WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የዋናው አቁማዳ ==>ደብዳቤ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 22, 23, 24  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1569
Location: Mars

PostPosted: Mon May 01, 2006 6:36 pm    Post subject: ... Reply with quote

Rolling Eyes ! ይገባኛል ግና ቅቅ 8 የንግግር ክፍሎች ዉስጥ ልመድባቸዉ ሥጥር የአማርኛ ሶፍት -ዌሬ አልቀበልልኝ አለ ተቸገርኩ !! ቅቅቅቅ ... እስኪ ቀጥል ምናልባት ዓዲስ አማርኛ ትፈጥር ይኆናል ! ማን ያዉቃል !ቅቅ

ዋኖክሥኛ ( የአንተዉን ነው የኔዉን አይደለም )
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon May 01, 2006 7:06 pm    Post subject: Reply with quote

ዘጠኝ ሰሀት ሆነ
ትንሣሔውም ሆነ

ዶሮ ግን አልጮወም
-በግ ነው የባነነ
ኩስም አልሸተተ
-ሽንኩርት አልታጠነ

ጉንፋን ተጎናጽፈው
ዛሬን ነጻ ወጥተው
''እኔን የነካህ ...?'' ብለው
እዚህም ሞት እዛም ሞት
-ብለው ተሰላልቀው
ጥሬም ቢያጡ ጭረው
የፋሲካን ቢላ ማለፉን አመሰግነው

ደምም አልፈሰሰ
የዛሬስ ፋሲካ
-በዳቦ ኣለፈ ::
ጉንፋናማው ዓውዳመት
-እንዲህ እንደቀፈፈ

ዋናው _________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1569
Location: Mars

PostPosted: Mon May 01, 2006 8:05 pm    Post subject: ተብታባዉ Reply with quote

Rolling Eyes ተብታባዉ የብዕር -ሰዉ ልበልሕ ይኆን !!

ምን !! ይሻለኛል እሄን ፊደል -ገደፋሕን !! እረ በፈጠረሕ ዒዲት አድርግ ቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun May 07, 2006 7:13 pm    Post subject: Reply with quote

እሺ ወዳጄ ዋኖስ ሰሞኑን ጸሀፊ ለመቅጠር እያሰብኩ ነውና እስቲ የተሻለ ያልገደፈ ፅሑፍ ላቀርብ እሞክራለሁ ቅቅቅ

ግን አመስግኜያለሁ ::

ዋናው _________________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon May 08, 2006 4:19 pm    Post subject: Reply with quote

ፊደል አንኳኩቼ
ምናብ አንጋግቼ
በምጥ የወለድኩት ሐሳቤን አምጥቼ
-ቦርድ ቀብቅቤ ሞኒተር ላይ አፍጥጬ
ጽፌ ውልደተ -ሀሳብ
አትሜ በምናብ
ደቂቃን ደቅድቄ
-ቃላትን ስሾርብ ......
አጣጥሜው ዳግም
-ላንባቢዬ ሳስብ

ሰብሚት አልኩትና
ፎረም ሳይደርስ ገና
ጠፋብኝ ፅሁፌ እንደጉም ተነነና
የመረጃው መረብ
-ውጦ አስቀረውና ::

አያድርስ እናንተዬ የዚህ ዓይነት ፈተና

ዋናው _______________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed May 10, 2006 1:38 pm    Post subject: Reply with quote

አንቺ የፀደይ አበባ ...
የፍንጥቅ ብርሀን
-የፍቅር ጌጥ ካባ
የህይወት ምሳሌ
-የጣዝማ ወለላ

ፍቅርሽ አነፈረኝ
በቁሜ አናወዘኝ
ውስጤን እያጦዘኝ
የመታደል ህግን
-ለስሙ አስይዞኝ
ልከተልሽ ደግሞ ኮቴሽን ልመርምር
ባጣም ባገኝሽም በፍለጋ ልዙር
ዓለም 'ንድሆን ጠቧል ሳላገኝሽ አልቀር
ጦስሽ አስክሮኛል አንቆኛል በፍቅር

የጨቅላ ንፍዘቴን
የድንግል ስሜቴን
ዛሬን ተናንቆብኝ ባየው ድሮነቴን

ዳግም ተጸንሼ
ለወተት አልቅሼ
በፍቅርሽ ሙጠምጢምወዲህ ተመልሼ
ዛሬን ተጃጅዬ አንቺን ስል አልቅሼ
.
.
.
ዋናው ______________________________________:[/url]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat May 13, 2006 9:51 pm    Post subject: Reply with quote

____ሕልሜን በሕልሜ አየሁት ____

ነፍሴ ተንሳፈፈች
በዕንቅልፍ እየጦዘች
በደከመ ዕይታ ብርኃን 'የሸሸች
በአልጋ ተፈናጣ ሠማያት 'የሮጠች

በሕልም ዓለም ነውልዬ
በቅኔ ድንግዝግዝ ስጋዬን እዛ ጥዬ
አየው ምስቅልቅሉን
-ይመስለኛል ብዬ
ቀለም ባልጎላበት
-ምስል ገፅ አስተውዬ

ብቻ እዛም ስር ቦዝዤ
በስጋት ፈዝዤ
አየውት ዕኔነቴን በድካም ነፍዤ

አሁንም ዝዬ በጣም ድካሜ መጣና
ድል አልባው ዕንቅልፌ ዓይኔን ጨፈነና
ዳግም ተብረክርኬ አሸላለብኩና
ስብጥርጥር ዕይታን ፈጠጥኩ ዕንደገና ::
ኣለምኩ ሌላ ሕልም አሁንም ተኛውና
ሕልምን ሕልም ወልዶት
-ሳይይፈታ እንደገና
.
.
.
ዛሬስ ማን ይፍታልኝ
ማን ይጠንቁልልኝ
የንሁስ ሕልምን ሚስጥር
-ማን ይመርምርልኝ ?

ዋናው ____________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon May 15, 2006 4:22 pm    Post subject: Reply with quote

.
.
.
ጠዋትን ማልጄ ከሕልሜ ስባንን
ዓይኔን ሳብስ በጄ ሳየው ሕያውነቴ
ያሰለሰ ሕልም እየወረረው ውስጤን
ዓይኖቼ ደንብረው ቢያበሩት ቀኔን
ለካስ ሕልም ነበር
ይሄም መደናበር
የኔ ማግጠጥ __ ለዛሬ መደንበር

ምስል አመጣ ዓይኔ ::
ዳሰሰው በድኔ :
ሸተተው አፍንጭዬ ::
-'እፎይ !' አለ ጎኔ ::
ግና __ካልኖርኩበት
-የትኛው ነው የኔ ?
በምን ይታወቃል
-ከሕልም መባነኔ __________________?

ዋናው ___________________________________::
[/list]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አወዳይጫት

አዲስ

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 13
Location: canada

PostPosted: Mon May 15, 2006 5:19 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድም ጽሁፍህ ይመቻል ...ትቅሚያለሽ እንደ Cool አነጋገርህ እንደመረቀነ ስው ነው .
_________________
ethiopia will naver be colonised by meles
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu May 18, 2006 4:43 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅ አቶ አወዳይ ሠላም
በቅድሚያ ለአድናቆትኦ አመሰግናለሁ
እኔ ግን የብህር ዙርባ ውስጤን ያመረቀነው እንጂ ከጫቱ 'ንክዋን እምብዛም ነኝ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun May 21, 2006 7:17 pm    Post subject: Reply with quote

ኃሣብና ስሜት ባንድነት ተጣምረው
ሆኖ ሲታዘበው ልብን ልብ ሊለው
የመሆንን አለመሆን
-ድርጊቱ ቢያስቆጣው
እንደሌላው ኬሬዳሽ
ብሎ ንቆ ሳይተው

ይፍልቃል ስንኙ
-ይሾረባል ቃሉ
ይወርዳል ጥበቡ
-ሀቅ ስሜት ሲሉ
በደም የሾለከን
-የአፈር ሚሥጥር ካሉ
የውላጅ እኔነት
-አርፍደውም ቢያበቅሉ
.
.
.
_________________ለዳሞት ነው እቀጥላለሁ ::

ዋናው _______________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Fri May 26, 2006 7:01 pm    Post subject: Reply with quote

.
.
.
ብህር ያጮልቃል
አሻግሮ ማዶውን
-ወንዙን ሁሉ ይቀዝፋል

ያስቃዣል ምናቡ
ያስሮጣል በቀልቡ
ይሄዳል በትዝታ
-የክታቡን ውል ሲያስቡ
የቅኔውን ፍተሀት
-በዳንቴሉ ቃሉ ...

ስሜት ማንነቱ በውስጡ ገንፍሎ
በቃላት ውዥንብር ሚስጥር ሚስጥር ብሎ
ያረገዘ ፊደል ላይወልድ እንደበቅሎ
ብቻ በምጥ ዝሎ
ቋንቋ መወለድን ባፈር አንከባሎ

ወንጌልን ላልደገምን
መልህክተን ላልቆጠርን
ላቦጊዳ ሽፍቶች ፈረንጅን ላስቀደምን ...
ፎቅ ነው ሕሳብ -ቃሉ
ጠጣር ነው ፊደሉ
ቅኔ ነው ሓሳቡ ...
ብለን ፉካረ -እልሁን
-በደንብ ሳናጤነው
የደም ቃሉን ህትመት
-ላደራው ሳንበቃው
.
.
.
እሱስ ውልደቱ ነው የግዴታው አሻራ
ገሳ ነው ልባሱ -ቅኔ ዋሸራ
ይፈልቃል ጅረቱ ትውልዱን እየጠራ
እድሜውን አለምልሞ ያኑሮው ባደራ ::

_________________ ዝነኛው ገጣሚ ዳሞት /ዋኖስ

ዋናው ____________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1569
Location: Mars

PostPosted: Sat May 27, 2006 6:07 am    Post subject: ቅቅቅ ... Reply with quote

Rolling Eyes እዚሕ ጋም ተጀምሯል ! ቅቅ

ኧረ ! በቃ ይቅር ይሕ ቅኔ መወድሥ

ጆንያዬ ሞልቷል እኔ አልጪንም ፈረሥ ::

በሽሩቡ -ኆሄ ደም -ግባት ባነቀዉ

-ቅኔ -ዋሸራሕ መድረኩን ቢሞላዉ

"ኃሴት " አሰከረኝ እዚሕ ገባሁ እሄው ::

ዕንደ -ቀለም ቅቡ ሾርቦ -በፊደል

ሕብር -ሥንጥር ሚስጢር ሕያዊነት ቃል

አስዉበሕ ማቅርቡ እጂግ ይደነቃል ::

=====ዳሞት ========
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Jun 06, 2006 7:33 pm    Post subject: Reply with quote

..........(666)...........

________ዕለተ ሤይጣን _______

ዛሬ ስድስተኛው ቀን ስድስተኛው ወር ሁለት ስድስተኛው አመትምህረት ነው :: እዚህ ለንደን ትራፋልጋር የተባለ ስፍራ እና ካምደን ታውን የተባለ ስፋር ዕለቱ ይከበራል ልክ ይህንን እኔ ስፅፍ እዛ ሤይጣን እየተወደሰ ነው : ኦመን የተሰኘ ስለሠይጣን የሚተርክ ፊልምም እዚህ ለንደን ለህዝብ መቅረብ የሚጀምረው ዛሬ ነው ::
ትላንትና አንድ ጋዜጣ ላይ ያነበብኩት በዚች ቀን ከናቱ ማህፀን የወጣ ህፃን ሲያድግ እንደነማን አይነት ሰዎች ሊሆን እንደሚችል የተነበዩ ...ሰዎቹ አብዛኛዎቹ ሲሪያል ኪለር የሚሏቸው ዓይነቶች ናቸው
ሠዎች ለምንድነው ውስጣቸው ያለውን እኩይ ባህሪ አስተናግደው በገደብ አልባ ነፃነት ብዙዋን የማይቀበለውን ድርጊት ለመፈፀም የሚያስደስታቸው ?
ጥቁር ቀለም ለሠይጣናዊ መንፈስ መሸለሙ ያናደደን ጥቁር አፍሪካዊያን ብዙ ነን ምክኛቱም ይህ መንፈስ እኛን ዲስክሪምኔት ያደርጋል ብለን እናስባለን በርግጥ ለዛ አላማ ከተተኮረበት እነሱ እንደሚሉት ፕረጂድስ ነው :: ግን እንደ ቀለም ስነልቦናዊ ስናየው ጥቁር ቀለም ጨለማ ነው ብርሀን ሊሆን የማይችል ብርሀንን መልሶ የማያንፀባርቅ ስትሮንግ ኦፔክ ቀለም ጥቁር ነው :: ሰው ሲያገባ ነጭ ይለብሳል ሰው ሲሞት ጥቁር ይለበሳል ለምን ? ይህንን ስነልቦናዊ ስሜት ማን ፈጠረው ? እኔንጃ ነጭ የንፁሕነት ተምሰሌት እንደሆነ /ቅዱስ ውስጥ ሁሉ አለ :: አንድ ጊዜ አንድ የማውቀው ባበሻ አገላለፅ (ጠማማ ) የሚባል አይነት ሁሉ ነገሩ ግራ የሆነ ሰው ''እኔ ሳገባ ሚስቴ ጥቁር ቬሎ ለብሳ ነው የምትሞሸረው እኔም እንደዛ '' ሲል ሁሉም ሠው ''ሟርተኛ !!!!'' ብሎ ጮኸበት ::

ዛሬ ይህንን ቀለማዊ ወሬ ያመጣውት ዕለቱን ሊያከብሩ የሚሰማሩት ሰዎች አልባሳታቸው ጥቁር በመሆኑ ነው : እናንተስ ስለዚህ ቀን የተለየ ገጠመኝ ይኖራችሁ ይሆን ? እኔንጃ ....
እስቲ እኔ ስንኝ ልቋጥር
.
.
.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Jun 06, 2006 7:52 pm    Post subject: Reply with quote

.
.
.
ፈረሠኛው ሚካኤል በጦሩ እንደወጋው
ጥፍሩን አሳድጎ ሽቅብ ያቃሰተው
ጠይሙ መልከኛ በዕሳት የታቀፈው
ስሙን አሤይጢነው
በነጭ አስዶቅሰው ....

ሌላ ነው በውስጤ ዕርኩስን የሳልኩት
ጥፍሩም አልሾለም ቀንድም አልሸለምኩት
ፊቱም የገረጣ ነጭ ነው የሳልኩት

ደሙንም አልጠጣ
አመድ ላይ አልተሰጣ
ኣተላም አይሻም እሱ መች ስራ አጣ ...
.
.
.
ቢከበር ዕለቱ
ሚስጥረ ቁጥሩ
መንፈሱን የታደሉ
-ለዕኩይ ! ቢሉ
እርኩሳስን ስሜት
- ለርሱ ቢገብሩ

ላማትብን ' እኔ ይሰውረኝ ብዬ
ከሤይጣኖች ሰፈር መስቀሌን አሹዬ
ለዚች ሸክላ ምድር
ላስስገበገብ ምዬ ....
ይረጭ ዛሬ ደጄ
ጧፉን ይዤ በጄ
መለዐክት አማልጄ

ዋናው _________________________________::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4 ... 22, 23, 24  Next
Page 3 of 24

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia