WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አስተያየት ስጡበት

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Apr 03, 2012 11:20 am    Post subject: አስተያየት ስጡበት Reply with quote

ሠላም ውድ ዋርካዊያን /ያት
እዚህ ሰፈር ፖስት ጋደረግኩ ቆየው ልበል መጣፊያው ሁሉ አዲስ ሆነብኝ ' ... የሆነው ሆኖ ዛሬ አመጣጤ እቺን ቪዲዮ አይታችሁ አስተያየታችሁን ስጡበት ለማለት ነው ይህን ቪዲዮ የሠራው ሠው ኢሜይል ሰደደልኝና በዛውም የኔን ስክሪፕት ማለትም ድርሰት ለሆም ቪዲዮ ስለተጠቀመበት አመሰገነኝ ነገሩ በርግጥ ገርሞኛል ... እንዴ ብዬ ስራዎቼን ጉግል ውስጥ ገብቼ ስጎለጉል በርካቶቹ ብዙ ድረ -ገጾች ላይ ተለጥፈው አገኘዋቸው አትላንታና ሌሎች ከተማዎች ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጣዎች ላይ መውጣታቸዉንም አየው ... በርግጥ ሕዝብ እንዲያነበው ነውና ድረ -ገፅ ላይ የጻፍኩት በርካታ ዓይኖች ስለጎበኙት እሰየው አልኩኝ ያገረመኝ ግን ሌላ ነው አዲሳባ የሚታተም አንድ የግል መፅሔት ላይ ምናልባት ታስታውሱት ይሆናል 'ከጨረቃ ስር ' የምትለዋን የቆየች ድርሰቴን ስሜን ገንጥለው ታሪኩን ትንሽ ቀይረው አወጡት የድርሰቱ ባለቤት በኩራት ስሙን ከድርሰቱ ራስጌ እና እግርጌ ለጥፎታል
በርግጥ አሁን ዘመኑ የዌብ 2.0 ነው ሁሉም ያለዉንም የሌለዉንም የፈጠረዉንም ያልፈጠረዉንም ሼር ለማድረግ የሚራወጥበት ዘመን ነው
የድርሰቴ እርዕስ ሸጥኳት ! ይሰኛል እቺን ይጫኑና ያግኟት የፊልሙ ባለቤት ሥራዉን ከአንድ ጋዜጣ ላይ እንዳገኘ ነግሮኛል ስሜን አድኖ እዚህ ምውደው ሰፈር ዋርካ ስር ስላገኘኝ ደስ ብሎኛል
ፊልሙን ለማየት እዚች ጋር ጠቅ ያድርጉ እኔ የራሴ በርካታ አስተያየቶች አሉኝ ቀድሜ መስጠቱ ትንሽ ግብዝነት እንዳያስመስልብኝ ብዬ ቀድሜ የናንተን አስተያየት መስማት ፈለግኩኝ

መልካም ቀን

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 03, 2012 9:28 pm    Post subject: Re: አስተያየት ስጡበት Reply with quote

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም ዋናው :-

'የቅጅ መብት ሣይጠብቁ የሌብነቱን ጉዳይ ':- ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ከማን የተማሩትን ሥራ ላይ ያውላሉ ብለህ ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ውጭ አገር ያሉት ሥምህን ካላወጡትና የአንተንም ፈቃድ ካልጠየቁ በአድራሻቸው ጽፈህ በይፋ እንዲያርሙ ብታደርግ አይከፋም :: መነበቡ ብቻ ሣይሆን ሕግና ሥርዓት ባለበት ዓለም ውስጥ እየኖሩ አገር ቤት እንዳሉት ሌባ ባልደረቦቻቸው ያሻቸውን እንዲያደርጉ መፍቀድ የለብንም ::

በለጠፍከው አድራሻ ዩቲዩብ ላይ የተቀመጠውን የቪዲዮ ክሊፕ አየሁት :: የአንተ ጽሑፍ ዋና የማጠንጠኛ ኃሣብ አንድ ሰዓሊ ስለሣላት የአንዲት ሴት ሥዕልና ከሥዕሏ ጋር በምናቡ የፈጠረውን ትሥሥር የሚተርክ ነው :: ቪዲዮ ክሊፑ ላይ ግን ሁለት ዓይነት ምሥሎችን እናያለን :- የሥዕል ንድፍና የአንዲት ሴት ፎቶግራፍ :: ሁለቱ ምሥሎች እንዴት የአንተን ድርሰት ኃሣብ ሊገልጹ እንደተፈለገ አልገባኝም :: ምናልባት ሠዓሊው ያለቀለትን ሥዕል ከንድፍ እስከ ሙሉ ሥዕል ሲያጎለብት በዚያ ሂደት የተፈጠሩበትን የሥሜት ቁርኝት የሚያሣይ ተከታታይነት ያለው ቅንብር ቢሆን ትርጉም ሊሠጥ ይችል ነበር :: እንዲያውም ፎቶግራፉ ላይ የምትታየዋ ሴት እኮ የላሊበላ መስቀል በአንገቷ ላይ አላጠለቀችም Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes :: በእኔ አስተያዬት የቪዲዮ ክሊፑ ሙሉ ሥራ ለመሆን ገና ብዙ ይቀረዋል :: ሙከራው ግን የሚበረታታ ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፕላዞግ

አዲስ

Joined: 06 Dec 2008
Posts: 31

PostPosted: Tue Apr 03, 2012 11:55 pm    Post subject: Reply with quote

ዋናው ነገር የዋናው ስራ ተደብቆ አለመቅረቱ : ዞሮ ዞሮ መውጣቱ !! ድንቅ ፍልስፍና እና እይታ ነው ::
ከተቻለ ሌላ ክሊፕ አንተው ራስህ ሰርተህ ዩቲዩብ ላይ ብታስቀምጥ ይሄኛው በክብር ቢነሳ መልካም ይመስለናል :: የተከበሩ ሰዐሊው መንተባተብ : ተድላም ጠቆም እንዳረገው ከጭብጡ ጋር የማይሄድ ምስል ያውም 'ፎቶ ': ጭስ የሌለው ትምባሆ : ኤክስፕሬሽን የጎደለው ትረካ : ድምፅ እና ምስል ኤዲት ሳይደርግ ስናየው ለዚህ ምርጥ ስራ አይገባም ነበር ግን ሆነ ...ብለን ተቆጨን !!!
መካሰሱና መከሳከሱ ሌላ የጊዜና የሞራል ፍጆታ ይኖረዋል : ይሄ እንደማስጠንቀቅያ ቢወሰድ እና ያሉትን ነገሮች ሰብሰብ አድርጎ በጊዜ ወደኛ የዋንሽ ተደራሲያን ወርወር ለማድረግ ተፍ ተፍ ቢጀመርስ ? ተጀምሮም ከሆነ ትኩረት ቢሰጠውስ ? የፍርድ ሂደት ከምንከታተል የዋናውን በረከት ብንኮመኩምስ ...
በርታ ሲለጥቅም አትጥፋ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 312

PostPosted: Wed Apr 04, 2012 3:36 am    Post subject: Reply with quote

አልሰሜን ግባ በለው አሉ :: ዋኒቾ ሙሉው ጥላአልባ ራሱ ተጠርዞ እየተሸጠ ነው :: ዝግችሎት ፈልገህ ጥላአልባን ግዛና መጨረሻውን ትወደው እንደሁ እይ :: አትላንታ የምታውቀው ሰው ካለ ፈልጉልኝ በላቸው :: መደምደሚያውን የጻፈው ጠራዡ ሌባ ነው ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1198
Location: united states

PostPosted: Thu Apr 05, 2012 8:05 am    Post subject: Reply with quote

-...- እንደጻፈ(ች)ው:
አልሰሜን ግባ በለው አሉ :: ዋኒቾ ሙሉው ጥላአልባ ራሱ ተጠርዞ እየተሸጠ ነው :: ዝግችሎት ፈልገህ ጥላአልባን ግዛና መጨረሻውን ትወደው እንደሁ እይ :: አትላንታ የምታውቀው ሰው ካለ ፈልጉልኝ በላቸው :: መደምደሚያውን የጻፈው ጠራዡ ሌባ ነው ::

መርዶ በቃ እንዲህ በአደባባይ ሆነ የሚነገረው :: ..... ግን በቃ በጣም ብሶበታል ማለት ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Apr 06, 2012 8:32 pm    Post subject: Reply with quote

እንሰት እንደጻፈ(ች)ው:
-...- እንደጻፈ(ች)ው:
አልሰሜን ግባ በለው አሉ :: ዋኒቾ ሙሉው ጥላአልባ ራሱ ተጠርዞ እየተሸጠ ነው :: ዝግችሎት ፈልገህ ጥላአልባን ግዛና መጨረሻውን ትወደው እንደሁ እይ :: አትላንታ የምታውቀው ሰው ካለ ፈልጉልኝ በላቸው :: መደምደሚያውን የጻፈው ጠራዡ ሌባ ነው ::

መርዶ በቃ እንዲህ በአደባባይ ሆነ የሚነገረው :: ..... ግን በቃ በጣም ብሶበታል ማለት ነው ::

ወንድሜ እንሰት :-

"አገር ሲበላሽ ጓጉንቸር ያፈላል " ይባላል :: እና ዛዲያ የአገሪቱ የጥበብ ሰዎች በዘመናት ድካም ያወረሱንን ትውፊት የዘመኑ ሞጭላፊዎች እንደራሳቸው ሥራ እያደረጉ ሲነግዱበት የሚያስተውል ትውልድ ሥርቆት የዕርድና መለኪያ አድርጎ ተቀብሏል :: ይህ ድርጊት ሊቆም የሚችለው ከትንሿ ሌብነት ጀምሮ ያለውን ጥፋት መከላከል ስንጀምር ብቻ ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Apr 07, 2012 1:30 am    Post subject: Reply with quote

Very Happy Very Happy Very Happy

ምን ጎርጓሪ ምን ያወጣል ነው 'ሚባለው ...
አያረጉትም አይባልም ድሮም የወደቀ ዛፍ መጥረቢያ እንደሚበዛበት ይታወቃል ... ደግነቱ እሩብ ሚልዮን ዕይታን ያፈራች ጥላ ዓልባ አባቷ ማን እንደሆነ አይታወቅም ቢባል አይታመንም እናም ደፍረው ቢያደርጉት 'ንኳን ዋርካዊያን /ያት ተደራሲዎቼ ከመፀሐፉ ግርጌ ያለዉን የሀሰት ስም ፍቀው የባለቤቱን ስም እንደሚፅፉበት ጥርጣሬው የለኝም :: (ድሮም ዓላማዬ ቸብችቦ ሳንቲም ከመቁጠር ምናቤን በማጋራት ከምወደው ወገኔ ጋር በሀሳብ መገናኘት ነውና )
ስለጥላ -ዓልባ ከተነሳ መቼም ከዚህ በፊት የተኛ ቤት እንደሆነ እንጃ 'ንጂ አውርቼው ነበር የመቋረጡ ምክኒያት መካከለኛው ምስራቅ የሚታተም አንድ አበሻዊ መፀሔት ላይ በተከታታይ ክፍሎች እየወጣ መሆኑን ሳታውቁት አትቀሩም :: መጀመሪያ ላይ ብዙም ተቃውሞ አልነበረኝም ዋርካን ገልጠው ማንበብ ለማይችሉ መዳረሱንም ወድጄው ነበር ኋላ ግን የዋርካ ወንድምና እሕቶቼንም ምክር ስሰማ እኔም 300 በላ ገፆች ያሉትን ስራ ለመፃፍ ካፈሰስኩት ጊዜ አኳያ ሳስበው ለዛዉም በቅጡ ፈቃድ ሳልጠየቅ ዝም ብዬ እነሆ በረከቱን ማለቱ ወደጅልነት ያመራብኝ መሰለኝ ::
በርግጥ የድርሰቱ መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ፅሑፍ አስፍሬ ነበር
ታዲያ ኮፒራይቱ በሣይበር ኢቲዮጲያ አላፊነት ቢሆንም አደራ በመተማመን ይሁን አዎ ሳይበር ኢትዮጵያዎች እንደምናውቀው ዋርካችን በትክክል ለመስራቱ ሳይታክቱ ከመጣር ውጪ ለማንም ለምንም ግድ የላቸዉም ዋናው የሚባል አንድ ባተሌ ስለመኖሩ ሁሉ ላያውቁ ይችላሉ ያም ሆነ ይህ መተማመኑ ከጠፋ ጥላ -ዓልባ ለጊዜው ጥላ ስር አረፍ ብትልስ ብዬ ከጓሮ ሸጎጥኳት ብዙዎቹ እንደሚያደርጉት ላጲስ ይዤም አልተመለስኩባትም ::
እኔም የመጻፉ ጥማት ስላለብኝ ካንባቢያኖቼ ጋር መገናኛ ይሆነኝ ዘንድ
አጫጭር ልቦለዶች ብዬ መጻፌን ቀጠልኩኝ እየው ዛሬ ላይ ደርሼ ከዚህም ሰፈር መዘገን ተጀመረ :: በርግጥ እውነቱን ለመናገር አልከፋኝም ቢጣፍጥ ነው የተዘገነው ብዬ ደስ አለኝ ::
በዚህ አጋጣሚ መፃፍ የማቋረጤ ምክኒያት ከዚህ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ተረዱልኝ ሕይወት ሁሌም አትደላም አንዳንዴ ለሱስ የሚተራርፉ ሽርፍራፊ ጊዜያትንም ትነጥቃለች ::

ወደ ቤቱ ርዕስ ልመለስ
ወንድሞቼ ፕላዞ እና ተድላ ለምክራችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ አደርገው ዘንድም ብርታቱን እንዲሰጠኝ በፀሎታችሁ አትርሱኝ (ምን እናድርግ የዛሬ 8 እና 9 ዓመት ከዳሞት ቅኔ ቤት ሆነን እዚህ ዋርካ ስር ቋንቋን ስንማር ታላላቅ የዋርካ ፀሐፍት እና የቋንቋ ጠበብት የተፃፈ ሁሉ መፀሐፍ የተገጠመ ሁሉ መድብል አይሆንም ብለው ስላስተማሩ ' ነው :Smile በዚህ ላይ ለሁሉም ጊዜ አለው ::

ሸጥኵት ወይም ወደፊልም የቀየረ ሰው እንዳለው ሠዓሊው የሚለው ስራ ስራዉን እኔ ባየዉበት ዕይታ ያየው አይመስለኝም ወይም የራሱን ቴክኒክ ተጠቅሞ ይሆናል የሰራው ግን ግን ፊደላቱን ስጋ አልብሶ ስላሳየኝ አመሰግነዋለሁ ... ስለፊልም ጥበብ አሁን ተማሪ ቤት ገብቼ እየተንደፋደፍኩበት ያለ ጉዳይ ስለሆነ ባሕሩ ጥልቅና ሰፊ መሆኑን ስለማውቅ እሱ የሰራዉን ማቅለሉ ይከብደኛል ደፍሮ ከጀመረው ደፍሮ እንደሚያሻሽለው ግን ተስፋ አለኝ ::
እዚህ አጭር ፊልም ውስጥ ብዙ ነገር ማካተት ይቻላል በርግጥ ከረጅም ፊልም አጭር ፊልም መስራት ይከብዳል አጭር ፊል ማለት በራሱ ግጥም እንደማለት ነው በትንሽ ዕይታዎችና ንግግር ብዙ መናገር መቻል ማለት ነው ዛሬ አንቱ የተባሉ የፊልም ዳይሬክተሮች የመጀመሪያ ሥራዎቻቸው አጫጭር ፊልሞችና ማስታወቂያዎች ናቸው
እነኚህ ዋና የፊልም ጥበብ ቅመሞች በደምብ ቢሠሩበትስ
Story
Diegesis
Plot
continuity

እና የመሳሰሉት
ገፀ -ባሕሪን ስለመላበስ ... .... በፊልም ርዕስ ከሆነ ምናወራው ቢቆየን ይሻላል Wink ይህንንም ያልኩት የተሰራው ስራ እንደወርክሾፕ ይሆናል ብዬ በማመን ነው ::

ቸር ቆዩልኝ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 312

PostPosted: Sun Apr 08, 2012 11:50 pm    Post subject: Reply with quote

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:
ምን ጎርጓሪ ምን ያወጣል ነው 'ሚባለው ...
አያረጉትም አይባልም ድሮም የወደቀ ዛፍ መጥረቢያ እንደሚበዛበት ይታወቃል ... ደግነቱ እሩብ ሚልዮን ዕይታን ያፈራች ጥላ ዓልባ አባቷ ማን እንደሆነ አይታወቅም ቢባል አይታመንም እናም ደፍረው ቢያደርጉት 'ንኳን ዋርካዊያን /ያት ተደራሲዎቼ ከመፀሐፉ ግርጌ ያለዉን የሀሰት ስም ፍቀው የባለቤቱን ስም እንደሚፅፉበት ጥርጣሬው የለኝም :: (ድሮም ዓላማዬ ቸብችቦ ሳንቲም ከመቁጠር ምናቤን በማጋራት ከምወደው ወገኔ ጋር በሀሳብ መገናኘት ነውና )
ስለጥላ -ዓልባ ከተነሳ መቼም ከዚህ በፊት የተኛ ቤት እንደሆነ እንጃ 'ንጂ አውርቼው ነበር የመቋረጡ ምክኒያት መካከለኛው ምስራቅ የሚታተም አንድ አበሻዊ መፀሔት ላይ በተከታታይ ክፍሎች እየወጣ መሆኑን ሳታውቁት አትቀሩም :: መጀመሪያ ላይ ብዙም ተቃውሞ አልነበረኝም ዋርካን ገልጠው ማንበብ ለማይችሉ መዳረሱንም ወድጄው ነበር ኋላ ግን የዋርካ ወንድምና እሕቶቼንም ምክር ስሰማ እኔም 300 በላ ገፆች ያሉትን ስራ ለመፃፍ ካፈሰስኩት ጊዜ አኳያ ሳስበው ለዛዉም በቅጡ ፈቃድ ሳልጠየቅ ዝም ብዬ እነሆ በረከቱን ማለቱ ወደጅልነት ያመራብኝ መሰለኝ ::
በርግጥ የድርሰቱ መግቢያ ላይ እንዲህ የሚል ፅሑፍ አስፍሬ ነበር ታዲያ ኮፒራይቱ በሣይበር ኢቲዮጲያ አላፊነት ቢሆንም አደራ በመተማመን ይሁን አዎ ሳይበር ኢትዮጵያዎች እንደምናውቀው ዋርካችን በትክክል ለመስራቱ ሳይታክቱ ከመጣር ውጪ ለማንም ለምንም ግድ የላቸዉም ዋናው የሚባል አንድ ባተሌ ስለመኖሩ ሁሉ ላያውቁ ይችላሉ ያም ሆነ ይህ መተማመኑ ከጠፋ ጥላ -ዓልባ ለጊዜው ጥላ ስር አረፍ ብትልስ ብዬ ከጓሮ ሸጎጥኳት ብዙዎቹ እንደሚያደርጉት ላጲስ ይዤም አልተመለስኩባትም ::

ሞኝ የዘራውን ብልህ ያጭደዋል ይባላል :: ዋኒቾ ይበልህ :: 300 ገጽ ጽፈህ አመታት ሳታሳትመው 10 አመት ቁጭ ያልክበት ከመቃብር ድንጋይህ ላይ እንዲጻፍልህ ነው ? ከሰነፍክ እንደፓኑ ለዩኒቨርሲቲ ማተሚያ ቤት ስጠውና በስምህ ታትሞ ቅርስ ይሁንህ :: ሌባው ጠራዥማ ውስኪዉን ለብለብ አድርጎ ጣጥ ሲል ደራሲ ነኝ ግን የኛ ሕዝብ ጥሩ መጽሀፍ አፕሪሺየት አያደርግም ምክንያቱም 4700 ብቻ ነው የተሸጠልኝ እያለ ያማርራል :: አንጎሉና ህሊናው ያልተረዳው ነገር 4700 ኮፒ 20 ዶላር 94000 ዶላር ያልደከመበትና ለሱ የማይገባውን ማግኘቱ ነው ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia