WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ስለ ሀገራችን ከተሞች እንወያይ
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 17, 18, 19  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጋርቢቲ

ኮትኳች

Joined: 06 May 2004
Posts: 179

PostPosted: Wed Mar 02, 2005 12:21 pm    Post subject: ሞኒካ Reply with quote

እግዜር ይይልሽ በንዴት አንዱን መልክት ሁለቴ ፖስት አስደረግሽኝ አይደል ? Smile Smile Smile :: እንዴት አድርገሽ ይቅርታ እንደምትጠይቂኝ ሳስበው እኔ ላንቺ ደከመኝ ::

ጋርቢቲ ነኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Mar 02, 2005 12:21 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ የዚህ አምድ ተከታታዮች እንደተለመደው ዛሬ
ዋድላና ደላንታ ወረኢሉ ካቤ
የጠጁ የጮማው አይጠፋም ከልቤ
እንዲሁም
እንዴነው ቦረና የነስበር ሀገር
ቲጠሉ ነው እንጂ ሲወዱ ገራገር
ወደተባለላቸው የወሎ ግማሽ አካል ጉዞየን ተዴሴ ለመቀጠል ስንቄን ቆጣጥሬ ለሊትን ተገን በማድረግ ከሰኞ ገባያ ጀመርኩ ትንሽ አለፍ ብየ ተበሽታ ፈዋሽ ነው ተብሎ ሚታመንበትን የሸህ አሊ ጂሩ ቢለንን ዉሀ በቁሜ ለቅለቅ ብየበት ጉዞየን ቀጠልኩ . ዉድ የሆነችው ካቤ ከተማ ማምሻው ላይ ነበር የደረስኩት .
የግሩ መንገድ አድክሞኝ ስለነበር ገብጋባ አትበሉኝና ሆቴል 1.50 ከፍየ መደቡዋ ላይ ጋደም ብየ ለሊይቱን አሳለፍኩ . በነገታው ቀኑ የሳምንቱ እሮብ ትለነበር እንዳገሬው በጡዋት ተነስቼ ቁንጣየን አጥልቄ ከላይ ጋቢየን ጣል አድርጌ . ጎፈሬየን ሞሸጥኩኝና ሪጋየን (መፋቂያ ) አንስቸ ተሙዋሙጨ ጉዞየን ወደገበያው አመራሁ . እዛም እንደደረስኩ የያዝኩዋትን ሻሂ (ስኩዋር ) በጣሳ እየሰፈርኩ ታጠናቀኩ በሁዋላ ባተረፍኩዋት ፍራንካ አንዲት አነስ ያለች የፍየል ግልገል ቢጤ ገዝቼ እንደሰው ጉዞየን ወደማማ ደመቁ ጠጅ ቤት አመራሁ . ገና ተበሩ እንደደረስኩ የያዝኩዋትን ፍየል ተበር ላይ ታለው እንጨት ሸብ አድርጌ ወደዉስጥ ገባሁ . ዉስጥ የነበረው ጨዋታና ድልቂያ ገና ፉት ታልል ነበር ያደመቀኝ ውነትም የጠጁ እያልኩ በል እንካ እየተባባልን ጨዋታ ተጀመረ ጠጅ ቤቱን እንደጨረቃ በንጉርጉሮዋቸው ያበሩት አዝማሪውች ሰውን እየተቀበሉ ማዘማቸውን ይዘውታል . ተራው የኔ ደርሶ በይ እኮ ተከተይ አልኩዋት
እንዸምነው ዴሴ
እንዴምነው ዴሴ
አይጠገብዋን
አይጠገብዋን
እንዴነው ደረባ
እንዴነው ደረባ
አዪጠገብዋ
አይጠገብዋ
ሰዉ ተናፋቂ
ሰው ተናፋቂ
ጥሪያቸው አይዋ
ጥሪያቸው አይዋ
ባካባቢው የነበረው ሰው ድልቂያውን (ጭፈራውን ) ተያያዘው የኔን ዜማ ቲያዳምጡኝ የነበሩት እማማ ደመቁ ተደስተው በይ እኮ ለዪህ ለወጣት አንድ ቅጂለት አሉዋት . ምንም እንኩዋን ሀገሩ በጨዋታው በጮማውና በጠጁ ቢታወቅም ፍራንካ አላከስርም ብዬ 1ብር ሺሮ በልቸ ነበር ጠጁዋን የተያያዝኩዋት . እንደው ገና ወደ 4ኛዋ ትሸጋገር እራሴን እንደዉጋት ቢጤ ቢጀምረኝም ቀጠልኩበት . ሰዉ ሁሉ የልብ የልቡን በዜማ ፍርድ ቤት ዪመስል ቲያንጎራጉር ቆይቶ ወደ ማምሻዋ ላይ እኔም ሞቅ ብሎኝ ወደማደሪያየ ትወጣ መቸም አንዳንድ ሸረኛ አይጠፋም ግልገለን እሱዋኑ በመሰለ ዉሻ ቀዪረው ወስደውብኛል እኔ ደግሞ እንደው እንደስካር ቢጤ ይዞኝ ይህን አላስተዋልኩም እንደው ፈትቸ ጉዞየን ቀጠልኩ መሀል መንገድ ላይ እያለ ቲጮህ ስሰማ እረ ተይ አንቺ ፍየል አታስቂኝ ብየ ወደሁዋላ ዘዎር እላለሁ ነገሩዋ ተለውጣለች . ለላ ምን አደርጋለሁ እንዲሁ ጉድ እያልኩ ወደ ማደሪያየ ህእድኩ .

ዉድ ታዳሚዎች ባሁኑ ፕሮግራም የካቤዎችን ባህል በተለይ የሚታወቁበትን የጠጅ ቤት እንጉርጉሮ ለመቃኘት ሞክሪያለሁ ይበልጥ የሚያቃት ካለ ደግሞ ሰፋ አድርጎ ቢነግረን እላለሁ

ይመቻቺሁ
አክባሪያችሁ
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Wed Mar 02, 2005 5:18 pm    Post subject: Re: ጋርቢቲ ዛሬስ ይቅር አትይኝም Reply with quote

ያስብላል ከእሁድ ለት ጨዋታችን በህዋላ ጋርቢቲንና ጋቢናን እያምታታሁኝ :: Embarassed Embarassed
የኔ ቆንጆ እረ ማሪኝ በናትሽ ዛሬስ ምንም excuse የለኝም !!!
ጋቢና ይሄንን ቢያነብ ይቺ ልጅ ከኔ ፍቅር ይዟታል ነው የሚለው Laughing
ይድፋኝኝኝኝኝኝኝ ሙች ከምሬ ነው !!!
ምን ነካኝ ግን ??????
ይቅርታ የኔ ቆንጆ እወድሻለሁ እሽ
አክባሪሽ
ሞኒካ
ጋርቢቲ እንደጻፈ(ች)ው:
አይይይይይይይ ሞኒክ ...... አሁንስ ማጣላታችን ነው :!! እኔን አታምታቺኝ ስልሽ ጭራሽ ባደባባይ ... "ደስ የሚል ቀልድ ነው ሙት "......"ግን የቱጋ እንዳትለኝ " ትይኛለሽ : እኔ ሴት ነኝኝኝኝኝ Evil or Very Mad Evil or Very Mad Evil or Very Mad ... ... ጋቢና ምናምን እያልሽ በፈጠረሽ አትደበላልቂኝ እሺ ::

እህትሽ ጋርቢቲ ነኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 03, 2005 3:10 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዉድ የዚህ አምድ ተከታታዮች
እኖሆ ዛሬ አቶ ይመር ቦሩን ለማግኘት ያላደረኩት ጥረት የለኝም አጋጣሚ ነገር ሆኖ ዴሴ እሮቢት ገበያ ላይ በቀሎ ቲያሰፍሩ ነበር ያገኘሁዋቸው እነም ቀደም አድርጌ
ፈልጌ አስፈልጌ ያንሰሞን ያጣሆት
አቶ ይመር ቦሩ ገበያ አገኘሆት
ብየ ሰላምታየን ጀመርኩ እሳቸውም ያሀገራችን ሰው እንደምታውቁት ከደሙ ንጹህ ነው ይሄ ጉዋያ ነው ጌይ የምትሉት ነገር አያገኛቸውም እንደው አንገቴ ስር ጥምጥም ብለው አዙዋዙረው ሳሙኝ . እኔን በማየታቸው በጣም ነበር ደስ ያላቸው የሆነ ሆኖ በቅርቡ ነበር አሉ ከስርቤት የወጡት ምን ሳጋጥሞሁ ነው ትላቸው እሳቸውም እዪህ ከተመው ፊት ሚነገር አይደለም ባይሆን ተሰአት በሁዋላ እዚያው እጎጆየ ብለውኝ ተለያየን . አይደርስ የለምና ሰአቱ ደርሶ እኔም ያቶ ይመር ቦሩን ጨዋታ ለናንተ ለማቅረብ ጉዞየን ወደ ቦሩ ለመጀመር ከሆጤ ሰፈር ታክሲ በመያዝ መናፈሻ ላይ ጋሪ በመቀየር ታያያዝኩት ሰአቱ ጠራራ ቢሆንም ያፋቸውን ጥፍጥና እያጣጣምኩን ከዚያው ደረስኩኝ . እኔን በመጠበቅ ላይ የነበሩት አቶ ይመር ባለጋርውን ታሰናበቱ በሁዋላ ወደበታቸው እየመሩ ተታዝያው (ፎቅ ) ላይ አስቀመጡኝ . ከዚያም በዚያ በሚያምር ድምጻቸው ብርቄ በይኮ ነይ እንግዳው መቱዋል አሉዋት . እሱዋም ደግ አለች . እሳቸውም እንደው ብታይ እንዴት ያለች ሚስት አግብቻለሁ ብታይ ደግሞ የወርቅ ጥርስ አላት ዘወር በማለት አንቺ ብርቄ ነስቲ ሳቂለት ብለው የባስ ገደሉኝ . ወይዘሮ ብርቄም ሰላምታቸውን በማስቀደም የዘንጋዳ እንጀራ የያዘውን ማዳቸውን ከፊታችን አቀረቡት የዛን ቀን የበላሁት ምግብ የትም ኦታ ቀምሸው አላውቅም . ምን እናንተ ከተሜዎች ቡስታ ሞርካኒ ( pasta n makaroni) እያላቺሁ ይህን አትወዱ እያሉ ባፍ ባፌ እየለጠቁ (እያከታተሉ ) ታበሉኝ በሁዋላ መቸም ያለቡና አይሆንም እኮ ብርቄ ወደማሳቀጫው አሉዋት

ይቀጥላል
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጋርቢቲ

ኮትኳች

Joined: 06 May 2004
Posts: 179

PostPosted: Fri Mar 04, 2005 10:54 am    Post subject: ለሞኒክ Reply with quote

APPOLOGY ACCEPTED !! አይድገምሽ እንጂ !! Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy

እህትሽ ጋርቢቲ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Fri Mar 04, 2005 11:15 am    Post subject: Re: ለጋርቢቲዬ Reply with quote

አመስግናለሁ ይቅር ስላልሽኝ ሁለተኛ አይለምደኝም የኔ ቆንጆ ::
አክባሪሽ
ሞኒካ
ጋርቢቲ እንደጻፈ(ች)ው:
APPOLOGY ACCEPTED !! አይድገምሽ እንጂ !! Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy

እህትሽ ጋርቢቲ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Fri Mar 04, 2005 11:17 am    Post subject: ለቅማል Reply with quote

ስላም ያገርልጅ
ይሄ ጨዋታህ በጣም ደስ ይሚል ነው እና መጨረሻውን እየጠበቅኩኝ ነው አደራ ቶሎ ተመልስህ ጨረስልን ::

አክባሪህ
ሞኒካ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Mar 04, 2005 2:41 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ የሀገር ልጆች እንደምን ከርማችሁዋል
እነሆ ዛሬ ከዴሴ ከተማ ሰባት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከቦሩ ከተማ ካቶ ይመር ቤት እገኛለሁ . ምሳው ተበልቶ ጊዜው የቡና በመሆኑ ለጀበናው ከተሰጠው ክብር አኩዋያ ጀበናው ወደታዝያው ስለማይወጣ እኛ በምትኩ ከታዛው ወረድን . አቤት ባህል ማስደሰቱ ይባል አቶ ይመርም በጆሮየ ጠጋ በማለት ቡናው ስኒው ላይ እስተሚቀዳ ድረስ ወግ አይወጋም ብለው ባህላችን ነው አሉኝ እኔም ደግ ብየ ተመደቡ ላይ እተነጠፈው አጎዛ (የፍየል ቆዳ ) ቁጭ አልኩኝ ወይዘሮ ብርቄም ቡናውን ከመቅዳታቸው በፊት ህጻናቶቹ ወደውጭ እንዲወጡ ባይናቸው ምልክት ከሰጡ በሁዋላ ራሳቸው ላይ ሻሻቸውን ጣል በማድረግ አንገታቸውን ደፋ አድርገው አዎል ጀባ ቆሀ ጀባ አሉ
እኔም ሁለት እጀን ወደላይ ከፍ በማድረግ አመን ማለቱን ተያያዝኩ አቶ ይመርም ባባወርነታቸው ምርቃቱን ጀመሩ

ያማን ቤት የበረካ (የሲሳይ ) ቤት ያድርገው
እርዝቃችንንም (ሲሳያችንም ) አላህ ያስፋው
እኔም አሜን ማለቱን ያዝኩ

አቶ ይመርም ቀጠሉ
አዎ እንግዲህ ምቀኛችንንም እንግዲህ አላህ ያጥፋልን , ወደእኔ ዘወር ብለው አንተም እንግዲህ እኛን ያገር ሰው ብለህ እንደመጣህ ያሰብከውን ያሳካልህ . እኔም ከመቀመጫየ ብድግ በማለት አመን ማለቱን ተያያዝኩ
አዎ እንግዲህ እሱ አይሳነውም በሰርጉ ያስደሳህ , የመጀመርያ ልጅህን አብዮት ጠባቂ ያርግልህ ( በዚያን ግዜ እነሱ አካባቢ አብዮት ጠባቂ ማለት ከፍተኛ ስልጣን ነበር ምክንያቱም መሳርያ ስለሚሰጣቸው ሁሉም ሰው እንደመንግስት ነበር የሚያያቸው ) ከዚያም ወደሚስታቸው ዞር በማለት እንግዲህ አንቺንም በትሽን የንግዳ መቀበያ ያርግልሽ ብለው አጠናቀቁ . በደንቡ መሰረት ሰው መርቆ ሲጨርስ ተነስቶ እጅ መሳም ስለነበር እኔም ከተቀመጥኩበት ብድግ ብየ እጃቸውም ሳም አድርጌ ቁጭ አልኩ . አቶ ይመርም በይ እንግዲህ ብርቄ እኒህ ከተሜዎች ታለሻሂ (ስኩዋር ) ስለማይጠጡ በሱዋ ለውሽለት አሉዋት እሱዋም መጀመርያ በባህሉ መሰረት ለመራቂው ባሊ አፋሾ ስኒ [/quote] ትልቅ ስኒ ላባዎራዎች ብቻ የተመደበ አቀበለችና ወደኔ ተሸጋገረች . በደንቡ መሰረት አዎሉን (የመጀመርያውን ) ቶናውን (ሁለተኛውን ) በረካውን (የመጨረሻውን ) አካትመን ወደጨዋታችን ለመሸጋገር ወደታዝያው ተመልሰን ወጣን
በርግጥ የቡና ባህላቸው በሆዴ
ባህሌን ባህሌን ያደኩበትን
እኔ ወደዋለሁ ..........
ሚለውን እንዳንጎራጉር ነበር ያደረገኝ በጣም ነበር ደስ የሚለውይቀጥላል
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳዊት 1

ዋና ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2004
Posts: 525
Location: israel

PostPosted: Fri Mar 04, 2005 10:06 pm    Post subject: ለቅማል Reply with quote

ታዲያስ ውድ የሀገር ልጅ ቅማል ሰላም ነህ ወይ ?::
ስለ ሀረር ያልኩት ተመቺቶህ ቀጥልበት ካልከኝ ......እንግዲህ ይመቺህ ...
..ይህውልህ ስለ ሀረር ብዙ ማለት ይቻላል ::...ማለት ስለ ቦታው ..ስለ ጀጎል ስለ ሀረር እሴቶች .....ግን ለዚህ ሁሉ ነፍስ የሚሰሩበት ልዩ ተስጥኦ ጫታቸው ነው ::
እውን በፊልም ካየህው እነሱ ጫት ትልቅ ቦታ አለው :: ያለሱ አይሆንም ::
ውድ ቅማል መቸም ሀረሮች ከላይ ከገለጽሗቸው ነገሮች በተጨማሪ ሲያወሩም መሳደብ በነሱ ደንብ ነው ::.....
እና አንድ ሰሞን ምን ሆነ መሰለህ ?......አንድ ጋዜጠኛ ወደ ሀረር ይሄድና ካንዱ ሀረሬ ጋር ቃለ መጥይቅ ያደርጋል ::....እናም ....

ጋዜጠኛ ........ስምህ ማን ነው ?
ተጠያቂ .........እንቶኔ (ስሙን ስለማላስታውስ ነው )
ጋዜጠኛ ........ድሮ ሀረሮች የሚታወቁት በስራቸው ነበር ?
ተጠያቂ ........አሁንሳ ምን ልትሉ ነው ?
ጋዜጠኛ ........አሁንማ ጫትና ስድብ ነው የምናየው ከናንተ ..በተለይም ይህ ""እናትህ ትበዳ ""የሚለው ቃል አብዛኛውን በናንተ ይሰማል ::
ተጠያቂ ......ማን ነው እንደዚህ የሚለው ?.....እናቱ ትበዳ ::....እኛ ሀረሮች እንደዚህ አንልም ..እናትህ ትበዳ !

ሰላም ሁን ...
ዳዊት ነኝ ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 05, 2005 12:23 am    Post subject: Re: ለቅማል Reply with quote

ሰላም ዳዊቴ በጣም ቁም ነገረኛ ነህ . ጨዋታህ በጣም ነው ያሳቀኝ የስድቡዋ ነገርማ አይነገርም እንደውም ሚገርምህ አንድ የማቃት ልጅ ለስራ ጉዳይ 3 ወር እዚያ ሀረር ሄዳ ስትመለት copy pest በላት በቃ ሁለ ነገሩዋ እነሱን እና አንድግዜ እናቱዋ ጋር እያወራች እናቱዋን ሳታስበው አቦ እናት .... አለቻትና መለስ ብላ እንዴ እማየ ለካ አንቺ ነሽ ብላ ያፉዋን ሳትጨርስ እናቲቱ ብዲግ ብለው ጋቢያቸውን ጣል አድርገው እነ አረጉ በማለት የሰነዘሩት ቡጢ (ቦክስ ) የላሱዋት ጥፊ እኔንም ነበር የነዘረኝ . anyway እንደው ከቻልክ ብቅ እያልክ ጣል ጣል አድርግብን መቸም ሀረር ብዙ ታሪክ አላት የነ አባ ጅፋር ምናምን , እሱንም ዳሰስ አድርገው ወንድም .

tnx
አክባሪህ
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Mar 05, 2005 3:06 pm    Post subject: Reply with quote

ዉድ የሀገር ልጆች እንዴምን ከረማቺሁ
ማሳሰቢያ ለሁሉም () ሚለውን እንደ () አንብቡት
ወደጫዋታጭን እንመለስ ምን ላይ ነበር ያቆምኩት
ህምምም አዎ ወደ ታዝያው (ፎቁ ) ላይ ዘለቅን (ወጣን ) ከዚያው ላይ ከተጎዘጎዘችው ደረቅ ሳር ላይ ደልደል ብለን ከተቀመጥን በሁዋላ አቶ ይመር ፊታችን ከቀረበው ሸሆታ (ቀሪቦ , ቡቅሪ ) ቀዳ አድርገው በለንካ ያዝ ብለው ለራሳቸውም ፉት እያሉ ጨዋታጨውን ጀመሩ , አፋቸው ከማር ይጣፍጥ ነበር . አጀማመራቸው ይኸውልህ እንግዲህ በጥሞና አዳምጥ ሰዉ ሁሉ እንደሳቀብኝ አንተም እንዳትስቅብኝ እያሉ ከማስጠንቀቂያ ጋር ነበር . እኔም ዴግ ብየ ጆሮየን ነቃ በይ ብየ ቀሰቀስኩ . ዪኸውልህ አንድግዘ እርሻ ዉለን እዚያው እያረምን ታለ እኒህ በተሰብ ምጣኔ ሚሉዋቸው መጡና ይኸውላቺሁ ያገራችን ህዝብ በዛ ትለዚህ ያለው መላ የግዴታ በመከላከያ መቀነስ አለብን አራርቆ መውለድን ማወቅ አለብን እያሉ እስተመጨረሻው ነገሩን እኔ ደግሞ ተይህ ቀደም እንደ አሊዋ ሙሄ ይህን ሰምቶ በተግባር አዉላለሁ ብሎ አንዱዋን ልጁን ሀይቅ አንዱዋን ልጁን ኸይህ ቦሩ አንዱዋን ወረባቦ አንዱዋን ለላ ቦታ ወልዶ እንደተሞኘው ላለመሞኘት እስቲ ንገሩና እንዴት ነው አራርቆ መውለድ ሚቻለው በማለት ለጥቄ (ቀጥየ ) ጠየቅኩ እነሱም ዪህእውላቺሁ ኮንዶ (condom) ሚባለውን መጠቀም አለባችሁ ብለው ነገሩን እኔ ደግሞ በውነቱ ይህ ሀሳብ ሸግየ ነው ማድረግ አለብኝ ብየ እርሻየን እንደጨረስኩ ማምሻውን በዚያው ወደ ከኒና ቤት (መድሀኒት ቤት ) በመሄድ ከኒና አዳዩን ኮንዶ ስጠኝ አልኩት እሱም ደግ ብሎ ሰጠኝ ታያ ወዴቤተ አመራሁ ታያ ማታ ላይ እኔ ልሞክር ከኒና መስሎኝ ሚስቴን መዋጫ ዉሀ አምጪ ብዬ አወጣሁና ብበሸክተው በቅቤ የታሸ ኸረጪት ባወጣው በእቤ የታሸ ኸረጪት ሚስቴ ሁሉ ሳቀችብኝ አፈርኩ አውረቴ (ሀፍረተ ገላ ) ሁሉ ተሸማቀቀ ምጨብጠው ሁሉ ጠፋኝ ቆይ ግዴለም እኔ ይመሩ ባልሰራለት ብየ ጡዋት ሱብሂ ታይነጋ በርሬ ከኒናው ቤት ትሄድ ከኒና አዳዩ ዉሀ እያርከፈከፈ አገኘሁት እንዴው በያዝኩት ዱላ ቅንጥ ቅንጡን ትለው እዚያው ድፍት አለ የታባክ ሰራሁልህ ብየ ገና ተመንቀሳቀሴ እኒህ ቡሊሶቹ ተሁዋላየ መተው ጨበጡኝ እና ታያ ማጎሪያቸው ዉስጥ ዶሉኝ ተዚያ ሁዋላ ዋናው ጠርቶኝ ጠየቀኝ እኔ ዴሞ ይኸውልህ ጉድ ሰራኝ ሚስተኤ እንኩዋ ሳቀችብኝ ትለው እንዴሱ እኮ አይደለም ይሄ ኮንዶው ሚጠለቅ ነው ብሎ ነገረኝ ሁዋላ ምን ይዋጠኝ ወይ አለመተማሬ ጉድ ትኦን ብየ በስንት ግዜየ ለቀቁኝ ያም ከኒና አዳዩ ዲኖ ወዴስራው ገባ እልሀለሁ . እኔም የመሳቁ እድል ስላላጋጠመኝ አፌን ጉንፋን እንደያዘው ሰው በመሀረብ በመሸፈን እምስል አስመስየ አወጣሁት . የሁዋላ ሁዋላ ጊዜው በመምሸቱ ቶሎ መሄድ ስላለብኝ እሳቸውን ለመስተንግዶው አመስግኘ ጉዞየን በጋሪ ወደዴሴ አመራሁ መንገድ ላይ የምሺት ነፋሱን ከባለጋሪውና ከፈረሱ ድራማ ጋር እያጣጣምኩ ተያያዝኩት . ጉዞዋችን ላይ አጋጣሚ ፈረሱ ደከም ብሎ ቆም እንደማለትና ወደጎን ዞር እንደማለት ሲል ባለጋሪው የያዛትን አለንጋ እንደ ብርድ ማላቀቂያ አረቂ ይመስል ለፈረሱ በመስጠት ሂድይ ይሄ ምን ይላል ደግሞ ጎረቤቱን እንዴምን አደራችሁ እንደሚል እየዞረ ይመለከታል እንዴ እያለ በሳቅ ነበር የገደለኝ .

ውድ የዚህ አምድ ተከታታዮች እንግዲህ ያቶ ዪመር ወህኒ ቤት ታሪክ ይህን ይመስላል እግረመንገዴንም የገጠር ቡና ceremony ለመቃኘት ሞክሪያለሁ .

በሚቀጥለው ወሎ ገጠር ከተገኘሁባቸው ሰርግ ስርአት አንዱን ለመዳሰስ እሞክራለሁ

ሰላም ለሁላችሁ
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅማል

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 May 2004
Posts: 511
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Mar 06, 2005 1:36 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዉድ የሀገር ልጆች እረ ምነው ሁላችሁም ዝምታን መረጣችሁ . እረ ብቅ ብቅ . who knows one day we might published one book ግን መጸሀፉ ሲታተም በለጥ ያለውን ብር እኔ ነኝ የምዎስደው ካሁኑ ማስጠንቀቂያ ነው ቅቅቅ

ወደቁም ነገሩ ልሂድና የሸገር ሰዎች የዛሬው ፕሮግራም ከናንተ የሰርግ ስነስራት በጣም ስለሚለይ ጆሮዋችሁን ከፈት አድርጋችሁ በጥሞና አዳምጡ .

ህዳር 12,1987 ከደሴ ከተማ 16 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ ከተማ ላይ በዘመዶቼ ሊደረግ በታሰበው ሰርግ ላይ በታዳሚነት ብቻ ሳይሆን በስርሚዜነትም ነበር የተጋበዝኩት . በባህላቸው መሰረት ስርሚዜ 15ቀን በፊት መገኘት ስላለበት እኔም ጉዞየን ወደዚያው አመራሁ . ከዚያም ስገባ ያካባቢው ሰው ለብቅል ሰበራውና ለአብሽ ግንፋታው (15 ቀን በፊት የቡቅሪም ሆነ ጠላ ምናምን መሰረት መጣያ ቀን ) ስነስርአት ተሰባስቦ አካባቢው ደመቅ ብሎ ነበር እኔም በሰሌን ሳጣራ የያዝኩዋትን ልብሴን ለአክስቴ ልጅ ለሙሽራው በማስረከብ ከመደቡዋ ላይ ቁጭ አልኩኝ , ወዲያው ቁርስ ተብሎ የተጠበሰ እንቁላል በንጀራ መጣ ያችን እንደነገሩዋ ብለን ወደውጭ ወጣን . ማታ ላይ ወንዱም ለብቻው ሴቱም ለብቻው ድልቂያውን (ጭፈራውን ) ይዞታል . ለሰርጉ አምስት ቀን ሲቀረው ሙሽራው እኔና ሌሎቹ የቀሩት ሚዜዎች ተሰባስበን ባቅራቢያው 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሀይቅ ወደምትባለው ከተማ ለሰርጉ ቀን ሚለበስ ልብስ ለመግዛት አመራን . ከዚያም አንድ ሱቅ በመግባት ጥቁር ተሰፍቶ የተዘጋጄ ካኪ ልብስና አንድ ቆዳ ጫማ ለሙሽራው ካነሳን በሁዋላ ለኛ ደግሞ አረንጉዋዴ የተሰፋ ካኪና አንዳንድ ሸራ ጫማ ገዝተን እግረመንገዳችንን እዚያው ከምትገኝ አንድ ጠጅ ቤት ገብተን ሰዉነታችንን ካሙዋሙዋቅን በሁዋላ ዱላችንን ወደላይ ቀጥ አድርገን ያሆ እያልን ወደመጣንበት ተመለስን . የሰርጉ ቀን እየቀረበ በመጣ ቁጥር ሽርጉዱም በዚያው ልክ ነበር . ሰርጉ ሶስት ቀን ሲቀረው የሰፈሩ አረዳ ተሰብስቦ ግማሹ ድንኩዋን ሲጥል ሌላው ደግሞ ዱር ላግዳሚ ወንበርነት የሚሆን ዛፍ ለመቁረጥ ሄዱዋል .. እኛም በበኩላችን ጠጉራችንን ለመቆረጥ ባካባቢው ከምትገኘው አፍ አውጥታ ነገ እወድቃለሁ ማለት ከቀራት ትንሽየ ድንኩዋን መሳይ ነገር ዉስጥ ከባለመቀሱ ጋር ተራ በተራ ሰላምታ ከተለዋወጥን በሁዋላ እንደደጋ በግ ተሸላተን ወደቤታችን ተመለስን .......
ይቀጥላል
_________________
Keguwad Qmal gar 1 ermja wedefit

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወሎ ገራገሩ

አዲስ

Joined: 08 Mar 2005
Posts: 11
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Mar 08, 2005 8:33 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዉድ የዚህ አምድ ተከታታዮች እነሆ ዛሬ በደስታው ቀን የብዕር ስሜን ለወጥ በማድረግ በወሎው አድባር ብቅ ብያለሁ .

ወደታሪካችን እንግባና
እለቱ ቅዳሜ በሀገሬው ሰው አጠራር ለሴቱ አካባቢ ሽንኩርት ከተፋ ቀን እና የንጀራ ጋጋሪ ቀን የሰፈሩ ሰው በመሰባሰብ ባለው አቅም ተባብሮ ሚሰራበት እንዲሁም ደግሞ የፈለገ ለደጋሾቹ የንጀራ ጋጋሪ እያለ ባለው ሁለትም ሆነ ሶስት ብር ያለውም ከዚያ በላይ ጣል ጣል ሚያደርግበት ሲሆን ለወንዱ ደግሞ የበሬ መጣያ ቀን ነው . ቀኑን ሙሉ ሁሉም በስራላይ ተጠምዶ ነው ሚውለው . ማምሻው ላይ የሸገሩም የሌላውም ሰው ለድግሱ ሲገቡ አቀባበል አድርገን ስንጫወት አመሼን . በናጋታው ትልቅ ስራ እንደሚጠብቀኝ ስለማውቅ በግዜ ነበር የተሸበለልኩት . የሰርጉ ቀን በጡዋት ተነስተን ወንዝ ዳር ሄደን ገላችንን ለቅለቅ ብለን ተመለስን . ቀጣዩ ፕሮግራም የጥፍር ቆረጣ ነበር ( ይህም ባህል ሙሽራው ወደ ሴቱዋ ቤት ከመሄዱ በፊት ወንበር ላይ ተቀምጦ ጎድጎድ ባለ ሰሀን ላይ እግሩን ያስቀምጥና ከላይ በጣሳ ነገር እግሩ ላይወተት ይፈስበታና እናቱ ወይም ትልቅ እህቱ ጨፌ ነገር (ሳር ) ይዘው እዚያ ወተት ላይ ነከር እያደረጉ የግሮቹን እና የጆቹን ጥፍሮች በዚያ ሽው ሽው ያደርጋሉ ) ካበቃ በሁዋላ እዚያው እያለ ጎንበስ ይልና ጀርባው ላይ ሁለት ከስንዴ የተጋገረ ሙጌራ (ድፎ ) ይቆረስበታል ታድያ ይህ ሁሉ ሁኔታ እልልልልልልልና ወፌ ላላ እየተባለ እየተጨፈረ ነው ሚሆነው . መቸም ወሎየ ሆነህ ይሄ እንዴት ይጠፋሀል አትበሉኝና ባህል መሆኑን እንጂ ለምን እንደሆነ ምክንያቱን አላውቅም ከዚህ አምድ ተከታታዮች የሚያቅ ካለ በሰፊው ብትነግሩን ደስ ይለናል . ዳቦው ተቆርጦ እንዳበቃ ለሁሉም ሰው ይታደላል ድርሻ ድርሻችንን ይዘን ያን ቡቅሪ ( የጠላ ታናሽ እህት ) እያማግን ስንበላ ያን ቀን የማልረሳው ገጠመኝ አንዲት በኬክና ባይስክሬም የቀለጠች ከሸዋ ቀበሌ የመጣች የዘመዴ ልጅ በጣም ትንሽ ናት ያን ስንበላ የዳቦውን ጠቆር ማለትና የቡቅሪውን መልክ አይታ ወደእናቱዋ ተጠግታ እንዴ እማየ እኒህ ሰዎች ግድግዳውን በጎርፍ በሉት ብላ እንደመዘግነን አላት መሰል ፊቱዋን ሸፈን አለች . ውይ ፈጣሪየ ብየ በሳቅ ነበር የወደኩት

ይቀጥላል
አክባሪያችሁ
ቅማልን በጉያ ይዤ ባዲሱ ስም ወሎ ገራገሩ
_________________
Luck is what happens when preparation meets opportunity.

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወሎ ገራገሩ

አዲስ

Joined: 08 Mar 2005
Posts: 11
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 10, 2005 7:30 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የሀገር ልጆች . እሚገርመው ደባደቦም እንደመሸበት ሰው ግድግዳ ስር አስገድፎን ጠፋ ዳዊትም አነካክቶን አቀጠነ ሞኒካም ስለ ሸገር አመጣለሁ ብላ የበላት ጅብ ድምጹ ጠፋ , እረ ምን ጉድ ይሆን . ወጣ ወጣ በሉ እንጅ ጎበዝ .

እስኪ የጀመርኩትን ልዝለቀው ጎበዝ .
የጥፍር ቆረጣውን ጊዜ አጠናቀን ወደመለባበሻችን ሄደን ኮትና ቦላሌያችንን ታተለቅን በሁዋላ ሙሽራውን ከፈረሱ ላይ በማንጠልጠል እኔም ለሙሽራዋ መመለሻ የምትሆን በቅሎ ይዘን ጉዞዋችንን ሙሽራዋ ቤት አመራን . ከሴቱዋም ቤት እንደደረስን ቀጥታ ወደ ሙሽራዋ ጋር ለመግባት ከሱዋ ሚዜዎች ጋር የነበረው ግብግብ የባህር ሰላጤውን ቀውስ ነበር የሚመስለው (ከመግባታችን በፊት ስጦታ ካልሰጠን በራፉን ዪዘጋሉ ) ሆኖም በጃችን የያዝናትን አንድ ሽቶ አስጨብጠን በሩን ለቀቁልን . እኔም እንደፈረደብኝ በስርሚዜነቴ ወደጉዋዳ ገብቼ እሱዋን ቼቼ ብየ ወደዉጭ በልልታ ታጅበን ወጣን . ከዉጭ ካለው አግዳሚ ወንበር መሳይ የተጋደመ የዛፍ ግንድ ላይ ተደላድለን ቁጭ ብለን ቤት ካፈራው እየተባለ ከሁሉም ከቀማመስን በሁዋላ ማድ (ገበታ ) ማንሻ ተብሎ ከኛ ጋር ከመጡት ሽማግሌዎች እጅ ቢያንስ 200 ብር በላይ እዚያው ጣል ይደረግና ምርቃት ይጀመራል . እንዳበቃ እንደ ኬክ ዪቆረሳል ተብሎ በዉስጡ እንቁላልና የዶሮ ስጋ አዝሎ ከተዘጋጀው ድፎ ዳቦ ከሙሽሮቹ ፊት ቀርቦ ቆርጠው ከተቁዋደስን በሁዋላ ሳይመሽብን ጉዞዋችንን ወደመጣንበት ለመቀጠል ሙሽራዋን አዝየ ያመጣሁት በቅሎ ላይ እኔም አብሬ ከሁዋላ በመፈናጠጥ ጀመርን . ከቤታችን ስንደርስ ሙሽራዋን ለልጁ ከተዘጋጀው ጎጆ ጉዋዳ አስገብቼያት ወደድንኩዋኑ ሁላችንም በመሰባሰብ እራት ከበላን በሁዋላ እንደፈረደብኝ ሙሽራው ጋር አብሬ ገባሁኝ ( ገጠር ስር ሚዜ ማታ ሙሽራው ሲተኛ አብሮ መግባት አለበት ምክንያቱ ቢደክመው ለመርዳት ወይ ደግሞ ልጂቱ ልጃገረድ ካልሆነች እዉነቱን ለማወቅ እንዲያጋርፍ ) ባህል እስከሆነ ድረስ እምቢ ማለት አልችልም 'ወደሽ ከገባሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ' ነበር ነገሩ , ሆኖም እነሱ አልጋቸው ላይ ሲንጠላጠሉ እኔም ጥጌ ላይ ሆኜ ጆሮየን ደፍኜ አይኔን ጨፍኜ ቁጭ አልኩ . ትንሽ ሳይቆይ ሙሽራው ከነበረበት ተንደርድሮ መጣ .......

ይቀጥላል

አክባሪያችሁ
_________________
Luck is what happens when preparation meets opportunity.

[URL=http://www.theimagehosting.com][/URL]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አስራር

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 17 Oct 2004
Posts: 94
Location: united states

PostPosted: Thu Mar 10, 2005 11:35 am    Post subject: ቅቅቅቅቅቅ ቅማል በጣም ይመቻል በርታ ግን በመንገድ ላይ ጭፈራ የለም እንደ ? Reply with quote

በል እኔ ልጀምርና አንተው ጨርሰው :

ያሆ ያሆ ያሆ የሴት አዳሪ ልጅ ይበላል ፈትፍቶ ያሆ ያሆ አንድ ሲናገሩት ይመልሳል መቶ ያሆ ያሆ

ወንድ ይዋጋል እንጂ እንጀራ አይጋግርም ያሆ ያሆ
ይዘጋያል እንጂ ያሰብነው አይቀርም ያሆ ያሆ

ሀህይ ግርማንግፎ ላለይ ግርማ ግንፎ ላለይ .......... ገፋገፋ አድርጌ ባውጣሁት መንገድ .......... ሀህይ ገርማንግፎ ..... አህያ ነዱበት አወይ ነገር መውደድ ........ ሀሀይ ገርማንግፎ

ሳላይሽ ወዬ ....ሳላይሽ ባድር ናድ ይላል ምድር ምድር ምድር ........... ናድ ይላል ምድር ምድር ምድር ናድ ይላም ምድር

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በቃ ያለኝ ይህ ነው አንተም ካለህ ጣል ጣል አድርገው መቼም ሰው ያለውን ከወረውረ ይባል የለ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 17, 18, 19  Next
Page 2 of 19

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia