WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
/ በየነና / መረራ ከህብረት አመራርነታቸው ሊነሱ ነው

This forum is locked: you cannot post, reply to, or edit topics.   This topic is locked: you cannot edit posts or make replies.    WARKA Forum Index -> Warka News - ዋርካ ዜና

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ENH

መንገደኛ

Joined: 03 Oct 2003
Posts: 0
Location: Addis Abeba, Ethiopia

PostPosted: Tue Oct 25, 2005 8:15 pm    Post subject: / በየነና / መረራ ከህብረት አመራርነታቸው ሊነሱ ነው Reply with quote

አዲስ ዜና - 25-10-2005

አስራ አራት የፖለቲካ ድርጅቶችን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረትን (ኢዲኃህ ) በመንፈቅ ልዩነት እየተፈራረቁ ሲመሩ የነበሩት / በየነ ጴጥሮስና / መረራ ጉዲና ከህብረት አመራርነታቸው ሊነሱ እንደሚችሉ ከፓርቲው አካባቢ የተገኙ ምንጮች አመለከቱ።

ይቀጥላል...

News provided by Ethiopian News Headlines
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
በማእረጉስ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 29 May 2005
Posts: 61
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Oct 28, 2005 6:46 pm    Post subject: Reply with quote

እነርሱን የመሰሉ ጠንካራና አስተዋይ መሪዎችን በማንሳት እነ ማንን ለመተካት እንደተፈለገ አላውቅም :: ይህ ደግሞ የሚጠቅመው ወያኒውን ብቻ ነው :: የነርሱ እስከተቻለ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተቻላቸውን ሁሉ መሞከር የሚደነቅና ሊከበሩ በተገባ ነበር :: ይህኛው መንገድ አያስኪድም የምንል ከሆነ ደግሞ ሱሪን ጠበቅ አድርጎ የቀድሞውን የወያኒውን መንገድ በመጠቀም ለቆራጥ ትግል መነሳት ብቻ ነው :: ለነርሱም የሚገባቸው ይህ ብቻ ነውና .... በቀረውስ ሁለቱን መሪዎች በሆነ ባልሆነው በመጎናተል ተስፋ እንዳናስቆርጥና አስተዋይ መሪዎችን እንዳናጣ እናስብ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃኘው

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Oct 2003
Posts: 749
Location: Man

PostPosted: Fri Oct 28, 2005 8:02 pm    Post subject: ትክክለኛ አገላለጽ ያገር ሰው ! Reply with quote

ችግራችን ምንድነው ምንስ ያስፈልገዋል ብለን ባለመረዳታቺን ባለማሰባቺን ነው እዚህ ግራ የሚያጋባ ሁኔታዎች ውስጥ ያለነው :

መንገዱ 2 ብቻ ነው 3-4 ሳይሆን ! እሱም በሠላማዊና በህዝብ ፍላጎት በተጣመረ ስትራተጂ መታገል :: ታልሆነም የህወኃት ወያኔን ሻቢያን መመሪያና መታገያ የነበረን ከልብ አምኖ ወደ ማነጣጠሩ መሄድ ? እዚህ ላይ ያንንስ ቢሆን እንዴት አድርጎ አመራሩን አካሄዱንና የመታገያውን ሥፍራ የመምረጥና በቆረጠ መንፈስ የሚታገሉ ስንቶቹ ናቸው ?

እነኛ ሁሉ ባጠቃላይ የኛው ናቸው የኔናቸው ብሎ አንድ ሰውነቱ በውጪ በጫካና በውድማ በተራራዎች ላይ የሚኖር ግማሽ አካሉን የሚያስብ ሁሉም ዜጋ ሊገኙ ይቺላሉ ወይ ወይስ ወሬ በመቀባበል ብቻ ነው ::

አሁን የዶክተር በየነ ጴጥሮስና የዶክተር መረራ ጉዲና ስትራተጂ በወቅቱ ትክክል ነው እላለሁ :: ሌላ አማራጭ የላቸውም :: እንዴት የላቸውም ? አዎ ህወኃት በኦፒዲኦ የጡት ልጁ አማካኝነት ቢሯቸውን ሲሰባብርና ማህተማቸውን ሚስጢራዊ መዝገቦቻቸውን ሲያቀብል ባሉበትና እንዲሁምጽህፈት ቤቶቹን እየዘጋ ቁልፍ እየቀየረ ባለበት ጊዜና እንዲሁም የፓርቲዎቹ ህልውና በጥያቄ ላይ ወድቆ በሚገኝበት ጊዜ እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ለስብሰባ እየተባለ መሪዎቹ ጀነራሎቹ ማለት ነው ሲከርሙ ወታደሮቻቸው ደግሞ ማለትም የፓርቲው አመራሮች እንዲሁም ማህበራቸውን የሚያፈራርሱ ወጠጤዎች ጉድ እየሰሩ መሆናቸውን በወቅቱ ተነግሯቸው ከሰሞኑ ገብተን እናስተካከለዋለን እንዳላሉ ሁሉ ነገር ግን እነኛዎቹ 2 ሰዎች ጨርሰው መዓከላዊ ምክር ቤቱን ጠርተው ዶክተሩን የማያውቋቸው መሆኑን ባስታወቁበት ሰዓት ምንኛ ድንጋጤ ነበረ ?

ይህንና ሌላውን ጥሩ አድርጎ መገመት ይገባል :: ከዚያስ በቀጥታ ወደተከፈተው ሸንጎ ገብተዋል :: በእርግጥ ጥሩ ዘዴ ነው :: ማህበርተኞቻቸውን እንደያዙ አንደኛው 37 መቀመጫውን ሌለኛውም የቀረውን ባጠቃላይ 57 ወንበሮች ተቆጣጥረዋል ::

እንግዲህ ይህ ታክቲካዊ አሰራርና እንዲሁም የሠላማዊ ትግል የሚያሳያቸው ዕይታቸው ነው :: ከዚያ የበለጠ ሊሄዱ አይቺሉም ምክንያቱም የተነሱት ከዚያ ለሚያልፍ ትግል ለማካሄድ አይደለምና :: ያንን የሰፋና ብዙ መስዋይትነትን ለሚጠይቅ ትግል እንደዚህ በድረስ ደረስ ሳይሆን ከነሱ የተለየ ኃሣብ ያላቸው ታጋዮች ታሉ አሁንም ቢሆን መንገዱን ጨርቅ ያርግላቺሁ የሚሉትና ያሉት መሪ እዚያው ቦታቸው ነው :: ታዲያ እነኝህን በበእራቸው ብቻ እየተዋጉ ያሉ ምሁራንን ጠመንጃ አንስተው አልሸሹም ዞር አሉ ወደሚባለው አምባ እንዲገቡ ይፈለግ ነበር ወይ ?

ያልሰለጠኑበት ሁኔታ ነው እሱ :: ከዚያ የበለጠ ከነሱ መጠበቅ አይኖም ለማለት ነው :: በመጀመሪያ እዚህ ዋሽንግተን ዲስ ይህ ህብረት የሚባለው ሲሰበሰብ አገር ወዳዶችንና እንዲሁም የትጥቁም ሆነ የደኑ ጥራኝ ትግል ልምድ ያላቸውን ሰዎች የሚመሩትን ድርጅትና ቡድን እንዲከስም በማድረግ ድምጹንም በመቀማት ቺላ የተደረገው ማንን ለመጥቀም ነበር ::

በሌላ ዕይታ ደግሞ በዚያን ወቅት ለነበሩት የህብረቱ አጠናቃሪ ጊዚያዊ ኮሚቴዎች ከአለም አገሮች ከሳኃሊን ሳይቀር ጥሪ ቀርቦላቸው በተለይ ብዙዎቹን ኢትዮጵያን እንደህይወታቸው የሚወዷትን ልጆቷን የስድብና የፉከራ መዓበል አድርሰዋል :: ለሴትዮዋም ቢሆን እጅግ ክቡር የሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች በኢማይልና እንዱም በተገኘው መገናኛ ሁሉ ተነገረች ግን አሁንም ያው ተፈጥሯዊ ንቀታቸውና አሮጋንሣዊ አስተሳሰብና አመለከታቸው አሁን ለደረሰው ስህተት ዳረጋቸው ::

ማንኛውም ውጥን ሲደረግ እንደ ቅመም አገር ወዳዶች በማህላቸው እስከሌሉ ድረስ በምንም ዓይነት ኃሣቦቻቸው ከግቡ አይደርሱም :: ፖለቲካው ብቻ ሳይሆን የህዝብን ስሜትና ኃሣብ እንዲሁም ምኞቶቹን ከልባቸው ውስጥ ሁኖ የሚመነጭባቸው የማይተዋወቁት አገር ወዳዶችም ጭምር ናቸውና :: ያነው ያልገባቸው ::

አሁንም ተስፋ ለማስቆረጥ ሳይሆን ይህን የምጽፈው ለወደፊቱም አንድ ጅማሬ ሲጀመር ጭለማ ቢሆን ለመሆኑ ለጉዟቺን ካርታና ኮምባሱን የምንመለክለትበት ባትሪ የያዘ ከውስጣቺን አለ ወይ ብሎ የቡድኑ መሪ ማሰብና ማስያዝ አለበት ይህን ያላደረገ መሪ ከግቡ አቃጫ ቃርቶ ሜዳውንና ገደሉን ሳይመለከት ወደ ገደል አፋፍ ላይ እንደሚደርስ ሰንጋ ይሆናል ማለት ነው ::

ስለዚህም ለወደፊቱ የረቀቀ ሁኔታ መታሰብ ይኖርበታል :: ዶክተር መረራና ዶክተር በየነ እዚያም ገብተው የሚታገሉ ይመስለኛል እስከዚህ ሊያስቆጨን አይገባም :: የሚያስቆጩን ግን እነኛ የትጥቅ ትግሎችን የሚያነሱ ሰዎችን እንደ ጉድ እንደ የዋአህ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎችን ነው :: ዶክተር ቅጣው እጅጉን አስቡ እንዴት አዋክበው ከመሐላቸው ከኦዲተርነት እንዲወጡ አደረጓቸው ? ከዚያስ የከፋኝ ኢትዮጵያ የጀግኖች ግንባር ባሉት የውጪ ተጠሪዎቹ በኩል ጥያቄ አቅርቦ ለምን ሳያስገቡት ቀሩ ? እነሱ ያስገቧቸው ቢኖር የም ዕራብ ሱማሌ ተገንጣይን ቡድን ያውም በሌሉበት በመልክት ነበር ከነኛም ጋር ተቆጥሮ ነው 14 ድርጅቶች የሚባልልን :: ያን ያን ሲመለከቱት አሳዛኞች ናቸው ከማለት በስተቀር ሌላ ምን እንደሚባሉ አላውቅም ::

"ዶክተሮቹ ! ያላቸው ምርጫ አንደኛዋ ብቻ ነቺ :: ያቺንም ተጠቅመው ካለፈው የበለጠ ድምጽ ይዘው ቀርበዋል :: ከዚያ ያለፈ አንዲት ስንዝር ዕልፍ እላለሁ ቢሉ ምን እንደሚያጋጥማቸው ጥሩ አድርገው የሚያውቁ ይመስሉኛል "

በዚያ ምክንያት ዶክተሮቹ የወሰዱት አቋም ትክክል ነው የኔ መልስ ::

አመሰግናለሁ

ቃኘው
(ሰሐሊን )በማእረጉስ እንደጻፈ(ች)ው:
እነርሱን የመሰሉ ጠንካራና አስተዋይ መሪዎችን በማንሳት እነ ማንን ለመተካት እንደተፈለገ አላውቅም :: ይህ ደግሞ የሚጠቅመው ወያኒውን ብቻ ነው :: የነርሱ እስከተቻለ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተቻላቸውን ሁሉ መሞከር የሚደነቅና ሊከበሩ በተገባ ነበር :: ይህኛው መንገድ አያስኪድም የምንል ከሆነ ደግሞ ሱሪን ጠበቅ አድርጎ የቀድሞውን የወያኒውን መንገድ በመጠቀም ለቆራጥ ትግል መነሳት ብቻ ነው :: ለነርሱም የሚገባቸው ይህ ብቻ ነውና .... በቀረውስ ሁለቱን መሪዎች በሆነ ባልሆነው በመጎናተል ተስፋ እንዳናስቆርጥና አስተዋይ መሪዎችን እንዳናጣ እናስብ !

_________________
tank you
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
mrmuluwork

ኮትኳች

Joined: 20 May 2005
Posts: 210
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 8:20 am    Post subject: በሰላም የመጣ ነው ሰላምን የሚቀበል :: Reply with quote

ሁለቱም ውድ የሆኑ የኢትዮጲያ የተማሩና በውነት ታግለው የሚያታግሉን እራሳቸውን ለኢትዮጲያ አሳልፈው የሰጡ እውነተኛ ሙሁር ናቸው ::ዘውትርም በኢትዮጲያ ታርክ ስማቸው በወርቅ ተጽፎ ለታሪክ የሚቀመጥ ሀቀኛ ኢትዮጲያኖች ናቸው ::እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለንም ::

ዳሩ ግን ወያኔ ናዚው ሰላም የሚገባው እና ለሰላምም የቆመ ባለመሆኑ በሰላም ከወያኔ ናዚው የሚገኘው ሞት እና መዋረድ መሰቃየት ብቻ ነው ::ስለዚ አንዴ ሞተን የቀረው እና አዲሱ ትውልድ በነጻነት መኖር አለባቸው ::ነጻነት ወይም ሞት !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Report post
ሊቃውንት

ዋና ኮትኳች

Joined: 10 Oct 2004
Posts: 554
Location: Far_east

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 1:05 pm    Post subject: Reply with quote

ድሮም በውጭ እና በውስጥ መመሆን የሚመራ የፖለቲካ ፓርቲ አንድ አይነት ወጥ የሆነ አመራር ስለማይኖረው ለእንደዚህ አይነት ውድቀት ይጋለጣል ::

እነዚህን ሰዎች ሊተኩ የሚችሉ የፖለቲካ ሰዎች እነማን ይሆኑ Question
_________________
The truth is out there.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እንድሪያስ

አለቃ

Joined: 19 Mar 2004
Posts: 2130
Location: *****

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 10:56 pm    Post subject: Re: ትክክለኛ አገላለጽ ያገር ሰው ! Reply with quote

አቶ ቃኘው በሀሳብህ ፈጽሞ አልስማም ::
ለምን ከአልክ .... ሀሳቤን ወይም ደግሞ የምለውን ማለት እችላለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
በማእረጉስ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 29 May 2005
Posts: 61
Location: ethiopia

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 11:25 pm    Post subject: Reply with quote

mrmuluwork ታዲያ ለተባለው ትግል መፈክርና ማውገዝ ብቻኮ በቂ አይሆንምና እውነተኛ ሀገር ወዳድነት ከሚፈተንበት ቦታ ላለነው እርስዎን መሳይ ፎካሪን ልናገኝ እንወዳለንና ብቅ ይላሉ ?
ወይስ የተለመደ ፉከራና ርግማንዎን እያነበብን እንክረም ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቃኘው

ዋና ኮትኳች

Joined: 23 Oct 2003
Posts: 749
Location: Man

PostPosted: Sat Oct 29, 2005 11:50 pm    Post subject: Re: ትክክለኛ አገላለጽ ያገር ሰው ! Reply with quote

ሰላም አንድርያስ !
ትክክል ነህ እኔ በግሌ በኃሣብ እየመጣ የሚያስቸግረኝን ነው የጻፍኩት :: አንተም ወገኔ ደግሞ መልክትህን ጻፍልኝንና ስህተቴን አርሜ በኃሣብህ እስማማለሁኝ ::

ይረዳኛል ዶክተሮቹ መጀመሪያ ቃል እንደገቡበት ለምን ጸንተው ያልቆዩ መሆኑን እረዳለሁ :: ግን የኢትዮጵያን ሁኔታ ታውቀዋለህ :: በዚያ ምክንያት ይመስለኛል ::

ለአንድ ዓላማ አብረው ተነስተው የነበሩት ሰዎች ከመሐላቸው በመክዳት የወያኔ ኦፒዲኦ ሎሌ ሆኑና የቢሯቸውን ቁልፍ ወስደው በቁጥጥር ስር ማንኛውንም አደረጉባቸው ::

በዚያ ምክንያት ይመስለኛል ኃሣባቸው ለሁለት ቦታ የተከፈለው ቀጥሎም በውጪ ያሉት ተቃዋሚዎቹ በዚያ በአሳሳቢ ሰዓት ዶክተሮቹን ወደ ውጪ መጥራት ይኖርባቸው ነበር ወይ :: ወታደር ያላዝማች ሁኖ ነው ነገሩ የተበላሸው የነበረው ::

ያንተን ኃሣብ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ::

ዘወትር አክባሪህ

ቃኘው
(ሰሐሊን )

እንድሪያስ እንደጻፈ(ች)ው:
አቶ ቃኘው በሀሳብህ ፈጽሞ አልስማም ::
ለምን ከአልክ .... ሀሳቤን ወይም ደግሞ የምለውን ማለት እችላለሁ ::

_________________
tank you
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
Display posts from previous:   
This forum is locked: you cannot post, reply to, or edit topics.   This topic is locked: you cannot edit posts or make replies.    WARKA Forum Index -> Warka News - ዋርካ ዜና All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia