WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 369, 370, 371 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Jemjem

መንገደኛ

Joined: 14 Jul 2012
Posts: 5

PostPosted: Wed Jul 18, 2012 9:50 pm    Post subject: Reply with quote

ውድ ጎሳ ! የጥንቱ ባልንጀራህ ፀባዩ /ባህሪው ከባለሱቅ ጋር ይመሳሰላል !!! የኢሮብ ሲስተር ጉዳይስ በምን ሁኔታ ተጠናቆ ይሆን ? ምስኪን የአሊቴና ልጅ !! ኢሮብን በሚገባ አውቃታለሁኝ :: ከአሲምባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ Vatican of Ethiopia የምትሰኝ ድንጋያማና በበለስ ፍሬ የተሞላች ምድር :: የአሲምባን ማር ደግሞ በወቅቱ ወደ ነጻይቱ አሲምባ 1969 . የተመሙ ኢህአፓ ልጆች ያውቁታል ::

ባለሱቅ ቀሽም ነህ :: ምክንያቱም ስለ ጀምጀም ማንነት ግምትህ ለዛሬው ስላልተሳካልህ !!

እኔ ክብረ መንግስት በነበርኩበት ጊዜ አንቺ ጩጬ ነበርሽ :: ስለ አንተ ትዝ የሚለኝ ከቢሉ /ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ በጪቃ ላይ በባዶ እግርህ ከሃጅ ሃሰን ልጅ ጋር እየተንሸራተትክ ስትሄድ ለምን መንገዱን ታጨቀያለህ ብሎ ፍቃዱ አቦምሳ የኮረከመህን አስታውሳለሁኝ :: ለነገሩ ፍቃዱ አቦምሳ እድሜ ልኩን ሲኮረኩምህ እንደኖረ በዚሁ በዋርካ ድህረ ላይ ገጽ አንተም ተናዘሃል :: በተለይ የቢሉ ተማሪ ለምሳ ሲለቀቅ ከላይ ከጋሼ አሰጋሃኝ መኖሪያ ቤት ጀምራችሁ ታች እስከ ጋሼ አሰጋሃኝ ወፍጮ ቤት ድረስ በሜጫ ሰፈር ላይ የምታደርጉት ሸርተቴ ልክ በረዶ ላይ እንደሚንሸራተት ሰው ነበር የምትጋልቡት ::

እኛ በዚያን ጊዜ እነ ሳሙኤል አቦምሳ ቤት ከነ ወልደ እስራኤል ጋር ሉፍ ለመቃም ስንሄድ መንገዱን ታጨቀይብን ነበር :: የፍቃዱ አቦምሳ ኩርኩም ግን ብዙም አላስታገሰችህም :: ያኔ የተኮረኮመችው ራስ አሁን ግን ተመልጣለች አሉ :: መላጣ !! ቂቂቂቂ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Thu Jul 19, 2012 12:23 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
የምትጨዋወቱት ታሪክ ማርኮኛል አንድ ያሳቀኝ ነገር ግን የባለሱቅ ፍራቻ ነው :
Quote:
አሁን ጀምጀም ሚያወራውን ነገር በሙሉ .... ድሮ ድሮ ይሄ ቤት ሲከፈት አውርተን ስቀን ተበሻሽቀን አልፈነዋል
እንደገና ክለሳ ምናምን ይወዳል እንጂ ይሄ ብሽቅ ጀምጀም

ባለሱቅ ጀምጀምን ፈርተህ ቶሎ ፊልድ እንዳትወጣ ሰጋሁ ::
ጎሳ አንዳንዴ የምታስታውሳቸውና ያሳለፍካቸው አጋጣሚዎች በጣም ያስደንቃሉ የገዳም ቆይታህና የፖስታዋ ነገር ጥሩ ስክሪፕት ጸሀፊ ብታገኝ አጭር ፊልም
( short story Film ) ሊወጣት የምትችል ጥዑም ታሪክ ናት ::
ጀምጀም ኢሮብን እንደምታውቅ ጽሁፍህን ሳነብ በሆነ ወቅት እዛችው ቦታ የቆየ ወንድም ስለነበረኝ ያጫውተኝ የነበረውን ታሪክ በቦታው እንደነበረ ሠው በደንብ
አስታውሳለሁ ባጭሩ ሳላያት አውቃታለሁ ማለት ይቻላል ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jul 19, 2012 3:18 pm    Post subject: Reply with quote

ጎስና
Quote:
ለሊቱን እንቅልፍ አጥተን ያዘጋጀናት ደብዳቤ ለጊዜውም ቢሆን ጓደኛዬን በዜሮ አስቀረችው እላችኌለሁ ::

ዋጋውን ነው ያገኘው ... ቅቅቅቅቅቅቅ እስኪ የያዘውን አጥብቆ እንደመያዝ ... ያየው ሁሉ አይለፈኝ ..... ምን የሚሉት በሽታ ነው
ይሄ ጀምጀም ደሞ ብሎ ብሎ
Quote:
ውድ ጎሳ ! የጥንቱ ባልንጀራህ ፀባዩ /ባህሪው ከባለሱቅ ጋር ይመሳሰላል !!!

ይለኛል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እሰይይይ አገኘሁህ ... አታቀኝም ማለት ነው ጀምጀምዬ
እኔ
አንደኛ ያየሁት ሁሉ አይለፈኝ አልልም
ሁለተኛ ለሴት ልጅ ደብዳቤ ፅፌ አላውቅም

ለጓደኞቺ ግን (ላንተም ጭምር ሳይሆን )... ደብዳቤ አርቅቄ እና አድርሼ አውቃለሁ
ለራሴ ብዬ ግን አንዲትም ቀን ብዬ አልዋሽም ... ግን በአንደበቴ መናገር አቅቶኝ ደብዳቤ ፅፌ አላውቅም
ምን -አልባት እድሜ እኔ ሳላቀው አልፎኛል ... ወይም .... የሚፃፍለት ሰው አልነበረም .... እናንተ ሰፈር
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ለማንኛውም ግን ከመሀመድ -ረሺድ (ነፍሱን ይማረው ) ጋር እናደርግ የነበረውን የጭቃ ላይ ሸርተቴ በማስታወስህ ... በጣም ገርመኸኛል
የሚገርመኝ ነገር እኔ ... ራስብሩ 6አመት ... ቢሉ 2አመት ሀይስኩል 4አመት በት / አሳልፌአለሁ ... እንደቢሉ / ቤት ግን ልቤ ውስጥ የቀረ .. ወይንም በህልሜ የሚመጣ ... ቦታ የለም
የተለየ ትዝታ ሊኖረኝ አይችልም ... 5 እና 6 ክፍል ምን አይነት ትዝታ ሊኖር ይችላል
ነገር ግን ... አረንጓዴ ሜዳ ላይ የምንቦርቀው .... መቸም አይረሳኝም
ራስብሩ --እዛ የአፈር ሜዳ ላይ ትልልቆቹ እንጂ እኛን ሚያስጠጋን ስላልነበር ይሁን .. አላውቅም
ግን ቢሉ / ሰፊ የሳር ሜዳው ላይ ... የምንቦርቀው ... (በረፍት ሰአት )...
እናም የወረቀት አውሮፕላን እየሰራን ....
የማን መሬት ሳትወድቅ .. ሩቅ እንደሄደች የምንወዳደረው
እናም የተከልኳት ዛፍ ... መቸም አትረሳኝም

ከጋሽ አሰጋኸኝ ቤት ... ሳይሆን .... ከነ -ጌቱ አልዩ ቤት ጀምሮ እስከ -ጋሽ አሰጋኸኝ ወፍጮ ቤት ያለውን ቁልቁለት ... በጭቃ ሸርተቴ ተራግጠንበታል
እኔ እንኳን ጎበዝ አልነበርኩም ... ቶሎ ነበር ምወድቀው
መሀመድ ረሺድ ... በአንድ ጊዜ እስከ 50ሜትር ገደማ ሳይወድቅ የሚሄደው በጣም ይገርመኛል .... 50ሜትር ያልኩት ተሳስቼ ሊሆን ይችላል .. ግን በጣም ሩቅ መሄድ እንደሚችል እና በሱ እቀና እንደነበር አስታውሳለሁ

በተረፈ ... የፍቃዱ አቦምሳን ኩርኩም ስታነሳ ... ምን ትዝ አለኝ መሰለህ
21 አመቴ ምልጠት ሲጀምረኝ ... በመጀመሪያ የረገፈችው ፀጉሬ እሱ በኩርኩም ያደቀቃት ቦታ ነበረች
ምናልባት ያኔ እኔን የመታ መስሎት ብዙ ፀጉሮችን በኩርኩም አድቅቋቸው ,,... ከነስሩ አንስቷቸው ሳይሆን አይቀርም
ከዛዚያ ውጭ ግን ... ገበያ ለማዘር እቃ ለማድረስ የምሸከመው የሚሸጥ እቃ (ብቅል .. ከሰል ... ዱቄት ... ጨው ) ምናምኑ የምሸከመው ይመስለኛል ... ፀጉሬን መልጦት የቀረው ... 02 እስከ ገበያ ክፍል
እና
ፍቃዱ ብቻ አይደለም ተወቃሽ ..ኑሮም ነው ... ለማለት ነው ... አታጣላኝ ከጥሩ ወዳጀ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ራስብሩ ...
እኔ ምፈራው ነገር ያለ ይመስልሀል ስታስበው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ አይ አለመተዋወቅ አለች ኤሊ
እኔ የፈራሁት ...ይሄ ጀምጀም ነገሮችን ነካክቶ ሲያበቃ .... የደበቅኩትን የራሱን ታሪክ ባደባባይ እንዳላወጣበት ፈርቼ እንጂ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

በተረፈ ጨዋታህ ግን በጣም ጥማኛለች ጀምጀሚሻ

በርታ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jul 19, 2012 7:25 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችንም !!

ራስብሩአችን ከዚህ በታች ያለውም ትንሽ ይጨመርበታ ፊልም ነገር ከታሰበ ቅቅቅ :: ኧረ የካቶሊኩ ትዝታማ ተዝቆ አያልቅም ::

Quote:
ውድ ጎሳ ! የጥንቱ ባልንጀራህ ፀባዩ /ባህሪው ከባለሱቅ ጋር ይመሳሰላል !!! የኢሮብ ሲስተር ጉዳይስ በምን ሁኔታ ተጠናቆ ይሆን ? ምስኪን የአሊቴና ልጅ !! ኢሮብን በሚገባ አውቃታለሁኝ :: ከአሲምባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ Vatican of Ethiopia የምትሰኝ ድንጋያማና በበለስ ፍሬ የተሞላች ምድር :: የአሲምባን ማር ደግሞ በወቅቱ ወደ ነጻይቱ አሲምባ 1969 . የተመሙ ኢህአፓ ልጆች ያውቁታል ::

ጀምጀማችን ! ባለሱቅ ነገሮችን በደፈናው እየካደ ነው ቅቅቅቅ :: ምናልባት ያለፈ ድርጊቶችን ረስቷቸው ሊሆን ስለሚችል መቼም አንተ ስለማትረሳቸው ጠቀስ ጠቀስ እያረክ አስታውሰው እስቲ ቅቅቅቅ :: ባለሱቃችን ቅልጥፍናው ሌላ ነገር ላይ እንጂ ቀሚሶቹ ጋር አይመስለኝም ቅቅቅ ቢሆንም ደግሞ የጓደኛዬን ያህል በፍጹም ልሆን አይችልም ብዬ ግግም አላለሁ ::

ምስኪን የአሊቴና ልጅማ ታሪኳ መች በዚያ አበቃ ብለህ ነው ጀምጀማችን !
የካቶሊክ ሲስተሮች እና ቄሶች በየሶስት አመቱ የሶስት ወር እረፍት አላቸው :: በዚያ የእረፍት ጊዜያቸው አብዛኛዎቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄደው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እረፍታቸውን ያሳልፋሉ :: የፖስታው ነገር ትንሽ ክፍተት ቢፈጥርባቸውም ፈረንጇ ወደ አሜሪካ ስትመለስ ስፖንሰር እንድትፈልግለት የጻፈላት ደብዳቤ እንደነበርና የካደበትም ምክንያት ፈረንጆቹ ለቅስና ስጠብቁት እንዴት በጎን ስፖንሰር ታፈላልጋለህ ብለው ሊያባርሩት ስለሚችሉ ያንን ፈርቶ መካዱን ካሳመናቸው በኌላ ግንኙነታቸውን ይቀጥላሉ :: ከተወሰኑ ወራት በኈላ የሲስተሯ የሶስት ወር የእረፍት ጊዜያቸው ደርሶ ወደ ኢሮብ ለመሄድ ሲዘጋጁ ለሶስት ወር ሙሉ መለያየቱ በጣም ስለከበዳቸው ልጁ አንድ ሀሳብ ያፈልቃል : ቄሶች ቅዳሴ ሲቀድሱ የሚለብሱትን ልብስ በሲስተሯ እርዳታ ከቤተክርስቲያን ያስወጣና የተቀባ ክህን "አባ ማርቆስ " ሆኖ ኢሮብ ድረስ ተከትሏቸው ይሄዳል :: የሲስተሯ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ብዙ የመኖሪያ ክፍል ስላልነበረው ቄስ እና ሲስተር አይነካኩም በሚል ሰበብ ማደሪያቸውን በመጋረጃ ብቻ በመክፈል አንድ ክፍል ውስጥ ያሳድሯቸዋል :: በመኝታው ሰአት እዚያ ክፍል ውስት የሚደረገውን ነገር መጋረጃው አንደበት ኖሮት ቢናገር ...

የተጻፈ ህግ ባይሆንም አንድ ቄስ በቀን አንድ ቅዳሴ መቀደስ ወይም መካፈል ስላለበት አባ ማርቆስም ሁል ጊዜ ከራት በፊት ያለምንም ክህነት በድፍረት ብቻ እቤት ውስጥ ያነበረውን ዳቦ እና ለስላሳ በመጠቀም ትክክለና ቅዳሴ እየቀደሰ (የቅዳሴ ቃላቶች ሁሌም አንድ አይነት ስለሆኑና እና ማንም ሰው በቃል ስለሚችል ምንም አይነቃበትም ) ሲስተሯን እና ቤተሰቦቿን ጎረቤቶችንም ጭምር እያስቆረባቸው (ቅዱስ ቁርባን እየሰጣቸው ) ማታ ማታ ደግሞ የተለመደውን የጽድቁን ስራ ሲሰራ አንድ ወር ቆይቶ ለሶስት ወር ብሎ የሄደውን እረፍት ባንድ ወሩ ብቻውን ተመልሶ መጣ ::

"ምንድነው አባ ማርቆስ : ለሶስት ወር አልነበር እንዴ የሄድከው : ለምን ባንድ ወርህ መጣህ ?'

"ባክህ እኔ ትክክለኛ ቄስ የሆንኩ እስኪመስለኝ ጀዘብኩ :: ወሬው ሁሉ መንፈሳዊ ሆነብኝ : ሰዎች ቀርበው ነጻ ሆነው አያጫውቱኝም : ከሷ ጋር ብቻ ደግሞ እጅ እጅ አለኝ :: ብታይ የቆንጆ አይነት ያለበት ቦታ ሆኖ እያየኌቸው ተሰቃየሁ :: ኧረ እዚህ እንደፈለኩ መሆኑን ለምጄ እንዴት ሆኜ ሶስት ወር እዚያ እኖራለሁ '

"እና ሲስተሯን ምን ብለሀቸው መጣህ ?'

"በጣም እንዳመመኝ ሆኜ አንድ ሙሉ ቀን ተኛሁ :: አዲስ አበባ መታከም አለብኝ ብዬ ነገርኳት :: ምን አማራጭ አላት ::'

አባ ማርቆስ ከሲስተሯ ጋር ጀምሮ እያለ ሌላ የአንድ ባለሀብት ሚስት በሆነ አጋጣሚ ተዋውቋት አስከንፏታል :: እሷ በጣም ወጣት እና የሁለት ትናንሽ ልጆች እናት ስትሆን ባሏ በእድሜ ገፍቷል :: እሷን አዲስ አበባ ጥሏት እሱ ጂማ መንገድ ትልቅ የእንጨት መሰንጠቂያ ፋብሪካ ነገር ስለነበረው አብዛኛውን ጊዜውን እዚያ ነው የሚያሳልፈው :: ለሳምንት እና ሁለት ሳምንት ሁሉ ወደ አዲስ አበባ አይመጣም :: ሴትዮዋ የቤት መኪና ትይዝ ነበር :: አንዳንዴ መኪናውን ታውሰው ስለነበር አልፎ አልፎ ይዞ ይመጣና ሻይ ቡና እያለኝ ትንሽ ያዞረኝ ነበር :: ታዲያ ሴትዮዋን "አክስቴ " ናት እያለ ከሲስተሯ ጋር ሲያስተዋውቃት ሲስተሯን ደግሞ "ሲስተር እና የስራ ሀላፊዬ " ብሎ ሁለቱን አገናኝቷቸው ሴቶቹ ጉዳቸውን ሳያውቁ በመኪናቸው ልጁን ይቀባበሉት ነበር :: ከኢሮብም በጊዜ ተመልሶ የመጣው አዲስ አበባ ያለችውም ጠፋ ብላ ሌላ ወንድ እንዳትጀምር ፈርቶም ሳይሆን አይቀርም ቅቅቅ ::

ከኢሮብ ከተመለሰ ከጥቂት ቀናት በኌላ ማታ ከምሽቱ አራት ሰአት አካባቢ ደውሎልኝ በጣም ወፈር ባለ ድምጽ " አንተ ቁልፉን ረስቼ ስለወጣሁ እኔ ሳልመጣ እንዳትተኛ ' ብሎ ስልኩን ዘጋብኝ :: እኔ እኖርበት የነበረው ቤት ከሱ ቤት ጸዳ ያለ ስለነበርና ትርፍ መኝታ ክፍልም ስላለው አንዳንዴ መጥቶ እኔ ይደር እንጂ የቤቴን ቁልፍ አልሰጠሁትም :: ሁሌ እኔ ባለሁበት ብቻ ነው የሚመጣው :: ምን ለማለት እንደፈለገ ስላላወቅኩኝ እያጠናሁ የነበረውን ጥናቴን ሁሉ አስጠፋብኝ ::

ወደ አንድ ሰአት ከቆየ በኌላ በሩን አንኳኩቶ ስከፍትለት ምን የመሰለች ልጅ አቅፎ በሬ ላይ ቆሞ ሳየው ደነገትኩኝ :: የልጅቷን ያህል እንኳ ሰላም ሳይለኝ : ወደ ቤት ውስጥ ገብቶ ሲቆም እኔ የምናገረውን ነገር አጥቼ ደብተሬን ይዤ ለጥናት ቁጭ ስል
"ተነስና ተኛ እንጂ !:: ከአምስት ሰአት በኌላ ጥናት አታጥና ብዬህ አልነበር እንዴ ? ነገ ጧት እንዴት ሆነህ ነው በቂ እንቅልፍ ሳትተኛ /ቤት የምትሄደው :: ሰው የምልህን መስማት ትተሀል !!"

ቆሽቴ እያረረ ምንም ሳልናገር ወደ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ስተኛ እነሱ ሳሎኑ ውስጥ አባሮሽ ይጫወታሉ መሰለኝ ቤቱ እስኪነቃነቅ ኮቴያቸው ይሰማኛል :: ምን እንደሚሰሩ ብቻ ተነስቼ ላይ ብፈልግም ያልሆነ ነገር ላይ እችላለሁ ብዬ ዝም ብዬ ለመስማት ብቻ ተገደድኩ ::

ጧት ከእንቅልፌ ተነስቼ ሻይ ነገር ጠጥቼ ቁልፉን ልሰጠው የተኛበትን መኝታ ክፍል ቀስ ብዬ ባንኳኳ ልጅቷ በአንሶላ ተሸፋፍና ከፈተችልኝ ::

"ደህና አደርሽ ዬታል ልጁ ?"
"ዶላር ዘርዝሬ መጣሁ ብሎ ወጣ ካለ ትንሽ ቆየ :: ያን ያህል ይርቃል እንዴ :: ደግሞ መኪና ስለምይዝ ዬትም ቢሆን ያን ያህል አያቆየውም '
"ማታ መኪና ይዞ ነበር እንዴ ?"
"አዎ መኪና ይዞ ነበር "

መኪናው የሴትዮዋ መሆኑን አልተጠራጠርኩም :: ነገር ግን የዶላሩ ጉዳይ አልገባኝም :: እኔ እስከማውቀው ድረስ ምንም ዶላር በእጁ ነክቶ አያውቅም :: አንድ ዘመድ ካገር ውጭ የለውም :: ፊልም መሆኑ ገብቶኝ የምሆነውን አጣሁ ::

"እኔ ትምህርትቤት ደርሶብኛል :: ተነስተሽ ትለባብሺ ? ቤቱን ዘግቼ መሄድ ስላለብኝ ነው "

""እንትን " የተደረኩበትን ገንዘብ ሰጥቶሀል ወይ ፊልም መሆኑ ነው ?

የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም :: እንደዚያ አይነት ቋንቋ ከወንዶች አፍ አልፎ አልፎ ብሰማም ሴት ልጅ አፍ አውጥታ እንደዚያ ስትናገር ሰምቼ አላውቅም ::
ቶሎ ለባበሰችና የውጭውን በር ከፍታ ከፎቅ ወደ ታች አይታ

"ፖሊስ እንድጠራልህ ትፈልጋለህ ? ገንዘብ ከሌለው የናቱን 'እንትን ' ሄዶ 'እንትን " አያረግም እንዴ ? የኔ እኮ ይከፈልበታል "

ጎረቤት ሰምቶ ቢወጣ ምን ይለኛል ብዬ

"እባክሽን እንደዚያ አትበይ : እሽ ስንት ነው የምሰጥሽ ?'

ማመን የማልችለውን ገንዘብ ጠራች :: ኪሴ ውስጥ ያለውንም አራግፌ ብሰጣት እሷ የጠራችውን እሩቡን አይሆንም :: ያለኝን ሁሉ አውጥቼ ስሰጣት እግሯ ላይ ሁሉ መውደቅ እያሰብኩ ነበር :: ከት /ቤት ከቀረሁ ከት /ቤቱ ተደውሎ አለመግባቴ ወዲያው ለፈረንጆቹ ስለሚነገራቸው ፈረንጆቹ ወይ ይደውላሉ ወይም ይመጣሉ :: ብቻ እግዜር ሲረዳኝ

"አንተ አሳዛኝ የሆንክ ፍጡር ነህ : እሱን ግን እበቀለዋለሁ " እያለች ያለኝን ሁሉ ወስዳብኝ ሄደች ::

ማታ ከት /ቤት ስወጣ መኪና ይዞ በር ላይ ቆሞ እየጠበቀኝ ነበር :: መኪናውን እየከፈተልኝ

" ግባ !! ሲደወል ደግሞ ሰው ይጠብቀኛል አትልም ቀስ ብለህ ነው ከግቢው የምትወጣው ":: እዚያ የሚማሩት ተማሪዎች የሀብታም ልጆች ብቻ ሲሆኑ ለመሀላ አንድ እኔ ብቻ ነበርኩ : ለዚያውም ከጎሳ ቅቅቅ :: አብዛኛዎቹን ቤተሰቦቻቸው እየመጡ በመኪና ፒክ ያረጓቸዋል :: እኔም በስንት ጊዜዬ ዛሬ በመኪና ፒክ መደረጌ ነው :: ቀኑን ሙሉ እያስታወስኩት ደሜ ሲፈላ የነበረው አሁን ሳየው ያንን ሁሉ ረስቼ በስራው መሳቅ ጀመርኩኝ :: ቀጥታ ወደ ምግብ ቤት ወስዶኝ ደህና ነገር ካበላኝ በኌላ ሳንቲም ነገርም አስጨብጦኝ እኔን ቤት አድርሶኝ እሱ መኪናውን ለሴትዮዋ ለመመለስ ሄደ ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Jemjem

መንገደኛ

Joined: 14 Jul 2012
Posts: 5

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 12:45 am    Post subject: Reply with quote

ጎሳ የምትነግረን ታሪክ ራስ ብሩ እንዳለው አንድ ጥሩ ፊልም ይወጣዋል :: የሚገርም ታሪክ ነው !!

የባለሱቅ ፍርሃት ይገባኛል :: ብዙ ታሪኮቹን በማስታወሻዎቼ ከትቤያለሁኝ :: አንድ ባንድ እየተመዘዙ ይወጣሉ !! 'የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል ' እንደሚባለው ፈራህ አልፈራህ እኔ እንደሆን መጻፌን አላቆምም ::

ሙላት ከበደ የሚባል አሁን ነጌሌ ቦረና ግብርና /ቤት የሚሰራ የክብረ መንግስት ልጅ ስለ ባለሱቅ የነገረኝን ጉድ ላውጣ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 12:51 pm    Post subject: Reply with quote

ጎሳ
እኔ ባነበብኩህ ቁጥር ጓደኛህን ጥምድድድ አድርጌ ይዤዋለሁ .... ንድድድድድ አድርጎኛል ከምር
እኔ የሴት ልጅ ህይወት ላይ የሚጫወት ሰው ... አይመቸኝም ............ እናትና እህት የለውም እንድል ያደርገኛል
ያቺ ሴት ምንም ትሁን ምን .... ለማኝ : ሸሌ : አጭበርባሪ : ናቂ ... በሽተኛ ... የሆነችው ትሁን ... እኔን የሚያክል ነፍስ የተሸከመች ... ክብርት የእግዜር ፍጡርን የማያከብር ሰው ..... አይስማማኝም
እና ታሪክህን ሳነበው .... እያናደደኝ ... ነገር ግን ከብዙዎቹ እሱዎች አንዱ ስለሆነ ... አዝኜ ነው ያለፍኩት

Quote:

የባለሱቅ ፍርሃት ይገባኛል :: ብዙ ታሪኮቹን በማስታወሻዎቼ ከትቤያለሁኝ :: አንድ ባንድ እየተመዘዙ ይወጣሉ !! 'የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል ' እንደሚባለው ፈራህ አልፈራህ እኔ እንደሆን መጻፌን አላቆምም ::አንተ ልጅ በጣም እየተመቸኸኝ ነው ከምር ..... በማስታወሻህ ላይ የሚከተብ የባለሱቅ ታሪክ በእጅህ ካለ ... በእውነት እኔ ራሴ እራሴን አላውቅም ማለት ነው .... ይህንን ያህል የሚፃፍ ታሪክ አለኝ ለካስ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፕሊስ ፕሊስ በናትህ አንብብልኝ እራሴን

Quote:

ሙላት ከበደ የሚባል አሁን ነጌሌ ቦረና ግብርና /ቤት የሚሰራ የክብረ መንግስት ልጅ ስለ ባለሱቅ የነገረኝን ጉድ ላውጣ ?

ዋውውውውውውውው ሙላቱ ... በናትህ በፈጠረህ ንገረኝ ምን ብሎ እንደነገረህ
ሙላቱ ማለት በአለም አንደኛ ተንኮለኛ ልጅ ... ውይ ውይ .... በሱ አፍ አለመግባት ነበር
ነገር ግን ይሁን ካልክ .... በለኝ
እኔም የማውቃትን አንዲት ትንሽዬ ታሪክ እነግርሀለሁ ስለሙላቱ

ፕሊስ ንጋቱ አይቸውን ታውቀዋለህ ?
በአላህ የት ነው ያለው ይሆን
ቤተሰቦቹስ ?

ዝምተኛ ጎበዝ የሆነ ልጅ ነው
ደስስስ ይለኝ ነበር

እስኪ ፕሊስ ፅሁፍህን አታሳጥርብኝ
በጉጉት እየጠበኩህ ነው

ደሞ ከወልደ -እስራኤል እነፍቃዱ አቦምሳ ቤት እንቅም ነበር ይለኛል እንዴ ....
አሁን እኮ ነው ያየሁት
ምን አገናኛቸው ... ወልደ -እስራኤልና ፍቃዱን

ወልደ -እስራኤልን ሳቀው ,..... ውሎው በሙሉ ከፀጋዬ መርጊያ ጋር ብቻ ነበር
ወይስ ከላይ እስከታች ነበር ይሆን ጓደኞቹ
ወይስ ያቺን ቆንጅዬ የአቦምሳ ልጅ ለማየት ይሆን የሚሄደው
እኛ በበራቸው ስናልፍ ... ውበቷን ለማየት .. በአጥር ቀዳዳ ...
አይይይይይይይይይይይይ ይቅር ተወው ... አታንሳብኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 3:08 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
እንደዚህ ያሉ አሳዛኝ ድርጊቶችና አጋጣሚዎችን እኔም ከመስማት አልፎ አንዴ ለቫኬሽን ወደቤት ሄደን ያየሁትን የምረሳው አይደለም ::
ያንተም ባልንጀራ በጣም ጸያፍ ድርጊት ነው ያደረገው በውነት እኔም እንደባለሱቅ እየተናደድኩ ነው ያነበብኩት ::

በነገራችን ላይ ባለሱቅ አይዳ የማነ ስለምትባል ልጅ ሰምተህ ታውቃለህ ? ፕሊስ የራሷን ታሪክ ራሷ ናት በራዲዮ የምትናገረው እባክህ ስማው ::
http://betengna.etharc.org/listenin/Sheger%20FM%20Broadcasts/Aida%20Yemane
ከመጀመሪያው ጀምሮ አዳምጠው ::

ስለ ወልደእሥራኤልና ፍቃዱ አብረው መቃም አለማወቅህ አስደናቂ ነገር ነው
እኔም በአንዲት ጉዳይ አንድ ሁለት ቀን ያንን ማዕድ ተካፍያለሁ ::
ይታጠቅ ያኔ በጣም ትንሽ ልጅ ነበር አሁን መቼም ትልቅ ይሆናል ባየውም አላስተውሰውም ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 3:31 pm    Post subject: Reply with quote

ጀምጀማችን ታሪኩ ባለሱቅን እንዲህ ካናደደው ምንም ፊልም ሳይሰራበት ይቀበር ቅቅቅ ::ብዙ ትዝታ ነበረኝ : አሁን ግን የአሊቴናዋን ብቻ መቋጫ ላብጅላት ::

Quote:
ጎሳ
እኔ ባነበብኩህ ቁጥር ጓደኛህን ጥምድድድ አድርጌ ይዤዋለሁ .... ንድድድድድ አድርጎኛል ከምር
እኔ የሴት ልጅ ህይወት ላይ የሚጫወት ሰው ... አይመቸኝም ............ እናትና እህት የለውም እንድል ያደርገኛል
ያቺ ሴት ምንም ትሁን ምን .... ለማኝ : ሸሌ : አጭበርባሪ : ናቂ ... በሽተኛ ... የሆነችው ትሁን ... እኔን የሚያክል ነፍስ የተሸከመች ... ክብርት የእግዜር ፍጡርን የማያከብር ሰው ..... አይስማማኝም
እና ታሪክህን ሳነበው .... እያናደደኝ ... ነገር ግን ከብዙዎቹ እሱዎች አንዱ ስለሆነ ... አዝኜ ነው ያለፍኩት

ባለሱቃችን !! የልጁ ሁኔታማ ማንንም ያናድዳል :: የጥንት የገዳም ጓደኛዬ ስለነበር ብቻ እንጂ ስራውንማ ስታስበው ልትቀርበው እራሱ አትፈልግም :: እነኚያን አናዳጅ ታሪኮቹን ትቼ የኢሮብን ሲስተር መጨረሻ ብቻ ላስነብብህ ::

ከሶስት ወር እረፍታቸው ተመልሰው የገዳሙን ህይወት መልመድ ሲያቅታቸው የማዕረግ ልብሳቸውን አውልቀው ለማህበሩ መልሰው ገዳሙን ተሰናብተው ከመውጣታቸው በፊት ደህና ሳንቲም ከት /ቤቱ "ተበድረው " "አባ ማርቆስ " ባንክ ሂሳብ ያስገባሉ :: ገዳሙን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀው በወጡ በሁለት ሳምንታቸው ከልጁ ጋር ተያይዘው ጆሀንስበርግ ይገቡና ከዚያ ወደ እነ አይፋ አገር ይጨረድዳሉ :: ከዚያ በኌላ ግንኙነታችን ተቋርጦ በስንት ጊዜዬ አሁን አግኝቼ ባለፈው ሳናግረው

"አባ ማርቆስ ሲስቱካ ሰላም ናቸው ወይ ? ስንት ልጅ ወለዳችሁ ?'

"እባክህን ተው ጎሳ : ቆየን እኮ ከተለያየን "

"ይታየኝ ነበር : ሁለት ወር ኢሮብ አብረሀቸው መኖር ያልቻልከውን እድሜ ልክ እንዴት ችለህ ትኖራለህ ድሮ :: ሲጀመርም ማግባት አልነበረብህም :: አሁንም አመልህ አልለቀቀህም አይደል ? ቅቅቅ "

"ጎሳ በውነት እልሀለሁ ካዲስ አበባ ስወጣ ያንን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቼ ጥሩ የትዳር ህይወት መኖር ጀምሬ ነበር :: ታውቀኛለህ አልደብቅህም :: እዚህ አገርም በሰላም በመኖር ላይ እያለን ፖለቲካ መረዘን "

"ምን ማለትህ ነው ...ሳውቅህ እኮ ከመስቀሉ እንጂ ከፖለቲካው አልነበርክም ? እንዴት ፖለቲከኛ ሆንክ ?"

"እኔ አይደለሁም እባክህን : ዬት አግኝተዋት እንደሰበኳት አላውቅም አንድ ቀን ስብሰባ ልካፈል ነው ብላ ሄደች :: ከዚያም ስለ ወያኔ ጥሩነት ታወራልኝ ጀመር :: እኔ ፖለቲከኛ ባልሆንም ወያኔ አገራችንን ስለከፋፈለው ብቻ እንደ ጠላት ነው የማየው :: ይኽንን ሀሳቤን ላስረዳት ብሞክር መግባባቱ ቀርቶ ጧት ማታ ጭቅጭቅ ሆነ :: እኔም ድሮ የማልፈልገውን ፖለቲካ አንዳንዴ ስብሰባዎችን መከተል እና የተጻፉትን ማንበብ ጀመርኩ እሷን በሀሳብ ለመምታት :: በሰላም የጀመርነው ክርክር በጥል ተጠቅቆ እንለያይ ነበር :: ያልተለመዱ ስልኮች ይደወሉና በትግርኛ ለረዥም ጊዜ ይወራ ጀመር :: በቃ ነብሴ ሰላም አጣች :: ሁለታችንም ፖለቲካን ትተን እንደ ድሮው በሰላም እንኑር ብላት : እንደ አንድ ዜጋ ባገሬ ጉዳይ መሳተፍ አለብኝ ብላ እምቢ ስትለኝ ከዚያ በላይ መቆየት ስላልቻልኩ ጥያት ወጣሁ :: ብዙም ሳትቆይ አንዱን የትግራይ ሰው ማግባቷን ሰማሁልህ እልሀለሁ :: ጎሳ አንፍድ ነገር ልምከርህ ትሰማኛለህ ?'

"ምንድነው የምትመክረኝ ? ስለፖለቲካ እንዳይሆን "

" ማግባት አለማግባትህን አልነገርከኝም አይደል ...እግዚአብሔርን እልሀለሁ ከማግባትህ በፊት የፖለቲካ አስተሳሰቧን የግድ ማወቅ አለብህ :: የተለያየ ሀይማኖት የሚከተሉት ሰዎች አብረው ሊኖሩ ይችላሉ :: ነገር ግን በፖለቲካ አስተሳሰብ ከተለያያችሁ ትዳራችሁ ይፈርሳል :: መርዝ ነገር ነው ::"

"እምምምም :: ሚስቴ ዜና እንኳ መስማት አትፈልግም :: እኔም ገና የራሴ የምለው የምደግፈው የፖለቲካ ድርጅት የለም :: እሷ እስክትመርጥ እጠብቃትና እሷን እከተላለሁ :: እንዳንተ እንዳልከስር ቅቅቅ ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ :: አንተስ ከዚያ ወዲህ አላገባህም "

"ለነገሩ እኔም ከሰድስት ወር በፊት ካንዷ ጋር አብረን መኖር ጀምረናል :: ሳታረግዝ ሁሉ አትቀርም :: ፍጥነቷ ቢያስፈራኝም እሷ ትሻለኛለች "
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 4:36 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ ሸጋው
Quote:
በነገራችን ላይ ባለሱቅ አይዳ የማነ ስለምትባል ልጅ ሰምተህ ታውቃለህ ? ፕሊስ የራሷን ታሪክ ራሷ ናት በራዲዮ የምትናገረው እባክህ ስማው ::

ብዙ ብዙ አሳዛኝ ታሪኮች ሰምቻለሁ .... የአይዳንም በቅርብ እሰማለሁ
የጭንቅ ቁስል ስለሚባል ታሪክ ያነበብክ ይመስለኛል :: አንድ ሰሞን መነጋገሪያ አርስት አድርጌው ነበር የሆነ ክፍል ገብቼ
ኤኒዌይ አመሰግናለሁ ስላካፈልከኝ .... በቅርብ አዳምጠዋለሁ

አንተ ብሽቅ ጎሳ

Quote:
ባለሱቃችን !! የልጁ ሁኔታማ ማንንም ያናድዳል :: የጥንት የገዳም ጓደኛዬ ስለነበር ብቻ እንጂ ስራውንማ ስታስበው ልትቀርበው እራሱ አትፈልግም :: እነኚያን አናዳጅ ታሪኮቹን ትቼ የኢሮብን ሲስተር መጨረሻ ብቻ ላስነብብህ ::

እንዲህማ አትለኝም
ሰው ስለተናደደ መፃፍ ያለበት ታሪክማ መቆም የለበትም .... ሌሎች ይማሩበታል .... ያሁኑን የሰው ስሜት አትይ ....
ፃፈው
እየተናደድኩም ቢሆን አነበዋለሁ ... ልክ የጭን ቁስልን አንብቤ በጨረስኩበት አቅሜ
አይዞህ አልፈራርስም .... ቶሎ ተናድጄ ቶሎ ምረሳ አይነት ሰው ስለሆንኩ .. አታስብ

የጓደኛህ መጨረሻ ግን ያሳዝናል ... በፖለቲካ ምክንያት መለያየት ያሳዝናል
አዲሲቷ ሄዋንን በደንብ እንዲንከባከባት በቤቱ ስም የጋራ ምክርህን አቅርብልን
.......................

ራስብሩ ... ቆይ ቆይ የወልደ -እስራኤል እድሜ ስንት ነው ..... ቅቅቅቅቅቅቅ
ውይ ለካስ ያንተ ጓደኛ ነው
ረስቼ ነው ተወው በቃ

ኤሊያስ ተባባል አንዴ ባወጣው ዘፈኑ ላይ ... ምን አለ መሰላቹ
..... ግን አምላክ ይመስገን ድርሻዬን ይዣለሁ
እድሜዋ ከገፋ ካገሬ ልጅ ጋራ ተወዳጅቻለሁ
እድሜዋን ብጠይቅ 35 አለች 35 አለች
ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ምንድነው
የፍቅር ጣም ያለው ጠና ካለ ሴት ነው

ፍቅር ይኑር እንጂ እኩያ ምንድነው
ድሮም ያንዳንዱ እድሜ ዘጠኝ ቅናሽ አለው

ይህች ዘፈን መዘፈን የነበረባት ግን ለወንዶቹ ነበር ... በተለይ ለኔና ለራስ -ብሩ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ገደለኝ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 10:07 pm    Post subject: Reply with quote

ራስ ብሩአችን ይቅርታ አናዳጅ ታሪክ ጽፌ ላናደድኩህ : አይለመደኝም ቅቅቅቅ ::

ባለሱቃችን !!!!
Quote:
ፃፈው
እየተናደድኩም ቢሆን አነበዋለሁ ... ልክ የጭን ቁስልን አንብቤ በጨረስኩበት አቅሜ
አይዞህ አልፈራርስም .... ቶሎ ተናድጄ ቶሎ ምረሳ አይነት ሰው ስለሆንኩ .. አታስብ

ኌላ ደምግፊትህ ትንሽ ቢጨምር በኔ ልታሳብብ ነው ወይ ቅቅቅቅ ጸጉርህ እንደሆን ድሮም በኩርኩምም በምንም ተሰናብቶሀል አሉ ቅቅቅ ::

Quote:
ኤሊያስ ተባባል አንዴ ባወጣው ዘፈኑ ላይ ... ምን አለ መሰላቹ
..... ግን አምላክ ይመስገን ድርሻዬን ይዣለሁ
እድሜዋ ከገፋ ካገሬ ልጅ ጋራ ተወዳጅቻለሁ
እድሜዋን ብጠይቅ 35 አለች 35 አለች
ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ምንድነው
የፍቅር ጣም ያለው ጠና ካለ ሴት ነው

ሁሌም የሚገርመኝ እንዴት ግጥሞቹን አሳታውሰሀቸው እንደምትጽፋቸው ነው :: ደግሞ ለሀሳብህ ተስማሚ ዘፈን እንደምንም አታጣም :: እውነትም እነኝያን የዶሌን እና የአንፈራራን "ደን " ያመነመንከው አንተ ሳትሆን አትቀርም ቅቅቅ ለዚያውም ግብርና / ውስጥ እየሰራህ ቅቅቅቅ

ጀምጀማችን እስቲ እየመዘዝክ አሰማና ስለ ባለሱቃችን :: ምንም ወደ ኌላ አትበል :: እኛም ጆሯችንን እንደ አንቴና መዘን እንሰማሀለን ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1334

PostPosted: Fri Jul 20, 2012 10:28 pm    Post subject: Reply with quote

ቄስ ገበዝ ጎሳ ..የጀመሩትን ታሪክ ሳየጨርሱ ..እንደገና ሌላ ታሪክ ጀምረው እንዲጽፍ ሲያበረታቱት ሳይይይይይይ ...አይ ስው ብዬ ውልቅ ..
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jul 21, 2012 6:55 pm    Post subject: Reply with quote

ገልብጤ እንደጻፈ(ች)ው:
ቄስ ገበዝ ጎሳ ..የጀመሩትን ታሪክ ሳየጨርሱ ..እንደገና ሌላ ታሪክ ጀምረው እንዲጽፍ ሲያበረታቱት ሳይይይይይይ ...አይ ስው ብዬ ውልቅ ..

ወንድማችን ገልብጤ !!!
ቅቅቅቅቅ :: ጃጀሁ መሰለኝ : አንዱን ጥዬ አንዱን አነሳለሁ :: ድሮም ቅስናውን ካፈረሰ ሰው ምን ቁምነገር ይገኛል ብለህ ነው ቅቅቅ :: ያኔ ታሪኩን ስጀምረው ለዋርካው በጣም ፍሬሽ ስለነበርኩ ነው መሰለኝ ቀኑን ሙሉ እየለቀለኩ ብውል ምንም አይሰማኝም ነበር :: አሁን እንደዚያ አይነት ትዕግስት ለምን እንዳጣሁ አላውቅም :: ስንት ጊዜ ጀምሬ ሁለት መስመር እንደጻፍኩ ሰልችቶኝ ትቼያለሁ መሰለህ :: ትንሽ ጾም ነገር ይዤ " ሀይሌን አድስልኝ " ብዬ መጸለይ ያለብኝ ይመስለኛል ቅቅቅ :: ታሪኩን እስካሁን እስካሁን ባለመርሳትህ ደስ ብሎኛል :: እስቲ እንደሚሆን እናደርጋለን :: ተባረክ ወንድሜ !!
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jul 21, 2012 7:33 pm    Post subject: Reply with quote

በችኮላ ፅፌ የኤሊያስን ዘፈን አበላሸሁበት
ቢጥምም ባይጥምም እንደገና አስተካክዬ እንዲህ አቀርበዋለሁ .... ራስብሩን ለማብሸቅ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ግን አምላክ ይመስገን ድርሻዬን ይዣለሁ
እድሜዋ ከገፋ ካገሬ ልጅ ጋራ ተወዳጅቻለሁ
24 አመት ጎሮምሳ ልይ ያላት ጎሮምሳ ልጅ ያላት
እኔ ምን ቸገረኝ ልቤ ከወደዳት
እድሜዋን ስጠይቅ 35 አለች 35 አለች
ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ብትዋሸኝ ምንድነው
ድሮም ያንዳንዱ እድሜ ዘጠኝ ቅናሽ አለው
ፍቅር ይኑር እንጂ እኩያ ምንድነው
የፍቅር ጣም ያለው ጠና ካለ ሴት ነው

እያለ ነው ሚቀጥለው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እዚያው ዘፈን ላይ ምን የሚል ነገር አለው መሰላቹ

ከቤቷ አሳድራኝ በጣም አሳቀችኝ በጣም አሳቀችኝ
አልጋ መውረጃ ብል መሰላል ሰጠችኝ መሰላል ሰጠችኝ
እግዚአብሄር ያለለት ወይ ሎቶሪ ገዝቶ ባንድ ብር ይከብራል
ጥፋ ያለው ደሞ ውኃ አንቆት ይሞታል

እያለ ይቀጥላል
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ጎሲቲ ለምን ይዝ ዘፈን ትዝ እንዳለኝ እኔም አላቀውም ... ግን ግጥምጥም ይልልኛል
ምን ታረገዋለህ .... መረገም ያመጣው ችሎታ ነው
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ገልብጤ ወንድሜ
ስሜትህ ይገባኛል ... ነገር ግን ጎሳ የጀመረውን ታሪክ እንዳይጨርስ ያዘዝኩት እኔ ነኝ ....
እኔ የመለስ ዜናዊ .... ተማሪ
ምንም የማይሳነኝ ... ከሰማይ በታች ማድረግ የፈለኩትን በሙሉ ማድረግ የሚችል ጉልበት ያለኝ ... እኔ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እና ቁርጥህን እወቅ ... በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ... የፅጌን ታሪክ አታገኘውም .... ..ከጎሳ
በጣም ያስፈልገኛል ... እሱን ካልሰማሁ ውኃም አልጠጣም .. እንቅልፍም አይወስደኝም ... ምሳዬንም አልበላም ካልክ ግን
እነግርሀለሁ ... በድብቅ .. በጆሮህ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ጎሳን ግን አታስቸግረው .... ኦኬ !.... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አቤት አለቃ ብሆን ደንበኛው ዲክታተር እኮ ነኝ
ሳስፈራ
!

እረ ጀምጀምን የበላ የቦረና ጅብ አልጮህ አለ
ሙላቱ ከበደን ለመጠየቅ ሄዶ ... አረቀሎ ላይ እርጎ ሲያገኝ በዚያው ቀረ ይሆን .. አንዷን የቦረና ሸጋ ወዶ

እስኪ እየጠበቅንህ ነንና
ብቅ በል አንተ ጉጂ
የባለሱቅ ዲያሪ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Jul 21, 2012 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቃችን !!!
ስራ ቦታ ሆኜ ድሮ የጻፍካቸውን ወደ ኌላ ተመልሼ ሳነብ ነው ያደርኩኝ :: የሆነ ቦታ ስደርስ ኮሽታ በማይሰማበት በውድቅት ሌሊት በጣም ከት ብዬ በመሳቄ ሰው ፊት አዋረድከኝ :: እንዴት ብዬ ልንገራቸው አብረውኝ ለሚሰሩ ሰዎች :: ጅል አደረጉኝ :: የስራህን ይስጥህ ቅቅቅቅ :: ለካ እንዲህ አይነት ሰው ነህ :: ትዝ ይልህ እንደሆን ልጥቀስልህ ::
Quote:
ሁሌ እነግርህ የለንም .... ለምንድነው ወደጨረቃ ዞረህ ምትሸናው :: ሁለተኛ ወደጨረቃ ዞረህ አትሽና
> ምች መቶህ እኮ ነው ... ወደ ጨረቃ ዞረህ ስለምትሸና
አይ ምችችችች ለካስ እንደዚህ ነው ሚመታው ወደ -ጨረቃ ዞረው ሲሸኑ ምች ድርግምምምምምምም ያደርጋል አሉ
ሁለተኛ ወደ -ጨረቃ ዝፕራቹ አትሽኑ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ትዝ ይልሀል እዚያ ወንዙ የሰራኸው ቅቅቅቅ ::
ታላቁ አደቆርሳ ያለህን ደግሞ ልጥቀስልህ
Quote:
ባለሱቅ አንተ እዚህ ቤት ባትኖር ጸሀፊውም አንባቢውም ከአስር አይበልጡም ነበር ከምር ዛሬ የኛን
ልጆች በሳቅ አድምቀሀቸው ነው የቆየኸው ::
ደሀ ነገ ካልጻፈችልህ ሌላ ሰው ይጽፍልሀል ቅቅቅ ቅቅቅቅቅቅ ቅቅቅቅቅቅቅቅ

በጣም በጣም እስማማለሁ :: ጉደኛ ሰው ነህ ::

ግጥሙን ስታሻሽለው ትርጉሙን ጨመረ ቅቅቅቅ :: ግን ለምን ራስብሩአችንን እንደምትነካካበት አልገባኝም ሚስጢሩ ቅቅቅ ::

Quote:
ገልብጤ ወንድሜ
ስሜትህ ይገባኛል ... ነገር ግን ጎሳ የጀመረውን ታሪክ እንዳይጨርስ ያዘዝኩት እኔ ነኝ ....
እኔ የመለስ ዜናዊ .... ተማሪ
ምንም የማይሳነኝ ... ከሰማይ በታች ማድረግ የፈለኩትን በሙሉ ማድረግ የሚችል ጉልበት ያለኝ ... እኔ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እና ቁርጥህን እወቅ ... በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ... የፅጌን ታሪክ አታገኘውም .... ..ከጎሳ
በጣም ያስፈልገኛል ... እሱን ካልሰማሁ ውኃም አልጠጣም .. እንቅልፍም አይወስደኝም ... ምሳዬንም አልበላም ካልክ ግን
እነግርሀለሁ ... በድብቅ .. በጆሮህ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ጎሳን ግን አታስቸግረው .... ኦኬ !.... ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
አቤት አለቃ ብሆን ደንበኛው ዲክታተር እኮ ነኝ
ሳስፈራ

ቅቅቅቅ ቪቶ ፓወሩንም እንዳትረሳ ቅቅቅቅ :: በግድ በሰላም አገር ያንተ ተገዢ አደረከኝ እኮ ቅቅቅ :: ገልብጤ አያምንህም ብዬ አላምንም : ሰውን የማሳመን ስጦታ በትልቁ ተችሮሀል ቅቅቅቅ ::

በል አሁን ወደቤት መሄጃ ጊዜዬ ደርሷል :: ግን በወንዙ ዳር ስራህ እንደሳቅኩ ነው እቤቴ የምደርሰው :: ቅቅቅቅ
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Jul 22, 2012 12:15 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

http://www.diretube.com/tilahun-gessesse/japanwan-wodje-fan-made-dedicated-to-tilahun-video_fff3383dd.html

ከላይ የቀረበው ሙዚቃ ላይ (ጃፓንዋን ወድጄ ) ባለሱቅን እንድታዩት ነው ያቀረብኩላችሁ ::
ባለሱቅ ከጃፓኗ ፍቅረኛው ውፍረቱን ቀንሶ ሸንቀጥ ብሎ ነው የሚታየው ::
በጣም ስለምቸኩል ነው ::በተነሳው ወሬ (ጨወታ ) ላይ እመለሳለሁ ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 369, 370, 371 ... 381, 382, 383  Next
Page 370 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia