WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 360, 361, 362 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Apr 04, 2012 3:01 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ብሩክ !!!

ሰሞኑን እኔም ትንሽ ወጣ ብዬ ስለነበር ለተወሰኑ ቀናቶች ዋርካን የማየት ዕድሉ አላጋጠመኝም ::

Quote:
"ሀኒ " ፍራሽ አንጥፋ ጠበቀችው -- ጓደኛዋ ቤት
ጫት ሲፈርሹ ዋሉ --- ወደማታም ገራባው ተነስቶ -- የፍቅር ናፍቆታቨውን ተወጡ --- ቅቅቅ እሱም በሷ እሷም በሱ ቀለጡ -- አሌክስ ደስ አለውውውው

ቅቅቅቅቅቅቅ አቤት ጫት እና ስራው !!! ስንት ሰው አስታወስከኝ መሰለህ :: ወይ ሞፊቲ !!! ማለቴ .... ወይ ብሩክ !!! ሞፊቲ ለም ትዝ እንዳለኝ እንጃ ቅቅቅ ::

ጓደኛህ ባለማመኑ አልፈርድበትም ብሩኬ :: እራስ ላይ ሲደርስ ታሪኩ ለየት ይላል :: ባንድ ወቅት እኔም እሷ ከምትኖርበት በጣም ርቄ ነበር የምኖረው :: አንድ ቀን በጣም የማምነው : ብትቸገር አንድ ነገር ብትሆን ድረስላት ብዬ አደራ ያልኩት ሰው ስልክ ደውሎልኝ "" ቅዳሜ ቀን ከምሽቱ ሁለት ሰዐት ላይ አዚያ ቦታ ከሆነ ሰው ጋር ታቃቅፈው ቆሞ ...."":: ፌንት አበላኝ :: ትንሽ እንኳ ብጠራጠራት ኖሮ ምናልባትም አልጎዳም ነበር :: ግን 100% እያመንኳት ድንገት ይህ "መረጃ " ስደርሰኝ ልቤ አለመቆሙ እራሱ ምን ያህል ተማመን ልብ እንዳለኝ አረጋገጥኩኝ :: እና ትንሽ መለስ ስልልኝ ""ምነው ይህ ነገር ህልም በሆነ ...ምናልባትም እኮ ህልም ልሆን ይችላል ...ግን እኮ ህልም ቢሆን ኖሮ እነኚህ መኪናዎች ድምጽ እያሰሙ ሲያልፉ ለምን ከእንቅልፌ አልነቃም ነበር ....እስቲ ትንሽ ግዜ ልጠብቅ ከዕንቅልፌ እንቃ እንደሆን ብዬ ቁጭ ባልኩበት ስልኬን አውጥቼ ጓደኛዬ ስልክ ደወልኩ :: ልጁ ሲያናግረኝ ...በቃ ህልም አይደለም እዉነት ነው ብዬ ልደመድም ስል እንደገና ተመልሼ ግን እኮ በህልም እንኳን በህይወት ያለ ሰው ይቅርና ከአመታት በፊት ሞቶ ያስቀበርከውንም ማናገር ይቻል የለ እንዴ ... ብዬ ከራሴ ጋር ስጨቃጨቅ አንድ የሚያውቀኝ ሰው ሰላም ሲለኝ ...እሱን እራሱ በህልሜ እያየሁት ይሆን እንዴ ብዬ ከተጠራጠርኩ በኌላ የማብድም ስለመሰለኝ "" በቃ በህልሜ አይደለም "" ብዬ እዉነቱን እየመረረኝ ዋጥኩኝ ::

ስልክ ደወልኩላት ::

"" እናትዬ ቅዳሜ ማታ ሁለት ሰዐት አካባቢ ዬት ነበርሽ ?""
"" እቤት እንጅ ሌላ ዬት እሆናለሁ ጎስካዬ ""
"" እዚህ ቦታ አንድ ሰው ጋር ተቃቅፋችሁ ... እንደነበር ሰምቻለሁና ምንም ሳትደብቅኝ ንገሪኝ ""
""እኔ ? ማዘርን ጠይቃት :: እንቺ አዮ : ቅዳሜ ከዚህ ቤት ወጥቻለሁኝ እኔ ? ንገሪው እስቲ ..አላመነኝም ""
"" ምን እያልካት ነው ልጄ ?: ከአርብ ጀምሮ ታማ ዛሬ ገና ነው ቀና ያለችው :: እሷ በዚህ ሳምንት ከቤትም ወጥታ አታውቅም ""
"" እሽ አዮ : መልሰሽ ስጭያት ስልኩን ""
"" አሁን አመንከኝ ? አንተ ለካ ትጠረጥረኛለህ አይደል ? ማነው ግን የነገረህ ይህንን ጉዳይ :: አዉቃለሁ ደግሞ ማን ሊነግርህ እንደምችል ::እገሌ ነው :: / የስራውን ይስጠው :: የራሱን ጥፋት ሊሸፍን እኔን መወንጀል አለበት ወይ ?""

በምን ቃላት ይቅርታ ልጠይቃት ... አንተ ልጅ / የስራህን ይስጥህ ....

"እናቴ በጣም ይቅርታ አርጊልኝ :: በጣም በድዬሻለሁ :: ምን ላድርግ እሱ የኔ ነው ብዬ ስለማስብ ነበር ያመንኩት :: ከዛሬ ጀምሮ ምንም ከማንም ላልሰማ ቃል እገባልሻለሁ ::""

" አንተ ማንም በሌለህ በዚያች ከተማ ለምን ያሰቃዩሀል ? ለምን ያስጨንቁሀል ? የኔና ያንተ ጉዳይ እንኳ ቀላል ነው :: ምንም አልበደልከኝም :: ሳትናደድ በጸባይ መጠየቅህ እራሱ የበቃኛል :: አንተ ግን እሱንም አትጣው :: ይቅር በለው :: ምን ቸገረህ ...እኔና አንተ ያው ያው ነን :: ከእንግዲህ መጠንቀቁ እንጂ ላለፈው ሌላ ጥል ማንሳቱ ጥሩ አይደለም ..""

ለማንኛውም የተነገረንን ሁሉ ማመን የለብንም :: ግን እንደኔ ቸኩላችሁ የሌላውንም ሰው ልብ እንዳታደሙ ብዬ ነው :: የይመኙሻልንም ሆነ የአለክስን መጠራጠር እንደ ክፋት አላይም :: እኛ ደግሞ ለክፋት እስላልሆነ ድረስ ያለውን ሀቅ ለጓደኞቻችን የመንገር ሀላፊነት ያለብን ይመስለኛል እነሱ ቢያምኑንም ባያምኑንም ::
በተረፈ ብቅ እያልክ እንድህ አውጋን እንጂ : ይጥማልና ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Apr 05, 2012 11:47 am    Post subject: Reply with quote

ሰኞ እለት
ሀረር አራተኛ ግርድና ሚኒስቴር
ቢሮ ውስጥ
> አንተ ባለሱቅ
> ስማ አንተን እኮ ነው
+ አቤት ከቤ ምነው አፍጠህ አየኸኝ
> ሚስትህ እሁድ የት ነበረች
+ እንዴ ቤቷ ይሆናላ ... ምነው
> ሀማሬሳ ዘመድ አላት ?
+ እንጃ ብዙ አላውቅም ... እሷ ግን የሀረር ልጅ አይደለችም ... ምነው ጠየከኝ
> ሀማሬሳ ዱቄት ፋብሪካው ጋር ሚኒ -ባስ ስትሳፈር አይቻት ሳናግራት ዘጋችኝ
+ አላወቀችህ እንዳይሆን
> እንዴት አታውቀኝም ... አብረን ሁለት ቅዳሜ አንተ ቤት አልቃምንም እንዴ
+ እንግዲህ ያኔ ያየጭ በሽርጥ ... እንዲህ ሱሪ ስትታጠቅ አይታህ አታውቅም ይሆናላ
> አንተ ግን እያሾፍክ ነው እንዴ .... እኔ እኮ ከምሬ ነው ... ቆጭቶኝ
+ ዌል እንግዲህ እጠይቃታለሁ .... ቴክ ኢት ኢዚ .... የኔ ሚስት በአለም አንደኛ ናት .... አታስብ ,.,... ተማመን ... ወገን
ግን ልቢቱ ትንሽ ደንግጣለች
እውነት ግን ምን ልታደርግ ሄዳ ነው
አሁን ነገር ማካበድ አያስፈልግም ብዬ እንጂ .... የውስጥ አይኔ ደም ለብሷል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አይ ፎንቃ ... አለ ብሩክ ወንድሜ

ጎሲና ... በቃ ጣል ጣል አደረካቸው አይደለም ፅጌና ... ይመኝን

ታዝቤሀልሀለሁ
እስከ -ሰኞ
ሰላም ሁኑ
ገጠር መግባቴ ነው
ባይይይይይይይይይይይይይይይ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Apr 07, 2012 11:11 pm    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል

Last edited by Gosa on Tue May 29, 2012 12:35 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Apr 07, 2012 11:17 pm    Post subject: Reply with quote

ይቀጥላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Sun Apr 08, 2012 8:56 pm    Post subject: Reply with quote

ህምምምምም

የማነበው ልበ -ወለድ ነው ወይስ Question Question
ዋው ያስብላል ጎሳ ከምር እኔንም እምባዬን አስፈሰስከኝ ...ኦውውውውው
Quote:
ጎሳ
ንጹህ ፍቅር አገኘሁ : ተሳካልኝ ብዬ ስደሰት ደስታዬ ባጭሩ የሚቀጭ መሆኑን ምነው ትንሽም ብሆን ብጠራጠር ! "ጌታ ሆይ ምንም እንኳ ካላቸው ቤተሰቦች ተወልጄ ቁሳዊ በሆኑ ነገሮች ደስታን ማግኘት ባልችልም በሰጠኽኝ ምንም በሌላቸው ቤተሰቦቼ እርካታን አግኝቼ ምናልባትም ገንዘብ ሊገዛው የማይችለውን የውስጥ ሰላምና ደስታን ስለሰጠኽኝ ተመስገን " እያልኩ ሰላማዊ ህይወት በመኖር ላይ እያለሁ ነበር ካንተ ጋር የተዋወቅነው :: እየተገናኘን እየተዋወቅን እና እየተላመድን ስንመጣም ደስታዬ ቀጣይነት እንዲኖረው / እራሱ አስቦልኝ የፈጠረልኝ የግሌ ሀብት ነህ ብዬ ነበር የደመደምኩት ::
በመጀመሪያ አንተም ያው እንደሌሎቹ በተዋወቅን ማግስት ሌላ ጥያቄ የምታነሳብኝ መስሎኝ በጥንቃቄ ብቀርብህም እየዋለ እያደር ግን ያሰብኩት ትክክል እንዳልነበር ተረዳሁ :: ዝምተኛነትህ በጣም ተመቸኝ :: በዚያ በዝምታ ውስጥ እንኳ ልብህ አንደበት የማያፈልቃቸውን ጣፋጭ የፍቅር ቃላቶችን ሲረጩ ይታወቀኝ ነበር :: እዚያች ሆቴሏ ክፍል ውስጥ ደረትህ ላይ ተኝቼ ያለምንም ንግግር ጸጥ ብለን የየልባችንን የምናዳምጥበትን ግዜ እንዴት አድርጌ ልረሳው እችላለሁ ? እኔ በተፈጥሮዬ ብዙ ንግግር አልችልም :: ግን ካንተ ጋር ስሆን ነጻነት ተሰምቶኝ የተሰማኝን ሁሉ ያለ ፍርሀት ማውራት ጀምሬ : ገና እንደ ህጻን ልጅ አፌን የፈታሁ ነበር የመሰለኝ :: 'ለካ እኔም ከሰው ጋር ስሆን እንደ ሰው ሁሉ ማውራት እና መጫወት እችላለሁ " ብዬ
ባገኘሁት ልበል አንተ በሰጠኽኝ ዕድል እራሴን ማወቅ ቻልኩ :: በራሴም እንድተማመን ምክንያት ሆንከኝ :: ዛሬ ግን ያንን ሁሉ አጣሁ ::
ምናለበት ጨካኝ ሆነህ ቀርበኽኝ አስቀይመኽኝ ብትለየኝ ! ምናለ ባለፈው "ግዜ እና ቦታ አይመችም " ብዬ ባልከለክልህ ! ዛሬ "የሚፈልገውን አግኝቶ ሄደ " ብዬ ልጠላህ በቂ ምክንያት ይሆነኝ ነበር :: አሁን ግን ጥለኽኝ ከመሄድህ ሌላ ምን አደረከኝ ብዬ ጠልቼህ ልርሳህ ? ብትችልና ፈቃድህ ቢሆን አንድ ቀን ቀርበህ በአንደበትህ "አልፈልግሽም " ብቻ በለኝ :: በጣም በምትወደው ሰው ይዤሀለሁ :: ላታገኘኝ ከወሰንክ ግን በጣም እጎዳለሁ ጎሳ ::

ሁሌም የደስታዬ ምንጭ : ጓደኛዬም ለሆነች ለእናቴ ስላንተ አንዱንም ነገር ሳላስቀር ዝክዝክ አድርጌ ነግሬያት አንተን የምታይበትና የምትተዋወቅበትን ግዜ በጣም ጓጉታ በተቻላት መጠን ያቅሟን ያህል ተዘጋጅታ ልትጠብቅህ ደፋ ቀና ማለት ከጀመረች እንደቆየች ዛሬ ብነግርህ ለሷ አዝነህላት ትመለስልኛለህ ብዬ አይደለም : እኔ ምን ያህል ቦታ ሰጥቼህ ምን ያህል አምላክ የሚሰጠኝን ቀሪ ህይወቴን
ካንተ ጋር ለማሳለፍ እጓጓ እንደነበር እንድትረዳልኝ ብዬ እንጂ :: ዛሬ ግን ምን ብዬ "ትቶኝ ሄዷልና እሁድ እሁድ ለሱ ብቻ ብለሽ የምትቀመጭዋን ጉልት ከእንግዲህ ተይ " ልበላት ? በጣም ይከብዳል ጎሳ :: እሷም እንደ ማንኛውም እናት ወግ ማዕረጌን ልታይ ብትጓጓም ድሀ መች የጓጓለትን ነገር በቀላሉ ያገኛል ብለህ ነው :: ዕድላችን ነው : አልቅሰን ይወጣልን ይሆናል :: አንተን ግን ክፉ አይንካህ : መቼም ብሆን ጥሩህን ያሰማን :: ብትሸሸኝም በጣም እወድሀለሁ

አብሶማ ይቺን ሳነባት ..አይይይይይ ..ከምር ትጽፈዋለህ እኮ ነው የሚባለው

አጻጻፍህ ራሱ ልቦለዳዊ ይዘት አለው
እግዛቤር ይይልህ ጎሳ ራሴን አሳመምከኝ ...ከምር ፓሬስታሞል ልዋጥ ...
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Apr 10, 2012 1:56 am    Post subject: Reply with quote

ጎሳ
የፃፍከውን በጥሞና አነበብኩት
አንዴ አይደለም ... ሁለት ሶስቴ
ብዙ ነገርህ አናዶኛል
እንኳን ሞፍቲን ያልሆንኩ እንጂ
ቦጫጭቅህ ነበር ከምር
አሁን ብዙ የምልህ የለኝም
ዝምምምምምምምምምምምምምምም
ሙድ ሲመጣ በደንብ ሰድብሀለሁ
ስላጫወትከን ግሩም ጭውውት ግን ከልቤ ሳላመሰግንህ ማለፍ አልፈለኩም
እና ከልብ አመሰግንሀለሁ
ጨዋታህ ልብ ይማርካል
ስሜት ሰርቆ ያስኮርፋል ... ያስደስታል ... ያበሳጫል

ደሞ በደንብ አታነበኝም ትላለህ እንጂ
እኔ ሳነብህ ውስጥህ ገብቼ ነው .... አንተን ሆኜ ....
እና ስሜቱ በጣም ነው ሚረብሸኝና
እኔ ብሆን ... እልና
አቤት የማደርገው
አቤት ልዩነታችን
እንደመልካችን
ደስ ስንል ግን

ኤኒዌይ
እስኪ ሲመጭ ብቅ በልና ጨርስልን
በተረፈ
ቸር ሰንብት
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Tue Apr 10, 2012 10:54 am    Post subject: Reply with quote

አንተ ጉደኛ ለካ ሙሉ ሆቴልም ዶርመህ ነበርና !?
ወይ ጉዴ !? ጋሽ ፍቃዱ ይህን ሁሉ መአትና ጉድ ሳይነግረኝ ይቅር ????
ብቻ ያንተን ነገር የመጨረሻህን አይቼ ባወራው ይሻለኛል እንጂ ! አሁን ምንም ለማለት የምችል አይመስለኝም ::
አይፋም መታልሀለች :: በበርጫ ካልሆነ ይህን ሁሉ ጉድሽን እንዴት ግዜ አግኝተሽ ታነቢዋለሽ ብያታለሁ ?
ከቻልክ አንድ ጥቅል በለጬ ካለህበት አቀብላት !

ዝዋይ ....ዝዋይ .... ዝዋይ ......አለ ነገር !! አማቾችህን መቼም አትረሳም አይደል ? ላጋልጥ !???

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Apr 10, 2012 11:58 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ትንሽ አይ ኢንፈክሺን ለሁለት ቀን ኮምፒዉተሩን እንዳልከፍት አረገኝ :: ሞፊቲ ሊበቀለኝ ቫይረስ ላከብኝ መሰለኝ :: ግዴለም :: እንደምንም የጀመርኩትን እጨርሰዋለሁ ግዜ ይፍጅ እንጂ ::

ገልብጤ !!! ሶሪ : ታርጌቴ ሞፊቲን ማናደድ እንጅ አንተን ፓራሴታሞል ማክሰር አልነበረም በተወደደ መድሀኒት :: ግን አስደሰትከኝ :: አመሰግናለሁ ከልቤ :: እንደ ሞፊቲ ሞራል ሰባሪ በሞላበት ዐለም እንዳንተ አይነቱን / አስቦ ባይፈጥርልን ኖሮ ምን ይውጠን ነበር ! በድጋሚ ላመሰግንህ እወዳለሁ ወንድሜ ::

ባለሱቅ !!!
አንተማ መች የሞፊቲን ያህል እንኳ ትግስት አለህና ነው የማትገነጣጥለኝ ? ሁለቱ ሱቆችህም የተዘጉት ደንበኞችህ እቃ ለመምረጥ ሲፈልጉ "" ይሄንኑ ከገዛህ ግዛ : ካልፈለክ ሂድ " እያልካቸው ስላማረርካቸው አድመውብህ ነው ::
ከምር እንደምታነበኝማ አዉቃለሁ :: አንድ አንተን ተስፋ በማድረግ ነው የምጽፈውም :: ሌላ ሰው ባያነብ ባለሱቅ ማንበቡ አይቀርም እያልኩ :: እንዳልከኝም ሲመቸኝ እቀጥላለሁ ::ታንክስ ብሮ ::

ሞፊቲ አንተ እኮ እብድ ነህ ... አታጋልጥም አይባልም :: ለነገሩ ከዚህ በላይ ምኑን ታጋልጥ :: ለማንኛውም ለከፈትከው ሶስተኛ ሱቅ እንኳን ደስ ያለህ :: መቼም በባለሱቅ ቀንተህ ነው :: ደግነቱ የተለያየ አገር መሆናችሁ ...አሊያማ ...

ደግሞ ትላንት ትልቅ ንብረት ከኢትዮ አስገብተሀል አሉ : ኮንግራ :: ሞኮኒሳ አልነበረበትም ወይ ? ካለበት አይፋን ጀባ በላታ :: እኔ ሳውቃት ግን እሷ ያንን ጨወታ አትጫወትም :: ከተብካት ማለት ነው በክፉ አመልህ :: ግን አላምንህም : እሷ አታረገውም :: እንክዋን በለጬ ማልጋኖንም ነክታው እንደማታውቅ እመሰክርላታለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Wed Apr 11, 2012 3:34 pm    Post subject: Reply with quote

ጎሳ ጀምሮ በመጥፋት ጊነስ ቡክ ላይ መስፈርህ ላይቀር ..እስኪ ብቅ በልና የነጽጌን ነገር በትንሹም ቢሆን ከትብ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Apr 11, 2012 8:08 pm    Post subject: Reply with quote

ገልብጤ !!!!!!!!
Quote:
ጎሳ ጀምሮ በመጥፋት ጊነስ ቡክ ላይ መስፈርህ ላይቀር ..እስኪ ብቅ በልና የነጽጌን ነገር በትንሹም ቢሆን ከትብ

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ :: ገደልከኝ ነው የምልህ :: ታዝኑልኛላችሁ ብዬ ታሪኬን ባጫውታችሁ መጥፎ በመስራት ተወዳዳሪ እንደሌለው ሰው ለጊነስ ቡክ አሰባችሁኝ ...ቅቅቅቅ ::ከእንግዲህማ .....""ዝም ጭጭ ልበል ከነ ሚስጥሬ ""... ብሏል ዘፋኙ :: ቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 12, 2012 2:05 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ሰዎች :-

ሰላም ራስ ብሩ :-

ከፊርማህ በታች ይህንን የራስ ብሩ ወልደገብርኤል ፎቶግራፍ ማስቀመጥ ትችላለህ ::

ምንጭ :- ራስ ብሩ ወልደገብርኤል በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ የንግሥ በዓል ወቅት በለበሱት የማዕረግ ልብሣቸው የተነሡት ፎቶግራፍ ::

'Gosa' አንዳይሆን ጀምረህ መሐል መንገድ ላይ ትተኸን ጠፋህኮ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes የቁራ መልዕክተኛ አትሁን እንጂ Rolling Eyes እየጠበቅንህ ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Thu Apr 12, 2012 10:41 am    Post subject: Reply with quote

እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ !!!
ውድ ልጅ ተድላ አስበህ ስላደረከው ከልቤ አመሰግንሀለሁ
እንዳልከኝ ከታች ፊርማ ሥር ለማኖር ሞከርኩኝ አልሆነም ምናልባት ከበፊቱ የተለየ ነገር ሊኖር ከቻለ ማታ ስመለስ አንብቤ እሞክራለሁ ::
ከዚ በፊት የራስብሩን ፎቶግራፍ ለማግኘት ብዙ ሞክሬ ነበር አላገኘሁም ታሪካቸውን የያዘ ፅሁፍ ግን ልዑል አስፋው ወሰንን ጠይቄ የሰጡኝን ፖስት አድርጌዋለሁ ::
አሁን አንተ ስላመጣህልን ምስል በድጋሚ ምስጋናዬ ይድረስህ ::
የዚህ ቤት ልጆች መሰባሰብና መገናኘት መሰረቱ ራስብሩ የመሰረቱት ትምህርት ቤት ነው ::
2004 ጀምሮ እስካሁን ድንቅ የፍቅር ታሪክ እስከምናነብበት ጊዜ ድረስ በርካታ ቀደምት ታሪክና ቁምነገሮችን ማግኘት የቻልነው በራስብሩ መሰረትነት ነው

መልካ የፋሲካ በዓል ለሁላችሁም እመኛለሁ

ራስብሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Apr 12, 2012 6:02 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ተድላ ሀይሉ
Quote:
'Gosa' አንዳይሆን ጀምረህ መሐል መንገድ ላይ ትተኸን ጠፋህኮ የቁራ መልዕክተኛ አትሁን እንጂ እየጠበቅንህ ነው
ቅቅቅቅ :: ግድ የለም ተድላ አልጠፋም :: ዘመኑ እኮ አሁን ተሻሽሏል :: ቁራውም እንደ ድሮ አይደለም ቅቅቅ ቢያንስ እነ ሞፊቲ ብቅ የሚሉትን ያህል ተመልሶ መምጣት ጀምሯል :: ባይሆን እንደነ አይፋ በለኝ እንጂ መውቀስህ ላልቀረ ቅቅቅቅ :: እኔማ በሁለት መስመር መዝጋት ስላልፈለኩኝ ነው :: ጥሩ ግዜ ወስጄ እጽፋለሁ ብዬ ነውና እኔ ብቅ እስክል እናንተው አሟሙቁት ቤቱን ::

ራስብሩአችን !!!

Quote:
በርካታ ቀደምት ታሪክና ቁምነገሮችን ማግኘት የቻልነው በራስብሩ መሰረትነት ነው
:: ምን ጥርጥር አለው ብለህ ነው :: መሰረታችን : ሰብሰቢያችን ራስ ብሩ ነው :: ብቅ ስትል እንዴት ደስ ይላል መሰለህ !!! አንተንም እንኳን አብሮ አደረሰን ወንድማችን ::

ባለሱቃችንስ ? ብሽቅ ቀሽም ጉጂ ወም ጣፋጭ ጉጂ የሚሉት ስድቦችህ አቤት እንደናፈቁኝ !!! ጣል ጣል እያደረክ ታዲያ ::

አይፋችን ትንሳዔውን ነው እንዴ የምትጠብቀው ? ሳይሞቱ መነሳት እንደሌለ አልሰማችም መሰለኝ ቅቅቅ ካልጠቀምሽን ለራሽያ እንመልስሻለን ቅቅቅቅ

ኦዶ ሻኪሶ ምነው ጥፍት አልክሳ :: በል ቢያንስ ዶሮውን እንደበላህ ምቀኞቹን ወደ አንድ ጎን አድርገሀቸው ካትብልን ያሳለፍከውን ::

ሞፊቲ : ካንተ ጋርማ ተጣልተናል :: የራስህ ጉዳይ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 12, 2012 6:42 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ !!!
ውድ ልጅ ተድላ አስበህ ስላደረከው ከልቤ አመሰግንሀለሁ
እንዳልከኝ ከታች ፊርማ ሥር ለማኖር ሞከርኩኝ አልሆነም ምናልባት ከበፊቱ የተለየ ነገር ሊኖር ከቻለ ማታ ስመለስ አንብቤ እሞክራለሁ ::
ከዚ በፊት የራስብሩን ፎቶግራፍ ለማግኘት ብዙ ሞክሬ ነበር አላገኘሁም ታሪካቸውን የያዘ ፅሁፍ ግን ልዑል አስፋው ወሰንን ጠይቄ የሰጡኝን ፖስት አድርጌዋለሁ ::
አሁን አንተ ስላመጣህልን ምስል በድጋሚ ምስጋናዬ ይድረስህ ::
የዚህ ቤት ልጆች መሰባሰብና መገናኘት መሰረቱ ራስብሩ የመሰረቱት ትምህርት ቤት ነው ::
2004 ጀምሮ እስካሁን ድንቅ የፍቅር ታሪክ እስከምናነብበት ጊዜ ድረስ በርካታ ቀደምት ታሪክና ቁምነገሮችን ማግኘት የቻልነው በራስብሩ መሰረትነት ነው

ሰላም ራስ ብሩ :-

በሚከተለው አድራሻ ፎቷቸውን ታገኛለህ ::
ራስ ብሩ ወልደገብርኤል

ካስፈለገም 'postimage.org' አንተው ራስህ ማስቀመጥ ትችላለህ :: እኔም 'postimage.org' ላይ አስቀምጨዋለሁ ::

እዚህ ዋርካ ላይ ደግሞ እንደቀድሞው Warka5 ላይ ፎቶግራፎችን ማሣዬት ይቻላል ::

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
መልካ የፋሲካ በዓል ለሁላችሁም እመኛለሁ

ራስብሩ

አሜን ለሁላችንም መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Thu Apr 12, 2012 10:14 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Apr 12, 2012 9:12 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

መልካም የስቅለትና የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ ምኞቴ ነው ::

የጎሳ ታሪክ መጨረሻ የሁሉንም ልብ እንደሰቀለ ይገመታል ::ይህ ልጅ በዚህች አጭር እድሜው
ያጨቀው ታሪክና ገጠመኙ ተዝቆ የማያልቅ ሆኑአል ::እንደአይናፋርነቱና ቄስ እንደመሆኑ መጠን
ሴቶቹም አውቀው ነው መሰል የሱ ልብ ላይ ተንጠልጥለው መጨረሻቸው መጨረሻ አቷል ::

ባለፈው ሰሞን ያነሳንት ጎሳ ክሊኒክ የነበረች ልጅ (እኛ የአዲስ አበባ ልጅ ናት ነበር የምንለው ) መከራችንን
ታበላን ስለነበር በርጫችንን ይዘን የሷን ውበት ማደነቅና የኔ ናት የኔ ናት ማለት ስራችን ሆኖ ነበር ::ይቺ ልጅ የቦረና ልጅ
እንደነበረች ያወኩት አሁን በቅርቡ ጎሳ ሲነግረኝ ነው ::
ይሄ ጉደኛ ልጅ አንድ ወቅት ላይ አዋሳ ሆተል ይዞ
እንደተኛ ከተፍ ትልበታለች ::ድሮ ለያዥ ለገላጋይ ያስቸገረች ልጅ ምንም ወሬ ሳታበዛ ሻወር መውሰድ እፈልጋለው ብላ ልብሷን ፊቱ አወላልቃ የሻወር ቤቱን ሳትዘጋ
ወደመጣጠብያው ስታመራ የጎሳ ልብ ቀጥ ልትል እንደነበር ጎሲቲ አጫውቶኛል ::መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል
ሳናወራ ነበር ጎሳ ስልኩ የተቋረጠው ::ወደፊት ይችን
ጉዳይ ጎሳ እንደሚመለስባት እርግጠኛ መሆን ይቻላል ::
ለማንኛውም ''የሴቶች ጉዳይ '' የሚለውን የነ ፅጌን ርእስ ቁጭት በጉጉት ከሚጠብቁት ውስጥ አንዱ ነኝ ::
አንዳንድ ነገሮች እኔም ስለማላውቃቸውና አንተ በግልህ የዳከርክባቸው ስለሆኑ እንድ አዲስ ማንበብ (ማስታወስ ) ይኖርብኛል ::

ቸር እንሰንብት !!!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 360, 361, 362 ... 381, 382, 383  Next
Page 361 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia