WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
4 ሰዎችን ህይወት ለቀጠፈው ግጭት ተጠያቂው ማነው ? VOA
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue May 01, 2012 2:54 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
በዚህ ጉዳይ ላይ ሚስተር -x እና ጋሽ ተድላን አጥብቄ እቃወማለሁ :: የምታወሩት ነገር ትክክለኛ እንዳልሆነ አምናለሁ :: ትክክለኛም ቢሆንም ግን አሁን ባሉት መጠነ ሰፊ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮች አንጻር የምንሰጠው አስተያየት እና ሀሳብ እየከሰሳችኋቸው ያላችሁትን ወገኖች ለዘብተኛ የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል እንጂ የሚያስቆጣቸው መሆን የለበትም :: እሁንም ግን ካለች ታሪካዊ ግንዛቤ እና በእድሜየም ከደረስኩበት ማህበራዊ ግንኙነት አንፃር በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የጥላቻ መንፈስ ላይ የተመሰረተ እስልምና ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረት ይኖረዋል ብየ አልገምትም :: ግብዐቱም ታሪካዊ መሰረቱም የለውም :: ህወሀት ሊፈጥር የሞከረው አክራሪነትም ይሁን ለዘብተኛ አፍቃሪ ምዕራብ እስልምና ተቃውሞ እየገጠመው እንደሆነ የሚያሳይ ነገር ነው እያየን ያለነው ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

አዬ ናፖሊዮን ዳኘ :-

ትክክል ያልሆንበትን ምክንያቱን ከእነ መረጃው አሣዬንና ምናልባት ልታሣምነን ትችል ይሆናል :: 'political correctness' ብለህ ለዘብተኛ መሆን ግን ኢትዮጵያን አያድናትም ::

ለመሆኑ ግራኝ አህመድ የሚባል ከአዳል -ሱማሌ የተነሣ ጦረኛ በቱርኮችና በአረቦች ድጋፍ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሠውን የጥፋት ታሪክ አታውቅም ? እኒህ "ወያኔን እንቃወማለን " የሚሉት የወሃቢያ ዕምነት አራማጅ አክራሪ እስላሞች ለግራኝ አህመድ በጦር ሜዳ የወደቀበት ሥፍራ እንፍራዝ (ደምቢያ - ጣና አጠገብ : ጎንደር ክፍለ ሀገር ) ሐውልት ሊሠራለት ይገባል ብለው ብዙ ብጥብጥ አስነስተው እንደነበረና በእነ መብራቱ ገብረሕይወት (በረከት ስምዖን ) ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው ታውቃለህ ?

አቋምህን መርምር ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue May 01, 2012 3:21 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

በህግ አምላክ ጋሽ ተድላ ! ስለ አህመድ ግራኝ ያለህ ግንዛቤ ራሱ ትክክል አይደለም :: ፕሮፌሰር መርድ ያደረጉት ምርመር እና ያስተማሩን አንተ ከምትለው በጣም የተለየ ነው :: አሁን በእጄ ላይ ማቴሪያሉ የለኝም :: ግን የአህመድ ግራኝ ጦርነት አንተ እንደምትለው አይደለም ::

አሁን ሀገር ቤት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ በዜና ማሰራጫ የአህባሽን በኢትዮጵያ እስልምና ላይ መጫን በመቃወም ከሚደረገው ተቃውሞ ውጪ ብዙ መረጃ የለኝም :: እያልኩ ያለሁት ግን የእስልምና አክራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊም ሆነ ማህበራዊ መሰረት የለውም ነው ::

ባጋጣሚ ግጪት ቢነሳ እንኳን በተለያየ ሁኔታ ሊነሳ እንደሚችል ግጪት ወስዶ ግጭቱን ለመፍታት የበሰለ የኮንፍሊክት ሪሶሉሽን አያያዝ ነው እንጂ የሚያስፈልገው ይሄን ነገር ማራገብ ---ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር --ልድገመው ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር ---ትርጉም የሌለው ብቻ ሳይሆን በጣም ጎጂ ነው ::

እንደውም እስልምናው ውስጥ ያሉትን አመራሮች ( በየከተማው ) በማህበራዊ ደረጃ መቅረብ እና በጋራ መስራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ መስራት ይቻላል ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
በዚህ ጉዳይ ላይ ሚስተር -x እና ጋሽ ተድላን አጥብቄ እቃወማለሁ :: የምታወሩት ነገር ትክክለኛ እንዳልሆነ አምናለሁ :: ትክክለኛም ቢሆንም ግን አሁን ባሉት መጠነ ሰፊ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ችግሮች አንጻር የምንሰጠው አስተያየት እና ሀሳብ እየከሰሳችኋቸው ያላችሁትን ወገኖች ለዘብተኛ የሚያደርግ ቢሆን ይመረጣል እንጂ የሚያስቆጣቸው መሆን የለበትም :: እሁንም ግን ካለች ታሪካዊ ግንዛቤ እና በእድሜየም ከደረስኩበት ማህበራዊ ግንኙነት አንፃር በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የጥላቻ መንፈስ ላይ የተመሰረተ እስልምና ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረት ይኖረዋል ብየ አልገምትም :: ግብዐቱም ታሪካዊ መሰረቱም የለውም :: ህወሀት ሊፈጥር የሞከረው አክራሪነትም ይሁን ለዘብተኛ አፍቃሪ ምዕራብ እስልምና ተቃውሞ እየገጠመው እንደሆነ የሚያሳይ ነገር ነው እያየን ያለነው ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

አዬ ናፖሊዮን ዳኘ :-

ትክክል ያልሆንበትን ምክንያቱን ከእነ መረጃው አሣዬንና ምናልባት ልታሣምነን ትችል ይሆናል :: 'political correctness' ብለህ ለዘብተኛ መሆን ግን ኢትዮጵያን አያድናትም ::

ለመሆኑ ግራኝ አህመድ የሚባል ከአዳል -ሱማሌ የተነሣ ጦረኛ በቱርኮችና በአረቦች ድጋፍ በኢትዮጵያ ላይ ያደረሠውን የጥፋት ታሪክ አታውቅም ? እኒህ "ወያኔን እንቃወማለን " የሚሉት የወሃቢያ ዕምነት አራማጅ አክራሪ እስላሞች ለግራኝ አህመድ በጦር ሜዳ የወደቀበት ሥፍራ እንፍራዝ (ደምቢያ - ጣና አጠገብ : ጎንደር ክፍለ ሀገር ) ሐውልት ሊሠራለት ይገባል ብለው ብዙ ብጥብጥ አስነስተው እንደነበረና በእነ መብራቱ ገብረሕይወት (በረከት ስምዖን ) ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው ታውቃለህ ?

አቋምህን መርምር ::

ተድላ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue May 01, 2012 3:41 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

--------------

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 10:38 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue May 01, 2012 4:13 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
በህግ አምላክ ጋሽ ተድላ ! ስለ አህመድ ግራኝ ያለህ ግንዛቤ ራሱ ትክክል አይደለም :: ፕሮፌሰር መርድ ያደረጉት ምርመር እና ያስተማሩን አንተ ከምትለው በጣም የተለየ ነው :: አሁን በእጄ ላይ ማቴሪያሉ የለኝም :: ግን የአህመድ ግራኝ ጦርነት አንተ እንደምትለው አይደለም ::

ስለ ግራኝ አህመድ የጥፋት ወረራ ሟቹ ፕሮፌሠር መርዕድ ወልደአረጋይ ካደረጉት 'ማርክሣዊ -ሌኒናዊ -ስታሊናዊ ' የታሪክ ምርምር ጽሑፍ ይልቅ በጊዜው የግራኝ አህመድ አማካሪና ታሪክ ጸሐፊ የነበረው ሺሃብ አድ -ዲን አሕመድ ቢን አብደልቃድር የጻፈውን የዐይን እማኝነት አምናለሁ ::
ምንጭ :- Sihab ad-Din Ahmad bin 'Abd al-Qader b. Salim b. Uthman, (). Futuh Al-Habasha: The Conquest of Abyssinia (Futuh Al-Habasa). Translated by Paul Lester Stenhouse (September 2003).

እኔም : አንተም ታሪክን የተማርነው ምንም አገራቸውን ቢወድዱም በማርክሣዊ -ሌኒናዊ -ስታሊናዊ የፖለቲካ ምኅዳር ሥር ሆነው ታሪክን ለማስተማር በሚጣጣሩ ለዘብተኛ የምዕራብ -ቀመስ ትምህርት ምሁራን ነው :: ስለ አገራቸው የተጻፈውን ታሪክ ያጠኑት በፖርቱጋሎች : በእስፓኞች : በእንግሊዞች : በፈረንሣዮች : በጀርመኖች : በጣሊያኖች : በአረቦችና በሌሎችም የውጭ ዜጎች በተጻፉ መጻሕፍት ዋቢነት ላይ ተመርኩዘው ስለሆነ ከታሪካዊ ዳራው የመራቅና ሲብስም በየወቅቱ ከሚነሣው የፖለቲካ ትኩሣት አንፃር ፖለቲካዊ ትንታኔ ትክክለኛነት ላይ ያመዝናሉ :: ስለዚህ አንተ እንዴት እንደተረዳኸው አሣውቀን እንጂ የፕሮፌሠር መርዕድ ጥብቅና አያዋጣህም :: ስለታሪኩ በቂ መረጃ ከሌለህ በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን የገንዘብ ሚኒስትርና በኋላም የዘውድ አማካሪ የነበሩት ማቹ አቶ ይልማ ዴሬሣም በአማርኛ ቋንቋ የጻፉት መጽሐፍ አለ :: እኒህን ሁለቱን ብታንብ ምናልባት ተጨማሪ ዕይታ ይፈጥሩልሃል ብዬ እገምታለሁ ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
አሁን ሀገር ቤት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ በዜና ማሰራጫ የአህባሽን በኢትዮጵያ እስልምና ላይ መጫን በመቃወም ከሚደረገው ተቃውሞ ውጪ ብዙ መረጃ የለኝም :: እያልኩ ያለሁት ግን የእስልምና አክራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊም ሆነ ማህበራዊ መሰረት የለውም ነው ::

የአህባሽንና የወሃቢያን ዕምነቶች የሚያስፋፉት ሁለት የአደሬ አክራሪ እስላሞች ናቸው :: ስለማንነታቸው የሚገልፅ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀደም ባለው መልዕክቴ ጠቁሜያለሁ ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ባጋጣሚ ግጪት ቢነሳ እንኳን በተለያየ ሁኔታ ሊነሳ እንደሚችል ግጪት ወስዶ ግጭቱን ለመፍታት የበሰለ የኮንፍሊክት ሪሶሉሽን አያያዝ ነው እንጂ የሚያስፈልገው ይሄን ነገር ማራገብ ---ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር --ልድገመው ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር ---ትርጉም የሌለው ብቻ ሳይሆን በጣም ጎጂ ነው ::

አዬ ናፖሊዮን :-

የምን ስለወደፊቱ በአጋጣሚ ስለሚነሣ ግጭት ታወራለህ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes እነርሱ እኮ ቀደም ብለው ኢትዮጵያን የአክራሪ እስላሞች አገር ለማድረግ ዕቅድ ነድፈው ጨርሠዋል :: በየጊዜው ደግሞ የተግባር ዕቅዶቻቸውን ይከልሣሉ :: ለመሆኑ 1983-87 .. በነበረው ጊዜ የሱዳን እስላማዊ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ 19 የማያንሱ ቆንሲላዎችን ከፍቶ ምን ያከናውን እንደነበረ አታውቅም ነበር ? ያኔ የት ነበር የምትኖረው ? በጅማና ኢሉባቦር ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ላይ የነበሩትን ካህናት 'አላህ -ክበር ' እያሉ ሲጨፈጭፉ የነበሩት እነማን ሆኑና Rolling Eyes በአዲስ አበባ : በጎንደር : በደሴ : በስልጤ : በሐረር : በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ክርስቲያኖችን በአደባባይ በግፍ የሚጨፈጭፉና ቤተክርስቲያን የሚያቃጥሉት የድሮዎቹ ሰላማዊ እስላሞች መሠሉህ እንዴት ? በአጠቃላይ የምንወያየው እኮ ዛሬ ስለተጀመረ ጉዳይ አይደለም : ከወያኔ አገዛዝ ጋር እኩል ስለተመሠረተና አብሮ ስለጎለመሠ አጥፊ የአክራሪ እስላሞች እንቅስቃሴ እንጂ Exclamation

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
እንደውም እስልምናው ውስጥ ያሉትን አመራሮች ( በየከተማው ) በማህበራዊ ደረጃ መቅረብ እና በጋራ መስራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ መስራት ይቻላል ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

በሕይወት መቆየት ከፈለግህ ከእነዚህ ሠሞኑን "ወያኔን እንቃወማለን " ከሚሉት አክራሪ የወሃቢያ ዕምነት ተከታይ አክራሪ እስላሞች አርባ ክንድ ራቅ :: ያለበለዚያ ሠይፋቸውን የሚመዙት በመጀመሪያ በአንተ እና መሠል የዋሃን ላይ ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue May 01, 2012 4:50 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

ሰላም ጋሽ ተድላ

ፕሊስ ስለ ፕሮፌሰር መርዕድ የምታውቅ አይመስልም ከምታወራው ነገር :: በፍጹም የኮሚኒስትነት ዝንባሌ ያላየሁባቸው ሁነኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው :: እንዲያውም የሳቸው አይዲዮሎጂ ኢትዮጵያ ናት የምትመስለኝ :: ብዙ በውጪ ሀገር ዮኒቨርስቲዎች የማስተማር ዕድል ሲሰጣቸው ሀገሬን አለቅም ብለው ያገለገሉ ሰው እንደሆኑ ነው የማውቀው :: በባህሪያቸውም ያሳዮ የነበሩት ነገር ይሄው ነው :: እጂግ በጣም የተከበሩ ነበሩ በዲፓርትመንቱም በዮኒቨርሲቲውም ---እስከማውቀው ::

ስለ አህመድ ግራኝ ጦርነት በምንጭነት የጠቀስከው የሺሀበዲን ስራ ልክ ነው ቀዳሚ የሆነ ምንጪ ነው ልክ የነገስታቱ መዋዕለ ዜና በምንጭነት እንደሚያገለግለው :: ከዚያ ውጭ የበቃ የነቃ የታሪክ ትንተና አይደለም ::የእስልምና አክራሪነቱን በተመለከተ -ፍጹም እንግዳ ነው :: 83-87 ያልከውን ሁነት ፈጽሞ አላውቀውም :: የሰጠኸው ማብራሪያ ሁሉ ለኔ እንግዳ ነው ::

እናመሰግንሀለን :-

ከሀገር ቤት ከወጣሁ አስር ደፍኛለሁ :: ድሮ በሰላታቸው እና ባንዳንድ ጉዳዮች እየተቀላለድን በእኛም እየቀለዱ አብረውኝ ያደጉ ሙስሊም ልጆች ዛሬ ድረስ እንገናኛለን :: ምንም የተለየ መንፈስ አላየሁባቸውም :: እርግጥ ሀገር ቤት ስደውል የእስልምና አማኞች ጽንፍ እየያዙ ነው የሚል ነገር እሰማ ነበር ...አጥብቄ ግን አልጠየኩም :: ችግሩ በዚህ ደረጃ ስላልመሰለኝ :: እናንተ በምትሉት ደረጃ ደርሶ ከሆነ በእርግጥም አሳሳቢ ነው :: መፍትሄው ግን አሁንም የጋራ ግንዛቤን መፍጠር (በእምነት ሳይነቃቀፉ በሰላም በመቻቻል መኖር ) የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸቱ ነው የሚሻለው :: ከዛ ውጪ ወደ ግብ ግቡ የሚወስድ መንገድ ከመረጥን ህወሀት የፈጠረውን የዘር ችግር በማያዳግም መልኩ ተፈቶ ሳያልቅ እንደገና ሌላ ተጨማሪ እና በዚህ ጊዜ ያልቃል የሚባል ነገር ውስጥ ነው የሚገባው :: ምክንያቱም እምነት የጎሳን መስመር ሁሉ የማጥፋት ዝንባሌ ስለሚኖረው ነገሩ በሁለት ትልልቅ ነገር መሀል የሚፈጠር የማያባራ ጉዳይ ነው የሚሆነው :: እስልምናም አምስት ሳንቲም አይጠቀምም ከእንደዚህ አይነቱ አካሄድ ::

ለማንኛውም የበለጠ እስከማውቅ ድረስ በጉዳዮ ላይ ብዙ ከመናገር መስማቱ ይሻላል ለጊዜው ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
በህግ አምላክ ጋሽ ተድላ ! ስለ አህመድ ግራኝ ያለህ ግንዛቤ ራሱ ትክክል አይደለም :: ፕሮፌሰር መርድ ያደረጉት ምርመር እና ያስተማሩን አንተ ከምትለው በጣም የተለየ ነው :: አሁን በእጄ ላይ ማቴሪያሉ የለኝም :: ግን የአህመድ ግራኝ ጦርነት አንተ እንደምትለው አይደለም ::

ስለ ግራኝ አህመድ የጥፋት ወረራ ሟቹ ፕሮፌሠር መርዕድ ወልደአረጋይ ካደረጉት 'ማርክሣዊ -ሌኒናዊ -ስታሊናዊ ' የታሪክ ምርምር ጽሑፍ ይልቅ በጊዜው የግራኝ አህመድ አማካሪና ታሪክ ጸሐፊ የነበረው ሺሃብ አድ -ዲን አሕመድ ቢን አብደልቃድር የጻፈውን የዐይን እማኝነት አምናለሁ ::
ምንጭ :- Sihab ad-Din Ahmad bin 'Abd al-Qader b. Salim b. Uthman, (). Futuh Al-Habasha: The Conquest of Abyssinia (Futuh Al-Habasa). Translated by Paul Lester Stenhouse (September 2003).

እኔም : አንተም ታሪክን የተማርነው ምንም አገራቸውን ቢወድዱም በማርክሣዊ -ሌኒናዊ -ስታሊናዊ የፖለቲካ ምኅዳር ሥር ሆነው ታሪክን ለማስተማር በሚጣጣሩ ለዘብተኛ የምዕራብ -ቀመስ ትምህርት ምሁራን ነው :: ስለ አገራቸው የተጻፈውን ታሪክ ያጠኑት በፖርቱጋሎች : በእስፓኞች : በእንግሊዞች : በፈረንሣዮች : በጀርመኖች : በጣሊያኖች : በአረቦችና በሌሎችም የውጭ ዜጎች በተጻፉ መጻሕፍት ዋቢነት ላይ ተመርኩዘው ስለሆነ ከታሪካዊ ዳራው የመራቅና ሲብስም በየወቅቱ ከሚነሣው የፖለቲካ ትኩሣት አንፃር ፖለቲካዊ ትንታኔ ትክክለኛነት ላይ ያመዝናሉ :: ስለዚህ አንተ እንዴት እንደተረዳኸው አሣውቀን እንጂ የፕሮፌሠር መርዕድ ጥብቅና አያዋጣህም :: ስለታሪኩ በቂ መረጃ ከሌለህ በቀዳማዊ ኃይለሥላሤ የአገዛዝ ዘመን የገንዘብ ሚኒስትርና በኋላም የዘውድ አማካሪ የነበሩት ማቹ አቶ ይልማ ዴሬሣም በአማርኛ ቋንቋ የጻፉት መጽሐፍ አለ :: እኒህን ሁለቱን ብታንብ ምናልባት ተጨማሪ ዕይታ ይፈጥሩልሃል ብዬ እገምታለሁ ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
አሁን ሀገር ቤት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ በዜና ማሰራጫ የአህባሽን በኢትዮጵያ እስልምና ላይ መጫን በመቃወም ከሚደረገው ተቃውሞ ውጪ ብዙ መረጃ የለኝም :: እያልኩ ያለሁት ግን የእስልምና አክራሪነት ኢትዮጵያ ውስጥ ታሪካዊም ሆነ ማህበራዊ መሰረት የለውም ነው ::

የአህባሽንና የወሃቢያን ዕምነቶች የሚያስፋፉት ሁለት የአደሬ አክራሪ እስላሞች ናቸው :: ስለማንነታቸው የሚገልፅ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀደም ባለው መልዕክቴ ጠቁሜያለሁ ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ባጋጣሚ ግጪት ቢነሳ እንኳን በተለያየ ሁኔታ ሊነሳ እንደሚችል ግጪት ወስዶ ግጭቱን ለመፍታት የበሰለ የኮንፍሊክት ሪሶሉሽን አያያዝ ነው እንጂ የሚያስፈልገው ይሄን ነገር ማራገብ ---ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር --ልድገመው ከኢትዮጵያ ጥቅም አንጻር ---ትርጉም የሌለው ብቻ ሳይሆን በጣም ጎጂ ነው ::

አዬ ናፖሊዮን :-

የምን ስለወደፊቱ በአጋጣሚ ስለሚነሣ ግጭት ታወራለህ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes እነርሱ እኮ ቀደም ብለው ኢትዮጵያን የአክራሪ እስላሞች አገር ለማድረግ ዕቅድ ነድፈው ጨርሠዋል :: በየጊዜው ደግሞ የተግባር ዕቅዶቻቸውን ይከልሣሉ :: ለመሆኑ 1983-87 .. በነበረው ጊዜ የሱዳን እስላማዊ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ 19 የማያንሱ ቆንሲላዎችን ከፍቶ ምን ያከናውን እንደነበረ አታውቅም ነበር ? ያኔ የት ነበር የምትኖረው ? በጅማና ኢሉባቦር ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ላይ የነበሩትን ካህናት 'አላህ -ክበር ' እያሉ ሲጨፈጭፉ የነበሩት እነማን ሆኑና Rolling Eyes በአዲስ አበባ : በጎንደር : በደሴ : በስልጤ : በሐረር : በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ክርስቲያኖችን በአደባባይ በግፍ የሚጨፈጭፉና ቤተክርስቲያን የሚያቃጥሉት የድሮዎቹ ሰላማዊ እስላሞች መሠሉህ እንዴት ? በአጠቃላይ የምንወያየው እኮ ዛሬ ስለተጀመረ ጉዳይ አይደለም : ከወያኔ አገዛዝ ጋር እኩል ስለተመሠረተና አብሮ ስለጎለመሠ አጥፊ የአክራሪ እስላሞች እንቅስቃሴ እንጂ Exclamation

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
እንደውም እስልምናው ውስጥ ያሉትን አመራሮች ( በየከተማው ) በማህበራዊ ደረጃ መቅረብ እና በጋራ መስራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ መስራት ይቻላል ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

በሕይወት መቆየት ከፈለግህ ከእነዚህ ሠሞኑን "ወያኔን እንቃወማለን " ከሚሉት አክራሪ የወሃቢያ ዕምነት ተከታይ አክራሪ እስላሞች አርባ ክንድ ራቅ :: ያለበለዚያ ሠይፋቸውን የሚመዙት በመጀመሪያ በአንተ እና መሠል የዋሃን ላይ ነው ::

ተድላ

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሚስተር -x

ውሃ አጠጪ

Joined: 02 Feb 2009
Posts: 1257

PostPosted: Tue May 01, 2012 4:56 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ናፖልዮን

ከአገር ከወጣህና ሳትመለስ ከቆየህ ብዙ ጊዜ ያደረግህ ይመስለኛል :: ዋሀቢዝም ዘልቆ ገብቷል :: ያኔ የምናውቀው እስልምና አይደለም ባገራችን ያለው :: እነሱ ጾመው እኛ አብረናቸው እናፈጥር የነበረበት : አብረን ካንድ መሶብ የቀረብንበት ዘመን ላይመለስ ሄዷል :: የደርግ ጥይት ጔደኞቼን ሰለሞንንና ኑረዲንን በአንድ ቀን ሲጥል በሺህ የሚቆጠር በሰልፍ ለቀብር የወጣው ወጣት ሀይማኖት አልነበረውም :: ባንድ ቀን ከሰዓት በፊት ኑረዲንን ከሰዓት በኌላ ሰለሞንን ቀብረናል በየሀይማኖታቸው የቀብር ቦታ እየዘመርን ::

ሰለሞን ለምን ተገደለ
በትግል ነጻነት ይገኛል ስላለ
ኑረዲን ለምን ተገደለ
በትግል ነጻነት ይገኛል ስላለ

ዛሬ የለም :: ጉርብትና ቀርቷል :: ድሮ የምታውቃቸው የነኑረዲን ቤተሰቦች ወስነው ክርስቲያኑን አግለለውታል ከንግድ ልውውጥ ባሻገር :::

መርዙን ሆን ብሎ ያስገባው ወያኔ ነው :: የክርስቲያኑ ልብ አልተለወጠም :: እስላሙ ግን የሚነግርህ ""ሀይማኖቴን አላውቀውም ነበር አሁን ይሄ መንግስት ነጻነት ሲሰጠን ነው እውነተኛውን ትምህርት የተማርነው ብለው አረፉ :: አረብ ከጥንት የደገሰልንን ይተገብሩት ጀመር ::

በክርስቲያኑ ላይ በግብጽ እንደሚያደርጉት በኢትዮጵያ ማድረግ ጀመሩ :: አሁን አይነካብን የሚሉት ዋሀቢዝም ይሄ ነው :: አላማውም ኢትዮጵያን ለሸሪያ ሕግ ማዘጋጀት ነው ::

አበቃሁ ::
_________________
እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ …የማንየ ለትርስዐኒ። ወይጥጋዕ ልሳንየ ባጉርዔየ ለእሙ ኢተዘከርኩኪ!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ናፖሊዮን ዳኘ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 18 Apr 2008
Posts: 1878

PostPosted: Tue May 01, 2012 5:20 am    Post subject: Reply with quote

ስላም

በአስር አመት ውስጥ በዚህ ደረጃ ለውጥ ማየት እጂግ በጣም የሚገርም ነው ::

እንግዲህ የሆነው ሆኗል :: የምናውቀው "ኢትዮጵያዊ እስልምና ላይመለስ ሄዷል ብለን " ግን ማሰብ የመፍትሄ አቅጣቻችንን ያስተን ይመስለናል :: የኔ ጥያቄ ስለዚህ እንደምትሉት እስልምና በዛ ደረጃ ከሯል ብንል መፍትሄው ምንድን ነው ?? ነገሩ የሚላላበት መንገድ ካልተፈለገ እኮ ነገ እንደናይጀሪያ መሆን ሊመጣ ነው :: መፍትሄው ምንድን ነው ??

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ሚስተር -x እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ናፖልዮን

ከአገር ከወጣህና ሳትመለስ ከቆየህ ብዙ ጊዜ ያደረግህ ይመስለኛል :: ዋሀቢዝም ዘልቆ ገብቷል :: ያኔ የምናውቀው እስልምና አይደለም ባገራችን ያለው :: እነሱ ጾመው እኛ አብረናቸው እናፈጥር የነበረበት : አብረን ካንድ መሶብ የቀረብንበት ዘመን ላይመለስ ሄዷል :: የደርግ ጥይት ጔደኞቼን ሰለሞንንና ኑረዲንን በአንድ ቀን ሲጥል በሺህ የሚቆጠር በሰልፍ ለቀብር የወጣው ወጣት ሀይማኖት አልነበረውም :: ባንድ ቀን ከሰዓት በፊት ኑረዲንን ከሰዓት በኌላ ሰለሞንን ቀብረናል በየሀይማኖታቸው የቀብር ቦታ እየዘመርን ::

ሰለሞን ለምን ተገደለ
በትግል ነጻነት ይገኛል ስላለ
ኑረዲን ለምን ተገደለ
በትግል ነጻነት ይገኛል ስላለ

ዛሬ የለም :: ጉርብትና ቀርቷል :: ድሮ የምታውቃቸው የነኑረዲን ቤተሰቦች ወስነው ክርስቲያኑን አግለለውታል ከንግድ ልውውጥ ባሻገር :::

መርዙን ሆን ብሎ ያስገባው ወያኔ ነው :: የክርስቲያኑ ልብ አልተለወጠም :: እስላሙ ግን የሚነግርህ ""ሀይማኖቴን አላውቀውም ነበር አሁን ይሄ መንግስት ነጻነት ሲሰጠን ነው እውነተኛውን ትምህርት የተማርነው ብለው አረፉ :: አረብ ከጥንት የደገሰልንን ይተገብሩት ጀመር ::

በክርስቲያኑ ላይ በግብጽ እንደሚያደርጉት በኢትዮጵያ ማድረግ ጀመሩ :: አሁን አይነካብን የሚሉት ዋሀቢዝም ይሄ ነው :: አላማውም ኢትዮጵያን ለሸሪያ ሕግ ማዘጋጀት ነው ::

አበቃሁ ::

_________________
ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue May 01, 2012 5:29 am    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ጋሽ ተድላ

ፕሊስ ስለ ፕሮፌሰር መርዕድ የምታውቅ አይመስልም ከምታወራው ነገር :: በፍጹም የኮሚኒስትነት ዝንባሌ ያላየሁባቸው ሁነኛ ኢትዮጵያዊ ናቸው :: እንዲያውም የሳቸው አይዲዮሎጂ ኢትዮጵያ ናት የምትመስለኝ :: ብዙ በውጪ ሀገር ዮኒቨርስቲዎች የማስተማር ዕድል ሲሰጣቸው ሀገሬን አለቅም ብለው ያገለገሉ ሰው እንደሆኑ ነው የማውቀው :: በባህሪያቸውም ያሳዮ የነበሩት ነገር ይሄው ነው :: እጂግ በጣም የተከበሩ ነበሩ በዲፓርትመንቱም በዮኒቨርሲቲውም ---እስከማውቀው ::

ኧረ ተው ናፖሊዮን :-
የዩኒቨርሲቲውን የታሪክ ምሁራን ከደርግ እስከ ወያኔ የአገዛዝ ዘመኖች ድረስ ተግባራቸውን ከሞላ ጎደል አውቃለሁ : ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልገኝም :: ለመሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁራን አንድ ወጥ የሆነ የኢትዮጵያ ታሪክ ማስተማሪያ መጽሐፍ ማዘጋጀት ሣይችሉ እንዴት ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እነርሱ ብቻ የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ ታሪክ ዕውቀት ሊቆች ተደርገው ሊወሠዱ ይችላሉ ? ሟቾችን ጭምር ወቃሽ አያድርገኝ እንጂ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም "ጻፍኩት " ብለው በዚህ ዓመት ያሣተሙት 'ትግላችን ' መጽሐፍ ታሪክ ጸሐፊዎች :-
    3 ዶክተር (በኋላ ፕሮፌሠር ) መርዕድ ወልደአረጋይ (ነፍስ ይማር - በታኅሣሥ 2002 .. አርፈዋል )
    4 ዶክተር (አሁን ፕሮፌሠር ) ባህሩ ዘውዴ
    5 ዶክተር (በኋላ ፕሮፌሠር ) ብርሃኑ አበበ (ነፍስ ይማር በሰኔ 2000 .. አርፈዋል )
    6 አቶ (አሁን ፕሮፌሰር ) ሽፈራው በቀለ

ነበሩ :: ሥም መጥቀስ አያስፈልግም እንጂ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ የኢትዮጵያን ታሪክ አስተምረውኛል :: ሌሎችንም ከታሪክ ትምህርት ጋር በተያያዘ አቋማቸውን አጥርቼ አውቃለሁ :: ፕሮፌሠር መርዕድ በእርግጥ በኢትዮጵያዊነታቸው አጥብቀው የሚያምኑ እንደነበሩ አምናለሁ (አፈሩ ይቅለላቸውና ) :: ማለት ግን የሚያምኑበት ርዕዮተ -ዓለም ኢትዮጵያዊ -ብሔረተኝነት ነበረ አያስብልም ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ስለ አህመድ ግራኝ ጦርነት በምንጭነት የጠቀስከው የሺሀበዲን ስራ ልክ ነው ቀዳሚ የሆነ ምንጪ ነው ልክ የነገስታቱ መዋዕለ ዜና በምንጭነት እንደሚያገለግለው :: ከዚያ ውጭ የበቃ የነቃ የታሪክ ትንተና አይደለም ::

በመጀመሪያ አንብባቸውና ከዚያ በኋላ ግምገማህን ማስከተል ትችላለህ ::

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
የእስልምና አክራሪነቱን በተመለከተ -ፍጹም እንግዳ ነው :: 83-87 ያልከውን ሁነት ፈጽሞ አላውቀውም :: የሰጠኸው ማብራሪያ ሁሉ ለኔ እንግዳ ነው ::

ለማንኛውም የበለጠ እስከማውቅ ድረስ በጉዳዮ ላይ ብዙ ከመናገር መስማቱ ይሻላል ለጊዜው ::

ናፖሊዮን ዳኘ ::

እኔም ሆንኩ ሌሎች ይህን ያህል የምንቸከችከው እኮ ስለነባራዊው ሁኔታ ያለብህን የመረጃ ክፍተት ስለተገነዘብን ነው :: እስከዚያው እንዳልከው ግራ -ቀኙን አጣራ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue May 01, 2012 5:56 am    Post subject: Reply with quote

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
ስላም

በአስር አመት ውስጥ በዚህ ደረጃ ለውጥ ማየት እጂግ በጣም የሚገርም ነው ::

ከብዙ በጥቂቱ :-
ምንጮች :-
1 ..... Uploaded by Abugidainfo on Oct 24, 2006. Ethiopian Government incited killing in Jimma, Ethiopia.

2 ..... Uploaded by Acts17Apologetics on Dec 16, 2011. Muslim Mob Burns Down Ethiopian Church (with Help from Police).

3 ..... Uploaded by Mahlet49 on Dec 24, 2011. The rise of Islamic extremism in Ethiopia.

ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው:
እንግዲህ የሆነው ሆኗል :: የምናውቀው "ኢትዮጵያዊ እስልምና ላይመለስ ሄዷል ብለን " ግን ማሰብ የመፍትሄ አቅጣቻችንን ያስተን ይመስለናል :: የኔ ጥያቄ ስለዚህ እንደምትሉት እስልምና በዛ ደረጃ ከሯል ብንል መፍትሄው ምንድን ነው ?? ነገሩ የሚላላበት መንገድ ካልተፈለገ እኮ ነገ እንደናይጀሪያ መሆን ሊመጣ ነው :: መፍትሄው ምንድን ነው ??

ናፖሊዮን ዳኘ ::

ሣይመሽ ነባራዊውን ሃቅ መቀበል ብቻ ነው የሚያዋጣው :: "የዋህነት ለበግም አልበጃት : አንድ ሆኖ ገብቶ ሺውን ተኩላ ፈጃት " ተብሏልና :: ከአክራሪዎች ጋር ድርድር አያዋጣም :: ስለዚህ እነርሱን ከወያኔ ያነሡ ጠላቶች አድርጎ መገመት አይቻልም :: ሁለቱም ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሡ የሠይጣን ፈረሶች ናቸው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Tue May 01, 2012 8:42 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ በዚህ እርዕስ ስር ብዙ ቁምነገሮችን እንድናውቅ ነው ያደረከን ::

እናመሰግንሃለ� የጽሁፍህ tone ከተለመደው ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ በጣም የወጣ ነው :: ሀሳብህን የበለጠ ክፍፍል በማይፈጥር መልኩ እንደ ሚስተር x እና ተድላ ድንጋዩን ድንጋይ እያል ማቅረብ ስትችል የማይገባ አቀራረብ ለምን እንደመረጥክ አልገባኝም :: ከጻፍካቸው ሁሉ "ሀረር ሌላውን ኢትዮጵያ 10 እስከ 20 አመት ይቀድማል " በሚለው መቶ በመቶ እስማማለሁ ::

በቤተ ክርስቲያን በምዕራብያኑ የሚደገፉ ጴንጤዎች ኦርቶዶክስ መስለው ገብተው ተአድሶ እናካሄዳለን ብለው መበጥበጥ የጀመሩት በሀረር ነበር :: በሙስሊሞች በኩል ወሐብያ በሳውዲአረብያ እየተደገፈ በሀረር መስፋፋት የጀመረውና ሰዎች ሱሪያቸውን መቁረጥና ጺማቸውን ማሳደግ የጀመሩት 20 አመት አካባቢ ነው :: ሁለቱም እንዳሳባቸው አልተሳካላቸውም እንጂ በውጭ ሀይሎች እየተደገፉ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ የሆነ ነገርን ለማጥፋት ሞክረዋል ::

አሁን አዲስ የሆነው ተአድሶን የቤተ ክርስቲያን ልጆች በተለይ ሰንበት ተማሪዎች ተፋልመው ከቤተ ክርስቲያን ሲያጸዱት ወሐብያን ግን በተደራጀ መልኩ የሚቃወመው አካል በሙስሊም በኩል ስላልገጠመው በጣም ተስፋፍቶ ቤተ ክርስቲያናትን ለብዙ አመታት ካቃጠለ እና ክርስቲያኖችን ካረደ በኃላ ወያኔ ለስልጣኑ አሰጋው መሰለኝ አሁን ሊፋለመው ቆርጦ የተነሳ ይመስለኛል ::

በሌላ በኩል ምንም እንኳን ተአድሶዎች ከሞላ ጎደል ከሀረር ሆነ ከተቀረው ኢትዮጵያ ከሚገኙ ቤተ ክርስቲያን ተባረዋል (የጴንጴዎች ቸርች ገብተዋል ) የቀሩትም እባብ ጭንቅላቱን እንደሚደብቅ ተደብቀዋል ወይም እዚህ ሰሜን አሜሪካ ስደተኛው ሲኖዶስ በሚባሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ በስፋት ቄስ ዘማሪ ሰባኪ ተብለው ይገኛሉ :: እነዚህም ቢሆኑ ጊዜ ይፈጃል እንጂ በስደተኛው ሲኖዶስ ከሚተዳደሩ ቤተክርስቲያኖች ተነቅቶባቸው መባረራቸው አይቀርም ::

በየዘመኑ እንደዚህ አይነት ጉድፎች አይጠፉምና ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ የሆኑትን ነገሮች የመጠበቅ አላፊነት የሁላችንም ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እናመሰግንሃለ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2009
Posts: 811

PostPosted: Tue May 01, 2012 9:56 am    Post subject: Reply with quote

-------

Last edited by እናመሰግንሃለ on Tue Sep 03, 2013 10:39 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2962

PostPosted: Tue May 01, 2012 5:50 pm    Post subject: Reply with quote

የንፍጥ ጭንቅላት መዓት ....ተድላ ;ሚስተር -x; እናመሰግንሀለን

የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች እምነታቸውን መከተል የሚችሉት ራሳቸው ወይም ሀይማኖታቸው በፈቀደላቸው ህግ መሰረት እንጂ እናንተ ባሰመራችሁት መስመር አይደለም .........የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ ጥቂት ሰዎች በፕሮቴስታንት እና በተሀድሶ እምነት ተከታዮች ላይ ያደረሱትን የህይወት እና የአካል ጉዳት በዝርዝር ካየነው እኮ አሸባሪ መባል ያለባት የእናንተው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች Idea ነገር ግን በጥቂት ግለሰቦች ምክንያት አንድን እምነት በጅምላ መፈረጅ የእናንተ የንፍጥ ጭንቅላቶች ስራ ነው Exclamation

ደግሞ ልክ እንደሚያውቅ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሙስሊሙ እና ክርስቲያኑ መካከል እንደድሮው የተሳሰረ ጉርብትና ቀርቷል ስትሉ አለማፈራችሁ Laughing Laughing Laughing ደደቦች .......ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው አንድም ነገር አታውቁም ...በደመነፍስ ; በቅዠት መቀባጠር Exclamation

ዳግማዊ ዋለልኝ ነኝ
የእምነት ነፃነት እና እኩልነት ካከበሩትና ካስከበሩት ወያኔዎች አምባ
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
AddisMeraf

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 01 Nov 2009
Posts: 1576

PostPosted: Tue May 01, 2012 6:15 pm    Post subject: Reply with quote

የሙሥሊሞች እና የፖሊስ ግጭት በአርሲ

የኦሮሙያ ፖሊስ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ በምዕራብ አርሲ ልዩ ስሙ አሳሳ በተባለ አካባቢ በአክራሪነት ጸርጥሮ ባሰራቸው በአንድ ያካባቢው ኢማሙ ደጋፊዎች እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት አሥር ፖሊሶች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የኦሮሙያ ፖሊስ ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ኦሮሙያ ፖሊስ ኮሚሽን ለግጭቱ መንሥዔ ናቸው የተባሉት ኢማም በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ሙሥሊሞችን ለጦርነት ቀስቅሰዋል በማለት ይወነጅላል። በምዕራብ አርሲ ስለታየው ግጭት የአዲስ አበባ ወኪላችን ታደሰ እንግዳው የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማልን አነጋግሮዋል፤ አቶ ሽመልስ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች ሙሥሊሞች አነሱት ስለተባለው ተቃውሞ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመግለጽ፡ ስለ ምዕራብ አርሲው ግጭት ግን ለዶይቸ ቬለ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ታደሰ እንግዳው
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

የሙሥሊሞች እና የፖሊስ ግጭት በአርሲ የጀርመን ሬድዮን ሰፊ ዘገባ ለመስማት እዚህ ተጫኑ
_________________
Remembering Meles Zenawi's Era! >> http://www.youtube.com/watch?v=uK1oi0-8uyQ&feature=youtu.be
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
AddisMeraf

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 01 Nov 2009
Posts: 1576

PostPosted: Tue May 01, 2012 6:26 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
በአርሲ በፖሊስና በህዝቡ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አራት ሰዎች ተገደሉ

በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፤ የታሰሩም እንዳሉ የአይን ምስክሮች ገልጸዋል

ሔኖክ ሰማእግዜር ፈንቴ
ዋሽንግተን ዲሲ

በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ከተማ የዓርብ ጸሎት አድርሰው ከመስጊድ በሚመለሱ ሰዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያስ 4 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ሽፋን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲመሩ የነበሩ አንድ የአሳሳ ከተማ ነዋሪን የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ሲያውሉ፤ ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት በሰው ላይና በንብረት ጥፋት ደርሷል ብሏል።

በስፍራው የነበሩ የአይን ምስክሮች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰው፤ ለምን እንደሚታሰር፤ ከታሰረም መብቱ ተጠብቆ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመራ፤ ወይም የአካባቢው ማህበረሰብ ለህግ እንዲያቀርብ በጠይቁ ጊዜ ፖሊሶች ሁኔታውን ባለመቀበል ሰውየውን ሲያስሩ፤ ማህበረሰቡ በቁጣ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን ይገልጻሉ። ለዚህ ቁጣ የፖሊስ አጸፋዊ ምላሽ ጥይት በቀጥታ ውደ ሰዎች መተኮስ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ አዛዥ አቶ ደበሌ አዱኛ የእስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የጅሃድ ጦርነት ሲቀሰቅስ የነበረ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ፤ ጥቂት ግብረ አበሮቹ በፈጠሩት ሁከት 4 ሰዎች መገደላቸውንና 10 ፖሊስ መቁሰሉን አቶ ደበሌ የመንግስቱ ልሳን ለሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ገልጸዋል። ከሰላማዊ ሰዎች የቆሰለውን ቁጥር ይፋ አላደረጉም።

“ይሄ ቡድን የሚያራምደው ሃይማኖት አይደለም፤ በሃይማኖት ሽፋን ድብቅ የፖለቲክ አጀንዳ ያለው ነው። ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ያረጋገጠውም የግለሰቦቹ አላማ ይች አገር የተያያዘችውን የልማትና የእድገት ጉዞ ማደናቀፍ ነው” ብለዋል።

አቶ ደበሌ አክለውም በአሳሳ በተቀሰቀሰው ሁከት የህዝብ አገልግሎቶች ማለትም የስልክና የፖስታ ቤት ህንጻዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ያላቸውን ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጸዋል።

የመንግስቱን ቃልና የአሳሳ ከተማ ነዋሪዎችን የምስክርነት ቃል በዚህ ዘገባ ያዳምጡ

_________________
Remembering Meles Zenawi's Era! >> http://www.youtube.com/watch?v=uK1oi0-8uyQ&feature=youtu.be
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

ዋና አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2962

PostPosted: Tue May 01, 2012 6:38 pm    Post subject: Re: የእስላሞች የአርብ ተቃውሞ ቀጥሏል - 5 ተቃዋሚዎች ተገደሉ Reply with quote

ደብተራው እናመሰግንሃለ� እንደጻፈ(ች)ው:
አሁን 4 ዓመታት በኋላ ደግሞ አገር ቤት ስደውል የምሰማው ክርስቲያኖች ሙስሊሞች ትንሽ በዛ በሚሉባቸው አካባቢዎች "ውጡ " እየተባሉ እንደሚታዘዙ ነው :: ይሄ የኔ ቤተሰቦችን ይጨምራል :: አደራህን : "ይሄማ ዱሮም ነበረ " እንዳትል :: የመጨረሻ የሚባል ዓይነት ማሳሰቢያ ነው እየተነገራቸው ያለው :: ብዙ ክርስቲያኖችም "ነገር ሳይመጣ " እያሉ ቀስ በቀስ እየለቀቁ ወደመሃል አገር እየተተጉ ይገኛሉ -በየቦታው ::

"ሀገር ቤት ደውዬ ".......ዋና የዋርካ ተረት ተረት መግቢያ Laughing Laughing Laughing Laughing ሀገር ቤት ደውዬ ይልና በቃ ማለቂያ የሌለውን የፉገራ መዓት ሲቀድ ይውላል Laughing Laughing Laughing

1. ሰላሳ ጊዜ ሀገር ቤት ብትደውል ልትደውልለት የምትችለው ሰው ስለራሱ ካልሆነ በስተቀር በጠቅላላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ነገር ማስረጃ ሊሆን አይችልም ...ዲየዲየብ Exclamation

2. ልደውልለት የምትችለው ሰው ሞስት ፕሮባብሊ እንዳንተ አይነት ንፍጥ ጭንቅላት ነው Laughing Laughing Laughing Laughing

3. ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ውጡ ያሏቸው የት ቦታ ነው Question Wink የአንተን ቤተሰቦች ጨምሮ Laughing

መልስ ካጣህ ደግመህ ሀገር ቤት ደውል Laughing Laughing Laughing

ዳግማዊ ዋለልኝ ነኝ
የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
Page 4 of 7

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia