WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 46, 47, 48 ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Sun Jun 24, 2012 7:00 pm    Post subject: Reply with quote

የተከበርክ ልጅ ተድላ እንደምን አለህ ?
ጽሁፉን በመላ አነበብኩት
የቀነኒሳ ማሸነፍ ተስፋ ሰጥቶኛል በውነት ደስ የሚል ነገር ነው ::
ያልገባኝ ነገር አንደኛ የመርጋ ከውድድር መሰረዝ በምን ምክኒያት ነው ?
ሁለትኛ ቀነኒሳ በቀለን እንዳይወዳደር የሚያግድ ህግ ለምንድነው በሀገር ውድድር ላይ ማናጀር ይወስናል ይሄ ህግ ነው ትላለህ ? እባህ አብራራልኝ ::
አክባሪህ ኮሎኔል ነኝ
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jun 24, 2012 7:37 pm    Post subject: Reply with quote

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
የተከበርክ ልጅ ተድላ እንደምን አለህ ?

እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ :: እርስዎም ከእነ ቤተሰብዎ ደህና እንደሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
ጽሁፉን በመላ አነበብኩት
የቀነኒሳ ማሸነፍ ተስፋ ሰጥቶኛል በውነት ደስ የሚል ነገር ነው ::
ያልገባኝ ነገር አንደኛ የመርጋ ከውድድር መሰረዝ በምን ምክኒያት ነው ?

ኢማኒ መርጋን እና ሌሊሣ ዲሣሣን እንዳይወዳደሩ ያስደረገው የበርሚንግሃም ውድድርን ያዘጋጀው አካል እንጂ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አይደለም :: 'ለምን ?' ለሚለው ግን እኔም ምክንያቱን ማወቅ አልቻልኩም :: ምናልባት ለአትሌቶቹ ውድድር የሚያፈላልጉላቸው ደላሎች እጃቸውን አስረዝመው ተፅዕኖ እያሣደሩ ይሆን ?

Quote:
ሁለትኛ ቀነኒሳ በቀለን እንዳይወዳደር የሚያግድ ህግ ለምንድነው በሀገር ውድድር ላይ ማናጀር ይወስናል ይሄ ህግ ነው ትላለህ ? እባክህ አብራራልኝ ::
አክባሪህ ኮሎኔል ነኝ

እንግዲህ ድሮ የምናውቀው ፌዴሬሽን ሉዓላዊነቱን የማያስደፍር ነበር :: አሁን : አሁን ግን በጥቅማ -ጥቅም የሚደለሉ ሆዳሞች የበዙበት ዘመን ስለሆነ በተለይ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የሚሠራው ሥራ ከባለሥልጣኖች ጥቅም የማግኘትና ያለማግኘት ጋር እየተመዘነ ሲታይ ችግሩ ግልፅ ይሆንልናል :: የቀነኒሣም ሆነ የአብዛኞቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር አፈላላጊ ደላላ ጆስ ሔርመንስ የሚሉት (ምሩፅ ይፍጠርን በውድድር ማሸነፍ አቅቶት ሩጫ ያቆመ ) የሆላንድ ዜጋ ነው :: ይህ ሰው ባሉት የንግድ ግንኙነቶች መሠረት ውድድሮችን እያፈላለገ ሯጮች እዚያ እንዲወዳደሩ የሚያደርገው በመጀመሪያ የራሱን ጥቅም አስቀድሞ ስለሆነና በፌዴሬሽኑ ውስጥ ያሉትም ሹሞች በአሠራራቸው እንደፈለገው ጣልቃ እንዲገባ እስከፈቀዱለት ድረስ ያሻውን ያደርጋል :: እኔ ግልፅ የሆነልኝ ጉዳይ ይህ ነው ::

አክባሪዎ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Tue Jun 26, 2012 9:35 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
የሰሞኑ ኳስ ጸጥ አድርጎን ነው የከረመው :
የያዝነው አመት 2012 የኢሮፕ ዋንጫ የተሻለ ቴክኒክ እና ብዙ ለውጥ ያየንበት ነው ሲል አንድ ጀርመናዊ የስፖርት ተንታኝ ተናግሯል ::
እኔም በትክክል ይህንን ሀሳብ የምጋራ ሲሆን ባለፈው እሁድ እንግሊዞች ያሳዩት ማራኪ ጨዋታ እምብዛም ፋውል ያልታየበት የረጋና ጥሩ የፉትቦል መንፈስ ያለበት ነበር ::
በርግጥ ጥልያኖቹ በሁለተኛው ግማሽ በጫና የተጫወቱ ቢሆንም እንግሊዞቹ ግን ከኳሷ ጋር የሚገናኙት በሂሳብ ነው ::
ቱርካዊው የኳስ ተንታኝ ሜህመት ሾል መሬት ያለችን ኳስ በተረከዝ ጥቅም ላይ ማዋል የሚደረግ ነገር ነው በአየር ላይ ግን ሌላ ደረጃ ነው !
በማለት ለትንታኔ በተጋበዘበት የጀርመን ቴሌቪዥን እንግሊዛዊውን ዳኒ ዌልቤክን አሞግሶታል ::
ጀርመኖች እንግሊዞችን ከሌላ ታሪክ ጋር በተያያዘ ቢሆንም በተለይ በፉትቦል ንቀትም ጥላቻም አለባቸው ዘንድሮ ግን ባሳዩት ድንቅ ጨዋታና ስፖርታዊ ጨዋነት *ሪስፔክት ለእንግሊዞች * ብለዋል ::
ይህንን ከጀርመን ስፖርት ሪፖርተሮች መስማት ትልቅ ነገር ነው ::
ጊዜው ቆየት ቢልም ታዋቂውና አንደበተ ርቱዑ የኢትዮጵያ ስፖርት አባት ይድነቃቸው ተሰማ በአንድ ወቅት ስለብራዚሎች የኳስ ጥበብ አንድ የተናገሯትን ነገር አስታውሳለሁ :
ጥያቄው የቀረበላቸው ስለ አርጀንቲናዊው ዲያጎ ማራዶና እና ብራዚላዊው ፔሌ ችሎታ ሲሆን ስለ ልዩነታቸው የተናገሩትን ትቼ ስለ ብራዚላውያን የኳስ ችሎታ የተናገሩትን ልጥቀስ
** አርጀንቲናዎች ኳሷን ይመቷታል ብራዚሎች ግን ኳሷን ያብሷታል ** ነበር ያሉት ::
የፉትቦሉ ፈጣሪዎች የሆኑትና የአህጉራቸውን ዋንጫ አንድም ጊዜ አንስተው የማያውቁት እንግሊዛውያን እሁድ ዕለት ኳስን እያበሱ ሜዳውን በውብ እንቅስቃሴ ሲሞሉት በማየቴ በኅሊናዬ የነበረውን የይድነቃቸው ተሰማን አባባል በአይኔ እንዳየሁ ያህል ነበር የተሰማኝ ::
እጅግ በጣም አስደሳችና ማራኪ ጨዋታ ነው ::
እርግጠኛ ነኝ በርካታ የአለም ተመልካቾችንም የማራኪ ፉትቦል ጥማቸውን አርክተዋል ::
በጣልያን እና በእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን መካከል የተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ምንም እንኳን ደጋፊያቸው የነበርኩ ብሆንም እስካሁን ከነበሩት ሁሉ ድንቅ እንቅስቃሴ ያየሁበትና የተደሰትኩበት ጨዋታ ነው ::
በሌላ በኩል ደሞ በብዙዎች ዘንድ የዘንድሮውን ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን ?
የሚል ጥያቄ ቢኖርም እስካሁን ባለው ሁኔታ መልሱ ብዙ ርቆ የሚታይ አይደለም ::
ጀርመኖች ከምን ግዜውም ይበልጥ በወጣቶችና ቴክኒካል ብቃት ባላቸው ተጨዋጮች የተደራጀ ከመሆኑም በላይ እስካሁን ድረስ አንዴም መሸነፍ አልቻለም ::
ዘንድሮ ዋንጫውን ያነሳል ተብሎም በብዙዎች ዘንድ ተገምቷል የኔም ግምት ከዚህ የራቀ አይደለም ::
ለመጀመሪያ ጊዜ የጀርመንን ብሄራዊ ቡድን በመደገፍ ባንዲራውን ማውለብለብ መጀመራችንም የአዲሱን ብሄራዊ ቡድን አደረጃጀት በመደገፍ ነው ::
ጀርመን ለረዥም ዘመን የጃርሳ ቡድን በመባል ይታወቅ ነበር ሉተር ማቲያስ 150 ጊዜ በላይ ለብሄራዊ ቡድን በመጫወት ክብረወሰን ያለው ነው ::
ዘንድሮ በሆላንድ ቡድን ላይም ይህ ተመሳሳይ አስተያየት እየተሰጠ ነው የጃርሳ ቡድን እየተባለ ::
ጀርመን ይህንን ወጣት ቡድን ለመገንባት ብዙ ብዙ ደክመዋል አሰልጣኙ ዮሀኪም ሎቭ በዚህ ረገድም የተሳካላቸው ሠው ሆነዋል ::
በተለይ ተወላጆቹን እና ስመ ገናናዎቹ እነ ሚካኤል ባላክን ጨምሮ ሌሎቹም ምንም እንደማይፈይዱ ቀድመው በመረዳታቸው እንዲሁም አለም አቀፋዊነትን መቀበል ግዴታቸው መሆኑን ዘግይተውም ቢሆን በመቀበላቸው በተለይም እነፍራንዝ ቤከንባወርን አሸንፈው እንዲህ ያለ ቡድን በመስራታቸው አሁን ያገኙት የድጋፍ አጸፋ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጡት ያደርጋቸዋል ብዬ አምናለሁ ::
ከፊል ተጫዋቾቹን የውጪ ሀገር ተወላጆች አድርጎ የተሰራው የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ዘንድሮ ዋንጫውን ያነሳል የሚል ትልቅ ቅድመ አመኔታ ተሰጥቶታል ::
እኔም ይህንን ድል ከልብ እመኛለሁ !
ለዛሬ ሠላም ሁኑ

ራስብሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jun 27, 2012 12:32 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ራስ ብሩ :-

ኧረ እንዲያው እዚያ ዋናው ቤት የነበሩት ፊታውራሪዎች ጠፍተዋል :: እስኪ አንድ መንገድ ዘይድና ቀስቅሣቸው ::

ዘንድሮ የአውሮፓን ዋንጫ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ጨዋታዎች ለመመልከት ዕድሉ አጋጥሞኛል :: በእኔ ዕይታ እስካሁን ከባድ ፉክክር የታየበት ጨዋታ እስፓኝ እና ክሮሺያ ያደረጉት ነበር :: ከዚያ ቀጥሎ እንግሊዝና ስዊድን ለመሸናነፍ ያደረጉት ፉክክር የሚሥብ ነበር :: በተቀረ የእንግሊዝና የጣሊያን ጨዋታ በእኔ ግምጋሜ የመጨረሻ ደካማ ከሚባሉት መካከል የሚመደብ ነው :: እንግሊዞች እንደተለመደው ያለአማካይ ተጨዋቾች ገብተው በጣሊያን የእግር ኳስ ቴክኒሽያኖች በእነ ፒሪሎ መጫዎቻ ሆነዋል :: ባለፉት 12 ዓመቶች የጀርመን ቡድን ከውድድር ወደ ውድድር ከፍተኛ የአጨዋወት ለውጥ እያሣየ የመጣ ቡድን ሆኗል :: ዘንድሮ ሜዳ ላይ የምናየው የጀርመን ቡድን የድሮውን የብራዚልን ቡድን አጨዋወት የሚከተል ነው :: ምንም እንኳን ተጨዋቾች እንደ ድሮው ቡድን አባሎች ግዙፍ ቢሆኑም አንዳቸውም ኳስ የሚጠልዙ ተጨዋቾች አይደሉም :: ጎል የሚደርሱት ውበት ባለው የኳስ ቅብብልና የሚያገቧቸውም ጎሎች የሚያረኩ ናቸው :: ጀርመን እስካሁን ባደረጋቸው ጨዋታዎች ያለመሸነፉ ብቻ ሣይሆን ሲያሸንፍም በአስተማማኝ ሁኔታ በልጦ ነው :: እስካሁን ግን የጀርመን የተከላካይ መሥመርና በረኛው ጠንካራ ፈተና ስላልገጠማቸው ከነገ ወዲያ ከጣሊያን ጋር በሚያደርጉት ግጥሚያ ምን ያህል ጥንካሬ እንዳላቸው እናያለን ::

ራስ ብሩ :- ስለ ቀነኒሣ የሠሞኑ ብቃት ምነው ምንም አላልክም ?

የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jul 02, 2012 4:55 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ከሰኔ 20/2004 .. ጀምሮ ለአምሥት ቀናት በፖርቶ ኖቮ (ቤኒን ) የተካሄደው የአፍሪቃ የአዋቂዎች የአትሌቲክስ ፉክክር ዛሬ እሑድ ተጠናቋል :: በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ማስመዝገብ የቻለችው 1 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ብቻ ሲሆን ምናልባትም በቅርብ ዘመን በዚህ ዓይነት ውድድር ከተገኙት ውጤቶች የዘንድሮው ዝቅተኛው ሣይሆን አይቀርም :: ሆኖም ኢትዮጵያ 55 አትሌቶች አሠልፋ እንዲህ ያለ ዝቅተኛ ውጤት መገኘቱ የሚያሣሥብ ነው :: ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ በምንታወቅባቸው የረዥም ርቀት የሩጫ ውድድሮች መካከል ሜዳሊያ ማግኘት የተቻለው በሴቶች ምድብ በጎይተቶም ገብረሥላሴ ተክለእግዚ አንድ ብቻ የነሐስ ሜዳሊያ ብቻ መሆኑ ነው :: ብርቱካን አዳሙ አሊ 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ያልተጠበቀ የብር ሜዳሊያ ስታመጣ ለወደፊቱ ተስፋ የሚሠጥ ውጤት በሴቶች 20 . እርምጃ ውድድር ተመዝግቧል (አይናለም እሸቱ ሽፈራው የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች ) :: በሁሉም ውድድሮች የኢትዮጵያ አትሌቶች ያስመዘገቡት ውጤት ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል ::

ምንጭ :- የውጤት ሠንጠረዥ ::

10 ሺሕ ሜትር ሩጫ
የሴቶች ምድብ

4 ..... መሪማ መሐመድ ሐሰን _____ 33 ደቂቃ 9.25 ሴኮንድ
5 ..... ምሕረት ደርቤ ደምሴ ______ 33 ደቂቃ 45.88 ሴኮንድ
7 ..... አፈራ ጐደፋይ በርሄ _______ 34 ደቂቃ 30.23 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
4 ..... ጠበሉ ዘውዴ ____________ 28 3.16
__ ..... ሰለሞን ደክሢሣ ጎንፋ ______ በውድድሩ አልተሣተፈም
-- ..... ገብረፃዲቅ አብርሃ አድሃና ___ በውድድሩ አልተሣተፈም

5 ሺሕ ሜትር ሩጫ
የሴቶች ምድብ

3 ..... ጎይተቶም ገብረሥላሴ ተክለእግዚ ___ 15 ደቂቃ 53.34 ሴኮንድ
4 ..... ዓለሚቱ ሃሮዬ ባናታ ____________ 15 ደቂቃ 55.36 ሴኮንድ
5 ..... ሽቶ ወዴሳ ኦሱ ________________ 16 ደቂቃ 14.49 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
4 ..... ቶሎሳ ገደፉ ፉፊ _______ 13 ደቂቃ 33.96 ሴኮንድ
8 ..... ይታያል አጥናፉ ________ 13 ደቂቃ 58.69 ሴኮንድ
9 ..... ጥሩነህ ቢረሣው ጀንበር ___ 13 ደቂቃ 59.16 ሴኮንድ

3 ሺሕ ሜትር የመሠናክል ሩጫ
የሴቶች ምድብ

2 ..... ብርቱካን አዳሙ አሊ ___ 9 ደቂቃ 45.41 ሴኮንድ
4 ..... መቅደስ በቀለ ታደሰ ____ 9 ደቂቃ 53.97 ሴኮንድ
6 ..... ለምለም በርሄ ያቸም ____ 10 ደቂቃ 9.53 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
4 ..... ናሆም መሥፍን ታሪኩ ___ 8 ደቂቃ 20.23 ሴኮንድ
5 ..... ታፈሰ ሠቦቃ ጅማ ______ 8 ደቂቃ 26.33 ሴኮንድ
6 ..... ሐብታሙ ጃለታ ፈይሣ ___ 8 ደቂቃ 29.03 ሴኮንድ

1,500 ሜትር
የሴቶች ምድብ

4 ..... ፋይኔ ጐደቶ ገመዳ _____ 4 ደቂቃ 8.29 ሴኮንድ
6 ..... ጌጤ ዲማ ዱቃለ _______ 4 ደቂቃ 13.15 ሴኮንድ
-- ..... ዓለም ገረዝሔር ገብረማርያም _ በውድድሩ አልተሣተፈችም

የወንዶች ምድብ
6 ..... አብዮት አብነት ብርሃኑ ___ 3 ደቂቃ 38.46 ሴኮንድ
10 ... ዘነበ አለማየሁ በቀለ ______ 3 ደቂቃ 41.00 ሴኮንድ
-- ..... ዳንኤል ግደይ ____________ በውድድሩ አልተሣተፈም

800 ሜትር ሩጫ
የሴቶች ምድብ

5 ..... ዓለም ገረዝሔር ገብረማርያም ___ 2 ደቂቃ 2.68 ሴኮንድ
8 ..... ሶፍያ ሸምሱ ጨገን ___________ 2 ደቂቃ 7.09 ሴኮንድ
-- ..... ማንጠግቦሽ መለሰ ____________ በውድድሩ አልተሣተፈችም

በወንዶች
5 ..... ሽፈራው ውሌ ገንዴ ____ 1 ደቂቃ 48.26 ሴኮንድ
7 ..... ማሙሽ ሌንጫ ሺርኮ ___ 1 ደቂቃ 48.98 ሴኮንድ
-- ..... እሥራኤል አወቀ ______ በውድድሩ አልተሣተፈም

400 ሜትር ሩጫ
ሴቶች

14 ..... ሰላም አብርሃላይ ታረቀ ___ በግማሽ ፍፃሜ 53.84 ደቂቃ (በማጣሪያው ውድድር 10 እና 53.47 ደቂቃ )
19 ..... ትዕግስት አሰፋ ተሰማ ____ በግማሽ ፍፃሜ 55.58 ደቂቃ (በማጣሪያ ውድድር 14 እና 54.05 ደቂቃ )
24 ..... ማኅሌት ሙሉጌታ ዓለሙ __ 55.62 ደቂቃ (በማጣሪያ ውድድር ማጣሪያ )

ወንዶች
11 ..... በረከት ደስታ ገብረፃዲቅ ___ በግማሽ ፍፃሜ 47.05 ደቂቃ (በማጣሪያው ውድድር 14 እና 47.02 ደቂቃ )
20 ... ሃጐስ ታደሰ ገብረመስቀል ___ በግማሽ ፍፃሜ 48.19 ደቂቃ (በማጣሪያው ውድድር 19 እና 47.47 ደቂቃ )
27 ..... ጐንፋ በቀለ ዳጌቲ ________ 49.64 ደቂቃ (በማጣሪያው ዙር ውድድር ማጣሪያ )

200 ሜትር ሩጫ
የሴቶች ምድብ

-- ....... ፈትያ ከድር ______ ከውድድሩ ውጭ ተደርጋለች
20 ..... ትዕግስት ታማኙ ___ በግማሽ ፍፃሜ 25.50 ደቂቃ (በማጣሪያ 25.30 ደቂቃ )

የወንዶች ምድብ
31 ..... ሊንጐ ኡባንግ ኡጅሉ ___ 21.98 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )
39 ..... አብዮት ሌንጮ ለጋሞ ___ 22.09 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )
42 ..... ወጠረ ገለልቻ ጋቢሦ __ 22.46 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )

100 ሜትር ሩጫ
የሴቶች ምድብ

27 ..... ትዕግስት ታማኙ ___ 12.74 (በማጣሪያው ዙር ብቻ )
-- ..... ፈትያ ከድር _______ ከውድድሩ ውጭ ተደርጋለች

የወንዶች ምድብ
33 ..... አብዮት ሌንጮ ለጋሞ ____ 11.00 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )
37 ..... ወጠረ ገለልቻ ጋቢሦ ____ 11.10 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )
41 ..... አለባቸው ደርሶ ጌታሁን __ 11.19 ሴኮንድ (በማጣሪያው ዙር ብቻ )

400 ሜትር የመሠናክል ሩጫ
የሴቶች ምድብ

14 ..... ወሰኔ በላይ ወንድሙ ___ 59.06 ሴኮንድ (በማጣሪያ ዙር ብቻ )

20 ኪሎ ሜትር የዕርምጃ ውድድር
የሴቶች ምድብ

3 ..... አይናለም እሸቱ ሽፈራው ___ 1 ሰዓት 49.45 ሴኮንድ
4 ..... አሥካለ ጢቂሣ በንቲ ______ 1 ሰዓት 56.01 ሴኮንድ
5 ..... አዳነች መንግሥቱ አየለ ____ 2 ሰዓት 4.45 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
5 ..... ቸርነት ሚቆሮ አኒሦ ___ የገባበት ሰዓት አልተጠቀሰም
6 ..... ሚሦቦ ሚናሞ ጋሞ ___ የገባበት ሰዓት አልተጠቀሰም
-- ..... አሰፋ ግዛቸው ካሣ ____ ውድድሩ አቋርጦ ወጥቷል

የዲስከስ ውርወራ
የሴቶች ምድብ

9 ..... መሠረት ገብረእግዚአብሔር ገብረፃዲቅ ___ 39.17 ሜትር

የወንዶች ምድብ
-- ..... ምትኩ ጥላሁን ምናለ ___ በውድድሩ አልተሣተፈም

የጦር ውርወራ
የሴቶች ምድብ

8 ..... መብራት ገብረሚካኤል ገረሥላሤ ___ 43.96 ሜትር

ወንዶች
8 ..... ምትኩ ጥላሁን ምናለ ___ 62.00 ሜትር
11 ..... ሣፖ ሣንጃ ሠንፄ _____ 53.60 ሜትር

በርዝመት ዝላይ ወንዶች :-
10 ..... ሊንጐ ኡባንግ ኡጅሉ ___ 7.26 ሜትር

4X400 ሜትር የዱላ ቅብብል ሩጫ
የሴቶች

7 ..... ኢትዮጵያ (ትዕግሥት አሰፋ ተሰማ : ወሰኔ በላይ ወንድሙ : ምሕረት ሙሉጌታ ዓለሙ : ሰላም አብርሃሌ ታረቀ ) ___ 3 ደቂቃ 41.10 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
-- ..... ኢትዮጵያ (ሃጐስ ታደሰ ገብረመስቀል : ሰለሞን ኃይሉ ማሩ : ጅብሪል ገለልቻ ጋቢሦ : በረከት ደስታ ገብረፃዲቅ ) ___ ከውድድሩ ውጭ ተደርገዋል

ከእነዚህ ሁሉ ተወዳዳሪዎች ለወደፊቱ ምን ያህሉ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ጥሩ ውጤት የማምጣት ተስፋ ይኖራቸዋል ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Jul 02, 2012 7:30 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;

ተድልሽ = ዝም ጭጭ ነው ::አሳፋሪ ሁጤት ከመሆኑ አንጻር ኢትዮጵያ በአስራ አራቱም ሻምፒዮና የወርቅ መዳልያ ያላገኘ
ችው አሁን ብቻ መሆኑም አሳሳቢ ይሆናል ::

በተለይም በሁለቱ በምንታወቅባቸው ርቀቶች (5 10) የበታች ሆነን መጨረሳችን አስደንጋጭም ነው ::
ለነገሩ እሄው እስከዛሬ ኦሎምፒክና በአለም ሻምፒኦና ላይ 12 አመት በላይ በምናውቃቸውና ምትክ በለላቸው አትሌቶች ብቻ
ለውድድር የምንቀርብ መሆናችንም ምን ያህል ምንም አይነት ስራ እንደማይሰራ አመላካች ነው :: ኬንያ በሁሉም
ርቀቶች ተተኪዎችን በማዘጋጀት ሁሌም አዳዲስ አትሌቶች ይዛ መቀረቧም ትምህርት ሆኖን እንኳ የሚያውቅ አይመስለንም ::

አፍሪካ አትለቲክስ ሻምፒዮና ያን ያህል እንኳ ትልቅ ፉክክር የሚታይበት ነው ባንልም በዚህ ውድድር ተተኪዎችን
ማሳየት ያለመቻላችንና ለመጀመርያ ግዜ በርቀቶቹ ሁሉ ምንም የወርቅ መዳልያ ያለማግኘታችን ተስፋ አስቆራጭና
ዛሬም እንቅልፍ ላይ መሆናችንን ያሳያል ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jul 06, 2012 9:26 pm    Post subject: Reply with quote

ሞፊቲ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ;;

ተድልሽ = ዝም ጭጭ ነው ::አሳፋሪ ሁጤት ከመሆኑ አንጻር ኢትዮጵያ በአስራ አራቱም ሻምፒዮና የወርቅ መዳልያ ያላገኘ
ችው አሁን ብቻ መሆኑም አሳሳቢ ይሆናል ::

በተለይም በሁለቱ በምንታወቅባቸው ርቀቶች (5 10) የበታች ሆነን መጨረሳችን አስደንጋጭም ነው ::
ለነገሩ እሄው እስከዛሬ ኦሎምፒክና በአለም ሻምፒኦና ላይ 12 አመት በላይ በምናውቃቸውና ምትክ በለላቸው አትሌቶች ብቻ
ለውድድር የምንቀርብ መሆናችንም ምን ያህል ምንም አይነት ስራ እንደማይሰራ አመላካች ነው :: ኬንያ በሁሉም
ርቀቶች ተተኪዎችን በማዘጋጀት ሁሌም አዳዲስ አትሌቶች ይዛ መቀረቧም ትምህርት ሆኖን እንኳ የሚያውቅ አይመስለንም ::

አፍሪካ አትለቲክስ ሻምፒዮና ያን ያህል እንኳ ትልቅ ፉክክር የሚታይበት ነው ባንልም በዚህ ውድድር ተተኪዎችን
ማሳየት ያለመቻላችንና ለመጀመርያ ግዜ በርቀቶቹ ሁሉ ምንም የወርቅ መዳልያ ያለማግኘታችን ተስፋ አስቆራጭና
ዛሬም እንቅልፍ ላይ መሆናችንን ያሳያል ::

ቸር እንሰንብት !!!

ሰላም ሞፊቲ :-

ዝም ጭጭ ካልን እኮ እንደ የዋኋ በግ ከመታረድ አናመልጥም :: በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተቃውሞን ከመግለጽ መቆጠብ አይኖርብንም :: ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአትሌቶችን አመራረጥ ሥብጥር ከተመለከትከው 'የወርቆቹ ዘሮች ' ብልጫውን እየያዙ መጥተዋል :: እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ኢትዮጵያ ያሏት ምርጥ አትሌቶች እኒህ ብቻ አይደሉም :: አዝማሚያቸው ያኔ በሲድኒ ኦሎምፒክ 25 የትግራይ አትሌቶችን ብቻ ለውድድሩ ለማሠለፍ ዐይናቸው በጨው ታጥበው የቀረቡበትን አጋጣሚ ያስታውሠኛል :: ዘንድሮ ለኦሎምፒክ ውድድር የሚሠለፉ አትሌቶችን በመምረጡ ሂደት ካለፉ ጊዜያት በከፋ ሁኔታ ዘረኝነት እንደሚነግሥ ፍንጮቹን እናያለን :: ስለዚህ አስቀድሞ ፊሽካ መንፋቱ አይከፋም ::

ዛሬ አርብ ሰኔ 29 ቀን 2004 .. በሊዬዥ (ቤልጅግ ) ከተደረጉት የአትሌቲክስ ውድድሮች መካከል በሥፍራው የተገኘውን ተመልካች የሣበው በአበራ ኩማ እና በሌሊሣ ደሢሣ መካከል 10,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር የታየው ፉክክር ነበር :: ምንም እንኳን ሁለቱም በሎንዶን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር የሚያበቃቸውን ሰዓት ለማስመዝገብ ባይበቁም ( ምንጭ :- ዘንድሮ እነ ቀነኒሣ 27 ደቂቃ 2.59 ሴኮንድ ገብተዋል ) ፉክክሩ በራሱ ጥሩ ማነቃቂያ ነበር :: ውድድሩን ሌሊሣ ደሢሣ 27 ደቂቃ 18.17 ሴኮንድ በመጨረስ ሲያሸንፍ አበራ ኩማ 0.27 ሴኮንድ ተቀድሞ 2 ሆኗል ::

ምንጭ :- የሊዬዥ አውራጃ (ቤልጅግ ) ኢንተርናሽናል የአትሌቲክስ ፉክክር : 10,000 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jul 06, 2012 10:14 pm    Post subject: Reply with quote

አርብ ሰኔ 29 ቀን 2004 ..

7ኛው ዙር የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር (ቅዱስ ዴኒስ : ፓሪስ (ፈረንሣይ )::

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ዛሬ በፓሪስ ከተማ የቅዱስ ዴኒስ የውድድር ሥፍራ በተደረገው የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር በወንዶች ምድብ 5,000 ሜትር ሩጫ በሎንዶን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሣተፉትን ሯጮች ለመለዬት የሚያበቃ ቅደም -ተከተል የተመዘገበ ይመስላል :: በዛሬው ውድድር ደጀን ገብረመስቀልና ሀጎስ ገብረሕይወት ተከታትለው በመግባት ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ የኔው አላምረው የአራተኛነት ደረጃ አግኝቷል :: ቀነኒሣ በቀለ በእንግሊዛዊው ፋራህ የተመዘገበውን የዓመቱን ፈጣን የተባለውን ባነሠ ጊዜ ቢገባም ያገኘው ደረጃ 9 ነው :: (ምንጭ :- እስካሁን ባላቸው ውጤት መሠረት 5,000 ሜትር ሩጫ የተሻለ ሰዓት ያላቸው በዚህ ውድድር ያላቸውን ደረጃ በተከተለ መንገድ ነው :-) ደጀን : ሀጎስ : የኔው እና ታሪኩ :: ስለዚህ ቀነኒሣ የዛሬ ሣምንት በሚደረገው የሎንዶን ታላቁ የአቪቫ ውድድር የተሻለ ሰዓት ማስመዝገብ ካልቻለ በስተቀረ በሎንዶን ኦሎምፒክ 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድር የምናየው አይመስለኝም :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመስላሉ ::

የወንዶች ምድብ

5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ..... ደጀን ገብረመስቀል ___ 12 ደቂቃ 46.81 ሴኮንድ
2 ..... ሀጎስ ገብረሕይወት ___ 12 ደቂቃ 47.53 ሴኮንድ
4 ..... የኔው አላምረው _____ 12 ደቂቃ 48.77 ሴኮንድ
7 ..... ታሪኩ በቀለ ________ 12 ደቂቃ 54.13 ሴኮንድ
9 ..... ቀነኒሣ በቀለ ________ 12 ደቂቃ 55.79 ሴኮንድ
-- ..... ኢማኒ መርጋ ________ ውድድሩን አላጠናቀቀም

3,000 ሜትር መሠናክል የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
6 ..... ሮባ ጋሪ __________ 8 ደቂቃ 13.65 ሴኮንድ
9 ..... ብርሃን ጌታሁን _____ 8 ደቂቃ 18.63 ሴኮንድ

የሴቶች ምድብ

1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

3 ..... አበባ አረጋዊ _____ 3 ደቂቃ 58.59 ሴኮንድ

3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::
3 ..... ሶፊያ አሰፋ _______ 9 ደቂቃ 29.57 ሴኮንድ
4 ..... ዘምዘም አህመድ ___ 9 ደቂቃ 29.89 ሴኮንድ
6 ..... ሕይወት አያሌው ___ 9 ደቂቃ 30.24 ሴኮንድ
7 ..... እቴነሽ ዲሮ _______ 9 ደቂቃ 36.41 ሴኮንድ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jul 08, 2012 1:57 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

17ኛው ኦሎምፒክ : ሮም (ጣሊያን ) : 1952 .. (... 1960) ::

የሮም ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምበል አበበ ቢቂላ አማካይነት በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችበት ውድድር ነበር :: ሻምበል አበበ 42 .. 195 ሜትር የሚሆነውን ርቀት የሮጠው በባዶ እግሩ ስለነበረና እንዲሁም የውድድሩ መጀመሪያና መጨረሻ ሥፍራ አካባቢ 25 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን የወረረው የፋሽስቱ አምባገነን ሙሶሊኒ ለወታደሮቹ በየጊዜው የክተት አዋጁን የሚያሠማበት አደባባይ ስለነበረ በታሪካዊነቱ ትልቅ ሥፍራ አለው :: ለዚሁ ድል እና በኋላም አጋሩና የአገሩ ልጅ ሻምበል ማሞ ወልዴ 12 ዓመታት በኋላ በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ 3ኛውን የማራቶን ድል ሲያስገኝ ዕውቁ የስፖርት ጋዜጠኛ : የዜማና ግጥም ደራሲ ሟቹ ሰለሞን ተሰማ "ማራቶን ልዕልቷ " የሚለውን ዜማ አበርክቶላቸዋል :: የሰለሞን ተሰማን ዜማ በኢንተርኔት ማግኘት አልቻልኩም :: ቢሆንም ሻምበል አበበ ቢቂላ እንዴት እንዳሸነፈ ከዚህ በፊት ካቀረብኩት የቪዲዮ ፊልም አንዱን ልጋብዛችሁ ::
ምንጭ :- Uploaded by 5cense on Aug 23, 2010. Abebe Bikila wins marathon in 1960 Rome Olympics... barefoot.

በሮም ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት ስፖርተኞች ብዛት 9 ነበር :- አትሌቲክስ 5 እንዲሁም ብስክሌት 4 :: የእኒያን አባላት ሥም : የተወለዱበት ዘመንና ዕድሜያቸው : የተወዳደሩባቸው የስፖርት ዓይነቶች እንዲሁም ያገኙት ደረጃም ሆነ ሜዳሊያ እንደሚከተለው ቀርቧል ::

. .___ ሥም ________ የተወለዱበት ዘመን (ዕድሜ ) _________________________ የተወዳደረበት የስፖርት ዓይነት __ ደረጃ (ሜዳሊያ )
1 ..... ንጉሤ ሮባ ______ ጳጉሜን 5 ቀን 1929 .. (Sep. 10, 1936) (23 ) __________________ 100 ሜትር ሩጫ :: በመጀመሪያ ማጣሪያ 7 (ሜዳሊያ - የለም )
2 ...... ሙሣ ሰይድ ____ መስከረም 22 ቀን 1931 .. (October 2, 1938) (21) _______________ 400 እና 800 ሜትሮች ሩጫ :: __ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ (5 እና 6) (ሜዳሊያ - የለም )
3 ...... ገብሩ መርዓዊ ___ ጳጉሜን 6 ቀን 1924 .. (September 11, 1932) (27) ______________ 5,000 እና 10,000 ሜትሮች ሩጫ :: __ በማጣሪያው 8 : ውድድሩን አልጨረሠም (ሜዳሊያ - የለም )
4 ...... አበበ ቢቂላ ___ ነሐሴ 1 ቀን 1924 . . (August 7, 1932) (28 ) ____________ ማራቶን _______ 1 (2 ሰዓት 15 ደቂቃ 16.2 ሴኮንድ )(የወርቅ ሜዳሊያ )
5 ...... አበበ ዋቅጅራ ____ ጥቅምት 11 ቀን 1913 .. (October 21, 1921) (38 ) _______________ማራቶን _____________ 7 (2 ሰዓት 21 ደቂቃ 9.4 ሴኮንድ ) (ሜዳሊያ - የለም )
6 ...... ገረመው ደንቦባ __ ጥር 6 ቀን 1927 .. (December 15, 1934) (25) ______ የግል ግልቢያ እና 100 . የቡድን ቅብብሎሽ _____________ ውድድሩን አልጨረሠም : 28 (ሜዳሊያ - የለም )
7 ...... ክፍሉ አልአዛር __ ሐምሌ 18 ቀን 1923 .. (July 25, 1931) (29) ______ የግል ግልቢያ እና 100 . የቡድን ቅብብሎሽ _____________ ውድድሩን አልጨረሠም : 28 (ሜዳሊያ - የለም )
8 ...... አሙሤ ተሰማ __ መስከረም 15 ቀን 1924 .. (September 25, 1931)(28 ) ______ የግል ግልቢያ እና 100 .. የቡድን ቅብብሎሽ _____ ውድድሩን አልጨረሠም : 28 (ሜዳሊያ - የለም )
9 .... ንጉሤ መንግሥቱ __ መጋቢት 2 ቀን 1924 .. (March 11, 1932) (28 ) _______ የግል ግልቢያ እና 100 .. የቡድን ቅብብሎሽ ______ ውድድሩን አልጨረሠም : 28 (ሜዳሊያ - የለም )

ምንጮች :-
1 ..... በሮም ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ቡድን የውጤት ሠንጠረዥ ::

2 ..... በሮም ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ብስክሌት ቡድን የውጤት ሠንጠረዥ ::

ይቀጥላል Arrow

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jul 09, 2012 3:52 am    Post subject: Reply with quote

እሑድ ሰኔ 30 ቀን 2004 ..

የሣምንቱ ታላቅ ዜና

20 ቀናት በኋላ በሎንዶን ከተማ (እንግሊዝ ) በሚጀመረው 30ኛው ኦሎምፒያድ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሠለፉት ስፖርተኞች ሥም ዝርዝር ይፋ ሆኗል ::

አትሌቲክስ

400 ሜትር ሩጫ
ወንዶች
:-
በረከት ደስታ

800 ሜትር ሩጫ
ሴቶች
:-
ፋንቱ ሚጌሦ
ወንዶች :- መሐመድ አማን

1,500 ሜትር ሩጫ
ሴቶች
:-
አበባ አረጋዊ : ገንዘቤ ዲባባ እና መሥከረም አሰፋ
ወንዶች :- መኮንን ገብረመድህን : ዳዊት ወልዴ እና ተሾመ ደሬሣ : አማን ወቴ (ተጠባባቂ )

3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ
ሴቶች
:-
ሶፊያ አሰፋ : ሕይወት አያሌው እና እቴነሽ ዲሮ : ዘምዘም አህመድ (ተጠባባቂ )
ወንዶች :- ሮባ ጋሪ : ብርሃኑ ጌታነህ እና ናሆም መሥፍን

5,000 ሜትር ሩጫ
ሴቶች
:-
መሠረት ደፋር : ገለቴ ቡርቃ እና ገነት ያለው : ጥሩነሽ ዲባባ (ተጠባባቂ )
ወንዶች :- ደጀን ገብረመስቀል : ሀጎስ ገብረሕይወት እና የኔው አላምረው

10,000 ሜትር ሩጫ
ሴቶች
:-
ጥሩነሽ ዲባባ : በላይነሽ ኦልጂራ እና ወርቅነሽ ኪዳኔ : አበሩ ከበደ (ተጠባባቂ )
ወንዶች :- ቀነኒሣ በቀለ : ታሪኩ በቀለ እና ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም : ሌሊሣ ደሢሣ (ተጠባባቂ )

ማራቶን
ሴቶች
:-
ጢቂ ገላና : አሠለፈች መርጊያ እና ማሬ ዲባባ : ብዙነሽ በቀለ (ተጠባባቂ )
ወንዶች :- አየለ አብሽሮ : ዲኖ ሠፈር እና ጌቱ ፈለቀ : ታደሰ ቶላ (ተጠባባቂ )

ውኃ ዋና
ሴት
:-
አንድ (ሥም አልተጠቀሰም )
ወንድ :- አንድ (ሥም አልተጠቀሰም )

ቦክስ
ብዛት እና ሥም አልተጠቀስም

ምንጭ :- Markos Berhanu on Jul 8th, 2012. Ethiopia releases athletes list for London Olympics.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jul 10, 2012 10:10 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2004 .. 14ኛው የዓለም የወጣቶች የአትሌቲክስ ፉክክር በእስፓኟ ደቡባዊ ከተማ በባርሤሎና ተጀምሯል :: ውድድሮቹም እስከ መጪው እሑድ ድረስ ይቀጥላሉ :: በዛሬው የመክፈቻ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 10,000 እና 3,000 ሜትር የፍፃሜ የሩጫ ውድድሮች ተካፍለው ነበር ::

በወንዶች ምድብ በተደረገው 10,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር 18 ዓመቱ ይግረም ደመላሽ ለራሱ አዲስ ጥሩ ሰዓት በማስመዝገብ 28 ደቂቃ 16.07 ሴኮንድ በአንደኝነት ፈፅሟል : የአገሩ ልጅ ክንዴ አጣናው 28 ደቂቃ 53.02 ሴኮንድ በመግባት 4 ወጥቷል (ምንጭ :- IAAF) :: የይግረም አጨራራስ አስደናቂ ነበር :- 4 ሯጮች በስተቀረ ሌሎቹን 30 ተወዳዳሪዎች አንዴና ሁለቴ ዙር እያጠፈ ከሁለተኛው ሯጭ 80 ሜትር የማያንስ ርቀት ቀድሞት ጨርሷል :: የልጁ አሯሯጥ ልክ እንደ ኃይሌ ገብረሥላሤ ነው (ፊልሙን እንዳገኘሁ እለጥፋለሁ ):: እንግዲህ እርሱም ተራው ደርሶት ኢብርሒም ጄይላን : ቀነኒሣ በቀለ : ኃይሌ ገብረሥላሤ : አዲስ አበበ እና ሌሎችም በወጣትነታቸው ባሸነፉበት በዚህ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል :: ይህ ልጅ ምናልባትም የወደፊቱ የኢትዮጵያ 10,000 ሜትር ርቀት ሩጫ ተስፋ ይሆናል ብዬ አስባለሁ ::

በሴቶች ምድብ በተደረገው 3,000 ሜትር ርቀት የፍፃሜ የሩጫ ውድድር ሕይወት ገብረኪዳን 9 ደቂቃ 9.27 ሴኮንድ 2 ስትወጣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ሐፍታምነሽ ተስፋይ 4 ሆናለች (እርሷ የገባችበት ሰዓት :- 9 ደቂቃ 10.02 ሴኮንድ ) (ምንጭ :- IAAF):: እኒህ ወጣቶች የራሣቸውን ሰዓት ማሻሻል ችለዋል :: ስለሆነም ለወደፊቱ ልምድ እያገኙ ሲመጡ ጥሩ ለወርቅ ሜዳሊያ ሊሮጡ የሚችሉ አትሌቶች ይወጣቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ከእኒህ ሁለት የፍፃሜ ውድድሮች ሌላ በሴቶች 3,000 ሜትር ርቀት የመሠናክል ሩጫ ውድድር ጠጅነሽ ገቢሣ የዓለም ወጣቶች ፉክክርን የውድድር ሰዓት ሬኮርድ በመሥበር (10 ደቂቃ 1.48 ሴኮንድ ) ከምድቧ በአንደኝነት ለፍፃሜው ውድድር አልፋለች :: ከሌላው ምድብ የአብሥራ ቢተው 5ኛነት አጠናቃ እርሷም ለፍፃሜው ውድድር የሚያበቃትን ሰዓት አስመዝግባለች (የገባችበት ሰዓት 10 ደቂቃ 22.84 ሴኮንድ ) (ምንጭ :- IAAF)::

በዚህ ፉክክር በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቁ ከነበሩት ውድድሮች አንዱ የወንዶች 1,500 ሜትር ሩጫ ነበር :- ምክንያቱም የቃጣሩ ሐምዛ ዲሩች እና ኢትዮጵያዊው ተሾመ ድሪሣ ለበላይነት የሚያደርጉት ፉክክር (ምንጭ :- IAAF, Tuesday, July 10, 2012. Driouch and Dirirsa commence rivalry. ) :: ሐምዛም ሆነ ተሾመ የየምድባቸው አሸናፊዎች ሆነው ለፍፃሜው ውድድር አልፈዋል :: የኔው ጠብቀው ከምድብ ሁለት 2 ሆኖ የፍፃሜው ውድድር ተፎካካሪ ሆኗል (ምንጭ :- IAAF)::

በሴቶች 800 ሜትር የማጣሪያ የሩጫ ውድድር ዱሬቲ ኤዶ ለግማሽ ፍፃሜው ውድድር አልፋለች : ዘይቱና መሐመድ ግን አልተሣካላትም (ምንጭ :- IAAF) ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jul 11, 2012 8:48 pm    Post subject: Reply with quote

ረቡዕ ሐምሌ 4 ቀን 2004 ..

የሁለተኛው ቀን የዓለም የወጣቶች የአትሌቲክስ ፉክክር ውሎ (ባርሤሎና : እስፓኝ )::

ኢትዮጵያውያት ሯጮች የተሣተፉባቸው ውድድሮች ሁለት ብቻ ነበሩ :- የሴቶች 800 ሜትር ርቀት የግማሽ ፍፃሜ እና 5,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ::

800 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ዱሬቲ ኤዶ አልቀናትም :: ከምድቧ ከምድብ 1 የመጨረሻውን ደረጃ (7) በማግኘቷ ለፍፃሜ የሚያበቃትን ሰዓትና ደረጃ ማስመዝገብ አልቻለችም (ምንጭ :- IAAF, 800 Metres - Women Semi-Final.)::

በተቃራኒው 5,000 ሜትር ርቀት ሩጫ የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያት እስከመጨረሻ ለመሸናነፍ ያደረጉት ፍልሚያ ቀላል አልነበረም :: እንዲያውም አሸናፊዋ ቡዙዬ ድሪባ መሆኗ የተለየው በፎቶግራፍ ነበር (ምንጭ :- IAAF, 5000M Women Photo-Finish.) :: ብዙዬ 15 ደቂቃ 32.94 ሴኮንድ አሸናፊ እንዲሁም ሩቲ አጋ 0.01 ሴኮንድ ተቀድማ ሁለተኛ ወጥተዋል (ምንጭ :- IAAF, World Junior Athletics Championships, 5000 Metres - Women's Final.)::

በትላንትናውና በዛሬው ውድድር ብቻ ኢትዮጵያ 2 የወርቅ : እና 2 የብር ሜዳሊያዎች በማግኘት በአንደኝነት ትመራለች (ምንጭ :- IAAF, 14th World Junior Athletics Championships, Barcelona. Medal Tables.):: በጣም ደስ ይላል Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy

አትሌቶቻችን ነገ ሁለት ውድድሮችን ያካሂዳሉ :- የአብሥራ ቢተው እና ጠጅቱ ገቢሣ 3,000 ሜትር ርቀት የመሠናክል ሩጫ የፍፃሜ ውድድር የሚካፈሉ ሲሆን (ምንጭ :- IAAF, World Junior Athletics Championships, 3000 Metres Steeplechase - Women's Final.) ተሾመ ድሪሣ እና የኔው ጠብቀው ደግሞ 1,500 ሜትር ርቀት ሩጫ የፍፃሜ ውድድር ይፎካከራሉ (ምንጭ :- IAAF, World Junior Athletics Championships, 1500 Metres - Men's Final Entry List.) በነገው ዕለት በሚደረጉት ውድድሮች ቢያንስ ሁለት የብር ሜዳሊያዎች አናጣም ብዬ እገምታለሁ ::

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን Exclamation Exclamation Exclamation Exclamation

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 8:57 pm    Post subject: Reply with quote

ሐሙስ ሐምሌ 5 ቀን 2004 ..

የሦሥተኛው ቀን የዓለም የወጣቶች የአትሌቲክስ ፉክክር ውሎ (ባርሤሎና : እስፓኝ )::

ዛሬ አንድ የብር ሜዳሊያ በጠጅነሽ ገቢሣ አማካይነት አግኝተናል (ምንጭ :- IAAF, World Junior Championships - Women's 3000 Metres Steeple Chase Result.):: 1,500 ሜትር ርቀት ሩጫ የተካፈሉት ወንዶች አልቀናቸውም :- የኔው ጠብቀው 8 : ተሾመ ድሪሣ 9 ሆነዋል (ምንጭ :- IAAF, World Juniors Championships - 1,500 Metres Men's Final Results.)::

ነገ አርብ ከሚደረጉት ውድድሮች መካከል ኢትዮጵያውያን በሁለቱ ይካፈላሉ :- በሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የማጣሪያ ሩጫ ውድድር ሠንበሬ ተፈሪ እና ዓለም አምባዬ (ምንጭ :- IAAF, Women's 1,500 Metres Heats - Starting List.) እንዲሁም በወንዶች 800 ሜትር ርቀት የማጣሪያ ሩጫ ውድድር ጄና ዑመር እና ፍቅር በለጠ ለውድድሮቹ የሚቀርቡት ሯጮች ናቸው (ምንጭ :- IAAF, Men's 800 Metres Heats Starting List.)::

እስካሁን ኢትዮጵያ 2 የወርቅ እና 3 የብር ሜዳሊያዎች በአጠቃላይ 5 ሜዳሊያዎች የፉክክሩ 1 ሆና ዘልቃለች ::

ለአትሌቶቻችን መልካም ዕድል እመኝላቸዋለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jul 13, 2012 6:24 pm    Post subject: Reply with quote

አርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004 ..

የአራተኛው ቀን የዓለም የወጣቶች የአትሌቲክስ ፉክክር ውሎ (ባርሤሎና : እስፓኝ )::

በዛሬው የውድድሩ መርኃግብር ኢትዮጵያውያን የተሣተፉባቸው ሦሥቱም የማጣሪያ ውድድሮች ነበሩ ::

ምንጭ :- የወንዶች 3,000 ሜትር ርቀት የመሠናክል ሩጫ የማጣሪያ ውድድር ::
መረሣ ካህሣይ ከምድቡ ከምድብ 1 : 3 ሆኖ ለእሑዱ የፍፃሜ ውድድር አልፏል :: በምድብ 2 ተደልድሎ የነበረው አንሙት ምናሉ በውድድሩ አልተሣተፈም ::

ምንጭ :- የሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የማጣሪያ የሩጫ ውድድር ::
ሠንበሬ ተፈሪ ከምድብ 2 1ኛነት እንዲሁም ዓለም አምባዬ ከምድብ 3 2ኛነት ውድድራቸውን አጠናቅቀው እሑድ ለሚደረገው ለፍፃሜው ውድድር አልፈዋል ::

ምንጭ :- የወንዶች 800 ሜትር ርቀት የማጣሪያ የሩጫ ውድድር ::
በምድብ 3 ተደልድሎ የተወዳደረው ጄና ዑመር 2ኛነት ጨርሶ ለነገው የግማሽ -ፍፃሜ ውድድር ለማለፍ በቅቷል :: በምድብ 5 የተወዳደረው ፍቅር ይበልጣል ግን 400 ሜትር ያህል እየመራ ከሮጠ በኋላ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል ::

ነገ ቅዳሜ በወንዶች 5,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ፀጋዬ መኮንን እና ሙክታር እድሪስ ይወዳደራሉ (ምንጭ :- IAAF, Men's 5000 Metres Final Starting List.) እንዲሁም ከላይ እንደተገለፀው ጄና ዑመር በወንዶች 800 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ይካፈላል ::

ለሁሉም አትሌቶቻችን መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው እመኛለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jul 14, 2012 8:48 pm    Post subject: Reply with quote

ቅዳሜ ሐምሌ 7 ቀን 2004 ..

የአምሥተኛው ቀን የዓለም የወጣቶች የአትሌቲክስ ፉክክር ውሎ (ባርሤሎና : እስፓኝ )::

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

በዛሬው የውድድር ውሎ ኢትዮጵያ በሙክታር እድሪስ አማካይነት አንድ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች :: ሙክታር እድሪስና ፀጋዬ መኮንን በውድድሩ መጀመሪያ ጀምሮ ሲመሩ ቆዩና ከኋላ የኤርትራ : የኬንያና የኡጋንዳ ሯጮች እየተቀያየሩ መምራት ቀጠሉ :: ሆኖም የመጨረሻው ሁለት ዙር ያህል ሲቀር ሙክታር ከቀዳሚ ሯጮች መካከል ሾልኮ ወጥቶ በፍፁም የበላይነት ውድድሩን አሸንፏል :: ፀጋዬ መኮንን 5 ሆኗል ::
ምንጭ :- IAAF, World Junior's Athletics Championships, Men's 5000 Meteres Result.

800 ሜትር የግማሽ -ፍፃሜ የሩጫ ውድድር የተካፈለው ጄና ዑመር ከምድቡ ከምድብ 1 3ኛነት ቢፈፅምም ለፍፃሜው ውድድር ሊያልፍ አልቻለም (ምንጭ :- IAAF, Results of Men's 800 Meteres Semi-finals. ) ::

ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን የሚካፈሉባቸው ውድድሮች ነገ እሑድ መረሣ ካህሣይ 3,000 ሜትር ርቀት የመሠናክል ሩጫ የፍፃሜ ውድድር (ምንጭ :- IAAF, Men's 3,000 Metres Steeple Chase Final Starting List.) እንዲሁም በሴቶች 1,500 ሜትር ርቀት የፍፃሜ የሩጫ ውድድር ሠንበሬ ተፈሪ እና ዓለም አምባዬ ይፎካከራሉ (ምንጭ :- IAAF, Women's 1,500 Mtres Final Starting List.) ::

አስቀድሞ ለመተንበይ ቢከብድም ነገ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ልናገኝ እንችላለን ::

ለሁሉም አትሌቶቻችን መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው እመኛለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 46, 47, 48 ... 53, 54, 55  Next
Page 47 of 55

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia