WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ከበደ ሚካኤል

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Fri Mar 09, 2012 9:42 pm    Post subject: ከበደ ሚካኤል Reply with quote

ሰላም የዋርካ ደንበኞች ::ዛሬ የታላቁን ደራሲ የከበደ ሚካኤልን ስራ ላካፍላችው ብቅ ብያለው :: ምንም እንኩዋን አብዛኛሆቹን የምታውቋቸው ቢሆንም ለትዝታ ያህል በተከታታይ አቀርብላችዋለው :: እናንተም የዋርካው ጥላ ስር በፀጥታ ተቀምጣቹ በትዝታ ተጎዙ በቃላቶች ውበት ተዝናኑ :: ለዛሬ

የብረት ድስትና የሸክላ ድስት ::
አንድ ቀን ብረት ድስት ሸክላ ድስትን አለው ::
እኔን ነው በሁሉ መልክህ የሚመስለው ::
ወንድሜ ነህ እኮ ባታውቀው ነው እንጂ
ከዛሬ ጀምሮ እንሁን ወዳጂ ::
እኔን እንደ መቅረብ መሸሽህ ልምን ነው ?
አካሌ አካላትህ የኔ ቤት ያንተም ነው ::
አሁን በል ተነሥ ፍቅራችንም ይጥና
ሽር ሽር እያልን እንናፈስና ::
መፋቀራችንን ይይልን ሰው ሁሉ
የማንተዋወቅ ለምን ነው መምሰሉ ::
አጥቂ ቢመጣብን ዘሎ የሚማታ
እኔ እሆንሃለው ኅይለኛ መከታ
ለፀሐይ ላቧራው እየሆንኩን ድንኳን
እደግፍሃለው ቢያነቅፍህ እንኳን ::
በደካማነቱ ቅር እያለው ሆዱ ::
ተነሣ ሸክላ ድስት አንድነት ሊሄዱ
አንድ መቶ እርምጃ እንደ ተራመዱ
ድንገት ተጋጩና አቶ ብረት ድስት
ረግተው ሲቆሙ ያላንዳች ጉዳት ::
የሸክላ ድስት ግን በፈራው ጎዳና
ተሰብሮ ወደቀ እንክትክት አለና ::
ወዮ :: እንኳን ለማልት ጊዜ ሳያደርሰው
የገሉ ስባሪ ምድሩን አለበሰው ::
እንዲያው ሰው ያላቻ እየተንጠራራ
ለመሻረክ ቢያስብ ከበላዩ ጋራ ::
መቼም አይጠፋና ከኅይለኛ ግፍ
ከጉዳት በስተቀር ምንም አያተርፍ ::
ሰሆች ከሰው ጋራ ሸሪክ ስትሆኑ
ዐቅማችውን በፊት አይታችሁ መዝኑ ::መልካም ግዜ ....
_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Sat Mar 10, 2012 2:06 am    Post subject: Reply with quote

ጽጌ ረዳና ደመና

የፀሐዩ ንዳድ ያጠቃት በብዙ
ጠውልጎ የሚታይ የቅጠልዋ ወዙ ::
አንዲት ድጌ ረዳ ቃልዋን አስተዛዝና
እንዲህ ተናገረች ለሰማይ ደመና ::
ድርቀት በጣም ጎድቶኝ እየኝ ስንገላታ
እባክህ ጣልልኝ የዝናም ጠብታ ::
ቶሎ ካላራስኸኝ ጉልበቴ እንዲጥናና
ምንም ተስፋ የለኝ መሞቴ ነውና ::
አሁን መሄዴ ነው ለትልቅ ጉዳይ
ስመለስ መጥቼ ሳልፍ ባንቺ ላይ ::
እዘንምልሻለው ጠብቂኝ እያለ
ምንም ሳይጥልላት መንገዱን ቀጠለ ::
ጉዳዩን ጨርሶ ቁይቶ ሲመጣ
ያቺ ጽጌ ረዳ ሥርዋ ውሃ ያጣ ::
እንደዚያ አስተዛዝና ጭንቋት ያዋየችው
የፀሐዩ ንዳድ አድርቋት ቁየችው ::
እስኪጎርፍ ድረስ የወንዝ ውሃ ሙላት
ወዲያው እንደ መጣ ዝናቡን ጣለላት
ግን ደርቃለችና አልቻለም ሊያድናት ::
ሳልደርስላት ቀረሁ እዬ ጉድ እያለ
ደመናም ጉዞውን ወደ ፊት ቀጠለ ::
ሰውም እንደዚሁ ጭንቁን እያዋየ
በችግሩ ብዛት እየተሠቀየ ::
ብዙ ጊዜ ኖሮ ቆይቶ ሲጉላላ
የሚረዳው አጥቶ ከሞተ በኃላ ::
ዘመድ ወዳጆቹ እንባ እያፈሰሱ
ተዝካር ቢያወጡለት አርባ ቢደግሱ
ይህ ሁሉ ከንቱ ነው አይጠቅመውም ለሱ ::
እውነት ከወደደው ሲቸገር ሲጎዳ
በሕይወቱ ሳለ ሰው ወዳጁን ይርዳ ::

_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Mon Mar 12, 2012 12:01 am    Post subject: Reply with quote

አጫጭር ግጥሞች

የሰዎችን ጠባይ የተመራመረ
አንድ ፈላስፋ ሊቅ እንዲህ ተናገረ ::
በጣም በማስተዋል ከላይ እስከ ታች
ስመለከታቸው የሰውን ልጆች ::
እያጣሁባቸው ግብሩ እሚመሰገን ::
እንቃቸው ጀመር እጅግ አለመጠን ::
*************************************
የደንቆሮ መንፈስ ምንኛ ታደለ ::
ብልጥነት አላጣም ጅል እየመሰለ ::
እንኳን መጽሐፍ ማንበብ ፊደል ሳያጠና
ሁሉንም ያወቀ ይመስለዋልና ::
**************************************

የሊቅ ሰው መከራ የብልኅ አባዜ
ሲጨነቅ መኖር ነው ባሳብ በትካዜ ::
አቶ ዐሳበ ቢስ ይተኛል ዝም ብሎ
ከተራሱ ጋራ ዐሳቡን ጠቅሎ ::
************************************

ኩራትና ተእቢት የሞሊት አናት
ሰይፍና ጎራዴ የመቱን አንገት ::
አይገላገሉም እንዲህ በቀላሉ
እመሬት ላይ ወድቀው ሳይንከባለሉ ::
**************************************

ገንዘብ መፈጠሩ ለሰው አገልባይ
ሆኖ ሊሠራበት አልነበረም ወይ ::
አሁን ግን መስገብገብ በጣም ስለ በዛ
ሰው ባሪያ እየሆነ ለገንዘብ ተገዛ ::
**************************************

የሐሰት ወገኖች ተመቸን እያሉ
ብዙ ግዜ አድመው እየተማማሉ ::
እውነትን ካለም ላይ ሊያጠፉዋት ተነሡ
እውነት ግን ሁል ጊዜ መከታ ለነሱ ::
ታግላ እያሸነፈች ስትኖር ረግታ
ጠላቶችዋ ሁሉ በሱዋ ጥፋት ፈንታ ::
አንድ ባንድ ወድቀው እየተሰበሩ
ከስማቸው ጋር ሁሉም ጠፍተው ቀሩ ::
**************************************

ባለም ላይ ተሠርቶ በብዙ ጥበብ
ማዕርግ የሚባለው የደረጃ ግንብ ::
በዚህ የሚያዳግት ባቀበት መንገድ
ግማሹ ሲወጣ ግማሹ ሲወርድ ::
ክወደ ዳር ቆሞ ማስተዋሉን ሳይተው
ምንኛ ደስ ይላል ለተመለከተው ::
*****************************************
ብልኅ አስተዋይ ሰው ያለምን ነገር
ዘልቆና ጠንቅቆ የሚመራመር
ትልቅ ቁም ነገር ነው ረቂቅ ምስጢር ::
ብለው በሹልክታ አድርገው ሽፍን
የዚህ አለም ሰዋች የሚያወሩትን ::

_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Sat Mar 24, 2012 3:15 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
1975 . በማስታወሻዬ ከመዘግብኳቸው ገጠመኞች አንደኛዋ እንዲህ ትላለች :: ትናንትና ማታ ለትንሹ ልጀ ለአሉላ የገዛሁለት ጫማ በጣም ስለተለቀበት በልኩ የሚሆን ለመለወጥ ዛሬ ጳጉሜን ሶስት ቀን ጠቃት ፒአያሳ እያለን ወምንጠራው አደባባይ ክወንዶሞቹ ጋር ወስጃቸው የገዛሁበት አንበሳ ጫማ እስኪከፈትልን ድረስ ስነጠባበቅ ከጣቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ላይ አቶ ከበደ ሚካኤል ሲያልፉ እጅ ነሳኋቸው :: እሳቸውም አንገታቸውን ጎንበስ አርገው አለፉ :: ጥቁር ለብሰዋል : ጥቁር ባርሜጣ ደፍተዋል : ጥቁር ጥላ ይዘዋል ሽክ ብለዋል ::

ካለፉኝ በህዋላ መለስ ብለው ....ሰማኝ ! ያኔ ቤቴን ለመረከብ አንተም ደክመህበታል :: ምንም ሳይሆን ቀረ ! ለኢትዮጵያ ህዝብ ያን ያህል ደክሜያለሁ :: ይኼ ሁሉ ቀጣት ደርሶ አሁንም ግፍ የሰራል :: ህዝቡም አያስተውልም ?:: ህዝቡ ባይሰማ እኔ ምን ላድረግ ? ታዲያ ቤቴን ተቀምቼ ቀረሁ :: ወንብዴ መንግስት እንዲህ ይሰራል ! ..አሉኝ :: በጣም ተቆጥተዋል :: እኔም መልስ እስከስጣቸው አልታጋሱም :: ከአስር በላይ የሚሆኑ ተላላፊዎች ከበውን ንግግራቸውን ያዳምጡ ነበር :: ልጅ እግሮች አዛውንቶች ሴቶችና ወንዶች ነበሩ :: አቶ ከበደ ወዲያው ጉዟቸውን ቀጠሉና ወደፊት እልፍ እንዳሉ እንደገና ተመለሱና ..ይህን ሁሉ የሚሰራ ምን መስለህ ? ደጃዝማች ግርማቸው ነው :: (ደጃዝማች ግን 1966 . መጨረሻ ጀምሮ በድረግ ስር ቤት ነበሩ ) እነርሱ በመኪና እየሄዱ እኔ በሆቴል እኖራለሁ :: እኔ ከበደ ሚካኤል ነኝ :: ሀያን ሰላሳ ዓመት ላገሬ ይህን ሁሉ ከሰራሁ በኋላ እንደዚህ መጣል ይገባኝ ነበር ? ትሰማኛለህ ? ..ብለው አፈጠጡብኝ :: እኔም ምነው ማዘዣው ተስጽፎሎዎት አልነበረም ? ቤቱን አልተረከቡም ? እንዴ ? አልኳቸው ::

ምኑን እረከበዋለሁ ? ፈርሷል እኮ ! ያፈረሱትን ቤት እኮ ነው ተረከብ ያሉኝ :: ይህም ሁሉ ደረሶበት ይህ ህዝብ አልተቀጣም ? ግዴለም የስራውን ዋጋ ያገኛል ! ክፉ ህዝብ ነው :: ሃያ ሰላሳ ዓመት ከደከምኩ ይህ ሁሉ ግፍ ሊደርስብኝ ይገባ ነበር ? ብለውኝ ወደፊት ሄዱ ......
ዝርዝሩ ይቀጥላል :: በአቶ ማሞ አቅራቢነት አቶ ከበደ ያመለክቱት ማመልክቻም ተያይዟል :: የብስጭታቸው እና ችግራቸው ድምር ወዳጅ ጠላቱን መለየት እስኪያቅታቸው አድርሷቸው ነበር ::

ሀተታው "የደረስኩበት ማሞ ውድነህ እኔና ትዝታዎቼ " በሚል ካሳተሙት ክፍል ሁለት መጽሀፍ የተወሰደ ነው :: አቶ ከበደ ሚካኤል በችግር ሲንግላቱ ኖረው ሊሞቱ አቅራቢያ ..አክብረን ዶክተር ብለናቸዋለን እና ዶክተር በሏቸው ተብሎ ነበር :: እሳቸው "ክፉ ህዝብ " ያሉት ቤታቸውን አፍራርሶ ከሞቱ በኋላ ዶክተር ይላቸዋል :: በቅርቡም መርካቶ የነበራቸውን ቤታቸውን ባስመለከተ ..ጠጅ ቤት ..ሆቴል ምናምን መሆኑን አስመልክቶ ኢቲቪ ዶኩመንትሪ ሰርቷል :: ግን ምን ዋጋ አለው ?

እዚህ አሜሪካ (ልናገር የምችለው የማውቀውን ቦታ ነውና ) የነ ከበደ ሚካኤል አይነት ታላላቅ ሰዎች ቤት ሂስቶሪካል ማርከር ተብሎ ሚዝየም ይሆናል :: ወንበራቸው አልጋቸው ..ምናምናቸው ሳይቀር ይደረደርና ትውልድ ይማርበታል :: ቫልዩንተሮች የአጸዱን ሳር ያጭዳሉ ...ሰው ያስጎበኛሉ :: ሀብታሞች የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ይለግሳሉ :: ይህ ደግሞ ለታላቅዋ ዩኒየን አሜሪካ ተቃዋሚ ኢቭን በኮንፍዴሬት ታሪከኞች ሁሉ እየተፈጸመ ያለ ነው :: ባሜሪካ አሜሪካ በቃኝ ብሎ ኪዩባ ገብቶ የሞተውን የኧርነስት ሄሚግዌይን ቤት የገዙት በፈቃደኘነት ሚዝየም ሲያደርጉ ...እኛ ግን ነጥቀን ጠጅ ቤት ! እንዴት ትውልድ ከታላቁ ከበደ የዕውቀት ትሩፋት ይልቅ ያውቶቢስ ተራን "ተራ
"ጠጅ ይመርጣል ...ምናለበት ታላላቆቻችን ብንወድና ብናከብር ? ለምንስ አክብሮት መለኪያው ሁልጊዜ የፖለቲካ ኩታራዎች ዲስኩር ይሆናል ?!
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4215
Location: united states

PostPosted: Sat Mar 24, 2012 4:22 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ ውቃው
የሀገራችን ጸሀፊዎች መጨረሻ እንዲህ አሳዛኝ መሆኑን ስልሳየ ጽሁፍህ ተባረክ ::ሌላውድንቅ ጸሀፊ በግልም የረዳኝ ብርሀኑ ዘሪሁን እንዲሁ ቤቱን እዳ ውስጥ የከተተ እዚህ ብጠቅሰ ሙት ወቃሽ የሚሆን አንቱ የተባለ ጸሀፊ ጦስ ነበር ::አቤ ጉበኛም ትንሽ ሳስታውስ በችግር ሁኔታ ነው ያረፈው ::ከጸፊዎች በደህና ኑሮ ያለፉ ጥቂቶች ጸሀይ መስፍን ፍቅር ታሪክና አርበኝነት ጀብዱ ደራሲ ቢትወደድ መኮንን / አዲስ አለማየሁ ነጋድራስ ተሰማ ብላቴን ጌታዎቹ ህሩይና ሲራክ ናቸው ::
እስኪ በያለንበት የእነዚህ ውድ ደራሲዎች ቅርስ እንጠብቅ
በአንዳንዶቹ ስም ለተመሰረቱ ቻርቲ የሚቻለን አንርዳ !
///////-----------/////////------//////=====/////
ሰንበሌጥ ብርቱ ንፋስ ሲመጣ ለጥብላ ያሳለፈችና አቶ ዛፍ በትቢት ተገትሮ በነፋስ የተገነደሰ የከበደ ሚካኤል ጽሁፍ የልጅነቴ የመጀመሪያውን ሬዲዮ መልክቴ ነበር ::
///////////////-------------////////////////////////
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክትክታው

ኮትኳች

Joined: 27 Jun 2011
Posts: 122

PostPosted: Sat Mar 24, 2012 6:28 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ አምድ ታዳሚዎች

የመረረው እንድናስታውስና እንድንካፈል ላቀረብከው የታላቁን ከበደ ሚካኤልን ስራ በጣም ጥሩ ነው። ቀጥልበት

ውቃው እና ዲጎኔ ያቀረባችሁት ሀሳብ እጅግ የሚመስጥ ነው። እንደአለመታደል ሆኖ ለአገራቸው በተለያየ ሙያና ችሎታ የደከሙና የተቸገሩ አብዛኛዎቹ የመጨረሻ እጣ ፈንታቸው እናንተ እንዳስቀመጣችሁት የትም ወድቆ መቅረት ነው። ይህ ችግር ይወገዳል የሚል ተስፋ ቢኖርም ከጊዜ ወደጊዜ እየባሰ እንጂ እየተሻለ አልመጣም። ለዚህም ነው አሁንም ከድንቁርና ከችግር አርቆ ከማስታዋል አልላቀቅ ብለን በዚሁ አዙሪት የምንሽከረከረው። ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት በሞከሩበት አጭር ጊዜ መትረውት የሄዱትን እንደ እነ አበበ አረጋይ የመሳሰሉትን ውድ ኢትዮጵያውያን አርበኞችና ምሁራንን ነበር። እነ ኮሎኔል መንግስት /ማርያም ስልጣን እንደያዙ የመጀምሪያ የስራ ርክክብ ያደረጉት በነበርው ላይ መጨመር ሳይሆን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ማጥፋት ማውደም ነበር። ይህም አገሪቱን ብዙ ወደ ኋላ ጎትቷል። በዚህም አገሪቱን ባዶ አድርገው አጽድተው ለወያኔ ከፋፍተው ሄዱ። አሁን ደግሞ “በአማራ የብሄር ጭቆና ስም” አገራችን እጅግ በጣም ከሚያሳዝንና ከሚያስፈራ ሁኔታ ላይ በሸዐቢያ ውላጆች ስር ወድቃለች። ፖለቲከኞቹም፡ ታሪኳም፡ ቅርሷም፡ ማንነቷም እየተደመሰሰ ነው።

ስለዚህ ዲጎኒ እንዳለው ቢያንስ በየአለንበትና በየአጋጣሚው ሁሉ አገራችንን በተመለከተ የሚገኙትን ቅርስ (የደራሲያንን ጨምሮ ) ለመሰብሰብ ለመጠብቅ እንሞክር።

“ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሁፍ” በሚለው አምድ ላይ ትንሽ ወጣ ያለ አስተያየት በማቅረቤ የዋርካ ታዳሚዎችን ይቅርታ እጠይቃለሁ

ክትክታው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Sun Mar 25, 2012 8:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ተሳታፊዎች :: ክትክታው ስለ አስተያየትህ አመስግናለው ::

አገር

አገር በታሪክ በቌንቌ በሃይማኖት በልማድ በተስፋ በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ህዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው ::

አገር ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱብት አድገውም በጀግንነት ከውጪ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም ሥራ ሠርተው ዕድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻቸውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጎድ ነው ::

በመወለድ እትብት በመሞት አካል ከአፈሩ ጋር ስለሚዋሐድ የአገሩ አፈር ሕዝቡ በላዩ የሚኖሩበት ማለት ነው ::

እግዚአብሔር ከምድሯ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር እያጠባች የምታሳድግ ፍቅሯ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው ::

ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን ተራራውን ሜዳውን ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ አባቶች በሕይወትና በሞት የሠሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለቀረ በአገር አስካሉ ሲታይ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው ::

አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድኽነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ አደራ የተሰጠ ገንዘብ ነው ::

መልካም ቀን ::
_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Sun Mar 25, 2012 9:30 pm    Post subject: Reply with quote

እኛ ኢትዮጲያውያን ባሁኑ ጊዜ በግድ ልንከተለውና ልንፈጽመው የሚገባን ሃሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው ::

አንደኛ : ኢትዮጵያዊ የሆንህ ሰው ሁሉ ሰንደቅ ዓላማህ አገርህና ነጻነትህ የሚጠቁበትን ነገር በማስወገድ ወይም ደግሞ እነሱ የሚጠቀሙበትን ሥራ ለመፈጸም ብለህ በሞትህ ጊዜ በሰማይና በምድር ስምህ በወርቅ ቀለም የሚጻፍበትን የሰማዕትነት ሥራ መስራትህን ልብህ ተረድቶ ደስ ይበለው ::

ሁለተኛ :- አገርን መውደድ ማለት አገርህ የምትጠቀምበትንና የምትከበርበትን ሥራ መሥራት ነው ::

ሦስተኛ :- አገርህንና ወገንህን የሚያስንቅ ወይም የሚጎዳ ሥራ ከመሥራት መሞት ይሻልኻል ::

አራተኛ :- እኛ ኢትዮጵያውያን የምንሠራው ሥራ መልካም ቢሆን አገራችን ኢትዮጵያ እንደምትከበር የምንሠራው ሥራ መጥፎ ቢሆን ግን እንደምትዋረድ አትርሳ ::

አምስተኛ :- ኢትዮጵያ አገርህ ከሌሎች ከማንኛዎቹም አገሮች ሁሉ ይልቅ የምትበልጥብህ መሆንዋ ቀንም ሆነ ሌሊት በዐሳብህ ውስጥ ሳይረሳና ሳይዘነጋ ተጽፎ ይጉር ::

ስድስተኛ :-ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ለተወለደባት አገሩ የሚያስብላት መልካም ዐሳብ ወይም የሠራላት መልካም ሥራ ሲነገር በሰማህ ወይም ተጽፎ ባየህ ጊዜ አንተም ደግሞ እንደዚሁ ይህንኑ ያህል ላገርህ ለኢትዮጲያ ልታስብላትና ልትሠራላት የሚገባህ መሆኑን ዕወቀው ::

ሰባተኛ :-አንድ ኢትዮጲያዊ ሲበደልና ሲጠቃ ባየህ ጊዜ የተበደለችውና የተጠቃችው እናትህ ኢትዮጲያ መሆንዋን ተረዳው ::

ስምንተኛ :- ኢትዮጵያ አገርህ በእውነት ትልቅ ሳትሆን ወንድሞችህም ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሳይደላቸው አንተ ብቻህን የምታገኝው
ደስታ ገንዘብና ተድላ በሕልም እንደ ተገኝ ወርቅ መና ባዶ ሆኖ የሚቀር መሆኑን ልብህ አይዘንጋው ::

ዘጠነኛ :- ብዙ ገንዘብና ብዙ ርስት ከማግኘት ይልቅ ለአገሩ ትልቅ ሥራ የሠራላት ስው ስሙ ለዘለዓለም በታሪክ ሲጠራ ይኖራል ::

ዐስረኛ :- ሌሎቹ የዓለም ነገሥታት የደረሱበት የሥልጣኔ ደረጃ ላይ አገራችን ኢትዮጵያ በቶሎ እንድትደርስ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማሰብና መጣጣር ይገባናል :: ድካማችንና ትጋታችንም በተለየ ለዚሁ አሳብ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል ::

_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
MeronZG

አዲስ

Joined: 12 Nov 2011
Posts: 35
Location: Seattle

PostPosted: Wed Mar 28, 2012 4:35 pm    Post subject: Reply with quote

የመረረው . እንደጻፈ(ች)ው:
እኛ ኢትዮጲያውያን ባሁኑ ጊዜ በግድ ልንከተለውና ልንፈጽመው የሚገባን ሃሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው ::

አንደኛ : ኢትዮጵያዊ የሆንህ ሰው ሁሉ ሰንደቅ ዓላማህ አገርህና ነጻነትህ የሚጠቁበትን ነገር በማስወገድ ወይም ደግሞ እነሱ የሚጠቀሙበትን ሥራ ለመፈጸም ብለህ በሞትህ ጊዜ በሰማይና በምድር ስምህ በወርቅ ቀለም የሚጻፍበትን የሰማዕትነት ሥራ መስራትህን ልብህ ተረድቶ ደስ ይበለው ::

ሁለተኛ :- አገርን መውደድ ማለት አገርህ የምትጠቀምበትንና የምትከበርበትን ሥራ መሥራት ነው ::

ሦስተኛ :- አገርህንና ወገንህን የሚያስንቅ ወይም የሚጎዳ ሥራ ከመሥራት መሞት ይሻልኻል ::

አራተኛ :- እኛ ኢትዮጵያውያን የምንሠራው ሥራ መልካም ቢሆን አገራችን ኢትዮጵያ እንደምትከበር የምንሠራው ሥራ መጥፎ ቢሆን ግን እንደምትዋረድ አትርሳ ::

አምስተኛ :- ኢትዮጵያ አገርህ ከሌሎች ከማንኛዎቹም አገሮች ሁሉ ይልቅ የምትበልጥብህ መሆንዋ ቀንም ሆነ ሌሊት በዐሳብህ ውስጥ ሳይረሳና ሳይዘነጋ ተጽፎ ይጉር ::

ስድስተኛ :-ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ለተወለደባት አገሩ የሚያስብላት መልካም ዐሳብ ወይም የሠራላት መልካም ሥራ ሲነገር በሰማህ ወይም ተጽፎ ባየህ ጊዜ አንተም ደግሞ እንደዚሁ ይህንኑ ያህል ላገርህ ለኢትዮጲያ ልታስብላትና ልትሠራላት የሚገባህ መሆኑን ዕወቀው ::

ሰባተኛ :-አንድ ኢትዮጲያዊ ሲበደልና ሲጠቃ ባየህ ጊዜ የተበደለችውና የተጠቃችው እናትህ ኢትዮጲያ መሆንዋን ተረዳው ::

ስምንተኛ :- ኢትዮጵያ አገርህ በእውነት ትልቅ ሳትሆን ወንድሞችህም ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሳይደላቸው አንተ ብቻህን የምታገኝው
ደስታ ገንዘብና ተድላ በሕልም እንደ ተገኝ ወርቅ መና ባዶ ሆኖ የሚቀር መሆኑን ልብህ አይዘንጋው ::

ዘጠነኛ :- ብዙ ገንዘብና ብዙ ርስት ከማግኘት ይልቅ ለአገሩ ትልቅ ሥራ የሠራላት ስው ስሙ ለዘለዓለም በታሪክ ሲጠራ ይኖራል ::

ዐስረኛ :- ሌሎቹ የዓለም ነገሥታት የደረሱበት የሥልጣኔ ደረጃ ላይ አገራችን ኢትዮጵያ በቶሎ እንድትደርስ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ማሰብና መጣጣር ይገባናል :: ድካማችንና ትጋታችንም በተለየ ለዚሁ አሳብ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል ::እንዲህ አይነት መልክት እንደማስታወሻ አስፈላጊ ነው . Happy to see we are moving away from all the negativity which oddly people seem to enjoy. We need more of this.
_________________
Ethiopian Music (7000+) http://www.hubesha.com/audio.php
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዲያስፖራ

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Apr 2009
Posts: 714
Location: no

PostPosted: Wed Mar 28, 2012 5:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሳያቁ አለቁ ነበረ ተረቱ ; እያወቁ ማለቅ መጣ በሰአቱ ::
ከበደ ሚካኤል
_________________
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Wed Mar 28, 2012 11:30 pm    Post subject: Reply with quote

ሰንደቅ ዓላማ

ሰንደቅ ዓላማ የነጻነት ምልክት የአንድ ሕዝብ ማተብ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው ::
""ተመልከት ዓላማህን
ተከተል አለቃህን ""::
ነጋሪት እየተጎሰመ ሠራዊቱ እየተመመ ሲሄድ ሰንደቅ ዓላማ ተእምርት ኅይል
ትእምርተ መዊዕ ነው ::

ሰንደቅ ዓላማችን አረንጎዴ ብጫና ቀይ ሦስት ቀለማት ናቸው :: ምሳሌያቸው ተስፋ ልምላሜና
ሀብት :: ብጫው ሃይማኖት አበባና ፍሬ ቀዩ ፍቅር መዝዋዕትነትና ጀግንነት ነው ::

ሰላም ለዚህ ቤት ተሳታፊዎች ለሁላችሁም ሰላምታዬ ይድረሳችው :: መልካም ቆይታ ::
_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-

Last edited by የመረረው. on Thu Mar 29, 2012 4:15 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የመረረው .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2012
Posts: 98
Location: USA

PostPosted: Thu Mar 29, 2012 12:11 am    Post subject: Reply with quote

ጥሩም ነገር ቢሆን ከመጠን ካለፈ ሁል ግዜ መጥፎ ነው ::

ትዕቢትና ውርደት አካልና ጥላ ናቸው :: ሳይለያዩ ሁል ጊዜ ቀዳሚና ተከታይ ሆነው ተያይዘው ሲሄዱ ይኖራሉ ::

እህልና ውሃ ሰውነትን እንደሚመግቡት ሁሉ መጻሕፍትን ማንበብም እንደዚሁ መንፈስን ይመግበዋል ::

ከበላይ ያሉትን ሰዋች እያየህ በልብህ ቅናት አይደርብህ :: ይልቅስ ካንተ በታች ያሉትን ችግረኞች እየተመለከትህ ዕድልህ ከነሱ የተሻለ በመሆኑ ፈጣሪህን አመስግነው ::

ምንም እንኳን የሚያስመሰግንህ ትልቅ ሥራ ብትሠራ ምን ጊዜም ቢሆን አትመካበት :: ትምክሕት ማንኛውንም ዋጋ ቢሆን ያቀለዋል ትሕትና ግን ከሁሉ ሞያ የበለጠ ዋጋ ያለው ባሕርይ ነው ::

ሰው በሕይወቱ ሲኖር የሚያገኘውን ነገር ሁሉ የሚቀበለው ከተወለደባት አገር ሰለ ሆነ አስፈላጊ ምክንያት በመጣ ጊዜ ያለውን መልካም ነገር ሁሉ ሕይወቱን እንኳን ሳይቀር ሳያመነታ ላገሩ ሲል ሊሠዋ ይገባዋል ::

አንድ ትልቅ ሊቅ ስለ ስንፍና መጥፎነት ሲናገር እንዲህ አለ :: ማናቸውንም ዐይነት ጥፋት ያጠፋ ሰው ሁሉ ይቅርታ ቢደረግለት የተገባ ነው :: ምሕረት ሊደረግለት የማይገባው አንድ ብቻ አለ እሱም ሰነፍ ሰው ነው ::

ከጥንት ጀምሮ ሲነገር የሚኖር አንድ የላቲን ተረት እንዲህ ይላል :: ጦርነት እንዳይመጣብህ ብትፈልግ ሁል ጊዜ ለጦርነት የተሰናዳህ ሆነህ መቀመጥ ይገባሀል ::

ፀሐይ ጡዋት ጡዋት የምትወጣው የሱን ድምጥ ሰምታ የሚመስለው በልቡ ሲኮራ የሚኖር አንዳንድ አውራ ዶሮ አለ ይባላል :: በሕዝብም መካከል እንዲሁ ሊሠሩት የማይችሉትን ትልቅ ሥራ የሠሩ እየመሰላቸው በከንቱ ሲመኩ የሚታዩ ሰዎች ይገኛሉ ::

ምቀኛ ሰው የክፋቱ ብዛት የሞቱ ሰዓት በደረሰች ጊዜ እኔ ከሞትኩኝ በኃላ ዓለም ጨለማ ሁና ትቅር ብሎ በማሰብ የሚቻለው ቢሆን ኖሮ ፀሓይን አጥፍቶዋት ለመሞት በወደደ ነበር :: ቅን ሰው ግን ለዓለም የሚጠቅም ሥራ ለመሥራት ሲል ሕይወቱን ይሠዋል ::

_________________
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia