WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 368, 369, 370 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 13, 2012 5:06 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ሞፊቲ !!
Quote:
መነሻ ሀሳቡን ከቦኔያ ላይ የዘረፍክ ይመስለኛል ::ለነገሩ አንተ ግጥምም ሴትም እንደዘረፍክ ነው ::
ወይ አማርኛ !!! ሁሌ እንደተዘረፍኩ ነው እድሜዬን የጨረስኩኝ : አንድ ሳልዘርፍ :: በኔያ አሁን ፈዟል እኮ : አንተ እንደምታውቀው አይደለም :: ከምር ከሱ ምንም አልኮረጅኩም ::

ሁሌ ከቦሬ የመጣ እንግዳ አንተ አይጠፋም :: አስመጪ እና ላኪ ሆነሀል እንዴ ? ህገ -ወጥ ሆኖ ብቻ ሌላ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ቅቅቅ :: ደግሞ አታስጎምዠና የማይሆን ወሬ እያወራህ :: እኛ እንግዳ በክብር ሲስተናገድ እንጂ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ ሲል አናውቅም ቅቅቅ :: የቀና እና ምን የሆነ ...ብቻ እንዳትለኝ ቅቅቅ ::

ውድ ራስብሩ ስለአስተያየትህ እግዜር ይስጥልኝ :: ስራ ስፈታ የምጭረው ነገር ነው ::

ባለሱቅ ለሁለት ቀን ብቅ ይልና ለሁለት ወር ይጠፋል :: ለነገሩ እሱ ይሻላል እኮ እንደነ አይፋ ለዘመን መለወጫ ብቻ 'እንክዋን አደረሳችሁ " መልዕክት ይዘው ባመት አንዴ ብቅ ከሚሉት :: እሱ ሲመጣ አንበሻብሾን ነው የሚመለሰው :: ደግሞ የክፉ ቀኔ ስለሆነ ምንም ቅር አልሰኝበትም :: ይመችህ ባለሱቃችን !!
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jul 14, 2012 1:51 pm    Post subject: Reply with quote

ኦህ አምላኬ
የበቆሎ ቂጣ በአሬራ
ሞፍቲዬ ሆዴን አስጮህክብኝ ከምር
ያሳደገኝ የልጅነት ምግቤ (ዌል በሳምንት አንዴ ነው እሱንም ምናገኘው ... የነበረው )
አቤት ሲጥምምምምምምምም የበቆሎ ቂጣ ባሬራ

አሁን ልሄድለት አይደል
ኦውገስት ኢትዮጵያ ነኝ ....
ዊውውውውውውውውውውውውውው ቅኑ ምናባታቹ ታረጉኛላቹ ....
አዮን ይዤ እመለሳለሁ ... አመት ሞላት እኮ
ብቸኝነቱ ገድሏት እመለሳለሁ አለችኝ እኒንጂ ... ዝም ብላ ብትቆይ ደስ ይለኝ ነበር
ለማንኝኣውም እንደገባች ነው የበቆሎ ቂጣ ባሬራ እንድታዘጋጅና ... ይሄ ሞፍቲን የማስቀናው

ጎስዬ
ምን እንደምልህ አላውቅም
ግጥምህን ሳነበው ምን እንደታየኝ ታውቃለህ
የጀመርከውን ታሪክ የጨረስክበት መስሎ ነው የተሰማኝ
ከኢትዮጵያ ያመጣኸው ሰው ሳይሆንልህ ቀርቶ የሞሪሽየስ ቆንጆ ላይ አምላክ ጥሎህ
እንደተደሰትክና እንደተቸገርክ
ይህወት እንደዚህ አይደልም

ራስብሩአችን
መልክት ካለህ በጓሮ ሹክ በለኝ
ብትደውል አታገኘኝም ... ዘመቻ ላይ ነኝና

ቆይ ቆይ ያልገባኝ ነገር
ሞፍቲ እንግዳ መጥቶ የበቆሎ ዳቦ አስጋግሮ በአሬራ የሚጠጣው ... ሚስቱ ምን እየሰራች ነበር
ወይስ ያዲሳባዋን ነው ላፍ ያደረገው ... እንደኔ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለችኝ ሚስትህ ብትሰማ
ምክንያቱም ሙያ ስለሌላት
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንዱ ኡጋንዳዊ ምን አለኝ መሰላቹ ...
> የኢትዮጵያ ሴቶች ሙያ የላቸውም
* እንዴ ለምን ... ስለው
> የሆነ መሀረብ የመሰለ ክብ ነገር ሰርተው መሀሉ ላይ ወጣወጥ ነገር ያደርጉና ለባላቸው ያቀርባሉ
* እሱ እኮ ምርጥ የሆነ የሀገራችን ምግብ ነው
> እረ ወዲያ ... እኛ ምግብ ምንለው ሩዝን ወይም ፖሾን ነው ... ዳቦ እንኳን ምግብ አይባልም .. እንኳን መሀረብ የመሰለ ነገር
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አየህ ይህ የባህል ልዩነታችን ነው .... ላንተ ጨርቅ የመሰልህ ነገር ለኛ ደሞ ምርጥ የሆነ ምግባችን ነው ..
አንተ ምታወራው ሩዝና ፖሾ .. እኛ አገር ሳይ -ዲሽ ነው ሚባለው .. ዋና ምግብ አይደለም
ህምምምምምምምምምምምምምምምም
ሳንግባባ ላንስማማ ተስማምተን ተለያየን
ደስ አይልም የባህል ልዩነት ... በተለይ ከአገሩ ወጥቶ ለያማውቅ ሰው

እና ያቺ ያዲሳባ ሚስትህን አስተምራት
ሰው አታሰድብ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደለችኝ መቸም ካወቀችኝ

ሞፍቲ በናትህ አስታርቀኝ .. ለመናገር ብዬ ነው እንጂ ለመናገር ፈልጌ አይደለንም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በተረፈ

ምነው አይፋ የጎሳን ታሪክ ሰምታ ምንም አለማለቷ
ወይስ ገና ከኢትዮጵያ በአካል እንጂ በነፍስ አልመጣችም

እስኪ አንድ በይን አንቺ አጣባሽ
አይዞሽ እኛ አናስቸግርሽም .. እራሳችንን የቻልን ነን

ጭልፊት በወንጪፍ ከሰማይ እንጠልፋለን .. እንኳን ከፊልም ቤት ሰልፍ ውስጥ ቀርቶ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ሁኑ አቦ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Jemjem

መንገደኛ

Joined: 14 Jul 2012
Posts: 5

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 12:23 am    Post subject: New Member from Adola Weyu Reply with quote

በአጋጣሚ google አዶላን ስጎለጉል ራስ ብሩ የሚል የቀድሞ /ቤቴን ስም በማየቴ የነ ባለሱቅን አስቂኝ ጉዶች በማየት ቀኑን ሙሉ በጽሁፎቹ ስዝናና ዋልኩኝ :: ሰሞኑን ወደ አዶላ ብቅ ብዬ ገፉማና ዳቦ ሸዌ በአይኔ ሳላይ ተመለስኩኝ :: አስፋልቱ ግን ተመችቶኛል :: ከተማ ሲያረጅ አዶላን ይመስላል የሚለው አባባል በቅርቡ ይለወጣል ብዬ አስባለሁ :: በቆይታዬ ስለ ክብረ መንግስት በድሮ ትዝታ ብዙ የተዝናናሁበትን ሰሞኑን ብቅ ብዬ አወጋለሁ :: ጥሬ በጉንጩ ይባል ስለነበረው አስተማሪ (ነብሱን ይማረውና ), የአባ ዝናብን በግ ይሰርቁ ስለነበሩት ቀማኞች , አሁን ጃፓን ስለሚኖረው ጉደኛ የአዶላ ጩሉሌ የሰማሁትን ብዙ አስገራሚ ነገሮች , ኔንቆ ስለሚባል ጎበዝ ተማሪና አባት ጦር ስለሚባሉት ዳሬክተር , ሌሎችም .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 12:59 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖቼ እንደምን አላችሁ ? የከበረ ሰላምታዬን ከወገቤ ጎንበስ ብዬ አቀርባለሁ ! ራስ ብሩ የኔ አስታዋሽ : አንተ ነህ የጠፋ ሰው ብለህ ስሜን ያነሳህ ; ወንድሜ ጎሳ እንኳን ደስ አለህ ! መቼም ታሪከኛ ሰው ነህ ! በእዉነት አላዉቅህም ነበር ማለት ነው ! የጻፍካቸዉን ለማንበብ ሞክሬ ማመን ነው ያቃተኝ ::እኔም እንዳንተው የአምላክ ፈቃድ ሆኖ = የአብስራ እንዲሁም ቅጽል ስምዋ ( የጀምጀም ወርቅ የቦሬ አበባ ) የተባለች ህጻን አባት ሆኛለሁ :: ወንድሞቼ እህቶቼ ሰላም ሁኑልኝ ! ረዥም ጊዜ ለጠፋሁት ከፍተኛ ይቅርታ እጠይቃለሁ !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 5:23 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ውድ ወንድሜ ወቤ (ጃሎ )
እኔ እዚህ ቤት መግባት ከጀመርኩ ወዲህ አይቼህ ባላውቅም ሁሉም ሰው ወቤ (ጃሎ ) ጠፋ እያሉ ብዙ ጊዜ ሲያማህ : ይህ ወቤ (ጃሎ ) የሚባል ሰው ምን አይነት ሰው ይሆን ብዬ ወደ ኌላ ተመልሼ መጣጥፎችህን በርብሬ ሳነባቸው እንደው 'እንዴት ጠፋ " እያሉ አንተን ማማታቸው ሳይሆን "አቤት " የሚባልበትን ቅሬታ ሰሚ አካል ፈልገው አንተ እንድትመለስ አንድ መላ አለመፍጠራቸው ነበር የገረመኝ :: እኔ ብሞክር ደግሞ "ዱባ ዱፍቴ ሀዻ ምና ታቴ " ይሉኛል ብዬ ስለፈራሁ ይህችኑ የዛሬዋን ቀን ከመጠበቅ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም :: ከጽሁፎችህም ማንነትህን ስረዳማ እጅግ በጣም ታሪከኛ ሰው መሆንህን ስለማውቅ በጽሁፎችህ ተደሰትኩ እንጂ ምንም አልተገረምኩም :: ቦሬ በነበርክበት ወቅት ካንተ ጋር ለመዋል ብዙ እድል ባላገኝም ኡሞ ስላንተ ይነግረኝ በነበረው ነገሮች ብቻ ገና ቦሬ ውስጥ ሳይህ ሳቄ ይመጣ ነበር :: ያን ደግሞ ሞፊቲ እንኳ ይመሰክርልኛል ::
Quote:
በእዉነት አላዉቅህም ነበር ማለት ነው ! የጻፍካቸዉን ለማንበብ ሞክሬ ማመን ነው ያቃተኝ

ሞፊቲም እንዲሁ ይለኛል ሁሌ : ያኔ ስታዩኝ ያን ያህል የተኛ ሰው እመስላለሁ እንዴ ? ቅቅቅ ::
Quote:
እኔም እንዳንተው የአምላክ ፈቃድ ሆኖ = የአብስራ እንዲሁም ቅጽል ስምዋ ( የጀምጀም ወርቅ የቦሬ አበባ ) የተባለች ህጻን አባት ሆኛለሁ ::

እንኳን ደስ ያለህ ወንድማችን :: ስሟ ደግሞ ይመቻል ነው የሚባለው :: አንተማ ታድለሀል : ጧት ማታ ታያታለህ :: የኔን አላውራው :: በል እባክህን ከእንግዲህ እንዳጸወርብን ::

አዲሱ እንግዳችን ጀምጀም : ምን እንደምልህ () አላውቅም :: አጀማመርህ () ብቻ ሳይሆን አመጣጥህ () በጣም አስፈራርቶኛል :: በጉግል በኩል ልክ እንደ ኦራል ወይም አይፋ መኪና ዳገት ቁልቁለቱን ሰባብረህ () ነው የመጣኽው (ሽው ):: መከራዬን ስላየሁ እንደ ልማዴ 'እርስዎ " ብል ይሻለኛል : ግን በክፉ አይውሰዱብኝ :: በሚቀጥለው ፖስትዎ ጾታዎን እንደሚነግሩን እና ከዚህ ጭንቅ እንደሚገላግሉን እተማመንብዎታለሁ :: እና ገና አረፍ ሳይሉ አስደንጋጭ አስደንጋጭ ስም ጠሩብን ' ቅቅቅ :: ለመሆኑ ጎበዝ ተማሪ ነው ያሉት ኔንቆ አሁንም እዚያው የሚማር ሰው ነው ወይስ ጡረታ ሁሉ የወጣውን ነው የሚጠሩልን ? ብቻ እስኪመለሱ ድረስ ጓጉተናል :: ሰሞኑን ትንሽ ነገሮችን እየረሳሁ ስለተቸገርኩ ድንገት የዚህ ቤት ፓስወርድ ቢጠፋኝ እንኳ አብሮን በተማረው 'ንጉሤ ' ስም እመጣለሁ :: እንደው የጎሳንም ስም መቀየር ፈልጌያለሁ ቅቅቅ :: በሉ ቶሎ ተመልሰው ስለእነኚያ ስላነሷቸው ሰዎች ከዋርካው ስር አረፍ ብለው ያውጉን ::

የክፉ ቀናችን ባለሱቃችን !!!
Quote:
ጎስዬ
ምን እንደምልህ አላውቅም
ግጥምህን ሳነበው ምን እንደታየኝ ታውቃለህ
የጀመርከውን ታሪክ የጨረስክበት መስሎ ነው የተሰማኝ
ከኢትዮጵያ ያመጣኸው ሰው ሳይሆንልህ ቀርቶ የሞሪሽየስ ቆንጆ ላይ አምላክ ጥሎህ
እንደተደሰትክና እንደተቸገርክ
ይህወት እንደዚህ አይደልም

ቅቅቅቅ :: ያን ያህል የረቀቀ አእምሮማ ከዬት አመጣለሁ ብለህ ነው : ሌላውን ታሪክ በሌላ ታሪክ ግጥም የምቋጨው :: የጽግዬ ታሪክማ እንዲህ ቢያስመርረኝ ኖሮ ስሟንም ለማስታወስ አልፈቅድም ነበር :: አንዱ ጓደኛዬ የገጠመውን ነው የሰጠኝ ለዋርካችን ትሆን እንደሆን አስቦ :: በኮፒራይት ህግ ደግሞ እንዳትወቅሱኝ ቅቅቅ ::

ባለሱቃችን አይፋ ደግሞ ሰሞኑን ብቅ እንደምትል ውስጤ እየነገረኝ ነው :: ወቤ (ጃሎ ) ብቅ ብሎልን እሷ ብቻ ጨክና የምትጠፋበት አንጀት ድሮ እንዳልነበራት አውቃለሁ :: ያሁኑን እንግዲህ እንጃ :: ደግሞ ኦገስት ሄዳለሁ ነው ያልከው ? እዚሁ ቦሬ ላይ የበቆሎ ቂጣ ባሬራ አሰርቼ መንገድ ላይ እጠብቅሀለሁ : አዮን ገና ከመንገድ እንደገቡ ከምታስቸግራቸው ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 7:07 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
የተወደዳችሁ የክብረመንግሥትና አካባቢው ልጆች እንዲሁም መላው ወዳጆቻችን በሙሉ እንደምን ሠንብታችኍል ::
ከጥቂት ዓመታት በፊት ማለትም ከዛሬ ዓምስት ዓመት በፊት ጀምሮ
ወላጆቻቸውን በተለያዩ ሁኔታዎች በሞት ያጡና
ጎዳና ላይ ለመኖር የተገደዱ ወላጅ አልባ ህጻናትን አሰባስበን
ወደትምህርት ቤት እንዲሄዱ ለማድረግ ችለናል ::
እነሆ ሁሉም ልጆች እስካሁን ድረስ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ ::
<< ጓደኞቼ ወደትምህርት ቤት ሲሄዱ እቀና ነበር >> ያለችው 12 ዓመቷ ታዳጊ ትዝታ መሰረት ዛሬ ለኮሌጅ የሚያበቃትን ውጤት አግኝታ መጪውን የትምህርት ዘመን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች ::
ከሶስት አመት በፊት የላኩትን የምስጋና መልክት ከዌብ ሳይታቸው መመልከት ይቻላል
http://www.adola-kibremengst.com/
በአውሮፓ በአሜሪካና በኤሺያ የምንኖር የራስብሩ ተማሪዎችና በተለይም የነዚህን ህጻናት ህይወት ለመታደግ በገንዘብም በሀሳብም በሞራልም ስትደግፉ አብራችሁን ላላችሁ ሁሉ ወንድሞችና እህቶቻችን ባጠቃላይ እጅግ የከበረ ምስጋና በህጻናቱ ስም አቀርባለሁ ::
በለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ልጆቹ እድሜያቸው እያደገና
ፍላጎታቸውም እየሰፋ በመምጣቱ ሞግዚት ኮሚቴው የየወሩ ድጎማ እንዲያድግላቸው በጠየቀን መሠረት እኔም በፓል ሩም እንድንገናኝ አድርጌ ብዙ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተን መነጋገራችን ይታወሳል ::
እኛ የተወያየንበትና የተስማማንበትን ሀሳብ ልጆቹን በቅርበት ለሚከታተላቸው የአካባቢው HIV ዴስክ ኃላፊ አቶ ደበበ ሳህሌ አሳውቄ ሁኔታውን ካጠኑ በኍላ
ለልጆቹ ቋሚ ነገር ለማሰራት ሙሉ ኃላፊነቱን ለመስጠትም ሆነ ለመቀበል ከባድ እንደሆነባቸው ነግረውናል :: ይህም ማለት ስራውን የኔ ብሎ ወጪን ተቆጣጥሮ
ከስግብግብነት የጸዳ ሆኖ ከቢሮክራሲ የሚገጥመውን ውጣ ውረድ ተቋቁሞ
ግዢና አገልግሎትን ..... ወዘተ ይሰራል ብለን የምናምንበት ሰው ልናገኝ አንችልም !
በማለት ግልጽ የሆነ መልስ ሰጥተውን እንደነበር የሚታወስ ነው ::
እንዲህም አሉ በማስከተል ቀላል ሆኖ የሚታየኝ ለባለ ኮንትራት ሰራተኞች መስጠት ነው ይህንንለማድረግ ደግሞ የሚጠይቀን ወጪ አሁን ካለን ገቢ ጋር የሚነጻጸር አይደለም ስለዚህ ወደፊት ሰፋ አድርገን እንድናስብበት ጊዜ ወስደን አሁን ግን ቢቻላችሁ ለልጆቹ የወር ክፍያቸው ላይ ትንሽ ትንሽ ጨምረን እንድንሰጣቸው ብትፈቅዱ የተሻለ ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጭተዋል ::
ኢትዮጵያ ሀገራችን ለዘመናት መጠሪያዋ ሆኖ የቆየው ችግርና ሰቆቃ እያንዳንዱን ጥሩ ኢትዮጵያዊ የሚያመው ጉዳይ መሆኑ አያጠያይቅም : ምክንያቱም ስለምን ተቸገርን ስለምንስ እንዲህ ተባልን ሳይሆን የአንድነታችን ኃይል ማነቆ የሆነው ሰንሰለት ውጤት መሆኑን መረዳታችን ነው ::
አንድ ሰው ጥቂት ብቻ የሚችለውን ቢያደርግ ለሀገሩም ለወገኑም ትልቅ እርዳታ ነው ለነዚህ ልጆች በወር ለመላክ ያሰብነው ሀያ ዶላር ብቻ ነው
ይህቺን በወር ልከንላቸው ከጎዳና ላይ ተነስተው ወደትምህርት ቤት መሄድ ችለው ስናይ
ከእኩዮቻቸው እኩል መሆን መቻላቸውን ስናይ
ምንም ተስፋ ካለመኖር ተምረው በተስፋ ራሳቸውን ወደመቻል ሲሄዱ ስናይ
ሳይበሉ ጦማቸውን አፈር ላይ ከመተኛት ሳይራቡ ማደር መቻላቸውን ስናይ
እርዳታ ማለት ትንሽ ነገር መሆኑን እንረዳለን ::
በህይወታችንስ ይህቺን ያህል አድርገን ይህን የሚያህል ቁምነገር ከማየት የበለጠስ ምን ደስታ ይኖረናል ?
ከወራት በፊት ትምህርት ቤት ደውዬ ያገኘሁት አንድ መምህር ከነገረኝ ውስጥ ነግሬያችሁም ከሆነ ልድገመውና “ሙሉቀን ሮጦ የማይደክመው ጥሩ ስፖርተኛ ወጥቶታል ......
ሙሉቀን ታምራት ማለት ከሀያ አንዱ ውስጥ በእድሜው ትንሹና 5 ዓመት ልጅ የነበረው ነው :: አሁን 10 ዓመት ሞልቶታል :: ትዝ ባለኝ ቁጥር ውስጤ በደስታ ይሞላል ::
http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Adola_childrens_Aid_ACA.jpg ውድ ወንድሞችና እህቶቻችን እነዚህን ልጆች እናስተምራችኍለን ብለን ቃል ገብተንላቸው ከየነበሩበት አስከፊና ተስፋቢስ ሁኔታ ወጥተው
አሁን ትምህርታቸውን በሚገባ በመከታተል ላይ ይገኛሉ : ሆኖም ግን ገና ጨርሰው ራሳቸውን አልቻሉም ጥቂት ጊዜያት ልንደግፋቸው ይገባናል ::
አሁን እኔንም ጨምሮ በዚህ ሁኔታ ትንሽ ወደኍላ ያልን እባካችሁ ለእነዚህ ወጣት ልጆቻችን እንድረስላቸው :
ሀያ አንዱም ውስጥ አንዱም እንኳን በትምህርቱ የደከመ የለም ሁሉም ጎበዝና ጥሩ ተማሪዎች ናቸው ::
እንዳልኳችሁ የፈለኩትን ሁኔታዎች አሟልቼ ማግኘት እንደቻልኩ በቅርቡ ስለ እያንዳዳቸው ልጆች አሁን ያሉበትን የትምህርትና የኑሮ ሁኔታ የሚዳስስ ቢቻል በዶኩሜንት የተደገፈ
ሪፖርት በቀጣዮቹ ቀናቶች ውስጥ አቀርባለሁ ::
እጃችሁን ከመዘርጋት ወደኍላ የማትሉ የአዶላና አካባቢው ልጆች የራስብሩ ወልደገብርኤል ተማሪዎች የምትወዱን እና የምንወዳችሁ ወዳጆቻችን ልጆቻችን መንገድ ላይ እንዳይቆሙእና የወጡበትን የተስፋ መቁረጥ ህይወት ተመልሰው እንዳያዩት የእያንዳዳችን ድጋፍ ወሳኝ ነውና ለህጻናቱ እንድረስላቸው ::
http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Scan0004.jpg

አክባሪያችሁ ራስብሩ

_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 7:44 pm    Post subject: Reply with quote

ውድ ጀምጀም ቤት ለምቦሳ ብለናል እንኳን በደህና መጣህ //
ይህንን ሩም ስላገኘህ እንደተደሰትክ ከጽሁፍህ መረዳት ይቻላል ስለ አስፋልቱ ጀመር ይድርገህ ነበር እስቲ በደንብ ንገረን ከምን ደረሰ ? ትዝታዎችህንም አካፍለን ::

ወቤ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል በውነት የናፍቆት ቤት ነው አንተ ስትመጣ የሆነ ደስታ ነው የተሰማኝ የቦሬ አበባ ትለምልምልህ ::
ዘንድሮ በኦሎምፒክ ምክንያት እንገናኛለን ብለን ነበር አለቆች ፈቃድ ከለከሉ እንደውም አለበለዚያ በዚያው ሁሉ ሲሉን ፈርተናል እልሀለሁ ::
በል አትጥፋ
ባለሱቅ እሺ እደውላለሁ በተረፈ ሰላም ሁኑ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 8:06 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ ወንድሜ

ለመልካሙ ዜናህ ከልቤ እያመሰገንኩህ ... እኔም በቅርብ ቀን የድርሻዬን ለበጅሮንድ የግል እንደምልክ ቃል እገባለሁ

ያልከውንም ሀሳብ እቀበላለሁ .... በየወሩ የሚሰጣቸው ገንዘብ ላይ መመሩ አስፈላጊ ይመስለኛል
ሌሎቹም በሀሳቡ ከተስማሙ .. Please Go Ahead

አንድ ጥያቄ ግን አለኝ
ይህ የልጆቹ ሆምፔጅ መቼ ነው ተገንብቶ ሚያበቃው ...
ሁሌ Under Construction ማለቱ አልተመቸኝም
እዛ ውስጥ እየገባን .. እንድንዘባርቅ በሩን ደሞ አሳየን አቦ

የግልዬ መቸም እስከዛሬ ስለታገስሽኝ አመሰግንሻለሁ ... ከዚህም በኃላ ትንሽዬ ብቻ እንደምትታገሺኝ አምናለሁ
በቅርብ ጊዜ ሁሉ ነገር ስለሚስተካከል
አብሽር ቃል የገባነውን እናሟላለን

...........................//...................
ጀምጀም
አዲሱ እንግዳችን
እንኳን ደህና መጣህ
ኔንቆን አውቀዋ ;ለሁ ... ረጅም ቀይ ጎበዝ ልጅ ... አሁን የት እንዳለ አላውቅም እንጂ
እስኪ የምታውቀውን አካፍለን
ስለ -የአባዝናብ በግ ከዚህ በፊት ብዙ ስላወራንበት ... መለስ ብለህ አንብብና የቀረ ነገር ካለ ካንተም እንጠብቃለን
እግር የያዝከው አንተ ሳትሆን አትቀርም

ለማንኛውም እንኳን ደህና መጣህ

የአማርኛ አጣጣልህ ... ደንበኛ ቤተኛ አስመስሎሀልና .. በርታልን
/መንግስት አስፋልት ገባ ነው ያልከኝ /
እስኪ በደንብ ዘርዘር አድርገህ ንገረኝ ... ከአዋሳ ጀምሮ አስፋልት ነው ወይስ ከተማ ውስጥ ብቻ ነው /
..............................................//..................................
ውቤ ጃሎ
ዋውውው ብያለሁ ... በተጨማሪም /.// የደስታህ ተካፋይ ነኝ
እንኳን ደስ ያለህ አንተም እሷን
ዋው ያስባለኝ .. ፍጥነቱ ነው /.... በአንድ አመት ውስጥ ሁለት .... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ገደልከኝ
ሶሪ ከተዋወቅን እራሱ አንድ አመት የሞላው ስላልመሰለኝ ነው ... ቀን ቆጠራ በጣም ደካማ ነኝ
ለነገሩ
እኛ ላይ ለመድረስ እንደሆነ ስለገባኝ .. እንኳን ደስ ያለህ ብዬ አልፌዋለሁ

ጎሲና .... እስኪ በናትህ ያቺ አይፋንና የቦሪቲን ... ካሉበት ቆስቁሰህ ጥራቸው

እነ መናኸሪያ ... ቅሩንፉድ ... አደቆርሳ እና አንፈራራ ካልመጡ አንገባም ያሉ ይመስላሉ

ይሁና ምን ይደረጋል

ሁሉንም ባሉበት አምላክ ሰላም ያኑርልን

አሚንንንን
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 8:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ወቤ ወቤ ...ማመን አልቻልኩም :: አብ ስራ አደገች ማለት ነው ? አሁን ፋታ ተገኘ እንዴ !? አንተንና አደቆርሳን ተለማምጠን
ሞትን እኮ ? ድሮ ድሮ አደቆርሳ ከዚህ ቤት የሚለየኝ ሞት ነው ሲል እውነት ይመስለኝ ነበር ...
ብቻ ልባችን ከናንተ እንዳለ አውቀህ አንተ በመመለስህ ደስ ብሎኛል ..ጓደኛህም አንተን አይቶ ስለማያስችለው ብቅ ይል ይሆናል ::

በጉግል ያገኘኧን የሀገር ልጅ ጀምጀም እንኳን ደህና መጣህልን :: አያያዝህ ብዙ የሚያስጉዘን ነውና ተመልስህ
እስካነብህ ቸኩያለሁ ::

ራስ ብሩ =ምንም አስተያየት የለኝም ::እንዳልከው ነው ::

ሱቂቲ = ለባለቤቴ ያልከውን አስተላልፌአለሁ ::ሀረሮች ቂጣ ጋግረን አናውቅም ብላሀለች ::
እንደውም ያኔ ድሬደዋ እያለህ ሳታውቅህ የምትቀር አልመሰለኝም ::አንድ ቀዥቃዣ ስንጥር የመሰለ የክ /መንግስት
ልጅ ካድሜው ነበር :;አሁን ይሄ በምን ሰውነቱ ነው ይሄን ሁሉ በርጫ የሚቀለምጥው ብዬ ተገርሜ ሁሉ ነበር ብላኛለች ::
የዛሬን አያድርገውና ለካ ድሮ ብትር ነበርክ ?ቅቅቅቅቅቅቅ

ቸር እንሰንብት !!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Jemjem

መንገደኛ

Joined: 14 Jul 2012
Posts: 5

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 10:46 pm    Post subject: Reply with quote

ውድ ባለሱቅ !
ወደ ክብረ መንግስት ለመሄድ አስበህ ከሆነ የአስፋልቱ ነገር ሙሉ በሙሉ አላለቀም :: ከክብረ መንግስት እስከ ሃገረ ሰላም ካለው 100km ውስጥ በግምት 50% ያህሉ አስፋልት ነው :: በተለይ አንፈራራ ከላይ ጀምሮ እስከ ታች አስፋልት ነው :: የአንፈራራን ጥቅጥቅ ያለ ውብ ደን እያየህ በአስፋልቱ ላይ ስትንፈላሰስ እጅግ አስደሳች ከመሆኑ የተነሳ ልብህ በሃሴትና በእረካታ ትሞላለች !!!!!! ሆኖም 160 ኪሎ ሜትሩ ሙሉ በሙሉ እስኪያልቅ ድረስ ቢያንስ 2 ረጅም ዓመታትን መጠበቅ አለብን :: እስከዚያው ፍላጎት ተሳክቶ እፎይ እስኪባል ድረስ - ትእግስትና ተስፋ የሚለውን እፎይታ መፅሃፍ እያነበብክ መቆየት ሊኖርብን ነው ::

ወርቁ መንግስታችን ወርቁን ለመሰብሰብ ባይታገስም መንገዱን ለመጨረስ ግን ታገሱ እያለን ነው :: በነገራችን ላይ ! ሰሞኑን ደግሞ አጭሩ ሰውዬ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ ባለመመገኘቱ የተነሳ በጠና የመታመሙ ዜና እየተናፈሰ በመሆኑ የአስፋልቱም ግንባታ ሰውዬው እስከሚድን ወይም እስኪሞት ድረስ የህዳሴ አስፋልታችን ግንባታ ሊዘገይ ይችላል እየተባለ ነው :: ሰውዬው የታመመው የዋልድባን ገዳምና የህዝበ ሙስሊሙን ሃይማኖት በመንካቱ ነው ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ግን እውነት ይሁን ውሸት አልታወቀም :: ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ !! ፕሬዚደንቱና ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በታመሙበት በአሁኑ ጊዜ ሃገሪቱ ያለ መሪ ቀረች እኮ !! ምን ይሻላል ? ይሄኔ ነው የኤፍሬም ታምሩን ሃገር አማን ነው ወይ ? የሚለውን ዜማ ለፕሬዚደንቱና ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ መምረጥ ያለብን ::

ክብረ መንግስት በነበርኩበት ጊዜ ከተማው ተቆፋፍሮ አፈር እየተሞላ በነበረበት ጊዜ በከተማው መቆፋፈር የተነሳ አንዳንድ ሰዎች ትንሽ ፈገግ የሚያደርግ ፖለቲካዊ ቀልድ ጀምረው ነበር :: ወያኔ መሞቻው ስለደረሰ መቃብሩን ክብረ መንግስት ከተማ ውስጥ እየቆፈረ ነው ሲሉ ይደመጡ ነበር ::

ውድ ባለሱቅ !!
ኔንቆ ሶርሳ 6 ዓመታት በፊት የይርጋ ጨፌ ወረዳ ጤና /ቤት ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ እንደነበር አንድ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል :: 2 ዓመት በፊት (2009) ደግሞ በጌዲኦ ዞን ጤና መምሪያ ውስጥ Officer of Family Health Planning and Programming ሆኖ ማገልገሉን google ጎልጉለህ ማየት ትችላለህ :: ሆኖም አንድ የቀድሞ ወዳጄ እንዳለኝ በቅርቡ ኔንቆ በአንድ የአሜሪካ NGO ውስጥ HIV/AIDS ፕሮገራም ላይ እየሰራ መሆኑን ጨምሮ ሹክ ብሎኛል ::

የኔንቆና የአባት ጦር ያለፈ ትዘታ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልኝ :: 1976 . አካባቢ ነው አሉ ኔንቆ በአንድ ቴስት (ፈተና ) 10 10 ሲያገኝ ሽፈራው የተባለ የኔንቆ ክላስ ሜትና የኔነቆ ተቀናቃኝ ያንን ቴስት (ፈተና ) 9 10 በማግኘቱ ሽፈራው እጅግ አምርሮ ሲያለቅስ እነ ግርማ ርዕሶም (ነብሱን ይማረውና ) ሲያባብሉት እንደነበርና አሁን በተገላቢጦሽ ደግሞ ሽፈራው የተዋጣለት የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ዶክተር ሲሆን ኔንቆ በበኩሉ ያልተዋጣለት GEOLOGIST ሆኖ ከአአዩ ቢባረርም በነርሲንግ ዲፕሎማው ሃገሩንና ወገኑን በገጠሪቱ ጌዲኦ ዞን በሚገባ አገልግሎአል :: 10 10 አገኘህ ወይም 9 10 የህይወት መንገድህ የሚመራው ያው ቀድሞ በተጻፈልህ ልክ ነው :: ክብረ መንግስት ተወለደን ስንቶቻችን ነን ኑሮአችን አውሮፓ ; አሜሪካ ወይም ሩቅ ምስራቅ ብለን በህጻንነታችን ያሰብን ‘በመሰለኝና በደሳለኝ’ ካልሆነ በስተቀር .::

ሌኒን መማር መማር አሁንም መማር ቢልም እኔ ደግሞ መስራት መስራት አሁንም መስራት ብዬ ወደ ስራዬ ሄጃለሁኝ :: ቻዎዎዎዎዎዎ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Jul 17, 2012 3:56 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
የኔንቆና የአባት ጦር ያለፈ ትዘታ ለሌላ ጊዜ ይተላለፍልኝ :: 1976 . አካባቢ ነው አሉ ኔንቆ በአንድ ቴስት (ፈተና ) 10 10 ሲያገኝ ሽፈራው የተባለ የኔንቆ ክላስ ሜትና የኔነቆ ተቀናቃኝ ያንን ቴስት (ፈተና ) 9 10 በማግኘቱ ሽፈራው እጅግ አምርሮ ሲያለቅስ እነ ግርማ ርዕሶም (ነብሱን ይማረውና ) ሲያባብሉት እንደነበር

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አንተ ምን አይነት ክፉ አስታዋሽ ልጅ ነህ በናትህ
እኔ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ባላውቅም ... ሽፈራውና ኔንቆ እንዲሁም በድሩ .. ጌቾ .. ግርማ (ነፍስ ይማር 9 አንድ ላይ እንደነበሩ ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ
ለካስ ሽፌ አልቃሻ እልህእኛ ልጅ ነበረች
ወይኔ ላግኘው ቆይ ... አሁን ሄድለት የለ ...
ከአዋሳ ደሞ ከመቼው ተቀይሮ ነው አዲሳባ የገባው
አዋሳ ጥቁር ውኃ ክሊኒክ እኮ የራሱ ነበር ሚመስለኝ
በጣም ጎበዝና የማደንቀው ልጅ ነው
እንዲሁ ግን እልሁና እልቅሻው ታየኝና ... ጉብዝና ሲያንሰው ነው አልኩኝ
Quote:
አሁን በተገላቢጦሽ ደግሞ ሽፈራው የተዋጣለት የጥቁር አንበሳ እስፔሻላይዝድ ዶክተር ሲሆን ኔንቆ በበኩሉ ያልተዋጣለት GEOLOGIST ሆኖ ከአአዩ ቢባረርም በነርሲንግ ዲፕሎማው ሃገሩንና ወገኑን በገጠሪቱ ጌዲኦ ዞን በሚገባ አገልግሎአል :: 10 10 አገኘህ ወይም 9 10 የህይወት መንገድህ የሚመራው ያው ቀድሞ በተጻፈልህ ልክ ነው :: ክብረ መንግስት ተወለደን ስንቶቻችን ነን ኑሮአችን አውሮፓ ; አሜሪካ ወይም ሩቅ ምስራቅ ብለን በህጻንነታችን ያሰብን ‘በመሰለኝና በደሳለኝ’ ካልሆነ በስተቀር .::

በትክክል አስቀምጠኸዋል ወዳጄ

በመሰለኝና በደሳለኝ እንጂ ... አሁንስ እኛ ያለንበት ይህ የዋርካ ቤት ውስጥ እንገናኛለን ብለን አስበን እናውቃለን ?>

ዲስቲኒህ ቀድሞ ተፅፏል ብለው ከሚያምኑት ወገን ባልሆንም .... አንዳንዴ ግን .... ታዲያ ምን ሊባል ነው ብዬ እራሴን እከራከራለሁ
መልሱን ታዲያ ለጌታ ነው ምተወው
ምን አዳረቀኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቆይ እኔ ምለው .... መማር መማር አሁንም መማር ያለው ሌኒን ነው ብለሀል
መስራት መስራት አሁንም መስራት ያለው ማን እንደሆነ ጠፍቶህ ነው አንጠልጥለህ የተውከው
ባለሱቅ ነው
ተዋወቀው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጀምጀሚሻ ... እንዳመጣጥህ በቀላሉ ምንላቀቅ አልመሰለኝም
እስኪ ብዙ ብዙ አውራንና ... እኛም ትዝ የሚለንን እና የረሳነውን ... ስናስታውስ ጀባ እንልሀለን
.......................................//.........................

ሞፍቲሻ
ምን አለች ነው ያልከው
እኛ የሀረር ልጆች ቂጣ ጋግረን አናውቅም ....? .
አሳቅሽኝ በላት .... ሀረር ባልኖር ይቆጨኝ ነበር

የቆቱን ቂጣ በሆጃ (ወተት በሻይ ) እየቀቀለ ለባሉሽካ ሚያቀርበው ማን ሆነና ...
ከበርጫ በፊት ሆጃ በቆቱ ቂጣ (ስሙ ጠፋኝ ) እንዴት ረሳሽው በልልኝ

ደሞ ሞያ እንዳላት ታወራለች ... ቅቅቅቅቅቅቅቅ
እኔ ሀረር ሳለሁ ከሁሉም የማይረሳኝ
"ማሽላ ካልተጨመረባት ምጣዷ ትይዛለች " የሚሉት አባባል ነው
ንፁህ የጤፍ ዱቄት እንጀራ መብላት እኮ ዘበት ነው .... ምጣዷ የማሽላ ዛር አለባት መሰለኝ ... ሊጡ ውስጥ የማሽላ ዱቄት ካልተቀላቀለበት .... እንጀራው አይወጣም ይላሉ
ባለሙያዎቹ .... የሞፍቲ ሚስቶች
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለችኝ

ሌላው በጣም የማይረሳኝ ደሞ ... አሁን ውጭ አገር ስንከራተት ለመድኩት እንጂ
ዶሮ ወጥ በድንች ሲሰራ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ሀረር ነው
አሁንም ኢትዮጵያ ሆኜ ይህንን መልክት የምፅፍ ቢሆን ... በሙያቹ እስቅ ነበር
ግን ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ቀድማቹ የአለምን ሙያ የተቀበላቹ በመሆናቹ
ልትደነቁ ይገባል በልልኝ
የማሽላዋም እንዲሁ (አሁን በሩዝ ተቀይራለች እንጂ )

ኤኒዌይ ... የቂጣዋን ነገር ግን አልስማማበትም
ባይሆን ቅቤ ማውጣትና አሬራ መስራት እንደማትችሉ ... አውቃለሁ
ሀረሮች

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለችኝ ውድህ

እስኪ ትምጣና አንዴ ትረማመድብኝ በዚያ በሚጣፍጠው አንደበቷ
"... ወር .. አንተ አፍህን ዝጋ .." ብላ ስትጀምር ታየኝ .. እና ጓጓሁ
ለመስማት
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Jemjem

መንገደኛ

Joined: 14 Jul 2012
Posts: 5

PostPosted: Tue Jul 17, 2012 10:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሽፈራው ብቻ ሳይሆን ባለሱቅም አልቃሻ እንደነበርክ ሰምቼያለሁኝ :: ባለፈው ጊዜ አንድ የቅርብ ወዳጅህ እንዳጫወተኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሃረር (አለማያ ) የሄድክ ዕለት (1979 .) አውቶቡሱ ተነስቶ ወደ ሃረር ጉዞ ሲጀምር እህትህንና የአጎትህን ልጅ ተሰናብተህ አቃቂ እስክትደርስ ድረስ እያለቀስክ እንደነበር ያለሰማሁ አይምሰልህ ::

ሆኖም ፈጣሪ ለቅሶህን አይቶልህ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ተመድበህ (1983 .) ወደእዚያው ወደ ሃረር ስትሄድ አንዲት ቀይ ቆንጆ ልጅ አውቶቡስ ውስጥ ተዋውቀህ በዚያው ወዳጅነትህን ቀጥለህ ያቺኑ ልጅ ሚስትህ እንዳደረካት ሰምቼያለሁኝ :: 1979 . የፈሰሰው እምባ ፈሶ አልቀረም :: 1983 . ታበሰ ::

ሞባይል የእጅ ስልክ ባልነበረበት በዚያ ጊዜ አዲሳባ ላይ በሰኔ ወር 1979 . በአጋጣሚ ያገኘሃትን አንዲት የአዲሳባ ኮረዳ ለመስከረም 3 1980 . 8 ሰዓት ጆሊባር (4ኪሎ ) ቀጥረሃት በተባለው ቀንና ሰዓት እንዳገኘሃት ስሰማ እጅግ ነው የገረምከኝ :: 1979 . ላይ ሆነህ 1980 . ሴት መቅጠርህ ሲያስገርመኝ ልጅቱም በተባለው ቀንና ሰዓት መምጣታ ደንቆኛል :: በዚህ አይነት አሁን ወደሃገር ቤት ስትሄድ ሞባይልህ ምን ያህል busy እንደሚሆን ለመገመት አያስቸግርም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Jul 17, 2012 11:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!!

ወንድማችን ጀምጀም :

ባለፈው የኔንቆን ስም ስታነሳ እኔም ኔንቆ የሚባል (አይፋ ታውቀዋለች ) ዘመድ ስለነበረኝ ስለኔው ዘመድ የምትጽፍ እየመሰለኝ ደንግጬ ነበር :: እንኳኑ የዚያን ቀን ስሙን ጠራህ እንጂ ዛሬ ስለ ባለሱቃችን ካጫወትከን በኌላ የኔንቆን ስም ብትጠራ ኖሮ እያንዳንዱን ክስተት እንደ ታሪክ ተመራማሪ ቀኑን እና አመተምህረቱን ጠቅሰህ ስለምትዘግብ ስጋቴ ክፉኛ በጨመረ ነበር ቅቅቅ :: ለመሆኑ ባለሱቃችን አንተ እስከነቀኑ የምታስታውሳቸን ያህል ያስታውሳቸው ይሆን ?
Quote:
1979 . ላይ ሆነህ 1980 . ሴት መቅጠርህ ሲያስገርመኝ ልጅቱም በተባለው ቀንና ሰዓት መምጣታ ደንቆኛል ::

ቅቅቅቅቅ ባለሱቃችን አገር ቤትም እያለህ መቼም ትልቅ Diary ሳይኖርህ አይቀርም :: ኧረ ገና ስንት ጉድህ ይሰማል ማለት ነው ቅቅቅ ::

ወንድማችን ጀምጀም ዋርካችንን ደህና እያሟሟቅክልን ስለሆነ በርታልን :: ገና ያልተበላ ጥሬ ትዝታዎች ሞልተውሀል መሰለኝ ቅቅቅ :: አጻጻፍህ ደግሞ ግሩም ነው ::

ባለሱቃችን አይፋንማ በጓሮ በኩልም ጠርቼያት አልሰማችኝም :: ብዙ ስለቆየች መግቢያ ቁልፉም ዬት እንዳለ የምታስታውስ አይመስለኝም :: ቦርቲ እኮ እኔ አልደረስኩባትም : ቀድማኝ ነው የሄደችውና እሷን ደግሞ ሀላፊነቱን ላንተ ትተናል ::
በሉ ይመቻችሁ
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Jul 18, 2012 5:11 pm    Post subject: Reply with quote

አንተ ጀምጀም
Jemjem እንደጻፈ(ች)ው:
ሽፈራው ብቻ ሳይሆን ባለሱቅም አልቃሻ እንደነበርክ ሰምቼያለሁኝ :: ባለፈው ጊዜ አንድ የቅርብ ወዳጅህ እንዳጫወተኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሃረር (አለማያ ) የሄድክ ዕለት (1979 .) አውቶቡሱ ተነስቶ ወደ ሃረር ጉዞ ሲጀምር እህትህንና የአጎትህን ልጅ ተሰናብተህ አቃቂ እስክትደርስ ድረስ እያለቀስክ እንደነበር ያለሰማሁ አይምሰልህ ::

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ቆይ እስኪ ምንና ምንን ነው ያገናኘኸው ባክህ
እኔ ለማርክ ብዬ አላለቅስም ... እልህ ውስጥም አልገባም
ከእህቴ ስለይ ግን ,.... አዎን ድብንን ብዬ አልቅሻለሁ
እንዳንተ ደረቅ ልብ የለኝም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ንገሩኝ ባይ ....
Quote:

ሞባይል የእጅ ስልክ ባልነበረበት በዚያ ጊዜ አዲሳባ ላይ በሰኔ ወር 1979 . በአጋጣሚ ያገኘሃትን አንዲት የአዲሳባ ኮረዳ ለመስከረም 3 1980 . 8 ሰዓት ጆሊባር (4ኪሎ ) ቀጥረሃት በተባለው ቀንና ሰዓት እንዳገኘሃት ስሰማ እጅግ ነው የገረምከኝ :: 1979 . ላይ ሆነህ 1980 . ሴት መቅጠርህ ሲያስገርመኝ ልጅቱም በተባለው ቀንና ሰዓት መምጣታ ደንቆኛል :: በዚህ አይነት አሁን ወደሃገር ቤት ስትሄድ ሞባይልህ ምን ያህል busy እንደሚሆን ለመገመት አያስቸግርም ::

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
በሳቅ ነው እኮ እየገደልከኝ ያለኸው እና
በእልህ ያንተንም ታሪክ .. እስከዛሬ ተደባብቆ የቀረውን ታሪክህን እዚህ ቁጭ እንዳላደርግ
ብታርፍ ይሻልሀል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ደሞ እኔ በዚያ ጊዜ ጆሊ -ባር ሚባል አላቅም ነበር
የተቀጣጠርነው .... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አልነግርህም
አቤት ቅናትትት ግን ....
አየህ እኛ ያኔም እንኳን ቀጠሮ አክባሪ እና ቀጠሮ የሚያከብር ሰው ነበር ምንተዋወቀው
9ሰአት ቀጠሮ ከጠዋቱ 3ሰአት ጀምሮ እንደሚጠብቁት ጅጅጋዎች
ወይም ...
ቀጥረውክ ሲያበቁ .... በራቸውን ቀርቅረው ... በቀዳዳ እያዩ እና ለጓደኛቸው እያሳዩህ ... እንደሚስቁብህ የሰፈርህ ልጆች
ወይም ደሞ
ቀጥረው ከነጭርሱ የውሀ ሽታ ሆነው እንደሚቀርዩትና ... በመጨረሻም እንደሚቆጫቸው አይነት ልጆችን
አልቀጥርምምምምምም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገቢቶ
በቀጠሮ .. በጊዜ ... በስሜት ... እና በፍቅር ቀልድ የለም እኛ
50አለቃን ሰላም በለው ደሞ .... ውስጥህ ያለውን የዋቴ -ታኪቾውን 50 አለቃ ....
ብታርፍ ይሻልሀል በለው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጎሲቲ

አሁን ጀምጀም ሚያወራውን ነገር በሙሉ .... ድሮ ድሮ ይሄ ቤት ሲከፈት አውርተን ስቀን ተበሻሽቀን አልፈነዋል
እንደገና ክለሳ ምናምን ይወዳል እንጂ ይሄ ብሽቅ ጀምጀም
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፕሊስ ጀምጀምዬ ... ሌላም እስኪ የምታውቀውንና ... እነ በእርግጥ የረሳሁትን ነገር እያስታወስክ አጫውተን ፕሊስ
አደራ ታዲያ
እዛች የጥናት ቤት ውስጥ አንዴ እጄን ጠምዝዘህ ... አፈር ድሜ አብልተህ የደበደብከኝን ነገር እንዳታነሳ
አደራ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ሰላም ሁን አቦ
ነፍስ ዘራህባት በቤቷ
ብሽቅ ጉጂ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Jul 18, 2012 7:04 pm    Post subject: Reply with quote

የዛሬን አያርገውና ካቶሊክ ቄስ ሊሆን ከኔጋር ሲማር የነበረውን አንድ የጥንት ጓደኛዬን እነአይፋ አገር መኖሩን ሰምቼ አይገቡ ገብቼ ቁጥሩን አግኝቼ ዛሬ ሳናግረው ስንት ትዝታ ቀሰቀሰብኝ መሰላችሁ :: እዚያ አዋሳ ገዳም ውስጥ በነበርንበት ወቅት እንኳ በኔና በሱ መካከል ምንም ሚስጢር (የሴቶች ቅቅቅ ) አልነበረም :: ስለ እሱ ዬቱን አውርቼላችሁ ዬቱን እንደምተው አላውቅም ::

ከቅርቡ ልጀምርና ጊዜው ከነ ጽጌ ዘመነ ፍቅር የተወሰኑ ወራት ቀደም ብሎ ነው ::ቦታው ደግሞ አዲስ አበባ ነው :: ልጁ ሀይስኩሉን ስለጨረሰ የካቶሊክ ፈረንጆቹ እሱንም ሌላ ቤት ተከራይተውለት : ታንዛኒያ ዋናውን የቅስና ትምህርት እንዲጀምር ከመላካቸው በፊት በተወሰነ ስራ ላይ ተመድቦ ጸባዩ በቅርብ ክትትል መጠናት ስለነበረበት ካንዱ የካቶሊክ /ቤት ረዳት መምህር ሆኖ እንዲያስተምር ይመደባል :: የትምህርት ቤቱ ዳይረክተር የነበሩት ቆንጅዬ ወጣት ሲስተር (nun) ሲሆኑ (ሲስተር እስከሆኑ ድረስ "አንቱ " ማለት ስላለብኝ ነው : እንዳትደናገሩ ) ትውልዳቸው ኢሮብ የሚባል ቦታ (ትግራይ ውስጥ ይሆናል ብዬ ነው የማምነው ) ነበር :: ጓደኛዬ የቅስናን ትምህርት ተገን በማድረግ መጽሀፍ ቅዱስና እብድ የሚያህል መስቀል ተሸክሞ በየሰው ጓዳ እየገባ ይሰራ የነበረውን ይነግረኝ ስለነበር እንኳን ቄስ ሊሆን ቀርቶ እጃቸውንም መሳለም የማይገባው አይነት ሰው ነበር ብዬ አምናለሁ ቅቅቅቅ :: ታዲያ ምላሱ ምላስ አልነበረምና /ቤቱን በረገጠበት በሶስት ሳምንት ውስጥ ማንም ነክቷቸው የማያውቀውን ሲስተር በፍቅር አጡዟቸው በራሳቸው መኪና ውስጥ ሌላ ስቪል ልብስ ቀይሮላቸው በየፔንሲዮኑ ያዞራቸው ጀመር :: ከሲስተሯ ጋር እንዲህ 'የሚያስኮንን " ፍቅር ውስጥ ዘልቀው በሚስጢር አለማቸውን በመቅጨት ላይ እያሉ አንዲት ወጣት ነጭ አሜሪካዊት ለተወሰኑ ወራት የበጎ ፈቃድ ሰራተኛ (volunteer) ሆና እዚያው /ቤት ለማገልገል ስትመደብ ልጁ "ጠብ ካረኳት ውጭ ትወስደኛለች " በሚል እምነት ፈረንጇን ማኖ ማስነካት ብፈልግ ቋንቋ ከዬት ይምጣና እርኩስ ሀሳቡን ይግለጥላት ቅቅቅ :: እኔና እሱ ሆነን ለሊቱን ሙሉ ከትልቁ Oxford Dictionary ጋር በቁምነገር ስንታገል አድረን ያቅምቲን ያህል ያቀናበርናትን የፍቅር ደብዳቤ በማግስቱ ሲስተሯ ከመምህራን ቢሮ ወጣ እስኪሉ ጠብቆ ያንን ፖስታ ለነጯ ያቀብላታል :: ነጯ ከፍታ ሳታነበው ተቀብላው ብቻ የጅ ቦርሳዋ ውስጥ አስቀምጣ ቦርሳዋን ቢሮው ውስጥ ትታ ለሆነ ጉዳይ ወጣ ስትል አጅሬው ብታጋልጠኝስ በሚል ጥርጣሬ ተሞልቶ ወዲያው ቦርሳዋን ከፍቶ የሰጣትን ፖስታ ወስዶ ኪሱ ይከታል :: ነጯ ተመልሳ ቦርሳዋን ከፍታ ፖስታውን ፈልጋው ስታጣው እሱ እዚያው ክፍል ውስጥ ስለነበር ፖስታው በዚያች ቅጽበት ዬት እንደገባ እና ከማን እንደሆን እንዲነግራት ልጁን በመጠየቅ ላይ እንዳለች ዳይረክተሯ ስትገባባቸው ልጁሆዬ ምንም ፖስታ እንዳልሰጣት እና ፖስታ የሚባል ነገርም እንዳላየ ድርቅ ብሎ ይክዳል :: በሁኔታው ግራ የተጋባች ነጭ የልጁ እና የፖስታው ሚስጢር ስላስፈራት ጉዳዩን ለዳይረክተሯ ካሳወቀች በኌላ "ይህንን ልጅ ፈርቼዋለሁ : እሱ ባለበት አልሰራም " ብላ ወደቤት ስትሄድ /ቤቱ ደግሞ ልጅቷን ከሚያጧት ልጁን በሰላም ማሰናበቱን መርጦ ሲያሰናብተው ለሊቱን እንቅልፍ አጥተን ያዘጋጀናት ደብዳቤ ለጊዜውም ቢሆን ጓደኛዬን በዜሮ አስቀረችው እላችኌለሁ ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 368, 369, 370 ... 381, 382, 383  Next
Page 369 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia