WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቀልቤለጌ

አዲስ

Joined: 31 Aug 2005
Posts: 35
Location: UAE

PostPosted: Mon Sep 12, 2005 2:55 pm    Post subject: Re: ትንሽዬ ትዝታ Reply with quote

እኔ ደሞ ኩርኩም የማውቀው የሀብቱ ኪዳኔን ነው ::ሀብቱ ሲኮረኩም እጁን ይጨብጥና የመሀል ረዥሙን ጣቱን በምራቁ አስነክቶ መሬት አሸዋላይ ጠቀስ ያረጋታል ;ያቺ ምራቅ የነካት ቦታ ይዛ የመትነሳው አሸዋ መሀል አናት ላይ ስታርፍ አቤት .........ግማሽ ቀን ታሳብዳለች ::እናልህ ፍቃዱም መኮርኮም የጀመረው በሀብቱ ኩርኩም እልሁን ከጨረሰ በኋላ ነው ::ለነገሩ ሀብቱ እኔን ኮርኩሞኝ አያውቅም ::ለምን ?እንዳትለኝ ::ቸር ያቆየን ::
ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
አደቆርሳ ... የሰው ስም ዝርዝር ደርድረህ በትዝታ አንበሸበሽከኝ እኮ ....

የፍቃዱ አቦምሳ ኩርኩም ያልቀመሰ ... የኔ ባች 02 ቀበሌ ልጅ ይኖር ይሆንንንንንንንንንንን ....

አንዴ ምን አደረገኝ መሰላቹ ... 7 ክፍል ሳለሁ .... እዛች ነጯ በድንጋይ የተሰራችው ክፍል ውስጥ ነበር የተማርኩት ... እነ ፍቃዱ አቦምሳ ደሞ 8 ክፍል ነበሩ መሰለኝ ... በእንጨት የተሰሩ ክፍሎች ትዝ ይሉኛል .....
ከነጀማል ሀሰን ጋር ሲያጠኑ እላላክ ነበር .... የሀጂ ሀሰን የኪስ ክፍል አለች .. ከጎን ተለጥፋ የተሰራች .... ታቋት ይሆን ????... ኤኒዌይ እየተላላኩ አብሬአቸው የተወረወረ ጫትና ገራባ እያቃምኩ ሳጠና ይመስላኛል .... ትንሽ ትንሽ ጎበዝ ነበርኩ መሰለኝ
"አንተ ነገ ልትደርስብን ነው እንዴ ብሎ የመታኝ ኩርኩም አይረሳኝም "..... ለኔ ግን ብርታት ነበር የሰጠኝ ...
ሳላመሰግነው አላልፍም በዚህ አጋጣሚ ....

በቡጡ እሸቴ ላይ ደሞ ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም .... በዚያን ዘመን አንድ ወንድ ከሴት ጋር ተያይዞ መሄድ ማለት ነውር ነበር ... አይተን አናቅማ .... ባለጌ እያልን .... ልጅቷን ልቀቃት እያልነው ተከታትለን ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም 02 ልጆች ጫጩቶ ብል ይሻለኛል .. ተሰባስበን ከቆጪ ገባያ አንስተን በማርያም ዳገት አድርገን ... በኳስ ሜዳ ድረስ እየተከተልነው .. ጉሮሮ የሆንበት አይረሳኝም ... ልጅቱ ደሞ የሻኪሶ ልጅ ነበረች .... እሱ ደሞ የተደነቀ የተጨበጨበለት አብዶ ሰሪ ... ዋውውውው ...
አሁን እህት ኖሮኝ ብክሰው ደስ ይለኝ ነበር .... ግን ቆንጆ እህት የለኝም .... ቅቅቅቅቅ

ግፉ ግን በኔም ላይ ደርሶብኛል አሰላ ሳለሁ ... አሁን አይነገርም ... ኡስስስስስስስስስስስስስስ

ባለፈው ሄጄ ያየሁት ጊዜ ያፈርኩት እፍረት ... እሱ ረስቶት ይሆናል .. እኔ ግን ሁሌ ባየሁት ወይም ባስታወስኩት ቁጥር አፍራለሁ ...
አይ ልጅነትትትት ....
አይ ሞኝነትትትት ....

በሚቀጥለው ጊዜ ሲኖር .... አባባ ክብረት ከአሳምነው (አሳምሚት ) ጋር ያስተዋወቁበትን የልጅነት ትዝታዬ አወጋችዋለሁ ...

_________________
Kelbe lege shegie ney ney .........................................................................................!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Sep 13, 2005 6:44 am    Post subject: ከትዝታዎቻቹ ማህደር Reply with quote

ሰላም ቀልቤ -ለጌ እና አደቆርሳ

ብዙ ብዙ የምታነሷቸው ሰዎችን በስም እንጂ በአካልና በድርጊት አላቃቸውም .... የጀነሬሽን ጋፕ ይሆን ወይስ ... ሳላቃቸው ቀርቼ አላቅም ...
ግን ደስስ ይላል ትዝታቹ በሙሉ ...

ድኩላ .. ሚዳቋ አደን ሲወራ እንጂ እድሉ አልገጠመኝም ....
ትዝ የሚለኝና በኔ ጊዜ የነበረው ልጅና ወጣት ያደርግ የነበረው .... ያቺ የማርያም ወንዝ ውስጥ መዋኘት .... እዛ ለጥጥጥ ያለ ሜዳ ላይ ... ሌሊት ተነስተን የምንሰራው አክሮባት ... ቀን ቀን / ከሌለ በርጫችንን ይዘን ማርያም ዳገት ላይ ቁጭ ብለን ... ወይም ወደ ኩቾ በር .. ወይም ወደ ጅሪንቲቲ ተራራ .. ዛፎቹ ውስጥ በዚያ በሚቀዘቅዘውና የነፍስን ስሜት በሰላማዊ ደስታ ወጥሮ በሚያዝናናው ቀዝቃዛ አየር ውስጥ የምንቅመው በርጫ ነው ትዝ የሚለኝ .... የኛዎቹ ልጆች አደን የሚያድን ጉልበት አልነበረንም መሰለኝ ....
ምን ይደረግ ከላያችን ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ተሰደው ታስረው ተገለው ... እኛ ምን ከማን እንማር .... እውር ድንብራችንን ነበር የምንጓዘው ማለት እችላለሁ ....
ላካፈላቹን ትዝታ ግን ከልቤ አመሰግናለሁ ....
ምናለ ባልሞታቹና ከናንተ ብዙ ብዙ በተማርን .... በዚያን ዘመን የሚቃጠል ሽፍታ ወይም ፀረ -አብዮተኛ ወጥታቹ እዩ ስንባልና ስናይ ትዝ ይለኛል ... አቤት የህፃን ጭንቅላት ውስጥ የሚፈጥረው ስሜት ....
ይኸው ፈሪ ትውልድ ሆነን ቀርተናል ... ሚዳቋ እንኳን ማደን የማይደፍር ትውልድ ነን ...

ቀናሁባቹ አቦ !

እስኪ ብዙ ብዙ ንገሩን ስለብዙዎቹ ያገሬ ልጆች ... እራሴንም መለስ ብዬ እንዳይበት

ቸር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Sep 13, 2005 2:15 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ ሰላም ይሁንልህ :ይገርምሀል ዛሬ ጠዋት ሥራ ከመግባቴ በፊት ታናሽ ወንድሜ ደወለና በዚያው ሰለራስ ብሩ ጥሪ አንስተን ምን አለኝ መሰለህ
/አደቆርሳ ጽሁፎቹ ደስ ይላሉ ግን ከሚጠቅሳቸው ስሞች አንዳንዶቹን ጨርሶ አላውቃቸውም /በባለሱቅ ጽሁፍ ትዝታ ግን ....................ብሎኛል ::ታድያ ኮምፒዩተሩን አስነስቼ ወደዚሁ ገጽ አመራሁና ያንተን ጽሁፍ ሳነብ በጣም ገረመኝ ::ስለ አባባልህ እና ስለ ልዩነታችን በቅርቡ እስርቤት ትዝታችንን የሚዳስስ ሌላ ትዝታ ይዤ ስለምመጣ ምናልባት እዚያ ላይ አንዳንድ ነገሮች ለግንዛቤ ይረዱህ ይሆናል ::በዚህ ላይ የማስታወስ ችሎታም አንዱ ኅይል ነው ::በነገራችን ላይ በጣም ልጅ ሳለን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እያንዳንዱን ነገር ሳይረሳ በጣም የማስታወስ ችሎታው ልዩ ነው የምንለው ልጅ ምናልባት ታውቀው ይሆን አላውቅም ::የሚኖረው በምድረ ስካንዲኔቪያንስ ነው ::እኔም እንደሱ አልሆንም እንጂ ከቄስ /ቤት እስከ 8ተኛ ክፍል የነበረውን ዘመን ስለምወደው በጣም አስታውሰዋለሁ ::ዳሩ ትዝታችንም እኮ ዘመን ነው :ከዚያ በኋላማ ምን ትዝታ ሊኖር ........................የሚገርምህ እኒያ በአደን ከጠቀስኩልህ ሁሉ አሁን ብዙዎቹ ካገር ወጥተዋል ከፊሎቹም አልፈዋል እስካሁን እዚያው /መንግስት ያለ ሲሳይ ሳንታ ብቻ ነው ::ያኔኮ ደሞ ሁላችንም (Juniour) የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ነበርን .........ይህ የማያልቅ ታሪክ ስለሆነ :ወደ አምዳችን እንመለስ ::ሰሞኑን ደሞ ቤቱ ጭር ብሏል :ቅሩንፉድ በዚህ አመት ብቅም አላለችም :
ያቺ የግሏ ደሞ ያንን የፈረንጅ ውሀ መንገድ እያነሳች ያለሁበት ቦታ ባህርዛፍ ባህርዛፍ እስኪሸተኝ ድረስ በትዝታ የምታፍነከንከኝ :ምንድነው ነገሩ :በኍላ ሌላ ነገር እንዳታመጪ እኔ በዛ መንገድ !!!:
ወንድሜም ሊያውቅህ ይፈልጋል እንግዲህ ይጽፍልህ ይሆናል ::ዛሬ ምናልባት አደቆርሳ ማን እንደሆነ ሲያውቅ የሚለኝን ደሞ እጠብቃለሁ ::
አንተ ፖስታቤትሰፈሬ ምነው ጠፋህሳ ?ግምቴ ልክ ከሆነ ""ድንጋይ በኪስህ ይዘህ የተማሪ ደብተር የምታስጥለው ትዝ ይልሀል ወይ በልልኝ Sadግምቴ ልክ ካልሆነም አላወቅሁህም ) ማለት ነውና :ቸር ይግጠመን ::ወንድማችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ !!
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅሩንፉድ

ኮትኳች

Joined: 15 Apr 2005
Posts: 454
Location: germany

PostPosted: Tue Sep 13, 2005 9:36 pm    Post subject: ሰላም ወዮዎች አመትበዓል እንዴት ነበር ? Reply with quote

በኔ በኩል እንግዲህ የልኳንዳ ስፈርን ስጋ አስመጥቼ ስከታትፈው ነው በሀሳቤ የመጣብኝ :: ምነው እንአደቆርሳ ሴክቴን ጠጥታችሁ ሙዚቃዬን አዳምጣችሁ : አሜን ያላላችሁ :: Laughing Laughing Laughing የግልዬን አይመለከትም ::

ቀልቤለጌ ስለወፉ አንድ ነገር ትዝ አለኝ :: አንድ ጊዜ እማዬ ቡና ስታፈላ መጥቶ ቁጭ ብሎ ጠጣ ጠጣና : ሊወጣ ሲል እህቴን ሳታስበው ድርግም አርጎ ሳማት :: ከዛ ቱፍ ቱፍ እያለች የዘለለችው አይረሳኝም :: ያም ትመጣለህ የሚለውን ነገር እኔም አልረሳውም :: የቺካጎ ማህበር ጥሩ ነው :: እኔም ዘመዶች አሉኝ እዚያ :: የእነፍርዬ ገዳም ቤተስቦች ናቸው ::

በሉ እንግዲህ እስከሚቀጥለው ::

አክባሪያችሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Wed Sep 14, 2005 1:22 am    Post subject: አዲስ አመትማ በክ /መንግስት ትዝታ አለፍ Reply with quote

ስላምምም ለሁላቸውው ተጠፋፋንን አይደልልል አንዳንዲምም ትዝታ ይዞ ይጠፋልል እኮ እኒምም ቢዚ ነበርኩ ራስ ብሩ የስጠኝኝን የስራ ድርሻ ለመወጣትት ባቅራቢያዩ ላሉትት የወዩ ልጆቸ የዋርካንን ሆም ፒጅ እየደዋወልኩኝኝ እየስጠሁኝኝ ነውው ሚገርማቸውው አንዲት ጋደኛዩ ስደውልል ሀዋ አደምን አገኛሀት ለሳምምም የክ / ልጆቸ ኦን ላይን ላይ እየተገናኝንን ስላትት በጣምም ነውው ደስስ ያላትት የቺካጎውን የክ / መሀበርር ስነግራት ደስታዋ መጠንን አልነበረውምም ለወንድማም እንደምትነገረውው ነግራኛለቸ ቀድሞ ይህንን ፒጅጅ ካላገኝውው እንግዲህ እንበርታ ቀልቢ ለጊና አደቆርሳ የምትናገሩትት ትዝታ ባለሱቅቅ እንዳለውምም ባላልፈበትም በዛንን ጊዚ የነበረውው የቀይሽብርር ሁኒታ በልጅነት አይምሮዩ ውስጥ ይታዩኛልል አባቡታና አስታወሳለውው , ከምን እንደድረስም ባላውቅቅ , ያቆብ ደስታምም ቦሪ ነውው ሂኖክክ ወንድሙም አዲስአባ ነበር ከማስታወሳቸውውበሉ እንግዲህ አይለይንን በርቱልኝኝኝ ቁርንፍድዩ በይ በርቺልኝኝ አንቺምም ባለሽብትት የናተውው የወዩዋ የግልል ነኝኝኝኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Ellenie

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jul 2005
Posts: 1086
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Sep 14, 2005 2:15 am    Post subject: የግል ቅቅቅ Reply with quote

ምነው ልጄ በሳቅ ትገይኝ እንደዚ ! Very Happy ቅቅቅ እነኛ የተደጋገሙት ፊደሎች ቻት ሩም ሸሽተው ነው ? ውይ ኧረ ብሳቅ ገደልሽኝ ቅቅቅ ልሞት ነው Very Happy ምንም እኮ አልገባኝም ጽሑፉ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
Smile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Sep 14, 2005 4:52 am    Post subject: የማስታወስ ችሎት Reply with quote

በትክክል ተመልሷል ::
በውነት ነው ምልህ አደቆርሳ ... የማስታወስ ችሎታዬ እየቀነሰ እየጠፋ እየተስለመለመ አሁን ያለሁበት ደረጃ ደርሷል .... መቸ እንደጀመረኝ ባላውቅም ... ወይም በተፈጥሮ ሆኖ የማስታወስ ችሎታ የለኝም ይሆን እንጃ ...
ይገርምሀል የጎረቤቶቼን ስም ጠቅሰው ሲያወሩ እንኳን .... ማነው እሱ ያልኩበት ጊዜ አለ ... እንዳልከው ሁላችንም የተለያየ የማስታወስ ችሎታ አለን .... ለዚያም ይሆናል ኃላ የቀረሁት ...
ግን በሙሉ ፅሁፍህን ወድጄልሀለሁ ... ቀንቼብምሀለሁ ..... ቅቅቅ አዲስ አማርኛ ፈጠርክ እንዳትለኝ ብቻ ... እንደመጣልኝ ስለማወራ ይቅርታ ...

ምናልባት ታናሽ ወንድምህ በደንብ ያቀኝ ይሆናል ... እስኪ የክ /መንግስት ሀይስኩል አንዲት የዱርዬ ትዝታዬን ላውጋቹ ...
የበቆሎ ተከሉ ዘመቻ ነበር .... እኔና ጓደኛዬ የተሰጠንን መስመር ይዘን ሁለት ሁለት ፍሬ እየተከልን ሄድን ብዙ ብዙ .... እኔ በመርዝ የተነከረ በቆሎ ይዣለሁ ጓደኛዬ ከኔ እየወሰደ ቆፈር ቆፈር እያደረገ ይተክላል .... ወደመጨረሻ አካባቢ ልንደርስ ስንል ... በቃ ተመለሱ የሚል ትዕዛዝ ተላለፈ ... በእጄ የቀረ ብዙ የበቆሎ ፍሬዎች ነበር ... ጓደኛዬም .. አለ
ባክህ ማን ይዞ ይመለሳል ... አስገባው እዙህ ጉድጓድ ውስጥ
..ቆፈር ቆፈር ....
ክትትትትት ወደ 40ፍሬ ይሁኑ ይሆን .... ቅብርርር አደረኩት
ታዲያ ይህንን ስናደርግ የሚያይ አንድ ልጅ ነበር .... ከጎናችን ካለው መስመር እየተከለ ይሄድ የነበር ....
ነፍሱን ይማረውና የአበራ በሪ ልጅ .... ምስራቅ አበራ ...
ጓድ ሊቀመንበራችን መንግስቱ /ማርያም /መንግስት ለጉብኝት መጥቶ ዘንባባ ካንፕ አሰርቶ ያደረ ጊዜ ... ምግብ አቅራቢ አበራበሪ ሆቴል ነበር ... ስራ ሊያግዝ ሄዶ ነው አሉ ... ልክፍት መትቶት ባንድ ቀን በሽታ ያረፈው መሰለኝ ...
እናላቹ ... ይህ ጓደኛችን .. ሄዶ ላባጦር ... ንግር ...
እንትናና እንትና አንድ እፍኝ በቆሎ ጉድጓድ ውስጥ ከተቱ .. ብሎ .... ምስኪንንን .. ትክክል ነበር መናገሩ ... ግን ጦሱ ለብዙ ነገር ዳረገን እንጂ ...
ተጠቁሞብን ሊይዙን ሲመጡ .. በሌላ ቀን ማለት ነው ... ጓደኛዬ (ታላቄ ነው መሰለኝ )... እግር አውጪኝ ብሎ በአጥር ዘሎ ሄደ .... እንደሄደ በዚያው ቀረ ... ውትድርና ...
እኔ አንድ ግማሽ ቀን ታሰርኩና ... በማግስቱ ጠዋት በተማሪዎች ፊትለፊት ንግግር እንዳደርግ ... የይቅርታ ንግግር ... ተደርጌ ገባሁ
ውትድርና የሄደው ግዋደኛዬ ወንድሙ ግን ምስራቅን ሊደበድበው እቅድ ነበረው ... ቀድሞ ሞተ እንጂ .... አምላክ ነፍሱን በፀጋ ይቀበለው ...

ታዲያ ይህች የበቆሎ ታሪኬ 11 ክፍል ተከትላኛለች ...
ከድሪርሳ (የምወደው የሀይስኩል ዳይሬክተር .. ምስጋና ለሱ ይገባዋል .. አሁን አለሁበት ደረጃ ያደረሰኝ የሱ ቁንጥጫ ነው ).... ከድሪርሳ ጋርም አጋጭታኛለች .... 11 ክፍል ላይ .... የሆነች ስተት ሰርተን 4ተማሪዎች ከት / ቤት ተባረን .... ከጊቢዬ ውጣለኝ ፖሊስ ሳልጠራልህ ሁሉ ተብዬ 3ሳምንት በኃላ ለናቴ ነግሬአት ይዛኝ ልትለምንልኝ ሄደን ቢሮው ውስጥ እያግባባነው እያለ ... አባጦር በመሀል ይገቡና .... ይሄ ይሄ የሀገር ጠር ... አገር ምድር በርሀብ ሲቆላ እሱ አንድ እፍኝ በቆሎ ....,ናምን ምናምን .... 9 ክፍል እያለ ብለው ሊራራልኝ የነበረውን ሰውዬ Twisted Evil Evil or Very Mad ... ምን ብዬ ልናገር ...
አቤትትትት ልጅነት .. ሞኝነት ...

እስኪ ደሞ ሻፊ ሻይ ቤት ቆቆር እየበላን የራስ -ብሩን ትዝታዬን እንጨዋወታለን

ቸር ይግጠመን

አንቺ የግል ለምንድነው ምትጠፊው ... የአዲስ አመት ካርድ ልከልሽ አመሰግናለሁ እንኳን አይባልም እንዴ ?.. ቆይይይ ባልቆነጥጥሽ ..

ቅሩንፉድዬ ... ልኳንዳ አሁን ቀዝቅዞ ይሆን .... ከአለማየሁ ባንቲ መኖሪያ ቤት በላይ ያለው ልኳንዳ .. ባይኔ ላይ ዞረ እኮ .... የሰዎቹ ወጠምሻነት ... ይህንን ስጋ ነርተው ነርተው ... ዋውውው ሲያስፈሩ ... ሰክረው ሲጣሉማ ... ተዋበች ጠጅ ቤት ጎራ ብለው ....

ያም ትመጣለህ !!!!!... አለ ወፉ .. በቦቅስ ሲነርተኝ

ችር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Sep 14, 2005 6:37 pm    Post subject: አይ ልጅነት Reply with quote

እንዴት ዋላችሁ ?
ቅሩንፉድዬ ያንን የልኳንዳ ጮማ (የነገነት እሸቱን :ቤት የጎድን ጥብስ 10 አለቃ ተሰማንቤት ጭቅና የነ አገኘሁ ዱባለንቤት ሽንጥ ባንቺ ቢኖ እያወራረድኩ በዚህላይ በባለሱቅ ትዝታ አዶላን እያስተዋልኩ ባንቺና በሌሎቹም የልጅነት ወግ .........ምን ልበልሽ ዓውዳመቱን እንደኔ የተደሰተበት አለ ብለሽ ነው ?
በይ ምስጋናዬ ይድረስሽ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
የግልነሽ ሀዋ አደምን አገኘሁዋት ስትል እኔም አሊ አደምን አስታወስኩ ::አሊ የት /ቤት ጓደኛዬ ነው ::/ቤት እኩል ባንገባም 3ተኛ A ክፍል አብረን ነበርን አስተማሪያችን ቲቸር ዘሪሁን ይባላል (ቀይ ቀጭን ረዥም )ዓሊ የሩቅ ሰፈር ልጅ ቢሆንም አንድ ክፍል ስለነበርን በኳስ እንግባባ ነበር ::ዓሊ በባዶ እግሩ በፑንት የሚመታት ኳስ ለበረኛው ለአብዶሼ አሳር ነበረች ::ሰኔ 30 ደርሶ ከየክፍሉ 1-3ተኛ የወጡ :ከሆልሴክሽን 1-3 የወጡና በተለያዩ ሳብጀክቶች ቶፕ ውጤት ያላቸው ሁሉ ብቻ ያኔ ሽልማት ብዙ ነበር ::ታድያ በዚያ የወላጆች ቀን ወላጆች በልጆቻቸው የሚደሰቱበት እና የሚያዝኑበት በመሆኑ ትልቅ ቀን ነው ::እኔም አሊም እንደምናልፍ አረጋግጠን ነበርና :ዝግጅቱን (ሥነስርዓቱን )ትተን ወደ ኳስ ጨዋታችን እንድንሄድ ዓሊ ግድ አለኝ :እኔም ሌላ 3 ክፍል የነበረ ወንድሜን ጠርቼ ተያይዘን ከት /ቤቱ በስተምዕራብ ባለችው የኳስ ሜዳ ስንራገጥ ቆይተን ስንመለስ ዝግጅቱ ተጠናቋል ::አባታችን ሽልማታችንን ተቀብሎ በኛም ያልጠበቀው ሁነታ በጣም ተናዶ ተመልሷል ::እቤት ስንደርስ የዋልንበትን ያቺ አንድ አይነት ፍራቢ ሸራ ጫማችን ትመሰክራለች :Sadለወላጆች ቀን አጥበን ነበር ያረግናት )ገና ስንገባ እንደምንገረፍ አውቀን ነበርና እኔ ዓሊ ዓሊ ነው እያልኩ ወንድሜ ደሞ በኔ እያመኻኘ ነበር ከዚያማ ተያዝና :እናታችን ባትረዳን ...
አልቆልን ነበር ::በጣም የሚገርመው ግን ዓሊ አደምም ተሸላሚ ነበር ::ትልቁ ወንድማቸው ጋሼ ያደረገውን እስካሁን ያስታውሳል ::እስካሁን ሳገኘው ወቅሰዋለሁ ::
የግሏ አመሰግናለሁ ::የወላጆች ቀን የስፖርት ትርዕይት ታስታውሻለሽ ?ግርማ ይስሀቅን ፍቃዱ አቦምሳን ሽብሩ ግርጃን ወዘተ .
ቸር ይግጠመን ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 15, 2005 5:02 pm    Post subject: አደቆርሳ Reply with quote

የትዝታ ኮሮጆ የሰው ስም ማትረሳ
የቦታ ገጠመኝ ሁሉን ምታነሳ
በናፍቆት ሰቀቀን ጥለህ ምታስነሳ
04 ወዲያ ስምህ አደቆርሳ
ላንተ አድናቆቴን እስኪ አኔም ላውሳ :
በብዕሬ ቅለም ትንሽ ልጠቃቅሳ !::

.... ይገርማል የሉካንዳ ሰፈር ሰዎችን ስም ስታነሳ እያንዳንዱን ሰው አቀዋለሁ ... ግን ለብቻኅ ጥራቸው ብትለኝ ... በፍፅም ነው መልሴ ..... እንዴ ነው ግን የሰው ስም ማትረሳው ጃል ...
በተለይ አገኘው ዱባለን ስጠራው ግርምምም ነው ያለኝ ... ምክንያቱም አውቀዋለሁና .... ባንድ አመት መሰለኝ በክፍል ምንለያየው ... ደሞ የሰፈሬ የቀበሌዬ ልጅ ነው እንጂ ... አንተ ካዶቆርሳ መጥተህ የሱን ስም አስታውሰህ እኔ ስረሳ ... እራሴን እንድታዘብ ነው ያድረከኝ ...

እረ ስሞትልህ ስለአንዳርጌ ቤተሰቦች የምታቀውን አጫውተኝ .... ያንዳርጌን መኪና ብዙ ጊዜ ተሳፍሬዋለሁ ... ቢሉ / ቤት ስማር ....
አንዲት ልጁን ደሞ .... ቅቅቅቅ ወድጃት ሞቼ ነው የተነሳሁት .... ሚስጢር ነው .... ወይ ፍቅርርርርርርርርር .. ባዶቆርሳ / ቤት ጊቢ .....

በነገራችን ላይ ቢሉ / ቤት የተከልኵት ዛፍ አለች በሄድኩ ቁጥር የማያት ... እንዴት አድጋለች መሰለህ ... ስወዳትትትትትት

በል ፕሊስ ከትዝታዎችህ ብዙ ብዙ አካፍለኝ ... ወድጄልሀለሁ ያንተን ጨዋታና የማስታወስ ችሎታ ...

በቅናት ልሞት ነው ስልህ ግን ሌላ ሰው እንዳይሰማ እያፈርኩ ነው .... ምክንያቱም 02 ልጅ ነኛ !... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አቤትትት 02 እና 04 ቀበሌ የእግርኳስ ጨዋታ ያለ ጊዜ ያለው ፉክክርና ድብድብ ... መቸም አይረሳኝም ...
አንድ ጊዜ ተሸንፈን ግን ,,,, ዋንጫዋን በድንጋይ ሰብረናታል ... በእንጨት መሰንጠቂያ መኪና ላይ እየጨፈሩ ሲሄዱ ... ተናደን ድንጋይ ወርውረን ... ስይድ ከድሮ አንዱ ድንጋይ ወርዋሪ ነበር .. 01 ቀበለኤ ይሁን እንጂ እኛን ነበር ሚያግዝው መሰልኝ ....

እረ ሮዛ ከድሮን ሚያቅ ማነው ... ቁንጅናዋ .... የኢድ ቀን እሷን ለማየት የምንንጋጋው ትዝ እያለኝ ግርምምምም ይለኛል ... ኒውዮርክ እንዳለች ተነግሮኛል ግን ያው አሁንም በጭንቅላታችን ውበቷ ተስሎ እንዳለ እንድታቅልን ይነገርልን ..ንጎረቤቶቿ አደራቹን አርሱልንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንንን

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቸር ይግጠመን አቦ
\
አደቆርሳን አያሳጣን ... የትዝታችን ማህደር
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA

Last edited by ባለሱቅ on Sat Dec 23, 2006 2:30 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 15, 2005 8:12 pm    Post subject: Reply with quote

ትዝታ ለብቻ ከሆነኮ ህመም ነው :ከወዳጅ ጋር ግን እነሆ ትዝታ ነው ::እንዴት ከረምክ ወዳጄ ባለሱቅ :: አድናቆትህን ከፍ ካለ ምስጋና ጋር ተቀብያለሁ ::ወደ ልኳንዳ የወሰደቺኝማ ቅሩንፉድ ነቻ ወፉ እህቴን ግጥም አድርጎ ሳመ ስትል ቀኑን ሙሉ ስስቅ አይደል እንዴ የዋልኩት :: ወይ ጉድ !!
ጠላትህ ይሙት እኔ ስለ ጋሽ አንዳርጌ ቤተሰብ አላውቅም ::የማውቀው ያንን አመለ ሸጋ , ጂኒየስ ,ቀልደኛና የዋህ አድማሱ አንዳርጌን ነው ::የማይረሳኝ አንድ የሚወዳት እና ካፉ የማትጠፋ ዘፈን ነበረችው :(Thebirds........flying...)ምንታረገዋለህ :""ስብሀት
ለእግዚአብሄር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብዕ "":እንዳለ ሉቃስ :2:14 የክርስቶስ መወለድ ለሙታን ትንሳኤ ባይሆን ኖሮ በእነዚያ ሰማዕት በሰው ክፋት ለሞቱ ወጣቶች ዛሬ
የኛ ስራ በቀል ብቻ ነበር ::ነገር ግን በቀል የእግዚአብሄር እንጂ .....::ወዳጄ ሆዴ ባለሱቅ እንደው ወዳላሰብኩት ወሰድከኝ :ይልቅ ወደ ኳስ ጨዋታችን እንመለስና :04 በረኛ የነበረው ተስፋዬ ለማ በዚያን አንተ በምትለው ግዜ ኮከብ ነበር ::02 ጌታቸው ይርዳውን አልረሳውም ::ከአስተማሪ ስፖርተኞች ማን ማንን ታስታውሳለህ ?ምናልባት እነ ኮርማ ዱግዳ እነሙሉጌታ አስመላሽን ታውቃቸዋለህ ?
እናንተ ቀበሌስ ዮሀንስ አለማየሁ ያሰለጥናቸው ከነበሩ
ልጆች አሁን ጥሩ ደረጃ ደርሰዋል የመትላቸው አሉ ?
ክብሮምስ (ክብሪት )የት ነው ያለው ?ከሴቶች ጥሩ ስፖርተኛስ ?
በል ለዛሬ በዚሁ ይብቃን ቸር ይግጠመን ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅሩንፉድ

ኮትኳች

Joined: 15 Apr 2005
Posts: 454
Location: germany

PostPosted: Thu Sep 15, 2005 8:42 pm    Post subject: ስላም አዶላዎች Reply with quote

አዶቆርሳ እና ባለሱቅ መቼም ትዝታ አያልቅባችሁም :: ክብረ መንግስት እንደስሟ ትናፍቃለች :: ገንዬ ጎደኛዬ ነበረች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አብረን ነበር የተማርነው :: እነሶሎሜ ገብረትንሳዬንስ የሚያስታውስ አለ :: አንድ ጊዜ ያዕቆብ የወይነሽት ምትኬን እህት ትንሿን : እህቶቿ አዲስ አበባ ሄደው ነበር ያኔ : መንገድ ላይ ያገኛትና ነይ እስቲ አንቺ ቡና አፍይ ይላታል :: አፍልታለት ቡናው በድንብ አልደቀቀም መስለኝ ቱፍ እያለ ጠጣና : አቦ አንቺስ ቡና ቦርድ ነሽ አላት :: በሌላ ቀን ደግሞ እንዲሁ በይ ዛሬ እስቲ ነይ ወተት አፍይልኝ ብሏት : ወተቱን ደግሞ ስኳር አበዛችበት መሰለኝ : አንቺስ ቡና ቦርድ ብቻ አይደለሽም : ወተት ቦርድም ነሽ ይላታል :: አይ ያኔ የሳቅነው ሳቅ ! ቂቂቂ Laughing Laughing Laughing

የግልዬ እንዴት ነሽ ነብሷ የወዩ ልጅ ! ደውይልኝ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንግዳ ነኝ

መንገደኛ

Joined: 15 Sep 2005
Posts: 1
Location: united states

PostPosted: Thu Sep 15, 2005 11:34 pm    Post subject: እንግዳ ነኝ Reply with quote

ታዲያስ የወዩ ልጆች

እንዳው ትገርማላቹ ምንም እንካን ፍቅራችሁ ቢያስቀናም ይሄን ያህል ለዚች አመዳም ከተማቹ (እንዳው ከተማ ልበለው ስሙን አሳምሬ ) Rolling Eyes
/መንግስት ማለት አበዛቹ ::

ቂቂቂቂቂ ...........
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Sep 16, 2005 4:03 am    Post subject: አቤትትትትትትት Reply with quote

አደቆርሳ ጥያቄ በጥያቄ አደረከኝ አቦ ...
ብዙ ብዙ ሰው አስታውሳለሁ ስም ግን ጥራ አትበለኝ ... ምክንያቱም ቅድም እንዳልኩህ ጭንቅራቴ በልዟል ....
ከአስተማሪዎች ... ! የቦሬ ልጅ ረጅሙ ... ናስር ነው መሰለኝ ስሙ .... ኮርማ ዱግዳ ስሙን ታላቅ እህታችን ስታነሳ ትዝ ይለኛል .. አጭር ፈጣን ተጫዋች ነበር መሰለኝ ... ዝነኛ አብዶ ሰሪ ...
ያልከውን 04 በረኛ ዋውውውው በጣም ነው ማስታውሰው ... አሞራው ነው አይደል ... ሲወረወር እኮ ጭልፊት ነበር .. አቦ .....
ግን ግን አሞራው 03 በረኛ ይሆን .. ፀጉሩ ረጅም አጭር ተወርዋሪ .... ተስፋዬ ያልከው ረጅም መሰለኝ ... አቦ ተምታታብኝ እኮ ...
ክብሮም ኃይለዝጊ ጓደኛዬ ነው ... ክብሪት .... መሀመድ ረሺድን ታቀው ይሆን ... ነፍሱን ይማረውና ... እሱ ደሞ ወንድሜ ነው ..... ወይ ጉድ ራሴን አጋለጥኩ እኮ ...
አቦ አንድ ጊዜ እኔ ሀብቱ ተወልዴ ... ግርማ ርዕሶም ክብሮም ኃይለዝጊ ኤፍሬም ኃለዝጊ (ነፍሱን ይማረው ) ሆነን የሉፍ ጫት ገዝተን በጠዋት በእግራችን ሻኪሶ ድረስ በእግር ወክ ያደረግነው አይረሳኝም ....
ጀብዱ ነበር ለኛ 20 ምናምን .... ወክ ማድረግ ... የፈራነው አባሎ አካባቢ ያሉትን ዝንጀሮዎች ነበር ... ሰው ከዛፍ ጋር አስረው በጉንዳን ያስበሉታል የሚባል ወሬ ማን እንዳወራ አናቅም ... በፍራት ነበር ያለፍናት ያቺን መንገድ ... አይ ልጅነትትት

የሴት እስፖርተኞች አልከኝ ... የእጅ ኳስ ነበር ትዝ የሚለኝ .. እዛ ቆጭ ገበያ ካለው የስፖርት ሜዳ ላይ ... ሴቶች ሲጫወቱ ... 02 ቀበሌ የሜጫ ሰፈር ልጅ ስሟ ጤፋብኝ ... 01ቀበሌም ጎበዝ ልጆች ነበሩ ... እረ ስም መርሳት በሽታ መዳኒቱ ምን ይሆን ....

ቅሩንፉድዬ የባላምበራስ /ትንሳኤ ቤተሰቦች የምወዳቸው ቤተሰቦቼ ናቸው ... አሁን በብዛት አሜሪካ ነው ያሉት ... ሌሎቹም አዲሳባ ..... ያቆብ /ትንሳኤ ተንኮለኛ ነበር ማለት ነው .... ቅቅቅቅ

ለእንግዳ ነኝ
እናመሰግናለህ ላድናቆትህና ለትችትህ ... ስለህንፃው ድልድዩ ድንጋዩና ተራራው እያወራን አይደለም ... ስለ ሰው ነው ምናወራው ... ሰው ደሞ ከምንም ነገር በላይ የተከበረ ፍጡር ነውና .... የትም ተወለድ የትም እደግ ... ቅመምህ የሰውነት መለኪያህ ... ህብረትህና ፍቅርህ ነው ዋናው ያንድ አገር ቅመሙ ..... እንጂ ህንፃው መንገዱ አስፋልቱ አዋራው አይደለም .... ስለዚህ ሳቅህን ውጠህ በመጣህበት እግርህ ብትመለስ ደስ ይለናል
እናመሰግናለን
ፊርማ የማይነበብ
የክብረመንግስት ልጆች
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1054
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Sep 16, 2005 4:13 am    Post subject: ቅሩንፉድዬ Reply with quote

ወይኔ እንደገና ሳነብሽ ምን እንዳየሁ ታውቂያለሽ .... የወይንሸት ምትኬ !,,,, ዋውውውውውውውውው አውቃታለሁ እኮ .. ወይንሸትን .... ወፍራሟ ናት አይደል .... ውይይይይ 6 ክፍል ሚኒስትሪ ወድቃ ያለቀሰችው አይረሳኝም ... ቅቅቅቅቅቅ ግን በስተት ነው ተብሎ ተስተካክሎላታል መሰለኝ .... የኔ ባች ናት .... ከማህደረ /ትንሳኤ ጋር ሆነን ... ብዙ ብዙ ትዝታ አለን ... ከወይንሸት ጋር
የት ይሆን ያለችውውውውውውው
እረ ያለማየሁ ባንቲ ልጆችስ ... እነ ኤልሳ ትግስት ወዘተ ... እስኪ የሚያውቃቸው ይተንፍስብንንንንንን

ቸር ይግጠመን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Fri Sep 16, 2005 5:34 am    Post subject: ስላምምም ለክ /መንግስቶቸ Reply with quote

አደቆርሳና ባለሱቅቅ በትዝታ ይዛቸሁኝኝ ወደ ወዩ ነጎዳቸውው ባለሱቅቅ የጠፋቸብህ የሲት ስፓርተኛ ዝነኛዎ ከካስ ሚዳ የማትጠፋው ለመለም በረሂ ናት አሁንን ያለቸው ጀረምን ነው ሊላዋ በአክሮባት የታወቀቸው ባልሳሳት ምህረት ርሶም ናት እስቲ ቁርንፍድዩ እርጂኝኝ ባክሽ ሊሎቸንንም ሶሪ ልቢ በዚህ አምድ ላይ ጠፈቶ ስልክክ መደወል ረሳው ስሞኑን ደውላለው በጣም ነው ድምፅሽንን ለመስማት የጋጋሁት ብታዩ ቀልቢ ለጊ , ዝምታ , ፖስታ ቢት ስፈሪ ምነው አደፈጣቸውው ብቅ በሉና እንጫውት የወዩንን ትዝታ ከዛም አንድ ቀንን ብለንን ተነስተን ያቺን ራስብሩ እናቀናለንን በተረፍ እንግዲህ ባለሱቅና አደቆርሳ አትለዩን ቁርንፍድዩም እንደዛው
በርቱልኝኝ ካይን ያውጣንን የወዩ አምላክክ
የናተውው የወዩዋ የግልልል ነኝኝኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5 ... 381, 382, 383  Next
Page 4 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia