WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ማምዳውን .. ግውውውውውው
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 7:25 pm    Post subject: ማምዳውን .. ግውውውውውው Reply with quote

Code:
ሰላም ጓድ ውቃው :-

ብሎ ብሎ ይኼ ልጅ ፍልስፍናም አማረው     ዝም ብሎ ዜማውን ቢያንቆረቁር ይሻለዋል :: ለነገሩ አገሩ ሰው ስለጠፋበት ምርኮኛ የብሔራዊ ውትድርና ሠልጣኞች ጄኔራሎች የሚሆኑበት : የተወሠኑት ደግሞ ዋናዎቹ የፊልምና የድራማ ደራሲና አዘጋጅ እየተባሉ የሚሞካሹበት : በአጠቃላይ አገር የውዳቂዎች መጫዎቻ በሆነችበት ዘመን ላይ ስለደረስን ቴዲ አፍሮ በአቋራጭ "ፈላስማ ሆኛለሁ " ቢለን የሚያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይሆንም ::

አሜሪካዊቷ ማርጋሬት ሚሸል "Gone with the Wind" በሚል ርዕስ . . . 1939 የጻፈችውንና አሁን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ : የቀድሞው የኢሕአፓ አባልና የከርቸሌ እሥረኛ ነቢይ መኮንን "ነገም ሌላ ቀን ነው " ብሎ ግማሹን ክፍል የተረጎመውን መጽሐፍ አንብበኸው ይሆን   ብቻ ነገም ሌላ ቀን ስለሆነ በአዝማሪ ፈላስፎች ዘመን የምንሠማውን ፈጣሪያችን በልቦናችን አያሣድረው ::

ጋሽ ተድላ

እዛው የጻፍክበት መልስ ልሰጥ አልኩና ደግሞ ቀይመስመር ባልፍስ ብዬ እዚህ መጣሁ Laughing እኔው ያሰመርኩትን ብጥስም ምንም የሚለኝ የለም በማለት ... ለሁሉም ቴዲና ምርምሮቹ .. ትንሽ ፈኒ ናቸው .. የሚገርመው ከቴዲ ዘፈኖች ጋር አለመስማማት ወይንም የቴዲን ዘፈን አለመውደድ ልክ የሀገር መክዳት ወንጀል ያክል ከባድ እየሆነ ነው እና ሰው እንዳይጠላኝ እያልኩ ብዙም አልዘባርቅ Laughing የሚደፍር ከተገኘ ግን ያው ጥግ ይዤ እስቃለሁ ... ጥሩ ድምጽ አለው ... ጎበዝ ደራሲ ነው .. የኦዲየንሶቹን ሴንሲቲቭ በተን ያቃታል .. የቱጋር ነካ እንደሚያደርግ ... መቼ ይሆን ስለ አጼ ቴድሮስ የሚዘፍንልን ? ወይንስ ለምን እስከዛሬ የአገር አንድነት ላይ ትልቅ አስተዋጾ ያደረገውን ታላቁን መሪ ያልተዘፈነለት ይሆን ? ጃንሆይ , ሚኒሊክ .. ቀጣዩ ማን ይሆን ...

ለማንናውም ... ጋሽ ተድላ አባ መላኩ ላይ የተነሳው ተቃውሞን በተመለከተ የተናገሩዋት ብዙም ባትጥመኝም በዚህ ክሰውኛልና እዚህ አምጥቻለሁ .. ቀይ መስመር ሳልጥስ Smile
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1

Last edited by recho on Sun May 06, 2012 5:32 am; edited 3 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 8:06 pm    Post subject: Re: ሚኒሊክ ጥቁር ሰው ... ጋሽ ተድላ .... አባ መላኩ Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
Code:
ሰላም ጓድ ውቃው :-

ብሎ ብሎ ይኼ ልጅ ፍልስፍናም አማረው     ዝም ብሎ ዜማውን ቢያንቆረቁር ይሻለዋል :: ለነገሩ አገሩ ሰው ስለጠፋበት ምርኮኛ የብሔራዊ ውትድርና ሠልጣኞች ጄኔራሎች የሚሆኑበት : የተወሠኑት ደግሞ ዋናዎቹ የፊልምና የድራማ ደራሲና አዘጋጅ እየተባሉ የሚሞካሹበት : በአጠቃላይ አገር የውዳቂዎች መጫዎቻ በሆነችበት ዘመን ላይ ስለደረስን ቴዲ አፍሮ በአቋራጭ "ፈላስማ ሆኛለሁ " ቢለን የሚያንስበት እንጂ የሚበዛበት አይሆንም ::

አሜሪካዊቷ ማርጋሬት ሚሸል "Gone with the Wind" በሚል ርዕስ . . . 1939 የጻፈችውንና አሁን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ : የቀድሞው የኢሕአፓ አባልና የከርቸሌ እሥረኛ ነቢይ መኮንን "ነገም ሌላ ቀን ነው " ብሎ ግማሹን ክፍል የተረጎመውን መጽሐፍ አንብበኸው ይሆን   ብቻ ነገም ሌላ ቀን ስለሆነ በአዝማሪ ፈላስፎች ዘመን የምንሠማውን ፈጣሪያችን በልቦናችን አያሣድረው ::

ጋሽ ተድላ

እዛው የጻፍክበት መልስ ልሰጥ አልኩና ደግሞ ቀይመስመር ባልፍስ ብዬ እዚህ መጣሁ Laughing እኔው ያሰመርኩትን ብጥስም ምንም የሚለኝ የለም በማለት ... ለሁሉም ቴዲና ምርምሮቹ .. ትንሽ ፈኒ ናቸው .. የሚገርመው ከቴዲ ዘፈኖች ጋር አለመስማማት ወይንም የቴዲን ዘፈን አለመውደድ ልክ የሀገር መክዳት ወንጀል ያክል ከባድ እየሆነ ነው እና ሰው እንዳይጠላኝ እያልኩ ብዙም አልዘባርቅ Laughing የሚደፍር ከተገኘ ግን ያው ጥግ ይዤ እስቃለሁ ... ጥሩ ድምጽ አለው ... ጎበዝ ደራሲ ነው .. የኦዲየንሶቹን ሴንሲቲቭ በተን ያቃታል .. የቱጋር ነካ እንደሚያደርግ ... መቼ ይሆን ስለ አጼ ቴድሮስ የሚዘፍንልን ? ወይንስ ለምን እስከዛሬ የአገር አንድነት ላይ ትልቅ አስተዋጾ ያደረገውን ታላቁን መሪ ያልተዘፈነለት ይሆን ? ጃንሆይ , ሚኒሊክ .. ቀጣዩ ማን ይሆን ...

ለማንናውም ... ጋሽ ተድላ አባ መላኩ ላይ የተነሳው ተቃውሞን በተመለከተ የተናገሩዋት ብዙም ባትጥመኝም በዚህ ክሰውኛልና እዚህ አምጥቻለሁ .. ቀይ መስመር ሳልጥስ Smile

አንቺ ልጅ ምነው የፋሲካን በዓል አላከበርሽም ወይ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ለማንኛውም እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሠሽ : ወርኃ -ፋሲካም የሰላም ጊዜ ይሁንልሽ ::

ቴዲ አፍሮ እንደዘመኑ ወጣት ነው :- ገበያው የሚፈልገውን ያውቃል :: ከዚያ በተረፈ የኢትዮጵያዊነት እንጥፍጣፊ ከልቡ ውስጥ አለ :: በሌላ ወገን ግን እንደ ተመቸው የሐረር ሠንጋ ከአዲስ አበባ ውጪ አገር እየተገላበጡ ከበር -ቻቻ የሚያበዙት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ዘፋኞች ግን ምኅዋራቸውን የሣቱ አዝማሪዎች ናቸው :: በኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ አዝማሪ የሚለው መጠሪያ "ያለውን እና ባለሥልጣንን አሞካሽቶ ኑሮውን የሚገፋ ዜማ አዋቂ " ማለት ነው :: እንግዲህ ቴዲ ለይቶለት "ቅንድቡ የሚያምረው " ብሎ የከንቱ ውዳሤ ዜማ እስኪያሠማ ድረስ ኢትዮጵያዊነቱን ልክድ አልፈልግም :: ፈላስፋነት ግን ጫት እየተቃመ ጥቂት መጻሕፍትን በማንበብ የሚመጣ አይደለም :: ቢቻል ትምህርት ቤት ገብቶ ቢማር ጥሩ ነበር : አሁንም አልዘገየምና :: ካልተቻለም ከአድናቂዎቹ የሚቀርብለትን 'አብረኸን ሁን : አትለየን ' ግፊት እንደምንም ተቋቁሞ መጻሕፍትን ቢያነብ ጥሩ ነበር :: በአንድ ወቅት ከራሱ አንደበት እንደሠማሁት ቃሊቲ እሥር ቤት በመግባቱ የጠቀመው ሠፋ ያለ የንባብ ጊዜ በማግኘቱ ነበር :: ለማንበብ አሁንም ዳግም እሥር ቤት መግባት አይኖርበትም :: ምናልባት የትዳር ጓደኛው ወደዚያ ዓይነት ሕይወት የምትመራው ከሆነ እግዚአብሔር ረድቶታል ብዬ እገምታለሁ :: በተቀረ ግን አንድን የጥበብ ሰው በድንገት እንዲህ ሕዝብ ሠማይ ሲሠቅለው ጥሩ አይደለም : ሲንኮታኮትም ፍፃሜው አያምርምና :: ከጥቁር አሜሪካውያን መካከል ማይክል ጃክሠን በቅርቡ ደግሞ ዊትኒ ሒውስተን የደረሠባቸው አሣዛኝ ፍፃሜ በራሣችንም ሰው ላይ ተደግሞ ማዬት አልፈልግም :: የእኔ ኃሣብ በዚህ ዙሪያ ያጠነጠነ እንጂ ለቴዲ ምንም ዓይነት የጥላቻም ሆነ የንቀት ስሜት የለኝም ::

ስለ ቴዲ ዜማዎች የራሴ አስተያዬት አለኝ :- እስካሁን ወቅታዊ እንጂ ብዙም ዘመን ተሻጋሪ (classical) ሥራዎች የሉትም :: እስኪ እርሱ ካዜማቸው ዜማዎች መካከል እስካሁን ድረስ ከሕዝብ ልብ ያልጠፉትና ዘወትር የሚደመጡት ምን ያህል ናቸው ? ጥሩ ጥሩ ግጥምና ዜማዎችን ለማግኘት ምናልባት ወደኋላ 35 እና 40 ዓመታት መመለስ ሊኖርብን ይችላል :: ከደርግ ዘመን ጀምሮ የሚደመጡት አብዛኞቹ ዜማዎች ለወቅታዊ ቅስቀሣ የሚዘጋጁ እንጂ ለዘለቄታው ሊደመጡ በሚችሉ ግጥሞች የታጀቡ አይደሉም :: ይባስ ብሎ አሁን አሁን ደግሞ የድሮውን ዜማ ሠርቀው እየከለሱ የራስ አድርጎ ማቅረብ እንደ ትልቅ ድምፃዊ የሚያስቆጥርበት ዘመን ላይ ደርሠናል :: አዲሱ ትውልድ ግን የቀረበለትን የዜማ ማዕድ ከመቋደስ በቀር ምርጫ ስለሌለው ያንኑ ደግሞ ያንጎራጉራል :: በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሥነ -ጥበብ ውጤት በፋብሪካ የሚመረት ተራ ሸቀጥ ሆኗል :: ስለዚህ ቴዴ አፍሮ የተለየ ተዓምር እንዲፈጥር አይጠበቅም ::

ስለ አባ መላኩ ያነሣሽው አልገባኝም :: እኔ 'ውቃው ' ወንድሜን የወቀስሁት ጉዳዩን ያለሥፍራው በማንሣቱ ነበር :: እዚያ ቤት ደስ ደስ የሚሉ ቀልዶችና አንዳንዴም ጥርስ የሚያፋጩ የኃሣብ ፍጭቶች ሲደረጉ አያለሁ እንጂ ኃይማኖትን በሚመለከት ደጉ ወንድማችን ሌሎችን ነገር ፈልጎ ወይም ጋብዞ ሲወያይ ወይም ሲያወያይ አላየሁም :: ለዚያ ነው :: አሁንስ ኃሣቤ ግልፅ ሆነልሽ ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 8:53 pm    Post subject: Reply with quote

ውይ ጋሽ ተድላ ይቅርታ እንኩዋን አደረሶት ሳልል አይደል ? እንኩዋን አደረሶት !!!! መልካም የበአል ሳምንት ለሁላችን .. !

ስለቴዲ የጻፉትን ምንም አልጨምርበት .. በሙሉ አልፍዋል ! Smile

የአባ መላኩ ጉዳይ ... እውነት ለመናገር እንደውም አሪፍ ቦታ ነው ውቃው ያስቀመጠው ... በዛላይ ዋርካ ላይ ተያያዥነት ያለው ጽሁፍ ማንም ሲጽፍ አላየሁም ... የተጀመረበት ርእስ ሌላ የሚወራው ለላ ሆኖ ነው የሚያልቀው በተለምዶ ... እኔ እንዳየሁት ውቃው የክስተቱን ታሪክ ዘገበ እንጂ ለተቃዋሚዎቹ ወይንም አባ መላኩ ወግኖ ያለው ነገር ያለ አይመስለኝም ... ምናልባት ሳነብ የዘለልኩት ካለ እንጃ .. ያስቅ ነበረ ወይ የሚል ካለ በጣምምምምም ያስቃል .. እንዲሁም ይገርማል !!!! ሰዎቹ የመቃወም መብታቸውን ተጠቅመው የመሰላቸውን ብለዋል ... እኛንም ፋሲካን በሳቅ እንድናሳልፍ አርገዋል .. ዌል አትሊስት እኔን ... ለዚህ ደግሞ ውቃውን ከልብ አመሰግናለሁ Laughing Laughing Laughing Laughing

አባመላኩ ምን አሉ ? ምንም Laughing Laughing
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 367

PostPosted: Tue Apr 17, 2012 9:44 pm    Post subject: Reply with quote

ማነው አባ መላኩ ........? ስለአባመላኩ የተጻፈ ስላላየሁ ነው
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 1:00 am    Post subject: Reply with quote

ሪጮ
እኔ ..ጓድ ተድልሽን "እርስዎ " ማለትሽ አልተመቸኝም :: በቁም ነገርኛነቱ እና በሚጽፋቸው አስተያየቶች አክብረሸው ቢሆንም እንኳ እሱን ብቻ መርጠሽ ተገቢ አይደለም :: ሚዛናዊ ሆነሽ ለእኔም "ታላቁ " " የኔ ጌታ " "አንበሳዬ " "ዓይኑካ " " ዉቁቅቅይይዬ " ምናምን ብባል አኮ አይከፋኝም : አስቢበት ::

ወደ ጓድ ተድላ ሰመለስ ...ያቀረብክብኝ ቀይ መስመር የማለፍ ክስ መስረተ -ቢስ እና አግባብ ባለው ህግ ሊያስጠይቅህ እንድሚችል ላሳስብህ እወዳለሁ :: እንደ እውነቱ የሆነ እንደሆነ ....አንተ የፈደራል ኢትዮጵያን ህገ መንግስት በዋርካ ለመናድ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተህ እየሰራህ መሆኑን አገር እያወቀው ሳለ : እኔ አንድ ጭቁን አብዮተኛው የመጻፍ መብቴን ተጠቅሜ አንዲት ቪድዮ ከነማብራሪያው ፖስት ስላደረኩ አንተና ዋለልኝ ቀይ ቀለም እየተቀባበላችሁ መስመሮች በማስመር መሄጃ እንዳጣ ለማድረግ መሞከራችሁ ያካባቢውን ህብረተስብ አነጋግሮ ያለፈ ጉዳይ ሆኗል ::

ሌላው .ደግሞ .. ደጉሰው ሃይማኖትን በሚመለከት .... ሌሎችን ጋብዞ ሲወያየም ሆነ ሲያወያይ አላየሁም [pharaphrased በኔ ]በማለት ጽፈህ ስሜን በሃሰት ለማጥፋት ሞክረሃል :: ስለ እውነትና ፍትህ ብለን የሩቁን ፖስት በመተው የቅርቡን እንኳ ብናይ ...ደጉ ማንም ሳያዘውና ሳይጠይቀው በራሱ አነሳሽነት ..አንዲት ማሪያም ነኝ የምትል ሴትን ቪድዮ እንድናየው በማለት ...ከአስተያየቱ ጋር ለጥፎን ነበር :: እኔም በወቅቱ ቀዳሚ በመሆን አስተያየት ስጥቻለሁ :: ይህ አንክዋር ፍሬ ጉዳይ ባንተ የዋርካ ሬከርድ ክፍል አገላባጭነት ችሎታ ሳይታወቅ ቀረ ብሎ ማለት በእጀጉ ያዳግተኛል :: እንደ እውነቱ ከሆነ ያኔ ደጉ ፖስት ባረገው አስቂኝ ቪድዮ እና እኔ ባደረኩት መካከል ጭብጡ እና መቼቱ እንደልዩነት ካልተቆጠረ በቀር አስቂኝነቱ እና አስገራሚነቱ ተቀራራቢ ነው :: አንተ ግን የዋርካ ህግ አንቀጽ አንድ / መስመር አንድና ሁለት By participating on Warka, you agree, through your use of this forum, that you will not post any material which is false [መስመር የኔ ] የሚለውን ..ደጉ በሀይማኖት ጉዳይ ሌሎችን ሲያወያይ አላየሁም በማለት ሁለት ጊዜ ሁለት ቦታ ሁለት ነጭ ኩሽት በመዋሸት ህጉን ተላልፈሃል ::

ሁኔታውን አግባብ ላለው የፍትህ አካል መውሰድ ብችልም : ያለብህን የቤተሰብ ኃላፊነትና ህገ -መንግስቱን የመናድ ስራህን ግምት ወጥ በማስገባት ..ያቀረብከውን ቅደመ -ክስ ይቅርታ ተቀብዬ ለጊዜው በነጻ ተስነብተሃል ::

አባ ዉቃው
ፊርማ የሚነበብ ከታች
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 1:18 am    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ወደ ጓድ ተድላ ሰመለስ ...ያቀረብክብኝ ቀይ መስመር የማለፍ ክስ መስረተ -ቢስ እና አግባብ ባለው ህግ ሊያስጠይቅህ እንድሚችል ላሳስብህ እወዳለሁ :: እንደ እውነቱ የሆነ እንደሆነ ....አንተ የፈደራል ኢትዮጵያን ህገ መንግስት በዋርካ ለመናድ ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተህ እየሰራህ መሆኑን አገር እያወቀው ሳለ : እኔ አንድ ጭቁን አብዮተኛው የመጻፍ መብቴን ተጠቅሜ አንዲት ቪድዮ ከነማብራሪያው ፖስት ስላደረኩ አንተና ዋለልኝ ቀይ ቀለም እየተቀባበላችሁ መስመሮች በማስመር መሄጃ እንዳጣ ለማድረግ መሞከራችሁ ያካባቢውን ህብረተስብ አነጋግሮ ያለፈ ጉዳይ ሆኗል ::

ይህንን አንቀፅ አንብቤ እንኳን ሣልጨርስ Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing አጠገቤ ሰው ያለመኖሩ በጀኝ እንጂ "ምን ሆኖ እንዲህ እንባው ዱብ ዱብ እስኪል ድረስ ያሥቀዋል " ብሎ ሣያሽሟጥጠኝ አይቀርም ነበር :: ለዚህ ጨዋታህ ብዬ አይደል ትንሽ ተንኮስ ያደረግሁህ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ውቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ሌላው .ደግሞ .. ደጉሰው ሃይማኖትን በሚመለከት .... ሌሎችን ጋብዞ ሲወያየም ሆነ ሲያወያይ አላየሁም [pharaphrased በኔ ]በማለት ጽፈህ ስሜን በሃሰት ለማጥፋት ሞክረሃል :: ስለ እውነትና ፍትህ ብለን የሩቁን ፖስት በመተው የቅርቡን እንኳ ብናይ ...ደጉ ማንም ሳያዘውና ሳይጠይቀው በራሱ አነሳሽነት ..አንዲት ማሪያም ነኝ የምትል ሴትን ቪድዮ እንድናየው በማለት ...ከአስተያየቱ ጋር ለጥፎን ነበር :: እኔም በወቅቱ ቀዳሚ በመሆን አስተያየት ስጥቻለሁ :: ይህ አንክዋር ፍሬ ጉዳይ ባንተ የዋርካ ሬከርድ ክፍል አገላባጭነት ችሎታ ሳይታወቅ ቀረ ብሎ ማለት በእጀጉ ያዳግተኛል :: እንደ እውነቱ ከሆነ ያኔ ደጉ ፖስት ባረገው አስቂኝ ቪድዮ እና እኔ ባደረኩት መካከል ጭብጡ እና መቼቱ እንደልዩነት ካልተቆጠረ በቀር አስቂኝነቱ እና አስገራሚነቱ ተቀራራቢ ነው :: አንተ ግን የዋርካ ህግ አንቀጽ አንድ / መስመር አንድና ሁለት By participating on Warka, you agree, through your use of this forum, that you will not post any material which is false [መስመር የኔ ] የሚለውን ..ደጉ በሀይማኖት ጉዳይ ሌሎችን ሲያወያይ አላየሁም በማለት ሁለት ጊዜ ሁለት ቦታ ሁለት ነጭ ኩሽት በመዋሸት ህጉን ተላልፈሃል ::

እንዴ ኃይማኖትን እና 'cult' የሚሉትን ለይ እንጂ :: አሁንም ቢሆን ደጉ ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ሲያወያይ አላውቅም :: በተለያዩ ኃይማኖት -መሠል 'cults' ላይ ጥሩ ጥሩ መልሶች ይሠጣል : ለዚያውም የተነታራኪ አልቃሻ አማራሪዎችን አፍ እያስዘጋ :: ስለዚህ ወይ እኔ ኃይማኖት ነው ብዬ የምቀበለውና አንተ ውቃው ወንድሜ በጥቅሉ ኃይማኖት ነው ብለህ የምትቀበለው ይለያያል : ያለበለዚያም እኔ በደንብ አላስተዋልኩም ማለት ነው ::

ውቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ሁኔታውን አግባብ ላለው የፍትህ አካል መውሰድ ብችልም : ያለብህን የቤተሰብ ኃላፊነትና ህገ -መንግስቱን የመናድ ስራህን ግምት ወጥ በማስገባት ..ያቀረብከውን ቅደመ -ክስ ይቅርታ ተቀብዬ ለጊዜው በነጻ ተስነብተሃል ::

አባ ዉቃው
ፊርማ የሚነበብ ከታች

ፈጣሪያችን ሆይ ! እንዲህ ቃሊቲና ዴዴሣ ሣያጉሩ ይቅርታ የሚያደርጉ ደጋግ መሪዎችን አምጣልን !

ሌሎቻችሁ አሜን ! አትሉም ወይ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ወንድሜ ይመችህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 3:44 am    Post subject: Reply with quote

-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ማነው አባ መላኩ ........? ስለአባመላኩ የተጻፈ ስላላየሁ ነው

ጥሩ ጥያቄ ነው Laughing http://www.youtube.com/watch?v=itx845M21-4&context=C417655fADvjVQa1PpcFOlu1yO951A_lvDdVfnqs2dC00-pcCAw1U=

ኢንጆይ ! Laughing

ጋሽ ተድላ እና ውቄው ... አዎ እንደዚህ ነጻ ውይይት አሪፍ ነው ... Laughing ያቺ ማሪያም ነኝ ያለችቺው ሴቲዩ ታሪክና የአባ መላኩ ታሪክ እኮ ታዲያ ተመሳሳይነት አለው .. ሁለቱም ፈኒ ነው Laughing መቸም ውቃውም ሆነ ደጉ ይሄ ታሪክ አያምልጣቸው ብለው ዋርካ ሲያመጡት እንድንዝናናበት ነው .. ስለዚህ ቦታውነው ባይነኝ አሁንም

ውቃው ነብር አየኝ በል .. የምናባህ ቁልምጫ ነው ደግሞ .. መከበሪያህ ሲደርስ ጋሼ ትባላለህ ... አሁን በዚህ ይቀናል እስቲ ጋሽ ተድላ ... Laughing

ሰላም እደሩ እስቲ
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 4:03 am    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
ውቃው ነብር አየኝ በል .. የምናባህ ቁልምጫ ነው ደግሞ .. መከበሪያህ ሲደርስ ጋሼ ትባላለህ ... አሁን በዚህ ይቀናል እስቲ ጋሽ ተድላ ... Laughing

ሰላም እደሩ እስቲ

አንቺ ልጅ ደግሞ ቀጥተኛ ባህሪ ካለው ከወንድሜ ከውቃው ጋር ልታጣይኝ ነው Rolling Eyes "ነብር አየኝ በል " እያልሽ የምታስፈራሪው Embarassed ብታስቢውም አሁን አሁን እኮ ነብሩም በቀላል የሚገኝ እንዳይመስልሽ Cool ከኒውዮርክ -ብሮንክስ የእንሥሣት ግቢ ከሆነ ውቃው ይቀርባልና ቀድሞሽ ሠልፍ ይዞ (ዘቡሌውን ለምናምን የሚሆን ፍሉስ በጥሶላቸውም ቢሆን ) ነብሩን ተረክቦ በሠንሠለት እየጎተተ ይመጣልሻል Laughing :: ከሣን -ፋራንሲስኮ ከሆነ ግን ባታስቢው ይመረጣል ... እዚያ ያሉት 'ነምሮች ' የሰው ሥጋ የለመዱ ናቸውና አንችኑ ቁርስ እንዳያደርጉሽ Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1334

PostPosted: Thu Apr 19, 2012 4:27 pm    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ማነው አባ መላኩ ........? ስለአባመላኩ የተጻፈ ስላላየሁ ነው

ጥሩ ጥያቄ ነው Laughing http://www.youtube.com/watch?v=itx845M21-4&context=C417655fADvjVQa1PpcFOlu1yO951A_lvDdVfnqs2dC00-pcCAw1U=

ኢንጆይ ! Laughing

ጋሽ ተድላ እና ውቄው ... አዎ እንደዚህ ነጻ ውይይት አሪፍ ነው ... Laughing ያቺ ማሪያም ነኝ ያለችቺው ሴቲዩ ታሪክና የአባ መላኩ ታሪክ እኮ ታዲያ ተመሳሳይነት አለው .. ሁለቱም ፈኒ ነው Laughing መቸም ውቃውም ሆነ ደጉ ይሄ ታሪክ አያምልጣቸው ብለው ዋርካ ሲያመጡት እንድንዝናናበት ነው .. ስለዚህ ቦታውነው ባይነኝ አሁንም

ውቃው ነብር አየኝ በል .. የምናባህ ቁልምጫ ነው ደግሞ .. መከበሪያህ ሲደርስ ጋሼ ትባላለህ ... አሁን በዚህ ይቀናል እስቲ ጋሽ ተድላ ... Laughing

ሰላም እደሩ እስቲ

ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote:
የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን

_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Thu Apr 19, 2012 6:07 pm    Post subject: Reply with quote

[quote="ገልብጤ "]

ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote:
የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን

ይሆናል እንጃ Laughing ሰዎቹ አባ መላኩ ላይ ተቃውሞ አላቸው ምንክኒያቱ ቤተክርስቲያኒትዋ ከየትኛውም ወገን ሳይሆን ኒውትራል አቁዋም ነው ያለኝ አይነት ነው የሚከተለሉት ... ከሁለቱም ሲኖዶስ አንሆንም ገለልተኛ አቁዋም ነው ያለኝ ስላሉ በቀጥታ የለምንም ማንደርደሪያ ወያኔ ናቸው ብለዋቸዋል ... ስለዚህም ነው አባ መላኩ ምን አሉ ? ምንምምምም የመታው .. ግን እንደተመለከትኩት ምእመኑ በአሉን አክብሮ በሰላም ወደቤቱ ሲሄድ ነበር ... ተቃዋሚዎቹም በግምቴ መሰረት 5 ሰዎች መሰሉኝ ... የሚሰማው ድምጽ ከዛ በላይ አይመስልም .. ኤኒሁ ... ፈኒ ነው ... ፖለቲክሱ ምናምን ወይንም የተፈጠረው ነገር ሳይሆን ድርጊታቸው ፈኒ ነው ... ለኔ ! Laughing Laughing Laughing
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 19, 2012 7:42 pm    Post subject: Reply with quote

[quote="recho"]
ገልብጤ እንደጻፈ(ች)ው:

ሪጮ ...14:58 ላይ ቪድዮውን አቁሜ ሳነበው እንዲህ ይላል ሰውየው የያዘው መፈክር
Quote:
የጸሎት ቤታችን የወያኔ ካድሬወች መስብሰቢያ አይሁን

ይሆናል እንጃ Laughing ሰዎቹ አባ መላኩ ላይ ተቃውሞ አላቸው ምንክኒያቱ ቤተክርስቲያኒትዋ ከየትኛውም ወገን ሳይሆን ኒውትራል አቁዋም ነው ያለኝ አይነት ነው የሚከተለሉት ... ከሁለቱም ሲኖዶስ አንሆንም ገለልተኛ አቁዋም ነው ያለኝ ስላሉ በቀጥታ የለምንም ማንደርደሪያ ወያኔ ናቸው ብለዋቸዋል ... ስለዚህም ነው አባ መላኩ ምን አሉ ? ምንምምምም የመታው .. ግን እንደተመለከትኩት ምእመኑ በአሉን አክብሮ በሰላም ወደቤቱ ሲሄድ ነበር ... ተቃዋሚዎቹም በግምቴ መሰረት 5 ሰዎች መሰሉኝ ... የሚሰማው ድምጽ ከዛ በላይ አይመስልም .. ኤኒሁ ... ፈኒ ነው ... ፖለቲክሱ ምናምን ወይንም የተፈጠረው ነገር ሳይሆን ድርጊታቸው ፈኒ ነው ... ለኔ ! Laughing Laughing Laughing

ሪቾ :-

አንዳንድ ነገሮችን በሥሜት እዚህ ከመለጠፍሽ በፊት ግራ ቀኙን አጣሪ : በተለይ ደግሞ ኃይማኖትን በሚያህል የሰዎችን ውስጣዊ ስሜት በሚነካ ጉዳይ ::

አባ መላኩ ማን ናቸው ? በአባ ጳውሎስ ተሹመው በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንደኛው አንጃ ሊቀ -ጳጳስ (አቡነ ፋኑኤል ) ናቸው :: ለአንቺ 'ፈኒ ' ቢሆንም እነዚያ ሲቃወሙ የምታያቸው ምዕመናን ግን ሊያሣውቁ የሚፈልጉት ነገር አለ : ተቃውሟቸውም ለእነርሱ በቂ ምክንያት አለው :: የሚከተሉት ምንጮች ስለሁኔታው በጣም በጥቂቱ ፍንጮችን ይሠጡሻል ::

ምንጮች :-

1 ..... ገብር ኄር (ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ ) : Posted on November 9, 2011:: የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ ???

2 ..... ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች : Posted at 7:33 PM Wednesday, March 28, 2012. ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ የተናገሩት ::

ረጋ ብለሽ የምታስቢበት ልቦና ይስጥሽ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 1:50 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

ሪቾ :-

አንዳንድ ነገሮችን በሥሜት እዚህ ከመለጠፍሽ በፊት ግራ ቀኙን አጣሪ : በተለይ ደግሞ ኃይማኖትን በሚያህል የሰዎችን ውስጣዊ ስሜት በሚነካ ጉዳይ ::

አባ መላኩ ማን ናቸው ? በአባ ጳውሎስ ተሹመው በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንደኛው አንጃ ሊቀ -ጳጳስ (አቡነ ፋኑኤል ) ናቸው :: ለአንቺ 'ፈኒ ' ቢሆንም እነዚያ ሲቃወሙ የምታያቸው ምዕመናን ግን ሊያሣውቁ የሚፈልጉት ነገር አለ : ተቃውሟቸውም ለእነርሱ በቂ ምክንያት አለው :: የሚከተሉት ምንጮች ስለሁኔታው በጣም በጥቂቱ ፍንጮችን ይሠጡሻል ::

ምንጮች :-

1 ..... ገብር ኄር (ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ ) : Posted on November 9, 2011:: የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ ???

2 ..... ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች : Posted at 7:33 PM Wednesday, March 28, 2012. ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ የተናገሩት ::

ረጋ ብለሽ የምታስቢበት ልቦና ይስጥሽ ::

ተድላ
አይይይ እንግዲህ አሁንስ በዛ ! የፈለኩትን የማለት መብት አለኝ ... ለዛ መስሎኛል ቀይ መስመር ምናምን ብለህ የለቀለቅክበት ቦታ መጥቼ ምንም ያላወራሁት ... አክብሬ አንቱ ብዬ እንደያዝኩህ መቀጠል ከቻልን አሪፍ ካለዛ የምጽፈን አታንብ ኮመንትም አታርግ .... ስለጉዳዩ በጥልቀት ለማወቅ ምንም ፍላጎት የለኝም .. ማወቅ የምፈልገውን ያክል አውቂያለሁ ... ከዛ በላይ ያለውን አንተው ተመራመርና ድረስበት .. ለኔ ለጊዜው አያስፈልገኝም .. አሁንም ቪዲዩው ያስቃል .. ስቂያለሁ አሁንም እስቃለሁ ...!!! ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቴ ነው ... ! ፋይል ዘግቻለሁ ... እየመጣህ ለቅልቅ ..

አንተም እንደ እድሜህ እንድታስብ እግዜር ይርዳህ

ሪቾ Twisted Evil
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 2:01 am    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

ሪቾ :-

አንዳንድ ነገሮችን በሥሜት እዚህ ከመለጠፍሽ በፊት ግራ ቀኙን አጣሪ : በተለይ ደግሞ ኃይማኖትን በሚያህል የሰዎችን ውስጣዊ ስሜት በሚነካ ጉዳይ ::

አባ መላኩ ማን ናቸው ? በአባ ጳውሎስ ተሹመው በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንደኛው አንጃ ሊቀ -ጳጳስ (አቡነ ፋኑኤል ) ናቸው :: ለአንቺ 'ፈኒ ' ቢሆንም እነዚያ ሲቃወሙ የምታያቸው ምዕመናን ግን ሊያሣውቁ የሚፈልጉት ነገር አለ : ተቃውሟቸውም ለእነርሱ በቂ ምክንያት አለው :: የሚከተሉት ምንጮች ስለሁኔታው በጣም በጥቂቱ ፍንጮችን ይሠጡሻል ::

ምንጮች :-

1 ..... ገብር ኄር (ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ ) : Posted on November 9, 2011:: የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ ???

2 ..... ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች : Posted at 7:33 PM Wednesday, March 28, 2012. ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ የተናገሩት ::

ረጋ ብለሽ የምታስቢበት ልቦና ይስጥሽ ::

ተድላ
አይይይ እንግዲህ አሁንስ በዛ ! የፈለኩትን የማለት መብት አለኝ ... ለዛ መስሎኛል ቀይ መስመር ምናምን ብለህ የለቀለቅክበት ቦታ መጥቼ ምንም ያላወራሁት ... አክብሬ አንቱ ብዬ እንደያዝኩህ መቀጠል ከቻልን አሪፍ ካለዛ የምጽፈን አታንብ ኮመንትም አታርግ .... ስለጉዳዩ በጥልቀት ለማወቅ ምንም ፍላጎት የለኝም .. ማወቅ የምፈልገውን ያክል አውቂያለሁ ... ከዛ በላይ ያለውን አንተው ተመራመርና ድረስበት .. ለኔ ለጊዜው አያስፈልገኝም .. አሁንም ቪዲዩው ያስቃል .. ስቂያለሁ አሁንም እስቃለሁ ...!!! ደግሞ ህገመንግስታዊ መብቴ ነው ... ! ፋይል ዘግቻለሁ ... እየመጣህ ለቅልቅ ..

አንተም እንደ እድሜህ እንድታስብ እግዜር ይርዳህ

ሪቾ Twisted Evil

"የዘሬ ቢለቀኝ ያንዘርዝረኝ :" እያልሽ ነው Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing ወያኔነት የማይታፈርበት ዘመን ላይ ስለሆንን እንደ እነ ስልኪና ዳግማዊ ዋለልኝ ያሻሽን ማለት ትችያለሽ : በኋላ ማጣፊያው እንዳያጥርሽ እንጂ ::

በቤተክርስቲያን ላይ ለማፌዝ ከሆነ እንደ ቢዮንሴ አዲስ አበባ ሄደሽ ከአባ ገብረመድህን ጋር ዳንኪራሽን ማቅለጥ ትችያለሽ :: ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ላይ ማላገጥ አትችይም Twisted Evil Twisted Evil Twisted Evil Twisted Evil Twisted Evil Twisted Evil ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 2:05 am    Post subject: Reply with quote

አመት ያስቃል Laughing Laughing Laughing Laughing አይደለሁም እንጂ ብሆን እንኩዋን ወያኔ .. መብቴ ነው ... ዘሬን ቆጥረሀል ማለት ነው .. አሪፍ ነዋ ... ለማንኛውም .. ቤተሰቦቼ ሲያሳድጉኝ ከእንዳንተ አይነት ሰው ጋር አፍመካፈትን አብረው አላስተማሩኝም ... ስለዚህ እንዳከበርኩህ እዚህ ጋር እናብቃ .. ከንግዲህ ተድላ ሀይሉ ለሚባል ኒክኔም መልስ አልሰጥም .. በጣም ስለማከብርህ ..

ረጅም እድሜ ከመልካም ጤንነት ጋር ላንተ ! ቻው
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 2:15 am    Post subject: Reply with quote

ተዉ ልጆችዬ አትጣሉ :: በማርያም ይዣችኋለሁ ! ተዉ :: እንዴ .. እንዴት ነው ነገሩ ? ይህ እኮ የፍቅር መድረክ ነው :: ጠብ ይቅር : ጦሳችሁንም ይዞ ይሂድ :: ሰለውነት ከተባለ እኮ ....እንኳን አባ መላኩ ከተቃዋሚዎቻቸው ይቅርና ..አሜሪካ ያለው ሲኖዶስና ኢትዮጵያ ያለው ሲኖዶስ ሊታርቁ /ሊግባቡ ንግግር ላይ ናቸው :: እንዲያ ተወጋገዘው የተለያዩ አባቶች ..አሁን ለእርቅ በየጊዜው ለእርቅ ወደ አንድ መድረክ ሲመጡ ማየትን እኮ ትንሽ ነገር አርጋችሁ አትዩት :: አንድ ቀን መድሀኒያለም ሲፈቅድ ቤትክርስቲያኗ አንድ ትሆንና ሁሉ ነገር ያበቃል ::

አቡነ ጳውሎስ ወያኔ ናቸው ተብሎ ከተረጋገጠ በቃ አቡነ መርቆሪዮስም ደርግ ኢሠፓ ናቸው የሚለው ያስኬዳል :: እምነት ግዴታ ሳይሆን ነጻነት ነው :: አሁን እኮ ኢትዮጵያ ያለው የኦርቶዶክስ ምዕመን በጠቅላላው አቡነ ጳውሎስ ወደ ሚያስተዳድሩት ቤተክርስቲያን ይሄዳል ይገለገላል :: በአሜሪካ ያለው ደግሞ ባብዛኛው በአቡነ ማርቆሪዮስ ወደሚተዳደሩት ይሄዳል :: ሁሉንም ማንም አላስገደዳቸውም ::

ሌላው ደግሞ አሁን ያሉት አባቶች ዘልዓለማዊ አይደሉም :: ሳያልፉ ሁለቱም ሲኖዶሶች ተስማምተው አቡነ መርቆሪዮስም ሆነ አቡነ ጳውሎስ ከስልጣን ወርደው ..በምርጫም ሆነ በስምምነት አንድ ፓትሪያርክ መርጠው ...ለወደፊት ችግር እንዳይግጥም የቤትክርስቲያኖንም ህግ አሻሽለው ...ቢያልፉ በክርስቶስ ቀኝ አይውሉም ትላላችሁ ?!
ቤተክርስቲያኗስ ከፍ ከፍ አትልም ?! ምዕመኑስ አያክብራቸውም ? ፍቅርስ አይወርድም ?

የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 1 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia