WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ ::
Goto page 1, 2  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Mon May 07, 2012 5:12 am    Post subject: 2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ :: Reply with quote

ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል :: ለዝርዝሩ እቺን ይጫኑ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Mon May 07, 2012 12:09 pm    Post subject: Re: 2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ :: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል :: ለዝርዝሩ እቺን ይጫኑ ::

ሰላም ክቡራን

ፈቃደኛ ከሆንክ ባቀረብክው ዜና ላይ እንደነጻ ጋዜጠኛ አንዳንድ የግልህን አስተያየቶች እንድጸጠኝ ፈልግወ ነበር

እነዚህ ሁለቱ "አሸባሪዎች " ማንነታቸው አልተገለጸም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ አረቦች ከማለት ውጪም የምን አገር ዜጎች እንደሆኑ ወይንም በምን አገር ፓስፖርት ወደአገራችን እንደገቡ አልተገለጸም ኢቬንቶቹ ደግሞ በጣም ፈጣን ነበሩ "አሸባሪዎቹ "ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ደረሱ በቀጥታ ወደአንዋር መስጊድ አመሩ ወረቀት በተኑ ለጂሀድ ቀሰቀሱ ...ወዲያውኑ ተያዙ በመቱበት አውሮፕላን የዛኑ እለት ዲፖርት ተደረጉ ...

እንግዲህ ልጠይቅ የፈለግኩት እነዚህ "አሸባሪዎች " ማንነታቸውና የመጡበት አገር መገለጽ አልነበረበትምን ? ከዚህም አልፎ ለአገሪቱ አደገኛ ከመሆናቸው አንጻር በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ ሊደረግባቸው ማለትም ተለኮዋቸው ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በቂ ምርመራ መደረግ አልነበረበትም ? የስዊድንን እና የአውሮፓ ህብረትን ጠንካራ ዲፕሎማስያዊ ጫና ተቋቁሞ ጋዜጠኞችን ያሰረው መንግስት የነዚህን ሰዎች ማንነት እና የመጡበትን አገር መግለጽ ምን ያስፈራዋል ?

እንዲህ ያለ ለብሄራዊ ደህንነት የሚያሰጉ ሰዎችን ዜና እንዲሁ ሾላ በድፍን አይነት ዜና ማቅረቡ ፋብሪኬትድ የሆነ ዜና አያስመስልበትም ?

እንደነጻ ጋዜጠኛ የግልህን አስተያየት ብትሰጠኝ ብዬ ነው

አመሰግናለው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Mon May 07, 2012 4:10 pm    Post subject: Reply with quote

አሰላማላኬሙ ወልዲያ ወንድሜ :: አስተያየትህን አንብቤዋለሁ :: በጣም ሰፊና አወያይ ይመስለኛል ...እኔ የምገምተውንና በውስጤ የሚሰማኝነ እነገርሀለሁ :: ከዛ ባለፈ ደሞ ሲል ላገራችን ሰላምና ፍቅር የሚያመጣው የትኛው መንገድ ነው ብዬም ለመጠቆም እመክራለሁ :: ያም ሲባል ሰላም በመቻቻልና በመፈቃቀድ እንጂ ባንዱ የምነት ኪሳራ እንደማይህንም እገነዘባለሁ :: ከዚህም ሁሉም በላይ ሁላችንም የምታስተሳስረን ሪጋርደልስ ኦፍ ሪሊጂየስ , ፖሎቲካል ኦር ፊልሲፊካል ዲፈርነስስ በጋራ የምትማጋርን ማገር አለችን ...ኢትዮጵያን ልልህ ብዬ ነው ::ባለፉት ዘመናት ኢትዮፕያዊው ሙስሊም ከክርስቲያን ጎረቤቱ ጋር በሰላም በፍቅር በመቻቻልና በመከባበር ለረጅም ዘመን ኖሯል :: እዚህ የክርስቲያን በሬ ሲጣል እዛ ሀላል ተብሎ የታረደ የስላም ሰንጋ እየተጣለ አብረን ደግሰናል :: ቤተሰቦቻን ሳያቁ የትኛው የስላም የትኛው የክርስቲያን መሆኑን ሳናውቅ እየጣፈጠን በልተናል :: በርግጥ አልፎ አልፎ ችግሮች መቀስቀሳቸው አልቀረም :: እናንተ አክራሪዎች እንዳሉ ሁሉ እኛም ቤትም አሉ :: ማጆሪቲው ግን ያን አይልም :: ይሄን ካልኩ በኌላ እኔም ስለ ሀጂ አባሺ አንዳንድ ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ :: የኛው ሰው ናቸው አሉኝ ሀረሬ ናቸው ይባላል :: ከኢትዮጵያ ምድር ወጥተው ባለም ዙሪያ ይሄን ያህል ተከታይ ሊኖራቸው እንደቻለ ሳስብ ስለኚህ ሰው የማወቅ ፍላጎት አደረብኝ :: እስኪ አንተም ስለ ሀጂ ህባሺ ( የአል ሀባሺ መስራች ) የምታውቀውን ንገረኝ :: እምነትህን ሳይሆን የውስጥ እውነትህን አስረዳኝ :: ከትምህርታቸው ጋር ላትስማማም ትችል ይሆናል :: ግን እኔ የምፈልገው አንድ None Muslim ለሆነ ሰው በሚገባው መልኩ ስለ ኢትዮጵያውው ሀጂ አበሺ እንድትነግረኝ ነው :: አደራ እምነህትና ፋክቶች ተደባልቀው እኔን እንዳያምታትቱኝ ጥንቃቄ አድርግልኝ :: እውነትን ተናገሩ ያም እውነት ነጻ ያወጣችሁአል ይላልና ቅዱስ ወንጌሉ :: እርግጠኛ ነኝ በቅዱስ ቁራኑ ላይም ይሄ አለ ብዬ አስባለሁ :: የውስጥህን ( የህሊናህን ) እውነት ለማለት ያህል ነው :: ይሄን ካልኩ በኌላ ደሞ አንድ ወቅታዊ የሆነች ጽሁፍ ሳነብ ያገኘኌትን ላካፍልህ ... የወቅቱን ሁኔታ ታሳያለች :: ከላይ ስለጠቀስካቸው መጤ አረቦች የማውቀውን ይዥ እመጣለሁ :: ሰላም ያውለን :: ወደ ጽሁፉ በዚች ሙዚቃ ...ስቀልድ ነው .. Very Happy

"" ያይን ምስክርነት ;-
ያኔ ልጅ ነበርኩ፡፡ ገና ኢህአዴግ ስልጣን ላይ መውጣቱ ስለነበር አገር አልተረጋጋም፡፡ እዛ እኛ ወረዳ - አርሲ ሽርካ ይባላል - ጃራ የሚባሉ ክርስትያኑን እየለዩ የሚያርዱ ወንበዴዎች ነበሩ፡፡ ቀይ ጉፍታ ጠጉራቸው ላይ ይሰካሉ፡፡ ክላሽ ከትከሻቸው አይጠፋም፡፡ ማንም አይናገራቸውም፡፡ በሙስሊሙ ስም ይነግዱ ነበር፡፡ ሙስሊሙን ግን አይወክሉም፡፡ ይጠቀሙበታል እንጂ፡፡ ሙስሊም መሆናቸውንም እንጃ፡፡ የሚሰሩት ስራ ግን ሙስሊም አያሰኛቸውም፡፡ ኢህአዴግ መጥቶ ባይገላግለን ኖሮ ይሄኔ በህይወት አንኖርም፡፡ ብዙዎቹን በመትረየስ ገደሉአቸው፡፡ እናም አገር ተረጋጋ፡፡ አትጠራጠሩ ዛሬም እንደዛ አይነት ግለሰቦች አይጠፉም፡፡ ብጥብጥ የለት ከለት ህልማቸው የሆነ፡፡

በኔ አገር የማወውቀው አንድ ክርስቲያን ሲያገባ ሁለት በሬ ይታረዳል፡፡ አንደኛው ለሙስሊሙ ማህሰብ ሲቀርብ ሌላኛው ለክርስትያኑ ይቀርባል፡፡ አንድ ሙስሊምም ሲያገባ እንደዛው ነው፡፡ አብረን ነው የምንበላው - አብረን ነው የምንጠጣው - አብረን ከብት እንጠብቃለን - አብረን ለኢሬቻ ወደ ወንዝ እንወርዳለን፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ፤ አብረን አንድ ላይ በህብረት እንኖራለን፡፡ አንዳንዴ የነውጥ አባዜ ያለበቸው ግለሰቦች ለምን ሊበጠብጡን እንደሚፈልጉ አይገባኝም፡፡

ያሁኑ እንኩዋን ሳስበው ከአረቦቹ ጋር የተገናኘ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ከግብጽ፡፡ ለኛ መቼ ተኝታ ታድራለችና፡፡ እኛ ሰላም ካለን እኮ እናድጋለን፡፡ ካደግንና ጡንቻችን ከፈረጠመ ደግሞ አባይን በደንብ እንጠቀማለን፡፡ ከዚያ ---፡፡ እናንተው ጨርሱት፡፡ በሌላ መንገድ መጥተውብን ቢሆንስ¿ እንደ ሶማሊያ እንሆን ዘንድ አቅደውልን ቢሆንስ¿

ወዳጄ፣ ቀድሞ ነው ማሰብ፡፡ ቀድሞ መገኘት ነው ዋናው ቁም ነገሩ፡፡ እነአሜሪካ የቀደሙን ቀድመው ስላሰቡ ነው፡፡ ዘመኑ ቀድሞ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ ክርስትያን፣ ሙስሊም፣ ዋቄፈታ እያልን መከፋፈል ያለብን አይመስለኝም፡፡ ከተለያየን ድህነቱ ይቀጥላል፡፡ ድህነት እንዴት እንዳሳመመኝ ውስጤን ከፍቼ ላሳያችሁ አልችልም፡፡ ልጅ ሆኜ ርሃብ ክፉኛ አሰቃይቶኛል፡፡ ክፉ ነው ርሃብ፡፡ ሆዳችሁን እየሞረሞራችሁ መተኛት እንኩዋን አትችሉም፡፡ በዛላይ ክብር ሲነካ ! እኔ ዛሬ ሳይሻለኝ አይቀርም፡፡ እኛ አገር ልክ እንደኔ በልጅነታቸው በርሃብ የሚጠበሱ ብዙ ልጆች አሉ፡፡ እነሱን እናስባቸውና ፍቅር ይኑረን፡፡ ይሄ ክብረ ነክ ድህነት አብሮን የቆየው ፍቅር ስላጣን ነው፡፡ ፍቅር ሲኖረን ሁሉ ይኖረናል፡፡

የፍቅር አምላክ ፍቅር ያድለን !

ምንጭ :- ከሪፖርተር ያስተያየት አምድ የተገኘ

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Mon May 07, 2012 6:39 pm    Post subject: Re: 2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ :: Reply with quote

ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል :: ለዝርዝሩ እቺን ይጫኑ ::

ሰላም ክቡራን

ፈቃደኛ ከሆንክ ባቀረብክው ዜና ላይ እንደነጻ ጋዜጠኛ አንዳንድ የግልህን አስተያየቶች እንድጸጠኝ ፈልግወ ነበር

እነዚህ ሁለቱ "አሸባሪዎች " ማንነታቸው አልተገለጸም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ አረቦች ከማለት ውጪም የምን አገር ዜጎች እንደሆኑ ወይንም በምን አገር ፓስፖርት ወደአገራችን እንደገቡ አልተገለጸም ኢቬንቶቹ ደግሞ በጣም ፈጣን ነበሩ "አሸባሪዎቹ "ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ደረሱ በቀጥታ ወደአንዋር መስጊድ አመሩ ወረቀት በተኑ ለጂሀድ ቀሰቀሱ ...ወዲያውኑ ተያዙ በመቱበት አውሮፕላን የዛኑ እለት ዲፖርት ተደረጉ ...

እንግዲህ ልጠይቅ የፈለግኩት እነዚህ "አሸባሪዎች " ማንነታቸውና የመጡበት አገር መገለጽ አልነበረበትምን ? ከዚህም አልፎ ለአገሪቱ አደገኛ ከመሆናቸው አንጻር በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ ሊደረግባቸው ማለትም ተለኮዋቸው ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በቂ ምርመራ መደረግ አልነበረበትም ? የስዊድንን እና የአውሮፓ ህብረትን ጠንካራ ዲፕሎማስያዊ ጫና ተቋቁሞ ጋዜጠኞችን ያሰረው መንግስት የነዚህን ሰዎች ማንነት እና የመጡበትን አገር መግለጽ ምን ያስፈራዋል ?

እንዲህ ያለ ለብሄራዊ ደህንነት የሚያሰጉ ሰዎችን ዜና እንዲሁ ሾላ በድፍን አይነት ዜና ማቅረቡ ፋብሪኬትድ የሆነ ዜና አያስመስልበትም ?

እንደነጻ ጋዜጠኛ የግልህን አስተያየት ብትሰጠኝ ብዬ ነው

አመሰግናለው

ወልድያ ከክቡራን ብዙ አትጠብቅ ...ይልቅስ ስለሰወቹ ማንነት ከረፖርተር ላይ ያገኘሁትን ላካፍልህ
Quote:
በመንግስት ሚዲያዎች ሁለት ከዉጪ የመጡ አሸባሪዎች በአንዎር መስጂድ የሽብርተኝነት ወረቀት ሲበትኑ ተያዙ በማለት የቀረበዉ ዜና እዉነታ የሚከተለዉን ይመስላል : ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ የመጡት አባታቸዉ በጠና በመታመሙ ወደ ሀበሻ ሂዱና ቁርአን ሀድያ ስጡልኝ ስላላቸዉ ያባታቸዉን ትዕዛዝ ለመሙላት ነበር :: የአየር መንገድ ትኬታቸዉም ያስቆረጡት ጠዎት ገብተዉ ማታ ለመዉጣት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል :: ሁለቱ ሰዎች ኤርፖርት ከደረሱ ቡሀላ የት ሄደዉ መስጠት እንዳለባቸዉ ስላላወቁ በመንገዳቸዉ ላይ አንድ ሱቅ ላይ በአረብኛ የተፃፈ ፁሁፍ ስላነበቡ ወድ ሱቁ በመሄድ ሱቁ ዉስጥ ያገኙትን ሰዉ የመጡበትን አላማ በመግለፅ ምንም ቦታ እንደማያዉቁ ካስረዱ ቡሀላ ያነጋገራቸዉ ሰዉ ወደ አንዎር መስጂድ እንዲሄዱ ይጠቁማቸዎል :: ሰዎቹም በኮንትራት አንዎር መስጂድ ከደረሱ ቡሀላ የአባታቸዉን ሀዲያ ለሙስሊሙ ማከፉፈል ጀመሩ ::ይሰጡ የነበሩት "ሂስኑል ሙስሊም " የምትባለዉን መፅሀፍ ነበር :: ይህንን እያደረጉ ሳለ በፓሊስ ተያዙ :: ሰዎቹ የአባታቸዉን አማና ካደረሱ ቡሀላ ማታዉን ለመመለስ ነበር ትኬታቸዉን የቆረጡት :: በማያዉቁት ጉዳይ ባይያዙም ኖሮ ሰዎቹ ማታዉን ወደ ሀገራቸዉ ተመላሽ ነበሩ ::ይህንን እዉነታ ይፉ ያደረግነዉ እኛ ሙስሊሞች የፀረ አሸባሪነትን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ማለት ሳይሆን በዚህ ወቅት ይህንን ዜና እዉነታዉን በመደበቅ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸዉን የመብት ጥያቄዎች ከአሸባሪዎች ጋር ለማያያዝ ስለተፈለገ ብቻ ነዉ !! አሸባሪነትን እኛ ሙስሊሞች ከማንም በፊት እንዎጋዋለን !! እዉነትን መናገር ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ ! የሚያስገርመዉ ሌላኛዉ ጉዳይ ደግሞ አሸባሪ ተይዞ በየትኛዉ አለም ነዉ ቶሎ ሀገር ለቀህ ዉጣ የሚባለዉ ? በቅርቡ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ የተነገረላቸዉ እና በሀገራችን ድንበር ላይ የተያዙት የዉጪ ጋዜጠኞች ወንጀለኛ በመሆናቸዉ እስር ተፈርዶባቸዉ ነበር :: እነዚህ ሁለት ሰዎች አሸባሪ ከነበሩና የአሸባሪነት ወረቀት ከበተኑ ለምን ተለቀቁ ? ይህንን ለናንተ ትተነዎል :: አላህ የዉሸት መስካሪዎች ከመሆን ይጠብቀን :: የሀገራችንን ሰላም የምንጠብቅና የምናስጠብቅ ያድርገን !!

http://ethiopianreporter.com/news/293-news/6205-2012-05-05-10-06-29.html
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Mon May 07, 2012 7:46 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድም ጎባጤ እንዳዋከበው ...
Quote:
Code:
 ወልድያ ከክቡራን ብዙ አትጠብቅ ...ይልቅስ ስለሰወቹ ማንነት ከረፖርተር ላይ ያገኘሁትን ላካፍልህ

እዉነታ የሚከተለዉን ይመስላል : ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ የመጡት አባታቸዉ በጠና በመታመሙ ወደ ሀበሻ ሂዱና ቁርአን ሀድያ ስጡልኝ ስላላቸዉ ያባታቸዉን ትዕዛዝ ለመሙላት ነበር :: የአየር መንገድ ትኬታቸዉም ያስቆረጡት ጠዎት ገብተዉ ማታ ለመዉጣት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል :: ሁለቱ ሰዎች ኤርፖርት ከደረሱ ቡሀላ የት ሄደዉ መስጠት እንዳለባቸዉ ስላላወቁ በመንገዳቸዉ ላይ አንድ ሱቅ ላይ በአረብኛ   የተፃፈ ፁሁፍ ስላነበቡ ወድ ሱቁ በመሄድ ሱቁ ዉስጥ ያገኙትን ሰዉ የመጡበትን አላማ በመግለፅ ምንም ቦታ እንደማያዉቁ ካስረዱ ቡሀላ ያነጋገራቸዉ ሰዉ ወደ አንዎር መስጂድ እንዲሄዱ ይጠቁማቸዎል :: ሰዎቹም በኮንትራት አንዎር መስጂድ ከደረሱ ቡሀላ የአባታቸዉን ሀዲያ ለሙስሊሙ ማከፉፈል ጀመሩ ::ይሰጡ የነበሩት "ሂስኑል ሙስሊም " የምትባለዉን መፅሀፍ ነበር :: ይህንን እያደረጉ ሳለ በፓሊስ ተያዙ :: ሰዎቹ የአባታቸዉን አማና ካደረሱ ቡሀላ ማታዉን ለመመለስ ነበር ትኬታቸዉን የቆረጡት :: በማያዉቁት ጉዳይ ባይያዙም ኖሮ ሰዎቹ ማታዉን ወደ ሀገራቸዉ ተመላሽ ነበሩ ::ይህንን እዉነታ ይፉ ያደረግነዉ እኛ ሙስሊሞች የፀረ አሸባሪነትን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ማለት ሳይሆን በዚህ ወቅት ይህንን ዜና እዉነታዉን በመደበቅ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸዉን የመብት ጥያቄዎች ከአሸባሪዎች ጋር ለማያያዝ ስለተፈለገ ብቻ ነዉ !! አሸባሪነትን እኛ ሙስሊሞች ከማንም በፊት እንዎጋዋለን !! እዉነትን መናገር ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ ! የሚያስገርመዉ ሌላኛዉ ጉዳይ ደግሞ አሸባሪ ተይዞ በየትኛዉ አለም ነዉ ቶሎ ሀገር ለቀህ ዉጣ የሚባለዉ ? በቅርቡ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ የተነገረላቸዉ እና በሀገራችን ድንበር ላይ የተያዙት የዉጪ ጋዜጠኞች ወንጀለኛ በመሆናቸዉ እስር ተፈርዶባቸዉ ነበር :: እነዚህ ሁለት ሰዎች አሸባሪ ከነበሩና የአሸባሪነት ወረቀት ከበተኑ ለምን ተለቀቁ ? ይህንን ለናንተ ትተነዎል :: አላህ የዉሸት መስካሪዎች ከመሆን ይጠብቀን :: የሀገራችንን ሰላም የምንጠብቅና የምናስጠብቅ ያድርገን !!

ወንድም ጎባጤ የጽሁፌ መረጃ ያለው የሪፖርተር ዜና ደሞ የሚገልጸው ..
Quote:
Code:
በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን ከትናንትና በስቲያ በተለይ በአዲስ አበባ በሚገኙ መስጊዶች ሊደረግ የነበረው ብጥብጥ የመፍጠር ቅስቀሳ፣ መንግሥት ሚያዝያ   25 ቀን 2004 .. ባስተላለፈው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ምክንያት መክሸፉን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ላለፉት 11 ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ መስጊዶች፣ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የተለያዩ ረብሻዎችን ሲያደርጉ የነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ከትናንትና በስቲያም በአንዳንድ መስጊዶች ላይ ረብሻ ለመፍጠር የሞከሩ ቢኖሩም፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች ያለምንም ችግር ፀሎታቸውን አድርሰው ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡፡

ከትናንትና በስቲያ በተለይ በአንዋር መስጊድ ለፀሎት ተሰባስበው በነበሩበት ወቅት የሃይማኖቱ ተከታዮች ‹‹አላህው አክበር፣ የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አንፈልግም፣ በምክር ቤቱ ምርጫ አያገባውም፤›› እና ሌሎችን መፈክሮች በማሰማት በመስጊዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲዟዟሩ እንደነበር በስፍራው የነበሩ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ሚያዝያ 25 ቀን 2004 .. በሰጠው የማስጠንቀቂያ መግለጫ፣ አንዳንድ ግለሰቦች ሃይማኖታዊ ተቋማትን በመጠጋት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች ያነሱ እንደነበር አስታውቋል፡፡ ግለሰቦቹ በአወሊያና በሌሎቹም መስጊዶች ሰላማዊ ሙስሊሞች ፀሎት እንዳያደርሱ፣ ዘመን አመጣሽ ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ለከፍተኛ ረብሻና ጥፋት ይዘጋጁ እንደነበር ጠቁሟል፡፡ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት በሰላምና በፍቅር ይኖር የነበረውን የሃይማኖት ተከታይ፣ በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን መብት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበርም አስታውሷል፡፡

በሃይማኖት ስም ያልሆነ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ቀደም ባሉት ዓመታት በአንዋር መስጊድ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ለበርካታ ዜጐች ሕይወት መጥፋት ምክንያት በመሆናቸው፣ ፍርድ ቤት የወሰነባቸውን ቅጣት ጨርሰው የወጡ አንዳንድ ግለሰቦችም እንደሚገኙበት መንግሥት በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው አብረዋቸው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

አወሊያ ትምህርት ቤትንና የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫን በሚመለከት ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ቢሰጣቸውም፣ ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዳልተሰጠ በማድረግ ሰፊ አፍራሽ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ማካሄዳቸውን የመንግሥት መግለጫ ያትታል፡፡

ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች እየፈጸሙ ያለው መንግሥትን የማጥላላት ድርጊታቸው መረን እየለቀቀ መምጣቱን ያስታወቀው የመንግሥት መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ጅሀድ (የሃይማኖት ጦርነት ) እስከማወጅ መድረሳቸውን ጠቁሟል፡፡

በፀጥታ ኃይሎች ላይ ድብደባና የተለያዩ የማስፈራሪያ ዛቻዎችን የሚያደርሱት እነዚሁ ወገኖች፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በምዕራብ አርሲ ዞን በገደባ አሳሳ ወረዳ አሳሳ ከተማው ውስጥ ባነሱት ብጥብጥ ንፁኅን ዜጎች መጐዳታቸውን መግለጫ አስታውሷል፡፡
ሚያዝያ 12 ቀን 2004 .. በአንዋር መስጊድ አካባቢ በፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የነበረን ፖሊስ በመደብደብ ጉዳት እንዳደረሱበት፣ አወሊያ ትምህርት ቤት አካባቢ በተደጋጋሚ መንገድ በመዝጋትና ለፀሎት በሚመጡት ላይ ድንጋይ በመወርወር የተለያዩ የብጥብጥ መፍጠሪያ ስልቶችን ሲጠቀሙ እንደነበር አመልክቷል፡፡

በተለያዩ መስጊዶች በመገኘት የፀሎት ሥነ ሥርዓት የሚመሩ ኢማሞችንና የሃይማኖት አባቶችን የድምፅ ማጉያ በመንጠቅ የፀሎት ሥርዓቱ እንዳይካሄድ ያደርጉ እንደነበር መግለጫው አስታውሶ፣ በቅርቡ ከአማራ፣ ከትግራይና ከኦሮሚያ የተመለመሉና ለሕገወጥ ተግባር የተላኩ 13 ግለሰቦች ቄሌም ወለጋ ዞን ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አብራርቷል፡፡

መንግሥት የንቅናቄው መሪ መሆናቸውን ከሚናገሩት ጋር በተደጋጋሚ ውይይት በማድረግ የተጀመረው አካሄድ እንደማያዋጣቸው ቢመክራቸውም፣ ከውይይቱ በኋላ የመንግሥትን ስም ማጥላላት መጀመራቸውን ገልጿል፡፡ ነገር ግን ማወቅ ያለባቸው ነገር ‹‹መንግሥት መሻገር የማይችሉት ቀይ መስመር እንዳለው ነው›› በማለት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል፡፡  

ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ዓርብ ሁለት የውጭ ዜጎች ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንግሥት አስታወቀ፡፡ በደፈናው ከመካከለኛው ምሥራቅ መጥተዋል የተባሉት ሁለቱ የውጭ ዜጎች ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወደ አንዋር መስጊድ በመሄድ የያዙትን ጽሑፍ ሊበትኑ ሲዘጋጁ እንደተደረሰባቸው መንግሥት ያወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ገጣባው ጎባጤ .. Surprised አንተ ምንጭ ብለህ የጠቀስከው ሊንክ ውስጥ እኮ ከላይ ያስቀመጥከው ማስተባበያ የለበትም :: ለምን ዋሾና ባለጌ ሆነህ ወንድም ወልደያ እንዲዋሽና ወደ ሀጢያት መንገድ እንዲሄድ ታደርገዋለህ ?? አንተስ ወደ ጀሀነም ቤትህ እንድትሄድ መጀመሪያውኑ የተቆረጠ ነገር ስለሆነ ችግር የለውም :: Very Happy ድልብ መሀይም !! ቆይ እስኪ ኮርማ መሀይም ልበልህ መሰለኝ !! Smile ጌኛ !! ምን አይነቱ ነው እባካችሁ አስሳች :: አንተንስ ሸይጣን ይውቀርህ !! Laughing ሌባ !! እኔ የምለው ግን ከዚህ በፊትም ከሁለት አመት በፊት አንዱ የጻፈውን ድርሰት የራስህ አስመስለህ ዋርካ ፍቅር ላይ ስትጽፍ አንገትህን አልኩህ :: በዛ በንስሳው ስምህ !! አልደግመውም ታውቀዋለህ :: አንተ የማይታወቅብህ መስሎህ ነበር ..አሁን ደሞ ያልተጻፈ ነገር እየጻፍክና የማይገናኝ ሊንክ እየሰጠህ ሰዎችን ሚስ ኢንፎርም ታደርጋለህ ..... ለመሆኑ የጽሁፍ ሙስና በደምህ ውስጥ ነው እንዴ ያለው ?? Rolling Eyes ሌባ ..!! አንተን ቅቤ በጠገበ ዱላ ነበር ማሸት !! በኅ ድንጋይ !!_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Mon May 07, 2012 7:56 pm    Post subject: Reply with quote

ስማ አንተ የብብት ቅማል ወለድያ ያለህ ስለሰውቹ ማንነት ንገረኝ ነው የሚልህ አንተ ግን ማስቀየስህ ነው ..መጋኛ ይቀየስብህ የሆን ጥንብ አንሳ .. ሌላ ሰው የጻፈው ድርሰት ምናምን የምትለው እሱን ለሚመለከተው ለኔ አይደለም ይልቅስ ወለድያ የጠየቀህን ሳትመልስ ደግሞ ስትጠይቅ አታፍርም አንተ ድንጋይ ራስ መዥገራም አራዊት ..ደግሞ አንተን ብሎ እውነታ ዘጋቢ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Mon May 07, 2012 8:03 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ሰላም ክቡራን

ፈቃደኛ ከሆንክ ባቀረብክው ዜና ላይ እንደነጻ ጋዜጠኛ አንዳንድ የግልህን አስተያየቶች እንድጸጠኝ ፈልግወ ነበር

እነዚህ ሁለቱ "አሸባሪዎች " ማንነታቸው አልተገለጸም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ አረቦች ከማለት ውጪም የምን አገር ዜጎች እንደሆኑ ወይንም በምን አገር ፓስፖርት ወደአገራችን እንደገቡ አልተገለጸም ኢቬንቶቹ ደግሞ በጣም ፈጣን ነበሩ "አሸባሪዎቹ "ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ደረሱ በቀጥታ ወደአንዋር መስጊድ አመሩ ወረቀት በተኑ ለጂሀድ ቀሰቀሱ ...ወዲያውኑ ተያዙ በመቱበት አውሮፕላን የዛኑ እለት ዲፖርት ተደረጉ ...

ወለድያ የቴየቀህ ይህንን ነው ...አንተ ድንጋይ አንተ ግን ያልተባለከውን ትዘባርቃለህ ...የሆንክ ጥንብ አንሳ

ስለሰወቹ ማንነት ደግሞ ትክክለኛው ይህ ነው

Quote:
በመንግስት ሚዲያዎች ሁለት ከዉጪ የመጡ
አሸባሪዎች በአንዎር መስጂድ የሽብርተኝነት ወረቀት ሲበትኑ ተያዙ በማለት የቀረበዉ ዜና እዉነታ የሚከተለዉን ይመስላል : ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ የመጡት አባታቸዉ በጠና በመታመሙ ወደ ሀበሻ ሂዱና ቁርአን ሀድያ ስጡልኝ ስላላቸዉ ያባታቸዉን ትዕዛዝ ለመሙላት ነበር :: የአየር መንገድ ትኬታቸዉም ያስቆረጡት ጠዎት ገብተዉ ማታ ለመዉጣት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል :: ሁለቱ ሰዎች ኤርፖርት ከደረሱ ቡሀላ የት ሄደዉ መስጠት እንዳለባቸዉ ስላላወቁ በመንገዳቸዉ ላይ አንድ ሱቅ ላይ በአረብኛ የተፃፈ ፁሁፍ ስላነበቡ ወድ ሱቁ በመሄድ ሱቁ ዉስጥ ያገኙትን ሰዉ የመጡበትን አላማ በመግለፅ ምንም ቦታ እንደማያዉቁ ካስረዱ ቡሀላ ያነጋገራቸዉ ሰዉ ወደ አንዎር መስጂድ እንዲሄዱ ይጠቁማቸዎል :: ሰዎቹም በኮንትራት አንዎር መስጂድ ከደረሱ ቡሀላ የአባታቸዉን ሀዲያ ለሙስሊሙ ማከፉፈል ጀመሩ ::ይሰጡ የነበሩት "ሂስኑል ሙስሊም " የምትባለዉን መፅሀፍ ነበር :: ይህንን እያደረጉ ሳለ በፓሊስ ተያዙ :: ሰዎቹ የአባታቸዉን አማና ካደረሱ ቡሀላ ማታዉን ለመመለስ ነበር ትኬታቸዉን የቆረጡት :: በማያዉቁት ጉዳይ ባይያዙም ኖሮ ሰዎቹ ማታዉን ወደ ሀገራቸዉ ተመላሽ ነበሩ ::ይህንን እዉነታ ይፉ ያደረግነዉ እኛ ሙስሊሞች የፀረ አሸባሪነትን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ማለት ሳይሆን በዚህ ወቅት ይህንን ዜና እዉነታዉን በመደበቅ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸዉን የመብት ጥያቄዎች ከአሸባሪዎች ጋር ለማያያዝ ስለተፈለገ ብቻ ነዉ !! አሸባሪነትን እኛ ሙስሊሞች ከማንም በፊት እንዎጋዋለን !! እዉነትን መናገር ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ ! የሚያስገርመዉ ሌላኛዉ ጉዳይ ደግሞ አሸባሪ ተይዞ በየትኛዉ አለም ነዉ ቶሎ ሀገር ለቀህ ዉጣ የሚባለዉ ? በቅርቡ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ የተነገረላቸዉ እና በሀገራችን ድንበር ላይ የተያዙት የዉጪ ጋዜጠኞች ወንጀለኛ በመሆናቸዉ እስር ተፈርዶባቸዉ ነበር :: እነዚህ ሁለት ሰዎች አሸባሪ ከነበሩና የአሸባሪነት ወረቀት ከበተኑ ለምን ተለቀቁ ? ይህንን ለናንተ ትተነዎል :: አላህ የዉሸት መስካሪዎች ከመሆን ይጠብቀን :: የሀገራችንን ሰላም የምንጠብቅና የምናስጠብቅ ያድርገን !!

ስማ አንተ አምቡላህን እየተጋትክ ይህ እንትና ነው ይህ እንትና ነው ብትል የኔን ገልብጠነት ማንም አቀይረውም ....በህልም አለም የምትኖር ብኩን ነገር ነህ ..እየተከተልኩ የምትለቀልቀውን ከማጋለጥ ወደኍላ አልላትም , እንጂ የፈለከውን ስምስጥ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Mon May 07, 2012 8:25 pm    Post subject: Re: 2 አረቦች ካንዋር መስጊድ በቀጥታ ወዳገራቸው ተላኩ :: Reply with quote

ኦርግ ኦሮግ ...ኦርግ ..... .. Laughing .እንዴት አይነት ደረቅ ሌባ ነህ አንተ ..አረ አንተን በሳማ ነው ዛሬ የምለበልብህ ...!! .ምን ምድር ነው አንተን የፈጠረህ ...ኬሻ !! ቆስጣ ራስ !! ደሞ አታፍርም ?? ከሪፖተረር የጠቀስከው ሊንክ የሚለው ሌላ አንተ የጻፍከው ሌላ !! ያንን በመረጃ ጎን ለጎን አቀረብኩልህ .. .አንተ ግን .ሳታፍር መጣህ !! ለመሆኑ ኢትዮጵያዊ ነህ ወይስ ከቡርኪና ፋሶ ተግዘህ ነው የመጣሀው ?? እኛ እናፍራለን ...የቡርኪና ፋሶን ቡዙ አላቅም ግን ናይጀሪያውያንም እፍረት የሚባል ነገር እንዳለፈጠረባቸው አውቃለሁ :: አንተም ከዛ አካባቢ ሳትሆን አትቀርም :: አንኬሮ ..ከርከሮ !! Laughing የሰጠሀው መረጃ የተሳሳተ ነው ....ተሳስተህ ሰው ልታሳስት ሞክረሀል ...ስህተተኛ ነህ :: ስህተትን አምነህ ይቅርታ ጠይቅ !! ሰው ከሆንክ ማለቴ ነው :: የቤት እንስሳ ከሆንክ ደሞ እንደ በሬ ጠልፌ ይቅርታ እንድትጠይቅ አደርግሀለሁ :: ምርጫው ያንተ ነው ::

ገልብጤ እንደጻፈ(ች)ው:
ወልድያ እንደጻፈ(ች)ው:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
ከዜናው መረዳት እንደተቻለው ሁለቱ አረቦች የመጡት ከመካከለኛው ምስራቅ ሲሆን ትክክለኛ ዜግነታቸው ግን አልተገለጸም :: ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ያመሩትም ወደ ታላቁ ያንዋር መስጊድ ሲሆን ጂሀድ እንዲካሄድ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎችን መበተናቸውንና አመጽ አነሳሽ ንግግር በሙስሊሙ ህብረተሰብ መሀል እንዳደረጉ ዜናው ይገልጻል :: ሁለቱ አረቦች በፖሊስ ተይዘው በመጡበት አውሮፕላን ተመልሰዋል :: ለዝርዝሩ እቺን ይጫኑ ::

ሰላም ክቡራን

ፈቃደኛ ከሆንክ ባቀረብክው ዜና ላይ እንደነጻ ጋዜጠኛ አንዳንድ የግልህን አስተያየቶች እንድጸጠኝ ፈልግወ ነበር

እነዚህ ሁለቱ "አሸባሪዎች " ማንነታቸው አልተገለጸም ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ አረቦች ከማለት ውጪም የምን አገር ዜጎች እንደሆኑ ወይንም በምን አገር ፓስፖርት ወደአገራችን እንደገቡ አልተገለጸም ኢቬንቶቹ ደግሞ በጣም ፈጣን ነበሩ "አሸባሪዎቹ "ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ደረሱ በቀጥታ ወደአንዋር መስጊድ አመሩ ወረቀት በተኑ ለጂሀድ ቀሰቀሱ ...ወዲያውኑ ተያዙ በመቱበት አውሮፕላን የዛኑ እለት ዲፖርት ተደረጉ ...

እንግዲህ ልጠይቅ የፈለግኩት እነዚህ "አሸባሪዎች " ማንነታቸውና የመጡበት አገር መገለጽ አልነበረበትምን ? ከዚህም አልፎ ለአገሪቱ አደገኛ ከመሆናቸው አንጻር በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ምርመራ ሊደረግባቸው ማለትም ተለኮዋቸው ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በቂ ምርመራ መደረግ አልነበረበትም ? የስዊድንን እና የአውሮፓ ህብረትን ጠንካራ ዲፕሎማስያዊ ጫና ተቋቁሞ ጋዜጠኞችን ያሰረው መንግስት የነዚህን ሰዎች ማንነት እና የመጡበትን አገር መግለጽ ምን ያስፈራዋል ?

እንዲህ ያለ ለብሄራዊ ደህንነት የሚያሰጉ ሰዎችን ዜና እንዲሁ ሾላ በድፍን አይነት ዜና ማቅረቡ ፋብሪኬትድ የሆነ ዜና አያስመስልበትም ?

እንደነጻ ጋዜጠኛ የግልህን አስተያየት ብትሰጠኝ ብዬ ነው

አመሰግናለው

ወልድያ ከክቡራን ብዙ አትጠብቅ ...ይልቅስ ስለሰወቹ ማንነት ከረፖርተር ላይ ያገኘሁትን ላካፍልህ
Quote:
በመንግስት ሚዲያዎች ሁለት ከዉጪ የመጡ አሸባሪዎች በአንዎር መስጂድ የሽብርተኝነት ወረቀት ሲበትኑ ተያዙ በማለት የቀረበዉ ዜና እዉነታ የሚከተለዉን ይመስላል : ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ የመጡት አባታቸዉ በጠና በመታመሙ ወደ ሀበሻ ሂዱና ቁርአን ሀድያ ስጡልኝ ስላላቸዉ ያባታቸዉን ትዕዛዝ ለመሙላት ነበር :: የአየር መንገድ ትኬታቸዉም ያስቆረጡት ጠዎት ገብተዉ ማታ ለመዉጣት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል :: ሁለቱ ሰዎች ኤርፖርት ከደረሱ ቡሀላ የት ሄደዉ መስጠት እንዳለባቸዉ ስላላወቁ በመንገዳቸዉ ላይ አንድ ሱቅ ላይ በአረብኛ የተፃፈ ፁሁፍ ስላነበቡ ወድ ሱቁ በመሄድ ሱቁ ዉስጥ ያገኙትን ሰዉ የመጡበትን አላማ በመግለፅ ምንም ቦታ እንደማያዉቁ ካስረዱ ቡሀላ ያነጋገራቸዉ ሰዉ ወደ አንዎር መስጂድ እንዲሄዱ ይጠቁማቸዎል :: ሰዎቹም በኮንትራት አንዎር መስጂድ ከደረሱ ቡሀላ የአባታቸዉን ሀዲያ ለሙስሊሙ ማከፉፈል ጀመሩ ::ይሰጡ የነበሩት "ሂስኑል ሙስሊም " የምትባለዉን መፅሀፍ ነበር :: ይህንን እያደረጉ ሳለ በፓሊስ ተያዙ :: ሰዎቹ የአባታቸዉን አማና ካደረሱ ቡሀላ ማታዉን ለመመለስ ነበር ትኬታቸዉን የቆረጡት :: በማያዉቁት ጉዳይ ባይያዙም ኖሮ ሰዎቹ ማታዉን ወደ ሀገራቸዉ ተመላሽ ነበሩ ::ይህንን እዉነታ ይፉ ያደረግነዉ እኛ ሙስሊሞች የፀረ አሸባሪነትን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ማለት ሳይሆን በዚህ ወቅት ይህንን ዜና እዉነታዉን በመደበቅ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸዉን የመብት ጥያቄዎች ከአሸባሪዎች ጋር ለማያያዝ ስለተፈለገ ብቻ ነዉ !! አሸባሪነትን እኛ ሙስሊሞች ከማንም በፊት እንዎጋዋለን !! እዉነትን መናገር ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ ! የሚያስገርመዉ ሌላኛዉ ጉዳይ ደግሞ አሸባሪ ተይዞ በየትኛዉ አለም ነዉ ቶሎ ሀገር ለቀህ ዉጣ የሚባለዉ ? በቅርቡ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ የተነገረላቸዉ እና በሀገራችን ድንበር ላይ የተያዙት የዉጪ ጋዜጠኞች ወንጀለኛ በመሆናቸዉ እስር ተፈርዶባቸዉ ነበር :: እነዚህ ሁለት ሰዎች አሸባሪ ከነበሩና የአሸባሪነት ወረቀት ከበተኑ ለምን ተለቀቁ ? ይህንን ለናንተ ትተነዎል :: አላህ የዉሸት መስካሪዎች ከመሆን ይጠብቀን :: የሀገራችንን ሰላም የምንጠብቅና የምናስጠብቅ ያድርገን !!

http://ethiopianreporter.com/news/293-news/6205-2012-05-05-10-06-29.html

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Mon May 07, 2012 8:57 pm    Post subject: Reply with quote

እውነቱን እንደምትጋፈው አምቡላ ትጋታታለህ እንጂ ማንንም አታጭበረብረም

አንተም ይህን አስተያየት ያመጣህው ከዚህ ዜና ነው
http://ethiopianreporter.com/news/293-news/6205-2012-05-05-10-06-29.html
Quote:
ያኔ ልጅ ነበርኩ፡፡ ገና ኢህአዴግ ስልጣን ላይ መውጣቱ ስለነበር አገር አልተረጋጋም፡፡ እዛ እኛ ወረዳ - አርሲ ሽርካ ይባላል - ጃራ የሚባሉ ክርስትያኑን እየለዩ የሚያርዱ ወንበዴዎች ነበሩ፡፡ ቀይ ጉፍታ ጠጉራቸው ላይ ይሰካሉ፡፡ ክላሽ ከትከሻቸው አይጠፋም፡፡ ማንም አይናገራቸውም፡፡ በሙስሊሙ
ስም ይነግዱ ነበር፡፡ ሙስሊሙን ግን አይወክሉም፡፡ ይጠቀሙበታል እንጂ፡፡ ሙስሊም መሆናቸውንም እንጃ፡፡ የሚሰሩት ስራ ግን ሙስሊም አያሰኛቸውም፡፡ ኢህአዴግ መጥቶ ባይገላግለን ኖሮ ይሄኔ በህይወት አንኖርም፡፡ ብዙዎቹን በመትረየስ ገደሉአቸው፡፡ እናም አገር ተረጋጋ፡፡ አትጠራጠሩ ዛሬም እንደዛ አይነት ግለሰቦች አይጠፉም፡፡ ብጥብጥ የለት ከለት ህልማቸው የሆነ፡፡

በኔ አገር የማወውቀው አንድ ክርስቲያን ሲያገባ ሁለት በሬ ይታረዳል፡፡ አንደኛው ለሙስሊሙ ማህሰብ ሲቀርብ ሌላኛው ለክርስትያኑ ይቀርባል፡፡ አንድ ሙስሊምም ሲያገባ እንደዛው ነው፡፡ አብረን ነው የምንበላው - አብረን ነው የምንጠጣው - አብረን ከብት እንጠብቃለን - አብረን ለኢሬቻ ወደ ወንዝ እንወርዳለን፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ፤ አብረን አንድ ላይ በህብረት እንኖራለን፡፡ አንዳንዴ የነውጥ አባዜ ያለበቸው ግለሰቦች ለምን ሊበጠብጡን እንደሚፈልጉ አይገባኝም፡፡

ያሁኑ እንኩዋን ሳስበው ከአረቦቹ ጋር የተገናኘ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ከግብጽ፡፡ ለኛ መቼ ተኝታ ታድራለችና፡፡ እኛ ሰላም ካለን እኮ እናድጋለን፡፡ ካደግንና ጡንቻችን ከፈረጠመ ደግሞ አባይን በደንብ እንጠቀማለን፡፡ ከዚያ ---፡፡ እናንተው ጨርሱት፡፡ በሌላ መንገድ መጥተውብን ቢሆንስ¿ እንደ ሶማሊያ እንሆን ዘንድ አቅደውልን ቢሆንስ¿

ወዳጄ፣ ቀድሞ ነው ማሰብ፡፡ ቀድሞ መገኘት ነው ዋናው ቁም ነገሩ፡፡ እነአሜሪካ የቀደሙን ቀድመው ስላሰቡ ነው፡፡ ዘመኑ ቀድሞ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ ክርስትያን፣ ሙስሊም፣ ዋቄፈታ እያልን መከፋፈል ያለብን አይመስለኝም፡፡ ከተለያየን ድህነቱ ይቀጥላል፡፡ ድህነት እንዴት እንዳሳመመኝ ውስጤን ከፍቼ ላሳያችሁ አልችልም፡፡ ልጅ ሆኜ ርሃብ ክፉኛ አሰቃይቶኛል፡፡ ክፉ ነው ርሃብ፡፡ ሆዳችሁን እየሞረሞራችሁ መተኛት እንኩዋን አትችሉም፡፡ በዛላይ ክብር ሲነካ ! እኔ ዛሬ ሳይሻለኝ አይቀርም፡፡ እኛ አገር ልክ እንደኔ በልጅነታቸው በርሃብ የሚጠበሱ ብዙ ልጆች አሉ፡፡ እነሱን እናስባቸውና ፍቅር ይኑረን፡፡ ይሄ ክብረ ነክ ድህነት አብሮን የቆየው ፍቅር ስላጣን ነው፡፡ ፍቅር ሲኖረን ሁሉ ይኖረናል፡፡

የፍቅር አምላክ ፍቅር ያድለን

ይህንን አመጣህና ትክክለኛውን አስተያየት ግን አለፍከው ..አንተን ብሎ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ዘጋቢ ጋዜጠኛ

እኔ ያመመጣሁት ደግሞ ይህ ነው
Quote:
በመንግስት ሚዲያዎች ሁለት ከዉጪ የመጡ አሸባሪዎች በአንዎር መስጂድ የሽብርተኝነት ወረቀት ሲበትኑ ተያዙ በማለት የቀረበዉ ዜና
እዉነታ የሚከተለዉን ይመስላል : ሁለቱ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ የመጡት አባታቸዉ በጠና በመታመሙ ወደ ሀበሻ ሂዱና ቁርአን ሀድያ ስጡልኝ ስላላቸዉ ያባታቸዉን ትዕዛዝ ለመሙላት ነበር :: የአየር መንገድ ትኬታቸዉም ያስቆረጡት ጠዎት ገብተዉ ማታ ለመዉጣት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል :: ሁለቱ ሰዎች ኤርፖርት ከደረሱ ቡሀላ የት ሄደዉ መስጠት እንዳለባቸዉ ስላላወቁ በመንገዳቸዉ ላይ አንድ ሱቅ ላይ በአረብኛ የተፃፈ ፁሁፍ ስላነበቡ ወድ ሱቁ በመሄድ ሱቁ ዉስጥ ያገኙትን ሰዉ የመጡበትን አላማ በመግለፅ ምንም ቦታ እንደማያዉቁ ካስረዱ ቡሀላ ያነጋገራቸዉ ሰዉ ወደ አንዎር መስጂድ እንዲሄዱ ይጠቁማቸዎል :: ሰዎቹም በኮንትራት አንዎር መስጂድ ከደረሱ ቡሀላ የአባታቸዉን ሀዲያ ለሙስሊሙ ማከፉፈል ጀመሩ ::ይሰጡ የነበሩት "ሂስኑል ሙስሊም " የምትባለዉን መፅሀፍ ነበር :: ይህንን እያደረጉ ሳለ በፓሊስ ተያዙ :: ሰዎቹ የአባታቸዉን አማና ካደረሱ ቡሀላ ማታዉን ለመመለስ ነበር ትኬታቸዉን የቆረጡት :: በማያዉቁት ጉዳይ ባይያዙም ኖሮ ሰዎቹ ማታዉን ወደ ሀገራቸዉ ተመላሽ ነበሩ ::ይህንን እዉነታ ይፉ ያደረግነዉ እኛ ሙስሊሞች የፀረ አሸባሪነትን እንቅስቃሴ እንቃወማለን ማለት ሳይሆን በዚህ ወቅት ይህንን ዜና እዉነታዉን በመደበቅ ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸዉን የመብት ጥያቄዎች ከአሸባሪዎች ጋር ለማያያዝ ስለተፈለገ ብቻ ነዉ !! አሸባሪነትን እኛ ሙስሊሞች ከማንም በፊት እንዎጋዋለን !! እዉነትን መናገር ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ ! የሚያስገርመዉ ሌላኛዉ ጉዳይ ደግሞ አሸባሪ ተይዞ በየትኛዉ አለም ነዉ ቶሎ ሀገር ለቀህ ዉጣ የሚባለዉ ? በቅርቡ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉ የተነገረላቸዉ እና በሀገራችን ድንበር ላይ የተያዙት የዉጪ ጋዜጠኞች ወንጀለኛ በመሆናቸዉ እስር ተፈርዶባቸዉ ነበር :: እነዚህ ሁለት ሰዎች አሸባሪ ከነበሩና የአሸባሪነት ወረቀት ከበተኑ ለምን ተለቀቁ ? ይህንን ለናንተ ትተነዎል :: አላህ የዉሸት መስካሪዎች ከመሆን ይጠብቀን :: የሀገራችንን ሰላም የምንጠብቅና የምናስጠብቅ ያድርገን !!

ይህ ነው ..ወልድያ ለጠየቀው ትክክለኛ መልስ

ደግሞ ይቅርታ በል ትላለህ ..አንድ ከእንሰሳ የማይሻል ሰው ይቅርታ ከምል ከዋርካ ለምን አልታገድም የምትፈልገው ይህንን አይደል ..እውነትና ንጋት እያደረ ይጠራ [/quote]
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Tue May 08, 2012 2:59 am    Post subject: Reply with quote

አባ እኔ እኮ ወልደያ የጠየቀውን ጥያቄ አልመለሰም አላልኩም :: እሱ ጥያቄ ጠይቆአል :: የማውቀውንና የገባኝን ያህል እንደመምመለስለትም ተናግሬአለሁ :: በዚህ መሀል አንተ መጥተህ ከክቡራን ምንም አትጠብቅ ይሄ ነው እውነቱ አልክና እስክስታ ወረድክ :: Very Happy እኔም ስራ ካቀለልክልኝ ብዬ የለጠፍከውን ሊንክ ስመለከተው አንተ ከጻፍክው ጋር የማይሄድ ነው :: እንዳታጠፋው ኮፒ አድሬጌዋለሁ :: ይሄ ስህተት ነው ይቅርታ ጠይቅ ነው ያልኩት እንጂ እኔን ይቅርታ ጠይቀኝ አላልኩም :: እኔን እመታለሁ ብለህ የወረረከው ቅዝምዝም እኮ ነው መሀል አናትህን ብሎ የጣለህ ... Laughing እኔን ምን አደርግ ነው የምትለኝ ?? አንተን ካረካህ ልክ ነኝ የሚል ስሜት በውስጥህ የሚሰማህ ከሆነ (I mean if you dont feel any guiltiness dont really bother ) የሌለህን ህሊና ባንድ ምሽት አትፈጥረውም :: እኔም ያገኘሁበትን ምንጩን ካንተ በፊት ጠቅሸዋለሁ :: ልዩነቱ የኔ እንዳለ ከምንጩ የተቀዳ ነው ...የለወጥኩት ምንም ነገር የለም :: አንተ የለጠፍከው ሊንክና የጻፍከው ደሞ አይገናኝም እንዴት ብዬ ላስረዳህ ....ሰው ነህ ከርከሮ ነህ ....ኮርማ ነህ ....አንኬሮ ነህ , ግራዋ ነህ .......በምን ቌንቌ ላውራህ ..ግራ ገባኝ እኮ .. Very Happy አሁንም ትክክል ነኝ ብለህ ካምንክበት በዚሁ ቀጥል :: እኔ እንዳነበብኩህ ቡዙ አይኖች ግን ያነቡሀል :: ሰላም አምሽ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1335

PostPosted: Tue May 08, 2012 5:38 am    Post subject: Reply with quote

ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው:
አባ እኔ እኮ ወልደያ የጠየቀውን ጥያቄ አልመለሰም አላልኩም :: እሱ ጥያቄ ጠይቆአል :: የማውቀውንና የገባኝን ያህል እንደመምመለስለትም ተናግሬአለሁ :: በዚህ መሀል አንተ መጥተህ ከክቡራን ምንም አትጠብቅ ይሄ ነው እውነቱ አልክና እስክስታ ወረድክ :: Very Happy እኔም ስራ ካቀለልክልኝ ብዬ የለጠፍከውን ሊንክ ስመለከተው አንተ ከጻፍክው ጋር የማይሄድ ነው :: እንዳታጠፋው ኮፒ አድሬጌዋለሁ :: ይሄ ስህተት ነው ይቅርታ ጠይቅ ነው ያልኩት እንጂ እኔን ይቅርታ ጠይቀኝ አላልኩም :: እኔን እመታለሁ ብለህ የወረረከው ቅዝምዝም እኮ ነው መሀል አናትህን ብሎ የጣለህ ... Laughing እኔን ምን አደርግ ነው የምትለኝ ?? አንተን ካረካህ ልክ ነኝ የሚል ስሜት በውስጥህ የሚሰማህ ከሆነ (I mean if you dont feel any guiltiness dont really bother ) የሌለህን ህሊና ባንድ ምሽት አትፈጥረውም :: እኔም ያገኘሁበትን ምንጩን ካንተ በፊት ጠቅሸዋለሁ :: ልዩነቱ የኔ እንዳለ ከምንጩ የተቀዳ ነው ...የለወጥኩት ምንም ነገር የለም :: አንተ የለጠፍከው ሊንክና የጻፍከው ደሞ አይገናኝም እንዴት ብዬ ላስረዳህ ....ሰው ነህ ከርከሮ ነህ ....ኮርማ ነህ ....አንኬሮ ነህ , ግራዋ ነህ .......በምን ቌንቌ ላውራህ ..ግራ ገባኝ እኮ .. Very Happy አሁንም ትክክል ነኝ ብለህ ካምንክበት በዚሁ ቀጥል :: እኔ እንዳነበብኩህ ቡዙ አይኖች ግን ያነቡሀል :: ሰላም አምሽ ::

ትክክል ነኝ ..አሁንም እደግመዋለሁ ትክክል ነኝ ...ማንም ሰው ቢሆን ዜናውን ተከትሎ ነው ወደ አስተያየቱ መሄድ ያለበት ...አንት ግን ወለድያ ስለሰወቹ ማንነት ሲጠይቅህ ስለድሮ ታሪክ ታወራለህ ..እናም እኔ ስለሰወቹ ማንነት እና እና ያንተን አስትያየት ከየት እንዳመጣህው ሊንኩን ጠቆምኩ እንጂ ..እንዳንተ ከኔ በላይ አዋቂ የለም አላልኩ ..እንዳንተ አይነቱ የሰፈር የልምድ አዋላጅ ስላይደለሁ ......ደግሞ የፈለከውን ስም ድፈርድር
ክቡራን aka ጎተራ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ምክክር

ኮትኳች

Joined: 26 Jun 2008
Posts: 244
Location: Super Earth

PostPosted: Tue May 08, 2012 7:34 am    Post subject: Reply with quote

ክቡሻ :- የሰው ልጅ ሙያው እንዲከበር በቂጡ ሣይሆን በቅጡ ነው መጣር ያለበት :: ይህ ያንተን "ሙያዊ " ጉዳይ ከሚዛናዊነት ጋር የሚያያዝ ግልጽ ውይይት ስለሆነ ሌላ ፍሮንት ከፍተህ ከገልብጤ ጋር አትቀጣቀጥ :: ትንሽ ሰንበትበት ያልሽ ጮሌ የፒያሳ አራዳ ትመስያለሽ ? ይህ ትውልድ ሌላ ነው :: እሳት የላሰ ትውልድ ! እሳት ትልሣለህ አንተ ?

ይህን ርዕስ በተመለከተ ኮመን ሴንስ እንዲህ ይላል :-
1) መንግሥት የሰዎቹን ስም : ዜግነት በመግለጽ ክስ መመሥረት : ኬዙን ይፋ ለሕዝብ ማሳወቅ ያለበት መሆኑንና ...
2) ነፃ ጋዜጠኞችም (እንዲህ አንተን የመሳሰሰሉ ) ይህን ተከታትለው : መንግሥትን አፋጣው ሕዝቡ ሀቁን በገሃድ ማወቅ አለበት በሚል መርህ መታገል : መጣር እንዳለባቸው ሙያዊ ግዴታና ኃላፊነት ሲወጥራቸው መታየት አለባቸው .... .

ይህ ለምን አልሆነም ነው የወልድያና የገልብጤ ጥያቄ ?

የውሸት ክስ ነው ::

መንግሥት አሁን የተቀጣጠለውን የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ከሽብር ሊቋጥረው እንደሚያስብ ማሰባችንን እንኳ አለማሰቡ ይገርማል :: ከውጭ እጅ እንዳለበት ለማስመሰል እንዲህ ዓይነት ርካሽ ጨዋታ ጊዜው አልፏል .. ያው ፈጣንና አሳማኝ ልከካ ከአረቦች ጋር ማያያዝ ሆነ ... ያዋጣው መስሎታል :: እርድና ያለቀበት አራዳ !

የስዊዲንን ጋዜጠኞች አስሮ አልነበር እንዴ ? እነዚህ ዐረቦች ያውም ከአዲስ አበባ በቀጥታ አንዋር መስጊድ ...ከዚያ ሽብር ሊስብኩ ....ቂቂቂቂ ሌባ ተይዞ ዱላ ይጠየቃል ? ለምን አልቀፈደዳቸውም ? ምርመራ ተካሂዶስ ይፋ ለምን ለሕዝቡ አይወጣም ? ይህ እኮ ለኢህአድግ አንድ ፕላስ ስኬት ነው :: ያውም ስኬት እየጠማው :: ወይስ ክው ያለ ከንፈሩን ዓባይ አርሶታል ?

ክቡ :- የማይመስል ነገር ለዋርኪስቶች አትንገር ::

We are ahead of you kiddo.....

.......
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወልድያ

ኮትኳች

Joined: 24 May 2010
Posts: 492

PostPosted: Tue May 08, 2012 7:58 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖቼ ክቡራን እና ገልብጤ (ገልብጤ ለኢንፎርሜሽኑ አመሰግናለው ) ነገሩን ግን ሳናከር ብናየው ደስ ይለኝ ነበረ

ለክቡራን የነበረኝ ጥያቄ በሁለት ብከፍለው

አንደኛው ዜናውን ከፕሮፌሽናሊዝም እይታ ምን ይመስላል የሚል ሲሆን ሁለተኛው ከህግ አንጻር ተወሰደ ስለተባለው እርምጃ ይመለከታል

በተለይ የዜናው ጉዳይ ክቡራን እንደጋዜጠኛ ግላዊ አስተያየቱን ነበር የፈለግኩት
ክቡራን እርግጥ አንተ እንደግለሰብ የራስህ ርእዮተ አለም እምነት እንደሚኖርህ አውቃለው እንዲሁም በጋዜጠኝነትህ ልታከብረው ቃል የገባህለት ስነምግባርና መርሆዎች አሉ አሁንም እኔ የጠየቅኩህ በዚሁ በጋዜጠኝነት ካፓሲቲህ ዜናውን እንድትገመግምልኝ ነበረ

ከኔ በላይ እንደምታውቀው 10 የጋዜጠኛነት መርሆዎች አንዱ ቬሪፊኬሽን ነው

Verification Example: "Seeking out multiple witnesses, disclosing as much as possible about sources, or asking various sides for comment... [The] discipline of verification is what separates journalism from other modes of communication, such as propaganda, fiction or entertainment" (Principles of Journalism, from Project for Excellence in Journalism)

ታድያ የኔም ጥያቄ ይህን ዜና ቬሪፋይ ለማድረግ ዜናውን የለቀቀው አካል የነዚህን ሰዎች ማንነት እና ዜግነት እንክዋን መጥቀስ አልነበረበትም ወይ ? የሰዎቹ ማንነት አይደለም ዋናው የዜናው አዘጋገብ ላይ ነበረ Yጥያቄዬ

ዜናውን አንተ እንዳልዘገብከው አውቃለው የዘናው ምንጭ ቦስተን .ኮም ይላል መሰለኝ ግን ሽመልስ ከማልን ለተጨማሪ መረጃ ወጥረው መያዝ አልነበረባቸውም ? ከለላ አቅጣጫም ዜናውን ለማጣራት መሞከር አልነበረባቸውም እንዲህ አይነት ዜና ከኢቲቪ ቢሆን አይደንቅም ኢቲቪን የመንግስት ኢንተረስት እንጂ የጋዜጠኝነት መርሆዎች አይገዙትም ባብዛኛው የኢንፎርሜሽን ሳይሆን የፕሮፖጋንዳ ማሽን ሆኖ እያገለገለ ይገኛል ሆኖም የግል የኢንፎርሜሽን ምንጮች ተአማኒ ለመሆን ምን ያህል መስራት አለባቸው

እና አንተ በነጻ ጋዘጠኝነት አይን ተያዙ የተባለውን ሰዎቹ ማንነት ሳይሆን በዋናነት ዜና አቀራረቡን እራሱን እንድገመግምልኝ ነበረ ጥርጣሬን ሊፈጥር ይችላል ወይንስ at face value መወሰድ የሚችል ዜና ነው ?

ለላው ከህግ አንጻር ስታየው ሰዎቹ ፈጸሙ የተባለው ወንጀል ከባድ ወንጀል ነው ሁለት ኢትዮጵያውያን ሳውዲ ውስጥ አገሪቱን ለማበጣበጥ ሲሰሩ ቢገኙ በአውሮፕላን እንዲሸኙ አይደለም የሚደረገው እናም እነዚህ ሰዎች ፈጸሙ ከተባለው ወንጀል አንጻር ምርመራ ሊካሄድብቸውና ወንጀለኛ ሆነው ከተገኙ ለፍርድ ሊቀርቡ አይገባም ነበር ? መንግስት ለምን ለዘብተኛ እርምጃ ወሰደ ?መቸም የህግ ባለሙያ ባትሆንም ጋዜጠኛ ባብዛኛው ጠቅላላ እውቀት ስለሚኖረው ይህንንም የግልህን አስተያየት ብትሰጠኝ ብዬ ነው
__________________
__________________

አንተ ወዳነሳኸው ነጥብ ስመጣ ሙስሊም እና ክርስታያያን አብረን ኖረናል የራሴን ምሳሌ ልስጥህ የመጀመርያ ጓደኛየ ጥሩ ኦርቶዶክስ ክርስትያን ነው እኔ የምወድለት ባህርያትም አሉት መጠጥ የደረሰበት አይደርስም አይጨስም ጫትም አይወድም ጥሩ መካሪ ወንድም ነው ባህሪው መልካም ስለሆነ እናቴ ከለሎች ሙስሊም ጓደኞቼ ይልቅ እሱን ትወደዋለች እነም በተሰቦቹ ጋር ጥሩ አቀባበል አለን በኛ ምክንያት እናቴና እናቱ ይጠያየቃሉ በትምህርት አለም አብረን ነበርን ሲያገባ የመጀመርያ ሚዜው ነበርኩ እሱ ባገባ 15 ቀን እኔ ሳገባ የመጀመርያ ሚዜዬ ሆነ በኛ ምክንያት ባለቤቴና ባለቤቱ ግዋደኞች ሆነዋል ማሻአላህ ልጆቻችንም 20 ቀን ይሁን 22 ቀናት ልዩነት ተወለዱ አሁን ህጻናት ቢሆኑም guess what ታድያ they are best buddies Cool መስጊድ መግባት ሲኖርብኝ ሻይ እየጠጣ ይጠብቀኛል በተክርስትያን መግባት ሲኖርበት ሻይ እየጠጣ እጠብቅዋለው ማንኛውም እምነት ነክ የሆነ ስራ ላይ እንለያያለን መልካሙን ግዜ እንዲህ ነው ያሳለፍነው አሁን ምን ለማምጣት እንደሚሞከር አላውቅም

ስለአህባሽ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባልፈልግም ሰውየው እዚህ ተቀባይነት ስላላገኙ ነበር ወደሊባኖስ ያቀኑት እዛ ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ አላቸው በማን ? ብረትን መቁረጥ የሚቻለው በብረት ነው ብለው በተነሱ ሀይሎች ! ስለአምስተኛው ረድፍ ሰምተህ ታውቃለህ ክብራን ? አንድ ጀነራል አንዲትን አገር ሊወር ሄደ ከዛም ለበላዩ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ አገሪትዋን በአራት ረድፍ ከብብያታለው አገሪቱ መሀልም እነሱን መስሎ የሚሰራ አምስተኛ ረድፈኛ አለኝ ! አህባሽ አምስተኛ ረድፈኛ ነው :: አንተ እንዳልከው በአለም ዙርያ የሚባል ተከታይ የላቸውም ሁሉም ቦታ ተወግዘዋል
ሆኖም ጥያቄው አህባሽ ጥሩ ነው አይደለም አያስተምር አይደለም ጥያቄው የፕሪንሲፕል ነው የግዳጅ ጠመቃ አይኑር ነው / ሽፈራው እየቆነጠጥን እናስተምራለን እንዳሉ ሳትሰማው አትቀርም አህባሾች ያስተምሩ ሌላውን ያስተምር ሰው የፈለገውን ይምረጥ

ህዝቡ መጅሊሱ ላይ ያሉ አመራሮች አይወክሉንም እና ይነሱልን ነው ያለው ምንም አይነት ፖለቲካ ነክ ጥያቄ የለውም ህገ መንግስቱ የወረቀት ላይ ብቻ እስካለሆነ ድረስም የተነሱት ጥያቄዎች ህገ መንግስቱን እንደአገሪቷ ገዢ ህግ በመቁጥርና እሱን በመንተራስ ነው እዚህ ጋር መንግስት የአባትነትና የመንግስትነት ሚና መጫወት አለበት ያልተፈለጉትን የመጅሊስ አባላት አስወግዶ ህዝቡ በሚያምናቸው ጊዝያዊ አባላት መተካትና ምርጫ የሚደረግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ! ፕሮብሌም ሶልቭድ !

በያካባቢው የጽንፈኝነት ሁኔታዎች ሊታዩ ይችላሉ በአንድ ሀይማኖት ሳይሆን በሁሉም ሀይማኖቶች ! ይህንንም መንግስት ባለው ስልጣን ፈጣን እርምጃ ሊወስድበት ሲገባ አህባሽ ነው መፍትሄው ማለቱ አስገራሚ ነው የተወሰኑ ኦርቶዶክሶች የጽነፈኛ ባህሪ ቢያሳዩ መንግስት መፍትሄው የሮማ ካቶሊክ ወይንም የራሻ ኦርቶዶክስ ወይንም ተሀድሶ ኦርቶዶክስ መፍትሄ ይሆናል ብሎ ቀሳውስቱን ሰብስቦ ይህን ነው መማር ያለባቹህ ይህን ነው መስበክ ያለባቹህ ቢል ምን ይፈጠራል ????

ከሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Tue May 08, 2012 1:21 pm    Post subject: Reply with quote

http://www.youtube.com/watch?v=PJy69JpGNl0&feature=BFa&list=PL06F004455CD09946

ሰላም ወንድም ወልደያ ረዘም ላለውና በመልካም ስነ ምግባር ለጻፍካቸው መልሶች አመሰግናለሁ ::አላህ ይስጥልኝ :: ጥሩ ነጥቦችን አንስተሀል :: ከጊዜ አንጻር ሰፊና ረጅም መልስ ላልሰጥህ እችላለሁ :: ግን ከመካከለኛው ምስራቅ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከዛ ደሞ ወደ አንዋር መስጊድ አመሩ ስለተባሉት ሁለት አረቦች ከዜናው ባሻገር የራሴም ግምትና ጥርጣሬ ይኖሩኛል :: መንግስት የውጭ አገር ዜጎች ወንጀል ሰርተው ሲያገኝ የሚወስደው እርምጃ ሁል እንደ ሀገራችን ህግ ሳይሆን ካለም አቀፋዊ ህግ ከያገሮቹ ጋር ያለው የዲፕሎማሲ ስምምነት እንዲሁም ያለው ቀላል አማራጭ ( ሾርት ካት ) ምንድነው ? የሚለውን ያያል :: እነዚህ ሰዎች ፍርድ ቤት እንዲቆሙ ቢደረግ መንግስት ጠበቃ መቅጠር አለበት .. ከሪስፕኬቲቭ አገሮቹ ጋር ደብዳቤ መጻጻፍ ስለ ሰዎቹ ""ባክ ግራውንድ ቼክ "" መረጃ ማሰባሰብን ይጠይቃል ..ያገሩ መንግስታትም ዜጎቼ ተጉላሉ በሚል አንቻ ክራንቻ መፈጠራቸው አይቀርም :: የስር አያያዛቸው ትክክል አይደለም መብታቸው አልተጠበቀም , ደያስ አበሏቸው .... ሊነሱ የሚችሉ ነግሮች ናቸው :: የኢትዮጵያ መንግስት ይሄን ሁሉ ያውቃል የዋህ አይደለም ....ለዚህ የሚሆነው ጊዜውም ብሩም ያለው አይመስለኝም ጉዳዩን እንዴት አደርጎ መያዝ እንዳለበት ስለ ተገነዘበ መሰለኝ ...በመጡበት አይሮፕላን ጭኖ የመለሳቸው :: አሜሪካኖች ኦሳማ ላደን ላይ ቅጸበታዊ እርምጃ የወሰዱበት እሱን በህይወት ከመያዝ ተከትሎ የሚወጣውን ህጋዊ ኮኒሲከንስ ጫና ምናልባትም የህዝብን ዐፕ ራይዚንግ ለማስወገድ ነው :: ውሳኔው ባሜሪካ አንጻር ብልህነት ነው ...በኦሳማ ደጋፊዎች አንጻር የግፍ ውሳኔ ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል :: እንደምናይበት ኮርነር ይለያያል :: ከጊዜ አንጻር አጠር አጠር እያደረኩ እመለሳለሁ :: ያረፋ አብዱልከሪምና ያሊ ኢብራሂም ፈረሀን ተይዘው ወደ ቦሌ ሲሸኙ የምያሳየውን የዜና ቪዲዮ ተመልከተው እመለሳለሁ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5057

PostPosted: Thu May 10, 2012 3:43 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወንዴሜ ወልደያ ...መቼም የወሎ ሰው ትመስለኛለህ እንደው ስገምት ነው ....ወሎ ገነት ምድር ናት የሰላም አምባ ....ሼካው የሚዘይርባትቄሱ ማህሌት የሚወርድባት ..ቅድስት አገር ናት እቺ ወሎ ....መሀመድና ቡዙነሽ የታጋቡባት ...አንቺም ባሀይማኖቴ እኔም ባህያማኖቴ ብሎ ቴዲም ያዜሜላት አገር ናት ያች ወሎና ወሎይቷ ... ...Having said this I would like to transition to the point..በኔ እምነት እነዚህ አረቦች ለሰላም አልመጡም ....ስኬት ሊያስጽፉ እንደመጡ ነው የምገምተው አንዳንድ ነገሮችን እንይ :: እነዚህ ሰዎች መነሻ አገር አላቸው አምባሳደርም ወይ ቆንስላም ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራቸዋል :: ቢያንስ አምባሳደሩ ሰላማዊ ዜጎቼ ያለ ስማቸው ስም ተሰጣቸው ...ብሎ የኢትዮጵያን መንግስት ሲከስ አልተሰማም :: ዝም ነው ያለው :: ይሄ እኮ የቆንስላዎችና ያምባሳደሮች ዋና ስራ ነው :: ሰዎቹ ሳይሆኑ በያዙት ፓስፖርት ብቻ የዛን አገር ሰቨርጂኒቲ እንዳሰደፈሩ ይቆጠራልና :: ! ሌላው እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ከተባረሩ በኍላም ላገራቸው መንግስት ምንም አይነት ክስ አላቀረቡም እኛን ሰላማውያኑን የአላህ ቅዱሳን የኢትዮጵያ መንግስት እያክለፈለፈ ካገር አባረረን ብለው ለሰባዊ መብት ተማጔቾች ወይ ለመንግስታቸው አቤትታ አላሰሙም :: እውነት ለሰላም ጉዳይ ቢመጡ ኖሮ ባልሰሩት ስራ ካገር እንዲወጡ ሲደረግ ዝም ማለት አልነበረባቸውም ::ቢያንስ ላልጃዚራ መናገር አለባቸው :: ይሄ ይያዝልኝ :: እና ታዲያ ለምን መጡ ? ማንን ለመደገፍ መጡ ? ማንንስ ለመቃወም መጡ ? የኢትዮጵያዊው ሀጂ አበሻ ትምህርትስ ለምን ሙስሊሙን ህብረተሰብ ይሄን ያህል ሊያሸብረው ቻለ ?? ቻሌንጅ ያለበት ነገር ሁሉ ወይ እውነት አለበት ወይ የለየለት ውሸት ነው :: ለዚህ ነው .. በሚገባኝ መነገድ ለኔ ሙስሊም ላልሆንኩት ወንድምህ የሀጂ አበሻ ( ሀባሺ ) ትምህርት አትኩሮቱ ምንድነው ምን ላይ ነው ያልኩህ ..!! አንተ ከላይ እንደጠቀስከው ቡዙ ገፍተህ ልትሄድበት አልፈለክም :: ለምን ?
በርግጥ እምነትን በማስገደድ ሰዎች እንዲቀበሉት ማድረግ የማፊያና የወንጀለኖች ስራ ነው :: ግን ቁራን ቀርጾ ካስተማረና አንዱን ሙስሊም ካሳመነው ( የሀጂ ሀባሺ ) ተከታይ ካደረገው ችግሩ ያለው ትራዲየሽናል የሆነው የሙስሊም እምነት ላይ እንጂ የሀጂ አባሺ አስተምሮት ላይ ዐይመስለኝም :: እንዲህ አይነት ችግር በኛ በክርስትናው እምነት ውስጥ አለ :: የኦርቶዶክስ እምነት ቡዙ የጉዲፈቻ ልጆች አሏት :: በዙዎቻችን ከልጅነታችን ጀመረን በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ አድገን በተለያየ ምክንያት እናት ቤታችንን እየጣለን እንሄዳለን :: ቡዙ ጊዜ ማግኘት የሚገባን ባለማግኘታችን ሊሆን ይችላል ...ወይም ማየት ያለብንን ቅድስና ቤቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ አለማየታየችንም ይሆናል :.. ወይም የማናውቀውንም ነገር ስላወቅንም ይሆናል :: ወይም ይሄ ጥቅስ ማለት እኮ ሲፈታ እንደዚህ ማለት ሊሆን ይችላል በሚል እንደ ማግኔት ተስበን ይሆናል :: ለዚህ መፍትሄው ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ አባቶችና መሪዎች ናቸው :: መንጋቸውን እንዴት መጠበቅ እነደሚችሉ ካላወቁና ቅዱስ ቃሉን ለትውልዱ እንደሚገባ ካላስተላለፉ ብቻ በቂ አይደለም ካልኖሩበት ...ባዶ ቤተ መቅደስ ሊታቀፉ ይችላሉ :: በስልምናውም ቢሆን ሴም ሲትዩሽን ነው :: አል ሀባሺን ባስተምሮት በቅድስና በፍቅር መመከት ይቻላል :: በጩህእትና በሰላማዊ ሰልፍ የምትከላከለው አይመስለኝም :: እነዚህ ሁለት ሰዎች ከመካከለኛው ምስራቅ ድረስ እንዲመጡ የተደረገው ምን ስለሆኑ ነው ?? ቁራን ካገራችን ኢማሞች በላይ ስለሚያውቁ ነው ....አዲስ መገለጸ አግኝተው ነው ..? ወይስ የሰሞኑን ጅራፍ በደንብ ለማጮህ ነው ..?? ቡዙ ሊያወያይን ይችላል :: እስኪ መጣሁ ::

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2  Next
Page 1 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia