WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ቤተ - ሞንሟናው
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Jun 15, 2012 12:15 pm    Post subject: Reply with quote

የተውኩትን ነገር
ተመክሬ ተነግሬ በሃገር
ምን ጎትቶ አመጣብኝ
ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር

ጉድ ፈላ ዘንድሬ አቤት አቤት
_ማን አስተማረብኝ
ማስቲካ ሆኛለሁ ከረሜላ
_' አሳደረኝ

ይሄው ይሰማኛል ጥሩምባ
ይሄው ይነፋሉ ጥሩምባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
እረ ጉድ እረ ጉድ ፈላ
እፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ

እዩት ልጁን ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት በዚህ ጉዳይ
ወይ ቁመና ወየው ዛላ
ሰው እንደ 'ህል አይበላ
አለ ለካ የሰው ሃረግ
ደረት ክንዱ ባለ 'ማረግ

እስኪ በጆሮየ ፍቅርን ይድገም ያነብንብልኝ
ከትንፋሹ በልጦ የሚደመጥ
ምን ሙዚቃ አለኝ
በጁ ቢነካካኝ ድምጽ አወጣሁ
እኔም እንደ ጊታር
ጉድ አረገኝ መውደድ
ጉድ አረገኝ የዚህ ሰው ፍቅር

አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ፍቅሬን ላንተ ሰጥቻለሁ
አርገኝ የቤትህ እመቤት

.
.
.
እጂጋየሁ ጂጂ ---> http://www.youtube.com/watch?v=UAuNVxC8Fz0
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Jun 15, 2012 12:47 pm    Post subject: Reply with quote

የሰውን ልጅ የስሜት ላይ መውጣት ታች መውረድ ...መደሰት መከፋትን ...የኩነኔ ህይወትን ...የሰውን ልጅ ግራ አጋቢ ላይ ታች ህይወትን ....በውብ ቃላጼ ታንቆረቁራለች ...ደስታን ፍቅርንም ስጡኝ ስትልም ትለምናለች ....ፈጣሪዋን ትጠይቀዋለች ...ትለምነዋለች ....

እስኪ ከረብሻ ኳኳታ ዘፈን ወጣ በሉና በተረጋጋ መንፈስ ሆናችሁ አዳምጧት

እውነት ጂጂ ድንቅ አይደለችምን ?! Very Happy

http://www.youtube.com/watch?v=7VkrV-iFED4

አባ አለም ለምኔ
አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወጥታ አትገባም
ሳልሰራ ኩነኔ

ሰው ወደድኩ እያልኩ ' እጠላለሁ
' ይከፋኛል እደሰታለሁ
ዛሬ ቀጭን ኩታ ነገ ራቁቴን
አገኘው ስል ወዳጅ ' ማጣትን

አባ አለም ለምኔ
ለምን ለምን ለምን ለምን
አባ አለም ለምኔ
ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት ጤንነት አይሆነኝ

ሰው በአፉ እያነሳ በእጁ ይጥለኛል
የልቡን አላውቅም ግራ ይገባኛል
የልብን ጥያቄ ማን ነው የሚፈታ
ከአንተ በቀር አባት ከአንተ በቀር ጌታ
ዛሬ ጥያቄ አለኝ
ለምን ለምን ለምን
ደግሞ ለምን ይክፋኝ
ብስጭት ጭንቀት
ጤንነት አይሆነኝ

ደስታን ስጠኝ ለህይወቴ
አይሳንህምና አባቴ
አርቅልኝ ክፉውን
እንዳልማር ክፋቱን
በቀኝ አውለህ አሳድረኝ
ክፉ ነገር ሳይወጣኝ

ምን ሊሰራልኝ ጥላቻ ሃሜት
ሀብት አይሆነኝም ቤት አልስራበት
ልብ ያጨልማል ክፉ ነገር
ልቤን አብሩልኝ ስጡኝ ፍቅር

አባ አለም ለምኔ
ጀምበር ወጥታ አትገባም
ሳልሰራ ኩነኔ

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sun Oct 14, 2012 1:34 am    Post subject: Reply with quote

ይሄውላችቹ አንዱ ፌስ ቡክ ላይ ዋርካን ለምን ተውካት ቢያንስ የፍቅር ፎረምን ብሎ በጅንጀና በልመና ብዛት ቃል አስገብቶኝ አሁን ደግሞ እየቀመቀምኩ በምርቃና አመጣኝ Laughing Laughing ...ስጠረጥር የዋርካ አድሚን ሳይሆን አይቀርም Wink Wink ...እሱን ደግሞ መጋፋት ዴግ አደለም ....ደህና ናችሁ ግን ? አቤት እኔ ዋርካን በቃኝ ብዬ ቻው ብዬ ከሄድኩ በኋላ ስንቱ ነገር ግልብጥብጡ ወጣ ...መለስ ሞተ ....አዜብ እሪ አለች ....ሃይለማሪያም መጣ ....ጁነዲን ተባረረ ...አዜብም አልወጣም አለች ...ወዘተ ....እኛም አጨንቁረን እያየን ነው Smile ፖለቲካ ሰፈርስ እንዴት ናችሁ ? ለማንኛውም ፌስ ቡክ ላይ ፖስት የተደረጉ የፍቅር ግጥሞቼን ጄባ ልበላችሁ እስኪ :: እንቢ ለሃገር አለህ ? ሰላምታዬ ይድረሳችሁ የሃገር ልጅ በሞላ ...ወደ ግጥሞቹ ...ድድድድድ

አየሽ የኔ ዓለም
በዙሪያችን ያሉ ወንዶች የተባሉ
አፋቸውን ከፍተው አንችኑ ያያሉ
ያጉተመትማሉ ያንሾካሹካሉ
ጣፋጭ ከንፈርሽን በአይን ይስማሉ
ንጽህት ገላሽን ነክተው ሊያረክሱት
(ድፍረታቸው አያልቅ )
በሻከረ እጃቸው እንንካም ይላሉ

እናም ...ለምለም ቀዘባ ወለላ
ሽፍንፍን በይልኝ በሻሽ በነጠላ
ማንም አይይብኝ አንችን ከእኔ ሌላ
አይተው አያልፉሽም
ማራኪ ነው ገላሽ
ለአይን የሚያስጎመጅ በአይን የሚበላ

ነይልኝ ጠጋ በይ ሽሽግ በይ ከጎኔ
ከሰው ልከልልሽ ልብስ ልሁንሽ እኔ
አንችን እንደደብቅሁ ትፈጸም ዘመኔ

እኔ ብቻ ልይሽ ልያዝሽ ቀርቤ
አንች ጽላት ሆነሽ መቅደስ ትሁን ልቤ
ላሰማሽ ውዳሴ ልጠንሽ በከርቤ

የኔ ማራኪ የዱር ውስጥ እንኮይ
አይተው ከሚያረክሱ ከአይን ተከለይ
እንደ መነኮሳት ከዓለም ተለይ
ልቤ ገዳምሽ ነው ወደ ውስጤ ነይ

የበረሃ ላይ ምንጭ በሩቅ ተፍለቅላቂ
የወርቅ የአልማዝ የዕንቁ ፍልቃቂ
ሰው አንችን አይይሽ ወደ ውስጥ ዝለቂ
ስጋየን ተሻግረሽ ልቤ ውስጥ ጥለቂ
ከልቤ አትውጭብኝ እዚያው ተደበቂ ::

(ፍቅር ...ናፍቆት ...ስስት ...ቅናት ... በደረቁ ሌሊት Sad )

/ልጅ ሞንሟናው /
09-10-12

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/

Last edited by የተሞናሞነው on Sun Oct 14, 2012 2:34 am; edited 3 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sun Oct 14, 2012 1:50 am    Post subject: Reply with quote

ወዳ 'ንች ስመጣ
ከበረሃ ውሎ
በጸሃይዋ በሃሩሩ ግሎ
በውሃ ጥም ተቃጥሎ
_ወደ ምንጭ ለመድረስ
_እንደሚገሰግስ
ጣድፎና ቸኩሎ

ወዳንች ስመጣ
ጨቅላ ልጇን ትታ
ወደ ገበያ ወጥታ
_ጡቷ ወተት ሲያፈስስ
በናፍቆት ደንዝዛ
_እንደምትመለስ
ቅመሟን ሳትገዛ
እንደምትል ጥድ '
_እንደ አንጄተ -ስስ
እንደ 'ናት እንስፍስፍ

ወዳንች ስመጣ
አቤት መንሰፍሰፌ
አቤት መጣደፌ
አቤት ችኮላዬ
አቤቱ ደስታዬ
አቤቱ ፍጥነቴ
አቤቱ ጉልበቴ
..............
(ወዳንች ስመጣ )

/ልጅ ሞንሟናው /
11.10.12

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sun Oct 14, 2012 1:56 am    Post subject: Reply with quote

በሾለችው ብዕሬ
በነጭ ወረቀት ላይ
ሆሄያትን ደርድሬ
ቃላትን ቀምሬ

'እንኮይ ልስልስ ገላ
የአበቦች ቅምም
የኔ ማር ወለላ ...'

እያልኩኝ ላወሳ
ስምሽን ላነሳሳ
ቃል ስጥል ሳነሳ

እነሆ ስጀምር
ብሶት ላንጎራጉር
ፍቅራችን ልዘምር

አልቻልኩም አለሜ
በሆነ በመንፈስ
ወይ በአየር በነፋስ
(ወይም እውነት ይሆን ?)

መአዛሽ አወደኝ
እጆችሽ አቀፉኝ
ከንፈሮችሽ ሳሙኝ

ውስጤ ተላወሰ
እንባዬ ፈሰሰ
ወረቀቴም ራሰ

ቃላት ቀልጠው ጠፉ
በእንባዬ ጎረፉ

ነገሬን ተረድታ
ሁኔታዬን አይታ
ብዕሬም አልቻለች
አብራኝ አለቀሰች
በአይኗ ቀለም ተፍታ

(ሁላችንም ለቅሶ )

/ልጅ ሞንሟናው /

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Mon Oct 22, 2012 12:54 pm    Post subject: Reply with quote

ድሮ ድሮ ድሮ
ንጋት ያበስር ነበር
ከሰው ቀድሞ ዶሮ

አሁን ተለውጦ
ሌሊቱን ሙሉ
እንቅልፉን ለጥጦ

ከነጋ ይጮሃል
ጸሃይን እያዬ
እየተንጎማለለ
በሰፈር በቀዬ ::

/ልጅ ሞንሟናው /

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Oct 24, 2012 8:19 pm    Post subject: Reply with quote

ለመለስ ሞትና ለቅሶ ሰሞን የቋጠርኍቸው የሙሾ ስንኞች Wink

ትናንት ምድር ሆነህ
_ዛሬ በሰማይ
ታስለቅሰኛለህ
_እላለሁ ዋይ ዋይ

_____________________
አደባባይ ብቆም
_ደረቴን ሰጥቼ
ብተክዝ ብቆዝም
_ልማዴን አጥቼ
ይሄው ደበደብኩት
ቤትህ ውስጥ ገብቼ ::

_____________________
ምድረ ነፍጠኛ
እነ ትምክህተኛ
ቦዘኔ አደገኛ
ምድረ ፈሪ ሁሉ
እንኳን ተሳካልህ
ልብ አገኘህ አሉ
ከቤቱ ውስጥ ገባህ
ዛሬ እሱ ሲተኛ ::

______________________
(እምዬ ሚኒሊክ ለመለስ )

በቤልጅግ ነበረ
_ጠላቴን ገርፌ
ታሪክ የተውኩልህ
_በደም ቀለም ጽፌ
አንተ ግን
ቀየህን ናቅህና
አድዋን ተውካትና
ወደ ቤልጅግ ሄደህ
ተሸንፈህ መጣህ
_በትንሿ መርፌ ::

/ልጅ ሞንሟናው /

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1593

PostPosted: Thu Oct 25, 2012 5:54 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሞንሟናው !!!!

እንኳን በሰላም ተመለስክ !!!
እንግዲህ ዋርካዋ ሞቅ ሞቅ ልትል ነው ::

በርታ ወንድሜ

ሀዲስ

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀዲስ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 10 Mar 2010
Posts: 1593

PostPosted: Thu Oct 25, 2012 6:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሞንሟንሽ

እስኪ ይህችን የቆየች ዘፈን ለቤትህ ማሞቂያ አድርጋት ::

http://www.youtube.com/watch?v=ZezWmE7FjgM

ሀዲስ

_________________
what we learn from history is, we do not learn from history.

http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Oct 31, 2012 8:00 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድም ሀዲስ እንደምን አለህልኝ ?

ምላሽ ለመስጠት በመዘግየቴ ይቅርታን አስቀድሜ ለሰላምታህና ለሙዚቃ ግብዣህ ከልብ አመሰግናለሁ ::
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sun Nov 11, 2012 12:38 pm    Post subject: Reply with quote

(ናፍቆት እስክንድር ነጋ እና ጭራቆቹ )

ስለ ጭራቅ ተረት ትምህርት ቤት ሲወራ

ሁሉም ደንግጠው ውስጣቸው ሲፈራ

እሱ አልተሸበረም እንዲያውም ተኩራራ

እንደሚጥልለት አባቱን ተማምኖ

አስፈሪ ጭራቁን ጥሎ በዝረራ

ተረቱ አለቀና

ጭራቁን በውስጡ እያሰላሰለ

ቦርሳ በጀርባ አዝሎ እየተቻኮለ

ከትምህርት ቤት ወጣ ድክ ድክ እያለ

ገና ከሩቅ አየው ጀግና አባቱን ቆሞ

'አባ ' ብሎ ሮጠ ሳመው ተጠምጥሞ

'አባዬ ' ብሎ በኮልታፋ በልጅ አንደበቱ

ይነግረው ጀመረ ለጀግናው አባቱ

የሰማውን ሁሉ ከትምህርት ቤቱ

ስለ አስፈሪው ጭራቅ ሲወራ ተረቱ

ግና ምን ያደርጋል

አይናቸው ደም ለብሶ የሚያጉረጠርጡ

ደምን የሚያፈሱ አካል የሚቆርጡ

ጥማቸው ማይረካ የሰው ደም ካልጠጡ

ወሬውን ሳይጨርስ ጭራቆቹ መጡ

ከእቅፉ መንጭቀው ልጁን ወረወሩ

ልጅ ያቀፉ እጆቹን በካቴና አሰሩ

በማይገባው ቋንቋ እየተናገሩ

ወደ ጭራቆች ቤት ይዘውት በረሩ

ናፍቆት አለቀሰ 'ዋይ አባዬን ' አለ

ተረቱ እውን ሆኖ

ጭራቆቹን እንባ በሞሉ አይኖች

ፈርቶ እያስተዋለ ::

__________________________

'ጭራቆቹ መጥተው አስረው በካቴና

አባየን ወሰዱት ጭነው በመኪና

ከነበርንበቱ ባለፈው ታች አምና '

እያለ ነገራት ለጀግናዋ እናቱ

በኮልታፋው በልጅ አንደበቱ

ካሁኑ ናፍቆት ጀግናው አባቱ

ፍርሃት ይዞት ባዶ ሲሆን ቤቱ

በጭራቆች ስራ በዝቶበት ቁጭቱ

ባትሆንም እንግዳ ለጭራቆች ስራ

ናፍቆቷን ስታየው እንባውን ሲዘራ

ስታስታውስ

ከውልደት ጀምሮ ያየውን መከራ

የእናትነት ልቧ ... አዝና ተሸብራ

ስቅስቅ ብላ አነባች ከናፍቆቷ ጋራ

ግን ናፍቆቷን አቅፋ ከእንባዋ ባህር

ድንገት አየች ጀግና ቆፍጣና ደፋር

የጭራቅን ስራ ለጭራቅ ሲነግር

ብእር እያሳዬ ጭራቅ ሲያሸብር

'አዎ እሱ ነው ' አለች

'ጀግናዬ እስክንድር '!

ጀግናዋን እንዳየች ውስጧ ጠነከረ

ትንሹን ናፍቆትም ትነግረው ጀመረ

'አባትህ ጀግና ነው እውነት ተናጋሪ

ካንተም ከኔም ተርፎ ለሌሎቹ ኗሪ

ያየውን ሳይፈራ ለአለም መስካሪ

ጭራቅን በድፍረት እንደሰው መካሪ

ብእሩ ስለት ሰያፍ ጭራቅ አሸባሪ

እናም ሆድ አይባስህ አይዞህ ልጄ በርታ

ፍርሃትም አይግባህ በጭራቅ ድንፋታ

በሰው ለሚሸነፍ የማታ የማታ ::

________________________
ትንሹ ናፍቆት እስክንድር ነጋ

ስንት ቀን ሆነህ አባብየህን ካየህ

ካጣህው ከሚተኛበት አልጋ ?

ስንት ጊዜስ መሽቶ ስንት ጊዜ ነጋ ?

ስንት ቀንስ በህልምህ አየሀው

ተከቦ በጅቦች መንጋ ?

አይዞህ ናፍቆቴ እስክንድር

በርታ በል ልብህ ትጠንክር

ተማርልን ፊደልን ቁጠር

አንብብ ያባትህን ደብተር

ከትቦልሃል ብዙ ቁም ነገር

ስለ ጦቢያ ስለ እናት ሃገር

ስለ ነጻነት ስለ ሰው ክብር

በመለያየት ስላለ ፍቅር

ፈልግና ርስትህን ያዝ ከደብተሩ

እዚያ ነውና ያባትህ ጋሻና ጦሩ

የተዋጋበት ለናት ሃገሩ

የተገለጸበት ሰብአዊ ፍቅሩ ::

(ለናፍቆት እስክንድር ነጋ መታሰቢያነት ኦክቶበር 2011, የዛሬ አመት በፊት የተከተቡ ስንኞች )

ልጅ ሞንሟናው

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1198
Location: united states

PostPosted: Mon Nov 12, 2012 1:15 am    Post subject: Reply with quote

ስታናድድ
ምናለ ቤት ከፍቻለሁ ኑና እዩት ብትለን :: በል እስኪ እዚህ ዋርካ የበተንካቸውንም ስራዎችህን በመልክ በመልኩ ሰብስብና እዛኛው ቤትህ
[url]http://yetemonamonew.wordpress.com/[/url]
ተቁዋደሱ በለን ::
ከአክብሮት ምስጋና ጋር

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
የተውኩትን ነገር
ተመክሬ ተነግሬ በሃገር
ምን ጎትቶ አመጣብኝ
ያን ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር

ጉድ ፈላ ዘንድሬ አቤት አቤት
_ማን አስተማረብኝ
ማስቲካ ሆኛለሁ ከረሜላ
_' አሳደረኝ

ይሄው ይሰማኛል ጥሩምባ
ይሄው ይነፋሉ ጥሩምባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
እረ ጉድ እረ ጉድ ፈላ
እፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ

እዩት ልጁን ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት በዚህ ጉዳይ
ወይ ቁመና ወየው ዛላ
ሰው እንደ 'ህል አይበላ
አለ ለካ የሰው ሃረግ
ደረት ክንዱ ባለ 'ማረግ

እስኪ በጆሮየ ፍቅርን ይድገም ያነብንብልኝ
ከትንፋሹ በልጦ የሚደመጥ
ምን ሙዚቃ አለኝ
በጁ ቢነካካኝ ድምጽ አወጣሁ
እኔም እንደ ጊታር
ጉድ አረገኝ መውደድ
ጉድ አረገኝ የዚህ ሰው ፍቅር

አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ፍቅሬን ላንተ ሰጥቻለሁ
አርገኝ የቤትህ እመቤት

.
.
.
እጂጋየሁ ጂጂ ---> http://www.youtube.com/watch?v=UAuNVxC8Fz0
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Nov 13, 2012 6:24 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወንድም እንሰት

የኔ ነገር መቸስ የውልህ እንዲህ ነኝ ....ለእንግዶቻችን እንዳታንስ በማለት እስኪ ትንሽ ልጣጥፍ ልለጣጥፍባት ብዬ ነው ... አልረሳሁም Smile

ካታላቅ አክብሮት ጋር አመሰግናለሁ ወዳጄ !

ሞርኒንግ ሰን http://www.youtube.com/watch?v=QVJVKr6CCeU
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1198
Location: united states

PostPosted: Wed Nov 14, 2012 6:28 pm    Post subject: Reply with quote

እጅ ነስቻለሁ ::
በነካ እጂህ ያቺን የጀመርካትን ጽሁፍ ብትቀጥላትስ :: አሁንም ዝርዝሩዋ ሁሉ ተረሳኝ ::

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወንድም እንሰት

የኔ ነገር መቸስ የውልህ እንዲህ ነኝ ....ለእንግዶቻችን እንዳታንስ በማለት እስኪ ትንሽ ልጣጥፍ ልለጣጥፍባት ብዬ ነው ... አልረሳሁም Smile

ካታላቅ አክብሮት ጋር አመሰግናለሁ ወዳጄ !

ሞርኒንግ ሰን http://www.youtube.com/watch?v=QVJVKr6CCeU
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Wed Nov 21, 2012 12:45 pm    Post subject: Reply with quote

ብዙ ከመሬት ርቃ

ለዘመናት ቀልብን ሰርቃ

በብርማ ቀለም አብረቅርቃ

እንደምትታየው ደምቃ

_ሲደርሱባት ግን ምድረ በዳ

_አባጣ ጎርባጣና ጎድጓዳ

እንደሆነችው እንደ ጨረቃ

ደረቅ ...በረሃ ...ባዶ ...ኦና

እንዳትሆኝብኝ ሰጋሁና

መምጣቱን ትቼዋለሁ

በሩቁ መደመሙን

አቤት ውበቷ እያልኩኝ

መኖርን መርጫለሁ ::

/ልጅ ሞንሟናው /

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
Page 8 of 10

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia