WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እሁድ ጧቱ ድምጽ አረፈ !!

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Edit

አዲስ

Joined: 05 Jan 2008
Posts: 14

PostPosted: Sun May 27, 2012 2:52 pm    Post subject: እሁድ ጧቱ ድምጽ አረፈ !! Reply with quote

ዜና እንደሙዚቃ ይደመጣል ማለት
ታደሰ ተረኛ ሆኖ የገባ ለት

በንጉሴ አክሊሉ

የቀድሞው የእሁድ ጧት ሬድዮ አዘጋጅ ታደሰ ሙሉነህ አረፈ .... ለአድናቂዎቹ እና ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጣቸው ::

[/i]

Last edited by Edit on Mon Jun 11, 2012 3:23 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5049

PostPosted: Mon May 28, 2012 5:20 am    Post subject: Reply with quote

ነፍስ ይማር ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1631

PostPosted: Fri Jun 01, 2012 8:28 pm    Post subject: Re: ዜና እረፍት ! Reply with quote

ሪሊ በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው ::
ታደሰ ሙሉነህ በጣም ከማደንቃቸው ጋዜጠኞች መሀከል ዋነኛው ነበር ::
ፈጣሪ ነፍሱን ከፃድቃናት ጎን ያኑራት :: ቤተሰብ : ወዳጅና ዘመድንም መፅናናትን ይስጥ ::

ሀዲስEdit እንደጻፈ(ች)ው:
የቀድሞው የእሁድ ጧት ሬድዮ አዘጋጅ ታደሰ ሙሉነህ አረፈ .... ለአድናቂዎቹ እና ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጣቸው ::

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Jun 04, 2012 8:01 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ :-

በእውነቱ የሚያሳዝን ዜና ነው ::ታደሰ ሙሉነህ ታሞ ሆስፒታል እያለ VOA የሰጠውን ቃለ ምልልስ ሰምቼ ነበር ::እነ በበኩሌ ታደሰን የማውቀው በእሁድ ፕሮግራምና በእርሶም ይሞክሩት ነው ::ድምፁ በጣም የሚማርክ ጋዜጠኛ እንደነበር የሰማችሁት መመስከር ትችላላችሁ ::እስኪ 'በኢትዮጵያ ሥነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኃን ሽልማት ድርጅት ' የሚዘጋጀውን 1994 'የረጅም ዘመን ተሸላሚ ' በሆነበት ወቅት ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ከአንድ መፅሔት ላይ ስላገኘሁት ላካፍላችሁ ::

ታደሰ ሙሉነህ 1945 . አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋስዮን ሰፈር ተወለደ ::ታደሰ ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው በተፈሪ መኮንን (የአሁኑ እንጦጦ አጠቃላይ ) ትምህርት ቤት ነበር ::ከዚያም የቀ ..(አሁን አአዩ ) ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ትምህርቱን አቋርጦ አብዛኛውን ዕድሜውን ወዳሳለፈበት የጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማራ ::ታደሰ እንዴት ወደዚህ ሙያ እንዳዘነበለ ሲናገር :-

''አጋጣሚ ነው ::1959 .. አንደኛ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ ::የዩኒቨርሲቲውን ባህል ማዕከል አዘወትር የነበር ሲሆን እንዲያውም የመጀመርያውን Scholar Ship(25 ብር ) ከወጋየሁ ንጋቱ ጋር ያገኘሁት እኔ ነበርኩ ::ይህን ገንዘብና ጉርምስናን ስታስበው ምን ያህል ዋጋ እንደነበረው ልብ በል ::ያኔ እነ ወጋየሁ ንጋቱ (ነፍሱን ይማረውና ) ደበበ እሸቱ ኃይሌ ገሪማ አባተ መኩርያ ነበሩ ::ብዙ የሚያዝናና ነገር ያጋጥምሃል ::በወቅቱ የማዕከሉ ዳይሬክተር ተስፋዬ ገሠሠ ነበር ::ተስፋዬ ከዚህ ኃላፊነቱ በተጨማሪ የሬዲዮ የኪነ ጥበባት ፕሮግራም ስለሚሠራ አንድ ቀን አንድ ጽሑፍ አስነበበኝ ::በሚቀጥለው ቀን ራሴን የሬዲዮ ጋዜጠኛ ሆኜ አገኘሁት ::አድማጭ ተነጋገረብኝ ::ባለ ሥልጣኖቹ በእግር በፈረስ ፈለጉኝ ::አገኙኝም ::ቢሯቸው ስሄድ ይረሱኛል አያስገቡኝም ::ስጠፋባቸው ፈልገው ይመጣሉ ::በኋላ ዜና አንባቢነት እንድንለማመድ ተወሰነ ::ስቱዲዮ የምገባ የእለቱ እለት ማታ ተረኛው ዜና አንባቢ የደረሰበት ጠፋ ::በወቅቱ ኃላፊ የነበሩት አቶ መኮንን አየለ ተሸብረው ምድር ቁና ሆነችባቸው ::አማራጭ ስላልነበረ ዜናው ለእኔ ተሰጠኝ ::አቶ መኮንን ከመጨነቃቸው ብዛት ስቱዲዮ ውስጥ አብረውኝ ገቡ ::እንደ ደንቡ ከሆነ በስቱዲዮ ውስጥ ጋዜጠኛው ብቻውን መሆን ነበረበት ::ከምሰማው ብዙ ተምሬያለሁና ረጋ ብዬ 'እንደምን አመሻችሁ ?ዜና እናሰማለን !' ብዬ ማንበቤን ተያያዝኩት ::በጥሩ ሁኔታ አጠናቀቅኩ ::በመጨረሻም 'ዜናው እዚህ ላይ አበቃ ደህና አምሹ ' ብዬ አድማጭን ተሰናበትኩ ::ሙዚቃው ሲሰማና አቶ መኮንን ዘለው ሲጠመጠሙብኝ አንድ ሆነ ::

የእኛ senior የነበሩት አሳምነው ገብረወልድና ሰለሞን በቀለ በነጋታው ሲገናኙ የእኔ ጉዳይ የአፍ ማሟሻቸው ሆነ ::በአካል ተገናኝተን ተዋወቅን ::'አህያ በወለደች አረፈች ' አለኝ ሰለሞን ::እነሆ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህይወቴን በሙሉ ከምወደው ሙያ ጋር የተዋወቅኩት በእንዲህ ያለ መልኩ ነበር ::በዚያን የወጣትነት ዕድሜ ዕድለኛ ስለነበርኩ ከላይ የጠቀስኳቸውን ጨምሮ እነ በዐሉ ግርማ ገዳሙ አብርሃ ጳውሎስ ኞኞና ሌሎችም ጋዜጠኞች የገሃዱ ዓለም መምህሮቼ ነበሩ ::'

Arrow ታደሰ 1959-1985 በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰራ ሲሆን ለሙያ ማሻሻያም ወደተለያዩ አገሮች (በአጠቃላይ 16 አገሮች ) በመሄድ ሥልጠና ወስዷል ::ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተሰናበተም በኋላ በሞሃ ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ የህዝብ ግንኙነት በአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምክር ቤት የፕሮግራም አስተባባሪ እንዲሁም የተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በማማከር ሰርቷል ::

Arrow1974 .. ከሙያ አጋሩ ከነበረችው ከወይዘሪት ማርታ አማረ ጋር ትዳር መስርቶ አንድ ሴት ልጅ ወልደዋል ::

ይቀጥል ይሆናል !
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
የብዙሐኑ ሐሳብ

አዲስ

Joined: 14 Jan 2008
Posts: 16

PostPosted: Thu Jun 07, 2012 2:47 pm    Post subject: Reply with quote

በጣም የሚያሳዝን ዜና ነፍሱን ይማራት !!

ልክ ነው ብዙ ሊዘነጉን የማይችሉ ሰዎች አልፈዋል ግን ህልፈታቸው ትተውልን ባለፉት ጥበብ ደግነት እውቀት ምንጊዜም ስንዘክራቸው እንኖራለን :: አቶ ታደሰ ሙሉነህ በተለይ በቀድሞው የእሁድ ጧት የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጂት በሚያቀርባቸው ምርጥ ፕሮግራሞች የማንረሳው ሰው ነበር በዚህ አጋጣሚ የስራ ባልደረቦቹ ንጉሴ አክሊሉ እና አዲሱ አበበም ሁሌ አብረው ይታወሱናል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Edit

አዲስ

Joined: 05 Jan 2008
Posts: 14

PostPosted: Mon Jun 11, 2012 3:07 pm    Post subject: Reply with quote

7:20 ደቂቃ በኋላ አዳምጡ

http://www.voanews.com/wm/voa/africa/amha/amha1800a.asx
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia