽ ይቀባበሉት ዘንድ ማኅበር አቋቋመላቸው፡፡ከእርሱ ጋር ትክክል (አቻ ) የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንዲያገኙ ስጋውን እንዲበሉ እና ደሙን እንዲጠጡም ስርዓተ አምልኮ አስተማራቸው፡፡

ከህጎቹ ውስጥ እንዲህ የሚሉ ቃላት ነበሩበት፡፡ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን ? ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን ? ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።

እነዚህ ፈጣሪያቸው በማኀበር ያደራጃቸው ሰዎች በአለም ተበተኑ፡፡ከእነርሱ እና ከመጽሐፋቸው የተማሩ ሰዎች በኢትዮጵያም ይኖሩ ነበር፡፡ ከፈርኦን ልጆች ከእንጦኔ እና መቃሬ ኮርጀው በየዋሻው በየፍርኩታው በመላዋ ኢትዮጵያ በምናኔ እና ብትሕውና ይቅበዘበዙ ነበር፡፡ከብዙ ጊዜ በኃላ ነፍጥ ያነገቡ የሩቅ ምስራቅ ሰዎች መጥተው ዐጽመ ቅዱሳን ያረፈበትን መናንያን በኪደተ እግራቸው የባረኩትን መሬት ለስኳር እንደሚፈልጉት ነገሯቸው፡፡ “እኛ ምግባችን ቋርፍ ነው፤ አገዳ ምን ያደርግልናል ? ሲሉ ጾም ባደከመው ድምጻቸው ተናገሩ እኛም አደመጥን፡፡አስቀድሞ የስኳርን ለሰው ልጆች አስፈላጊነት ስለተናገረን እጅግ ግራ ገባን፡፡ የትኛውን ቄስ እንመን ?

ምንፍቅና (ከፍሎ ማመን )
መናፍቅ የሚለውን ቃል የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝግበ ቃላት ናፋቂ አናፋቂ የሚጠራጠር የሚያጠራጥር ጠርጣሪ አጠራጣሪ ሃይማኖቱ ሕጹጽ የኾነ ምሉእና ፍጹም ትክክል ያይደለ መንፈቁን አምኖ መንፈቁን የሚክድ ሲል ይተረጉዋል፡፡በዚህ ትንታኔ መሰረት ጉዳዩን ለማዛባት መሞከር ወይንም ከኢአማንያን አብሮ ቤተ ክርስቲያንን ለማሰወጋት የተዛበ የሞራል መሰረት ለመጣል መሞከር መናፍቅ ያሰኛል፡፡የመነኮሳይቱ ችግር ይመለከተናል ብለን ነገር ግን ከቤተ ክርስቲያኒቷ አስተምህሮ ወጪ እምነቷ ይሄ ነው ከማለት በላይ ምን ምንፍቅና አለ፡፡ ምክንያቱም ከእምነታችን መሰረታዊ ነጥቦች ጋር የሚጋጩ ምግባራት ላይ ተካፍለናል ወይም በዝምታችን ይሁንታን አጎናጽፈናቸዋል፡፡እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው። እንዲል መጽሐፍ ፡፡ከዚህ ከፍሎ ማመን ላለመደመር በብልሃት ስም ብልጣብልጥነትን በማስተዋል ስም የይሁዳን ስሌትና የሲሞንን ቀመር ባንደረድር ይመረጣል፡፡

አንዱ መናፍቅ (ከሁለቱም ርዕዮት የሚያጣቅስ ) እንዲህ አለ “ይነሳሉ የተባሉትአብያተ ክርስቲያናት በቁጥር ሦስት ናቸው፡፡ እነሱም ከገዳሙ ይዞታ ውጪ ያሉ ምእመናን የሚገለገሉባቸው ናቸው፡፡ የመነሳታቸው ምክንያትም ከገዳሙ ክልል ውጪ የሚገኙ ነዋሪዎች ለልማት ሥራው ሲነሱ የሚገለገልባቸው ስለማይኖር ነው፡፡” ምእመናን ባሉበት የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መኖር የግድ ነው ነገር ግን ሁሉም አድባራት እና ገዳማት ምዕመናን ስለሌሉ ይነሱ ማለት የእምነት ጉድለት ምንፍቅና እንዳለ ያሳያል፡፡

ሌላው መናፍቅ ለጠቀ “አብዮታዊነት ሳይሆን ሳይሆን መንፈሳዊነት ያልተለየው መፍትሔ” በሚል ማደናገሪያ ሊያልፍ ይሞክራል፡፡ልክ እንዳንዶች የፓርቲ ፓለቲካ ምናምን እያሉ ጥራዝ ነጠቅ እውቀታቸውን ተጠቅመው ለሁለት ጌቶች ለመገዛት እንደሚሞክሩት ያለ ዘዴ መሆኑ ነው፡፡ እኛስ ባልጠራ ኃልዮታችን ስንቱን ጎበዝ አደከምነው ? አብዮት ፓለቲካ ብለን ድንበር እናበጅለታለን፡፡ከክርስቶስ በላይ ማን ፖለቲከኛ አለ ? ማንስ አብዮተኛ አለ ? መጽሐፍቱም እያሉ ሊቃውነቱም በሕይወት እያሉ እንዲህ ያለ ቅጥፈት አያዋጣም፡፡ ወንጌሉን መሰረት አድርጎ በዝርዝር ማሳየት ይቻላል ሰፊ ስለሆነ ብዙ ያሰኬደናል እንጂ፡፡በአርአያው እና በአምሳሉ የፈጠረን ፈጣሪ ከፈቀደ እንመለስበታለን፡፡ መንፈሳዊ ብሎ በመቀጸል የመናናውያን አስተሳሰብ የተጫነው ትምህርት ማስፋፋት ተገቢ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ክርስቲያኖች የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ዜጎች ናቸው ይህች ምድር ግን በኃላ በዚያ በሰው ህሊና ባልታሰበችው ለሚኖረው ተድላ እና ደስታ አረቦን ማረጋገጫ የተሰጠች ናት፡፡ የእግዚአብሔርን መንግስት እየሰበኩ ከሌላው የሰው ዘር ጋር ፍቅርን እያወጉ የሚኖሩባት ክፉን እና ክፋትን የሚቃወሙባት አክሊል እና ሰይፍ ሲገኝ ዋጋ የሚቀበሉባት ናት ፡፡ይህ መንፈሳዊ ስጋዊ እያሉ ምእመናንን ከቤተ ክርስቲያን እና ከሀገር ለመነጠል መሞከር የትም አያደርስም፡፡

ግጭቱ የሀይማኖት ጉዳይ ነው “ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ ወኮነ ከመ’ እንስሳ” ይላል የኛ እምነት፡፡ይህን ደግሞ እነርሱ አይቀበሉተም “መች ክቡር ሆኖ ያውቃል ከአራዊቱ መካከል አንዱ ነው ስለዚህ በጉልበታችን የሚያስፈልገው ዳቦ በስኳር እናቀርብለታለን ፤ለእርሱ ደግሞ ቀን ሌሌት እየደከምን ነው” ይሉናል ይህ ያጣላናል፤ ለዚህ ደግሞ በእምነታችን ልክ (ከፍለን ካላመንን ) ጥብዐትን ይጠይቃል፡፡ይህንን ስንል ከሌሎች ወንድሞቻችን (በሌሎች እምነት ተቋማት ካሉ አሊያም ሰውን በሰውነቱ አክበረው በአመክንዮ እንዲህ መሆን አለበት ከሚሉ ) ጋር የምንጋራው እንጂ ለብቻችን ጠቅልለን የአራዊቱን ስህተት የምንደግምበት አይደለም ፡፡የሰው ልጆች የምድሪቱን ፍሬ ተካፋለው በሰላም እንዴት መኖር እንዳለባቸው ከጥንት ጀምሮ በተደረጉ ተዋስኦዎች የወለዷቸው ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ክርስቲያን መሆናችን ደግሞ ይህ መተማመን የበለጠ እንዲጎለበትና መፈቃቀር እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

አለም በየዘመናቱ ከቄሳሮች እስከ ኮሚንስቶች ራሳቸው ከእንስሳት ሳይሻሉ የሰው ልጅን እንደ በረሮ የሚመለከቱ ሰዎችን አስተናግዳለች፡፡ክርስትናም ዘመኑ የሚፈልገውን አመክንዮ፣ ሰማዕትነት እያቀረበች ጨው ሲያሰፈልግ ጨው፣ በጨለማ ውስጥ ብርሃን ሆና እኛ ዘመን ደርሳለች ፡፡አለም አሁን የበለጠ መራለች፡፡በአለመተማመን እና በክፋት ጨለማ ውስጥ እየዳከረች ነው ፡፡እዉነት የክርስትናው እንጥፍጣፊ በደማችን አለ ብለን ካመንን ጊዜው አሁን ነው፡፡ ዘመኑ አብዝቶ ሰማዐትነት ጨውነት እና ብርሃንነትን እየጠየቀን ነው፡፡ ሰማዕትነት አያምልጥህ እያሉ የተሸቀዳሙበት አለምን በጽድቅ ስራቸው የሚያበሩ አንደጨው የሚያጣፍጡ ክርስቲያኖች የነበሩበት ሀገር ዜጎች መሆናችንን አንርሳ፡፡ፍርድ ሲጓደል ደሀ ሲበደል ዝም ካልን፤ የመበለቲቷን ጩኸት፣ የድሀ አደጎችን ለቅሶ እና ዋይታ በዝምታ ካለፍን ምኑን በስሙ ተጠራን ? አሁን ሁሉ ነገር ግልጽ ሆኗል ጥያቄው ምእመን መሆን አለመሆነ ነው (to be or not to be that is the question.)

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃዲው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 03 Apr 2008
Posts: 88
Location: 12

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 1:47 pm    Post subject: Reply with quote

ኦኬ

ዋልድባ ለልማት ውሎ እውነት ሕዝብ ቢጠግብ ምንም ባልከፋ ::
እኔ ለምሳሌ ሙስሊም ነኝ የመርካቶ መስጊድ ፈርሶ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ቢሰራና በምትኩ ከላይ ፎቅ ተሰርቶ መስጊድ ቢሆን የሕዝብ ብዛት ያመጣው ክስተት ስለሆነ እቀበለዋለሁ እምነቴ ላይ ጣልቃ እስካልተገባብኝ ድረስ :: በከተማም ውስጥ የሩጫ መለማመጃ መስክ የሚመስሉ ሰፋፊ የቤተክርስቲያን መሬቶች ተገማምሰው መኖሪያ ቤት ሱቆችና ትምህርት ቤቶች ተሰርቶባቸው እሩቅ ሳንሄድ የቄሶቹ ልጆች ቢኖሩበት ቢቸረችሩበትና ቢማሩበት እሪ አያሰኝም ዋናው ከአንጀቱ የሚሰራ መንግስት መገኘቱ ነው ::
_________________
qadi
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 8:48 pm    Post subject: Reply with quote

ቃዲው እንደጻፈ(ች)ው:
ኦኬ

ዋልድባ ለልማት ውሎ እውነት ሕዝብ ቢጠግብ ምንም ባልከፋ ::
እኔ ለምሳሌ ሙስሊም ነኝ የመርካቶ መስጊድ ፈርሶ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ቢሰራና በምትኩ ከላይ ፎቅ ተሰርቶ መስጊድ ቢሆን የሕዝብ ብዛት ያመጣው ክስተት ስለሆነ እቀበለዋለሁ እምነቴ ላይ ጣልቃ እስካልተገባብኝ ድረስ :: በከተማም ውስጥ የሩጫ መለማመጃ መስክ የሚመስሉ ሰፋፊ የቤተክርስቲያን መሬቶች ተገማምሰው መኖሪያ ቤት ሱቆችና ትምህርት ቤቶች ተሰርቶባቸው እሩቅ ሳንሄድ የቄሶቹ ልጆች ቢኖሩበት ቢቸረችሩበትና ቢማሩበት እሪ አያሰኝም ዋናው ከአንጀቱ የሚሰራ መንግስት መገኘቱ ነው ::

ቃዲው :-

በመጀመሪያ ሙስሊም መሆንህን እጠራጠራለሁ :: ለመሆኑ 'በመካና በመዲና ያሉት የእስልምና ዕምነት ቅዱስ ሥፍራዎች በሙሉ ፈርሠው የእርሻ ቦታ ይሁኑ ወይም የሰዎች መኖሪያ ቤቶች ይገንቡባቸው ' የሚል ውሣኔ የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት ቢያስተላልፍ ትቀበለዋለህ ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃዲው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 03 Apr 2008
Posts: 88
Location: 12

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 9:16 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ቃዲው እንደጻፈ(ች)ው:
ኦኬ

ዋልድባ ለልማት ውሎ እውነት ሕዝብ ቢጠግብ ምንም ባልከፋ ::
እኔ ለምሳሌ ሙስሊም ነኝ የመርካቶ መስጊድ ፈርሶ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ቢሰራና በምትኩ ከላይ ፎቅ ተሰርቶ መስጊድ ቢሆን የሕዝብ ብዛት ያመጣው ክስተት ስለሆነ እቀበለዋለሁ እምነቴ ላይ ጣልቃ እስካልተገባብኝ ድረስ :: በከተማም ውስጥ የሩጫ መለማመጃ መስክ የሚመስሉ ሰፋፊ የቤተክርስቲያን መሬቶች ተገማምሰው መኖሪያ ቤት ሱቆችና ትምህርት ቤቶች ተሰርቶባቸው እሩቅ ሳንሄድ የቄሶቹ ልጆች ቢኖሩበት ቢቸረችሩበትና ቢማሩበት እሪ አያሰኝም ዋናው ከአንጀቱ የሚሰራ መንግስት መገኘቱ ነው ::

ቃዲው :-

በመጀመሪያ ሙስሊም መሆንህን እጠራጠራለሁ :: ለመሆኑ 'በመካና በመዲና ያሉት የእስልምና ዕምነት ቅዱስ ሥፍራዎች በሙሉ ፈርሠው የእርሻ ቦታ ይሁኑ ወይም የሰዎች መኖሪያ ቤቶች ይገንቡባቸው ' የሚል ውሣኔ የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት ቢያስተላልፍ ትቀበለዋለህ ?

ተድላ

አቶ ተድላ ስለጨዋነትህ ሳላመሰግንህ አላልፍም
ወደ ርእሱ ሳመራ መካና መዲና ያሉት ቅዱስ ቦታዎች ቅዱስነታቸውን የሚዳፈር ምንም ሀሳብ እና ድርጊት አልቀበልም :: ግን ዋልድባ አይነካ የተባለው ቦታ በጣም ሰፊና ስድስት ሰአት ያስኬዳል ሲባል ስለሰማሁ ያመጣሁት ሀሳብ ነው እንደ መካና መዲና በመቶዎች ሜትሮች ክልል ውስጥ ያለ ገዳም ከሆነ ግን መነካት የለበትም ::
_________________
qadi
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Mar 20, 2012 11:52 pm    Post subject: Reply with quote

ስለገዳማቱ ሥፋትና ክልል አንተን አይመለከትህም :: ይልቁንስ ጓደኞችህን ፈልገህ በምትግባቡበት ቋንቋ ከእነርሱ ጋር ኃሣብህን ተለዋወጥ :: እዚህ የማትፈለግበት ሥፍራ ገብተህ አትበጥብጥ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1211
Location: united states

PostPosted: Wed Mar 21, 2012 8:43 am    Post subject: Reply with quote

ቃዲ
ሜዳ ወይንም ሌላ እንደትምህርት ቤት ያለ ቦታ ጠፍቶ ነው መስጊድ የሚፈርሰው ? ቢያንስ ኡመር ሰመተር አለ ከአንዋር በፊት አላሁ አክበር በል አንተ !

ቃዲው እንደጻፈ(ች)ው:
ኦኬ

ዋልድባ ለልማት ውሎ እውነት ሕዝብ ቢጠግብ ምንም ባልከፋ ::
እኔ ለምሳሌ ሙስሊም ነኝ የመርካቶ መስጊድ ፈርሶ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ቢሰራና በምትኩ ከላይ ፎቅ ተሰርቶ መስጊድ ቢሆን የሕዝብ ብዛት ያመጣው ክስተት ስለሆነ እቀበለዋለሁ እምነቴ ላይ ጣልቃ እስካልተገባብኝ ድረስ :: በከተማም ውስጥ የሩጫ መለማመጃ መስክ የሚመስሉ ሰፋፊ የቤተክርስቲያን መሬቶች ተገማምሰው መኖሪያ ቤት ሱቆችና ትምህርት ቤቶች ተሰርቶባቸው እሩቅ ሳንሄድ የቄሶቹ ልጆች ቢኖሩበት ቢቸረችሩበትና ቢማሩበት እሪ አያሰኝም ዋናው ከአንጀቱ የሚሰራ መንግስት መገኘቱ ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃዲው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 03 Apr 2008
Posts: 88
Location: 12

PostPosted: Wed Mar 21, 2012 3:12 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ቃዲው እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ቃዲው እንደጻፈ(ች)ው:
ኦኬ

ዋልድባ ለልማት ውሎ እውነት ሕዝብ ቢጠግብ ምንም ባልከፋ ::
እኔ ለምሳሌ ሙስሊም ነኝ የመርካቶ መስጊድ ፈርሶ ትልቅ የገበያ አዳራሽ ቢሰራና በምትኩ ከላይ ፎቅ ተሰርቶ መስጊድ ቢሆን የሕዝብ ብዛት ያመጣው ክስተት ስለሆነ እቀበለዋለሁ እምነቴ ላይ ጣልቃ እስካልተገባብኝ ድረስ :: በከተማም ውስጥ የሩጫ መለማመጃ መስክ የሚመስሉ ሰፋፊ የቤተክርስቲያን መሬቶች ተገማምሰው መኖሪያ ቤት ሱቆችና ትምህርት ቤቶች ተሰርቶባቸው እሩቅ ሳንሄድ የቄሶቹ ልጆች ቢኖሩበት ቢቸረችሩበትና ቢማሩበት እሪ አያሰኝም ዋናው ከአንጀቱ የሚሰራ መንግስት መገኘቱ ነው ::

ቃዲው :-

በመጀመሪያ ሙስሊም መሆንህን እጠራጠራለሁ :: ለመሆኑ 'በመካና በመዲና ያሉት የእስልምና ዕምነት ቅዱስ ሥፍራዎች በሙሉ ፈርሠው የእርሻ ቦታ ይሁኑ ወይም የሰዎች መኖሪያ ቤቶች ይገንቡባቸው ' የሚል ውሣኔ የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት ቢያስተላልፍ ትቀበለዋለህ ?

ተድላ

አቶ ተድላ ስለጨዋነትህ ሳላመሰግንህ አላልፍም
ወደ ርእሱ ሳመራ መካና መዲና ያሉት ቅዱስ ቦታዎች ቅዱስነታቸውን የሚዳፈር ምንም ሀሳብ እና ድርጊት አልቀበልም :: ግን ዋልድባ አይነካ የተባለው ቦታ በጣም ሰፊና ስድስት ሰአት ያስኬዳል ሲባል ስለሰማሁ ያመጣሁት ሀሳብ ነው እንደ መካና መዲና በመቶዎች ሜትሮች ክልል ውስጥ ያለ ገዳም ከሆነ ግን መነካት የለበትም ::

ስለገዳማቱ ሥፋትና ክልል አንተን አይመለከትህም :: ይልቁንስ ጓደኞችህን ፈልገህ በምትግባቡበት ቋንቋ ከእነርሱ ጋር ኃሣብህን ተለዋወጥ :: እዚህ የማትፈለግበት ሥፍራ ገብተህ አትበጥብጥ ::

ተድላ

የቤቱ ባለቤት ስለሆንክ እሺ ከይቅርታ ጋራ ወጥቻለሁ ::
_________________
qadi
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Thu Mar 22, 2012 7:17 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅ ..ፈዛዛው የተዋህዶ ቄሰ እስፖርቱ አይሻልህም ነበር ......ደግሞ ገዳም የእብዶች መኖሪያ ....መሰፈሪያ መናሀሪያ መሆኑን ረሰተህ ነው እንዴ ኡኡ እምትለው ትለሀለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Mar 23, 2012 8:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የዋልድባ ገዳም ጉዳይ ከወያኔ በባሡና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተጣበቁ መዥገሮች አፍራሽ ተግባር ምክንያት ችግሩ ይበልጥ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው ::

ምንጭ :- አንድ አድርገን : አርብ መጋቢት 14 ቀን 2004 .. :: ‹‹ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ ›› ይህን ስላቅ ምን ይሉታል ?

Quote:
ቤተክህነቱ ዋልድባ ገዳምን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ህዝበ ክርስትያኑን ጨጓራውን ያሰረረ ነበር መንግስት እንኳን ከጥቅሙ አኳያ ስኳር ፋብሪካ እገነባለው ቢል መጀመሪያ መቃወም ያለበት ቤተክህነት ሆኖ ሳለ ከመንግስት ጋርም ወግኖ መንቀሳቀሱ ቤተክርስትያኗ ደህና የሚባል መንግስትን የሚቃወም አካል እደሌላት በግልፅ ያሳያል በመጀመሪያ የዋልድባ አባቶች ገዳማቸው ሳይታረስባቸው ታረሰብን አይሉም ሳይነካባቸው ተነካብንም ለማለት አይደፍሩም የመንግስት ባለስልጣናትን የታረሰው ቦታ ላይ እና እንወያይ መጀመሪያ ስራችሁን እዩት ሲሏቸው ቀድመው የሰሩትን ስራ ያውቁታልና ሽሬ ላይ ካልሆነ ብለው ባለስልጣናቱ እምቢ አሉ አባቶችም በቃ የሰራችሁትን ስራ ላለማመን እና አላደረግንም ለማለት ስለሆነ በምትጠሩት ስብሰባ ላይ አንገኝም ብለው በአንድነት ተነስተው ወጡ መንግስት ደግሞ እያለ ያለው የፖለቲካ አላማ ያላቸው የገዳሙ መነኮሳት ብሎ አስተያየት በኢቲቪ ሲሰጥ ስመለከት በጣም ተበሳጨው ሰው የፖለቲካ አላማ ለማረመድ ገዳም ምን ሊሰራ ይገባል ? የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እኮ ከተማ ነው ተመራጭ እንዴት እደሚያስቡ ራሱ ግራ የሚገባ ነገር ነው

ቤተክህነት እኛን ወክሎ ወደ ዋልድባ ያቀናው ሰው እና የመንግስት ስኳር ኮርፖሬሽን ሀላፊ አባይ ጸሀዬ ሁለት አይነት መልስ መስጠታቸውም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው አቦይ ስብሀት የሚነሳ መቃብር አለ እሱን ሌላ ቦታ ላይ የማስፈር ስራ ይሰራል በቤተክርስትያን አባቶች ቦታው ተባርኮ የነበሩትን አስከሬኖች በማንሳት ቦታ የመለወጥ ስራ ይሰራል ብለው አስተያየት ሲሰጡ አቶ ተስፋዬ የመንበረ ፓትርያርክ /ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ደግሞ ምንም ነገር እንዳልተከናወነ እና የስኳር ልማቱ እና ገዳሙ በጣም የተራራቁ መሆናቸውን ገልጸዋል በነገራችን ላይ ይህ ሰው ከጀነራል ዊንጌት ኤሌክትሪሲቲ ዲፕሎማ እንዲሁም በገበያ ጥናት አስተናደር ሌላ ዲፕሎማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚሰራበት ቦታ ጋር ምን ግንኙነት እንዳለው አቡነ ጳውሎስ ቢመልሱ መልካ ነው ባይሆን እንደኛ ሀሳብ የገበያ ጥናቱ ትምህርት የዋልድባን መሬት ከመንግስት ጋር በመደራደር ለመሸጥ የረዳው ይመስለናል ባለን መረጃ መሰረት ለዋልድባ ገዳም አባቶች ሀሳባቸውን በአግባቡ እንዳይገልጡ እንደ እርጎ ዝንብ እየገባ ሲበጠብጣቸው የነበረውም ይህ ሰው ነው ፡፡ ገዳሙ ከግድቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ እንዳለውም ገልጿል በተጨማሪ በጣም የገረመን አስተያየት የሸንኮራ ልማቱ ሲካሄድ በሚገደበው 138 ሜትር ግድብ የገዳሙ አባቶች አሳ ማጥመድ ይችላሉ የሚል አስተያየት መስጠቱም ጭምር ነው ቋርፍ የሚባል ገዳሙ የሚጠቀምበት ተክልም ብሎ ዘባርቋል ፡፡ ይህ ሰው በዚህ ብቃቱ እዚህ ቦታ ላይ መቀመጥ ይገባዋል ብለው ያስባሉ ? እኛ እንደምናስበው ይህ ቦታ የቤተክርስትያኒቱን አማኞች ለመምራት በመንፈሳዊ ሆነም በአስተዳደራዊ ትምህርቶች ለቦታው የሚመጥን ሰው መሆን አለበት የሚል አስተያየት አለን አሁን የኛ ትልቁ ችግር የማይገባቸው ሰዎች ቦታን በዘመድም ይሁን በገንዘብ ይቆናጠጡታል ኋላ የሚመጣውን የቤተክርስትያን ችግር ሲመጣ ደግሞ ቤተክርስትያኒቷን አሳልፈው ይሰጧታል ፤ትክክለኛው ሰው ትክክለኛ ቦታ ላይ ቢቀመጥ ግን ይህን የመሰለ ችግር ለመፍታት መንፈሳዊ ሆነ አስተዳደራዊ ብቃት ስለሚኖረው ችግሮችን ሊጋፈጥ እና መፍትሄ ሊያመጣ የመጀመሪያው ሰው ይሆናል አሁን ግን እየሆነ ያለው የተገላቢጦሽ ነው ፡፡

እኛ የአሳ ናፍቆት የለብንም እኛ ርስታችንን አትንኩ ነው የምንለው አሳ ለማግኝት በመኪና ሀዋሳ መውረድ ይቻላል የአባቶችን ርስት መቃብር በዶዘር አትፈንቅሉብን ነው የምንለው አቶ አቦይ ስብሀት ስለ ሚያነሱት አፅም በቂ እውቀት ላይኖራቸው ይችላል ይህ ግን ከቤተክህነት ተወክሎ የሄደ ሰው ከሰውየው ዘቅጦ መገኝቱ ያሳፍራል፡፡ ልሳነ ዘተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ በየወሩ የምትታተም መፅሄት ላይ 2004 . የአብይ ፆም እትም አቡነ ጳውሎስ ይህን ሰው ከፍተኛ ብቃት ያለው ሰው በማለት አሁን ላለበት ቦታ ሹመውታል፡፡

እኛም እንደ አባቶች ይግባኝ ለክርስቶስ ብለናል ቅን ፈራጅ እሱ ስለሆነ ለእሱ አሳፈናል ቤተክርትያን ጦር ሲነሳባት አብረው ከውስጥ ለሚወጓት ሰዎች ጊዜው ሲደርስ ባለቤቱ ይፋረዳቸው የአባቶችን ጸሎት አምላካችን ይሰማል በፍርድ ቀን መጽሀፉ እንዲህ ይላል ‹‹እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤›› ማቴዎስ ወንጌል 12 36 እናንተም ስለ ስራችሁ ትጠየቁበታላችሁ የአምላካችን ቃል አይታበይም ፡፡

የኢቲቪ ዜና ይህን ይመስላል
የልማት ፕሮጀክቱ የዋልድባ ገዳም ህልውና የማይነካ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወች

በምዕራብ ትግራይ ወልቃይት ወረዳ የሚካሄደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኘው የዋልድባ ገዳም ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች። በቤተክርስተያኗ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን በሰጠው መግለጫ የልማት ፕሮጀክቱ የገዳሙን ህልውና የማይነካና የስኳር ልማት ፕሮጀክቱ የሚከናወንበት ቦታና ግድቡ የሚገነባበት ስፍራ የማይገናኙ ናቸው ብሏል። ግድቡ የዛሪማ ወንዝ የሚጠቀምና ሲፈስ እንኳን ወደ ምዕራብ ትግራይ እንጂ ሽቅብ ወደ ገዳሙ እንደማይወጣ ከገዳሙ መነኩሳት፣ ከፕሮጀክቱ ኃላፊዎችና ከአካባቢው አስተዳድር አካላት ጋር በተደረጉ ውይይቶች መረዳት ተችሏል ነው ያለው አጣሪ ቡድኑ። ገዳሙ ከግድቡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ እንዳለውም ተገልጿል።በገዳሙ ውስጥ የሚያልፍ መንገድም ሆነ ፓርክ እንደሌለ አጣሪ ቡድኑ ማረጋገጥ ችሏል። ገዳሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ የሚፈልጉ መነኮሳት የሚሰጡት መረጃ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚያከናውኑት ተግባር ነውም ብሏል። እነዚህ አካላት ለሚያነሱት ሀሳብ ላይ ለመወያየት በተደጋጋሚ የተደረገው ጥረትም በእነሱ በኩል ፈቃደኝነትን ሊያገኝ እንዳልቻለ አጣሪ ቡድኑ ገልጿል። (ሪፖርተር ደባሱ ባይለልኝ )
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Mar 24, 2012 11:34 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በዋልድባ ገዳም ላይ በወያኔ አገዛዝ የሚደረገው የማውደም ተግባርና በገዳሙ የሚኖሩ መነኮሣትን የማፈናቀል ዕርምጃ ምን ሁኔታ ላይ እንደደረሠ የአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ የአማርኛው ክፍል ባልደረባ የሆነው አቶ አዲሱ አበበ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል :- ተከታተሉት ::

ምንጭ :- አዲሱ አበበ : ቅዳሜ መጋቢት 15 ቀን 2004 .. :: ዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Mar 27, 2012 10:26 pm    Post subject: Reply with quote

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በዋልድባ ጉዳይ ሕዝበ -ክርስቲያኑ በአንድ ላይ መቆም ይኖርበታል :: ኢትዮጵያውያንም ከእንግዲህ በማርክሲስት -ሌኒኒስ -ማዖይስት -ስታሊኒስት -ኤንቨር ሆዣይዝት ዛር በተለከፉ አምባገነኖች ሥር አገራቸውንና ኃይማኖታቸውን አስጠብቀው መዝለቅ እንደማይችሉ ግልፅ ሊሆንላቸው ይገባል :: በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጀመሩትን እንቅስቃሴ በሌሎችም የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሥፋት ሊሣተፉበት ይገባል ::

ምንጮች :-
1 ..... አንድ አድርገን : ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2004 .. :: የዋልድባ ገዳም መብት ለማስከበረ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ ::

2 ..... Uploaded by ESATelevision on Mar 26, 2012. ESAT:የተቃውሞ ሰልፍ ስለ ዋልድባ ገዳም Rally about Waldeba WashingtonDc Mar12.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Mar 31, 2012 6:16 am    Post subject: Reply with quote

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ስለ ዋልድባ ጉዳይ ዛሬ ያነበብኩትን ላካፍላችሁ ::

ምንጭ :- ደጀሰላም : ሐሙስ መጋቢት 20 ቀን 2004 .. :: በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን /ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ (ክፍል አንድ )::

Quote:
· ስብሰባው የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ፤
· “ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት )

“የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት” በዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ “የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማት” የሚል ስብሰባ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2004 . በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የስብሰባው አዘጋጅ የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሲሆን ለተመረጡ ሰዎች በየስማቸው የተሰራጨው የጥሪ ካርድ ደግሞ በጎንደር ከተማ ከንቲባ /ቤት ሓላፊ የተፈረመበት እና እንደ ሰርግ ካርድ “የጥሪው ካርድ እንዳይለይዎ” የሚል ማሳሰቢያም የሰፈረበት ነው፡፡ ጥሪው በአንድ በኩል የሀገረ ስብከቱን የአድባራት አስተዳዳሪዎችን፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትን፣ የጉባኤ መመህራንና ሰባክያነ ወንጌልን አለማካተቱ በአንጻሩም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው አቋም አጠራጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ከየቀበሌው የተጠሩበት መሆኑ የስብሰባው ዓላማ ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

ስብሰባው የተመራው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ነው፡፡ ከእርሳቸውም ጋራ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ዐብዩ በመድረኩ የተገኙ ሲሆን ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሞከሩት ዋነኛው ተናጋሪ ደግሞ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ናቸው፡፡

ከጠዋቱ 230 እንደሚጀመር ቀጠሮ የተያዘለት ስብሰባ ከረፋዱ 415 የተጀመረ ሲሆን እስከ ቀኑ 800 ድረስ ከዘለቀ በኋላ እንዲህ ባሉት ስብሰባዎች ድራማዊ በሆነ መልክ የሚዘጋጁ “የጋራ አቋም መግለጫዎች” ሳይነበቡበት ተጠናቋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ከቤቱ የሚቀርቡ አብዛኞቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ከሚሰጡት ምላሾች ጋራ አለመጣጣማቸው የተሳታፊዎችን ስሜት እያካረረው በመሄዱ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

የስብሰባውን ሂደት የታዘቡ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በገለጻ ረጅም ጊዜ የወሰዱት አቶ ኣባይ በአብዛኛው ያተኰሩት በመነኰሳቱም ይሁን በምእመኑ ባልተነሡና ደካማ በሆኑ ነጥቦች ላይ ነው - “ገዳሙ በውኃ አይጥለቀለቅም፤ ሸንኮራ አገዳ አይተከልበትም፤ ሕዝብ አይሰፍርበትም” በሚሉ ጉዳዮች፡፡ በመሆኑም ተሳታፊዎቹ አቶ ኣባይ ጥያቄያቸውን እየመለሱ እንዳልሆነ በማስገንዘብ “የገዳሙ መሬት በመንገድ ሥራ ይሁን በእርሻ ተነክቷል ወይስ አልተነካም፤ የቅዱሳን ዐፅም ተቆፍሮ ወጥቷል ወይስ አልወጣም፤ የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን አሉ ወይስ የሉም ? ለሚሉት ሦስት ዐበይት ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ግን አለባብሰው ከማለፍ ውጭ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ አልነበረም፡፡

ከአቶ ኣባይ ቀደም ሲል የሀገረ ስብከቱን /ቤት ጨምሮ ከደባርቅ፣ ወገራ፣ ጃናሞራ እና ከመሳሰሉት አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጣ ልኡካን ቡድን ወደ ፕሮጀክቱ ስፍራ በመሄድ ያደረገውን ቆይታ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ታይቷል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላት ከተሳታፊዎች ለተነሡ ጥያቄዎችም ምላሽ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

ከእነርሱም መካከል የጩጌ ማርያም ገዳም አበምኔት አባ ወልደ ገብርኤል እና የኮሶዬ /ወገራ / በኣታ ለማርያሙ ካህን የሰጡት ምስክርነት ከሌሎቹ ለየት ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የኮሶዬ /ወገራ / በኣታ ለማርያሙ ካህንም “ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈርስ ተነግሮናል፤ በሚፈርሱት አብያተ ክርስቲያን ቁጥር ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚልዮን ብር ካሳ እንሰጣችኋለን ሲሉ ሰምቻለሁ” ማለታቸው ተዘግቧል። ከሁለቱ የልኡካን ቡድኑ አባላት በተፃራሪ የጎንደር በኣታ እና የአዘዞ ሚካኤል አስተዳዳሪው አባ ብርሃነ መስቀል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ “የእሳት ጎረቤት እንጂ የውኃ ጎረቤት አይጎዳችሁም” እያሉ መነኰሳቱን ሲያግባቡ ታይተዋል፡፡ ለዚህ አነጋገራቸው ከቤቱ “ጃፓንን የጎዳት የውኃ ሱናሚ አይደለም ወይ ? እንዴት የውኃ ጎረቤት አይጎዳም ትላለህ ? የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡
አርእስተ ጉዳይ፡ -
· በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበው ‹የሀገረ ስብከቱ ልኡካን ቡድን› ዘገባ ከእውነታው ፈጽሞ የተለየ ስለ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተጋልጧል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባል የነበሩ አንድ አባት በተለያዩ አካባቢዎች 500 ሜትር እስከ ሦስት ሰዓት መንገድ የሚሆን የገዳሙ መሬት ታርሶ መመልከታቸውን መስክረዋል፡፡
· የሀ /ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከቀድሞ የተለየና ያልተጠበቀ አቋም ማሳየታቸው ብዙዎችን አስከፍቷል። ከቤተ ክህነቱና ከመንግሥት ሓላፊዎች በተደረገባቸው ጫና ሳይደረግባቸው አልቀረም ተብሏል።
· የመንግሥት ባለሥልጣናት በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ፣ በዓዲ አርቃይ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙትን ልዩ ጫናና ማስፈራሪያ እንዲያቆሙ ተጠይቋል፡፡ የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳቱ በልማቱ ላይ እንደተወያዩ በኢ .ቴቪ የተላለፈውን ዘገባ ተቃውመዋል፤ “ወደ ቦታው ሄጃለሁ፤ አይቻለሁ፤ ያየሁትን እናገራለሁ፤ ፊልሙ ተቆራርጦ ነው የቀረበው፡፡ ገዳማችንን ደፍራችሁታል፡፡ እዚያ መነኰሳቱን ስንጠይቃቸው ለእኛ የነገሩን ‹ገዳማችንን ደፍራችሁታል፤ ምነው በእኛ ዘመን ይህን አመጣብን ብለን እያዘንን፤ እየጸለይን፤ እያለቀስን ነው ያለነው፡፡ ጥያቄያችንን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ልከን መልስ እየጠበቅን ነው፡፡ ልማቱን ስለመደገፍ ሲጠየቁም እኛ የልማት ፀሮች አይደለንም ነው ያሉት፡፡ ነገር ግን በዓዲ አርቃይ፣ በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ የቤተ ሚናስ መነኮሳትን ስታስጨንቋቸው፣ ስታስፈሯሯቸው፣ ስትጫኗቸው አይቻለሁ፡፡ የቴሌቪዥኑ ጋዜጠኛ ከቆመበት በላይ ወደ ገዳሙ እስከ 500 ሜትር ታርሶ አይቻለሁ፡፡ አባ ነፃ በሚባለው የአትክልት (ሙዝ ) ስፍራ እስከ ሦስት ሰዓት የእግር መንገድ የሚሰድ ርቀት ታርሶ አይቼአለሁ፡፡”፤
· “በአባቶቻችን አፍረናል” በማለት የተናገሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች የቡድኑን አባላት እነርሱ እንዳልመረጧቸው፣ ሊወክሏቸውም እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
· “በፕሮጀክቱ 50,000 ሰው የሥራ ዕድል ያገኛል፤ 5000 መኖርያ ቤቶች ይሠራሉ ብላችኋል፡፡ መነኰሳቱኮ ዋልድባ ድረስ የሄዱት ዓለምን ጥለው ጥሞናን ሽተው ነው፡፡ ታዲያ እናንተ የገዳሙን ክልል ከተማ ማድረጋችኹ አግባብ ነው ወይ ? /ከተነሡት ጥያቄዎች አንዱ /
· ለተሳታፊዎች ጥያቄ ምላሽ ያልሰጡት አቶ ኣባይ ፀሃዬ አበው መነኰሳቱን ‹ፖሊቲከኞች› ገዳሙንም ‹የፖሊቲከኞች መሸሸጊያ› በሚል መናገራቸው በኢሕአዴግ አገዛዝ የቀጠለው ቤተ ክርስቲያንን የመናቅና የመዳፈር አስተሳሰብና ተግባር አካል መሆኑ በተሰብሳቢዎቹ ተነግሯቸዋል።
· አቶ ኣባይ የዋልድባ መሬት ‹ለአፈር ምርመራ› በሚል መታረሱንና ዐፅሞችም መነሣታቸውን ያመኑ ሲሆን በገዳሙ ክልል ውስጥና ውጭ ‹ከሕዝቡ ጋራ በመነጋገር› የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡
· የጠ //ክህነቱ ///አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ ወደ አዲስ አበባ ተልከው የሄዱ መነኰሳትን “መዋቅር ያልጠበቁ ሕገ ወጦች ናቸው” በማለት ዘልፈዋቸዋል፡፡
· አቶ ኣባይንና አወያዩን አቶ አያሌው ጎበዜን ሳይቀር ደስ ያላሰኘው የአቶ ተስፋዬ ‹ውዳሴ ኢሕአዴግ› በተሰብሳቢው ተቃውሞ ተቋርጧል፡፡
· በዕለቱ በስብሰባ አመራራቸው የተወያዮቹ መጽናኛ የሆኑት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ “ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ፤” በማለት ተሳታፊዎች ያነሷቸው ‹ስጋቶች› በምክክር እና ውይይት መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
· ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን አጣሪ ቡድን ልኰ የገዳሙን ህልውና የሚያስጠብቅ አቋም እንዲወስድ፤ መንፈሳውያን ማኅበራት ትክክለኛውን መረጃ ይዘው ገዳሙን የማስጠበቅ እንቀስቃሴ እንዲያካሂዱ፣ መንግሥትም ቀስ በቀስ በይፋ እያመነ የመጣቸውን መረጃዎች በተሟላ ይዘታቸው (እውነታቸው ) ለሕዝቡ ግልጽ በማድረግ ተነጋግሮ የማስማሚያ ነጥብ እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡

በተያያዘ ጉዳይ፦
· ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ዋልድባ ገዳም አምርቶ የፕሮጀክቱን ተጽዕኖ በመገምገም ይፋዊ ሪፖርት የሚያቀርብ የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱ እየተነገረ ነው፡፡
· መጋቢት 27 ቀን በዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም ክብረ በዓል (በዓለ ንግሥ ) ነው፡፡ በርካታ የጎንደር ከተማ ምእመን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከነገ መጋቢት 21 ቀን 2004 . ጀምሮ ወደ ስፍራው መጓዝ ይጀምራል - አንድም ለአክብሮ በዓል በሌላም በኩል ለገዳሙ ያለውን አለኝታ ለመግለጽ፡፡ ጉዞው ከጎንደር እስከ ዓዲ አርቃይ በተሽከርካሪ ከዚያ በኋላ 18 ሰዓታት የእግር መንገድ ነው፡፡
· “ዋልድባ ዓለም አቀፍ ገዳማችን ነው፤ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም !! (ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አንድ የዞኑ የደኅንነት መኰንን ዋልድባ በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ በልማቱ ላይ ጥያቄ ማንሣት እንደማይችሉ ለተናገራቸው ቃል የመለሱለት )

የአርእስተ ጉዳዮቹ ዝርዝር እንደረሰልን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
Page 1 of 7

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia