WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለክብረመንግስትና አካባቢው ልጆች !!!
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 313, 314, 315 ... 381, 382, 383  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Sat Oct 09, 2010 2:17 pm    Post subject: Reply with quote

በቅድሚያ አንፈራራ ሁለተኛውን ክፍል ልታሳየን እንደሆነ ነው የምገምተው ወደ ኢትዮጵያ ምትሄደው መልካም ዚና ነው : በተስፋ እንጠብቃለን :
ወንድማችን አዴቆርሳ እንኩዋን በደህና መጣህ ወዳጄ
መቸም ደግ ነገር ባለበት ክፉ ነገር አይጠፋም የዚችም ዓለም ምሳሌ ይህው ነው ::
ስለዚ ወንድሞቼ ሁላቹህም የምትናገሩት አስደሳች ነው ሳታስቡት መቶ በልዩ ስሜቱ ስለቤቱ የተናገረው አዴቆርሳ አስደስተህኛል ደስታየንም እንኩአን መጣህም ብየ ለመግለጽ ነው :
ውነት ነው የብርቱካን ሚደቅሳ መፈታት ጋር ያዴቆርሳም ዝምታ አብሮ ተፈታ
አክባሪያችሁ ኮሎኔል ነኝ
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 787
Location: united states

PostPosted: Sat Oct 09, 2010 3:55 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ለቤታቸን ይሁን .......................
እልልልልልልልልልልልልልል አደቆርሳ ተመለስ እንዴት ደስስስ ይላልል ባካቸውውው በል የቆየህበትን በሙሉ አንድ በአንድ አውጣቸው እሺ አገር ምድሩ ነው የናፈቀህ ደሞ ቅቅቅቅቅቅ እሺ ............................

እኔ ምለው የዚህን ቤት ሴቶቸ ምን በላቸው የሚያውቅ ካለ ይንገረኝ እስቲ ጉድ እኮ ነው ከምር ስንተ ነገር አብረን ጀምረን ጥሎ መጥፋት አለ ከምር በጣም ደስ አይልምና እስቲ ተመለሱ በገብሪል ይዢቸዋለው .........

መልካም ስንበት
የግል
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የቦሬ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Jan 2006
Posts: 85
Location: USA

PostPosted: Sat Oct 09, 2010 6:16 pm    Post subject: Reply with quote

ባለሱቅ ብራቮ !! ከአሁን በዋላ አዶቆርሳ ሲጠፋ ይቺን ቤት ሙቭ ማደረግ ነው :: የግልዬ በገብሬል ስትለምኝ አሳዘንሽኝ ከምር ግን ምን እየሆኑ ነው የሚጠፉት :: በተረፈ ለሁላችውም ሰላምታዬ ይደረሳችው ::

ቦሪቲ ነኝ ::
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=19378&start=960
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንሰት

ውሃ አጠጪ

Joined: 30 Jan 2005
Posts: 1210
Location: united states

PostPosted: Sun Oct 10, 2010 2:22 am    Post subject: Reply with quote

ሰላማት
ባለሱቅ ህመምህ አሞኝ ግን ምናልባት እነዚህ ዋርካን የሚያቆሽሹ ግለሰቦች አላማቸው ሰውን ተስፋ ማስቆረጥ ይሆናል ብዬ አልጠፋሁም :: ተስፋ ቆርጦ አለመጥፋት ነው :: ደግሞ እኮ ማስተዛዘኛ አደቆርሳን አግኝተህ የለ ::
አክባሪህ

ባለሱቅ እንደጻፈ(ች)ው:
ዋውውውውውውውውውውው
ብራቮ ባለሱቅ
ለአመት የተዘጋ አንደበት በአንዲት ቀን ቦምብ ፍንዳታ ጎትተን አመጣነው
ብራቮ ባለሱቅ
ወዳታ ብለንሀል ... አንተ ቀዥቃዣ
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
///////////////////////////////
አደቆርሳዬ .. ወንድሜ ወዳጄ ያገሬ ልጅ
እውነቱ ንገረኝ ካልከኝ ያንን ደባልነት ስጠይቅ እንዴት እንደከበደኝ እና እንደቀፈፈኝ ለመናገር ቃላቶች ያጥሩኛል

ሀሳቤም ደሞ ይህንን ገፅ በሌላ ገፅ በኩል ለማየት እንጂ ... ጨርሶ 5 አመት ፅሁፉን ዘግቶ አዲስ መክፈት አለነረም ... በፍፁም

ይህንን ቤት ከሌላ አምድ ለመገናኘት ከማሰብ የመጣ ትንሽዬ ጥፋት .... ግን ቦንብ አፈንድታ አንተን ይዛ የመጣች ጥፋት

ከልቤ ይቅርታ እንድታረጉልኝ እጠይቃለሁ .... ሀሳቤን በመጥፎ ወስዳቹት ለታዘባቹኝ ያገሬ ልጆች

እንዳልኩህ ይህንን ቤት ከሌላ አምድ ለመገናኜት ከነበረኝ ሀሳብ የተነሳ ነው .... ፊርማዬ ላይ ሊንኩን ያበጀሁት

እንዳላማረብኝ ግን ከአንድ ከማከብረው ሰው ስለተነገረኝ .... እግራቹ ላይ ወድቄ ይቅርታ በመጠየቅ ያንን የተውሶ የዳባል ቤት ትቼዋለሁ

ከሁ ;ሉም ያስደነገጠኝ እና የገረመኝ ግን 5 አመት ልፋት በከንቱ ለማስቀረት እንደተደረገ አድርጋቹ ስትቆጥሩ .ብኝ ..... እፍረቴ ቀይ ፊቴን አመድ አለበሰው

ለማንኛውም ....
ለሶስት ቀን ሽፍትነቴ እና ቀዥቅዝዣነቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ
ሀሳብም አላማዬም ግን አልነበረም ሌላ ሩም መክፈት
በቀላሉ አክሰስ ለማድረግ መስኮት ብትሆን ነበር አላማዬ
አልሆነም
ትቼዋለሁ
ከይቅርታ ጋር

አደቆርሳዬ ግን ስላየሁህ በጣም በጣም እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል
ያጠፋሁት ጥፋት ሁሉ ለራሴ ባንተ መምጣት እንደተካካሰ ነው የተሰማኝ
ለዚህ ነው በመግቢያዬ እንደገለፅኩት
እንኳን ቦንቡን አፈነዳሁት ያልኩት
አንተን ጠራልኛ !

በል እንግዲህ አትጥፋ ያገር ልጅ
የአንድ አመት ከረጢትህን ፍታና ... ጀባ በለን

በቀዳጅነታችን እንሰንብት
አሚን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Oct 10, 2010 11:58 am    Post subject: Reply with quote

ያደኩበት ሁኔታየ አይለቀኝም አይደል ? እንደው እምም አርጎኝ ቆይቼ ሳለሁ ወንድሜና ከልቡ የተረዳኝ አንፈራራችን መጥቶ
Quote:
አደቆርሳ ! እንኳን ደህና መጣህ ! የዚህ ቤት ነገር ስለማይሆንልህ ነው :: አይደል ?
በማለት ከህመሜ ፈወሰኝ ::

አንፈራራችን አዎን የዚህ ቤት እና የእናቴ ነገር አይሆንልኝም ግን ይገርምሀል ያው አደቆርሳ እንዲህ ነው እንዲያ ነው እንደሚባለው ሆኖ ነው እንጂ
ቆይ አንተ ባለሱቅ
Quote:
የምወዳችሁ ወራ አዶላ አነጋገሬና አባባሌ በትልቅ አክብሮትና ትህትና መሆኑን ተረዱልኝ :
ከማለት በላይ ምናባህ ብየ ልነግርህ ነው የፈለከውና ነው ?
Quote:
ከሁ ;ሉም ያስደነገጠኝ እና የገረመኝ ግን 5 አመት ልፋት በከንቱ ለማስቀረት እንደተደረገ አድርጋቹ ስትቆጥሩ .ብኝ ..... እፍረቴ ቀይ ፊቴን አመድ አለበሰው
የምትለው ?

እስከዛሬ እንደምወድህ አታውቅም ማለት ነው ? በእውነት እወድሀለሁ አንተን ምናልባት የሚቆጣ እንጂ የሚሰድብ አንጀት የለኝም ?
ዳሩ ምን አይነት ተፈጥሮ የታደለኝ መራራ ሰው እንደሆንኩ ..... በውነት እማማም ገብቷት ነው መሰል አልፎ አልፎ እንደው አንድ ልጅ ብትወልድ ምናለ ልጄ ? የምትለው ትክክል ሳይሆን አይቀርም : ያኔ ይተወኝ ይሆናል ግን ካሁን በኍላ ይወለዳል ብላችሁ ነው ቢወለድስ የጃርሳ ልጅ አዪይይይይ ከኍላ ያለ ወደፊት አያይም ይባል የለ !
ሞፊቲኮ ራስብሩ ከነወቀሳህ አንፈራራችን የግል የቦሪቲ አይፋችን አንቺ ጉደኛ ባለሱቅን የተረብሺው በሳቅ አፈንድቶኛል የጠፉትም ሁሉ የፍቅር ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ::
ግን ምነው ሶስትና አራት ብቻ ቀራችሁ ? ከተለያየን ጀምሮ እስካሁን ያለውን ደግሜ በደንብ ለማንበብ 50 ብር ፈጅቶብኛል ቅቅቅቅቅ አለች የግል : የግል እንደምነሽ ?
ደግ ሰው አለ ? ሁሌ አስታውሰዋለሁ ልረሳውም አልችልም ::
ኸረ ሁላችሁም እንደምን ከረማችሁ ? ከተለያየን መንፈቅ አመት አይሞላም ? ወርቅ መስሎ እንጂ ? የኢንተርኔት አገልግሎት በሀገራችን ኬብል ያለበት መሆኑ ቀርቶ ኤሌክትሪክ ያለበት ብቻ በቂ መሆን ተችሏል ካርዷን በሀያ ምናምን ብር ሸምቶ ሲያበቁ ቁጥሯን ወጋ ወጋ ነካ ነካ በማድረግ ሶስትና አራት ሰአታትን በጥሩ ፍጥነት ከአለም ሜዲያዎች ጋር አብሮ መቆየት ተችሏል ::
ያኔ እንደተለያየን ከአዲስ አበባ ወደ አዶላ የመጀመሪያው ጉዞዬ ልነሳ ......... መቸም ከናንተ ስገናኝ የሆንኩትን እና ያየሁትን ማካፈል እወዳለሁ እንደ አንድ የልብ ጓደኛም አይደል የማያችሁ ? ከምር ያለኝ ፍቅርና ፍቅር በቃ ፍቅር ምን ብዬ ልናገረው ሊተወኝ አይችልም
በጨዋታችን መሀል ስንት የሚዳሰሱ ነገሮችን በመቀሳሰም ልምድ እንዳካበትን በሚገባ እረዳለሁ
ባለሱቅ አራዳ ብሎ እገሌ እገሊት ሲል አብሮ ብዙ ነገሮችን እናስታውሳለን :

በነገራችን ላይ በክብረመንግሥት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ባላቸው እና በምንወዳቸው አባታችን በጋሽ በርሄ ዜና እረፍት የተሰማኝን ሀዘን ቢዘገይም ለመግለጽ እወዳለሁ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን ::
በክብረመንግሥት የድሮ ሰዎችና አባቶቻችን የመጨረሻ ዘመን ይመስለኛል በጣት ከሚቆጠሩ በቀር ብዙዎቹ ይህቺን ዓለም ተሰናብተዋል :: ቀሪዎቹን በእርጅና ዘመናቸው እድሜ ያጥግብልን እላለሁ ::

ከምን እንደምጀምር ግራ ገባኝ ከእናንተ ጽሁፎች ወይንስ ከራሴ ? ቆይ ክብረመንግሥት ደርሰን እንመለስማ
ወደክብረመንግሥት ለመሄድ ስነሳ ወደዋርካ ለመምጣት የነበረውን የግዜ ርቀት አብሬ እያሰብኩ ነበር ይገርማችኍል ከመገናነታችን በፊት የሆነ ጉዞ ሳደርግ እንዳሁኑ አብሮኝ እንዳለው ባህሪዬ ነው አሁን ግን የዚህ ቤት የራሱ የሆነ ባህሪይ እያሸነፈኝ በቃ ሌላ ሰው እየሆንኩ ነው የምሄደው :
ብዙ ጉዞ ላይ አነባለሁ ከጓደኛ ጋር ለመጓዝ እመርጣለሁ ወዘተ አሁን ግን እንደዛ አይደለሁም አካሄዴም ከወትሮው በጥቂቱ ለየት ካለ ሁኔታዎች ጋር ስለሆነ ላጫውታችሁ ወደድኩ

አቋቋምሽማ ልብ ያስደነግጣል
ተፈጥሮሽ ግሩም ነው ጭራሽ ነፍስ ያሳጣል
ጭራሽ ነፍስ ያሳጣል
ነፍስ የሚያሳጣ ውበት ግን አሁንም ክብረመንግሥት አለና እነሆ ላሳያችሁ ............................
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Oct 10, 2010 12:08 pm    Post subject: Reply with quote

አውቶቡሱ ወደከተማው ሲዘልቅ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ለወትሮው ቢሆን ኬላው ሲቆም ቀደም ብዬ ለመውረድ በሩጋ ጠጋ ብዬ ነበር የምጠብቀው ለምን እንደሆነ አላውቅም አሁንም ቢሆን ከመኪና ስወርድ መታየት ደስ አይለኝም ::ታዲያ ይህ ክብረመንግሥት ውስጥ ብቻ ነው ምናልባት በወጣትነት ዘበናችን የነበረ ስሜት አብሮኝ አድጎ እንደሁ እንጂ አሁን ትርጉም አልባ ነው ::
ፊትለፊት ከነጂው ጎን ስለተቀመጥኩኝ ነው መሰለኝ ተመችቶኝ ወጪወራጁን እያማተርኩ የናፈቀቺኝን ከተማ በጠራራ ጸሀይ ግራና ቀኝ እየቃኘሁ የሲኞር ጂዮቫኒን መኖሪያ በቀኝ ፋብሪካውን በግራ በነገራችን ላይ ይቺ ሰፈር ለኔ ልዩ ትዝታ ያላትና የማትረሳ ናት : ከፋብሪካው ፊት ለፊት ያለችው መንደር ወደውስጥ ገባ ያለች ስለሆነች ለጨዋታ ታመቸን ነበር በሲኞሩ መኖሪያና በነ አብዱቄ ጀርናሳ ቤት መሀል ወደ ኳስ ሜዳ ከምታወጣው መንገድ ጀምሮ ብዙ ታሪክ ሰርተን ያደግንባት መንደር ነች ምናልባት ጥልና ፍቅር የጀመርኩት እዛች መንደር ነው ብል አልተሳሳትኩም ::
የአካባቢው ማርጀት በቃል የሚነገር አይደለም የሀጂ ከድር ሰፈር ያደግንበት እስከማይመስል ድረስ አርጅቷል የሼህ እንድሪስ ጋሪ ጣቢያ ስደርስ በቅጽበት አንድ ነገር ታወሰኝና ሳላስበው ፈገግ አልኩ : ድኩላ ሥዩም ሳኒ ጀማል መሀመድ እንድሪስ ጋር ሆነን ያደረግነው የልጅነት ነገር አሳቀኝ :: የነሰበታን ወንድም ሎሎን ታስታውሱት ይሆን ? ብቻ ያሳለፍኩትን የልጅነት ትዝታ በአግራሞት እያጣጣምኩ አንዴ ፈገግ አንዴ ደሞ ቅዝዝ እያልኩ ዘለቅኩ የወይዘሮ ጦቢያው በያንን ቤት በግራ የጋሽ አህመድ መሀመድ ሰዒድን ቤት በቀኝ አልፎ ቁልቁል የቆጪም ቁልቁለት /አውቶቡሶች ድሮ ድሮ ገበያ ክፍልና ቆጪ ሲደርሱ ጋዲ ጋዲ ጋዲ ጋዲ እያሉ ሲገቡ ለነዋሪው ብዙ መልክቶችን ማስተላለፋቸውም እንደነበር ትዝ አለኝና የዛሬው አውቶቡስ መልክት አይናገርም ብዬ ታዘብኩት ::
ድሮ አውቶቡሶች ከተማ ሲገቡ ጋዲ ጋዲ እያሉ ክላስክ ማድረጋቸው የተለመደ ነበር እንግዳ ተቀባይም እቃ ተሸካሚውም አልቤርጎ አከራዩም ምግብ ሻጩም ይቺን ድምጽ ሲሰማ ነበር በፍጥነት የሚንቀሳቀሰው :: አውቶቡስ ድሮ ልክ ከቀኑ 8 ሠዓት ላይ (ገደማ ) ነበር የሚገባው እና ሰዓቱንም በማስታወስ ልክ አቶቢስ ሲጮህ እያልንም ሰአትን በማመላከት እናወራ ነበር ::
የዛሬው አውቶቡስ ጸጥ ብሎ እያንዛረጠ ሲገባ አይ አቶቢስ አልኩ በሆዴ አቶቢስ ድሮ ቀረ ::
ማሞ ካቻ :-መኮንን ነጋሽ :-ንሥረ ተፈሪ :- ወሎ ፈረስ :-
ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት :- ኸረ ስንቱ ቤታችን ቁጭ ብለን በጥሩንባቸው ለይተን እናውቃቸው ነበር ዛሬ እንደህዝብ ትራንስፖርት ሳይሆን እንደጦር ታንክ ካቅሙ በላይ መንገደኛ አጭቆ ሜዳውንም ዳገቱንም እያንዛረጠ እየተንከባለለ እንጂ እየተሽከረከረ የሚሄድ አይመስልም ::
የቆጪን ዳገት ሽቅብ ስንወጣ በስተግራ የአባባ አመንቴ መርጊያን ቤትና መስጊዱን በቀኝ የአባ ዝናብን የቀድሞውን ጅማ አባጅፋር ሻይቤት ከፍ ብሎ ደሞ የተስፋዬ ብራቱን ሱቅ እያየሁ አራዳ ደረስኩ ድሮ ድሮ አውቶቡስ ተራው ባለምባራስ ዓለማየሁ በንቲ ሆቴል በራፍ ላይ ነበር አሁን አውቶቡሱም ረስቶታል ዳሩ የዛሬ አውቶቡስ መቆሚያውን ቀርቶ ማደሪያውንስ መች ያውቃል ?
በጣም የሚገርመው ግን አንድም የማውቀው ሰው በመንገድ ላይ ማየት አለመቻሌ ነው ድሮ መንገድ የሚያቋርጡትን ፍየሎች እንኳን የማውቃቸው zare አንድም ሰው ማወቅ ሲያቅተኝ በጣም በጣም ነው የገረመኝ ::
መኪና ተራ ከሚባለው ፈጠን ብዬ ወጣ አልኩና ትራቭሊንግ ባጌን ትከሻዬ ላይ አድርጌ ትግስት ፍሬ ይሁን ቤተልሄም አዶላ ለምለም ልሂድ ሾፌሮች እያልኩ ሳመነታ እግሬ መራኝና ዝም ብዬ ወደትግሥት ፍሬ በረንዳው ላይ ቁጭ አልኩና ቡና አዘዝኩ እድሜዬ እዚህ እስከደረሰ ድረስ ለመጀመሪያ ግዜ ክብረመንግሥት ቡናቤት ላድር ነው ሁሉ ነገር አልዋጥልህ አለኝ አልመችህ አለኝ ግን ደሞ የት ልሂድ ?
ከፊት ለፊቴ የተቀመጠ ክርክስ ያለ ኑሮ ያልተመቸው ሰው ዝም ብሎ ያየኛል የሆነች ነገር ፈልጎ ይሆን ? አንዴ ደሞ የረሳሁት እንዳይሆን እያልኩ እኔም ሳየው ብድግ አለና ወደኔ መጣ ሳቅ እያለ ባልሳሳት አደቆርሳ ነህ አይደል ? አንድ የፊት ጥርሱ ወልቋል
አዎን ማነህ ?
በስመአብ ወልድ
ከሩቅ ስላየሁህ በአካሄድህ ለየሁህ በደንብ ሳይህ ደሞ አወኩህ
እኔ አላወኩህም ያው የርጅና ነገር ይሆናል ቅር እንዳይልህ አላወኩህም ::
አንተነህ ነኝ ?
አንተነህ ?
የሳሊማን ታሪክ ብሎ ሳይጨርስ ብድግ ብዬ ቆምኩና አቅፌ ሰላም አልኩት
ማሰልጠኛ ውስጥ በነበርኩበት በጣም አጭር ግዜ አብሮኝ የነበረ የክፉ ቀን ወዳጄ ነበር ::
ቆይ እዚህ ምን ልታረግ መጣህ ?
ወርቅ ይቆፈራል ብለውኝ ልቆፍር መጣሁ አንተስ ምን ታረጋለህ ?
እኔማ የክብረመንግሥት ልጅ ነኝ ሀገሬ ነው ?
የሲዳሞ ልጅ ..........
አዎ እሱን ተወውና ወደትዝታችን .........
ማደሪያዬን ሴትል አደረኩና በጋሪ ተሳፍረን ወደገበያ ክፍል ተመለስኩ የእማማን መልክት ፈጻጽሜ ለነገሩ በአንድ ቀን የሚፈጸም ነገር የለም ጀማምሬ መጠጥ ያለ የዶሌ ቁዳ ይዘን አራዳን እስከ ግማሽ ሌሊት ደስ የሚለውን ነፋሻማ አየር እየተቀበልን በምርቃና ዘለቅን የሰው ልጅ ያለበትን ውጣ ውረድ ስመለከት ይህንን ሰው እግዚአብሄር እኔን ለማስተማር የላከልኝ አድርጌ ተቀበልኩት ::
ጦር ሜዳ - ወህኒ ቤት - ሆስፒታል -
ነጋዴ - ተማሪ - ነጋዴ አሁንም እስር ቤት እንዴ .......ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ለመውለድ ጊዜ አጣሁ ሲል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ::
ይገርማል ብቻ የሱ ታሪክ ህይወትን አስተማረኝ በጣም መከረኝ ጉልበት ሆነኝና ወዳሰበበት አመቻችቼ በማግሥቱ ሸኘሁት :: እኔም መልክቴን ለማድረስ ጋሪ ተሳፍሬ ወደ ገበያ ክፍል ዘለቅኩ ::

ገበያ ክፍል ድሮ ከሸንኮራና ከጥንቅሽ ልጣጭ በስተቀር የሚያቆሽሻት አልነበረም አሁን የማያቆሽሻት ነገር የለም በጎቹም ፍየሎቹም ይቅማሉ መሰለኝ ክርክስ ብለዋል ናስሮን የምታውቁት ካላችሁ ነፍሱን ይማረውና አንድ የሚወደው ፍየል ነበረው ፍየሉ ይቅማል ይጨብሳል
የበቀለችን ጠጅ አንድ ብርሌ በአንድ ትንፋሽ ነበር ጭጭ የሚያደርገው ፍየሉ የጋሽ መገርሳ ነው ለነገሩ እኔ ሲቅም እንጂ ሲጠጣ አይቼው አላውቅም ግን የተነገረለት ቀምቃሚ ነበር :: በዚያን ዘመን አዲስ አበባ ቢራ የሚወድ በየባሩ እየገባ የሚያመሽ ፍየል ነፋስ ስልክ አካባቢ እንደነበረ በዕሁድ ራዲዮ ሰምቻለሁ ::
የድሮው አየር ማረፊያ አሁን አሞራ ማሳረፍ አይችልም
በስተግራ የነበረው ሰጋቱራ ማቃጠያ በአየር ጸባይ ለውጥ ምክንያት እርምጃ የተወሰደበት ነው የሚመስለው :: bebEtoch temoltual
ክብረመንግሥት አሁንም የቤቶች ሥራ ፍላጎትን የምታስተናግደው መንገድ ዳር እንጂ ገባ ብሎ የሚሰራ አልተገኘም ::
በውነት በጣም የሚገርም ነው አንድ ከተማ ሲቆረቆር ወደፊት ብዙ ነገር ታስቦ ይመስለኛል እስቲ አስቧት ክብረመንግሥት ያላትን ርዝመትና ወደጎን ያላትን ስፋት
አሁን ከአንፈራራ ጋር ገጥሟል ማለት ይቻላል እስከ ዋናው ከተማ 11 ኪሎሜትር ነው ከዛ እስከ ነጌሌ መውጫ እኔ በቅርብ አላየሁትም ከሚሽኑ በታች እስካለው ጨፌ ድረስ 5 ኪሎሜትር ይሆናል ባጠቃላይ 15 ኪሎሜትር ርዝመትና በግምት 1 ኪሎሜትር ስፋት ያላት ሆናለች :
ከራስብሩ ትምህርት ቤት እስከ ማሪያም ጨፌ ምን ያህል ይርቃል አምስት ስድስት መቶ ሜትር ?
%
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Oct 10, 2010 1:39 pm    Post subject: Reply with quote

ገበያው ቆሟል ለኔ ግን የተኛ ገበያ ያህል ምንም ቁብ አልሰጥ አለኝ ቢሆንም ቢሆንም መሀል መሀሉን እያልኩ ወደማዶው ስዘልቅ ቂቤ ተራ አካባቢ አይኔ አንድ ተአምር አየ መራመድ አቃተው በቃ ሊቆም ሆነ ማለፍ አቃተው ቆመ ......... ሠላም ? ሰላም እንዲህ ያለ ሳቅና ፈገግታ እንዲህ ያለ ውበት ..... ደህና ነሽ እመቤት ?
ደህና ?
አላወኩህም የሚለውን ቃል ሳትናገረው ሰማሁትና አደቆርሳ እባላለሁ :
ከሻኪሶ ነህ ?
አዎ አልኩ ከየት እንደመጣኝ አላውቅም
አንቺ የክብረመንግሥት ልጅ ነሽ ?
አዎን እዚህ ነው የተወለድኩት ?
የማን ልጅ ነሽ እንዳልል ? ሳልወድ አስዋሽታኛለች
የት ነው የምትኖሪው ?
አዲስ አበባ ነው
አዲስ አበባ የት አካባቢ ?
አንተ ያዲሳባ ልጅ ነህ ? አይደለሁም የአዋሳ ልጅ ነኝ
ውይ ባለቤቴ የአዋሳ ልጅ ነው
ባለቤቴ ?
አዎ
ክው ያርግሽ ያባቴ አምላክ ክው አረገቺኝ :
ምን አይነቷ ወንጀለኛ ናት በማምላክ ገና አይኔ አይቷት ሳይጨርስ ባለቤቴ ትላለች እንዴ ?
ቆይ ምን አጣደፈሽ ?
ለምኑ ?
ለማግባት ነዋ ! ቅቅቅቅቅቅ በሳቅ ፍርስ አለች
ታዲያ ምን ልጠብቅ ?
እኔን አትጠብቂም ነበር ?
እስካሁን አላገባህም ?
መች ትገኛላችሁ ገና ወሬ ሳይጀመር ባለቤቴ ምናምኔ ትላላችሁ ........ እንደዚህ ስቃ አታውቅም ከትከትከትከት
ደሞ ሲያምርባት ስትስቅ :
ባለቤትሽ ማነው አውቀው ይሆን ?
ታውቀው ይሆናል እገሌ ይባላል አሁን የለም ውጪ ነው ያለው ?
ምን ? ወጪ ?
አዎን
አላወኩትም ምናልባት ባየው አውቀው ይሆናል ግን አንቺን ጥሎ ውጪ ?
እኔም በቅርቡ እሄዳለሁ
እንደው ከዚ ከውጪ እኔ ብቻ .....................
የት ነው ያለው ?
ዩኤስ ፍሎሪዳ ነው ያለው ..............
ወይ ጉድድድ
ብቻ በደቂቃ ውስጥ ለጉድ የሚተዋወቁ መስለን ቁጭ ብለናል
ግን የክብረመንግሥት ልጅ መሆኗን ባትነግረኝም መገመቴ አይቀርም ነበር
ምክንያቱም የክብረመንግስት ልጆች መሽኮርመም አንገት መድፋት መወላከፍ ምናምን አያውቁም ቀጥ ያሉና ጣፋጭ ናቸው ሲወዱም ራሳቸው ከመጥበስ ይመለሳሉ ? ባላችሁ ነው ?
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባለሱቅ

ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Sep 2004
Posts: 1053
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 11, 2010 10:44 am    Post subject: Reply with quote

አደቆርሳዬ ... ዛሬ ደሞ የማላውቀውን ነገር ተናገርክ
Quote:
የክብረመንግስት ልጆች መሽኮርመም አንገት መድፋት መወላከፍ ምናምን አያውቁም ቀጥ ያሉና ጣፋጭ ናቸው ሲወዱም ራሳቸው ከመጥበስ ይመለሳሉ ? ብላችሁ ነው ?

እኔ አልስማማም
ወይ እንደሱ አይነቶቹ ጣፋጭ ልጆች ገጥመውኝ አያውቁም ይሆናል
ምስካሪ ራስብሩ
ምክንያቱም ስንትና -ስንት አመት ነው የፈጀበት ያችን የሰፈራችንን ልጅ በእጁ ለማስገባት
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
እኔ በበኩሌ የክ /መንግስት ልጅ ጠብሼም ... በክ /መንግስት ቆንጆ ተጠብሼም አላውቅም ...
አንድ ሁለቴ ሞክሬ
እስኪ ቀስ ብለህ እደግ
አንተ ደፋር ... ማን መሰልኩህ
የማነው ንፍጣም
መጀመሪያ ቀዳዳ ሱሪህን ጣፍ
ወይም ከነጭርሱ እኔ ስመጣ ... ሮጣ ጊቢዋ ገብታ በቀዳዳ እያጮለቀች የምታየኝን ቆንጆ ብቻ ነው ማስታውሰው .... ይሄ ታዲያ አይናፋርነት አይደለም
እስኪ ባክህ አደቆርሳዬ ቀጥል ይህ ጣፋጭ ጨዋታህን
እኔማ ጨዋታ አልቆብኝ ስለዶሮ ፍቅር ላወራ እየተሟሟቅኩ ሳለ ነው የመጣኸው
ገላገልከኝ አቦ
ግን ደሞ ወሰወስከኝ የሆነ የሆነ ብሎን ነገር እየነካካህ ....
እስኪ ቀጥልልን አቦ
ደሞ ይመችህ ብለናል
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=11833&start=4680
THANK YOU CYBERETHIOPIA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Oct 11, 2010 4:27 pm    Post subject: Reply with quote

ውይ መጣህ እንዴ ? እንኳን ደህና መጣህ የኔ ጃላ
ቤቱ ጭር ሲልብኝ አንተም የጠፋህ መስሎኝ እንደለመድኩት ሹልክ ልል ስል ነው የያዝከኝ ከመጣህማ የምፈልገው አንተን ነው ::
በቅድሚያ የናፈቁኝን የተቀበሉኝን ወዳጆቼን ላመስግን
የምወድህ ተድላ ኃይሉ : የጠዋቱ ወዳጄና አጋዤ ዝምታ እና የቤታችን ወዳጅ ኮሎኔል ከልብ የመነጨ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ ስለላካችሁልኝ መልክት በጣም ተደስቻለሁ :
ከልቤም አመሰግናለሁ ::
Quote:
እኔማ ጨዋታ አልቆብኝ ስለዶሮ ፍቅር ላወራ እየተሟሟቅኩ ሳለ ነው የመጣኸው

እግዚአብህእር ምስክሬ ነው ሆዴን አመመኝ
እስቲ እንዴት ነው የዶሮ ፍቅር አሳየኝ ወይ ድንገት እኔምኮ አውቅ ይሆናል ምን ይታወቃል ?

ወሬዬን ልጨርስልህና በሁለተኛው ቀን አዋሳ ድረስ በኮንኮላታ አብረን ሄድን እንደዛ አይነት ቆሻሻ እና አስቀያሚ መኪና አይቼ አላውቅም ጠዋት ተነስተን ማታ ነው አዋሳ የደረስነው :
እሷን አዋሳ ተሰናብቼ እኔ ማለፍ ነበረብኝ በይ የኔ ቆንጆ ይቅርታ የሰው ቆንጆ ደህና ሁኚ
ውይ በጣም ደስ የሚል ጉዞ ነበር አንተ ባትኖር በጣም ይደብረኝ ነበር በናትህ እንገናኝ ፌስ ቡክ አለህ ?
ፈስ ቡክም የለኝ እንቺ ቴሌፎን ስትሄጂ እሸኝሻለሁ ካልደወልሽም ደህና ግቢ ብዬ ተሰነባብተን ተለያየን .................. አሳጠርኩት አይደል ? ሚስጥሩን ሌላ ቀን አወጣው ይሆናል ቤቱንኮ መልመድ አቃተኝ ሁሉም ጠፉ ::
የክብረመንግሥት ልጆች ይግደረደራሉ ነው ያልከኝ ?
እንዳትሳሳት ምናልባት ዲሲፕሊንድ ከመሆናቸው የተነሳ ያለ ስርዓት ጠይቀሀቸው ይሆናል እንጂ እንደክብረመንግሥት ልጆች ቶሎ የሚገባቸው አላውቅም ለነገሩ ኢትዮጵያዊያን የተለየና በአንድ አይነት ካታጎራይዝ የምናረግባቸው መንገድ አለ አንዳንዴ ሴንቲሜንታል አንዳንዴም performance in respect እንዲሁም high ኪፒንግ ሰልፍ ዲግኒቲ ወይንም ቢዩቲ ራንክ ምናምን እንደሚባለው የድሮ አማርኛ ሀበሻ ሴቶች ቢወዱም ያቺን ከላይ ካነሳኋቸው አንዷን በደንብ እንዲመሰከርላቸው ይፈልጋሉ ባጠቃላይ ሴቶችን ሳይ ግን ምናልባት እንደናንተ ብዙ ዜጋ የማየት እድሉ አልገጠመኝም እንደሁ እንጂ ተዛማጅ ከለር ካሉን ጋር በሚገባ ተሞክሮ አለኝ :
ልዩነታችን ጉልህ ነው የኛን ወላጆችኮ ያየህ እንደሆነ ሚስት ሳይሆን እቃ ነበር በትዳር የሚያስቀምጡት ብዙ ዝርዝር እንዳላበዛ የክብረመንግሥት ልጆች ውነቴን ነው የምልህ ቀና እና ጣጣ የማይፈልጉ እንዲሁም ግልጽ ናቸው
ጅብ ካለፈ ሆነ እንጂ ያሁኖቹማ እንደድሮዎቹ ቆንጆ አይደሉም እንጂ ተወኝ አልኩህ ጎበዞች ናቸው ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon Oct 11, 2010 6:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ;እዚህ ቤት ይሁን ::

ውድ አደቆርሳ =የናፈኩተን ጨወታህን አጣጣምኩት ;;ቀጣይነት ስለነበረው አድፍጬ እያነበብኩህ ነበር ::
ቶሎ ከክብረመንግስት ወደአዋሳ እንደመለስከን አልገባኝም ::
እዛው አካባቢ ብዙ ታቆየናለህ ብዬ አስቤ ነበር ::በሌላው መልኩ ያለህን ነጻነት በጣም አደነኩልህ ::የሰው ቆንጆ
ለማማለል ስትሞክር አደቆርሲትን እንዴት አስቻላት ብዬ ነው ::

የጠፋው ሰው ቺኮ =በሰላም ከሀገር ቤት መመለስህን ሰማሁ ::አዲስ አበባ ላይ ሞፊቲ ነኝ ብሎ የሸወደህ ሰው
ነው መሄድህንና መምጣትህን የነገረኝ ::እንዴ !ምነው ግን ወደታች (ሻኪሶ ) ሳትዘልቅ ተመለስክ ::ያቺ ዱቄት ውስጥ
የከተተችህን ልጅ ቤተሰቦች ፈርተህ ነው አይደል ????
በል እስቲ ብቅ በልና ተናዘዝ .......

ቸር እንሰብት !!!!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Tue Oct 12, 2010 2:02 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ይህን ኮፒ አድርጌ ያመጣሁትን አስገራሚ ዘገባ ከዚሁ ከዋርካ ጄኔራል ነው ያገኘሁት ::የኛ ቤት አካል ነው ብዬ ስላሰብኩና ብዙ ነገር እንድናውቅ ስለሚረዳን ፕሊስ አንብቡት ::
Quote:
የሲዳማ ባህላዊ ሐይማኖት
(በኖሞናኖቶ )

ሲዳማ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል አንዱ ሲሆን፡ ቀድሞ የሲዳሞ ክፍለ አገር ይባል በነበረው እና በአሁኑ ጊዜ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት አካል በሆነው ሲዳማ ዞን ውስጥ የሚገኝ ህዝብ ነው። ህዝቡ ከሲዳማ ዞን ውጪ በአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ይኖራል። የህዝብ ብዛቱም ከአራት ሚሊዮን በላይ እንደሆነ የተለያዩ ዶክመንቶች ያመለክታሉ።

ሲዳማዎች የአፍሮ - እስያቲክ ግንድ ካላቸው እና በሰሜን አፍሪካ፣ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ እስያ ከሚነገሩ 375 ቋንቋዎች አንዱ የሆነ እና ከኩሽ ወይም ከኩሺቲክ የቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ቋንቋ ይናገራሉ። ከቋንቋቸው ባሻገር እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ባህል፣ እምነት፣ አስተዳደራዊ ስርዓት፣ መገበያያ ገንዘብ፣ የጊዜ እና ዘመን አቆጣጠር ስርዓት እና ሌሎች ማህበራዊ እሴቶች ያሉት ህዝብ ነው።

ሲዳማዎች ለዘመናት ከአባት ወደ ልጅ እያወረሱ ካቆዩት እሴቶቻቸው መካከል ባህላዊ ሐይማኖት ይገኝበታል። በሐይማኖቱ መሰረት ሲዳማዎች በማጋኖ ( አምላክ ወይም እግዚአብሔር ) ያምናሉ። ማጋኖ ሐላሌ ( እውነት ) እና አካካ ( አባቶች፣ አያቶች፣ ቅድመ አያቶች ) የእምነታቸው መሶሶዎች ናቸው። በእነዚህ ሶስቱ መሶሶዎች ላይ እና በእምነቱ አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳብ ላይ አንዳንድ ሀሳቦችን ከማንሳት በፊት ስለአካኮዎች ወይም አባቶች፣ አያቶች፣ ቅድመ አያቶች ወይም ስለሲዳማ ጎሳዎች ትንሽ ልበል።

ሲዳማዎች ከመካከለኛው ምስራቅ ባህርን ተሻግረው ወደ አፍሪካ ቀንድ መምጣታቸውን፣ በመጀመሪያ '' ዳዋ ''1 ከሚባል ቦታ ላይ መስፈራቸውን ቀጥሎም በባሌ አድርገው አሁን ወዳሉበት አከባቢ መምጣታቸውን የብሔሩ ሽማግሌዎች ይተርካሉ። በትረካቸውም አሁን ወዳሉበት አከባቢ እንዲመጡ ያደረጋቸው የአባታቸው ጉዛዜ መሆኑን ይናገራሉ። እንደሽማግሌዎቹ ገለፃ፡ ሲዳማዎች የሁለት አባቶች ልጆች ሲሆኑ፡ ቡሼ የሚባለው አንደኛው አባታቸው ሲሞት ከመቃራቸው ጉድጓድ የሚወጣው አፈር ከተቀበሩ በሃላ ሲመለስ ከመሬት ከፍ ወይም ዝቅ ከሚል ቦታ እንዳይቀብራቸው በተናዘዙት መሰረት የአባታቸውን ሬሳ በተለያዩ አካባቢዎች እና ቦታዎች ለመቅበር ሞክረው ስላልተሳካላቸው መጀመሪያ ከሰፈሩበት አካባቢ ተነስተው በባሌ አድርገው እግሬ መንገዳቸውን የአባታቸውን ሬሳ እየቀበሩ እያወጡ ዛሬ ወዳሉበት አከባቢ መጥተዋል። በአከባቢውም የአባታቸውን ሬሳ ሲቀብሩ በተናዘዙት መሰረት ከመቃብር ጉድጓድ የወጣው አፈር ወደ መቃብሩ ሲመለስ ከመሬት እኩል በመሆኑ የአባታቸው የመጨረሻ የመቃብር ቦታ ሆነ። ከአባታቸው የመቃብር አከባቢ መራቅ ያልፈለጉት ሲዳማዎችም በአከባቢው ሰፍረው እስከአሁን ይኖራሉ።

እንግዲህ ስለሲዳማዎች አባት ኑዛዜ አፍጻጸምያለምክንያት አይደለም ያነሳሁት፡ በብሔሩ ባህላዊ ሐይማኖት መሰረት የእርሱ የመቃብር ቦታ እና ሌሎች መሰል የጎሳ አባቶች መቃብሮች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ስላላቸው ነው። ወደታች በስፋት አነሳዋለሁ።

ለባህላዊ ሐይማኖቱ መሰረት የሆነው ሌላው ማጋኖ ነው። ከላይ እንዳነሳሁት የሐይማኖቱ ተከታዮች በማጋኖ ( አምላክ ወይም እግዚአብሔር ) ያምናሉ። ለማጋኖ፤ ካላቃ (ፈጣሪ ) ካሊቃ (ሃያል ሁሉን ቻይ ) እና ሐላላንቾ (እውነተኛ ) በማለት ሶስት ገጽታዎችን ይሰጡታል። ከዚህም በተጨማሪ ማጋኖ፤ እውነተኛ ወዳጅ፣ ለልጆቹ የሚሳሳ፣ የሚራራ፣ ሲያጠፉ የሚገጽጽ፣ ሀጢኣያታቸው የሚምር ሩህሩህ አባት ነው ይላሉ።

በሐይማኖቱ ማጋኖ አምሳያ የለውም። በአምሳሉ የተቀረጹ ወይም የቆሙ ወይም መልኩን የሚያሳዩ ቁሶች የሏቸውም፤ ነገር ግን ቀን በቀን ከመሃከላቸው እንደሚገኝ ያምናሉ። ስሙ በራሱ የሚፈራ እና የሚከበር በመሆኑ ለመልካም ስራ ካልሆነ ለክፉ ተግባራት ማለትም ለማታለሊያነት፣ ውሸት ለመናገር፣ ወዘተ አይጠራም። ለክፋት ስሙን ማንሳት ወይም መጥራት ማጋኖን ያስቆጣል ተብሎ ይታመናል።

ማጋኖ የሰውን ልጅ ከአፈር ፈጥሮ ትንፋሹን ከሰጠው በሃላ ወደ ሰማይ አረገ። ወደ ሰማይ ካረገ በሃላ ከፈጠው የሰው ልጅ ጋር በሐላሌ አማካይነት ይገናኝ ነበር። ሐላሌም በሰው እና በካሊቃ መካከል እንደድልድይ ሆነ ስለ ሰው ልጅ ያማልዳል ነበር።

የእምነቱ ተከታዮች እንደምሉት ከሆነ፤ ሐላሌ ሲዳማዎች ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበት ብቸኛው ድልድይ በመሆኑ ታላቅ ክብር እና ዋጋ ወይም ቫልዩ ይሰጡት ነበር። በመጀመሪያ ላይ ሐላሌ በአይን የምታይና በእጅ የምዳሰስ፤ ሰዎች በሚያሹት ወቅት በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ የሚገኝ ብሎም በሰው ልጆች መካከል የሚመላለስ ነበር።

ሐላሌ ለሲዳማዎች ቅርብ ከመሆኑ እና ሲዳማዎችም ለሐላሌ ካላቸው ክብር የተነሳ በእርሱ ይተዳደሩ ነበር፤ ሐላሌም ሲዳማን ያስተዳድር ነበር። ነገር ግን ከብዙ ዓመታት በሃላ የሰው ልጆች በክፋት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ክህደት እና በሌሎች ክፉ ተግባራት እየተሰማሩ የፈጣሪን ትዕዛዛት እየጣሱ ሲመጡ፤ ሐላሌ ከመሃከላቸው መመላለስን እና ማስተዳደሪን ትቶ ወደ ፈጣሪ ወይም ካሊቃ ዘንድ ለመሄድ ተነሳ።

ሐላሌ ከመካከላቸው እንደማይኖር እና ጥሏቸው ወደ ካሊቃ (ማጋኖ ) እንደሚሄድ የተረዱ እና ከእንግዲህ ከፈጣሪ ጋር እንደት ሆኖ እንደምገናኙ ያልተረዱት የእምነቱ ተከታዮች ሐላሌ ለማን ጥሏቸው እንደሚሄድ ጠየቁት። ሐላሌም ከእንግዲህ ከካሊቃ ጋር የምትገናኙት በአባቶቻችሁ በኩል ነው። አባቶቻችሁ ከፈጣሪ ጋር ያገናኟችሃል፣ ስለእናንተ ፈጣሪን ይማለዱላችሃል ብሏቸው ወደ ሰማይ አረገ።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐይማኖቱ ተከታዮች በሞት የተለዮቸው አባቶቻቸው፣ አያቶቻቸው፣ ቅድመ አያቶቻቸው ከማጋኖ ጋር ይኖራሉ ብለው አመኑ፤ ከማመንም በላይ ከማጋኖ ጋር ለመገናኘት አባቶቻቸውን መጠቀም ጀመሩ።

በእምነቱ ፊልስፊና መሰረት '' እኔ ከእኔ በላይ አባቴ ከአባቴ በላይ ቀደሚት አባቶቼ፣ ከቀደሚት አባቶቼ በላይ ካሊቃ (ማጋኖ ) '' ተብሎ ይታመናል። ከእምነቱ ጋር በተያያዘ እና በሌሎች ማህበራዊ ምክንያቶች የተነሳ ሲዳማዎች ለአባቶች እና ለአረጓውያን የተለየ አክብሮት አላቸው።

እንግዲህ ሐላሌ ወደ ካሊቃ ካረገበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አባቶች የእምነቱን ተከታዮች ከፈጣሪ ያገናኛሉ፣ ያስታርቃሉ፣ ስለእነርሱ ይማለዳሉ።ከዚህም ባሻገር የማህበረሰቡ ስነ ምግባር ወይም የግብረገብነት እና ሐይማኖታዊ ሕግጋት መከበራቸውን ይቆጣጠራሉ።

የአባቶቻቸው የመቃብር ቦታም የእምነቱ ስነስርዓት ማካሄጃ ቦታ ሆነው ያገለግላሉ። ከላይ ከመግቢያዬ ላይ እንዳነሳሁት፤ የሲዳማ ጎሳዎች አባቶች በተለይ ሁለቱ የሲዳማ ዘር የተነሳባቸው አባቶች መቃብር ቦታዎች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ቦታዎች ናቸው።

በሲዳምኛ '' ሞጎ '' ተብለው የሚታወቁት የአባቶች እና ቅድሜ አባቶች ወይም የአካኮች መቃብሮች፤ ታጥረው በጥንቃቄና በንፅህና የተያዙ፣ የእምነቱ ተከታዮች ፈጣሪውን ለማምለክ የሚሰባሰብባቸው፣ እንዲሁም ፈጣሪን መማጸኛ መስዋዕቶችን የሚያቀርቡበት ቅዱስ ስፍራ ነው።

በእነዚህ በትላልቅ ዛፎች በተሞሉ 2ቅዱስ ስፍራዎች የእምነቱ መሪዎች ይኖራሉ። በጥቅሉ ''ቃዶ '' ተብሎ የሚጠሩት እነዚህ የእምነቱ መሪዎች በቁጥር አራት ሲሆኑ፤ ከስራ ሐላፊነታቸው አንፃር ጋና፣ ቃሪቻ፣ዎማ እና ጋዳላ ይባላሉ።

ከላይ እንዳነሳሁት የእምነቱን ተከታዮች ከፈጣሪ ወይም ከካሊቃ ጋር እንደድልድይ ሆኖ ያገናኛቸው የነበረው እና ያስተዳድራቸው የነበረው ሐላሌ ወደ ካሊቃ ከሄደ በሃላ ከፈጣሪ ጋር የማገናኘቱን ስራ ለአባቶች ስሰጥ ህዝቡን የማስተዳደር ስራ ሐላሌን ተክቶ እንዲሰሩ ከእምነቱ ተከታዮች መካከል ለተመረጡ ሰዎች ተሰጥቷል። ሐላፊነቱን የወሰዱት እነዚሁ ቃዶዎች ናቸው።

የእምነቱ ተከታዮች ከእምነቱ እና ከእለትለት ማህበራዊ ኑሮ ጋር በተገናኘ የሚገጥሟቸውን ችግሮች እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ መንፈሳዊ ማበረታቻዎችን እና ማህበራዊ ፍትሕ ለማግኘት ወደነዚህ ቅዱስ ቦታዎች በመሄድ ቃዶዎቹን ያገኟቸዋል። ቃዶዎቹም ሐላፊነት ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ ከቅዱስ ቦታዎቹን እየተንከባከቡ እድሜ ልካቸውን እዛው ይኖራሉ በምትካቸው ሌላ ቃዶ የሚመረጠው ሲሞቱ ብቻ ነው።

አራቱም የተለያየ የስራ ሐላፊነቶች ሲኖሯቸው፤ አንደኛው በሌላኛው ስራ ላይ ጠልቃ መግባት አይችሉም። ከዚህም በተጨማሪ እነርሱ በምሰጡት ውሳኔዎች ላይ ማንኛውም ውጫዊ አካል ጠልቃ መግባት አይችልም።

እንግዲህ የሲዳማ ባህላዊ ሐይማኖትን በተመለከተ በጣም በጥቂቱ ይህንን የሚመስል ሲሆን፤ ባህላዊ ሐይማኖቱ እንደሌሎቹ የዓለማችን ትላልቅ ሐይማኖቶች ሁሉ የራሱ የሆኑ ሕጎች ያሉት፣ የራሱ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅሮች ያሉት፣ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት፣ የራሱ የሆነ ማምለኪያ ስፍራ ያለው እና በራሱ ሙሉ የሆነ ነው።

ኖሞናኖቶ ነኝ !
ቸር እንሰንብ
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 12, 2010 2:27 pm    Post subject: Reply with quote

ይቅርታ በቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ጽሁፉ ተሰረዘብኝ እንደገና ጽፌ ወደበኍላ ሰደዋለሁ
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Oct 12, 2010 9:32 pm    Post subject: Reply with quote

ከላይ ያለውን ጽሁፍ በደንብ አነበብኩት መነሻነቱና መድረሻነቱ እንዲታወቅ ማለቴ ሥሩን እንድናውቀው ፍንጭ ብናገኝበት መጣም ጥሩ ነበር ሞፊቲኮ ከቻልክ ፍንጭ እንድናገኝ እርዳን ::
በአጻጻፉ ውስጥ በርካታዎቹ ነገሮች በትክክል በጣም ጥቂቶቹ ደግሞ ለየት ያሉ የሲዳማ መገለጫዎችን አይቻለሁ ::
እንደምሳሌ ለማንሳት ያህል

Quote:
ማጋኖ የሰውን ልጅ ከአፈር ፈጥሮ ትንፋሹን ከሰጠው በሃላ ወደ ሰማይ አረገ። ወደ ሰማይ ካረገ በሃላ ከፈጠው የሰው ልጅ ጋር በሐላሌ አማካይነት ይገናኝ ነበር። ሐላሌም በሰው እና በካሊቃ መካከል እንደድልድይ ሆነ ስለ ሰው ልጅ ያማልዳል ነበር።

የአብ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን አገላለጽ የተላበሰ ነገር ግን አገላለጹ ለየት ያለ ይመስላል :
ጥቂት መናገር ቢቻል በሲዳምኛ ቋንቋ
መገኖ ማለት -- እግዚአብሄር
ሀላሌ ማለት -- እውነት
ካሊቃ የሚለውን ቃል በትክክል መግለጽ ከቻልኩ ፈጣሪ ማለት ነው ::
እንግዲህ እግዚአብሄር እውነትና ፈጣሪ - አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስቅዱስ ሰራጺ እንደማለት ነው ማለት ነው ይህ ትክክል ነው ::
እኔም እስከማውቀው ድረስ በሲዳምኛ እምነት ውስጥ ከመገኖ ሌላ ምንም አምላክ የለም

ምናልባት እንደዘመኑ የእምነት እርምጃ የተለያዩ አምልኮዎች ካልተደረጉ በስተቀር ::
ለምሳሌ በሲዳማ የፍቼ በአል በኦሮሞ ደሞ እሬቻ በአል የሚባሉት እየዋለ እያደረ ውስጥ ውስጡን በሚደረጉ ነገሮች ለወጡት እንጂ ትክክለኛ ሥርዓቱ የእግዚአብሄር አምልኮ በአል ነው ::
አካኮ እና አባ ገዳ ተመሳሳይነት ያላቸው የአምልኮ በአላት ናቸው
አሁንም እንደምሳሌ ለማንሳት ያህል በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ የጥምቀት በአል በሚከበርበት እለት ብዙዎቻችን ጭፈራ ለማየት አልያም ለመጥበስ እንዲያም ሲል ደሞ ለመጠጣትና ለመስከር ሌሎቻችን ደሞ ሸቀጥ ለመሸጥና ለመነገድ ወዘተርፈ ይህ አይነቱ ሁኔታ ከላይ ካነሳነው ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው እና መሰረቱ እውነት መሆኑን ለማመሳከር ይረዳናል ::
የአካኮ እምነት ትክክለኛውና ዋናው የሲዳማ ህዝብ ሀይማኖታዊ እሴት ነው አካኮ ማለት እኛ በአማርኛም እንደምንለው አያት ቅድማያት እንደማለት ነው አኩዬ የሴት አያት እና አካኮ የወንድ አያት ይባላል
እዚህ ላይ አንድ ነገር ለማለት ፈለኩ የሲዳማ ህዝብ ብቻውን አይደለም ወደኢትዮጵያ የመጣው ሲዳማና ኦሮሞ አንድ ህዝብና አንድ ዘር እንደነበሩ የመጡትም አብረው አብረው እንደሆነ አንዳንድ አስረጅ መዛግብት ይገኛሉ
እንደምሳሌ ከሚነገሩ አንዱን ላስታውስ
መስራቅ አፍሪካ በምስራቃዊው የኢትዮጵያ ክፍል ይኖሩ የነበሩ ከእነዚህ ጎሳዎች ውስጥ ተበታትነው ኖሮ ከረዥም ግዜ በኍላ ሲገናኙ አንደኛው አንዱን ወዴት ሄደህ ነበር ሲለው እንዲህ መለሰለት ይባላል :
ዲሬ ዳዋ (ዳውሞ ) ቁልቁለት ወርጄ መጣሁ አለው
ዲሬ ዳዋ ማለት በሲዳምኛ ቁልቁለት መውረድ ማለት ነው ::
ወዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆኖ የቆየው እዛች ቦታ ሊሄድ ፈልጎ (ሳፎ ) አለ ይባላል :

እንግዲህ ከዛን ግዜ ጀምሮ ድሬደዋ የሚለው ስም ለአሁኗ ድሬደዋ ተሰይሞ እንደቀረ ታሪክ ይናገራል ::
በቋንቋ ደረጃ ሲዳምኛ ኢትዮጵያ ከመግባቱ ቀደም ሲል ሆፋ በሚል የአለም ቋንቋ ይታወቅ ነበር ::
በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ተፈጥረውና ተምረው የታሪኩን ምንጭ ጥሩ አድርገው ከጻፉ እውቅ ተመራማሪዎች ውስጥ መቀመጫቸውን በእንልጣር ያደረጉ ፕሮፌሰር ክፍሌ ዋርታሞ የጻፉትን ማንበብ ጭብጥ መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል ::
Quote:
ሲዳማዎች የአፍሮ - እስያቲክ ግንድ ካላቸው እና በሰሜን አፍሪካ፣ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ እስያ ከሚነገሩ 375 ቋንቋዎች አንዱ የሆነ እና ከኩሽ ወይም ከኩሺቲክ የቋንቋ ቤተሰብ የሚመደብ ቋንቋ ይናገራሉ። ከቋንቋቸው ባሻገር እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔሮ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ባህል፣ እምነት፣ አስተዳደራዊ ስርዓት፣ መገበያያ ገንዘብ፣ የጊዜ እና ዘመን አቆጣጠር ስርዓት እና ሌሎች ማህበራዊ እሴቶች ያሉት ህዝብ ነው።

እውነት ነው ሲዳማ የራሱ የሆነ የዘመን ቀመር ካላቸው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብቸኛው ነው ::
በቋንቋ ዝርያ ከኦሮምኛ ጋር የቅርብ ቤተሰብ የሆነ የኩሽ ሥር ያለው ነው
አንድ ያነበብኩትን ላስታውሳችሁ
በኦሮምኛ ኖው ? ቤክታ ? ....... ኢንቤኩ - ኢን ቤኩ አይ ዶንት ኖው
በሲዳምኛ ኖው ? አፎቶ ? ........ ዲአፎሞ - አፎሞ
አይ ዶንት ኖው
ቃላቶቹን ኔጋቲቭ የሚያደርጋቸው ኢን እና የሚሉት ሁለቱም በእንግሊዝኛው የሚታወቁ አንድ ተመሳሳይ መግለጫነት ያላቸው ስርዓቶች ናቸው ከአማርኛው ጋር ግን ምንም ዝምድና የላቸውም ::
በሲዳማ ማህበረሰብ ውስጥ ሙሉውን ቁጥር የሚይዘው የአማኝ ብዛት ክርስትና ነው የሚሽነሪዎች ወንጌል መካነ እየሱስ ኦንሊይ ጂሰስ ጄሆሀ ዊትነስ ወዘተ ናቸው ::
እንግዲህ ከላይ ያለውን እና እኔም ያከልኩበትን ያጠፋሁን ወይንም የጨመርኩትን በደንብ ለማየት ይቻላችሁ ዘንድ የፕሮፌሰር ክፍሌ ዋርታሞን መጽሀፍ ብታነቡ በቂ መረጃ ልታገኙ ትችላላችሁ ::
ለተጨማሪ ዋቢ መረጃዎች ቤተና ሆጤሳ እንዲሁም ሥዩም ሀሜሶ ሌሎችም የጻፏቸውን ተመልከቱ ::
ስለመካነ እየሱስ ትንሽ ልበልና ላብቃ ::
መካነ እየሱስ ሲባል አንድ ትዝ የሚለኝ እና ከአይምሮዬ የማይጠፋ ነገር ላጫውታችሁ ነው ::
ስለ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ
ተስፋዬ ትውልዱም ዘሩም ሲዳማ ነው
በንጉሠ ነገስቱ ዘመነ መንግሥት በይርጋዓለም ሆስፒታል ውስጥ ለህመምተኞች በየእለቱ የወጌል ስብከት ይደረግ ነበር በህጻንነቱ የወንጌል ፍቅር የተገለጠለት ተስፋዬ ከፈረንጆቹ የበለጠ ሰባኪ ለመሆን ምንም ያገደው ነገር አልተገኘም ::
ስብከቱ ከህመምተኞች እንዳያልፍ የተደረገው ጃንሆይ መጤ ሀይማኖት በህዝባቸው ውስጥ እንዳይገባ ይፈሩ ስለነበር ነው ነጮቹ ደሞ ገባ ብለው ህዝቡን መስበክ ይፈልጋሉ ግን አይፈቀድላቸውም ነበር ::
ተስፋዬ ስል አዕምሮ ያለውና ኃይለኛ ስለነበር በአጭር ግዜ ውስጥ ብዙ ሰዎችን የመካነ እየሱስ አማኝ አደረገ ::
ይህ ሰው ህዝቡን እየለወጠ ነው ስለዚህ አንሱና ቢናገርም በጀ ወደማይለው (ሀይማኖቱን ወደሚያጠብቀው ) ወደ ጎጃም ውሰዱልኝ ብለው አዘዙ ወደጎጃም ተወሰደ
እዛም በርካታ ሰዎችን እየመሰከረ ለወጠ ጎጃምም አልተቻለም አንስተው ወደ ጎንደር ወስደው አሰሩት ጎንደር እስረኛው በሙሉ በመዝሙሩና በስብከቱ ተማረከ ይህንን ሰው አልቻሉትም አይ ይሄ ሰው እዛው ይመለስና እንደፈለገው ይሁን ከዚህ አውጡት ብለው ወደ ሲዳሞ መለሱት ደርግ ዘመነ በትሩን ሲረከብ ከሁሉም በላይ አብዮቱ ሲባል ተስፋዬ የማይዋጥለት ነገር ሆነ ከስደተኛ አራዳ ድረስ አሸዋ ላይ በጉልበቱ ሲያስኬዱት ድካም እንኳን አይሰማውም ነበር :
በወህኒ ሳለ በኤሌክትሪክ ገመድ እንዲገረፍ ታዞ አንዲትም አለንጋ እሱ ላይ ማሳረፍ የቻለ ፖሊስ አልተገኘም ሁሉም አልገረፉትም ጠዋት ጠዋት የሽንት እቃ አንገቱ ላይ እያሰሩ ይቀጡት ነበር ተስፋዬ በዚህ ስቃይ ወቅት ይዘምራል አምላክ እረኛዬ ነው እያለ ይጮሀል ሶስት ቀን ያለምግብና ውሀ ጭለማ ክፍል ውስጥ አስረው በሶስተኛው ቀን ሲያዩት ርሀብም ጥማትም አልደፈረውም ነበር :
ተስፋዬ ከሁሉም በላይ አብዮቱ በል አለበለዚያ ትገደላለህ ተብሎ በደርጉ ግራ መንገደኞች በነማቴዎስ ማዴቦ እና ሌሎችም ለቀረበለት ጥያቄ ለመሞት ፈጽሞ ዝግጁ ነኝ ብሎ በደስታ የመለሰ ጀግና ነው ::
ከሞት የማያንስ ስቃይ በህይወቱ የተቀበለ ልዩ ሰው ነው የተስፋዬን ዝናና ልዩ ሁኔታ የሰማ የአካባቢው ሰው እሱን ለማየትና ለመስማት ከተለያየ ስፍራ ይመጣም ነበር ምክንያቱም በአደባባይ የሚደርስበትን ቅጣት ያይ ስለነበረ ነው በአደባባ በከተማ ውስጥ እና በመንገድ ልያ የሚያሰቃዩት ሌሎች እንደሱ እንዳይሆኑ አስበው ቢሆንም የሱ ጽናት ብዙዎችን ወደሱ አመጣ እንጂ አልመለሰም
እሱም ይህንን በጽናት ይናገር ነበር : ሲሰቃይ ይዘምራል
ተስፋዬ ከሀገር ለመውጣት ከማንም ከምንም በላይ እድሎች ነበሩት አላደረገውም እንደው አስታወስኩት እንጂ ታሪኩ እጅግ ብዙ ነው በህይወት ዘመኔ ሁሉ በእምነታቸው የጸኑ እና አንገታቸውን የሰጡ ትልቅ ሰዎች ናቸው ከምላቸው ውስጥ ተስፋዬ ጋቢሶ አንዱና ዋናው ነው ::
እኔ የጴንጤ ቆስጤ እምነት ተከታይም ደጋፊም አይደለሁም ነቃፊም አይደለሁም ነገር ግን እንዲህ ያለ ለአምላኩ የጸና እና ተአምረኛ ሰው ማስታወስ ተገቢ መስሎ ስለታየኝ ከሲዳማ ህዝቦች ውስጥ ደሞ ልዩ ታሪክ ያለው በመሆኑ እነሆ ጻፍኩ ::
ተስፋዬን በአካልም አውቀዋለሁ አሁን በአዋሳ ድሮ ሹሉ ሚሽን በምንለው የራሱን ቸርች ከፍቶ ያገለግላል ::

ሞፊቲኮ ስሳቀረብክልን ኢንፎርሜሽን ላመሰግንህ እወዳለሁ

ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሀገረ አዶላ
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Wed Oct 13, 2010 10:20 am    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:

በቺሊ ሀገር በማዕድን ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች በህይወት እንዲተርፉ እግዚአብሄርን እንለምናለን
ቁፋሮው ተስፋ ሰጪ እየሆነ ነው እግዚአብሄር ይርዳቸው

አሜን አሜን ራስብሩ እግዚአብሄር እነሆ ረዳቸው ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ እየተከታተልኩ ነው እስካሁን ስድስተኛው ሰው ወጥቷል ሰባተኛውም በመውጣት ላይ ነው ሁሉም እንደሚወጡ እምነቴ ነው በዚህ በክፉ ዘመን የእግዚአብሄርን መልካምነት እያየን ነው
እርሱ ይክበር ይመስገን በጣም ደስ ብሎኛል ::

አደቆርሳይ መቼም ምን አይነት እንደሆንክ መናገር አልችልም የለመድኩትን በማግኘቴ ሌላው ያስደሰተኝ ነገር ነው :
አክባሪያችሁ ኮሎኔል
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Oct 13, 2010 9:19 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

አደቆርሳ =እንደገመትኩትና እንደጠበኩት ነው ትንታኔህን ያገኘሁት ::እኔ ምንጩን ከየት እንዳገኘሁ ቀደም ብዬ
ጽፌዋለሁ ::ኖሞናኖቶ በዋርካ ጄኔራል ላይ ያቀረበውን ነበር ኮፒ አርጌ ያመጣሁት ::እሱ የራሱ ምንጭ ይሁን ከሌላ ያግኘው የገለጸው ነገር የለም ::እኔም
እኛን የሚመለከትና ልንወያይበት እንዲሁም ልናውቀው ይገባል በሚል ነው ያመጣሁት ::በተለይ
ባንተ ትንታኔ ከልብ ረክቻለሁ ::ከመጀመርያውኑ አጣቅሰህ እንዲህ ያቀረብክልን ;-
Quote:
የአብ የወልድንና የመንፈስ ቅዱስን አገላለጽ የተላበሰ ነገር ግን አገላለጹ ለየት ያለ ይመስላል :
ጥቂት መናገር ቢቻል በሲዳምኛ ቋንቋ
መገኖ ማለት -- እግዚአብሄር
ሀላሌ ማለት -- እውነት
ካሊቃ የሚለውን ቃል በትክክል መግለጽ ከቻልኩ ፈጣሪ ማለት ነው ::
እንግዲህ እግዚአብሄር እውነትና ፈጣሪ - አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስቅዱስ ሰራጺ እንደማለት ነው ማለት ነው ይህ ትክክል ነው ::
እኔም እስከማውቀው ድረስ በሲዳምኛ እምነት ውስጥ ከመገኖ ሌላ ምንም አምላክ የለም

ትንታኔ አድናቆቴን እንደሁሌውም እንድሰጥህ ግድ ይለኛል ::

ምናልባትም ኖምኖት እኛ ቤት ብቅ ካለ በዚህ ነገር አንድ ነገር እንደሚለን ተስፋ አደርጋለሁ ::በተጻፈው ነገር ግን
ጥቂት ከማወቅ ባሻገር ብዙም እውቀት ስላልነበረኝ እርካታዬን በድጋሚ እገልጻለሁ ::

ቸር እንሰንብት ::
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 313, 314, 315 ... 381, 382, 383  Next
Page 314 of 383

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia