WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የዋናው አቁማዳ ==>ደብዳቤ
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 22, 23, 24
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋናው

ዋና አለቃ


Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Jun 27, 2011 11:57 am    Post subject: Reply with quote

ይድረስ ለናቴ


እትዬዋ ይሄንን ደብዳቤ ስጥፍልሽ ያዩኝ እዚህ ከሃገሬው የተመሳሰሉ ሃበሾች በሳቅ ሆዳቸው ንፍር ነው ያለው :: በዚህ ዘመን ብህር ከወረቀት አገናኝቶ ደብዳቤ ሚጥፍ ሰው ማየት ብርቅ ነው አሉ :: ሚገርመው ገጠር የኮምፕተር ደብዳቤ መነበብ እንደማይቻል ሊገባቸው አለመቻሉ ነው ::

እስቲ ተያቸው ስለነሱ ኋላ እመለስበታለሁ ... አንቺ እንዴት ነሽ ? ይሄው እንግሊዝ ኣገር ከገባው የፊታችን ባለግዚያር ለት ሁለት ወር ሊሞላኝ ነው እንዲያው የናንተ ናፍቆት ደርሶ ትክዝ እያደረገኝ መቆዘሜን ያዩ ሃገሬዎቹ ድፕሪሽን ይዞክ ነው እያሉ እንደወንጀለኛ በጥያቄ ያደክሙኛል ... እትይዬ አንቺ እንዴት ነሽ ? መቼም ይሄ በልግ ሲመጣ አስምሽ ተነስቶ ያሰቃይሻል እያልኩ ሁሌ ነው ማስብ ... እስቲ ባይሆን ወቅቱ እስኪቀየር ትልቋ እማማጋ ሂደሽ ክረሚ ... የኔ ነገር ዳሩ ከብቶችን ለማን አደራ ብለሽ ...? ጊደሬ እንዴት ነች ? አደገች ? የጋሽ አምሳሉ ኮርማ እንዳይደፍርብኝ አደራ እትይዬ ...
እስቲ ስለኔ ላጫውትሽ ... አየ ፈረንጅ ሃገር ... ምን ጉድ ነው እትየዋ ....? ገና ቀትር ' ነው ሚጨልም ... ፈጣሪ ምን ሲል ጀምበር እንደሰሰተባቸው ? በዚህ ላይ ውርጩ ክምር ልባሽ ተሸክሜ ውዬ ክምር ብርድ ልብስ ሰሸከም ተኝቼ ይነጋል ጠአይቱን እዚህ ከመጣው ሁለት ቀን ነው ያየዋት እሱንም አየዋት አይባልም እንደ እጅ ባትሪ ብልጭ ብላ ጥፍት ነው ያለችው እረ እስቲ ለብርዱ ሠው ከተገኘ ጥሩ ካቲካላ ስደጂልኝ
እዚህ ካየር መሳፈሪያው ወርጄ ጆሮዎቼ በነጎድ እንደነጎሉ ጓዜን ይዤ ስቅበዘበዝ የጋሽ አዘነ ወንድም ልጅ ደርሶ ተቀበለኝ ብረሓኑ ነው ስሙ ባለንጀሮቹ ግን ቡርኖ እያሉ ነው 'ሚጠሩት እንዴት ያለ ደግ ሠው :: 15 ዓመት ሙሉ ታክሲ ሲሾፍር ነው የኖረ ግን ክፉ ሚስት አለቸው መቼም እሱ አሟልቶ አይሰጥ ... እና እልሻለሁ በማግስቱ እጅ ስጥ ብሎ ቢያማክረኝ ... እኔ ያንቺ ልጅ ዘራፍ አልኩልሻ ዘርማንዘሬ አዳፍኖ ላሶጣው ነጫጭባ ደጁ ድረስ መጥቼ እንዴት እጅ ልስጥ ብዬ ዘራፍ አልኩልሽ .... ኋላ ለካስ ነገሩ ሌላ ነው ... እዚህ ሃገራቸው እንድቀር መላው ሂዶ ለነሱ የውሸት ማልቀስ ነው ... እትይዬ ... እስቲ ባክሽ የነፍስ አባትሽ አባ /ዮሓንስ ጋር ሂደሽ ይቅር ይለኝ ዘንድ አስለምኝሊኝ ... መቼም የዋሸዉት ውሸት እትይ ... መቼም አስተርጓሚ ተብዬው ሳያውቅብኝ የቀረ አይመስለኝም ...
መልሱ ለትንሳሔ አካባቢ ነው ሚደርሰው ብለዉኝ እየጠበቅኩኝ ነው :: እስከዛው ጎተራ ምታክል ክፍል ሰጥተዉኝ እዛ እኖራለሁ ግን ጸአዳ ነው ምግባቸዉን ግን ልለምደው አልቻልኩም እሳት ያልመታው ነጭ እንቁላል ንፍሮ ከመሰለ ነገር ጋር እየሰጡኝ ወስፋቴ ዝግት ብሎልሻል 'ንዲያው ለአጭ ለአጭ ' ነው 'ሚለው ይልቅ ብረሓኑ እየመጣ አንዳንድ ጊዜ ያገሬ ምግብ ያለበት ሆቴል ወስዶ ይጋብዘኛል ... እንጀራቸው ንጣቱ እንደበረዶ ነው ማባያዉን ግን ብዙም አልለመድኩት ብቻ ከምኖርበት ቤት ምግብ ይሻላል :: እትዬዋ ሳልረሳው ልንገርሽማ እዚህ ሃገር ከመጣው ዶሮዎቹን ፈጀዋቸው አልኩሽ : መቼም የዶሮ ግፍ ካለ እኔኑ ፈንግል ይዞኝ ፍንግል እንዳልል ፈራው አንዳንዴ ለኪስ ብለው ከሚሰጡኝ ሳንቲም ሁቴል ሄጄ በወረቀት ቁና ሙሉ ዶሮ ገዝቼ እበላለው ... የብዛቱ ነገር ተዪኝ ... በዚህ ላይ ብቻዉን ነው 'ሚበላው ሽንኩርት የለ በርበሬ የለ አንዳንዴ እንደገንፎ አፍ ውስጥ ከሚላወስ ድንች ጋር ይሰጡኛል

የመሳፈሪያዉን ነገር አታንሺው እንደቤታቸው ባለፎቅ አውቶብስ አላቸው እሱ ላይ መስታወቂያ ነገር ሹፌሩ መዘውር ላይ እያስነካን ነው ምንሳፈር አያምኗቸዉም መሰለኝ ሳንቲሙን ሌላ ቦታ ነው ምንከፍል ታዲያ ተንደርድሬ ፎቅ ላይ እወጣና ከተማይቱን ቁልቁል እየቃኘው ስዞር ይመሻል ሹፌሮቹ ከውካዋ ቢጤ ናቸው ተሳፋሪ መቀመጫ ሳይዝ ስለሚያበሩ ስንት ቀን የፈርንጅ አሮጊት ላይ ወደቅኩ መሰለሽ ? ደግሞ አሉ እዚህ ሃገር ሰው መንካት ነውር ነው አንድ ቀንማ አንዷ እንደቄብ ዶሮ ስታስካካብኝ ግንፍል ብሎኝ አደብ ግዢ ብዬ በቋንቋዬ ዘራፍ አልኩባታ ... መቼም ያንን ውሸት ያስፈታልኝ ተርጓሚ አግኝቼው ቢተረጉምልኝ አጥንት ሚነካ ስድብ እንደሰደበችኝ ቀልቤ ነግሮኛል
የባቡሩን ብዛት አታንሺው እትይዋ ... ሃገሩን ቀፎ አስቀሩትኮ እንደፍልፈል ከስሩ ፈልፍለው ፈልፍለው ደግሞ ሲበሩ እንደጥይት ነው ::

እትዬ አሁን ቋንቋ መማር ጀምሪያለው ሃገሬ እስከ 5 የተማርኩት ጠቅሞኛል ብቻ ያስተማሪዋ አፍ አልያዝ አለኝ እንጂ መጻፉንስ ደሕና ነኝ ሁለት መንፈቅ ከተማርኩ የነብርሓኑ ዓይነት አፍ እንደማወራ ተስፋ አለኝ :: ቋንቋ ተማሪ ቤት ስሄድ መንገድ ላይ ያገሬን ልጆች ሳይ እጅ ነስቼ ሰላምታ ስሰጣቸው ልክ እንደጸበኛ ገላምጠዉኝ ያልፋሉ ካንድም ሁለቴ ብረሓኑን ምነው ሰው ሃገር ፍቅር ነሳን ብዬ ጠየቅኩት ... "እዚህ ሃገር 'ማታውቀዉን ሠው ሠላም ማለት ነውር ነው " አይለኝም እረ እውቅና ይንሳቸው እትዬዋ ምጽዋት አልጠየቅኩ አሳድሩኝ አላልኩ የግዜር ሰላምታ ማንን ገደለ ?
አንድ ቀን ደግሞ የማሪያም ንግስ ቀን ብረሓኑ ቤተስኪያን ይዞኝ ሄዶ ሕጣናቱ ሁሉ ሂሳብ መደመሪያ ማሽን መሳይ ነገር ይዘው ነፋስ እንደሚወዘውዘው ዛፍ ግራ ቀኝ ዘመም ሲሉ ይውላሉ በዚህ ላይ ስጋዎ ደሙን ሲቀበሉም ያቺ ማሽን ከጃቸውና ካይናቸው አትነቀልም ... ክብረ -በዓሉ አልቆ ምዕመናኑ ሲበተን የኮረዶቹን አለባበስ አይቼ ማሪያምን ይቅር በዪኝ ብዬ ከደጇ ተመለስኩ ... እትይዬ መሰልጠን እንዲህ ነው 'ንዴ ?

መቼም ብዙ አወራሁብሽ ምን ላድርግ እዚህ ከመጣው ከልብ ያዋራዉት ሰው የለም ሁሉም ወተት እንደጣደ ጥድፍ ጥድፍ እንዳለ ነው ... የብርሓኑ ባለንጀሮች ቤት አንድ ሁለት ቀን ሄጄ ነበር ሙሉ ቤተ -ሰብ ተኳርፈው ቴሌቭዢን ላይ ያፈጣሉ ዓይኖቻቸው ከቴሌቭዢን ሲነቀሉ ልጆቹ ቅድም የነገርኩሽ ነገር ላይ ... አዋቂዎቹ ደግሞ ስልኮቻቸው ላይ አንገታቸዉን ይደፋሉ :: እትይ ከምር ሰው ከሰው ማያወራበት ምድር ' ነው የመጣዉት ::
ሳልረሳው ላውራልሽማ ... እዚህ ሃገር ሚሽቲቱ ሶፋ ላይ ጥፍሯን እያሾለች ባልየው ማጀት ገብቶ ዓይኖቹ በሽንኩርት ያነባሉ ... ተደብቄ "አበስኩህ ገበርኩህ " ብዬ አማተብኩኝ ::
በይ እስቲ ልተዉሽ እትይዋ ... ለሚቀጥለው እኔም ካገሬው ሃበሻ ጋር ለመመሳሰል በዛዉም ቋንቋዉን ለማወቅ በጉራማይሌ እጥፍልሻለው እስከዛው ሰላም ሁኚ ከዘመድ እስከ ጎረቤት ሳሚልኝ :: ብዙ ምታዋራ ካርድ ብረሓኑ ሲጠቁመኝ አዲሳባ እነአንዳርጌ ጋር ደውዬ ድምጼን አሰማለሁ ::

ሰላም ሁኚ ውይ ዬኔ ነገር ብረሃኑ ሰው ሲሰናበት "ችርስ " ነው ሚባል ብሎኝ ነበር



_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እአምሮ

ኮትኳች


Joined: 12 Apr 2004
Posts: 380

PostPosted: Tue Jun 28, 2011 11:59 am    Post subject: Reply with quote

ዋናው :

እጅግ ድንቅ ደብዳቤ ነው :: ባላገሩ ወገናችን ጥሩ ታዝቦናል ::

በርታልንና ደግሞ በመጽሀፈ መልክ አቅርብልን ::

አድናቂህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ


Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Fri Jul 08, 2011 12:03 pm    Post subject: Reply with quote

አመሰግናለሁ አእምሮ
አርብ ኦገስት 5 የባለፈው ፕሮግራም አለን ከተመቸህ ብቅ በል ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 22, 23, 24
Page 24 of 24

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia