WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 363, 364, 365 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed May 02, 2012 7:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
እንዴ ምነው ለልጁ ፋታ ስጠው እንጂ ከሥንት ቀናት በኋላ ብቅ ያልከው አንሶ ገና ከሠላምታህ ሥር ውርጂብኝ ምነው እንደጠማው ሰው ሆንክሣ አንድ ያላበው የሣንጆርጅን ጃምቦ አዝዤልሃለሁ :: ያንን በአፍህ አድርግና ከዚያ ሰላማዊ ጨዋታ ትጀምራለህ ::

ምን ዋጋ አለው ተድልሽ ? እዚህ ያለሁበት በደሌ ቢራ ብቻ ነው ያለው ::ሳንጆርጅን አዘህልኝ ጥሜን አባባስከው ::
ከጎሳ የመሰደድ ጉዳይ ሳይሆን አንዳንድ ነገሮቹን ሊደባብቅ ስለሚፈልግና እኔ ነካ ስለማደርገው አልመች
ብየው ነው ::ብታየው ዝምተኛ መስሎ .......አቤት ጉዱ .....አይይይይይይይይይይ ይቅር ብቻ !!!!!

ከራስ ብሩ የጀመራችሁትን አትሌቲክስ ጨወታ እያጣጣምኩት ነው ::ኮሎኔልም ስለመጡ ደስ ብሎኛል ::
እኔም ወደ 5000 ሺና 10000 ስትገቡ ብቅ እላለሁ ::
እስከዛው ልኮምኩማችሁ ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Fri May 04, 2012 12:23 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት

ፖለቲካል ሳይንስ መምህራን በመጀመሪያ ስለ ዲሞክራሲ የሚያስተምሩት Majority Rule, Minority Rights የሚለውን መርህ ነው :: ይህን ጉዳይ ዛሬ እዚህ ያመጣሁት አደቆርሳና እኔ እንዲሁም አንዳንድ ሌሎች በዚህ ቤት ይታይ የነበረውን ጸያፍ ጽሁፍ ላለማየት በማለት ወደ ኢትዮፎረም ከሄድንበት ምክንያት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው :: ያንንም ቤት ስንመርጥ ከዚህኛው ጋር በማነጻጸር ነበር :: እንዳገኘነውም በአንጻሩ ኢትዮፎረም በብዙ መልኩ ዋርካን ያስንቃል : ለደምበኞቹም የሚሰጠው እንክብካቤ እጅግ በጣም ጥሩ ነው :: ይሁን እንጂ ሌሎች የክ / አካባቢ ልጆች ወደዚያ ቤት እንዲመጡ ብዙ ጥረት ብናደርግም አልሆነም :: በተለይ "ጎሳ " የሚሉት ፍጡር ቅቅቅቅ ሲያመሻሽ የጮማ ቁርጥ ይዞ መጥቶ ከበር ምላሽ ማንበሽበሽ ሲጀምር ሮጠው ወደዚያኛው ቤት የሄዱትም (ራሳቸውን ያውቃሉ ቅቅቅቅ ) ወደዚህ መመለስ ጀመሩ :: በአብዛኛው እዚያ የቀረነው አደቆርሳና እኔ ነበርን ማለት ይቻላል :: ግን የማንታገለው ባለጋራ ሆነብን :: እድሜ ለጎሳ !! ቅቅቅቅ የአደቆርሳን እላውቅም እኔ ራሴ መሸትሸት ሲል ሰው ሳያያኝ ብየ የጎሳን የሚመስጥ ታሪክ መከታተሌ አልቀረም :: እግዜር ይስጥህ ወንድሜ ...ምን እላለሁ ሌላ ::

በዚህ ምክንያት ከላይ እንደጠቀስኩት ብዙሀኑ እዚሁ እንቀራለን ብለው ከወሰኑ ሌሎቻችን አሻፈረን ብለን በዚያው ቤት መቅረት አንድነታችንን ስለሚያናጋውና ላደግንባት አካባቢ ያለንን ክብር ስለሚቀንሰው እኔም በመጠኑ ቅር እያለኝ ተመልሻለሁ ::

ቅር አለኝ የምለው በሁለት ምክንያት ነው : 1ኛው እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮፎረም ብዙ ነገር --- ለምሳሌ ፎቶ ወይም ቪዲዮ ማስቀመጥን የመሰለ እድል ሲሰጥ --- በዚያ ላይ ኢሳት , ኢቲቪ , ሸገር ሬዲዮ , ቪኦኤ , ዶቼቬሌን የመሳሰሉትን በቀላሉ እንድንከፍት አመቻችትዋል :: 2ኛው ቅሬታየ ዋርካ ጄነራል አሁንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጸድትዋል ለማለት በሙሉ አፍ መናገር አይቻልም :: ቢሆንም ከአገሬ ልጆች ተለይቼ መቆየቱ ...በተለይ ደግሞ የነባለሱቅን ሞፊቲን ራስብሩን ጫወታ እንዲያመልጠኝ ስለማልፈልግ .... አንዱም ለዚያ ነው ብዙ ርቆ መቆየቱ የማይመች ሆኖ ያገኘሁ :: አሁንማ ጎሳ ከመጣ ወዲህ ቤቱ የተቃጠለ ይመስላል ...የዋርካ አስተዳዳሪዎች አዲሱን ደንበኛ ማመስገን ይገባቸዋል ::

ሆኖም የኢትዮፎረም ቤታችን አልተዘጋም ፎቶና ቪዲዮ ለማስቀመጥ ስትፈልጉ ወደዚያ ብቅ በሉ ::

በዚህ አጋጣሚ የምንወድህና የምናከብርህ አደቆርሳ ወደዚህ ቤት ተመለስ እልሀለሁ :: አገራችን ውስጥ ዲሞክራሲ ባይኖርም እዚሁ እኛ እየተማማርን ሥራ ላይ እናውለው ::

አክባሪያችሁ
አንፈራራ
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri May 04, 2012 12:47 am    Post subject: Reply with quote

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለዚህ ቤት

የፖለቲካል ሳይንስ መምህራን በመጀመሪያ ስለ ዲሞክራሲ የሚያስተምሩት Majority Rule, Minority Rights የሚለውን መርህ ነው :: ይህን ጉዳይ ዛሬ እዚህ ያመጣሁት አደቆርሳና እኔ እንዲሁም አንዳንድ ሌሎች በዚህ ቤት ይታይ የነበረውን ጸያፍ ጽሁፍ ላለማየት በማለት ወደ ኢትዮፎረም ከሄድንበት ምክንያት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው :: ያንንም ቤት ስንመርጥ ከዚህኛው ጋር በማነጻጸር ነበር :: እንዳገኘነውም በአንጻሩ ኢትዮፎረም በብዙ መልኩ ዋርካን ያስንቃል : ለደምበኞቹም የሚሰጠው እንክብካቤ እጅግ በጣም ጥሩ ነው :: ይሁን እንጂ ሌሎች የክ / አካባቢ ልጆች ወደዚያ ቤት እንዲመጡ ብዙ ጥረት ብናደርግም አልሆነም :: በተለይ "ጎሳ " የሚሉት ፍጡር ቅቅቅቅ ሲያመሻሽ የጮማ ቁርጥ ይዞ መጥቶ ከበር ምላሽ ማንበሽበሽ ሲጀምር ሮጠው ወደዚያኛው ቤት የሄዱትም (ራሳቸውን ያውቃሉ ቅቅቅቅ ) ወደዚህ መመለስ ጀመሩ :: በአብዛኛው እዚያ የቀረነው አደቆርሳና እኔ ነበርን ማለት ይቻላል :: ግን የማንታገለው ባለጋራ ሆነብን :: እድሜ ለጎሳ !! ቅቅቅቅ የአደቆርሳን እላውቅም እኔ ራሴ መሸትሸት ሲል ሰው ሳያያኝ ብየ የጎሳን የሚመስጥ ታሪክ መከታተሌ አልቀረም :: እግዜር ይስጥህ ወንድሜ ...ምን እላለሁ ሌላ ::

ሰላም ወንድማችን 'anferara' :-

ጎሳ ፍቅር በባቡር ጭኖ አምጥቶ ለአገር ለምድሩ ሲያድል 'እንዴት እርሱን ያህል ቸርና ለጋስ ወንድም ጥላችሁ ትጠፋላችሁ ' እያልን ሥናዝን ነበር :: ክበር : ተመስገን እንላለን Very Happy ::

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
በዚህ ምክንያት ከላይ እንደጠቀስኩት ብዙሀኑ እዚሁ እንቀራለን ብለው ከወሰኑ ሌሎቻችን አሻፈረን ብለን በዚያው ቤት መቅረት አንድነታችንን ስለሚያናጋውና ላደግንባት አካባቢ ያለንን ክብር ስለሚቀንሰው እኔም በመጠኑ ቅር እያለኝ ተመልሻለሁ ::

ትልቅ ውሣኔ ነው :: እኛም እልህ ይዞን ነው እዚህ እንደ ማስቲሽ ተጣብቀን ያለነው :: ለሥንቱ አምባገነን ተሠድደን እንችለዋለን :: አሜሪካኖች ወደው አይደለም "stand your ground" ብለው ሕግ ያወጡት - ምንም ዘረኛ ባለጌ ሕጉን ለዘረኛ ተግባሩ ቢያውለም ::

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
ቅር አለኝ የምለው በሁለት ምክንያት ነው : 1ኛው እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮፎረም ብዙ ነገር --- ለምሳሌ ፎቶ ወይም ቪዲዮ ማስቀመጥን የመሰለ እድል ሲሰጥ --- በዚያ ላይ ኢሳት , ኢቲቪ , ሸገር ሬዲዮ , ቪኦኤ , ዶቼቬሌን የመሳሰሉትን በቀላሉ እንድንከፍት አመቻችትዋል :: 2ኛው ቅሬታየ ዋርካ ጄነራል አሁንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ጸድትዋል ለማለት በሙሉ አፍ መናገር አይቻልም :: ቢሆንም ከአገሬ ልጆች ተለይቼ መቆየቱ ...በተለይ ደግሞ የነባለሱቅን ሞፊቲን ራስብሩን ጫወታ እንዲያመልጠኝ ስለማልፈልግ .... አንዱም ለዚያ ነው ብዙ ርቆ መቆየቱ የማይመች ሆኖ ያገኘሁ :: አሁንማ ጎሳ ከመጣ ወዲህ ቤቱ የተቃጠለ ይመስላል ...የዋርካ አስተዳዳሪዎች አዲሱን ደንበኛ ማመስገን ይገባቸዋል ::

ሆኖም የኢትዮፎረም ቤታችን አልተዘጋም ፎቶና ቪዲዮ ለማስቀመጥ ስትፈልጉ ወደዚያ ብቅ በሉ ::

አሁንማ የውዴታ ግዴታ ውስጥ አስገባኸን እኮ Rolling Eyes ብቅ እያልን ያለንን እናካፍላለን : እንሣተፋለን :: ሁለት የተለያዩ ድረ -ገፆች ላይ መድረክ ሲኖረን ደግሞ ምርጫችንም ይሠፋል ::

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
በዚህ አጋጣሚ የምንወድህና የምናከብርህ አደቆርሳ ወደዚህ ቤት ተመለስ እልሀለሁ :: አገራችን ውስጥ ዲሞክራሲ ባይኖርም እዚሁ እኛ እየተማማርን ሥራ ላይ እናውለው ::

አክባሪያችሁ
አንፈራራ

አደቆርሳ : አለህ ወይ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ባለህበት ሰላም ሁን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1333

PostPosted: Fri May 04, 2012 9:45 am    Post subject: Reply with quote

ይህ ቤት ስቲክ መደረግ አለበት ..በፍጹም ወደታች መውረድ የለበትም ..ለዋርካ አድሚን ሆላ እላለሁ እንዲህ የሚጽፍ ሰው ይከበራል ይወደዳል
በነገራችን ላይ ኬይ ቦርድ በመተምተም ( ብዙ በመጻፍ ) ሾተል ነበር አንደኛ ......አሁን ግን የሾተልን ሪኮርድ የሚሰብር ተገኝ ..ስሙም ጎሳ ይባላል ..
ባለሱቅ ደግሞ ሲለቀልቅ አወራረዱ እንደ ምግብ ቤት ሜኑ ቢያስመስለውም ከማድነቅ ወደኋላ አልልም
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri May 04, 2012 2:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ከቤቴ ዋርካን መክፈት ስፈልግ favorites ሴቭ ያደረኩትን ብቻ ስጫነው ቀጥታ ወደ ቤቱ ይወስደኛል :: በቅርቡ ደግሞ እንደምንም ዳክሬ ኢትዮፎረምንም ሹልክ ብዬ ገብቼ የነ አንፈራራንና አደቆርሳንም (በነገራችን ላይ የካሳም ጽሁፍ በጣም ተመችቶኛል ) ማንበብ ጀምሬ ስለነበር እሱንም እንደዚያው favorites ስነካ ብቻ እነ አንፈራራን ስለሚያሳየኝ ዛሬ ደግሞ ዋርካን ስከፍት የአንፈራራን ስም ሳይ በስህተት ኢትዮፎረም የገባሁ ነበር የመሰለኝ እንጂ አንፈራራችን ተመልሶ የመጣልን አልመሰለኝም ነበር :: ወደ ላይ ወደ ታች አድርጌ ካየሁ በኌላ ነው ዋርካ መሆኑን በስንት መከራ ያመንኩኝ :: አቤት የተሰማኝ ደስታ !! ጽሁፉ ደግሞ ይበልጥ አረካኝ :: እዉነትም ዲሞክራሲ !!! ወንድማችን እንኳን መጣህልን !!! እኔስ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ ብለህ ነው :: ደስታው ብዙ አያጽፈኝም ዛሬ :: ደግሞ ገልብጤ በመለቅለቅ ሪከርድ ሰበርክ አለኝ ቅቅቅቅ ::

ገልብጤ :
እኔም የባለሱቅን ጽሁፍ ሳይ ግርም ይለኛል :: ከሞባይል ነው የምጽፈው ብዬ እራሴን አሳምኛለሁ ቅቅቅቅ :: እንደኔ አይናፋር ነው መሰለኝ ሰው በርከት ሲል እሱ በተራው ይጠፋል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Fri May 04, 2012 7:50 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
በተለይ "ጎሳ " የሚሉት ፍጡር ቅቅቅቅ ሲያመሻሽ የጮማ ቁርጥ ይዞ መጥቶ ከበር ምላሽ ማንበሽበሽ ሲጀምር ሮጠው ወደዚያኛው ቤት የሄዱትም (ራሳቸውን ያውቃሉ ቅቅቅቅ ) ወደዚህ መመለስ ጀመሩ

አንፈራራችን በጣም አሳከኝ ....
ጎሳንማ በሀገርኛ አሳምኜው ወደዛ ይዤው ለመጣ ብለምነው ብሰራው እዚህ የተቀበለው ቀብዲ አለ መሰለኝ
ቡራከረዩ ብሎ አስቸገረኝ ::እኔም ያው ደበቅ እያልኩ መምጣት የጀመርኩት የሱን ቁርጥ ሳውቅ ነው ::
በዲሞክራሲያዊ መንገድ መምጣት መቻልህ አስደስቶኛል ::አደቆርሳ ሀገር ቤት ስላለ ቢሮክራሲ ስለሚጫነው እንዳንተ ቶሎ ለዲሞክራሲ እጅ የሚሰጥ አይመስለኝም ::
በመምጣትህ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ::ያኛውንም ቤት በፍጹም አንተወውም ::እንዳልከው የቪዲዮና ይፎቶ መረጃዎችን
እናስቀምጥበታለን ::ሲብስብንም ጠቅለል አርገን በድህና ግዜ ወደሰራነው ቤታችን ማምለጥ ነው ::
ይቺ ነገር እርግጥ ለተድላ አትመቸውም ::የምን እጅ መስጠት ነው ብሎ መከራከሩ አይቀርም ::
እውነቱን ነው በነጻ ሀገር እዚሁ መሟሟት እንጂ !!!!!
አደቆርሳ ኮቱ ወጂን ኦልና !

በግፍ በሽብር ወንጀል ተከሶ የሞት ፍርድ የሚጠብቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታላቁን የፔን ሽልማት በደማቅቅ ስነስራት መቀበሉ የወያኔን እርቃን በአለም ህዝብ ዘንድ እንደተለመደው ያጋለጠ ሆኑአል ::
በከፍተኛ ሁኔታ የሽብር ወንጅል ህግ ያለባት አሜሪካ በወያኔ መንግስት በሽብር የተከሰሰን ሰው ሽብርተኛ አይደለም
ብላ መሸለሟ ለወያኔ ትልቅ ውርደት ነው ::ለዚያውም ህጉን ከአሜሪካና እንግሊዝ ሙሉ ለሙሉ ቀድቼ ነው የወስድኩት ለሚለው አረመነው መለስ የውርደትም ውርደት ነው !!!!!!

እስክንደር ነጋ እውደሀለሁ !!! እንኳን ደስ ያለህ !!!!!!

ቸር እንሰንብት !!!!

ቸር እንሰንብት ::::::
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri May 04, 2012 8:52 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የዚህ የፍቅር ቤት ወገኖቻችን :-

ኢንተርኔት ያልያዘው ታሪክ የለም :: እስኪ ለቅምሻ ያህል 'Nordic Africa Institute' ያገኘሁትን ላቃምሣችሁ :: ታዲያ ስዊድን አገር የሚኖር የወዩ ልጅ ሠፋ ያሉ ሐተታዎችን ከምንጭ እየቀዳ እንደሚያካፍለን (እንደምታካፍለን ) አምናለሁ ::

ምንጭ :- The Nordic Africa Institute, searched under "Kibre Mengist."

Quote:
[Mineral 1966 p 160 & others]
"Even in the 1960s much secrecy still obscures details of mining -- One foreigner, a former overseer at Adola, informed the author that in the 1940s the labourers were paid Eth$ 2 for each Maria Theresa ounce of gold which they washed -- The majority of Ethiopians prefer not to discuss Adola and indeed know little about it. -- Gold is flown from Adola partly by civil aircraft and partly by military flights. This, and the fact that the flights are not scheduled, forbids calculation of the total weight of gold transported."

[Greenfield 1965 p 327-328]
A new road between Kibre Mengist and Shakiso was built around 1960.

An agreement to import machines from Rudnap in Yugoslavia for mining work at Kibre Mengist was signed in July 1961. The value of the transaction was about half a million Eth. dollars.

[News]
In 1962 there was an all weather road from the north and a dry weather road southwards to Negele.

Postal hand stamp had spelling KEBRE MENGIST around 1963.

The telephone line to Kibre Mengist was in operation by 1964.

The 120 km road from Negele to Kibre Mengist was improved from 1966 by the Highway Authority and the work was fully completed by August 1968.

It was decided in 1966 that the Ministry of Interior would design a master plan for Kibre Mengist, without engaging external consultants.

Serravalle G. & Franzetti C. Pte. Ltd. Co. /with what connection to the gold mining?/ in 1966 had a sharehold capital of Eth$ 70,000.

Population 6,595 as counted in 1967.

By 1967 there were 28 telephone numbers. Those on personal names were 11 of Ethiopian Christian type, 4 of Moslem type and Fraval Giovanni seemingly the only European.

Ras Biru primary school in 1968 had 657 boys and 402 girls, with 17 male teachers and one female.

A church school had 68 boys and 24 girls in grades 1-2, with 2 male teachers.

Ras Biru W. Gebriel junior secondary school in 1968 had 132 male and 54 female students in grades 7-8, with 6 teachers (Ethiopian).

Kibre Mengist had the southernmost centre of community development in Ethiopia.

ከዚያ ድረ -ገፅ ስለ ክብረ -መንግሥትና አዶላ (ወዩ ) ብቻ ሣይሆን ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ (በየከተማውና የገጠር መንደር የተደረገው ሣይቀር ) የተዘገበበትን ምንጭ ይጠቅሣልና ለሌላም ዋቢነት ይጠቅማል ::

አክባሪያችሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat May 05, 2012 10:21 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ተድላ
[/quote]Gold is flown from Adola partly by civil aircraft and partly by military flights. This, and the fact that the flights are not scheduled, forbids calculation of the total weight of gold transported."[quote]

እስከ ዛሬ ምን ያህል ወርቅ ከዚያች ምድር እንደተዘረፈ ለመገመት እራሱ ይዘገንናል :: ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ከጥንትም ጀምሮ እንደዚያ ሲዘረፍ አንድም መንግስት አንድ የሚረባ ሆስፒታል እንኳ ለአከባቢው ህብረተሰብ አለመስራቱ ነው :: ሁሉም ዘራፊ ዘርፎ ጭጭ ነው ::እግዜር ይይላቸው : ሌላ ምን እንላለን ::

እግዜር ይስጥልን ወንድማችን ተድላ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sun May 06, 2012 7:39 am    Post subject: Reply with quote

ማሻሻያ ተደርጎበታል

Last edited by Gosa on Thu May 17, 2012 1:54 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun May 06, 2012 8:12 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
'ቡጤ ቲያ እንዴት ነሽልን ? በጣም አመመሽ እንዴ ?'

"ልሞትባችሁ ነው መሰለኝ : ጎሳ ሊሰፋላችሁ ነው " ብላ ፈገግ አለች ::

ጎሳን ደግሞ ከቡጤ ውጪ ማሰብ አይቻልም :: መጀመሪያ ክሊኒኩ ሲቋቋም የተቀጠረች አንጋፋ ሰራተኛ ከመሆኗም በላይ ለሰው ሁሉ ያላት አስተያዬት እና አቀራረብ አንድ ነው

ጎሳ = ፍጹም ስሜቴን ሀዘን ውስጥ ይዞ የሚጓዝ ታሪክ ነው ዛሬ ይዘህ የመጣህብኝ ::ወርቅነሽ (ቡጤ ) ማንም ሊረሳት
የማይችል ልዩና ደግ ፍጡር ነበረች ;;በህክምና ሙያዋም በትክክል የህክምናን ስነምግባር የምታከብር በሷ ብቻ
ፈገግትና ተስፋ ለበሽተኞች መድሀኒት መሆንዋ እና
የነበራት እንክብካቤ ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም ::
በማህበራዊ ህይወቷም ከሰው የነበራት ቅርርብ ደግነቷ ሳቋ .. ሁሉም ነገርዋ ምቾተን የሚሰጥ ነበር ::
ቡጤ ከዚህ አለም ስተለይም የነበረው የሀዘን ስሜትና የሰዉ ብዛት (ከገጠር እስከከተማ ........)የሷን ጥሩነትና ፍቅር የሚያሳዩ ነበሩ ::
ጎሳ ዛሬ ከረዥም አመታት በኌላ አስታውሰሀት አንድ ሁለት ዘለላ እንባ እንዳፈስ አድርገኧኛል ::
ወርቅዬ (ቡጤ ) ዛሬም ነፍስ ይማር ብያለሁ ::

ጎሳ =ሌላው ስለ አባተህ ያነሳኧው ታሪክም ሆድ የሚያባባ ነው ::ወደ ጎሳ ስንመጣም ይሁን ይርባና ክብረመንግስት
ስንሄድ አባትህ እቤታችሁ በረንዳ ላይ ተቀምጠው ሁሌም ስለምናያቸው የማያውቃቸው ሰው አለ ለማለት አያስደፍረም ::
በጨወታ አዋቂነታቸውም ስለሚጠሩ እሳቸው ያሉትን እያነሳን እንነጋገርበትና እንስቅበት እንደነበርም ትዝ ይለኛል ::
መናጢ ወንድምህ በሳቸው ሳይወጣ አልቀረም ?
የገረመኝ ነገር ያኔ አንተ ወደ ናይሮቢ ስተወጣ ወንድምህን አፋጠን ይዘነው ነበር ::ለኔም አልነገረኝም ቢልም አላመነውም ነበር ::አሁን ስላረጋገጥክለት ክሴን አንስቼለታለሁ ::
አባተህ ከሁሉም በላይ የሚታወቁት ልጆቻቸውን በሙሉ እንዲማሩ የሚያደርጉት ጥረትና ለትምህእርት የነበራቸው በጎ አመለካከት ነው ::
እንደምታውቀው በገጠር አካባቢ ትንሽ በትምህርት ከተጓዝ የሚቀጥለው ነገር ጋብቻ ስለሆነ ብዙ የገጠር ልጆች በትምህርት ስኬታማ አይሆኑም ::
ጎሲቲ አንቺም 7 ክፍል እያለሽ ሳዱላ ልጃገረድ እንደታጨልሽ ትዝ ዪለኝ ነበር ::
እኚሁ ደጉ አባተህ ሽማግሌ ለልጅቱ ቤተሰብ ሲልኩ የተጠየቁት 8በሬ 4 ወይፈንና 7 ጊደር እንደነበርም ማስታውስ ይቻላል ::
ለውድ አባትህም አምላክ አጸደ ነፍሳቸውን በገነት እንዲያኖር ዛሬም አስባለሁ ::

ውድ ተድላ = ኮፒ ያረከውን የሀገራችንን ታሪክ አጣጣምኩት ::የሚገርም ነው የሆነብኝ ::አንተ መቼም
የማትቆፍረው ሊንክ የለም ::
በጣም ነው የማመሰግንህ ::

ቸር እንሰንብት !!!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon May 07, 2012 12:45 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም 'Gosa' :-

እንዲህ ተንፍሠኸው ይውጣልህ እንጂ : ያለበለዚያማ አንተኑ ውስጥህን በልቶ ይጨርስሃል :: የአንተ ታሪክ በአብዛኛው አገሩን ጥሎ ለሥደት የተዳረገው ወገናችን ታሪክ አካል ሥለሆነ ብዙዎች በያሉበት ከራሣቸው ኅሊና ጋር ዘወትር የሚወያዩት ጉዳይ ነው :: አዬ የዛሬው ትውልድ ዕጣና ፋንታ ... የማይጨበጥ ተስፋን ሠንቆ : አገር ጥሎ ወደማያውቁት አገር እና ሕዝብ መንጎድ Sad Sad Sad :: ብቻ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሠምቶ ያሠብከውን ያሣካልህ ወንድሜ :: ሥነ -ጽሑፍን ግን አትፍራው :: ለአንተ እንዴት እንደታየህ ባላውቅም (ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይዞህ ነው ብዬ እገምታለሁ ) ይህ የጻፍከው በራሱ እንኳን ብዙ የሚያስብል ነው :: በርታ Exclamation Exclamation Exclamation

*********************************

ሞፊቲ :-

እስኪ ይህንን ድረ -ገፅ በደንብ ፈትሸው :: ስለ እናንተ ቤት ብትጠይቀው አንድ ወሬ አያጣም Smile

ምንጭ :- The Nordic Africa Institute: Home.

ባለፈው ስለ 'ክብረ መንግሥት ' ካገኘኋቸው መረጃዎች የአንዱን ብቻ ለጥፌ የዋናውን ድረ -ገፅ አድራሻ ባለመለጠፌ ይቅርታ : ንፉግ እንዳልባል ነው ::

ከማራቶን ሠፈር አትጥፋ : አለዚያ የሣንጆርጅን ቢራ አታገኝም Smile

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Mon May 07, 2012 12:54 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ሞፊቲ ወንድሜ

[/quote] ጎሳ ዛሬ ከረዥም አመታት በኌላ አስታውሰሀት አንድ ሁለት ዘለላ እንባ እንዳፈስ አድርገኧኛል ::
ወርቅዬ (ቡጤ ) ዛሬም ነፍስ ይማር ብያለሁ :: [/quote]

በእውነት ጽሁፉን ስጀምር ስለ ውድ እህታችን ቡጤም ሆነ ስለ አባቴ እንደዚህ በዝርዝር እጽፋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር :: አንዳንዴ በሆነ ሀይል ውስጥ ገብተህ ተመስጠህ ስትጽፍ ያንን ሀይል እንደመጣልህ ተፍተህ መተንፈስ እንጂ አምቆ መያዙ አይመጣልህም :: በምንም መልኩ አሳዛኝ ነገር እዚህ ዋርካ ውስጥ አንስቼ ላስለቅስህ ጭራሽ አላሰብኩበትም :: ያኔ የነበረውን ነገር ሳስታውስ እንደዚያ ውስጤን ሞልታው ሳላነሳት ባልፍ ለሷ የነበረኝን ፍቅር ትንሽ እንኳ ባለማንሳቴ ካለችበት የምትታዘበኝ ስለመሰለኝ ነው ያነሳሁት :: ፈርቼ እንጂ በወቅቱ የነበርኩበትን ስሜት እንዳለ ብዘረግፈው ደስ ባለኝ ነበር :: ስለ ቡጤ አንተ ባጭር አረፍተነገር ስለጨረስከው እኔ ልተወው : ዳግም ወደዚያ ስሜት አልመለስ :: ግን ያው በሚቀጥለው ጽሁፌ ለተወሰነ ምክንያት ማንሳቴ ስለማይቀር በዚሁ ደግሞ አንባብዎቻችን እንዳይሰለቹን ይቅርታ እንጠይቃችኌለን ::

[quote]ጎሲቲ አንቺም 7 ክፍል እያለሽ ሳዱላ ልጃገረድ እንደታጨልሽ ትዝ ዪለኝ ነበር ::
እኚሁ ደጉ አባተህ ሽማግሌ ለልጅቱ ቤተሰብ ሲልኩ የተጠየቁት 8በሬ 4 ወይፈንና 7 ጊደር እንደነበርም ማስታውስ ይቻላል :: [/quote]

ቅቅቅቅቅ አባታችንማ እንድንማር እንጅ እንድናገባ አይፈልግም ነበር :: እዚህ ዋርካ ውስጥ “አልማርም” በማለቴ ገና ትንሽ ልጅ ሆኜ በአቶ አሰፋ በዻዻ መታሰሬን መጻፌን አስታውሳለሁ :: በነገራችን ላይ ቦሬ ከተማ ድረስ ተከታትላኝ አስፈልጋኝ ያሳሰረችኝ : ይህችው ወድ እህታችን ቡጤ ነበረች :: ካባቴ ጋር ተመካክረው ነበር ያሳሰሩኝ :: እኔማ ስንት ዉለታ አለብኝ መሰለህ የሷን ::

ወንድሜ ተድላ !!

[quote]አዬ የዛሬው ትውልድ ዕጣና ፋንታ ... የማይጨበጥ ተስፋን ሠንቆ : አገር ጥሎ ወደማያውቁት አገር እና ሕዝብ መንጎድ :: ብቻ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሠምቶ ያሠብከውን ያሣካልህ ወንድሜ :: [/quote]

አሜን ብያለሁ ወንድሜ :: አሁን ምንም አስተያየት አልስጥ :: ስንት ነገር አለ መሰለህ በስደት አገር :: እመለስበታለሁ ::

[quote]ሥነ -ጽሑፍን ግን አትፍራው :: ለአንተ እንዴት እንደታየህ ባላውቅም (ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይዞህ ነው ብዬ እገምታለሁ ) ይህ የጻፍከው በራሱ እንኳን ብዙ የሚያስብል ነው :: በርታ
[/quote]

ወንድሜ ምን ልበልህ : ስለሰጠኽኝ አስተያየት ከልቤ አመሰግንሀለሁ :: እግዚአብሄር ይስጥልኝ ወንድሜ ::እኔ እንኳ የምጽፈው ጽሁፍ በቁምነገር ይነበባል ብዬ አስቤ አላውቅም :: ለነገሩ እኔም ለመጀመሪያ ግዜ ነው እንደዚህ በጽሁፍ ሀሳቤን ለመግለጽ የሞከርኩት :: እናንተ ግን ሞራል እየሰጣችሁኝ እንዳስብበት እየገፋፋችሁኝ ነው :: ለነገሩ እኔም ሀሳቤን በመናገር ከመግለጽ ይልቅ ብጽፈው እንደሚቀለኝ ከድሮውም ጀምሮ አውቃለሁ :: እስቲ እናያለን :: በትዕግስት አንብበህ መጨረስህ እራሱ ለኔ ትልቅ ስኬት ነው :: በድጋሚ እግዜር ይስጥልኝ ወንድሜ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1333

PostPosted: Mon May 07, 2012 6:56 pm    Post subject: Reply with quote

እኔ ባላውቃችሁም ግን እዚህ ቤት ውስጥ ማንበብ ከጀመርኩ ጀምሮ እንዳንተ ቀልቤን የተቆጣጠረው የለም ..ይህን ጽሁፍ ሳነበውማ ...ህምምም የራሴው ነገር መስሎኝ እምባ ኮለል ..ኮለል ...አይ ጎሳ ሁሉን ነገር የተካንክ ሰው ነህ ለካስ ...መቼም ያክብርልኝ ብዬ ልውጣ እንጂ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
anferara

ኮትኳች

Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Tue May 08, 2012 3:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት

ተድላ ሞፊቲ ጎሳ ... የአዶላ ነገር ሲነሳ እንዳላችሁት ነዋሪው ሕዝብ ከሚመረተው ወርቅ የተረፈው ... ስቃይ እንጂ በማንኛውም ዘመነ መንግስት አንዲት ቤሳ ጥቅም አግኝቶ አያውቅም :: እዚያው ተወልዶ ካደገበት ከተማ እንኳን ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ሌላ ከተማ ልሂድ ቢል ያለ የይለፍ ፈቃድ ከከተማዋ የማይወጣበት ጊዜ ነበር :: የአዶላ ወርቅ .... የሚጠቅመው ባለስልጣኖችን ሕዝቡን አይደለም :: አንዳንዴ ወርቁ ለአካባቢው ሕዝብ እርግማን ነው ማለቱ ይቀላል ::

ተድላ ..የለንደን ኦሊምፒክስ ሲጀመር ብዙ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ስለሚመጡ ታዲያ ኢትዮፎረም እነዚህን ምስሎች ለማስቀመጥ የተመቸ ስለሆነ የስፖርት ገጽም ስላላቸው ካሁኑ ቢታሰብበት መልካም ይመስለኛል ::

ጎሳ ..... ያንተንና የጽጌን መጨረሻችሁን አይቼ ! በጣም የሚያግዋግዋ ታሪክ ነው :: በተለይ ሞፊቲን ታሪኩ ውስጥ ስታስገባው እርሱም ቢሆን አድብቶ ተራውን መጠበቁ አይቀርምና እንደሚከተልህ ተቀናቃኝ ወደ ኍላህ እየተገላመጥክ በጥንቃቄ መሄድ ነው : ቅቅቅ .... የአጻጻፍ ችሎታህ በጣም ደስ የሚልና በጣም የሚያስመሰግንህ ነው :: ይመችህ !!
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Tue May 08, 2012 7:59 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ጎሳ እንደምን አለህ ?
አይሱዙ ላይ ሰቅለኸኝ እዛው ቁጭ ብዬ ቀረሁኮ
ለምን አትለኝም ? ማርሳቤት ወይም ናይሮቢ የመጀመሪያው ደብዳቤ ያሚያመጣውን መልክት አብሬህ ለማንበብ ስለጓጓሁ ነው ! ::
አብዛኛው ሰው በእድሜ ዘመኑ የወጣትነት ኃይሉ የሚቸረውን ፍቅር ያሳልፋል ::
አንዳንዱ መሰናክል የሌለው ሌላው ደሞ ደሞ ቦግ ብሎ ቶሎ እልም የሚል አንዳንዱም ትልቅ መስዋዕትነትን የሚያስከፍል ሌላውም የሚያስኮበልል
ብዙ የፍቅር ታሪክ ከማንበብም ከመስማትም
አብሮ ኖሮ ከማወቅም ጭምር አውቃለሁ ::
አሁንም የፍቅር ታሪክ ማንበብ ወዳለሁ ......
ደራሲዎች ስለፍቅር መጻፍ ባያቆሙ ኖሮ ማለቴ ነው ::
ግን ውነቴን ነው የፍቅር Lovestory መጽሀፍ አሁን ይታተማል ? የሚታተም አይመስለኝም ዳሩ ደራሲዎቹስ ኬት አምጥተው ይጽፉታል ፍቅር ድሮ ቀረ !
የድሮው እንደሆን ድሮ ተጽፏል
ጎሳ በጽሁፍህ ጣዕም ረክቻለሁ ከኔ በላይ ግን
ከትልቁ ደራሲ የተለገሰህ አስተያየት ዋጋ አለው ::

ሌላው የአዶላ ወርቅ የአካባቢውን ሰው አጥፊው ሆኖ ነው የኖረው ቢባል እኔም እስማማለሁ ::
እድሜያቸውን ሙሉ በጉልበታቸው ወርቅ እያመረቱ ኖረው ጉልበታቸው ሲደክም የተጣሉና በረንዳ አዳሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁንም አስታዋሽ የላቸውም ::
ስለዚ ነገር ብዙ የተባለ ቢሆንም እውነተኛ ሰሚ እስኪገኝ መጮሀችንን አናቆምም ::

አንፈራራችን ልክነህ የለንደን ኦሎምፒክ ሲጀመር መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያመቸን ኢትዮፎረም ስለሚሆን በደንብ እንገናኝበታለን ::
ራስብሩ ሠላም ሁኑ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 363, 364, 365 ... 381, 382, 383  Next
Page 364 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia