WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 45, 46, 47 ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon May 28, 2012 1:36 am    Post subject: Reply with quote

ሞፊቲ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ተድልሽ = የሄንግሎውን ሁጤት በጉጉት እየጠበኩ ነበር ::ኢማነ መርጊያ በዚህ ውድድር ባመጣው ሁጤት
ለሎንዶን ኦሎምፒክ የማይመረጥ ቢሆን እጅግ ሊገርመኝ ይችላል ::በዚሁ አንጻርም የታሪኩ በቀለ 1 ሆኖ መጨረስ ቢያስደንቀኝም በሱ ልጅ ላይ ለምን እንደሆን ባላውቅም ሙሉ እምነት ኖሮኝ አያውቅም ::ስለሺ ስህንም በሩጫው አለም የመቆየቱን ያህል በሎንዶን ኦሎምፒክ ለተተኪዎች ለቀቅ ቢያደርግ መልካም ይመስለኛል ::ይህን ስል ለስለሺ ያለኝ ክብር ፍጹም ስይቀንስ ጭምር ነው ::

የቀነኒሳ ብቃት እንደቀድሞው ያለመሆኑ ምክንያት ዘግይቶ ወደ ውድድር የመግባቱ ሁነታ ቢሆንም ኦሎምፒክ ቢመረጥ አንድ ጥሩ ነገር ይሰራል የሚል እምነት አለኝ ::
ምናልባት በቀሪው ግዜ እራሱን አሻሽሎ የመመረጫ ካርዱን ይጨብጥ ይሆናል ::

በማራቶን በቂ ሀይል ያለን እንደሆነ ቢያሳምንም ካሉት ተፎካካሪ ሀገሮች አንጻር ትልቅ ትግል ይጠብቀናል ::
ባጠቃላይ ለዘንድሮው ኦሎምፒክ ሄሮዎች ስለሌሉን በሙሉ ልብ ሁጤታችን አጣጋቢ ይሆናል ለማለት የሚከብድ ይመስላል ::

ቸር እንሰንብት !!!

ሰላም ሞፊቲ :-

ዘንድሮ 10,000 ሜትር ውድድር ማን ኢትዮጵያን እንደሚወክል ይህን ያህል ያወዛገበው አለነገር አይደለም :: በመደበኛ ውድድሮች ከተገኙ ውጤቶች አንፃር ካየነው ኢማኒ መርጋ ዓመቱን ሙሉ ባይሆንም በአመዛኙ በጥሩ አቋም ላይ ይገኝ ነበር :: ነገር ግን ኢትዮጵያውያን 10,000 ሜትር ሯጮ ከሞላ ጎደል በሙሉ በተሣተፉበት ውድድር ያገኘው ውጤት 9 ደረጃ ነው :: ስለዚህ እርሱ ለሎንዶኑ ውድድር ይመረጣል የሚል ግምት የለኝም :: እኔን የሚያሣሥበኝ የቀነኒሣ በዚህ ውድድር ያለመሣተፍ ነው :: ባለፈው ሆላንዳዊው ማናጀሩ ጆስ ሔርመንስ 'የዓመቱ ጥሩ ሰዓት ስላለው እርሱ በቀጥታ ይመረጥ ' ብሎ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሥልጣኖች ጋር ድርድር እንዳደረገ እናስታውሣለን :: የዚያ ድርድር የመጨረሻ ድምዳሜ ምን እንደሆነ አናውቅም :: በወቅታዊ ብቃት ከተባለ በሔንግሎው ውድድር 1 - 3 የወጡት ይመረጡና 4 የወጣው ገብረእግዚአብሔር በተጠባባቂነት ይያዛል :: ስለዚህ ገና ብዙ ውዝግብ ይኖራል የሚል ፍራቻ አለኝ :: ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆነው የፌዴሬሽኑ ውሽልሽል አሠራር ነው :: እስኪ ይህንን የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ተመልከተው :-
ምንጭ :- ደረጀ ደገፋው : ሪፖርተር ጋዜጣ : እሑድ ግንቦት 19 ቀን 2004 ..:: ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በሔንግሎ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ::
Quote:
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ዛሬ በሔንግሎ ከሚሮጡት አትሌቶች የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ አራት አትሌቶች ተመርጠው ለለንደን ኦሊምፒክ ዝግጅት እንዲጀምሩ ይደረጋል፡፡ ቅዳሜ በአሜሪካ ዩጂን ከሚሮጡት ሴቶችም በተመሳሳይ እንደሚመረጡ፣ ነገር ግን እስከ ሰኔ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ በሔንግሎና ዩጂን ያልተሳካላቸው አትሌቶች ቀነኒሳን ጨምሮ ውድድሮችን ካገኙና የተሻለ ወቅታዊ ሚኒማ ማምጣት ከቻሉ ከኦሊምፒክ ቡድኑ የሚካተቱበት ዕድል እንዳለም ተነግሯል፡፡

...

ይሁንና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኩል ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው፣ አመራር አትሌቱ እስከ ሰኔ መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ የተሻለ ወቅታዊ ሰዓት የሚያመጣበት ውድድር ማግኘት ከቻለ ችግር እንደሌለው፣ ሆኖም ግን ሚኒማ ያላቸው አትሌቶች የተሻለ ሰዓት እንዲያመጡ እንዲሮጡ ተደርጐ እሱ ካለወቅታዊ ሰዓትና ብቃት የአምናው ሰዓቱ ብቻ ግምት ውስጥ ገብቶ ወደ ለንደን ሊያመራ እንደማይችል ስማቸውን ሳይገልጹ በተለይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ስለ ማራቶን እኔ የተሻለ እጠብቃለሁ :: ምክንያቱም አሁን ያሉን ሯጮች ብዙ ጉልበት አልጨረሱም : ኬንያውያን ደግሞ ጆፍሬይ ሙታይን ያህል ጠንካራ የማራቶን ሯጭ አያሠልፉም :: ስለዚህ የእኛ አሠልጣኞች የተለመደውን ጉልበት የሚያስጨርስ ልምምድ እያሠሩ ካላደከሟቸው በስተቀረ በማራቶን ዘንድሮ የተሻለ ተስፋ ይኖረናል ብዬ እገምታለሁ ::

800 ሜትር ሩጫስ ? መሐመድ አማን ዛሬም ራባት (ሞሮኮ ) ላይ አሸንፏል :: በጥሩ ሞራል ላይ ስለሚገኝ በጥሩ ጤንነት ላይ ከቆየ ወርቅ እንኳን ባይሆን የብር ሜዳሊያ ለማጥለቅ ተስፋ አለው ብዬ እጠብቃለሁ ::

መልካም ሣምንት ይሁንልን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue May 29, 2012 7:45 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ሰኞ ግንቦት 20 ቀን 2004 ..:- በየዓመቱ በቦልደር (ኮሎራዶ ግዛት : አሜሪካ ) በሚደረገው 10 .. የጎዳና ላይ የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በሴቶች ምድብ ማሚቱ ደስቃ ውድድሩን 33 ደቂቃ 6.5 ሴኮንድ በማጠናቀቅ አሸንፋለች :: ማሚቱ አምና 2 ሆና ተመሣሣዩን ውድድር አጠናቅቃ ነበር : ከዚያ በፊት በነበሩት 2 ዓመታት በተከታታይ አሸናፊ ነበረች :: ስለዚህ 4 ዓመት ውድድር 3ቱን በማሸነፍ የሥፍራው ንግሥት ሆናለች :: በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያውያኑ ታደሰ ቶላ እና ብርሃኑ ገደፋ በኬንያዊው አላን ኪፕሮኖ ተቀድመው 2ኛና 3 ሆነው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል ::

ምንጭ :- Brian Howell, Boulder Daily Camera, Posted: 05/28/2012 07:02:06 PM MDT (Updated: 05/28/2012 09:32:04 PM MDT). 2012 bolder boulder: Ethiopia's Mamitu Daska dashes ahead of Bolder Boulder women's field once again.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu May 31, 2012 9:28 pm    Post subject: Reply with quote

ሐሙስ ግንቦት 23 ቀን 2004 ..

የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር : ሦሥተኛ ዙር ውድድሮች : ሮም (ጣሊያን )::

ዛሬ መሠረት ደፋር 5,000 ሜትር ሩጫ የዓለም የወቅቱ ሻምፒዮና የሆነችውን ኬንያዊት ቪቪየን ኬፕኬሞይ ቼርዮት ለማሸነፍ ያደረገችው ትግል ቀላል አልነበረም :: በመጨረሻዎቹ 100 ሜትሮች ፍጥነቷን ይበልጥ ጨምራ ብትፋለምም ፍፃሜው ላይ በሴኮንዶች ሽርፍራፊ በቪቪየን ተቀድማለች (ቪቪዬን 15 ደቂቃ 34.62 ሴኮንድ እንዲሁም መሠረት 15 ደቂቃ 34.65 ሴኮንድ ጨርሠዋል )::
ምንጭ :- የሴቶች 5000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
2 ..... መሠረት ደፋር _____ 14 ደቂቃ 35.65 ሴኮንድ
4 ..... ገለቴ ቡርቃ ________ 14 ደቂቃ 41.43 ሴኮንድ
7 ..... ገነት ያለው ________ 14 ደቂቃ 48.43 ሴኮንድ (በግሏ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት )
8 ..... አዝመራ ገብሩ ______ 14 ደቂቃ 58.23 ሴኮንድ (በግሏ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት )
9 ..... ዋጋነሽ መካሻ _______ 15 ደቂቃ 7.35 ሴኮንድ (በግሏ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት )

በሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት ሩጫ አበባ አረጋዊ በአስደናቂ አጨራረስ በርቀቱ የዓለምን የወቅቱን ፈጣን ሰዓት : የዓመቱን የአልማዝ ደረጃ ውድድርን ፈጣን ሰዓት እንዲሁም የኢትዮጵያን ሬኮርድ በሙሉ ሠባብራለች :: ታስታውሱ እንደሆነ የዛሬ 12 ቀን በሻንጋይ ተደርጎ በነበረው 2ኛው ዙር የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር ገንዘቤ ዲባባ በርቀቱ የኢትዮጵያን እና የውድድሩን ሬኮርድ ሠብራ ነበር :: ዛሬ ገንዘቤ ሬኮርዶቹን እና አሸናፊነቱን ለአበባ አረጋዊ አስረክባታለቸ :: ስለዚህ ከሯጮቻችን ወቅታዊ አቋም በመነሣት በሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ እንጠብቅ ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes
ምንጭ :- የሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::
1 ..... አበባ አረጋዊ _______ 3 ደቂቃ 56.54 ሴኮንድ (የዓመቱ የዓለም ፈጣን ሰዓት : የውድድሩ ሬኮርድ : የኢትዮጵያ ሬኮርድ )
3 ..... ገንዘቤ ዲባባ _______ 4 ደቂቃ 0.85 ሴኮንድ

ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአጭርና መካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ላይ ያለችው ፋንቱ ሚጌሶ ማኔሦ ዛሬ ሌላዋ ባለአሸብራቂ ድል ባለቤት ሆናለች :: ከሁለት ሣምንት በፊት ግንቦት 6 ቀን በሴቶች 800 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር በውድድሩ መክፈቻ ሥፍራ በዶሃ (ቃጣር ) በተደረገው ውድድር ያስመዘገበችውን አዲስ የኢትዮጵያ ሬኮርድ በድጋሚ ሠብራለች :: ዛሬ የገባችበትም ሰዓት : 1 ደቂቃ 57.56 ሴኮንድ ሲሆን የዓለም የቤት ውስጥ ሬኮርድ 1 ደቂቃ 53.28 ሴኮንድ ነው (በቼክ ሪፓብሊክ ዜጋ በጃርሚላ ክራቶችቪቮላ ... በጁላይ 26 ቀን 1983 .. 29 ዓመታት በፊት የተመዘገበ ነው ::) :: ፋንቱ በዚህ ጠንካራ አቋሟ ከቀጠለች በሎንዶን ኦሎምፒክ ብቻ ሣይሆን በተከታታይ ዓመታት በመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች ብዙ አስደናቂ ድሎችን ማስመዝገብ የምትችል አትሌት ናት ::
ምንጭ :- የሴቶች 800 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::

ዘንድሮ 10,000 ሜትር ይልቅ በመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች የተሻለ ውጤት በመመዝገብ ላይ ይገኛል : በሎንዶን ኦሎምፒክም ይደገም ይሆን Question Question Question

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Thu May 31, 2012 10:09 pm    Post subject: Reply with quote

የተከበርክ ልጅ ተድላ እንደምን አለህልኝ
እኔ ደህና ነኝ
መቸም ብዙ ነገር የማገኘው ካንተ ነው እዚሁ ላይ ብውልም መች መች እንደሚካህእድ ስለማላውቅ አላነብም ::
ባውቅም ይቋንቋም ጉዳይ አለ ያንተን ሪፖርት ነው ጠብቄ የማየው ::
የቀነኒሳ ነገር ዘንድሮ ምኑም አላማረም በአለም ኦሎምፒክ ሎንዶን ላይ ተስፋ የማረግበት ነገር ስለቸገረኝ ነው ::
በፊት እንደውም ከበፊት ጀምሮ ከናበበ ግዜ ጀምሮ ማሞንም ምሩጽንም ስንሸኝ ወርቅ እንደሚመጣ ሙሉ ተስፋ ይዘን ነው ::
ኃይሌንና ደራርቱንም እንደዛው ሁዋላ ላይ እስተ ቀነኒሳ ድረስ በውነት ተስፋ ጠፍቶብን አያውቅም :
ውነት እልሀለው ልጅ ተድላ እንደዘንድሮ ፈርቸም አላቅ ::
ግምጋሜያችሁን ጥሩ እከታተል ነበር አልተመቻችሁም ::
የሆነው ሆኖ አዳዲሶቹ ኬንያን ታግለው ካመለጡ ሰርፕራይዝ መጠበቅ ነው ::
አክባሪህ ኮሎኔል
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu May 31, 2012 10:55 pm    Post subject: Reply with quote

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
የተከበርክ ልጅ ተድላ እንደምን አለህልኝ
እኔ ደህና ነኝ

እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ :: ደህና መሆንዎን መስማት ጥሩ ነው :: ሙሉ ጤንነትዎን ያድልዎት ::

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
መቸም ብዙ ነገር የማገኘው ካንተ ነው እዚሁ ላይ ብውልም መች መች እንደሚካህእድ ስለማላውቅ አላነብም ::
ባውቅም ይቋንቋም ጉዳይ አለ ያንተን ሪፖርት ነው ጠብቄ የማየው ::
የቀነኒሳ ነገር ዘንድሮ ምኑም አላማረም በአለም ኦሎምፒክ ሎንዶን ላይ ተስፋ የማረግበት ነገር ስለቸገረኝ ነው ::
በፊት እንደውም ከበፊት ጀምሮ ከናበበ ግዜ ጀምሮ ማሞንም ምሩጽንም ስንሸኝ ወርቅ እንደሚመጣ ሙሉ ተስፋ ይዘን ነው ::
ኃይሌንና ደራርቱንም እንደዛው ሁዋላ ላይ እስተ ቀነኒሳ ድረስ በውነት ተስፋ ጠፍቶብን አያውቅም :
ውነት እልሀለው ልጅ ተድላ እንደዘንድሮ ፈርቸም አላቅ ::
ግምጋሜያችሁን ጥሩ እከታተል ነበር አልተመቻችሁም ::
የሆነው ሆኖ አዳዲሶቹ ኬንያን ታግለው ካመለጡ ሰርፕራይዝ መጠበቅ ነው ::
አክባሪህ ኮሎኔል

ቀነኒሣን ካለፈው የቤጂንግ ኦሎምፒክ ጀምሮ ፌዴሬሽኑም : ፖለቲከኞችም አጉል እየለከፉት : በዚያ ላይ በጉዳት ለረዥም ጊዜ ከውድድር እየራቀ ዘንድሮ በተስፋ የምንጠብቀው ሣይሆን በሥጋት "ውድድሩን ይሣተፍ ይሆን " እንድንል ሆነናል :: እግዚአብሔር ይጠብቀው እንጂ ለውድድሩ ከቀረበ እንኳን አያሣፍረንም : ምንጊዜም የአንበሣ ልብ ያለው ልጅ ነው :: ደግሞም ኬንያውያን የእኛን ሯጮች በወሣኝ ውድድሮች ላይ ሲያገኙ ልባቸው በፍርሃት ስለሚሸበር 10,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ማሸነፉንስ እናሸንፋለን :: አሁንም ቢሆን ግን ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያልጠራ ነገር ስላለ እርሱን እንፍራ ::

በተረፈ ከእነ ራስ ብሩ እና ሞፊቲ ጋር የጀመረነውን ውይይት እንቀጥላለን :: እርስዎም አንዳንዴ ብቅ ሲሉ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት እንቅስቃሴ ስለነበሩት ጉዳዮች ኃሣብዎን ያካፍሉን ::

ቸር እንሠንብት ::

አክባሪዎ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Fri Jun 01, 2012 6:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

Quote:
ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአጭርና መካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች አበረታች ውጤት በማስመዝገብ ላይ ያለችው ፋንቱ ሚጌሶ ማኔሦ ዛሬ ሌላዋ ባለአሸብራቂ ድል ባለቤት ሆናለች :: ከሁለት ሣምንት በፊት ግንቦት 6 ቀን በሴቶች 800 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር በውድድሩ መክፈቻ ሥፍራ በዶሃ (ቃጣር ) በተደረገው ውድድር ያስመዘገበችውን አዲስ የኢትዮጵያ ሬኮርድ በድጋሚ ሠብራለች :: ዛሬ የገባችበትም ሰዓት : 1 ደቂቃ 57.56 ሴኮንድ ሲሆን የዓለም የቤት ውስጥ ሬኮርድ 1 ደቂቃ 53.28 ሴኮንድ ነው (በቼክ ሪፓብሊክ ዜጋ በጃርሚላ ክራቶችቪቮላ . . . በጁላይ 26 ቀን 1983 . . 29 ዓመታት በፊት የተመዘገበ ነው :Smile :: ፋንቱ በዚህ ጠንካራ አቋሟ ከቀጠለች በሎንዶን ኦሎምፒክ ብቻ ሣይሆን በተከታታይ ዓመታት በመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች ብዙ አስደናቂ ድሎችን ማስመዝገብ የምትችል አትሌት ናት ::
ምንጭ :- የሴቶች 800 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::

ዘንድሮ 10,000 ሜትር ይልቅ በመካከለኛ ርቀት የሩጫ ውድድሮች የተሻለ ውጤት በመመዝገብ ላይ ይገኛል : በሎንዶን ኦሎምፒክም ይደገም ይሆን

ተድልሽና ኮሎኔል ሰላም ብያለሁ ::

ባለፈው እንደገለጽኩት የሎንዶኑን ኦሎምፒክ ስጋት ውስጥ እንደገባ ያደረገኝን ምክንያት ኮሎኔልም መጋራታቸውን
ስመለከት የጋራ ሀሳብ እንዳለን እረዳለሁ ::የሁለታችንም ስጋት እንደቀደሞው ሁሉ ወንዶቹንም ሴቶቹንም የሚወክል
""ሄሮ "" የሌለን በመሆኑ ነው ::

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ቢሮ 10 ሺንና የመሳሰሉትን የትራክ ውድድሮች ከምድረገጽ ለማጥፋት በመሯሯጥ
ላይ መሆኑና የዚህ ውድድር እየጠፋ መምጣት በልጆቻችን ላይ ከፍተኛ ተጽኖ እንዳሳደረ አይካድም ::
ዘንድሮ (2012) በአለማችን ላይ የተደረጉት 10ሺህ ውድድሮች የሄንግሎውን ጨምሮ ሁለት ብቻ ነበሩ ብል
ይህ እንደማስረጃ እንደሚቆጠርልኝ እርግጥ ነው ::
ውድድሮች እንደቀድሞው ካልተካሄዱ ደግሞ በዚህ መስክ ብቃት ያላቸውን ልጆች ማየትና ማግኘት ከባድ ይሆናል ::
በመሆኑም ያለው አማራጭ ወደ አጭር ሩጫ የመምጣት ዝንባሌን ማሳየት ነው ::
ይህም በመሆኑ እነ ፋንቱ 800 እያሳዩት ያሉት ብቃት ይህን መንገድ አጥብቆ መያዝን ግድ እንደሚል ያመለክታል ::

አለም አቀፉ አትሌኢክስ ቢሮ እንደሚለው ከሆነ 10 ሺህ ሜትር ሁሌም የኬንያና ኢትዮጵያ አትሌቶች
መፎካከራቸው ብቻ ሳይሆን 27 ደቂቃ በስታድየም ውስጥ ሆኖ ዙሩን ማየትትም አሰልቺ ነው የሚል ሁለተኛ ምክንያትም ይሰጣል ::
እነ ሁሴን ቦልት (100) በተመልካች ዘንድ የመወደዳቸውና ስቴድይሙ ጢም ብሎ የመታየቱ ዋናው ምክንያት
ውድድሩ በሴከንድ ስለሚያልቅና ተጀመረ ተብሎ አለቀ የሚለው ነገር ስለሚያጓጓም ጭምር ነው ይላሉ ::
ይህም በመሆኑ እንደዚህ አይነት ፈጣን ውድድር ባለበት ያንን ሁሉ ዙር ቁጭ ብሎ የሚመለከት ተመልካች መጥፋቱ
አንድም ውድድሩን ኬንያንስና ኢትዮጵያውያን መቆጣተራቸውና እነሱን ብቻ ማየት ከገቢም ከተመልካችም አንጻር
ከግምት መግባቱና የዙሩ አሰልቺነትም ጭምር ነው የሚል ነው ::
በሆመኑም እንግዲህ የትራክ ውድድር በቅርቡ ከምድረገጽ እንዲጠፋ የሚወሰን ሲሆን ይህንንም በማገናዘብ ሀገራችንም
እንደነፋንቱ በአጭርና በመሳሰሉት መስኮች ልጆችዋን ማፍራት ይጠበቅበታል ::
በነገራችን ላይ 10 ሺህ ውድድር በዚህ አመት ባለመኖሩ ሀገራችን ልጆችዋን ለመምረጥ ስለተቸገረች
ወደ ሄንግሎ የላከችው 16 አትሌቶችን ነበር ::

እንግዲህ ተድላ እንዳለው ሁሉ ፌዴሬሽናችን ወፈፍ ካላደረገው በስተቀር በአሁኑ ሰአት ብርቅዬውን ልጃችንን
ቀነኒሳን መተናኮስ የሚጠበቅበት አይሆንም ::እሱ በውድድሩ የመካተቱ ተገቢነት ከሞራልም አንበስነትንም አንጻር እርግጥ መሆን አለበት ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jun 01, 2012 10:51 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሞፊቲ :-

እንዴት ነህ ? እባክህ ያንን ልጅ (ጎሣን ማለቴ ነው ) በምታውቀው ዘዴ አባብለህ የጀመረውን እንዲጨርስልን አድርግልን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes
*****************************************

የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበሮች ፌዴሬሽን የሚታዘዘው በሐብታሞች ስለሆነ እንኳን 10,000 ሜትር ሩጫን ይቅርና 'የማራቶን ውድድር ይቅር ' ቢባሉ ታሪካዊውን ውድድር ከመሠረዝ አይመለሱም :: በተቃራኒው ደግሞ የሚከተሉትን ሁኔታዎች እናስተውላለን :-
    @ ..... በታላላቅ የስፖርት ፉክክሮች 25 ዓይነት የውኃ ዋና ውድድሮች ይደረጋሉ :: ውኃ ዋና ጥሩ የስፖርት ዓይነት ነው :: ነገር ግን ይህንን ያህል የተለያዩ የውኃ ዋና የውድድር ዓይነቶች ያስፈልጋሉ ?

    @ ..... ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የትራያትሎን (ውውሀ ዋና : ቢስኪሌትና ማራቶን ) ውድድርን በሥፋት ለማስተዋወቅ ሲጥሩ ይታያል :: ይህ የስፖርት ዓይነት የሰውን ልጅ የተፈጥሮ ጥንካሬ እጅግ የሚፈታተን ሥለሆነ ውድድሩን ሊጨርሱ የሚችሉት ተወዳዳሪዎች ጥቂቶች ብቻ ናቸው :: ያንን ለማካካስ አትሌቶች ጥንካሬ -ሠጪ ንጥረ -ነገሮችን ለመጠቀም ይገደዳሉ :: ነገር ግን ይህንን ስፖርት በሥፋት የሚሣተፉበት ነጮቹ ስለሆኑ አሸናፊዎችም እነርሱ ብቻ ናችው ::
እኒህ እንዲያው ለናሙና ያነሣኋቸው ናቸው :: ሆኖም ነጮች በጥቁሮች የሚበለጡባቸውን ወይም ዜጎቻቸው ሊያሸንፉ ያልቻሉባቸውን የስፖርት ዓይነቶች በሙሉ ትኩረት እንዳያገኙ ቢያደርጉ መደነቅ የለብንም ::

በተቃራኒው ደግሞ 10,000 ሜትር የትራክ ውድድር በመቀዝቀዙ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት እና የማራቶን ሯጮች ያልታሠበ በረከት ወርዶላቸዋል :: ለንፅፅር ያህል 10 ወይም 20 ዓመታት በፊት ምን ያህል የማራቶን ሯጮች ነበሩን ? በቅርብ ጊዜያት ግን ለመምረጥ እስኪከብድ ድረስ ብዙ የማራቶን ሯጮች አግኝተናል :: ስለዚህ እነርሱ (የዓለም የአትሌቲክስ ማኅበሮች ፌዴረሽን ) የውድድር ዓይነቶችን ሲያሸጋሽጉ ኢትዮጵያውያን ሯጮችም ከሁኔታው ጋር የተሻለ ውጤት ወደሚያስመዘግቡበት ውድድር መግባቱ ያዋጣቸዋል ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Jun 03, 2012 12:28 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ በት ይሁን ::

http://www.zehabesha.com/?p=7320

ኮሎኔል ይቺን ሊንክ ነካ ያድርጉት ::ደስታዎትን እንደሚያቋድሱኝ ተስፋ አደርጋለሁ ::
ትንሽዋ የአንበሳ ግልገል እርሶ ላሳሰቦት ኦሎምፒክ የመሳተፏን ነገር አረጋግጣለች ::

ቸር እንሰንብት !!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jun 03, 2012 3:20 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሞፊቲ :-

ዛሬ ልብህ ትንሽ ተረጋጋ አይደል Smile አናብስቱ ካሉ ሌላውም አዲስ ሯጭ ይበረታታል :: ጥሩነሽ እንደምታሸነፍ ጥርጣሬውም አልነበረኝም :: ነገር ግን ሌሎቹ 10,000 ሜትር ሯጮች የት ገቡ ? ስንታየሁ እጅጉ : መሠለች መልካሙ : ውዴ አያሌው : ... አሁንም ቢሆን በዚህ ርቀት ጥሩነሽን ሊያግዟት የሚችሉ በቂ አትሌቶች ያሉ አይመስለኝም ::

በሌላ በኩል ደግሞ ቀነኒሣ በተደጋጋሚ 5,000 ሜትር ሩጫ እየተካፈለ ጉልበቱን ለምን እንደሚጨርስ ግልፅ ሊሆንልኝ አልቻለም Rolling Eyes ይኼ ደግሞ ለሞራሉም ጥሩ አይደለም : መቅደም እንጂ መቀደም : ማሸነፍ እንጂ መሸነፍ ያልለመደ ሥነ -ልቡና ያለው አትሌት በተደጋጋሚ 3 ደረጃ በታች ሲገባ ጥሩ አይደለም :: ለመሆኑ የውድድር መርኃግብሩን የሚያቀናጁለት ሰዎች ይህ ጠፍቷቸው ነው ? አልገባኝም Confused Confused Confused

መልካም የሣምንት መጨረሻ ይሁንላችሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jun 07, 2012 10:00 pm    Post subject: Reply with quote

ሐሙስ ግንቦት 30 ቀን 2004 ..

አምሥተኛው ዙር የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር (ኦስሎ : ኖርዌይ )::

በዛሬው ዕለት በተደረጉት ውድድሮች በወንዶች 5,000 ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያን በሎንዶን ኦሎምፒክ እነማን እንደሚወክሉ ፍንጭ ታይቷል :: በሴቶች ምድብ ደግሞ ሶፊያ አሰፋና ሕይወት አያሌው 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ እንዲሁም አበባ አረጋዊና ገንዘቤ ዲባባ 1,500 ሜትር ሩጫ በጥሩ አቋም ላይ እንደቀጠሉ ባስመዘገቧቸው ውጤቶች አስመስክረዋል :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመስላሉ ::

የወንዶች ምድብ

የወንዶች 5,000 ሜትር ርቀት ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::[/b]
1 ..... ደጀን ገብረመስቀል _____ 12 ደቂቃ 58.92 ሴኮንድ
2 ..... ሀጎስ ገብረሕይወት _____ 12 ደቂቃ 58.99 ሴኮንድ (በግሉ ጥሩ ሰዓት )
3 ..... ኢማኒ መርጋ __________ 12 ደቂቃ 59.77 ሴኮንድ
4 ..... ታሪኩ በቀለ ___________ 13 ደቂቃ 0.41 ሴኮንድ
5 ..... ቀነኒሣ በቀለ ___________ 13 ደቂቃ 0.54 ሴኮንድ (ለዓመቱ በግሉ ፈጣን ሰዓት )
7 ..... ስለሺ ሥህን ___________ 13 ደቂቃ 1.39 ሴኮንድ
8 ..... ይግረም ደመላሽ _________ 13 ደቂቃ 3.30 ሴኮንድ
9 ..... የኔው አላምረው _________ 13 ደቂቃ 8.12 ሴኮንድ
10 ... ይታያል አጥናፉ ዘሪሁን ____ 13 ደቂቃ 8.13 ሴኮንድ (ለግሉ ጥሩ ሰዓት )
12 ... አበራ ኩማ ______________13 ደቂቃ 9.32 ሴኮንድ

የወንዶች 1 ማይል ርቀት የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
3 ..... መኮንን ገብረመድህን _____ 3 ደቂቃ 50.02 ሴኮንድ (ለዓመቱ የግሉ ጥሩ ሰዓት )
9 ..... አማን ወቴ ____________ 3 ደቂቃ 53.02 ሴኮንድ (ለግሉ በርቀቱ ጥሩ ሰዓት )

የሴቶች ምድብ

የሴቶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

2 ..... ሶፊያ አሰፋ _______ 9 ደቂቃ 9.00 ሴኮንድ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬኮርድ )
3 ..... ሕይወት አያሌው ___ 9 ደቂቃ 9.61 ሴኮንድ (በግሏ ለርቀቱ ጥሩ ሰዓት )
8 ..... ብርቱካን አዳሙ ____ 9 ደቂቃ 36.40 ሴኮንድ (ለዓመቱ በግሏ ጥሩ ሰዓት )
10 ... መቅደስ በቀለ ______ 9 ደቂቃ 39.09 ሴኮንድ

የሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
1 ..... አበባ አረጋዊ _____ 4 ደቂቃ 2.42 ሴኮንድ
2 ..... ገንዘቤ ዲባባ _____ 4 ደቂቃ 03.28 ሴኮንድ

*************************************************

በአጭር ቀናት ልዩነት (ግንቦት 23 ቀን በሮም (ጣሊያን ) ግንቦት 25 ቀን : በኢውጂን (ኦሬገን ግዛት : አሜሪካ ) እና ዛሬ ግንቦት 30 ቀን በኦስሎ (ኖርዌይ )) በተደረጉት ውድድሮች በሎንዶን ኦሎምፒክ ምን ዓይነት ውጤት መጠበቅ እንደሚኖርብን አንዳንድ ጠቋሚ ውጤቶች እየታዩ ነው ::

# ..... በወንዶች 5,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር አስተማማኝ የሆነ ተወዳዳሪ የለንም :: በዚህ ርቀት የእንግሊዙ ፋራህ እና ኬንያውያን በተሻለ አቋም ላይ ይገኛሉ :: ምናልባትም በኦሎምፒክ ከነሐስ ግፋ ቢል ከብር ሜዳሊያ የዘለለ ውጤት መጠበቅ አንችልም :: ቀነኒሣ በተደጋጋሚ ያስመዘገባቸው ውጤቶች በርቀቱ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችለው አቋም ላይ እንደማይገኝ ያሣያሉ (ዘንድሮ በርቀቱ ያስመዘገበው ፈጣን ሰዓት 13 ደቂቃ 0.54 ሴኮንድ ሲሆን ... 2004 በሔንግሎ (ሆላንድ ) ያስመዘገበውና በራሱ የተያዘው የዓለም ሬኮርድ 12 ደቂቃ 37.35 ሴኮንድ ነው )::

# ..... በሴቶች 1,500 ሜትር አበባ አረጋዊ እና ገንዘቤ ዲባባ በርቀቱ በዓለም ካሉት የሴት ሯጮች በአሁኑ ሰዓት በተሻለ አቋም ላይ ይገኛሉ :: ስለዚህ በዚህ ርቀት ከወርቅና ከብር ሜዳሊያዎች ቢያንስ አንዱን አናጣም ::

# ..... በሴቶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ሶፊያ አሰፋ በተደጋጋሚ በኬንያውያን እየተቀደመች 2 ብትወጣም ዛሬ በኦስሎ በተደረገው ውድድር 3 ደቂቃ 9 ሴኮንድ በመግባት የራሷን ሬኮርድ አሻሽላ የኢትዮጵያን ሬኮርድም ሠብራለች :: ከእርሷ ሌላ ሕይወት አያሌው በከፍተኛ ሁኔታ ውጤቷን በማሻሻል 9 ደቂቃ 9.61 ሴኮንድ መግባት ችላለች :: መቅደስ በቀለና ብርቱካን አዳሙ ለሎንዶን ኦሎምፒክ የሚያስፈልጋቸውን የሰዓት ሚኒማ የሚያሟሉ ከሆነ በርቀቱ ቢያንስ : ቢያንስ የነሐስ ሜዳሊያ አናጣም ::

በሌሎች ርቀቶች ገና ያልለየለት ስለሆነ የቀሪ ውድድሮችን ውጤቶች በመገምገም እመለስበታለሁ ::

ቸር እንሠንብት ::

አክባሪያችሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Sat Jun 09, 2012 2:46 pm    Post subject: Reply with quote

እንደምን አላችሁ ? እኔ ደህና ነኝ
አስተያየቶቻችሁ ትክክለኛ ናቸው ሞፍቲ እርግጥ ነው በኛ አገር ብቻ ሳይሆን በብዙ የአፍሪካ አገሮች ወደ አጭር ርቀት የማንዘንበል ሁኔታ ይታያል :
መጀመሪያ ካአሰልጣኞች ነው የሚጀመረው እነሱ ቶሎ ከፍ ማለት እንችላለን ብለው ባጭር ርቀት ላይ እየሰሩ ነው ::
አትሌቱንም እንደየት ቶሎ ከፍ ማለት እንዲቻል በደንብ ይሰብኩታል እውነትም አለበት ስለዚህ የኛንም አገር ጨምሮ ጧት ማታ እየሰሩ ነው ::
በዚህ ረገድ የተያዘው አካሄድ ጥሩ ቢሆንም እንደባህል የምናቀው ረጅም ትንፋሽ ስለሆነ ችላ ማለታቸው መጥፎ ነው ::
እንደሚመስለኝ በግሌ ማንም አሰልጣኝ ይሁን መሪ ኪሱ ይሙላንጂ ኢትዮጵያ ሰምደቅአላማ የሚለው ነገር ምናቸውም አይደል ::
ይሄ ስለቀረ ነው እንጂ ስፖርተኛ ሊጠፋ አይችልም ::
ዜናውን አይቼ ረካሁ ጥሩነሽ ዲባባ መሰለፍዋ አስደሳች ነው ኦሎምፒክ ላይ ደሞ ሰአት ሳይሆን ልምድ የበለጠ ነው ::
አደራ የኦሎምፒክ ዜና ነገር ካለ አካፍሉኝ
ልጅ ተድላ የቀነኒሳ ነገር አሁንም ድረስ ልቤ አልቆረጠም ምን እንደሚደረግ እግዜር ይወቅ :
ከዛሬ ጀምሮ ደሞ የኢሮፕ ሻምፒዮና እንያያለን ስፔን ምን ታመጣ ይሆን ዘንድሮ ::
ጀርመን ሆላንድ እንግሊዝ ፈረንሳዪ ግሩም ጨዋታ ያሳዩናል በጣም የምደሰትበት ነው ::
አክባሪያችሁ ኮሎኔል
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jun 09, 2012 10:17 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኮሎኔል :-

የሎንዶን ኦሎምፒክ እስኪጀመር ድረስ (July, 27 - August, 12, 2012) በሌሎች ሥፍራዎች ብዙ የአትሌቲክስ ውድድሮች ይኖራሉ :: ስለዚህ በመጪዎቹ 48 ቀናት ገና ብዙ የአትሌቲክስ ወሬዎች እንኮመኩማለን ::

በዘንድሮው የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ላይ የዘረኝነት ችግር ገና ከመክፈቻው ዕለት ጀምሮ መጥፎ ጥላውን አጥልቶበታል :: ትላንት በቴዎድሮስ ገብረሥላሤ ላይ ጥቂት ዘረኛ የሩሲያ ደጋፊዎች 'የዝንጀሮ ዓይነት ጩኸት ' እያሠሙ ሲሣለቁበት ውለዋል :: ውድድሩ ግን ከአጀማመሩ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበት ሆኗል ::

በተረፈ የዛሬ እና የነገ የአትሌቲክስ ውድድሮች ስላሉ ጎራ እያሉ ውጤቶቹን ይከታተሉ ::

ለእርስዎና ለቤተሰብዎ መልካም የሣምንት መጨረሻ ይሁንላችሁ ::

አክባሪዎ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jun 09, 2012 11:17 pm    Post subject: Reply with quote

ቅዳሜ ሰኔ 2 ቀን 2004 ..

ስድስተኛው ዙር የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር (ኒውዮርክ : አሜሪካ )::

በዛሬው ዕለት በተደረገው ውድድር ኢትዮጵያውያት ሯጮች በሁለት የውድድር ዓይነቶች ተወዳድረው ነበር :- በሴቶች 800 እና 5,000 ሜትሮች ርቀቶች የሩጫ ውድድሮች :: በሁለቱም ውድድሮች ተሣታፊ የነበሩት ሯጮቻችን ያስመዘገቧቸው ውጤቶች አስደናቂዎች ነበሩ ::

በሴቶች 800 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያን በብቸኝነት የወከለችው ፋንቱ ሚጌሦ ነበረች :- ዛሬም በድጋሚ በርቀቱ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሬኮርድ ሠብራለች : ውድድሩንም 1 ደቂቃ 57.48 ሴኮንድ በመግባት በአሸናፊነት አጠናቃለች (ምንጭ :- IAAF, Adidas Grand Prix, New York, Sat June 9, 2012. Women 800 Meters Results.)::

5,000 ሜትር ርቀት በተደረገው የሩጫ ውድድር የመጨረሻዎቹን 400 ሜትሮች የተፎካከሩት ጥሩነሽ ዲባባ እና መሠረት ደፋር ነበሩ :: ዛሬም በድጋሚ ጥሩነሽ መሠረትን ቀድማት አሸንፋለች :: ስለዚህ ከሞላ ጎደል በሴቶች 5,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉት ሯጮች ተለይተው የታወቁ ይመስላል :: ዘንድሮ (... 2012) ባስመዘገቡት ሰዓት መሠረት ያላቸው ደረጃ የሚከተለውን ይመስላል ::

ምንጮች :-
1 ..... IAAF, Women 5,000 M Records for 2012 ((Updated as at:07/06/2012).

2 ..... IAAF, Adidas Grand Prix New York City, NY (USA) - Saturday, Jun 09, 2012. Women 5,000 M Results.

አጠቃላይ ደረጃ _ሰዓት (ደቂቃ : ሴኮንድ ) _____ ስም __________ የውድድር ሥፍራ __ቀን (...)___በውድድሩ ያገኘችው ደረጃ

1 ........................... 14:35.65 ______ መሠረት ደፋር ________ ሮም (ጣሊያን ) ____ 31/05/2012 _______ 2

2 ........................... 14:41.43 ______ ገለቴ ቡርቃ ________ ሮም (ጣሊያን ) _______ 31/05/2012 ______ 4

3 ............................ 14:48.43 ______ ገነት ያለው ________ ሮም (ጣሊያን ) ______ 31/05/2012 ______ 7

4 .......................... 14:50.80 _______ ጥሩነሽ ዲባባ _______ ኒው ዮርክ (አሜሪካ ) __ 09/06/2012 ______ 1

5 ........................... 14:58.23 _______ አዝመራ ገብሩ ________ ሮም (ጣሊያን ) ____ 31/05/2012 _______ 8

6 ........................... 15:01.20 _______ አፈራ ጎደፋይ ________ ራባት (ሞሮኮ ) ____ 27/05/2012 _______ 4

7 .......................... 15:04.65 _______ ወርቅነሽ ኪዳኔ _______ ኒው ዮርክ (አሜሪካ ) _ 09/06/2012 ______ 4

8 ........................... 15:07.35 _______ ዋጋነሽ መካሻ ________ ሮም (ጣሊያን ) ______ 31/05/2012 ______ 9

9 .......................... 15:11.53 _______ ቡዙዬ ድሪባ ___ ሞንትሩዪል --ቡዋ (ፈረንሣይ ) _ 05/06/2012 ______ 1

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jun 23, 2012 7:46 pm    Post subject: Reply with quote

ቅዳሜ ሰኔ 16 ቀን 2004 ..

ቀነኒሣ አንበሣ በበርሚንግሃም አገሣ ::

ዛሬ በርሚንግሃም (እንግሊዝ ) ውስጥ 10,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ተደርጎ ነበር :: አንበሣው ቀነኒሣ ዘንድሮ በርቀቱ ከተመዘገቡት ሰዓቶች 3ኛውን ፈጣኑን ሰዓት በማስመዝገብና የሥፍራውን ሬኮርድ በመሥበር (27 ደቂቃ 2.59 ሴኮንድ ) ዳግም አይበገሬነቱን አስመሥክሯል :: በዚህም መሠረት በሎንዶን ኦሎምፒክ 10,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉት ሯጮች ከሞላ ጎደል ታውቀዋል :: ቀነኒሣን ተከትለው ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ 2 (27 ደቂቃ 3.24 ሴኮንድ ) እና ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም 3 (27 ደቂቃ 3.58 ሴኮንድ ) ሆነዋል ::

ምንጭ :- Matthew Brown (for the IAAF), Saturday, June 23, 2012. Bekele breaks all-comers record at UK Trials, Day 1.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jun 24, 2012 12:44 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ነገ እሑድ ሰኔ 17/2004 .. በሕትመት መልክ የሚሠራጨው ሪፖርተር ጋዜጣ የሚከተለውን አስገራሚ ዜና ይዞ ቀርቧል ::

ምንጭ :- ደረጀ ጠገናው : ሪፖርተር ጋዜጣ : እሑድ ሰኔ 17 ቀን 2004 .. :: ኢማና መርጊያ ከትናንቱ ውድድር ለምን ተሰረዘ ?

Quote:
- በጉዳዩ የአወዳዳሪዎች እጅ እንዳለበት የሚናገሩ አሉ

በየአራት ዓመቱ የሚከናወነው ኦሊምፒክ ዘንድሮ 30 ጊዜ በእንግሊዝ ለንደን ሊከናወን ቀናት ቀርተውታል፡፡

ኢትዮጵያ ከሜልቦርኑ 16ኛው ኦሊምፒያድ ጀምሮ በተከናወኑ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከሦስቱ በቀር ስትሳተፍ ቆይታለች፡፡ በመጪው ክረምት ለሚከናወነው ለንደን 2012 ኦሊምፒክ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች ትገኛለች፡፡

ይሁንና አገሪቱ በመድረኩ ለረዥም ዓመታት ውጤታማ በመሆን የምትታወቅበት 10 እና አምስት ሺሕ ሜትሮች ውድድሮች በዓለም ላይ በበቂ ሁኔታ እየተዘጋጅ አለመሆኑን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት 10ሺሕ ሜትር አገሪቱን በኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መቸገሩ ይነገራል፡፡

ፌዴሬሽኑ፣ አትሌቶች ወቅታዊ ብቃታቸውን እየገመገሙ በሚያስመዘግቡት ሰዓት መሠረት የሚፈለጉትን ለመለየት የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀም መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከነዚህ አማራጮች፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በሆላንድ ሄንግሎ ያዘጋጀው ውድድር ይጠቀሳል፡፡ በወቅቱ የተወዳደሩ አትሌቶች ያስመዘገቡት ሰዓት በርቀቱ በለንደን ኦሊምፒክ ይወዳደራሉ ተብሎ ከሚጠበቁት ተወዳዳሪዎች አንፃር በቂ ባለመሆኑ እንደገና ትናንትና በእንግሊዝ በርሚንግሃም ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ በርካታ ተስፋ የተጣለባቸው አትሌቶች በውድድሩ እንዲሳተፉ ቅድመ ዝግጅቶች ተሟልተው ከተጠናቀቁ በኋላ፣ በተለይም በለንደን ኦሊምፒክ 10 ሺሕ ሜትር ሜዳሊያ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል ኢማና መርጊያ ሁሉንም ዝግጅት አጠናቅቆ ወደ ውድድሩ ቦታ ለመጓዝ ሰዓታት ብቻ ሲቀሩት ከውድድሩ የመሰረዙ ዜና መሰማቱ ታውቋል፡፡ ይህም ፌዴሬሽኑን ያሳዘነ ከመሆኑም በላይ ኢማናና ሌሊሳ እንዳይሳተፉ የተደረገበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የፌዴሬሽን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

ፌዴሬሽኑ፣ ኢማና መርጊያና ሌሊሳ ዲሳሳ በትናንቱ ውድድር ቢሳተፉ ኖሮ 10 ሺሕ ሜትር የመጨረሻዎቹን አትሌቶች ለመምረጥ አቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን በተፈጠረው ችግር የተነሣ በርቀቱ የመጨረሻ ተሰላፊዎችን ለመለየት እንደገና ተጨማሪ አማራጭ ለማየት እንደሚገደድ ተናግሯል፡፡

በጉዳዩ ሁለቱን አትሌቶች ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም፣ ነገር ግን አንዳንድ በውጪ አገር አወዳዳሪ ከሆኑ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ ድርጅቶቹ በሚያዘጋጁት ውድድር እነሱ የሚመርጡት አትሌት ካልሆነ ሌሎችን ለማሳተፍ እንደማይገደዱ፣ ይህም የተለመደ አሠራር እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ሄንግሎ ላይ በተደረገው 10 ሺሕ ሜትር ውድድር የውድድሩ አዘጋጅ ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ የሌሎች ታላላቅ አትሌቶች ማናጀር ጆን ሄርመንስ ቀነኒሳ በውድድሩ መሳተፍ እንደሌለበት፣ ነገር ግን የማናጀሩ ማሳሰቢያ ውድቅ ተደርጐ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የግድ ቀነኒሳ መወዳደር አለበት የሚል ከሆነ ግን ውድድሩን ለመሰረዝ እንደሚገደድ ማሰጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የአፍሪቃ የአዋቂዎች የአትሌቲክስ ፉክክር (ሰኔ 20 - 24/2004 ..) : ፖርቶ -ኖቮ (ቤኒን ) >>> African Senior Championships - African Championships (27/06/2012 - 01/07/2012), Porto Novo (Benin)

Quote:
ከሰኔ 20 እስከ 24 ቀን 2004 .. ድረስ በቤኒን ከተኑ 18 ጊዜ በሚከናወነው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ይፋ ሆኑ፡፡ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ኮሙኒኬሽን ክፍል የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የአፍሪካ ከዋክብት አትሌቶች በሚሳተፉበት የኮተኑ ሻምፒዮና፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ የውድድር ዓይነቶች 55 አዳዲስ አትሌቶች ትሳተፋለች፡፡

ውድድሩ 10 ሺሕ ሜትር ጀምሮ ውርወራና ዝላይን የሚያካትት ሲሆን፣
10 ሺሕ ሜትር ሴቶች :- መሪማ መሐመድ፣ ምሕረት ደርቤና አፈራ ጐደፋይ፣
ወንዶች :- ጠበሉ ዘውዴ፣ ሰለሞን ደክሲሳና ገብረፃዲቅ አብርሃ ሲሆኑ፣

በአምስት ሺሕ ሴቶች :- ጎይተቶም ገብረሥላሴ፣ ሽቶ ወዴሳና ዓለሚቱ ሃሮዬ፤
ወንዶች :- ይታየል አጥናፉ፣ ቶሎሳ ገደፉና ጥሩነህ ቢረሳው ናቸው፡፡

3 ሺሕ ሜትር መሰናክል ሴቶች :- ብርቱካን አዳሙ፣ መቅደስ በቀለና ለምለም በርሄ፣
በወንዶች :- ናሆም መስፍን ሐብታሙ ጃለታና ታፈሰ ሰቦቃ ሲሆኑ፣

1 ሺሕ 500 ሜትር ሴቶች :- ፋይኔ ጐደቶ፣ ጌጤ ዲማና ዓለም ገረዝሔር ሲሆኑ፣
በወንዶች :- አብዮት አብነት ዘነበ አለማየሁና ዳንኤል ግደይ ናቸው፡፡

800 ሜትር ሴቶች :- ማንጠግቦሽ መለስ፣ ዓለም ገረዝሔርና ሶፍያ ሸምሱ ሲሆኑ፣
በወንዶች :- እስራኤል አወቀ ሽፈራው ውሌና ማሙሽ ሌንጫ፣

እንዲሁም
400 ሜትር ሴቶች :- ሰላም አብርሃላይ ትዕግስት አሰፋና ማህሌት ሙሉጌታ፣
ወንዶች :- ሃጐስ ታደሰ፣ ጐንፋ በቀለና በረከት ደስታ ናቸው፡፡

200 ሜትር ሴቶች :- ፈትያ ከድርና ትዕግስት ታማኙ ሲሆኑ፣
ወንዶች :- አብዮት ሌንጮ ወጠረ ገለልቻና ሊንጐ ኡባንግ፣

እንዲሁም
100 ሜትር :- ሴቶች ፈትያ ከድርና ትዕግስት ታማኙ ናቸው፡፡
ወንዶች :- አብዮት ሌንጮ፣ ወጠረ ገለልቻና አለባቸው ደርሶ፣

እንዲሁም
400 ሜትር መሰናክል ሴቶች :- ወሰኔ በላይ በብቸኝነት ስትሳተፍ፣

20 ኪሎ ሜትር ዕርምጃ ሴቶች :- አስካለ ቲክሳ አይናለም እሸቱና አዳነሽ መንግሥቱ ሲሆኑ፣
ወንዶች :- ቸርነት ሚቆሮ ሐብታሙ ጃለታና ታፈሰ ሰቦቃ ናቸው፡፡

በዲስከስ ውርወራ ሴቶች :- መሰረት ገብረእግዚአብሔርና
ወንዶች :- ምትኩ ጥላሁን በብቸኘት ይሳተፋሉ፡፡

እንዲሁም
በጦር ውርወራ ሴቶች :- መብራት ገብረሚካኤል
ወንዶች :- ሳንጃ ሰንኤ እና ምትኩ ጥላሁን ሲሆኑ፣

በርዝመት ዝላይ ወንዶች :- ሊንጐ ኡባንግ ናቸው፡፡

እንዲሁም
4X400 ሜትር ዱላ ቅብብል ሴቶችና ወንዶች በአጠቃላይ 10 አትሌቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 45, 46, 47 ... 53, 54, 55  Next
Page 46 of 55

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia