WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ማርቆሶች ተሰብሰቡ
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Sat Jun 16, 2012 2:27 pm    Post subject: ማርቆሶች ተሰብሰቡ Reply with quote

እዚህ ላይ እስኪ ማርቆስ 1975 ጀምሮ የነበራችሁ ተስብሰቡና እናውራ .

በተልይም የድብዛውን ትምህርታችንን እንወያየው .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Tue Jul 24, 2012 5:55 pm    Post subject: Reply with quote

75 ትንሽ ራቅ አለ .... ፍሬንዴ ...
እስኪ 80ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ማዉራት የሚችል ካለ ጎራ ይበል ....

አሁን ኪነ ጥበቡን እየመሩት ካሉት የነ በዉቀት ስዩም ዘመን .... ሚዲያዉን እነ ኤልሳቤጥ እና አበባየዉ የአዲስ አድማሷ .... የነሱ ዘመነ ሰዎች አላችሁ ? አሪፍ አሪፍ ትዝታዎች ይኖሩናል .... ድብዛን ጨምሮ Wink ... ከአብማ ጠላ .... እስከ ሸዋ በር መናፈሻ .... ከኪዳነ ምህረት ..... እስከ የኮቼ የሚዳቋ አደን (እነ ዉቃዉ የከተማ ልጆች ስለ ሚዷቋ አደን ሲወራ ትልቅ ጀብድ ይመስላችሁ ይሆናል ) .... ከዉትርን እስከ ዉሰታና አባይም የዋና እና የዉሀ እናት አደን ለቺኮች ,,,, ... ,,, አቦ .... ገጠር እንደማደግ ጣፋጭ ነገር ይኖር ይሆን ? Wink
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Tue Jul 24, 2012 7:51 pm    Post subject: Reply with quote

በል እሽ የሆኑ ነገሮችን ጠቁመሀል ግን ወጣት ስትሆን አትቀርም ሆኖም ግን ከጠቀስካቸው ውስጥ በእውቀቱን በቅርብ አዲስ አበባ ሎምባርድያ አግንቸው ምሳ ነገር ሞክረናል ይሁን እንጂ ትንሽ ወጣትነት አያጣችሁም ለመሆኑ እስኪ ገጠር ያልከው እስክየት ነው ?

የሸዋብሩ ጠላ ብዙም አይደለም እንዲያውም አብማም ጠፍቷል :
እኛ የነበርነው ዮሀንስ የድብዛ ዳይሬክተር በነበረብት ጊዘኤ ነው :
እስኪ ብዙ ሳልቀባጥር መግቢያ ነገር ስጠኝ :

ከቺኮችም ብትጠቅስልኝ ሳላውቅ አልቀርም

እኔን ያስተማሩኝ

እነ ጌቸው አበሹ
እነ አለማየሁ እንግሊዘኛ ዝቅ ብለው ደግሞ እነ

ደሳለኝ አስፋው በል አንተም የበኩልህን በል

የምፈራው መጨረሻ አንድ ብልህእኛል እንዳትለኝ ነው

ሁሉ አልፏል ባስቀይምህም እርሳው :

ብዙ ሳልናገር እስኪ ለዚህ መልስ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Wed Jul 25, 2012 9:03 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለማ 12
አዎ የማስታዉሳቸዉን መምህራን ነዉ የጠቀስከዉ .... ድብዛ 2 አመታት ተምሪያለሁ 85/86 በኛ ዘመን አቆጣጠር .... ለቫኬሽን ግን ብዙ ክረምቶችን አያቶቼ አሳልፊያለሁ .... ከኔ ዘመን ሰዎች አሁን በትንሹም ቢሆን ወደ ሚዲያዉ የገቡትን ነዉ የጠቀስኩልህ .... እንጂ በየቢሮዉ ትላልቅ ደረጃ የደረሱ ብዙዎቻችንም አባቶች ሁነናል .....ከበዉቄ አንድ ባች ነን .... ... አባቱን ታስታዉሳቸዉ ይሆን ? እንግሊዝኛ መምህር ጋሽ ስዩም ? በጣም ቀልደኛ ነገር ነበሩ Wink

ጌታቸዉ አብሾ .... ኬሚስትሪ አስተማሪ .... አሁንም አለ አያቶቼ ስሄድ አይቸዋለሁ ... ደሳለኝ አስፋዉ እንግሊዝኛ መምህሩ ይሆን ? .... ሁሌም በከረባት ሽክ የሚል በኢህአፓ ሰበብ የተደበደበና የዛ ዉጤትም ወደ ሲጋራዉና ቅምቀማዉ ዘዉ ብሎ ያስገባዉ ግን ጂኒየስ ይመስላል ....

እኔ ስማር ርዕሰ መምህር የነበረዉ አቶ አስራት ነዉ (ስሙን ያልረሳሁት ቆንጆ ቆንጆ ሴት ልጆች ነበሩት እነ መለሰች አስራት እና ትንሿ ስሟን አላስታዉሰዉም Wink ) .... ... ከርዕሰ መምህሩ በላይ ዘበኞች ይፈሩ የነበረ ይመስለኛል .... መንግስቴ ... አበበ ምናምን አይነት ስም ያላቸዉ ...

ከማስታዉሳቸዉ መምህራን .... ጋሽ ምንላርግህ ... ሀሀሀ ... ስሙ ራሱ ደስ የሚል ነዉ ባህሪዉም ከሌሎች መምህራን ለየት ይላል ..... የሱ ወንድ ልጁ አንድ ክፍል ቢቀድመኝም ጓደኞች ነበርን አሁንም ነን ... ደረጀ ምንላርግህ የኒዉ አቢሲኒያ ኮሌጅ ሼር ሆልደር ነዉ ሙሉ የሙዚቃ አልበም እንደሰራ አዉቃለሁ ነጠላ ዜማዉን እንደቀለቀቀም እንዲሁ .... ሙሉዉንም አልበም ምናልባትም ጀባ ይለን ይሆናል ... ...

ገጠር የምትለው የቱን ነዉ ላልከኝ ....
11 የደብረማርቆስ ቀበሌዎች ዳር ዳር ያሉትን .... ቀቢ ለአስተርዮ ማርያም ሄጃለሁ ..... የቦ ሾላ ለመልቀም .... ወንቃ ጎተራዉን ለማየት Wink የኮቼ ዳሊጋዉ ለሚዳቋ አደን ... እንድማጣ በሩቁ ነዉ ማዉቀዉ ... እናም በስቴዲየሙ በኩል ያሉ እነ አራት መከራከር Wink ..... አይበቃህም እንዴ ?

ለማ ...
የእዉነቴን ነዉ ማወራህ .... ብዙ ቦታዎችን አይቻለሁ ኑሪያለሁም (ከሀገር ዉጭም ሀገር ዉስጥ ያሉ ትላልቅ ከተሞችም ) ... .... እንደ ማርቆስ የምወደዉ ከተማ የለም ... በነገርህ ላይ እድሜዉን ከሰጠኝ የጡረታ ጊዜዬን የማሳልፈዉ እዛዉ ነዉ የሚሆነዉ .... ከወዲሁ አሪፍ ቪላ ሰርቻለሁ :: ቂቂቂ ... አጠቃላይ ወጭዉን ብነግርህ ትስቃለህ Laughing .... ከአዲስ አበባ ስታስተያየዉ በጣም ትንሽ
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Wed Jul 25, 2012 1:05 pm    Post subject: Reply with quote

ሰው ?

ሰላም

አዎ ሰወችንም ነገሮችንም ነካካሀቸው

ምላርግህ ሽፈራው አስተምሮሀል ????? ቅቅቅቅቅ

አቶ አስራት በኔ ጊዤ ምክትል ርሰመምህር ነበር

አሁን ግን እሱ ሞቷል የሚገርመው አባቱ አሉ

የጋሽ አስራት አባት አቶ አድማሴን ታውቃቸው አለህ ?

አንድ ጊዜ ቀብለ 4 ማለትም እነሱ ሰፈር አንድ ልጅ ራሱን ሰቅሎ ሞተና ሲመርቁ

የሳቸው ትንሹ ልጅ በጣም ረባሽ ስለነበር ምን አሉ መሰለህ ?

በጣም ነው የሚያሳዝነው ጎብዝ ልጅ ነበር አሉና እንግዲያማ የኔ ልጅ ይቺን ይሞክራታል እዚህም ድረስ ወንድ ነት ብለው ልቅሶኛውን አስቀዋል

እነም እንደአንተ ማርቆስን በጣም ነው የምወደው የጥራሀውን ገጸር ሁሉ አውቀዋለሁ በተልይ 4 መከራክር የሚባለውን ሄጀ አይቸዋለሁ በጣም ደስ ይላል

አዎ ደሳለኝ አስፋው እኔን አስተምሮኛል ግን በኢሀፓ ተደብድቦ በጨ እንደማለት ብሏል በጣም ፈኒ ነው

ያስተምሩን የነበሩ በሙሉም ባይሆን አሉ ግን በጣም ተጎሳቁለውል

ጌታቸው አበሹ በጣም የምወደው አስተማሪዬ ነበር ምሽቱ ሞታበታለች አሁን :

አላገኝሁትም

እኛ እንጫወት የነበረው ከን ሄለን ሰሎሞን : ከነ ሙሉጎጃም ........

ያያስራት ልጆች መልከ መልካም ቢሆኑም ለጥብስ አልደረሱም ነበር :
የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲወሰታ ትምህርት ቤት አጠገብ ነው የተሰራው ብዙም የሚያስደስት አይደለም

ማርቆስ ቡና ቤት ፈርሶ እየተሰራ ነው ማን እንደሚሰራው አላውቅም

ጨሞጋ የሚሉት ትምህርት ቤት ነበር ከከተማ ልጆች ጋር ድብድብ ነበር አይ ጊዜ በጣም ነው ትዝ የሚልርኝ

ማርቆስ 11ዱን ቀበሌ በደብ ከማወቄም በላይ ሳልባልግበት ያለፍኩት ያለ አይመስለኝም :

አንድ ጊዜ ከአበባው አላምረው ጋርክርክር ገጥሜ የሳቁት ትዝ ይለኛል

መንግስቴ የሚባለው ዘበኛ በጣም ይፈራኝና ይወደኝ ነበር አሁን ወያኔ ሆኖ የቀበሌ ተመራጭ ነው

አንተ አልደርሰክባቸው ይሆናል አባ ቸኮል የሚባሉ ዘበኛችን ነበሩ ድብዛ በጣም ቀልደኛ ነበሩ በተልይ ቺኮችን ሲፎግሮ ያስቁኝ ነበር :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Wed Jul 25, 2012 1:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሀሀሀሀ .... አቶ አድማሴ የተናገሩት በሳቅ ገደለኝ .... ከነ አክሰንታቸዉ የሰማሁት ነዉ የመሰለኝ ...

እስኪ ስለ ቺኮች ,,,, ያዉ እኔ መፈጠሬን ከሚያስወድዱኝ የአምላክ ፍጥርታት .... አንዳኔ የአምላክ ምርጥ ስጦታዎችም እንደሆኑ ይሰማኛልና እስኪ ወጋችንን በነሱ ላሟሸዉ .... ... ማርቆስ እኔም እንዳንተ ሁሉንም ቀበሌ አዳርሻለሁ ..... ለቺክ ብዬ ተካንቻለሁ Wink

ሄለን ሰለሞን ..... ማርቆስ 2 ሄለን ሰለሞኖችን አዉቃለሁ ... አንዷ ኤርትራዊ የጦርነቱ ጊዜ ከነቤተሰቦቿ እንደሄደች ሰምቻለሁ ፍቅር አስጨራሽ ስትማር አንድ ሁለቴ ሸኝቻታለሁ Laughing .... ሁለተኛዋን ግን በአካል አላዉቃትም .... ስለዉበቷ በጣም የሚወራላት .... ማርቆስን በዉበቷ መአዛ ያወደች .... ብዙዎቹ የሰገዱላት ነበረች ሲባል እሰማለሁ .... ያኔ ኢሮፕ እንደምትኖርም ታናሽ እህቷ ሰናይት ሰለሞን በኩራት አጫዉታኛለች (ስለነ ሰኒ ግሩፕ ካወካቸዉ በሰፊዉ እንቀዳለን ) .... ወንድሜ የነ ሰኒ ወንድማቸዉ አንዱ ዘፋኝ ነዉ .... ካሴት ምናምን አዉጥቷል ሲባል ሰምቻለሁ ..... አንዱን ግን አዉቀዋለሁ ስፖርተኛ ነገር ... ስሙ ካልተሳሳትኩ ታዲዎስ ? .... አዎ ፊቱን ግን እስከመቸዉም አልረሳዉም ከሲኒማ ቤቱ ጀርባ ከእህቱ ስቀድ አይቶን ማጅራቴን አንጠልጥሎ አይኑን ያጉረጠረጠብኝን አልረሳዉም .... ሰኒን ባለፈዉ አመት ይመስለኛል ሂልተን አዲስ ተገናኝተናል ... በመከራ ነዉ ያስታወሰችኝ

ሙሉጎጃም ? .... ይሄ ስም በብዛት አለ ጎጃም ዉስጥ አንተ የምትላት ኤፍሬም ታምሩ የዘፈነላት ነች ? ቂቂቂ ስቀልድ ነዉ ....
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Wed Jul 25, 2012 7:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም
እባክህ ያገሬን ትዝታ አታስነሳብኝ .

አዎ ሄለን አንተ የሸኘሀት ሳትሆን ሁሉንም ያሰግድችው ባሪያ ናት የጥበበ ሰሎምን እህት :: በል ተወው ይህን ገባ ብዬ ካወራሁ ብዙው ሰዉ ስለሚያውቀኝ እንግደልህ ነው የሚሉኝ የድሮው ጉልበቴ የለ : ቅቅቅ

ሙሉጎጃም ያልኩህ ብዙ ናቸው ግን የትኛዋን ላውጋህ በተልይ ሙሉጎጃም የመረብ ካስ ለመጫወት ትሞክር ነበር ይህን ስልህ ዋናዋን የመረብ ካስ ተጫዋች ማለቴ አይደለም ውንዋን ደሳለኝ አስፋው ያደረጋትን ልንገርህ

በጣም ስለምትኮራ ደግሞ ተማሪ ላወጣ ነው እያለች ስትፈክር እነ ዮሴፍ ደሳለኝ አስገድደው ስኒማ ቤቱ ውስጥ እንዲያመጣላቸው አድርገው የፈጸሙባት ግፍ ይህ ነው አይባልም ፊልም ማየት ትወድ ነበር :
እጨለማ ቤት አስገብቶ አስረከባቸው : ከዚያ የሆነውን መገመት ትችላለህ :

እን ወይዝሪት ሰኒን አውቃቸዋለሁ ግን ብዙም አልጠጋቸውም ነበር አንዱ ዘሎ ተነክሮ ስለነበረ ነው :

የወይዝሮ ማርታ ልጆችም ነበሩ እረ ስንቱ ................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 9:35 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለማ 12
እትዬ ማርታ ያልካቸዉን አላወኳቸዉም ...

ጋሽ ምንላርግህን ያስተማረህ ይመስለኛል . ... በመልካም ከማስታዉሳቸዉ መምህራኖቼ አንዱ ነዉ .... ትንሽ ወጣ ያለ ባህሪ ነበረዉ .... 9 ክፍል እንግሊዝኛ አስተምሮኛል ቂቂቂ ለዛ ነዉ እንግሊዝኛ በጣም ጎበዝ የሆንኩት Laughing ... ከምር ግን ጥሩ እንግሊዝኛ ተናጋሪ እንድንሆን ፍላጎቱ አሁንም ድረስ ይገርመኛል .... አልተጠቀምንበትም ....

ስለሱ ከማስታዉሰዉ ,,,
1992 በተካሄደዉ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ የግል ተወዳዳሪ ነበር .... ምልክቱም ጀበና Laughing እንዳሁኑ ሳይሆን ያኔ በኢህአዴግ ተቃዋሚነት ተወዳዳሪ ያልነበረን ጎረምሶች ነበርንና በግሩፕ በተማሪ ሀቅማችን ከአዲስ አበባ /ማርቆስ ድረስ ሄደን ጋሽ ምንላድርግህ እንዲመረጥ ሎቢ እናደርግ ነበር ,,, ... ,,, ዉጤቱ ጥሩ አልነበረም ... ብዙም ሳይቆይ እንዳረፈ ሰማሁኝ ... በጣም ነበር ያዘንኩት

9 ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ወቅት እንግሊዝኛ አስተምሮኛል .... ያዉ ቅምቀማ ላይ በጣም ይታማ ነበርና .... የእንግሊዝኛ ቃላት እየሰጠ አረፍተ ነገር ስሩ ይለናል ... ... ዲፊካልት በሚለዉ ቃል አረፍተ ነገር ስሩ ... የሚል ነገር እንደነብረዉ አስታዉሳለሁ .... በፍጥነት ሰርቼ ቁጭ እንዳልኩኝ ጨረስክ ? አዎ ቲቸር .... እሽ አንብበዉ .... ድሪንኪንግ አልኮሆል ኢዝ ዲፊካልት አልኩኝ .... ተማሪዉ በሳቅ ወደቀ .... ካሽ ምንሌም ... ተዉንጂ ጎበዝ ትንሽ ትንሽማ ምንም አይልም አለ ሌላ ሳቅ .... ኤኒዌይ በጣም የሚመቸኝ አስተማሪ ነበር ...

ትንሽ ስለ ከተማዉ ወጣቶች ....

የዛ አካባቢ ወጣት ሲበዛ ጀብደኛ ነዉ ልበል ? Wink ይሄ ጀብደኝነት ሌላ አካባቢ በመጥፎ የሚነሳ ነዉ .... በግሩፕ መደባደብ ... በግሩፕ ሴት ማዉጣት .... ምናምን ብዙም አስነዋሪ አልነበረም .... አሁን እንኳን እንደዛ አይመስለኝም .... ከላይ ሲኒማ ቤት ዉስጥ ያደረጋችሁትን ስታወራ እዉነትነቱን ምንም አልተጠርጠርኩም Wink ... ቂቂቂ ደብረማርቆስ ሲኒማ ቤት .... ጨለማ ቤቷንም አስታወስኩኝ .... አንዴ ጩጬ እያለሁ ክረምት ለማሳለፍ ሄጄ ... የሆነ አሪፍ ፊልም ማስታወቂያዉ ተለጥፎ አየሁ ... እናም መግቢያዉ 1 ብር ነዉ :: ቂቂቂ አያቶቼን 1 ብር ለፊልም ስል .... ቂቂቂ .... አቤት የጮሁት .... አንደኛ የብሩ ብዛት .... ቂቂቂ .... ሁለተኛ ለፊልም ? የዱሩዬነት መገለጫ ነዋ Wink ..... ሌላ ጊዜ ሳለቅስ እናቱ ናፍቃዉ ነዉ ምናምን ተብሎ የምፈልገዉ ነገር ይደረግ ነበር ያኔ ግን ተዉት ያልቅስ .... ምን አይኑ ዳር ቤት አልተሰራ Laughing ...

እኔ ያንቺ ወንድም ታዲያ ያኔም የምፈልገዉን ነገር ከማድረግ ወደ ሗላ ማለት መሸነፍ ነዉ ሚመስለኝና ሄጄ ፊልም መግባት እፈልጋለሁ ብር ግን የለኝም አልኳቸዉ .... አስፈራርተዉ ሊያባርሩኝ ፈለጉ .... ቂቂቂ ንቅንቅ አላልኩም ... .... የፈለጋችሁትን የጉልበት ስራ እሰራለሁ ... አዳራሹንም አጸዳለሁ ... ወንበር አስተካክላለሁ ምናምን ብዬ ድርቅ ስል ..... ሁኔታዬ ግርም ብሏቸዉ በል እሽ ግባና አጽዳ ተባልኩ .... ቂቂቂ አጸዳሁ Wink እንደዉም የአቀማመጥ ስትራቴጂ ሁሉ ቀይሼ እንዲህ ብታደርጉት አሪፍ ነዉ ... አንዱ አንዱን አይከልልም አይነት ምክር ቂቂቂ ምናልባት 10 ወይንም 11 እድሜ ላይ ብሆን ነዉ .... ሙሉ ክረምቱን በነጻ Wink ... ችግሩ አንድ ፊልም በተደጋጋሚ 1 ወር ሊታይ ይችላል

እስኪ ሁሌም ስለማስታዉሰዉ አደን ትንሽ ቆይቼ እቀዳለሁ ...
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 1:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነው ?

አዎ የሚያስቅ ነው ያደረከው ወሮ ማርታን ያልከኝ ማርታ ሀይሌ ቡና ቤት ማለቴ ነበር እንልፈው ለጊዜው

አንድ ጊዜ ያደረግነውን ልንገርህ 3ኛው ክፈለ ጊዜ እስፖርት ነበረን ከዚያም ወጥተን ወደ እስፖርት ስንሄድ እሽንት ቤቱ ዝንድ ስንደርስ ዘመን አደምን ማለትም ያባ አደምን ልጅ አገኘነው እኔም ጥጋበኛ ስለነበርኩ አሁን እግርህን ወደላይ እራስህን ወደታች አድርጌ ሽንት ቤት ሳልከትህ ብር አምጣ አልኩት ቅቅቅቅቅ የሀብታም ልጅ ነውና : እሱም ሳያቅማማ ያለውን 10 ብር ሰጠን በኛ ጊዜ ይህ በጣም ብዙ ነው ያነን ይዘን እስፖርት ቆየንና በዚያው ወደጠላ ቤት መረሽን በሙሉ ሴቶችንም ጨምረን ቅቅቅቅ ስንቀመቅም ውለን በመጨረሻ ማለትም 6ኛው ክፍለ ጊዜ ተሰልፈን አንዲቱን በእንስራ ጠላ አሸክመን ገባን 6ኝውም ክፍለ ጊዜ እርሻ ነበረንና መምህሩም መስፍን በጉ ነው የሚባለው ይዘን እንድይከሰን አንገራገርነውና ዝም አስባልነው : ቅቅቅቅቅቅ
ይህ አልበቃ ብሎን ሲደወል ሰንደቅ አላማ የምናወርድ እኛ ነን ብለን ተሰለፍን : አንዱ ሰንደቅ አላማውን ሊአወርድ ሲሞክር እሱስ ወደላይ ነው የሚስበው : ቅቅቅቅ ... ዘምረን ስንጨርስ ሰንደቅ አላማው እዚያው ነው እናም ተማሪው ሳቀብን ረሰ መምህሩ አሰፋ ስለሽ ይባል ነበር አሁን ምንም ችግር የለም ነገ እንነጋገራለን ብሎ ዝም አለን : ቅቅቅቅቅ .
እኛም ተማሪዉን እየመራን መሀል ከተማ ድረስ እየለፈልፍን ቀጠል እስከ እንስራው ጠላ ጨምሮ :
ቅቅቅቅቅ ....

በነጋው የጠበቀንን መለስ ብዬ አጫውትህ አለሁ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
-...-

ኮትኳች

Joined: 09 Feb 2012
Posts: 313

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 6:54 pm    Post subject: Reply with quote

ከየቦ ማርያም አካባቢም ሰላም ብለናችሁ አለን ለማለት ያህል ነው
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 8:51 pm    Post subject: Reply with quote

-...- እንደጻፈ(ች)ው:
ከየቦ ማርያም አካባቢም ሰላም ብለናችሁ አለን ለማለት ያህል ነው

ሀሀሀ ሰርጎ ገብ አለመሆንህን ለማረጋገጥ እስኪ የየቦ ጎረቤቶችን ዘርዝርልን ... Wink

ለማ 12

በሳቅ ነዉ የገደልከኝ .... ታየኝ ' ጠላ በእንስራ አሸክማችሁ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ .... ለዛ ' ነዉ የዛ አካባቢ ወጣት ጀብደኛ ነዉ ያልኩት ... ... በተለይ ከነበርኩበት ቦታ ሳስተያየዉ ብዙ ይሚገርሙኝ ነገሮች አሉ ...

ትንሽ ስለ አደን
መጀመሪያ የመሳሪያ ድምጽና ተኩስ ሰምቼ የተለማመድኩት ሰንተራን አልፈህ ያሉ የአያቴ ገባሮች .... ገባርነታቸዉን አሁንም ድረስ መተዉ የማይፈልጉ ክፍሎች (አማራ አምራን ያስገብር ነበር ብል በብሄር ደረጃ ተበደልን የሚሉ ምን ይሉ ይሆን ? Wink እነዚህ የዋህ ሰዎች አሁንም ድረስ በህይወት ያሉት የዛ ትዉልድ ሰዎች ሴት አያቴ በህይወት ስላለች እሸት እየተሸከሙ ይመጣሉ ብል ማን ያምነኝ ይሆን ? አምላክ የተመሰገነ ይሁን መሆን ያለብኝን ያክል ሁኘላቸዋለሁ ) ... ,,, ... እድሜየ 10 ሳይደርስ ይመስለኛል .... ለዛዉም አብዛኛዉን መንገድ በእግሬ እንድጓዝ ተደርጌ .... የቆመ ኢላማ ተሰጥቶች ተኮስኩ ... ከድምጹ የመሳሪያዉ እርግጫ ሀሀሀ (መሳሪያዉ አልቤን ነበር ) .... ለአደን ወደ አባሊባኖስ ምናምን ስሄድ ነዉ አጭር ሚኒሽር የታጠኩት .... ያኔ ተጀመረ ...

በጣም የምውደዉ አደን ግን ... ደብረ ማርቆስ ከተማዉ ዉስጥ ካሉ የእድሜ እኩዮቼ ... ሀይለኛ የሚባሉ የሰፈር ዉሾችን ይዘን ዉትርንን ተሻግረን በምኞትና በጀብድ ረሀብ ወደ ዳሊጋዉ ጫካ .... የካምፕ ልጆችን ካልፈራን ደግሞ 15 ሻለቃ (ስለነሱ ልጆች የዋርካዉ ሾተል የሆነ ነገር ይለን ይሆናል Wink ሚስጥር አወጣሁ ይሆን ? ) ጀርባ ካለዉ ጫካ ዉስጥ ወይንም ወርቅነህ የማነ ጫካ (ከማርቆስ ጸበል አካባቢ ) .... ሚዳቋ ... ጥንቸል ... ካገኘን አራዉጠን ይዘን እየጨፈርን ወደ ሰፈራችን የምንሄደው ... ካመለጠችን ዉሻዎቻችንን እየገረፍንና እየተርገምን የምንመለሰዉ ... .... ለምንድን ነበረ የማይርበን ? ምናልባት ጠሗት 3 ሰዐት ላይ የሄድን አደናችን ካልተሳካ እስከ ምሽቱ 2 ሰዐትም ልናምሽ እንችላለን .... ያዉ ክረምት እንደምሄድ ነገሪያችሗለሁ አይደል ? ቂቂቂ ዉትርን ከሞላብንም መሻገር አንችልም እዛዉ ከጅብ ተፋጠን ማደር ....

ቆቅም እናጠምድ ነበር .... ዋዉ ወጥመድ አጠማመድ በራሱ ሳይንስ ነበረዉ ቂቂቅ ... የአንገቷ ማስገቢያ ነገር አዘጋጅተን ጥሬ እንበትናለን ... እሱን ለመልቀም አንገቷን ስታሰግ ነዉ የምትንጠልጠለዉ ... ..
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀሪከን 2

ዋና ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2008
Posts: 721

PostPosted: Fri Aug 03, 2012 3:34 am    Post subject: Reply with quote

አንች ሰውየ ግን ግርማ የሚሉት ልጅ ወይስ ዴኒልሰን ትሆኝ ይሆን Laughing
ጽንፈኝነትን አጥብቀን እንቃወማለን Laughing
_________________
each mind is a different world
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Fri Aug 03, 2012 6:04 am    Post subject: Reply with quote

ሀሪከን 2 እንደጻፈ(ች)ው:
አንች ሰውየ ግን ግርማ የሚሉት ልጅ ወይስ ዴኒልሰን ትሆኝ ይሆን Laughing
ጽንፈኝነትን አጥብቀን እንቃወማለን Laughing

ሀሀሀሀ ... ሀሪክ ሌባዉ ... Wink እግዚአብሄርን አንድ ሁለት ሙከራ ብትሞክር ጋማ ትለኛለህ Wink

ግርማ ከበደ (ሶቅራትስ ) UNHCR አሶሳ ሰራተኛ ነዉ ... ... እንደበፊቱ እንዳይመስልህ ... ሀሀሀ እሱን አይደለሁም .... ግን በጣም በጣም ግዋደኛዬ

ዴኒልሰን (ዝናቡ Wink የምናዉቀዉ ዝናዉ አሁን የለም ... ከሳምንት በፊት ተገናኝተን ነበር ሁለተኛ ድግሪዉን እየሰራ ነዉ ) ,,, .... በነገርሽ ላይ ሁለቱም ደብረ ማርቆስ የቀበሌ 6 ልጆች ናቸዉ Wink

እዛኛዉ ቤት 11 እና 12 ያልሽዉ ተሳስተሻል ወይንም ተሳስቻለሁ ... ሁሉንም ሲርየስሊ አትዉሰጅዉ Wink

አመዳም ነገር ነህ .... ይሄ ምኑ ነዉ ጽንፈኝነት ? ... ደግሞ እዛኛዉ ቤት የአዲስ አበባ ልጅ ምናምን ያልከዉ ከየታባክ አምጥተህ ነዉ ? ማርያምን የአዲስ አበባ ልጅ አይደለሁም Laughing ... አለመሆኔም ያጣሁት ነገር ምናልባት በከተማ አዉቶብስ እየተመላለሱ አለመማር ወይንም ሜዳ አጥተዉ አስፋልት ዳር ኳስ መጫወት .... .... ቂቂቂ እስኪ አስበዉ .... የአዲስ አበባ ልጆች በክረምት ዳጥ ያድጣሉ ? Wink ..እንቆቆ ... አጋም .. ቀጋ ...ለቀማ ወደ ጫካ ይሄዳሉ ? ... ሽመለ ቀንድዮሽ ይጫወታሉ ? .... በአንዳዉላና በደባይ ጦርነት ይገጥማሉ ? Wink ....
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...

Last edited by ሙዝ1 on Fri Aug 03, 2012 9:20 am; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለማ 12

ኮትኳች

Joined: 16 Jun 2012
Posts: 471

PostPosted: Fri Aug 03, 2012 7:05 am    Post subject: Reply with quote

[/u]ሰላም የቤቱ ታዳሚዎ

እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ አለ ዘመዳችሁ በሉ ተሰብሰቡ :

አንተ የየቦው እስኪ ስለ ጋሽ መኮነን ዘበናይ ትንሽ ንገረን :

በሉ የጋሽ አሰፋን ታሪክ ልጨርስልችሁ
በነጋው የጥዋት ተማሪዎች ነበርንና ብዥታው ለቆን ስለአደረ በስነ ስራቱ ተሰልፈን ሳለ ሰንደቅ አላማው ተከብሮ ሲያልቅ መጣና በሉ እናንተ ትንበርከኩ አለን እአም እኛም ያደረግነውን ስለምናውቅ ተንበረከክን : ቅቅቅቅቅ
እሱም በያዘው ዱላ ( ወባይ ) እየተከተለ ይደውለን ጀመር እንድይደርስብን ስንፈጥን ቀደም ይልና ዝግ በሉ እያለ ይወርድብናል ዝግ ስንል ደግሞ ፈጠን በሉ እያለ ይወርድብናል : ቅቅቅቅቅ
እስከ 2 ክፍለ ጊዜ ወደክፍል ስንገባ የለበስነው ዩኒፎርም ከጥቅም ውጪ ሆኖ ቁጭ አለ እኛም ገብተን አንማርም ብለን አሻፈረን አልን መምህሩ ሊከሰን ሲል በሩን አስገብተን ዘጋንበት ይህ መምህር አሁን አሜሪካ ነው ያለው : ቅቅቅቅቅ ...

አሁን ግን ስብስባችሁ ስለአስፈራኝ ብዙ ከመናገር ላቆም ነው :
ይዚህን ርእሰመምህር ግፍ በሚቀጥለው እጨምራለሁ በጣም ግፈኛ ነበር : ቅቅቅቅ እኛም ጥጋበኞች ነበርን
የሚቀጥለውን ጠብቁ :...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሙዝ 1

ዋና አለቃ

Joined: 22 Feb 2006
Posts: 2614

PostPosted: Fri Aug 10, 2012 5:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለማ .... በሰላም ነዉ የጠፋኸዉ ?

የያኔዋን ማርቆስ ሳስብ ምን ትዝ አለኝ መሰለህ ? ፎቶ ቤቶቿ .... ቂቂቂ ሁሉም በአንድ መስመር ላይ ይገኛሉ ... ከፖሊስ ጣቢያዉ እስከ በግ ገበያዉ .... ...
ማርስ .... ሙሉአለም ... ሀይሌ .... በየነ አምዴ .... የሁሉም ፍቶዎች ስቱዱዮዉ ተመሳሳይ ነዉ ..... የሆነች መደገፊያ ያላት ወንበር .... ከወንበሯ ፊት ልፊት በትንሽዬ ጠረጴዛ አርቲፊሻል አበባ ... .... አርቲፊሻል የሴት ጸጉር .... መነጽር (የሳይትም ሊሆን ይችላል ..... ብቻ የሆነ ሰዉ ትጠቅሞ የጣለዉ መሆን አለበት ) ..... ክብ ማርልቦሮ ቆብ (ለምንድን ነበር ማርልቦሮ የተባለዉ ?) ... በመጋረጃ የሚጋረድ የግድግዳ ስዕል ..... ጉርድ ፎቶ ለመታወቂያ አይነት ነገር ሲሆን መጋረጃዉ ይዘጋል .... በተረፈ ያች የጀርብ ዛፍ የበዛባት ጀማሪ ሰዐሊ የሳላት የግድግድ ስዕል ትከፈታለች

እነዚህ ፎቶ ቤቶች ሳስታዉስ ሁሌም ተመልካች አለማጣታቸዉ ግርም ይለኛል .... ቂቂቂ .... አንዳንድ ሰፈሮች እንደዉም ለቅምቀማ ያልደረሱ ጉብሎች (ልጆች ) ከመዝናኛ ፕሮግራሞቻቸዉ አንዱ ከተማ ሄዶ ፎቶ ማየት ሳይሆን ይቀራል ? .... ብዙ ጊዜ ፎቶዎች አይቀየሩም ... ሰርግ ምናምን ካልነበረ .... ያም ሆኖ ዛሬም ነገም እነዛን ፎቶዎች መመልከት አንዱ የመዝናኛ አካል ነዉ ::

አዲስ ሸራ ጫማ በቁምጣ የለበሰ ፍንዳታ .... ሳስበዉ ፎቶ ሲነሳ ዋናዉ ታርጌቱ አብዛኛዉ የእድሜ እኩዮች ፎቶ የማየት ልምድ እንዳላቸዉ ስለሚያቅ አዲሷን ሸራ ጫማ እንቁልልጭ ለማለት ይመስለኛል ... ቂቂቂ ፎቶ አነሳሱ የማርልቦሮዉን ቆብ አድርጎ .... አበባዉን በእጁ ይዞ ትንሽ በርከክ .... የጥቅሻ ያክል የምትታይ ግማሽ ፈገግታ .... የፎቶቤቱን መነጽር በቄንጥ ሰክቶ .... ሌላዋ ደግሞ ትናንሽ የቤተሰቦቿን አባላት ይዛ እሷ ከመሀል ... ሌሎቹ ከጎን ተግተልትለዉ ..... አንዳንዶቹ ሆያ ሆዬ ብለዉ ባጠራቀሙት ፍራንክ .... ከጨርቅ የተሰራችዉን ኳስ በረኛዉ ወይንም የሰፈሩ ጉልቤ ይዞ ይጋደምና ሌሎች በሁለት ረድፍ ተደርድረዉ ...

ሰርግ ከነበረ ደግሞ ከሙሽሪት ቤት እስከ የራባ ,,,, ከዛ ሙሽራዉ ቤት ድረስ ያሉ ፎቶዎች ልክ እንደ ኤግዚቢሽን ለህዝብ ክፍት ይሆናሉ Laughing .... እነ ሀሪከን ታዲያ እየተመላለሱ አንድ ሳምንት የፎቶዉ ቀለም እስከሚል አፍጥጠዉ ይዉላሉ
_________________
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4  Next
Page 1 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia