WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
አማራው : ጎሰኝነት ወይስ ሕብረ -ብሔራዊነት

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Fri Apr 13, 2012 6:26 pm    Post subject: አማራው : ጎሰኝነት ወይስ ሕብረ -ብሔራዊነት Reply with quote

አማራው፡ ጎሰኛነት ወይስ ሕብረ -ብሔራዊነት ?

1991 አማጽያኑ ጦርነቱን አሸንፈው አዲስ አበባ ሲገቡ ሰሞን አንድ ከነሱ የሰማሁት ነገር በጊዜው በጣም ገርሞኝ ነበር። በዚያን ጊዜ የደርግ መውደቅ ደስ ያለን ቢሆንም በምትኩ ምን አይነት መንግሥት ይመሠረት ይሆን የሚል ጭንቀት ነበረን። ባጠቃላይ ግን ስለኢሕአዴግና ሻዕቢያ በሚዲያ ስንሰማው የነበረው ነገር ሁሉ ባመዛኙ አሉታዊ ስለነበር የነሱ መምጣት ብዙም አያጓጓንም ነበር ማለት ይቻላል። የደርግ ሚዲያ “ተገንጣዮች” እና “አስገንጣዮች” እያለ በንቀት ከመመልከትና የኢትዮጵያን ሠራዊት ኃያልነት ከማደንቆር በስተቀር ትክክለኛ ገጽታቸውን ለመረዳትና ቢያሸንፉ ወደፊት ሊከተሉ ስለሚችሉ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችሚዛናዊ ግንዛቤ ለመያዝ የሚያስችለንን ጥናትና ትችት አይሰነዝርም ነበር። አማጽያኑ በኦፊሴል የሚናገሩትንና መንግሥት በመረጃ የደረሰበትን የድርጅቶቹን ትክክለኛ ማንነትና ዓላማ ለማስጨበጥ የተደረጉ ጥረቶችን አላስታውስም፡ ለነገሩ ቢኖርም ብዙዎቻችን ለደርግ በነበረን ጥላቻምክንያት ሁሉንም እንደተለመደ ፕሮፓጋንዳ በመቁጠር ለማዳመጥ ዝግጁ አልነበርንም። አቶ ገብረመድኅንና አቶ አብርሃም ያየህ የተሻለ ግንዛቤ የሰጡን ቢሆንም አማጽያኑ በሜዳውም ሆነ በስነ -አእምሮው ጦርነት የበላይነትን እስኪይዙ ድረስ የዘገየ ስለነበር ብዙም ውጤት አልነበረውም። አብዛኛው ሲቪል ሕዝብ ጦርነቱ የደርግ መንግሥትንና አማጽያኑን ብቻ የሚመለከት ይመስለዋል እንጂ በአገሪቱና በእያንዳንዱን ዜጋ ሕይወት ላይ ያለውን አንደምታ በውል የሚያስተውለው አልነበረምና “ገለልተኛ” ሆኖ የሚያይ ነበር። ወታደሩም ቀስ በቀስወደዚህ አይነቱ “ግዴለሽነት” አዘመመና የመንግሥት ለውጥ እንጂ እሱ የማይነካ ስለመሰለው ለውድቀቱ ተዳረገ።

ደርግ አማራጭ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት እንዳይወጣ በሩን ሁሉ በመዝጋቱና ባሳላፍነው የጭቆናና የድንቁርና አስተዳደር በመማረራችን “የመጣ ቢመጣ መቼም ከዚህየባሰ መንግሥት አይመጣም” በሚል ሃሳብና ፀሎትአዲሱን ዘመን ከመጠበቅ በስተቀር ሌላ አቅም አልነበረንም።የሆኖ ሆኖ በበኩሌ (ሌሎችም የኔ አይነት ግምት ያላቸው ብዙዎች እንደነበሩ አስባለሁ ) አዲሶቹ ባለሥልጣናት ትንሽ እየቆዩ እስከምናያቸው ድረስ በምንም አይነት ሁኔታ ኢትዮጵያን ወደ ጎሳ ፖለቲካ ያስገቧታል የሚል ግምትአልነበረኝም። ብዙዎቻችን በዚያ አይነት ሁኔታ “ለጎሳ ፖለቲካ እውር” መሆናችንን ሳስበው ባለፉት ረዘም ያሉ የታሪክ ዓመታት አገሪቱ (ምንም እንኳን በተከታታይ መንግሥታት መራር ጭቆና ያልተለያት ብትሆንም ) ለዘላቂ አንድነትና እኩልነት የሚጠቅም የሕብረ -ብሔራዊነት አስተሳሰብ እያዳበረች እንደነበር እንገነዘባለን። አዲሶቹ ባለሥልጣናት ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ መፍትሔ ብለው በተለሙት ተጻራሪ መንገድ ለመሄድ ጉዞ መጀመራቸውን አበሰሩ።

ይኽንን አዲስ ርዕዮተ ዓለም ያበሰረውን ዜና ነው ከላይ በመግቢያየ ላይ በጣም የገረመኝ ነገር ያልኳችሁ። ኢሕአዴግና ሻዕቢያ ..የገቡ ሰሞን የአፍሪካ አንድነት ስብሰባ በሌላ የአፍሪካ አገር ይደረግ ነበር (አቡጃ ላይ መሰለኝ ) በዚያ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚገኘው ቡድን መሪ የነበሩ ሰው ይመስሉኛል (ካልተሳሳትኩ አቶ ስዩም መሥፍንሊሆኑይችላሉ ) በቢቢሲ ሬዲዮ ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው የማልረሳው ነገር ተናግረው ነበር። ጋዜጠኛው “ከእንግዲህ የመንግሥትን ኃይል መያዛችሁ ነውና የመጀመሪያ ዕቅዳችሁ ምንድን ነው ? ብሎ ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ “የመጀመሪያው ስራችን የአማራውን አከርካሪ መስበር ነው” የሚል ነበር። በበኩሌ በነበረኝ ግንዛቤ ሰውየው ምን ለማለት እንደፈለጉ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። የአማራው አከርካሪ የትኛው ነው በማለት ለማገናዘብ ብሞክርም ፍንጩን ለማግኘት አልቻልኩም። የነበሩት መንግሥታዊ ተቋማት በሙሉ ከነችግራቸውም ቢሆን የኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የዚህ ወይም የዚያኛው ጎሳ አይመስሉኝም ነበር። በክፍለሃገር በአውራጃ በወረዳ በከተማ በቀበሌ የተከፋፈለው አገራችን በሙሉ መንግሥት ለአስተዳደር እንዲያመቸው ቢከፋፍላቸውም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ንብረትና ሕዝቡም የራስህ ወገን እንጂ የአንዱ ወይም የሌላው ጎሳ ስለሆኑ የተለዩ ናቸው ብየ አስቤው አላውቅም ነበር። ሕብረ -ብሔራዊ በሆኑ አገሮች የዚህ አይነት ethnic blind የሆነ ግንዛቤ ላይ ሊደረስ የሚችለው በረዥም የታሪክ ሂደት ነው። በሌላ በኩል ግን ሕዝብን በተወሰኑ መስፈርቶች መሠረት በጎሳ በመከፋፈል የማይሻገሩት የልዩነት ወሰኖችን ለመመሥረት ቀለል ይላል። ኢሕአዴግ በተጀመረው ሂደት ላይ በመቀጠል የቆዩ ድክመቶችን ለማረምና የዲሞክራሲና የእድገት ጥያቄዎቻችንን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲችል የታሪኩን ጎማ ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር በመካከላችን መለያየትን ለማስረጽ መወሰኑ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው።

የኢሕአዴግ አዲስ ፖለቲካ ለሌሎቻችን ድንገት የደረሰ በመሆኑ ለመቃዎም እንኳን መልክ ያለው መልስ አልነበረንም። በተለይም አማራ የተባለው ክፍል ባብዛኛው ከጎሰኛ አስተሳሰብ ያለፈ ግንዛቤ ስለነበረው በዚያ መልክ በጠባቡ የመደራጀት ዝንባሌ አልነበረውም።ብሔረተኞቹ ግን ይኽንን የሕዝብ ሳይኮሎጂ በማጣመም “አማራው ሕብረ -ብሔራዊነት የሚለው እንደለመደው በአንድነት ስም ሌሎቹን ብሔር /ብሔረሰብ /ሕዝብ ለመጨቆን ስለሚፈልግ ነው” በሚል ያወግዙታል። በፕሮፌሰር አስራት የተጀመረው መአሕድበጎሳ ለመደራጀት ፈራ -ተባ እያለ ቢጀምርም ወደ ጠንካራ ድርጅትነት ለመሸጋገር ያልቻለው በውስጡ ጎሳዊ ስሜቱየዳበረ ተከታይ ስላልነበረው ነው። ኢዴፓን የመሠረቱት ልጆች በመጀመሪያ በመአሕድ ከቆዩ በኋላ ትክክለኛው ጎዳና ሕብረ -ብሔራዊ አደረጃጀት ነው ብለው አምነውበት ነው ድርጅቱን ያቋቋሙት። በአጭር ጊዜ ውስጥም ከፍተኛ ታዋቂነትን ለማግኘት የቻሉት አብዛኛው ሰው ሕብረ -ብሔራዊነትን ይደግፍ ስለነበር ነው። ከዚያም መአሕድ ራሱ ወደ ሕብረ -ብሔራዊ ድርጅትነት ተለወጠ። ሆኖም አማራው በጎሳ መደራጀትን ባይመርጥም ሕብረ -ብሔራዊ የሆኑ ድርጅቶችን እንዲጠናከሩ ለማድረግ አልቻለም ወይም አልፈለገም ለዚህም አንድ ማስረጃ ከማንም በላይ እውነተኛ የሕብረ -ብሔራዊነት ፖለቲካን የሚያራምደው ኢዴፓ ከፍጥረቱ ጀምሮ በመአሕድ ሰዎች የአሉባልታ ሰለባ መሆኑ ነው። ድርጅቱ በጎሳ ድርጅቶች በበጎ አለመታየቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ሕብረ -ብሔራዊ ነን በሚሉት እንደ መኢአድና ኢሕአፓ ባሉድርጅቶች ዓይንህን ላፈር ሲባልና እንዲጠፋ ሲወገዝ መቆየቱ “ምን አይነት ፖለቲካ ላገሪቱ ይበጃል ? በሚለው የስትራቴጂ ጥያቄ ላይ የሰፈነውን ብዥታ ያሳያል። ባጠቃላይ እስካሁን ድረስ ላለፉት 20 ዓመታት እንዳየነው ከሆነ የርእዮተ ዓለም ጥያቄውየተቋጨ አይመስልም። በተለይም አማራው ልቡ አጣብቂኝ ሁኔታ ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። በሕብረ -ብሔራዊነት እና በብሔረተኝነት /ጎሰኝነት መካከል በመዋለል ላይ ነው። በዚህም ሳቢያ ይመስለኛል የፖለቲካ ትግሉ ተተብትቦ ወደፊት እንዳይራመድ አንድ ሁነኛ ምክንያት የሆነው።

በኔ እምነት ከሁለት አንዱን መንገድ ባስቸኳይ መወሰን ለሥርዓት ለውጥ የሚደረገውን ትግል ለማገዝ በጣም አስፈላጊ ነው። ጎሰኝነትንና ሕብረ -ብሔራዊነትን ሁለቱንም እኩል ጎን ለጎን ለማስኬድ አይቻልም። ውሳኔያችን ለግባችን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የተመሠረተ ነው። የምናውቃት ኢትዮጵያ በአንድነት እንድትቀጥል የምንሻ ከሆነ የግዴታ ሕብረ -ብሔራዊነትን መምረጥ ይጠቅመናል። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ማለት ሕብረ -ብሔራዊነት ማለት ነውና። ዓላማችን የራስን identity መገንባት ከሆነ ግን ጎሳዊ አደረጃጀትን የሚያራምድ ርእዮት መከተል ነው። አውቀን ልንገባበት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ግን ወደ መገንጠል የሚያመራን መሆኑን ነው።ምክንያቱም ከብዙ አገሮች ታሪክ እንደምንረዳው ethnic movement የመጨረሻ ውጤቱ የራስን ሪፐብሊክ ከመመሥረት ሊዘል አይችልም። ሱዳን የቅርብ ምሳሌ ናት። / ጆን ጋራንግ የሱዳንን አንድነት የሚያጠናክር የፍትሕና የዲሞክራሲ ትግል ሲያደርጉ የቆዩ እንጂ መገንጠል ዓላማቸው አልነበረም፡፡ ከሳቸው ሞት በኋላ የተተኩት የድርጅቱ መሪዎች ግን የደቡብ ሱዳንን የመገንጠል ሂደት በማፋጠን ነጻ ሪፐብሊክ ለማዎጅ በቁ። ኢሕአዴግ ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ጎሰኛ እንቅስቃሴ ለአገር አንድነት ዋስትና የሚሰጥ ሳይሆን የመበታተን ቅድመ -አዋጅ ነው። መተማመን ስለሌለ እንደ ጅብ ጎን ለጎን በጥንቃቄ የሚጓዙበት ሥርዓት ነው። የጎሳ ፖለቲካ ከውጭ ለማስመሰል ከሚያሳየው የዲሞክራትነት ገጽታ ይበልጥ ውስጡን በከፍተኛ የበቀልና የጥላቻ ስሜት የሚናጥ ስለሆነ ብዙ አይነት ጎሳዎች ባሉበት አገር ለአንድነት አይጠቅምም። መለያየት ቢመጣ የማይጨነቅና ብሎም የሚፈልገው በመሆኑ በኃላፊነት ስሜት፡ በትእግስት፡ በመቻቻልና በመከባበር ልዩነቶችን ከመፍታትይልቅ ክሩ እስኪበጠስ ድረስ ማክረርን ይከተላል።

ሕብረ -ብሔራዊነትግን ከድርጅቶች ጠባብ ፍላጎት ይልቅ የሐገርን ጥቅም የማስቀደም ፀጋን ያጎናጽፋል። ይበልጡን በግለሰብ መብቶች በማተኮርየሕግ የበላይነት የነገሠበት፡ የፖለቲካ ልዩነቶችመቻቻልና መከባበር የሰፈነበት፡ አሸናፊ በሰለጠነና በጨዋ የሃሳብ ክርክር የሚለይበት፡ ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ የሚሰሩበት ሥርዓት እንዲፈጠር ለማድረግ ያስችላል። ካለፈው የሕብረ -ብሔራዊ ፓርቲዎች ልምዳችን እንደምናየው ግን ባንድ በኩል ያገሪቱ ሕግና የፖለቲካ ሥርዓት በጎሳ /ብሔር ላይ የተመሰረተ ስለሆነና በሌላ በኩል ብዙዎቹ ፓርቲዎች በዚያው መሠረት የተቀመሩ በመሆናቸው በመጣው ተጽእኖ ምክንያት የሕብረ -ብሔራዊነትን ጣእም ለማጣጣምና ለማጎልበት አልቻልንም።በርግጥ እነ አቶ ስዬና / ነጋሶን የመሰሉ ሰዎች ወደ ሕብረ -ብሔራዊነት መምጣታቸው ታላቅ የድል ፍንጣቂ ቢሆንም ባጠቃላይ ጎሳ -ዘለል አስተሳሰብ የበለጠ አለመጥራቱና አለማደጉ አሳሳቢ ነው። እነ ልደቱ የሚከተሉት መርሕ ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ በእኩል አይን እንዲያዩ ስለሚያስገድድ ይኸኛው ሕዝብ ጠላታችን ነው ብለው ለመፈረጅ አይቻላቸውም። በትግራይ ሕዝብና በወያኔ /ኢሕአዴግ መካከል ልዩነት አለ ሲሉ ሌሎች ያኮርፏቸዋል። ከዚህም አልፎ ልደቱ ኢሕአዴግ እንደ አንድ አገር -በቀል ፓርቲ የተሳሳተ አመለካከት ስለሚያራምድ የምንታገለው ኃይል እንጂ እንደውጪ ወራሪ ጠላት የምናየው አይደለም ሲል የገዥው ፓርቲ ደጋፊና የውስጥ አርበኛ ነው ይባላል። ሕብረ -ብሔራዊነት ማለት የጋራ ኃላፊነት ሸክም ስለሆነ ሕዝብን በሚከፋፍሉ አክራሪ ቅስቀሳዎች እስከመዝለቅ የሚያስኬድ ተስፋ መቁረጥን ቦታ አይሰጠውም። እኔ በዚህ አስተሳሰብ የምናምን ሰዎች ሕብረ -ብሔራዊ የሆኑ ድርጅቶችን ከልብ እንዲደገፉ ለማድረግ ብንችል የተሻለች አገርና ትኖረናለች ብየ አምናለሁ።

በርግጥ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የጎሳ ፖለቲካ በሌሎች አገሮች እንደታየው ሕዝቡን በሚገባ እየከፋፈለና ጎሰኛ ስሜቶችን እያጎለበተ ይገኛል። የጎሳ ፖለቲካ ባለበት ሁሉ አድላዊነት የማይቀር ነው። ምክንያቱም ድርጅቶች ወገንተኛነታቸውን አስቀድመው አውጀው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። በዚህ ለሃብት፡ ለስልጣን፡ ለታሪክ .. ክፍፍልና ሽሚያ በሚደረግ ግብግብ በመካከል የቆዩ የአንድነት ክሮች እየተበጣጠሱ ስለሚሄዱ የጠላትነት ስሜት እያደገ ይሄዳል። ቀድሞ ይታዎቁ የነበሩ የጋራ የሞራል መለኪያዎች ይሸረሸራሉ። እያንዳንዱ ጎሳ ክልሉን ከጸጉረ -ልውጦች /መጤዎች ማጽዳትን ይፈልጋል። ሰሞኑን ከደቡብ ኢትዮጵያ አማራ የሆኑ ሰዎች መባረራቸው አንዳንዶችን አስደንግጧል። ሆኖም ይኽ የማይቀር የጎሳ ፖለቲካ ባሕሪይ መሆኑን ማዎቅያስፈልጋል። ወደፊት ከዚህ የከፋ ታሪክ ሊፈጸም ይችላል። ጎሰኛ ፖሊሲና ሕብረ -ብሔራዊነት ተቻችለው የሚኖሩ አይደሉም። ጎሰኛ እንቅስቃሴ ወቅት እየጠበቀ የሚፈነዳ ገሞራን የተሸከመ ነው።ስለዚህም አንዳንድ አማሮች በጎሳችን መደራጀት አለብን ፡አገሪቱን ማቆየት ባንችል እንኳን ቢያንስ ራሳችንን ለማዳን እንችላለን እያሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ገዢው ፓርቲ የሚያደርስበት ጥቃት ብቻ ሳይሆን ብዙ አማራ ያልሆኑ ጎሳዎችም ለዘመናት በተደረገላቸው ቅስቀሳ ምክንያት በአማራው ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንደያዙ እየታወቀ የአማራው እጁን አጥፎ መቀመጥ መጥፊያውን መጠበቅ ነው ይላሉ። አማራው ተደራጅቶ ራሱን የሚከላከልበት ኃይል መፍጠር እስካልቻለ ድረስ ወደፊት ለመገንጠል በሚደረጉት ጦርነቶች አማራው መራኮቻ ይሆናል ብለው ይሰጋሉ። ከዚህም አልፈው ለመገንጠል የሚፈልጉ ክፍሎች ስላሉና ያገሪቱም ሕግ ይኸንኑ ስለሚፈቅድ ያኔ ሌሎች ሲገነጠሉ አማራው ራሱን ችሎ እንደሐገር ለመቀጠል እንዲችል ከአሁኑ መደራጀት ያስፈልገዋል ብለው ያስባሉ።

የሆኖ ሆኖ ስሜታዊ ጩኸት ከማሰማት ይልቅ በሰከነ ሁኔታ የሚበጀውን ማሰብና በተግባር ለመደራጀት መንቀሳቀስ አዋቂነት ይመስለኛል።
በአንድ በኩል የጎሳ አደረጃጀትን እያወገዙ በሌላ ወገን ደግሞ መፍትሔ ይዞ የሚታገልን ሕብረ -ብሔራዊ ድርጅት ማዳከም ግን ውሉን የሳተና ግቡንም ያልተረዳ ውዥንብር ነው ::

Idea
.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Fri Apr 13, 2012 10:21 pm    Post subject: Re: አማራው : ጎሰኝነት ወይስ ሕብረ -ብሔራዊነት Reply with quote

እንደ አጀንዳ ያነሳኽው ጉዳይ እና አንዳንድ የሰጠሀቸው አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ትክክል ሆነው እግረ መንገድህን (እግረ መንገድም ላይሆን ይችላል ) ግን የሰራኸው ስራ ""እነ ልደቱ "" መሸጥ ነው :: ከልደቱ በላይ ለኢትዮጵያ አንድነት ጥሩ እይታ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉ ::

ከሰነዘርካቸው ሀሳቦች ---

Quote:
የምናውቃት ኢትዮጵያ በአንድነት እንድትቀጥል የምንሻ ከሆነ የግዴታ ሕብረ -ብሔራዊነትን መምረጥ ይጠቅመናል። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ማለት ሕብረ -ብሔራዊነት ማለት ነውና። ዓላማችን የራስን identity መገንባት ከሆነ ግን ጎሳዊ አደረጃጀትን የሚያራምድ ርእዮት መከተል ነው። አውቀን ልንገባበት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ግን ወደ መገንጠል የሚያመራን መሆኑን ነው።ምክንያቱም ከብዙ አገሮች ታሪክ እንደምንረዳው ethnic movement የመጨረሻ ውጤቱ የራስን ሪፐብሊክ ከመመሥረት ሊዘል አይችልም። ሱዳን የቅርብ ምሳሌ ናት። / ጆን ጋራንግ የሱዳንን አንድነት የሚያጠናክር የፍትሕና የዲሞክራሲ ትግል ሲያደርጉ የቆዩ እንጂ መገንጠል ዓላማቸው አልነበረም፡፡ ከሳቸው ሞት በኋላ የተተኩት የድርጅቱ መሪዎች ግን የደቡብ ሱዳንን የመገንጠል ሂደት በማፋጠን ነጻ ሪፐብሊክ ለማዎጅ በቁ። ኢሕአዴግ ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ጎሰኛ እንቅስቃሴ ለአገር አንድነት ዋስትና የሚሰጥ ሳይሆን የመበታተን ቅድመ -አዋጅ ነው። መተማመን ስለሌለ እንደ ጅብ ጎን ለጎን በጥንቃቄ የሚጓዙበት ሥርዓት ነው። የጎሳ ፖለቲካ ከውጭ ለማስመሰል ከሚያሳየው የዲሞክራትነት ገጽታ ይበልጥ ውስጡን በከፍተኛ የበቀልና የጥላቻ ስሜት የሚናጥ ስለሆነ ብዙ አይነት ጎሳዎች ባሉበት አገር ለአንድነት አይጠቅምም። መለያየት ቢመጣ የማይጨነቅና ብሎም የሚፈልገው በመሆኑ በኃላፊነት ስሜት፡ በትእግስት፡ በመቻቻልና በመከባበር ልዩነቶችን ከመፍታትይልቅ ክሩ እስኪበጠስ ድረስ ማክረርን ይከተላል።

የሚለው ትክክለኛ ነው :: የሰርቦችም ታሪክ የሚነግረን ይሄንኑ ነው :: ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ እና ተሞክሮ እንደዛ አይነት ጨለምተኛ አስተሳሰብ ላይ ለመድረስ በቂ ባይሆንም ውሎ አድሮ እና ከውስጥም ከውጪም ከተራገበ እዚያ ደረጃ ላይ መድረሱ አይቀርም ::

ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ይኖሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተወሰደውን ግፈኛ እና ጎሰኛ የፖለቲካ ርምጃ ከዚህ በፊት ከጎሰኛ አስተሳሰብ ጋር ጥል የነበራቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በግድ ገፍቶ (በሲቪክ ደረጃም ይሁን ምን ይሁን ) በቋንቋ እንዲደራጁ የገፋፋ ክስተት እንደሆነ ባምንም ሌላ መሰረታዊ ምክንያት አልነበረውም ማለት ግን አይቻልም :: እንዳልከው በህወሀት የሀያ ዓመት የአገዛዝ ዘመን የአማርኛ ተናጋሪው ህብረተሰብ በተለየ ሁኔታ እንደ ጭራቅ እና ግፈኛ እንዲታይ መደረጉ እና በዛም ምክንያት በተለያየ ጊዜ የደረሰት ነገር የዚህን እሳቤ መሰረት አልጣለም ማለት አይቻለም :: ያለኝን ሚዛናዊነት ሁሉ አሟጥጨ ሳየው ይሄ የህብረተሰብ ክፍል ከማንም የተለየ ምንም ያላገኘ እና የሚያርሳአት ኩርማን መሬት ሳትቀር ጠፍ ብትሆንበት በሀገር ውስጥም ቢሆን ያልታረሰ መሬት ፍለጋ ተሰዶ ከሌሎች ጋር ተስማምቶ ተጋብቶ ተዋልዶ ቋንቋቸውን እየተናገር የኖረ ህዝብ ነው :: ወደ ዘር ፖለቲካ ሳይገባ ለዚህን ያህል ዘመን የኖረበትም ምክንያት ዘሩን ብቻ ሳይሆን እምነትም ጭምር ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የተወራረሰ ነው :: በህወሀት እንደተዘራው የዘር ጥላቻ ብዙ ጉዳይ ያልደረሰውም ለዚህ ነው :: ሰሞኑንም በተወሰደው ርምጃ ከመስተዳድሩ አካላት በስተቀር ህዝቡ በሀዘን እና በለቅሶ እንደሸኛቸው ነው የተሰማው ::

እንደገባኝ የተፈናቀለው ህዝብ የተወሰደበት ርምጃ ተመሳስሎት እና ተዋልዶት ሲኖር ከነበረው የህብረተሰብ ክፍል እንዳልሆነ በውል ተገንዝቧል :: በሌላ በኩል ደሞ ህወሀት የዘረጋውን የመስተዳድር መዋቅር ተጠቅሞ ርምጃውን እንዳስወሰደ ተረድቷል :: እንደ አዲስ በብሄር እንደራጂ የሚለውም ነገር እንደገባኝ ለህወሀት መልስ እንጂ ከሌሎች ዝህቦች ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም :: ሆኖም ግን ትክክል ነው አይደለም የሚል ጥያቄ ይነሳል :: ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው :: መመጠን ያስፈልጋል ነገሩን :: የቋንቋ ተናጋሪነቱ ስሜት ከሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር የነበረውን የአንድነት ( በመጋባት በመዋለድ በጋራ በማመን ) እና ስብጥር በሚጎዳ እና በሚያስረሳ መልኩ መሆን የለበትም :: አስተዋይ ባልሆኑ ሰዎች እና ተከታዮች ከገባ ነገሩ እንደተጠቆመው አደገኛነቱ ያመዝናል :: ኢትዮጵያንም እንደሚያድንልን እርግጠኛ አይደለሁም :: ነገሩ በጣም ስትራቴጂካዊ አስተሳሰብን የሚጠይቅ ነው :: ብልህነትን የሚጠይቅ ነው :: ፍትሀዊነትን እና አርቆ አሳቢነትን የሚጠይቅ ነው ::

ህወሀት እንደብሄር ለመኖር የሚያስችለውን አብዛኛውን ቅድመ ዝግጂት የጨረሰ ስለመሰለው ( ከኢኮኖሚ ጀምሮ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ሀይሉን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በሚስል መልክ በማደራጀቱ ) ለወደፊት አደገኛ ሁኔታ ይደቅኑብኛል ብሎ የሚያስባችውን ነገሮች በማያንሰራሩበት መልኩ ማምከን ይፈልጋል :: እየሞከረውም ነው :: በግልጽ ደሞ እንቅፋት የሚሆንበት በኢትዮጵያዊነት የሚደራጀው ሀይል ነው :: ህወሀት ግን በዚህም ሀይል ውስጥ የሚያየው ብሄር ነው :: በአነሳሺነት እና በባለቤትነት የሚፈራውም ደሞ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ነው :: ነባራዊ ሁኔታው ግን ሌላ ነው :: ዛሬ ኦነግ በስል ያለ ፖለቲካው አካሄድ በመምረጥ በኢትዮጵያዊነት ላይ የይገባኛል ጥያቄ እያነሳ ነው :: ከሌሎች ጋር በመተባበር ከባይተዋርነት ወደ መሪነት እና ባለቤትነት ተሸጋግሯል :: ሰሞኑን ራሱ ( በእንግሊኛም ቢሆን ) ህወህት በደቡብ ኢትዮጵያ የወሰደውን ርምጃ ኮንኗል :: አውግዞታል :: እንዲህ ያለ ነገር እየተፈጠረ ባለበት ሁኔታ በህቤር እንደራጂ የሚለውን አስተሳሰብ አጠንክሮ መያዝ አያስፈልግም ባይ ነኝ እኔም :: ከዛ ውጪ ግን ህወሀት እንደወራሪ ሀይል መታይት የለበትም የሚለው ፈሊጥ አይገባኝም :: ከዚያ በላይ ነው :: በዚያም መንፈስ ነው ነገሩን ሁሉ ህወህት ላይ እንዲጠመጠም አድርጎ መስራት የሚያስፈልገው ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::ቀደምት እንደጻፈ(ች)ው:
አማራው፡ ጎሰኛነት ወይስ ሕብረ -ብሔራዊነት ?

1991 አማጽያኑ ጦርነቱን አሸንፈው አዲስ አበባ ሲገቡ ሰሞን አንድ ከነሱ የሰማሁት ነገር በጊዜው በጣም ገርሞኝ ነበር። በዚያን ጊዜ የደርግ መውደቅ ደስ ያለን ቢሆንም በምትኩ ምን አይነት መንግሥት ይመሠረት ይሆን የሚል ጭንቀት ነበረን። ባጠቃላይ ግን ስለኢሕአዴግና ሻዕቢያ በሚዲያ ስንሰማው የነበረው ነገር ሁሉ ባመዛኙ አሉታዊ ስለነበር የነሱ መምጣት ብዙም አያጓጓንም ነበር ማለት ይቻላል። የደርግ ሚዲያ “ተገንጣዮች” እና “አስገንጣዮች” እያለ በንቀት ከመመልከትና የኢትዮጵያን ሠራዊት ኃያልነት ከማደንቆር በስተቀር ትክክለኛ ገጽታቸውን ለመረዳትና ቢያሸንፉ ወደፊት ሊከተሉ ስለሚችሉ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችሚዛናዊ ግንዛቤ ለመያዝ የሚያስችለንን ጥናትና ትችት አይሰነዝርም ነበር። አማጽያኑ በኦፊሴል የሚናገሩትንና መንግሥት በመረጃ የደረሰበትን የድርጅቶቹን ትክክለኛ ማንነትና ዓላማ ለማስጨበጥ የተደረጉ ጥረቶችን አላስታውስም፡ ለነገሩ ቢኖርም ብዙዎቻችን ለደርግ በነበረን ጥላቻምክንያት ሁሉንም እንደተለመደ ፕሮፓጋንዳ በመቁጠር ለማዳመጥ ዝግጁ አልነበርንም። አቶ ገብረመድኅንና አቶ አብርሃም ያየህ የተሻለ ግንዛቤ የሰጡን ቢሆንም አማጽያኑ በሜዳውም ሆነ በስነ -አእምሮው ጦርነት የበላይነትን እስኪይዙ ድረስ የዘገየ ስለነበር ብዙም ውጤት አልነበረውም። አብዛኛው ሲቪል ሕዝብ ጦርነቱ የደርግ መንግሥትንና አማጽያኑን ብቻ የሚመለከት ይመስለዋል እንጂ በአገሪቱና በእያንዳንዱን ዜጋ ሕይወት ላይ ያለውን አንደምታ በውል የሚያስተውለው አልነበረምና “ገለልተኛ” ሆኖ የሚያይ ነበር። ወታደሩም ቀስ በቀስወደዚህ አይነቱ “ግዴለሽነት” አዘመመና የመንግሥት ለውጥ እንጂ እሱ የማይነካ ስለመሰለው ለውድቀቱ ተዳረገ።

ደርግ አማራጭ የሆነ የፖለቲካ ድርጅት እንዳይወጣ በሩን ሁሉ በመዝጋቱና ባሳላፍነው የጭቆናና የድንቁርና አስተዳደር በመማረራችን “የመጣ ቢመጣ መቼም ከዚህየባሰ መንግሥት አይመጣም” በሚል ሃሳብና ፀሎትአዲሱን ዘመን ከመጠበቅ በስተቀር ሌላ አቅም አልነበረንም።የሆኖ ሆኖ በበኩሌ (ሌሎችም የኔ አይነት ግምት ያላቸው ብዙዎች እንደነበሩ አስባለሁ ) አዲሶቹ ባለሥልጣናት ትንሽ እየቆዩ እስከምናያቸው ድረስ በምንም አይነት ሁኔታ ኢትዮጵያን ወደ ጎሳ ፖለቲካ ያስገቧታል የሚል ግምትአልነበረኝም። ብዙዎቻችን በዚያ አይነት ሁኔታ “ለጎሳ ፖለቲካ እውር” መሆናችንን ሳስበው ባለፉት ረዘም ያሉ የታሪክ ዓመታት አገሪቱ (ምንም እንኳን በተከታታይ መንግሥታት መራር ጭቆና ያልተለያት ብትሆንም ) ለዘላቂ አንድነትና እኩልነት የሚጠቅም የሕብረ -ብሔራዊነት አስተሳሰብ እያዳበረች እንደነበር እንገነዘባለን። አዲሶቹ ባለሥልጣናት ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ መፍትሔ ብለው በተለሙት ተጻራሪ መንገድ ለመሄድ ጉዞ መጀመራቸውን አበሰሩ።

ይኽንን አዲስ ርዕዮተ ዓለም ያበሰረውን ዜና ነው ከላይ በመግቢያየ ላይ በጣም የገረመኝ ነገር ያልኳችሁ። ኢሕአዴግና ሻዕቢያ ..የገቡ ሰሞን የአፍሪካ አንድነት ስብሰባ በሌላ የአፍሪካ አገር ይደረግ ነበር (አቡጃ ላይ መሰለኝ ) በዚያ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚገኘው ቡድን መሪ የነበሩ ሰው ይመስሉኛል (ካልተሳሳትኩ አቶ ስዩም መሥፍንሊሆኑይችላሉ ) በቢቢሲ ሬዲዮ ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው የማልረሳው ነገር ተናግረው ነበር። ጋዜጠኛው “ከእንግዲህ የመንግሥትን ኃይል መያዛችሁ ነውና የመጀመሪያ ዕቅዳችሁ ምንድን ነው ? ብሎ ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ “የመጀመሪያው ስራችን የአማራውን አከርካሪ መስበር ነው” የሚል ነበር። በበኩሌ በነበረኝ ግንዛቤ ሰውየው ምን ለማለት እንደፈለጉ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። የአማራው አከርካሪ የትኛው ነው በማለት ለማገናዘብ ብሞክርም ፍንጩን ለማግኘት አልቻልኩም። የነበሩት መንግሥታዊ ተቋማት በሙሉ ከነችግራቸውም ቢሆን የኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የዚህ ወይም የዚያኛው ጎሳ አይመስሉኝም ነበር። በክፍለሃገር በአውራጃ በወረዳ በከተማ በቀበሌ የተከፋፈለው አገራችን በሙሉ መንግሥት ለአስተዳደር እንዲያመቸው ቢከፋፍላቸውም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ንብረትና ሕዝቡም የራስህ ወገን እንጂ የአንዱ ወይም የሌላው ጎሳ ስለሆኑ የተለዩ ናቸው ብየ አስቤው አላውቅም ነበር። ሕብረ -ብሔራዊ በሆኑ አገሮች የዚህ አይነት ethnic blind የሆነ ግንዛቤ ላይ ሊደረስ የሚችለው በረዥም የታሪክ ሂደት ነው። በሌላ በኩል ግን ሕዝብን በተወሰኑ መስፈርቶች መሠረት በጎሳ በመከፋፈል የማይሻገሩት የልዩነት ወሰኖችን ለመመሥረት ቀለል ይላል። ኢሕአዴግ በተጀመረው ሂደት ላይ በመቀጠል የቆዩ ድክመቶችን ለማረምና የዲሞክራሲና የእድገት ጥያቄዎቻችንን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲችል የታሪኩን ጎማ ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር በመካከላችን መለያየትን ለማስረጽ መወሰኑ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው።

የኢሕአዴግ አዲስ ፖለቲካ ለሌሎቻችን ድንገት የደረሰ በመሆኑ ለመቃዎም እንኳን መልክ ያለው መልስ አልነበረንም። በተለይም አማራ የተባለው ክፍል ባብዛኛው ከጎሰኛ አስተሳሰብ ያለፈ ግንዛቤ ስለነበረው በዚያ መልክ በጠባቡ የመደራጀት ዝንባሌ አልነበረውም።ብሔረተኞቹ ግን ይኽንን የሕዝብ ሳይኮሎጂ በማጣመም “አማራው ሕብረ -ብሔራዊነት የሚለው እንደለመደው በአንድነት ስም ሌሎቹን ብሔር /ብሔረሰብ /ሕዝብ ለመጨቆን ስለሚፈልግ ነው” በሚል ያወግዙታል። በፕሮፌሰር አስራት የተጀመረው መአሕድበጎሳ ለመደራጀት ፈራ -ተባ እያለ ቢጀምርም ወደ ጠንካራ ድርጅትነት ለመሸጋገር ያልቻለው በውስጡ ጎሳዊ ስሜቱየዳበረ ተከታይ ስላልነበረው ነው። ኢዴፓን የመሠረቱት ልጆች በመጀመሪያ በመአሕድ ከቆዩ በኋላ ትክክለኛው ጎዳና ሕብረ -ብሔራዊ አደረጃጀት ነው ብለው አምነውበት ነው ድርጅቱን ያቋቋሙት። በአጭር ጊዜ ውስጥም ከፍተኛ ታዋቂነትን ለማግኘት የቻሉት አብዛኛው ሰው ሕብረ -ብሔራዊነትን ይደግፍ ስለነበር ነው። ከዚያም መአሕድ ራሱ ወደ ሕብረ -ብሔራዊ ድርጅትነት ተለወጠ። ሆኖም አማራው በጎሳ መደራጀትን ባይመርጥም ሕብረ -ብሔራዊ የሆኑ ድርጅቶችን እንዲጠናከሩ ለማድረግ አልቻለም ወይም አልፈለገም ለዚህም አንድ ማስረጃ ከማንም በላይ እውነተኛ የሕብረ -ብሔራዊነት ፖለቲካን የሚያራምደው ኢዴፓ ከፍጥረቱ ጀምሮ በመአሕድ ሰዎች የአሉባልታ ሰለባ መሆኑ ነው። ድርጅቱ በጎሳ ድርጅቶች በበጎ አለመታየቱ የሚጠበቅ ቢሆንም ሕብረ -ብሔራዊ ነን በሚሉት እንደ መኢአድና ኢሕአፓ ባሉድርጅቶች ዓይንህን ላፈር ሲባልና እንዲጠፋ ሲወገዝ መቆየቱ “ምን አይነት ፖለቲካ ላገሪቱ ይበጃል ? በሚለው የስትራቴጂ ጥያቄ ላይ የሰፈነውን ብዥታ ያሳያል። ባጠቃላይ እስካሁን ድረስ ላለፉት 20 ዓመታት እንዳየነው ከሆነ የርእዮተ ዓለም ጥያቄውየተቋጨ አይመስልም። በተለይም አማራው ልቡ አጣብቂኝ ሁኔታ ላይ እንደተንጠለጠለ ነው። በሕብረ -ብሔራዊነት እና በብሔረተኝነት /ጎሰኝነት መካከል በመዋለል ላይ ነው። በዚህም ሳቢያ ይመስለኛል የፖለቲካ ትግሉ ተተብትቦ ወደፊት እንዳይራመድ አንድ ሁነኛ ምክንያት የሆነው።

በኔ እምነት ከሁለት አንዱን መንገድ ባስቸኳይ መወሰን ለሥርዓት ለውጥ የሚደረገውን ትግል ለማገዝ በጣም አስፈላጊ ነው። ጎሰኝነትንና ሕብረ -ብሔራዊነትን ሁለቱንም እኩል ጎን ለጎን ለማስኬድ አይቻልም። ውሳኔያችን ለግባችን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የተመሠረተ ነው። የምናውቃት ኢትዮጵያ በአንድነት እንድትቀጥል የምንሻ ከሆነ የግዴታ ሕብረ -ብሔራዊነትን መምረጥ ይጠቅመናል። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ማለት ሕብረ -ብሔራዊነት ማለት ነውና። ዓላማችን የራስን identity መገንባት ከሆነ ግን ጎሳዊ አደረጃጀትን የሚያራምድ ርእዮት መከተል ነው። አውቀን ልንገባበት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር ግን ወደ መገንጠል የሚያመራን መሆኑን ነው።ምክንያቱም ከብዙ አገሮች ታሪክ እንደምንረዳው ethnic movement የመጨረሻ ውጤቱ የራስን ሪፐብሊክ ከመመሥረት ሊዘል አይችልም። ሱዳን የቅርብ ምሳሌ ናት። / ጆን ጋራንግ የሱዳንን አንድነት የሚያጠናክር የፍትሕና የዲሞክራሲ ትግል ሲያደርጉ የቆዩ እንጂ መገንጠል ዓላማቸው አልነበረም፡፡ ከሳቸው ሞት በኋላ የተተኩት የድርጅቱ መሪዎች ግን የደቡብ ሱዳንን የመገንጠል ሂደት በማፋጠን ነጻ ሪፐብሊክ ለማዎጅ በቁ። ኢሕአዴግ ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ጎሰኛ እንቅስቃሴ ለአገር አንድነት ዋስትና የሚሰጥ ሳይሆን የመበታተን ቅድመ -አዋጅ ነው። መተማመን ስለሌለ እንደ ጅብ ጎን ለጎን በጥንቃቄ የሚጓዙበት ሥርዓት ነው። የጎሳ ፖለቲካ ከውጭ ለማስመሰል ከሚያሳየው የዲሞክራትነት ገጽታ ይበልጥ ውስጡን በከፍተኛ የበቀልና የጥላቻ ስሜት የሚናጥ ስለሆነ ብዙ አይነት ጎሳዎች ባሉበት አገር ለአንድነት አይጠቅምም። መለያየት ቢመጣ የማይጨነቅና ብሎም የሚፈልገው በመሆኑ በኃላፊነት ስሜት፡ በትእግስት፡ በመቻቻልና በመከባበር ልዩነቶችን ከመፍታትይልቅ ክሩ እስኪበጠስ ድረስ ማክረርን ይከተላል።

ሕብረ -ብሔራዊነትግን ከድርጅቶች ጠባብ ፍላጎት ይልቅ የሐገርን ጥቅም የማስቀደም ፀጋን ያጎናጽፋል። ይበልጡን በግለሰብ መብቶች በማተኮርየሕግ የበላይነት የነገሠበት፡ የፖለቲካ ልዩነቶችመቻቻልና መከባበር የሰፈነበት፡ አሸናፊ በሰለጠነና በጨዋ የሃሳብ ክርክር የሚለይበት፡ ድርጅቶችና ፖለቲከኞች ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ የሚሰሩበት ሥርዓት እንዲፈጠር ለማድረግ ያስችላል። ካለፈው የሕብረ -ብሔራዊ ፓርቲዎች ልምዳችን እንደምናየው ግን ባንድ በኩል ያገሪቱ ሕግና የፖለቲካ ሥርዓት በጎሳ /ብሔር ላይ የተመሰረተ ስለሆነና በሌላ በኩል ብዙዎቹ ፓርቲዎች በዚያው መሠረት የተቀመሩ በመሆናቸው በመጣው ተጽእኖ ምክንያት የሕብረ -ብሔራዊነትን ጣእም ለማጣጣምና ለማጎልበት አልቻልንም።በርግጥ እነ አቶ ስዬና / ነጋሶን የመሰሉ ሰዎች ወደ ሕብረ -ብሔራዊነት መምጣታቸው ታላቅ የድል ፍንጣቂ ቢሆንም ባጠቃላይ ጎሳ -ዘለል አስተሳሰብ የበለጠ አለመጥራቱና አለማደጉ አሳሳቢ ነው። እነ ልደቱ የሚከተሉት መርሕ ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ በእኩል አይን እንዲያዩ ስለሚያስገድድ ይኸኛው ሕዝብ ጠላታችን ነው ብለው ለመፈረጅ አይቻላቸውም። በትግራይ ሕዝብና በወያኔ /ኢሕአዴግ መካከል ልዩነት አለ ሲሉ ሌሎች ያኮርፏቸዋል። ከዚህም አልፎ ልደቱ ኢሕአዴግ እንደ አንድ አገር -በቀል ፓርቲ የተሳሳተ አመለካከት ስለሚያራምድ የምንታገለው ኃይል እንጂ እንደውጪ ወራሪ ጠላት የምናየው አይደለም ሲል የገዥው ፓርቲ ደጋፊና የውስጥ አርበኛ ነው ይባላል። ሕብረ -ብሔራዊነት ማለት የጋራ ኃላፊነት ሸክም ስለሆነ ሕዝብን በሚከፋፍሉ አክራሪ ቅስቀሳዎች እስከመዝለቅ የሚያስኬድ ተስፋ መቁረጥን ቦታ አይሰጠውም። እኔ በዚህ አስተሳሰብ የምናምን ሰዎች ሕብረ -ብሔራዊ የሆኑ ድርጅቶችን ከልብ እንዲደገፉ ለማድረግ ብንችል የተሻለች አገርና ትኖረናለች ብየ አምናለሁ።

በርግጥ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የጎሳ ፖለቲካ በሌሎች አገሮች እንደታየው ሕዝቡን በሚገባ እየከፋፈለና ጎሰኛ ስሜቶችን እያጎለበተ ይገኛል። የጎሳ ፖለቲካ ባለበት ሁሉ አድላዊነት የማይቀር ነው። ምክንያቱም ድርጅቶች ወገንተኛነታቸውን አስቀድመው አውጀው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። በዚህ ለሃብት፡ ለስልጣን፡ ለታሪክ .. ክፍፍልና ሽሚያ በሚደረግ ግብግብ በመካከል የቆዩ የአንድነት ክሮች እየተበጣጠሱ ስለሚሄዱ የጠላትነት ስሜት እያደገ ይሄዳል። ቀድሞ ይታዎቁ የነበሩ የጋራ የሞራል መለኪያዎች ይሸረሸራሉ። እያንዳንዱ ጎሳ ክልሉን ከጸጉረ -ልውጦች /መጤዎች ማጽዳትን ይፈልጋል። ሰሞኑን ከደቡብ ኢትዮጵያ አማራ የሆኑ ሰዎች መባረራቸው አንዳንዶችን አስደንግጧል። ሆኖም ይኽ የማይቀር የጎሳ ፖለቲካ ባሕሪይ መሆኑን ማዎቅያስፈልጋል። ወደፊት ከዚህ የከፋ ታሪክ ሊፈጸም ይችላል። ጎሰኛ ፖሊሲና ሕብረ -ብሔራዊነት ተቻችለው የሚኖሩ አይደሉም። ጎሰኛ እንቅስቃሴ ወቅት እየጠበቀ የሚፈነዳ ገሞራን የተሸከመ ነው።ስለዚህም አንዳንድ አማሮች በጎሳችን መደራጀት አለብን ፡አገሪቱን ማቆየት ባንችል እንኳን ቢያንስ ራሳችንን ለማዳን እንችላለን እያሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ገዢው ፓርቲ የሚያደርስበት ጥቃት ብቻ ሳይሆን ብዙ አማራ ያልሆኑ ጎሳዎችም ለዘመናት በተደረገላቸው ቅስቀሳ ምክንያት በአማራው ላይ የተሳሳተ አመለካከት እንደያዙ እየታወቀ የአማራው እጁን አጥፎ መቀመጥ መጥፊያውን መጠበቅ ነው ይላሉ። አማራው ተደራጅቶ ራሱን የሚከላከልበት ኃይል መፍጠር እስካልቻለ ድረስ ወደፊት ለመገንጠል በሚደረጉት ጦርነቶች አማራው መራኮቻ ይሆናል ብለው ይሰጋሉ። ከዚህም አልፈው ለመገንጠል የሚፈልጉ ክፍሎች ስላሉና ያገሪቱም ሕግ ይኸንኑ ስለሚፈቅድ ያኔ ሌሎች ሲገነጠሉ አማራው ራሱን ችሎ እንደሐገር ለመቀጠል እንዲችል ከአሁኑ መደራጀት ያስፈልገዋል ብለው ያስባሉ።

የሆኖ ሆኖ ስሜታዊ ጩኸት ከማሰማት ይልቅ በሰከነ ሁኔታ የሚበጀውን ማሰብና በተግባር ለመደራጀት መንቀሳቀስ አዋቂነት ይመስለኛል።
በአንድ በኩል የጎሳ አደረጃጀትን እያወገዙ በሌላ ወገን ደግሞ መፍትሔ ይዞ የሚታገልን ሕብረ -ብሔራዊ ድርጅት ማዳከም ግን ውሉን የሳተና ግቡንም ያልተረዳ ውዥንብር ነው ::

Idea
.

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Sat Apr 14, 2012 12:51 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ይኽንን አዲስ ርዕዮተ ዓለም ያበሰረውን ዜና ነው ከላይ በመግቢያየ ላይ በጣም የገረመኝ ነገር ያልኳችሁ። ኢሕአዴግና ሻዕቢያ . .የገቡ ሰሞን የአፍሪካ አንድነት ስብሰባ በሌላ የአፍሪካ አገር ይደረግ ነበር (አቡጃ ላይ መሰለኝ ) በዚያ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚገኘው ቡድን መሪ የነበሩ ሰው ይመስሉኛል (ካልተሳሳትኩ አቶ ስዩም መሥፍንሊሆኑይችላሉ ) በቢቢሲ ሬዲዮ ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው የማልረሳው ነገር ተናግረው ነበር። ጋዜጠኛው “ከእንግዲህ የመንግሥትን ኃይል መያዛችሁ ነውና የመጀመሪያ ዕቅዳችሁ ምንድን ነው ? ብሎ ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ የመጀመሪያው ስራችን የአማራውን አከርካሪ መስበር ነው” የሚል ነበር። በበኩሌ በነበረኝ ግንዛቤ ሰውየው ምን ለማለት እንደፈለጉ ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። የአማራው አከርካሪ የትኛው ነው በማለት ለማገናዘብ ብሞክርም ፍንጩን ለማግኘት አልቻልኩም። የነበሩት መንግሥታዊ ተቋማት በሙሉ ከነችግራቸውም ቢሆን የኢትዮጵያዊያን ሁሉ እንጂ የዚህ ወይም የዚያኛው ጎሳ አይመስሉኝም ነበር። በክፍለሃገር በአውራጃ በወረዳ በከተማ በቀበሌ የተከፋፈለው አገራችን በሙሉ መንግሥት ለአስተዳደር እንዲያመቸው ቢከፋፍላቸውም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ንብረትና ሕዝቡም የራስህ ወገን እንጂ የአንዱ ወይም የሌላው ጎሳ ስለሆኑ የተለዩ ናቸው ብየ አስቤው አላውቅም ነበር። ሕብረ -ብሔራዊ በሆኑ አገሮች የዚህ አይነት ethnic blind የሆነ ግንዛቤ ላይ ሊደረስ የሚችለው በረዥም የታሪክ ሂደት ነው። በሌላ በኩል ግን ሕዝብን በተወሰኑ መስፈርቶች መሠረት በጎሳ በመከፋፈል የማይሻገሩት የልዩነት ወሰኖችን ለመመሥረት ቀለል ይላል። ኢሕአዴግ በተጀመረው ሂደት ላይ በመቀጠል የቆዩ ድክመቶችን ለማረምና የዲሞክራሲና የእድገት ጥያቄዎቻችንን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሲችል የታሪኩን ጎማ ወደ ሌላ አቅጣጫ በማዞር በመካከላችን መለያየትን ለማስረጽ መወሰኑ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው።

ሰላም

የልደቱን ስም ከመጥቀስህ ውጪ ቆንጆ ጽሁፍ ነው ያቀረብከው :: ልደቱ ከመሪነቱ የወረደ መስሎኝ ... እንደፑቲን ከኋላ ሆኖ እያሽከረከረ ይሆን እንዴ Question Wink ለማንኛውም ለወደፊት ትምህርት እንዲሆንህ ... ብዙ ሰው ልደቱን እንደማይደግፈው እያወቅክና ... ስልጣኑን ለሌላ አሳልፎ እያለ ... "እነ ልደቱ " እያልክ ... ዛሬም የግል ንብረትነቱ እንዳለ ነው እንዴ ከምታስብለን ... "እነ ሙሼ " ማለት ይልመድብህ Laughing

ወደ ዋናው ነጥብ ስመለስ

ስንቶቻችሁ አንብባችሁት ይሆናል አላውቅም :: ነገር ግን ከላይ የጻፍካቸው ነጥቦች ትክክል እንደሆኑ የሚያረጋግጥልን አንድ ሊነበብ የሚገባ ድንቅ መጽሀፍ አለ :: መጽሀፉ የወያኔን "ደርቲ ፖለቲክስ " ከበርሀ ጀምሮ እስከ ምርጫ 97 ድረስ በሰፊው ይዳስሳል :: መጽሀፉን ማንበብ እነ መለስ የሚጫወቱት ቁማር ከመሰረቱ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ይረዳል :: የትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ባህልና ስነልቦና (ለዘፈን /ጓይላ ያለውን ስሜት ሳይቀር ) እንዴት exploit አድርገው ጥቅም ላይ እንደሚያውሉት ኢን ዴፕዝ ያሳያል :: በትክክል ፖለቲከኛ ከሆንክና የትግል አቅጣጫህ ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስጨንቅህ ከሆነ ይህን መጽሀፍ ማንበብ ይኖርብሀል :: የወያኔ የፖለቲካ ሂደት ወደፊት ምን ሊመስል ይችላል ... የሚለው የሚያስጨንቀው ካለም ... ይህን መጽሀፍ ያንብበው :: መጽሀፉ "ትሬንዱን " ያሳያችኋል :: ትሬንዱን ተከትሎ ፕሪዲክት ማድረግ ደግሞ የፖለቲከኞች ስራ ይሆናል ::

http://img2.imagesbn.com/images/141480000/141489187.JPG

ይህን መጽሀፍ ለመጠቆም ያነሳሳኝ በተለይ በቀይ ያቀለምኩት ጽሁፍህ ነው :: ሰብ -ታይትሉ ላይ እንደምታየው "The making of Enemies and Allies ..." ነው የሚለው :: ስዩም ወዶ አይደለም እንደዛ ያለው ... በርሀ ጠጥቶት የመጣ የቅስቀሳቸው ውጤት ነው ::

ጥቂት ከመጽሀፉ ያገኘኋቸውን ነጥቦች ላካፍላችሁ ...

1. በርሀ እያሉ ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበት መፈክር "አማራ የትግራይ ......... ጠላት " እንደሆነ የሚያሳዩና ለቅስቀሳ የሚጠቀሙባቸው ዘፈኖች , ድራማዎች , የፕሮፓጋንዳ ናሬቲቮች ወዘተ ለብቀላ የሚያነሳሱ እንደነበሩ

2. የህውሓት ታጋዮች ትግራይን 80/81 አካባቢ ከደርግ አገዛዝ "ነጻ ካወጡ " ብኋላ ትግላችንን ጨርሰናል የሚል አቋም እንደነበራቸው

3. ባልታወቀ ምክንያትና በጥቂት የአመራሩ ሰዎች ተነሳሽነት ... ትግሉ በትግራይ ብቻ ሳይወሰን ... ገፍቶ ኢትዮጵያንም እንዲያዳርስ አዲስ ቅስቀሳ መደረጉ ... :: ግራ የገባው ታጋይ ... እንዴት ለጠላታችን ነጻነት እንታገላለን ብሎ ቢጠይቅ ... መፈክሮች ተለውጠው ... አማራው ሳይሆን ገዢው መደብ ነው ጠላትህ በሚል የቅስቀሳ ፕሮፓጋንዳ መተካቱን ... በወቅቱ የታገልነው ለትግራይ ነው ከዚህ በላይ አንታገልም ያሉ በርካታ ታጋዮች ... መድረሻቸው እንዳልታወቀ :: ወዘተ

4. ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ እቅዳቸው ... "Deconstructing and reconstructing Ethiopia/History" ... እንደነበር :: ዲኮንስትራክሽኑ እንዴት እንደተገባደደ (ናሽናል ሲይምቦሎች እንዴት እንደሚያጠፏቸው ) እና ... ሪኮንስትራክሽኑ ምን ምን እንደሚያካትት

5. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ... አማራውን ወደ ... ........ . ወዳጅነት እንዴት እንደቀየሩት ... ከጦርነቱ ብኋላ ነገሮችን ወደ ነበሩበት እንዴት እንደመለሷቸው ... በተለይ 97 አካባቢ

6, ......... ብዙ ብዙ ነገሮችን ይዟል ::

የወያኔን ስራ ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ስነ ልቦናንም በደንብ ይዳስሳል :: ሁላ ቅስቀሳ ተደርጎም ... ህዝቡ ውስጥ የተለየ ነገር እንደማይታይ ... ትግሬው ለኤርትራዊውና ለአማራው .... አማራው ለትግሬውና ለኤርትራዊው ... ኤርትራዊው ለአማራውና ለትግሬው ያላቸውን አመለካከት ... ከህዝቡ በተገኙና በሚያስደንቁ ናሬቲቮች ተገልጿል :: ... እንዲህውም በመሀከል መጠቀሚያ የሆኑት ኦሮሞ , ጋምቤላ , ሶማሊ , ወላይታ , ወዘተ ተጠቅሷል :: ባጭሩ ....... የማይዳስሰው ነገር የለም ብል ይቀላል :: የዘር ፖለቲካን እስከተመለከተ ድረስ ::

አይደንቲቲ ፖለቲክስ ... ጓዳቸው ድረስ ገብታ (ግማሽ ኤርትራዊ , ኢትዮጵያዊ በሚል ስሜት ) ... እነሱኑ ራሱ እርስ በእርስ እንዴት ልትከፋፍላቸው እንደደረሰችም አለበት ::

ባጠቃላይ መጽሀፉን አንብቡትና በርካታ ጭብጦችን ታገኛላችሁ :: ስርዓቱን ለመቀልበስና ነጻነትን ለመቀዳጀት ... በጎሳ መደራጀት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ... ይህ መጽሀፍ ምስክር ሊሆነን ይችላል :: የትግራይን ጉዳይም በሰከነ መንገድ መያዝ እንዳለብን ሳይጠቁመን አይቀርም :: ሁሉን ያቀፈ ህብረ ብሄራዊ ትግል ... ውጤታማና ዘላቂ ስልት ነው ::

አንዳንድ ከብቶች እንደሚሉት (እኔ እንኳን አንዳንዴ ለማመንም ያስቸግረኛል - ሰርጎ ገቦች መሆን አለባቸው ነው የምለው ) በጎሳ ተደራጅቶና ትግራይን ከወያኔ ሳይለዩ መግጠም ነው መፍትሄ ይላሉ :: እንደው ሰርጎ ገቦች ካልሆኑ እንደዚህ የሚሉት ሰዎች ምንም አይነት የፖለቲካ ግንዛቤ የሌላቸው መሆን አለባቸው ::

በኔ ዕይታ ወያኔን ለማሸነፍ ያለው አማራጭ "ሁለት ነጥቦችን የያዘ " አንድ ብቸኛ አማራጭ ነው ::

1 ሁሉን አቀፍ ህብረ ብሄራዊ ትግል ማካሄድና
2. ሁሉን አቀፍነቱ ትግራይንም ማካተት ከቻለ ብቻ ነው

በአንደኛው ነጥብ ብዙም የሚከራከር ሰው አይኖርም :: በሁለተኛውን ነጥብ ግን አንዳንድ ስሜታውያን ላይቀበሉት ይችላሉ :: ሲምፕል ሎጂኩ ግን ወዲህ ነው
አንደኛ ስርዓቱን ሊደግፍ የሚችል ፖቴንሺያል ሀይል መቀነስ ነው
ሁለተኛውና ዋነኛው (የተያያዘ ነው ) ሪስክን ከወዲሁ አቮይድ ማድረግ ነው :: ሁላችንም እንደምናውቀው ... ወያኔ ጦር መሳርያውን ያከማቸው በብዛት ወደ ትግራይ አካባቢ ነው :: ማንኛውም ፓርቲ ጦር መሳርያውን ከወያኔ እጅ መንጠቅ አይችልም :: ተኳሽ ሊሆን የሚችል ፖቴንሺያል "ወታደር /ታጋይ " በመንጠቅ ግን ባዶ መሳሪያውን ታቅፎ እንዲቀር ማድረግ ይቻላል :: ትግራይን ያቀፈ ትግል እስከተደረገ ድረስ ::

ለዚህም ነው ሊቀ ሊቃውንቱ አይተ ሓየት ደደቦችን በዋርካ የምገራው Wink
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቀደምት

ዋና ኮትኳች

Joined: 20 Feb 2006
Posts: 654

PostPosted: Mon Apr 16, 2012 6:55 pm    Post subject: አማራው ጎሰኝነት ወይስ ሕብረብ Reply with quote

ሰላም ወገን፡ እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ !

ለአስተያየታችሁ አመሰግናለሁ። እኔ ዋናው ለማንሳት የፈለግሁት ሃሳብ ጎሳዊ ወይስ ሕብረ -ብሔራዊ አደረጃጀት ይሻላል የሚለውን ክርክር ነው። በዚህ ሃሳብ ዙሪያ በተለይ አማራው በኢሕአዴግ ዘመነ -መንግሥት ከተከተለው ፖለቲካዊ አደረጃጀት በምሳሌነት የሚጠቀሱትን ክስተቶች አንስቻለሁ። አንዳንዶቻችሁ እንደው በቀላሉ ስለምትጨነቁ ነው እንጂ ስለ ልደቱ የግል ጉዳይም አይደለም ትኩረቴ። ያነሳሁትን የርእዮተ ዓለም ጥያቄ በተመለከተ በተፈጸመው ታሪክ ውስጥ ግን ልደቱና ኢዴፓ በግድ ሳይጠቀሱ የሚታለፉ አይደሉም። ወደዳችሁትም አልወደዳችሁትም ሰውየው በዚህ ታሪክ ላይ ያደረገውን ተሳትፎ ለመፋቅ አይቻልም። እናንተ ግን ለምን የሱ ስም ይጠቀሳል ማለታችሁ በጣሙን የሚገርም ነው። አገሪቱን ወደብ -አልባ አድርገውና የሕዝቡን አንድነት እስከወዲያኛው የሚንድ ሥርዓትን የመሠረቱትን እነ ስዬንና ነጋሶን እንኩዋንወደ ሕብረ -ብሔራዊነት መምጣታቸው በጎ ነገር መሆኑን እያወሳን ባለበት ሁኔታ ልደቱ የትኛውን የሐገር ጠንቅ የሆነ ፖሊሲ አራምዶ ነው በፍጹም ጥላቻ ታሪኩን ለመፋቅ የምትሹት ? እስቲ ይኸ ነው የምትሉትን ምክንያት አስረዱኝ።

በመሠረቱ ሁሌም ችግሩ የሚወሳሰበው አንዴ የይምሰል ሕብረ -ብሔራዊነትን ሌላ ጊዜ ደግሞ ያልተሸፋፈነ የጎጥ ስሜታዊነትንበሚያደባልቁ ሰዎች ምክንያት ነው። ናፖሊዎን፡ ጥልቁ፡ ተድላን የመሳሰሉት ሰዎች ከዚህ ጎራ የሚመደቡ ናቸው። ሕብረ -ብሔራዊነትን እደግፋለሁ ካልክ የመርሆቹ አክባሪና አስከባሪ መሆን አለብህ፡፡ በአንድ በኩል ጎሰኛ ፖለቲካንና ጎሰኛ አስተዳደርን እቃወማለሁ ትላለህ በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ የፖለቲካ ምህዋር ውስጥ ስትሽከረከር ከመገኘትህም ሌላ በብዙ ችግር ውስጥም ሆነው ሕብረ -ብሔራዊነታችን እንዲያብብ የሚታገሉ ሰዎችን ለማጥፋትና ድርጅታቸውን ለማዳከም አሉባልታ ትነዛለህ። የጎሳን አጥር የተሻገረ አመለካከት አለኝ ካልክ አጀንዳህ መሆን ያለበት የሰውየው ማንነት ሳይሆን የሃሳቡ ምንነት ነው። ሃሳቡን ባትደግፈው እንኳን ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ በእኩል አይን ማየት የመጀመሪያው ርምጃ ነው። ስለዚህ ልደቱም ሆነ ብርቱካን፤ መለስም ሆነ ስየ፤ እስክንድርም ሆነ ሌንጮ ...ሁሉም የኛው ጉዶች ናቸው። የታያቸውን የፖለቲካ አመለካከት የማንጸባረቅ እኩል መብት አላቸው። ጥያቄያችን ማንም ሰው ሃሳቡን በነጻ አቅርቦ በሕዝቡ ውሳኔ የሚዳኝበትን ሥርዓት የመመሥረቱ ጉዳይ ነው።

አሁንም የአማራውን የአደረጃጀት ጉዳይ በሚመለከት የሰሞኑ አጀንዳ ስለሆነ እስካሁን ድረስ የቆየንበትን ሁኔታ መለስ ብሎ ማየቱ ለመጪው ጉዞ ጠቃሚ ስለመሰለኝ ነው ግልጽ ያለ ሃሳቤን ለማካፈል የምሞክረው። ስለዚህ ጉዳዩን ማለባበስ ሳይሆን እምነታችንን በሃቅ ልንለዋወጥ እንችላለን። በተለይ ከሕብረ -ብሔራዊነት አኳያ ማለቴ ነው። ጎሳዊ አደረጃጀትን በተመለከተ ግን በእንደዚህ ያለው ግልጽ መድረክ እውነቱን ለመነጋገር አይቻልም። ምክንያቱም የጉዳዩ ባለቤት የሆኑትን ስብስቦች የሚመለከት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በጎሰኛ እንቅስቃሴ ውስጥ “ሞያ በልብ ነው” ስለሆነእውነተኛውን ነገር መነጋገር የሚቻለው በዚያው በጎሳው ውስጥ እንጂ ብዙ ጊዜ ከዚያ ውጭ ለሌሎች የሚገለጹ አስተያየቶችና አቋሞች ሙሉ በሙሉ እውነትነት ስለሌላቸውም ጭምር ነው።

ብዙ አይነት ጎሳዎች ባሉበት ሕብረተሰብ ውስጥ በዚሁ ርዕዮት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ማካሄድ ያለው አንዱ ትልቁ ድክመቱ ይኸው ነው። ሰዎች የራሳቸው ጎሳ አባል ከሆነ ሰው በስተቀር “የሌላ ወገን” የሆነ ሰው የሚያቀርበው ሃሳብ የቱንም ያህል ሚዛናዊ ቢሆን አያማልላቸውም። የራስህ ጎሳ አባል ሆኖ ደግሞ በትንሹም ቢሆን የሌሎችን ሃሳብ የሚጋራ ሆኖ ከተገኘ ከሃዲ ነው። ጎሳውን የካደ ይባላል። ስለዚህም ነው የነመለስ ቡድን እነ ስዬን ከሃዲ የሚሏቸው። ስለዚህም ነው የኢዴፓ ልጆች ሕብረ -ብሔራዊ ፓርቲ በማቋቋማቸው ጋዜጠኛው አቶ እስክንድር ልደቱን አግኝቶ “ልደቱ ከዳኸን፡ እኛ የአማራውን ድርጅት ለማጠናከር እየፈለግን” በማለት የተናገረው። የሆኖ ሆኖ የአማራው ድርጅት የተዳከመው ወጣቶቹ ከመአሕድ ስለወጡና ኃይሉን ስለከፈሉት ሳይሆን ከላይ እንደጠቀስኩት በወቅቱ አብዛኛው አማራ በጎሳ የመደራጀት ዝባሌው ስላልዳበረ ነው። ነገር ግን እነ እስክንድር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እነ ልደቱን ስላወገዙም ሆነራሳቸው የአማራውን ድርጅት መርተው እንቅስቃሴውን አላጠናከሩትም። አሁን አምባሳደር እምሩ እንደሚሉት ከሃያ አመት በኋላ ጊዜው ፈቅዶ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ፖለቲካ ሁሌም ባለበት ቦታ አይቆይምና። በተለይም ጎሳዊ ሕገመንግሥት ጸድቆና ጎሳዊ አስተዳደር ተፈጥሮ ሰዎች ኢትዮጵያዊነታቸው ሳይሆን ብሔረሰባዊ ማንነታቸው በየቀኑና በየቦታው በዋናነት በሚሰበክበት አገር የቆየው የሕብረ -ብሔራዊነት ሕዝባዊ ሳይኮሎጂ እንዳለ ይቀጥላል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ስለሆነም አማራው በእድር መልክ ከመደራጀትም አልፎ ነገ “አማራው የራሱን መንግሥት መመሥረት አለበት” የሚል ቡድን ቢነሳ የማይጠበቅ አይደለም።

ስለሆነም እኔ የአማርኛ ተናጋሪውን በጎሳ የመሰባሰብ ሃሳብ ለመቃዎም አልችልም። ለማለት የፈለግሁት ግን አንዱን ምረጡ ነው። ጎሰኛ አመለካከት ይሉኝታ ስለሌለው የታየህን ጠባብ አስተሳሰብ በገሃድ ተናገረው፤ ግን በሕብረ -ብሔራዊነትንካባ ለመደበቅ አትሞክር ነው የምለው። ለምሳሌ ዛሬ ካለው ትውልድውስጥ የአንድ ወይም የጥቂት ሰዎችን አስተሳሰብ በመውሰድ የእነ እንቶኔ ዘር ከፊትም ጀምሮ እንደዚህ ነበሩ እያሉ ጥላሸት መቀባት የሕብረ -ብሔራዊነት አስተሳሰብ አይደለም። ባለፈው ሰሞን በዋርካ ላይ የትግራይ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የባንዳነት ባሕሪይ እንዳለው ለማስረዳት ሲሞክሩ የነበሩ ሰዎችን አይቻለሁ። ጎሳዊ ፖለቲካና አስተዳደርን ገዥ ሃሳብ ለማድረግ ሲደከም ስለኖረ ዛሬ ያለፉ ነገሥታትን በብሔረሰባቸው በመፈረጅ “የኛ” እና “የነሱ” የሚባባሉ ኢትዮጵያዊያንን በአደባባይ ዘልቀው እያየን ነው። በእውነት ግን እንደዚህ አይነቱ አካሄድ የሕብረ -ብሔራዊነት ፍላጎትን ያንፀባርቃል ? እንዴት ብሎ ? በጋራ አገር ውስጥ ለመኖር ያስችለናል ? በጭራሽ። መለያየትን አጀንዳው ያደረገ አካል ነው በሌላው ላይ ማንኛውንም አይነት ጉድፍ ከመለጠፍ የማይመለሰው።ሕዝብን ላለማራራቅ ሲባል ያለፉ በደሎችንና ስህተቶችን እንኳን መሸፋፈን የሚያስፈልግበት ሁኔታ አለ። የታሪክ ጉድፎችን እየጎረጎረ ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርግ የጎሳ ፖለቲካ ብቻ ነው።ሌላው ነገር የቱንም ያህል በደል ቢፈጸምና ቀን ቢጨልምበት ከእምነቱ ዝንፍ የማይል ጽኑ እንዳለ ሁሉ፤ ለጠላት ማጎንበስና ወገንን መክዳት ምንጊዜም ሊኖር የሚችል የሰው ልጅ ባሕሪይ ነው። ለጣሊያንም ሆነ ለሌላ የአገር ጠላት ያደሩ ሰዎች ከሁሉም ጎሳዎች ነበሩ። የነገሥታቱም የአገዛዝ ፖሊሲ የብሔረሰባዊ ማንነታቸው መለያ ሳይሆን የወቅቱ አስተሳሰብና የግል ግንዛቤያቸው ውጤት ስለሆነ በአሁኑ ወቅታዊ ፖለቲካ መለኪያዎችየሚመዘን የስሜታችን ማስተንፈሻና ሕዝብን መከፋፈያ አጀንዳ መሆን የለበትም።

እስቲ ዘና ለማለት (የአመት በዓል ሰሞንም ስለሆነ ) አንድ ሙዚቃ ልጋብዛችሁ። ግን መልእክትም አለው፡ “ተቻችሎ መኖር ነበር ወግ ማዕረጉ፤ የያዙት ይጠፋል ሌላ ሲፈልጉ” ትላለች እቴነሽ፡

http://www.youtube.com/watch?v=HokuEyuNEzA&feature=related

.
Idea
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2792
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Mon Apr 16, 2012 9:08 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልን አይተ ቀደምት

አሁንም የልደቱን ነገር ወደጎን ትቼ ... ጥሩ ነጥብ እንዳነሳህ ለመግለጽ እወዳለሁ ::

በበኩሌ የሚመስለኝን የጻፍኩ መሰለኝ :: የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምዱ ሰዎች ችግር ያለባቸው ብቻ ናቸው :: ባጭሩ ከሚከተሉት ሶስት ችግሮች የአንዱ ሰለባ ከሆኑ ብቻ ነው :-

1. ጥቅም አሳዳጆች ከሆኑ አገርን የመምራት ዕድል ሲጠብ በጎሳ ፖለቲካ ስር ተሰባስበው ... ጎሳዬ /ብሄሬ /ዘሬ የሚሉትን ወገን ለመበዝበዝ ነው ::

2. ስሜታዊነት የሚያጠቃቸው ከሆኑም ለጊዜው መፍትሄ የሚመስላቸው በጎሳ ተደራጅቶ ቢያንስ ራስን መከላከል የሚሉት ማጃጃያ ሀሳብ በማቅረብ ነው :: አብሮ የሚረገዘው የማንነት ዴፊኒሽንና ባውንደሪ እንዲህውም ተያይዞ የሚመጣው ጦስ አይታያቸውም ::

3. በመከፋፈሉ ስራ ላይ የተጠመዱ የወያኔ ቅጥረኞቹ ከሆኑም በተለይ አማራን በጎሳ እንዲደራጅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም :: አንድ አብነት ለመጥቀስ ራሱን የዶሮ IQ ብሎ የሚጠራ አንድ ነፈዝ ሰው አለ እዚህ ዋርካ ላይ :: ... ገና ዋርካን በዚህ ስሙ ሲቀላቀል ጀምሮ ... ከፋፋይ የሆነ በዘርና በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያነጣጠረ ብልግና በማቅረብ ይታወቃል ... ዛሬ ምኞቱና ጥረቱ የተሳካለት ይመስላል ... አማራን በአማራነቱ ለማደራጀት የሚራኮቱ ስሜታውያን አጋጥመውታልና ::
_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Mon Apr 16, 2012 10:05 pm    Post subject: Reply with quote

ወርቅ ላበደረ ጠጠር ይሔ ነው ::

ማንነትህን እያወኩ ያነሳኸው ርዕሰ ጉዳይ ስቦኝ ለመወያየት ብሞክር ጮርቃነትን መርጠህ የማይሆን ነገር ውስጥ ገባህ :: በልደቱም ሆነ በመለስ ዜናዊ ላይ ማንም ዜጋ እንደ ዜጋ ኦፒኒየን ሊኖረው ይችላል :: ኦፖኒየኑን ፎርም የሚያደርገው ከፖለቲካ ባህሪያቸው እና ከሚያሳዮት አካሄድ በመነሳት ነው ::

ህወሀትን ሆነ አመራሩን በተመለከት የኢትዮጵያ ጠላት አይደሉም ፖለቲከኞች ናቸው የምትለኝ ከሆነ በኢዴፖ አንቀልባ አዝለሀቸው ልትኖር ትችላለህ ::

አሁንም ደጋግሞ የሚገርመኝ ነገር ህዝቡ ህወሀትን በጠላትነት መንፈስ እንዲያስ ያስገደደውን የህወሀትን አካሄድ ራሺናላይዝ እያደረጉ በህዝቡ የሚፈረደው ነገር ነው ::

እንደማይህ የዘር ፖለቲካ ብራይትነት የማየው አንተ ራስህ ላይ ነው :: ውይይትህን በጥሞና እየተከታተልኩ ባዶ አደርግሀለሁ እንዳልል ኢዴፓ እና ህወሀት የሚተዛዘሉ ክፉ የፖለቲካ ብላቴኖች እንደሆኑ ከታወቀ ሰነበተ :: ስለዚህ ከወዳጂህ ከአየተ ሓየት 11 ቁጥር ጋር እንድትላላጡ በትህትና እያሳሰኩ ጉዳየን እዚህ ላይ እጨርሳለሁ ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::
_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia