WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የወያኔ ራስን በራስ የማጥፋት ዘመቻ

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ላፊሶ

ኮትኳች

Joined: 02 Sep 2009
Posts: 211

PostPosted: Sat Jun 16, 2012 4:31 pm    Post subject: የወያኔ ራስን በራስ የማጥፋት ዘመቻ Reply with quote

ስካይፕን መጠቀም ወንጀል ነዉ የሚል ነገር ኢንተርኔት ላይ አንብቤ ስተት መሆን አለበት ወያኔን የሚጠሉ ወሸታሞች የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ይሆናል አልኩ :: ለማንኛዉም ግን ነገሩን ለማረጋገጥና እስኪ ይሀን ነገር በሚመለከት ኢሕአዲግ ምን ይላል ብየ ድረገፃቸዉጋ ሄድኩ :: ጉዳየዩን በሚመለከት የተፃፈ ነገር ድረገፃቸዉ ላይ የለም ነገር ግን አምስት የቻይና ሊቆች የኢትዮጵያን መንግስት ባለስልጣኖች የዜና ምንጮችንና ኢንተርኔትን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያስተምር ስልጠና አረጉ የሚል ነገር ሳይ መጠራጠር ጀመርኩ :: የቻይና መንግስት ባለም ላይ ከታወቀባቸዉ ነገሮች አንዱ ኢንተርኔትን በማፈን ነዉ :: የዚህ አገር ልዑካን የኢትዮጵያን መንግስት እንዴት ኢንተርኔትን ተጠቅሞ የሕዝብን እዉቀት ማዳበር ኢንደሚቻል እንደማያስተምሩት አቃለሁ :: የሚያሰተምሩት ነገር ቢኖር የተካኑበትን ያፈና ዘዴ ነዉ :: ባጋጣሚ ይህ ስልጠና የተደረገዉ ባለንበት ወር መጀመርያዎች አካባቢ ሲሆን አወጁ ወጣ የተባለዉ ባለፉት ሁለት ቀናት ነዉ :: መጥፎ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ብየ ለምን በስካይፕ አገርቤት ደወየ አላረጋግጥም አልኩና አንድ የማዉቀዉ ወዳጄን ደወልኩለት :: ቪዲኦው አይታይም ድምፁም ይቆራረጣል ትንሸ ቆይቶ ከነጭራሹ ግንኙነቱ ተቐረጠ ቴክኒካሊ ስካየፕን መጠቀም አይቻልም :: አይን ያወጣ አፈና መሆኑ ገባኝ ::
የኢሕአዲግ መንግስት የቻይናን ኢካነሚክ ሞዴል ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ረገጣና የአፈና ዘዴያቸዉንም የለምንም ለዉጥ አገራችን ዉስጥ ሊጠቀምበት እየተዘጋጀና ካድሬዎቹን እያሰለጠነ መሆኑ በጣም አሰሳቢ ነዉ :: ጥያቄዉ ግን ለምን እንደዚህ አይነት የከረረ ያፈና ዘመቻ አሰፈለገ ነዉ :: በሰሜን አፍሪካ በግብፅ :ቱኒዚያና ሊቢያ የተደረገዉ የሕዝብ አመፅ ቴክናለጂ የጠናከረዉ መሆኑ ከወያኔ ምንግስት የተደበቀ ሚስጢር አይደለም ምናልባት የወያኔ መንገስት የህዝብ አመፅ ድንበራችንን ጥሶ ከመግባቱ በፊት እናፍነዉ ከሚል ግምት ይሆን :: ወያኔዎች በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ የለዉ ተጨባጭ ሁኔታ ከላይ ከጠቀስዃቸዉ ከሰሜን አፍሪካ አገሮች የተለየ ስለሆነ ተመሳሳይ አመፅ ኢትዮጵያ ዉስጥ መምጣት እንደማይችል ነግረዉን ነበር በተግባር የሚያደርጉት ነገር ግን ባሉት ነገር ላይ ምንም እምነት እንደሌላቸዉ ያሳያል :: የምዕራብ አገሮች የዲማክረሲ አሰራር አገራችን ወስጥ አይሰራም አገር ዉስጥ የተተከለና ያደገ Organic የሆነ ዲማክረሲን ማፍራት አለብን ብለዉ እንዳልነገሩን ሁሉ የቻይናን አፈናና ሰብአዊ መብት ረገጣ ግን copy and paste ሲያረጉት ሕዝብ ይታዘበናል ብለዉ አያፍሩም ::
አንድ አንዶች እንደሚሉት የወያኔ መንግስት ምንም ላገር የሚበጅ ነገር አልሰራም ብየ አላምንም :: ኢካነሚዉ እያደገ ነዉ ብሄር ብሄረሰቦች ባህላቸዉንና ቐንቐቸዉን ማዳበር ችለዋል :: ካለፉት መንግስታት ጋር ሲተያይ አገራችን የተሻለ ጎዳና ላይ ነዉ ያለችዉ :: የወያኔ መንግስት በነዚህ መልካም ነገሮች ላይ ተሟርክዞ አገሪችንን ወደተሻለና መቀልበስ ወደማይችል ፍንኦት ሊመራት ይችል ነበር ምርጫዉ ግን ሕዝብን በማፈንና ሰብአዊ መብትን በመርገጥ መጨረሻዉ ወደማያምር ጨለማ የቻይናን እጅ ይዞ መዝገም ነዉ :: የወያኔ መሪዎች ማየት የተሳናቸዉ እዉነታ አገራችን ዉስጥ ከኢሕአዲግ የተሻለ አማራጭ ስለሌለ ሕዝቡ በነሱ ላይ የሚነሳበት ምክንያት በወቅቱ አለመኖሩን ነዉ :: ባለፉት አመታት የወያኔ መንግስት እያሰራ ያለዉ ድርጊት ግን ቀስ በቀስ የሕዝብን መብት እየገፈፈ የዲማክረሲን ምንገድ እያጠፋና ነፃ የመገናኛ ምንጮችን ከስር ነቅሎ አፈናን መስፋፋት ነዉ ::በሌላ አባባል ለህዝብ አመፅ የሚገፋፉ ችግኞችን እየተከለ ነዉ :: እነዚህ ችግኞች ፍሬ ማፍራታቸዉ ይዋል ይደር እንጂ አይቀርም ደብረዉም ወያኔን ያጠፉታል ያሲሆን ግን ወያኔ ለራሱ መጥፋት ምንስኤዉ ራሱ መሆኑን ከወዲሁ መገንዘብ አለበት ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ላፊሶ

ኮትኳች

Joined: 02 Sep 2009
Posts: 211

PostPosted: Sat Jun 16, 2012 10:32 pm    Post subject: Reply with quote

ከላይ የጠቀስኩትን ወያኔና የቻይና መንግስት የሚያረጉትን የአፈና ትብብር ለማንበብ እዚህ ተጭነዉ የመጀመርያዉን ሊንክ ከፍተዉ ይግቡ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሓየት 11

ዋና አለቃ

Joined: 06 Apr 2008
Posts: 2779
Location: ላን'ሊይ

PostPosted: Sun Jun 17, 2012 1:10 am    Post subject: Re: የወያኔ ራስን በራስ የማጥፋት ዘመቻ Reply with quote

ጤና ይስጥልን አይተ ላፊሶ

ሊቁ ወዳጆ ለረዥም ጊዜ ሲያስተጋባው የኖረውን እውነታ በማንጸባረቆ በውነቱ ሊመሰገኑ ይገባል .

በተቃዋሚ ተብዬዎች ስብእናና ብቃት ወያኔ ምንጊዜም ቢሆን ሊነቃነቅ እንደማይችል ሆኖም ግን አቦይ ስብሓት በአንድ ወቅት ሳያስቡት በተናገሩት እውነታና የወያኔን ግንባር ቀደም አላማን በማሳካት መሰረት "ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ " ሲያጠፋ ብቻ በኢትዮጵያ ተፈላጊው ለውጥ ሊኖር እንደሚችል በዚህ ፎረም ለበርካታ ጊዜያት ስናገረው የነበረ ሀቅ ነው :: ራሱን በራሱ በማጥፋት ከዋርካ የተገለለውን ጥልቁ 1 መጠየቅ ይቻላል ::

እዚህ ዋርካ እንደምናያቸው አይነት ከብት ተቃዋሚ ተብዬዎች ስርዓቱ ሊናጋ ቀርቶ ጫፉ ሊነካ እንደማይችል ግልጽ ነው :: የለውጥ ፈላጊ አካል ከሆኑ ግን ይህንን ራስን በራስ የማጥፋት ዘመቻ ማበረታታት እንጂ ማሳሰብ ያለቦት አይመስለኝም ::

ሓየት አስራአንድ ነኝ Wink

ላፊሶ እንደጻፈ(ች)ው:
ስካይፕን መጠቀም ወንጀል ነዉ የሚል ነገር ኢንተርኔት ላይ አንብቤ ስተት መሆን አለበት ወያኔን የሚጠሉ ወሸታሞች የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ይሆናል አልኩ :: ለማንኛዉም ግን ነገሩን ለማረጋገጥና እስኪ ይሀን ነገር በሚመለከት ኢሕአዲግ ምን ይላል ብየ ድረገፃቸዉጋ ሄድኩ :: ጉዳየዩን በሚመለከት የተፃፈ ነገር ድረገፃቸዉ ላይ የለም ነገር ግን አምስት የቻይና ሊቆች የኢትዮጵያን መንግስት ባለስልጣኖች የዜና ምንጮችንና ኢንተርኔትን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያስተምር ስልጠና አረጉ የሚል ነገር ሳይ መጠራጠር ጀመርኩ :: የቻይና መንግስት ባለም ላይ ከታወቀባቸዉ ነገሮች አንዱ ኢንተርኔትን በማፈን ነዉ :: የዚህ አገር ልዑካን የኢትዮጵያን መንግስት እንዴት ኢንተርኔትን ተጠቅሞ የሕዝብን እዉቀት ማዳበር ኢንደሚቻል እንደማያስተምሩት አቃለሁ :: የሚያሰተምሩት ነገር ቢኖር የተካኑበትን ያፈና ዘዴ ነዉ :: ባጋጣሚ ይህ ስልጠና የተደረገዉ ባለንበት ወር መጀመርያዎች አካባቢ ሲሆን አወጁ ወጣ የተባለዉ ባለፉት ሁለት ቀናት ነዉ :: መጥፎ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል ብየ ለምን በስካይፕ አገርቤት ደወየ አላረጋግጥም አልኩና አንድ የማዉቀዉ ወዳጄን ደወልኩለት :: ቪዲኦው አይታይም ድምፁም ይቆራረጣል ትንሸ ቆይቶ ከነጭራሹ ግንኙነቱ ተቐረጠ ቴክኒካሊ ስካየፕን መጠቀም አይቻልም :: አይን ያወጣ አፈና መሆኑ ገባኝ ::
የኢሕአዲግ መንግስት የቻይናን ኢካነሚክ ሞዴል ብቻ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ረገጣና የአፈና ዘዴያቸዉንም የለምንም ለዉጥ አገራችን ዉስጥ ሊጠቀምበት እየተዘጋጀና ካድሬዎቹን እያሰለጠነ መሆኑ በጣም አሰሳቢ ነዉ :: ጥያቄዉ ግን ለምን እንደዚህ አይነት የከረረ ያፈና ዘመቻ አሰፈለገ ነዉ :: በሰሜን አፍሪካ በግብፅ :ቱኒዚያና ሊቢያ የተደረገዉ የሕዝብ አመፅ ቴክናለጂ የጠናከረዉ መሆኑ ከወያኔ ምንግስት የተደበቀ ሚስጢር አይደለም ምናልባት የወያኔ መንገስት የህዝብ አመፅ ድንበራችንን ጥሶ ከመግባቱ በፊት እናፍነዉ ከሚል ግምት ይሆን :: ወያኔዎች በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ የለዉ ተጨባጭ ሁኔታ ከላይ ከጠቀስዃቸዉ ከሰሜን አፍሪካ አገሮች የተለየ ስለሆነ ተመሳሳይ አመፅ ኢትዮጵያ ዉስጥ መምጣት እንደማይችል ነግረዉን ነበር በተግባር የሚያደርጉት ነገር ግን ባሉት ነገር ላይ ምንም እምነት እንደሌላቸዉ ያሳያል :: የምዕራብ አገሮች የዲማክረሲ አሰራር አገራችን ወስጥ አይሰራም አገር ዉስጥ የተተከለና ያደገ Organic የሆነ ዲማክረሲን ማፍራት አለብን ብለዉ እንዳልነገሩን ሁሉ የቻይናን አፈናና ሰብአዊ መብት ረገጣ ግን copy and paste ሲያረጉት ሕዝብ ይታዘበናል ብለዉ አያፍሩም ::
አንድ አንዶች እንደሚሉት የወያኔ መንግስት ምንም ላገር የሚበጅ ነገር አልሰራም ብየ አላምንም :: ኢካነሚዉ እያደገ ነዉ ብሄር ብሄረሰቦች ባህላቸዉንና ቐንቐቸዉን ማዳበር ችለዋል :: ካለፉት መንግስታት ጋር ሲተያይ አገራችን የተሻለ ጎዳና ላይ ነዉ ያለችዉ :: የወያኔ መንግስት በነዚህ መልካም ነገሮች ላይ ተሟርክዞ አገሪችንን ወደተሻለና መቀልበስ ወደማይችል ፍንኦት ሊመራት ይችል ነበር ምርጫዉ ግን ሕዝብን በማፈንና ሰብአዊ መብትን በመርገጥ መጨረሻዉ ወደማያምር ጨለማ የቻይናን እጅ ይዞ መዝገም ነዉ :: የወያኔ መሪዎች ማየት የተሳናቸዉ እዉነታ አገራችን ዉስጥ ከኢሕአዲግ የተሻለ አማራጭ ስለሌለ ሕዝቡ በነሱ ላይ የሚነሳበት ምክንያት በወቅቱ አለመኖሩን ነዉ :: ባለፉት አመታት የወያኔ መንግስት እያሰራ ያለዉ ድርጊት ግን ቀስ በቀስ የሕዝብን መብት እየገፈፈ የዲማክረሲን ምንገድ እያጠፋና ነፃ የመገናኛ ምንጮችን ከስር ነቅሎ አፈናን መስፋፋት ነዉ ::በሌላ አባባል ለህዝብ አመፅ የሚገፋፉ ችግኞችን እየተከለ ነዉ :: እነዚህ ችግኞች ፍሬ ማፍራታቸዉ ይዋል ይደር እንጂ አይቀርም ደብረዉም ወያኔን ያጠፉታል ያሲሆን ግን ወያኔ ለራሱ መጥፋት ምንስኤዉ ራሱ መሆኑን ከወዲሁ መገንዘብ አለበት ::

_________________
An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ላፊሶ

ኮትኳች

Joined: 02 Sep 2009
Posts: 211

PostPosted: Sun Jun 17, 2012 3:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላምታ ሐያት
Quote:
እዚህ ዋርካ እንደምናያቸው አይነት ከብት ተቃዋሚ ተብዬዎች ስርዓቱ ሊናጋ ቀርቶ ጫፉ ሊነካ እንደማይችል ግልጽ ነው :: የለውጥ ፈላጊ አካል ከሆኑ ግን ይህንን ራስን በራስ የማጥፋት ዘመቻ ማበረታታት እንጂ ማሳሰብ ያለቦት አይመስለኝም ::

በቅድምያ ሀሳብህን የምጋራዉ ብሆንም አቀራረብህን ግን አወግዛለሁ :: አንተ ከብቶች የምትላቸው ሰዎች እንዳንተዉና እንደኔ አገራቸዉን የሚወዱ ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ ተሳስተዋል ማለት አንድ ነገር መሳደብ ግን ሌላ ስለዚህ የሚቃወምህን ቡድን ስብእና መጠየቅ ያንተንም ጥያቄ ዉስጥ ስለሚከተዉ እንደዛ አይነት ቋንቋ መጠቀሙ ማንንም የሚጠቅም አይመስለኝም :: በተረፈ ዛሬ የተደራጀና ህዝብን አቀራርቦ መምራት የሚችል የተቃዋሚ ሀይል አለ ብየ አላምንም :: በወቅቱ ያሉት Interest Groups ናቸዉ :: አንዱን ወይም ሌላዉን የህብረተሰብ ክፍል ሊወክሉ ይችላሉ ነገር ግን የኢትዮጵያን ህዝብ ማስተዳደር የሚያስችል ራኢ የላቸውም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
myusername

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 02 Jun 2012
Posts: 53

PostPosted: Mon Jun 18, 2012 2:46 am    Post subject: Reply with quote

ላፊሶ እንዳለ ()
Quote:
አንድ አንዶች እንደሚሉት የወያኔ መንግስት ምንም ላገር የሚበጅ ነገር አልሰራም ብየ አላምንም :: ኢካነሚዉ እያደገ ነዉ ብሄር ብሄረሰቦች ባህላቸዉንና ቐንቐቸዉን ማዳበር ችለዋል :: ካለፉት መንግስታት ጋር ሲተያይ አገራችን የተሻለ ጎዳና ላይ ነዉ ያለችዉ ::

አይ ላፊሶ አንተ እንደምትለዉ ወያኔ ኢኮነሚዉን ካሳደገ ለምን ህዝቡ ይራባል ታድያ :: አዋቂ ሰዉ መስለህእኝ ነበር ይህን የወያኔን ወሸት ማየት አለመቻልህ ግን ገርሞኛል :: የወያኔ እድገት እኮ ወረቀት ላይ ያለ እንጂ ለህዝቡ ምንም የጠቀመዉ ነገር የለም :: በጣም ያሳዘነኝ አባባልህ ግን የብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋና ባህል አለማ ስትለኝ ነዉ ::
ወያኔ ህዝብን ለማጣላት ያረግዉን የክልል አስተዳደር እንደ እድገት የምታይ ከሆነ በጣም አዝናለሁ :: አንተ የምትወክለዉ የወረሞ ህዝብ ዛሬ እስር ቤት እየማቀቀ ነዉ :: እኔን ካላመንክ ወያኔ የነበረዉን ስየን ጠይቀዉ :: ወያኔ ካማራ በላይ የሚጠላዉ ወረሞን ነዉ እንዲያዉ በቂም በቀል ታዉረህ ካልሆነ ይህን እነኳ ማየት የሚሳንህ አይመስለኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ላፊሶ

ኮትኳች

Joined: 02 Sep 2009
Posts: 211

PostPosted: Tue Jun 19, 2012 1:20 am    Post subject: Reply with quote

myusername,
Quote:
አይ ላፊሶ አንተ እንደምትለዉ ወያኔ ኢኮነሚዉን ካሳደገ ለምን ህዝቡ ይራባል ታድያ :: አዋቂ ሰዉ መስለህእኝ ነበር ይህን የወያኔን ወሸት ማየት አለመቻልህ ግን ገርሞኛል :: የወያኔ እድገት እኮ ወረቀት ላይ ያለ እንጂ ለህዝቡ ምንም የጠቀመዉ ነገር የለም :: በጣም ያሳዘነኝ አባባልህ ግን የብሄር ብሄረሰቦችን ቋንቋና ባህል አለማ ስትለኝ ነዉ ::
ወያኔ ህዝብን ለማጣላት ያረግዉን የክልል አስተዳደር እንደ እድገት የምታይ ከሆነ በጣም አዝናለሁ :: አንተ የምትወክለዉ የወረሞ ህዝብ ዛሬ እስር ቤት እየማቀቀ ነዉ :: እኔን ካላመንክ ወያኔ የነበረዉን ስየን ጠይቀዉ :: ወያኔ ካማራ በላይ የሚጠላዉ ወረሞን ነዉ እንዲያዉ በቂም በቀል ታዉረህ ካልሆነ ይህን እነኳ ማየት የሚሳንህ አይመስለኝም ::

ባንተ ግምት አገር ካደገ ሁሉም ጠግቦ መብላት አለበት ማለት ነው :: ያማ ቢሆነ ያደጉት አገሮች ዉስጥ የሚራብ ሰዉ ሊኖር አይችልም ማለት ነዉ :: እኔም አንተም እንደምናቀዉ የሚራቡ ሰዎች በሰለጠኑ አገሮች አሉ ስለዚህ ከላይ ያሰፈርከዉ ነገር በዉነት ላይ የተመሰረተ አይደለም ::

በተረፈ እኔ ወረሞ አይደለሁም ወረሞ ምን ማልት እንደሆንም አላዉቅም :: ኦረሞ ማለት ፈልገህ ከሆነ ትርምትህን ተቀብለህ ሁለተኝ እንዳትደግመዉ :: መካድ የማይቻል ነገር ቢኖር ብሄር ብሄረሰቦችን በተመለከት ወያኔ ጥሩ ነገር ሰርታለች ስለዚህ ያንን ጥላሸት መቀባት ከፈለክ ትችላለህ እኔ ግን አላደርገዉም :: እኔ የወያኔ ደጋፊ አይደለሁም የጻፍኩትን አንብበህ ከሆነ መረዳት የሚያዳግትህ አይመስለኝም ነገር ግን የኔ ተቃዉሞ ጭፍን በሆነ ጥላቻ ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ምክንያታዊ የሆነ ነዉ :: ስህተት ሲሰሩ መሳሳታቸዉን እናገራለሁ መልካምም ሲሰሩ እስየሁ እላለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia