WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 311, 312, 313 ... 379, 380, 381  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Sep 21, 2010 7:59 pm    Post subject: Reply with quote

እስኪ በናታቹ እየጮሀቹ ዝፈኑልኝ እንደጥላሁን
አንቺ ጤና ሆነሽ ፍቅሬ ..... እኔ ጤና እያጣሁ
ከስቼ ጠቁሬ ፍቅሬ .... ከሰውነት ወጣሁ
አለማየቴ እንጂ ... ፍቅሬ .... እኔ አላረገውም
ፍቅር እንዲህ መሆኑን .. ፍቅሬ ... ባውቅ አልጀምረውም
........................//...................
እንደገና ፍቅር ያዘኝ እኮ
ከራሴ ጋር
ወይ ጉድድድድድድድድድድድድድድድድ
እስኪ ራስብሩ ወንድሜ ... ፒያኖውን አውጣና አናግረው
.................
በኔ ተረዳሁት ,.... ሸጌዋ ... ሰው ፍቅር ከያዘው
ለካስ በድንኑ ነው .. የሚወዛወዘው
...........
ጮኬ አላውራው እንጂ ... ማፍቀሬን አልክድም
ጤና ነስተሽኛል ... ጨርሼ ባላብድም
ወይ ጉድድድድድድድድድድድድድድድ .. ምን ነካኝ በናታቹ
.................
ዛሬስ .. ደሞ ምን ነካኝ
ምነውውውው የሚያስተክዘኝ
ምነውውውውውው ምን ጉድ አገኘኝ
.............................
የዛሬውስ መውደድ ... እንሰፍስፍ አረገኝ
እንስፍስፍ አረገኝ አስጨነቀኝ
........................
ምነው ዛሬስ የሌለኝን አመል እግሬን መንገድ መንገድ
ከርተት አይኔ ሆዴም ባባ ባባ ልቤን ጎርደድ ጎርደድ
ሰውነቴም ጎኔም ጠጋ ጠጋ ካንቺው ለመድ ለመድ
.....................//.........
እረ ምን ነካኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝ
የትም ይሁን የትም .... መች ትዘነጊያለሽ
ድንገት ከፊቴ ላይ ድቅን ትያለሽ
ዘወትር በሀሳብ ካንቺ ጋር ስላለሁ
ምንም ምንም ሳረግ አስታውስሻለሁ
ምንም ምንም ሳረግ አስታውስሻለሁ
እማዬ ደህና ነሽልኝ ዎይይይይይይይይይ
እወድሻለሁ በጣምምምምምምምምምም
.........................//..................
እስኪ ይብቃኝ
ልውጣ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የጃማ ጦስኝ

ኮትኳች

Joined: 02 Sep 2007
Posts: 238
Location: ጃማ

PostPosted: Wed Sep 22, 2010 12:12 am    Post subject: Reply with quote

ታስሬ ከርሜ ዛሬውን ወጣ ስል ;
ላምሮት በላሁ ብዬ ነገር ሳሰላስል ;
ለቃቅሜ ቃምኩት ቀልዱን ጫት ይመስል ;
ከየስንኙ ስር አገኘው ይመስል ::
አሁን ምን ሊረባኝ የስንኝህ ፍሬ ;
ድንገት ብቅ ብትል ልደበቅ አፍሬ ;
ተው በዘመድ ሀገር ጡር ነው ደግም አይደል ;
በትዝታህ ቅሪት ባምሮት ሰው አትግደል !ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
የእናትህ ቀምጣላ አንተ ልዩ ፍጡር ;
የመውደድህ ቅሪት ሆነናል ነፍሰ ጡር ::
ዛሬ ቀበጥ አርጎኝ ነገሩና ባላውቅም ;
አንተም አንጎራጎርክ እኔም ቃልክን ልቅም ;ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝኝን
የከበረ ሰላምታዬ ለሁሉም ይድረስ ::

ቅርንፉድዬ በደህና ነው የጠፋሽው ?

እህታችሁ የጃማ ጦስኝ ]
_________________
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ Question

http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=26693
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Sep 22, 2010 8:06 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ታስሬ ከርሜ ዛሬውን ወጣ ስል ;
ላምሮት በላሁ ብዬ ነገር ሳሰላስል ;
ለቃቅሜ ቃምኩት ቀልዱን ጫት ይመስል ;
ከየስንኙ ስር አገኘው ይመስል ::

ታስሮ የከረመ ለግላጋ ገላ
ለላንቲካ ብሎ ነገሬን ቢበላ
ቀልዴን ጫት ይመስል ለቃቅሞ ቅሞት
ገራባ አሳጣን ከመቃሚያው ቤት
መጥኔ ለእንትና
Quote:

ተው በዘመድ ሀገር ጡር ነው ደግም አይደል ;
በትዝታህ ቅሪት ባምሮት ሰው አትግደል !

በዘመድ አገር ስም ጡር አትቋጥሪብኝ
እንደወረድሽ መጥተሽ እንትን ልቀቂብኝ
መቶ ብር አማረኝ እንዳለችው ሚስቴ
አምሮሽ አምሮሽ አምሮሽ
አምሮሽ ይለቅሻል አታስቢ እህቴ
Quote:

የእናትህ ቀምጣላ አንተ ልዩ ፍጡር ;
የመውደድህ ቅሪት ሆነናል ነፍሰ ጡር ::

የናቴ ቀምጣላ እኔ ልዩ ፍጡር
በንፋስ አውቄያት አረኳት ነፍሰጡር
9ወር ሲሞላት አስታቅፋኝ ልትበር
እምቢየውውውውውውውውው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
....................//..................
ጃሚቲ ስምሽን ሳየው እንዴት ደስ አለኝ መሰለሽ
እረ አትጥፊ ሙች
ልትረሺ ሩብ ደቂቃ ሲቀር ነው የመጣሽው

ያቺ ወለዬ እህትሽ እንደሆነ .... ራስብሩ አጣልቶን ... ይኸው በጣሊያን መቀርቀሪያ ... ጥርቅም አድርጋ ዘግታኛለች
እስኪ ይዘሻት ነይ
እንደድሮው ይመርባቹ ... ተቃቅፋቹ ፎቶ ተነሱና ላኩልኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Wed Sep 22, 2010 10:04 pm    Post subject: Reply with quote

-- ለቃቅሜ ቃምኩት ቀልዱን ጫት ይመስል .......
ግርም ብሎኝ ነው የሳቅኩት :
ሳላስብ ተይዤ በሷ ፍቅር ተቃጥዬ
ለመኖር አጠራጠረኝ ከዚያች ልጅ ተነጥዬ
ምን ልሁን መድረሻው ጠፋኝ የዛች ልጅ
በድንገት ፍቅሯ ገረፈኝ ....... ወዘተ የሚል ካሴት ጥላሁን አለው
ይቺ ካሴት ከሌሎቹ የተለየች ናት ታስታውሳታለህ ?
እንዴት ዘፋኝ እንዳልሆንክ ገርሞኛል ይቅርታ ለካ ዘፍነህ አልሸጥልህ ብሎህ ነው
የተውከው እስቲ ከዛች ለማሳተም ከሞከርካት ካሴትህ ግጥሞች አንድ ሁለቷን ስንኝ
አሰማን ::
ሌላ ደሞ አንድ ዘፈን ትዝ አለኝ
የፖሊስ ያለህ የጦር ሰራዊት
ያቺን ልጅ ጥሩልኝ የኔን መድሀኒት ............. ዘፋኙ ማነው ?

ጽሁፉን አንስቼዋለሁ
ባለሱቅ ስለ አራዳ ቆንጆዎች አንተስ ምን ትላለህ ?
ልጁን ተሳስተህ ነው ቆንጆ ያለው እኛ አካባቢ ነው አራዳ ምን ቆንጆ አለና ነው ?
ልለው ነበር አንተን ፈርቼ ተውኩት ::

ሰላም ሁኑ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg

Last edited by ራስብሩ on Thu Sep 23, 2010 3:36 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 23, 2010 2:29 pm    Post subject: Re: ቅሩንፉድዬ Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
ወይኔ እንደገና ሳነብሽ ምን እንዳየሁ ታውቂያለሽ .... የወይንሸት ምትኬ !,,,, ዋውውውውውውውውው አውቃታለሁ እኮ .. ወይንሸትን .... ወፍራሟ ናት አይደል .... ውይይይይ 6 ክፍል ሚኒስትሪ ወድቃ ያለቀሰችው አይረሳኝም ... ቅቅቅቅቅቅ ግን በስተት ነው ተብሎ ተስተካክሎላታል መሰለኝ .... የኔ ባች ናት .... ከማህደረ /ትንሳኤ ጋር ሆነን ... ብዙ ብዙ ትዝታ አለን ... ከወይንሸት ጋር
የት ይሆን ያለችውውውውውውው
እረ ያለማየሁ ባንቲ ልጆችስ ... እነ ኤልሳ ትግስት ወዘተ ... እስኪ የሚያውቃቸው ይተንፍስብንንንንንን

ቸር ይግጠመን

ራስብሩ ወንድሜ
ዛሬ ያወራኸውን ወሬ አይቼ የዛሬ 5አመት ነካክቼ የተውኩት ነገር ነው ትዝ ያለኝ .....
ከላይ እንደምታየው የፃፍኩት መስሎኝ ነበር ... ግን አልፃፍኩትም እና እንድፅፈው አድርገኝ
እና
እና ዛሬ ላንተና ለዶ / ተስፋ መልስ ከመፃፌ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ወደድኩ
1: / ተስፋ ጤና ጣቢያ ነው ወይስ መብራት ኃይል ነው ሚሰራ የነበረው
2: በስንት አመተምህረት ነበር እህቴን ያሽኮረመመው
3 : ሱቃቸው ምኑ ነው ... ወይም የማን ልጅ ናት ....
በጨረፍታም ቢሆን ይህችን ነገር ትንፍሽ ካለኝ ... እኔም የማውቀውን ቱስስስስ እልላቹዋለሁ .... እንደሽንብራ ፈስ

እና ኳሱ ያለው ራስብሩ እና አዲሱ ጓደኛው ጋር ነው

እኛ ሳናውቅ የሱቆቻችን ልጆች በቀላሉ ደብዳቤ አይፅፉም ለወንድ ... በልልኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ኳሷን በቶሎ ወዲህ መልሳት እና ላጫውታቹ ጉዳዩን

አለበለዚያ ልጅቷ ጋር እደውል እና .... እንዳልድራት ለሌላ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Thu Sep 23, 2010 3:55 pm    Post subject: Reply with quote

እንደው አንተ ልጅ ምን ይሻልሀል ? እኔ የጻፍኩትና አንተ ትዝ አለኝ የምትለው ምን ያገናኘዋል ? ብዙ አትቃም አላኩህም ቅቅቅቅ እንደልማድህ ውረድብኝ
ደሞስ አንተ የጠየከኝን ጥያቄ ከመለስኩልህማ አንተ ምን ልትናገር ነው ?
እንደገባኝ ግን ታሪኩን ታውቀዋለህና አጫውተን
ለማንኛውም ልጁ ራሱ ቤታችንን በደንብ ጎብኝቶ መደሰቱን ከመግለጹም በላይ አጠቃላይ ትዝታውን ሊያጫውተን ስለፈለገ የኔን አንስቼዋለሁ ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 23, 2010 5:01 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
እንደው አንተ ልጅ ምን ይሻልሀል ? እኔ የጻፍኩትና አንተ ትዝ አለኝ የምትለው ምን ያገናኘዋል ? ብዙ አትቃም አላኩህም ቅቅቅቅ ::

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አይ ራስብሩ
የዛሬ 5 አመት የፃፍክት ነገር ውስጥ አንተ የማይታይህ እኔ ብቻ የማውቀው ታሪክ አለ ..... በሰአቱ ልፅፈው አስቤ እንደነበር ነገር ግን ያልፃፍኩት .... ነካክቼ የተውኩት ነገር ነው
በጥሞና ካላነበብከው .... በፍፁም አታገኜውም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ሲበላህ ይክረም አቦ
ብሽቅ
ህየራሳቹን ኮታ ቅማቹ ቅማቹ ቅማቹ .... አሁን በኛ ታሾፉ ጀመር አይደል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ይልቅ ቶሎ ጫፍ ጫፉን ንገረኝ .. ወይም ጓደኛህ ራሱ መጥቶ ካላጫወተን .... ምንም አልናገርም
ዲዴ
ጪጭ
ዝምምምምምምም ነው ምለው

እንዴ እንዴ ይህንን እየጥሣፍኩ እያለ ነው ፅሁፉን እንዳነሳህ ያየሁት
ምን ነካህ .... ምን ተፈጠረ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ተደረሰበት እንዴ ጉዳዩ
ወይኔ ጉዴ .... የታባቴ ልግባ ይሆን
እውነትም ቀዥቃዣ .... ነጋዴ
በጩሉሌ በርጫ መርቅኜ ... ምዘላብድ ነኝ ለካስ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በቃ እኔም አንስቼዋለሁ
ጓደኛህ እስኪያወራው እየጠበኩ ነው
በተረፈ
Quote:

ባለሱቅ ስለ አራዳ ቆንጆዎች አንተስ ምን ትላለህ ?
ልጁን ተሳስተህ ነው ቆንጆ ያለው እኛ አካባቢ ነው አራዳ ምን ቆንጆ አለና ነው ?
ልለው ነበር አንተን ፈርቼ ተውኩት ::

ያልከውን አይቼ እንደው ግርምምምምምምምም ሲለኝ ነበር ያደረው
እናንተ ሰፈር ቆንጆ ቢኖር ነው እንዴ .. ያንን ሁሉ ዳገት ቁልቁለት .... ወንዝና ሸንተረ ....
የውሻ ጩኸትና ... የኛን ግልምጫ ችለህ
ያቺን የመሰለች ወርቅ ሚስት ያገኘኸው
ወይስ ተረሳህ አጠገብህ ያረካት ውቧ ሳሪቲ የማን እንደሆነች ?
ወይስ ስታገባት ... ጊዜ የራስህ አድርገሀት እንዳንተው 01 ቀበሌ የገባች መሰለህ እንዴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ብዙ ልወርድብህ ነበር
አሳዘንከኝ
አስኮናኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በል ግንባሯ ላይ ሳምልኝ ሳሪቲን
ልብ አድርግ እጠይቃታለሁ !
!.... እንዳላስመልስብህ
ቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Sep 25, 2010 8:33 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ራስ ብሩ ጽፎ የሰረዘውን ጽሁፍ ስላነበው በመቅረቴ በጣም ተቆጭቻለሁ ::የጀመራችሁትንም ጨወታ
ላለማባለሸት አይን አይናችሁንም ብናይ
ብቅ የሚል ሲጠፋ ግዜ ሰላም ለማለት ጥልቅ ብያለሁ ::አሁን ከለሊቱ 1:20 ሆኗል ::
አርብ ለቅዳሜ አጥብያ ማለት ነው ::ያው እንደሚታወቀው
አርብ ጾም ስለሆነ ጠብቄ 12:00 (ሚድ ናይት ) ጾም መፍታቴ የተለመደ ሆኗል ::ከዚህ ሰአት በኌላ ወደ ቅዳሜ ስለሚቆጠር
እኛም ከስጋው መቆንጠራችን አግባብነት እንዳለው ከያዝነው ብርጭቆ መረዳት ይቻላል ::
በሞቅታ መንፈስ አንድ ሁለት መተንፈስ እስከናካቴው ከዋርካ እንዳያጠፋኝ ብዙ ሳልዘላብድ ባይይይይይይይይይይይ ብያለሁ ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sat Sep 25, 2010 9:31 am    Post subject: Reply with quote

የቆየ የፍቅር አጀማመር ታሪክ ነው ሞፊቲኮ በል ብርጭቆህን እንደያዝካት ነገ እሁድ ባለፈው የቀረህበትን ምክንያት ይዘህ ለመምጣ ሞር
ሌሎቻችሁም ደግማችሁ እንዳታሰጡን አደራ ከወዲሁ እላለሁ
ዛረ ፍራንክፈርት የመስቀል በአል በድምቀት ይከበራል አሁን ወደዛው
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Sep 26, 2010 6:54 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

በዛሬው የፓልቶክ ውሎ ለጥቂት ደቂቃዎች ከተወያየን በኌላ ራስ ብሩ በነበረት ጥሪ ከምሄድበት ቦታ ኮንታክት ሊያደርገን
እንደሚችል ቢገልጥልንም እስካሁን ብቅ አላለም ::
ራስ ብሩ ከፍራንክፈር ወጣ ያለች መንደር ላይ ከነቤተሰቡ የመስቀል ክትፎ ተጋብዞ እንደሄደ ብንረዳም ምናልባትም
የክትፎው ማወራረጃ አወራርዶት በዛው የቀረ ይመስለኛል ::

ለማንኛውም እኛም ከምንደበር ብለን አንድ ሁለት ሙዚቃዎችን የለቀቅን ሲሆን የግል የአስቴር ሙዚቃን
በራሷ ድምጽ በማንቆርቆር ተንቆርቁራለች ::
ሞፊቲም የቴዲን አዲሱን ፍቅር ያሸንፋል የሚለወን ተወዳጅ ሙዚቃ በሀኒከን አስተዋዋቂነትና በሄኒሲ ኮኛክ አጃቢነት በራሱ ድምጽ ሲያሰማ
ሩሙ በሙሉ ነበር የተነቃነቀው :: ይሄ ሙዚቃ ማስታወሻነቱ ዛሬ ለተወያየንበት ይሁንልን ::
ፍቅር ያሸንፋል !!!!!!!!!!!
ዘምባባ ይሟሻል !!!!(ራስ ብሩ ተንከትከት አሉ ?)

ቸር እንሰንብት !!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Sep 26, 2010 7:33 pm    Post subject: Reply with quote

አይ ያንተ ነገር እስክመጣ ድረስ እንደህ አይነት ነገር እንድርሚጠብቀኝ በደንብ ገምቼ ነበር እንዳሰብኩምትም ሆነ ::
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በሳቅ ገደልከኝ አንተ ጉጂ
ይገርምሀል የመጣንበት ቤት ኮምፒዩተር ላይ ፓልቶክ ሎግ ኢን ሳደርግ አዲስ አፕዴት አድርግ አለኝና ኦኬ ስለው ይሄው አንድ ሰአት ሊሆነው ነው ኮምፒዩተሩ ከየት እንደሚያመጣው አላውቅም እስካሁን ተኝቶበታል : ቢቸግረኝ ወደዚህ ብቅ ስል ሞፊቲ እንደጠመኩህ አገኘሁህ ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Sep 28, 2010 1:49 pm    Post subject: Reply with quote

እንኳን ለመስቀል አድርሶ አሳለፋቹ
ክትፎ የበላቹም
ዶሮ የበላቹም
በግ ያረዳቹም
ዳመራ የዳመራቹም
ቦሾ በልተን ከዋልነው ጋር
እንኳን በሰላም አደረሳቹ እናም አሳለፋቹ

ብትናፍቁኝ ነው ብቅ ማለቴ
እባካቹ አትጥፉ በሞቴ
የግል መኑዬ ቅሩንፉድ
ቦሪቲ አይፋ የኛ ውድ
ድምፃቹን ሳጣ አስቤ
በጣም ተጨንቄ ተጠብቤ
በግጥም ጠራኃቹ ከልቤ

ባላህ በግዜር እረ
ይጫጫስ ከርቤው እጣኑ
ቡናው ይፈላ .. ይፍካ ፈንዲሻ
ደስ እንዲለው ይህ ሆደባሻ
ራስብሩ ጋቼ የቤቱ ጋሻ

ሞፍቲ ባለሱቅ አንፈራራ
ሽልንጌ ቺኮ ....የተራ
እንጥራውን ባንድ ድምፅ ያንን ኮስታራ
አደቆርሳችን የኛ ባንዲራ
የቤታችን ዋልታ አንተ ቀብራራ
ለዛህ ጨዋታ የማይጠገብ
አንተ የሰው ሰው የሰው ገንዘብ
የህይወት መፅሀፍ ሁሉን አዋቂ
ለተባት እንስቱ ተናፋቂ

እረ አደቆርሳ ቶሎ
ሴቱ ተለክፎ ባንተው ዝና
ካልመጣህ ብሎ አምፅዋልና
ቶሎ ሸጋው ቶሎ
የወዩ አድባር አኩርፏልና
የስሙኒ ቅቤ ይዘህ ቶሎ
ቶሎ .. አንተ ሰው ቶሎ
ልክ እንደ ያኔዋ ደሀ ... ቡና
በናፍቆት ብሽቀት ደም ታፈላና
ሳልከሰክሰው ይህን ጀበና
ቶሎ ጋሼ ቶሎ
........................//......................
ዸሀብዬ ደህና ነሽ በናትሽ
ድምፅሽ ናፈቀኝ ከምር
.........................//...................
ያገሬ ልጆች በርቱና
አንፈራራ ላይ ውጡና
ለአደቆርሳ ቅርቡ ነውና

እስኪ ተጣሩ ከፍ አድርጉና
ሁላቹም አንድ ላይ ሁኑና

........................................................ ... ....
አደቆርሳሳሳ
................ ተብለሀል ወደ ...ምሳ
ዋርካዋስ ስር እንቋደስውሳ
!
ሰላም ክረሙ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 782
Location: united states

PostPosted: Wed Sep 29, 2010 2:14 am    Post subject: Reply with quote

[quote="ባለሱቅ "]እንኳን ለመስቀል አድርሶ አሳለፋቹ

ብትናፍቁኝ ነው ብቅ ማለቴ
እባካቹ አትጥፉ በሞቴ
የግል መኑዬ ቅሩንፉድ
ቦሪቲ አይፋ የኛ ውድ
ድምፃቹን ሳጣ አስቤ
በጣም ተጨንቄ ተጠብቤ
በግጥም ጠራኃቹ ከልቤ

##################################

ዋውውው ባለስቅዩ ግጥም ብሎ ዝምምምምምምምምምምም
ደስስስስስ ስትል አንተ ድምፅ ብቻ ሳይሁን ግጥምም ትቸላለህ ለካ ጎሽ ጎበዝ ትንሽ ቆይተህ ደሞ የግጥም መፅሀፈ አውጥቻለሁና ሽጪ እንዳትለኝ ቅቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ ከምርርርርር ..........................

ውድድድድድድድድ
የግልልል
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Fri Oct 01, 2010 2:33 pm    Post subject: Reply with quote

ጽፌ ጽፌ ገደል ገባ
አይ ዋርካ ዛሬ አናደደቺኝ ደግሞ ለመጻፍ ሞራሉም ይጠፋል
ለሁላችሁም ሰላም ብያለሁ

ባለሱቅ የግጥም ችሎታህን አድንቄያለሁ ቺኮ እና ሽልንግዬ ብቻ መስለውኝ ነበር ለካ የዋዛ አይደለህም ::
ራስህ የጻፍካቸውን የዘፈንህን ግጥሞች ብቻ ለምን እንደደበቅካቸው ግን አላውቅም ::
ሰላም ሁኑ
በቺሊ ሀገር በማዕድን ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች በህይወት እንዲተርፉ እግዚአብሄርን እንለምናለን
ቁፋሮው ተስፋ ሰጪ እየሆነ ነው እግዚአብሄር ይርዳቸው
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1043
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Oct 03, 2010 1:12 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ ሸግዬ
እስኪ ፉገራህን ትተህ .... ዋርካ የበላብህን ፅሁፍ እባክህ እንደገና በሞራል ፃፈው ..... እጅ መስጠት እማ አይገባህም ... ወንድ አይደለህም እንዴ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ... ሴቶቹ እኛስ ብንሆን ምን በፆታ ትለያያለህ ችሎታ ሲሉኝ ሰማኃቸው ....
ምን ጊዜው የነሱ ሆኗል ..... እንዳሉት ይሁንና ... ራስብሩ ወንድሜ .... እየጠበኩ ነው
ብዙ ብዙ ማወራቹ ነበረኝ .... ሙድ ፈጣሪ ጠፋ እንጂ .....
የግልም እየሳቀች ... እያስካካች ውልቅ ሆኗል ስራዋ
ሞፍቲም .... ልጅ መሸከም ጀመረ መሰለኝ .. እንደኔ ..... እጆቹ ኮምፒተር ከነኩ ወራቶች ተቆጠሩ ....
እኔ ልጅ ስሼከም ..... ጀርባዬ ላይ ጥፍር አድርጌ አስረውና .... ጡጦውን ..... በብብቴ መሀል አሾልኬ አፉ ላይ ደቅኜ .... እጆቼን ነፃ አድርጌ ነው ዋርካ ምመጣው ...... ደግነቱ ጀርባዬ ላይ ሲሆን .... ይመቸዋል መሰለኝ ... ወዲያው ነው እንቅልፍ ሚወስደው
ሞፍቲሻ ... እንዴት ነው ጀርባህ ... እንደጣውላ ጠፍጣፋ ነው እንዴ ...... እንደጃፓን ሴት .... ወገብ ብሎ እግር አይነት ነህ መሰለኝ ... የተሸከምከው ልጅ እንዳስቸገረህ ታስታውቃለህ ... ከዋርካ አጠፋፍህን ሳየው

እስኪ ሶፋው ላይ አስተኛውና .. ጡጦ አፉ ላይ ደቅነህ .. ብቅ በል .. እና አጫውተን .... ስለ ..... እንትን ....
ልታወራ ፈልገህ አፍነህ ስላስቀመጥከው ነገር
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
............................
እናንተ ዶሮ አፍቅራቹ ታውቃላቹ
ወላሂ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በዶሮ ፍቅር ብክንክንንንን ብዬላቹዋለሁ
ወይ ጉድድድድድድድድድድድ
ዶሮ አሳዳጊዎች ምን ይሉኝ ይሆን
እስኪ ሙድ ሲመጣ አጫውታቹዋለሁ .... ማስታወሻ ላይ ያሰፈርኩት ነገር የለም ... ካልተረሳኝ .... ከመጀመሪያው ጀምሮ አወጋቹዋለሁ
ደሞ የምን የዶሮ ታሪክ ልታወራ ነው እንደምትሉኝ አምናለሁ
ባለሱቅ ማለት እንደዚህ ነው ...... ካዳመጡት ሚረባ ማይረባውንም ነው ሚዘከዝከው
ሰሞኑን በዶሮ ፍቅር ተለክፏል
አትሳቁበት አደራቹን
ከልቡ ነውና የሚያወራው

በተረፈ
ሙድ ቤቱ ውስጥ ሲገባ .... ያወራቹዋል የሰሞኑን የዶሮ ፍቅር
ጥላሁን ምን አለ መሰላቹ
ባህር ይገባሉ ወንዞች ወርደው ወርደው
አብረው ይኖራሉ እርግቦች ተዋደው
እንስሳት አእዋፋት ጥንድ ጥንድ ናቸው
ሲያዩት ይማርካል የዘውትር ኑሮ 'ቸው

በርግጥ ይህንን ግጥም የገጠመው ሰውዬ .... የእንስሳቶችን የጋለ ፍቅር አይቶ ተረድቷል ማለት ነው .... እራሱን የቻለ ትልቅ የጥናት ውጤት የሚወጣው ነገር እኮ ነው
እንዴት ያምራል ባካቹ የተፈጥሮ ውበት
ብዙ ተመራማሪዎች እንዳጠኑት እና ብዙ እንደፃፉበት ባውቅም .... አንብቤ ስለማላውቅ .... እንደአዲስ ... እንደሞኝ ... ከተፈጥሮ ጋር ... በጎረቤት ዶሮ ምክንያት ፍቅር ወድቄአለሁ
የደላህ እንደምትሉኝ አምናለሁ
ደልቶኝ ግን አይደለም .... በቢዚ ህይወቴ ውስጥ እየገቡ እንድከታተላቸው .... ስላስገደዱኝ እንጂ ....
ዶሮዋና ዶሪቷ

በምሽት ጨረቃ ... በንጋት ፀሀይም
ህይወታችን ፋፋ በጣም ....
ተፈጥሮን አድንቀን ... ውበትን ስናይ
ወይ ጣፈጠን ... አንቺን ስለሰጠን
ውበት
የግዜር ጥበብ .. አትጠገብ
እውነት እኮ ነው ..... የተፈጥሮ ውበት ሁሌ አዲስ ነች

ውበት የግዜር ጥበብ ... ማትጠገብ /..... አለ ጥልዬ .... ነፍስ ይማር
በተፈጥሮ ውበት ... በዶሪቷ ፍቅር ውድቅቅቅ ብዬላቹዋለሁ
እባካቹ አትሳቁብኝ
በልጅነቴ ዶሮ ኖሮኝ ስለማያውቅ ይሆናል ... ዛሬ እንዲህ ያደረገኝ
ወይ ተፈጥሮ

ኦህ ... ሰላም ቆዩኝ

የአደቆርሳ ጥሪዬን ምነው ጣል ጣል አደረጋቹዋት
ራስብሩማ .... እኔን አንዱን መናጤ የብዕር ቦጫሪ ምስኪን ... ከነ -ሽልንግዬ እና ቺኮ ጋር እያወዳደረኝ ... የመልክቴን ጭብጥ ገሸሽ አደረገብኝ
በጣም አዝኛለሁ
እባካቹ .. ሰዎች
ጥሩልኝ ያንን ሰው
ቤቱን የምታውቁ ...
አሳዩኝ ልሂደው

እባካቹ ሰዎች ውሰዱኝ ስትሄዱ
ፍቅር ጋር መድረሻ በየት ነው መንገዱ
እያላቹ ለአደቆርሳ ዝፈኑልኝ
በጣም ነው የናፈቀኝ እኔን

እናንተንስ

እስኪ እንመለሳለን ...
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 311, 312, 313 ... 379, 380, 381  Next
Page 312 of 381

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia