View previous topic :: View next topic
Author
Message
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Tue Apr 17, 2012 7:25 pm Post subject: ማምዳውን .. ግውውውውውው
Code: ሰላም ጓድ ውቃው :-
ብሎ ብሎ ይኼ ልጅ ፍልስፍናም አማረው ዝም ብሎ ዜማውን ቢያንቆረቁር ይሻለዋል :: ለነገሩ አገሩ ሰው ስለጠፋበት ምርኮኛ የብሔራዊ ውትድርና ሠልጣኞች ጄኔራሎች የሚሆኑበት : የተወሠኑት ደግሞ ዋናዎቹ የፊልምና የድራማ ደራሲና አዘጋጅ እየተባሉ የሚሞካሹበት : በአጠቃላይ አገር የውዳቂዎች መጫዎቻ በሆነችበት ዘመን ላይ ስለደረስን ቴዲ አፍሮ በአቋራጭ "ፈላስማ ሆኛለሁ " ቢለን የሚያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይሆንም ::
አሜሪካዊቷ ማርጋሬት ሚሸል "Gone with the Wind" በሚል ርዕስ እ .ኤ .አ . በ 1939 የጻፈችውንና አሁን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ : የቀድሞው የኢሕአፓ አባልና የከርቸሌ እሥረኛ ነቢይ መኮንን "ነገም ሌላ ቀን ነው " ብሎ ግማሹን ክፍል የተረጎመውን መጽሐፍ አንብበኸው ይሆን ብቻ ነገም ሌላ ቀን ስለሆነ በአዝማሪ ፈላስፎች ዘመን የምንሠማውን ፈጣሪያችን በልቦናችን አያሣድረው ::
ጋሽ ተድላ
እዛው የጻፍክበት መልስ ልሰጥ አልኩና ደግሞ ቀይመስመር ባልፍስ ብዬ እዚህ መጣሁ እኔው ያሰመርኩትን ብጥስም ምንም የሚለኝ የለም በማለት ... ለሁሉም ቴዲና ምርምሮቹ .. ትንሽ ፈኒ ናቸው .. የሚገርመው ከቴዲ ዘፈኖች ጋር አለመስማማት ወይንም የቴዲን ዘፈን አለመውደድ ልክ የሀገር መክዳት ወንጀል ያክል ከባድ እየሆነ ነው እና ሰው እንዳይጠላኝ እያልኩ ብዙም አልዘባርቅ የሚደፍር ከተገኘ ግን ያው ጥግ ይዤ እስቃለሁ ... ጥሩ ድምጽ አለው ... ጎበዝ ደራሲ ነው .. የኦዲየንሶቹን ሴንሲቲቭ በተን ያቃታል .. የቱጋር ነካ እንደሚያደርግ ... መቼ ይሆን ስለ አጼ ቴድሮስ የሚዘፍንልን ? ወይንስ ለምን እስከዛሬ የአገር አንድነት ላይ ትልቅ አስተዋጾ ያደረገውን ታላቁን መሪ ያልተዘፈነለት ይሆን ? ጃንሆይ , ሚኒሊክ .. ቀጣዩ ማን ይሆን ...
ለማንናውም ... ጋሽ ተድላ በ አባ መላኩ ላይ የተነሳው ተቃውሞን በተመለከተ የተናገሩዋት ብዙም ባትጥመኝም በዚህ ክሰውኛልና እዚህ አምጥቻለሁ .. ቀይ መስመር ሳልጥስ _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1 Last edited by recho on Sun May 06, 2012 5:32 am; edited 3 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Tue Apr 17, 2012 8:06 pm Post subject: Re: ሚኒሊክ ጥቁር ሰው ... ጋሽ ተድላ .... አባ መላኩ
recho እንደጻፈ(ች)ው : Code: ሰላም ጓድ ውቃው :-
ብሎ ብሎ ይኼ ልጅ ፍልስፍናም አማረው ዝም ብሎ ዜማውን ቢያንቆረቁር ይሻለዋል :: ለነገሩ አገሩ ሰው ስለጠፋበት ምርኮኛ የብሔራዊ ውትድርና ሠልጣኞች ጄኔራሎች የሚሆኑበት : የተወሠኑት ደግሞ ዋናዎቹ የፊልምና የድራማ ደራሲና አዘጋጅ እየተባሉ የሚሞካሹበት : በአጠቃላይ አገር የውዳቂዎች መጫዎቻ በሆነችበት ዘመን ላይ ስለደረስን ቴዲ አፍሮ በአቋራጭ "ፈላስማ ሆኛለሁ " ቢለን የሚያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይሆንም ::
አሜሪካዊቷ ማርጋሬት ሚሸል "Gone with the Wind" በሚል ርዕስ እ .ኤ .አ . በ 1939 የጻፈችውንና አሁን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ : የቀድሞው የኢሕአፓ አባልና የከርቸሌ እሥረኛ ነቢይ መኮንን "ነገም ሌላ ቀን ነው " ብሎ ግማሹን ክፍል የተረጎመውን መጽሐፍ አንብበኸው ይሆን ብቻ ነገም ሌላ ቀን ስለሆነ በአዝማሪ ፈላስፎች ዘመን የምንሠማውን ፈጣሪያችን በልቦናችን አያሣድረው ::
ጋሽ ተድላ
እዛው የጻፍክበት መልስ ልሰጥ አልኩና ደግሞ ቀይመስመር ባልፍስ ብዬ እዚህ መጣሁ እኔው ያሰመርኩትን ብጥስም ምንም የሚለኝ የለም በማለት ... ለሁሉም ቴዲና ምርምሮቹ .. ትንሽ ፈኒ ናቸው .. የሚገርመው ከቴዲ ዘፈኖች ጋር አለመስማማት ወይንም የቴዲን ዘፈን አለመውደድ ልክ የሀገር መክዳት ወንጀል ያክል ከባድ እየሆነ ነው እና ሰው እንዳይጠላኝ እያልኩ ብዙም አልዘባርቅ የሚደፍር ከተገኘ ግን ያው ጥግ ይዤ እስቃለሁ ... ጥሩ ድምጽ አለው ... ጎበዝ ደራሲ ነው .. የኦዲየንሶቹን ሴንሲቲቭ በተን ያቃታል .. የቱጋር ነካ እንደሚያደርግ ... መቼ ይሆን ስለ አጼ ቴድሮስ የሚዘፍንልን ? ወይንስ ለምን እስከዛሬ የአገር አንድነት ላይ ትልቅ አስተዋጾ ያደረገውን ታላቁን መሪ ያልተዘፈነለት ይሆን ? ጃንሆይ , ሚኒሊክ .. ቀጣዩ ማን ይሆን ...
ለማንናውም ... ጋሽ ተድላ በ አባ መላኩ ላይ የተነሳው ተቃውሞን በተመለከተ የተናገሩዋት ብዙም ባትጥመኝም በዚህ ክሰውኛልና እዚህ አምጥቻለሁ .. ቀይ መስመር ሳልጥስ
አንቺ ልጅ ምነው የፋሲካን በዓል አላከበርሽም ወይ ለማንኛውም እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሠሽ : ወርኃ -ፋሲካም የሰላም ጊዜ ይሁንልሽ ::
ቴዲ አፍሮ እንደዘመኑ ወጣት ነው :- ገበያው የሚፈልገውን ያውቃል :: ከዚያ በተረፈ የኢትዮጵያዊነት እንጥፍጣፊ ከልቡ ውስጥ አለ :: በሌላ ወገን ግን እንደ ተመቸው የሐረር ሠንጋ ከአዲስ አበባ ውጪ አገር እየተገላበጡ ከበር -ቻቻ የሚያበዙት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ዘፋኞች ግን ምኅዋራቸውን የሣቱ አዝማሪዎች ናቸው :: በኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ አዝማሪ የሚለው መጠሪያ "ያለውን እና ባለሥልጣንን አሞካሽቶ ኑሮውን የሚገፋ ዜማ አዋቂ " ማለት ነው :: እንግዲህ ቴዲ ለይቶለት "ቅንድቡ የሚያምረው " ብሎ የከንቱ ውዳሤ ዜማ እስኪያሠማ ድረስ ኢትዮጵያዊነቱን ልክድ አልፈልግም :: ፈላስፋነት ግን ጫት እየተቃመ ጥቂት መጻሕፍትን በማንበብ የሚመጣ አይደለም :: ቢቻል ትምህርት ቤት ገብቶ ቢማር ጥሩ ነበር : አሁንም አልዘገየምና :: ካልተቻለም ከአድናቂዎቹ የሚቀርብለትን የ 'አብረኸን ሁን : አትለየን ' ግፊት እንደምንም ተቋቁሞ መጻሕፍትን ቢያነብ ጥሩ ነበር :: በአንድ ወቅት ከራሱ አንደበት እንደሠማሁት ቃሊቲ እሥር ቤት በመግባቱ የጠቀመው ሠፋ ያለ የንባብ ጊዜ በማግኘቱ ነበር :: ለማንበብ አሁንም ዳግም እሥር ቤት መግባት አይኖርበትም :: ምናልባት የትዳር ጓደኛው ወደዚያ ዓይነት ሕይወት የምትመራው ከሆነ እግዚአብሔር ረድቶታል ብዬ እገምታለሁ :: በተቀረ ግን አንድን የጥበብ ሰው በድንገት እንዲህ ሕዝብ ሠማይ ሲሠቅለው ጥሩ አይደለም : ሲንኮታኮትም ፍፃሜው አያምርምና :: ከጥቁር አሜሪካውያን መካከል ማይክል ጃክሠን በቅርቡ ደግሞ ዊትኒ ሒውስተን የደረሠባቸው አሣዛኝ ፍፃሜ በራሣችንም ሰው ላይ ተደግሞ ማዬት አልፈልግም :: የእኔ ኃሣብ በዚህ ዙሪያ ያጠነጠነ እንጂ ለቴዲ ምንም ዓይነት የጥላቻም ሆነ የንቀት ስሜት የለኝም ::
ስለ ቴዲ ዜማዎች የራሴ አስተያዬት አለኝ :- እስካሁን ወቅታዊ እንጂ ብዙም ዘመን ተሻጋሪ (classical) ሥራዎች የሉትም :: እስኪ እርሱ ካዜማቸው ዜማዎች መካከል እስካሁን ድረስ ከሕዝብ ልብ ያልጠፉትና ዘወትር የሚደመጡት ምን ያህል ናቸው ? ጥሩ ጥሩ ግጥምና ዜማዎችን ለማግኘት ምናልባት ወደኋላ 35 እና 40 ዓመታት መመለስ ሊኖርብን ይችላል :: ከደርግ ዘመን ጀምሮ የሚደመጡት አብዛኞቹ ዜማዎች ለወቅታዊ ቅስቀሣ የሚዘጋጁ እንጂ ለዘለቄታው ሊደመጡ በሚችሉ ግጥሞች የታጀቡ አይደሉም :: ይባስ ብሎ አሁን አሁን ደግሞ የድሮውን ዜማ ሠርቀው እየከለሱ የራስ አድርጎ ማቅረብ እንደ ትልቅ ድምፃዊ የሚያስቆጥርበት ዘመን ላይ ደርሠናል :: አዲሱ ትውልድ ግን የቀረበለትን የዜማ ማዕድ ከመቋደስ በቀር ምርጫ ስለሌለው ያንኑ ደግሞ ያንጎራጉራል :: በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሥነ -ጥበብ ውጤት በፋብሪካ የሚመረት ተራ ሸቀጥ ሆኗል :: ስለዚህ ቴዴ አፍሮ የተለየ ተዓምር እንዲፈጥር አይጠበቅም ::
ስለ አባ መላኩ ያነሣሽው አልገባኝም :: እኔ 'ውቃው ' ወንድሜን የወቀስሁት ጉዳዩን ያለሥፍራው በማንሣቱ ነበር :: እዚያ ቤት ደስ ደስ የሚሉ ቀልዶችና አንዳንዴም ጥርስ የሚያፋጩ የኃሣብ ፍጭቶች ሲደረጉ አያለሁ እንጂ ኃይማኖትን በሚመለከት ደጉ ወንድማችን ሌሎችን ነገር ፈልጎ ወይም ጋብዞ ሲወያይ ወይም ሲያወያይ አላየሁም :: ለዚያ ነው :: አሁንስ ኃሣቤ ግልፅ ሆነልሽ ?
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Tue Apr 17, 2012 8:53 pm Post subject:
ውይ ጋሽ ተድላ ይቅርታ እንኩዋን አደረሶት ሳልል አይደል ? እንኩዋን አደረሶት !!!! መልካም የበአል ሳምንት ለሁላችን .. !
ስለቴዲ የጻፉትን ምንም አልጨምርበት .. በሙሉ አልፍዋል !
የአባ መላኩ ጉዳይ ... እውነት ለመናገር እንደውም አሪፍ ቦታ ነው ውቃው ያስቀመጠው ... በዛላይ ዋርካ ላይ ተያያዥነት ያለው ጽሁፍ ማንም ሲጽፍ አላየሁም ... የተጀመረበት ርእስ ሌላ የሚወራው ለላ ሆኖ ነው የሚያልቀው በተለምዶ ... እኔ እንዳየሁት ውቃው የክስተቱን ታሪክ ዘገበ እንጂ ለተቃዋሚዎቹ ወይንም አባ መላኩ ወግኖ ያለው ነገር ያለ አይመስለኝም ... ምናልባት ሳነብ የዘለልኩት ካለ እንጃ .. ያስቅ ነበረ ወይ የሚል ካለ በጣምምምምም ያስቃል .. እንዲሁም ይገርማል !!!! ሰዎቹ የመቃወም መብታቸውን ተጠቅመው የመሰላቸውን ብለዋል ... እኛንም ፋሲካን በሳቅ እንድናሳልፍ አርገዋል .. ዌል አትሊስት እኔን ... ለዚህ ደግሞ ውቃውን ከልብ አመሰግናለሁ
አባመላኩ ምን አሉ ? ምንም _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
-...- Joined: 09 Feb 2012 Posts: 315
Posted: Tue Apr 17, 2012 9:44 pm Post subject:
ማነው አባ መላኩ ........? ስለአባመላኩ የተጻፈ ስላላየሁ ነው _________________ እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 969
Posted: Wed Apr 18, 2012 1:00 am Post subject:
ሪጮ
እኔ ..ጓድ ተድልሽን "እርስዎ " ማለትሽ አልተመቸኝም :: በቁም ነገርኛነቱ እና በሚጽፋቸው አስተያየቶች አክብረሸው ቢሆንም እንኳ እሱን ብቻ መርጠሽ ተገቢ አይደለም :: ሚዛናዊ ሆነሽ ለእኔም "ታላቁ " " የኔ ጌታ " "አንበሳዬ " "ዓይኑካ " " ዉቁቅቅይይዬ " ምናምን ብባል አኮ አይከፋኝም : አስቢበት ::
ወደ ጓድ ተድላ ሰመለስ ...ያቀረብክብኝ ቀይ መስመር የማለፍ ክስ መስረተ -ቢስ እና አግባብ ባለው ህግ ሊያስጠይቅህ እንድሚችል ላሳስብህ እወዳለሁ :: እንደ እውነቱ የሆነ እንደሆነ ....አንተ የፈደራል ኢትዮጵያን ህገ መንግስት በዋርካ ለመናድ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተህ እየሰራህ መሆኑን አገር እያወቀው ሳለ : እኔ አንድ ጭቁን አብዮተኛው የመጻፍ መብቴን ተጠቅሜ አንዲት ቪድዮ ከነማብራሪያው ፖስት ስላደረኩ አንተና ዋለልኝ ቀይ ቀለም እየተቀባበላችሁ መስመሮች በማስመር መሄጃ እንዳጣ ለማድረግ መሞከራችሁ ያካባቢውን ህብረተስብ አነጋግሮ ያለፈ ጉዳይ ሆኗል ::
ሌላው .ደግሞ .. ደጉሰው ሃይማኖትን በሚመለከት .... ሌሎችን ጋብዞ ሲወያየም ሆነ ሲያወያይ አላየሁም [pharaphrased በኔ ]በማለት ጽፈህ ስሜን በሃሰት ለማጥፋት ሞክረሃል :: ስለ እውነትና ፍትህ ብለን የሩቁን ፖስት በመተው የቅርቡን እንኳ ብናይ ...ደጉ ማንም ሳያዘውና ሳይጠይቀው በራሱ አነሳሽነት ..አንዲት ማሪያም ነኝ የምትል ሴትን ቪድዮ እንድናየው በማለት ...ከአስተያየቱ ጋር ለጥፎን ነበር :: እኔም በወቅቱ ቀዳሚ በመሆን አስተያየት ስጥቻለሁ :: ይህ አንክዋር ፍሬ ጉዳይ ባንተ የዋርካ ሬከርድ ክፍል አገላባጭነት ችሎታ ሳይታወቅ ቀረ ብሎ ማለት በእጀጉ ያዳግተኛል :: እንደ እውነቱ ከሆነ ያኔ ደጉ ፖስት ባረገው አስቂኝ ቪድዮ እና እኔ ባደረኩት መካከል ጭብጡ እና መቼቱ እንደልዩነት ካልተቆጠረ በቀር አስቂኝነቱ እና አስገራሚነቱ ተቀራራቢ ነው :: አንተ ግን የዋርካ ህግ አንቀጽ አንድ / መስመር አንድና ሁለት By participating on Warka, you agree, through your use of this forum, that you will not post any material which is false [መስመር የኔ ] የሚለውን ..ደጉ በሀይማኖት ጉዳይ ሌሎችን ሲያወያይ አላየሁም በማለት ሁለት ጊዜ ሁለት ቦታ ሁለት ነጭ ኩሽት በመዋሸት ህጉን ተላልፈሃል ::
ሁኔታውን አግባብ ላለው የፍትህ አካል መውሰድ ብችልም : ያለብህን የቤተሰብ ኃላፊነትና ህገ -መንግስቱን የመናድ ስራህን ግምት ወጥ በማስገባት ..ያቀረብከውን ቅደመ -ክስ ይቅርታ ተቀብዬ ለጊዜው በነጻ ተስነብተሃል ::
አባ ዉቃው
ፊርማ የሚነበብ ከታች _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Apr 18, 2012 1:18 am Post subject:
ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው : ወደ ጓድ ተድላ ሰመለስ ...ያቀረብክብኝ ቀይ መስመር የማለፍ ክስ መስረተ -ቢስ እና አግባብ ባለው ህግ ሊያስጠይቅህ እንድሚችል ላሳስብህ እወዳለሁ :: እንደ እውነቱ የሆነ እንደሆነ ....አንተ የፈደራል ኢትዮጵያን ህገ መንግስት በዋርካ ለመናድ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተህ እየሰራህ መሆኑን አገር እያወቀው ሳለ : እኔ አንድ ጭቁን አብዮተኛው የመጻፍ መብቴን ተጠቅሜ አንዲት ቪድዮ ከነማብራሪያው ፖስት ስላደረኩ አንተና ዋለልኝ ቀይ ቀለም እየተቀባበላችሁ መስመሮች በማስመር መሄጃ እንዳጣ ለማድረግ መሞከራችሁ ያካባቢውን ህብረተስብ አነጋግሮ ያለፈ ጉዳይ ሆኗል ::
ይህንን አንቀፅ አንብቤ እንኳን ሣልጨርስ አጠገቤ ሰው ያለመኖሩ በጀኝ እንጂ "ምን ሆኖ እንዲህ እንባው ዱብ ዱብ እስኪል ድረስ ያሥቀዋል " ብሎ ሣያሽሟጥጠኝ አይቀርም ነበር :: ለዚህ ጨዋታህ ብዬ አይደል ትንሽ ተንኮስ ያደረግሁህ
ውቃው እንደጻፈ(ች)ው : ሌላው .ደግሞ .. ደጉሰው ሃይማኖትን በሚመለከት .... ሌሎችን ጋብዞ ሲወያየም ሆነ ሲያወያይ አላየሁም [pharaphrased በኔ ]በማለት ጽፈህ ስሜን በሃሰት ለማጥፋት ሞክረሃል :: ስለ እውነትና ፍትህ ብለን የሩቁን ፖስት በመተው የቅርቡን እንኳ ብናይ ...ደጉ ማንም ሳያዘውና ሳይጠይቀው በራሱ አነሳሽነት ..አንዲት ማሪያም ነኝ የምትል ሴትን ቪድዮ እንድናየው በማለት ...ከአስተያየቱ ጋር ለጥፎን ነበር :: እኔም በወቅቱ ቀዳሚ በመሆን አስተያየት ስጥቻለሁ :: ይህ አንክዋር ፍሬ ጉዳይ ባንተ የዋርካ ሬከርድ ክፍል አገላባጭነት ችሎታ ሳይታወቅ ቀረ ብሎ ማለት በእጀጉ ያዳግተኛል :: እንደ እውነቱ ከሆነ ያኔ ደጉ ፖስት ባረገው አስቂኝ ቪድዮ እና እኔ ባደረኩት መካከል ጭብጡ እና መቼቱ እንደልዩነት ካልተቆጠረ በቀር አስቂኝነቱ እና አስገራሚነቱ ተቀራራቢ ነው :: አንተ ግን የዋርካ ህግ አንቀጽ አንድ / መስመር አንድና ሁለት By participating on Warka, you agree, through your use of this forum, that you will not post any material which is false [መስመር የኔ ] የሚለውን ..ደጉ በሀይማኖት ጉዳይ ሌሎችን ሲያወያይ አላየሁም በማለት ሁለት ጊዜ ሁለት ቦታ ሁለት ነጭ ኩሽት በመዋሸት ህጉን ተላልፈሃል ::
እንዴ ኃይማኖትን እና 'cult' የሚሉትን ለይ እንጂ :: አሁንም ቢሆን ደጉ ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሲያወያይ አላውቅም :: በተለያዩ ኃይማኖት -መሠል 'cults' ላይ ጥሩ ጥሩ መልሶች ይሠጣል : ለዚያውም የተነታራኪ አልቃሻ አማራሪዎችን አፍ እያስዘጋ :: ስለዚህ ወይ እኔ ኃይማኖት ነው ብዬ የምቀበለውና አንተ ውቃው ወንድሜ በጥቅሉ ኃይማኖት ነው ብለህ የምትቀበለው ይለያያል : ያለበለዚያም እኔ በደንብ አላስተዋልኩም ማለት ነው ::
ውቃው እንደጻፈ(ች)ው : ሁኔታውን አግባብ ላለው የፍትህ አካል መውሰድ ብችልም : ያለብህን የቤተሰብ ኃላፊነትና ህገ -መንግስቱን የመናድ ስራህን ግምት ወጥ በማስገባት ..ያቀረብከውን ቅደመ -ክስ ይቅርታ ተቀብዬ ለጊዜው በነጻ ተስነብተሃል ::
አባ ዉቃው
ፊርማ የሚነበብ ከታች
ፈጣሪያችን ሆይ ! እንዲህ ቃሊቲና ዴዴሣ ሣያጉሩ ይቅርታ የሚያደርጉ ደጋግ መሪዎችን አምጣልን !
ሌሎቻችሁ አሜን ! አትሉም ወይ
ወንድሜ ይመችህ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Wed Apr 18, 2012 3:44 am Post subject:
-...- እንደጻፈ(ች)ው : ማነው አባ መላኩ ........? ስለአባመላኩ የተጻፈ ስላላየሁ ነው
ጥሩ ጥያቄ ነው http://www.youtube.com/watch?v=itx845M21-4&context=C417655fADvjVQa1PpcFOlu1yO951A_lvDdVfnqs2dC00-pcCAw1U=
ኢንጆይ !
ጋሽ ተድላ እና ውቄው ... አዎ እንደዚህ ነጻ ውይይት አሪፍ ነው ... ያቺ ማሪያም ነኝ ያለችቺው ሴቲዩ ታሪክና የአባ መላኩ ታሪክ እኮ ታዲያ ተመሳሳይነት አለው .. ሁለቱም ፈኒ ነው መቸም ውቃውም ሆነ ደጉ ይሄ ታሪክ አያምልጣቸው ብለው ዋርካ ሲያመጡት እንድንዝናናበት ነው .. ስለዚህ ቦታውነው ባይነኝ አሁንም
ውቃው ነብር አየኝ በል .. የምናባህ ቁልምጫ ነው ደግሞ .. መከበሪያህ ሲደርስ ጋሼ ትባላለህ ... አሁን በዚህ ይቀናል እስቲ ጋሽ ተድላ ...
ሰላም እደሩ እስቲ _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Wed Apr 18, 2012 4:03 am Post subject:
recho እንደጻፈ(ች)ው : ውቃው ነብር አየኝ በል .. የምናባህ ቁልምጫ ነው ደግሞ .. መከበሪያህ ሲደርስ ጋሼ ትባላለህ ... አሁን በዚህ ይቀናል እስቲ ጋሽ ተድላ ...
ሰላም እደሩ እስቲ
አንቺ ልጅ ደግሞ ቀጥተኛ ባህሪ ካለው ከወንድሜ ከውቃው ጋር ልታጣይኝ ነው "ነብር አየኝ በል " እያልሽ የምታስፈራሪው ብታስቢውም አሁን አሁን እኮ ነብሩም በቀላል የሚገኝ እንዳይመስልሽ ከኒውዮርክ -ብሮንክስ የእንሥሣት ግቢ ከሆነ ውቃው ይቀርባልና ቀድሞሽ ሠልፍ ይዞ (ዘቡሌውን ለምናምን የሚሆን ፍሉስ በጥሶላቸውም ቢሆን ) ነብሩን ተረክቦ በሠንሠለት እየጎተተ ይመጣልሻል :: ከሣን -ፋራንሲስኮ ከሆነ ግን ባታስቢው ይመረጣል ... እዚያ ያሉት 'ነምሮች ' የሰው ሥጋ የለመዱ ናቸውና አንችኑ ቁርስ እንዳያደርጉሽ
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ገልብጤ Joined: 26 Jun 2010 Posts: 1151
Posted: Thu Apr 19, 2012 4:27 pm Post subject:
ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote: የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን
_________________ SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Thu Apr 19, 2012 6:07 pm Post subject:
[quote="ገልብጤ "]
ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote: የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን
ይሆናል እንጃ ሰዎቹ አባ መላኩ ላይ ተቃውሞ አላቸው ምንክኒያቱ ቤተክርስቲያኒትዋ ከየትኛውም ወገን ሳይሆን ኒውትራል አቁዋም ነው ያለኝ አይነት ነው የሚከተለሉት ... ከሁለቱም ሲኖዶስ አንሆንም ገለልተኛ አቁዋም ነው ያለኝ ስላሉ በቀጥታ የለምንም ማንደርደሪያ ወያኔ ናቸው ብለዋቸዋል ... ስለዚህም ነው አባ መላኩ ምን አሉ ? ምንምምምም የመታው .. ግን እንደተመለከትኩት ምእመኑ በአሉን አክብሮ በሰላም ወደቤቱ ሲሄድ ነበር ... ተቃዋሚዎቹም በግምቴ መሰረት 5 ሰዎች መሰሉኝ ... የሚሰማው ድምጽ ከዛ በላይ አይመስልም .. ኤኒሁ ... ፈኒ ነው ... ፖለቲክሱ ምናምን ወይንም የተፈጠረው ነገር ሳይሆን ድርጊታቸው ፈኒ ነው ... ለኔ ! _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Thu Apr 19, 2012 7:42 pm Post subject:
[quote="recho"] ገልብጤ እንደጻፈ(ች)ው :
ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote: የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን
ይሆናል እንጃ ሰዎቹ አባ መላኩ ላይ ተቃውሞ አላቸው ምንክኒያቱ ቤተክርስቲያኒትዋ ከየትኛውም ወገን ሳይሆን ኒውትራል አቁዋም ነው ያለኝ አይነት ነው የሚከተለሉት ... ከሁለቱም ሲኖዶስ አንሆንም ገለልተኛ አቁዋም ነው ያለኝ ስላሉ በቀጥታ የለምንም ማንደርደሪያ ወያኔ ናቸው ብለዋቸዋል ... ስለዚህም ነው አባ መላኩ ምን አሉ ? ምንምምምም የመታው .. ግን እንደተመለከትኩት ምእመኑ በአሉን አክብሮ በሰላም ወደቤቱ ሲሄድ ነበር ... ተቃዋሚዎቹም በግምቴ መሰረት 5 ሰዎች መሰሉኝ ... የሚሰማው ድምጽ ከዛ በላይ አይመስልም .. ኤኒሁ ... ፈኒ ነው ... ፖለቲክሱ ምናምን ወይንም የተፈጠረው ነገር ሳይሆን ድርጊታቸው ፈኒ ነው ... ለኔ !
ሪቾ :-
አንዳንድ ነገሮችን በሥሜት እዚህ ከመለጠፍሽ በፊት ግራ ቀኙን አጣሪ : በተለይ ደግሞ ኃይማኖትን በሚያህል የሰዎችን ውስጣዊ ስሜት በሚነካ ጉዳይ ::
አባ መላኩ ማን ናቸው ? በአባ ጳውሎስ ተሹመው በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንደኛው አንጃ ሊቀ -ጳጳስ (አቡነ ፋኑኤል ) ናቸው :: ለአንቺ 'ፈኒ ' ቢሆንም እነዚያ ሲቃወሙ የምታያቸው ምዕመናን ግን ሊያሣውቁ የሚፈልጉት ነገር አለ : ተቃውሟቸውም ለእነርሱ በቂ ምክንያት አለው :: የሚከተሉት ምንጮች ስለሁኔታው በጣም በጥቂቱ ፍንጮችን ይሠጡሻል ::
ምንጮች :-
1 ..... ገብር ኄር (ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ ) : Posted on November 9, 2011:: የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ ???
2 ..... ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች : Posted at 7:33 PM Wednesday, March 28, 2012. ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ የተናገሩት ::
ረጋ ብለሽ የምታስቢበት ልቦና ይስጥሽ ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Fri Apr 20, 2012 1:50 am Post subject:
አይይይ እንግዲህ አሁንስ በዛ ! የፈለኩትን የማለት መብት አለኝ ... ለዛ መስሎኛል ቀይ መስመር ምናምን ብለህ የለቀለቅክበት ቦታ መጥቼ ምንም ያላወራሁት ... አክብሬ አንቱ ብዬ እንደያዝኩህ መቀጠል ከቻልን አሪፍ ካለዛ የምጽፈን አታንብ ኮመንትም አታርግ .... ስለጉዳዩ በጥልቀት ለማወቅ ምንም ፍላጎት የለኝም .. ማወቅ የምፈልገውን ያክል አውቂያለሁ ... ከዛ በላይ ያለውን አንተው ተመራመርና ድረስበት .. ለኔ ለጊዜው አያስፈልገኝም .. አሁንም ቪዲዩው ያስቃል .. ስቂያለሁ አሁንም እስቃለሁ ...!!! ያ ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቴ ነው ... ! ፋይል ዘግቻለሁ ... እየመጣህ ለቅልቅ ..
አንተም እንደ እድሜህ እንድታስብ እግዜር ይርዳህ
ሪቾ _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ተድላ ሀይሉ Joined: 17 Mar 2006 Posts: 4459 Location: ኢትዮጵያ
Posted: Fri Apr 20, 2012 2:01 am Post subject:
recho እንደጻፈ(ች)ው : አይይይ እንግዲህ አሁንስ በዛ ! የፈለኩትን የማለት መብት አለኝ ... ለዛ መስሎኛል ቀይ መስመር ምናምን ብለህ የለቀለቅክበት ቦታ መጥቼ ምንም ያላወራሁት ... አክብሬ አንቱ ብዬ እንደያዝኩህ መቀጠል ከቻልን አሪፍ ካለዛ የምጽፈን አታንብ ኮመንትም አታርግ .... ስለጉዳዩ በጥልቀት ለማወቅ ምንም ፍላጎት የለኝም .. ማወቅ የምፈልገውን ያክል አውቂያለሁ ... ከዛ በላይ ያለውን አንተው ተመራመርና ድረስበት .. ለኔ ለጊዜው አያስፈልገኝም .. አሁንም ቪዲዩው ያስቃል .. ስቂያለሁ አሁንም እስቃለሁ ...!!! ያ ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቴ ነው ... ! ፋይል ዘግቻለሁ ... እየመጣህ ለቅልቅ ..
አንተም እንደ እድሜህ እንድታስብ እግዜር ይርዳህ
ሪቾ
"የዘሬ ቢለቀኝ ያንዘርዝረኝ :" እያልሽ ነው ወያኔነት የማይታፈርበት ዘመን ላይ ስለሆንን እንደ እነ ስልኪና ዳግማዊ ዋለልኝ ያሻሽን ማለት ትችያለሽ : በኋላ ማጣፊያው እንዳያጥርሽ እንጂ ::
በቤተክርስቲያን ላይ ለማፌዝ ከሆነ እንደ ቢዮንሴ አዲስ አበባ ሄደሽ ከአባ ገብረመድህን ጋር ዳንኪራሽን ማቅለጥ ትችያለሽ :: ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ላይ ማላገጥ አትችይም ::
ተድላ _________________ የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 3000 Location: Earth
Posted: Fri Apr 20, 2012 2:05 am Post subject:
አመት ያስቃል አይደለሁም እንጂ ብሆን እንኩዋን ወያኔ .. መብቴ ነው ... ዘሬን ቆጥረሀል ማለት ነው .. አሪፍ ነዋ ... ለማንኛውም .. ቤተሰቦቼ ሲያሳድጉኝ ከእንዳንተ አይነት ሰው ጋር አፍመካፈትን አብረው አላስተማሩኝም ... ስለዚህ እንዳከበርኩህ እዚህ ጋር እናብቃ .. ከንግዲህ ተድላ ሀይሉ ለሚባል ኒክኔም መልስ አልሰጥም .. በጣም ስለማከብርህ ..
ረጅም እድሜ ከመልካም ጤንነት ጋር ላንተ ! ቻው _________________ "ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 969
Posted: Fri Apr 20, 2012 2:15 am Post subject:
ተዉ ልጆችዬ አትጣሉ :: በማርያም ይዣችኋለሁ ! ተዉ :: እንዴ .. እንዴት ነው ነገሩ ? ይህ እኮ የፍቅር መድረክ ነው :: ጠብ ይቅር : ጦሳችሁንም ይዞ ይሂድ :: ሰለውነት ከተባለ እኮ ....እንኳን አባ መላኩ ከተቃዋሚዎቻቸው ይቅርና ..አሜሪካ ያለው ሲኖዶስና ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ሊታርቁ /ሊግባቡ ንግግር ላይ ናቸው :: እንዲያ ተወጋገዘው የተለያዩ አባቶች ..አሁን ለእርቅ በየጊዜው ለእርቅ ወደ አንድ መድረክ ሲመጡ ማየትን እኮ ትንሽ ነገር አርጋችሁ አትዩት :: አንድ ቀን መድሀኒያለም ሲፈቅድ ቤትክርስቲያኗ አንድ ትሆንና ሁሉ ነገር ያበቃል ::
አቡነ ጳውሎስ ወያኔ ናቸው ተብሎ ከተረጋገጠ በቃ አቡነ መርቆሪዮስም ደርግ ኢሠፓ ናቸው የሚለው ያስኬዳል :: እምነት ግዴታ ሳይሆን ነጻነት ነው :: አሁን እኮ ኢትዮጵያ ያለው የኦርቶዶክስ ምዕመን በጠቅላላው አቡነ ጳውሎስ ወደ ሚያስተዳድሩት ቤተክርስቲያን ይሄዳል ይገለገላል :: በአሜሪካ ያለው ደግሞ ባብዛኛው በአቡነ ማርቆሪዮስ ወደሚተዳደሩት ይሄዳል :: ሁሉንም ማንም አላስገደዳቸውም ::
ሌላው ደግሞ አሁን ያሉት አባቶች ዘልዓለማዊ አይደሉም :: ሳያልፉ ሁለቱም ሲኖዶሶች ተስማምተው አቡነ መርቆሪዮስም ሆነ አቡነ ጳውሎስ ከስልጣን ወርደው ..በምርጫም ሆነ በስምምነት አንድ ፓትሪያርክ መርጠው ...ለወደፊት ችግር እንዳይግጥም የቤትክርስቲያኖንም ህግ አሻሽለው ...ቢያልፉ በክርስቶስ ቀኝ አይውሉም ትላላችሁ ?!
ቤተክርስቲያኗስ ከፍ ከፍ አትልም ?! ምዕመኑስ አያክብራቸውም ? ፍቅርስ አይወርድም ?
የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን :: _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!