WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 370, 371, 372 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Sun Jul 22, 2012 1:10 am    Post subject: Reply with quote

ራስ ብሩ , ባለሱቅ , ጎሳ , ሞፊቲ , ሁላችሁንም ላደረጋችሁልኝ መልካም አቀባበል በጣም አመሰግናለሁ ::ወንድሜ ባለሱቅ መልካም የረመዳን ጾም ይሁንልህ ! Gosa Jemjem በተከታታይ የምታጫዉቱን ዉበት ያለዉና ትዝታን ቀስቃሽ ጽሁፎች በጣም ደስ ይላሉ ::ሞፊቲ እንዳልከው ፋታ ሲገኝ መሆኑ ነው : ወንድሜ ጎሳ ! <ዱባን ዱፍቴ ሀዳ ማና ታቴ > ብለህ የተረትካት ከልብ ነው ያሳቀችኝ : እንደው እባክህ -< ኡሞ > ብለህ ስታነሳ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ አንተን አማላጅ ላድርግህ አሰብኩ : ነገሩ እንዲህ ነው , በአንድ ወቅት ሞፊቲን እሱን በአደራ የሆነ እቃ ጎሳ ወስደው እንዲሸጡልኝ ልኬያቸው በቦሬ አካባቢያችን አባባል <ኤቤሌ ጩሊቴ > ወይም < ሎን ቡሌ ቃሪቴ > ይሄው እስከአሁን ዉሾን ያነሳ ! እንደሚባለው ቀልጦ ቀረ ! እና እባክህ አማልደኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Jul 22, 2012 1:16 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ባለሱቅ እንደዚ አይነት ዘፈን ተዘፍኖ እንደነበረ እንኳን አላውቅም በውነት ግጥሙን ሳነብ ዜማው እንዴት ይሆን ብዬ ለማዳመጥ ፈለኩ ::
አንድ ዘፈንን በደንብ የምናዳምጥበት ወቅት ነበር ::
ጥሩ ስፒከር የተገጠመለት ቴፕ ውስጥ የካሴት ክሩ ይጨመርና ጸጥታ ይሰፍናል
ከዛ እያንዳንዷን የዜማ አወራረድ ፒች ሪትም ግጥሞቹን በቃ በጣም በጣም እናዳምጥ ነበር :: ከዛም ትልቅ ርዕስ አድርገን እንነጋገርበታለ :
እነጸጋዬ መርጊያ ለቫኬሽን /መንግሥት ስለምንገናኝ ርዕስ እናነሳና
ስለ ወቅቱ ዘፈኖች ዘርዘር ያሉ ትንታኔዎችን እና መረጃዎችንም እናገኝ ነበር ::
ከሙዚቃ ውጪ ህይወት ያለም አይመስለኝም ነበር ::
በህይወቴ ሁሉ በጣም በፍቅር የምወደውና እንዳንተ አባባል የሙዚቃ .........
የወሰደው ሙሉቀን መለሠ ነው ::
የሙሉቀን ዘፈኖች አሁንም ድረስ ቀልቤን ይቆጣጠሩታል ::
እስከዘመኔ ጥግ ድረስም እወዳቸዋለሁ ::
የጥላሁን ገሠሠ መለያየት ሞት ነው (የድሮው )
እንደውም ይሄውልህ አዳምጠው
የአየለ ማንዶሊን እና የኦርኬስትራው ቤዚስት ለጥላሁን ድምጽ ተስማምተው
እንዴት ውብ ሙዚቃ እንደሚሰሩ በደንብ አዳምጥ ::
እንደዛሬው በኤሌክትሮኒክስ ጫካ ውስጥ ያልተደበቀ ውብ የተፈጥሮ ድምጽና ንጹህ ሙዚቃ
http://www.diretube.com/tilahun-gessesse/meleyayet-motnew-video_9f611c9da.html

አሁንም ስሰማው የልጅነት ስሜት እንደትላንት ሆኖ ነው የሚሰማኝ ::
የአስቴር አወቀን የመጀመሪያ ሁለትና ሶስት ካሴቶች በፍቅር እንወደው ነበር
የመጀመሪያዋ ሙሉ ቅጂ የታተመው በደሳሳ ጎጆ የሚለው ነው ከዛ በፊት ከውብሸት ጋራ ዘፍናለች ::
እምቧይ ኮለል ብላ ሸብሸቦ ነው ልብሱ የማድጋ ውሀ አለቅሳለሁ እንጂ ....................... አቤት አዳምጨ አልጠግባቸውም ነበር ::
የመሀሙድ አህመድ ትዝታዎች የመልካሙ ተበጀ ተወኝ ባክህ
ሙዚቃ ድሮ ቀረ ::
ወቤ (ጃሎ ) በኦሮምኛዬ እንዳትስቅብኝ እንጂ ነገሩ ዱራ ነመኬኒቱፊ ቤኪ .... ኬኒቱኬ ዱራ እንደሚባለው ነው ::
ሞፊቲኮ ያው ዛሬ አለቀልኝ ማለት ነው ታዲያ በአማርኛ አይቻልም ::
ጎሳ እኔ ካንተ ባላውቅም ብትቀጥል ለማንበብ ጉጉ ነኝ
ሆኖም ያቆምክበት ምክንያት በቂ ሆኖ ከተሰማህ መቼስ ማል .....
በሌላ መልኩ እናገኘው ይሆናል ....... ማለቴ መገናኘታችን ስለማይቀር ያኔ ታመጣታለህ ::

ሠላም ሁኑ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Jul 22, 2012 3:23 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ራስብሩአችን የአስቴርን ዘፈን አምጥተህ መጥፎ ትዝታ ቀሰቀስክብኝ :: እንዴት እንደምተኛ አላውቅም :: በተለይ በተለይ
"አለቅሳለሁ እንጂ ባይኔ ሙሉ ሙሉ
ከእንግዲህ አካል ሰው አይገኝም ቢሉ
ወይ እሩቅ አይደለህ አልተሰወርክ ካይኔ
ትዝ ያልከኝ ለምን ነው በህልሜም በውኔ

እኔው ልቃጠለው እንደፈረደብኝ

ምን አንቺ ብቻ እኔንም አቃጠልሺኝ እንጂ አስቱ :: ሀይለኛ ጴንጤ ሁሉ ልሆን ሞክሬ የዘፈን ጉዳይ በጭራሽ ከደሜ ሊወጣ ስላልቻለ ለምን ዝም ብዬ ልልፋ ብዬ ቸርቹንም ተውኩኝ :: አንተ እንዳልከውም እስከወዲያኛውም ቆየት ያሉትን ዜማዎች ከመስማት ወደ ኌላ አልልም :: ኡፍፍፍፍፍፍፍ ::

ወቤ !!!!
Quote:
እንደው እባክህ -< ኡሞ > ብለህ ስታነሳ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ አንተን አማላጅ ላድርግህ አሰብኩ : ነገሩ እንዲህ ነው , በአንድ ወቅት ሞፊቲን እሱን በአደራ የሆነ እቃ ጎሳ ወስደው እንዲሸጡልኝ ልኬያቸው በቦሬ አካባቢያችን አባባል <ኤቤሌ ጩሊቴ > ወይም < ሎን ቡሌ ቃሪቴ > ይሄው እስከአሁን ዉሾን ያነሳ ! እንደሚባለው ቀልጦ ቀረ ! እና እባክህ አማልደኝ ::

መቼም አባቶቻችን ቢሆኑ ለአማላጅነት ተልከው ሰኞን አይጠብቁም ብዬ አንጀቴን አስሬ አንድ ካርድ ገዝቼ ኡሞ ስልክ መታሁ

"ኡሞ የወቤ ጃሎን የአደራ ዕቃ መብላታችሁ በባህላችን ያለ ነገር ነው ወይ ? ልጁ እስካሁን ደም ያለቅሳል እኮ : ኧረ አንድ በሉት "

"ጎሳ : እሱ ደም ያልቅስ : ዕቃውን ተጠቅመው ደም አስመልሷቸው እና ደም አስቀምጧቸው : ስንቶቹ ሆስፒታል ተወስደው ደም ተሰጥቷቸው : ስንቶቹ ደግሞ የገዛ ደማቸውን ቀብሯል መሰለህ :: እኛ እራሳችን በማናውቅበት ምክንያት እስር ቤት ገብተን ደም ተፍተን ነው የወጣነው :: እሱ ገና ብዙ የደም ካሳ አለበት : እባክህን አድራሻውን ስጠኝ "

"እንዴ .....ምን ማለት ነው ? መርዝ ነው እንዴ "በትኑ " ብሎ የሰጣችሁ ?'

"ወንድሜ እሱ መጥቶ ዕቃውን ሲሰጠን እንኳን እኛ አሜሪካኖች እራሳቸው ስለ አንጥራክስ አንድ የሚያውቁት ጉዳይ አልነበረም :: ሽታው ሁሉ እንዳይታወቅ ቤንዚን ቀብቶ አመጣው :: 'ጆንያውን ትንሽ ላምባ ነገር ነክቶት ነው " ብለን በርካሽ ዋጋ ለምስኪን ህዝብ ቸብችበን ህዝባችንን አስጨረስን :: መጥተን 'እርዳን : የሆነ ቦታ ወስደኽን ደብቀን :: በጉዳዩ እየተፈለግን ነው ' ብለን ብንማጸነው " ዮና ማጡ ኪያሌን ኦኮሌ ኦኮሌ ጀዼ ሶቦቆ " ብሎ ተርቶብን የባቱ ኮንስትራክሺን መኪና ከላይ ተሳፍሮ ጠፋ :: ኧረ ምን እሱ ብቻ ሌላም ግፍ አለበት "

"ደግሞ ሌላ ምን አጠፋ ልትለው ነው ?'

"የተሰረቀ የራዶ ሰአት በአንዳንድ ሺህ ብር አመጣላችኌለሁ ብሎ አንዳንድ ሺህ ብር ከኔና ከጸግሼት ተቀብሎን እኛ የጠራ ራዶ ሰአት ስንጠብቅ "የተሻለ ትርፍ ያለበትን ነገር አግኝቼ ይዤላችሁ መጣሁ " ብሎ ከዬት ብቻ እንዳመጣ የዘላለም እንቆቅልሽ የሆነብንን አንዳንድ ኩንታል ቆዳ ጫማ አምጥቶ አራገፈብን :: ታዲያ ያንን ጫማ የገዙት አብዛኛዎቹ ቢያንስ አንዳንድ እግሮቻቸውን ተቆርጧል :: የማይድን ነቀርሳ በትኖብን ሄደ :: አኔም አንድ ቀን ብቻ ጫማውን ላረኩት አሁን ጸሀይዋ ትንሽ ሞቅ ስትል ጥፍሬ ድረስ ያቃጥለኛል :: ዬት እንዳለ ማወቅ አልቻልኩም እንጂ እንደምንም አንድ መረጃ ሰብሳቢ ጥሩ ሳይንቲስት ቀጥሬ ባሸባሪነት ከሰዋለሁ "

ሲለኝ
"ኧረ ተወው በቃ እኔ ራሴ ዬት እንዳለ አላውቅም :: ሁለተኛ ይህንን ጉዳይ አላነሳብህም "
ብዬ አረጋግቼው ለቀሰቀስኩበት መጥፎ ትዝታ ካሳ ይሆነው ዘንድ በቅርቡ ትንሽ ዶላር ልልክለት ቃል ስለገባሁለት አንተም የበኩልህን እንደምትረዳኝ እተማመናለሁ ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Jul 23, 2012 2:47 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ሁሌ እነግርህ የለንም .... ለምንድነው ወደጨረቃ ዞረህ ምትሸናው :: ሁለተኛ ወደጨረቃ ዞረህ አትሽና
> ምች መቶህ እኮ ነው ... ወደ ጨረቃ ዞረህ ስለምትሸና
አይ ምችችችች ለካስ እንደዚህ ነው ሚመታው ወደ -ጨረቃ ዞረው ሲሸኑ ምች ድርግምምምምምምም ያደርጋል አሉ
ሁለተኛ ወደ -ጨረቃ ዞራቹ አትሽኑ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አንተ ብሽቅ ጎሳ .... እስኪ እስከዛሬ ይህንን ሳታነብ ቀርተህ ነው እንዴ ... ከኔ ጋር አሁን ምታወራው
በል በደንብ አንብበኝና እወቀኝና ከዚያ በደንብ ስንተዋወቅ ,,... እንቀደዋለሁ በሰፊው
ያኔ ግን ከምር እነ -ራስብሩ ነበር እኮ እንደዚያ ይጫወቱብን የነበረው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ለነገሩ እሱ ጨፌ ሄዶ ሚያቅ አይመስለኝም .... 01 ልጆች 02ትን ስለሚፈሩ ወደኛ ጨፌ አይመጡም ነበር ለዋና ... እንጂ ቢመጣ ያው አንዱ እንደሚሆን እተማመናለሁ
ገደለኝ

ራስብሩ ወንድሜ ... ቀልቤን ነው የገዛኸው ... እንዲህ እያልክ ፅፈህ
Quote:
ከዛ እያንዳንዷን የዜማ አወራረድ ፒች ሪትም ግጥሞቹን በቃ በጣም በጣም እናዳምጥ ነበር :: ከዛም ትልቅ ርዕስ አድርገን እንነጋገርበታለ :
እነጸጋዬ መርጊያ ለቫኬሽን /መንግሥት ስለምንገናኝ ርዕስ እናነሳና
ስለ ወቅቱ ዘፈኖች ዘርዘር ያሉ ትንታኔዎችን እና መረጃዎችንም እናገኝ ነበር ::
ከሙዚቃ ውጪ ህይወት ያለም አይመስለኝም ነበር ::
በህይወቴ ሁሉ በጣም በፍቅር የምወደውና እንዳንተ አባባል የሙዚቃ .........
የወሰደው ሙሉቀን መለሠ ነው ::
የሙሉቀን ዘፈኖች አሁንም ድረስ ቀልቤን ይቆጣጠሩታል ::
እስከዘመኔ ጥግ ድረስም እወዳቸዋለሁ ::
የጥላሁን ገሠሠ መለያየት ሞት ነው (የድሮው )
እንደውም ይሄውልህ አዳምጠው
የአየለ ማንዶሊን እና የኦርኬስትራው ቤዚስት ለጥላሁን ድምጽ ተስማምተው
እንዴት ውብ ሙዚቃ እንደሚሰሩ በደንብ አዳምጥ ::
እንደዛሬው በኤሌክትሮኒክስ ጫካ ውስጥ ያልተደበቀ ውብ የተፈጥሮ ድምጽና ንጹህ ሙዚቃ

ዋውውውው በጣም ትክክለኛ አባባል ነው ያልከው ከምር

እኔ ግን እንዳንተ የሚዚቃ ክብረ -ንፅህ የነበረኝ አይመስለኝም .... ማዘር ሆድ ውስጥ ሳለሁ ሁሉ ሙዚቃ እየሰማሁ እራገጥ እንደነበር ትዝ ይለኛል ...
ቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሲሉ ነው የሰማሁት
......................//........................
ሞፍቲሻ
አቤት ፈልፍለህ አወጣኸኝ አይደል ....
ተደብቄ እኖራለሁ ስል ... እንዲህ ባደባባይ በጥላሁን ሙዚቃ ታጋልጠኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ናቹ ያገሬ ልጆች
በጣም ቢዚ ሆኛለሁ አቦ ... ሰሞኑን

እስኪ ጊዜ ሳገኝ ብቅ እላለሁ

ጎሲና ግን ወደ -ኃላ እየሄድክ የልጅነት እኔነቴን እንደገና እያመጣህ አታስጎምጀኝ አቦ
በጣም ነው ምቀናበት በሱ ልጅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1336

PostPosted: Mon Jul 23, 2012 7:25 pm    Post subject: Reply with quote

አኒኬራ ለዚህ ቤት ባላባቶች ...አንድ ጥያቄ ነበረኝ

ደርግ ከመውደቁ በፊት የሲዳሞ ወረዳ አስተዳዳሪ ማን ይባሉ ነበር ... ለማወቅ ፈልጌ ነበር
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Jul 23, 2012 8:22 pm    Post subject: Reply with quote

ገልብጤ እንደጻፈ(ች)ው:
አኒኬራ ለዚህ ቤት ባላባቶች ...አንድ ጥያቄ ነበረኝ

ደርግ ከመውደቁ በፊት የሲዳሞ ወረዳ አስተዳዳሪ ማን ይባሉ ነበር ... ለማወቅ ፈልጌ ነበር

ሰላም ገልብጤ :-
ጥያቄህ አምታታኝ ::ምክንያቱም የሲዳሞ ወረዳ የሚባል ሰምቼ አላውቅም ::
ሲዳማ አውራጃ
ወይም ሲዳሞ ክፍለሀገር የሚባል ነበር ::
ምናልባት የሲዳሞ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ ማን ነበሩ ለማለት ፈልገህ ከሆነ አሁን በናይሮቢ ከተማ በስደት የሚኖሩት
ተፈራ እንዳለ እንደነበሩ አስታውሳለሁ ::
ካልተመለሰልህ በድጋሚ እንገናኝ ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1336

PostPosted: Mon Jul 23, 2012 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ምናልባት የሲዳሞ ክፍለሀገር አስተዳዳሪ ማን ነበሩ ለማለት ፈልገህ ከሆነ

አዎ ለማለት የፈለኩት ክፍለሀገር ነበር ...ጥያቄው የተመለሰ አይመስለኝም ..ወሬው የተነሳው እንዲሁ በጨዋታ ላይ እያለን ነበር እናም ዋርካ ላይ የክብረመንግስት ልጆች ያውቃሉ ብዬ ነበር ጥያቅዬን ወደዚህ ያመጣሁት ...መኮንን የሚባል ነው አስታዳዳሪ የነበረው ነው የሚሉኝ ሰወች

አመሰግናለሁ ለመልስህ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Tue Jul 24, 2012 11:47 am    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
አኔኪራ ገልብጤ
ጥያቄው የክፍለሀገሩ አስተዳደር ከሆነ ከተፈራ እንዳለ በኍላ አስተዳዳሪ የሆነ ሰው ያለ አይመስለኝም አስተዳዳሪው ታመው እንደነበረ ትዝ ይለኛል ቢሆንም ጊዜው አልቆ ስለነበር ከዛ በኍላ አስተዳዳሪ ለመሾም የሚያስችል ጊዜ የነበረ አይመስለኝም ::
መኮንን ዶሪንም (ፊታውራሪ ) አስውሻቸዋለሁ እሳቸው የደቡብ አካባቢ ሰው ቢሆኑም ማዕረጋቸው በሚኒስትር ደረጃ ስለሆነ እሱም መልስ አይሆንም ::
ማታ ጥያቄውን አንብቤ የመኮንን ያለህ ብል ምንም መልስ አጣሁ :: ክብረመንግሥት ግን አቶ ተሾመ መኮንን የሚባሉ አስተዳዳሪ ነበሩ ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jul 26, 2012 2:46 pm    Post subject: Reply with quote

ገልብጤ ወዳጄ
Quote:
ደርግ ከመውደቁ በፊት የሲዳሞ ወረዳ አስተዳዳሪ ማን ይባሉ ነበር ... ለማወቅ ፈልጌ ነበር

አዪዪ ይህንን ጥያቄ ድሮ ብታቀርበው አሪፍ ነበር መሰለህ

ራስብሩ ካልመለሰልህ
ወይ አደቆርሳ .. ወይም አንፈራራ
ወይንም ደሞ ወልደ /ስራኤል
ቢኖሩ ኖሮ
የአስተዳዳሪውን ስማቸውን ብቻ ሳይሆን
የሚነዷትን መኪና ቀለም .... የጫማቸውን ቁጥር ... የሚወዱትን ነገር
እረ ከፈለክ ከሀረጋቸው ከመሰናበታቸው በፊት ለመጨረሻ ጊዜ
የበሉትን የቁርስ አይነት
የተጫሙትን ጫማ ቀለም
እረ ቡታንታቸውን ሳይቀር ይነግሩህ ነበር
ከረፈደ መጣህ ነው ሚባለው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
....................

ጎሲና አንተ ውድ ልጅ
አየኸው አይደል ጀምጀምን በቡካት ከመድረክ እንዳባረርኩት ... እና አንገቱን እንዳስደፋሁት

አንዲት ነገር ቢተነፍስ ... እኔም ዝክዝክክክክ አድርጌ ማወራው ብዙ ነበረኝ
አስኮናኝ በልልኝ ልጅ ጀምጀምን
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አይ ጀምጀም .. ለዚቹ ነው ሁሉ ድንፋታ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በተረፈ አንድ አሳዛኝ ዜና አለኝ

ዜና እረፍት

ሰኞ እለት ... በሞዛምቢክ አውራ -ጎዳና
እኔ ካሜራዬ እና 400 ዶላሬ ወደ -ባንክ ስንጓዝ
በተፈጠረ አደጋ
ካሜራዬና 400 ዶላሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል

የአደጋው መንሴ ባይታወቅም የሞዛምቢክ ቆፍጣና ፖሊሶች ኪስ -አውላቂዎች (pick Pocketing) ያደረሱት አደጋ እንደሆነ በአይናቸው በብረቱ እንዳዩ በመሰከሩ ሰዎች አማካኝነት አረጋግጠዋል

ያዩ ሰዎች አደጋውን ለማዳን .. አደጋ አድራጊዎቹ በኃላ የሚያደርሱትን ጥፋት በመፍራት ... ዝም ብለው የአደጋውን ቲያትሩን በማየት መናናትን እንደመረጡ ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል

ያቺ የግል ... ምን አይነት እድል ናው ያላት ባካቹ
ጠፍቼ ጠፍቼ ... ልልክላት ስሄድ ነው አደጋው የደረሰው

እሱስ ጦሱን ይውሰድ ... ጊዜው ስለደረሰ እና አምላክም ሰማይ ቤት ጥሩ ቦታ ስላኖረለት ይሆናል
ግን 16GB ዳታ ይዞ ለአደጋ እራሱን ያጋለጠው ካሜራዬ
ትንሽ እንኳን ለኔ አያዝልንኝም >?
የልጆቼን የስራዬን የትዝታዬን ፎቶግራፎች ሁሉ ይዞ እኮ ነው
ካንተ ጋር መኖር ሰለቸኝ ብሎ .. ለአደጋ እራሱን ያጋለጠው
ህምምምምምምምምምምምምምምምምምም
ከእንዲህ ያለ አደጋ አምላክ ይሰውራቹ

ለሞቱትም መጥፅናናትን
ላሉትም አዲስ ካሜራ ይስጥልን እያልን
እንሰናበታቹዋለን

መልካም ረመዳን ለሙስሊም ወንድሞቼ
ትግላችን ይቀጥላል
ወያኔን እናርበደብደዋለን ... ሽንቱን መቆጣጠር እስኪያቅተው
ውይ ለካስ ኦሬዲ አቅቶታል ... ሽንታምምምም
ምስኪንንንንን ወያኔ

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jul 26, 2012 5:27 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አንተ ብሽቅ ጎሳ .... እስኪ እስከዛሬ ይህንን ሳታነብ ቀርተህ ነው እንዴ ... ከኔ ጋር አሁን ምታወራው
በል በደንብ አንብበኝና እወቀኝና ከዚያ በደንብ ስንተዋወቅ

ቅቅቅቅቅቅ እኔማ ድሮ ልጅ በነበርክበት በጣሊያን ጊዜም ጨዋ ስለመሰልከኝ እንጂ ይህንን ታሪክህን አስቀድሜ ባነብ ኖሮ ስምህንም አልጠራም ነበር ::

እኔ የምልህ ባለሱቃችን : ግን ሰርቀውህ ነው ወይስ ዘርፈውክ ነው ? ካሜራውን መቼም ከጅህ ሳይነጥቁህ አልቀሩም :: ዶላሮቹ ግን አጠፋፋቸው አንተ እንደምታስበው ላይሆን ይችላል ':: እነኚያ ዶላሮች ወይ አልተዘረዘሩ : ወይ ከሌሎች ዶላሮች ጋር አልተቀላቀሉ ኪስህ ውስጥ ብቻቸውን ለዘመናት ታፍነው በመክረማቸው ፍትህ ፍለጋ ያመለጡ ነው የሚመስለኝ :: እነኚያ "ኪስ -አውላቂዎች " የመሰሉህ "የዶላር ነጻ አውጭ ግንባር አባላት " ሳይሆኑ አይቀርም ::

ጀምጀምማ መዝገቡን አስሰረቅክበት መሰለኝ በዚያው ጸጥ አለ ':: እኔ ደግሞ ልቀዳው ተዘጋጅቼ ነበር ::እሱ ያንተን ብዙ ነገር ቢያወራ እንኳ : አንተ ግን አደራ ስለ እሱ ምንም አትተንፍስ : የካሜራውን አርባ እስክታወጣ ድረስ :: ቅቅቅቅ

በል ባለሱቃችን ዛሬ ኪስህን የገቡ ሰዎች ነገ ለቡታንታህም ስለማይመለሱ ....
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Jul 26, 2012 8:49 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ቅቅቅቅቅቅቅ ...... ወይ ባለሱቅ ወይ ባለሱቅ .....በጠራራ ሰአት አነጠፉህ ......
ወይኔ ወንድሜን ! ከሁሉም የገረመኝ በየግል ማማረርህ ነው ::
ደግሞም ቂል መሆንህ ነው እንጂ ሞዛምቢክ የሚገኘው ሱማሌ ተራ ወይም ምን አለሽ ተራ ወይም ........
ብታፈላልግ ትንሽ ሳንቲም ከፍለህ ዳታውንም ቢሆን ታገኘው ነበር ::

ጎሳ = መልእክት ልኬልሀለው ::እንዲህ እራስህን እስክትስት ድረስ ለምን ትተኛለህ ? ደጋግሜ ደውዬልህ ነበር ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Thu Jul 26, 2012 9:16 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ባክህ ተነስ እንውጣ ረፈደኮ ?
ቆይ በናትሽ ባለሱቅን እግዜር ያጥናህ ልበለው
ወይ በስማም ምነው ምን ሆነ ?
አነበብኩላትትት
ታዲያ ምን እግዜር ያጥናህ ትለዋለህ እግዜር ይስጥህ በለው እንጂ !!
ማን እንደሆነች አልነግርህምምም
ደህና ዋሉ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 27, 2012 7:23 am    Post subject: Reply with quote

ታዘብኳቹ
ምን አይነት ልጆች ናቹ
እናዋጣልህ ነው እንጂ ሚባለው .... ዶላሮቹ እንደ -ሙስሊም ኢትዮጵያን ፍትህ ፍለጋ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነው በዚያው ያመለጡ ናቸው ይለኛል እንዴ
ይሄ ጣፋጭ ጎሳ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሞፍቲሻ እና ራስብሩ እንዲሁም የማላቅሽ ትላንትና ከራስብሩ ጋር አብረሽ ወደ -ከተማ የወጣሽው ልጅ
ስላስተዛዘናቹኝ በጣም ነው ማመሰግነው

ሞፍቲሻ በየግል ላይ ያሳበብኩት እኮ ወድጄ አይደለም
ሲፈጥረኝ ዶላር በኪሴ ይዤ ወጥቼ አላውቅም
ሲያቀብጠኝ ... ከሰላማዊ አገሬ እንደመላክ ... ከዚሁ ልላክላት ብዬ
ዶላሩን በካሜራው ኪስ ውስጥ ከትቼ (መደበቄ እኮ ነው ... በኔ ቤት ... ዲንቄም አለች ሌቦ )
እናላቹ ...ባንክ ከመድረሴ በፊት ካሜራዬን ሲመነትፉኝ ... ዶላሩ እንዳለ ማወቃቸውን እጠራጠራለሁ
ካሜራውን ብቻ ወስደው ቦርሳዋን ከጣሏት .... የሞዛምቢክ አፈር በላት 400ዶላሬን
ዋይ ዋይ ዋይ ሚባለው ያኔ ነው ....
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
የታባቱ ለኛ አላለውም

በይ እያንዳንድሽ አንዳን ጣል አድርጊ
ሀዘን ቤት ተደርሶ ማስተሳዘኛ ... ምፅ ብሎ ከንፈር ብቻ መጦ መሄድ ነውር ነው

ጣል ጣል
ምን ታየኛለህ .... ቆመህ
ጣል ጣል .. አድርጉ እንጂ

አይ ጊዜ ... አለ የመለስ መንፈስ
ያኔ በየጫካውና በየጥሻው ... ሱካር ልሰን ... ሀረግ አጭሰን ... ዘለን ቦርቀን ... አሸንፈን .... ይህንን 80ሚሊዮን ህዝብ ቀጥቅጠን እንዳልገዛን ....
ነፍሳችን በዚች ትረታ !
ሁሉ ያጠራቀምነው ሀብት ... የገነባነው ዝና ...አሁን ምን ሊሆን ነው
ኤዲያ
ህይወት ከንቱ ... አለ ሰለሞን

ሰላም ሁኑ .. ቦጠሊቃ አታናግሩን እየነካካቹ

ጣል ጣል አድርጉ እስኪ

ጣል ጣል
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Fri Jul 27, 2012 2:12 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ለቤታቸን ይሁን ...........................
ሀይ ባለሱቃቸን ስላም ነው Question.............ምን ስላም አለ በለኝ የልጆቼን $400.00 አዘርፈህብኝኝ ጉድ እኮ ነው ...................... በል እንግዲህ ካሜራውን እኔ ገዝቼ ልክልሀለው አንት ግን ያቺን ..................
$400.00 ላክልኝ እሺ ቅቅቅቅቅ ከምሪ ነው የምልህ እንደገና አጠራቅምና ላካት ........የግል በልጆቻ ቀልድ አታቅም ..........................ድሮ ድሮ ............ ደጉስው ነበር በአንተና በራሱ ስም ለልጆቹ የሚልከው አሁን ግንን እሱም የወሀ ሽታ ሆናል እና እንግዲህ ራስህን ቸለህ ላክ ...

ስለ ደረስብህ የመዘረፈ አደጋ ..........አዝናለው ........................... Rolling Eyes Rolling Eyes

መልካም ስንበት
ከብዙ መውደድድድ ጋር
የግልልልል
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jul 28, 2012 8:50 am    Post subject: Reply with quote

አቤት ዘመድ ማለት እንደዚህ ነው
የግልዬ ምናባቴ ላርግሽ
በጣምምም አመሰግናለሁ
እናም
ባንድ አፍ ብያለሁ
ስለዚህ
Quote:
በል እንግዲህ ካሜራውን እኔ ገዝቼ ልክልሀለው አንት ግን ያቺን ..................

ባልሽው መሰረት
ለምን እንደዚህ አናደርግም
አንቺ የምትገዢልኝን የካሜራ ዋጋ ጠይቂና (መቸም ባለ -አንድ ዶላሩን Use and throw ካሜራ እንደማትገዢልኝ ልቤ ነግሮኛል )
ዋጋውን ካወቅሽ በኃላ .... እኔ ካሜራውን እዚህ ልግዛ ... እና ልዩነቱን ልላክልሽ (400 ከበለጠ ልዩነቱን አንቺ ነሽ ምትልኪው ማለት ነው )
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ምን ይመስልሻል

አሪፍ ሸቃይ አይደለሁም (ለዚያውም የቦታጀራው )
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ለሀሳብሽ ግን እጅግ በጣም አመሰግናለሁ
እምምጷ ግንባርሽ ላይ

ሰላማዊ የሆነ አገር ስደርስ ዱብ አደርግልሻለሁ

አብሽር
በተረፈ ...
ሰላም ሁኑልንንንን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 370, 371, 372 ... 381, 382, 383  Next
Page 371 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia