WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 371, 372, 373 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Jul 31, 2012 6:15 am    Post subject: Reply with quote

እንዴ ነገሩ እንዴት ነው
ራስብሩ
ሞፍቲ
ጎሳ
ጀምጀም
ገልብጤ
ጋሽ ተድላ
አንፈራራ
የግል

እንዴት ነው ነገሩ
ሰውዬው ደየመ እንዴ ?
ሀዘን የተቀመጣቹ ትመስላላቹ /

እረ ለኛም አብስሩንና ... ለቀብር ባንደርስ 40 እንኳን መጥተን ሀዘናችንን እንግለፅ እንጂ
ምንስ ክፉ ቢሆን 21 አመት አስተዳድሮን የለ እንዴ (አልጋችን የተለያየ ቢሆንም )

ነገሩ እንዴት ነው እንዴት ነው ነገሩ እንዴት ነው
ስመጣ ስሄድ ሀሳቤ ላንተ ብቻ ነው

እረ ንገሩን
የሀዘን ቤት አስመሰላቹት እኮ
... አለች የሌሊት ወፍ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Tue Jul 31, 2012 10:59 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
እንዴ ነገሩ እንዴት ነው
ራስብሩ
ሞፍቲ
ጎሳ
ጀምጀም
ገልብጤ
ጋሽ ተድላ
አንፈራራ
የግል

እንዴት ነው ነገሩ
ሰውዬው ደየመ እንዴ ?
ሀዘን የተቀመጣቹ ትመስላላቹ /

እረ ለኛም አብስሩንና ... ለቀብር ባንደርስ 40 እንኳን መጥተን ሀዘናችንን እንግለፅ እንጂ
ምንስ ክፉ ቢሆን 21 አመት አስተዳድሮን የለ እንዴ (አልጋችን የተለያየ ቢሆንም )

ነገሩ እንዴት ነው እንዴት ነው ነገሩ እንዴት ነው
ስመጣ ስሄድ ሀሳቤ ላንተ ብቻ ነው

እረ ንገሩን
የሀዘን ቤት አስመሰላቹት እኮ
... አለች የሌሊት ወፍ

እሄውልህ ሱቂቲ እንደጠረጠርከው አውላላ ሜዳ ላይ በትኖን ደየመ ....ደየመ .... ...

አንተስ አይቆጭህም አንዴም ቢሆን ያኔ ጃፓን የመጣ ግዜ ሽንቁጥቁጥ ብለህ ገልምጠኧዋል ...ማለተ አስተናግደኧዋል ::
ይብላኝልን ለኛ ! አንድ ቀን እንኳ በአካል አግኝተነው ባስለመደን ስድብ ወራዳ ! ጨምላቃ ! ሌባ ! ሳንለው መንገዱን
ጨርቅ አደረገለት ! ሄደ ነጎደ !
በቃ ! ለዚሁ ነበር ! ሌሎቹስ ምን ይማሩ ይሆን ?
የምንወዳት ሀገራችንን እግዚያብሄር ይጠብቅልን !!!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!!!!!

ቸር እንሰንብት !!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 4:23 pm    Post subject: Reply with quote

መከራ አየን እኮ ሰዎች !!!
የማፑቶው ሌባ የባለሱቃችንን ዶላር ብቻ ሳይሆን ጊዜያችንንም ጭምር ነው የሰረቀው :: ይኸውልህ ውዱ ባለሱቃችንን ባዕድ አገር ባለው ወንድማችን አንጨክንም ብለን ካሜራውን እህታችን የግል ትተካው ብለን እኛ ግን ግማሹንም ቢሆን የጠፋውን ዶላር ልንተካ የሆነ ፈንድሬይዚንግ ነገር አስተባብረን ነበር :: የተገኘውን ነገር ሞፊቲ እንዲልክልህ ርስቂውን ወስደን ሳናስፈርመው ሰጥተነዋል :: በምን እንዳፈዘዘን አናውቅም ::

ስለሰሞኑ ወሬ አናንሳ :: ኢሳት እና ቢቢሲ ግራ አጋቡን :: ለነገሩ ቆንጆ የወሬ አርዕስት ስላገኘን : ቢድንም ቢሞትም አንዴ እንደተደበቀ ይቆየን ቅቅቅ :: መደበሪያ አግኝተናል ቅቅቅ
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 6:49 pm    Post subject: Reply with quote

Gosa እንደጻፈ(ች)ው:
መከራ አየን እኮ ሰዎች !!!
የማፑቶው ሌባ የባለሱቃችንን ዶላር ብቻ ሳይሆን ጊዜያችንንም ጭምር ነው የሰረቀው :: ይኸውልህ ውዱ ባለሱቃችንን ባዕድ አገር ባለው ወንድማችን አንጨክንም ብለን ካሜራውን እህታችን የግል ትተካው ብለን እኛ ግን ግማሹንም ቢሆን የጠፋውን ዶላር ልንተካ የሆነ ፈንድሬይዚንግ ነገር አስተባብረን ነበር :: የተገኘውን ነገር ሞፊቲ እንዲልክልህ ርስቂውን ወስደን ሳናስፈርመው ሰጥተነዋል :: በምን እንዳፈዘዘን አናውቅም ::

ስለሰሞኑ ወሬ አናንሳ :: ኢሳት እና ቢቢሲ ግራ አጋቡን :: ለነገሩ ቆንጆ የወሬ አርዕስት ስላገኘን : ቢድንም ቢሞትም አንዴ እንደተደበቀ ይቆየን ቅቅቅ :: መደበሪያ አግኝተናል ቅቅቅ

ጎሳ =ያዋጣችሁት ገንዘብ አልሞላ ብሎኝ ወድያና ወዲህ እየተንከራተትኩ ነው ::ባለሱቅ ደግሞ የጠፋበትን ብቻ
ሳይሆን ብሩ ቢኖር ኖሮ የሚወልደውንም ጭምር ስለሚያስብ የግድ ከነትርፉ ካልሰጠኧው ስማችንንም ሊያጠፋ ይችላል ::
ደግሞ አደነዘዘኝ የምትለው እኔ ነኝ እንዴ የጅሎ ጩቶን መፋቅያ ይዤ የወጣሁት ?

ከሁሉም ደግሞ የገረምከኝና እዛ መፍብረክያ ቤትም ገብተህ የምትጽፈውን እንደተመለክትኩት ኢሳትን
ለማጣጣል መሞከርህ ነው ::
እስቲ ዜናውን ደጋግመህ አድምጠው ::ክራይስስ ግሩፕ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሰጡትን ምንጭ በተለያየ መልኩ ከዲፕሎማቶችና ከመሳሰሉት አጣርቼ አቀረብኩ አለ እንጂ
ክራይስስ ግሩፕ ኦፊሻሊ ዜናውን ኢሳት አልሰጠም ::
ከዚህም ውጪ ቢቢሲም ቢሆን የቱልቱላውን የበረከት ስምኦን የውሸት ዋሽንት ነው የነፋው እንጂ ቢቢሲ እራሱ
የደረሰበት ዜና የለም ::በደንብ ካነበብከው የመንግስት ቃል አቀባይ ደህና ናቸው አሉ ብሎ ነው ዜናውን የሰራው ::
ከዚህ ውጪ ኢሳትና ቢቢሲ ግራ አጋቡን ከምትል ግራ ያጋባህን ኢቲቪን ለምን ለመውቀስ አልሞከርክም ?
ምክንያቱም ኢሳት ሞተዋል ብሎ ካረጋገጣ አልሞቱም የሚለው ኢቲቪ ደግሞ መለስን እሄው ብሎ አሳይቶ ወሬውን ማክሸፍ ነበረበት ::
ወይስ የመለስ ጣራሞት በረከት ነው ? ማንም እንደሚረዳው እንዲህ አይነት ውዥንብር በሀገሮች ላይ ሲፈጠር እውነትን
በመስራት ወሬውን ማረጋገጥ ብቻ ነው ::
ስለዚህ 42 ቀን ሳይታዩ የጠፉትን መሪ አሉ የሚለው አካል በድምጽም ይሁን በምስል አቅርቦ ማሳየት አለበት ::
ለማንኛውም በተደጋጋሚ ስትጽፍ ስላየውህ ነው መልስ ለመስጠት የሞከርኩት እንጂ ይህን መድረክና ይህን ቤት
በዚህ መልኩ እንድንቀጥልበት አይደለም ::

ቸር እንሰንብት !!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 7:07 pm    Post subject: Reply with quote

ሞፊቱካ Laughing Laughing Laughing የጅሎ ጩቶ መፋቂያን እኮ ካስተምስ አናስገባ ብለው ወሰዱብኝ ቅቅቅ :: ባለሱቅ ደግሞ በጊዜ ወለዱን አስቦ ይንገረና ቅቅቅ

ደግሞ ስለ ኢሳት : ታማኝነቱ ያው መለየቱ ይቀራል እንዴ ? ማጣጣሌማ አይደለም :: ግን ኦፊሺያሊ ያላገኘው መረጃ ከሆነ ከዚያ አገኘሁ ብሎ ምንጩን መጥቀስ መረጃውን ሊክ ያረጉለትን ሰዎች ሊጎዳ ይችላል ብሎ አያስብም እንዴ ? እስቲ እናየው የል ? እኛን ምን በባዶ ሜዳ አከራከረን ? ቀለል አርገው እንጂ ቅቅቅቅ
Quote:
ከሁሉም ደግሞ የገረምከኝና እዛ መፍብረክያ ቤትም ገብተህ የምትጽፈውን እንደተመለክትኩት ኢሳትን
ለማጣጣል መሞከርህ ነው ::

_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 7:23 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ሞፊቱካ Laughing Laughing Laughing የጅሎ ጩቶ መፋቂያን እኮ ካስተምስ አናስገባ ብለው ወሰዱብኝ ቅቅቅ :: ባለሱቅ ደግሞ በጊዜ ወለዱን አስቦ ይንገረና ቅቅቅ

ደግሞ ስለ ኢሳት : ታማኝነቱ ያው መለየቱ ይቀራል እንዴ ? ማጣጣሌማ አይደለም :: ግን ኦፊሺያሊ ያላገኘው መረጃ ከሆነ ከዚያ አገኘሁ ብሎ ምንጩን መጥቀስ መረጃውን ሊክ ያረጉለትን ሰዎች ሊጎዳ ይችላል ብሎ አያስብም እንዴ ? እስቲ እናየው የል ? እኛን ምን በባዶ ሜዳ አከራከረን ? ቀለል አርገው እንጂ ቅቅቅቅ

አንተ ምቼ እንዲህ በባዶ ሜዳ ተከራከርክና ነው ?
ለማንኛውም ዜና በተለያየ መልኩ መስራት እንደሚቻል ማወቅ ያስፈልጋል ::
ኦፊሻሊ የሚሰጥ ምንጭ እንዳለ ሁሉ ከውስጥ ምንጭ ኦፊሻሊ ያለሆነ ዜናም ይሰራል ::
ቢቢሲ ሲኤንኤን የመሳሰሉ ዜናዎችም በዚህ መልኩ ይሰራሉ ::ከዲፕሎማት ምንጮች ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
ምስራያ ቤት ከውስጥ ባገኘነው ምንጭ ከመከላከያ / ባገኘነው አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ እያልክ ዜና መስራት ትችላለህ ::እዚህ ላይ የሰራኧው ዜና እውነተኛ ለመሆኑ የራስህን ማረጋገጫ በተለያየ መልክ ትወስዳለህ ;;ትጥራለህ ::
እንዳልከው ከውስጥ ምንጭ ሲባል ሰዎቹን አያስወቅሳቸውም ላልከው ምንም የሚገናኝ ነገር የለውም ::
እነዛ ዜናውን የሰጡህ ሰዎች እኮ ፐፕሊክ እንደምታወጣው ያውቁታል ::ብቻ ብዙ ነገር ማለት ይቻል ነበር ..በዚሁ እናብቃ ! ለማንኛውም ለመተዛዘብ ያብቃን ! እዛችው ድሮ
አብረን ጠጅ የምንጠጣባት ታዱ ! ቤት !

ቸር እንሰንብት !
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 8:30 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድምዬ እውነቱን ብንወያይ : የመለስ መሞት ምን የሚያመጣው ለውጥ ይኖራል ? የሚመጣው ለውጥ እንኳ ቢኖር ጥሩ ለውጥ ስለመሆኑ ምን የሚታወቅ ነገር አለ አንድ ደህና ተቃዋሚ በሌለበት አገር ? የስልጣን ውጊያ ቢጀመር እኛ ውጪ ነን : ምንም ስለማይደርስብን ሁካታ እና ግርግሩ ይናፍቀን ይሆናል :: እዚያ አገር ቤት ያለው ህዝብ ግን አንድ ተኩስ በተሰማ ቁጥር ስንቴ እንደሚጨነቁ ያሰበላቸው የለም ::

ሌላው ደግሞ አንዳንድ እንደ ኢምቴሪያልስት ያረጀ ያፈጀ ሁሉ የድሮውን ስራት መልሶ አምጥቶ በስንት ዘመን ያገኘናትን በቁቤ የመጠቀም እድላችንን እንኳ ከናዚነት እየቀጠረ : ጎጠኛ : ናዚ : ገንጣይ እያለን ምንም ላያመጣ አንድነትን እየሰበከ ጥላቻን ሲለቀልቅ ይውላል :: በዚህ ምኑም ባልተረጋጋ ሁኔታ : በተቃቃሚዎች ትክክለኛ ቅንጅት እና መተባበር : የአላማ አንድነት እና መግባባት በሌለበት ባሁኑ ወቅት ሌላ ሁካታ እንዲፈጠር አልጸልይም :: ሰሞኑን ፖለቲካ ሩም ገብቼ ያየሁትን የጥላቻ መንፈስ እኔ ነኝ የማውቀው ::
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 8:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላምምምምምምምምምምምምም
እንደምን አላቹ ያገረ ልጆች
በቅድሚያ እኔ ወለድ እና ኢንተረስት አልወስድም ... በእስልምና በጣም የተከለከለ ነገር ስለሆነ
ይልቅ ያጠራቀማቹት ነገር ካለ .. በቶሎ ላኩልኝ ... ነየግል በኩል .... የጎደለውን ሞላልቼ ላስደስታት
እሷ ያው ካሜራየን ስለምትችለኝ .... ተረጋግቼ ተቀምጫለሁ
.......................................//.......................
ሞፍቲና ጎሳ .. እንደት ነው ፖለቲካ ነገር የጀመራቹ ይመስላል \ዝም ብዬ ላልፋቹ ፈለኩና ... ነገር ግን ዛሬ አዲሳባ የገጠመኝን ነገር ሳልነግራቹ ብቀር
አላህም ይታዘበኛል ብዬ
ልነግራቹ መጣሁ
ለለላ ሰው እንዳትናገሩ ,,,, እዚሁ በኔና በናንተ ይቅር \አደራ
ለምን እንዲህ አልኩ መሰላቹ
ማውራት ስለማልፈልገው ነገር እንዳወራ ስላደረጋቹኝ
........................................................................../................................
አዲሳባ ከምሽቱ 3ሰአት ገደማ ነበር የገባሁት
ግዋደኛዬ ከእርፖርት ተቀበለኝና .... (በነገራችን ላይ እርፖርት እንደድሮው ውስጥ ድረስ ገብቶ መሸኘትም መቀበልም የለም .... ሰኩሪቲ ነው አሉ ... የፈረደበት ግንቦት 7 እና ኦነግ እንዲሁም ኦብነግ ህገመንግስቱን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እንዳይንዱት ተፈርቶ ነው አሉኝ
እና
እናማ
በርጫችንን ገዝተን እስከጠዋቱ 12ሰአት ድረስ ጨፈጨፍነው የናፈቀንን
ከዚያ በኃላ ግን ትንሽ ተኛሁኝና ... ከጠዋቱ 4ሰአት ገደማ ወጣሁ \ግዋደኛዬ ነግቶበት ወደስራ ገብቷል
እነ ዎክ እያደረኩ .. ለአንድ ሰአት ያህል ከተጓዝኩ በኃላ አንድ በተስኪያን ማስታወቂያ አጠገብ ደረስኩ
"ለቡ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን .... የጌታን ተአምር ለማየት !"... የሚል ማስታወቂያ የተፃፈበት ምልክት ጋር ደሰርኩና ... \
ወደ -ቀኝ ሳይ ... ዳገቱ ላይ በተስኪያን አየሁ \እላይ ድረስ ለመውጣት አቅሙ እንደለለኝ ባውቅም .... ዝም ብዬ ዋናውን መንገድ ተገንጥዬ ወደ -ቤተስኪያኑ አመራሁ
ዳገቱ መጀመሪያ ላይ ስደርስ አየሁዋት
የአበሻ ቀሚስ አድርጋለች
ለግራ በኩል ተቀዷል ቀሚሱ ... የተቀደደውን ክሮች ለማማያዝ እየሞከረች ነው
ቀይ ቢጫ አረንግዋዴ ጥለት ያለው ቀሙኢሷና ነጠላዋ ... መልኩን ቀይሯል
አጠገቧ የደረቀ ሙታንታ ተቀምጧል
ሳያት ለምን እንደሆነ አላውቅም ሳበኝ ሁኔታዋ
ላወራት ነው
ተከታተሉኝ
ፖለቲከኞች ሁላ
ሞፍቲና ጎሳ
እመለሳለሁ
አሁን መንገድ ላይ ነኝ
ቻዎ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Aug 02, 2012 10:16 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቃችን ቶሎ ቀጥላ ! እስካሁን እያናገርካት ነው እንዴ ? ቅቅቅቅ :: ቀድሞ ነገር አንተ እየፈረሽክ አድረህ ምን በጧት ወደ ቤተክርስቲያን ይወስድሀል ? መቼም "ረመዳን እየጾምኩ ለመሳለም ሄድኩ "አትለንም ቅቅቅቅ :: እንደ ሰውዬው ጤንነት ግራ አታጋባና ቅቅቅ :: እስቲ እዚያ ስለ ሞት እና ህይወት ምንድነው የሚወራው ? በዚያ በምናውቃት በኮዱ ነው ታዲያ የምትጽፍልን :: ደግሞ ከርቸሌ ወርደህ ለጉቦ ሌላ ፈንድሬይዝንግ አታስቸግረን :: የተሰበሰበው እራሱ የሚደርስህ አይመስለኝም : ልጁን ፈራሁት ቅቅቅ
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጉዱ ካሳ

ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2003
Posts: 431

PostPosted: Fri Aug 03, 2012 6:44 pm    Post subject: Reply with quote

ጎስሽ ...ቅቅቅቅ አይገርምም ! የዚህ ባለሱቅ ጉዳይ ?! ግን የሆነው ሆኖ ሳበኝ ያልከው አጠገቧ ያለው የደረቀው ሙታንቲዋ ነው ወይስ እሷ ! ቅቅቅቅቅቅ .....ግን ደህና ነህ ?
ይመችህ አቦ ! ይሄኔ አሳንቡሳ ከቁጢ ሻይ እያፈጠርክ ይሆናል ! ለማንኛውም ረመዳን ከሪም ብያለሁ ! Smile
_________________
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Gosa

ኮትኳች

Joined: 21 Nov 2011
Posts: 358
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Aug 03, 2012 9:04 pm    Post subject: Reply with quote

ጉዱ ካሳ እንደጻፈ(ች)ው:
ጎስሽ ...ቅቅቅቅ አይገርምም ! የዚህ ባለሱቅ ጉዳይ ?! ግን የሆነው ሆኖ ሳበኝ ያልከው አጠገቧ ያለው የደረቀው ሙታንቲዋ ነው ወይስ እሷ ! ቅቅቅቅቅቅ .....ግን ደህና ነህ ?
ይመችህ አቦ ! ይሄኔ አሳንቡሳ ከቁጢ ሻይ እያፈጠርክ ይሆናል ! ለማንኛውም ረመዳን ከሪም ብያለሁ ! Smile

ጉዳችን !! እንኳን እዚህም መጣህልን ::
Quote:
ሳበኝ ያልከው አጠገቧ ያለው የደረቀው ሙታንቲዋ ነው ወይስ እሷ !
Laughing Laughing Laughing ድሮም የባለሱቃችን የማሽተት ችሎታው A+ መሆኑንና በትርፍ ጊዜው ከነ ቦቢ ጋር ቦርደር ሴኪዩሪቲ (ካስተምስ ) ፓርታይም ስራ እንደሚሰራ አንድ ወዳጄ ሹክ ብሎኝ ነበር አላምን ብዬ እንጂ :: ዛሬ ነው ልክ መሆኑን ያረጋገጥኩኝ Laughing Laughing
_________________
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Sat Aug 04, 2012 3:03 pm    Post subject: Reply with quote

ጉዱ ካሳ እንደጻፈ(ች)ው:
ጎስሽ ...ቅቅቅቅ አይገርምም ! የዚህ ባለሱቅ ጉዳይ ?! ግን የሆነው ሆኖ ሳበኝ ያልከው አጠገቧ ያለው የደረቀው ሙታንቲዋ ነው ወይስ እሷ ! ቅቅቅቅቅቅ .....ግን ደህና ነህ ?
ይመችህ አቦ ! ይሄኔ አሳንቡሳ ከቁጢ ሻይ እያፈጠርክ ይሆናል ! ለማንኛውም ረመዳን ከሪም ብያለሁ ! Smile

############################################

ጉድሽካ ...............እንኳዎን ደህና መጣህ ቤታቸንንን ስላም ነው ብሮ ሁሉም አማንንን ከምር የባለሱቅና የጎሳቸን ጫወታ የማይስበው የለምም እዚህ ቤትትት ከምርርር ስምህን ሳይ ደስስስ ብሎኝ ነው የገባሁትትትት ...........ይልመድብህ ብያለው .......እስቲ ያን ጌታንም በለመደ እጅህ ጎትተህ አምጣልኝኝኝኝኝ ............መልካም ስንበትትት

አደቆርሳሳሳ ...........ያየ ..................................አደቆርሲትትት እባክሽንን አደቆርሳንን አውጪው ከደበቅሽበትትትትት ፕሊስስስስስስ

ሞፈቲኮ ስላም ብያለው ............ራስብሩም እንደዛው

በሉ ስላም ዋሉ
የግልልልልል
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Aug 14, 2012 6:38 am    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ እንደፃፈው
Quote:
ወደ -ቀኝ ሳይ ... ዳገቱ ላይ በተስኪያን አየሁ \እላይ ድረስ ለመውጣት አቅሙ እንደለለኝ ባውቅም .... ዝም ብዬ ዋናውን መንገድ ተገንጥዬ ወደ -ቤተስኪያኑ አመራሁ
ዳገቱ መጀመሪያ ላይ ስደርስ አየሁዋት
የአበሻ ቀሚስ አድርጋለች
ለግራ በኩል ተቀዷል ቀሚሱ ... የተቀደደውን ክሮች ለማማያዝ እየሞከረች ነው
ቀይ ቢጫ አረንግዋዴ ጥለት ያለው ቀሙኢሷና ነጠላዋ ... መልኩን ቀይሯል
አጠገቧ የደረቀ ሙታንታ ተቀምጧል
ሳያት ለምን እንደሆነ አላውቅም ሳበኝ ሁኔታዋ
ላወራት ነው

ጉዱ ካሳ እንደጻፈ(ች)ው:
ጎስሽ ...ቅቅቅቅ አይገርምም ! የዚህ ባለሱቅ ጉዳይ ?! ግን የሆነው ሆኖ ሳበኝ ያልከው አጠገቧ ያለው የደረቀው ሙታንቲዋ ነው ወይስ እሷ ! ቅቅቅቅቅቅ .....ግን ደህና ነህ ?
ይመችህ አቦ ! ይሄኔ አሳንቡሳ ከቁጢ ሻይ እያፈጠርክ ይሆናል ! ለማንኛውም ረመዳን ከሪም ብያለሁ ! Smile

እንደው ምናባቴ ላድርግህ አንተ ጉዱ ካሳ
አሳፍረኸኝ እኮ ከቤቱ አስጠፋኸኝ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እውነቱን ልንገርህ ግን ... የሳበኝ የተቀደደው ቀሚሷ ... የደረቀው ሙታንታዋ .... የቆመችበት ቦታ
የለበሰችው የቆሸሸ የሀገር ልብስ (ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ጥለት ያለበት )
እና ቁመቷ ... እናም የፊቷ ላይ ቁጣ
በጠዋቱ ምን ገጥሟት ይሆን
በሽተኛ ትሆን ....
ላናግራት አላናግራት
ብትፈነክተኝስ .... በሽተኛ ከሆነች
ስፈራ ስቸር አወቀችብኝ መሰለኝ ... በጎረነነ ድምፅ
> ደሞ አንተ ማነህ ?
+ እኔን ነው
> አዎን አንተ ራስህ .... ምን አፍጠህ ታየኛለህ እንደማታቀኝ ሰው
ግራ ስለገባኝ ዝም ብዬ አየኃት
> እኮ ምን ታየኛለህ ....
ናማ ... ናማ .. እዚህ ተቀመጥ .... ጠላቴም ሁን ወዳጄ ....
አንተም አንዱ ልጄ ነህ ....
እስኪ .... ንገረኝ .. ተረኛው አንተ ነህ እንዴ
+ የምኑ
> የምትተኛኝ
+ በስማም .... ምን ማለትሽ ነው
> ያው ናቹ ... ሁላቹም እየመጣቹ ተኝታቹኝ ጥላቹኝ ስትሄዱ ነው እማውቀው .... 3 ዘመን ሁሉ
ደነገጥኩኝ ... ካማን ጋር ነው ማወራው ይሆን
> አይዞህ አይዞህ አይግረምህ ... እኔ ነኝ .. እናትህ ... አገርህ .... እወዳታለሁ እያልክ .... ቦጭቀኸኝ ... ዘልዝለኸኝ ...
> የመጣው ሁሉ በጉልበት ተኝቶኝ ጥሎኝ ሲጠፋ .... ከንፈርህን እየመጠጥክ .... ብቻ ... የምታየኝ ... እኔው እናትህ ነኝ ...
+ አልገባኝም አልገባኝም ... እኔ ደሞ ምን አደረኩ
> መቸም አይገባህም ... እያየኸኝ እንዳላየህ እያለፍከኝ ... እንዴት ሊገባህ ይችላል
> ትላንት ነው አይደል ከውጭ የመጣኸው
> ጥላቹኝ ከሄዳቹ በኃላ ለምን ከትከሻዬ አትወርዱም .... ለምን ... እኮ ለምን
> ሀገሬን እወዳለሁ ... እናቴን እወዳለሁ .... ... ወሬ ብቻ ናቹ ... ወሬኞች .... ምን ፈዘህ ታየኛለህ ....
> አዲስ ሆንኩብህ ?... አይተኸኝ አታቅም አይደል .... እርምህን አውጣ ... እኔው ነኝ ... በውሸት የምትኮራብኝ እናትህ ... ሀገርህ ....
አሁን ተረጋጋሁና ላወራት ወሰንኩ
+ ኢትዮጵያ ነሽ ?
> አዎን ምነው ጠየከኝ
+ ፓንቱ ምንድነው ?
> ጥሩ ጥያቄ .... 3 አመት የመጣው እየደፈረኝ .. እየተኛኝ ... ሲሄድ .. አይዞሽ የሚለኝ ... የሚረዳኝ ልጅ በማጣቴ .... ምን አታገለኝ ብዬ .... አወለቅኩላቸው .... አደብ እስክታገኙ .... በክብር እስክታኖሩን .... ድፈሩኝ ... ያውላቹ
> አሁን ደሞ ተረኛው ማን ይሆን .... ይሄኛው ... ከጠፋ ወራት አስቆጥረውታል .... ተረኛውን እየጠበኩ ነው
+ እስከዛሬ የሚያከብርሽ እና ያንቺን ፍላጎት ያሟላ .. ምንም አልነበረሽም ማለት ነው
> 3 ዘመን ... አንድም
+ እንዴ ያለፉትስ ... የጥንቶቹ
> እኔ ለኔ አሳቢ እና የኔን ክብር የሚጠብቅ ... ሁሉንም ልጆቼን በአንድ አይን የሚያይ አንድም እስከዛሬ አልገጠመኝም
> የራሱን እንድሜ ለማራዘም ... አንዱን ካንዱ ሲያጋጭ ... ሸርና ተንኮል ሲጠነስስ .... አንዱ የበላይ ሌላው ከነመፈጠሩም የማይታወቅበት .... ምን ልበልህ ... እኔ የንጀራ ልጅ የለኝም
> ሁላቹም ልጆቼ ናቹ ... ሁላቹንም በአንድ አይን የሚያይ .... ሰው አልሰጠኝም ... ጌታ
ግራ ገባኝ ... ምን እንዲህ እንዳማረራት ማወቅ አቃተኝ ... ስለዚህ ዝም ብዬ አየኃትና ,.... የመጣልኝን ጥያቄ ጠየኳት
+ ቀሚስሽን ምን ቀደደው
> ተባረክ ተባረክ ... ጥሩ ጥያቄ ጠየከኝ .....
> ለመሆኑ መፃፍ ታነባለህ ?.... የምታነብ ከሆነ ምን ተብሎ ተፅፏል መሰለህ
> ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ -ሰማይ ትዘረጋለች :: ተብሏል .... እና ... ብዙ አመት ዘረጋሁ .... አንድም ጥሩ ልጅ ሲከለክለኝ ... እራሴው እራሴን ለመከላከል .... እጄን ከዘረጋሁበት አውርጄ ... በጉልበት የሚደፍሩኝን ለመከላከል ሞክሬ ነበር የዛሬ 40 አመት ገደማ
> ግን እንደምታየው ... ትርፉ ቀሚሴን ቀድጄዋ አረፍኩት ...... አንድ ቀን ልጆቼ በህብረት ተነስተው ከዚህ ስቃይ ያድኑኛል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር
> ይለይለት ብሎ የዛሬ 20 አመት ገደማ .... ተስፋዬን አስቆርጠው .... ፓንቴንም አስጣሉኝ .... አወለኩላቸው ...
> ያው እንዳሻህ አድርገኝ አንተም ተረኛ ከሆንክ
+ እንደሱማ ተስፋ መቁረጥ የለብሽም .... ቆይ ግን አሁን እዚህ ቦታ ላይ ምን እየሰራሽ ነው
> ምን እየሰራሽ ነው ?.... ምን አገባህ ... ለማወቅ ከፈለክ ደሞ .... እዚህ ቁጭ ብዬ በተስኪያን የሚወራውን እየሰማሁ ነው ....
> ከሰአት በኃላ ደሞ ሌሎች ልጆቼ እዚያ አንዋር መስጊድ የሚሰሩትን ለማየት ሄዳለሁ
> ምን እንደሚያሳዝነኝ ታውቃለህ .... በልጆቼ ውስጥ መተማመን ጠፍቷል
> በብሄር
> በሀይማኖት
> በዘር በሰፈር በጎጥ .. የተከፋፈለ
> በጥርጣሬ የተሞላ ትውልድ ....
> አርቆ ማሰብ ያቆመ አጋሰስ ልጆች ነው የቀሩኝ
> እናንተም ጥላቹኝ ወጥታቹ ... ከላዬ ላይ ወርዳቹ ያላለቃቹ ....
> የምታስቡልኝ እየመሰላቹ የበለጠ የምትጎዱኝ
> መቼ ነው ባለፈው ጥፋት ተማምናቹ .... ይቅር ለግዜር ተባብላቹ ... እኔን እናታቹን የሁሉም ህብረተሰብ እኩል እናት ... የሁሉም ሀይማኖት እኩል መሬት አድርጋቹኝ ...
እናንተው በመረጣቹት ባል የምታስተዳድሩኝ
+ ምንድነው ግን እንዲህ አስመርሮ በልጆችሽ ተስፋ ያስቆረጠሽ
> ምን የሚታይ ተስፋ የሚሰጥ ነገር አለ .... ሁሉም በሆዱ እየተብሰለሰለ .... እየተቆጨ .... እየተናደደ .... ከንፈሩን እየመጠጠ ዛሬ ስለሚበላውና ስለሚተኛበት ነገር ብቻ የሚያስብ ትውልድ እኮ ነው አሁን እኔ የማየው
> ባለፈው ጊዜ ምን ሆነ መሰለህ .... ጦላይ ሄጄ ነበር .... እዚያ የተሰበሰቡት ልጆቼ የሚያወሩትን ለመስማት
> ግምገማ ታውቃለህ .... ካድሬ ልጆቼ ግምገማ ላይ ነበር
እያወራች ቀሚሷን ሰብሰብ ... ፓንቷን ጠቅለል ጠቅለል ... በትሯን ያዝ አደረገችና
> ቆይ ሰአት ደረሰብኝ ... መስጊድ ደርሼ እመጣለሁ ..... ከሰታ እንቀጥላለን
ብላኝ ሄደች .... እንደጉም ብንንን ትንንንን እያለች
እኔም አንጋጥጬ ቀረሁ

ሰላም ዋሉ ሁኑ ክረሙ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Aug 15, 2012 9:39 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ውድ ባለሱቅ ይሄን ትልቅ መልክትህን አንብቤ ብቀር የኢትዮጵያ አምላክ ምን ይለኛል ብዬ FB ጓደኞቼ
አካፍያቸዋለሁ ::
ድንቅ ሰው ነህ !
አምላክ ይባርከህ
እጅህ ይለምልም !

ቸር እንሰንብት !!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sun Aug 19, 2012 8:41 pm    Post subject: Reply with quote

ኢድ ሙባረክ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 371, 372, 373 ... 381, 382, 383  Next
Page 372 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia