WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ሌዮኔል ሜሲ የሁልግዜውም ምርጥ እግርኳስ ተጫዋች

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቲኪ _ታካ

አዲስ

Joined: 05 Jun 2012
Posts: 17

PostPosted: Sun Jun 10, 2012 2:14 am    Post subject: ሌዮኔል ሜሲ የሁልግዜውም ምርጥ እግርኳስ ተጫዋች Reply with quote

በዛሬው እለት አርጀንቲና እና ብራዚል በኒውጀርሲ መታላይፍ ስቴድየም ያደረጉት ጨዋታ እጅግ አዝናኝና በርካታ ጎሎች የተቆጠሩበት ከመሆኑን በላይ ታላቁ ሜሲ ሀትሪክ አስቆጥሮ አረንቲናም 4-3 እንድታሸንፍ ረድቷታል :: እሱን በተመለከተ የፉትቦል ህጎች ሞዲፋይ ካልተደረጉ በስተቀር ሜሲን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አይቻልም :: ለምሳሌ እሱ የሚጫወትበትን የሚገጥም ቲም 15 ተጭዋች እንዲሰለፍ ወይንም ደሞ ከፔናሊቲ ሳጥን ውስጥ የሚያስቆጥራቸውን ጎሎች አለመቁጠር የመሳሰሉት ህጎችን ዲዛይን ካልተደረገ በቀር ይህን ሰው ሌሎችን ከማዋረድና በየአመቱ 70 በላይ ጎሎች ከማግባት የሚያግደው አይኖርም :: የምናውቀው እግርኳስ ለዚህ ድንቅ ልጅ በጣም ቀሎታል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jun 10, 2012 10:16 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ቲኪ _ታካ :-

በእርግጥም ሊዮኔል ሜሢ ተዓምረኛ ተጫዋች ነው :: በአሁኑ ወቅት እርሱን የሚልቅ የእግር ኳስ አጥቂ ተጫዋች አለ ለማለት አይደፈርም :: የትላንቱ የብራዚልና የአርጀንቲና ጨዋታ ቅንጫቢ ይኼው :-

ምንጭ :- Posted by ongrojinho, Sun June 10, 2012. Brazil v Argentina.

በነገራችን ላይ .. 1994 ወዲህ የብራዚል ቡድን የሚጫወተው እንደ ቀድሞው የምዕራብ ጀርመን ቡድን እንጂ ድሮ እንደሚወደድላቸው ዓይነት ውበት ያለው እግር ኳስ መጫወት ትተዋል ::

ሜሤ በአጥቂነት ችሎታው ብቻ ሣይሆን ዱላ የሚችልና እንደሌሎች አጭበርባሪ አጥቂዎች (የፖርቱጋሉ ሮናልዶ ) ሣይጎዳ በመውደቅ ዳኞችን ለማታለል የማይሞክር በመሆኑ ጭምር ይታወቃል ::

ምንጭ :- LeoMessiFootball, Published on May 19, 2012. Lionel Messi never dives (Ultimate Compilation).

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቲኪ _ታካ

አዲስ

Joined: 05 Jun 2012
Posts: 17

PostPosted: Mon Jun 11, 2012 12:43 am    Post subject: Reply with quote

ሄሎ ተድላ :: አመሰግናለሁ ስለሊንክና ገለጻህ :: ስለ ሜሲ ነገር ምን ያልተባለ አለ ? አሁን አሁን የልጁን ችሎታ ለምደን ከርሱ የሚጠበቅ አርገን ስለወሰድነው በየጨዋታው የሚያረጋቸው ነገሮችን ችላ እንላለን እንጂ ብዙ ተአምሮችን ነው እየሰራ ያለው :; እኔም በበኩሌ እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ የሆነ ነገር ተአምራዊ ክስተት ፈጥሮ የሚወጣ ተጭዋች ከሜሲ ውጭ አይቼም ለወደፊቱም የማይ አይመስለኝም :;ሜሲ ችሎታው ወረደ የሚባልለት ለሁለትና ሲስት ጨዋታ ጎል ካላገባ ነው :: ይህ ምን ያህል ስታንዳርዱ ከፍተኛ የሆነ ሰው እንደሆነ ያስገነዝበናል :: ጎሎቹ ባብላጫው ተራ ተጭዋች እንኳን ሊያገባቸው ሊያልማቸውም የሚከብዱት አይነት ናቸው :: በዛ ላይ እኔን ደሞ የሚገርመኝ ልጁ አይጎዳም ወይም ተጎድቶ ሲንፈራፈር አታየውም :: ደክሞትም አይቀየርም :: በጣም ነው የሚያስደምመው :: እንግዲህ እስኪያረጅ ድረስ ችሎታውን መኮምኮም ነው ::

ስለብራዚል ያልከውም ትክክል ነው :: ብራዚሎች በስም ብቻ የቀረ ቡድን ናቸው :: አሁን ራሱ አውሮፓ ዋንጫ ላይ ጣልያን ሆላንድ ራሽያ እና ስፔን ከብራዚል መቶ ግዜ የሚሻል ማራኪ አጨዋወት አላቸው ::ሁሉም ሰው ግን ብራዚል ብራዚል ይላል :: በእርግጥ ኢንዲቪጅዋል ችሎታ ያላቸው ጨዋታን ባንዴ መለወጥ የሚችሉ ሀይለኛ ተጫዋቾች አላቸው :: በቡድን አጨዋወት ግን ይህን ያህል ናቸው :: በኔ እድሜ ራሱ ብራዚል ሲደነቅ እንጂ በጨዋታው ከሌሎች በልጦ አንጀቴን አርሶኝ ያውቁም :: በድሮ በረ እያረሱ ይመስላል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Tue Jun 12, 2012 5:15 am    Post subject: Reply with quote

ጨዋታውን ላይቭ እንዳየሁት ሜሲ ያሳየው እንቅስቃሴ ተሚያምር ነው ግን ብራዚል ያሰለፈ የኦሎንፒክ ቲሙን እንጂ ዋናውን አይደለም አርጀቲና ያላትን በአጠቃላይ ለቃቅማ ነው የገባችው ብራዚል ግን ወሳኝ የሆኑ ፍልዶችና ተከላካዮች አልገቡም ግን እነዚህ ታዳጊዋች ያሳዩት እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው አገርዋ ላይ ዋንጫው እንደሚቀር ያሳያል ያመላክታል ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Tue Jun 12, 2012 5:33 am    Post subject: Reply with quote

ሜሲ ጥሩ ተጫዋች ነው ግን አሁንም ቢሆን መታየት ያለበት ለአገሩ አንድ ነገር ሲሰራ ነው ማራዶና ስሙን የተከለው እና ሰሙ የሚነሳው ለናፖሊ ባደረገው ነገር ብቻ አይደለም ላገሩ ባደረገው እንጂ ለምሳሌ እነቫንባስተ ጉሌት ፕላቲኒ ያን ያህል ስማቸው ሲጠራ አይሰማም ለምን ላገራቸው የክልላቸውን ዋንጫ እንጂ የአለምን አላገኙም ብራዚልም ቢሆን እነዚኮ ሶቅራስ ፋልካዋ ስማቸው የለም ምንም ላገራቸው ያደረጉት የለም ከሶስቱም 9ሮናልዶ ትልቅ ነገር ላገሩ የሰራ ነው ለጉዳት ባይዳረግና ረጅም ጊዜ ባያርፍ እስካሁን መጫወት የሚችል ከፔሌ የበለጠ ታሪክ የሚሰራ ነው እስከዛሬ ማን ተጫዋች የሱን ያክል በአለም ዋንጫ ያገባ የለም 2002 የአለም ዋንጫ 2 አመትተኩል ኳስ ሳይነካ ትሬሊንግ ብቻ አድርጎ ለብራዚል ተሰልፎ 32 አመት በውሀላ 7 ጨዋታ 8 በማግባት ተአምር የሰራ ተጫዋች ነው ስለዚህ ሜሲም ለአገሩ አንድ ነገር አድርጎ ማሳየት አለበት አለበለዛ እንደነ ባቲ ጎል ሲያቆም አብሮ ስሙ ይቆማል ;;

Last edited by መጽናናት on Tue Jun 12, 2012 6:09 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Tue Jun 12, 2012 5:39 am    Post subject: Reply with quote

የብራዚልና የአርጅንቲና ጨዋታ እስቲ በሀሳብክ ;ዳኔል አልቪስ ;ዲጎ ሲልቫ ; ራማሬዝን አስገባና ካካን ; ሮቢኒኖን ጭምረክ እየው ተአምረኛ ቲም ነው የሚሆነው ; Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Tue Jun 12, 2012 5:58 am    Post subject: Reply with quote

[/img]http://www.youtube.com/watch?v=ww7TENIsWE0&feature=g-logo-xit
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ኤጀርሳ ጎሮ

አዲስ

Joined: 14 Jul 2010
Posts: 16

PostPosted: Tue Jun 12, 2012 8:38 pm    Post subject: Reply with quote

በትክክል መጽናናት አንድ ተጫዋች ለሀገሩ ካልሰራ ስሙ አይገንም ግን ሜሲ ገና ብዙ የሚጫወት ስለሆነ ጊዜ አለው ;; እስቲ እንየው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቲኪ _ታካ

አዲስ

Joined: 05 Jun 2012
Posts: 17

PostPosted: Wed Jun 13, 2012 3:20 am    Post subject: Reply with quote

መጽናናት እንዲሁም ኤጄርሳ ጎሮ ጥሩ ነጥብ ነው ያነሳቹት :; እሱን እኔም ራሴ በፊት እለው የነበረው ነገር ነበር :: ሌዮኔል ሜሲ ግን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከአለም ዋንጫ በባሰ አስቸጋሪ ውድድርና የአለም የምርጦች ምርጥ ተጭዋቾች በያመቱ እየገጠመ ተአምራቶቹን ሳያቋርጥ እያስኮመኮመን ነው ያለው :: ማን ተጭዋች ነው እስኪ ሜሲ በአለፉት 5 ሲዝኖች ብቻ በቻምፒየንስ ሊጉ ያስገኛቸውን ድሎችና እሚገርሙ ታሪክ የማይረሳቸው እንቅስቃሴዎችን ያደረገው ?
ለናሙና ያህል ካቻምና ከአርሰናል ጋር 4 ጎሎችን ያገባበት ጨዋታ , አምና ሪያል ማድሪድን በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ኑካምፕ ላይ ሲያሸንፉ ያገባቸው 2 ጎሎች ዘንድሮ ሪከርድ የሰበረበት ባየርን ሌቨርኩዝን ላይ ያገባቸው 5 ጎሎች ብቻ ማስታወሱ ምን ያህል ዶሚናንት ተጭዋች እንደሆነ ነው የሚያሳየን :: እርግጥ የሚጫወትበት ባርሴሎና ቲም ምርጦች የተሰባሰቡበት ቡድን ነው :: ግን ያለ ሜሲ እንደዚህ ለተጋጣሚ ፍዳ የሚያሳዩ ሊሆኑ እንደማይችሉ ከቼልሲ ጋር እርሙን ጎል መንገዱ ቢጠፋበት ያየነው ነገር ነው :: ሜሲ ፈረንጆች ultimate compitator የሚሉት እልህኛም ተጭዋች ነው :: በቀደም ራሱ ሲናገር እስካሁን ድረስ በቼልሲ ውድድሩ የወጡበት መንገድ እያንገበገበው ንዴቱ እንዳልበረደለት ነው የተናገረው :: ፋውል ሲሰራበት የማይወድቀውና የማያለቃቅሰው ከምንም በላይ ማሸነፍ ከደሙ የተዋሀደና ስፖርቱን ከልቡ መጫወት የሚወድ ታላቅ ፕሮፌሽናል ስለሆነም ነው :: 90 ደቂቃን መጫወት ሁልጊዜ ዲማንድ የሚያረገው ኢጎ ስላለበት ሳይሆን ኳስ መጫወት ብቸኛና ብቸኛው ህይወቱ ስለሆነ ነው :: እሱን ቀምተከው ምን ይውጠዋል ?
አለም ዋንጫ አሁን አሁን ለዛውን እያጣ የመጣ ውድድር ሆንዋል :: ድሮ በነፔሌ ግዜ ተጭዋቾች እንደልብ ከክለብ ክለብ የመዘዋወር ፍቃድ ስላልነበር አራት አመት ጠብቀው ነበር ሀገራት የሚፈታተሹት :: ውድድሩም በዛ ሰበብ በናፍቆት ይጠበቅ ነበር :; አሁን ግን ሜሲና ኔይማር ሲፎካከሩ ለማየት የግድ 4 አመት መጠበቅ የለብንም :: ክለቦች ሚኒ ናሽናል ቲም ሆነው ብሄራዊ ሊጋቸው አልያም በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ ሲገናኙ እንደውም የምርጦችን ምርጥ አካተው ስለሚቀርቡ ፉክክሩም እጅግ የጠነከረ ነው :: ማራዶና ናፖሊን ብቻውን ይዞ ለድል ያበቃው አንድ ክለብ 3 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች መያዝ በማይፈቀድበት ዘመን ነበር :: እርግጥ የማራዶናን ድል ለማሳነስ አይደለም የፈለኩት ግን ያንን ዘመን እና ያሁኑን አመሳክሮ ሜሲ የግድ እንደዛ ይሁን ማለት ስለሚከብድ ነው :: በኔ አመለካከት የሜሲን ኮንሲስተንሲ እና አስደናቂ አፍ የሚያስከፍት ክህሎት በተደጋጋሚ ጨዋታዎችን ዶሚኔት የሚያርግበት ነገሩ አለም ዋንጫን እንኳን ባያገኝ የምንግዜውም ምርጥ ሊያስብለው የሚችልበት ሁኔታ ነው የሚታየኝ :: እንበልና ዴስቴፋኖ , ፔሌ , ፕላቲኒ , ማራዶና , ክራይፍ , ሮናልዶ (ብራዚሉ ), ዚዳን እና ሜሲን በእኩል እድሜያቸው ላይ አምጥተንና when they are on top of their game ማን ልቆ ይታያል ብለክ ታስባለክ ?

ለኔ መልሱ ቀላል ነው :; ሌዮኔል ሜሲ ::

የአለም የሁልግዜውም የምርጦች ምርጥ ለመባል የግድ አለምዋንጫን ማሸነፍ ያለበት አይመስለኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Wed Jun 13, 2012 6:14 am    Post subject: Reply with quote

አባብልክን ለመቀበል እቸገራለው አንተ ድሮ እኔም እንደዛ እል ነበር ያልከው ያንተ ቡድን አርጀንቲና ይመስለኛል ከአለም ዋንጫ ጋር ስለተራራቁ የቆዩ መሰለኝ ስለዚህ ያለምን ዋንጫ ጣል ጣል አደረከው ; Smile Smile ከእግር ኳስ ውድድሮች ሁሉ ከባድ የአለም ዋንጫ ነው ;; አለም ዋንጫ ላይ ጥሩ ሆኖ ክለቡ ላይ ደካማ የሆነ ተጫዋች በብዛት አላየሁም ግን ክለብ ላይ ጎበዝ ሆኖ አለም ዋንጫ ላይ ደካማ ብዙ አለ ;; አሁንም ስለሜሲ የምልህ ነገር ጎበዝ ነው በጣም ግን በምንም አይነት ከሮናልዶ ; ፔሌ ;ማራዶና ;ጋር አላወዳድረውም ምክንያቱ ትልቅ ግዙፍ ነገር ይቀረዋል ;; የአውሮፓን ዋንጫ ውድድሩ ከባድ ቢሆንም ያልተጠበቁ ቲሞች ሲያገኙት ይታያል ;;የአለም ዋንጫ ላይ ግን የለም ለምን የምርጦች ምርጥ የሚገናኙበት ስለሆነ ለምሳሌ ብትወስድ እራሳቸው ተጫዋቾች ለክለባቸው ዋንጫ ሲያገኙ እንባ ሲተናነቃቸው አይቼ አላውቅም ግን ያለም ዋንጫ ላይ የተለየ ነው ያሸነፈም የተሸነፈም ሲያለቅስ እናያለን ምክንያቱ ስምህን ለዘመናት የምታስጠራበት ነው ስለዚህ ሜሲም ይህ ፈተና ይጠብቀዋል ግን ችግሩ ባርሳ ያሉት ተጫዋቾችን አይነት ማግኘት አለበት አርጀንቲና ውስጥ ደግሞ ያሉ አይመስለኝም ስለዚህ እግዚህአብሄር ይርዳው ;; በአሁኑ ሰአት ከነ ፔሌ ; ማራዶና ;ሮናልዶ ጋር አታወዳድረው ምክንያቱም ፔሌ 3 የአለምን አግኝቶ ማራዶና 86 ታሪክ ሰርቶ ሮናልዶ 3 የአለም ዋንጫ ላይ 2 ወርቅ እና 1 ብር መዳሊያ አግኝቶ ያለፉ ናቸው ;;ሜሲስ .......

Last edited by መጽናናት on Wed Jun 13, 2012 9:58 pm; edited 4 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1348
Location: united states

PostPosted: Wed Jun 13, 2012 6:23 am    Post subject: Reply with quote

ለላ የምጠይቅክ የአለም ዋንጫ ቀላል ከሆነ ሜሲ 2010 አለም ዋንጫ ላይ የት ነበር ? ምንም ሳያሳየን የትሄደ ? የክለቡን 25% እንኳን አልተጫወተ ;; የጀርመን ተጫዋች አርጀንቲናን 4-0 ካሸነፉ በውሀላ ያለው ሜሲን ያየሁ ማልያ ስንቀያየር ነው ; Laughing Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia